#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን
===================
ቀለል ያሉ ሌሎች ጫወታዎችን ሲጫወቱ አመሹና እቤቷ ድረስ ሸኝቷት በብዙ ነገር ተወስውሶ ወደቤት ተመልሶ ገባና የወንደላጤ ቤቱን ከፍቶ ባዶ ቤት ውስጥ ባዶ አልጋ ላይ ብቻውን ተኝቶ ማሰላሰል ጀመረ፡፡
ሰሎሜ ደጋግማ እንደጠየቀችው..ከተማውንም ሆነ ሁሉንም ጓደኞቹን ድንገት ጣጥሎ ፖሊስ ማሰልጠኛ የገባበት የራሱ የሆነ ምክንያት አለው..በቂና ጠንካራ ምክንያት ነበረው::
አለማየው የፈራረሰና ጣሪያው የዛገ ባለአንድ ክፍል ቤት ውስጥ ከእናትና አባቱ እና ከታናሽ ወንድሙ እና የሴት አያቱ ጋር የድህነት ግን ደግሞ ጣፋጭ ሳቅና ደስታ የሞላበት ኑሮ ይኖር ነበር፡፡ነበር እንዲህ ህልም ሆኖ አይን ጨፍኖ ሲገልጡ እንደሚበን ማሰብ ይከብደል፡፡ያ ሞቀትና የደመቀ… በፍቅር ሀውልት የተገናባ የቤተሰብ ትስስር በአንድ ወር ውስጥ ነው ድርምስምሱ ወጥቶ የፈረሰው፡፡በወቅቱ እሱ የ13 አመት ወጣት እና የ7 ክፍል ተማሪ ነበር፡፡ድንገት አባትዬው ታመምኩ አለና አልጋ ያዘ፡፡በሶስተኛው ቀን ሰፈር ያለ ጤና ጣቢያ ወሰዱት ፡፡አንድ ቀን አድሮ እስከወዲያኛው አሸለበ፡፡ ያልተጠበቀ ስለነበረ ሁኔታው ጠቅላላ ለቤተሰቡ እንደመቅሰፍት ነበር ፡፡በተለይ ለእናቱ…፡፡አባትዬው በሞተ በማግስቱ ተቀበረ፡፡ከቀብር መልስ እናትዬው ወደ ድንኳን ውስጥ ገብታ በተነጠፈላት የሀዘንተኛ ፍራሽ ላይ ተቀምጣ ሊያስተዛዝኗት የመጣውን የሩቅም ሆነ የቅርብ እንግዶችን በመቀበል ፋንታ ወደቤት ገብታ ከባሏ ጋር ትተኛበት የነበረበት አልጋዋ ላይ ገብታ ጥቅልል ብላ ተኛች፡፡.በሶስተኛው ቀን እስትንፋሷ በውስጧ አልነበረም…፡፡ጉድ ተባለ..፡፡ፍቅር እስከመቃብር….ማለት ይሄ ነው ተባለ…፡፡
የአለማየሁና የወንድሙ እጣ ፋንታ ግን በደካማና እድሜዋ በጋፋ ተጦሪ አያቱ እጅ ነበር የወደቀው፡፡፡ድሮም የድህነት መቀመቅ ላይ የነበረ ቤተሰብ ውሉ የጠፋበት ሆነ፡፡ ምርጫ አልነበረም፡፡አለማየሁና ታናሹ ለመለያየት ተገደዱ፡፡አያትዬው ጎንደር ለሚኖር ሌለኛው ልጃቸው..‹‹ቢያንስ አንደኛውን ልጅ ውሰድልኝ ››ብለው ተማፀኑት..አጎትዬው ታናሹ ይሻለኛል ብለው መረጡና እሱን ወሰዱት፡፡አለማየሁና አያትዬው ቀሩ..፡፡ይሄ ሁሉ ሲሆን ግድግዳ ሚጋሩት ቀጥሎ ካለው የቀበሌ ቤት የሚኖሩት ሰሎሜና እናትዬው ከጎናቸው ነበሩ፡፡በማፅናናቱም ካላቸው ላይ ቆረስ እያደረጉ በማጉረሱም አልተለዬቸውም ነበር፡፡ከዛ አያትዬው ሁለመናው ጭልምልም ሲልባቸው.የሰሎሜ እናት እቴቴን ፊት ለፊታቸው አስቀምጠው‹‹ …እኔ በቃኝ፡፡ ለራሴ ማልሆን ሰው የልጅ ልጄን ጠቅመዋለው ብዬ እዚህ አልቀመጥም…፡፡ጭራሽ ሸክም ነው የምሆንበት፡፡አንቺ ለእናቱ ጎደኛዋ ነበርሽ…አለማየሁንም ልክ ከሰሎሜ እኩል አንቺም አሳድገሽዋል ፡፡..ልጅሽ ነው…፡፡አሁንም አንቺው ነሽ ምታጎርሺን.. ስለዚህ እኔ የልጅ ልጄን ላንቺ ጥዬ ወደ ገዳም መሄዴ ነው…ባይሆን እዛ ሄጄ ፀልይልሻለሁ››በማለት አለማየሁን ለሰሎሜ እናት ጥለውት ጠቅልለው ገዳም ገቡ፡፡አለማየሁ ብቻውን ቀረ …፡፡
ከዛ ሁሉ ከሞላ ቤተሰብ አመት ባልሞላ ጊዜ ቀስ በቀስ እየበነኑ ጥለውት በመሄዳ ባዶውን አስቀሩት፡፡ በቃ ባዶውን…፡፡ግን ሰሎሜና እናትዬው ከመጠን በላይ እንዲሰበርና አልፈቀዱለትም፡፡ለሰሎሜም እህት ለእሳቸውም ሁለተኛ ልጅ ሆነ ፡፡በመሀከል የሚያዋስናቸውን ግድግዳ ቀደው የውስጥ ለውስጥ በር አበጁለትና አንደኛውን በር ዘጉት፡፡ሁለት የተለያ ክፍል የነበረው ቤት ሁለት ክፍል ያለው አንድ ቤት ሆነ፡፡
እሱ ከትምህርት ቤት በተረፈው ጊዜ ሰፈር ውስጥ እየተሯሯጠና እየተላላከ በሚያገኘው ብር እራሱን መደጎም ቀጠለ፡፡የሰሎሜ እናት በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የመዝገብ ቤት ሰራተኛ ስለሆኑና ቆሚ ደሞዝ ስላላቸው..ምንም እንኳን የተትረፈረፈ ኑሮ ባይኖራቸውም ለሁለቱ ልጆችና ለእራሳቸው ለለት ጉርስ የሚቸግራቸው አይነት ሰው እልነበሩም…አለማየሁን ከልጃቸው እኩል ለማኖር የእለት ጉርስንና የአመት ልብሱን ለመሸፈን ቸግሯቸው አያውቅም፡፡በዛ ላይ አለማየሁን ከልጅነት ጀምሮ ሚወዱትና ከእናትዬው ጋር ካላቸው ቅርበት የተነሳ ብቸኛ ልጃቸውን ክርስትና የነሳቸው የእሱ እናት ስለሆነች ልጄ ወንድም ይሆናታል በሚል አመለካከት ከልባቸው ነበር የተቀበሉት፡፡በዛ ላይ ከዚህ በፊት ልጃቸው በህይወትና በሞት መካከል ሆና ሆሲፒታል በገባች ጊዜ ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እሷን ለማትረፍ ያደረጉትን ታሪካዊ ድርጊት መቼም አይረሱትም…እናም ደግሞ ለሌላ ለማንም ሰው የማይነግሩት ተጨማሪ ዋና ምክንያትም ነበራቸው፡፡
.ከዛ ቀስ በቀን ከሰሎሜ ጋር ያለውን ግንኙነት እያላላ ከእናትዬውን ግን በወጉና በስርኣቱ በስልክ እየጠየቀ ስልጠናውን ጨርሶ በምክትል መቶ ሀለቅነት ተመረቀ..ከዛ አዲስ አበባ አካባቢ የመመደብ እድል ቢኖረውም በራሱ ምርጫ ድሬደዋ እንዲመድቡት አድርጎ እርቆ ሄደ፡፡ይሄንን ታሪክ ሰሎሜ ሆነች ሌሎች ጓደኞቹ አያውቁም..አይደለም በዛ ጊዜ ዛሬም እንዲህ ነበር ብሎ ሊነግራትና ሊያብራራላት አይችልም….ከባድ ነው፡፡በሀሳብ ሰውነቱ ስለዛለ ለመተኛት ወደ መኝታ ቤቱ ሄዶ …ድንገት ሳያስበው የአላዛር ምስል በአእምሮ ተሰነቀረ፡፡
‹‹አሁን አላዛር ህክምናው ባይሳካለትስ…?ሰሎሜ ወደፍርድ ቤት ጉዳዩን ይዛ እንድትሄድ መክራታለው ወይስ ምን አደርጋለው….? ፍርድ ቤቱ እንዲፋቱ ከወሰነስ በኋላ ከእሷ ጋር ያለኝ ግንኙነት እንዴት ነው የሚሆነው…?አሁን ሳይቸግረኝ ሳፈቅራት እንደኖርኩና አሁንም እንደማፈቅራት ነገሬታለሁ…እና በቀጣይ ፡፡ ርቃታለሁ ወይስ የበለጠ ከእሷ ጋር ያለኝን ጓደኝነት አጠናክራለሁ….?እና ከዛስ…አሁን ተራው የእኔ ነው አግቢኝ እላታለሁ? ወይስ ?››..እራሱን አመመው፡፡
ስለምንም ነገር ማሰብ አቁሞ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ለመተኛት በመፈለግ የለበሰውን ልብስ አውልቆ ቢጃማ እየቀያየረ ሳለ ስልኩ ድምጽ አሰማ..አነሳውና አየው… መልዕክት ነው፡፡ሰሎሜ ነች የላከችው፡፡
‹‹አሌክሶ ..በሰላም እቤት ገባህ..?››ይላል፡፡
‹‹አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለና መልስ ፅፎ ላከላት‹‹አዎ….ቢራ ቢሮዋ ሰላም ገብቼለሁ?››
ከልጅቷ ጀምሮ በጣም ቀጭን እና በንፋስ ግፊት በአየር ላይ ተንሳፋ የምትበር ስለምትመስል ቢራቢሮ የሚል ቅፅል ስም አላት…ብዙውን ጊዜ እሱ በዚህ ስም ነው የሚጠራት፡፡
‹‹ጥሩ…ደስ የሚል ምሽት ነበር ያሳለፍነው…አመሰግናለሁ››
‹‹እኔም የልጅነት ጊዜዬን ወደኋላ ተመልሼ እንዳስታውስ ስላደረግሺኝ ደስ ቢለኝም የተዳፈነ የልጅነት ፍቅሬን ስለቀሰቀሺብኝ ችግር ላይ ነኝ፡፡››ብሎ ፃፍላና ላከላት፡፡
‹‹አንተ ባለትዳር እኮ ነኝ…ለምን ታሽኮረምመኛለህ?››
‹‹ይቅርታ ምን ላድረግ..?እንደምታውቂው ፍቅር ይሉኝታ ቢስ ስሜት ነው፤ለማንኛውም አላዛርን ሰላም በይልኝ››
‹‹አይ …እራስ ደውለህ ሰላም በለው፤.ሌላ ነገር እንዲያስብ አልፈልግም…በመጀመሪያ ጉዳዩን ስለነገርኩህ እራሱ በጣም ቅር ብሎታል?፡፡››
‹‹አይ ታዲያ ምን ማድረግ ትችይ ነበር..?እስከመቼ ለብቻሽ በጉዳዩ መሰቃየት ትችያለሽ?››
‹‹አየህ አንተ ከልጅነቱ ጀምሮ የምታውቀው ጓደኛው ነህ.. ሁለታችሁም በጋራ የምታውቋቸው በርካታ ሰዎች አሉ ....ይሄንን ጉዳይ አንተ አወቅከው ማለት ሌሎች እሱንና አንተን የሚያውቁ ሰዎችም የማወቅ እድል ይኖራቸዋል ማለት ነው. .ይሄ ደግሞ ስነልቦናውን ይበልጥ ይጎዳል…..በዛ ላይ እንደምታውቀው የእናንተ የወንዶች ኢጎ ከፍተኛ ነው፡፡››

👍65❤6👏2
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
///
እሱ በራፉን ለመክፈት ሲሄድ አለም ቶሎ ብላ ቦርሳዋ ውስጥ ገባች እና በጣም የሚያምር ውድና ጌጠኛ ብእር አወጣችና ወደቤቱ በራፉ ፊት ለፊት በመወርወር ወደፊት ራመድ ብላ እስኪመለሱ መጠበቅ ጀመረች፡፡
‹‹እ..ሰላም ነው..?ስልክህ አይነሳም፡፡››አቶ ፍሰሀ ነው ተናጋሪው፡፡
‹‹ውስጥ ቻርጅ ላይ እርጌው አላየሁትም…ግባ››ኩማንደሩ መለሰለት፡፡ ወደውስጥ ሲገባ አለምን ስላያት ነገሩ ገባው፡፡
‹‹እንዴት ነህ አቶ ፍሰሀ?››
‹‹ሰላም ነኝ…አንቺስ?››
‹‹አለሁ..››አላችና ‹‹በሉ እንግዲህ መሄዴ ነው››ስትል አከለችበት፡፡
‹‹ምነው ..እኔ ስመጣ ነው እንዴ ምትሄጂው?››
‹‹አይ መጀመሪያውኑም ለመሄድ ስል ነው የመጣሀው…ጉዳዬን ጨርሼለው..ተራውን ለአንተ ልልቀቅ፡፡››አለችና ሁለቱንም ተሰናብታ ወጣች፡፡
ገመዶ እና አቶ ፍሰሀን አስከትሎ ወደውስጥ ለመግባት ሲራመድ በራፉ ጋር ሲደርሱ አቶ ፍሰሀ ጎንበስ አለና አይኑ የገባውን ብዕር አነሳ፡፡
‹‹ይሄን የመሰለ ብዕር ትጥላልህ እንዴ?››ብሎ ወደ ኩማንደሩ ዘረጋለት፡፡ኩማንደሩ ተቀብሎ አገላብጦ ተመለከተውና‹‹ወይ የእኔ አይደለም…የአለም መሰለኝ›››አለና ስልኩን አውጥቶ ደወለላት፡፡
‹‹ሄሎ››
‹‹ ምነው ከአሁኑ ናፈቅኩህ እንዴ?››
‹‹ባክሽ ሌላ ቦታ ጥዬዋለው ብለሽ እንዳትፈልጊ ነው…አንድ ብዕር ጥለሽ ሄደሻል..ካልራቅሽ ተመለሺና ውሰጂው››
‹‹ወይ እንዴት ጣልኩት…?ለማንኛውም በጣም ከምወደው ሰው የተሰጠኝ ስጦታ ነው…ከኪስህ እንዳይወጣ …ስንናኝ ትሰጠኛለህ››አለቸው፡፡
‹‹እሺ ቻው››አለና ስልኩን በመዝጋት ብእሩን ደረት ኪሱ ውስጥ ሻጠውና ከአቶ ፍሰሀ ጋር ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ….
‹‹ቢራ ልክፈትልህ››
‹‹በጣም ደስ ይለኛል››
ለሁለቱም ቢራ ከፈተና ፊት ለፊት ተቀመጠ፡፡
‹‹መጥፎ ሰዓት ነው እንዴ የመጣሁት?››አቶ ፍሰሐ ጠየቀ፡፡
‹‹አይ እንደውም በተቃራኒው ጥሩ ሰዓት ላይ ነው የመጣሀው..በጣም አደጋ ላይ ነን››
‹‹ማለት››
‹‹ይህቺ ልጅ ከጠበቅኳት በላይ አደገኛ ነች…ሳታጠፋን አርፋ አትቀመጥም….››
‹‹ማለት….አንተ እንዲህ ካልክ ነገሮች ከባድ ናቸው ማለት ነው››
‹‹አዎ…ስለእያንንድ የሶሌ ኢንተርፕራይዝ የአክሲዬን ድርሻ…ማን ስንት ፐርሰንት እንዳለው…አክሲዬኑ መቼ እንዳገኘነው….ዝርዝር መረጀ አላት፡፡››
አቶ ፍሰሀ ልብ ምቱ በደቂቃ ውስጥ ሲጨምር ታወቀው….
‹‹ምን እያልከኝ ነው?››
‹‹አዎ….የእናቴን ሞት ተከትሎ የአንዳችሁ አክሲዬን ተቀንሶ ለሌሎቻችሁ የተጨመረው ለምንድነው ብላ ጠየቀችኝ…?፡፡››
‹‹ይሄ እኮ ወደእውነት እየቀረበች መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡››
‹‹አዎ…አንድ ውሳኔ መወሰን አለብን፡፡››
አቶ ፍሰሀ ወዲያው ስልኩን አወጣ…መጀመሪያ ዳኛ ዋልልኝ ጋር ደወል…አሁኑኑ ወደቤት እንዲመጣ ነገረውና ስልኩን ዘግቶ መልሶ ልጁ ጁኒዬር ጋር ደወለ..ቤት እንደሆነ ነገረው…ሳይወጣ እንዲጠብቀው ነግሮ ዘጋውና‹‹በል ተነስ እንሂድ….አሁኑኑ ተነጋግረን አንድ ነገር ማድረግ አለብን፡፡››
///
ከምሽቱ አራት ሰዓት አራቱ ሰዎች ምድር ቤት በሚገኘው የአቶ ፍሰሀ ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው ፊት ለፊት ተፋጠዋል…በጠረጴዛው መሀከል ሙሉ የውስኪ ጠርሙስ ሲኖር በመሀከላቸው ግማሽ ድረስ የተሞላ ብርጭቆ አለ….
‹‹እኔ ከመጀመሪያውም ነግሬችሁ ነበር..ይህቺን ሴት አንድ ነገር አድርጓት ስላችሁ ነበር››ዳኛው በንዴት ደነፉ፡፡
‹‹አሁን ያለፈውን ገር እያነሳን ልንወቃቀስ አይደለም የተገናኘው…አሁን እንዴት አድርገን እናሳቁማት የሚለው ነው ወሳኙ ነገር፡፡››
‹‹ለምን ሁችንም ባለንበት አግኝተናት ይሄንን ጉዳይ እንድታቆም ለመጨረሻ ጊዜ አናሳጠነቅቃትም››አለ ጁኒዬር፡፡
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ….መቼስ ልጅቷን ግትርነት ከአንተ በላይ የሚያውቅ ያለ አይመስለኝም፡፡ እኔ በበክሌ እዚህ እግሯ ከረገጠበት ቀን አንስቶ በሰላምም በማስፈራራትም ይህንን ጉዳይ እንዳታቆም ያልጠየቅኳት ቀን የለም…አንድም ቀን ሽብርክ ስትል አልሰማዋትም…ዛሬም የነገረችኝ ጉዳዩን ከማቆም መሞትን እንደምትመርጥ ነው፡፡››ሲል አስተያየቱን ያቀረበው ኩማንደሩ ነበር፡፡
‹‹እሱማ ትክክል ነህ …እኔም ያልሞከርኩበት ቀን የለም…›አለ ጁኒዬር፡፡
‹‹አዎ…ይሄ ጉዳይ አይሰራም፡፡››
ዳኛው ትእግስት አልባ በሆነ ንግግራቸው‹‹በቃ በንግግር ማስቆሙ ካልሰራ …አስወግዷታ
…መቼስ ይሄንን ስታደርጉ የመጀመሪያችሁ አይደለም››አለ ፡፡
በገመዶና በጂኒዬር ላይ የተከሰተው ድንጋጤ የተለየ ነበር…..እርስ በእርስ ተያዩ….ከዛ ሁለቱም በእኩል ጊዜ ወደአቶ ፍሰሀ ዞሩ….አቶ ፍሰሀ አይናቸው ተጉረጥርጧል…ለመናገር እየፈለጉ እየተናነቃቸው ነው፡፡ከአንደበታቸው ቃል ማውጣት የከበዳቸው መሆኑን ያስታውቃል…ከዛ እንደምንም አሉና መናገር ጀመሩ፡፡
‹‹ይሄንን ለሁላችሁም ነው የምናገረው…ለሁላችሁም….እዚህች ልጅ ላይ የመግደል ሀሳብ አይደለም አንዲት ፀጉሯን ለመንቀል ብታስቡ ቀጥታ ፀባችሁ ከእኔ ጋር ነው፡፡ማንም እጣቱን በእሷ ላይ ሊያነሳ አይችልም፡፡››
ዳኛው አይናቸውን አጉረጠረጡ‹‹ለምን ተብሎ..ለአንድ ዲቃላ ልጅ ሲባል የእኛ ህይወት መመሰቃቀል አለበት፡፡.እናንተ ማድረግ ካልፈለጋችሁ እኔ አደርገዋለው፡፡››
አቶ ፍሰሀ ልክ እንደጎረምሳ ከተቀመጡበት ተስፈንጥረው ተነሳና ከወገቡ ያለውን ሽጉጥ መዞ ሽማግሌው ዳኛ መላጣ ጭንቅላት ላይ ደቀነው፡፡
ገመዶና ጁኒዬር በርግገው ከተቀመጡበት ተነሱ‹‹እንዴ አባዬ ….!ምን እያደረክ ነው?››
‹‹አንተ ፈርሳም ሽማግሌ….ከዛሬ ጀምሮ እንደውም ለልጅቷ ጠባቂ ቀጥረህ እንቅፋት እንኳን እንዳይነካት ብታስጠብቃት ይሻልሀል….በማንም ሆነ በማን አንድ ነገር ገጠማት ሲባል ብሰማ ይሄንን ምላጭ በአንተ ጭንቅላት ላይ ለመሳብ ለሰከንድ እንኳን አላቅማማም፡፡››
‹‹ጋሼ በቃ…..ወደመቀመጫህ ተመለስ..ተረጋጋ…››አለ ገመዶ፡፡
አቶ ፍሰሀ የደቀነውን ሽጉጥ መልሶ ወደ ወገብ ሻጠው እና መደመቀመጫው ተመለሰ
…..ሁሉም በፀጥታ ማሰላሰል ውስጥ ገባ…ገመዶ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደመስኮቱ ተጠግቶ ሲጋራውን ለኮሰና እያጬሰ ማሰብ ጀመረ፡፡ሲጋራውን እንደጨረሰ ወደመቀመጫው ተመለሰና ከውስኪው አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨ በኃላ ‹‹እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ››ሲል የሁሉንም ቀልብ ሳበ፡፡
‹‹ምንድነው እንስማው››ሁሉም ተነቃቁና ኩማንደሩ የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ሆነ፡፡
‹‹የሚቀጥሉት ስድስት ወራት ወሳኝ ጊዜዎች ናቸው..ማለቴ ከጂኒዬር የምርጫ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ይሄ የክስ ጉዳይ ወደፊት ከገፋና እንዲህ አይነት ወሬዎች ህዝቡና ሚዲያው ጆሮ መግባት ከጀመሩ ነገሮች ድብልቅልቃቸው ነው ሚወጣው፡፡እንደእኔ ለተወሰነ ጊዜ ወደሆነ ቦት ዞር አድርገን ብናስቀምጣት፡፡››
‹‹ዞር አድርገን ስትል….?ግልፅ አድርገው?፡፡››
‹‹በቃ ከሰው እያታ ውጭ የሆነ ቤት ወሰድን እዛ ሁሉ ነገር እንዲሞላላት እድርገን ግን ደግሞ ከማንም የማትገናኝበትን ሁኔታ ብናመቻች ጥሩ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ጥሩ…እኔም እስከዛ ጡረታ ወጣና ከዚህ ከተማ ዞር እላለሁ››በማለት ዳኛው ቅድሚያ ተስማማ፡፡
አቶ ፍሰሀ ‹‹ጥሩ ሀሳብ ይመስላል….እንደውም ይርጋ ጨፌ የቡና እርሻችን ያለበት ቦታ ብንወስዳት ማንም ሊያገኛት አይችልም……እዛ ሁሉን ነገር እናሟላላታለን…እኛም በየተራ እየሄድን እንጠይቃታለን..መጥፎ ሰዎች እንዳልሆን እንድታምን እናደርጋለን፡፡

❤51👍8😱2
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
///
‹‹በተሰቀለው…አሁን ምንድነው የምናደርገው?››
‹‹አላውቅም…ለአባትህ ደውልለትና በአስቸኳይ ይምጣ…እዛ ይርጋጨፌ ምንም አያደርግም››
‹‹ደውዬለታለው… እየመጣነው››ሲል መለሰ ጁኑየር
‹‹ዳኛውም እየደወለልኝ ነበር››
‹‹እሱን ተወው ባክህ..ከአሁኑ በልብ ድካም እስከወዲያኛው ማንቀላፋቱ አይቀርም..ለማንኛውም እዚህ ምንም አንሰራም ..ወደቤት እንሄድ›› ተባባሉና ሁለቱም ወደ መኪናቸው በመግባት ተከታትለው ወደእነ ጁኒዬር ቤት መጓዝ ጀመሩ፡፡
በማግስቱ ጥዋት አንድ ሰዓት በሶሌ ኢንተርፕራይዝ ህንፃ የአቶ ፍሰሀ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው እየተወያዩ ነው፡፡
‹‹ያሰማራናቸውን ሰዎች ምንም ፍንጭ አላገኙም››አቶ ፍሰሀ ናቸው ጠያቂው፡፡
‹‹እዚህ ከተማ ውስጥ ያለች አይመስለኝም….እያንዳንዱን ሆቴል እና ፔንሲዬን አሳስሼለው….የለችም፡፡››ገመዶ መለሰ፡፡
‹‹ወደ አዲስአበባ ተመልሳ ሊሆን ይችላል?››
‹‹ወደዛም ሰው ልኬለው…..እንግዲህ የሚሆነውን እናያለን፡፡››
‹‹ጥሩ …ዩቲዬብ ባለቤትስ ማግኘት ችለናል…..?››አቶ ፍሰሀ ናቸው ሌላ ጥያቄ የጠየቁት፡፡
‹‹አዎ አናግሬው ነበር…የፈለገውን ያህል ብር እንደምንከፍለውና ቀጣዩን ስራ እንዳይለቅ ጠይቄው ነበር…››
‹‹እና?››
‹‹እናማ…ቀጣዩን አልሰጠችኝም…እራሷ ቀርፃ ነው የምትልክልኝ ….››የሚል መልስ ነው የሰጠኝ፡፡
እንደዛ ከሆነ እኮ አሪፍ ነው…ለልጁ ደህና ብር ስጡትና ቀጣዩን ታሪክ ልታስረክበው ስትቀጥረው ይደውልልን እና እናገኛታለን ማለት ነው››ዳኛው በአዲስ ተስፋ ተሞልተው ተናገሩት፡፡
ኩማንደር ፈገግ አለና‹‹ክቡር ዳኛ….ይሄንን ማሰብ የሚያቅተኝ ይመስልሀል?››
‹‹አይ በፍጹም እንደዛ አላልኩም….ውይይት ላይ ስለሆን የተሰማኝን በግልፅ ነው የተናገርኩት››
‹‹ጥሩ…ለልጁ ይሄንን ሀሳብ አቅርቤለት ነበር….ወዲያው ይሄንን መልእክት አሳየኝ፡፡››
‹‹ምንድነው?››
በዩቲዬብ የተለቀቀውን የወንጀል ታሪካችሁን መንደርደሪያ ስትሰሙ መጀመሪያ ምታደርጉት ወደእዚህ ዩቲዩበሩ ልጅ ጋር ሄዳችሁ በገንዘብም በማስፈራራትም ቀጣዩን እንዳይለቀውና በእሱ አማካይነት እኔን ለመያዝ እንደምትሞክሩ አውቃለው….ለዛም ነው ቀድሜ ይሄንን መልዕክት ልጁ ጋር የተውኩት፡፡አንደኛ ከአሁን በኃላ ቀጥታ ልጁን አላገኘውም .. የተቀረፀውን በሌላ መንገድ ነው ምልክለት፡፡ሁለተኛ ልጅን የምታቆሙት ከሆነ እየተቆራረጠ በአምስት ክፍል ይለቀቅ የነበረውን ለሌላ ዩቲዬበር አንዴ ሰጥቼው በአንዴ እንዲለቀቅና ነገሮች ፍርጥርጥ እንዲሉ አደርጋለው ….ያ ማለት ደግሞ ለማሰቢያ እና የተሻለውን መንገድ መምረጫ ጊዜ ያሳጣችኋላ..እንግዲህ ምርጫው የእናንተ ነው፡፡››ይላል፡፡
‹‹ምን አይነት ጉድ ልጅ ነች?››አቶ ፍሰሀ ነው የተናገረው፡፡
‹‹ብዬችሁ ነበር..አልሰማ ብላችሁ ሁላችንንም መቀመቅ ውስጥ ከተታችሁኝ….በጊዜ ትወገድ ብያችሁ ነበር፡፡››ዳኛው ተወራጩ፡፡
‹‹አንተ ቀበተት ሽማግሌ…በዚህ እድሜህ አንድ ፍሬ ልጅ ትገደል ስትል ትንሽ አይቀፍህም?››አቶ ፍሰሀ በንዴት መለሰ፡፡
‹‹አሁንማ እንድትገደል ብንስማማስ የት እናገኛታለን?በዚህ ሁሉ እድሜዬ አንተንና ኩማንደሩን በእንደዚህ አይነት ጫወታ የበለጠች ብቸኛዋ ሴት እሷ ብቻ ነች፡፡በጣም ብጠላትም በጣም የምትደነቅ ጀግና የሆነች ልጅ ነች››ሲል ዳኛው ተናገረ፡፡
በዚህ ሰዓት ድንገት የኩማንደሩ ስልክ ጠራ ..ከኪሱ አወጣና አየው…..የማያውቀው ቁጥር ነው፡፡አነሳው‹‹ውዴ በጣም ናፍቀኸኛል››
በስልኩ በእግር በፈረስ የሚፈልጋትን የአለም ድምፅ እየሰማ መሆኑን ማመን አልቻለም
‹‹አንቺ…የትነሽ ያለሽው?››
‹‹ቅርብህ ነኝ….ጁኒዬርም አብሮህ ነው አይደል?››
‹‹ምን እያወራሽ ነው?››
‹‹ሁለችሁም ናፍቃችሁኛል?››
‹‹ቀለድሽብን ማለት ነው?››
‹‹አይደለም…መቼስ ሁለታችሁንም እንደምወዳችሁ አትጠራጠሩም አይደል..?ልክ እንደእናቴ… እኔም አፈቅራኋላው፡፡››
ሁሉም አፍጥጠው ይመለከቱት ነበር‹‹እና ምንድነው የምትፈልጊው?፡፡››
‹‹ምፈልገውንማ መጀመሪያ ከተገናኘንበት ቀን አንስቶ መች ደብቄችሁ አውቃለው››
‹‹እና አሁን ምን ይሁን ነው የምትይው?››
‹‹ምንም ….እኔ አሁን እየፈለኩት ስላላው ፍትህ ወይም በቀል ላወራችሁ አይደለም የደወልኩት ..ድምፃችሁን ልሰማ ነው..እባክህ ስልኩን ለጁኒዬር ትሰጠዋለህ፣በጣም ነፍቆኛል…››
‹‹ገደል ግቢ››አለና ስልኩን ጠረቀመው፡፡
‹‹ምንድነው ..ስልኩን ለምን ዘጋህባት?››ጁኒዬር በንዴት ጠየቀው፡፡
‹‹እሷ ኮመዲ እየሰራችብን ነው..እንደናፈቅካት ተናግራ ካንተ እንዳገናኛት ነው የምትፈልገው››
‹‹ታዲያ ለምን ሳታገኛኘን?››
‹‹ምነው ?አንተም ናፍቃሀለች እንዴ?››
‹‹ተረጋጉ…ሁላችም ወደመቀመጫችሁ ተመለሱ››አቶ ፍሰሀ በመሀከል ጣልቃ ገብተው ሁሉም ወደቀልባቸው እንዲመለሱ አደረጉ፡፡
‹‹ልጆች አይታያችሁም እንዴ..?ይሄ እኮ የበቀሏአንዱ አካል ነው፡፡››
‹‹ማለት..?››ገመዶም ሆነ ጁኒዬር በአንድነት አቶ ፍሰሀ ላይ አፈጠጡ፡፡
‹‹በሁለታችሁ መካከል ቅሬታ በመፍጠር ኃይላችንን ለመበታተን እየጣረች ነው….›› ጁኒዬር ባለማመን ‹‹እንደዛ አስባ ይመስልሀል?፡፡››ሲል በጥርጣሬ ጠየቀ፡፡
‹‹ታዲያ ያንተን ስልክ እያወቀች ለምን ብላ ነው ለገመዶ ደውላ ከጁኒዬር ጋር አገናኘኝ ናፍቆኝ ነው የምትለው?››
‹‹አባዬ እውነትህን ነው….››
///
በተሰጣቸው ሶስት ቀን ውስጥ እሷን አድነው መያዝ አልቻሉም…እሷንም ቀጣዩን ክፍል በተመሳሳይ በዩቲዩብ ገፅ እንዳትለቅ ማድረግ አልቻሉም…ይሄ ሁለተኛው ግን ከመጀመሪያው በበለጠ ጫና ውስጥ ከተታቸው፡፡የከተማው የገዢው ፓርቲ ፅህፈት ቤትም ጁኒዬርን አስጠርቶ በሶሻል ሚዲያው ስለሚዘዋወረው ነገር ማብራሪያ እንዲያቀርብና በአፋጣኝ እየተሰነዘረበት ካለው ክስ ራሱ ነፃ እንዲያደርግ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው፡፡
‹‹አባዬ..ይህ ምርጫ ለምን አይቀርብኝም?››
‹‹ለምን እንደዛ አልክ?››
‹‹የፓርቲው ሰዎች እኮ ቁም ስቅሌን እያሳዩኝ ነው፡፡በአንድ ሳምንት ውስጥ በእኔና በቤተሰቦቼ ላይ እየተነዛ ያለውን ሀሚት ማጥራት ካልቻልኩ በእኔ ጉዳይ ላይ አቋም እንደሚወስዱ ነግረውኛል››
‹‹ምን አይነት አቋም››
‹‹ይመስለኛል..እጩ መቀየር የሚችሉት እስከዚህ ወር መጨረሻ ድረስ ነው፡፡እዚህ ከተማ ላይ በተቃዋሚዎች መሸነፍ አይፈልጉም ..ስለዚህ በሌላ እጩ ሊተኩኝ እያሰቡ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ወይ ነዶ..ያን ሁሉ ብር ከስክሰን እንደዚህ ጉድ እንሁን…የክልል ወዳጆቻችንም ለእኔ ደጋግመው እየደወሉልኝ ነው፡፡ልጅቷን መያዝ ካልቻላችሁ እኛ እናግዛችሁ እያሉ ነው፡፡››
‹‹እንዴት አድርገው ነው የሚያግዙን››ጁኒዬር ጠየቀ፡፡
‹‹በአካባቢው ያሉትን የከተማ የፀጥታ አካላት በማነጋገር ፍላጋው ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ ነዋ››
‹‹ታዲያ አሪፍ እድል አይደል?››
‹‹አሪፍ እድል ነው..ግን ደግሞ እገዛቸውን አልተቀበልኩም››
‹‹ለምን?››
‹‹ምክንያቱም እሷን በማደኑ ላይ የመንግስት የፀጥታ አካላት ከገቡበት ድንገት ባልታሰበ ሁኔታ ልትጎዳ ትችላለች…ያንን ሪስክ መውሰድ አልችልም››
‹‹አባዬ..እዚህች ልጅ ላይ የምታሳየው የርህራሄ ስሜት ከእለት ወደእለት እያስደመመኝ ነው፡፡የተለየ ምክንያት አለህ እንዴ?››

❤52👍7😁1