#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
===================
አላዛር አልጋ ላይ ተጋድሞ በጥልቀት እያሰበ ነው፡፡ሰሎሜ ቀን ከሂሩት ጋር ያወራችውንና የዶለተችውን ነገር መልሳ በደንብ እያመዛዘነች ስለሆነ ፈጥና ወደመኝታ ቤት ለመግባት አልፈለገችም፡፡ሳሎን ሶፋ ላይ ተዘርግታ አይኖቾን የተከፈተው ቲቪ ላይ በመሰካት በሀሳብ ግን ነጉዳለች፡፡
በተመሳሳይ አላዛርም የባለቤቱን የከረረ የስሜት መለዋወጥ በእራት ሰዓት ስላስተዋለ ጥልቅ ትካዜ ውስጥ ገብቷል፡፡ ‹‹እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምቀጥለው?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ሚስቱን ያፈቅራታል..፡፡በጣም ነው የሚያፈቅራት፡፡ለመጀመሪያ ቀን ካገባት ቀን ጀምሮ በሙሉ ልቡ እየተንከባከባት ነው፡፡ግን ምንም ያህል ቢጥር ደስተኛ ሊያደርጋት አልቻለም፡፡እስከአሁን እንደወንድሟ ነው አብሯት እየኖረ ያለው፡፡መሆን የሚገባው የሚጠበቅበትም ግን እንደባሏ መሆን ነበር፡፡እንደዛ ቢሆን ልክ እንደተመኘው ሙሉ ደስተኛና ፍልቅልቅ ትሆንለት ነበር፡፡ ያንን ማድረግ ግን አልቻለም…፡፡በጣም እያስጨነቀው ያለው ደግሞ እስከአሁን አለመቻሉ አይደለም..፤ መቼ ሊችል እንደሚችል ፍፁም አለማወቁ ነው፡፡እጅን አንቀሳቀሰ እና ወደቢጃማ ኪሱ ሰደደ..ስልኩን አወጣና ጎግል ከፈተ፡፡ ስንፈተ ወሲብ ብሎ ሰርች ሲያደርግ ብዙ ምርጫዎች መጡለት፡፡
ከመካከላቸው በደመነፍስ መረጠና አንዱን ከፈተው፡፡ትራሱን ቀና አድርጎ አስተካከለና የሆነ የሚጠቅም ነገር ባገኝ በሚል ተስፋ ማንበብ ጀመረ፡፡
ርእሱ ‹‹የስንፈተ ወሲብ አይነቶች ፤ምክንያቶችና መፍትሄዎቹ›› ይላል፡፡
በወንዶች ላይ የሚታዩት የስንፈተ ወሲብ ችግሮችን በሶስት መልኩ ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ አንደኛው የብልት መነሳት ችግር ወይም በሌላ አገላለፅ ስንፈተ ወሲብ እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡ ሁለተኛው እርካታ ደረጃ ሳይደርስ የዘር ፈሳሽ ማውጣት ወይም ገና አካባቢው ጋር እንደደረሱ መርጨት ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ የወሲብ ስሜት አልባነት ወይንም ጭሩሱኑ ወሲብ ለማድረግ ፍላጎት ማጣት ናቸው፡፡
አላዛር ንባቡን ገታ አደረገና ስላነበበው ነገር ማሰላሰል ጀመረ..‹‹ከእነዚህ ሶስት ምክንያቶች መካከል የእኔ ችግር የትኛው ላይ ነው የሚያርፈው?››ሲል እራሱን ጠየቀና
ማሰላሰል ጀመረ፡፡የእሱ ችግር ሙሉ በሙሉ የወሲብ ስሜት ማጣት እንደሆነ ተረዳ፡፡እና ንባቡን ካቆመበት ቀጠለ፡፡
የመጀመሪያውን ስንመለከት የብልት መነሳት ችግር ያለባቸው ሰዎችን በብዛት እናገኛለን፡፡ ይሄ አይነት የወሲብ ችግር በተለያየ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ላይ የሚከሰት ቢሆንም በተደጋጋሚ ወደ ህክምና የሚመጡት ግን ዕድሜያቸው ከስልሳ ዓመት በላይ የሆኑት ሰዎች ናቸው ፡፡ አንዳንድ ወጣቶችም አልፎ አልፎም ቢሆን የዚህ ጉዳይ ተጠቂዎች መሆናቸውን ሪፖርት ሲያደርጉ ይታያል፡፡
ችግሩ ከየት ይነሳል? ብለን ስንመለከት ሁለት አይነት ምክንያቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ከስነ ልቦና ጋር የተያያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተለያዩ በሽታዎች በሚፈጥሩ የጎንዬሽ ተፅዕኖ ምክንያት ይከሰታል፡፡ ዋነኛው የስንፈተ ወሲብ መንስኤ ተብሎ የሚጠቀሰው የስነ-ልቦና ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአዕምሮ ውጥረት ፤ ጭንቀት እና የተለያዩ ሀሳቦች ለስንፈተ ወሲብ ችግር ያጋልጡናል፡፡ የአካል ድካም እና መዛልም ሌለኛው ምክንያት ነው፡፡ ለምሳሌ አካሉ በብዙ ስራ ሲንገላታ የዋለ ሰው በግንኙነት ወቅት የብልት መነሳት፣ ስሜት ማጣት አሊያም ለወሲብ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሊገኝ ይችላል፡፡
አንድ ሰው የሀሳብ መደራረቦች በአእምሮው እንደታጨቀ ወሲብ ለማድረግ በሚሞክርበት ጊዜ ብልት ትክክለኛው ጥልቀት ላይ ደርሶ ተገቢውን እንቅስቃሴ ከማድረጉ በፊት አስቀድሞ ጥንካሬውን የሚያጣበት ሁኔታ ይከሰታል ፡፡ ይህን በምሳሌ ብንመለከት ከፍቅር ጓደኛው ጋር ወሲብ በሚፈፅምበት ወቅት ነጋዴ ከሆነ ስለተጋረጠበት የንግድ ችግር የመስሪያ ቤት ኃላፊ ከሆነ ስላልተሳኩ የድርጅቱ እቅዶች ካለው ኃላፊነት ጫና የተነሳ በአዕምሮው ሊመላለሱበት ይችላሉ፡፡ ይህም ጥሩ ያልሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳይከውን ምክንያት ይሆነዋል፡፡ግብረስጋ ግንኙነት ደግሞ በባህሪው ሙሉ ለሙሉ ትኩረት የሚሻ የስሜት ተራክቦ ነው፡፡ ሌላው በባልና በሚስት መካከል አለመግባባት እና ቅሬታ በሚኖርበት ጊዜ ተነሳሽነቱ በሁለቱም ወገን ይቀንሳል፡፡……..
እስከአሁን ያነበባቸው የስንፈተ ወሲብ ችግር የሚያጋልጡ ምክንያቶች ለጠቅላላ እውቀት ጥሩ ግንዛቤ የሰጡት ቢሆንም ቀጥታ የእሱን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል መፍትሔ ሚጠቁሙ ሆነው አላገኛቸውም..ቢሆንም ግን ተስፋ ቆርጦ ንባቡን ማቋረጥ አልፈለገም…ትንፋሹን ሰበሰበና ማንበቡን ቀጠለ፡፡
የአንድሮጂን ሆርሞን መመረት ወንዶች ላይ ብዛት ያለው የደም ፍሰት ወደ ብልት እንዲዘዋወር በማድረግ ብልት እንዲነሳ ያደርጋል፡፡ ከላይ የጠቀስናቸው እንደ ጭንቀት፤በስራ መዛል ወዘተ አይነት ምክንያቶች ይህን ሆርሞን በተገቢው መንገድ እንዳይመረት ያደርጋል፡፡በዛም ምክንያት ወደብልት የሚፈሰው የደም መጠን አናሳ ስለሚሆን የብልት በተገቢው ጥንካሬ የመቆም ችግር ያጋጥመዋል፡፡ይሄን ለማካካስ ሲባል በተለይ በወጣቶች የወሲብ ፊልሞች ለማየት ወደመነሳሳት ያዘነብላሉ፣ ይሄም በጫና፣ በሃዘን እና በድካም ላይ ሆነንም የወሲብ ስሜታችን እንዲነሳሳ ያደርጋል፡፡ያ ደግሞ በተለይ ለብልት መነሳሳት አና ለፍላጎት መጨመር ጊዜያዊ መፍትሄ ሆኖ ቢያገለግልም በቆይታ ግን የራሱ የሆነ የጎንዬሽ ጉዳት ማስከተሉ አይቀርም፡፡የፊልም ኢንደስትሪው ሚያመነጫቸው የወሲብ ፊልሞች በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከዛም አልፎ በጎልማሶች ዘንድ በደንብ የሚታዩ ናቸው፡፡እንዚህ ወሲብ ፊልሞች ከላይ ሲታዩ እጅግ ማሪኪ ስሜት ቀስቃሽና መንፈስ አነቃቂ መስለው ቢታዩም በሚያየው ወጣት ላይ የሚያስከትሉት ስነልቦናው ቀውስ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡አንደኛ ወጣቱ የአካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ዝግጅት ሳያደርግ ወጣ ያሉ አፈንጋጭ ወሲባዊ ተራክቦ እንዲያደርግ ይወሰውስታል፡፡ያ ደግሞ ለቋሚ የጤና ችግርና ወሲባዊ ችግር ይዳርገዋል፡፡ሁለተኛ በፊልሞቹ የሚደረጉ ወሲባዊ ተራክቦዎች ከሰውኛ ይልቅ ሜካኒካል ገፅታ ያላቸው ከ30 ደቂቃ አስከአንድ ሰዓት የሚዘልቁ አይነቶች ናቸው፡፡
እርግጥ አንድ ሰው በውሲብ ግንኙነት ያንን ያህል ሊቆይ አይችልም ለማለት አይደለም….ግን ከሺ ጥንዶች በአንዶቹ የሚከሰት ነገርን እንደኖርማልና የተለመደ አድርጎ ማቅረብ በአብዛኛው ላይ የሚፈጥረው ስነልቦናዊ ውዥንብር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ለምሳሌ በስንፈተወሲብ ችግር የሚመደበው ቀድሞ መርጨት ችግር የሚባለው አንድ ሰው ወሲብ ጀምሮ ከአንድ ደቂቃ በታች በሆነ የጊዜ ርዝመት ውስጥ የዘርፍሬውን ካፈሰሰ ነው፡፡እንግዲህ ሁለትም ሶስትም አምስትም ደቂቃ ኖርማልና በብዙ ውንዶች የሚከሰት ነው ማለት ነው፡፡ይሄንን ሀቅ ወንዱም ሆነ ሴቷ ማወቅ አለባቸው፡፡ሀያ ..ሰላሳ ደቂቃ መቆየት የቻለም እንደዛው ያንን እንደጀግንነት ማውራት ትርጉመ ቢስ ነው፡፡ዋናው ምን ያህል የጊዜ ርዝመት ቆየ ሳይሆን በቅፅበት ውስጥም ቢሆን ምን ያህል ፍፃማዊ ደስታ ተቀያይረናል…ምን ያህል በአየር ላይ ተንሳፈን ነበር…?ምን ያህልስ ሰዓት አንዳችን በሌላችን ውስጥ ጠፍተን ነበር…?የሚለውን ነው መመዘኛ መሆን ያለበት… እና አንድ ሰው በተቻለው መጠን እነዚህን የምራባዊያን የወሲብ ፊልሞችን ከማየት እራሱን

👍53❤10
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
አዲስ አለም በራሷ መኪና ግን ሹፌር እየነዳላት ከአዳማ ወደአዲስ አበባ እየተጓዘች ነው፡፡
የተቀመጠችው ከኋላ ወንበር ላይ ሲሆን ከግራዋ የራሷ ልጅ ቅዱስ ሲኖር ከግራዋ ደግሞ የፀአዳ ልጅ ምሰር ትገኛለች፡፡
አዲስአለም ወደአዲስ አበባ የምትሄደው እናቷን ለመጠየቅ ነው፡፡ይሄ ቤተሰቦቾ አዳማ ለቀው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ በወር ወይም በሁለት ወር አንዴ የምታርገው ነገር ስለሆነ ማንም ለምን እንዴት ብሎ የሚጠይቃት የለም፡፡ምስርን በምን ሰበብ አስፈቅዳ ከእሷ ጋር ይዛት እንደምትመጣ ግን ግራ ገብቷት ነበር፡፡ማታ ነበር ፀአዳ ጋር የደወለች፡፡
‹‹እሺ ጓደኛዬ እንዴት ነሽ?››
‹‹ሰላም ነኝ ምነው ቀን ተገናኝተን ነበር እኮ..በዚህ መሀከል ምን ትሆናለች ብለሽ አሰብሽ?››.
‹‹አንቺ ደግሞ ከአፍሽ ቀና ነገር ቢወጣ ምን አለበት?››
‹‹በይ አሁን ምን ፈልገሽ ነው ወደገደለው ግቢ….››
‹‹በእናትሽ ነገ እነማዬ ጋር አብረን እንሂድ››
‹‹ነገ ››
‹‹አዎ ነገ››
‹‹ያምሻል እንዴ…?ስንት ስራ እንዳለብኝ ስነግርሽ ውዬ እንዴት የማልችለውን ነገር ትጠይቂኛለሽ?››
‹‹ውይ ለካ ስራ አለብሽ..ብቻዬን መሄድ እኮ ደብሮኝ ነው››
ብቻሽን መሄድ ከደበረሽ ታዛዥ እና ጣፋጭ የሆነ ምርጥ ባል አለሽ እሱን አስከትለሽ ሂጂ››
‹‹አንቺ እየሰማሽ እኮ ነው››
‹‹ላውድ ላይ አድርሽ ነው እንዴት የምታወሪኝ… አንቺ እኮ ቅሌታም ነሽ….ለነገሩ ሚኪን በተመለከተ መጥፎ ነገር እንደማልናገር እርግጠኛ ስለሆንኩ እንደፈልገሽ››
‹‹መጥፎ ነገር እንደማትናገሪ እኔም ምስክር ነኝ … ውሸት ግን ትናገሪያለሽ..ምን አልባት እንዳልሺው ጣፋጭ ሊሆን ይችላል ታዛዣ ግን አይደለም..ልክ እንደአንቺው ስራ አለኝ አልችልም የሚል መልስ ነው የሰጠኝ››
‹‹በቃ ከልጅሽ ጋር ሒጂ››
‹‹ወይ እንደውም ተውት ከልጆቼ ጋ ሄዳለው…ምስርን ቆንጆ አድርገሽ አሳምሪያትና ወደስራ ስትሄጂ ይዘሻት ውጭ.. በዛው መጥቼ ወስዳታለው››
‹‹ምን እያልሽ ነው?››ፀአዳ እንደመበሳጨት አለች፡፡
‹‹የራስሽው ምክር እኮ ነው፡፡ልጆቹን ይዤ ሄድና ዘና እንላለን…እናንተም ካለልጆቻችሁ ይድላችሁ…እሁድ ማታ ተመልሰን እንመጣለን፡፡››
‹‹አንቺ እኮ የሆነ መዠገር ነገር ነሽ…እኔ ለራሴ ስንት ስራ አለብኝ..?ገና አሁን እሷን ሰውነቷን ሳጥብ..ፀጉሯን ሰሰራ….››
አላስጨረሰቻትም፡፡‹‹በቃ…ጥዋት ሁለት ተኩል አካባቢ ስራ ቦታሽ እመጣና ወስዳታለው..ደህና እደሪ..እወድሻለው፡፡››ብላት ስልኳን ዘጋችው፡፡እንዳለችውም ጥዋት ስትሄድ ፀአዳ ከነንጭንጯ ልጇን ምስርን አስባና አሳምራ ነበር የጠበቀቻት፡፡
‹‹ውይ ጎደኛዬ ንዴት እንደሸወድኩሽ ስታውቂ እንዴት ትናደጂ ይሆን?›› ብላ አሰበችና ብቻዋን ፈገግ አለች፡፡
ሹፌሩ ጎሮ አካባቢ የሚገኘው የቤተሰቦቾ ቤት ካደረሳት በኃላ ሚካኤል እንዲገዛለት ያዘዘው ዕቃዎች ስለሉ ወደመርካቶ ለመሄድ ተዘጋጀ….
‹‹በቃ ነገ አስር ሰዓት አካባቢ እዚህ ድረስ ››አለችው አዲስ፡፡
‹‹እዚህ የምትንቀሳቀሺበት አይቸግርሽም?››
‹‹ችግር የለውም..የትም የመውጣት እቅድ የለኝም…ምን አልባት የምወጣም ከሆነ ራይድ እጠቀማለው››አለችና ሸኘችው፡፡
ከዛ ልጆቹን ወደቤት አስገብታ እናቷን በቅጡ እንኳን ሰላም ሳትል ነው ወደጓሮ ሄዳ ስልክ የደወለችው፡፡ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ‹‹እንዴት ነህ ዘሚካኤል?››
‹‹ሰላም ነኝ..ግን አልተሳካልኝም ብለሽ እንዳታበሳጪኝ››
‹‹አረ ተሳክቶልኛል…መጥተናል እማዬ ቤት ነው ያለነው፡፡››
‹‹በጣም ጎበዝ…..በቃ ጎሮ አካባቢ ነው ያልሺኝ፡፡››
‹‹አዎ… ትክክለኛ አድራሻውን በሚሴጅ ልክልሀለው››
‹‹በቃ..በአንድ ሰዓት ውስጥ እመጣለው››
‹‹ጥሩ ነው..እኛም ገና አሁን መድረሳችን ስለሆነ እስከዛ ከእማዬ ጋ እንጫወታለን…በል ቻው››
‹‹አዲስ በጣም አመሰግናለው…ቻው››
ስልኩ ተዘጋ ፣፣እሷ ግን ፈዛ ቀረች…ከዘሚካኤል ጋር በዚህ መጠን መቀራረብ መቻሏ የተአምር ያህል ነው….ለዘመናት ስታልመውና ስትመኘው የነበረ ነገር ነው፡፡ግን በዚህ መንገድ ይሆናል ብላ ፈፅሞ ሀሳብ አልነበራትም..እሱ የእሷን የልብ ጓደኛ አፍቅሮ እሷ ደግሞ እሱን ከሚያፈቅራት ልጅ ጋር ለማቀራረብ ስትጥር….በራሷ ድርጊት ፈገግ አለች፡፡
‹‹ምን አለበት…. ለሚያፈቅሩት ሰው የሚያፈቅረውን ነገር እዲያገኝ መርዳት ትንሽ ህመም ቢኖረውም ግን ደግሞ ደስ የሚል ስሜት አለው፡፡››አለችና ለስሜቷ ድጋፍ ለመስጠት ሞከረች…የባሏ ሚካኤል ምስል በድንገት መጥቶ አየሩን ሞላው‹‹ፍቅሬ ምን እያሰብሽ ነው…?የገዛ ወንድሜን!!!››ብሎ በሀዘን በተሰበረ ስሜት ሲወቅሳት አየች፡፡
‹‹አንተ ደግሞ ይሄ እኮ ያለፈ ታሪክ ነው….ታውቃለህ እሱን ለማግኘት ስትጥር ነበር ከአንተ ጋር የተቀራረብኩት…ከዛ እሱም ሀገር ጥሎ ጠፋ አንተም ለእኔ ምርጥና ተወዳጅ ሆንክልኝ..እናም በሙሉ ልቤም ወድጄ አገባሁህ››
‹‹ግን ስታገቢኝ…ወደሽ ነው..ወይስ አፍቅረሺኝ?››
‹‹አይ አንተ ደግሞ ምን ቃላት ትመነዝራለህ….ለማንኛውም..የእሱ ያለፈ የአፍላ የወጣትነት ስሜት ነው..አሁን እየቀረብኩትና እየረዳሁት ያለሁት ያንተ ወንድም ስለሆነ ብቻ ነው››
‹‹እንዴ…!!ምንድነው ጓሮ ተደብቀሽ ብቻሽን ምታወሪው?››የእናትዬው የመገረም ንግግር ነበር ከገባችበት ቅዠት መሰል ሀሳብ አባኖ ያወጣት፡፡
‹‹አይ እማዬ ..ምንም አይደል ..የሆነ ነገር እያሰብኩ ነበር››
‹‹የሆነ ነገር..ምነው ከሚካኤል ጋር ተጣላችሁ እንዴ?››
‹‹ወይ እማዬ ምንድነው የምታወሪው..?ከሚካኤል ጋር ለምንድነው የምጣለው?››
‹‹ባልና ሚስት ለምንድነው የሚጣሉት?››
‹‹እኔ እንጃ..እኔና ሚኪ ስንጣለ አይተሸን ታውቂያለሽ?››
‹‹እሱ መልካምና ታጋሽ ባል ስለሆነ ነዋ…እንጂማ እንደአንቺ መመነጫጨቅ ቢሆን… ››እናትዬው ነግግሯን ሳታገባድድ አንጠልጥላ ተወችው፡፡
‹‹እማዬ ደግሞ… የእኔ እናት ነሽ የእሱ?››
‹‹የሁለታችሁም…ባሌ ነው ብለሽ አምጥተሸ ካስተዋወቅሺኝ ቀን ጀምሮ እኮ ልክ እንደአንቺ እሱም ልጄ ሆኗል…በዛ ላይ አሁን ወርቅ የሆነ የልጅ ልጅ ሰጥቶኛል…በይ አሁን ነይ ግቢ ቁርስ ቀርቧል…››አሏትና ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ፡፡
ዘሚካኤል እንዳለውም ከአንድ ሰዓት በኃላ በራፍ ላይ ደርሶ ደወለላቸው፡፡ተዘጋጅታ ስትጠብቀው ስለነበረ ወዲያውኑ ነው ልጆቹን ይዛ የወጣችው፡፡ከግዙፉ ሀመር መኪናው ወርዶ በራፍን ከፍቶ ቆሞ እየጠበቃቸው ነበር…የስድስት አመቷ ምስር እንዳየችው ደነገጠች…..መጀመሪያ የት እንደምታውቀው ነበር ግራ የገባት..ከዛ የምትወደው ዘፋኝና ተዋናይ መሆኑን ስታውቅ ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት እየተንደረደረች ወደ እሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ከቆመበት እጆቹን ዘርግቶ ወደእሷ ተንቀሳቀሰ…እቅፉ ውስጥ ወደቀች.. ጭምቅ አድርጎ አቀፋትና በአየር ላይ አንጠለጠላት..የምስርን ድርጊት ያየው ቅዱስ እጆቹን ከእናቱ እጅ አስለቅቆ ኩስ ኩስ እያለ ምስር እንዳደረገችው ወደዘሚካኤል ሮጠ….አዲስአለም በልጆቹ ያልተጠበቀ ድርጊት በድንጋጤ አፏን ከፈተች ….ሚካኤል ቅዱስ ስሩ ሲደርስ ምስርን ወደአንዱ እጁ አዘዋወራትና ጎንበስ ብሎ ቅዱስን አቅፎ ወደላይ አነሳውና ጉንጮቹን እያገላበጠ ሳመው…..በዚህ ጊዜ አዲስ አለም ከመደነቅ ሳትወጣ ስራቸው ደርሳ ነበር፡፡
‹‹ቆይ ከእነዚህ ልጆች ጋር ከዚህ በፊት ትተዋወቁ ነበር እንዴ?››
ጉንጮቾን እያገላበጠ ሰማት..ትንፋሹ ልክ ሰው ፊት ላይ እደሚበትን አደንዛዥ ዕፅ ኃይል አለው…

👍66❤17
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ራሄል ዶ/ር ኤልያስን ማግኘት ስለፈለገች ስልኳን አንስታ መጀመሪያ ሞባዩሉ ላይ ደወለች….ዝግ ነው፡፡ከዛ ሆስፒታል ደወለች፡፡ከተወሰነ ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ እባኮት ዶ/ር ኤልስን ማግኘት እችላለው?››
‹‹ይቅርታ የእኔ እመቤት ዶ/ሩ ዛሬ ስራ ››
‹‹ነገር ግን ዶክተር ኤልያስ የግድ ማግኘት አለብኝ››አለች ኮስተር ብላ፡፡… ራሄል የረጠበ ጨርቅ በፀጋ ፊት ላይ እያስቀመጠች የሰውነቷን ሙቀት ለማስተካከል በመጣር ስልኩን እያወራች ነው። ከሁለት ቀናት በፊት ከቤታቸው ከተከናወናው የበጎ አድራጎት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ጀምሮ፣ ፀጋ ተለዋዋጭ በሆነ የጤና ችግር እየተሰቃየች ነው፡፡
በዛን ቀን ከሌንሳ መንታ ልጆች ጋር አብራ ስትጫወት ነበር ፡፡ምን አልባት ከእነሱ የሆነ ጉንፋን አይነት በሽታ ወስዳ ሊሆን እንደሚችል ጠረጠረች። ሌንሳ ትናንት ለራሄል ደውላ አንደኛዋ ልጇ ትንሽ ንፍጥ እና ትኩሳት እንዳለባት ነግራት ነበር። ለፀጋ በጣም ተጨነቀች፣ እና አሁን ጭንቀቷ ትክክል የሆነ ይመስላል።
በስልክ መስመር ላይ ያለችው የዶክተሩ ፀሐፊ ‹‹ይህን ተረድቻለሁ ግን የሱን ቀጠሮዎች በሙሉ ወደሌላ ቀን ለማዘዋወር በሂደት ላይ ነኝ። ይቅርታ፣…. በቤተሰብ ላይ ባጋጠመው ድንገተኛ ችግር ምክንያት ለአንድ ሳምንት ያህል ወደስራ መግባት አይችልም፡፡››
ራሄል ሴትዮዋን አመሰገነች እና ስልኩን ዘጋችው‹‹ ዔሊ ምን አይነት የቤተሰብ ችግር ነው ያጋጠመው?››ፍርሀት ሰውነቷን ወረራት፡፡ባለፈው ምርጥ ጊዜ አሳልፈው በመጥፎ ሁኔታ እንደተለያዩ አሰበችና እራሷን ወቀሰች፡፡ስለ ፀጋ ምን ማድረግ እንዳለባት መወሰን አልቻለችም፡፡
ፀጋ አይኖቿን በእጆቿ እያሻሸች‹‹መጠጣት እፈልጋለሁ›› አለቻት ።ራሄል አንድ ብርጭቆ ጭማቂ ሰጠቻት፣ከዚያም አብራት በኩሽና ወንበር ላይ ተቀምጣ አቀፈቻት ።ራሄል ብርጭቆውን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች እና ፀጋን በእርጋታ እያወዛወዘች ለስለስ ያለ ዘፈን ትዘፍንላት ጀመር። ሌላ ምን ማድረግ እንዳለባት አላወቀችም።ፀጋ ጧዋት ሙሉውን ጊዜ ስትበሳጭ ነው ያረፈደችው፣ እና የሙቀት መጠኑ በጣም ከፍተኛ ባይሆንም ራሄል መጨነቋን ማቆም አልቻለችም ።ራሄል የእህቷን ጭንቅላት በስሱ ሳመቻት፡፡
‹‹ኤሊ የት ነው ያለኸው?›› ብላ በሹክሹክታ ተናገረች፡፡
ነገሮች እንዴት በፍጥነት እንደተቀየሩ አስቂኝ ሆነውባታል። እሷ በዚህ መጠን እሱን ማነጋገር መፈለጓ በጣም የሚገርም ነው…. የዚያን የዝግጅት ቀን ምን እንደተሰማት ለማስረዳት ፈልጋለች። በሁለቱ መካከል ስላለው ነገር በጥንቃቄ ማስረዳት ፈልጋለች፣ ግን ይህን ማድረግ በእሱ እይታ ምን ያህል የተጋለጠች እንደሚያደርጋት ፍራቻ አድሮባታል። ፀጋን መልሳ ወደ አልጋው ወስዳ አስተኛቻት… ፀጋ አልተቃወመችም… ይህም ለራሄል ልጅቷ ምን ያህል እንደታመመች እንድትረዳ አደረጋት። ከሰአታት ስቃይ በኋላ ተኛች። እሷን ሊያሳስብ በሚችል ጸጥ ባለ ጽናት ነው የተኛችው።ትንሽ ተጨማሪ ጉልበት እንድታሳይ ፈለገች። ለብዙ ደቃቂ ስሯ ከተቀመጠች በኃላ በጸጥታ ክፍሉን ለቃ ወደ ቢሮዋ ሄደች። ከፋውንዴሽኑ የፋይናንስ ክፍል የቀረበውን ዘገባ አነበበች፣ ሮቤል እንዲከታተል የሚያሳስብ ጥቂት ማስታወሻዎችን አዘጋጅታ ጥቂት የስልክ ጥሪዎችን አደረገች።ከዛ ለዔሊያስ ለመደወል ሞከረች… ነገር ግን ያገኘችው የመልስ ማዳመጫ ማሽኑን ድምፅ ብቻ ነው.፡፡
ራሄል ብቸኝነት ተሰማት።ወደ ፀጋ ክፍል ስትመለስ ኮሪደር ላይ አለምን አገኘቻት።
‹‹ራሄል የደከመሽ ትመስያለሽ…ለምን ለትንሽ ጊዜ ወጣ ብለሽ አትመለሺም?ጸጋን እኔ ልከታተልሽ። ››አለቻት፡፡
‹‹ፀጋ አሁንም መተኛቷን ለማረጋገጥ ወደክፍሏ ዘልቃ ገባችና ተመለከተቻት።ተኝታለች ፣ተመልሳ ወጣችና በራፍ ላይ ካለችው አለም ጋር ማውራቷን ቀጠለች፡፡
‹‹ በጣም ፈታኝ ይመስላል…አለም››
‹‹ግድየለሽም …ሞባይልሽን ይዘሽ መውጣት አለብሽ… ፀጋ ተኝታለች፣ ደህና ትሆናለች..ችግር ካለ ወዲያው ደውልልሻለው።››የሚል ሀሳብ አቀረበችላት፡፡
‹‹ራሄል አለም ትክክል እንደሆነች ታውቃለች። ከገቢ ማሰባሳቢያው ቀን ጀምሮ፣ ስለ ዔሊያስ መርሳት አልቻለችም። በምትኩ እራሷን ወደ ስራ እና ፀጋን በመንከባከብ ውስጥ አስገብታ ነበር። ዓይኖቿ እስኪቃጠሉ ድረስ የቢሮዋን ስራ በቤቷ ውስጥ ሠርታለች፣ ነገር ግን እራሷን ስለእሱ እንዳታስብ ለማድረግ የወሰደችው እርምጃ ሙሉ በሙሉ አልሰራላትም። ከሁሉም በላይ ዔሊያስን የሳመችበት ክፍል ውስጥ መገኘቱ ትዝታውን ደጋግሞ እንዲቀሰቀስባት አድርጎታል። በአእምሮዋ ውስጥ ሌሎች ሀሳቦችን ለማስቀመጥ ፤ለጊዜውም ቢሆን ያንን ክፍል ለቃ መውጣት አለባት።ሞባይሎን እና የመኪናዋን ቁልፍ ይዛ ‹‹እሺ ከአንድ ሰአት በኋላ እመለሳለሁ››ብላ ወጣች…. መኪናዋን አስነሳችና ተንቀሳቀሰች፡፡
ከአርባ ደቂቃ ጉዞ በኃላ ራሔል በድንገት የ ዔሊያስ አዲሱ ቤት በሚገኝበት ጎዳና ላይ እራሷን አገኘችው፡፡ የመኪናውን ፍጥነቱን አቀዘቀዘች። እሷ በዚህ መንገድ ለመምጣት አላሰበችም ነበር፡ በእውነቱ የጉዞው ምክንያት ስለ ዔሊ ለመርሳት ነበር። ሳታስበው ግን እሱ ቤት ፊት ለፊት ተገኝታለች፡፡ፀሐፊው የቤተሰብ ችግር አጋጥሞት ከከተማ እንደወጣ ነበር የነገረቻት ነገር ግን የዔሊ ሞተር ሳይክል ከቤቱ ፊት ለፊት ዛፍ ጥላ ስር ቆሞ ነበር።
‹‹ርቆ ቢሄድ ኖሮ ሞተር ሳይክሉን ከእሱ ውጭ ሌላ ሰው መኖር ባልጀመረበት ቤት በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ጥሎ አይሄድም ነበር..››ስትል አሰበች
በውስጧ ሲጉላላ የከረመውን በእሱና በእሷ መካከል ስላለው ነገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስተካከል አለባት።እሷ ዔሊን መንከባከብ ትፈልጋለች, እሱ እንደሚያስብላት ታውቃለች…እሷም በጣም ታስብለታለች…ትጨነቅለታለች፡፡ግን ደግሞ በልቧ ውስጥ ፍራቻ ሚረጭባትን ስሜት ለእሱ መንገር እንዳለባት ታውቃለች፡፡ወደእሱ ለመቅረብ ታመነታ ነበር …አዎ፣ ወደ ሌላ ግንኙነት ለመግባት ፈርታለች። ቀድሞውንም ይሄንን ብታብራራለት ይረዳት ነበር። ሁለቱም ትልልቅ ሰዎች ናቸው። በመሀከላቸው ያለው ነገር ቀላል መሆን አለበት…. መኪናዋን ከሞተር ሞተሩ አጠገብ አቆመችና የቤቱን ደረጃ ወጣች ። የቤቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ገጽታ ውስጡን ለማየት እንድትጓጓ አድርጓታል። የቤቱ ውጫዊ ክፍል በቅርብ ጊዜ የሚጠናቀቅ አይነት ቢሆንም ግቢው ተጨማሪ ሥራ እንደሚያስፈልገው አስተዋለች። ጠርዝ ላይ ባለው የአበባ አልጋ ላይ ምን ዓይነት ተክሎች መቀመጥ እንዳለባቸው በምናቧ እየቀረጸች አሰላሰለች, በሩ ተከፈተ። ዔሊ ከፊት ለፊቷ ቆመ፣ ያልተላጨ ፂሙ፣ ክፍት ሸሚዙ፣ መላ ቁመናውን በሰከንድ ሽርፍራፊ አስተዋለች።
‹‹ሄይ… ራሄል ምን አመጣሽ?››
ፊቱ ላይ ምንም አይነት የተለየ ስሜት ማንበብ አልቻለችም ፡፡ ‹‹ትንሽ አየር ልውስድ ብዬ በመኪና ወጥቼ ነበር፣ድንገት በዚህ ሳልፍ የሞተር ሳይክልህን አየሁና ፣ እናም...››
በእጁ አንድ ወረቀት ይዟል..እጇቹ እየተንቀጠቀጡ መስሎ ተሰማት፡፡ ፎቶ መሆኑን ለየች ፣ወዲያው ከእጁ አመለጠውና ወደቀበት… ራሄል ልታነሳለት ጎንበስ ስትል ኤሊያስ እጁን በፍጥነት ዘረጋና ለቀም አደረጋት።አስደነገጣት፡፡
በሻከረ ድምጹ‹‹ተይው እኔ አነሳዋለው፣ቆሻሻ ነው ›› አላት ፡፡

❤56👍1🔥1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
‹‹ለፈረሶች የምታሳየውን ፍቅር ግማሹ ለሰው ብታሳይ እንዴት ጥሩ ነበር….ፈረሶችህን በትህትና ስታናግር ከቆየህ በኋላ ከሰው ጋር ማውራት ስትጀምር ቶንህ ወዲያው ይቀየርና ተናዳፊ ትሆናልህ››
የምፀት ፈገግታ ፈገግ አለና‹‹ለፈረሶችም ሆነ ለሰዎች የሚገባቸውን ነው ማደርገው….››አለና አጥሩ ላይ የተንጠለጠለውን ኮርቻ በማንሳት ፈረሱ ጀርባ ላይ አድርጎ አሳሰረውና የፈረሱን ሉጋም ይዞ ወደመውጫው መሄድ ጀመረ፡፡
ግራ ተጋብታ
"ወዴት ትሄዳለህ?"ስትል ጠየቀችው
" ትንሽ መጋለብ ፈልጋለው"
ከንዴቷ አንፃር ማልቀስ አማራት ‹‹ላናግርህ እፈልጋለሁ..ለምን እንደመጣሁ እያወቅክ ጥለኸኝ ልትሄድ ነው..?›› አለችው
ፈረሱ ላይ ወጣና ወደእሷ ቀረበ…እጁን ዘረጋላት….ግራ ተጋብትና በቆመችበት አይኖቾን አቁለጨለጨች….
‹‹እጅሽን ስጪኝ››አላት…..ዝምብላ ቀኝ እጇን ወደላይ ሰቀለችለት.. አጥብቆ ያዛትና ወደላይ ጎተታት…ጥንካሬው አስገረማት….እርካብ ላይ እግሯና አኖረችና እንጣጥ ብላ በመውጣት ከጀርባው ፈረሱ ላይ ተፈናጠጠች፡፡ከዛ ለፈረሱ ሉጋሙን ለቀቅ ሲያደርግለት ፈረሱ እየሰገረ ወደፊት ተስፈነጠረ ፡፡በፍራቻ ወገቡን አጥብቃ አቀፈችው….የኮረኮንች መንገዱን ይዞ ወደ ከተማዋ መውጫ ሽምጥ መጋለብ ጀመሩ….፡፡
"ትላንትና ማታ በቡና ቤት ውስጥ ከማን ጋር ነበር የተገናኘሽው?"
"ይሄ የኔ ጉዳይ ነው ኩማንደር …ለምን ተከተልከኝ?"ልትጠይቀው የምትፈልገው ብዙ ጥያቄዎች ነበራት፣ ነገር ግን በእያንዳንዱ የፈረስ እንቅስቃሴ ከተቀመጠችበት እንጣጥ ብላ ጀርባው ላይ ስትለጠፍበት ስለነበር አእምሮዋን በጀመረው ሀሳብ ላይ ፀንቶ እንዲቆይ ማድረግ ከባድ ሆነባት። እንደምንም ወደ አእምሯዋ የመጣውን የመጀመሪያ ጥያቄ ጠየቀችው።
"አንተ እና እናቴ እንዴት የቅርብ ጓደኛሞች ሆናችሁ?"
"አብረን ነው ያደግነው" አለ በንቀት። ተንፋሽ ወሰደና ቀጠለ"ት/ቤት መጫወቻ ሜዳ ላይ ተጀምሮ በእድሜ እየገፋን ስንሄድ ተሻሻለ"
"አስቸጋሪ ሆኖ አያውቅም?"
"አይ አንዳችን ከሌላችን የምደብቀው ምንም ምስጢር አልነበረንም. እንዲያውም ያንቺን ካሳየሺኝ የእኔንም አሳይሻለው እያልን እንጫወት ነበር."አለና ፈገግ አለ።‹‹በአጠቃላይ በእኔ እና እሷ መካከል አይነኬ የተባለ የውይይት ርዕስ አልነበረም ።››ሲል አከለበት፡፡
"ያ አንድ ሴት ልጅ ከሌላ ሴት ጋር የሚኖራት አይነት ግንኙነት አይደለምን?"
‹‹ብዙውን ጊዜ ግን ሰሎሜ ብዙ የሴት ጓደኞች አልነበራትም, አብዛኛዎቹ ልጃገረዶች በእሷ ይቀኑ ነበር."
"ለምን፧"
አለም መልሱን ቀድሞውንም ብታውቅም ከእሱ አንደበት መስማት ፈለገች፡፡ "በአንተ ምክንያት ነበር አይደል? ካንተ ጋር የነበራት ወዳጅነት?"
"ምናልባት ሊሆን ይችላል, ዋናው ጉዳይ ግን እሷ በጣም ቆንጆ ነበረች…በዙሪያዋ ያሉ አብዛኞቹ ልጃገረዶች እንደ አጋር ሳይሆን እንደ ተቀናቃኝ ነበር የሚቆጥሯት፡፡….ቆይ አንዴ።›› ፈረሱን አቅጣጫ ከመቀየሩ በፊት አስጠነቀቃት እና ፈረሱ ጓድጓዳ አካባቢ ሲረግጥ ወደ ፊት ገፋት፣ እሱ ላይ ተለጠፈች። በደመ ነፍስ ወገቡን አጥብቃ አቀፈችው።
"ፈረስ ቁልቁል ሲወርድ ወደፊት መንሸራተቱ የሚጠበቅ ነው….››
ስትረጋጋ“እናቴ ሁሉንም ሚስጥሮቾን እያመጣች ለአንተ ትዘረግፍ እንደነበረ እየነገርከኝ ነው?›› ብላ ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ, እንደዛ ነበር የምታደርገው…እሷ እንደአንቺ አይነት ውስብስብ ሴት አልበረችም…ለምሳሌ አንድ ቀን ምንም ሳትነግረኝ ከትምህር ቤት ቀረች እና የሆነ ችግር እንዳለ አውቄ ነበር...ተጨንቄ ስለነበር በእረፍት ወደ ቤቷ ሄድኩ. አያትሽ በሥራ ላይ ስለነበሩ ሰሎሜን ብቻዋን እያለቀሰች ነበር ያገኘዋት…ፈርቼ ምን እንደሆነች እስክትነግረኝ ድረስ ጨቀጨቅኳት።"
‹‹ጉዳዩ ምን ነበር?"
‹‹ የወር አበባዋን ለመጀመሪያ ጊዜ መቶባት ነበር….አያትሽ የወር አበባን በተመለከተ የሀጥያት ፍሬ እና እርግማን እንደሆነ የሚተርኩ አስፈሪ ታሪኮች ነግረዋት ስለነበር በጣም አዝና ነበር ያገኘኋት ፡፡ እንዴት ነው አያትሽ ለአንቺም እንደዛ አይነት አስፈሪ ታሪኮችን ይነግሩሽ ነበር?››
አለም ወገቡን ሳትለቅ አንገቷን እንደምንም ቀና አደረገችና‹‹ያን ያህል የሚረብሹ አይነት ታሪኮችን ነግራኝ አታውቀኝም… ምናልባት አያቴ እኔን ማሳደግ በጀመረችበት ጊዜ ተሻሽላ ሊሆን ይችላል።ለአቅመ አዳም በደረስኩበት ጊዜ በቀላሉ ነው የተቀበልኩት።››
ፈረሱ ግልቢያውን እስኪያቆም ድረስ አለም ያሉበትን ቦታ አላስተዋለችም ነበር፡፡መኖሪያ ቤቱ ደርሶ ነበር ያቆመው፡፡
" ከዛስ እንዴት ሆነ?"
‹‹አፅናናኋት እና የወርአበባ ማለት ሴትነቷ በይፋ የታወጀበት ድንቅ ቀን እንደሆነ እና መደስት እንጂ ማልቀስ እንደማይገባት ነገርኳት።››
"ሰራ ታዲያ?"
"እንደምገምተው አዎ። ማልቀሷን አቆመች"
'እና...?'' አለም የታሪኩን በጣም አስፈላጊ ክፍል እንዳልነገራ ስላወቀች እንዲቀጥል አነሳሳችው።
"ከዛማ.. በቃ ።››አለና ቀድሞ ከፈረሱ ላይ በቀላሉ በመውረድ ‹‹ እግርሽን አንሺው።" አለና እሷን ለማውረድ እጁን ዘርግቶ በጠንካራ እጁ ወገቡ ላይ አቀፋትና ወደ መሬት አወረዳት።
ከእናቷ ጋር ሲሳሳም ሚያሳየውን ፎቶ መመልከቷን አስታወሰች ። "ለቅሶዋን ካቆመች በኃላ ሳምካት አይደል?"
በትከሻው የማይመች እንቅስቃሴ አደረገ። "ከዚያን ቀን በፊትም ስሜያት ነበር።" "ግን ያ የመጀመሪያው እውነተኛ መሳም ነበር አይደል?"
እሷን በጥልቀት ተመለከታትና ወደ ቤቱ በረንዳ ወጥቶ በሩን ገፋው ። ወደኃላ ዞር አለና
‹‹መግባትም ሆነ አለመግባት የአንቺ ጉዳይ ነው።››አለና ክፍት አድርጎ ተወው… ወደ ውስጥ ገብቶ ጠፋ, ተስፋ የቆረጠች ቢሆንም ግን ደግሞ ተጫማሪ የማወቅ ጉጉት ስላላት ተከተለችው።
መየፊት ለፊት በር በቀጥታ ወደ ሳሎን ተከፈተ። በግራዋ በኩል ባለው በር በኩል የመመገቢያ ቦታ እና ኩሽና ማየት ችላለች። በተቃራኒው በኩል ያለው የመተላለፊያ መንገድ ወደ መኝታ ክፍል ይወስዳል፣ እሱም ሲያወራ ትሰማለች። የሳሎኑን በር ዘጋች፣ መነጽርዋን አውልቃ ዙሪያዋን ተመለከተች።ቤቱ የወንደላጤነት ወዝ ነበረው …ፈሪኒቸሮቹ መጠነኛና ቅልብጭ ያሉ ናቸው፡፡በግራ ግድግዳ ያለው መደርደሪያ ላይ ያሉት መጻሕፍቶች የተዘበራረቁ ነበሩ፣ ፡፡
"ቡና ትፈልጊያለሽ?"
"ባገኝ ደስ ይለኛል።››
ወደ ኩሽና ገባ። የቀዘቀዙ እግሮቿ የደም ዝውውር እንዲስተካከል እያፍታታች በክፍሉ ውስጥ መዞሯን ቀጠለች። ከመጽሐፍ መደርደሪያው በላይ ወደተቀመጠው አንድ ረጅም ዋንጫ ቀልቧ ተሳበ። በላዩ ላይ የኩማንዱሩ ስም እና ቀኑ በግልፅ ፊደላት ተቀርጾበታል።
"ይህ ትክክለኛው ቀለም ነው?" ዘወር ስትል አንድ ኩባያ ቡና ይዞላት ወደ እሷ እየቀረበ ነበር።
"አመሰግናለሁ።" ብላ ተቀበለችውና …ጭንቅላቷን ወደ ዋንጫው በማዘንበል "ይሄ ያንተ ምርጡ አመት አይደል?"ስትል ጠየቀችው፡፡
"ምን አልባት"
"ምነው ?እርግጠኛ አይደለህም?"
ወደ ወንበሩ ሄደና ተቀመጠ ፡፡ "ያኔ እንደዛ ተሰምቶኝ ነበር እና አሁንም ድረስ በወቅቱ የሚደግፈኝ ጥሩ ቡድን እንደነበረኝ ይሰማኛል።ሌሎች በእጩነት የቀረቡት ተጫዋቾችም እንደኔ ዋጋ ያላቸው ነበሩ።"
"ለምሳሌ ጁኒየር?"
"አዎ እሱም ከነሱ አንዱ ነበር " ሲል መለሰ፣
‹‹ሽልማቱን ያሸነፍከው አንተ እንጂ ጁኒየር አይደለም።››ዓይኖቹ ወደሷ አፍጠጠ፡፡
"ውድ አቃቢህግ ከእኔ ጋር የጀመርሽውን ጫወታ አቁሚ እና በአእምሮሽ ያለውን ነገር ቀጥታ ተናገሪ።"

❤40👍4🔥1