አትሮኖስ
281K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ



ከወ.ሮ ላምሮት ቤት እንደተመለሱ ቀጥታ ወደራሄል  ወላጇቾ ቤት ነው የሄዱት፡፡ኤልያስ ቤት ድረስ አብሯቸው የመጣው በሁለት ምክንያት ነው…አንድም ሊሸኛቸው ሲሆን ሌላው ግን ጥዋት ከቤት ወጥቶ አብሯቸው ሲሄድ  ሞተር ሳይክሉን እዛው ጥሎ ስለነበረው የሄደው እሱን ለመውሰድ ነው…"ካለበለዚይ ጥዋት ወደስራ ለመግባት ታኪሲ ፍለጋ መጋፋት ሊጠበቅበት ነው…ያ ደግሞ በጣም የሚጠላው ነገር ነው፡፡

ደርሰው  ራሄል መኪናውን ፓርክ አድርጋ እንዳቆመች እሱ ፈጠን ብሎ ወረደና ፀጋን አንስቶ አቀፋት..ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷት ስለነበረ ሲያቅፍት  ልጥፍ አለችበት፡፡ራሄል ቦርሳውን አንስታ አንጠለጠለችና ተከተለቻቸው እና ወደ ግዙፍ ቤት ተከታለው ሲገቡ ጥዋት ተሰምቷት የነበረ ስሜት ተመልሷ ተሰማት…ባሏ… ተወዳጅ ልጇን አቅፎ ወደቤት ሲገቡ….ሀሳቡ የደስታ  ውስጧ በደስታ ስሜት እንዲጥለቀለቅ ስላደረጋት ‹‹እንዴት ደስ ይላል››ስትል በለሆሳሳ አንሾካሾከች፡፡ከፊት ቀደመችና ሳሎኑን ሰንጥቃ እየመራች ወደፀጋ
ክፍል ይዛው ሄደች… ቶሎ ብላ ብርድ ልብሱን ገለጠችለት…ቀስ ብሎ አስተኛትና ተጋግዘው አለባበሳትና ቆመ…ተከትላው ቆመች…በመሀከላቸው ያለው ርቀት ከአንድሜትር አይበልጥም…አንደኛው ሌለኛው ላይ አፍጥጧል….በሚገርም ሁኔታ የትንፋሽ ማጠር አጋጠማት. …ቀስ እያለ ተጠጋትና እጇቹን በወገቧ ላይ አሳረፈ፡፡
ውርር የሚያደርግ ጥሩ ስሜት ተሰማት…ከዛ በምን ፍጥነት እንደሆነ ሳታውቅ ከንፈሮቹ በእሷ ከንፈር ላይ አረፉ …የራሄል አይኖች ተዘጉ፤ እና ለአፍታ ድንጋጤ ተሰማት ፣  እጆቹ በወገቧ ዙሪያ  ተጠመጠሙባት እና ወደራሱ ጎትቶ አስጠጋት። ራሄል ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ  ሙሉ በሙሉ በቀጣይ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር የማወቅ ጉጉት ተሰማት። የበለጠ ልትለጠፍበትና ልትደገፍበት ፈቀደች፡፡ ‹‹ይህ ጥሩ ሥነ ምግባር አይደለም?››በውስጧ ነበር ያሰበችው… በድንገት የከበደውን ከባቢ አየር ማቅለል ፈለገች። ለብዙ ዓመታት ሳትወድቅ ከቆየችበት ቦታ ለመመለስ ተፍጨረጨረች።

‹‹የእህቴን  ሐኪም መሳም ?››ከእቅፉ ሳትወጣ  የሹክሹክታ ድምፅ አሰማች።ወደፊቷ የተደፋውን  ፀጉሯን ወደኃላ በመመለስ አስተካከለላት፡፡ከዚያም ,  ቀስ ብሎ ከከንፈሯም ከአካሏ ተላቀቀ እና እራቅ አለ።

‹‹ ፀጋ ቅሬታ እንደማታቀርብ አምናለው››አለችና  ዓይኗን በእፍረት ደፍች፡፡  ለእሱ ያላትን መስህብ በውስጧ መቅበር እስከቻለች  ድረስ፣ እራሷን ከእሱ ለይታ ማቆየት እስከቻለች ድረስ፣ እነዚህን አዳዲስ እና አደገኛ  ስሜቶች መቋቋም እንደምትችል ታስብ ነበር።አሁን ግን?በጣም ለረጅም ጊዜ የናፈቀችውን ነገር ቀምሳለች። ከንፈሯ ላይ መች ተጠግቶ እንደተጣበቀባት  እንኳን አላወቀችውም። ፍቃዷን እና ሙሉ  ስሜቷን ለዚህ ሰው እስክትሰጥ ቅፅበት ድረስ  ልቧን በኪሩቤል የመቃብር ቦታ ለዘመናት ቀብራው ነበር፡፡ በደረሰባት ኪሳራ ተበሳጭታ ስለነበረ  ራሷን ዳግመኛ እንደዚህ ላለ ሁኔታ ለማጋለጠ ፈፅሞ እንደማትፈቅድ ቃል ገብታ ነበር። አንድን ሰው በጥልቀት ለመንከባከብ መፍቀድ ራስን ነገ በድንገት ለሚመጣ ህመም ማመቻቸት እንደሆነ ህይወት አስተምራታለች።ከዛ ስቃይ ለማገገም እና እንደገና ወደህይወት  ለመመለስ ዓመታት ፈጅቶባታል።

‹‹ይሄ ጉዳይ  በጣም ያስፈራኛል።››አለችው፡፡
አገጯን በአውራ ጣት ዳባበሳት እና ‹‹ምንም አይደለም እኔም  እፈራለሁ:: ግን  ፍርሀታችንን ለማለስለስ ብዙ ጊዜ አለን››አለና ሊያበረታታት ሞከረ፡፡
በረጅሙ ተነፈሰች፣ ከዚያም ፈገግ አለች።

ጭንቅላቷ ላይ ሳማትና ከዚያም በሹክሹክታ ‹‹ባዬ ራሄል››በማለት ክፍሉንም  ቤቱንም ለቆ ወጣ ።ራሄል እስከሳሎን ተከተለችውና  ከኋላው በሩን ዘጋች፡፡ የሞተር ሳይክሉን ድምፅ በመኪና መንገዱ ላይ ሲንደቀደቅ ሰማች። ጭንቅላቷን ቀዝቃዛው  መስታወት ላይ አስደገፈች፡፡ …በድንገት መጸለይ እንዳለባት ተሰማት።‹‹ጌታ ሆይ እሱን ጠብቀው›› አለች ‹‹ራሷን ለሌላ ሰው በዚህ መንገድ እከፍታለው ብላ ፈፅሞ አስባ አታውቅም ነበር? የፀጋ የታፈነ ጩኸት  ተሰማት…ራሷን ከተደገፈችበት  መስታወት  ቀና አደረገች እና ተንቀሳቀሰች…ከዛ ወደ ፀጋ ሄደች። እህቷን ለመከታተል ወደ ደረጃው እየሮጠች ስትሄድ፣ ቀድሞ የነበረባትን ስሜት እየሰመጠ እንደሆነ ተረዳች።
///
ዔሊያስ የቤቱን ዙሪያ ገባ ተመለከተ። ምንም ያማረ ነገር የለም። በራሱ ቤት ውስጥ በራሱ ሶፋ ላይ ተቀምጦ የነበረ ቢሆንም፣ አእምሮው ከአንድ በሰአት በፊትና በተለያት ሴት ላይ ተጣብቆ ነበር።ከአንድ ሰአት በፊት የሳማት ሴት አሁንም ልቡ ውስጥ እየተገላበጠች ነው።እንደዛ ያለ ድንገተኛ እርምጃ እንዲወስድ ያነሳሳው ምንድን ነበር?ቢያስብ ቢያስብ ሊገለፅለት አልቻለም፡፡
እረፍት አጥቶ ከሶፋው በመነሳት ቢንያም ወደተኛበት
ክፍል ተራመደ… ሀሳቡ  ዋና መኝታ ቤቱ በጥቂት ቀናት ውስጥ ማለቅ እንዳለበት ሊነግረው ነበር ። ነገሮች እንዳሰበው ሚሄዱ ከሆነ እና የገንዘብ እጥረት ካላጋጠመው ቤቱ በስድስት ወር ውስጥ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋል። በእቅዱ መሰረት ቤቱን ካጠናቀቀ በኃላ ቀጣዩ እቅዱ አዲስ መኪና መግዛት ነው።  እና ከዚያ ምናልባት ይህንን ንፁህ እና በስርዓት የተቀነበበ  ህይወቱን የምትካፍለው ሴት መፈለግ ይኖርበት ይሆናል። ከአመታ በፊት  እቅዱን  በዚህ መንገድ በቅደም ተከተል ሲያስቀምጥ ሁሉም ነገር እንከን የለሽ እንደሆነ እርግጠኛ ነበር፡፡  ነገር ግን ያ ራሔል ከፊቱ ከመጋረጧ በፊት ነበር ።

የወንዱሙን
ክፍል ለመክፈት እጄታውን ከያዘ በኃላ ሀሰቡን ቀየረ…ራሴ ተረብሼ ለምን እሱን እረብሸዋለው..በማለት ወደኃላ ተመለሰና ወደራሱ መኝታክፍል ገባ፡፡የልብሱን መሳቢያ ከፍቶ ከአሳዳጊ ወላጆቹ ቤት ያመጣውን የስጋ ወላጇቹን የፎቶ ሳጥን አወጣ ፡፡ራሄል ያቀረበችለትን ሀሳብ በድጋሚ አሰበበት።  ምናልባት አሳዳጊዎቹ ይሄንን የወላጆቹን ፎቶ ከእሱ ለማራቅ ጥሩ ምክንያቶች ነበሯቸው።በወላጆቹ ፊት ላይ የራሱን አሻራ ለማግኘት እየሞከረ ፎቶውን አገላብጧ ተመለከተ። አገጩን በእናቱ፣ ዓይኖቹ በአባቱ መልክ ላይ በጨረፍታ የተመለከተ መስሎት ነበር። ወይም ምናልባት ምኞት እንደዛ ስለሆነ ይሆናል፡፡ ፡፡እሱ እንደ አብዛኛው የማደጎ ልጆች ፣ስለ ወላጆቹ  ይበልጥ ለመማር  እና ለማወቅ ፍላጎት ነበረው ።እሱን በተመለከተ  በህፃናት ማሳደጊያ ተቋሙ ውስጥ ያለው ፋይል ውድ የሆኑ ጥቂት መረጃዎችን የያዘ ሲሆን አንዳንድ ነገሮችን እንዲያውቅ አድርገውታል፡፡ታዲያ ለምን መርካት አልቻለም?

ራሄል የማንቂያ ሰዓቱን ላይ ባለማመን አፈጠጠች።እንቅልፍ አልወስዳት ብሎ  ከግራ ወደቀኝ እየተገላበጠች ለአንድ ሰአት ተሰቃየች… የሰዓቱ መንቀርፈፍ የዘለአለም መሰላት። ደጋግማ  ከኤሊ ጋር ስታጫውተው የነበረውን ትዕይንት አዲስ እንደወጣ ተወዳጅ ፊልም ደጋግማ በምልሰት በማሰብ  አጣጣመችው፣ የከንፈሮቹን ንክኪ እንደገና ተሰማት።መላልሳ ባሰበችው ቁጥር በእያንዳንዱ ትውስታ  አዲስ ስሜት ይሰማት ነበር። በቀጣይ ምንድነው የሚሆነው….?እራሷን ትጠይቃለች….አእምሯዋ ለጥያቄዋ መልስ ከመስጠት ይልቅ ግራ መጋባት ውስጥ  አሽቀንጥሮ ይጥላታል፡፡
ያለፈውን የልቧን ጭለማ ጓዝ  እንዴት መልቀቅ እንዳለባት እስከአሁን አላወቀችም፣ አልደፈረችም።
47👍9👏2