አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
579 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
‹‹ጋሽ ፍሰሀ..አንተ ነህ…?››

‹‹አዎ አለም…እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?››አውሬው ካስደነገጠው በላይ የእሷ በዚህ ሰዓት እዚህ አካባቢ መገኘት አስደነገጠው፡፡

‹‹እንዴ ስልክ እያወራን ነበር እኮ የተቆረጠው….መኪናህ እንደተገለበጠች እርግጠኛ ስለነበርኩ ወዲያውኑ ወደእዚህ የመጣሁት…መኪናህን ቀድሜ ባገኛትም ውስጡ የለህም..ግን የሚንጠባጠበውን ደም እየተከተልኩ ደረስኩብህ››

‹‹ስሩ ደርሳ ደገፈችው››

‹‹አብሮሽ ማን አለ?››

‹‹አረ ማንም የለ….መንገድ ላይ ሆኜ ለጁኒዬር ደውዬለታለው..ይሄኔ እየመጡ ይሆናል፡››

‹‹ይገርማል..የሆነ ነገር ቢያጋጥምሽስ?››

‹‹ሀሳቤ ሁሉ ያንተን ደህንነት ማረጋገጥ ላይ ስለነበር እሱን አላሳብኩትም ነበር…እውነቱን ንገሪኝ ካልከኝ ግን አሁን በፍራቻ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡››

‹‹በጣም ነው ያስገረምሺኝ..አይዞሽ አሁን አምስት ደቂቃ ነው ደርሰናል….እንደውም እዛ መብራት ጭልጭል የሚልበት ቦታ ይታይሻል …?እዛ ነው ጎጆው…በአቅራቢያው የእኔ ሰራተኞች ቤትም አለ…››

‹‹ በአንድ እጇ ደግፋው በሌላ እጇ ደግሞ የስልኳን ባትሪ ከፊት ለፊት እያበራች ወደፊት በዝግታ መራመዳቸውን ቀጠሉ፡፡
አቶ ፍሰሀ ከአውሬው ጋር የነበረው መፋጠጥ አሁንም ከምናብ ሊደበዝዝ አልቻለም… ልቡ ለምን እንዲህ ከመጠን በላይ መታ? ጉዳዩ ምን ነበር? የዱር አውሬው በጣም አስፈርቶት ነው? አይደለም፡፡ እሱ ስለእነሱ አላሰበም። በህይወቱ የበለጠ አስፈሪ ነገሮችን አሳልፎ ያውቃል። ወዲያው ከኃላቸው እየተንሾካሾኩ የሚመጣ የእግር ኮቴ ሰሙ…መንገዱን ለቀቁና ጢሻውን ተከልለው ቆሙ..ሲጠጎቸው ማንነታቸውን በድምፅ ለዩ…‹‹ገመዶ››
ባትሪውን ሲያበራባት ፈጽሞ እዚህ አገኘዋለሁ ብሎ ያላሰበውን አቶ ፍሰሀን በአለም ተደግፋፎ ልክ እንደተወዳጅ ልጁ ስሩ ተሸጉጣ ሲያይ አይኑን ማመን አልቻለም፡፡

ሁሉም ተንደርድረው ከበቧቸው‹‹ጋሼ ምን እየተካሄደ ነው?››

‹‹አይዞችሁ አትደንግጡ… ተርፌለው››

‹‹ተርፌለው ማለት?››ኩማንደሩ በመገረም ጠየቀ፡፡

‹‹የመኪና አደጋ እንደደረሰብኝ ሰምታችሁ አይደለም እንዴ የመጣችሁት?››

‹‹አረ በፈጣሪ..ተርፍክ ታዲያ…?እኛ አልሰማንም..እሷን ከከተማ ስትወጣ አይተን ተከትለናት ነው የመጣናው…ከጠላቶቻችን ጋር ልትገናኝ መስሎን ነበር››

‹‹አይ እሷ እኔን ለማትረፍ ነው የመጣችው››

‹‹እንዴት ከእኛ ቀድማ ልትሰማ ቻለች?..ነው ወይስ በአደጋው ላይ የእሷ እጅ አለበት?››

‹‹እሱን ጎጆው ጋር  ደርሰን ትንሽ ካረፈ በኃላ ብትጠይቀው አይሻልም?››አለችው አለም በንዴት፡፡

‹‹ለምን ወደጎጆ እንሄዳለን? መኪናችንን እኮ በቅርብ ርቀት ላይ ነው ያቆምናት..እዚሁ ጠብቁኝና ይዣት ልምጣ..ቀጥታ ወደከተማ ሄደህ ህክምና ማግኘት አለብህ››

‹‹አይ ደህና ነኝ..አሁን ማረፍ ነው የምፈለገው..ወደጎጆ ውሰዱኝ››

‹‹ተው  እንጂ  ፍሰሀ  ..ሀኪም  ሊያይህ  ይገባል››ዳኛው  ጣልቃ  ገብተው  ለኩማንደሩ ድጋፋቸውን ሰጡ፡፡

‹‹የበለጠ  እያደከማችሁኝ  መሆኑን  ልብ  አላላችሁም  እንዴ..?ወደጎጆ  መሄድ  ነው የምፈልገው›› በማለት የማይቀየር አቋማቸውን አሰሙ፡፡

‹‹ይቅርታ ጋሼ..አንተ ካልክ እሺ ወደጎጆ እንወስድሀለን….እነ ጁኒዬርም አሁን ደውለውልኝ ነበር …መገንጠያው ጋር ደርሰዋል….ከደቂቃዎች በኃላ ይደርሳሉ..››አለና ሄዶ በሌላ ጎኑ አቶ ፍሰሀን ደገፈ….ከ5 ደቂቃ በኃላ ጎጆዋ ደረሱ፡፡ፋኖስ አበሩ፣ መኝታው ተስተካክሎ እንዲተኛ ተደረገና በቅርብ ርቀት ያሉ ሌላ የሳር ቤት ውስጥ ወደሚኖሩት የእነሱ ሰራተኞች ተቀስቅሰው መጡ..እሳት እንዲቃጣጠል ተደረገ…ጁኒዬርና ሳራ የመጀመሪያ ለእረዳታ መስጫ የሚያለግሉ ቁሳቁሶች ይዘው እያለከለኩ ደረሱ…ለተወሰነ ጊዜ ለቅሶና ግርግር በጠባቧ ጎጆ ነገሰ..ከዛ ቀስ በቀስ ወደመረጋጋት ቢመጣም በሰው ብዛት በታፈነችው ጎጆ ውጥረትና ጭንቀት ነግሶ ነበር፡፡

‹‹ቆይ እኔ ያልገባኝ…ምንድነው የሚያስጠብቀን..?ለምንድነው ወደከተማ ይዘነው ሔደን ሀኪማ የማያየው?››ሳራ ነች ግራ በመጋባት ተመሳሳይ አይነት ጥያቄ ለሶስተኛ ጊዜ ያነሳችው፡፡

‹‹ጋሼ አልፈልግም ስላለ እኮ ነው…ጋሼ አሁን ትንሽ አርፈሀል፣ብንሄድ ምን ይመስልሀል?››ኩማንደር ነው ተናጋሪው፡፡

‹‹አይ ዛሬ ማንም ከዚህ አይሄድም…አሁን ሰዎቹን ሸኞቸውና የምንነጋገረው ነገር አለ››ሲል ሁሉም በቀጣይ ምን ሊፈጠር ነው በሚል እርስ በርስ ተያዩ፡፡

ጁኒዬር ከጎረቤት ጎጆ የመጡትን ባልና ሚስቶች ከነልጆቻቸው አመስግኖ ወደቤታቸው እንዲሄዱ ካደረገ በኃላ የጎጆዋ ቤት ተዘጋ፡፡አሁን ስድስት ሰዎች ፊት ለፊት ተፋጠጡ …ሁለቱ ሴቶች እና አዛውንቱ ዳኛ አቶ ፍሰሀ ጎን የተቀመጠችውን አለምን በከፍተኛ ጥላቻን መጠየፍ ነበር የሚመለከቷት፡፡

አቶ ፍሰሀ ከትራሱ ቀና አደረገና አስተካክሎ በመደገፍ መናገር ጀመረ‹‹ዛሬ እየሆነ ያለው ሁሉ ነገር ተአምር ነው…እኔ እቅዴ እንደማንኛውም ቀን ስራ ውዬ ወደቤቴ መግባት ነበር….ነገር ግን የሰሞኑን ውጣ ውረድ እያሰላሰልኩ ሳላስበው ከከተማ ወጣሁና እራሴን እዚህ ሶሌ ደን አካባቢ አገኘሁት..እንዴት እዚህ ልደርስ ቻልኩ? ብዬ እየተገረምኩ ሳለ ያልጠበቅኳት አለም ደወለችልኝ..ከእሷ ጋር እያወራው ሳለ ድንገት ሳላስበው አውሬ ገባብኝና እሱን አድናለው ስል መኪናዬ መንገድ ስታ ተገለበጥኩ…እንደአደጋው መሞት ነበረብኝ..ግን ከተወሰነ ጭረት በስተቀር ምንም አልሆንኩም…እግዜር አሳይቶ ከሞት ደጃፍ መለሰኝ..ከመኪናው ወጥቼ በጫካው እያሳበርኩ ወደእዚህ እየመጣው ሳለ ከጅብ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጥኩ…እሱንም ወደሰማይ ተኩሼ አስበረገግኩትና ሁለተኛውን ፈተና አለፍኩ..ከዛ ወዲያው አለምን ከፊት ለፊቴ አገኘኃት..ወዲያው እነ ገመዶና መጡ…ጎጆው እንደደረስን ደግሞ ልጄና ባለቤቴ መጡ …እኔ ለማናችሁም አደጋ ደረሰብኝ ብዬ አልደወልኩም..በአደጋው ጊዜ ስልኬ ወደየት እንደጠፋም አላውቅም..ግን ሁላችሁም እዚህ ተገኝታችኃላ..ሁላችንን እዚህ ያለነው ለምክንያት ነው፡፡ከአለም ጋር የጀመርነው ድብብቆሽ እዚህ ጋ ማብቃት መቻል አለበት፡፡

‹‹አዎ ማብቃት አለበት …ይህቼ ሴት ከዚህ በፊት ንብረቴ እንዲቃጠል አደረገች… ዛሬ ባለቤቴን ገድላብኝ ነበር….››ሳራ ተንዘረዘረች…ዳኛውና ስርጉት አይናቸውን በማጉረጥረጥ እና በመገላመጥ ለሳራ ያላቸውን እገዛ አሳዩ ፡፡

‹‹ሳራ ተይ ..ዛሬ የምንበሳጭበትና ራሳችንን ሀጥያት ለመሸፈን ሌላ ስው በሀሰት የምንወቅስበት ቀን አይደለም..እኔ አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሁለት ሞት ነው የዳንኩት…ይሄ ያለምክንያት አይደለም..ይህቺን ልጅ ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በድለናታል…ሁላችንም ለእሷ መናዘዝ መቻል አለብን..እውነቱን ልንነግራት ይገባል..ከዛ አመዛዝና ከፈለገች ትበቀለን… ከፈለገች ደግሞ ወደፍትህ አደባባይ ወስዳ ታሰቅለን፡፡

የአቶ ፍሰሀን ንግግር የሰሙት ዳኛው ጫንቃቸውን አላባቸው፡፡ይሄ ሰውዬ በተገበጠበት ወቅት ጭንቅላቱን ተመቶ ማሰቢያው ላልቶ ይሆን እንዴ?››ሲል አሰበና አይኑን ገመዶና ጁኒዬር ላይ አንከራተተ…የሆነ ነገር ብለው የጀመረውን ቅዠት የመሰል ድርጊት እንዲያስቆሙት ነው ፍላጎቱ.
50👍4