#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ፡
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
///
እንደ ቤቱ ሁሉ በረቱም የተሠራው ከድንጋይ ነው። በረቶቹ በሁለት ረድፎች መተላለፊያ ተከፍለዋል በመደዳ ተደርድረዋል።በዚህ እርባታ ድርጅት የሚደልቡ ሰንጋዎች ቀጥታ ወደውጭ ገበያ ነው የሚቅርቡት፡፡ከላሞቹ የሚገኘው ወተት ግን እዛው ግቢ ውስጥ ባለ ፋብሪካ ተቀናብሮ እና ታሽጎ በዋናነት በሻሸመኔና ለአዋሳ ገበያ ይቀርባል፡፡ በግዙፉ ግቢ ውስጥ አንድ ኪሎ ሜትር ርቆ ግዙፍ የሆነ የእጨት መሰንጠቂያ ፋብሪካ የሚያሰማው ድምፅ ይሰማል፡፡ይሄ ጣውላ የሚመረትበት የእንጨት ፋብሪካ ነው፡፡ፋብሪካው የሚጠቀምበትን ጥሬ እቃ ከከተማዋ በቅርብ ኪሎ ሜትሮች ላይ ከሚገኝ ሶሌ ከሚባል ቀበሌ ላይ ከሚገኝ ግዙፍ ደን ነው የሚመጣው…ደኑም በአብዛኛው የአቶ ፍሰሀ የግል ሀብት ነው፡፡እናም ይህ ፋብሪካ በቀን ከ10 መኪና በላይ ጣውላ አምርቶ ወደ አዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች ይልካል፡፡በተጨማሪም ከአካባቢው ከዚህ ፋብሪካ ወደ አፍንጫዋ የገባው የበሰበሰ ሳርና የእበት ሽታ በተወሰነ መጠን ረበሻት፡፡ በጸጥታ ወደዚያው አመራች፣ የተከፈተ ክፍል አልፋ ገበች። በአንድ ጊዜ ብዙ ፈረሶችን የሚለማመድበት ክብ ሜዳ አየች።ወዲያው ኩማንደር ገመዶ በጋጣው ውስጥ ካሉ ፈረሶች ጋር በቁጭት ሲያወራ ሰማች። ፈረሱ በርግጎ ለመውጣት ሞከረ።
"ተረጋጋ፣ተረጋጋ ››ይለዋል
"ምን ነካው?"ስትል ጠየቀችው…. ዞር ብሎ አላያትም ወይም ድምጿን በመስማቱ መገረሙን አላሳየም።
‹‹የምታምር ፈረስ ነች..ምን ሆና ነው?›› ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
"ምንም አልሆነችም..ግን ሁሉ ጊዜ የሆነ ነገር እንደሆነች ማስመሰል ትወዳለች…እሷ ከእኔም ሆነ ከማንም በላይ ብልህ እንደሆነች ታስባለች።
እውነታው ግን አዎ እንደምታስበው በጣም ጎበዝ ነች ፤ ለሳዕታት ያለድካም በፍጥነት መጋለብ ትችላለች ፣ በውጤቱ መጨረሻ ግን መጎዳቷ አይቀርም።ስነግራት ስለማትሰማኝ..ስትጎዳም አታሳዝነኝም"አላት፡፡
እፍኝ እህል ዝቆ በውስጥ እጁ ላይ በማድረግ ፈረሱን እያበላው ነው።
"ይህ ለእኔ የተላለፈ ማጣቀሻ ነው አይደል? እንደ ማስፈራሪያ ልውሰደው?" ።” ስትል ጠየቀችው
ኮስተር ብሎ‹በፈለግሽው መንገድ መውሰድ ትችያለሽ››አለ
‹‹እሺ..ግን ታውቃለህ አይደል..?በጣም ትሁት የሆንክ ሰው ነህ››አለችው፡፡ የእሷን ስላቅ ችላ ብሎ"ስለ ፈረስ ብዙ አታውቂም አይደል?" ሲል ጠየቃት፡፡
"ግልፁን ለመናገር…አላውቅም" ብላ መለሰችለት።
"እዚህ ለመምጣት እንዴት አሰብሽ?"
"ጁኒየር ጋብዞኝ."
‹‹ጥሩ መራጭ ነሽ››
የአለም ደም በንዴት ተንተከተከ"የጁኒየር ወይም የሌላ የማንም ሰው አይደለሁም። እኔ እደምታስበው በቀላሉ የምዘገን ሴት አይደለሁም።››
ጀርባውን አዙሮ ወደ ተቃራኒው የሕንፃው ጫፍ ተራመደ"ቆይ! ጥቂት ጥያቄዎችን ልጠይቅህ እፈልጋለሁ።"አለችው
"ጠይቂኝ"
"ገመዶ…እባክህ ከስራ ውጪ በሆኑ ጉዳዬች ላይ ማውራት እፈልጋለሁ ። የራሴን የማወቅ ጉጉት ለማርካት ነው" አለችው::
"ቴክኒኩን አውቀዋለሁ አቃቢ ህግ፡፡ እኔ እራሴ ብዙ ጊዜ ተጠቅሜበታለሁ። አንቺ ከተጠርጣሪው ጋር በቸልተኝነት ትጫወቻለሽ፣ በመዘናጋት ሊደብቀው የፈለገውን ነገር ዘርግፎ ይነግርሻል…ከዛ መራጃሽን ታጠናክሪያለሽ ።"
"እንደዚያ አይደለም ማውራት ብቻ ነው የምፈልገው."
"ስለ ምን?"
"ስለ ሶሌዎች "
"ስለ እነሱ?"
እግሩን አንፈርክኮ ቆመና፣ እጆቹን ወደ ጂንሱ የኋላ ኪስ ውስጥ አስገባ ፣ አቋሙ የሚያስፈራራ ወንድ ሆኖ ነው የተሰማት። እያናደዳት ቢሆንም ስሜቷን ቀስቅሷታል።
"ፍሰሀ እና ሳራ ደስተኛ ትዳር ያላቸው ይመስልሀል?"
ጥያቄዋ ከጠበቀው ውጭ ስለሆነበት ዓይን ዓይኗን እያየ "ምን?"ሲል አፈጠጠባት፡፡ "እንዲዚህ አትየኝ ፡ የምጠይቀው የአንተን አስተያየት እንጂ ሞያዊ ትንታኔ አይደለም።" "በእግዚያብሄር ስም … ልዩነት ምንድነው?"
"ሳራ ጆ…. ፍሰሀ እንዲያገባት የምጠብቃት አይነት ሴት አይደለችም …ለዛ ነው የጠየቅኩህ።"
"ስለ ጉዳዩ አስቤበት አላውቅም." " አብረው ይተኛሉ ?››
‹‹ በአልጋ ላይ የሚያደርጉት ወይም የማያደርጉት ነገር የኔ ጉዳይ አይደለም። በተጨማሪም
፣ ግድ የለኝም። ››
"እሺ…አቶ ፍሰሀ ሌሎች ሴቶችን ጋር ይሄዳል?"
ከጥቋቁር ዓይኖቹ ጀርባ ብስጭት ተመለከተች። ከእሷ ጋር ያለው ትዕግስት እየተሟጠጠ ነበር።
"ሳራ ጆን እንደ ስሜታዊ ሴት ነው የምታስቢያት?"
"አይ" አለም መለሰች።"ጋሽ ፍሰሀ ጤናማ የወሲብ ፍላጎት አለው ብለህ ታስባለህ?" "እንደ ምግብ ፍላጎቶቹ ከሆነ አዎ እንደዛ አስባለው።"
"ግንኙነታቸው ጁኒየር ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል?"
"እንዴት ያንን ማወቅ እችላለው? እሱን ጠይቀው።" "እሱንም መጠየቄ አይቀርም፡፡››
"አንቺን በማይመለከትሽ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገባሽ እንደሆነ የሚነግርሽ ሰው መኖር አለበት››
የሱ ስላቅ እንዲያስፈራራት አልፈቀደችም።"የወላጆቹ ግንኙነት ጁኒየር ለሶስት ያልተሳካ ትዳር ዳርጎታል… ለምን እንደሆነ ታብራራልኛለህ? ››
‹‹ይህ አንቺን የሚመለከት ጉዳይ አይደለም…አልኩሽ እኮ!!››
"የእኔ ጉዳይ ነው."ፍርጥም ብላ መለሰችለት፡፡
"እንዴት? "
‹‹ምክንያቱም ጁኒየር እናቴን ይወዳት ስለነበረ።››ቃላቱ በእርጋታ ከአንደበቷ ወጡ ፡፡
የኩማደሩ ኮስታራ ፊት የበለጠ ተኮሰታተረ ፡፡ ‹‹ማን ነገረሽ?››
‹‹ሁለታችሁም እንደምትወዷት ነግሮኛል።››
ለረጅም ጊዜ አፈጠጠባት፣ ከዚያም ትከሻውን ነቀነቀና ‹‹በአንድ ወይም በሌላ መንገድ እንወዳት ነበር…ታዲያ ምን ይጠበስ.?››
"ለዚህ ነው የጁኒየር ትዳሮች ያልሰሩት? አሁንም እናቴን በልቡ ታቅፎ ይዞ ስላለ ነው?"
" እዚህ ጉዳይ ላይ ምን አይነት አስተያየት መስጠት አልችልም."
‹‹እባክህ››
"ሰሎሜ ከጁኒየር ትዳሮች ጋር ምንም ግንኙነት ያላት አይመስለኝም። የጥፋተኝነት ስሜት ሳይሰማው በየመዝናኛ ስፍራው ከሚያገኛቸው ሴቶች ጋር ለመቅበጥ እንዲችል በየተወሰነ ዓመት ሚስቶቹን ይፈታል ።የእኔ ግምት ይሄ ነው፡፡››
የሰጠው መግለጫ እሷን ለማስከፋት ታስቦ ነበር, እናም ተሳክቶለታል፡፡ ቢሆንም ምን ያህል እንዳበሳጫት ላለማሳየት ሞከረች።
"በዚህ ጉዳይ የጥፋተኝነት ስሜት የሚሰማው ለምን ይመስልሃል?" "ጄኔቲክስ. ምን አልባት ከእናቱ የወረሰው ለስላሳ ባህሪ ይመስለኛል››
"አንተስ?"
"የማደርገው ማንኛውንም ነገር አስቤና ተጨንቄ ስለማደርገው የጥፋተኝነት ስሜት አይሰማኝም."
"ግድያ ቢሆንም እንኳን?"
ፈገግታው ጠፋ እና ዓይኖቹን ጨፈነ። "አግብተህ ታውቃለህ?"
"አይ።"
"ለምን ሳታገባም?"
‹‹ማግባት እኮ ሀይማኖታዊ ግዳጅ አይደለም …ይሄ የፍላጎት ጉዳይ ነው…ልክ እንደአንቺ ማለት ነው››
‹‹ገባኝ። እስኪ ስለ አባትህ ንገረኝ?" ቀስ በቀስ ኩማደሩ ፈረሶቹ ወደሚዝናኑበት ሜዳ ተጠጋ
….እሷም ከኃላ ከኃላ እተከተለችው ነው። ጠንከር ባለ ቀዝቃዛ እይታ ተመለከታት።
አለም "አባትህ ገና ትምህርት ቤት እያለህ እንደሞተ አውቃለሁ። ጁኒየር ዛሬ ነግሮኛል። ከሞተ በኃላ እዚህ ከነጁኒዬር ጋር ለመኖር መጣህ።"
‹‹አለም… ስለማወራው ነገር የማወቅ ጉጉት አለሽ?።"
"የማወቅ ጉጉት የለኝም። ከምርመራዬ ጋር የተያያዙ እውነታዎችን እየፈለግኩ ነው።››
"ኦህ፣ እርግጠኛ ነሽ?እንደ ጋሽ ፍሰሀ የወሲብ ሕይወት ያሉ ተዛማጅ ነገሮች ለምርመራሽ ስለምትፈልጊያቸው ነው የምትቆፍሪው?።››

❤47👍8