#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ
‹ከሃያ ደቂቃ በኋላ ቢሮዬ እንገናኝ።››
በእሺታ ራሷን ነቀነቀች፣ ከዚያም አልፋው ጥላው ሄደች፡፡
ከግማሽ ሰአት በኋላ ራሄል ቢሮው መጥታ ከጠረጴዛው ማዶ ተቀመጠች፣ በአንድ እጇ እስክሪብቶ፣ በሌላ እጇ ማስታወሻ ደብተር ይዛለች። ሁኔታዋ አስገረመው ፡፡
ዶ/ር ዔሊያስ መናገር ጀመረ ‹‹ፀጋ በቴክኒካል ተርሙ ሄሚፕሌጂያ ተብሎ የሚጠራ በሽታ ተጠቂ ነች፡፡በሌላ አነጋገር ሴሬብራል ፓልሲ ታማሚ ነች ማለት ነው፡፡ በሰውነቷ አንድ ጎን በግራ እጇ እና በግራ እግሯ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮባታል..አጥንቶቾ በጣም ደካማ ስለሆኑ እንደልብ ለመንቀሳቀስ ትቸገራለች…በተወሰነ መልኩ የመስማትና ቃላቶችን አቀላጥፎ የማውራት ችግርም አለባት።የእሷን ጤና ሁኔታ ለማሻሻል በሚደረገው ሂደት ውስጥ የሚሳተፉትን - ፊዚዬ ቴራፒስት ጨምሮ፣ ብዙ ባለሞያዎች አሉ.. እና እያንዳንዱን መቼ መቼ ማየት እንዳለባት አስረዳት፡፡
‹‹በተጨማሪም የጆሮ ኢንፌክሽንን እየተዋጋች ስለነበረ አንቲባዮቲክ ትወስዳለች።››ዔሊ የራሔልን እይታ በመሸሽ እስክሪብቶውን አንሥቶ መሞነጫጨር ጀመረ።
ራሄል ትዕግስት በማጣት‹‹ዶክተር ሌላ ልትነግረኝ የሚገባ ነገር እንዳለ ይሰማኛል››አለችው.
‹‹ትሁት ከጊዜ ወደ ጊዜ በንዴት በሽታ እየተሰቃየች ነው ። ስለዚህ ስሜቷን በጥንቃቄ መከታተል እና የሚያበሳጮትን ነገሮች ማስወገድ ያስፈልግሻል ማለት ነው ።ያው እንድትናደድ ከፈቀድሽላት የሚጥል በሽታ ስላለባት ነገሮች ይባባሳሉ… እንደ አለመታደል ሆኖ ይሄንን ጉዳይ በመድኃኒቷን ማስተካከል አልቻልንም።››
‹‹ትሁት ማለት?››ግራ በመጋባት ጠየቀችው
‹‹ይቅርታ..ፀጋ ወደእናንተ ቤት ከመምጣቷ በፊት ወላጅ እናቷ ትሁት ብላ ነበር ስም ያወጣችላት….ከዛ ነው አባትሽ ፀጋ ያለት፡፡እና እኔ ትሁት የሚለውን ስም ለረጅም ጊዜ ስለተጠቀምኩበት በቀላሉ ከአእምሮዬ ላወጣው አልቻልኩም…..››
‹‹አይ ችግር ለውም..ትሁትም ደስ የሚል ስም ነው››
‹‹አዎ…እና እንዳልኩሽ ፀጋ ማለት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋት ልጅ ነች፣፣በተለይ መናደድ የለባትም….ምክንያቱም ከንዴቷ በኋላ የሚከሰተው የሚጥል በሽታ ሌሎች ብዙ የጤና ችግሯቾን ነው የሚያናጋባት››
በራሔል ፊት ላይ የፍርሃት ብልጭታ ሲያይ ተገረመ።
‹‹የሚጥል በሽታ ሊነሳባት መሆኑን እንዴት አውቃለሁ እና ምን ያህል መጥፎ ነው?››
‹‹ትለይወለሽ…እጆቿ ይንቀጥቀጣሉ… የዐይን ሽፋኖቿን ይርገበገባሉ እነዚህን እና የመሳሰሉት ምልክቶችን ታሳያለች፡፡የዛን ጊዜ አጓጉል ወድቃ እራሷን እንዳትጎዳ ጥንቃቄ መውሰድ ይገባሻል፡፡ ማንኛውም አሳሳቢ የጤና ችግር ሲያጋጥማት በአፋጣኝ ወደሆስፒታል ልትወስጂያት የግድ ነው፡፡ በመደበኝነት በሳምንት ሶስት ቀን ሆስፒታል የህክምና ክትትል አለት፡፡በመሀል አስፈላጊ ሲሆን ለእኔ በማንኛውም ሰዓት ልትደውይልኝ ትችያለሽ ፣ ወዲያውኑ ልመጣ እችላለሁ።..›› ዔሊያስ መጀመሪያ ያሰበው ለፀጋ ነው።‹ራሔል በዚህች ልጅ ላይ ያለውን ችግር በሙሉ ማወቅ አለባት› ሲል በውስጡ አሰበ፡፡
‹‹ፀጋን ከተወለደች ቀን ጀምሮ እየተንከባከባት ነበር…እናትዬው ተስፋ ቆርጣበት በሆስፒታል አልጋ ላይ ማሽን እንደተሰካካባት ጥላት ስትሰወርም አንደኛ እናትዬውን ከልጅነት ጀምሮ የሚያውቃት ጓደኛው ስለሆነች ሲሆን ሁለተኛም ከራሱ ህይወት ጋር አያይዞ ሲንከባከባትና እንደወላጅ ስለሚጨነቅላት ነው፡፡በመጨረሻም ከስድስት ወር የሆስፒታል ቆይታዋ በኃላ የራሄልን ወላጆችን በግሉ ፈልጎ በማግኘት በጉዲፈቻ እንዲወስዷት በማድረግ ሂደት ላይ የአንበሳውን ድርሻ የእሱ ነው፡፡ከዛም በኃላ በቃ በኃላፊነት የሚያሳድጓት እና የሚንከባከቧት ወላጆች አግኝታለች ብሎ አልተዋትም፤ በቆሚነት የእሷ ሀኪም በመሆን እነ አቶ ቸርነት ቤት ድረስ እየተመላለሰ ሁኔታዋን ይከታተላል፤ ታማለች ብለው ሲደውሉለት ያለምንም ማቅማማት ሞተሩን ተረክ አድርጎ በሮ ይሄድና ያያታል…እናም ይህቺ ልጅ ለእሱ እንደአንድ ታካሚው ብቻ አይደለችም…የህይወቱ አካል ነች….ስቃዮ ያመዋል…ለቅሶዋ ይሰማዋል….ፈገግታዋ ያስቀዋል….ለዛ ነው ራሄልን በትክክል እናቷ በምትንከባከባት መጠን ትንከባከባታለች ብሎ ሊያምን ያልቻለው፡፡
‹‹ራሄል ምን መሰለሽ ፀጋን እንዲህ ስታያት በአካላዊ እይታ ጥሩ ሁኔታ ላይ ያለች ሊመስልሽ ይችላል, ግን ውስብስብ በሆነ የህክምና ሂደት ውስጥ እያለፈች ነው፡፡ ሰውነቷ እየሰጠ ያለው መልስ በጣም ደካማ ነው. ለሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በጤና እሷን ማቆየት ከቻልን ትልቅ ድል ነው…በህክምናው ሂደት ከባድ ችግር እያጋጠመን ነው ››
ራሔል በፍጥነት ማስታወሻ እየወሰደች ሲሆን በእጇ ላይ ትንሽ መንቀጥቀጥ አየ፡፡‹‹ስለ ምን ዓይነት የሕክምና ችግሮች ነው የምታወራው?››
‹‹በአእምሯዋ ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት ጀምሮል እና ተጨማሪ ኢንፌክሽኖች እና ሌሎች ችግሮችም እየተከሰቱባት ነው፡፡››
እሺ፣ ምናልባት ትንሽ አክብዶባት ሊሆን ይችላል ግን ማወቅ አለባት። የበለጠ መረጃ ባላት ቁጥር እሷ ማድረግ የምትችለው የተሻሉ ውሳኔዎች ትወስናለች፣ ።
‹‹ወላጆቼ ግን ፀጋ ያለባትን ይሄን ሁሉ የጤና ችግር ያውቃሉ?››
‹‹አዎ..እንደውም ለአንቺ በጥቅሉ ነው የነገርኩሽ እንሱ ግን እሷን ለማሳደግ ከመወሰናቸው በፊት እያንዳንዱን በዝርዝር አስረድቻቸዋለው…..ግን ለምን ጠየቅሺኝ?››
‹‹እኔ እንጃ…..በዚህ ሁሉ የጤና እክል ውስጥ ሆኖ ምን አልባትም የመሞቻ ቀኗን እየተጠባበቀች ያለች እና ክፉና ደጉን የማታውቅ ልጅ እንዴት ለማሳደግ እንደፈቀዱ ግራ ስለገባኝ ነው፡፡››
‹‹ትክክል ነሽ….እኔም ወላጆችሽን በጣም የማከብራቸውና ከልቤ ማደንቃቸው በዚህ ውሳኔያቸው ነው…እነሱ ያደረጉትን ማንም ሌላ ሰው ያደርገዋል ብዬ አላስብም..እነሱ ለእኔ የህይወት ዘመን ጀግናዎቼ ናቸው፡፡››አለና ካርዱን ከጠረጴዛው ላይ አንስቶ ሰጣት። ‹‹ይህ የሆስፒታሉ የድንገተኛ አደጋ ቁጥር፣የቤቴ ቁጥር እና የሞባይል ቁጥሬ ነው። በፈለግሺኝ ጊዜ ደዉይልኝ››ራሄል መረጃውን እንደያዘች ረጅም እና ዘገምተኛ ትንፋሽ ወደ ውስጣ ሳበች ከዛ ወደ ውጭ ተነፈሰች፡፡ ወረቀቱን እና ካርዱን በቦርሳዋ ውስጥ አስገባች።
‹‹ከመሄዴ በፊት ግን አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ልጠይቅህ?››
‹‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ››አላት በጉጉት፡፡
‹‹ፀጋን ቤተሰቦቼ እንዲያሳድጓት በግል የጠየቅካቸውና ያሳመንካቸው አንተ ነህ….ለሌሎችም ታካሚዎችህ እንደዛ ታደርጋለህ?››ስትል ያለሳበውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹እውነቱን ለመናገር የፀጋ እናት የልጅነት ጎደኛዬ ነች…አንድ ሰፈር ነው ያደግነው…ህይወት ባልሆነ መንገድ መርታ ያልሆነ ማጥ ውስጥ ጨመረቻት እንጂ እንዲህ እንደቀልድ ልጇን ጥላ የምትሰወር ልጅ አልነበረችም….እና ፀጋን ዝም ብዬ ችላ ብዬ ማደጎ ቤት ስትገባ ማየት አልቻልኩም…የምተማመንባቸው አሳዳጊዎች መፈለግ ጀምርኩ..መጀመሪያ የራሴ ወላጆች ነበር የመጡልኝ..ግን የጽጌረዳ ሰፈር እዛው ስለነበረ ትንሽ ልክ መስሎ አልተሰማኝም….ከዛ ምክንያት ነው ወላጆችሽን ያገኘሁት…እናም ደግሞ ሁሉንም ነገር በግልፅ ነግሬያቸዋለው….ምንም የማያውቁት ነገር የለም፡፡››
‹‹አባቷስ?››
‹‹ምን ያህል እውነት እንደሆነ አላውቅ…አባቷ እንደሞተ ነው የነገረችኝ… ሌላ ጥያቄ ይኖርሻል?››
‹‹ አይ የለኝም..አመሰግናለው…. ››አለች… ቆመች… እጁን ለመጨበጥ ከጠረጴዛው አሻግራ እጇን ዘረጋች፡፡

❤65👍3
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ
ይህ ፋውንዴሽን አሁን የደረሰበት ደረጃ የደረሰው በዚህ መንገድ ነበር, አሰበች እንደ ሮቤል ያሉ ሰዎች የወላጆቿ ሀብት የፋውንዴሽኑን የጀርባ አጥንት እንደሆነ ነው የሚያስቡት፣ ገንዘብ በቀላሉ ወደ ሣጥን ውስጥ እንደሚገባ ያስባሉ ። ፣ ከቅርብ ረዳቶቿ ከሆኑ በጣም ጥቂት ሰዎች በስተቀር፣ በዚህ ስራ ውስጥ ግንኙነቶች ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አይረዱም። ግንኙነቶች፣ መተማመን እና ከፍተኛ የስራ ስሜት ወሳኝ ነገሮች ናቸው። ገንዘቡ ወደፋውንዴሽኑ ከሚገባት ፍጥነት ሚወጣበት ፍጥነት ይበልጣል።ራሄል የፋውንዴሽኑን አስተዳደር ስትረከብ፣ የሂሳብ መዝገቡ አሁን ባለበት ሁኔታ ጤናማ አልነበረም።
ወላጆቿ ጥሩ ልብ ያላቸው የሰው ልጅን ያለልዩነት ለመርዳትና ለማገዝ ከልብ የሚጥሩ ቀና ሰዎች ቢሆኑም የተሳሳቱ ሰዎችን አምነው ስለነበር ለከፍተኛ ምዝበራ ተጋልጠው ነበር።እና ራሄል ስራዋን ከወላጇቾ ሙሉ በሙሉ ከተረከበች በኃላ አጠቃላይ የፋውንዴሽኑን ተቋማዊ አቅም ለማሻሻል ጥቂት አመታትን እና አንዳንድ ከባድ ውሳኔዎችን እንድትወስድ አስገድዷታል፣ከዛ ቀስ በቀስ ፋውንዴሽኑን አሁን ያለበት አቋም ላይ እንዲገኝ ማድረግ ችላለች፡፡ የተቋቋሙ ያገኘውን ገቢ በጥንቃቄ ለተከበሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን እንደሙዳይ…ሜቅዶኒያ ላሉ ገንዘብን ለታለመለት አላማ ብቻ ለሚያውሉ ተቋማት ያከፋፍላል፡፡ቀዳዳቸውን ይደፍናል ጉድለታቸውን ይሞላል፡፡
‹‹ሮቤል፣ ስለዚህ ጉዳይ አሁን ማውራት አልችልም። አሁንም ከሎዛ ጋር መገናኘት እና ከዚያም ፀጋን ከመዋለ ሕጻናት መውሰድ አለብኝ።ከዛ ቀጥታ ወ.ሮ ላምሮትን ሄጄ አገኛታለው….ደውልላት እና ከአንድ ሰዓት በኋላ እቤቷ እንደምገኝ ንገራት፡፡››አለችው፡፡ ወይዘሮ ላምሮት ብዙ ጊዜዋን እየወሰደች ነበር፣ ሴትየዋን ወደ ሎዛ ለማስተላለፍ አልደፈረችም ፡፡ለዚህ ነው ቀጥታ እራሷ ልታገኛት የወሰነችው፡፡
ቦርሳዋን ይዛ ከቢሯዋ ወጣች፡፡
ከአስራ አራት ደቂቃ በኋላ ወደ መዋዕለ ሕጻናት ማእከሉ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ስትገባ ጎማ በጭቃ ውስጥ ገባ። ቦርሳዋን እና ቁልፏን ይዛ ከመኪናው ውስጥ ዘላ ወጣች፣ ጉልበቷን የበሩን ጠርዝ መታት..አቃሰተች እና ጎንበስ ብላ እያሻሸች መንገዷን ቀጠለች .. የሞባይል ስልኳ እየጠራ ቢሆንም ችላ ብላ የመዋዕለ ሕፃናት ማቆያውን የመስታወት በሮች ከፍታ ወደውስጥ ገባች ፡፡ለአባቷ የገባችው ቃል ኪዳን እና በኤሊያስ አይኖች ውስጥ ያነበበችው ጥርጣሬ ለፀጋ አስፈላጊውን ጊዜ መድቦ ተገቢውን እንክብካቤ ለማድረግ ቁርጠኛ እንድትሆን አድርጓታል። ከሁሉም በላይ ግን ፀጋ እህቷ ነበረች። እና ምንም አይነት አስቸጋሪ ቢሆንም በክፉ ቀን ቤተሰብ ለቤተሰብ መከታ መሆን እንዳለበት ታምናለች፡፡ ፀጋ ሰዓቱን በትኩረት በምትመለከተው የቀን ተንከባካቢ ሰራተኛ እቅፍ ውስጥ ሆና እየጠበቀቻት ነበር። አፏ እና ጠባብ አይኖቿ ስትመለከት ነገሮች ጥሩ እንዳልሄዱ ገመተች።
‹‹ሴት ልጃችሁን በፕሮግራማችን ስታስመዘግቡ ፖሊሲያችንን በግልፅ አሳውቀናችኋል።›› ሴትዬዋ በጠንካራ ንጭንጭ ተቀበለቻት፡፡
‹‹ይገባኛል... ›› አለች‹‹እና እህቴን በሰዓቱ ስላልወሰድኩ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ››ስትል አከለችበት ፡፡
‹‹በጣም ዘግይተሻል››የሚለው ቃል አከለችበት ። ጎንበስ ብላ የፀጋን ዳይፐር ከቦርሳ አወጣች እና ከዚያም ወደ እህቷ ተጠጋች ።‹‹ቶሎ ልናገኝሽ ሞክረን ነበር።›› ወይዘሮ ባንቺ ወደ ፀጋ ተመለከተች እና ፊቷን አኮሰታተረች። ያን ጊዜ ነበር ራሄል የልጅቷን በእንባ የታጠበ ጉንጯች ያስተዋለች። ‹‹ፀጋ ጥሩ ቀን አላሳለፈችም። ነርሷ የሙቀት መጠንዋን ስትወስድ ከፍ ብሎ ነበር፣ በተቻለ ፍጥነት ሀኪም ቤት እንድትወስዷት ተናግራለች ።››
‹‹እንዴ አሁን?...ለማለት የፈለኩት ይህ ምን ያህል አጣዳፊ ነው? ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ልውሰዳት ወይስ ሁኔታዋን መከታተል አለብኝ?››ስትል ጠየቀች፡፡
ወይዘሮ ባንቺ ‹‹ወዲያውኑ ብትወስጂያት መልካም ይመስለኛል.. እህትሽ ካለባት የጤና ችግር አንፃር የበለጠ ንቁ መሆን ይገባታል።
‹‹ያንን አስቤ ነው ወደዚህ ያመጣኋት… በቃ ወስዳታለው›› የፀጋ የሰውነት ሙቀት በልብሷ አልፎ እየተሰማት ነው። ላለባት ቀጠሮ ሰዓቷን ለማየት አልደፈረችም። ሆስፒታሉ ከመዋዕለ ህጻናት ብዙም ባለመራቁ አመሰገነች፡፡
ከሃያ ደቂቃ በኋላ ወደ ሆስፒታሉ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ገባች እና በድንገተኛ ክፍል በሮች ቸኩላ ስታልፍ ትዝታዎቹ እየተጣደፉ መጡባት።በእቅፏ ወደተቀመመችው ፀጋ ተመለከተች እና አዲስ ፍርሃት መላ ሰውነቷን ተቆጣጠራት። ወደ መቀበያ ጠረጴዛው እየገሰገሰች ስትሄድ፣ ቀድሞውንስ ይሄን ጉዳይ እንዴት አድርጋት ልትወጣ እንዳሰበች ተገረመች። ላለፉት ስምንት አመታት በድንገት የሚደፈርስ ስሜት እና ከቁጥጥር ውጪ የሚወጣ ድንገተኛ ብስጭትን ስትዋጋ ነው የኖረችው። አሁን የአንዲት ቀጫጫ ነርስን ማይረብ ጥያቄዎችን በትዕግስት እየመለሰች ነው።እንደጨረሰች በውስጧ እየበቀሉ ያሉ አሮጌ እና አዲስ ፍራቻዎችን እየታገለች፣ ለሆስፒታሎች ልዩ የሆኑትን የተለመዱ ሽታዎች እያሸተተች በተጨናነቀው የመጠበቂያ ክፍል ውስጥ ተመልሳ ተቀመጠች።
ከድንጋጤዋ የተነሳ መላ ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው ፡፡ለፀጋ ስትል ትኩረቷን ለመሰብሰብ መሞከር አለባት።ፀጋ እጆቿ ይንቀጠቀጣሉ፣ ከሰውነቷ የሚወጣው ሙቀት በየደቂቃው እየጨመረ ነው። ነርሶቹ በስራ ተጠምደዋል፡፡ችሎታ ያለው እና ኃላፊነት የሚሰማው ዶ ር ለማግኘት ዙሪያውን አማተረች። አንዳቸውም ወደ ራሔል ዞር ብለው አላዩትም።ሰዎች ወንበሮች ላይ ተቀምጠው ይንቆራጥጣሉ፣ አንዳንዶቹ ጎንበስ ብለው ያቃስታሉ፣ ሌሎች ደግሞ ደንዝዘው እያንጓላጅጁ ነው፡፡
እያንዳንዳቸው በራሳቸው መከራና ሀዘን ተይዘዋል..ስለ ራሄል እና በእቅፏ ውስጥ እየተቃጠለች ስላለችው ህፃን ደንታ አልነበራቸውም።ከዚያም ፀጋ እየደነዘዘች ሄደች፡፡ ድንጋጤ የራሄልን ጉሮሮ አነቃት። አምላክ ማንኛውንም ነገር እንደሚያደርግ ብታምን ኖሮ አሁን በዚህ አስጨናቂ ጊዜ ትጸልይ ነበር።እግዚአብሔር ግን ከዚህ በፊት ከልቧ በፀለየችበት ጊዜ ትኩረት አልሰጣትም ነበር እና አሁንም እሱ ላይ መንጠልጠል አልፈለገችም፡፡ ፀጋ ማቃሰቱን አቁማ እንደገና በመጠኑ ዘና ስትል እፎይታ ተሰማት። ራሄልን ቀና ብላ ተመለከተች፣ታናሽ እህቷ ለስላሳ ቡናማ አይኖቿን ራሄል ላይ አንከባለለችባት፡፡ ራሄል በምላሽ ልቧ ሲዘል ተሰማት። ከዚያም ራቅ ብላ ተመለከተች።
ፀጋ ለእሷ ግዴታዋ ነበርች ይህች ልጅ ቀስ በቀስ የፍቅር እሳት በልቧ ዙሪያ እንዲቀጣጠል እያደረገች ነው። እንደ ፀጋ ካለች ልጅ ጋር መጣበቅ ማለት ልቧን ለህመም እና ማጣት እምቅ ስቃይ መከፈት ማለት እንደሆነ ታውቃለች።እና ያንን በራሷ ላይ እንደገና ማድረግ ፈፅሞ አትፈልግም ነበር ፡፡ግን ደግሞ በምርጫዋ እያደረገችው ያለ ነገር አይደለም፡፡ከአሰልቺ ጥበቃ በኃላ ነርሷ መጥታ በመጋረጃ ወደተሸፈነው ክፍል ወሰዳቻቸው። ራሄል እህቷን አልጋው ላይ በጥንቃቄ አስቀመጠቻት።ነርሷ የጥያቄዎችን ፣ የአለርጂዎችን ፣ የመድኃኒቶችን ዝርዝር ጠየቀቻት። ራሄል የምትችለውን ያህል መለሰች።እንደጨረሰች ነርሷ ጆሮዋ ውስጥ ቴርሞሜትር ጨመረች ..በዛ ቅፅበት አንድ ዶክተር ኮሪደሩን ሰንጥቆ ወደ እነርሱ ሲመጣ ተመለከተች። ነጭ ጋወን አድረጎ ስቴቶስኮፕ አንገቱ ላይ አንጠልጥሏል ።ኤሊ ነበር።

❤41
#እናትነት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//////
የእኔ ቅንዝርነት የልጅቷ ድህነት፤እናትነት እና ተስፋ ቢስነት
ስሟ ግን ማን ነበር?
ምን አይነት ችግር ላይ እንዳለሁ ልትገምቱ አትችሉም፡፡ ሀገር አማን ነው ብዬ በእንቅልፍ ዓለም ከተዋጥኩ በኋላ በእኩለ ለሊት ላይ ለመንገድ መብራት ማቆሚያ እደተተከለ የእንጨት ምሰሶ ቀጥ ይላል፡፡ ቀጥ ማለቱ ብቻ አይደለም እኮ የሚያበሳጨኝ ቀጥ በማለቱ ውስጥ ጥዝጣዜ ነገር አለው፡፡ የመነዝነዝ ዓይነት እና ለመግለፅ የሚያስቸግር ግራ አጋቢ ህመም ከእቅልፍ እስከማባበነን ድረስ የሚደርስ ኃይል ያለው ህመም ፡፡እስከአሁን ስለምን እንደማወራችሁ አልገባችሁም አይደል?
እንጠራራ እና ከእንቅልፌ ጋር እየታገልኩ ዓይኔን እያሻሸው በዳበሳ ወደ ሽንት ቤት ሄዳለው… ምን አልባት ሽንቴ ወጥሮኝ እንደሆነ ብዬ…ግን ብጨምቀው ባልበው ጠብ አይለኝም ፡፡
በንጭንጭ ወደ አልጋዬ እመለስና እያተገላበጥኩ እንቅልፍ እስኪያሸንፈኝ እሰቃያለው፡፡ከሰዓታት በኃላ እንደምንም እንቅልፍ ያሸንፈኛል፡፡ሊነጋጋ ሲል መለልሶ ይቀሰቅሰኛል፡፡የዚህኛውን ጊዜ እንኳን ፊት አልሰጠውም …ከነ ተረቱ ‹ የጥዋት ቁ› ይባል የለ …ሽንት እንዲወጠር እድርጎት ይሆን ትክክለኛ አምሮት ይሁን መለየት አይቻልም…ሀሰተኛ መሲ ነገር ነው፡፡
ይሄ ነገር እየተደጋገመ ሲያስቸግረኝ ህልሜን ሁሉ የከተማዋ ቆነጃጅቶች እና በአካልም በምናብም የማውቃቸው ሴቶች ሲሞሉት የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ወሰንኩ…፡፡ በእኔ ምክር ሳይሆን በተፈጥሮ ህግ የሚመራውን ቅንዝሬን የሆነ ዘዴ ፈጥሬ ማቀዝቀዝ አለብኝ..ስለዚህ ግዢ ልወጣ ወሰንኩ፡፡
ሰፈሩን ባልነግራችሁም …ለግዢ ምቹ ናቸው ሲባሉ ከሰማዋቸው የከተማዋ ጉድ ሰፈሮች መካከል ወደ አንዱ ነው የሄድኩት…ቺቺኒያ አይተንሀል አላችሁኝ…..?ምን አልባት እኔን የመሰለ ሰው አይታችሁ ይሆናል እንጂ እኔ ወደ እዛ ሰፈር ዝር አላልኩም…ደግሞስ እናንተ ራሳችሁ እዛ ሰፈር ምን ስትሰሩ ነበር? ለማንኛውም ያልኳችሁ ቦታ ሄድኩ …ቀድሜ አልጋ ተከራየው….
ከዛ ወደ ቡና ቤቶቹ ወይም ወደ ጭፈራ ቤቶቹ አልነበረም ጎራ ያልኩት፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ ጎዳናው ነው የወጣሁት…፡፡ከቤት ውስጥ ግዢ የውጩን ለምን እንደመረጥኩ አልገባኝም…. ብቻ ስሜቴ ወደ እዛ ነው የገፋኝ ፡፡ዞሬ ለመምረጥ… መርጬ ለማነጋገር እና ለመስማማት..ተስማምቶም ይዞ ለመሄድ ..አንድ ሰዓት ገደማ ፈጀብኝ፡፡
ልጅቷ የተከራየሁት ቤርጎ ገብታ አልጋው ጠርዝ ላይ እንደተቀመጠች ፊቷን ለማንበብ ሞከርኩ..፡፡ፊቷ ሜካፕ የነከካው ቢሆንም በስርዓቱ አልተዳረሰም… የሆነ መዝረክረክ ይታይበታል፡፡ከቀይ ዳማ መልክ ወደ ግራጫ የተቀየረ የፊት ቀለም ይታየኛል..፡፡የዓይኖቾ ቅንድቦች ቀና ማለት ደክሟቸው መሰለኝ ተደፍተዋል፡፡ጉንጮቾ ወደ ውስጥ ስርጉድ ብለው በረሀ ላይ ውሃ እንዲወጣባቸው የተቆፈሩ ጉድጓዶች ነው የሚመስሉት ...፡፡ከንፈሮቾ ቁርፍድፍድ ብለው የመሰነጣጠቅ ምልክት ይታይባቸዋል፡፡ግን በተቀባችው ቀይ ሊፒስቲክ ልትሸፍነው ሞክራለች፡፡ውጭ ከመብራቱ ፖል አቅራቢያ ከሚገኝ ግንብ አጥር ጋር ተጣብቃ ግማሽ ብርሀን እና ግማሽ ጨለማ ከቧት ሳነጋግራት ይሄ ሁሉ አሁን የዘረዘርኩላችሁን የመልኳ ሁኔታ አልተገለፀልኝ ነበር.፡፡አቋሟን እና የፊቷን ቅርጽ በከፊል ነበር የገመገምኩት….፡፡ገምግሜም አስፓልቱ ላይ ከተኰለኰሉት መሀከል እሷን የመረጥኳት…መርጬም ያነጋገርኳት …አነጋሬም የተሰመመማነው… ተስማምተን ወደ ተከራየውት ቤርጎ ይዤት የገባሁት፡፡
አሁን ..ከገባችና በመጠኑም ፈንጠር ብላ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣ ሳስተውላት ግን አሁን ከላይ እንደዘረዘርኩላችሁ የተለየች ሆና ነው ያገኘኋት፡፡ ገና ያልበሰለች የ16 ዓመት አካባቢ ጨቅላ ወጣት ነች ፡፡ቢሆንም ውስጧ የ60 ዓመት …የጎበጠች እና የጨረጨሰች አሮጊት በእሷነቷ ውስጥ ተደብቃ ትታያለች፡፡ ወጣትነቷ በፍጥነት ወደ መጠውለግ ሲንደረደር ይታያል፡፡
‹‹ተጫወቺ እንጂ …ምነው ከእኔ ጋር ማደሩ ደስ አላለሽም እንዴ? ››አልኳት፡፡
ፊቷን እንዳጨማደደች አላስፈላጊ ጥያቄ እንደጠየቀ ሰው በግርምት እያየችኝ
‹‹መደሰት እና አለመደሰት እዚህ ጋር ምን አመጣው›ስትል መለሰችልኝ፡፡
‹‹አልገባኝም››
‹‹እንዴት አይገባህም..እኔ ገንዘብህን ነው የምፈልገው፡፡ ከፍለኸኛል….ከከፈልከኝ ደግሞ ደስ አለኝም አላለኝም አብሬህ ማደር ግዴታዬ ነው››አለችኝ እና ልብሶቾን ማወላለቅ ጀመረች፡፡
እኔም አወላለቅኩና ተከተልኳት..ተያይዘን አንድ አንሶላና ፍራሽ ከስር..አንድ አንሶላና ብርድ ልብስ ከላይ አድርገን ከመሀከል ገባን…፡፡
‹‹እዛ ባዶ ቤት ብቻውን በነበረበት ሰዓት ዘራፍ እያለ እረፍት ይነሳኝ የነበረው አጅሬን‹‹ አሁን እስቲ ጉዱህን እየዋለው….ሜዳውም ፈረሱንም ያው አመቻችቼለታለው… ›› አልኩት.፡፡
ግን ለእኔም ሆነ ለአጅሬው እንደአሰብነውና እደጓጓነው የሆነልን አይመስለኝም ….የሆነ ደስ የማይል ስሜት እየተሰማኝ ነው…እሱም አንዴ ቀጥ ከዛ መልሶ እንደመልፈስፈስ እያለ ፈራ ተባ ውስጥ ገብቷል፡፡ወደ እሷ ፊቴን አዞርኩና እጄን ትከሻዋ ላይ ጣል አደረግኩ..ስጠጋት ከሰውነቷ የሚረጨው ጠረን ተምዘግዝጎ ወደ አፍንጫዬ ሲገባ ደስ የማይል ስሜት ነው የተሰማኝ..እርግጥ ከለበሰችው ልብስ አልፎ ሰውነቷ ላይ የቀረ የሽቶ ሽታ አለ ..፡፡ግን ከሽቶው ተደባልቆ ና ተዋህዶ የሚበተን ሌላ ጠረን አለ..ምንነቱን ልለየው ያልቻልኩት ትንሽ የሚረብሽ ጠረን….፡፡
እንደዛም ሆኖ በደንብ ተጠጋኋት ..ሰውነቴን ከሰውነቷ አጣበቅኩ…እዳብሳት እና አሻሻት ጀመርኩ፡፡..ቀስ በቀስ ሰውነቴ እየጋለ እየሞቀ ቢመጣም ከእሷ ወደ እኔ እየተላለፈ ያለ ምንም አይነት ሙቀት ሊሰማኝ አልቻለም…. አሁንም በረዶ እንደሆነችና ሰውነቷ ከፍሪጅ እደወጣ ስጋ እንደደረ ነው፡፡ማሻሸቴ ቀጥሎ ጡቶቾ ጋር ደረሰ ....ጨመቅ ለቀቅ.. ጨመቅ ለቀቅ ሳደርግ አስደንጋጭ ፈሳሽ ከጡቶቾ ፊን ብሎ ደረቴ ላይ ተረጨ..ደነገጥኩ ፡፡
በደነገጥኩበት ፍጥነት አሷም ይበልጥ በመበሳጨት ጮኸችብኝ፡፡
‹‹በናትህ ዝም ብለህ ማሻሻቱን ጥለህ ..ማድረግ አትችልም ?››
‹‹ምድነው ከጡትሽ የወጣው?››
‹‹ምን እንዲወጣ ትፈልጋለህ… ነዳጅ…››.በማሾፍ መለሰችልኝ፡፡
‹‹እሱማ ወተት ነው…ግን እንዴት...?እንዲህ ይሆናል እንዴ?››
‹‹እመጫት ስለሆንኩ እና ስለማጠባ ነው››ግዴለሽ እና ስሜት አልባ በሆነ ስሜት መለሰችልኝ፡፡
‹‹ማ….? አንቺ?››
‹‹አዎ …የሁለት ወር አራስ ልጅ ቤት ጥዬ ነው የመጣሁት››
በድንጋጤ ከመኝታዬ ተስፈንጥሬ በመነሳት ቁጭ አልኩ
‹‹ አቤት ጭካኔ ..የሁለት ወር አራስ ቤት አስተኝቶ ለሽርሙጥና መሰማራት ሀጥያት ብቻ ስይሆን ወንጀልም ነው..ምን አይነጠቷ አውሬ ነሽ በእግዚያብሄር…!!!!››አልኳት፡፡
ተንፈቅፍቃ የሹፈት ሳቅ ሳቀችብኝ‹‹ሀጥያት አልክ ..?ማነው እኔን ወንጀለኛ እና ሀጥያተኛ ነሽ ብሎ ሊፈርድብኝ የሞራል ብቃት ያለው..?ያሳደገኝ ማበረሰብ…? ሚያስተዳድረኝ መንግስት …?ቄሱ..?ፓስተሩ…? አንተ ..

❤34😢3