#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////
አለም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባቷ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ አያቷ የህግ ሙያ እንድታጠና አጥብቃ ትገፋፋት ነበር..በወቅቱ ምክንያቱ አይገባትም ነበር…እንዲሁ ሰዎች.. የልጅ ልጅሽ ጠበቃ ነች ወይም ዳኛ ነች እንዲሏት ካላት ምኞት ተነስታ የምትገፋፋት ይመስላት ነበር..አሁን ነው ነገሮችን ስታገጣጥም ምክንያቱ ፍንትው ብሎ የተገለፀላት፡፡
አለም በትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪ ነበረች እና በመጨረሻ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍልም ወርቅ ሜዳሊያ አጥልቃ ነበር የተመርቀችው። የህግ ትምህርት አያቷ የመረጠችለት እና በእሷ ዘንድ በልጅነቷ ያላገኘችውን ሞገስ ለማግኘት ስትል የገባችበት ሙያ ነበር፣ ግን ከተማረችው በኋላ አያቷን ደጋግማ አመሰግናታለች… ምክንያቱም በጣም የሳባት እና ያስደሰታት መስክ ነው። የማወቅ ጉጉት ያለው አእምሮዋ ወደ ውስጡ የህግ ዕውቀቷቹን መጦ ሲያስገባ በደስታ ነው፡፡ ወደስራም ስትሰማራ በሙሉ የራስ መተማመንና በከፍተኛ የስራ ንቃት ነበር፡፡
አቃቢ ህጉ የእጅ ሰዓቱን ተመለከተ.. ከዚያም ሲጋራውን በከንፈሮቹ መካከል አስገብቶ ቆመና ኮቱን ከመስቀያው አነሳ "ያለ በቂ ማስረጃ የግድያ ክስ እንደገና መክፈት አልችልም። ታውቂለሽ። ከሀያአምስት አመት በፊት ተፈፅሞ የነበረ ወንጀልን ወደኋላ ተጉዞ መረጃ ማሰባሰብ ብራንድ ልብሶችን ለብሶ በመዘነጥ የአዳም ዘርን እንደማማለል ቀላል ስራ አይደለም…..እና መጀመሪያ እኔን አሳምኚኝ..ምን አልባት ከዛ በኋላ ስለክሱ ሁኔታ መልሰን እንንጋገርበት ይሆናል››
ልቅ የሆነ ንግግሩን ችላ ብላ በብስጭት ተመለከተችው፡አጠያየቋ በጣም ድፋረት የታከለበትና እና ቅንነት የጎደለው መሆኑን ታውቃለች።እሷ በእሱ ቦታ ብትሆን ከረጂም ደቂቃ በፊት ክፍሉን ለቃ ትወጣ ነበር፡፡
"አየሽ አለም፣ ይህ የምትጠይቀኝ ጉዳይ እንደምትይው ቀላል አይደለም…እነዚህ ሰዎች በደቂቃ ውስጥ ይህንን ቢሮ ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ መቀየር የሚችሉ ናቸው። አንገቴን ልታስቀነጥሺኝ ካልፈለግሽ በስተቀር ይሄንን የአያትሽን ከንቱ ጥርጣሬ መልሰሽ ታነሺብኛለሽ ብዬ አልጠብቅም››ብሎ መንገዱን ቀጠለ፡፡ወደ ቢሮው ደጃፍ ሲያመራ ተከተለችው
"ክቡር አቃቢ ህግ ይሄ ለእኔ ጥልቅ ትርጉም ያለው ጉዳይ ነው። እንዴት እምቢ ትለኛለህ..የምታስበው ስለራስህ ብቻ ነው?።"
"እውነትሽን ነው እኔ እራስ ወዳድ ነኝ።
"ሲል መለሠላት።
"በሌሎች ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረጌን እንዳለ ሆኖ ይህን ግድያ እንዳጣራ ፍቃድ ስጠኝ።"ሙጭጭ አለችበት፡፡
"እኛ ምን አይነት ውዝግብ እንዳለብን ታውቂያለሽ? መአት አንገብጋቢ ጉዳዮች እጃችን ላይ አሉ ፤ሀያ ምናምን አመት የተረሳ...መዝገብ እራሱ በአቧራ የተበላ ጉዳይን በቀላሉ ለፍርድ ማቅረብ አንችልም።"
"እሺ በትርፍ ሰዓቴ እሰራለሁ፣ ሌሎች ኃላፊነቶቼ ላይ በምንም አይነት ተፅዕኖ እንዲያሳድር እላደርግም፣ለዛ ቃል ገባልሀለው ።"
"አለም"
"እባክህ … ግርማ በቅርቡ አንድ ተጫባጭ ፍንጭ ከላገኘሁ ..ጉዳዩን እርግፍ አድርጌ ተወዋለሁ...ከዚያ በኋላ ስለ ጉዳዩ በጭራሽ ከእኔ አትሰማም.››
በትኩረት ተመለከታት እና ፊቷን አጠና ። "ለምን እንዲህ አይነት ውስብስብ ነገር ውስጥ ራስሽን ታስገቢያለሽ ..እንደማንኛውም ወጣት ዘመናዊ ሴት .ዘና ያለ የህይወት መንገድን አትመርጪም፡፡ ።"
ፊቷን አኮስታተረችበት ።
"እሺ፣ እሺ፣ ምርመራውን መጀመር ትችያለሽ፣ ነገር ግን በትርፍ ጊዜሽ ብቻ ነው። ተጨባጭ የሆነ ነገር ይዘሽ ነይ። አለበለዛ ውሳኔዬን ታውቂዎለሽ .አሁን ከቀጠሮዬ አዘግይተሽብኛል።››ብሎ በቆመችበት ጥሏት ሄደ፡፡
በእርካታ ተነፈሰች፡፡ሸክሟ ከባድ ነበር ፡፡ እያቷ በእናቷ ግድያ ላይ ያላት መረጃ የተወሰነ ነበር። በጋዜጣ ላይ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ እናቷን በመግደል የተወነጀለው ሰው የአእምሮ ብቻ ሳይሆን የመስማትም ችግር እንዳለበት ነው፡ ።እነሱ መሠረታዊ እና ቀላል ችግሮች ነበሩ. የአእምሮ ዝግመት ችግር የነበረው ሊቁ የተባለው ሰው በግድያው ቦታ በተያዘበት ጊዜ የሟቾ እናቷን ደም በጠቅላላ ልብሱ ላይ ተነክሮ እንደነበረ ተዘግቦ ነበር።በተጨማሪም በተያዘበት ወቅት ተጎጂዋን ገድሎበታል የተባለበትን የቀዶ ጥገና መሳሪያ በእጁ ይዞ ነበር።በዛ ምክንያት ወዲያው በቁጥጥር ስር ውሎ ታስሯል፣ ተጠየቋል
እና ተከሷል። በቀናት ውስጥ ነበር ችሎት የቀረበው። ወዲያው ዳኛው ካለበት የጤና እክል የተነሳ ለፍርድ የመቅረብ ብቃት እንደሌለው አውጀው በመንግስት የአእምሮ ሆስፒታል ውስጥ አንዲታሰር ትዕዛዝ አስተላለፉ።ተጠርጣሪው ግን ወደአእምሮ ሆስፒታል ተመዘዋወሮ ብዙም ሳይቆይ እራሱን አጠፋ ተባለ፡፡ በውቅቱ ወንጀለኛውን አሳዶ ለመያዝ
..ከዛም ፍርድ ለማስተላለፍና ፋይሉን ለመዝጋት የነበረው ጥድፊያ ያስደነግጣል፡፡ እናም ከፍተኛ ጥርጣሬም በአለም አእምሮ ውስጥ ጭሯል፡፡
በሶስተኛው ቀን ያገኘችውን ተጨማሪ መረጃ ይዛ ዋና አቃቢ ህጉ ፊት ለፊት ቀረበች፡፡መረጃዎቹን ካቀበለችው በኃላ
‹‹የእረፍት ቀን እንዴት ነበር?›››ስትል ለጫወታ መጀመሪያ ጠየቀችው፡፡
"ድንቅ ነበር. ካንቺ የበለጠ ውጤታማ ቀናቶችን አሳልፌለሁ ብዬ አስባለው። ብዙ ነገሮችን የማንበብ እድል ነበረኝ።"
ፋይሉን ገልጦ ይዘቱን መቃኘት ጀመረ። "እህም" የመጀመሪያ ንባቡ ትኩረቱን ለመሳብ በቂ ነበር። ወንበሩ ላይ ተደግፎ በጥንቃቄ በድጋሚ አነበበው።
"ይህ ዶ/ር ታደሰ የተባለው … ሊቁ የታሰረበት የነበረበት የአእምሮ ሆስፒታል ሐኪም ነው?"
‹‹አዎ ነው››
‹‹ታዲያ አግኝተሸ ማነጋገር አልቻልሺም?››
"አልቻልኩም እንዳለመታደል ሆኖ ከጥቂት ወራት በፊት ሞቷል." "አስደሳች ነው."
"አስደሳች?" አለም በንግግሩ ተበሳጨች። ወንበሯን ትታ ዞረች እና ከኋላው ቆመች
"ይሄ ታደሰ የተባለው ዶክተር ሊቁ የግድያ ወንጀል ለመፈፀም ብቃቱ እንዳለው ሙያዊ ውሳኔ ላይ ሲደርስ ለመጨረሻ ጊዜ የተከታተለው ሌላ የስነ አእምሮ ሃኪም ግን ሊቁ የተባለው ግለሰብ የአእምሮ በሽተኛ ቢሆንም ምንም አይነት ሰውን የማጥቃት ዝንባሌ አሳይቶ እንደማያውቅ በሪፖርቱ አስፍሯል.. ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት እንደሌለው እና
አመፀኝነትም ታይቶበት እንደማያውቅ ተናግሯል፡፡ እና በዶክተሩ ሞያዊ አስተያየት መሠረት እሱ እኔን ዋጋ እንዳስከፈለኝ አይነት የግድያ ወንጀል መስራት እንደማይችል ነው ያረጋገጠው።ገደለ በተባለው ሰው ላይ ሁለቱ ባለሞያዎች የተለያ አይነት ምልከታ ነበራቸው…ይሄም ከመዝገቡ ጋር ተያይዞል..ዳኛው የባለሞያዎቹን ውሳኔ ሚዛናዊነት ለመጠበቅ የሶስተኛ ባለሞያ አስተያየት መጠየቅ ሲገባቸው ባልታወቀ ምክንያት የአንደኛውን አስተያየት ውድቅ አድርገው የሌለኛውን ተቀብለዋል፡፡በአጠቃላይ…ሊቁ የተባለው ሰው እናቴን አልገደላትም የሚል በጣም ጠንካራ እምነት አለኝ።›› አቃቢ ህጉ ሌሎች በርካታ አጭር መግለጫዎችን አነበበ፣ ከዚያም አጉተመተመ፡-
"በአጭር ቀናት ከዚህ የበለጠ ተአምራዊ የሆነ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ አልችልም። ጉዳዩ ሃያ አምስት አመት ያስቆጠረ ነው። ተስፋ የማደርገው ይሄ ጉዳዩን በ ዳኞች ፊት ለማቅረብ በቂ ምክንያት ነው። በተጨማሪም የዓይን እማኝ የማግኘትም ትንሽም ቢሆን እድል አለኝ
።"
አቀቢ ህጉ‹‹አለም.››ሲል ተጣራ "አቤት"

❤44👍5