#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
ፀጋ አባቷ እቅፍ ላይ እንዳለች ፈገግ በማለት የራሄልን ትኩረት ለመያዝ ሞከረች፣ በዚህ ጊዜ እናቷ ጣልቃ ገብታ መናገር ጀመሩ ፡፡
‹‹ራሄል፣ ከዶክተር ኤሊያስን ጋር እንድትተዋወቂ እፈልጋለሁ። እሱ የፀጋ ሐኪም ነው…ዔሊ ይህች ልጃችን ራሄል ናት።››
ዶ/ሩ በስሱ ፈገግ በማለት ‹‹ሰለአንቺ ብዙ ሰምቼያለው ..አንድ ቀን እንደምንገናኝ አምን ነበር›› በማለት እጁን ወደ እሷ ዘረጋ
ጨዋነት ያልጎደለው ፈገግታ ፈገግ አለችለት እና የዘረጋውን እጅን ጨበጠች፡፡ወላጆቿ ከእሱ ጋር አማች ለመሆን እያሴሩ እና እሱንም እያደፋፈሩት እንደሆነ ታውቃለች…ቢሆንም የሱ ጥፋት አልነበረም።
‹‹የሞተር ሳይክሉ ሰው ነህ አይደል?››
‹‹አዎ… ነኝ›› አላት፡፡
እጁ ሞቃታማ፣ ጣቶቹ ረዣዥም ነበሩ፣ እና ሲነካት ለረጅም ጊዜ በእንቅልፍ የመወሰድ አይነት የግንዛቤ ብልጭታ በአእምሯዋ ተንፀባረቆ ነበር….ስሜቱን አልወደደችውም። ‹‹በዛ ፍጥነት ስታበር ገርሞኝ ነበር››አለችው፣ትንፋሽ ወሰደችና ‹‹ደግሞ ዶክተር መሆን እና …..››
‹‹እና ምን?›› ከአንደበቷ ቀልቦ ጠየቃት።
‹‹ከተሸከምከው ሃላፊነት አንፃር ሞተር ማሽከርከር….አንድ ነገር ቢደርስብህስ?››
‹‹ለጊዜው አቅሜ የሚፈቅደው ርካሹ እና ፈጣኑ መጓጓዣ ሞተር ነው. እና ደግሞ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አደርጋለሁ.››ሲል መለሰላት፡፡
ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ‹‹ሁሉም የሚያቀነቅናቸው ታዋቂ የመጨረሻ ቃላቶች ናቸው…ጥንቃቄ አደርጋለው..››አለች በንዴት፡፡
በመጠኑ ደፍረስ ባሉት አይኖቹ በትኩረት ተመለከታት…ከመተዋወቃቸው እየሰጠችው ያለው ጠንከር ያለ አስተያየት ግራ አጋብቷታል…
እናትዬው ፀጋን ከአቶ ቸርነት እቅፍ ወሰድና፡፡‹‹በሉ ወደምግብ ጠረጴዛው እንሄድ….ምሳ ዝግጁ ነው››ሲሉ አወጁ፡፡
ሁሉም ወደምግብ ጠረጴዛው ተከታትለው ሄዱ፡፡ራሄል፣ የተለመደውን ቦታዋ ላይ ተቀምጣለች፣ ዔሊያስ ከእሷ ፊት ለፊት ተቀምጠ።››
አቶ ቸርነት በቀኝ እጇቸው የሴት ልጇቸውን እጅ ግራ እጇቸው ደግሞ በዔሊያስ ትከሻ ላይ ዘረጉና። ‹‹ብዙውን ጊዜ ከምግብ በፊት እንፀልያለን››ሲሉ ለዔሊያስ ገለጹለት።
‹‹እኔ ደስተኛ ነኝ. በቤተሰቦቼ ቤትም ስርዓቱ እንዲሁ ነው.››ሲል መለሰ፡፡አባቷ እጇን ጨምቀው ነበር፣መጸለይ ሲጀምሩ አንገቷን ዝቅ አደረገች።አባቷ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገሩ ማዳመጥ ብትጀምርም ከጸሎቱ ጋር በልቧ መቀላቀል አልቻለችም። እሷ በሀይማኖት ስርዓት ውስጥ ተወልዳ ያደገች ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ከመስመር ወጥታለች። አምላክ በህይወቷ ጣልቃ እንዲገባ አትፈልግም ወይም ደግሞም እሱ ራሱም ለእሷ ደንታ እንደሌለው ታምናለች።ስለዚህ ለምን ትጨቀጭቀዋለች፡፡ ወላጆቿ በዚህ መሳኔዋ ደስተኛ እንዳልሆኑ በደንብ ታውቃለች ቢሆንም ግን ርቀታቸውን በመጠበቃቸው ታመሰግናቸዋለች። እና ምናልባት ወደቀልቧ እንድትመለስ ዘወትር ለእሷ በድብቅ ይፀልዩላት ይሆናል፡፡
ፀሎቱ ተገባዶ በ‹‹አሜን›› እንደተዘጋ እናትዬው ‹‹በሉ እራሳችሁን አስተናግዱ ››አለቻቸው፡፡ሁሉም ፊት ለፊቱ ባለው ሳህን ላይ ፊለፊታቸው ከተደረደሩት በርካታ የምግብ ዓይነቶች የሚፈልጉትን መጠን መውሰድ ጀመሩ፡፡ተ
‹‹ከቻልክ ክትፎውን አቀብለኝ››ስትል ራሄል ወደኤልያስ እያየች አጉተመተመች፣
እናትዬው የራሄልን አስተያየት ውድቅ በማድረግ እጆቿን እያወዛወዘ ‹‹እስኪ እንደአንበሳ ስጋ ማሳደድሽን አቁሚ።››በማለት ገሰፃት፡፡ ቀጠል አደረጉና ‹‹ለሚያገባሽ ሰው አዝንለታለው።››ሲሉ አከሉበት፡፡
‹‹ደህና፣ ደስ ሚለው ነገር ፍቅረኛ የለኝም ››አለች ራሄል፡፡
‹‹እነዚህማ የተለመዱ ቃላቷችሽ ናቸው››
እናቷ በራሄል ንግግር ተከፍተው ‹‹አንድ ቀን ያንን በብቸኝነት የቀዘቀዘ አፓርታማሽን እርግፍ አድርገሽ ጥለሽ እንደ ዶ/ር ኤሊያስ ቤት አይነት ግቢ ወዳለው ቤት ትቀይሪ ይሆናል።››ሲሉ ምኞታቸውን ተናገሩ፡፡
እናትዬው ወደ ዶ/ሩ ዘወር አሉን‹‹ቤትህን በማስተካከል ላይ እንዳለህ ሰምቼያለው?››
‹‹በእውነቱ ወንድሜ ቢንያም ነው እየተከታተለው ያለው። እሱ አናጺ ነው። ስለ ኩሽና አሰራር አንዳንድ ውሳኔዎችን እንድወስን እየጨቀጨቀኝ ነበር, ነገር ግን ዘመናዊ ይሁን ወይም ባህላዊ ጭብጥ ይኑረው የሚለውን ለመወሰን እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም››
አቶ ቸርነት‹‹ራሄልን ይዘሀት ብትሄድ ልትረዳህ ትችል ይሆናል››የሚል ሀሳብ አቀረቡለት። ዔሊያስ የራሔልን መኮሳተር ችላ በማለት እንደ ተወደደ ልጅ ፊቱ እያበራ ነው።
አንቷም ‹‹አዎ የእኔ ልጅ …በኢንቴርዬር ዲዛይን ላይ በጣም ጎበዝ ነች።››ሲሉ የአባትዬውን ሀሳብ ደገፉ፡፡
ራሄል ስለእሷ የተሰጠ ያለው አስተያየት ከየት እንደመጣ አታውቅም። ወላጆቿ አፓርታማዋን በሚጎበኙበት ጊዜ በዕቃዎቾ፤በምንጣፎች እና በመኝታ ቤቷ ቀለም ..ብዙ ብዙ ኔጌቲቨ የሆነ አስተያየት ሲሰጧት እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ እንደውም እናቷ ‹ጥቂት እንኳን ለስሜቷ ሳይጨነቁ ቤቷን መኖሪያ ቤት ሳይሆን ሙዚየም እንዳስመሰለችው ነግረዋት ነበር፡፡
‹‹የምፈልገውን በትክክል አውቃለሁ። ትልቁ ችግሬ ግን ውሳኔዎችን ለመወሰን ጊዜ ማግኘት አለመቻሌ ነው ›› ሲል ኤሊያስ መለሰ።
ራሄል የሆነውን ነገር የተረዳች መስላ‹‹እንድትጨርሰው የምትገፋፋህ ሴት የለችም?››ስትል ጠየቀችው፡፡
አባቷ ራሄልን በግንባራቸው ገፆት ፡፡
ዶ/ሩ ‹‹ለጊዜው አቋሜ ልክ እንደአንቺው ነው….ለሴት ዝግጁ አይደለሁም››ሲል መለሰ።
ራሄል ውይይቱ ወደ መሃል ከተማ የትራፊክ ፍሰት፣ የኑሮው ውድነትና ፣ እና የፖለቲካ ውዥንብር.እና የሰላም እጦት የመሳሰሉት ጉዳዬች ላይ ሲያተኩር እፎይ አለች፡፡
በመሀል ወደ ዶ/ሩ አትኩራ እየተመለከተች ‹‹በቅርቡ የኖብል ፋውንዴሽን አመታዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አለ።በዝግጅቱ ላይ መገኘትህን ማረጋገጥ አለብህ››አለችው፡፡
‹አረ ችግር የለውም..አታስቢ እገኛለው››ሲል ቃል ገባላት፡፡
እናትዬው‹‹ቀኑ ደረሰ እንዴ..?እንግዲህ በስራ ጫና ድራሽሽ ሊጠፋ ነው››ሲሉ ስጋታቸውን ገለፁላት፡፡
ራሄል ‹‹እማዬ ደግሞ ….እኔ ብቻዬን የማደርገውን አስመሰልሺው ። አብዛኛውን ስራ የሚሰሩልኝ ትላልቅ ሰራተኞች አሉኝ እኮ››
‹‹ነገር ግን ለሰራተኞችሽ በቂ ውክልና አትሰጪም።ቅድስትን ለመተካት እነዚያን ሁለቱን ረዳቶች መቅጠርሽን ስሰማ ብዙ የስራ ጫናሽን ያቃልሉልሻል ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን አሁን እንደማየው ከሆነ የበለጠ ስራ ነው ያበዛብሽ፡፡››
‹‹ሰራተኞቹ በጣም አዲስ ናቸው ። ፋይሎቹን ብቻ ሰጥቻቸው ሁሉንም ነገር በራሳቸው እንዲቋቋሙት መጠበቅ አልችልም።››
‹‹ዬኒቨርሲቲ ዲግሪ ያላቸውና …በደንብ የሰለጠኑ ናቸው እኮ።››
‹‹አዎ ትክክል ነሽ..ግን የፋውንዴሽኑን ስራ በተመለከተ ትንሽ ተጨማሪ ልምድ ያስፈልጋቸዋል፣ሁሉም ሰው ወደሆነ አዲስ ስራ ሲሄድ ለተወሰነ ጊዜ ከአሰራሩ ጋር እስኪለማመድ አዲስ ሆኖ መገኘት አይቀርም››ለእናቷ ሌላ የማስጠንቀቂያ እይታ ሰጠቻት። ይህን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በማያውቁት ሰው ፊት መወያየታቸውን አልወደደችውም ።
‹‹ውዴ እወድሻለሁ፣ ግን ደግሞ አውቅሻለሁ።››ሲሉ እናትዬው በአቋማቸው መፅናታቸውን አረጋገጡላት፡፡
የራሄልን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት ‹‹እና ሁሉንም ነገር መቆጣጠር እንደምትችይ ማሰብ ማቆም አለብሽ። አንዳንድ ነገሮችን ለእግዚአብሔርን መልቀቅ አለብሽ።››ሲሉ ንግግራቸውን ደመደሙ፡፡

❤53👍5