አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
በፍርድ ቤቱ የስብሰባ ክፍል ውስጥ የነበረው ትእይንት መቀበል ከምትፈልገው በላይ አንቀጥቅጧታል።ግን ደግሞ ጭንቅላቷን ወደ ላይ ቀና አድርጋ እና ደረቷን ነፍታ ነበር ቢሮውን ለቃ የወጣችው ።እራሷን ለመቆጣጠርና የድንጋጤዋንና የፍራቻዋን ቅንጣት እንኳን ለእነሱ ሳታሳይ ስብሳባውን በድል ለማገባደድ ያደረገችው ጥረት የመታፈን አይነት ስሜት  እንዲሰማት  ነበር  ያደረጋት፡፡ስብሰባው  ባቀደችው  መሰረት  ነው የተካሄደው፣ እስኪጠናቀቅ ድረስም በጣም እንደተረጋጋች ነበር።

አለም ወደ ሆቴሏ ከተመለሰች በኃላ ሱፍ ኮቷን አልጋ ላይ ወረወረች።እጆቿ በላብ ተጠምቀው ስለነበረ እርጥብ ነበሩ እና ጉልበቶቿ መንቀጥቀጣቸው አሁንም  አላቆሙም
ከመደንገጧ የተነሳ የማቅለሽለሽ ስሜት ነበራት። አልጋዋ ለይ ተዘርራ ተኛችና ስለቆይታዋ በምልሰት ማሰላሰል ጀመረች፡፡

በጣም መጥፎው ጉዳይ ወደፊት የሚከሰተው እንደሆነ ብታስብም ለጊዜው ደስ ብሏታል፣ ቢሆንም ነገ ተነገ ወዲያ ስለሚሆነው ነገር መፍራቷ አልቀረም። ዛሬ ያገኘቻቸው ሶስት ሰዎች በዋናነት ዳኛው ደግሞ በተዘዋዋሪ ከእናቷ ጋር የሚያያይዝ ታሪክ ያላቸው ናቸው። ከዘመናት በኋላ እነሱን መጋፈጥ ቀላል ውሳኔ አልነበረም እና በምንም አይነት ሁኔታ እሷን በማየታቸው ደስተኞች ሊሆኑ እንደማይችሉ መጀመሪያም ግምቷ ነበር፣ እናም ካገኘቻቸው
በኃላም የተረዳችው ያንን ነው..ትንሽም ቢሆን ጁኒዬር ካልሆነ በስተቀር ኩማንደሩና አቶ ፍሰሀ ጥላቻቸው በግልፅ ግንባራቸው ላይ ይነበብ እንደነበረ ታዝባለች፡፡

አቶ ፍሰሀ በሻሸመኔ ከተማና በአካባቢው በጣም ሀብታም እና ኃያል ሰው ነው። ያንን ደረጃ ያገኘው ደግሞ በመልካም አመራር እና በስራ ትጋቱ ብቻ አይደለም። ዕድሜ ልኩን ያካበተውን ሀብት ጠብቆ ለማቆየት ባለው ኃይል ሁሉ በስውርም ሆነ በግልፅ ሲዋጋ እና ሲፋለም ኗሯል።አቶ ፍሰሀ እና ቤተሰቡ ላይ እያቀረበችውን አይነት ክስ ማቅረብ እንደእብደት እንደሚቆጠር ታውቃለች..ከዳኛው ፊት ላይ ያነበበችውም ያንኑ ስሜት ነው፡፡ አይደለም በጥርጣሬ ግድያ ቀርቶ እጅ ከፍንጅ ተኩሰው ሲገድሉ ቢታዩ እንኳን ባርቆባቸውን ነው በሚል ተስተካክሎና ለዛም ምስክርና ማስረጃ ተጠናክሮ በቀላሉ ነፃ እንዲወጡ እንደሚደረግ በቀላሉ መገመት ትችላለች፡፡ግን ከእሷ ጋር መጋፈጥም ቀላል እንዳልሆነ በሂደት እንዲረዱ እንደምታደርገቻው እርግጠኛ ነች፡፡

ስለ ጁኒየር ስታስብ የተሰማት የተለየ ነገር ነው፡፡በሴቶች ዙሪያ ያለው አመለካከት የተለየ ስለሆነ አቀራረቡም ከአባቱና ከኩማንደር ጓደኛው በመጠኑም ቢሆን የሚለይ ማራኪ ሆኖ ነው ያገኘችው። አለም በጉርምስና ዕድሜው ላይ እያለ ካያቸው ፎቶ ግራፉ ብዙም አልተለወጠም። መልከ መልካምነቱን ፍላጎቱን ለማሳካት እና እንስቶችን ለማማለል ሲጠቀምበት እንደኖረ ታውቃለች። ለእሱ ሰውን ከመግደል ይልቅ በፍቅር መውደቅ ቀላል እንደሚሆንለት አሰበች፡፡እናም በገዛ ሀሳቧ ፈገግ አለች፡፡

ቀጥሎ ወደአእምሯዋ የተሰነቀረው ኩማንደር ገመዶ ነው፡፡እስከአሁን ኩማንደሩን ለማንበብ እና እንዲህ ነው ብሎ ለመተንበይ በጣም ከበድ ነው የሆነባት.. እርግብ ይሁን እባብ… ወይንም ሁለቱንም አዳብሎ የያዘ እስስት ለመለየት ከባድ ነው የሆነባት፡፡ ስለ እሱ የነበራት ግንዛቤ ትንሽ የተለየ ነው።በስብሰባ ክፍል ውስጥ እንደሌሎቹ አይኖቹን ማየት አልቻለችም። እሱ ከአያቷ የፎቶ ማከማቸ ሳጥን ውስጥ የልጅነት ፎቶውን ካየችው ከዛ ወጣት ልጅ በእጅጉ የተቀየረ ….የበለጠ ከባድ እና ጠንካራ የሆነ መስሎ ታየት። የመጀመሪያ እይታው ተንኮለኛ፣ ወዳጃዊ ያልሆነ እና አደገኛ መስሎ ነበር የተሰማት።ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ እናቷን እንደገደለ እርግጠኛ ነች። እናቷ ሰሎሜ በተከሳሹ ሊቁ እጅ አልተገደለችም።

"አለም ክሱን ከእንደገና ማስከፈት እና የእናትሽን እውነተኛ ገዳይ ለፍርድ ማቅረብ የአንቺ ኃላፊነት ነው፡፡" በየቀኑ ለራሷ የምትነግረው ጉዳይ ነው።"ይህ ለእናትሽ ልታደርጊው የምትችይው ትንሹ ነገር ነው."

ብዙውን ጊዜ አያቷ በቤቱ ውስጥ ተበታትነው ከነበሩት ብዙ የድሮ ፎቶግራፎች ውስጥ አንዱን በተደጋጋሚ ጊዜ በጥንቃቄ ይመለከቱ ነበር።ያ ፎቶ ደግሞ እናቷ ሰሎሜ በአፍላ ወጣትነቷ ዘመን ከእድሜ እኩዬቿ ጁኒዬር እና ገመዶ መሀከል ቆማ የተነሳችው አሮጌ ፎቶ ነው፡፡ ፎቶውን መመልከት ሁልጊዜ እንድታዝንና እና በናፍቆት እንድታለቅስ ያደርጋታል፣ እና የልጅ ልጇ ምንም ነገር ብታደርግ ሊያስደስታት አይችልም ነበር።ይሁን እንጂ እስከ ጥቂት ወራት ድረስ አለም ጎበና እናቷ ሰሎሜን በመግደል ተጠርጣሪው ማን እንደነበረ አታውቅም ነበር።ያንን ሚስጥር ያወቀችበት እለት በአለም ሕይወት ውስጥ በጣም ጨለማው ቀን ነበር።

ትዝ ይላታል በወቅቱ የስራ ገበታዋ ላይ ሆና እየሰራች ሳለ….ከሜቅዶኒያ ተደውሎላት በአስቸኳይ ድረሺ ስትባል በፍጥነት ነበር የሄደችው… ፡፡ተቋሙ ጸጥ ያለ፣ በበጎ ፍቃደኞች እና በተንከባካቢ ባለሙያዎች የተሞላ ነበር። አያቷ ወደ ሆስፒታል ተወስደው ነበር…. ወዲያው ወደሆስፒታል አመራች፡፡ በሽታዋ የእርጅና በሽታ የተጫጫነው ነበረ፡፡ተስፋ መቁረጥ እና እርጅና ከካንሰር በሽታቸው ጋር ሲደመር የመጨረሻ እስትንፋሳቸውን እየሳቡ እንደሆነ ገባት፡፡ ዶክተሮቹንም ስታናግር አያቷ አስጊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ተነገራት። ፀጥ ወዳለው የአያቷ ክፍል ገብታ ወደ አልጋቸው ተጠጋች። የአያቷ አካል በሚታይ ሁኔታ ተዳክመው ነበር።አለም የጎበኘቻቸው ከሳምንት በፊት ስለሆነ በነዛ ጥቂት ቀናት ውስጥ እንደዛ አይነት ጉልህ ለውጥ ማየቷ አስደነገጣት።አያቷ መላ አካላቸው ድቅቅ ብሎ ቢደክምም ዓይናቸው ግን ህያው ነበር፣

"እዚህ አትግቢ"  ትንፋሿቸውን አጠራቅመው   ጮሁባት "አንቺን ማየት አልፈልግም
…በአንቺ ምክንያት ነው!"

"ምንድነው አያቴ?" አለም በጭንቀት ጠየቀች።

"ምንድን ነው የምታወሪው?" "እዚህ አልፈልግሽም."

አለም አያቷ እሷ ላይ ባሳዩት ብስጭት እና ጥላቻ በመሸማቀቅ ወደ ሐኪሙ እና ወደ ነርሶች ዞር ብላ ተመለከተቻቸው። "ልታየኝ ለምንድነው የማትፈልገው? ያለዋት ብቸኛ ዘመድ እኔ ነኝ…የልጅ ልጇ ነኝ፣››በእፍረት ተውጣ ልታስረዳቸው ሞከረች፡፡

አያትዬው ወቀሳቸውን ቀጠሉ"እናትሽ ባንቺ ጥፋት ነው የሞተችው፣ ታውቂያለሽ፣ ባንቺ ምክንያት ባይሆን ኖሮ ልጄ አትሞትም ነበር. . " አያቷ ማልቀስ ጀመሩ…..አለም ምታደርገው ነገር ጠፋት ፡፡

"ለእናቴ ሞት ተጠያቂዋ እኔ ነኝ እንዴ?"
የአይቷ አይኖች ከተደበቁበት ፈጠው ወጡ። "አዎ" ብላለው በቁጣ አረጋገጡላት።

"እኔ እናቴ ስትሞት ገና ሕፃን ነበርኩ እኮ፣ ጨቅላ ህፃን" ስትል ተከራከረች፣የአያቷን የአእምሮ ጤንነትም መጠራጠር ጀመረች፡፡"እንዴት በጨቅላ እድሜዬ የምትይውን ማድረግ እችላለሁ?"

" ጠይቂያቸው።"
‹‹ማንን አያቴ? ማንን ልጠይቅ?"

"የገደሏትን...ፍሰሀ… ልጁ ጁኒዬር እና ኩማንደር ገመዶን… እናም አንቺም ነበርሽ አንቺ ነሽ "አያቷ ንግግራቸውን ሳይቆጩ ጥልቅ ኮማ ውስጥ ገቡ፡፡ ከዛ በኋላ አለም ከክፍሉ በዶክተር እየተመራች ወጣች። በገዛ አያቷ የቀረበባት አስቀያሚው ክስ እስክትደነዝዝ ድረስ ነበር ያስጨነቃት፡፡ በአንጎሏ ውስጥ ተንሰራፍቶ ማሰቃየት ብቻ ሳይሆን ነፍሷ ድረስ ዘልቆ ነው ያጠቃት ።አያቷ ለእናቷ ሞት እሷን ተጠያቂ አድርገው እንደሚያስቧት ከሰማች ጊዜ በኋላ ስለእናቷም ሆነ ስለአስተዳደጓም ወደኋላ መለስ ብላ እንድታስብ ተገደደች፡፡ አያቷ ከእሷ ጋር የነበራት ግንኙነት ለምን የሻከረ እንደነበረ ሁል ጊዜ
42👍3🔥2