አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
502 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ

ይህ
ፋውንዴሽን አሁን የደረሰበት ደረጃ የደረሰው በዚህ መንገድ ነበር, አሰበች እንደ ሮቤል ያሉ ሰዎች የወላጆቿ ሀብት የፋውንዴሽኑን የጀርባ አጥንት እንደሆነ ነው የሚያስቡት፣ ገንዘብ በቀላሉ ወደ ሣጥን ውስጥ እንደሚገባ ያስባሉ ። ፣ ከቅርብ ረዳቶቿ ከሆኑ በጣም ጥቂት ሰዎች በስተቀር፣ በዚህ ስራ ውስጥ ግንኙነቶች ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አይረዱም። ግንኙነቶች፣ መተማመን እና ከፍተኛ የስራ ስሜት ወሳኝ ነገሮች ናቸው። ገንዘቡ ወደፋውንዴሽኑ ከሚገባት ፍጥነት ሚወጣበት ፍጥነት ይበልጣል።ራሄል የፋውንዴሽኑን አስተዳደር ስትረከብ፣ የሂሳብ መዝገቡ አሁን ባለበት ሁኔታ ጤናማ አልነበረም።

ወላጆቿ ጥሩ ልብ ያላቸው የሰው  ልጅን ያለልዩነት ለመርዳትና ለማገዝ ከልብ የሚጥሩ ቀና ሰዎች ቢሆኑም  የተሳሳቱ ሰዎችን አምነው ስለነበር  ለከፍተኛ ምዝበራ ተጋልጠው ነበር።እና ራሄል ስራዋን ከወላጇቾ ሙሉ በሙሉ ከተረከበች በኃላ አጠቃላይ የፋውንዴሽኑን ተቋማዊ አቅም ለማሻሻል ጥቂት አመታትን እና አንዳንድ ከባድ ውሳኔዎችን እንድትወስድ አስገድዷታል፣ከዛ ቀስ በቀስ ፋውንዴሽኑን አሁን ያለበት አቋም ላይ እንዲገኝ ማድረግ ችላለች፡፡ የተቋቋሙ ያገኘውን ገቢ በጥንቃቄ  ለተከበሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን እንደሙዳይ…ሜቅዶኒያ ላሉ  ገንዘብን ለታለመለት አላማ ብቻ ለሚያውሉ ተቋማት ያከፋፍላል፡፡ቀዳዳቸውን ይደፍናል ጉድለታቸውን ይሞላል፡፡


‹‹ሮቤል፣ ስለዚህ ጉዳይ አሁን ማውራት አልችልም። አሁንም ከሎዛ ጋር መገናኘት እና ከዚያም ፀጋን ከመዋለ ሕጻናት መውሰድ አለብኝ።ከዛ ቀጥታ ወ.ሮ ላምሮትን ሄጄ አገኛታለው….ደውልላት እና ከአንድ ሰዓት በኋላ እቤቷ እንደምገኝ ንገራት፡፡››አለችው፡፡ ወይዘሮ ላምሮት ብዙ ጊዜዋን እየወሰደች ነበር፣ ሴትየዋን ወደ ሎዛ ለማስተላለፍ አልደፈረችም ፡፡ለዚህ ነው ቀጥታ እራሷ ልታገኛት የወሰነችው፡፡

ቦርሳዋን ይዛ ከቢሯዋ ወጣች፡፡

ከአስራ አራት ደቂቃ በኋላ ወደ መዋዕለ ሕጻናት ማእከሉ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ስትገባ ጎማ በጭቃ ውስጥ ገባ። ቦርሳዋን እና ቁልፏን ይዛ ከመኪናው ውስጥ ዘላ ወጣች፣ ጉልበቷን የበሩን ጠርዝ መታት..አቃሰተች እና ጎንበስ ብላ እያሻሸች መንገዷን ቀጠለች .. የሞባይል ስልኳ እየጠራ ቢሆንም   ችላ ብላ  የመዋዕለ ሕፃናት ማቆያውን የመስታወት በሮች ከፍታ ወደውስጥ ገባች ፡፡ለአባቷ የገባችው ቃል ኪዳን እና በኤሊያስ   አይኖች ውስጥ ያነበበችው ጥርጣሬ  ለፀጋ አስፈላጊውን ጊዜ መድቦ ተገቢውን እንክብካቤ ለማድረግ    ቁርጠኛ እንድትሆን አድርጓታል። ከሁሉም በላይ ግን ፀጋ  እህቷ ነበረች። እና ምንም አይነት አስቸጋሪ ቢሆንም በክፉ ቀን ቤተሰብ ለቤተሰብ መከታ መሆን እንዳለበት ታምናለች፡፡ ፀጋ  ሰዓቱን በትኩረት በምትመለከተው የቀን ተንከባካቢ ሰራተኛ እቅፍ ውስጥ ሆና እየጠበቀቻት ነበር። አፏ እና ጠባብ አይኖቿ ስትመለከት ነገሮች ጥሩ እንዳልሄዱ ገመተች።

‹‹ሴት ልጃችሁን በፕሮግራማችን ስታስመዘግቡ ፖሊሲያችንን በግልፅ አሳውቀናችኋል።›› ሴትዬዋ በጠንካራ ንጭንጭ ተቀበለቻት፡፡

‹‹ይገባኛል... ›› አለች‹‹እና እህቴን በሰዓቱ ስላልወሰድኩ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ››ስትል አከለችበት ፡፡

‹‹በጣም ዘግይተሻል››የሚለው ቃል አከለችበት ። ጎንበስ ብላ የፀጋን  ዳይፐር ከቦርሳ አወጣች እና ከዚያም ወደ እህቷ ተጠጋች  ።‹‹ቶሎ ልናገኝሽ ሞክረን ነበር።›› ወይዘሮ ባንቺ ወደ ፀጋ ተመለከተች እና ፊቷን አኮሰታተረች። ያን ጊዜ ነበር ራሄል የልጅቷን በእንባ የታጠበ ጉንጯች ያስተዋለች። ‹‹ፀጋ  ጥሩ ቀን አላሳለፈችም። ነርሷ የሙቀት መጠንዋን ስትወስድ  ከፍ ብሎ ነበር፣ በተቻለ ፍጥነት ሀኪም ቤት እንድትወስዷት ተናግራለች ።››

‹‹እንዴ አሁን?...ለማለት የፈለኩት ይህ ምን ያህል አጣዳፊ ነው? ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ልውሰዳት ወይስ ሁኔታዋን መከታተል አለብኝ?››ስትል ጠየቀች፡፡

ወይዘሮ ባንቺ  ‹‹ወዲያውኑ  ብትወስጂያት መልካም ይመስለኛል.. እህትሽ ካለባት የጤና ችግር አንፃር  የበለጠ ንቁ መሆን ይገባታል።

‹‹ያንን አስቤ ነው ወደዚህ ያመጣኋት… በቃ ወስዳታለው›› የፀጋ የሰውነት ሙቀት በልብሷ አልፎ እየተሰማት ነው። ላለባት ቀጠሮ  ሰዓቷን ለማየት አልደፈረችም። ሆስፒታሉ ከመዋዕለ ህጻናት ብዙም ባለመራቁ አመሰገነች፡፡
ከሃያ ደቂቃ በኋላ ወደ ሆስፒታሉ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ገባች እና በድንገተኛ ክፍል በሮች ቸኩላ ስታልፍ ትዝታዎቹ እየተጣደፉ መጡባት።በእቅፏ ወደተቀመመችው ፀጋ ተመለከተች እና አዲስ ፍርሃት መላ ሰውነቷን ተቆጣጠራት። ወደ መቀበያ ጠረጴዛው እየገሰገሰች ስትሄድ፣ ቀድሞውንስ ይሄን ጉዳይ እንዴት አድርጋት ልትወጣ እንዳሰበች  ተገረመች። ላለፉት ስምንት አመታት በድንገት የሚደፈርስ ስሜት እና ከቁጥጥር ውጪ  የሚወጣ ድንገተኛ ብስጭትን  ስትዋጋ ነው የኖረችው። አሁን የአንዲት ቀጫጫ ነርስን ማይረብ ጥያቄዎችን በትዕግስት  እየመለሰች ነው።እንደጨረሰች  በውስጧ እየበቀሉ ያሉ  አሮጌ እና አዲስ ፍራቻዎችን እየታገለች፣ ለሆስፒታሎች ልዩ የሆኑትን የተለመዱ ሽታዎች እያሸተተች በተጨናነቀው የመጠበቂያ ክፍል ውስጥ ተመልሳ ተቀመጠች።

ከድንጋጤዋ የተነሳ  መላ ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው ፡፡ለፀጋ ስትል ትኩረቷን ለመሰብሰብ  መሞከር አለባት።ፀጋ እጆቿ ይንቀጠቀጣሉ፣ ከሰውነቷ የሚወጣው ሙቀት በየደቂቃው እየጨመረ ነው። ነርሶቹ  በስራ ተጠምደዋል፡፡ችሎታ ያለው እና ኃላፊነት የሚሰማው ዶ ር ለማግኘት  ዙሪያውን አማተረች። አንዳቸውም ወደ ራሔል ዞር ብለው አላዩትም።ሰዎች ወንበሮች ላይ ተቀምጠው ይንቆራጥጣሉ፣ አንዳንዶቹ ጎንበስ ብለው ያቃስታሉ፣ ሌሎች ደግሞ ደንዝዘው እያንጓላጅጁ ነው፡፡

እያንዳንዳቸው በራሳቸው መከራና ሀዘን ተይዘዋል..ስለ ራሄል እና በእቅፏ ውስጥ እየተቃጠለች ስላለችው  ህፃን  ደንታ አልነበራቸውም።ከዚያም ፀጋ እየደነዘዘች ሄደች፡፡  ድንጋጤ የራሄልን ጉሮሮ አነቃት። አምላክ ማንኛውንም ነገር እንደሚያደርግ ብታምን ኖሮ አሁን  በዚህ አስጨናቂ ጊዜ ትጸልይ ነበር።እግዚአብሔር ግን ከዚህ በፊት ከልቧ በፀለየችበት ጊዜ ትኩረት አልሰጣትም ነበር  እና አሁንም እሱ ላይ መንጠልጠል አልፈለገችም፡፡ ፀጋ ማቃሰቱን አቁማ  እንደገና  በመጠኑ ዘና ስትል እፎይታ ተሰማት። ራሄልን ቀና ብላ ተመለከተች፣ታናሽ እህቷ  ለስላሳ ቡናማ አይኖቿን ራሄል ላይ አንከባለለችባት፡፡ ራሄል በምላሽ ልቧ ሲዘል ተሰማት። ከዚያም ራቅ ብላ ተመለከተች።

ፀጋ  ለእሷ   ግዴታዋ ነበርች ይህች ልጅ ቀስ በቀስ የፍቅር እሳት  በልቧ ዙሪያ እንዲቀጣጠል እያደረገች ነው። እንደ ፀጋ ካለች ልጅ ጋር መጣበቅ ማለት ልቧን ለህመም እና ማጣት እምቅ ስቃይ መከፈት ማለት እንደሆነ ታውቃለች።እና ያንን በራሷ ላይ እንደገና ማድረግ ፈፅሞ አትፈልግም ነበር ፡፡ግን ደግሞ በምርጫዋ እያደረገችው ያለ ነገር አይደለም፡፡ከአሰልቺ ጥበቃ በኃላ ነርሷ መጥታ በመጋረጃ ወደተሸፈነው ክፍል ወሰዳቻቸው። ራሄል እህቷን አልጋው ላይ በጥንቃቄ አስቀመጠቻት።ነርሷ የጥያቄዎችን ፣ የአለርጂዎችን ፣ የመድኃኒቶችን ዝርዝር ጠየቀቻት። ራሄል የምትችለውን ያህል መለሰች።እንደጨረሰች ነርሷ  ጆሮዋ ውስጥ ቴርሞሜትር ጨመረች ..በዛ ቅፅበት  አንድ ዶክተር ኮሪደሩን  ሰንጥቆ ወደ እነርሱ   ሲመጣ ተመለከተች። ነጭ ጋወን አድረጎ ስቴቶስኮፕ አንገቱ ላይ አንጠልጥሏል ።ኤሊ ነበር።
46