#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
እሁድ የእረፍት ቀን ስለሆነ ኤልያስ ከወንድሙና ከጓደኛው ጋር ካፌ ቁጭ ብለው ቁምነገሩንም ቀልዱንም ሲጫወቱ አረፈድና ሌላ የሚሄዱበት ቦታ ስለነበር ተያይዘው ወጡ፡፡ሶስቱም የቢኒያም መኪና ወዳቆመችበት ቦታ እየተለፉ እየሄዱ ሳለ ድንገት ኤልያስ ከወንድሙ ከቢኒያም ጉሽሚያ ለማምለጥ ወደኃላው ሲሸሽ ከአንድ ውብ ሴት ጋር ተላተመ ፡፡ሴትዬዋ በእጇ የያዘችው ወረቀቶቿ ከእጆቿ ተንሸራተው ወደቁ እና ቦርሳዋ ከተከሻዋ ተንሸራቶ ሊወድቅባት ነበር…እሷም ተነገዳግዳ ሚዛኗን ለመሳት ስትጥር ኤልያስ በፍጥነት ተስፈነጠረና ክንዷን ያዛት ። ተረጋግቶ ሲያያት አይኖቹን ማመን ነው ያቃተው ።፡ራሄል ነች፡፡ ሞባይል ስልኳ አንድ ጆሮዋ ላይ ተጣብቆል…ስልክ እያወራች እንደነበር ተገነዘበ፡፡
አቀርቅራ የተበተኑ ወረቀቷቾን እያየች‹‹ምንድነው…አይንህ አያይም እንዴ? አብደሃል?››ስትል ጮኸችበት ።ከዚያም ቀና ብሎ አያት።ሀዘን ያረበባቸው አይኖቿ እሱን ሲያዩት ፣ ንዴቷ በጥልቀት ወደ ውስጡ ዘልቆ ሲገባ ተሰማው። በልቡ ክልል ውስጥ የሆነ ቦታ ላይ የብርሃን ብልጭታ ፈነጠቀ።ድንገት ወደጎን ዞር ብላ እሱ መሆኑን ስታውቅ በንግግሯ አፈረች፡፡‹‹እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ››ብላ አጉተመተመች፣ክንዷን ወደኋላ ጎተተች። አሁንም እንደያዛት ረስቶት ነበር። ፈጠን ብሎ ለቀቃት። ርቀቱን ጠብቆ በጉጉት እያዩ ወደነበሩት ወንድሙ እና ጓደኛው እየተመለከተ። ‹‹ይቅርታ አላየሁሽም….ከወንድሜ ቢኒ ጡጫ እራሴን ለማራቅ እየሞከርኩ ነበር.››አላት፡፡
‹‹ምንም አይደለም፣ እኔም ቀልቤ የማወራው ስልክ ላይ ስለነበር መጠንቀቅ አልቻልኩም ።›› በማለት ወረቀቶቿን ለማንሳት ጎንበስ አለች።
‹‹ቆይ እኔ ላንሳልሽ›› ብሎ እሱም ጎንበስ አለ… ሁለቱም በአንድነት እጇቸውን ወደወረቀቱ ሲሰዱ እርስ በርስ ተነካኩ ፡፡በመሀከላቸው የኤሌክትሪክ ንዝረት አይነት ቅፅበታዊ ብልጭታ ተፈጠረ፡፡
‹‹እባክህ አትጨነቅ›› የውስጥ ስሜቱን የሚቆሰቁስ አይነት እንደገና የሚያነቃቃ ፈጣን ፈገግታ ሰጠችው።
ወረቀቶቹን ሰብስበው ከተነሱ በኋላ‹‹ለመሆኑ እዚህ ሰፈር ምን እግር ጣለሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ለስራ ጉዳይ››ስትል አፏ ላይ የመጣላትን ምክንያት ሰጠችው፡፡
‹‹ በእረፍት ቀን ትሰሪያለሽ እንዴ?››
ራሄል ፊቷን አኮሳትራ‹‹ስራ እስካለኝ ድረስ ቀን ሳልመርጥ ነው የምሰራው..ታውቃለህ …ሥራዬ በጣም አስፈላጊ ነው።››ስትል መለሰችለት፡፡
‹‹ደህና፣ በቃ እንገናኛለን።››
‹‹ተስፋ አደርጋለው።›› አለችና መንገዷን ቀጠለች ፡፡
‹‹አሁንም አለሽ ራሄል?›› ከያዘችው የሞባይል ስልክ የአንድ ወንድ ድምፅ ተሰማ። እናም ራሄል እስከአሁን ስልኳ እንዳልተቆረጠ ስትረዳ ‹‹ ሮቤል በቃ ቆይቼ ደውልሀለው … መንገድ ላይ ያልሆነ ነገር አጋጥሞኝ ነው›› ብላ ስልኩን ዘጋችው፡፡
ከዛም እርምጃዋን ሳታቋርጥ ወደ ዔሊያስ ዞር ብላ ተመለከተች …በተገተረበት ቆሞ እያያት ነበር ..የሆነ ውርር የሚያደርግ ስሜት ተሰማት ፡፡መንገዱን አቋርጣ ወደካፌው ታጠፈችና ከእይታው ተሰወረች፡፡
ሁኔታውን በትኩረት ሲከታተሉ የቆዩት ቢንያም እና ጓደኛው ወደ እሱ ሮጠው ከጎኑ ቆመ
‹‹በቀጣዬቹ አመታት ውስጥ ያለህ የሕይወት እቅድ ውስጥ ሴት እንደሌለችበት ደጋግመህ ነግረኸኝ ነበር? ››አለው ቢኒያም፡፡
‹‹እና ታዲያ?››
‹‹እናማ ይህቺ ሴት ማን ነች?።››
ዔሊያስ ለወንድሙ ‹‹የህይወት እቅዴ ላይ ምንም ማስተካከያ አልተደረገበትም..ያንን ካወቅክ ይበቃል።››ብሎት ወደመኪናው ጉዞውን ቀጠለ፡፡
ወንድሙም ከኋላው ተከትሎት‹‹እቅድህን ማስተካከል ትችላለህ …በቅድሚያ ግን ብድርህን ክፈል፣ ሞተርህን ሽጥና ትክክለኛ መኪና ግዛ፣ ከዛ ኑሮህን የምትጋራ ሴት መፈለግ ትችላለህ››አለው
ዔሊያስ ሕይወት ሁል ጊዜ እንደማይተነበይ ከግል ተሞክሮ ያውቃል ። ዔሊ በስድስት ዓመቱ ወደ ማደጎ ቤት ለመግባት ተገዶ ነበር፡፡ በወቅቱ ጮርቃ ልጅ ነበር እና ስለ ተፈጥሮ ወላጆቹ የሚያውቀው ብቸኛው ነገር አባቱ ሉቃስ እናቱ ደግሞ ትእግስት እንደምትባል ብቻ ነው፡፡ስለ እነሱ ያለው የመጨረሻ ትዝታ ቤተሰቡ በአንድ ላይ ሆነው እየተጓዙ እያለ አባቱ መኪናውን መቆጣጠር ተስኖት ሲጯጯሁ ነበር፡፡አንድ አመት ሙሉ በህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ተጣለ፡፡በዛን ተመሳሳይ ወቅት ቢኒያምም የአንድ አመት ህፃን ሆኖ በወላጇቹ ተጥሎ እዛ ማደጎ ቤት ከእሱ ጋር ነበር፣ እንደእድል ሆኖ አሳዳጊዎቻቸው ለሁለቱም ልባቸው ራራና አንድ ላይ ወደቤታቸው ወስደው እንደገዛ ልጇቻቸው ተንከባክበው አሳደጓቸው..እነሱም እርስ በርስ የሚዋደዱና የሚደጋገፉ ወንድማማቾች ሆነው አደጉ፡፡ አሳዳጊ ወላጆቻቸው ሁለቱንም በፍፁም ፍቅር እና …በስርዓት አስተምረው ለዚህ ደረጃ አበቁዋቸው፡፡
ቀጥታ ጓደኖቾ ይጠብቋት ወደነበረው ካፌ ገባች፡፡በጠረጴዛ ዙሪያ እየተጨዋወቱ እና እየሳቁ ካሉት ከጓደኞቿ ጋር ተቀላቀለች፡፡
‹‹ደህና ናችሁ ፣ ውድ ጓደኞቼ››
እንዴት ነሽ ንግስቲቷ›› ሜሮን ነች ቀድማ ለሰላምታዋ መልስ የሰጠቻት፡፡ከዛ ያሬድና ሌንሳ ተከተሉ፡፡እነዚህ ሶስቱ የልጅነት የትምህርት ቤት ጓደኞቾ ናቸው፡፡ራሄል ልጅ ሆና ፈጣን እና ጎበዝ ተማሪ ነበረች እና በዚህ ምክንያት ሁለት ክፍል በመዝለሏ ትምህርት ቤት ከገባችባቸው ልጆች ትንሿ ነበረች። አንድ ቀን በክፍሏ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ልጃገረዶች በመጫወቻ ስፍራው ላይ ወደ ጥግ ወስደው ይሳለቁባት ጀመር። እንደአጋጣሚ ሶስቱ ጓደኛሞች በአካባቢው ሲያልፉ ሁኔታውን ተመለከቱ ..ዝም ብለው ሊያልፉ አልፈለጉም…ጣልቃ ገብተው ራሄልን በክንፋቸው ስር ከልለው ታደጓት። ከዛን በኃላ ቋሚ ጓደኞቾ ሆኑ..ይሄው እስከዛሬ በህይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ፣ የእርሷ ምስጢረኞች አማካሪዎች እና ውድ ጓደኞቿ ሆነዋል።እና ከአራት አመት በፊት ሌንሳና ያሬድ የጓደኝነት ግንኙነታቸውን ወደፍቅር ቀይረው በመጋባት መንታ ልጆችን ለመውለድ ችለዋል፡፡
ያሬድ የራሄልን የተዘበራረቀ ሸሚዞን እና የተበታተነ ወረቀቷን ተመለከተና ‹‹ደህና ነሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹አዎ..ደህና ነኝ››
‹‹ቆይ ምን ሆንሽ?››ሜሮን ተቀበለችው፡፡
‹‹ከመኪናዬ ወርጄ ወደእዚህ ስመጣ ..፣ከአንድ ጓረምሳ ዶ/ር ጋር ተጋጨው ››
‹‹ምን…!ከጎረምሳ…?ወይስ ከዶክተር?››ሌንሳ ጠየቀቻት፡፡
‹‹ጓረምሳ የሆነ ዶ/ር ..ምነው ግልፅ አይለም እንዴ?››
‹‹እኔ ያልገባኝ..ጎረምሳ መሆኑን በእይታ አወቅሽ እንበል..ዶክተር መሆኑንስ?››ሜሮን ጠየቀች፡፡
‹‹ባክሽ የማውቀው ሰው ነው …የእህቴ የፀጋ ዶክተር ነው፡፡››ሸሚዙ እንደተከፈተ፣ እና ፀጉሩ በግንባሩ ላይ ተደፍቶ እንደነበረ ላለማሰብ ታገለች።
ሁሉም በአንድ ላይ አስካኩባት፡፡
‹‹ስሙ ማን ነበር?››ሌንሳ በማሾፍ ጠየቀች፡፡
ራሄል ግን ጥያቄዋን በቁም ነገር ወስዳ‹‹ዓሊ››ስትል መለሰች፡፡
‹‹ኤሊ ማለት?››ያሬድ በገረሜታ ጠየቀ፡፡
‹‹ማለቴ ኤልያስ….ዶ/ር ኤልያስ››
ሌላ የህብረት ሳቅ ተከተለ፡፡
‹‹ተመልከቷት ነገሩ ስር የሰደደ ይመስላል ። የዔሊን ስም ሲነሳ መልኳ በደቂቃ ተለወጠ›› ሜሮን ጮኸች።
‹‹እንዴት ነው ግን…?››ለሊሴ ጠየቀቻት፡፡
‹‹ እሱ ቆንጆ ነው ማለት ይቻላል...›› ቡድኑን ዞር ብላ ተመለከተች እና በራሷ ሳቀች።‹‹እንደ ያሬድ ወንዳ ወንድ ነው›› ስትል አከለችበት፡፡
ሁሉም ሳቃቸውን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡

❤56👍3