አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
480 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

ከወ.ሮ ላምሮት ጋር የተደረገው ስብሰባ በጣም ረጅም ጊዜ ወስዶ ነበር እና  ውጤቱ በጣም ጥቂት የሚባል ነበር፡፡

ራሄል  በጣም የደክማት ቢሆንም  ቢሮዋ ገብታም ስራዋን ቀጥላለች፡፡

‹‹ጥሩ ነው…በብሮሹሮች ላይ ስህተቶችን አግኝቻለሁ.››

ሎዛ  ወረቀቶቹን በመካከላቸው ባለው የእንጨት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠች። ራሄል በተቀመጠችበት የቆዳ  ሶፋ ላይ ወደ ኋላ ተደግፋ ከፊቷ ያለውን  ብሮሹር  ቃኘች። ‹‹ይህ ሰማያዊ ቀለም በጣም ደማቅ ነው….እና ይህ ቢጫው ደግሞ እንዲጠናከር እፈልጋለሁ። የቀረውን ደግሞ ደውዬ አሳውቃቸዋለሁ››

‹‹ለምን ያን እኔ ራሴ  እንድከታተል አትፈቅጂልኝም?›› አለች ሎዛ

‹‹አመሰግናለሁ ሎዛ.. ግን ማየት የምፈልገውን በትክክል አውቃለሁ።››

ሎዛ  ራሷን በይሁንታ ነቀነቀች፣  ራሄል ግን  በእሷ ውሳኔ ደስተኛ እንዳልነበረች አይታለች።

‹‹ለአሁን እንዳደርግ የምትፈልጊው ሌላ ነገር አለ?››ሎዛ ጠየቀች።

‹‹ አይ ምንም የለም… በቃ እጅሽ ላይ ያሉ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጊ።››የሚል ትእዛዝ ሰጠቻት፡፡

ራሄል ወረቀቶቹን በጠረጴዛዋ ላይ አስቀመጠች እና ሎዛ ቢሮዋን ስትለቅ ወደ ሮቤል ዞረች።

‹‹ሮቤል አንተ የሆነ ነገር አንድታደርግልኝ እፈልጋለው››አለችው፡፡

ሮቤል ጎንበስ ብሎ ከቆዳው ቦርሳ ውስጥ አንድ ወረቀት አወጣና‹‹ጥቂት ስልክ ደዋውዬ ከምንጩ  ያገኘሁት  መረጃ ነው።›› በማለት ተጨማሪ ወረቀቶችን አቀበላት።

‹‹ከስብሰባው ጥቂት ቀደም ብሎ ከድርጅቱ ኃላፊ ጋር በግል ተወያይቼ ነበር።››

‹‹ጉልበቱን ከየት አመጣው?››ስትል አሞገሰችው፡፡ ራሄል ከወ.ሮ ላምሮት  ጋር ከተገናኘ በኋላ ስላከናወናቸው ውይይቶችና ስለተለዋወጦቸው ቃላቶች በማሰብ ደክሞት  ነበር።‹‹ይህ በጣም ጥሩ ነው፣ቀጣዩ እርምጃችን የበጎ አድራጎት ልገሳ ሁኔታቸውን ማረጋገጥ እና ከቻልን በእነሱ ላይ አንዳንድ ጥልቅ የጀርባ ስራዎችን መስራት ነው።››

‹‹እንደተፈጸመ ቁጠሪው.››ሲል ሮቤል ፈገግ አለ። በዚህ ጊዜ ስልኳ ጠራ…እናቷ መስመር ላይ ነበረች።‹‹እንደገና አመሰግናለሁ ሮቤል።በቅርብ ጊዜ ፋውንዴሽኑን እንደተቀላቀለ ሰው ምርጥ ስራ ሰርተሃል.›› ብላ ስልኩን አነሳች፡፡

ራሱን ነቀነቀና ዞር ብሎ ከቢሮ ወጣ።ራሄል ከኋላው ባለው ትልቅ የቆዳ ወንበር ላይ ለመቀመጥ በጠረጴዟ ዙሪያ  ዞራ ሄደች።

‹‹ጤና ይስጥልኝ እናቴ››

‹‹ደህና ነኝ የእኔ ልጅ››

‹‹ እየሮጥኩ ያለሁት ባንቺ  ጉዳይ እንደሆነ ከግምት ውስጥ በማስገባት ልትደሰቺ ይገባሻል።››ስትል ራሄል ወንበሯ ላይ በመቀመጥ ተሸከረከረች፡፡

‹‹ውዴ፣ ሁሌም በአንቺ ደስተኛ ነኝ ፡ ታውቃያለሽ?››

‹‹እማዬ አውቃለው…የቸኮሌት ኬኩ በጣም ጥሩ ነበር. ሮቤል እና ሎዛ  አመስግኚልኝ ብለዋል.››

‹‹እንደተካፈላችሁት  በማወቄ ደስተኛ ነኝ። ግን አንቺን አንድ ውለታ ልጠይቅሽ ነው። አያቶችሽ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ አድዋ ሄደን እንደንጠይቃቸው ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን  ፀጋን ይዘን ለመሄድ መድፈር አልቻልንም ።እስክንመለሰ እሷን  ለመጠበቅ ፈቃደኛ ነሸ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡ራሄል  በድንጋጤ ስልኩ ሊያመልጣት ነበር..በመከራ ነው አጥብቃ የያዘችው።

‹‹ፈቃደኛ? ምናልባት…ቆይ እስኪ ፕሮግራሜን ልመልከት››አለችና የቀጠሮ ደብተሯን ለማየት ማስታወሻ ደብተሯን ከፈተች።  በዛን ወቅት የማይሰረዝ ፕሮግራም ኖሯት ያንን እንደምክንያት ማቅረብ እንድትችል በውስጧ ፀለየች፡፡

የወሩ የመጨረሻ ቅዳሜና እሁድ…..ቢንጎ …የበጎ አድራጎት ፈንድ የመሰብሰብ ፕሮግራም አለባት። ‹‹ይቅርታ እማዬ ባልሻቸው ቀናት መሰረዝ የማልችላቸው ፕሮግራሞች አሉብኝ…በነዛ ቀናት  አመታዊ የፋውንዴሽኑ ፈንድ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አለብኝ ።››

‹‹ኦህ ውዴ፣ አያትሽ ቤት የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ብቻ ነው።›› በለሆሳስ ተነፈሰች። እና ፀጋን  ከማንም ጋር ልተዋት እችላለው? ….እንደምታውቂው እስካሁን በጣም ደካማ ነች።››

‹‹ለምን ስለችግርሽ ከዶክተር ዔሊያስ  ጋር አታወሪበትም››ስትል ሀሳብ አቀረበች።

‹‹በእርግጥ ትክክል ብለሻል .. እሱ የግል ነርሲንግ ኤጀንሲን ወይም ተመሳሳይ ነገርን ሊመክረኝ ይችላል?››

ራሄል አሰበች፤ የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማት አይገባም። ወላጆቿ ይችን ልጅ ለማሳደግ መወሰናቸው  የሷ ሀሳብ አልነበረም። እና ፀጋ ብቃት እንደሌላት እና አቅመ ቢስነት እንዲሰማት ያደረጋት የሷ ስህተት አልነበረም።

‹‹እሷን መንከባከብ ካልቻልሽ ችግር የለውም…›› እናቷ ቀጠለች‹‹እርግጠኛ ነኝ ዔሊ ፀጋን የት ልንወስደት እንደምንችል ያውቃል።››

‹‹እንደሚያውቅ  እርግጠኛ ነኝ››ስትል ራሄል ተስማማች፣ እፎይታም ተሰማት።

‹እና ስለ ዶክተር ዔሊያስ ምን አሰብሽ? ››እናትዬው እንደቀልድ ሌላ ርዕስ ከፈተች፡፡

‹‹እሱ በጣም ደስ የሚል ሰው ነው…. ከፀጋ ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት አለው ››

ከእሷ ጋር ሊጣመር የሚችልበት ምንም እድል እንደማይኖር  ለእናቷ ግልፅ ለማድረግ ጊዜው አሁን እንደሆነ ተሰማት ‹‹ግን እሱ የእኔ ምርጫ አይደለም ።››ስትል መለሰችላት፡፡

‹‹ምን አልሽ?››

‹‹እማዬ… እባክሽ አሁን ለማንም  ቢሆን ጊዜ የለኝም… ታውቂያለሽ››

‹‹ባለፉት ስምንት አመታት ውስጥ ለማንም ጊዜ አልነበራሽም። ብዙ ማህበራዊ ህይወት የለሽም። የምታደርጊው አንድ ነገር ቢኖር ስራ መስራት ብቻ ነው።››

ራሄል ወንበሯን ትንሽ እያወዛወዘች ፊቷን ከሰከሰች። ‹‹ይህን ስራ እፈልገዋለሁ እናቴ…ለህይወቴ ትርጉም የሰጠኝ ስራዬ ነው››

‹‹ከጌታ ጋር ያለሽ ግንኙነትስ? ያ እንዴት አድርጎ ነው  ስራሽን  የሚጋፋው?››ወደ ማትፈልገው ሌላ  ርዕስ ከተተቻት፡፡

‹‹‹እናቴ ሆይ፣ የእኔ ስራ የተቸገሩ ህፃናትንና  አቅመ ደካሞችን መርዳት ነው። ኢየሱስ በዚህ ምድር እንድናደርግ የሚፈልገውን ተግባር ነው እያደረኩ ያለሁት።››ራሄል እናቷን የሚያስደስት ትክክለኛ ቃላቶችን ታውቃለች እና ያለ እፍረት ተጠቀመችባቸው፡፡

‹‹ያለ እምነት ሥራ የሞተ ነው ውዴ።›› እናቷ ወደ እምነቷ ሲመጣ…ጥልቅ የማሰብ ችሎታ ስላላት  ሁሉንም የልጇን የማጭበርበሪያ ስልቶች ታውቃለች።

ራሄል በመጨረሻ ‹‹እኔ ማድረግ የምችለው  ይህን ብቻ   ነው እናቴ››አለች. ቀጠለችናም ‹‹ለወንድ ጓደኛ ጊዜ የለኝም እና ለአንድም ሰው ፍላጎት የለኝም። ስለዚህ እባካችሁ ከአሁን በኋላ የማልፈልገውን አይነት አስጨናቂ እራት ለማዘጋጀት አትሞክሩ።››ስትል ንግግሯን በመኮሳተር ደመደመች፡፡

የእናቷ ዝምታ እጅ የመስጠት ምልክት እንደሆነ ተስፋ አድርጋ ነበር።‹‹ደስተኛ ነኝ እማማ›› እናቷ ብርሃኑን እንድታይ ለማድረግ ቆርጣ ገፋችበት። ‹‹ዓላማ እና ትርጉም ያለው  ንቁ ህይወት ነው እየኖርኩ ያለሁት ። ጓደኞች አሉኝ እናም በማህበረሰብ ውስጥ  አስፈላጊ የሚባል  ስራ አለኝ። እና አንቺ እና አባዬ እና ፀጋም  አለችሁልኝ። ተጨማሪ አያስፈልገኝም።››

‹‹እሺ፣ ይቅርታ፣ አንቺና ዔሊ ትመጣጠናላችሁ ብዬ ስላሰብኩ ነው። እሱ ጥሩ እና ደግ ሰው ነው..ለዛ ነው ከእሱ መዛመድ የፈለኩት ።››

ራሄል ፊቱ ላይ ስለተመለከተችው ፈገግታ አሰበች‹ደህና፣ ለአንድ ሌላ ሴት ግሩም ባል እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ግን ያቺ ሴት እኔ አይደለሁም፣ እማማ።››

ወ.ሮ ትርሀስ ቃተቱ። ‹‹ካስከፋሁሽ ይቅርታ።››

‹‹አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጠርሺብኝ እንጂ አላስከፋሺኝም።››
61👍6