#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////
ጤና ይስጥልኝ..ከዞኑ ዋና አቃቢ ህግ ቢሮ ክብሩ አቃቢ ህግ አቶ ግርማን ወክዬ ነው የመጣሁት ….ስብሰባው በእኔና እና በእናንተ መካከል ይደረጋል ማለት ነው፡፡››የሚል ያልተጠበቀ አይነት አጭር ማብራሪያ ሰጠች፡፡
ከመሀከለኛው ወንበር የተቀመጡት በእድሜያቸው መጨረሻ ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ሰው"ምንም ችግር የለውም ለአንቺ እና ለሀለቃሽ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኞች ነን…እኔ ዳኛ ዋልልኝ እባላለው፡፡እሱ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኩማንደር ገመዶ ይባላል፡፡ሁለት ሰዎች ተራ በተራ እየጠቆመ። "እሳቸው አቶ ፍሰሀ ይትባረክ ይባላሉ እሱ ደግሞ ልጃቸው ጁኒየር ይባላል።የሶሌ ኢንተርፕራይዝ ዋና እና ምክትል ስራአስኪያጅና ባለቤት ናቸው፡፡የሶሌ ኢንተርፕራይ ማለት ከተማዋ የጀርባ አጥንት የሆኑትን በጣም
በርካታ ድርጅቶችን በጥምረት የሚያስተዳድር ግዙፍ ድርጅት ነው፡፡አቶ ፍሰሀ እና ልጃቸው በከተማዋ እጅግ የተከበሩ እና የተመሰገኑ ግለሰቦች ናቸው፡፡››ሲሉ የማስተዋወቅና የመግቢያ ንግግር አድርገው ከጨረሱ በኃላ ራሷን እንድታስተዋውቅ አይን አይኗን ይመለከቷት ጀመር፡፡
አለምም የዳኛውን ማብራሪያ በፅሞና ስታዳምጥ ከቆየች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህ ከፊት ለፊቷ ያሉትን ዳኛው የዘረዘሯቸውን ሶስት ሰዎች በማየቷ እንግዳ እና ሀይለኛ የማወቅ ጉጉት በውስጧ ሲንተገተግ ተሰማት፡፡በውስጧ ለእነሱ ያዳበረችው ጥላቻም ሲገለባበጥ ይታወቃታል፡፡ እነሱ ስለእሷ እና ስለ ስብሰባው አለማ ለማወቅ እንደጓጉ ሁሉ እሷም እነሱን ለማወቅ ፈልጋለች፣
አለም መጀመሪያ አቶ ፍሰሀን ነው የተመለከተችው….በእድሜ ከዳኛው ብዙም የሚያንስ አይመስልም…ግን እንደዳኛው ግርጅፍጅፍ አላለም፡፡ሰውነቱን በትኩረት ላየ‹‹አሁንም ገና እጅ አልሰጥም ››እያለ የሚፎክር ይመስላል፡፡ፊቱን በትኩረት ስትመለከት መሰላቸቱን ታዘበች፡፡የበጋው የከረረ ጸሀይ እና ፀሀይን ተከትሎ ያለው ሙቀት ያደከመው ይመስላል፣ የማሰብ ችሎታ ያላቸው የሚመስሉ ደማቅ ጥቋቁር አይኖቹ አፈጠጡባት።
አለም ከእሱ አይኗን ነቀለችና ቀጥሎ ወደተቀመጠው ኩማንደር አዘዋወረች፡፡ሙሉ የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ነው፡፡ጭንቅላቱ ላይ ያጠለቀው የፖሊስ ኮፍያ ወደታች አዘቅዝቆ ብድር እንዳለበት ሰው ከፊል ፊቱን እንዲሸፍን አድርጎታል፡፡ እድሜው አርባዎቹ አጋማሽ ላይ እንዳለ ብትገምትም ሰውነቱ ግን አሁንም የጎረምሳ ነው…ከፊቱ ላይ ምንም ማንበብ አልቻለችም ፡፡ቀዝቃዛና ስሜታ አልባ ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡ አካሉ ብቃት ያለው እና ጠንካራ ይመስላል። ማንም ሰው ከእሱ ጋር አካላዊ ፀብ ውስጥ ገብቶ መጣላትን ይጸየፋል። በዛ ላይ ጨካኝና ተንኰለኛ መሆኑን በእይታ እንኳን መገመት ያን ያህል ከባድ አይደለም፡፡ በመጨረሻ ጁኒዬርን ተመለከተች፤በእድሜ ከኩማደሩ ጋር እኩያ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ በሌሎች ነገሮች ግን ተቃራኒ ናቸው፡፡ጁኒዬር ከሁለቱም በተለየ ገራገር ሰው ይመስላል፡፡ፈገግ ሲል ልዩ አይነት መስህብ አለው ። ቀጥ ያሉ ነጭ ጥርሶቹ ብልጭ ድርግም ሲያደርጋቸው ቀልብን ይገዛሉ፡፡ ጥቁር ደማቅ አይኖቹ ከአባቱ በተለየ የጠለቀ ሀዘን ይነበብባቸዋል፡፡ ደግሞ ውብ ነው፡፡የወንድ ቆንጆ፡፡
በሽርፍራፊ ሰከንዶች ሁሉንም ገምግማ ካጠናቀቀች በኃላ ጉሮሮዋን አሟሸችና ስሟን ለመስማት በጉጉት እየጠበቁ ወዳሉት አራት ጥንድ አይኖች እየተመለከተች ።
"እኔ አለም ጎበና እባላለሁ፣ ጎደኞቼ አሌክስ ይሉኛል፡፡የሶሎሜ ሴት ልጅ ነኝ።"አለች
ንግግሯን ተከትሎ በቤቱ ኒዩክሌር ቦንብ የፈንዳ ይመስል በሶስትም ሰዎች ላይ የታየው ድንጋጤ የተለየ አይነት ነበር፡፡ዳኛው ግን ምኑም ስላልገባቸው የሌሎቹ መደንገጥ ድንግርግራቸው እንዲወጣ ነው ያደረገው…ለተወሰኑ ደቂቃዎች በክፍሉ ፍፁም አይነት ዝምታ ተንሰራፋ።
ዳኛው ግራ በመጋባት "ሰሎሜ ማን ናት?"ሲሉ ጠየቁ።
አቶ ፍሰሀ ወንበሩ ላይ እንደ ተሰባበረ አሻንጉሊት ወደ ኋላ ተንሸራተተና
"አንቺ…የሰሎሜ ሴት ልጅ….?
አምላኬ..እኔ አላምንም." አለ፡፡
ጁኒየር በሹክሹክታ" የማይታመን ተአምር።አንድ ሰው ህልም ነው ቢለኝ ደስ ይለኛል?" ሲል ተሰማ፡፡
በጡረታ መውጫው በር ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ዳኛ አሁንም ግራ እንደተጋቡ ነው። ሁሉም ድንጋጤ ውስጥ ስላሉ ለእሳቸው ማንም ትኩረት አልሰጠም።አባትና ልጅ ፊቷን በደንብ ለማጥናት አፈጠጡባት …አይኖቾ ከዘመናት በፊት ከሚያውቋት እናቷ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለቸው በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል።በደንብ ልብሱ ላይ የወታደር ኮፍያ ያጠለቀው ኩማንደር አሁን በትካዜ እግሯቹን እያወዛወዘ እንደሆነ አስተዋለች፡፡
"ከዚህ ሁሉ አመት በኋላ እዚህ ምን ልትሰሪ መጣሽ ?" አቶ ፍሰሀ ነው ያለይሉኝታ የጠየቋት።
‹‹ምን ልትሰሪ መጣሽ ነው..?ወይስ እንኳን ደህና መጣሽ?››በማሽሞጠጥ መልስ ሰጠች፡፡
"ስንት አመት ሆነሽ?" ጁኒየር የጠየቀው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር፡፡
"ሃያ አምስት." አለም ትክክለኛ እድሜዋን ነገረችው፡፡
"አያትሽ እንዴት ነች?"
"በአሁኑ ጊዜ አርጅታለች..በሜቅዶኒያ የአረጋዊያን መንከባከቢያ ተቋም ውስጥ ነው የምትገኘው…የጡረታ ደሞዟን ይዛ እዛ ገብታለች..በካንሰር በሽታ ተይዛ የመሞቻ ጊዜዋን እየተጠባበቀች ነው።
ማለቴ ኮማ ውስጥ ነች።››
"ይህን በመስማቴ አዝናለሁ."አለ ጁኒዬር፡፡
"አመሰግናለሁ።"ስትል በትህትና መለሰችለት፡፡
"ይህን ሁሉ ጊዜ የት ነበር የምትኖሪው?"አቶ ፍሰሀ ነው ጠያቂው፡፡
ህይወቴን በሙሉ አዲስ አበባ ነው የኖርኩት፡፡ቢያንስ እኔ እስከማስታውሰው ድረስ። እዚያው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን አጠናቅቄ ወደ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍልን ተቀላቀልኩ።ከአራት አመት በፊት ነው ግራጅዌት ያረኩት..እና ሶስት አመት እዛው አዲስአበባ አንድ የውጭ ካምፓኑ ውስጥ ተቀጥሬ ስሰራ ነበር..እና አሁን ለዞኑ ምክትል አቃቢ ህግ ሆኜ ከተመደብኩ አንድ ሳምንት ሆነኝ ።"
"የህግ ትምህርት ቤት ተመርቀሽ….እዚ የእኛ ዞን አቃቢ ህግ ። ደስ የሚል ነው››ጁኒየር በፈገግታ ተውጦ ተናገረ ፡፡
በዋናው አቃቢ ህግ ጥያቄ አቅራቢነት ይህንን ስብሰባ እንዲያዘጋጁ የጠየቁትና ያዘጋጁት አዛውንቱ ዳኛ ሁኔታው ምንም አላመራቸውም… ፡፡
"እንደዚህ አይነት ልብ የሚነካ አይነት መገናኘትን እጠላለሁ፣ ግን አሁንም በጨለማ ውስጥ ነኝ..ስለሚካሄደው ነገር ምንም የገባኝ ነገር የለም፡፡››ሲሉ ብሶታቸውን ተናገሩ፡፡
‹‹ሶሎሜ ማለት የእሷ እናት ነች፡፡እሷ ከመወለዷ በፊት የጁኒዬርና የኩማንደሩ የቅርብ ጓደኛ ነበረች፡፡ከዛም አልፏ ቤተሰብ ነበርን….ነፍሷን ይማርና ፈፅሞ የማይለያዩ የልብ ጓደኛሞች ነበሩ…. ››ከዚያም ጥቋቁር አይኖቹ ደመና አጠላባቸውና በሀዘን ራሱን ነቀነቀ..እና ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ "ሞቷ ለሁለችንም ከፍተኛ ሀዘን ያስከተለ ነበር….ክብር ዳኛ … የገዳዩን ችሎት እኮ እርሶ ነበር ያስቻሉት…የእኔ የእርባታ ግቢ ውስጥ አንድ እብድ በቢላዎ ወግቶ ከገደላት በኋላ ራሱን እስር ቤት ውስጥ ያጠፋው…፡፡››
የዳኛው ፊት ሲጠቁር በግልፅ ተመለከተች‹‹እኔ እንጃ ትዝ አላለኝም…የሽማግሌ ነገር ስንትና ስንት ችሎት አስታውሳለው ብለህ ነው?››በማለት ሸፋፍነው ለማለፍ ሞከሩ፡፡
አቶ ፍሰሀ ራሱን ለመቆጣጠር የተወሰነ ጊዜ በፀጥታ አሳለፈና። " ለማንኛውም ስለ አለም ሆነ ስለ አያቷ የሆነ ነገር ስንሰማ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያችን ነው።
ለማናኛውም እንኳን ወደእናትሽ የትውልድ ከተማ በሰላም መጣሽ››አላት፡፡

❤53👍3😢2🔥1