አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ጁኒዬር አለምን ይዞ ወደ ወላጆቹ ቤት ሲደርስ ሳሎን ያለው አባቱ ብቻ ነው፡፡አቶ ፍሰሀ ከመቀመጫቸው ተነስተው እጇን እየጨበጡ"ጁኒየር ስላገኘሽ እና እንድትመጪም ስላሳመነሽ ደስ ብሎኛል" አላት፡፡

"እኔም  እዚህ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ።"

"ደህና….ተቀመጪ››
ተቀመጠች፡፡

"ምን ትጠጫለሽ?"ሲል ጁኒዬር ጠየቃት፡፡ "ነጭ ወይን ካለ ደስ ይለኛል….  እባክህ" አለች.

አቶ ፍሰሀ  በጥቋቁር አይኖቹ ትኩር ብሎ እያያት "ነጭ ወይን,? እንዳጋጣሚ ባለቤቴም የነጭ ወይን አፍቃሪ ስለሆነች ከእኛ ቤት ጠፍቶ አያውቅም… አሁን ትመጣና ትቀላለናለች
፡፡››አላት

ጁኒየር መጥሪያውን ሲጫን የቤቱ አገልጋይ ከውስጠኛው ክፍል እየሮጠች መጣች…ነጭ ወይን አምጥታ ለአለም እንድትቀዳላት አዘዛት፡፡ወይኑ መጣና ተቀዳላት..አቶ ፍሰሀና ልጃቸው ጁኒዬር ቢራ ያዙ፡፡

‹‹ጁኒዬር ወደቤት ይዞሽ እንዲመጣ ጠይቄው ነበር..እንዲህ በፍጥነት ይሳካለታል አላልኩም ነበር፡፡››

አለም ግራ ተገባች..እናም ወደ ጁኒዬር ዞር ብላ‹‹ወደእዚህ እንድመጣ ያንተ ፍላጎት መስሎኝ ነበር እኮ››

‹‹እሱማ የእኔም ፍላጎት ነው››አላት በእፍረት አንገቱን አቀርቅሮ፡፡ አለምም ወደ ፍሰሀ ዞራ "እሺ ለምን ነበር የፈለከኝ?"አለችው፡፡

በእሷ ቀጥተኛነት ለጊዜው ያልተደሰተ ይመስላል፣ ቢሆን እሱም በተመሳሳይ መንገድ መለሰላት

"ጠላቶች እንድንሆን… አንቺን በደንብ ማወቅ እፈልጋለሁ።"አላት፡፡

"እኔም የመጣሁት ለዚህ ነው አቶ ፍሰሀ።"አለችው ፍርጥም ብላ፡፡

እሷን ትንሽ ጊዜ ወስዷ ሊያጠናት ሞከረ። "እንዴት ጠበቃ ለመሆን ፈለግሽ?"የተለመደ ግን ደግሞ ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቃት፡፡

"የእናቴን ግድያ ለመመርመር ወንጀለኛውን ለፍርድ ለማቅረብ እንድችል.››

መልሱ በድንገት ወደ ከንፈሮቿ የመጣ ነው፣ ይህም መልሷ እንሱን ብቻ ሳይሆን አለምን እራሷን አስገርሟታል። እሷ ከዚህ በፊት የእናቷን ገዳይ መፈለግ ዋና ግቧ እንደሆነ ተናግራ አታውቅም።በዚህ የእናቷ ግድያ ወንጀል ላይ እሷ ራሷም በአያቷ ዘንድ ይፋዊ ተጠርጣሪ ሆና መቅረቧ ነገሩን በቁርጠኝነት እንድትይዘው ገፊ ምክንያት ሆኗታል፡፡ በመጨረሻ ሞት አፋፍ ላይ የምትገኝ አያቷ ለእናቷ ሞት ዋና ተጠያቂ እሷ እንደሆንች በግልፅ ቃል ደጋግማ ነግራታለች።አያቷ የተናገረችው ስህተት እንደሆነ የሚያረጋግጥ ሌላ ማስረጃ እስካላገኘች ድረስ ጥፋቱን እስከ ህይወቷ ድረስ ይዛ ለመኖር ትገደዳለች ። እና አሁን ከሻሸመኔ ከተማ ሃያሎቹ ጋር ተፋጣ የምትገኝት ዋና ምክንያት ራሷን ነፃ ለማውጣት ነው፡፡

አቶ ፍሰሀ "ባል የለሽም? ልጆችስ?"ሲል ሌላ ጥያቄ ጠየቃት፡፡

"አይ የለኝም።

" "ለምን?"

"አባ" አለ ጁኒየር በአባቱ እፍረት ማጣት አፍሮ ‹‹አለም ልተዝናና እንጂ በጥያቅህ እንድታጨናንቃት ይዣት አልመጣሁም››

" ጁኒየር ምንም ችግር የለውም። ይህ የተለመደ ጥያቄ ነው።"አለች አለም፡፡

" እሺ እንደዛ ካልሽ መልስሽ ምንድነው?"አቶ ፍሰሀ ጠየቃት፡፡

"ጊዜ ወይም ዝንባሌ የለኝም."

"በዚህ በእኛ አካባቢም ተመሳሳይ ብዙ ጊዜ እና በቂ ዝንባሌ የለንም."

ጁኒየር በጠወለገ እይታ አባቱን ተመለከተው።የተነገረው አሽሙር እሱን የሚመለከት እንደሆነ ያውቃል"አባዬ የከሸፉብኝን ትዳሮቼን እየጠቀሰ ነው።››በማለት አብራራላት፡፡

"ጋብቻዎች? ስንት ነበሩ?"አለም በጉጉት ጠየቀች
"ሶስት" በማለት ተናዘዘ።

"እና አንዳቸውም እኔን አያት የማድረግ ፍላጎቱም ሆነ ብቃት አልነበራቸውም››አቶ ፍሰሀ ዋና ቅሬታውን ተናገረ፡፡

በዚህ መካከል ከፎቁ ወደታች የሚወርድ የጫማ ኳኳታ ሰሙና በተመሳሳይ ሦስቱም ዞሩ። አንዲት ሴት በተከፈተው በር ላይ ቆማ ነበር። አለም የአቶ ፍሰሀ ሚስት እና የጁኒዬር እናት መሆኗን አወቀች።  ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ፀጉሯ ድረስ ምን እንደምትመስል አእምሮአዊ ምስል ቀርጾ ነበር። ወይዘሮዋ ግን የአለምን አእምሮአዊ ምስል ተቃራኒ ነበረች።

ጁኒዬር እናቴ ጀማይካዊት ነች ስላላት..የሆነች ፈርጣም ..ጠቆር ያለች.. ከንፈረ ትልልቅ…የፀጉሯ ድሬድ መቀመጫዋን የሚነካ አይነት አድርጋ ነበር የሳለቻት…እሷ ግን ቅንጥስጥስ ያለች ቀጭን…ቀይ ቆንጆ ግን ደግሞ ስልችት ያለው ፊት ያየዘች…ሀበሻ መሳይ
ሴት ነች፡፡ጁኒዬር ያንን አፍዛዣ መሳይ ውበቱን እና ለስላሳ ባህሪውን ከማን እንደወረሰው አሁን በግልፅ ገባት ፡፡

"ሃኒ ይህቺ አለም ጎበና ነች" አለ አቶ ፍሰሀ ።

የጁኒዬር እናት ባለቤቷን ችላ ብላ ፈካ ያለ ፊቷ አብርቶ ቀጥ ያለ ቀጭን ከንፈሯ ወደቀኝ በመጠምዘዝ ‹‹አለም ወደቤታችን እንኳን በሰላም መጣሽ…ሳራ እባላለው..የጁኒዬር እናት ነኝ
››አለችና ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡

አለም ከሴትዬዋ ንግግር የፍሰሀ ባለቤት ከመሆኗ በላይ የጁኒዬር እናት በመሆኗ ኩራት እንደሚሰማት ነው የተረዳችው፡፡

"አመሰግናለሁ።"ስትል መለሰች፡፡

ጁኒየር ከተቀመጠበት ተነሳና አንድ ብርጭቆ ነጭ ወይን ቀዳና ለእናቱ አቀበላት.. ። በሚያብረቀርቅ ፈገግታ‹‹አመሰግናለው የእኔ ልጅ››በማለት ተቀበለችው፡፡

እሱም ጎንበስ ብሎ እናቱን የለሰለሰ ስርጉድ ጉንጯን ሳመ። "ራስ ምታትሽ እንዴት ነው?"

"ሙሉ በሙሉ አልተወኝም፣ ነገር ግን እንቅልፍ ረድቶኛል። ስለጠየቅከኝ አመሰግናለሁ።"

አለም የሴትዬዋን እጇች ስታይ ተገረመች …እጇ ነጭ ሲሆኑ … በአውሎ ንፋስ እንደተመታ አበባ በቀላሉ ተሰባሪ ይመስላል።

ባሏን " መቼስ ስለከብቶችና ፈረሶች እያወራህ እያሰለቸሀት ነው አይደል?"አለችው፡፡
"በራሴ ቤት ውስጥ፣ ስለምንስ ባወራ አንቺን ምን ጨነቀሽ?" አቶ ፍሰሀ ቱግ አለ፡፡ ጁኒየር ንግግራቸውን ከዛ በላይ እንዳይጠነክርና አለም ፊት እንዳያሳፍሩን ፈጠን ብሎ ጣልቃ ገባ፡፡

"እማዬ ስለ እርባታ አይደለም እያወራን ያለነው ። አባዬ ከሚስቶቼ  ወራሽ የሚሆን ልጅ ለመውለድ ባለመቻሌ እየወቀሰኝ ነበር።"ሲል አብራራላት፡፡

"ጊዜው ሲደርስ ከትክክለኛ ሴት ጋር ልጆች ትወልዳለህ››.አለችና  ወደ አለም ዘወር ብላ ጠየቀች፡- “ወ.ሪት አለም በፍፁም አላገባሁም ስትይ ሰምቻለሁ ልበል ?” ብላ ጠየቀችው።
"ልክ ነው"

"እንግዳ ነገር ነው…ቢያንስ የወንድ ጓደኛ ሊኖርሽ ይገባ ነበር፡፡››

"አለም የወንድ ጓደኛ የለኝም አላለችም እኮ

››ጁኒየር አስተካከላት. "በቃ መራጭ ነች"ሲል አከለበት፡፡

"አዎ ከጋብቻ እና ቤተሰብ ከመመሥረት ይልቅ ሙያዬን መርጫለሁ።ለጊዜው፣ ለማንኛውም ነገር ጊዜ የለኝም። ግን እናቴ የሆነ ሙያ ባለቤት ለመሆን ፍላጎት እንዳላት ገልጻ ታውቃለች?"

"እሷን እስከማውቃት ድረስ እንደዛ አይነት ምኞት አልነበራትም" ሲል ጁኒየር መለሰ፣ አለም በፀፀት ስሜት "በጣም ቀድማ በልጅነቷ ነበር የወለደችኝ" አለች።

"ምናልባት ያለዕድሜ ጋብቻ ውስጥ መግባቷ  እና ልጅ መውለዷ ወደ ሥራ እንዳትገባ አግዷት ይሆናል….ሰሎሜ የራሷን ምርጫ ነው ተግባራዊ ያደረገችው."ሲል መለሰላት፡፡
"የምታውቀውን ስለነገርከኝ አመሰግናለሁ.››

‹‹ አንድ ጊዜ እኔ እሷና ጀማል ለመዝናናት ወደወንዶ ገነት ሄደን ነበር፡፡በፍል ውሀ ስንታጠብና ስንዋኝ ከዋልን በኃላ በጣም ደክሞን ዛፍ ጥላ ስር ሳሩ ላይ ተዘርረን ሰማዩን አንጋጠን ስለ ምኞታችን ስናወራ እንደነበር ትዝ ይለኛል…ሁላችንም የዋና ልብስ ብቻ ነበር የለበስነው…እና እሷም በመሀላችን ተኝታ ነበር፡፡
44👍2