#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
ወደ ሆስፒታሉ በሚወስደው መንገድ ላይ ሞተሩን እያስጎራ በመብረር ላይ ነው፡፡ ሀሳቡ ግን አሁንም ወደኋላ እየጎተተው ነው፡፡ በዚህ የሰንበት ማለዳ ወደእነራሄል ወላጆች ቤት የሄድኩት ራሄል ፀጋን እንዴት እያስተዳደረች እንደሆነ ለማየት ብቻ ነበር። ጉብኝቱ የህፃኗ ሐኪም በመሆኔ ያደረግኩት ነው።››ሲል ለራሱ ነገረው፡
አሁን፣ ፀጉሯን በትና እና የደበዘዘ ቲሸርት የለበሰች እንዲት ቆንጆ ሴት በአእምሮው ሰሌዳ ላይ ብልጭ ድርግም እያለች እየረበሸችው ነው፡፡ በባዶ እግሯ እና በሰማያዊ ጂንስዋ ምን ያህል ውብ እንደሆነች እያሰበ ነበር፣እሷ የምትኖርበትን ቤት እንዴት ግዙፍ እንደሆነ እና ወላጆቿ ምን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው እያሰበ ነበር። እና የተከበረ የመኳንንት ዝርያ አለን ብለው የሚያስቡ ወላጇች እንዳሏት እያሰበ ነበር… እና ደግሞ እሱ ሰለወላጇቹ ምን ይሁኑ ምን የሚያውቀው ነገር እንደሌለም እያሰበ ነበር፡፡በዚህም ሆነ በዚያ ሀሳቡ በራሄል ዙሪያ ከመሽከርከር ሊያቅበው አልተቻለውም፡፡
ኤልያስ አሳዳጊ ወላጆቹ ስለስጋ ወላጇቹ ብዙ ጊዜ አይናገሩም ወይም የበለጠ እንዲያውቅ አያበረታቱትም። ወደፊት ፀጋም ልክ እንደእሱ ስለ እናቷ እና አባቷ ማወቅ እንደምትፈልግ ገመተ።ስለ ፀጋ ማሰቡ በትክክል ወደ ራሄል መለሰው።ሸሩባ የተሰራው ጥቁር ፀጉሯ ፊቷን እንዴት እንደአሳመረው እና ሀዘን ያጠላባቸው ጎላ ጎላ ያሉ አይኖቿ ከብለል ሲሉ እንዴት ልብን እንደሚያርዱ አሰበ። ሆስፒታል ደርሶ ሞተሩን ሲያቆም እንኳ ሀሳብን መግታት አልቻለም ነበር፡፡
///
ራሄል ትሁት ቁርስ ስትበላ ፊቷ ላይ የተዝረከረከውን በደረቅ ጨርቅ በጥንቃቄ ጠራረገችላት። እቃዎችን እያጣጠበች ሳለ ፀጋ ወደ በረንዳ በሮች ስትሄድ አየች። ሰራተኛዋ አለም ሁል ጊዜ መስኮቶቹን በሚያብረቀርቅ ንፅህና ነው የምትይዛቸው ፣ ዛሬ ግን እሷና ፀጋ ብቻቸውን ናቸው..ሰራተኛዋ የረፍት ቀኗ ስለሆነ ዘመድ ጥየቃ ሄዳለች።እቃ ማጠቧን እንዳጠናቀቀች..ትንሿን እህቷን ለማየት ወደበረንዳ ስትወጣ የጸጋ ትንሽዬ የእጅ ህትመቶች መስታወቱን ጠቅላላ አዳርሰውት ሌላ ቅርፅ ሰጥተውት አገኘች፡፡ መጀመሪያ መልሳ ለማፅዳት ስትሞከር ፀጋ ከኋላዋ እየተከተለች መልሳ ስታቆሽሽባት…በመናደድ ፋንታ ከት ብላ ሳቀችና ማፅዳቱን እርግፍ አድርጋ ተወችው፡፡
‹‹ከአንድ በላይ ልጅ ያላቸው ሰዎች እንዴት በህይወት መቆየት ቻሉ?››ስትል ገረሜታዋን ገለፀች ፡፡ከፀጋ ጋር በቀጣይ ምን ማድረግ እንደምትችል አሰበች.. ።ሰዓቱን ተመለከተች, ከዚያም ወደ እሷ ተመለሰች. ወላጆቿ ዘወትር እሁድ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሄዱ ታውቃለች። ወጣት ሳለች ሁልጊዜ አብራቸው ትሄድ ነበር፣ ነገር ግን እጮኛዋ ኪሩቤል ከሞተ በኋላ ወደቤተክርስቲያን መሄዱን እርግፍ አድርጋ ተወችው፡፡ ይህ ድርጊቷ ወላጆቿን በጣም እንደሚያበሳጫቸው ታውቃለች፣ እነሱ ስለሚፈልጉ ብቻ ነገሮችን ማድረግ እንዳለባት አታምንም። እሷ የራሷን ሕይወት እየመራች ነበር፣ እና እግዚአብሔር የህይወቷ አካል አይደለም።
ፀጋን ስትመለከት ግን በድንገት ተጨማሪ ሀላፊነት እንዳለባት ተሰማት። በእርግጥ የሁለት ዓመት ልጅ ነበረች፣ … ስለግል እምነቷ ለራሷ ውሳኔ ማድረግ እንደምትችል ብታምንም ለዚህች ልጅም ተመሳሳይ ነገር ማድረጉ ትክክል ሆኖ አልተሰማትም።ወላጇቾ ቢኖሩ ይዘዋት እንደሚሄዱ እርግጠኛ ነች፡፡
‹ስለዚህ ወደ ፀጋ ጎንበስ አለችና‹‹የእኔ ቆንጅዬ እህት .. ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ትፈልጊያለሽ?›› ብላ ጠየቀቻት ፡፡
ህፃኗ በደስታ እየዘለለች‹‹ቤተክርስትያን እንሂድ፣ ቤተክርስትያን እንሂድ››አለች ፡፡ ራሄልም ልብሷን ቀያይራ ካለባበሰቻት በኋላ ወደቤተክርስቲያን ይዛት ሄደች፡፡
ራሄል የኮሌጅ ትምህርቷን እስካጠናቀቀች ድረስ ንቁ ተሳታፊ ነበረች።ሁሉ ነገር የተቀየረው እጮኛዋ ከሞት በኋላ ነው።እና አሁን የመቅደሱ ዙሪያ ስትመለከት፣ የልጅነትና የጉልምስና ትውስታዎች ሁሉ ተግተልትለው በአእምሯ ውስጥ ብልጭ ድርግም አሉባት። የዚህ ቤተክርስቲያን መዘምራን አባል ሆና ለረጅም አመት አገልግላለች ፤እዚህ መድረክ ላይ ወጥታ ስለጌታ የአዳኝነት ስራ ስትዘምር ትዝ ይላታል፡፡ ድምፆ ተስረቅራቂ የሚባል አይነት ስለነበር ብዙውን ጊዜ ድምጽ ማጉያውን ይዛ መዝምራኖችን የምትመራው እሷ ነበረች፡፡እጮኛዋ ኪሩቤልንም እዚሁ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው የተዋወቀችው፡፡እሱም ልክ እንደ እሷ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነበር…. ከዚያ ከመቀራረብና አብሮ ከመዋል ብዛት የፍቅር ስሜት በመሀከላቸው ተፈጠረ፡፡በቤተክርስቲያኒቷ ፊት ቃልኪዳን ተግባቡ …ሀይስኩል ጨረሱ ..ኮሌጅ ገቡ….እስከዛን ድረስ ሁለቱም በእምነታቸው የፀኑ ወጣቶች ነበሩ…ሁሉን ነገር ሀይማኖቱ በሚያዘው እና ቤተሰቦቻቸው በሚደሰቱበት አግባብ ለማድረግ ነበር እቅዳቸው…ሰርጋቸውን ባደጉበትና ባገለገሉበት ቤተክርስቲያን አደባባይ ላይ ለማድረግ ነበር ውጥናቸውና ጉጉታቸውም…ግን ምን ሆነ ህልማቸውን ሊኖሩ ወራት ሲቀራቸው..፣ኪሩቤል ድንገት ከእሷ ጋር ወደተቀጣጠረበት ቦታ ሞተር ሳይክሉን እያበረረ ሲመጣ እየተክለፈለፍ በፍጥነት ከሚያበር መኪና ጋር ተላትሞ በከፍተኛ ጉዳት ሆስፒታል ገባ…ይድንልኛል..መልሶ በእግሮቹ ቆሞ እንጋባላን ብላ ሆስፒታል ደረቅ ወንበር ላይ እየተኛች አንድ ወር ከግማሽ አካባቢ አስታመመችው…ግን አልተሳካም….የኪሩቤል ነፍስ ወደፈጣሪዋ ተጠርታ ሄደች..ከዛ ወዲህ ራሄል ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ሆነች…ሆስፒታል አስጠላት…የመድሀኒት ሽታ ቀፈፋት…ቤተክርስቲያንና እምነት አንገሸገሻት..የታመመ ሰው ማየት አቃታት…ይሄው አሁን ለታናሽ እህቷ ስትል እዚህ ያደገችበት ቤተክርስቲያን ስትመጣ ቁስሏ ሁሉ ክፉኛ ተቀሰቀሰ፡፡ እና የሚቀስፍ አይነት ህመም ተሰማት፣ ከዚሁ ሁሉ በጣም የሚገርመው ግን ለአፍታ ያህል ኪሩቤል ምን እንደሚመስል እንኳ ማስታወስ አለመቻሏ ነው ። ከሞቱ በኋላ አብዛኛዎቹን የኪሩቤልን ምስሎች በወላጆቿ ቤት አስቀምጧቸው ነበር እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አልተመለከቷቸውም። በጣም ተጎድታ ነበር። አሁን ምን እንደሚሰማት ግራ ተገባች።በመጨረሻም ጓዳኛዋ ሌንሳ ከወላጆቿ እና ከሁለት መንታ ልጇቾ ጋር ተቀምጣ አየች። ራሄል ከጎኗ ሾልካ ገባች።
‹‹ቤተክርስትያን መሄድ እርግፍ አድርገሽ የተውሽ መስሎኝ ነበር›› ስትል ወደጀ ጆሮዋ ቀርባ አንሾካሾከችላት፡፡
ሌንሳ ወደኋላ ዞረችና እያወራቻት ያለችው ራሄል መሆኗን ስታውቅ በመገረም ‹‹ራሄል እዚህ ምን እየሰራሽ ነው?›› ስትል ወደኋላ ተስባ አቀፈቻት፡፡
‹‹ፀጋን ማምጣት እንዳለብኝ ተሰማኝ››ስትል የመጣችበትን ምክንያት ነገረቻት፡፡
‹‹እሺ በምንም ምክንያት ይሁን በምንም እዚህ በመገኘትሽ ደስ ብሎኛል.››
የሌንሳ ወላጆችም በደስታ ሰላም አሏት፡፡
ዝግጅቱ እናዳለቀ ፀጋን እንዳቀፈች እነ ለሌንሳን ተከትላ ወደአውደ ምህረቱ ሄደች…ከረጅም ጊዜ በፊት የምታውቃቸውን በጣም ብዙ የድሮ ጎደኞቾንና ወዳጆቾን አገኘች፡፡ ብዙ ሰው ለምን እንደጠፋች እየጠየቃት በመምጣቷ እንደተደሰቱ ይነግሯት ነበር፡፡

❤37👍4👎1😁1