#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
//////
ራሄል ፀጋን ስታበረታታ‹‹ነይ የኔ ማር ..አንድ ነገር መጠጣት አለብሽ››አለች ። እሷ ግን ከራሔል ደረት ጋር እንደተለጠፈች ጭንቅላቷን ወደ ጎን አዞረች። ራሄል ትንሿን ህፃን በምቾት መያዝ አልቻለችም ሰውነቷ በጣም ሞቃት እና የሚፋጅ ነበረ….ራሄል ዔሊያስ ባሳየት ዘዴ በመጠቀም የሙቀት መጠኑን ለመቀነስ ሞክራ ነበር፣ነገር ግን ለልጁቷ ጊዜያዊ እፎይታ ቢያስገኝላትም፣ የሙቀት መጠኑ ብዙም ሳይቆይ ከደቂቃዎች በኃላ እንደገና ይጨምሯል። ራሄል ደፍራ ለዔሊያስ ደውላ ሁኔታውን ልትነግረው አሰበችና ስልኩን ተመለከተች። ወዲያው ግን ትላንት ቤቱ በሄደች ጊዜ እንዴት እንዳስተናገዳትና ከህይወቱ ጭምር አሽቀንጥሮ እንዳስወገዳት ትዝ ሲላት እጇን ሰበሰበች፡፡ እንደገና መዋረድ ስላልፈለገች ከዔሊያስ ለመራቅ ወሰነች ። ከዛ ምንም ምርጫ ስለሌላት.. የሚሆነውን መጠበቅ ጀመረች፡፡
ከአንድ ሰዓት በኃላ ፀጋ ለውጥ እያሳየች መጣች…ከዛም በላይ እራሷን ችላ መቀመጥና በአሻንጉሊቶች መጫወት ጀመረች…ራሄል በጣም ደስ አላት..ከእሷ እቅፍ ላይ ወረደቻና ግዙፉ ሶፋ ላይ ሆና መጫወት ጀመረች…ራሄልም በተወሰነ መንገድ ስለተረጋጋችላት ተደስታ እዛው አጠገቧ ቁጭ ብላ አንዳንድ ሰነዶችን ማየት ጀመረች…ግን ብዙም ሳይቆይ አስጠሊታ ነገር ተከሰተ ፡፡ፀጋ ከተቀመጠችበት ተነስታ ከእሷ የሸሸውን አሻንጉሊት ለመያዝ እግሯን ስታነሳ የሶፋው ቆዳ አዳለጣትና ወደኃላዋ ወደቀች…ወደኃላዋ ስትወድቅ የሶፋው እጄታ ጭንቅላቷን መታት…ለሌላ ልጅ ቢሆን ምንም አይነት ጉዳት የሚያስከትል አይነት አልነበረም…ፀጋ ግን ልትቋቋመው አልቻለችም፡፡
ራሄል እዛው አጠገቧ ስለነበረች በእጇ የያዘችውን ወረቀት በትና ተንደርድራ ሄዳ አነሳቻት…ክንዷ ላይ ዝልፍልፍ ብላ ዝርግትግት አለች..አይነቾ ግልብጥብጥ አሉ….ራሄል እሪታዋን ስታቀልጠው..ከኪችን አለምና ረዳቷ ከውጭ አትክልተኛውና ዘበኛው እያለከለኩ መጥተው ከበቧት..አለም ፀጋን ከራሄል እጅ ላይ ተቀበለች…‹‹ቶሎ በሉ አምፑላንስ ደውሉ..አንፑላንስ ደውሉ….››ተንጫጩ..ራሄል ራሷን መቆጣጠር አቃታት…ልቧ መጥታ ጉሮሮዋ ላይ እንደተወተፈች እርግጠኛ ነች…መተንፈስ ሁሉ አቃታት..በእንብርክክ ሳሎኑና ታስሰው ጀመር ..…ከ30 ደቂቃ በኃላ አምፑላንሷ ቀፋፊ የሆነ ሳይረኗን እያስጮሐች ደረሰች…ባለሞያዎቹ ከአለም እጅ ጸጋን ተቀብለው በጥንቃቄ ወደውስጥ አስገብተው አልጋው ላይ አስተኞት..ከዛ ወዲያው የመተንፈሻ መሳሪያዎቹን ይሰካኩላት ጀመር… ራሄል በደመነፍስ ተከትላ ገባች…የአምፑላንሱ በራፍ ተዘጋና ተንቀሰቀቀሱ ፡፡
ሆስፒታል ከደረሰችና ፀጋን ለሀኪሞቹ ካስረከበች ከአንድ ሰዓት በኃላ ግን ነገሮች በብዙ እጥፍ እየተባባሱ እንደመጡ መታዘብ ቻለች፡፡ወደ ውስጥ ገብታ ከሚስኪን እህቷ ጎን መሆን ፈለገች…እግሯን ስታንቀሳቅስ ግን ‹‹እመቤት ፣ ወደእዛ መሄድ አትችይም።››ስትን ነርሷ አገደቻት ፡፡
መሄድ አለባት፣ ከፀጋ ጋር መሆን ነበረባት።ነርሷ ‹‹ሀኪሞቹ ሰራቸውን መስራት አለባቸው ልጅሽ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነች››አለቻት፡፡
ልጅሽ የሚለው ቃል አእምሮዋን በጦር ወጋት‹‹..አዎ የአደራ ልጄ ነች››ስትል አሰበች….‹‹ግን አንድ እናት ከማህፀኗ የወጣ ልጅ ሊሞትባት ሲያጣጥር ስታይ ምን አይነት ስሜት ይሰማት ይሆን …?እንዴትስ መቋቋም ትችላለች?››እራሷን ጠየቀች…መልሱን ማሰብ እንኳን ዘገነናት፡፡ ቃላቱ በራሔል አእምሮ ውስጥ ከላይ እንደተወረወሩ ጠጠሮች ወደቁ።ነርሷ ያለችው ገብቷታል.. ግን አልተዋጠላትም።
‹‹ለምን ዶክተሩ ራሱ መጥቶ ምን እየተፈጠረ እንዳለ አያሳውቀኝም ?።››
ነርሷን ስታያት ወጣት እና ከእሷ በላይ አጭር ነች፣ ነገር ግን ክንዷን የጨበጠው እጇ በሚገርም ሁኔታ ጠንካራ ነው።ራሄል ፀጋን ወደ ወሰዱበት ቦታ በጨረፍታ ተመለከተች፣ በተጨናነቀው ክፍል ዞር ብላ ስትመለከት በድንገት የጠፋች አይነት ስሜት ተሰማት። እንዴት እዚህ ደረጃ እንደደረሰች አታውቅም። የሚወዛወዘውን አምቡላንስ በድንጋጤ አስታወሰች፣ ሁለቱ ሰዎች በፀጋ ላይ ሲያንዣብቡ፣ ወደ ኋላ እና ወደ ፊት መመሪያ ሲሰጡ ድምፃቸው ጥርት ብሎ ይሰማት ነበር። መመሪያው በግልፅ ምትረዳቸው አልነበሩም ፡፡ከቤት ተነስተው ሆስፒታል እስኪደርሱ ነገሮች ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ አይነት ነበር…
ነርሷ በእርጋታ እየመራች ወደአንድ ክፍል ይዛት ገባችና ወንበር ስባ አስቀመጠቻት ..እሷ ከኮምፒዩተር ባሻገር ባለው ሌላ ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡ ከዛ ራሄል በጥያቄዎች ዝርዝር ታጣድፋት ጀመር ። አለርጂዎች የለባትም?ምን ምን መድሃኒቶች ነው የምትወስደው?. የሚከታተላት ዶክተር ማን ነው?።እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን ጠየቀቻት፡፡ቢያንስ ለነርሷ አስፈላጊውን መረጃዎች መስጠት ፀጋን በተወሰነ መጠንም ቢሆን መርዳት እንደሆነ በማሰብ በተቻላት መጠን በትኩረትና በትዕግስት መለሰችላት፡፡ በመጨረሻ ተጠናቀቀ ።
ራሄል ከነርሷ የቀረበላትን ውሃ አልተቀበለችም። ‹‹እህቴን መቼ ማየት እችላለሁ?›› ስትል ጠየቀች።
ነርሷ ተነሳች እና በፍጥነት ወደ ክፍሉ ሄደች፣ ራሄል በቁጣ እና በንዴት ተከተለቻት ። ብዛት ያላቸው የማታውቋቸው ዶክተሮች ፀጋ ህክምና ላይ እየሰሩ ነበር፣ ቢሆንም የገዛ እህቷን ፣የአደራ ልጇን እንዳታይ ተከልክላለች..ያ ደግሞ በጣም ያበሳጫል።ዓይኖቿን በመጠባበቂያ ክፍል ውስጥ ካሉት ሌሎች ሰዎች ራቅ አድርጋለች። አእምሮዋም ስቃያቸውንና ጭንቀታቸውን ሊቀበል አልቻለም።በመጨረሻ ነርሷ ተመለሰች።
‹‹አሁን የተረጋጋች ነች። ወደ ህፃናት ህክምና አይሲዩ አስተላልፈዋታል።››ራሄል ደረቷ ላይ ቀዝቃዛ ክብደት ያለው ብረት የተቀመጠባት መስሎ ተሰማት ።
‹‹ተረጋጊ ያልሽኝ መስሎኝ ነበር?።››ስትል ነርሷ ላይ አፈጠጠችባት።
‹‹ትክክል ነሽ ተረጋጊ ብዬሻለው…ግን ጥብቅ ክትትል ሊደረግላት ይገባል።›› ነርሷ ጥንቃቄ የታከለበት ፈገግታ ፈገግ አለችላትና ። ‹‹ለአሁን… ደህና ነች ።››የሚል ንግግር አከለችበት፡፡
‹‹ለአሁኑ?››
‹‹ከፈለግሽ ወደ እሷ ልወስድሽ እችላለሁ።››
‹‹በጣም እፈልጋለው።››ራሄል ነርሷን ተከትላ ተራመደች።ሰውነቷ ኤሌክትሪክ እንደጨበጠ ሰው እየተንዘረዘረ ነው፡፡ ሰዎች ወደ ሞሉበት ኤሊቬተር ውስጥ ገቡ፣ እና ራሄል እጆቿን ተመለከተች…በቀደም በወላጆቾ ቤት ለተዘጋጀው ዝግጅት ብላ የተቀባችው የጥፍር ቀለም ተፋፍቆ ነበር።…አለባበሷን ስታይ የበለጠ ገረማት…ለቀናት ከላዮ ላይ ያልወለቀ የቆሸሸ እና የተጨማደደ ቲሸርት የሆነ እንዴት እንደለበሰችው እንኳን ማታውቀው አመድማ የነተበ ጅንስ ለብሳለች።በህይወቷ እንደዚህ እራሷን ጥላ እና ሙሉ በሙሉ ዘንግታ እንዳማታውቅ እርግጠኛ ነች፡፡ከመቼ ወዲህ ነው ይህቺን ልጅ እደዚህ የወደደቻት….?
ሊፍቱ ቆመና ፣ በሮቹ ተንሸራተው ተከፍቱ.. ራሄል ነርሷን ተከትላ ወደ አንድ ክፍል ገባች
… ወደ ማጠቢያ ገንዳ ተወሰደች እና እጇን እንድትታጠብ ታዘዘች። እጆቿን በማድረቅ ነርሷ አገዘቻት ‹‹ጋውን እና ጭንብል ማድረግ አለብሽ››አለችና አቀበለቻት ።ከዛ ነርሷ በተቆጣጣሪዎች የተከበበ አራት ትናንሽ አልጋዎችን ወደያዘ ክፍት ክፍል መርታ ወሰደቻት።

❤53