አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
578 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////
ዶ/ር ኤልያስ ዛሬ ምን አልባትም በህይወቱ ፍፁም የሆነ ደስታ የተሰደሰተበት ቀን ስለሆነ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቷት ጥንቅቅ ብሎ ባለቀ ውብ ቤቱ ውስጥ ከክፍል ክፍል እየተመላለሰ  እንደህፃን እየቧረቀ ነው፡፡ስልኩን አነሳና ደወለ…፡፡ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡

‹‹ውድ ባለቤቴ እንዴት አለሽልኝ››

‹‹አንተ ያንን ቃል መጠቀም የምትችለው እኮ ሰማንያ ፈርመህ ቤትህ ስታስገባኝ ነው››አለችው እየሳቀች፡፡፡

‹‹ያው በይው..ዜናውን አልሰማሽም እንዴ…..?ሽማግሌዎቼ እኮ ወላጆችሽ ልጃቸውን ሊሰጡኝ በደስታ መስማማታቸውን አሁን ነግረውኝ በደስታ እያበድኩ ነው፡፡››

‹‹ከአንተ ቀድሜ ሰማሁ…ምነው ይከለክሉኛል ብለህ አስበህ ነበር እንዴ?››

‹‹እንዴ ምን ይታወቃል…..ምን አልባት ቅድሞ እደጅ እየጠና ያለ  ብረት መዝጊያ አማች ኖሮ ሀሳባቸው ወደእሱ ቢያጋድልስ?››

‹‹እሱስ እውነትህን ነው …ለአሁኑ ግን ተርፈሀል››

‹‹እኔም መትረፍ የምፈልገው ለአሁኑ  ብቻ ነው…የማገባው አንዴ ብቻ እኮ ነው…››ተሳሳቁ፡፡

‹‹እና ይሄንን ደስታ አብረን ማክበር የለብንም ትያለሽ…?››

‹‹አንተ ..ከአሁን ወዲህ እኮ እስከሰርጌ ቀን ድረስ ልታየኝ አይገባም…››

‹‹እንደዛ ከሆነማ ሰርጉን ነገውኑ ደግስ በይኛ››

‹‹አዎ ..ያን ያህል ከቸኮልክ አድርገው››
‹‹እሺ..አስበብበታለው..እውነት ግን በጣም ላገኝሽ ፈልጌለሁ…››

እሷም ከአንደበቷ አውጥታ አትናረው እንጂ በጣም ልታገኘው ፈልጋለች፡፡‹‹ ይቻላል..የትና መቼ?፡፡››

‹‹ምሳ ልጋብዝሽ …ሰባት ሰዓት ስካይ ላይት እንገናኝ፡፡››

‹‹ሰባት ሰዓት ..አሁን እኮ አራት ተኩል ሆኖል…..ለመዘጋጃጀት በቂ ጊዜ አይኖረኝም፡፡››

‹‹አንቺ ደግሞ..እንደውም ምንም መዘገጃጀት አያስፈልግሽም… እዛ ሆስፒታል በነበርሽበት ጊዜ ያለምንም ዝግጅት ምን እንደምትመስዬ እኮ አውቃለው…ለእኔ ብለሽ ለመቆነጃጀት ከሁለት ሰዓት በላይ ማጥፋት የለብሽም…ከዛሬ ወዲህ ባልሽ ነኝ፡፡ማለቴ ለጊዜው እጮኛሽ ነኝ..ግን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡››

‹‹‹ይሁንልህ እሺ…..ግን  ቅር ካላለህ አንድነገር ልጠይቅህ ››

‹‹ምን ጠይቂኝ››

‹‹ጸጋን ይዣት ብመጣ ቅር ይልሀል?››

‹‹አረ በፍፅም   ..እንደውም በተቃራኒው ደስ ነው የሚለኝ …እሷ ከመጀመሪያው ጀምሮ የፍቅራችን ብቸኛ ምስክር ነበረች..ዛሬ መገኘት ይገባታል….ጫጉላ ቀናችን ላይ አብራን ወደመኝታ ትግባ እንዳትይ እንጂ ለዛሬው ደስ ይለኛል››

ስለጫጉላ ሲያወራ እፍረትም ሙቀትም ተሰማት‹‹አንተ ምን እያልክ ነው..?በል ቸው››ብላ ስልኩን ዘጋች፡፡

እሱም ወዲያው ወደሻወር ቤት ገባና ሰውነቱን በፍጥነት ተለቃለቀ…ከዛ ፂሙን ላጨ…ሙሉ ሱፍ ለበሰና ዝንጥ አለ…፡፡ለመውጣት ዝግጁ ሆነ…፡፡ሰዓቱን ሲያይ 5 .ከሩብ ይላል….ከራሄልና ከፀጋ ጋር ወደሚገናኝበት  ቀጠሮ ከመሄዱ በፊት ማግኘት የሚገባው አንድ ሰው አለ…ከአመት በፊት በሆስፒታል አብራው ትሰራ የነበረች የህጻናት ሀኪም ነች ትናንትና ደውላ ላገኝህ እፍልጋለው ያለችው፡፡ለዚህች ዶ/ር የስራ ባለደረባው ነበር…ያለፈውን አንድ አመት ተጨማሪ ትምህርት እድል አግኝታ ኖሩዌይ ነበር ያሳለፈችው፡፡አሁንም ለሁለት ሰምንት ረፍት እንደመጣች እና መመለሻዋ እንደደረሰ እናም ከመሄዶ በፊት አንድ እቃ ልትሰጠው እንደምትፈልግ ነግራው ነው እግረመንገዱን ሊያገኛት የወሰነው፡፡

ሀያ ሁለት ነበር ቀጠሮቸው…እሷም ቸኩላ ስነበረ ቀጥታ ወደጉዳዩ ነበር የገባችው፡፡አንድ የታጠፈ ነጭ ፖስታ አውጥታ እጁ ላይ አደረገች፡፡ግራ ገብቶትም ደንግጦም‹‹ምንድነው ሲል?››ጠየቃት፡፡

‹‹ትዝ ይልሀል ከመሄዴ በፊት አብረን የምንከታተላት አንድ ታማሚ ልጅ ነበረች…እናቷ ከአንተ ጋር ትግባባለች…እንደውም የልጅነት ጓደኛዬ ነበረች ብለሀኛል››

‹‹ኦኬ ትክክል ነሽ..ስለፀጋ ነው…ማለቴ የዛን ጊዜ ስሟ ትሁት ነበር..ስለእሷ ነው የምታወሪው››

‹‹አዎ ስለእሷ ነው…ለመሆኑ እንዴት ነች…?አሁንም በህይወት አለች?››

‹‹አዎ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ነች…ግን ፖስታው ምን እንደሆነ አልገባኝም››

‹‹ፖስታውማ እናትዬው እዛ ሆስፒታል ውስጥ ህጻኗን ጥላ ከመሄዶ በፊት ይህንን ፖስታ ለአንተ እንድሰጥ አደራ ብላ ሰጥታኝ ..ነበር….እርግጥ በወቅቱ ልጇን ጥላ እንደምትሄድ አልገመትኩም እና እሺ ብዬ ተቀበልኮት….ግን በዛው ሰሞን አንተም ለሆነ ስራ ወደክፍለሀገር ወጥተህ ነበር..እኔም  ውጭ ለመሄድ በጣም እየተዋከብኩ ስለነበረ  እቤቴ ወስጄ እንደቀልድ እንዳስቀመጥኩት እረሳሁት እና ሳልሰጥህ ሄድኩ ..በቀደም ነው የድሮ ወረቀቶቼን ሳስተካክል ድንገት አገኘሁት..አድራሻውን ሳነብ ትዝ አለኝ….መጀመሪያ አፍሬ እንደተረሳ ልተወው ነበር›..በኃላ ሳስበው ግን ምን አልባት በጣም አስፈላጊ ነገር ቢሆንስ ብዬ…አይኔን በጨው አጥቤ አግኝቼ ልሰጥህ ወሰንኩ….ይቅርታ እሺ››

‹‹አረ ችግር ለውም…ያው ልጄን አደራ..ተከታተላት ምናምን የሚል መልዕክት ነው የሚሆነው….ያንን ደግሞ እሷ ባትለኝም አደርገዋለው››በማለት ፖስታውን ኪሱ ውስጥ ከተተና  ከእሷ ተሰናብቶ  መኪናው ወደ እስካይ ላይት አዞረ፡፡

ከቀጠሯቸው 10 ደቂቃ ቀድሞ ነበር የደረሰው፡፡ ወንበር ይዞ በጉጉት ይጠብቃቸው ጀመር..፡፡ድንገት ፖስታው ትዝ አለው፡፡ አወጣና አየው…፡፡ከጀርባው  ለማከበርህ ደ/ር ኤልያስ ከፅጌረዳ ይላል፡፡
እነ ራሄል እስኪመጡ ቀዶ ሊያነበው ፈለገ…መቅደድ ከመጀመሩ በፊት ፖስታውን ጠራጴዛው ላይ አስቀምጦ  ስልኩን ከኪሱ አወጣና ተመለከተው…ራሄል ነች፡፡አነሳው፡፡

‹‹እሺ የእኔ ፍቅር››

‹‹ቀድመንህ ደርሰናል መሰለኝ››

‹‹አረ እንዴት ተደርጎ…››አለና ያለበትን ቦታ ነገራቸውና እስኪያዩት ቆሞ ጠበቃቸው…. ራሄልን ሲያያት ልቡ ትርክክ አለ….ወደፊት ተራምዶ  ፀጋን ከእቅፏ ተቀበለና..ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ…. ወደ ጠረጴዛቸው ሄደው ተቀመጡ….ምሳ ታዘዘ እና እስኪመጣ ሞቅ ያለጫወታ ጀመሩ…..ራሄል ድንገት ፊት ለፊቷ የተቀመጠ ፖስታ አየችና በመገረም አነሳችና አየችው…፡፡

‹‹ፅጌረዳ ማን ነች?››ኮስተርተር አለች፡፡

‹‹ቀናሽ እንዴ?››

‹‹በኢንተርኔት ዘመን ፖስታ በምትልክልህ ሴት እንዴት ብዬ ነው የምቀናው?››

‹‹በፖስታው አድራሻ ላይ የተጠቀሰችው ፅጌረዳ ማለት የፀጋ እናት እንደሆነችና ፖስታው ከተፃፈ ከአመት በኃላ እንዴት እንዳገኘው… በእንግሊዘኛ ነገራት››ይሄንን  ያደረገው ፀጋ ፊት ስለእናቷ በምትሰማው ቋንቋ ለማውራት ስላልደፈረ ነው፡፡

‹‹እና..አልተከፈተም እኮ››

‹‹አዎ…አሁን ስለፀጋ እኔን ብቻ ሳይሆን አንቺንም ስለሚመለከት አብረን እናነበዋለን››

‹‹እርግጠኛ ነህ?››

‹‹ አዎ እርግጠኛ ነኝ››

‹‹እና እናንብበዋ››ብላ ልትቀደው ስትዘጋጅ፡፡

‹‹አይ …ይሄንን ጊዜያችንማ ለሌላ ጉዳይ አንጠቀምበትም…››ብሎ ፖስታውን ከእጇ ተቀበለና ከጎኗ ካለው ወንበር ላይ የተቀመጠው የራሷ ቦርሳ ውስጥ ከተተው፡፡

‹‹በቃ አንቺ ጋር ይሁንና ..ሰሞኑን አንድ ላይ ሆነን እናነበዋለን፡፡››ተስማማች…ምሳ ቀረበላቸው በሉ…ከዛ ወጥተው ወደአለም ሲኒማ ጎራ አሉና ፊልም አዩ….አሪፍና ጣፋጭ ቀን አሳለፉ….
54👍3👏1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////

ከኪሊንኩ ጀርባ ያለው የዶ/ር ኤሊያስ  ቢሮ ምናልባት አለም ከዚህ በፊት ካየቻቸው ቢሮዎች ሁሉ የተዝረከረከ ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡

"ዶክተር ኤሊያስ እኔን ለማየት ስለተስማማህ አመሰግናለሁ።"

"ችግር የለም …ዛሬ ብዙም ስራ አልነበረኝም " ከቀጥታ ከጠረጴዛው አጠገብ ያለውን የእንጨት ወንበር ላይ ያሉትን መጽሔቶችን አስነሳና ጠረጴዛ ላይ በማድረግ ለአለም እንድትቀመጥበት አመቻቸላት፡፡

"አንቺን ሳይሽ ብዙም አልተገረምኩም

"አላት በቅንነት ።

"ለምን?"

"ዋና አቃቢ ህጉ ደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎችን ልትጠይቂኝ እንደምትፈልጊ ነግሮኝ ነበር።"

"ዛሬ ከከተማ ውጭ ያለ መስሎኝ ነበር."

"አይ ከቀናት በፊት ነበር ሰሞኑን ትመጣለች ቡሎ የነገረኝ ።"

"ገባኝ…ለሊት የእሳት ቃጠሎ ቦታው እንስሳቶችን ለመርዳት ስትሯሯጥ ስለነበርክ…ዛሬ እንዲህ ንቁ ሆነህ ቢሮህ አገኝሀለው ብዬ አላሰብኩም ነበር።"

በመደነቅ‹‹እንዴ እዛ እንደነበርኩ በምን አወቅሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹እኔም እንዳጋጣሚ እዛ ነበርኩ…አሁን ጊዜህን ሳልሻማብህ ቀጥታ ወደጉዳዬ ልግባ …የእናቴ የሰሎሜን ግድያን በተመለከተ መረጃዎችን እየሰበሰብኩ ነው….እባክህ አንተ በአቶ ፍሰሀ የእንስሳት እርባታ ድርጅት ውስጥ የእንስሳት ሀኪም ሆነህ እንደመስራትህ የምታውቀው ነገር ይኖር ይሆን ?" ስትል አሳዛኝ በሆነ የድምፅ ቅላፄ ጠየቀችው፡፡

"በእርግጥ እናትሽን አውቃታለው . እሷ በጣም አስደማሚ ሴት ነበረች. በእሷ ሞት ያላዘነ ሰው የለም ››

"አመሰግናለሁ፣ በዛን ወቅት በአቶ ፍሰሀ የእርባታ ድርጅት ውስጥ የእንስሳቱን ጤንነት ሚከታተሉት አባትህ እንደነበሩ ማወቅ ችያለው፡፡ "

" ልክ ነው …በዛን ወቅት አባቴ ነበር….እሱ ከሞተ በኋላ ግን ስራውን እኔ ተረክቤያለሁ." "አባትህ ስለ ሰሎሜ ግድያ ሁኔታ የሆነ ነገር ነግሮህ ይሆን?››

"በቀዶ ጥገና ቢላዋ መገደሏን በሰማ ጊዜ እንደ ሕፃን ነበር ተንሰቅስቆ ያለቀሰው››

"አባትህ እናቴ የተገደለለችበት መሳሪያ ከየት እንደመጣ አውቋል›?›

"አዎ …ያ አባቴ እንስሳቱን ለማከም የሚጠቀምበት መሳሪያ ነበር፣እናቴ ነበረች የሸለመችው የስሙ የመጀመሪያ ፊደል ተቀርፆበት ነበር ፡፡እንዴት አድርጎ ከቦርሳው እንደወደቀበት ነው ግራ የገባው፡፡››

"እንደዛ አይነት ግድ የለሽነት ከእሱ ባህሪ ጋር አይሄድም አይደል?"

"ትክክል ነሽ….አባዬ ለህክምና እቃዎቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያደርግ አይነት ሰው ነው
…በቆዳ በተለበጠ የእንጨት ሣጥን ውስጥ ነበር የሚያስቀምጣቸው…ያ ስለት ከሳጥኑ እንዴት እንደወደቀ ፈጽሞ ማወቅ አልቻለም ነበር, ››

"እናቴ በሞተችበት ቀን አንተ እዚያ ነበርክ?"

"ይህን ቀድመሽ ታውቂያለሽ ብዬ አስባለሁ። አባዬን ለመርዳት ትምህርት ከሌለኝ በስተቀር እዛ እገኝ ነበር …በዛም ቀን  አብሬው ሄጄ ነበር።››

"ገመዶ እዚያ ነበር?"

"በእርግጥ ኩማንደር እዚያም ነበረ።››

"ለሊቱን ሙሉ."

‹‹እሱን እርግጠኛ አይደለሁም…በመሀል አቋርጦ የሄደ ይመስለኛል››

"አባትህ የህክምና ቁሳቁስ የሚይዝበትን ሳጥን የሆነ ቦታ አስቀምጦ ዞር ብሎ ያውቃል?" ኤሊያስ ማሰላሰል ጀመረ … መልስ መስጠት እንደማይፈልግ ነገራት፡፡

‹‹ በዚያ ቀን በዛ አካባቢ ሌላ ማን ነበር?"ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

ለማስታወስ ሲጥር ተመለከተች‹‹‹ጁኒየር፣ ገመዶ፣ ጋሽ ፍሰሀ….እናትሽ….ስርጉት."

‹‹ ማን… ስርጉት ነበረች? ››

‹‹አዎ ነበረች …ከዛ ወደ ቤት መሄድ እንዳለባት ተናገረች እና አካባቢውን ለቃ ሄደች፡፡

‹‹ከግቢው ወጥታ ስትሄድ አይተሃታል….››

‹‹አይ መሄድ አለብኝ ብላ ስታወራ እንጂ ወጥታ ስትሄድ አላየኋትም….›› " ስለ ሊቁ ምን ማለት ይቻላል? እሱ በአካባቢው ነበር?"

‹‹እሱ ሁሌ  በሁሉም ቦታ የሚዞር..በሄድሽበት ቦታ የማታጪው አይነት ንክ ነበር ፣እውነቱን ንገረኝ ካልሺን ግን በዛን ቀን እሱን እዛ ቦታ እንዳየሁት አላስታውስም››

"እርሱን ካላየኸው በሰሎሜ ደም በተሸፈነ ልብሱ በቁጥጥ ስር ሲውል አልተገረምክም?"

‹‹በእርግጥ አልተገረምኩም…. ምን አልባት እኔ ሳላየው ጊቢ ውስጥ ሲዞዞር ከአባዬ ቦርሳ የወደቀውን ቢላዋ እንዳገኘው ገምታለው፣ ከዛ እናትሽን ገድሏታል ብዬ አስባለው.››

‹‹ነገር ግን ከዛ ሁሉ የአባትህ የህክምና መሳሪያዎች መካከል አንድ ቢላዋ ብቻ ሾልኮ መውደቁ ግራ መጋባት ውስጥ አይከትም… ?››

ዝም አላት…..፡፡

ይህ ዶ.ር የሶስቱም ተጠርጣሪዎች ጓደኛ ነው። በዛ ላይ በቋሚነት ለአቶ ፍሰሀ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው፡፡የሚያውቀው ነገር እንኳን ቢኖር በምንም አይነት ተአምር አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደማይፈቅድ አወቀች፡፡ከዚህ በላይ ጊዜዋን ማባከን ፋይዳ እንደሌለው ስላመነች ከመቀመጫዋ ተነሳችና አመስግናው ወደ ሁለተኛ ጉዳዮ አመራች፡፡
///
የእርባታ ድርጅት የእንቅስቃሴ አልባ ሆኗል ። የጽዳት ሠራተኞች ከቃጠሎ የተረፈውን ፍርስራሹን እና አመዱን እየሰበሰቡ እና እየጠረጉ በአካባቢው የቆመው መኪና ላይ እየጫኑ ነው። ኩማንደሩ በአካባቢው ወዲህ ወዲያ እየለ የሚሰራውን እየተመለከተ ነው፡፡ አለም ከመኪናዋ ስትወርድ አይቶታል፣ ነገር ግን እሷን ለማናገር ሲሞክር በአካባቢው የነበረው የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪ ሰለጠራው ወደእዛ ለመሄድ ከተንቀሳቀሰ በኋላ ሀሳቡን ቀይሮ ቆሞ ጠበቃት፡፡ ደረሰችበት…ሰላም ይለኛል ብላ ስትጠብቅ

"እዚህ ምን እየሰራሽ ነው?"ብሎ ጠየቃት፡፡

‹ከሳራ ጋር ሻይ ልጠጣ ነው የመጣሁት።››

በመደነቅ አፍጥጦ ተመለከታ‹‹ከእሷ ጋር ደግሞ ከመቼ ወዲህ ነው ጓደኛ የሆናችሁት?››

“ሃሳብ የእኔ ሳይሆን የእሷ ነበር” አለችው።

"እሺ ተዝናኑ" አለና ፊቱን አዙሮ ሲጠራው ወደ ነበረው ሰውዬ ሄደ፡፡

እሷም ወደማረፊያ ቤቱ ተራመደች..አቶ ፍሰሀ  በቤቱ በረንዳ ላይ ቆሞ ነበር፣ ስትጠጋ ፍርሃቷ እንዳይታይ ለማድረግ ሞክራለች።

"እንዴት ነህ … ጋሽ ፍሰሀ?"

"  ሰዓት  አክባሪነትሽ  የሚደነቅ  ነው…እናትሽም  ልክ  እንደዚህ  ነበረች››አላት፡፡ለምን እንደመጣች እንደሚያውቅ ተረዳች

‹‹አመሰግናለው››አለችው፡፡

‹‹ምንም አይደል››

"ኩማንደሩ እሳቱን ያስነሳውን ሰው  በቁጥጥር ስር እንደሚያውለው  ተስፋ አደርጋለሁ። እኔም ተገቢን ፍትህ እንድታገኙ አስፈላጊውን ሁሉ አደርጋለሁ።"ስትል ቃሏን ሰጠችው፡፡

"አዎ፣ እኔም ተስፋ አደርጋለው… ሁሉንም ነገር ችላ ማለት እችላለሁ። ነገር ግን ያን የመሰለ ተወዳጁን የገመዶን ፈረስ እንዲሞት ያደረገውን ሰው ግን ይቅር አልለውም።ያን ፈረስ በማሳደግና በመንከባከቡ ይሰማው የነበረውን ኩራት እኔ ነበርኩ የማውቀው።"

በዚህ ጊዜ ጁኒዬር ከውስጥ ወጣ…በውብ ፈገግታ ተሞልቶ የሞቀ ሰላምታ ሰጣት፡፡ አለም"ወደ ውስጥ ብገባ ይሻለኛል… እናትህን ብዙ አላስጠብቃት" አለቸው ።
ጁኒየር እጁን ትከሻዋ ላይ ጫነና "እናቴ የትላንት ማታውን ጥፋቷን ማረም ትፈልጋለች። ግብዣዋን ስለተቀበልሽ በጣም ተደስታ ነበር። አንቺን ለማየት በጉጉት እየጠበቀችሽ ነው።››አላት

‹‹ጥሩ››ብላ ወደ ውስጥ ገባች፡፡
አገልጋይዋ በራፉ ድረስ መጥታ ተቀበለቻት።‹‹ግቢ።››ብላ ወደ ውስጠኛው ክፍል እየመራች ወሰደቻትና ከሳራ ጋር አገናኘቻት፡፡

ከሳራ ጋር ተጨባበጡና ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ፡፡
አለም የክፍሉን ዙሪያ ገባ እየተመለከተች"እንዴት የሚያምር ክፍል ነው?!"

"ወደድሽው?።"

‹‹በጣም እንጂ…››
44👍7👏2