#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ
================
አለማየሁ በቀጠሮው መሰረት ከአላዛርና አለማየሁ ጋር ከተገናኘ በኋላ ‹‹እሺ ባላና ሚስቶች ለምንድነው የፈለጋችሁኝ….?ለጥሩ ነገር እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡››ሲል የመጀመሪያ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡
ሁለቱም እርስ በርስ ተያዩ..አንተ ንገረው አንቺ ንገሪው እየተባባሉ የሚገባበዙ ይመስላል አላዛር ቅድሚያውን ወሰደ‹‹በሚቀጥለው ሳምንት ሁሴን እንደሚመጣ ታውቃለህ አይደል?››
ያልጠበቀውን ርዕስ ነው ያነሳበት‹‹ትክክለኛውን ቀን አላውቅም እንጂ እንደሚመጣ አዎ በቀደም ደውሎልኝ ነበር..››
‹‹ጥሩ እንግዲህ ..እናቱም አባቱም እንደሞቱ ታውቃለህ…..እዚህ ሌላ ዘመድ የለውም ..ከፋም ለማም የልጅነት ጓደኞቹና የቅርቡ ሰዎች እኛ ሶስታችን ነን››
በውስጡ ‹‹የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች›› የሚለውን ተረት እየተረተበት ‹‹አዎ ትክክል››ሲል መለሰ፡፡
‹‹እና እንዴት እንቀበለው የሚለውን ለመነጋገር ነው፡፡››
‹‹በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው፡፡ይሄ የድሮ ጓደኛችንን የመቀበል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን እኛም መልሰን ለአመታት ተራርቀን ከቆየንበት ለመቀራረብና መልሰን ጓደኝነታችንን ለማደስ ያግዘናል….››አለ
…እንደዛ ሲል በውስጡ ያለው ከአላዛር ወይም ከሁሴን ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ድሮ ጓፈደኛነታችው የመመለስ ጉጉት ኖሮት አይደለም..ከዛ ይልቅ ስለሰሎሜ በውስጡ እያሰበ ነው፡፡
‹‹በጥሩ ሁኔታ ብንቀበለው ደስ ይለኛል…እኔ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ….ዝግጅቱን እኔ ቤት ማድረግ እንችላለን››አለ…
‹‹አይ ከአንተ ቤት የእኛ ቤት ይሻል ይመስለኛል….ማለት የወንደላጤን ቤት ማድመቅ ይከብዳል›› ሰሎሜ ነች ተናጋሪዋ፡
‹‹እሺ እንዳልሽ…እኔ ቤት ብንቀበለው በዛውም የራሱን ነገር እስከሚያመቻች አኔ ጋር መቆየት ይችላል ብዬ ነው፡፡››
‹‹እኛ ጋርስ ለመቆየት ምን ይከለክለዋል…?እቤታችን እንደሆነ እንኳን እሱንና አንተም ብትጨመር በቂ ክፍት ክፍሎች አሉን ….እንደምታውቀው እዛ አፓርታማ ቤት ውስጥ እኔና እሱ ብቻ ነን....ልጅ የለን ምን የለን››
በሰሎሜ ንግግር አላዛር ሽምቅቅ አለ..ሆነ ብላ አስባበት የተናገረችው እንደሆነ ያውቃል….ግን ዋጥ አድርጎ በትዕግስት ከማሳለፍ ውጭ ምርጫ እንደሌለው ያውቃል፣ያደረገውም እንደዛ ነው፡፡
አለማየሁ‹‹በቃ እሺ እጅ ሰጥቼለው››ሲል በሀሳባቸው ተስማማ፡፡
‹‹ጥሩ በቃ …እንደዛ ከሆነ በፊታችን እሁድ ቤት ናና ስለዝርዝሩ እንነጋገርበታለን››
‹‹ጥሩ..እንደውም በሰበቡ ቤታችሁን አያለሁ››
‹‹አዎ ››
ከዛ በኃላ ብዙም ያወሩት ነገረ የለም ፡፡ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡
‹‹አላዛር እና ሰሎሜ በአንድ መኪና ገብተው ወደቤታቸው እየተጓዙ ወሬ ጀመሩ‹‹ግን እርግጠኛ ነህ..?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ምኑን?››
‹‹ማለቴ የሁሴን እኛ ቤት ማረፍ….ነው ወይስ አንድ ሁለት ቀን እኛ ጋር ካደረ በኃላ ሌላ ማረፊያ ፈልግ ልንለወው ነው፡?››
‹‹ለምን …አንቺን ካልደበረሽ እቤታቸን ሰፊ ነው…ሁሴን የማናውቀው ሰው አይደለም ….ለሁለታችንም ቅርብ የሆነ ሰው ነው፡፡››
‹‹ገባኝ….በደንብ አስበህበታል ወይ ለማለት ነው…?.እኔማ ደስ ይለኛል..ግን እወቅ እንደነገረኝ ከሆነ እስከሶስት ወር ሊቆይ ይችላል፡፡››
‹‹ችግር የለውም..ታውቂያለሽ የሆነ የእኛ የምንለው ሰው አብሮን እንዲኖር እንዴት እፈልግ እንደነበረ…እህቶቼም ሁለቱም ስላገቡ ወደቤታችን ላመጣቸው አልቻልኩም…የአንቺም እናት አሻፈረኝ ብላለች..እስኪ አሁን በጓደኛችን እንሞክረው፡፡››
‹‹እማዬ እኮ ከእናንተ ጋር አልኖርም አላለችም..እሷ ያለችው ልጅ ስትወልዱ እሱን ለማሳደግ መጣለሁ…አሁን ግን መጥቼ የእናንተ ሞግዚት መሆን አልፈልግም ነው ያለችው››።
‹‹እና በሞግዚት ኑሪ እንጂ ሞግዚት ሁኚን መች አልናት?››
‹‹ተወው አሁን… ለምን የማይሆን ጭቅጭቅ ውስጥ እንገባለን…ቁርጥ አድርጋ አቋሟን አሳውቃለች…መውለድ ስንችል ትመጣለች››
‹‹ይሁን እሺ… ለማንኛውም ስለሁሴን አትጨነቂ… ሁኔታዎች ካልተመቹት እኮ እራሱ አማራጭ ይፈልጋል፡፡››በማለት የተጣመመውን ርእስ እንደምንም ብሎ አቃናው፡፡
‹‹ጥሩ..ለእኛም ከብቸኝነት ጋር ከመታገል በተወሰነ መንገድ ይታደገናል…›› ስትል መለሰች፡፡
‹‹እኔም እሱን አስቤ ነው ››አላት..ግን ሁለቱም ስጋታቸው ሌላ እንደሆነ ግልፅ ነው…ሁሴን ልክ እንደአላዛር ሁሉ የሰሎሜ የልጅነት አፍቃሪዎ እንደሆነ ሁለቱም ያውቃሉ፡፡ለሁለቱም እኩል ጓደኛቸው ቢሆንም ለእሷ ግን በተለየ መልኩ አፍቃሪዋም ጭምር ነው…እና አሁን አንድ ቤት እሱን ጎትቶ ማምጣት ለዛውም አሁን ባልና ሚስቶቹ ባሉበት ሁኔታ ላይ አደጋ እንዳለውና የልታሰበ መዘዝ ሊያመጣ እንደሚችል…ለሁለቱም ግልፅ ነው….እና ሰሎሜ ደጋግማ ስለውሳኔው እርግጠኝነት እየጠየቀችው ያለው..ነገ አንድ ነገር ቢከሰት ኃላፊነቱን እንዲወስድ በማሰብ ነው፡፡
እሷ ያላወቀችው ግን የእሱን እቅድ ነው…እሱ ሁሴን ወደቤት እንዲመጣ ሲወስን መዘዙንም አስቦና አስልቶ ነው፡፡ምን አልባት የጀመረው የህክምና ጉዳይ ባይሳካለት ሊያደርግ የሚችለውን እቅድ አስቦና አስልቶ ጨርሷል..በቃ እራስ ወዳድ መሆን እንደሌለበት ገብቶታል…እየወደደም ቢሆን ከሰሎሜን ህይወት ሾልኳ መውጣት እንዳለበት ወስኗል.. ከህይወቱ ሲሸኛት ግን በተሰበረ ልብ ሆና ስነልቦናዋ ተጎድቶ መሆን እንደሌለበትም ነው የሚያምነው..ለእሱ መሆን ካልቻለች ከሁለት የልጅነት ጓደኞቾና ከልብ ከሚያፈቅሯት መቼም ቢሆን ሊጎዶት ለማይችሉት ለአንዱ ሊያስረክባት ነው ያሰበው….ለዛም ጥሪጊያ መንገድ ለመፍጠር ሁሴን በእንግድነት እሱ ቤት ማረፍ እንዳለበት ማድረግ እንዳለበት ተሰምቶታል፡፡፡ያንን ካደረገ ደግሞ አለማየሁም በተደጋጋሚ ወደእሱ ቤት ለመመላለስና ከሰሎሜ ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ የመገናኘት እድል ይኖራዋል፣በሂደት ከሁለት አንዱ ከእሷ ጋር በተሻለ መቀራረብ ይፈጥሩና ልቧን ማግኘት ይችሉ ይሆናል….ከዛ አንዱ ያገኛታል ማለት ነው፡፡ከዛ እሱ ሀዘኑን ለብቻው ያዝናል..ማጣቱን በማስታመም ቀሪ የብቸኝነት ዘመኑን ይገፋል…….፡፡እግዚያብሄር ቀንቶት ከተፈወሰ ደግሞ በቃ ምን ይፈልጋል…እና አሁን እያደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት ነው፡፡ይሄ ነው ሰሎሜን ያልገባት፡፡
ይሄ ጉዳይ ደግሞ ከሰሎሜ ይልቅ አለማየሁን ነው ፍፅም ግራ ያጋባው‹‹ሰውዬው ምን እየሰራ ነው?››የሚለው ሀሳብ በውስጡ መጉላላት የጀመረው ገና ከእነሱ እንደተለየ ነው፡፡እና ደግሞ አልተመቸውም….በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ወሳኝ ወቅት የሁሴን ወደሀገር ቤት ተመልሶ መምጣት ደስ አላሰኘውም ነበር፡፡፡በእሱ እምነት አላዛር ካልተሳካለት ቀጥታ ሰሎሜን የእሱ የማድረጉን ትግል በብቸኝነት ለመወጣት ነበር ዕቅዱም ምኞቱም..ሁሴን ደውሎ እንደሚመጣ ከነገረው በኋላ ግን ሌላ ተፋላሚ እየመጣበት እንደሆነ ነው ወዲያው የገባው…እንደውም መምጣቱ እራሱ ያጋጣሚ ነገር ሳይሆን ሆነ ብሎ የታሰበበት እንደሆነ ነው የሚጠረጥረው…ሰሎሜ አላዛርን ከማግባቷ በፊት ከእሱ ጋር ለረጅም ጊዜ እንደምትደዋወል ነግራዋለች..በእሷ እና በባሏ መካከል ያለውን ቦንብ ሚስጥር ለእሱ በተገናኙበት በመጀመሪያው ቀን ከነገረችው…ለረጅም ጊዜ ስትደዋወል ለነበረው ለዛውም ከባህር ማዶ ላለው ሁሴን ላትነግረው የምትችልበት ምክንያት ምንም እየታየው አይደለም…እንደጠረጠረው ነግራው ከሆነ ደግሞ በተለይ የሰሞኑን ግር ግር አብራርታለት ከሆነ የሆነ ምክንያት ፈጥሮ አጋጣሚውን ለመጠቀም እንደመጣ ነው የሚያምነው..እና ከእሱ ጋር

👍60❤14😁4
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
‹‹ጋሽ ፍሰሀ..አንተ ነህ…?››
‹‹አዎ አለም…እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?››አውሬው ካስደነገጠው በላይ የእሷ በዚህ ሰዓት እዚህ አካባቢ መገኘት አስደነገጠው፡፡
‹‹እንዴ ስልክ እያወራን ነበር እኮ የተቆረጠው….መኪናህ እንደተገለበጠች እርግጠኛ ስለነበርኩ ወዲያውኑ ወደእዚህ የመጣሁት…መኪናህን ቀድሜ ባገኛትም ውስጡ የለህም..ግን የሚንጠባጠበውን ደም እየተከተልኩ ደረስኩብህ››
‹‹ስሩ ደርሳ ደገፈችው››
‹‹አብሮሽ ማን አለ?››
‹‹አረ ማንም የለ….መንገድ ላይ ሆኜ ለጁኒዬር ደውዬለታለው..ይሄኔ እየመጡ ይሆናል፡››
‹‹ይገርማል..የሆነ ነገር ቢያጋጥምሽስ?››
‹‹ሀሳቤ ሁሉ ያንተን ደህንነት ማረጋገጥ ላይ ስለነበር እሱን አላሳብኩትም ነበር…እውነቱን ንገሪኝ ካልከኝ ግን አሁን በፍራቻ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡››
‹‹በጣም ነው ያስገረምሺኝ..አይዞሽ አሁን አምስት ደቂቃ ነው ደርሰናል….እንደውም እዛ መብራት ጭልጭል የሚልበት ቦታ ይታይሻል …?እዛ ነው ጎጆው…በአቅራቢያው የእኔ ሰራተኞች ቤትም አለ…››
‹‹ በአንድ እጇ ደግፋው በሌላ እጇ ደግሞ የስልኳን ባትሪ ከፊት ለፊት እያበራች ወደፊት በዝግታ መራመዳቸውን ቀጠሉ፡፡
አቶ ፍሰሀ ከአውሬው ጋር የነበረው መፋጠጥ አሁንም ከምናብ ሊደበዝዝ አልቻለም… ልቡ ለምን እንዲህ ከመጠን በላይ መታ? ጉዳዩ ምን ነበር? የዱር አውሬው በጣም አስፈርቶት ነው? አይደለም፡፡ እሱ ስለእነሱ አላሰበም። በህይወቱ የበለጠ አስፈሪ ነገሮችን አሳልፎ ያውቃል። ወዲያው ከኃላቸው እየተንሾካሾኩ የሚመጣ የእግር ኮቴ ሰሙ…መንገዱን ለቀቁና ጢሻውን ተከልለው ቆሙ..ሲጠጎቸው ማንነታቸውን በድምፅ ለዩ…‹‹ገመዶ››
ባትሪውን ሲያበራባት ፈጽሞ እዚህ አገኘዋለሁ ብሎ ያላሰበውን አቶ ፍሰሀን በአለም ተደግፋፎ ልክ እንደተወዳጅ ልጁ ስሩ ተሸጉጣ ሲያይ አይኑን ማመን አልቻለም፡፡
ሁሉም ተንደርድረው ከበቧቸው‹‹ጋሼ ምን እየተካሄደ ነው?››
‹‹አይዞችሁ አትደንግጡ… ተርፌለው››
‹‹ተርፌለው ማለት?››ኩማንደሩ በመገረም ጠየቀ፡፡
‹‹የመኪና አደጋ እንደደረሰብኝ ሰምታችሁ አይደለም እንዴ የመጣችሁት?››
‹‹አረ በፈጣሪ..ተርፍክ ታዲያ…?እኛ አልሰማንም..እሷን ከከተማ ስትወጣ አይተን ተከትለናት ነው የመጣናው…ከጠላቶቻችን ጋር ልትገናኝ መስሎን ነበር››
‹‹አይ እሷ እኔን ለማትረፍ ነው የመጣችው››
‹‹እንዴት ከእኛ ቀድማ ልትሰማ ቻለች?..ነው ወይስ በአደጋው ላይ የእሷ እጅ አለበት?››
‹‹እሱን ጎጆው ጋር ደርሰን ትንሽ ካረፈ በኃላ ብትጠይቀው አይሻልም?››አለችው አለም በንዴት፡፡
‹‹ለምን ወደጎጆ እንሄዳለን? መኪናችንን እኮ በቅርብ ርቀት ላይ ነው ያቆምናት..እዚሁ ጠብቁኝና ይዣት ልምጣ..ቀጥታ ወደከተማ ሄደህ ህክምና ማግኘት አለብህ››
‹‹አይ ደህና ነኝ..አሁን ማረፍ ነው የምፈለገው..ወደጎጆ ውሰዱኝ››
‹‹ተው እንጂ ፍሰሀ ..ሀኪም ሊያይህ ይገባል››ዳኛው ጣልቃ ገብተው ለኩማንደሩ ድጋፋቸውን ሰጡ፡፡
‹‹የበለጠ እያደከማችሁኝ መሆኑን ልብ አላላችሁም እንዴ..?ወደጎጆ መሄድ ነው የምፈልገው›› በማለት የማይቀየር አቋማቸውን አሰሙ፡፡
‹‹ይቅርታ ጋሼ..አንተ ካልክ እሺ ወደጎጆ እንወስድሀለን….እነ ጁኒዬርም አሁን ደውለውልኝ ነበር …መገንጠያው ጋር ደርሰዋል….ከደቂቃዎች በኃላ ይደርሳሉ..››አለና ሄዶ በሌላ ጎኑ አቶ ፍሰሀን ደገፈ….ከ5 ደቂቃ በኃላ ጎጆዋ ደረሱ፡፡ፋኖስ አበሩ፣ መኝታው ተስተካክሎ እንዲተኛ ተደረገና በቅርብ ርቀት ያሉ ሌላ የሳር ቤት ውስጥ ወደሚኖሩት የእነሱ ሰራተኞች ተቀስቅሰው መጡ..እሳት እንዲቃጣጠል ተደረገ…ጁኒዬርና ሳራ የመጀመሪያ ለእረዳታ መስጫ የሚያለግሉ ቁሳቁሶች ይዘው እያለከለኩ ደረሱ…ለተወሰነ ጊዜ ለቅሶና ግርግር በጠባቧ ጎጆ ነገሰ..ከዛ ቀስ በቀስ ወደመረጋጋት ቢመጣም በሰው ብዛት በታፈነችው ጎጆ ውጥረትና ጭንቀት ነግሶ ነበር፡፡
‹‹ቆይ እኔ ያልገባኝ…ምንድነው የሚያስጠብቀን..?ለምንድነው ወደከተማ ይዘነው ሔደን ሀኪማ የማያየው?››ሳራ ነች ግራ በመጋባት ተመሳሳይ አይነት ጥያቄ ለሶስተኛ ጊዜ ያነሳችው፡፡
‹‹ጋሼ አልፈልግም ስላለ እኮ ነው…ጋሼ አሁን ትንሽ አርፈሀል፣ብንሄድ ምን ይመስልሀል?››ኩማንደር ነው ተናጋሪው፡፡
‹‹አይ ዛሬ ማንም ከዚህ አይሄድም…አሁን ሰዎቹን ሸኞቸውና የምንነጋገረው ነገር አለ››ሲል ሁሉም በቀጣይ ምን ሊፈጠር ነው በሚል እርስ በርስ ተያዩ፡፡
ጁኒዬር ከጎረቤት ጎጆ የመጡትን ባልና ሚስቶች ከነልጆቻቸው አመስግኖ ወደቤታቸው እንዲሄዱ ካደረገ በኃላ የጎጆዋ ቤት ተዘጋ፡፡አሁን ስድስት ሰዎች ፊት ለፊት ተፋጠጡ …ሁለቱ ሴቶች እና አዛውንቱ ዳኛ አቶ ፍሰሀ ጎን የተቀመጠችውን አለምን በከፍተኛ ጥላቻን መጠየፍ ነበር የሚመለከቷት፡፡
አቶ ፍሰሀ ከትራሱ ቀና አደረገና አስተካክሎ በመደገፍ መናገር ጀመረ‹‹ዛሬ እየሆነ ያለው ሁሉ ነገር ተአምር ነው…እኔ እቅዴ እንደማንኛውም ቀን ስራ ውዬ ወደቤቴ መግባት ነበር….ነገር ግን የሰሞኑን ውጣ ውረድ እያሰላሰልኩ ሳላስበው ከከተማ ወጣሁና እራሴን እዚህ ሶሌ ደን አካባቢ አገኘሁት..እንዴት እዚህ ልደርስ ቻልኩ? ብዬ እየተገረምኩ ሳለ ያልጠበቅኳት አለም ደወለችልኝ..ከእሷ ጋር እያወራው ሳለ ድንገት ሳላስበው አውሬ ገባብኝና እሱን አድናለው ስል መኪናዬ መንገድ ስታ ተገለበጥኩ…እንደአደጋው መሞት ነበረብኝ..ግን ከተወሰነ ጭረት በስተቀር ምንም አልሆንኩም…እግዜር አሳይቶ ከሞት ደጃፍ መለሰኝ..ከመኪናው ወጥቼ በጫካው እያሳበርኩ ወደእዚህ እየመጣው ሳለ ከጅብ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጥኩ…እሱንም ወደሰማይ ተኩሼ አስበረገግኩትና ሁለተኛውን ፈተና አለፍኩ..ከዛ ወዲያው አለምን ከፊት ለፊቴ አገኘኃት..ወዲያው እነ ገመዶና መጡ…ጎጆው እንደደረስን ደግሞ ልጄና ባለቤቴ መጡ …እኔ ለማናችሁም አደጋ ደረሰብኝ ብዬ አልደወልኩም..በአደጋው ጊዜ ስልኬ ወደየት እንደጠፋም አላውቅም..ግን ሁላችሁም እዚህ ተገኝታችኃላ..ሁላችንን እዚህ ያለነው ለምክንያት ነው፡፡ከአለም ጋር የጀመርነው ድብብቆሽ እዚህ ጋ ማብቃት መቻል አለበት፡፡
‹‹አዎ ማብቃት አለበት …ይህቼ ሴት ከዚህ በፊት ንብረቴ እንዲቃጠል አደረገች… ዛሬ ባለቤቴን ገድላብኝ ነበር….››ሳራ ተንዘረዘረች…ዳኛውና ስርጉት አይናቸውን በማጉረጥረጥ እና በመገላመጥ ለሳራ ያላቸውን እገዛ አሳዩ ፡፡
‹‹ሳራ ተይ ..ዛሬ የምንበሳጭበትና ራሳችንን ሀጥያት ለመሸፈን ሌላ ስው በሀሰት የምንወቅስበት ቀን አይደለም..እኔ አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሁለት ሞት ነው የዳንኩት…ይሄ ያለምክንያት አይደለም..ይህቺን ልጅ ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በድለናታል…ሁላችንም ለእሷ መናዘዝ መቻል አለብን..እውነቱን ልንነግራት ይገባል..ከዛ አመዛዝና ከፈለገች ትበቀለን… ከፈለገች ደግሞ ወደፍትህ አደባባይ ወስዳ ታሰቅለን፡፡
የአቶ ፍሰሀን ንግግር የሰሙት ዳኛው ጫንቃቸውን አላባቸው፡፡ይሄ ሰውዬ በተገበጠበት ወቅት ጭንቅላቱን ተመቶ ማሰቢያው ላልቶ ይሆን እንዴ?››ሲል አሰበና አይኑን ገመዶና ጁኒዬር ላይ አንከራተተ…የሆነ ነገር ብለው የጀመረውን ቅዠት የመሰል ድርጊት እንዲያስቆሙት ነው ፍላጎቱ.

❤45👍4