አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
_
__
///
‹‹ነይ የኔ ማር፣ ዝም በይ፣ ላደርቅልሽ እፈልጋለሁ።››ራሄል ትሁትን ከመታጠቢያ ገንዳው ውስጥ አውጥታ በፎጣው  ጠቀለለቻት።

ወደ ምትሄድበት የስብሰባ ቦታ ፀጋን መውሰድ እንዳለባት ወስናለች፡፡  ህጻኗን ዛሬ ከሰአት በኋላ  ለረጅም ሰዓት እንቅልፍ እንድትተኛ አድርጋ ስለነበር  ማታ ከሶስት ሰዓት በፊት   እንደማትተኛ ታውቃለች። ልብስ ልታለብሳት እየተዘጋጀች ሳለ ሕፃኗ ከንፈሯ ላይ በጥፊ  መታቻት። ትልቅ ሰው በጥፊ ያጠናገራት ነው የመሰላት‹‹አንቺ ትንሽ ድርዬ›› ብላ አጉተመተመች፡፡ ‹‹ምን ፈልገሽ ነው የምትደባደቢው?›› ጠየቀቻት፡፡

  በዛው ቅፅበት  የበሩ ደወል ጮኸ። ለመክፈት ፊቷን ስታዞር የራሄል እግር ይዛ  ታገለቻት ሳትወድ በግዷ ጎንበስ ብላ አቀፈቻት፡፡ አሁንም በፎጣው ተጠቅልላለች። ራሄል በረዥሙ ኮሪዶር ላይ ወርዳ የራሷን ክፍል አልፋ ወደ መግቢያ በር ቀረበች። መጥሪያው ከእንደገና ጮኸ…

‹‹መጣሁ፣ መጣሁ››ስትል ራሄል አጉተመተመች፣ አሁንም በደረጃው ላይ ነች።ከታች ስትደርስ የእብነበረድ ወለሉ ቅዝቃዜ በባዶ እግሯ ዘልቆ ተሰማት ፡፡በሩን በዝግታ ከፈተችው።ዶ/ር  ኤልያስ ነበረ፡፡

ወደ ውስጥ ስትጋብዘው ተንደርድራ ጉንጩ ላይ ተጣብቃ ልትስመው ፈልጋ ነበር…እንደምንም እራሷን ተቆጣጠረች፡፡
እሱ የፀጋ ሐኪም ብቻ ነው። እሱ የእህቷን ደህንነትን ሊቆጣጠር እናሊከታተል ብቻ ነው ወደቤታቸው የሚመላለሰው ። በማለት እራሷን ለማረጋጋት ጣረች፡፡ የዔሊ ሞቃታማ ሰማያዊ አይኖች ቀና ብላ ስትመለከት፣ውስጧ ተናወጠባት፡፡
‹‹ኤሊ ውሰደኝ…››ትሁት ጮኸች፣
ራሄል እህቷን ችላ ብላ ከኤልያስ ጋር ማውራቷን ቀጠለች፡፡‹‹አንዲት ብዙ ገንዘብ ለፋውንዴሽናችን የምትለግስ ሴት ማግኘት አለብኝ እና ምርጫ ስለሌለኝ ፀጋን ይዣት ልሄድ ነበር ያሰብኩት…ምን ትላለህ?››

‹‹ማታስቸግርሽ ከሆነ ምንም ችግር የለውም….››አላት

‹‹ እሱ የእኔም ስጋት ነው….ድፍረት ካልሆነብኝ ልትረዳኝ ትችላለህ?››

‹‹ለምን አይሆንም?እዚህ ሆኜ እንድጠብቅልሽ ነው የምትፈልጊው?››

‹‹ኮስተር አለችበት‹‹እሱም ይቻላል..ግን አብረኸን ብትሄድና እዛ ሴትዬዋ ጋር በምነጋርበት ሰዓት አንተ ፀጋን ታጫውትልኛለህ ብዬነበር ያሰብኩት…እኔም እንዲህ ሆና ይሆን ከሚል ስጋት ተገላግዬ በተረጋጋ መንፈስ ከሴትዬዋ ጋራ አወራለው››አለችው፡፡

ሳቀባት…….
በሳቁ ግራ ተጋባች‹‹ምነው ያልሆነ ነገር ተናገርኩ እንዴ?››

‹‹አይ…አሁን ኦርጂናል እናት እየሆንሽ እንደሆነ ስለታዘብኩ ነው…እዚህ ለእኔ እንኳን ቢሆን አምነሽ ጥለሻት ልትሄጂ አልፈቀድሽም…በእውነት ደስ ብሎኛል…አብሬችሁ እሄዳለው››

‹‹እሺ ይህችን ልጅ  ላልብሳት እና እኔም ለብሼ መጣን ….አስር ደቂቃ ታገሰን››

‹‹ችግር የለም..ሂዱ›› ፈቀደላቸው…ሄለን ፀጋን እንዳቀፈች ወደመኝታ ቤት አመራች፡፡ፀጋን ካለበሰች በኃላ የራሷን ልብስ ቀየረችና መስታወት ፊት ስትቆም ቅድም ፀጋ የመታቻት ከንፈሯ ቀልቶ እና አብጦ ተመለከተች….፡፡
ወደፀጋ ዞራ ልንቦጯን ዘርግታ እያሳየቻት ‹‹ውይ አንቺ ልጅ ….እይው እስኪ ያደረግሺኝን››
ፀጋ እየተመለከተቻት ሳቀችባት፡፡ራሄል ከፍሬጅ ውስጥ በረዶ አወጣችና ያዘችበት፡፡ከዛ ቀይ ሊፒስቲክ አወጣችና በስሱ በመቀባት የቀላውን ከንፈሯን ከሌላው ክፍል ጋር አመሳሰለችው፡፡
ከዛ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ከተረዳች በኃላ ቦርሳዋን ይዛ በአንድ እጆ  የፀጋን እጅ ጨብጣ ወደሳሎን ሄደች፡፡ተያይዘው ከቤት ወጡ፡፡

ራሄል ከንፈሯን አስጨነቀች፣ ጸጋና መሀከላቸው አድርገው ወደ  ራሄል መኪና ሲያቀኑ ልክ በቅርብ የተጋቡ ባልና ሚስቶች ይመስሉ ነበር፡፡ፀጋን ከኋላ በስርዓቱ ቀበቶዋን አሰሩላትና እነሱ ገቢና ጎን ለጎን ተቀመጡ..መኪናውን የምታሽከረክረው ራሄል ነበረች፡፡
ለተወሰነ ደቂቃ በዝምታ ነበር የተጓዙት ያሉት፡፡በፋውንዴሽኑ ውስጥ ስላሏት ችግሮች ለአንድ ሰው መንገር ፈልጋ ነበር። የሮቤል ሚስጥራዊነት አሳስቧታል።ትናንት ማታ  አነጋግራዋለች። ለምን ጥሪዋን እንዳልመለሰላት ስትጠይቀው ሞባይሉን ቤቱ ረስቶ እንደነበር  ነው የነገራት።በበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ያገኘኛቸውን መረጃዋች በማጠናከር ላይ ተጠምዷ ስለነበር ጊዜ አልነበረውም .. እሱ የሚፈልገው አንድ ነገር እንዳለ በግልፅ ነግሯታል….እሷም ልታምነው ፈለገች ነገር ግን አልቻለችም እና ዛሬ ከሰአት በኋላ በፋውንዴሽን ከኮምፒውተሯ ጋር ስትገናኝ፣ ሌላ ሰው የቢሮውን ኮምፒውተር ላይ እንደገባ አስተዋለች። መረጃዋን የሚበረብር ማን እንደሆነ ግራ ተጋብታለች፡፡

የአእምሮዋን ፍጭት ያነበበ ይመስል‹‹የምታናግሪው ሰው አለ?›› ስል ጠየቃት። ራሄል ወደ
‹‹ስለዚህ ነገር በተለምዶ ከአባቴ ጋር ነበር የምንነጋገረው፣ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ እንደምታውቀው በእናቴ ጉዳይ በጣም የተጠመደ ነው እና እሱን ማስቸገር አልፈልግም።››

‹‹የፋውንዴሽኑ ቦርድ እንዴት ነው? አይረዳዱሽም እንዴ?››

ራሄል አንገቷን በአሉታ ነቀነቀች። ‹‹አይ አሁን ያጋጠመን … ውስጣዊ ችግር ነው እነሱን ወደዚህ ጎትቼ ማስገባት አልፈልግም….እኔ በራሴ በምችለውን መንገድ መፍትሄ መፈለግ አለብኝ››

‹‹ሁሉንም ነገር በራስሽ ብቻ ማድረግ የለብሽም››ኤሊ ተቃወማት ።በዚህ ጊዜ የሚሄዱበት ቦታ ደርሰው መኪናዋን እያቆመች ነበር፡፡
ትንሽ ሳቅ ብላ‹‹በቅርብ ጊዜ ሁሉንም ነገር በራሴ የማደርገው ይመስላል››ስትል ቦርሳዋን አንጠልጥላ ከመኪናዋ ወረደች፡፡ራሄል ከመኪናው ጎን በመጣችበት ጊዜ ኤሊያስ ፀጋን ከታሰረችበት ቀበቶ እየፈታት ነበር። የዳይፐር ቦርሳውን ለራሔል ሰጣት እና በሩን ዘጋው።  ራሄል ወደ ወ.ሮ ላምሮት መግቢያ ደረጃ ሲወጡ‹‹ልክ  እንደ ትንሽ ቤተሰብ እንመስላለን››ስትል አሰበች።

መግቢያ በራፉ ላይ ደረሱና ደወሉን ተጫኑት፡፡ ‹‹ማግባት ምን አይነት ጣዕም ሊኖረው  ይችላል?››እራሷን ጠየቀች፡፡ ጋብቻ ከኪሩቤል  በኃላ ያልተጠቀመችበት ቃል ነበር።የስሙ ትዝታ የደስታ ስሜት እንዲሰማት አደረጋት፣ ከዚያም የታማኝነት መጉደል ውስጧን ሲያንቀጠቅጣት ተሰማት። እንዲህ ያሉ የቀን ህልሞችን እንድታልም ስውር ኃይል የነበረው ኪሩቤል ብቻ ነበረች። ከዚህ በፊት ወይም በኋላ ማንም ሌላ ሰው ያንን  ስሜት ሊቀሰቅስባት አልቻለም ።
ራሄል ድጋሚ ደወሉን ልትደውል ስትል በሩ በራሱ ተከፈተ። ራሄል ወደ አንድ ትልቅ አዳራሽ መሳይ ሳሎን ውስጥ ገባች ወዲያው ጥርት ያለ ሰማያዊ ቀሚስ የለበሰች ሴት ተቀበለቻት።

‹‹ወ/ሮ ላምሮት ከኋላ ባለው አትክልት ስፍራ እየጠበቀችሽ ነው።››በማለት ዘወር ብላ ወደ ሌላ በር መራቻቸው፡፡ ወደ ዔሊ ተጠግታ በሹክሹክታ  ‹‹ፀጋ ከስርህ እንድትርቅ አትፍቀድላት። ››ስትል ተናገረች፡፡ፈገግ አለላት….በፊት ፀጋን በተመለከተ እንዲህ አድርጊላት… ይሄንን ተጠንቀቂላት… እያለ የሚያጨናንቃት እሱ ነበር..አሁን ግን ይሄው በተቃራኒው ለእሱ መመሪያ እየሰጠችው ነው፡፡እያሳየች ባለችው ለውጥ በውስጡ እርካታ ተሰማው፡፡
ወ.ሮዋ ከተቀመጠችበት መድረክ መሳይ ውብ ቦታ ባሻገር በሁለት በኩል በጡብ ግድግዳ የተከበበ አበባ ሞልቶ ነበር። ወ.ሮ ላምሮት በትልቅ ዣንጥላ በተከለለ የመስታወት ጠረጴዛ ጎን ከተቀመጠችበት ልዩ ወንበር ተነስታ ‹‹ ጤና ይስጥልኝ ራሄል …በድጋሚ እንኳን ደህና መጣሽ ›› አለቻት ፡፡
60👍3😱2👏1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///

ፀሀፊዋ አለምን አቁማ ወደዳኛው ቢሮ ተራማዳ በራፉን በጥንቃቄ አንኳኳች እና ወደውስጥ ገባች…ብዙ ሳተቆይ ተመልሳ ወጣችና ወደአለም ቀርባ …በአጭሩ

‹‹ሊያይሽ ተስማምቷል ››አለቻት፡፡

"አመሰግናለሁ።" አለችና እሷን አልፋ ወደ ክፍሉ ገባች።

"ወ.ሮ አለም …በዚህ ጊዜ ስለምንድነው የምታናግሪኝ?" ዳኛ ዋልልኝ ኮቱን ከመስቀያው ላይ እየጎተተ ነበር የሚያናግራት። "ያለ ቀጠሮ ሰው ቢሮ የመግባት መጥፎ ልማድ ያለሽ ይመስላል። እንደምታየው እኔ ልወጣ ነው። ልጄ ስርጉት ያለ እኔ እራት መብላት አትወድም እና እሷን ማስጠበቅ ለእኔ አሳፋሪ ነው።"

"ሁለታችሁንም ይቅርታ እጠይቃለሁ ክቡር ዳኛ… ለፀሀፊዎ እንደነገርኩት ጉዳዬ በጣም አስቸኳይ ስለሆነብኝ ነው ።"

"እሺ…ልስማው?"

"መቀመጥ እንችላለን?"

" ቆሜ መስማት እችላለሁ …ምን ልትነግሪኝ ፈልገሽ ነው?"

"የእናቴ አስከሬን ተቆፍሮ እንዲወጣ እና  ዳግም የፎረንስክ ምርመራ እንዲደረግበት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲሰጡልኝ እፈልጋለሁ."

ዳኛው ቀስ ብሎ ወንበሩ ላይ ተቀመጠ። አለም ግልፅ የሆነ ጭንቀት ተመለከተችበት።

"ይቅርታ፣ ምን አልሺኝ?፧"

"ክቡር ዳኛ  ያልኩትን እንደሰሙኝ አምናለሁ፣ ግን ጥያቄዬን መድገም አስፈላጊ ከሆነ፣ አደርገዋለሁ።"

ዳኛው  እጁን አወዛወዘ። "አይ. ቸሩ ጌታ አይሆንም. አንድ ጊዜ መስማት በቂ ነው…ለምን እንዲህ አይነት አስቀያሚ ነገር ማድረግ ፈለግሽ?"

"የመፈለግ ጉዳይ ሳይሆን ግድ ሆኖብኝ ነው, በጣም  አስፈላጊ ነው ብዬ ባላምን ኖሮ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልጠይቅም ነበር."

"አስቲ ተቀመጪና…  ምክንያቶችሽን አስረጂኝ።››

"እናቴ ላይ ወንጀል ተፈጽሟል ፣ነገር ግን ትክክለኛው ፍርድ ተገኝቷል ብዬ አላምንም ።"

"እንደዛ ማድረግ አትችዬም " ብሎ ጮኸ።
"አልሰማሽም።ከአመታት በኃላ ድንገት ከመሀከላችን ተገኘሽ፣ ወዲያው መሠረተ ቢስ ውንጀላ ይዘሽ ትረብሺኝ ያዝሽ፣ ለበቀል ቆርጠሻል።"

"ይህ እውነት አይደለም" ስትል ለመከላከል ሞከረች ፡፡ " ለመሆኑ ሀለቃሽ ግርማ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል?"

"አሱ ለጊዜው የለም ..ለጥቂት ቀናት እረፍት ወሰዶ ወደ አዲስአበባ የሄደ ይመስኛል።›› ዳኛው ተናደደ።

" ለማንኛውም ጥያቄሽ … ጥሩ ሀሳብ አይመስለኝም››

" ክቡር ዳኛ ማስረጃ እንድፈልግ ይፈቅዱልኛል?"

"ምንም ማስረጃ አታገኚም" ሲል አፅንዖት ተናገረ፡፡

"ከእናቴ አስከሬን የተወሰነ መነሻ ሚሆነን መረጃ ልናገኝ እንችላለን."

" የተገደለችውና ሬሳዋ የተገኘው እኮ ከዛሬ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ነበር ።"
"በዚያን ጊዜ ለሬሳ ምርመራ ለማድረግ ቴክኖሎጂዎች አልነበሩም… ..በአሁኑ ጊዜ ግን ነገሮች የተለዩ ናቸው፡፡እኔ በግሌ ጎበዝ የተባለ የፎረንሲክ ስፔሻሊስት አውቃለሁ።አሁን ለሚከሰቱ የወንጀል ድርጊቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ከእሱ ጋር የመስራት እድል ነበረኝ …እሱና ጎደኞቹ በጣም ውጤታማ ናቸው ..በዛን ወቅት ባለው ቴክኖሎጂ ሊገኝ ያልቻለ የሆነ ነገር ሊያገኝልን እንደሚችል ዋስትና እሰጥዎታለሁ።››

"ጥያቄሽን እንደጥያቄ እወስደዋለሁ።››

"መልሱ ለዛሬ ማታ ቢደርስልኝ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው ።"

" ይቅርታ ወ/ሪት አለም ማድረግ የምችለው በአንድ ጀምበር አስብበት እና በጠዋት መልሱን እሰጥሻለው።እስከዛው ሀሳብሽን ለውጠሽ ጥያቄውን እንደምትሰርዢ ተስፋ አደርጋለሁ።"

"አላደርገውም።››

ዳኛው ከተቀመጠበት ተነሳ። "ደክሞኛል፣ በዛ ላይ ርቦኛል፣ እናም በዚህ የማይመች ቦታ ላይ ስላስቀመጥሺኝ ተበሳጫችቻለሁ።" የክስ አመልካች ጣት አነጣጥሮባት። "እኔ እንደህ አይነት የተጨመላለቀ ነገር አልወድም."አላት፡፡

" ይህ በጣም አስፈላጊ ባይሆን እኔም አላደርገውም ነበር."

"አስፈላጊ አይደለም."

"እኔ ደግሞ እንደሆነ አምናለሁ" ስትል በግትርነት መለሰች።

" አሁን፣ በቂ ጊዜዬን ወስደሻል። ይሄኔ ልጄ ስርጉት ተጨንቃለች።››

‹‹ ደህና ይሁኑ ብላ ።"ከክፍሉ ወጣች።
///
አለም ቀጥታ  ወደመኪናዋ አመራችና ወደቤቷ ነው የነዳችው… መንገድ በትራፊክ ስለተጨናነቀ ወደቤቷ ለመመለስ ረጅም ጊዜ ነበር የወሰደባት፡፡

ክፍሏ ገብታ አልጋዋ ላይ ተዘርራ ትንሽ እረፍት ለመውሰድ ሞከረች…ከዛ ተነሳች….ማስታወሻዎቿን እንደገና ለመገምገም ሞከረች….ወዲያው ሰለቻት፡፡ ቴሌቪዥኑን ለመክፈት ወሰነች። ሪሞቷን አነሳችና ከፈተች፡፡ፊልም ላይ አደረገችውና ሰውነቷን ለመለቃለቅ ልብሷን አወላልቃ ወደሻወር ቤት ሄደችና መታጠብ ጀመረች……ታጥባ ከመጨረሷ በፊት አንድ ሰው በሯን ሲያንኳኳ ሰማች… እርጥብ ፀጉሯን በፎጣ ጠቅልላለች። ረጅምና ነጭ ካባዋን አደረገችና እና ወገቧ ላይ ያለውን መቀነት ለማሰር እያስተካከለች ወደሳሎን ሄደችና በበራፉ ቀዳዳ በማጮለቅ ማንነቱን ለማረጋገጥ ሞከረች፡፡

የሰንሰለት መቆለፊያው እስከሚፈቅደው ድረስ በሩን ከፈተችው "እንኳን ደህና መጣህ ኩማንደር ምነው በሰላም?"

ኮስተር ብሎ"በሩን ክፈቺ" አላት

"ለምን?"

" ካንቺ ጋር መነጋገር አለብኝ።"

"ስለ ምን?"

‹‹ወደ ውስጥ ካስገባሺኝ እነግርሻለሁ።
አለም  አልተንቀሳቀሰችም."በሩን  ልክፈት  ወይስ  ምን?"እለች  ከራሷ  ጋር  ሙግት ገባች፡፡ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለውን ሰዓት ተመለከተች….ለሶስት እሩብ ጉዳይ ይላል፡፡
"እዚያው ሆነህ ላናግርህ እችላለሁ።"

"በሩን ክፈቺ" ብሎ ጮኸ።

‹‹ሰውነቴን እየታጠብኩ ነበር."አለም ሰንሰለቱን አላቀቀችና በሩን ከፍታ ወደ ጎን ቆመች።

"አንድ ሰው እየጠበቅሽ ነበር?"

"አይደለም."

ኮፍያውን ከጭንቅላቱ አወለቀና ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ … ወደ ወንበር ሄዶ ተቀመጠ እና ወደ ቴሌቭዥን ስክሪን ተመለከተ፣ ልብስ ያልለበሱ ጥንዶች ተቆላልፈው ይሳሳማሉ ። ካሜራው የወንዱ ከንፈር ከሴቷ ጡት ጋር ሲጣበቅ እያሳየ ነው፡፡

"ስለአቋረጥኩሽ መናደድሽ አይገርምም።››አላት ሪሞቱን አነሳችና አጠፋችው "አያየሁት አልነበር."
"በራፍሽን ለሚያንኳኳ ሰው ሁል ጊዜ በርሽን ትከፍቺያለሽ?"

"በዚህ ከተማ ውስጥ ከፍተኛው የህግ አስከባሪ የፖሊስ መኮንን ነህ። አንተን ማመን ካልቻልኩ ማንን ማመን እችላለሁ?ይልቅ በዚህ ማታ ለምን መጣህ? እስከ ጠዋት ድረስ መጠበቅ አልቻልክም?"

"ዳኛ ዋልልኝ ደውሎልኝ ስለጠየቅሽው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነገረኝ.››

በንዴት ሲመታ የነበረው ልቧ በፍጥነት ቀዘቀዘ፣ "በዚህ ከተማ ውስጥ የግል የሚባል ነገር የለም ማለት ነው?"ብላ ጠየቀች፡፡

"ብዙ አይደለም"

"በከተማው ክልል ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው የእናንተ ቡድን ሳይፈቅድለት ማስነጠስ የሚችል አይመስለኝም።"

"እንደፈለግሽ ተርጉሚው …አንቺ ዙሪያችን እየተሸከረከርሽ ጉድጓዳችንን ስትቆፍሪ ምን እንድናደርግ ጠብቀሽ ነበር?"

"የእናቴን መቃብር እንዲከፈት ማድረግ ትክክለኛ የግድያዋን መንሴ ለማወቅ ወሳኝ እርምጃ ነው ብዬ ባላስብ ኖሮ የምረበሻት ይመስላችኋል?" ሞቅ ባለ ስሜት ጠየቀች ።

‹‹አንቺ ቋሚንም ሆን ሟችን ከመረበሽ ውጭ ምን ስራ አለሽ?››

"አምላኬ ሆይ ጥያቄውን ማቅረብ እንኳን ቀላል ብሎኝ ያደረኩት ይመስልሃል? እና ዳኛው ከ አንተ እና ከሰዎች ሁሉ ጋር መማከር ለምን አስፈለገው?"

‹‹ለምን ብለሽ ትጠይቂያለሽ እንዴ?… ተጠርጣሪ ስለሆንኩ ነዋ?"

"ዳኛው በዚህ ጉዳይ ከአንተ ጋር መወያየቱ ሞያዊ ሥነ ምግባር የጎደለው ሽማግሌ መሆኑን ነው የሚያሳየው "

"እኔ እኮ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ነኝ፣ አስታውሺ?"
39👍4