#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ሰለሞንና በፀሎት በስልክ እያወሩ ነው፡፡
‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለሽው?››ሲል ጠየቃት
‹‹ምነው ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ ..እንዲሁ ደህንነትሽ አሳስቦኝ ነው….ምን አልባት የማይመች ቦታ ካለሽ ልረዳሽ እችላለው፡፡››
‹‹ምነው ወደቤትህ ወስደህ ደብቀህ ልታኖረኝ አሰብክ››
‹‹ምነው ..ችግር አለው.?.የእውነት የማይመች ቦታ ካለሽ ንገሪኝ››
‹‹አሁን ካለሁበት ቦታ የተሻለ ሊመቸኝ የሚችለው ምን አልባት ገነት ነው….እሱንም ደግሞ ስላላየሁት እርግጠኛ አይደለሁም››
‹‹እንዴ…ከእናትና አባትሽም ቤት የተሻለ ቦታ ነኝ ነው የምትይኝ…ይሄንን ማመን አልችልም፡ ››
‹‹ነገርኩህ እኮ…››
‹‹‹እ ..ገባኝ››
‹‹ምኑ ነው የገባህ?››
‹‹ከእናትና አባት ቤት በበለጠ የሚመች ቦታ የፍቅረኛ ቤት ነው››
‹‹በጣም ተሳስተሀል..አዲስ ቤተሰብ አግኝቼለሁ…አራት ናቸው..ሽማግሌ አባትና እናት፣አንድ ዋንድ ሴትና ወንድ ልጅ አላቸው..ሁለት ክፍል ሰርቢስ ውስጥ ነው የሚኖሩት፣ኑሮቸው ከእጅ ወደአፍ ነው… ፍቅራቸው ግን ሞልቶ የፈሰሰ ነው….ለዘላለም ልጃቸው አድርገው ተቀብለውኛል…ከአሁን ወዲህ ባለው ህይወቴ ሙሉ አነሱ ወላጆቼ እና ቤተሰቦቼ እንደሆኑ እንዲቀጥሉ ምንም ነገር አደርጋለው››
‹‹የሚገርም ነው….እናትና አባትሽ ይሄንን ንግግርሽን ቢሰሙ ልባቸው የሚሰበር ይመስለኛል፡፡››
‹‹እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም…በእነሱ ስህተት ነው ከቤት የወጣሁትና እነሱን ያገኘሁት…አሁን አግኝቼ በደንብ አጣጥሜቸዋለው…እና ወደቤት ብመለስ እንኳን ወላጆቼን ከእነሱ ጋር ነው ማነፃፅራቸው…እና ለእነሱ ቀላል የሚሆንላቸው አይመስለኝም››
‹‹….ለመሆኑ ማንነትሽን ያውቃሉ?›
‹‹አይ አያውቁም.. እኔ ለእነሱ እናቷ የሞተችባት እና የእንጀራ አባቷ ሰክሮ በለሊት ሊደፍራት ሲል አምልጣ የወጣች ሚስኪን ሴት ነኝ››
‹‹ይሄንን ታሪክ አንቺ ነሽ የፈጠርሽው?››
‹‹አዎ…..››
‹‹የምትገርሚ ልጅ ነሽ ..እኔጋም መጥተሸ ተመሳሳይ ታሪክ ብትነግሪኝ አምኜ ልረዳሽ መሞከሬ አይቀርም ነበር››
‹‹የእነሱ እኮ መርዳት አይደለም….እናትና አባት መሆን ነው…..እንደልጃቸው መቀበል››
‹‹ የእውነት አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እኔ እራሱ ለመተዋወቅ ጓጓሁ› ›
‹‹መጓጓትህ ትክክል ነህ››
‹‹ነገሮች ከተስተካከሉ በኃላ ታስዋውቂኛለሽ ብዬ ገምታለው››
‹‹መጀመሪያ እስኪ እኛ ለመተዋወቅ ያብቃን››
‹‹እንዴ እኛኮ በደንብ ተዋወቅን፣ለአመታት የማውቅሽ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው..ያው አካል ለአካል አልተገናኘንም ብዬ ነው፡፡››
‹‹ባክሽ የስልኬ ጋላሪ ባንቺ ፎቶዎ ተጨናንቆል ››ብሎ ያልጠበቀችውን አስደንጋጭ ነገር ነገራት፡፡
‹‹እንዴ በምን ምክንያት?››
‹‹እንዴ ..ደንበኛዬ አይደለሽ?››
‹‹እና የሁሉንም ደንበኞችህን ፎቶ ትሰበስባለህ ማለት ነው?››
‹‹ቆንጆ እና የተለየ የሆኑትን ..አዎ››
‹‹በቻይንኛ ቆንጆ ነሽ እያልከኝ ነው፡፡››
‹‹እ..ምነው አይደለሽም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ ….ለማንኛውም ደስ የሚል ስሜት እንዲሰማኝ አድርገሀል…እና እኔስ የአንተን ፎቶ የማግኘት መብት ያለኝ አይመስልህም?››
‹‹አይ..አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እንድምታስተዋውቂኝ ቃል ካልገባሽ የምታገኚ አይመስለኝም››
‹‹አዲሶቹን ቤተሰቦቼን….እኔ እንጃ ..ስለምሰስታቸው የማደርገው አይመስለኝም››
‹‹‹ትገርሚያለሽ…፣ዋናዎቹን ቤተሰቦችሽን እኮ ተቆጣጥሬቸዋለው…..ለማንኛውም ይህን የመሰለ ቤተሰብ ስላገኘሽ ደስ ብሎኛል….ይሄውልሽ በህይወት ውስጥ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ፡፡ቅጠል የሆኑ ሰዎች… ቅርንጫፍ የሆኑ ሰዎችእና… ስር የሆኑ ሰዎች።ቅጠል የሆኑ ሰዎች ወቅትንና ሁኔታዎችን ጠብቀው ወደ ህይወትሽ የሚገብ ናቸው።ደካሞች ስለሆኑ በእነሱ ተፅዕኖ ስር ፈፅሞ እንዳትወድቂ። ከአንቺ የሚፈልጉትን የሆነ ነገር ስላለ ነው ወደህይወትሽ የሚመጡት... የመከራ ንፍስ በህይወት ዙሪያ ሲነፍስ መርገፍ ይጀምራሉ።እነዚህ ሰዎች አንቺን ማፍቀር የሚቀጥሉት በዙሪያሽ ያሉ ነገሮች ጥሩ እስከሆኑ ጊዜ ብቻ ነው።ንፋስ እንደመታው የወየበ ቅጠል ከላይሽ ላይ ተዘንጥለው ይረግፋሉ። ቅርንጫፍ ሰዎች ደግሞ በአንፃራዊነት ጠንካሮች ናቸው ግን ልትጠነቀቂያቸው ይገባል።ህይወት ጨከን ስትል መገንጠላቸው አይቀርም። ምክንያቱም ጠንከር ያለ የህይወት ጫና የመሸከም አቅም የላቸውም።ነገሮች ጨለምለም ሲሉ እና ተስፋም የሌላቸው ሲመስሉ ጥለውሽ ዞር ለማለት አያመነቱም። ሌሎቹ ልክ እንደአንቺ አዲሶቹ ቤተሰቦች ስር የሆኑ ሰዎች ናቸው። እነዚህ በህይወትሽ በጣም አስፈላጊ ሰዎች ናቸው።ለመታየት ብለው የሚሰሩት ስራ የለም።በመከራሽም በደስታሽም ጊዜ አብረውሽ ናቸው።አስከሞት የታመኑሽ ናቸው።ሲያፈቅሩሽ በነፃ ምንም መልስ ካንቺ ሳይጠብቁ ነው፣እንደዚህ አይነት አንድ ወይም ሁለት ሰው ከጎንሽ ማግኘት የህይወት ዘመን ሽልማት ነው፡፡
‹‹ጥሩ አድርገህ ገልጸኸዋል፡፡እነሱ ብቻ ሳይሆኑ፣አንተም ለእኔ ስር ነህ…በቃ ቸው…ነገ እንደዋወላለን፡፡››
‹‹ቸው …..ደህና ሆኚ››ብሎ ስልኩን ከዘጋ በኃላ …ባለበት ቆሞ ትካዜ ውስጥ ገባ..ይህቺን ልጅ በተመለከተ የተለየ አይነት ኬሚስትሪ በሰውነቱ እየተረጨ ነው….ነገሮች ወዴት እያመሩ ነው?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡
በማግስቱ……
በፀሎት ከሞላ ጎደል ጤንነቷ እየተመለሰ ነው…አረ እንደውም ድናለች ማለት ይቻላል..የእግሯ ስብራት ሙሉ በሙሉ ተጠግኖ በደንብ መራመድ ችላለች..የፊቷ ቁስለትም ሙሉ በሙሉ ጠጓል..አሁን ብቸኛ ችግሯ ፊቷ ላይ ተሸነታትሮ የሚገኘው ጠባሳ ብቻ ነው….እንግዲህ ግማሽ ፊቷን ባደረሰው በተበታተነው ጠባሳ ውስጥ ምን ያህሉ እንድሚጠፋና ከበፊት ቆዳዋ በቦታው እንደሚመለስ ምን ያህሉ ደግሞ እንዳዛው እንደሚቀር ምንም የምታውቀው ነገር የለም…ያንን ለማወቅ በርከት ያሉ ተጨማሪ የማገገሚያ ቀኖች ያስፈልጋታል…ከዛ በኃላ የቆዳ ስፔሻሊስቶች ጋር ሔዳ ሰርጀሪ መሰራትም የግድ ያስፈልጋት ይሆናል….ለጊዜው ያ እያሳሰባት አይደለም…‹‹እሱን ጊዜው ሲደርስና ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ወደቤት ከተመለስኩ በኃላ አስብበታለው››ብላ ወስናለች….አሁን ከጎኗ አቶ ለሜቻ ቁጭ ብለው እያጫወቷት ነው፡፡
‹‹ለልጆቾህ ያለህ ፍቅር ያስገርመኛል››
‹‹አይ ልጄ ሁሉም ወላጆች እኮ ልጆቻቸውን አብዝተው ይወዳሉ…››በትህትና መለሱላት፡፡
‹‹እሱን ማለቴ አይደለም..የእናንተ የተለየ ነው…አይኖችህ ከልጆቾህ ላይ አይነቀሉም….ሙሉ ትኩረትህ ልጆቾህ ላይ ነው..ስለእለት ውሏቸው ታውቃለህ….ጥዋትና ማታ አብረሀቸው ባንድ መሶብ ቀርበህ ሁለቱንም እያጎረስክ ነው የምትበላው፣ብዙ ብዙ ነገር…››
‹‹ልጄ ወድጄ አይደለም እኮ…. እንደምትይው እኔ አባትሽ በብዛት ተትረፍርፎ ያለኝ ፍቅር ነው…ገንዘብ ኖሮኝ ይሄን ስሩ ብዬ መቋቋሚያ..ወይም መነገጃ ጥሪት አልሰጣቸው….ሁል ጊዜ ታዲያ ይሄንን ነገር በምንድነው የማካክሰው ብዬ ሳስብ አንድ የማገኘው መልስ…ጊዜዬንና ፍቅሬን ሳልሰስት መስጠት ነው..አዎ ቢያንስ በዛ ነው ልክሳቸው የምችለው፡››
‹‹ግን እንሱ ምን ያህል እድለኞች መሆናቸውን ያውቃሉ?››
‹‹አይ እነሱ ሳይሆኑ እኔ ነኝ እድለኛ….ምንም ባላደርግላቸው እንኳን ማንም ፊት በኩራት አባዬ ብለው ይጠሩኛል፡፡በቀደም ለሊሴ ይሄ ፌስቡክ ነው ምን በምትሉት ነገር ላይ በተንዠረገገ ፂሜንና በጎፈረ ፀጉሬ የተነሳሁትን የተጎሳቆለ ፎቶ ለጥፋ አባዬ መልካም

👍84❤15🥰4👏4
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
አላዛር እጅግ ሸበላ የሚባልና እና የበዛ ውበት አላቸው ተብለው ከሚመደቡ ወንዶች መካከል አንዱ ነው፡፡አብዛኛውን ጊዜ አይደለም ሴቶች ወንዶችም እይታ ውስጥ ለመግባት ለእሱ ዠቀላል ነው፡፡በዚህም የተነሳ የቅርቧም ሆኑ ድንገት ያገኘቻቸው ሰዎች በተለይ ሴቶች እሱን ባሏ ማድረግ በመቻሏ በአለም ላይ ካሉ እድለኛ ሴቶች መካከል አንዷ እንደሆነች በእርግጠኝነት ደጋግመው ይነግሯታል፡፡እሷም በልብ ቁስለትና በፊት ፈገግታ ጥርሷን ብልጭ አድርጋ ምንም አስተያየት ሳትሰጥ ታልፈቸዋለች፡፡
ማታ ከአራት ሰዓት ጀምሮ ነበር ከባለቤቷ ከአላዛር ጋር ደስ ሚል ሙድ ውስጥ የገቡት፡፡ነጭ ወይናቸውን እየተጎነጩ…ጎን ለጎን ተጣብቀዋል፡፡..ጥልቅ የስሜት ትስስር ያለው መላ ሴልን የሚያነቃቃ አይነት ማራኪ የፍቅር ፊልም አብረው ሲያዩ ነው ያመሹት፡፡ወደ መኝታ ቤታቸው ተከታትለው ሲገቡ ከምሽቱ ስድስት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ሰውነቷ ሁሉ ግሏል …አረ ከዛም አልፎ እየተቃጠለች ነው ማለት ይቻላል፡፡‹‹ዛሬ የተለየ ነገር እንደሚኖር ተስፋ አደርጋለሁ››ስትል በልቧ እያብሰለሰለች ነበር ቧሏን በፈገግታ ተከትላ ወደመኝታ ቤቷ የገባችው፡፡እንደዛ ተስፋ እንድታደርግ ያበረታታት ደግሞ ባለቤቷ ላይ ያየችው ከወትሮ የተለየ መነቃቃትና በፈገግታ የተሞላ አስተያየት ነው፡፡
አልጋ ላይ ቀድሞ ወጣና ብርድልብሱን ገልጦ ከውስጥ ገባ ፡፡ሙሉ ቢጃማውን እንደለበሰ ነበር፡፡እሷም ተቃራኒው አወላለቀችና በፓንት ብቻ ተከተለችውና ከውስጥ ገብታ ተለጠፈችበት፡፡ በጀርባው ነበር የተኛው፡፡ ደረቱን ተንተራሰችና እጆቾን ወደ ሆዱ ላከች፡፡ በስሱ ማሻሸት ጀመረች፡፡ያለምንም እንቅስቃሴ በፀጥታ ላይ ነው፡፡ቀስ አለችና እጆቾን ወደታች አንሸራታ የለሊት ሱሪውን ሰቅስቃ ገባችና ወደታች ወደብልቱ ወረደች…ቀስ እያለች ጨብጣ ማሻሸት ጀመረች፡፡ያው እንደተለመደው ብልቱ ልፍስፍስ እንዳለ ነበር፡፡‹‹እንዴት ነው ግን ይሄንን የመሰለ ዝግባ መሰይ ጠንበለል ሰው እንዲህ አይነት ለንቆሳና ልፍስፍስ ብልት ባለቤት የሆነው?››ሁል ጊዜ ስለእሱ ስታስብ የምትደነቅበት ነገር ነው፡፡ግን አንድ ቀን እንደምንም ጠንካራና የልብ አድርስ ይሆናል የሚል እምነት አላት ፡፡ለዛ ነው ሁል ጊዜ ዘዴዎቾን እየቀያየረች ከመሞከር የማትሰንፈው ..ቀጥላለች….ምንም የሚያበረታታ ነገር እያየች አልነበረም፡፡ይባስ ብሎ እጁን አንቀሳቀሰና የእሷን እጅ ይዞ ቀስ ብሎ በማስለቀቅ እጇን ወደቦታው መለሰ፡፡ከደረቱ ላይ ቀስ ብሎ አንሸራቶ ትራስ ላይ አስተኛትና ፊቱን አዙሮ እንደተለመደው ጀርባውን ሰጣትና ሽብልል ብሎ ተኛ፡፡በወቅቱ ውስጧ ኩምትርትር ብሎ ሲጨማደድ ይታወቃታል…ከውስጥ ከልቧ አካባቢ የሆነ ታፍኖ ሲብላላ የከረመ እሳት ጎመራ ፈንድቶ እቶን እሳት በመላ ሰውነቷ ሲተፋ እየታወቃት ነው፡፡ቃጠሎውን አልቻለችም ነበር፡፡ .ትግስቷ ተሞጠጠ፡፡ካለመቻሉ በላይ ለመቻል የሚያደርገው ጥረት እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ ይበልጥ አበሳጫት፡፡
ከአልጋዋ ላይ ተፈናጥራ ተነሳች፡፡እጅግ ከፍተኛ የሚባል ንዴት ላይ ነበረች፡፡ተስፈንጥራ ከአልጋዋ ወረደችና እርቃኗን ሆና ቁልቁል አዘቅቃ ታየው ጀመረ፡፡በእውነት ከሆነ ልታንቧርቅበት…ኮመዲኖው ላይ ያለውን የራስጌ መብራት አንስታ ግንባሩን ልትፈረክሰው….ወይንም በጥፍሮቾ ሁለት አይኖቹን ፈጥርቃ ልታፈርጥለት…ብዙ ብዙ ነገር ማድረግ ፈልጋ ነበረ፡፡ግን ሁሉም የስሜት ህዋሳቶቾ ሊታዘዙላት አልቻሉም፡፡አንደበቷ ተላቆ እንኳን የሆኑ ሁለት ሶስት ቃላትን ለማውጣት አልቻለችም፡፡
ባለቤቷ አልአዛር አልጋው ላይ እንደተዘረረ ወደላይ አንጋጦ እየተመለከታት ነበር፡፡አቅፎ ሊያባብላት፤ ስሞ ሊያረጋጋት ይፈልጋል፡፡ግን ደግሞ እንደዛ ማድረግ አይችልም፡፡አዎ ለዛ የሚሆን ወኔ የለውም፡፡ፊት ለፊት ካለ ጠረጴዛ ላይ ያለውን ቢጃማውን አነሳችና አጠለቀች…ከኮመዲኖ ላይ ያለውን የመኪና ቁልፍ አነሳችና መኝታ ቤቱን ለቃ ወጣች፡፡ተከትሏት ተነስቶ ነበር፡፡ መኝታ ቤቱን ሳይለቅ ወደመስኮት አመራና አንገቱን አስግጎ እስከመጨረሻው ያያት ጀመር፡፡የውጩን በር በርግዳ ስትከፍት፤ወደመኪናው ገብታ ሞተሩን አስነስታ ጊቢውን ለቃ ስትወጣ ሁሉ በዝምታ እየተመለከታት ነበር፡፡
ሳሎሜ በውድቅት ለሊት መኪናዋን አስነስታ ቤቷን ለቃ ወጥታ ወደቄራ መስመር አምስት ኪሎ ሜትር በላይ ስለባሏ ክፉውንም ደጉንም እያሰላሰለ ከነዳች በኃላ ነው ሙሉ በሙሉ ወደቀልቧ መመለስ የቻለችው፡፡ምርር ያለ ንዴት ነበር የተናደደችው፡፡እርግጥ እንዲህ አይነት ንዴት መናደድ የጀመረችው ዛሬ አይደለም፡፤ባለፉት ሁለት አመታት አላዛርን አግብታ እቤቱ ከገባች ጀምሮ አብሯት ያለ ጨለማ ስሜት ነው፡፡የዛሬውን ልዩ የሚያደርገው ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ ነው፡፡
‹‹አሁን ወዴት ልሂድ?››ብላ..አሰበችና ተበሳጨች፡፡ብስጭቷን እጥፍ የሚያደርግባት ደግሞ ይሄ ነው፡፡በባሎ ተበሳጭታ ከቤቷ ለቃ ብትወጣም የትም መሄድ አትችልም.፡፡እናቷ ጋር መሄድ አትችልም፡፡ጓደኞቾ ጋርም ፍፅም አይታሰብም….ምክንቱም በምን ተጣላችሁ ተብላ ብትጠየቅ ማስረዳት አትችልም፡፡እንዴት ብላ፡፡እንባዋ ይረግፍ ጀመር፡፡እያለቀሰች በመሆኗ ደስ አላት፡፡አዎ ሁሉ ጊዜ እንዲህ አይነት አስጠሊታ ስሜት ላይ ስትሆን በማልቀስ እና እንባዋን በማርገፍ ነው ቀዝቀዝ ማለት የምትችለው፡›ማልቀስ ባይኖር እንደውም በውስጥ ሀዘኗ ደርቃ የምትሰነጣጠቅና የምትበታተን ነው የሚመስላት፡፡
መኪናዋን አዙራ ወደቤቷ ለመመለስ ወሰነች…መሪዋን ስትጠመዘዝ እየተክለፈለፈ ከሚመጣ ሴኖትራክ ጋር ፊት ለፊት ተጋጠመች፡፡ በ5 ሜትር ርቀት ላይ መሆኗን አየች፤በደመነፍስ ቅፅበታዊ ውሳኔ ወሰነችና መኪናዋን ወደግራ ጠመዘዘች በዚህን ጊዜ ከመንገድ ተፈናጥራ ወጣችና ፊት ለፊቷ ካለ የብሎኬት አጥር ጋር ተላተመች፡፡አጥሩ ተፈረካክሶ ሲረግፋ ና ፍርስራሹ የመኪናዋን አካል ሲያለብስ በሰመመን ታያት፡፡ ለደቂቃዎች እራሷን እንደመሳት አድርጎት ነበር፡፡ነቅታ አይኗቾን ስትገልጥ ግን ከግራና ከቀኝ ሶስት ፖሊሶች መሳሪያ ደቅነውባት በተጠንቀቅ ቆመው ነበር፡፡መጀመሪያ ህልም ውስጥ ያለች መሰሏት ነበር፡፡በጥንቃቄ ከፍተው ጎትተው ሲያወጧት ነው…ሁሉ ነገር ተጫባጭ እውነት እንደሆነ የተረዳችው፡፡..ካልጠፋ የአዲስአበባ አጥር ለዛውም በውድቅት ለሊት የፖሊስ ጣቢያ አጥር ጥሳ መግባቷን ማመን አልቻለችም፡፡ድንዝዝ ነው ያላት፡፡ምን ማሰብ እንዳለባት እራሱ ግራ ተጋብታ ነበር…በመሳሪያ አጅበው ወስደው አንድ ክፍል በመክፈት ከሴት እስራኞች ጋር ቀላቀሏት፡፡
የተኙትን ሰባት የሚሆኑ እስረኞችን እንዳትቀሰቅስ እየተጠነቀቀች..አንድ ኮርነር ላይ ያለች ባዶ ባታ ሄደችና ኩርምት ብላ ቁጭ አለች፡፡በህይወቷ እንደዚህ አይነት ቦታ በስህተት እንኳን ተገኝታ አታውቅም፡፡ከአንድ ሰዓት በፊት ዘመናዊ ቤላ ቤቷ ውስጥ በሞቀ አልጋ ዋ ላይ የቀዘቀዘ ባሏን አካል አቅፋ ተኝታ ነበር ..አሁን ግን ወንጀል ሰርታ ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር ታስራ መገኘቷ ፊልም እንጂ እውነተኛ ታሪክ እየመሰላት አይደለም፡፡የሰው ልጅ ህይወት እንዲህ ቅፅበታዊ በሆነ አጋጣም እንዳልሆነ ይሆናል የሚል ግምት ኖሯት አያውቅም ነበር፡፡
‹‹ሰሎሜ አብቅቶልሻል…››ስትል ለራሷ ተናገረች፡፡እንደዚህ ልትል የቻለችው የፖሊሶችን የእርስ በርስ ንግግር ስላዳመጠች ነው፡፡

👍65❤11
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
/////
እሱም ጃኬቱን ይዞ ተከተላት፡፡እራሱ እያሸከረከረ የምትፈልገው መስሪያ ቤት ድረስ ወሰዳት፡፡
‹‹እ…ትጠብቀኛለህ ወይስ ትሄዳለህ?››
‹‹ኸረ በፍፁም.. አብሬሸ እገባለው››
‹‹ተው እዚሁ መኪና ውስጥ ጠብቀኝ..ከአንተ ጋር የሆነ ቦታ መሄድ እኳ በሴቶች አይን ክፉኛ መገረፍ ነው..ታውቃለህ የሰው አይን ደግሞ ያቃጥላል፡፡››
‹‹አረ ባክሽ…!!!››ሞተሩን አጠፋና ከመኪናው ወረዳ… እሷም ወረደች…ክንዷን ያዘና ወደውስጥ መራመድ ጀመረ..መራመድ አቅቷት እግሯቾ ተሳሰሩባት፡፡ግን ምርጫ አልነበራትም፡፡
ግቢ ውስጥ ገቡና ወደኢንፎሪሜሽን ዴስክ ሲደርሱ እሱን እንግዳ ማረፊያ ወንበር ላይ አስቀጠችውና እሷ ወደዛው አመራች…ከአስር ደቀቂቃ በኃላ ግን አንገቷን ደፍታ ወደእሱ ተመለሰችና ከጎኑ ቁጭ አለች፡፡
‹‹ምነው ፍቅር…አገኘሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አይ ..ጠመሙብኝ …ሰውዬው ከአራት አመት በፊት የዚህ ቢሮ ዳሬክተር ዴሬክቶሬት ነበረ…አሁን የት እንዳለና ቢያንስ ስልኩን እንዲሰጡኝ ነበር የጠየቅኳቸው…››
‹‹ቆይ ሰውዬው ምንሽ ነው?››
‹‹ምኔም አይደለም..ጭራሽም አላውቀውም..ግን ስለአባቴ መረጃ እንዳለው በሆነ መንገድ አውቄለው…እሱን ካገኘው አባቴ ይሙት ይኑር ማወቅ እችላለው፡፡››
የነገረችውን ያለምንም ጥርጣሬ አመናት…አሳዘነችው፡፡‹‹የሰውዬው ስም ማን ነው?››
ሙሉ ስሙን ነገረችው፡፡
‹‹ቆይ እንደውም ተነሽ›› ብሎ እጇን ይዞ ወደኢንፎርሜሽን ዴስኩ መራመድ ጀመረ..እሷ ምን ሊያደርግ እንደሆነ ሳይገባት ዝም ብላ ተጎተተችለት፡፡እንደደረሰ በትንሿ መስኮት ጎንበስ ብሎ ሲመለከት ..ሁለት ልጅ እግር ሴቶች ታዩት
‹‹ጤና ይስጥልኝ?›› ሲላቸው ሁለቱም አፋቸውን ከፍተው ፀጥ አሉት፡፡
‹‹እባካችሁ የሆነ ነገር ላስቸግራችሁ ነበር››
‹‹ምን ፈለክ…?ምን እንርዳህ?››አንደኛዋ ከመቀመጫዋ ተነስታ በመንሰፍሰፍ ጠየቀችው፡፡
‹‹እሷ እህቴ ነች..ከኃላው ያለችውን ፀአዳን ተመለከተችና‹‹ማንን ነበር ያልሽን?››ስትል ድጋሚ ጠየቀቻት፡፡
ፀአዳ ነገረቻት፡፡‹‹ቆይ እስኪ ››አለችና በኋላው በራፍ በመውጣት ወደእነሱ መጣች..እስቲ ተከተሉኝ ጋሽ ይርጋ በደንብ ያውቃሉ፡፡ጋሽ ይርጋ ማለት እዚህ መስሪያ ቤት ለ30አመት የሰሩ የመዝገብት ቤት ሰራተኛ ናቸው፡፡››የምታወራውን እያዳመጡ ከኋላ ተከተሏት‹‹አስቸገርን አይደል..?››አላት፡፡
ወደኃላ ዞራ‹‹‹አረ ችግር የለውም…ለዛውም ላንተ..ባይ ዘወዌ በጣም አድናቂህ ነኝ››አለችው
‹‹አመሰግናለው››ትህትና ባልተለየው የድምፅ ቃና መለሰላት፡፡
ከ10 ደቂቃ በኃላ የሰውየውን ሙሉ አድራሻ ይዘው ከቢሮ ወጡ…መኪና ውስጥ ገብተው መጓዝ እንደጀመሩን‹‹አየሽ አንቺን ሰምቼ ከስርሽ ቀርቼ ቢሆን ኖረ ምን እንደሚያጋጥምሽ ተመልከቺ››አላት በኩራት፡፡
‹‹እሱስ እውነትህን ነው..አድራሻውን እንዲህ በቀላሉ አላገኘውም ነበር›
‹‹እና ሽልማት የለኝም?››
‹‹አለህ..ምን ትፈልገለህ…?መክሰስ ልጋብዝህ?››
‹‹አዎ ግን ቤትሽ››
‹‹ቤትሽ?››ግራ በመጋባት አፍጥጣ አየችው፡፡
‹‹አዎ ምነው ላደርስሽ አይደል…አሁን አስር ተኩልነው… አስራሁለት ሰዓት ሳይሆን እዛ እንደርሳለን…ከዛ ቤትሽ መክሰስ ትጋብዢኛለሽ››
‹‹ለምን መክሰስ..እራት ቢሆንልህ አይሻልም….በዛውም ታድራለህ››
በፈገግታ ተሞልቶ‹‹አንቺ እኮ ምርጥ ነሽ…….››ሲል መለሰ
‹‹አረ አላደርገውም …..ጎረቤቶቼስ ምን ይሉኛል.?.››
‹‹ምንም ይበሉሽ……››
‹‹አይ አይቻልም ከፈለክ ውጭ ልጋብዝህ››
‹‹ውጭ አልፍግም….. ባይሆን እዛ እስክንደርስ አስቢበት››አላት፡
ቀጥታ ወደአዳማ እየነዳ ነው፡፡‹‹አሁን ታዲያ እንዴት ልታደርጊ ነው?››
‹‹ግራ ገብቶኛል..ግን ምን ቢሆን ነው አንድ አመት ሙሉ አማኑኤል ህክምና ላይ የቆየው››
‹‹ያው አማኑኤል ምን ሲኮን ነው የሚቆየው? ጭንቅላቱን አሟት ነዋ….፡፡››መለሰላት፡፡
‹‹ታዲያ ከዛ ሲወጣ ሁሉን ነገር ጣጥሎ ቤተሰቦቹ ጋር ቦንጋ እንደገባ ነው የነገሩን ..እንዴት እንደዛ አይነት ውሳኔ ወሰነ…?ይታይህ በአንድ ወቅት ትልቅ ስልጣን ላይ የነበረ ጉምቱ ባለስልጣን በዛ ላይ ዶ/ር ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ቦንጋ …ከቦንጋም ገጠር ጠቅልሎ ሲገባ አይገርምም፡፡
‹‹ይገርማል..ግን እደእኔ እንደእኔ የብልህ ውሳኔ ነው የወሰነው ..ይሄ ሰው ጭንቀትና የአእምሮ በሽታ ካለበት ትክክለኛ መረጋጊያ ቦታ ገጠር ነው..ይታይሽ እዚህ አዲስ አበባ እንኳን ለአእመሮ ህመምተኛ ለጤነኛው ሰው ትርምሱና ኳኳታው አስጨናቂ ነው…ይልቅ እኔ ያሳሰበኝ ….አሁን ምን ልታደርጊ ነው?፡፡የሚለው ነው፡፡
‹‹ቦታው ላይ ሄጄ እድሌን ሞክራለው››ስትል በእርግጠኝነት መለሰችለት፡፡
‹‹የእውነት ?››አለ ደነግጦ፡፡
‹‹አዎ….ይሄ እኮ ሲሪዬስ ነገር ነው….››
‹‹አውቃለው ..ግን እዛ ደረስ ሄደሽ ምንም ሊነግርሽ ባይችልስ…..?ማለቴ ከጤናው አንፃር ምንም ነገር ባያስታውስስ?››
‹‹ምንም ይሁን ምን ሰውዬውን ፊት ለፊት አግኝቼው መሞከር እፈልጋለው….ካለበለዚያ,--እረፍት አላገኝም፡፡››ስትል መለሰችለት፡፡
///
አቶ ቅጣው አዲሱ ክፍሉ በጣም ተመችቶታል…እንደውም በፊት ካለበት ክፍል ጋር ሲነፃፀር ከሲኦል ወደገነት የመዘዋወር አይነት ነው፡፡መኝታ አልጋ ያለው ..በቂ ብርሀን የሚያስገባ ንፁህ ክፍል ነው ያስገቡት፡፡በዛ ላይ እግሩም ሆነ እጁ ከሰንሰለት እስር ነፃ ስለሆነና ምግብም ሰዓቱን ጠብቆ ስለሚመጣለት ሰውነቱ ተአምራዊ በሆነ መልኩ እያገገመ ነው፡፡ክፍል ውስጥም ቢሆን እንደፈለገው እየተንቀሳቀሰ ቀላል ስፖርቶችን መስራት ችሏል…በዛ ምክንያት መንፈሱም ሆነ አካሉ ልዩ ለውጥ አምጥቷል፡፡
አሁን ቁጭ ብሎ መፅሀፍ ቁዱስ እያነበበ ነው፡፡ይሄንን መፅሀፍ ቅዱስ ከ10 ቀን በፊት ነበር ጠያቂው እና መካሪው መነኩሴ ናቸው አምጥተው የሰጡት፡፡ወዲያው ግን ማንበብ አልቻለም ነበር…፡፡አይኖቹ ለወራት ጨለማ ክፍል ውስጥ ስለከረሙ በቀላሉ ከብዣታ አገግመው ፊደል እየለቀሙ ለማንበብ ተቸግረው ነበር…ከጥቂት ቀናት ወደዚህ ግን እንደምንም ለማንበብ ችሏል፡፡
መለኩሴው የመጡ ቀን እንደተለመደው..ጠያቂ አለህ ተብሎ ነበር ከክፍል የተወሰደው፡፡የሚጠብቁት ክፍል ውስጥ ሲገባ እንደወትሮ በሰንሰለት እጅና እግሮቹ ተጠፍሮ የተቀደደ እና የተቦጫጨቀ ልብስ ለብሶ ሳይሆን በተለየ ሁኔታ ነበር፡፡እና በዚህ ሁኔታ ይደነቃሉ ብሎ ጠብቆ የነበረ ቢሆንም መነኩሴው ግን ልክ እንደወትሮ በተመሳሳይ ስሜት ነበር ያተናገሩት
ልጄ ይህ ግንኙነታችን የመጨረሻችን ነው… ልሰናበትህ ነው የመጣውት..›› ሲሉት ከዚ በፊት ተሰምቶት የማያውቀው ብቸኝነት ነው የተሰማው፡፡
‹‹አባ ለምን…?መመላለሱን ሰለቹ እንዴ?››
‹‹አይደለም… ልጄ ልሄድ ነው››
‹‹ወዴት ነው የሚሄዱት?››
‹‹ወደአባቴ…ወደፈጣሪ››
ሌላ ድንጋጤ፣‹‹እንዴ ያሞታል እንዴ?››
ፈገግ አሉ‹‹ አይ ልጄ ወደፈጣሪ ለመሄድ እኮ የግድ መታመም የለብንም…አምላክ በቃ ወደእኔ ና ብሎኛል…የዛሬዋን የመጨረሻ ቀኔ አንተንና ሌሎች ልጆቼን ለመሰናብት ነው የሰጠኝ..መቼስ ፡እሱ ለቸርነቱ ዳርቻ የለው… እኔ ሀጥያተኛውን መሞቻ ቀኔን ነገሮች ለመሰናበቻ ሚሆን ቀን ፈቅዶልኝ…ተመስገን ነው ..ተመስገን፡፡››
መነኩሴው የሚያወሩትን ሊገባው አልቻለም፡፡‹‹አባ እኔ ሞት የተፈረደብኝ ሰው እያለው እርሶ…..››

👍61❤15😱1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ተደግፋ በተቀመጠችበት ወንበር ላይ ተኮራምታ ነው ያደረችው፡፡በጥዋቱ ተረኛ ዶክተሮች መጥተው እህቷን ቢመለከቷትም ምንም የተቀየረ ነገር አላገኙም…..ይህ መሆኑ ደግሞ ራሄልን ይበልጥ ተስፋ ቢስና ረዳት አልባ ስሜት እንዲሰማት አደረጋት፡፡መፅሀፍ ቅዱሷን አነሳችና …አነስተኛ ወንበር እህቷ አልጋ አጠገብ በማድረግ የፀጋን ትንሽዬ ጣት ይዛ መፀለይ ጀመረች…አምላክ ለሁለተኛ ጊዜ ልቧን እንደማይሰብራት ተስፋ አድርጋለች፡፡ ድንገት ቀና ስትል ዔሊያስ የሕፃናት ሕክምና አይሲዩ በር ላይ ቆሞ ተመለከተችው፣ ልቡ ከብዷል። ስለ ፀጋ እንዳወቀ ወደ ሆስፒታል በፍጥነት ነው የመጣው።
ኤልያስ ወደ ክፍሉ ከመምጣቱ በፊት የህክምና ቻርቱን አንብቦ መድሃኒቱን ሁለት ጊዜ ፈትሾ ነበር ….የፀጋን አሁናዊ ሁኔታ እና እየተደረገላት ያለውን እንክብካቤ ከህፃናት ሐኪም ጋር ተወያይቷል. ሁሉም ምርመራዎች ታዝዘዋል እና ረፋድ ላይ ሌላ ሲቲ ስካን ማድረግ እንደሚያስፈልጋት ተወስኗል።ፀጋ ለጊዜው ራሷን ስታለች ግን የተረጋጋች ነበረች።በአሁኑ ጊዜ ኤልያስን በጣም ያሳሰበው ከፀጋ እጅ ጋር የተጣበቀችው እና የገረጣችው ሴት ሁኔታ ነው፣ በመጋረጃዎቹ ክፍተት መሀል አልፎ የሚመጣው የጠዋት ብርሃን ጭንቅላቷ ላይ አርፎ ይታያል .. መጽሃፍ ላይ አቀርቅራ እያነበነበች ነው ። ራሔል አንድ ጊዜ ስልክ ለመደወል ከፀጋ ጎን ከመነሳቷ ውጭ ሌሊቱን ሙሉ ከጎኗ ሳትንቀሳቀስ እንዳሳለፈች ነርሷ ነግራዋለች፡፡
ለመጨረሻ ጊዜ እሱ ቤት መጥታ በመጥፎ ሁኔታ ካስተናገዳት በኋላ ከእርሷ ጋር የመነጋገር መብት እንደሌለው ተሰማው። በወቅቱ ባለበት ንዴት ተነስቶ በሰራው ስህተት በጣም ተቆጭቶ ስህተቱን ለማረም በመፈለግ ለእሷን ለመደወል ፈልጎ ነበር ..እሷን ማስቀየሙ እንዴት ህይወቱን እንዳመረረበት ሊነግራት ፈልጎ ነበር ። ለምን በእሷ ላይ እንደዛ እንደሆነ እና ስለወላጆቹ ማንነት ያወቀው አዲስ መረጃ ውስጡን እንዴት እንደሰባበረው ሊያስረዳትና አዝናለት ይቅር እንድትለው ለመጠየቅ ፈልጎ ነበር…ግን አንዱንም ማድረግ ሳይችል ነው.. ቆይ በኋላ ..ቆይ ትንሽ ልቆይ ሲል ድንገት ዛሬ ጥዋት ከሆስፒታል ተደውሎለት ስለፀጋ በአደገኛ ሁኔታ መታመም እና ለሊቱን ሙሉ ሆስፒታል እንዳደረች የተነገረውና ሲሮጥ የመጣው፡፡
አዎ አሁን ትልቅ ሰው ነው… አዎ እሱ የበለጠ ጥበበኛ ነው። አዎን፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ጠንካራ ቦታ አለው።ያ ሁሉ ቢሆንም ግን ከወላጆቹ የተቀዳ ተመሳሳይ ድክመት በደም ሥሩ ውስጥ ሊፈስ እንደሚችል መገመቱ አልቀረም ። ብዙውን ጊዜ አንድ ልጅ ከወላጆቹ የሚወርሳቸው ጥሩም ሆነ መጥፎ የባህሪ ውርሶች እንደሚኖሩ ለማወቅ በቂ የታካሚ ታሪኮችን አንብቧል.፡፡ራሄል በቤቱ ልትጠይቀው ስትመጣ መረጃውን ለመቀበል እየሞከረ ነበር…በህይወቱ ውስጥም የት ቦታ ሊያስቀምጠው እንደሚችል ለማወቅ በመጣር ላይ ነበር…. በዛ ምክንያት ነበር እሷን ሊያስቀይማት የቻለው፡፡
በጸጥታ ወደ ክፍሉ ገባ፣ አይኑ ወደ ተቆጣጣሪ ማሽኖቹ ተመለከተ፣ እየፈተሸ፣ እየለካ። ወደ አልጋው አጠገብ ሲደርስ ራሄል .ተስፋ ቆርጣ ታነብ ከነበረው መጽሐፍ ቀና ብላ ተመለከተችው። ፊቷ እርብሽብሽ ብሏል እና ስታለቅስ ተመለከተ።
ፊቷ ላይ ያለው ህመም በግልፅ ይነበባል። ለሌሎች ታካሚ ወላጆች እንደሚያደርገው አይነት በርህራሄ የተሞላ እንክብካቤ ሊያደርግላት ከጎኗ ቆመ። ማድረግ የፈለገው ግን ወደ እቅፉ ጎትቶ ደረቱ ላይ ለጥፎ ግንባሯን ደጋግሞ ለመሳም ነበር፡፡ ሊያበረታታት እና ሊያፅናናት ነበር ሚፈልገው ።
‹‹ደህና ትሆናለች?››አላት፡፡
ራሔል ቀና ብላ ተመለከተችው፣
‹‹ለአሁን የተረጋጋች ናት›› ሲል አከለበት፡፡
በዝምታ እያዳመጠችው ነው፡፡
‹‹ሲቲ ስካን ሰርተንላታል እና ስለ ደም ዝውውሯ ከላቦራቶሪ ውጤት በኋላ እናውቃለን ።››
የራሄል እንባ ዝርግፍ አለ…ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቆመች ፡፡በእጇ ይዛ ነበረውን መፅሀፍ አጠፈችውና ማውራት ጀመረች
‹‹ጉንፋን ብቻ ነበር ያመማት..ድንገት በዚህ ደረጃ እንዴት አቅም ልታጣና እራሷን ልትስት ቻለች?››ስትል ጠየቀችው፡፡
ዔሊያስ ራሱን ነቀነቀ።
‹‹አናውቅም… ከዚህ በፊት እንደነገርኩሽ የፀጋ የጤና ችግር ተደራራቢና የተወሳሰበ ነው….. አንዱ በሽታ ሲጀምር ሌላውም ይከተላል…አሁን በጣም አደገኛ የሆነው በአእምሮዋ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ነው፡፡
‹‹ከዚህ ስቃይ ትወጣለች?››
‹‹በአጠቃላይ ያቺ ትንሽ ልጅ ሳንባዋ ጥሩ ነው፤ልቧ ጠንካራ ነው። ከዚህ በሽታ እንደምታገግም አምናለሁ።››
ራሄል በሚናገርው ነገር ላይ እርግጠኛ እንዳልሆነ ተረዳች፡፡ ‹‹እግዚአብሔር በእርሱ እንድንታመን እንዴት እንደሚነግረን እና የልባችንን መሻት እንዴት እንደሚሰጠን እያነበብኩ ነበር…ይህን ታምናለህ?››ዔሊ ወደ ፀጋ ከዚያም ደግሞ ወደ ራሄል እያፈራረቀ ተመለከተ፡፡
‹‹እኔ በዚህ ወቅት ምን ማመን እንዳለብኝ አላውቅም። ለፀጋ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን እንደሆነ አውቃለሁ። እና እሷን በሕይወት ለማቆየት ባለን ቴክኖሎጂ ላይ እምነቴን ማሳረፍ እመርጣለው።››
ራሄል የደከመ ፈገግታ ፈገግ አለችለት‹‹ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ እግዚያብሄርን አመንኩኝ እና አሳዘነኝ. ..ማለቴ ስለ ኪሩቤል እያወራሁ ነው?››ራሷን ነቀነቀች፣ ከዚያም ቀና ብላ ተመለከተችው…በዛ ቅፅበት ነርሷ ወደ ፀጋ አልጋ መጣች።
‹‹ነርሷ ለሰዓታት እዚህ እንደተቀመጥሽ ነገረችኝ…ሄደን ቡና ብንጠጣ ምን ይመስልሻል? እስክንመጣ እዚህ ያለውን ነገር ነርሷ ትከታተለዋለች?›› አለና በቀስታ እጇን ጎተታት።
‹‹እኛ ስንሄድ ፀጋ ደህና ትሆናለች?።››ስትል ጠየቀች፡፡
ነርሷ እያስተካከለችው ያለውን መቆጣጣሪውን ቀና ብላ ተመለከተች..ወደ ዶ/ር ኤልያስ ተመለከተችና ‹‹አንድ ነገር ከተቀየረ ወዲያውኑ አሳውቅሃለሁ››አለችው ።
‹‹ለአሁን ነገሮች ደህና ሆነው ይታያሉ።››ራሄል ወደ ፀጋ ተመለከተች፣ ፡፡ጥላት መውጣቷ ብዙም ምቾት አልሰጣትም፡፡
በለሆሳሳ‹‹እሺ ..እንዳልክ እንሂድ››አለች ።ኤሊያስ መጽሐፍ ቅዱስን ከእጇ ወስዶ ከፀጋ አልጋ አጠገብ ባለው ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው። ከዚያም ከክፍሉ ይዟት ወደ ካፍቴሪያ ሄደ፡፡ወንበር ስበው ፊት ለፊት እየተዩ ተቀመጡ፡፡የሚፈልጉትን አዘዙ፡፡
አሁንም ከፀጋ ውጭ ምንም ነገር በአእምሮዋ የለም..‹‹ትናንት ከሰዓት ነው፡፡ትንሽ እንደመሻል ብሏት ነበር… ከእኔ በቅርብ ርቀት ሶፋው ላይ ሆና ስትጫወት ነበር…ድንገት አንሸራተታት እና ለስላሳ የቆዳ ሶፋ ላይ ወደቀች እና በጭንቅላቷን ወደኋላ ተኛች… ከዛ ተዝለፍለፈችብኝ..ጮህኩ..ወዲያው አምቡላንስ ተጠራ…ወደዚህ ይዘውን መጡ…..ይሄው እየባሰ ከመሄድ ውጭ ምንም መሻሻል አላየሁም፡፡››
‹‹አይዞሽ……ሁሉም ነገር ሰላም ይሆናል››
ያዘዙት ነገር መጣላቸው…..እሷ ጥቁር ቡና ብቻ ነበር ያዘዘችው፡፡
ትኩር ብሎ ሲያያት ያዘችው….ፀጉሯን ከፊቷ ላይ ገፋች እና ‹‹የባቡር አደጋ የደረሰብኝ መስያለው አይደል?››
ከዚህ በፊት አይቷት ከነበረው በተለየ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ እየተመለከታት ነው ፡፡የለበሰችው ልብስ የተዘበራረቀ እና የተዝረከረከ አይነት ነው… ምንም አይነት ሜካፕ አልተጠቀመችም እና ፊቷ ተጎሳቅሏል እና ደክሟታልል።

❤59👍1🥰1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት__በዘሪሁን_ገመቹ
……
ከባለፈው ክፍል ተቆርጦ የቀረ
///
ዝግጅቱ በተዘጋጀበት የከተማዋ ግዙፉ ሆቴል የጁኒዬርን እጅ ይዛ ስትገባ ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማት፡፡ ለስለስ ያለ ምርጥ ሙዚቃ እና እዚህማ እዛም በፈገግታ የታጀበ ሳቅ ይሰማ ነበር፡ከበርካታ ሰዎች ጋር አስተዋወቃት…ከብዙ ሰዎች ጋር የማውራት እድል አገኘች፡፡ አንዳቸውም ውይይቶች በእናቷ ግድያ ዙሪያ ያተኮሩ አልነበሩም። ያ በራሱ መንፈስን የሚያድስ ለውጥ ነበር። እረፍት ላይ እንዳለች መስሎ ተሰማት። ጁኒየር በመጠጥ ተፅዕኖ ውስጥ ገብቶ ሚስጥሩን ለእሷ አሳልፎ እንደሚሰጣት ቀድሞውንም አላመነችም። እሷ ምንም አስገራሚ ኑዛዜዎችን የመስማት ዕድል እንደሌለት ገምታ ነበር።ቢሆን ከምሽቱ አንድ ጠቃሚ ነገር ሊወጣ ይችላል የሚል ተስፋ መሰነቋ ግን አልቀረም. ፡፡
ከሁሉም በላይ፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ ከአቶ ፍሰሀ እና ከኩማደሩ ጋር በደንብ ከሚተዋወቁ እና ባህሪያቸውንና ድብቅ ተግባራቸው ከሚያውቁ ሰዎች ጋር የመቀላቀል እድል አላት፡፡
እንደተለመደው "ነጭ ወይን"ይዛ እየጠጣች ነው ጁኒዬር ከጎኗ አለ፡፡
"ሙዚቃው የእኔ ጣዕም አይደለም ነገር ግን መደነስ ከፈለግሽ እኔ ታዛዥ ነኝ.››አላት
ጭንቅላቷን በአሉታ ነቀነቀች። "አመሰግናለሁ …እኔ ከመደነስ ይልቅ ማየት እመርጣለሁ።››
ከጥቂት ዘፈኖች በኋላ ጁኒየር ጠጋ ብሎ በሹክሹክታ፣"እናትና አባቴ እዛ ጋር ናቸው….ሰላም እንበላቸው›› አለና..እየጎተተ ይዟት ሄደ፡፡
አለም በዳንስ ወለል ዙሪያ ለመመገቢያ ወደተዘጋጁት የጠረጴዛዎች ስብስብ አብሮት ሄደ። ሳራ ጆ እና አቶ ፍሰሀ በአንድ ላይ ተቀምጠዋል። ደረሱና
"ጤና ይስጥልኝ ወይዘሮ ሳራ ዛሬ ማታ ቆንጆ ሆነሻል።››አለቻት አለም
‹‹አንቺም እንደዛው ….እንኳን በሰላም መጣሽ››ስትል መለሰችላት፡፡
ሰላምታ ተለዋውጠው አንድ ጠረጴዛ ከበው የየግላቸውን መጠጥ በመጠጣት ጫወታቸውን ጀመሩ፡፡
‹‹የሙስጠፋን የሞተ አካል ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘሽው አንቺ እንደሆንሽ ሰማሁ››።ሲል ኮስተር ባለ ነገር ጫወታውን የጀመረው አቶ ፍሰሀ ነበር፡፡
"አባዬ ይህ ፓርቲ ነው…አለም ስለ እንደዚህ አይነት መጥፎ ነገር ማውራት አትይፈልግም."አለ ጁኒየር።
"አይ፣ ምንም አይደለም፣ ጁኒየር፣ ይዋል ይደር እንጂ እኔ ራሴ አነሳው ነበር።››
"ጥሩ ..ከሱ ጋር የተገናኘሽው በአጋጣሚ ነው ብዬ አላስብም።ያንን ደደብ ሽማግሌ ለምን ነበር ልታገኚ የፈለግሽው?"
"አይ….።››በማለት ከሙስጠፋ ጋር የነበራትን የስልክ ውይይት በዝርዝር ነገረቻቸው፡፡
‹‹ያ ውሸታም ሽማግሌ ሊያታልልሽና አንቺን አጓጉቶ ገንዘብ ሊቀበልሽና ..እግረ መንገዱንም እኔን ለመበቀል ሲያደባ ነበር…ግን ፈጣሪ የልቡን ተንኮል አይቶ ለሌላ ወንጀለኛ አሳልፎ ሰጠው፡፡››
"ኦህ፣ እንዴት በእርግጠኝነት እንደዛ ደመደምክ..?››
‹‹ ሙስጠፋ ከሰሎሜ ጋር ወደዚያ በረት ውስጥ የገባው ማን እንደሆነ አይቶ ሊሆን ይችላል፣ ግን የእውነት እንደሚለው ሰው አይቶ ከሆነ ሊያይ የሚችለው ሊቁን ነው።››ሲል ጁኒዬር አከለበት፡፡
አለም ..ለመናገር የፈለገውን ከተናገረ በኋላ …እንዲከራከር እድል አልሰጠችውም ፣ የሙስጠፋ ርዕስ ለጊዜው ባለበት እንዲቆም አደረገች ።መጠጣቸውን እንደጨረሱ፣ አቶ ፍሰሀ እና ጁኒየር ሴቶቹን ባሉበት ጥለው ሌሎች የቢዝነስ ሰዎችና ለማነጋገር ተያይዘው ሄዱ፡፡
ከሳራ ጆ ጋር ለረጅም ደቂቃዎች መቆየት ከባድ ነው ..ከእሷ ጋር ማውራትም ቀላል እንደማይሆን አሰበች፣ቢሆንም እንደምንም እራሷን አጀግና "ለረጅም ጊዜ የዚህ ማህበር አባል ናችሁ?"የሚል ጥያቄ ሰነዘረችላት፡፡
"ፍሰሀ ከመስራች አባላት አንዱ ነበር" ስትል ሳራ ግድ በሌለው ሁኔታ መለሰችላት ።
በመድረኩ ላይ በርካንታ ጥንዶች እየደነሱ እና እየተጎነታተሉ ይታያሉ፡፡አለም"አቶ ፍሰሀ በእያንዳንዱ የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እጁ ያለበት ይመስላል " ስትል አስተያየት ሰጠች.
"ትክክል ነሽ…የከተማዋ ጠባቂ እንደሆነ ነው የሚያስበው… እየሆነ ያለውን ሁሉ ማወቅ ይፈልጋል….በዛ ምክንያት ..ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ሲል ሁሉም ነገር ውስጥ ይገባል››ሳራ በረጅሙ ተነፈሰች እና ንግግሯን ካቆመችበት ቀጠለች "አየሽ ፍሰሀ በእያንዳዱ የከተማው ኑዋሪ …በባለስልጣናቱም ዘንድ ሆነ በነጋዴዎች ክበብ የመወደድ ፍላጎት አለው
፤ እሱ ሁል ጊዜ ፖለቲከኛ ነው ፣ ››
አለም እጆቿን ከአገጯ በታች አጣጥፋ በክርኖቿ ጠረጴዛው ላይ ተደግፋ። "አንቺ ያ.. አስፈላጊ ነው ብለሽ ታምኚያለሽ?"
"አይ አላንም።" አለችና ለመጀመሪያ ጊዜ አለምን በትኩረት ተመለከተች።
"ጁኒየር ለአንቺ የሚያሳይሽን እንክብካቤ ብዙም ትርጉም አትስጪው››በማለት አዲስ ርዕስ ከፈተች፡፡
"አቤት…ምን ማለት ነው?"
"ልጄ የሚያገኛት ሴት ሁሉ የማሽኮርመም ልክፍት አለበት እያልኩሽ ነው ››
አለም ቀስ ብላ እጆቿን ወደ ታች አወረደች። ንዴቷ ወደ ውስጥ ገባ፣ ነገር ግን ድምጿን ዝቅ አድርጋና እራሷን እንደምንም ተቆጣጥራ “ወ/ሮ ሳራ አንድምታይው ተናድጃለሁ።››
ሳራ ጆ በግዴለሽነት አንድ ትከሻ ከፍ ዝቅ አደረገች‹‹ግድ የለኝም ››የሚለውን መልዕክት ለማስተላለፍ ፈልጋ እንደሆነ አለም በግልፅ ገብቷታል፡፡
"ሁለቱም ወንዶቼ ቆንጆዎች ናቸው እና እነሱም ያንን ስለሚያውቁ አላግባብ ይጠቀሙበታል..አብዛኛዎቹ ሴቶች ደግሞ የእነሱ ማሽኮርመም ትርጉም የለሽ እንደሆነ አይገባቸውም."
" እርግጠኛ ነኝ ፍሰሀን በተመለከተ ያልሽው እውነት ነው፣ ስለ ጁኒየር ግን አይመስለኝም።
ሶስት የቀድሞ ሚስቶች ስለ እሱ ማሽኮርመም ከአንቺ ጋር ላይስማሙ ይችላሉ።››
"ሁሉም እሱን በተመለከተ ተሳስተው ነበር።"
"እናቴስ? እሷም እሱን በተመለከተ ታሳስታ ነበር?"ሳራ ባዶ አይኗን አሌክስ ላይ በድጋሚ ተከለች።
"አዎ ተሳስታለች ፤አንቺም እንደሷ ነሽ ….ታውቂያለሽ አይደል?።"
"እኔ?"
" አዎ!!አለመግባባት መፍጠር ያስደስትሻል። እናትሽ አስጨናቂ ነገሮችን በመፍጠር እርካታ አልነበራትም። ልዩነቱ አንቺ ከሷ በላይ ችግር እና መጥፎ ስሜትን በመፍጠር የተሻልሽ መሆንሽ ብቻ ነው። ብዙውን ጊዜ ብልሀት የሚጎድልሽ ቀጥተኛ ሴት ነሽ።››ዓይኖቿን ከአለም ጀርባ አሻግራ አንድ ሰው ትመለከት ጀመረ፡፡
"ደህና አመሻሽ ሳራ "
"ዳኛ ዋልልኝ" ጣፋጭ ፈገግታ በሳራ ጆ ፊት ላይ ታየ።በዛ ቅፅበት የሚመለከታት አንድ ሰው ከሴኮንዶች ቀደም ብሎ ከፍተኛ ንዴት ላይ እንደነበረች በጭራሽ መገመት አይችልም
‹‹… ሰላም ስርጉት።››አለም በሳራ ያልተጠበቀ ትችት የተናደደ ፊቷን ወደኋላ አዞረች። ዳኛው የእሷን እዛ መገኘት እንደትልቅ ጥፋት የቆጠረ እንደሆነ በሚያሳብቅ ስሜት ትኩር ብሎ ያያት ጀመር።
" ክብርት አቃቢት ህግ "
"ጤና ይስጥልኝ ክቡር ዳኛ " ከሳቸው ጎን የቆመችው ሴት አለምን ከሱ ጋር የሚዛመድ ተግሳፅ ተመለከተች ፣ ዳኛው የሴትየዋን ክንድ ነካ አድርገው ወደ ሌላ ጠረጴዛ ሄዱ
"ሚስቱ ናት?" አለም ለሳራ ጥያቄ አቀረበች ፡፡
ሳራ በመደነቅ "በእግዚያብሄር ስም….አረ አይደለችም..የሱ ሴት ልጅ ነች ስርጉት…የመጀመሪያ እና ብቸኛ ሴት ልጁ ነች፡››
ከላይ የለጠፍነው ከባለፈው ክፍል ተቆርጦ የቀረ ነው።
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
"ሰሎሜና ስትሞት ደስ ብሎኝ ነበር."
የጥርጣሬ ብልጭታ በአለም አይኖች ውስጥ ዘለለ፣ ‹‹አልዋሽሽም…የሆነ ተራራ ከጭንቅላቴ እንደወረደ እፎይታ ነው የተሰማኝ ››

❤56👍3👎1