#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በማግስቱ የናፈቀው ቢሮ የገባው አራት ሰዓት አካባቢ ነበር….የማታው ስካር አንጎበሩ ሙሉ በሙሉ አለቀቀውም…አሁንም ጭንቅላቱን እየወቀረው ነው፡፡ለፀሀፊው መምጣቱን
ስላልነገራት አልገባችም…ከፍቶ ገባና ቁጭ አለ ..የሚሰራው ስራ ስላልነበረ የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው..ስልክ አውጥቶ ደወለ፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…ለሊሴ?››
‹‹ደህና ነኝ ሰለሞን…እንዴት ነው ስራ?››
‹‹አሪፍ ነው..አሁን ተመልሼለሁ…ቢሮ ነው ያለሁት››
‹‹ውይ ለምን ሳትነግረኝ..ቀድሜ ገብቼ አፀዳድቼ ጠብቅህ ነበረ እኮ››
‹‹አይ ችግር የለውም..ቢሮው አሁንም ንፅና የተስተካከለ ነው››
‹‹አዎ እሱማ በሶስት ቀን አንዴ ከፍቼ አናፍሰዋለው….እና ስራህን ጨረስክ ማለት ነው?››
‹‹አይ አልጨረስኩም…በመሀል የሶስት ቀን እረፍት ስላለኝ ነው የመጣሁት…ለመሆኑ ያንቺ ነገር እንዴት ሆነ?››
‹‹የቱ?››
‹‹የሁለቱ ፍቅረኞችሽ ነገር?››
ለሊሴ ሰለሞን ባቀረበላት ሀሳብ መሰረት ከሁለት ፍቅረኞቾ መካከል አንዱን ለባልነት ለመምረጥ ምታደርገውን ጥረት ወዲያው ነበር የጀመረችው ….መጀመሪያ ነጋዴውን ለአንድ ወር ላታገኘው እንደማትችል ነግራ ከመንግስት ሰራተኛው ጋር ነበር የቀጠለችው..ሲደውልላት ትሄዳለች..ዝም ሲላት ትደውልለታልች….ከስራ መልስ ሳታገኘው ወደቤት አትገባም…እሁድ ቢያንስ ግማሹን ሰዓት ከእሱ ጋር ነች፡፡ይበልጥ ትኩረቷን ሰብስባ ከእሱ ጋር ባሳለፈች መጠን በፊት ከምታውቀው በላይ እያወቀችው …በፊት ከምታዳምጠው በላይ እያዳመጠችው መጣች፡፡አሁን ያለበትን የኑሮ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ..
የወደፊት እቅዶቹንና እነዛን እቅዶች ለማሳካት እያደረገ ያለውን ተጋድሎም እየተረዳችና እየተገነዘበች መጣች…..እሱ ላይ ያላት ቅሬታ ባገባው እኔን አኑሮ ቤተሰቦቼንም እንድረዳ የሚያበቃኝ ህይወት ሊሰጠኝ አይችልም የሚል ነበር…አሁን ስታስበው ግን ያንን ከእሱ ብቻ መጠበቅ እንደሌለባት ነው የገባት…እሱ ባለው ቁርጠኝነት ላይ እሷ ተጨምራበት ካገዘችውና ከጎኑ ሆና አብራው ከታገለች ጎዶሎው ሊሞላ የሚችል አይነት እንደሆነ ተረድታለች…ግን ውሳኔ ላይ ከመድረሷ በፊት ለእሱ የመደበችለት ወር ተገባደደ እና ለዛኛው የሰጠችውን ተመሳሳይ ምክንያት ሰጥታ ..ለአንድ ወር ያህል ልትደውልለትም ሆነ ልታገኘው እንደማትችል ነገራ ወደነጋዴው ሄደች፡፡
በእውነት ነገዴው ጋር ልክ እንደወትሮ ሁሉ ነገር ተሰርቶ ያለቀ ሆኖ ነው የጠበቃት…ቤቱ የተዘጋጀ..እቃዎቹ የተደራጁ ናቸው…አዎ እያንዳንዱን ሀብቱንና አኗኗሩን ተራ በተራ አሳያት፣ቀጥታ እንዳገባችው ሕይወቷን ወደመስራት ሳይሆን የተሰራ ህይወት ውስጥ ገብቶ ለመኖር መሞከር ብቻ እንደሚጠበቅባት ተረዳች ፣ግን ለምን ልቧ ወደኃላ እንደሚጎትታት ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም‹‹…ታግዬ ያላሸነፉኩት በሌላ እጅ የተሰራ ህይወት ምን ትርጉም ይኖረዋል?››እራሷን ጠየቀች… መልሱ ቀላል አልነበረም….፡፡
ሁሉንም ሂደት አንድ በአንድ ዘርዝራ አስረዳችው፡፡ ሰለሞንም‹‹እና ምን ተሰማሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አሁንም እንደተወዛገብኩ ነው…ግን በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱ ጥያቄዎች በፊት ከሚመላለሱት የተለዩ ናቸው…እንግዲህ እኔ በህይወቴ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ ከፍተኛ ድክመት እንደለብኝ ነው የተረዳሁት፡፡››
‹‹አይ እንደዛ አይመስለኝም …አንቺ ቀሪ ህይወትሽን አብሮሽ በደስታ የሚዘልቅና ከቤተሰቦችሽም ጋ ተሰስማምቶ የሚያኮራሽ ለፍፅምነት የተጠጋ ባል እየፈለግሽ ነው….በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ለፍጽምና የተጠጋ ነገር መምረጥ ቀላል ነገር አይደለም፡፡አንድ ታሪክ ልንገርሽ..
‹‹ደስ ይለኛል››
ደቀ መዝሙሩ መምህሩን ‹‹ፍፁምና በህይወታችን እንዴት አድርገን ነው ፍፅማዊ የሆነ ነገር መጎናፀፍ የምንችለው? ሲል ጠየቀው ፡፡ መምህሩም አሰብ አደረገና ‹‹የዚህን መልስ
እንድነግርህ ከፈለክ በፊት ለፊት በር ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ቀጥ ብለህ ግባ ።በመንገድህ ከምታገኛቸው አበቦች መካከል በጣም የሚያምረውንና ደስ ያሰኘህን ቀንጥስና በጎሮ በር ውጣ …አንዴ ያለፍከውን አበባ ከእንደገና ወደኃላ ተመልሰህ መቅጠፍ አትችልም አሉት።›› አለው ።እሱም ትዕዛዙን አክብሮ እንዳተባለው ወደ አትክልቱ ስፍራ ገባና እስከመጨረሻው ጥግ ከተጓዘ በኃላ ባዶ እጅን በጓሮ በር ወጣ።
መምህሩ ‹‹ለምንድነው አንድ ቀንበጥ አበባ እንኳን ይዘህ መውጣት ያልቻልከው?››ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ምርጥ የተባለውን አበባ ወዲያው እንደገባሁ ነበረ ያገኘሁት... ግን የተሻለ አገኛለሁ ብዬ በማሰብ ሳልቀነጥስ ወደፊት ቀጠልኩ .. መጨረሻው ላይም ደረስኩ.. ወደኃላ የመመለስ እድል ስለሌለኝ ባዶዬን ለመውጣት ተገደድኩ›› ሲል መለሰ።
መምህሩ መልሱን ሲሰሙ ፈገግ አሉና ‹‹አዎ! ትክክል ነህ ፤ህይወት እንደዛ ነው ።ፍፁምናን ለማግኘት ይበልጥ በዳከርን ቁጥር ብኩን እየሆንክ ትሄዳለህ።እውነተኛ ፍፁምናን መቼም የትም አታገኝም።››ሲሉ መለሱለት። ‹‹ገባሽ አይደል?››
‹‹አዎ ገብቶኛል››
‹‹እንግዲያው ፍፅም በምናብ አለም ካስቀመጥሽው ወንድ ጋር የሚስማማ ባል እንደማታገኚ አውቀሽ ለሚማጡት 10 ቀናት ሁለቱንም ሳታገኚ አስቢበት..ከዛ ማንኛቸው ናቸው የበለጠ የሚናፍቁሽ..የትኛው ቢያቅፍሽ ትፈልጊያለሽ ….?ማንኛቸው የልጆችሽ አባት ቢሆኑ ይሻላል..?በህልምሽ እየደጋገመ የሚመጣው የትኛው ነው?፡፡ለ10 ቀን አስቢበት፡፡››
‹‹እሺ እንደዛ አደርገላው..ግን አሁን አሁን እየገባኝ ያለው እኔ ከባሌ ምን እጠብቃለው ብቻ ሳይሆን ለባሌስ ምን ይዤለት ሄዳለው…?የሚለውን በጥልቀት ማሰብና መዘጋጀት እንዳለብኝ ነው፡፡ ››
‹‹ጎበዝ ነሽ…ይሄ ትልቅ መረዳት ነው..በይ ደህና እደሪ››
‹‹ውይ …ከመዝጋትህ በፊት…ድፍረት አይሁንብኝና ዛሬ ቤት ለምን አትመጣም››
‹‹ለምን?››
‹‹እማዬ የማሪያም ድግስ አለባት….ማህበርተኞቹ እስከ10 ሰዓት ነው የሚቆዩት 11 ሰዓት ብትመጣ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹አረ ተይ››
‹‹ምን አለበት…ቤተሰቦቼ በጣም ነው ደስ የሚላቸው››
‹‹11 ሰዓት ነው ያልሽኝ?፡፡››
‹‹አዎ 11 ሰዓት››
ብቻውን ሆኖ ስለአስቴር እያሰበ ከሚሰቃይ ከሰው ጋር ተቀላቅሎ የባጥ የቆጡን እያወራ ሊረሳት ቢሞክር እንደሚሻለው አሰበእና ‹‹በቃ እሺ መጣለሁ››አላት፡፡
‹‹በቃ አቃቂ ፖሊስ ጣቢያው ጋር ስትደርስ ደውልልኝ..ወጥቼ እቀበልሀለው››
‹‹እሺ ደውላለው››
ስልኩን ዘጋው፡፡ እሺ ማለቱን ፍጽም አላመነም….ጠበል ለመቅመስ ከሜክሲኮ
አቃቂ….ለመሆኑ በህይወቱ ጠበል የተጠራውና ጥሪውን አክብሮ የሄደው መቼ ነው..?ፍጽም አያስታውስም….
እንዳለችው …..እንደደወለላት ደቂቃ ሳታባክን ነው ወጥታ የተቀበለችው….መኪናውን
እዛው አስፓልት ዳር ፓርክ አደረገና ተከትሏት ይዛው ሄደችው.. ግን ወደሚያስደነግጥ ቦታ ነው ይዛው የሄደችው…ይሄንን ግቢ ትናንትና በዚህን ሰዓት መኪና ውስጥ ሆኖ ከአሰሪዎቹ ጋር በመሆን ሲሰልለው ነበር …‹‹ምን አይነት መገጣጠም ነው?››ለለሊሴ ምንም አይነት የመደነቅና የመገረም ስሜት ሳያሳያት ተከተላት፡፡አሁን ነገሮችን ገጣጥሞ ሲያስብ በፀሎት እሱን እንዴት እንዳገኘችውና ስልኩን ከማን እንደወሰደች ተገለፀለት፡፡

👍73❤5👎2
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================
‹‹እናንተ ደግሞ ጅል አትሁኑ…ሰሎሜ ሰው ነች…ሰው ስለሆነች ታማለች…የተመመ ሰው ደግሞ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ህክምና ካላገኘ ይሞታል….ይሄ ሀቅ ለሌላ ሰው ከሰራ ለሰሎሜም ይሰራል፡፡››ሁሴን ነበር የተናገረው፡፡
‹‹አንተ ደግሞ ሁሉን ነገር አውቃለሁ የምትለው ነገር አለ››አለማየሁ በብስጭት መለሰለት፡፡
‹‹ትክክል ነኛ..ከእናንተ በተሻለ ብዙ ነገር አውቃለሁ…ይልቅስ ሰሎሜ ቀዶ-ጥገናዋን እንድታደርግ እኛ ምን ማድረግ አለብን ?የሚለውን መነጋገር ነው የሚጠቅመን፡፡››
‹‹ትክክል ነህ..የመጣልህ ሀሳብ አለ?››አለማየሁ ነው በጉጉት የጠየቀው፡፡
የቀዶ ጥገና እንዲደረግላት የተወሰነበትንና እና የገንዘቡን መጠን የሚገልፅ ደብዳቤ ማግኘት አለብን›› ሁሴን ሀሳብ አቀረበ፡፡
‹‹አግኝተንስ ምን እናደርገዋለን?››አላዛር ጠየቀ፡፡
‹‹በሰፈር ጠቅላላ ዞረን እንለምናለን…በትምህርት ቤታችንም እንለምናለን፡፡››
‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው..ግን ያንን ሁሉ ብር የምናገኝ ይመስልሀል?››በጥርጣሬ ጠየቁት፡፡
‹‹እስከቻልነው እንሞክራለን…ካልሞላልን ደግሞ ሌላ ዘዴ እንፈልጋለን..አሁን ደብዳቤውን እንዴት እንደምናገኝ ማሰብ አለብን››
‹‹ለምን ሀኪም ቤት ሄደን ሰሎሜን የሚያክማትን ሀኪም አንጠይቀውም…››አላዛር ነው ሀሳቡን ያቀረበው፡፡
‹‹አይ አንተ ጅል የሆንክ ልጅ..አሁን ሄደን ብንጠይቀው ለ13 አመት ልጇች እንዲህ አይነት መረጃ ሚሰጠን ይመስልሀል?››
‹‹እኔ እንጃ ግራ ስለገባኝ እኮ ነው፡፡››
‹‹ለምን እቴቴን አንጠይቃትም..እሷ ደብዳቤውን ልታስወጣልን ትችላለች››
‹‹አሌክስ ትክክል ነው..ጊዜ ሳናባክን አቴቴን እናናግራት››ሁሴን በአለማየሁ ሀሳብ ወዲያው ተስማማ፡፡
‹‹ግን እኮ እሷ ሆስፒታል ነው ያለችው››
‹‹እኮ እንሂዳ››
ተስማሙና ቀጥታ ሰሎሜ ወደተኛችበት ሆስፒታል ነበር የሄዱት፡፡ሰሎሜ የተኛችበት ክፍል ገብተው ያለችበትን ሁኔታ ካዩ በኃላ‹‹እቴቴ አንዴ ውጭ ልናናግርሽ ፈልገን ነበር፡፡››ሲሉ ጠየቋት፡፡
‹‹ምነው በሰላም?››
‹‹በሰላም ነው..ሰሎሜ ስለተኛች እዚህ ስናወራ እንዳንቀሰቅሳት ነው››አለ ሁሴን፡፡
‹‹እሺ እንዳላችሁ ››በማለት ተስማምታ ተከትላቸው ወጣች፡፡እዛው ሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ካለ አግዳሚ ወንበር ላይ በመደዳ ተቀመጡ፡፡
ለነገሩ ብዙም ትኩረት ባለመስጠት‹‹እሺ ልጆች ..ለምንድነበር የፈለጋችሁኝ?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹ሰሎሜ እንዴት ነች?››
ቀዝቀዝ ባለ ስሜት ‹‹ደህና ነች..ምንም አትል››ስትል መለሰችላቸው፡፡
‹‹ማለት ስለቀዶ ጥገናው ነው የምናወራሽ…?እንዴት ነው የሚሆነው…?ያን ያህል ብር ከየት ታመጪያለሽ?››
‹‹ልጇች አትጨነቁ..ከየትም ብዬ ከየትም ይሄንን ብር አግኝቼ ብቸኛ ልጄን ማሳከም አለብኝ….አታስቡ ጓደኛችሁን እንድትድን የተቻለኝን አደርጋለሁ፡፡››ስትል እንባ እየተናነቃት መለሰችላቸው፡፡በእውነት ብሩን ከየት እንደምታመጣው…የትኞቹን ዘመዶቾን እንደምታስቸግር…የትኛውን ንብረቷን ብትሸጥ የተጠየቀችውን ብር ማግኘት እንደምትችል ምንም አይነት ሀሳብም ሆነ ተስፋ አልነበራት፡፡ግን ለልጆቹ ይሄንን ምን ብላ በምን አይነት ቋንቋ ልታስረዳቸው ትችላለች፡፡ለዛ ነው በደፈናው ልታፅናናቸው የወሰነችው፡፡
‹‹እቴቴ…ሰሎሜን ለማዳን የተቻለንን ብቻ ሳይሆን ከምንችለው በላይ ነው ማድረግ ያለብን…ሶስታችንም ልክ እንደአንቺ እሷን ለማጣት ዝግጁ አይደለንም…እና የሆነ ነገር ለማድረግ አስበናል፡››ሁሴን ነበር ተናጋሪው፡፡
አቴቴ ግራ በመጋባት‹‹ምን ማለት ነው …?እናንተ ደግሞ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?››
‹‹ከሀኪም ቤቱ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለባት መወሰኑን እና ለዛም የሚያስፈልገውን ብር የሚገልጽ ደብዳቤ እንዲሰጡሽ ጠይቂያቸው››
‹‹ማለት ..ደብዳቤው ምን ያደርግልኛል?››
‹‹አይ ላንቺ አይደለም..ለእኛ ያስፈልገናል››
‹‹ለምን .?.ምን ልታደርጉበት?››
ትምህርት ቤታቸውን ሆነ በሰፈራችን እርዳታ እየዞርን እንጠይቃለን..ከየአንዳንዱ ሰው አንድ ብርም ሆነ አስር ብር እየዞርን እንሰበስባለን…ለዛ ግን ሰው እንዲያምነን እና ስራችን ቀላል እንዲሆንልን መረጃው ያስፈልገናል፡፡››
በወቅቱ የሰሎሜ እናት ስሜቷን መቆጣጠር አልቻለችም ነበር…ሁሉንም አንድ ላይ አቅፋ ጉያዋ ውስጥ በመወሸቅ ስቅስቅ ብላ ነበር ማልቀስ የጀመረች፡፡
አለማየሁ ጉንጮ ላይ ያለውን እንባ በመዳፎቹ እየጠረገላት ‹‹እቴቴ አይዞሽ.. አታልቅሺ …ሰሎሜን እናድናታለን…እሷ የእኛ ንግስት ነች..ንግስታችንን ማጣት አንፈልግም፡፡››ሲል አፅናናት ፡፡
‹‹ያስለቀሰኝ ሀዘን አይደለም ደስታ ነው፡፡ልጄን ወንድም ወይም እህት ሳልወልድላት ብቸኛ አደረኳት ብዬ ብዙ ጊዜ አዝኜና አልቅሼ ነበር፡፡አሁን ግን እንደተሳሳትኩ በደንብ ነው የገባኝ፡፡ወንድሞች ቢኖሯትም እናንተ ከምትወዷትና ከምትንከባከቧት በላይ ሊንከባከቧት አይችሉም ነበር፡፡
በጣም ነው የማመሰግናችሁ፡፡ እናንተ ስላላችኋት ልጄ በጣም እድለኛ ነች››
‹‹አይ እቴቴ….እሷ ስላለችን እኛ ነን እድለኞች…አሁን መላቀሱ አይጠቅመንም…ሂጂና ዶክተሮቹን ጠይቀሽ ደብዳቤውን አግኚልን፡፡››
‹‹እሺ በቃ ውስጥ ገብታችሁ ጠብቁኝ …መጣሁ››ብላ በነጠላዋ ጫፍ በጉንጮቾ የረገፈ እንባዋን እየጠረገች ወደአስተዳደር ቢሮ ሄደች፡፡
ደብዳቤውን በእጃቸው ካስገቡ በኋላ ሰፈራቸው ወደሚገኝ ባነር መታሚያ ቤት ነበር የሄድት፡፡ ደብዳቤውን አሳይተውና ሁኔታውን አስረድተው…የሰሎሜ አሳዛኝ ፎቶ የሚታይበትንና ያለችበትን ሁኔታ እጥር ምጥን ባለ ግልፅ ዓረፍተ ነገር አፅፈው ሁለት ሜትር በአንድ ሜትር በሆነ ባነር አሳተሙ፡፡ ..በማግስቱ ወደትምህርት ቤት ይዘው ሄዱ፡፡ቀጥታ ወደ ዳሪክተሩ ቢሮ ሄዱና ሁኔታውን አስረዱት….፡፡.ተማሪዎች በተሰለፉበት ባነሩ ለሁሉም እንዲታይ ተዘርግቶ ሰሎሜ ያለችበትን ሁኔታና የሚያስፈልጋትን ነገር ለሁለቱም ፈረቃ ተማሪዎች ተነገረ…፡፡በእለቱ በኪሳቸው ያላቸው ተማሪዎች ወዲያውኑ ማዋጣት ጀመሩ…ሁለት ሺ ሶስት መቶ ብር አካባቢ ተሰበሰበ፡፡በማግስቱ ሁሉም ተማሪ ለወላጆቹ በማስረዳት የቻለውን ይዞ እንዲመጣና በስም ጠሪዎች አማካይነት በየክፍሉ እንዲሰበስብ ተደረገ፡፡
በአጠቃላይ በሶስት ቀን ውስጥ ከመላው ተማሪና አስተማሪዎች 23 ሺ ብር ተሰበሰበ፡፡ትምህርት ቤቱ የሰሎሜን እናት ጠርቶ ቀጥታ ብሩን አስረከባት፡፡ የትምህርት ቤቱን ቅፅር ግቢ በእልልታ አናጋችው….ሶስቱን የልጇን ጓደኞች እያገላላበጠች ሳመቻቸው፡፡ከልቧ መረቀቻቸው፡፡ከነፍሷ ወደደቻቸው፡፡
እነአለማየሁ ግን እንደእሷ ባገኙት ነገር ፍፅም ደስታ አልተሰማቸውም ነበር፡፡የእነሱ ግምት ቢያንስ 40 እና 50 ሺ ብር እናገኛለን የሚል ነበር፡፡ወዲያው ጊዜ ሳያባክኑ ባነሩን ለሁለት ጉን ለጉን ይዘው አንደኛው በአጀንዳ ላይ እያንዳዱ ሰው የሚሰጠውን ስምና ብር እየመዘገበ በሰፈር ውስጥ እያንዳንዱን ቤት እያንኳኩ እና የድርጅቶችንም ቢሮ ዘልቀው እየገቡ ጭምር መጠየቅ ጀመሩ፡፡
በአራት ቀን ውስጥ ሌላ 20 ሺ ብር አገኙና ለእናትዬው አስረከቧት..፡፡እሷ በፊት ደብተሯ ላይ የነበራትናን ከቢሮዋ ሰራተኞች ተዋጥቶ የተሰጣት አንድ ላይ ሆኖ እነሱ ከሰበሰቡት ጋር 50 ሺ ብር አካባቢ በእጇ ያዘች፡፡
ሶስቱም በአንድ ላይ ተሰብስበው ሄደው ‹‹እቴቴ..አሁን ስንት ብር ሆነልሽ?››ብለው ጠየቋት፡፡

👍59❤9👏1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
"ምንድነው የነገረችሽ?"
"እኔ ዲቃላ መሆኔን ."
የጁኒየር ፊት በድንጋጤ ባዶ ሆነ።
"እውነት ነው አይደል?"
ጁኒየር እጆቹን ዘረጋና እቅፉ ውስጥ አስገባት… እንባዋ በመጨረሻ የዐይን ሽፋኖቿን ሞልተው ያለከልካይ ፈሰሰ።
"ሰሎሜ ከኮፈሌ ተመልሳ መጣች። ከገመዶ ጋር ለመታረቅ ተዘጋጅታ ነበር።ፍቅራቸውን ለማደስ ተስማምተው ነበር …የመጋባት እድል ሁሉ ነበራቸው…በመሀል ግን ለማንኛችንም ሳትነግረን መልሳ ጠፋች….በኋላ ነው አንቺን ማረገዟን ስላወቀች እንደጠፋች ያወቅነው፡፡››ሲል አስረዳት፡፡
በእፍረት ፊቷን በእጆቿ ሸፈነች።
" ኦ አምላኬ በጣም ቢጠላኝ አይገርምም።››
ጁኒየር እጆቿን ከፊቷ ላይ አንስቶ በቅን ልቦና የሚወዳቸውን ጥቆቁር አይኖችን እየተመለከተ።
"ገመዶ አንቺን አይጠላሽም አሌክስ። ማናችንም ብንሆን አንጠላሽም…ያ ከአመታት በፊት ተጋፍጠን በይቅርታ ያለፍነው ጉዳይ ነው››
በንግግሩ በምሬት ሳቀች።‹‹ለምን አያቴ ሁሌ እኔ ላይ ጥብቅ እንደምትሆን እያሰብኩ እበሳጭ ነበር …በስንት ሰዓት ከቤት እንደወጣው? በስንት ሰዓት እንደተመለስኩ..?ከማን ጋር እንደነበርኩ ከአግባቡ ያለፈ ቁጥጥር ታደርግብኝ ነበር…ምክንያቷ አሁን ነው የገባኝ
…ለካ እናቴን ያጋጠማት ነገር እንዳያጋጥመኝ ፈርታ ነው፡፡አሁን ነው የገባኝ፡››
"ይሄ ከሃያ አምስት አመታት በፊት የሆነ ድርጊት ነው ፣ አሌክስ አሁን ስለዛ ማሰብ አቁሚ "
"አያቴ በእውነት እኔን ለምን እንደማትወደኝ የሚያብራራልኝ ታሪክ ነው… የሰሎሜን ህይወት አበላሽቻዋለሁ…እና ለዛ ፈጽሞ ይቅር ሳትለኝ ነው የሞተችው…. ሰሎሜ ገመዶን አጥታለች …ፍቅራቸው እንዳይሆን ሆኖ ተሰባብሯል … እና ሁሉም የሆነው በእኔ ምክንያት ነው››.
‹‹ኦህ፣በእግዚአብሔር !ተረጋጊ እንጂ!"
አለም ከእቅፉ ወጣችና ወደ መኪናዋ ሮጠች…መኪና ውስጥ በመግባት አስነሳችና አካባቢውን ለቀቀች።
."ምንድነው ነገሩ?" አለም ወደ መኪናዋ አቅጣጫ ስትሮጥ ያያት አቶ ፍሰሀ ጠየቀው።
"ሁለታችሁም እሷን ተዋት" ሳራ ከውስጥ እየወጣች ለባሏ መለሰች፡፡
ጁኒየር ወደ እናቱ ዞረና።
"እማዬ እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ? እንዴት ልጅቷን እንዲህ ትጎጂያታለሽ?"
"ልጎዳት አስቤ አይደለም የነገርኳት፡፡››
"ምን ነግራት ነው?" አቶ ፍሰሀ ጠየቀ ፡፡
ጁኒየር “በእርግጥ ጎድተሻታል። ደግሞ አቅደሽበት ነው ያደረግሽው… ለምን ነገርሻት?"
‹‹ምክንያቱም እሷ ማወቅ ስላለባት። አለምን የምትጎዳት እራሱ አለም ብቻ ነች። ሸቅዠቷን እያሳደደች ነው። የምትፈልጋት አይነት ቅድስት የሆነች እናት በሰሎሜ ውስጥ አልነበረችም። ሰሎሜ ምትባል ድንቅ እናት እንደነበረቻት በማይረባ ጭንቅላቷ ደምድማለች። እናቷ ምን ያህል ተንኮለኛ እና ሀጥያተኛ እንደሆነች ልጅቷ ማወቅ አለባት.. እናቷ ስትማግጥ እሷን ዲቃላ እንዳረገዘቻት የማወቅ መብት አላት››
" አንቺ እኮ ጤነኛ አይደለሽም!" አቶ ፍሰሀ ተበሳጨባት፡፡
…
አቶ ፍሰሀ በጸጥታ ወደ መኝታ ቤት ገባና ከኋላው በሩን ዘጋው፡፡ሳራ በአልጋዋ ላይ ያሉትን ትራስ ደራርባ ተደግፋ መፅሃፏን እያነበበች ነበር…እሱን ስታይ መፅሀፉን ከደነችና አጠገቧ ያለው ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠች ።
ወደአልጋው ቀረበና " ላናግርሸ እፈልጋለሁ።"አላት፡፡
"ስለ ምን?"
‹‹ዛሬ ከሰአት በኋላ ስለተፈጠረው ነገር።››
"ራስ ምታት እየፈለጠኝ ነው…ለእራት ወደታች ያልመጣሁትም ለዛ ነው"
‹‹የሆነ መድሀኒት አልወሰድሺበትም?"
"አዎ ወስጄለሁ…አሁን በመጠኑ እየተሻለኝ ነው ።"የሳራ የራስ ምታት በትዳራቸው ልክ አብሯት የቆየ ህመም ስለሆነ የተለመደ ነው፡፡
በአልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠ እና አቀርቅሮ ሀሳብ ውስጥ ገባ፡፡
" ምንድነው ፍሰሀ ?አሁንም የሚያሰጋን ችግር አለ እንዴ?››ጠየቀች፡፡
"አይ..ሁሉም ነገር ሰላም ነው።"
"ታዲያ ለምን ታስባለህ…?እግዚአብሔር ይመስገን ብቸኛው የሞተው ፈረስ የገመዶ ነው
።››
አቶ ፍሰሀ ምንም አስተያየት መስጠት አልፈለገም ። ሳራ ጆ ለገመዶ ያላት ስሜት ፈጽሞ አይለወጥም፤በዚህ ጉዳይ ከእሷ ጋር መነጋገር ጥቅም አልባ እንደሆነ እርግጠኛ ነው፡፡ከእሷ ጋር ሊወያይ የመጣው ስስ ስለሆነ ጉዳይ ነው። ቃላቱን በጥንቃቄ ለመምረጥ ትንሽ ጊዜ ወሰደበት.
"ሳራ ዛሬ ከሰአት በኋላ -……" "በጣም ተበሳጭቼ ነበር" አለችው፣ ፡፡
" ተበሳጭተሽ ነበር?" ፍሰሀ ትዕግሥተኛ ሆኖ ጠየቃት፡፡ወደ ድምዳሜው ከመዝለሉ በፊት ከእሷ ወገን ያለውን የታሪኩን ገጽታ መስማት ፍልጓል።
"የአለምን ስሜትስ የጎዳሽ አይመስልሽም…?"
"ዲቃላ መሆኗን ስላወቀች ብቻ አይደለም የተናደደችው….እሷ በተፈጥሮዋም ብስጩ ነች:: "
"እኔ በእሷ ቦታ ብሆን አይገርመኝም… ወላጆቼ የጋብቻ ሰርተፊኬት እንዳላቸው በጭራሽ አጣርቼ አላውቅም.., እና ባይኖራቸውም ምንም አይመስለኝም ነበር.››
" ሁሉም ሰው ለነገሮች ያለው ምላሽ የተለያየ ነው››
‹‹ አለም ግን ስሜታዊነት የሚያጠቃት ወጣት ሴት ነች።"
"እሷ ይሄን ታሪክ ለመቀበል የሚያስችል ጥንካሬ እንዳላት አምናለው."ስትል መለሰችለት
"በእርግጥ የምትይውን ያህል ጥንካሬ እንዳላት እርግጠኛ አይደለሁም።በረንዳ ላይ ቆሜ እያየችኝ እኔን እንኳን ሀሳትሰናበተኝ ነው ገፍትራኝ ሮጣ የሄደችው፡፡››
የሳራ ፈገግታ ተሰበረ። "ስለነገርኳት ትወቅሰኛለህ? ስህተት የሰራው ይመስልሃል?"ስትል ጠየቀችው፡፡
በዛ ልብን በሚሰረስር የግሏ የሆነ ልዩ እይታ ስታየው፣ ልቡ ቀለጠ። ሁል ጊዜም የዚህ አይነት አስተያየት ስታየው የሚሆነው እንደዚሁ ነው። ፍሰሀ በስሱ ይዳብሳት ጀመር፡፡
‹‹ውዴ ስለነገርሻት አልወቅስሽም። ግን የነገርሽበት መንገድ እንደዚህ ባይሆን ጥሩ ነበር፡፡ እንደዛ ከማድረግሽ በፊት ከጁኒዬር እና ከእኔ ጋር መመካከር ነበረብሽ…በህይወቷ ሙሉ ባታውቀው የሚሻል ታሪክ ነበር፡፡››
"አልስማማም" ስትል ሳራ ተከራከረች።
አቶ ፍሰሀም "እናቷ እና አባቷ አብረው ከተኙ በኃላ አለመጋባታቸው ወይ መጋባታቸው በእሷ ልጅነት ላይ አሁን ምን ለውጥ ያመጣል? ይህ በቡዙ ወጣት ሴቶች ህይወት ላይ የሚያጋጥም በጣም የተለመደ ነገር ነው..››አላት፡፡
"ልጅቷ ስለ ሰሎሜ ያላት አመለካከት ላይ ግን ለውጥ ያመጣል። ››
‹‹እንዴት?››
‹‹ሰሎሜ ልጅቷ የምታስባትን አይነት ቅድስት ሴት አይደለችም…ይሄን ማወቋ የእሷን የግድያ ጉዳይ ለማወቅ የምታደርገውን ልፋትና ጥረት ቆም ብላ እንድታይ ያግዛት ይሆናል….ይልቅ ከአሁን በኃላ ሁላችሁም ከአለም ጋር መገናኘቱን እና መወያየቱን ማቆም አለባችሁ፡፡››
"ለምን?"ግራ ገብቶት ጠየቀው፡፡
"ለምን? ምክንያቱም እሷ እኛን ለማጥፋት እየሞከረች ነው…ለዚህ ነው. እሷን ለመፋለም የወሰንኩ…. ያለኝን ጥይት ነው የተጠቀምኩት….አንተን እና ጁኒየርን ለመጠበቅ እየሞከርኩ ነበር."
በእውነቱ፣ ፍሰሀ እንደ አለም ያለ በራስ መተማመን የነበራትን ሴትን ለመጋፈጥ ለሣራ ትልቅ ድፍረት እንደሆነ አሰበ። ያደረገችው ስህተት ቢሆንም ሳራ ያደረገችውን ነገር ያደረገችው ቤተሰቧን ልትጠብቅ እንደሆነ ተረድቷታል። የጀግንነት ጥረቷ ከትችት የተሻለ ነገር ይገባዋል ብሎ አሰበ እና ጎንበስ ብሎ ግንባሯን ሳመ።
ለስለስ ባለ ንግግር" የትግል መንፈስሽን አደንቃለሁ… ግን ማናችንም ያንቺን ጥበቃ አንፈልግም ።"አላት፡፡

❤46👍3