አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

‹‹ለማንኛውም ተመልሼ መጣለሁ..ና ወደቢሮ እንመለስ …››ብለው ሰለሞንን አስከትለው ወደቢሯቸው ተመለሱ፡፡
‹‹በል አሁን ንገረኝ ልጄ እንዴት ናት?››
‹‹እኔ እንጃ እንዴት እንደሆነች አለውቅም?››

‹‹ማለት ደብዳቤውን ስትሰጥህ አይተሀት የለ..?ከስታለች…እንዴት ነች ተጎሳቁላለች?ልቧስ እንዴት ነው…?ታውቃለህ አይደል የልብ በሽተኛ ነች››
‹‹ደብዳቤውን በአካል መጥታ አይደለም የሰጠችኝ..ማለቴ ቢሮዬ በሚገኝበት ህንፃ መታጠቢያ ቤት አስቀምጣ ስልክ ደወለችና እንድወስድ አዘዘችኝ..ስልኬን ከየት እንዳገኘች አላውቅም…ሁሉን ነገር የተነጋገርነው በስልክ ነው…በወላጆቼ ትዳር መካከል አለመግባባት አለና እርዳቸው ብላ መቶ ሺ ብር በደብተሬ አስገብታለች….መልሼ ስልኳን ብደውልላት አይሰራም…እራሴ ስፈልግህ መልሼ አገኝሀለው ነው ያለችኝ..እኔ የማውቀው ይሄኑን ነው፡፡››
ኪሱ ገባና ቢዝነስ ካርዱን አውጥቶ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠ‹‹ይሄው አድረሻዬ …ቢሮዬ ሜኪሲኮ ኬኬር ህንፃ ላይ ነው….ዝግጁ ስትሆኑ ደውሉልኝ….ካልሆነም ይንገሩኝ ገንዘቡን ተመላሽ አደርጋለው፡፡አሁን ልሂድ፡፡››
‹‹እሺ በቃ…አመሰግናለው..አሁን ተረጋግቼ ማሰብ አለብኝ..ደውልልሀለው፣ልጆቹ ይሸኙሀል››አሉት፡፡
እሱም ሌላ ምንም ተጨማሪ ቃላት ሳይናገር  ቦርሳውን ያዘና ሹልክ ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡
በሁለተኛው ቀን የሚጠብቀው ቁጥር ተደወለ…የልብ ምቱ ፍጥነት እንደጨመረ እየታወቀው ነው…እንደምንም ለመረጋጋት ሞከረና አነሳው፡፡
‹‹አቤት …..››
‹‹ሃይለ ልኡል ነኝ….››
‹‹አወቅኮት፣ ሰላም ኖት ?››
‹‹ደህና ነኝ….እቤት ብቅ ብትል ይመችሀል?››ሰከን ባለና በተረጋጋ የድምፅ ቅላፄ ጠየቁት፡፡
‹‹መቼ…አሁን››
‹‹አዎ አሁን ብትመጣና ..በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ብናወራ ደስ ይለኛል››
‹‹እሺ….ከአንድ ሰዓት በኃላ እደርሳለሁ..››
‹‹አመሰግናለሁ….ከባለቤቴ  ጋ ሆነን እንጠብቅሀለን››

‹‹ጥሩ በቃ መጣሁ….››ስልኩን ዘጋና ቀጥታ ቦርሳውን ይዞ ከመቀመጫው ተነሳ….ወደፊት ለፊተኛው ክፍል ሲገባ ለሊሴ ፊትለፊቷ ያለውን ኮምፒተር ከፍታ አፍጥጣ ነበር….
‹‹ልወጣ ነው…ዘሬ ተመልሼ የምመጣ አይመስለኝም››
‹‹እሺ በቃ..ባለጉዳይ ከመጣ…ለነገ ቀጠሮ ይዤላቸዋለው››አለችው፡፡
‹‹ጥሩ እንደዛ አድርጊ….መልካም ውሎ››ብሏት ቢሮውን ሙሉ በሙሉ ለቆ ወጣ፡፡
መኪናውን እራሱ እያሽከረከረ….አእምሮውም በሀሳብ እየተሸከረከረ ቀጥታ ወደአቶ ኃይል ልኡል ቤት ነዳው…ምን እንደሚጠብቀው አያውቅም..እርግጥ ና ብለው ሲጠሩት በጣም በተረጋጋ እና በተለሳለሰ ድምፅ ነው…ግን ያንን ያደረጉት ሁሉ ነገር ሰላም ነው ብሎ በማመን በገዛ እጁ ሄዶ እጅ እንዲሰጣቸው አስበው ከሆነስ? ይሄ የእቅዳቸው አንዱ አካል ቢሆንስ?››እራሱን ደጋግሞ ጠየቀ…በሀሳብ ከመብሰልሰል ለደቂቃ እንኳን ሳያነጥብ ሰፈራቸው ደረሰ …መኪናውን ከሩቅ አቆመና ደወለ፣ስልኩ ተነሳ››
‹‹ኪያ እንዴት ነሽ?››
‹‹ሰልም ነኝ….አንተስ?››
‹‹አለው…እዛ የነገርኩሽ ቦታ ጠርተውኝ እየሄድኩ ነው››
‹‹የት?››
‹‹አንቺ ደግሞ …የጠፋችው ልጅ ወላጆች ጋር ነዋ››
‹‹ና ብለው ጠሩህ?››
‹‹አባትዬው አሁን ጠርተውኝ በራፋቸው ጋር ደርሼ ወደውስጥ ዘልቄ ከመግባቴ በፊት መኪናዬን አቁሜ ነው የምደውልልሽ››
‹‹ምነው ፈራህ እንዴ?››
‹‹አይ ለምን ፈራለሁ….ማለቴ ከገባሁ በኃላ በፀጥታ ከእነሱ ጋር ለመነጋገር ስልኬን ስለማጠፋ ድንገት ደውለሽ ስልኬ ካልሰራልሽ እንዳታስቢ ብዬ ነው››
‹‹አይ ጥሩ አደረክ…ለማንኛውም እንደወጣህ ደውልልኝ››

‹‹እሺ….ኪያ …ቸው››ስልኩን ዘጋ፡፡ቀለል አለው፡፡‹‹ቢያንስ አሁን እዛው በገባሁበት ከቀረሁ በቀላሉ አድርሻዬን ታገኘዋለች፡፡››ብሎ አሰበና መኪናውን አንቀሳቀሰ….የውጭ በራፍ ጋር ደረሰና ክላክሱን አንጣረረ….ወዲያው በራፉ ተከፈተና…ጠብደል ጥቁር ሱፍ የለበሰ ጠባቂ ወደእሱ መጣና …ማንነቱን ጠየቀው‹‹አዎ አንተን እየጠበቁሀ ነው››ብሎት መልሶ ሄደና በራሀፍን ከፈተለት ….ወደውስጥ ዘልቆ ገባና ከአራት መኪና በላይ ወደቆመበት ገራዥ በመሄድ ክፍት ቦታ ፈልጎ መኪናውን አቆመና ሞተሩን አጥፍቶ ወረደ…..ጠባቂው እየመራ ሳሎን በራፍ ድረስ ወሰደውና ወደኃላ ተመለሰ…
እራሳቸው አቶ ኃይለልኡል ነበሩ በራፍ ድረስ መጥተው በወዳጅነት አቀባበል አቅፈው የተቀበሉት….ወደሳሎን ይዘውት ዘለቁ…መጀመሪያ ምግብ እንብላ…‹‹እስከአሁን ቁርስ ሳንበላ እየጠበቅንህ ነው››አሉት፡፡
‹‹ዝም ብላችሁ ተቸገራችሁ….እኔ እኮ በልቼ ነበር የመጣሁት››
‹‹ቢሆንም…ና ቁጭ በል….››ቀድመው ተቀመጡና የሚቀመጥበትን ቦታ አሳዩት…ተቀመጠ
‹‹ልጇች..ስንዱን ጥሯት››
ሰራተኞቹ ግራ የገባቸው ይመስል ዝም ብለው ሰውዬው ላይ አፈጠጡ፡፡
‹‹ምን አፍጥጣችሁ ታዩኛላችሁ…ክፍሏ ነች…አንዳችሁ ሂዱና እንግዳው መጥቷል ነይ በሏት…የተቀራችሁ ቁርሱን አቅርቡ››
ሁሉም ትዛዙን ሰምተው ተበታተኑ
‹‹እንዴት ነው …ወ.ሮ ስንዱ ተሸላቸው?፡፡››ሰለሞን ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ…እድሜ ላንተ የልጃችንን ሰላም መሆን ዜና ካሰማሀን በኃላ ተሸሏታል…የተሳሰረ የነበረ እግሯቾም ታምራዊ በሆነ ፍጥነት ተላቀውላት አሁን በራሷ መራመድ ችላለች፡፡››
‹‹በእውነት በጣም እስደሳች ዜና ነው…ያልኳችሁን ስላመናችሁኝ ደስ ብሎኛል››
‹‹አይ እሱ እንኳን በቀላሉ አላመንህም…ስላአንተ ለሁለት ቀን ሳስጠና ነበር…በዛ ላይ ከእሷ ጋር የተደዋወላችሁትን የስልክ ልውውጥ አግኝቼ አዳምጬዋለው…የልጄን ድምፅ ሰምቼያለው…በሰላምና በጤና መኖሯን ያረጋገጥኩት ከዛ በኃላ ነው…በቀላሉ ላምንህ

ሳላልቻልኩ ይቅርታ….ደግነቱ እንዲህ በቀላሉ እንደማላምንህ ልጄ አስቀድማ ነግራሀለች…ይገርማል ይሄን ያህል ጠልቃ ምታውቀኝ አይመስለኝም ነበር››
‹‹ልጆት አይደለች…ልጆች እኮ ወላጆች የሚያደርጉትን እያንደንዱን ድርጊት በጥልቀት ያስተውላሉ ፣በአእምሮቸውም ይመዘግባሉ…ስለወላጆቻቸው በጥልቀት ነው የሚያውቁት››
‹‹ትክክል ነህ ..››ንግግራቸውን በወ.ሮ ስንዱ መምጣት ምክንያት አቆረጡ….ሰሎሞን ከመቀመጫው ተነስቶ በትህትና ሰላምታ ተቀበላቸው….ወንበር ስበው ተቀመጡ..ቁርስ ቀረበ….ጠረጴዛው ሙሉ ቢሆንም ያን ያህል አፒታይት የነበረው ሰው አልነበረም….ቁርሱ እንደተጠናቀቀ ከወንበራቸውን ተነስተው አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የአቶ ኃይለልኡል ቢሮ ተያይዘው ሄዱ.. ወደሶፋው ሄዱና ተቀመጡ..፡፡
‹‹እንግዲህ አሁን መነጋገር እንችላለን››አቶ ኃይለልኡል ጀመሩ
ወ.ሮ ስንዱ ተቀበሏቸው‹‹ልጄ እንደው አባክ እርዳን ..ልጃችን ወደቤቷ እንድትመለስ አሳምናት››ከመቀመጫቸው ተነስተው እግሩ ላይ ሊደፉ ሲሉ በአየር ላይ ትከሻቸውን ያዘና መልሶ አስቀመጣቸው፡፡
‹‹አይገባም..እኔ እዚህ ያለሁት እኮ ልረዳችሁ ነው..የእኔም ምኞትና ፍላጎት ያ ነው››
‹‹እኮ አድርገዋ….ያለችበትን እንድትነግርህ አሳምናት›››
‹‹አይ በእንደዛ አይነት ሁኔታ እንኳን ምትስማማ አይመስለኝም..እሷ ወደቤቷ ምትመለስበትን አንድና ብቸኛ መንገድ በግልጽ ተናግራለች…ምንም አይነት ችግር ሳይፈጠር ደስተኛ ሆና ወደቤቷ እንድትመለሰ ያለችውን አድርጎ ማሳየት ብቻ ነው ያለብን፡፡››
‹‹ይሄውልህ ልጄ…ልጃችን ያለችውን ለማድረግ እኔም ባለቤቴም ተስማምተናል…..ለዛ ቃል እንገባለን..አንተ ትረዳናለህ እኛም በመሀከላችን ያለውን ችግር እንፈታዋለን..››
👍7613
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

የገመሪ ተራራ

የተደበቀው ሚስጥር እንዳይወጣበት ከዛሬ ነገ እያለ እንደሌባ በሩቁ ይሸሻል፡፡ የሱ ጉዳዩ ከተፈፀመለት በኋላ፤ ተመልሶ ወደ ያሬድ ቤት አልሄደም፡፡ ጓደኛው ወደ ውትድርና መግባቱን ሲሰማ ስጋትና
ጭንቀት አላስቀመጠውም፡፡ የአበበችን ዓይን ማየት አልቻለም፡፡

ያለውን ንብረት እንዳይነቃበት በከፊል ሸጠ፡፡ ከእድላዊት ጋር ሃገር ለቀው ለመሄድ ተስማሙ፡፡ ለመንገድ የሚሆን በሶና ቆሎ አዘጋጁ፡፡ ስደትን መርጠዋል፡፡ ልጃቸውንና እናት አባታቸውን ያለጧሪ ፣ ቀባሪ ትተው ለመሄድ ተነሱ፡፡ አንጀታቸው አዘነ፡፡ አይናቸው አነባ፡፡ ልባቸው ግን ጨክኗል፡፡ ቤተሰቦቻቸውን ፀበል ነው የምንሄደው ብለው ዋሽተዋቸዋል፡፡ ጨለማ በተቀላቀለበት ሌሊት በዕለተ ሰንበት ሰው ወደ ቤተክርስትያን ለመሳም  በሚሄድበት ሰዓት እነሱ ወደ አረብ ሃገር ስደት ሆነ፡፡ ከሰም ጅረቱን አቋርጠው በደብረብርሃን አድርገው ወደ ወሎ ባቲ ተጓዙ፡፡

ከሶስት ቀን ጎዞ በኋላ ባቲ ከተማ እንደደረሱ በቀይ ሸራ ወደ ተሸፈነች የሻይ ድንኳን ጎራ አሉ፡፡

በጦስኝ ቅመም የተንቆጠቆጠ የባቲ ሻይ አዘዙ፡፡

አንድ መልከ መልካም ወጣት ወደ ሻይ ቤቷ ገባ፡፡

"ቶሎ በል አንድ ሻይ በዳቦ ስጠኝ ? ሰዎች እየጠበቁኝ ነው አለ ፤ ወጣቱ እየተጣደፈ፡፡

የሻይ አስተናጋጁ "እነማን ናቸው የሚጠብቁህ"? አለ፡፡

ወደ አረብ ሃገር የሚሄዱ ናቸው፡፡ ከመሃመድ ጋር አገናኝቻቸው ልመጣ ነው አለ፡፡ ያዘዘውን ሻይና ዳቦውን ሲበላ ለተመለከተው የቸኮለ ሰው ሳይሆን ከጎሬ የወጣ ጅብ ይመስል ነበር፡፡

ወደ አረብ ሃገር በየት እንደሚኬድ አያውቁም፡፡

"ይሄንን ልጅ እንጠይቀው" ? አለች እድላዊት፡፡ ወጣቱ ስለ አረብ ሃገር ሲያወራ ሰምታ፡፡

ተመስገን ለመጠየቅ ፈራ ተባ አለ፡፡ ኧረ! ለመሄድ ተቻኩሏል ሳይነሳ ጠይቀው አለች ? ደግማ፡፡

"ወንድም" ? አለ ፤ ተመስገን፡፡ ከሻይና ከዳቦ ጋር እየታገለ ያለውን ወጣት፡፡

"አቤት ጠራኸኝ" ? አለ ፤ ወጣቱ፡፡

"አዎ፤ አንድ ነገር ትተባበረኛለህ ?፡፡

አላመነታም፡፡ "ምን ልተባበራችሁ? ወደ አረብ ሃገር መሄድ ትፈልጋላችሁ? ፡፡

"አዎ፤ ለመሄድ ፈልገን ነበር ፡፡

"እኔ ደላላ ነኝ፡፡ ከሚልከው ሰው ጋር እንዳገናኛችሁ፡፡ ከፈለጋችሁ ሁለታችሁም አርባ አርባ ብር ክፈሉኝ ብሎ ለመሄድ ተነሳ፡፡

"እሽ እንከፍልሃለን፡፡ ታዲያ አሁን የት ልትሄድ ነው? አለው፡፡

"ሰው እየጠበቀኝ ነው፡፡ ቼኩያዓለሁ ፤ ከሄዳችሁ ብሩን አምጡና ተነሱ እንሂድ አላቸው፡፡

"እሽ" አሉ፡፡ የያዙትን ገንዘብ ከፍለው ደላላውን ተከተሉት፡፡

ወደ ውጭ ሃገር የሚልኳቸውን የሰዎች ማሰባሰቢያ ቤት ደረሱ፡፡ መሃመድ ለሚባል ደላላ አስረክቧቸው ተመለሰ፡፡

መሃመድ ተቀብሎ ወደ ውጭ ሃገር ሊወስዳቸው ካሰባሰባቸው ስምንት ሴትና አስር ወንዶች ጋር ቀላቅሎ በራሱ መኪና አሳፍሮ አስኢት ከተማ አደረሳቸው፡፡

እሱም ለአስኢት ደንበኛው ለከድር አስረክቧቸው ተመለሰ፡፡

የአስኢት ደላላው ከድር ከመሃመድ ዘጠኝ ሴቶችንና አስራ አንድ ወንዶችን በድምሩ ሃያ ሰዎችን ተቀብሎ ከአስኢት ከተማ ጉዞ በምሽት ጫካ ለጫካ በእግር ወደ የቡኪ ተጀመረ፡፡

የቡኪ የኢትዮጵያ አፋር መሬትን ጨርሶ የጅቡቲ መዳረሻ መሬት ማለት ነው፡፡

ከአስኢት የቡኪ ድረስ በእግር አራት ቀን ይፈጃል፡፡ ወደ ውጭ ሃገር ለመሰደድ የሚጓዙ ወጣቶች ለሚረከቧቸው ደላሎች ሁሉ የያዙትን ገንዘብ በየደረጃው እየሰጡ ነው የሚጓዙት፡፡

ከመካከላቸው አንድ ስደተኛ ይማም ይባላል፡፡ ወደ አረብ ሃገር ከዚህ በፊትም ተሰዶ ሳይሳካለት ከየመን ተመልሷል፡፡ ለእሱ ስደት አዲሱ አይደለም፡፡ በስደት ላይ ምን አይነት ችግሮች እንደሚያጋጥሙ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

"ገንዘባችሁን ሽፍቶች እንዳይዘርፏችሁ፡፡ ሲፈተሸ በማይገኝበት ቦታ መደበቅ አለባችሁ፡፡ አለ ይማም፡፡ አብረውት ለሚጎዙት ጓደኞቹ ፡፡ ወንዶቹ በልብሳቸው ጠርዝ እና የለበሱትን ሸበጥ በምላጭ በመሰንጠቅ አመሳስለው ሰፉት፡፡

ሴቶቹ ደግሞ እንደ ወንዶቹ የልብስ ጠርዛቸውንና ጫማዎቻቸውን ባይጠቀሙም የያዙትን ገንዘብ በስስ ፌስታል እየጠቀለሉ በብልታቸው ውስጥ ከተቱት፡፡

ከአስኢት እና የቡኪ መካከል ለስደተኛ መቅጫ የተፈጠረ ይመስላል፡፡ የአፋርና የጅቡቲን ሽፍቶች በውስጡ አቅፎ የሚኖር የገመሪ ተራራ፡፡ በጨለማ ለተመለከተው መሬት አልቃ የሰማይ ጥግ የደረሱ ይመስል ነበር፡፡ የገመሪን ተራራ ብቻ በእግር ለመውጣት ከሶስት ሰዓታት በላይ ይፈጃል፡፡ ሃያ የኢትዮጵያ ስደተኞች ተመስገንና እድላዊትን ጨምሮ የገመሪን ተራራ ለመውጣት ትንቅንቅ ገብተዋል፡፡

በውሃ ጥም እና በድካም የሞቱ የስደተኞች አስከሬን በተራራው ፣ በየእንጨቱ ላይ ተንጠልጥሎ ስጋቸው የአሞራ ምሳ ሆኗል ፡፡ ሲያዩት ተደናገጡ፡፡ ከነመፈጠራቸውም አምርረው ረገሙ፡፡ የገመሪን ተራራ በአራት እግራቸው እየዳሁ ስቃይና መከራቸውን አብዝቶታል፡፡

ተንቀሳቃሹ የቁም ስቃይና መከራ የሚያሳዩት የአፋርና የጅቡቲ ሽፍቶች ረሃብ እንደሰነበተበት የበርሃ ጅብ ከፊት ለፊታቸው ድቅን አሉባቸው፡፡

የመሳሪያ አፈሙዝ ደቀኑባቸው፡፡ በበረሃ ልምጭ ገንዘብ አምጡ እያሉ ገረፏቸው፡፡ እግዚአብሔር እባብን ፈጥሮ የአዳም ልጆች ራስ ራሱን እንዲቀጠቅጡት እንደተፈረደበት ተቀጠቀጡ፡፡

በኪሳቸው ያገኙትን ገንዘብ ሁሉ ቀሟቸው፡፡ ሽፍቶቹ በገንዘብ ብቻ አልተመለሱም፡፡ ሴቶችን እየገረፉ አሰቃዩዋቸው፡፡ ልብሳቸውን አስወለቋቸው፡፡

የደበቁትን ገንዘብ እንዳይወሰድባቸው ልብሳቸውን ሲያወልቁ ከፓንታቸው ጋር አመሳስለው በማውለቅ ቢያተርፉትም፡፡ መደፈሩ ግን አልቀረላቸውም፡፡

የጠይም መልከ መልካሟ እድላዊት ለሽፍቶች አለቃ በሞግዚቶቹ ተመርጣ ቀረበች፡፡ አይኖቿ በእንባ ተሞሉ፡፡ ተቁለጨለጨች፡፡ ጨካኙ የሽፍቶች አለቃ አላዘነላትም፡፡ እየረገጠና እያዳፋ ልብሷን አስወለቃት፡፡ እንደ እሳት በሚጋረፈው የገመሪ የፀሃይ ሃሩር እርቃነ ስጋዋን አስቀራት፡፡ አንዴ አፈንድጅ ፣ አንዴ ተገልበጭ እያለ አሰቃያት፡፡ ብልቱ የተለበለበ ማረሻ ይመስላል፡፡ ሊደፍራት ብልቱን አስጠጋ፡፡

እድላዊት ድንገት ከብልቷ የደም ፈሳሽ ፈሰሳት፡፡ እንዳፈነደደች በርግጫ ከመሬት ቀላቀላት፡፡ ወደ ሌሎች ስደተኞች ተመለሰ፡፡

ቅንጣት የሚያክል ርህርሄ የሌላቸው ወንበዴዎች እንደ አስፈለጋቸው የልባቸውን አድርሰው ለቀቋቸው፡፡

ከዘጠኙ ሴቶች አራቱ በደረሰባቸው አስገድዶ መድፈርና ድብደባ ህይወታቸው ወዲያውኑ አለፈ፡፡

የተቀሩት አምስት ሴቶች እድላዊትን ጨምሮ መትረፍ ሳይሆን ለመሰንበት ያክል ነብሳቸው ተረፈች፡፡

በውሃ ጥምና ረሃብ ተሰቃይተው የሽፍታ ዱላ እንደ እናታቸው ጠግበው መሄድ አቅቷቸው በጣረሞት ትንሽ እንደተጓዙ ሁለት ወጣት ወንዶች በመንገድ ላይ ህይወታቸው ተቀጠፈ፡፡ ቢደክማቸውም በእንጨት መሬት ቆፍረው ቀበሯቸው፡፡ ተለቃቅሰው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡

እድላዊት በደረሰባት አሰቃቂ ድብደባ ደከማት፡፡ መሄድ አቅቷታል፡፡ መንገድ ላይ ወደቀች፡፡ አብረዋቸው የነበሩ ጥለዋቸው ሄዱ፡፡ ተመስገን ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ የሚያቀምሳት በእጁ ላይ ምንም አልነበረም፡፡ ከቤት ሲወጡ ያዘጋጁትን ስንቅም ሳያስቀሩ የጅቡቲ ሽፍቶች ዘርፈዋቸዋል፡፡ ትንሽ አረፍ እንዳለች ትንፋሿ መለስ አለላት፡፡ እንሂድ ሌላ ሽፍታ ሳይመጣብን አለች፡፡ አብሯት ለቀረው ተመስገን፡፡

የሞት ሞቷን ተነሳች፡፡ ጥለዋቸው የሄዱትን ጓደኞቻቸውን የቡኪ ደረሱባቸው፡፡
👍5410😱2
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

የተዳፈነ እሳት

ከሁለት አጉል ሆነች፡፡ እንደ ባህር ላይ ኩበት ተንሳፈፈች፡፡ ከባለቤቷ ወይም ከቤተሰቦቿ ሳትሆን ቀረች፡፡ ባለቤቷ ለገበያ እንደሄደ ወደ ውትድርና መግባቱን ሰማች፡፡ የመኖር ተስፋዋ እንደ ተዳፈነ እሳት ውስጧ ተንቦገቦገ፡፡ የጨለማ ተከናነበ፡፡ ከባለቤቷ ጋር ሰርታ የመለወጥ ተሰፋዋ ከማህል ተቀጨ፡፡ የኑሮዋ መሻሻል ከጨለማ የመውጫ መንገድ ሳይሆን የጨለማ መግቢያ ሆናት፡፡ ቤተሰቦቿ ባላወቁት ጉዳይ አይንሽን ላፈር አሏት፡፡

ታዲያ አበበች አስቀድማም እንደሚገጥማት ብገምትም ለሰው መልካም ነገር ማድረግ ግን እንደዚህ የእሳት እረመጥ ይሆንብኛል ብላ አላሰበችም ነበር፡፡ አንዴ ያደላትን የመከራ ፅዋ ተጎንጭታ፡፡ ገና እናትና አባቱን እንኳን በደንብ ካለየ ህፃን ልጇ ጋር ያለ ዘመድና ያለ አይዞሽ ባይ ባዶ ቤት ለመኖር ተገደደች፡፡ ስታለቅስ ውላ ስታለቅስ ብታድርም ከልጅዋ በስተቀር አብሯት የሚያለቅስ ሰው አይደለም ወደ ቤቷ ዝር ብሎ አይዞሽ የሚላት እንኳን አልነበረም፡፡

ከእለታት አንድ ቀን የያሬድ አጎት አቶ አስፋው ከባለቤታቸው ከወ/ሮ የኔነሽ ጋር ቡና አፍልተው እየጠጡ ነው፡፡

"እንዴው ያችን የያሬድ ባለቤት ሳንጠይቃት ምን ትለን ይሆን ? ቤተሰቦቿም እደጃችንም እንዳትደርሽ ብለዋታል አሉ፡፡ ያሬድም ብቻዋን ባዶ ቤት አዳፍኖባት ወዶ ዘማች መሄዱ የሚገርም ነው" አሉ፡፡ አቶ አስፋው ፤ በጉንጫቸው ላይ የወረደውን ረጃጅም ፂማቸውን በእጃቸው እየደባበሱ፡፡

"ምን ተጠየቀች አልተጠየቀች ምን ጎሎባታል፡፡ ያለውን ንብረት ጥሎላት ነው የሄደው፡፡ እሷን ደግሞ ማን ይጠይቃታል፡፡ እቤት ተቀምጣ ባሏን ሳይሞት በቁሙ የገፋች ገፊ" አሉ፡፡ ምንም አዘኔታ እንኳን ሳይታይባቸው፡፡ ግን የአበበችን በደልና ስቃይ ቢያውቁ ኖሮ እንደዚህ ባልተናገሩ ነበር፡፡
አቶ አስፋው በሰል ያሉና ብዙ ውጣ ውረዶችን በትንሹም ቢሆን መከራና ስቃይን ያሳለፉ በመሆናቸው ለተጎዳ ሰው የሚያስቡና ትህትና ያላቸው ማለፊያ የእግዚአብሔር ሰው ናቸው፡፡ የባለቤታቸው ንግግር አልተዋጠላቸውም፡፡

አይ! አንች ከንቱ መሆንሽ ያሳዝናል፡፡ ለነገሩ የችግርን ነገር ስለማታውቂው አይፈረድብሽም፡፡

የአንች ነገር በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት እንደ ሚባለው ነው፡፡ በአንች ላይ ቢደርስብሽ ያኔ በደንብ ታውቂው ነበር አሉ፡፡

ምን የተባለውንና የተወራውን ነው፡፡ የተናገርኩት በእሷም የተነሳ አይደለም እንዴ፡፡ ወንድሟ ያሬድን ለመግደል እያደፈጠ ሲስተው የነበረው፡፡ ታዲያ ይህ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው አይደለም አሉ፡፡ ስኒ አጣጥበው እረከቦት ላይ እያደረጉ፡፡

"ዝም ብለሽ በማታውቂው ነገር ትዘላብጃለሽ፡፡ ያሬድ የተሳሳተው በራሱ ልክስክስነት እንጂ በአበበች ጥፋት አይደለም፡፡ እሷ ምን አጠፋች ባሌ ዲቃላ ቢወልድም እሱ ይሻለኛል፡፡ ስላለች አይደለም አባቷ አይንሽን ላፈር ያሏት፡፡ ለማንኛውም ምንም ቢሆንዐተዋልደናልና የእሷ ቤተሰቦች እንኳን ቢጠሏት ደግሞ በራሳችን ጥፋት ልንሸሻት አይገባም፡፡

ደግመውም ሌላ ንግግር ሳይነጋገሩ በይ እስቲ አሁን በቁሜ ቢሆን ደረስ ብዬ ልምጣ ብለው ዘንጋቸውን ይዘው ተነስተው ወደ አበበች ቤት ሔዱ፡፡

ቤቱ ተዘግቶ በግቢው ውስጥ ሰው አይደለም ከብትም አላገኙም፡፡ አቶ አስፋው፡፡ ወዴት ሔዳ ይሆን ? ቆይታ ይሆን ከሄደች ? እያሉ ግራ በመጋባት ከራሳቸው ሐሳብ ጋር እየተሟገቱ ወደ መጡበት ተመለሱ፡፡

አበበች ልጇን አዝላ ውሃ ቀድታና ከብቶቿን አጠጥታ ከወንዝ ስትመጣ ከአቶ አስፋው ጋር እመንገድ ላይ ተገናኙ፡፡

"ደህና ዋልሽ አበበች" ? አሏት አቶ አስፋው፡፡

እግዚአብሔር ሰላም ዋሉ ? አለች፡፡ አይኗን ወደ አቶ አስፋው አትኩራ እየተመለከተች፡፡

"እኔ እኮ እቤት ሄጄ ቤቱ ተዘግቶ ሳይ የት ሄደች ብየ ስመለስ ነው ያገኘሁሽ" አሉ፡፡

"ምን ላድርገው አንዴ ያደለኝን ከብት እንኳን የሚያጠጣልኝ ሰው አጣሁ፡፡ ችግር ሲደርስብኝ እንኳን ዞር ብሎ የሚያዬኝ ጠፋ፡፡ እግዚአብሔርም ጨከነብኝ አለች፡፡

"እኔም ዛሬ ነገ እያልኩ ሳልመጣና ሳልጠይቅሽ ቀረሁ፡፡ ብትቀየምም ዛሬ አይቻት ልምጣ ብዬ ነው የመጣሁት፡፡ ሰው በቁሙ ካልተረዳዳ ከሞተ በኋላ ዋይ ዋይ ቢሉት ተመልሶ አይመጣም፡፡ እንዴው ሰራተኛ አላገኝሽም ኖሯል? አሉ፡፡

አይ! ጋሸ አስፋው የት አገኛለሁ ሰራተኛ የሚገኘው ከሰው ሲገናኙ ነው፡፡ እኔ ከሰው አልገናኝ፡፡ ዘመዶቸም ጠልተውኛል፡፡ አሁን ደግሞ አዝመራ እየደረሰ ነው፡፡ ማሳውን ማን እንደሚያርስልኝ ጨንቆኛል፡፡ ብን ብየ እንዳልጠፋ ይሄን ጨቅላ ልጅ አቅፌ መሄዱ ከበደኝ፡፡… ልማደኛው እንባዋ ተናንቋት አለቀሰች፡፡

በቃሽ አታልቅሽ ተይ፡፡ አንች እያለቀስሽ ምንም የማያቀውን ህፃን አታስለቅሽ፡፡ ያሬድም እንደሆነ ይመጣል፡፡ ወዶ ዘማች የሄደ ሁሉ አይሞትም፡፡ ለሁሉም እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ ዛሬ ቢጨልምም ነገ መንጋቱ አይቀርም፡፡ አይዞሽ፡፡ አዝመራውም ይዘመራል፡፡ ነገ ወደ ሸንኮራ ዮሃንስ መሄዴ ስለማይቀር ሰራተኛ እዠልሽ እመጣለሁ፡፡

ደግሞም የሚቸግርሽ ነገር ካለ እኔም ቢሆን እየመጣሁ አግዝሻለሁ፡፡ በነጋ በጠባ ቁጥር ማልቀስ ጥሩ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርም አይወድም፡፡ እባክሽን ለልጅሽ ስትይ አታልቅሽ፡፡ አንችም ያለ እድሜሽ በሽታ ላይ ትወድቂያለሽ፡፡ ብለው አፅናንተዋት ተነስተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

ትንሽ የነበረባት የጭንቀት ጨለማ ፈገግ ያለ መሰላት፡፡ አቶ አስፋው አይዞሽ ብለዋት ሲሄዱ፡፡ ባለቤቷ ወዶ ዘማች በመግባቱ መልሳ በህይወት የምታገኘው ግን አልመስል አላት፡፡ ፈገግ ብሎ የነበረው የጨለማ ብርሃን መልሶ ይጨልምባታል፡፡

አበበች ሁለተኛ ልጇን መፀነሷን የታወቃት ያሬድ በሄደ በሁለተኛው ሳምንት የወር አበባዋ ሲቋረጥ ነበር፡፡

አቶ አስፋው ለአበበች በገቡላት ቃል መሰረት ሰራተኛ አግኝተው ቀጠሩላት፡፡ ባለቤቷ ያሬድ እንደነበረው ጊዜ የተደላደለ ህይወትን ባትኖርም በባዶ ቤት ሆና ከምታለቅሰው የተሻለ ህይወት መኖር ጀመረች፡፡
የቤተሰቦቿ መጥላት ሳያንሳት የተመስገን እናት ወ/ሮ አሰገደች ሲወጡና ሲገቡ የባልሽን ዲቃላ አሳዳጊ አደረግሽኝ ፡፡ ባልሽም ዲቃላውን እንዳይወስድ የሰራው ስራ አሳፍሮት አገር ለቆ ጠፋ፡፡ እያሉ አላስገባ አላስወጣ አሏት፡፡ አበበች ግን አልቅሳ ዝም ከማለት ውጭ ምንም ምላሽ አልነበራትም፡፡

ጉልላት የተባለው የአበበች ሰራተኛ ትንሽ ጠና ያለና ነብስ አወቅ ያደረገ ነው፡፡ አበበች ስታለቅስና ስትበሳጭ አይዞሽ እያለ እያፅናና ያበረታታል፡፡

ጉልላት ለሁሉ ታዛዥ ቅን ሰው ለመሆኑ ደከመኝ ሰለቼኝ ሳይል ሲያገለግላት ላየውና ለተመለከተው የእናት ልጅ እንኳን እንደሱ አድርጎ የሚሰራ አይመስልም ነበር፡፡

አበበች ባለቤቷ ያሬድ ከሄደ ከዘጠኝ ወር በኋላ አንድ ቀን በእለተ ሐሙስ በጥዋት ተነሳች፡፡ የሚሸጥ ስንዴ ቋጠረች፡፡ ለጉልላት ገበያ ልልከው አስባለች፡፡ ይሔን ስንዴ ሽጥና አንዳንድ ነገሮችን ግዛልኝና ና፡፡ እኔም ቀኔ ደርሷል ብላ የሚገዙትን የእቃ ዓይነቶች ነግራ ቁርሱን አብልታ ወደ ገበያ ላከችው፡፡
👍533
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

ሚስጥሩ

ከአራት ዓመት ከውጊያ በኋላ፡፡ እንደ ማንኛውም የሰራዊት አባላት ዓመታዊ የወር ፍቃድ ደረሰው፡፡ የታጠቀውን የመንግስት መሳሪያ ለቅርብ አመራሩ አስረከበ፡፡ የፍቃድ ወረቀት ተቀበለ፡፡ የትግል አጋሮቹ ወደ ቤተሰቦቹ ሸኙት፡፡

የወርሃዊ ፍቃድ የተሰጠው እለት አራት አመታትን እንዳልቆየ ባለቤቱንና ልጁን ቶሎ ደርሶ ለማየት አንድ ቀን ሌሊት አልነጋ አለው፡፡ ካሳለፈው አራት ዓመታት በላይ በአይኑ ላይ እንቅልፍ የሚባል እንኳን ሳያልፍ ፍጥጥ ብሎ አነጋ፡፡ የሌሊቱ እንቅልፍ ወደ ቀን ተቀይሮበታል፡፡ ከመኪና ወንበር እያወዛወዘ ያላትመዋል፡፡

ያሬድ ከሁለት ቀን የመኪና ጉዞ በኋላ፤ አመሻሽ ላይ የትውልድ ቀየው ደረሰ፡፡ ሰፈሩ ሁሉ ዓዲስ ሆነበት፡፡ አካባቢው ተቀያይሯል፡፡ ተገረመ ፤ ከቤቱ አካባቢ
ዳገቱ ላይ ሻንጣውን አውርዶ አረፍ አለ፡፡ አይኖቹን በእሱ ቤት ላይ ተከላቸው፡፡ የእሱ ቤት ሰርቶት እንደሄደ አላገኘውም፡፡ የጣራው ሳር እረግፏል፡፡

የግቢውም አጥር ወላልቋል፡፡ በውስጡ ሰው ያለበት አይመስልም፡፡ ቤተሰቦቹን የሚያገኝ አልመስል አለው፡፡ ሆዱ በፍራት ተዋጠ፡፡ አይኖቹ በእንባ ተሞሉ፡፡ ወደ ወላለቀውና ፈራረሰው ቤቱ ተጠጋ፡፡

ከቤቱ ደጅ ላይ ሁለት ወንድ ህፃናት ልጆች እየቦረቁ ይጫወታሉ፡፡ አትኩሮ ተመለከታቸው፡፡ አንደኛው ህፃን ትልቅ እና ሰውነቱ ለወጥወጥ ቢልበትም የራሱ ልጅ ምትኩ እንደሆነ አልተጠራጠረም ነበር፡፡

ሁለተኛው ህፃን ግን የማን እንደሆነ ሊያውቀው አልቻለም፡፡ ወደ ሚጫወቱት ህፃናት ተጠግቶ ልጁን ምትክ ምትኩ? ብሎ ተጣራ፡፡ ህፃኖቹ የራስ የራሳቸውን እየተጨዋወቱ ከስራቸው ተጠግቶ የቆመውን ያሬድን አላዩትም ነበር፡፡ ህፃን ምትኩ መጫወቱን ትቶ ቀና አለ፡፡ በሰውነቱ ግዙፍ የሆነ ሰው አዬ፡፡ አባቱ እንደሆነ አያውቅም፡፡ ፈርቶ የወንድሙን የሁሉባንተን እጅ እየጎተተ ሸሽተው ወደ ቤት ገቡ፡፡
ምን ሁናችሁ ነው የምትሮጡት? ውሻ አባረራችሁ እንዴ ? አለች አበበች፡፡ ልጆቿ እየሮጡ ሲገቡ ደንግጣ፡፡

"ህፃን ምትኩ በተቆራረጠ ትንፋሽ ውሻ አይደለም ፤ መጥቷል" አላት፡፡

"የማን ሰው ነው የመጣው" ?፡፡

"አላውቀውም ሲያዩት ያስፈራል፡፡ ውጭና እይው እውጭ ቁሟል አላት፡፡ ውጭ ውጭውን እየተመለከተ፡፡

አበበች ውጭ እና እይው ሲላት የባሰ ድንጋጤ ጨመረባት፡፡ የሚያስፈራ ሰው ደግሞ ከየት መጣብኝ፡፡ እንዲያው አምላኬ ምን ልታሰማኝ ይሆን? ቤቴን ሰው አያውቀው፡፡ እንዲያው ሰርታ በላች ብለው ሊጨርሱኝ ይሆን? ከሰው ጋርም ባይሆን ከራሷ ጋር ያወራችው ነበር፡፡

ወደ ውጭ ብቅ አለች፡፡ እውነትም የሚያስፈራ ሰው ነው፡፡ የውጩን በር ከፍቶ ገባ፡፡ ሰውነቷ ተርበተበተ፡፡ የሚያስፈራው ሰውየ እየቀረባት መጣ፡፡
ለአራት አመታት የተለያት ባለቤቷ ያሬድ ነው፡፡ ማመን አቃታት፡፡ለመራመድ እግሮቿ ተሳሰሩ፡፡ አይኖቿ ያሬድ ላይ እንደተተከሉ በናፍቆት እንባ ተሞሉ፡፡

አበበች በደረሰባት ስቃይና መከራ ተጎሰቋቁላለች፡፡ የሃያ አምስት አመት ወጣት መምሰሏ ቀርቶ የአምሳ አመት አሮጊት ሆናለች፡፡ ያሬድ አዘነ፡፡ እያለቀሰ ተጠመጠመባት፡፡ ቤቱ ከሃዘን እንባ ወደ ደስታ እንባ ተቀየረ፡፡ አበበች የደረሰባትን ስቃይና መከራ እንዲሁም ባለቤቷ ያሬድ ከሄደ ስለወለደችው ልጅ ሁሉባንተ አጫውታው ልጁም የራሱ እንደሆነ ነግራው አምኖ ተቀብሏት ፡፡ ያሳለፉትን ናፍቆትና ትዝታ እያስታወሱ ሲለቃቀሱና ሲያወሩ ቢቆዩም ስለተደበቀው ሚስጢር ምንም ነገር ሳያወሩ አድረው በማግስቱ ጥዋት ነበር፡፡

ቡና ተፈልቶ "እንዴት አደረግሽው ያንን ነገር ያላት ?

"የቱን ነገር ? አለች ጥያቄው ግራ አጋብቷት፡፡

"ሚስጢሩን ነዋ አላት"፡፡

"አይ! ምነው ሁሉንም ነገር ለማንም እንዳትነግሪ ብለኸኝ በባዶ ቤት ያለቤተሰብና ያለ ዘመድ አዳፍነህብኝ ሄደህ ፤ እንዴት ነው ሚስጢሩ የሚወጣው?፡፡ ይኸው ከዛን እለት ጀምሮ ተመስገን እኔ ደጀም አልደረሰም፡፡ እስካሁንም አላየሁት፡፡ ብላ የነበረውን ሁኔታ ስታነሳሳ ውስጧ ተረበሸ፡፡ የብሶት እንባ አለቀሰች፡፡

ያሬድ የሚለው የሚናገረውን ቢያጣ ግራ ቢገባውም፡፡ ከተመስገን ያልተገናኛችሁት እዚሁ እያለ ነው ወይስ ከሃገር ለቆ ነው? አለ፡፡

በፊቷ ላይ የሚወርደውን እንባ በፎጣዋ ጠረግ ጠረግ እያደረገች "እዚሁ እያለ ሲሸሸኝ ፣ ሲሸሸኝ ቆይቶ እህቱን እድላዊትን ወደ ፀበል ልወስዳት ነው፡፡ ብሎ ቤተሰቦቹን አታሎ ወደ ተባለበት ፀበል ሳይወስዳት ወደ አረብ ሃገር ተሰደው ምን እንደደረሰባቸው እንጃ እድላዊትም ከመጣች አንስታ ከአልጋ ላይ አልተነሳችም አሉ"፡፡

"ማን ነገረሽ ? እነሱ ቤት እንደማትደርሽ ነግረሽኝ ነበር"::

እድላዊት በጠና መታመሟን የነገረኝ ጉልላት ነው፡፡ እኔማ ከቤትም ስወጣ ሰው ሁሉ እንደ ዕብድ ውሻ ይሸሸኛል፡፡ አለች የፈላውን ቡና እየቀዳች፡፡

"ለዚሁ ሁሉ ስቃይና መከራ ያበቃሁሽ እኔ ነኝ፡፡ እንደበደልኩሽም አውቃለሁ፡፡ ግን ወድጀ አይደለም፡፡ የሃገር ጉዳይ ሆኖብኝ ነው፡፡ ጥየሽ የሔድኩት ፤ ብዙ አትፍረጅብኝ ሃገር ሰላም ካልሆነች እኛም ሰላም እንደማናገኝ አንችም ታውቂያለሽ" አለ ፤ ያሬድ፡፡

"እግዚአብሄር እንኳን ከእሳት አትርፎህ ለአይነ ስጋ እንድንገናኝ አበቃን እንጂ ያለፈው አልፏል፡፡ አሁንም አንተ ከመጣህ ጊዜው አይርቅም፡፡ የተደበቀው ሚስጢር ይውጣና እኔም እናቴ ናፍቃኛለች፡፡ ይሄው ካየኋት፤ አራት አመታትን ጨርሰን አምስተኛ አመታችንን ልንይዝ ነው፡፡ ምንም ቢሆን የእናት ክፉ የለውም፡፡ ባላወቀችው ነገር እንደጠላችኝ አውቃለሁ አለች፡፡ የቀሉ አይኖቿን እያሻሸች፡፡

እድላዊት በደረሰባት ጉዳት የተነሳ የአልጋ ቁራኛ ሆናለች፡፡ እህል እንኳን መቅመስ አቅቷታል፡፡

ተመስገን የቁም ስቃይና መከራ እያየ ባለበት ሰዓት ሞቷል እየተባለ የተወራለት ያሬድ መምጣቱን ሲሰማ

ወደ አረብ ሃገር ሲሰደድ ሶስት ሰዓት የፈጀበት የገመሪ ተራራ እፊቱ ላይ የተጋረጠበት ያክል መስሎ ተሰማው፡፡

ከአምስት ቀን እረፍት በኋላ፤ የተደበቀውን ሚስጢር ለማውጣት ይመለከታቸዋል የተባሉትን ዘመድና ሽማግሌዎች ለማነጋገር በጥዋት ተነሳ፡፡ የውጭ በሩን ከፍቶ ሳይወጣ ከቤቱ ማዶ ላይ አንድ ነጭ ጋቢ የለበሰ ሰው አየ፡፡ ወደ እሱ ቤት እየመጣ ይመስላል፡፡ ወደ አሰበበት መሄዱን ተወት አድርጎ ወደ እሱ የሚመጣውን መጠባበቅ ጀመረ፡፡

በጥዋት ጋቢያቸውን ተከናንበው ወደ ያሬድ ቤት የሚመጡት ቄስ አሻግሬ ነበሩ፡፡

"ደህና አደርህ ያሬድ" ? አሉ ቄስ አሻግሬ፡፡ እስሩ ደርሰው፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደሩ ቄስ አሻግሬ"?፡፡

"እንኳን ለሃገርህ አበቃህ" ፡፡

ልጆች ደህና ናቸው ?፡፡

"ደህና ናቸው ፤ እንዲያው አንተ ለጤናህ ደህናነህ ?

ደህና ነኝ፡፡ ወደ ቤት ይግቡ ? ቄስ አሻግሬ አለ፡፡

አይ! አልገባም ቸኮል እላለሁ፡፡ እንዲያው በጥዋቱ ተነስተህ ኖሯል፡፡ የምትሄድበት አለ እንዴ ? አሉ፡፡

አዎ፤ የምሄድበት ነበረኝ፡፡ ከማዶ ስትመጡ ሳይ ጊዜ ነው፡፡ ወደ እኔ መምጣትዎን ሳውቅ የጠበኩዎት፡፡ ብሎ ምን ነው ደህና አይደሉም እንዴ? አለ፡፡

አይ! እኔስ ደህና ነኝ፡፡ እንዲያው እኒያ ቄስ መልካሙ ወደ አንተ ልከውኝ ነበር፡፡ የመጣሁት አሉ፡፡

ምን ነው በሰላም ነው? አለ ያሬድ፡፡ እድላዊት ምን ሆነች ብሎ እየተጠራጠረ፡፡

ልጁን ወይም ማሳደጊያ ይክፈለን እኛም አቅማችን እየደከመ ነው፡፡ እድላዊትም በሽተኛ ሆናለች፡፡ አንድ ነገር ያድርግልን ብለው ነው የላኩኝ አሉ፡፡
👍443🎉2
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
====================
ከአንድ አመት በኃላ በትዳር ውስጥ ወሲብ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም፡፡ግን ደግሞ ሊቀር የማይችል ከዋነኞቹ አስፈላጊ ነገሮች መካከል አንዱ ነው፡፡በተጣማሪዎች መካከል የሚከሰትን ማንኛውንም የከረረ ነገር የሚያለዝበው፤ የተጣመመ ስሜታቸውን የሚያቃናው፤የጎበጠ ግንኙነታቸውን የሚያቃናው ወሲብ ነው፡፡
የኑሮ ችግር ቢኖር መፅናኛ..አለመመቸት ቢኖር ማስረሻ ነው..ወሲብ፡፡እናም ባለትዳሮች የኑሮቸውን ኢኮኖሚያው ቀዳዳ ለመድፋት በስራ ደፋ ቀና እንደሚሉት ሁሉ የስሜታቸውን ክፍተት ለመድፈን ስለወሲብ ብቃታቸውና ችሎታቸው እኩል ትኩረት መስጠት አለባቸው፡፡ለዛውም ያልተቆራረጠ ቀጣይነት ያለው ትኩረት ፡፡ምክንያቱም ወሲብ ለፍቅር ተጣማሪዎች ልክ እንደምግብ ነው፡፡ምግቡ ቁርስ ላይ  ያበሉት  ሆድ ምሳ ላይ አምጡ ብሎ እንደሚጠይቀው ሁሉ ወሲብም ሰኞ እስኪዝለፈለፉ አድርገው እሮብ ላይ ጭንቅላቶትን እስኪያዞሮት ሊያምሮት ይችላል፡፡ይሄ ለምን ሆነ ተብሎ መጠየቅ የለበትም..፡፡እንደውም የሰውነቶትንም ሆነ የአእምሮትን ሙሉ ጤናማነት የሚያሳይ አንድ ምልክት ተደርጎ መወሰድ ነው ያለበት፡፡
በአላዛርና በሰሎሜ ትዳር ውስጥ ዋነኛውና ብቸኛው ስብራት ይህ ነው፡፡ወሲብ፡፡ታዲያ ወሲብ ብቸኛው ችግራቸው ከሆነ እንዴት በመሀከላቸው ያለን አንድ ችግር መፍታት ያቅታቸዋል? በሌሎች ትዳሮች እኮ ከደርዘን በላይ የታጭቁ ችግሮች እያሉ እንኳን ትዳሩን በፀና መሰረት ላይ ማስኬድ ይቻላል፤ታዲያ የእነሱ እንዴት ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ግን ነገሩ ከላይ እንደሚታየው ቀላል አይደለም፡፡ወሲብ ማለት የፍቅር መግለጫ ማህተም ነው….ወሲብ ማለት የአብራክ ክፍይን መተኪያ ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ልጆች ደግሞ ለአንድ ትዳር የተለየ ትርጉም የሚሰጡ ፍፅማዊ በረከቶች ናቸው፡፡
ሰሎሜና አላዛር እናትዬውን ለመጠየቅ ኮዬ ፈጬ ከንደሚኒዬም ይገኛሉ፡፡የተለየ ጉዳይ ካልተፈጠረ በስተቀር በ15 ቀን አንዴ እንዲህ እየመጡ እናትዬውን ይጎበኛሉ፡፡ይሄንን በየ15 ቀን የሚደረጉትን ጉብኝት ከእነሱ በላይ እናትዬው ነች የምትናፍቀው፡፡ምክንያቱም እነሱ እንድታገለግላት ከቀጠሩላት አጋዥ ልጅ እግር ሴት  በስተቀር ለብቻዋ ነው የምትኖረው፡፡አላዛርም ሆነ ሰሎሜ አብራቸው እንድትኖር ደጋግመው ለምነዋት ነበር፡፡እሷ ግን ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡
አላዛርን ሳሎን እንደተቀመጠ ከጎኑ የተቀመጠችው ሰሎሜ  ከተቀመጠችበት ተነሳችና .‹‹ማሬ እስኪ እማዬን ኪችን ሄጄ ላግዛት፡፡››አለችው፡፡
‹‹ምነው ልጅቷ የለችም እንዴ?››
‹‹ዛሬ  ቤተሰቦቼን ልጠይቅ ብላ ፍቃድ ተሰጥቶት ሄዳለች.. ››አለችው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ እቴቴን ይዘናት ወጣ ብለን ውጭ መዝናናት እንችላለን..ኪችን ገብታ ለእኛ ምግብ ማዘጋጀት የለባትም ፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ እቴቴን የማታውቃት ይመስላል…ለማንኛውም መጣሁ…እንዳይደብርህ ሪሞቱ ያውልህ ቲቪውን ክፈተው፡፡››ብላው ወደኪችን ገባች፡፡እናትዬው በእስቶቭ ላይ ጎን ለጎን ሁለት ድስት ጥዳ አንዱን ስታማስል ነበር የደረሰችው፡፡
‹‹መጣሽ ልጄ?››
‹‹አዎ አማዬ…ምን ላግዝሽ?››
‹‹ምንም …በቃ እየበሰለ ነው፤ራባችሁ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም ..አርፍደን ከእንቅልፋችን ስለተነሳን  ቁርስ በቅርብ ነው የበላነው፡፡››
በሰጠቻቸው መልስ ባለመደሰት አፋቸውን ወደጎን በማሽሟጠጥ አጣመው‹‹ጥሩ ነው.. እስከአራት አምስት ሰዓት መተኛቱ ጥሩ ነው..ግን ዝም ብሎ መተኛት ምን ረብ አለው?››ሲሉ መለሱላት፡፡
የንግግራቸውን አቅጣጫ እያወቀች ‹‹እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?..››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹ካንቺ በኃላ ያገቡ ጓደኞችሽ ሁሉ እኮ  ወለዱ..ሌላው ይቅር ከአምስት ወር በፊት ያገበችው ቤተልሄም የዛሬ ሳምንት ወልደ ሄጄ ጠየቅኳት፡፡››
‹‹እንዴ እማ …ልጅ በዘጠኝ ወር አይደል እንዴ የሚወለደው?በአምስት ወር እንዴት ማድረስ ቻለች?››
‹‹ቀልጂብኝ…ደግሞ እኮ ስላረገዘች ነው ተካልባ ያገባችወ እያሉ ሲያሟት እኔም አብሬ ማማቴ..ምነው አንቺም ከማግባትሽ በፊት አርግዘሽ ቢሆን ኖሮ…፡፡››
‹‹እቴቴ…. እንተዋወቃለን እኮ..አሁን እደዛ አድርጌ ቢሆን አታዝኚብኝም ነበር..?››
‹‹ልዘና ..የተወሰነ ጊዜ ተነጫንጬ ተወዋለው…ምንም ባዝን አሁን እያዘንኩ እንዳለሁት አላዝንም…ደግሞም  እስካሁን በእግሩ ለመሄድ የሚታገል ወፌ ቆመች ወፌ ቆመች የምለው የልጅ ልጅ ይኖረኝ ነበር፡፡››
‹‹አይዞሽ እማዬ… በተከታይ ሶስት አራቱን አንጠባጥብልሻለሁ፡፡››
‹‹ልጄ እናት መሆን እንዲሁ ተራ ነገር አይምሰለሽ..ለህይወትሽ ጥልቅ ትርጉም የሚሰጥሽ እናትነት ነው፡፡እናት መሆን ማለት በህይወት ውስጥ ስርሽን የህይወት እንብርት ድረስ ዘረጋሽ ማለት ነው፡፡እናት ስትሆኚ ለህመም በቀላሉ እጅ አትሰጪም፤እናት ስትሆኚ ብትቸገሪ እራሱ በቀላሉ ተስፋ አትቆርጪም፤እናት ስትሆኚ ለቀናት እህል ባትቀምሺ ራሱ ተዝለፍልፈሽ ለመውደቅ  አትሞክሪም፤እናት ስትሆኚ  መሞት ብትፈልጊ እንኳን ለመሞት መብት የለሽም፤እኔ አንቺን አጎጉል በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ነው የወለድኩሽ..እንደእንቺ በወግ በማአረግ አግብቼ መሰረቱ የፀና ትዳር መመስረት አልቻልኩም፡፡እና ደግሞ አንቺን ስወልድ በደረሰብኝ የማህፀን ጉዳት ሌላ ልጅ ወልጄ ወንድም ወይም እህት እንዲኖርሽ ማድረግ አልቻልኩም…አሁን የምትወልጂያቸው ልጆች ልጆችሽ ብቻ አይደለም የሚሆኑት ወንድምና እህቶችሽም ጭምር ነው የምትወልጂው..ለዛ ነው ቀንና ሌት የምጨቀጭቅሽ፡፡››
‹‹ይገባኛል እቴቴ…አይዞሽ!! ››
ሁል ጊዜ ይሄንን ጥያቄ እናትዬው ባነሳችላት ቁጥር ‹‹አይዞሽ››ከማለት ውጭ ሌላ የምትመልስላት መልስ ኖሯት አያውቅም፡፡አሁን አሁን ግን መልሷ በጣም ከመደጋገሙ የተነሳ ለእናቷ ብቻ ሳይሆን ለእሷም በጣም እጅ እጁ እያላት ነው፡፡ግን ለጊዜው ሌላ ምርጫ የላትም፡፡
እናትዬው‹‹አይዞሽ ብቻ ምንም አይረባኝም…የምትጠቀሚውን መከላካያ መድሀኒት ዛሬውን አውጥተሸ  ሽንት ቤት እንድትጥይው ፈልጋለሁ፡፡፡››አሏት፡፡
‹‹እሺ እኮ አልኩሽ እማዬ..እሺ››
‹‹በይ ወጡ ደርሶል…ታጠቡና ተዘጋጁ፡፡ ››
‹‹እሺ›› ብላ በደፈረሰ ስሜትና በተከፋ ፊት ወደ ባሏ ተመለሰች፡፡ይሄ ጭቅጭቅ ምርር እያደረጋት ነው፡፡ደግሞ የእናቷ ብቻ ቢሆን ምን አለበት..ጠቅላላ የሚያውቋት ሰዎች በተለይ ትንሽ ጠና ያሉ ሴቶች በሙሉ በሆነ አጋጣሚ ፊት ለፊት ሲያገኞት‹‹..እሺ መቼ ነው ገንፎ የምንበላው…?ምነው ሰውነትሽ ጨመረ..?አረገዝሽ አይደል?››በቃ ቋቅ እስኪላት ድረስ ምርር ያደረጎት ጉዳዬች ናቸው፡፡
እናቷ ደጋግማ ስትጠይቃት…‹‹ትንሽ ልቆይ ብዬ ነው..መድሀኒት ስለምጠቀም እንጂ እስከአሁን አረግዝ ነበር ፡፡››የሚሉ መልሶችን ደጋግማ መልሳላቸዋለች፡፡ታዲያ ‹‹አይ እናቴ እስከአሁን ያላረገዝኩት ያገባሁት ባሌ ከእኔ ጋር ወሲብ መፈፀም እምቢ ስላለ ነው፡፡እስከአሁን ድንግል ስለሆንኩ ነው ፡፡››ትበላቸው እንዴት ? የዚህ ነገር መቋጫው የት እንደሆነ መገመት እራሱ እየከበዳት ነው፡፡
ምሳ ቀርቦ በልተው ካገባደዱ በኃላ ይዘው የመጡትን ወይን ለሶስቱም ተቀድቶ እሱን እየተጎነጩ በግማሽ ልብ የተከፈተውን ቴሌቭዥን እያዩ በግማሽ ልብ የባጥ የቆጡን ርእስ እያነሱ ሲጫወቱ ቆዩ ፡፡በድንገት ግን ቀልብ የሚስብ ፕሮግራም ወሬያቸውን እንዲያቆሙና ሙሉ በሙሉ ፀጥ ብለው እንዲያዳምጡ አስገደዳቸው፡፡ጣቢያው ኢቢኤስ ነበር፡፡
👍648😢2👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
ቢንያም እና ዔሊያስ አዲሱ ቤት ውስጥ ሆነው አንዳንድ ነገሮችን እያስተካከሉ ነው፡፡

‹‹እነዚህ ክፍሎች ከተጠናቀቁ በኋላ የሚቀጥለው ፕሮጀክት የሳሎኑን ሴራሚክ ማሰራት ነው›› አለ ዔሊ፡፡

ቢኒያምም ‹‹አዎ..እኔም እንደዛ ነው ያሰብኩት ››ሲል ለሀሳቡ ድጋፍ ሰጠው፡፡
‹‹ሰሞኑን በቤቱ የፊኒሽንግ ስራ ላይ ያለህ ትኩረትና ጉጉት ጨምሮብኛል ..ምነው ?ጉዳዩ ከራሄል  ጋር የሚያገናኘው ነገር አለው እንዴ?››ሲል ጠየቀው፡፡
ዔሊያስ የሚናገረው ማንኛውም ነገር በወንድሙ በተሳሳተ መንገድ እንደሚተረጎምበት ስለሚያውቅ  ዝም ለማለት ወሰነ ። የቀረውን የእንጨት ፍቅፋቂ ጠራርጎ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ጣላው፡፡

ቢኒያም ወደሌላ ተያያዥ ጥያቄ ተሸጋገረ‹‹በቤተሰቧቾ ግቢ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢ አመታዊ ዝግጅት ላይ  ቆንጆዎቹ ጥንዶች እናንተ እንደነበራችሁ  ሰምቻለሁ።››

‹‹ስለ ቆንጆው ክፍል አላውቅም, ግን አዎ  አብረን ጠቃሚ የሚባል ጊዜ አሳልፈናል.››ሲል መለሰለት፡፡
ቢኒያም መሳሪያዎቹን እየሰበሰበ ‹‹እሷ በጣም የምትስብ ሴት ነች፣ አይመስልህም?›› ሲል አከለበት።
ዔሊያስ ሳጥኑን አነሳና‹‹በአሁኑ ጊዜ ስለእሷ ምንም  ላለማሰብ እሞክራለሁ…ካለበለዚያ ችግር ውስጥ ያስገባኛል.››ሲል መለሰለት ።

የሚናገረው ነገር ሙሉ በሙሉ እውነት አልነበረም። ከዝግጅቱ ቀን  ጀምሮ፣ ብዙ ነገሮችን ከአእምሮው ማውጣት አልቻለም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እዛው በራሄል ቢሮ ውስጥ፣ ወደ ኋላ የተገፋ.. የተተወ ያህል ተሰምቶታል። በቀጣዮቹ ቀናት ብዙ ጊዜ፣ ወደቤቷ ተንደርድሮ ለመሄድ ስሜቱ ተፈትኗት ነበር።እሱ ግን እንደምንም ተቋቁሞት እራሱን አቅቧል። ለራሄል ልቡን ከፍቶ ነበር፣ እሷም እንዲሁ ያደረገች መስሎት ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ስለእሷ ያለውን ስሜት በትክክል ሲነግራት.. ቀዝቀዝ አድርጋዋለች።‹‹እንደዛ ማድረግ  ያለብን አይመስለኝም።›› ነበር ያለችው….ታዲያ ለምን እንዲስማት ፈቀደችለት?እና ለምን አሁንም ስለ እሷ ያስባል? እሷን ከአእምሮው ለማስወጣት ወስኗል። እሱ ትኩረቱን የሚያሳርፍበት የሚሠራው ቤት ስላለው አመሰገነ። እንደ ሞኝ እሷ በቀደደችለት ቦይ  ፈቃደኛ ሆኖ እንዲፈስ  አድርጋዋለች።

‹‹እሷን እንደ ፍቅር ጓደኛ አድርጎ ማሰብ ከመጠን ያለፈ ነው›› አለ ፡፡
ቢንያም ‹‹ከየትኛውም ሴት ጋር ለተወሰነ ጊዜ አላሳለፍክም። ይህችኛዋ የተለየ ምን አላት?››
ዔሊያስ ሱሪው ላይ ያለውን አቧራ ጠርጎ አራገፈው። ‹‹ እርግጠኛ አይደለሁም።››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ወደሀታል?››

ኤሊያስ ቅንነት በጎደለው እንቅስቃሴ እጁን አወዛወዘ። እሱ ካልወደዳት ለምን አብዝቶ ስለእሷ ያስባል ?‹‹የሆነ ሆኖ ..ለጊዜያዊ  ስሜት እንዳልፈለኳት  አውቃለሁ››
ቢንያም ቀጠለ‹‹ስለዚህ ጉዳይ ማውራት ትፈልጋለህ?››

‹‹አይ ..ርዕስ ብንቀይር ደስ ይለኛል››አለው፡፡

ቢንያምን ወንድሙ ስሜት ተረዳና ርእሱን ቀየረ ‹‹በቀደም ለሆነ የስራ ጉዳይ…እኛ የነበርንበት የህፃናት የማደጎ ድርጅት ሄጄ ነበር ..አስተዳዳሪዋ ወይዘሪት ሜላት ስለአንተ ስትጠይቀኝ ነበር፡፡ሰሞኑን ፋይል ሲያደራጁ በአንተ ፋይል ላይ በፊት ካሳየችህ  የተለየ ነገር እንዳገኘች ነገረችኝ፡፡››

ኤልያስ  በሰማው ነገር ደነገጠ ‹‹ታዲያ ለምን  አልነገርከኝም? ስለ ወላጆቼ የበለጠ ለማወቅ እንደምፈልግ ታውቃለህ።››
ቢንያም ‹‹ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደተሰማኝ ታውቃለህ.? አሳዳጊ ወላጇቼ የሚያስፈልገኝን   ሁሉንም ነገር ነው የሰጡኝ … ስለ ወለደችኝ  እናቴ ምንም ግድ የለኝም. አንተም ተመሳሳይ ነገር እንድታደርግ እመኛለሁ  ምክንያቱም ወላጆችህ ሞተዋል..ተመልሰው አይመጡም ..በዚህ ጉዳይ ላይ አእምሮህን እንድትበጠብጥ አልፈልግም..ለዛነው ችላ ያልኩት››

ዔሊያስ በማደጎ ወንድሙ ላይ ያለው ብስጭት አደገ ‹‹የአንተ እናት ‹መቼም ቢሆን ከልጄ ጋር ምንም አይነት  ግንኙነት ለማድረግ አልሞክርም› የሚል ስምምነት ፈርመዋል።የገዛ የስጋ እናትህ መቼም ቢሆን ከአንተ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዲኖራት አልፈለገችም…. የእኔ ግን የተለየ ነው … የወላጆቼ  ትዝታዎች  በልቤ ውስጥ ናቸው… ምንም እንኳን  አንተም ሆንክ አሳዳጊ ወላጆቻቼ  ስለ ወላጆቼ በጭራሽ እንዳውቅ ባትፈቅዱልኝም…..እኔ ግን ፍለጋዬን አላቆምም.››ሲል በቁጣ ተንዘረዘረበት፡፡

ቢኒያም በስክነት ‹‹ ብቻ እንደወንድምነቴ የተሰማኝን ነገሬሀለው….››አለው፡፡
ኤሊያስ  ምንም መልስ አልሰጠውም ። እሱ እና ቢንያምን ከዚህ በፊት  በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ተወያይተው ነበር ግን አንድም ቀን አንድ አይነት አቋም አራምደው አያውቁም። እሱ አሳዳጊዎቹ ከማደጎ ቤት ከተቀበሉት በኋላ በእውነት የቤተሰቡ አካል እንደሆነ ለማመን ብዙ አመታት ፈጅቶበት ነበር፣ እና ከዛም የገዛ ወላጆቹ እና የእነሱ አሳዛኝ ሞት ትዝታዎች ብዙውን ጊዜ ጣልቃ በመግባት በእሱና በአሳዳጊ ወላጆቹ መካከል ክፍተት እንደፈጠረ ነበር፡፡

‹‹ስለ መዛግብት ስላልነገርኩህ ይቅርታ… አስፈላጊ ነው ብዬ አላሰብኩም ነበር. ከዚህ ሁሉ በላይ የሆንክ መስሎኝ ነበር.››
ኤልያስ በሀሳብ ነሆለለ።የሚወዳት ልጅ  ራሔል ትዝ አለችው፡፡እሷ  በሁለቱም በኩል  ወደ ኋላ ዞራ የትውልድ ሀረጓን በኩራት መዘርዘር ትችላለች…ከዛም አልፎ በእናቷ የዘር ግንድ ሔዶ ሄዶ ከሰለሞን ዘር ይመዘዛል ብለው እናቷ  ነገረውታል…. በዚህም ምክንያት እሷ በተጠየቀች ቁጥር ከየት እንደመጣች ለሰዎች በኩራት መንገር ትችላለች። እሱ ግን የዘር ግንዱ በአጭሩ ብጥስ ብሎ መጥፋቱ ከሌሎች ሰዎች ያነሰ እንደሆነ እንዲሰማው አድርጎታል።አሳዳጊ ወላጆቹን  ይወዳቸዋል ። በወጣትነት ዘመናቸው ወደቤታቸው ወስደው… አመፁን እና አስቸጋሪ ፀባዩን ተቋቁመው በፍቅር አሳድገውታል..አሁንም ድረስ ስለእሱ ማሰብና እሱን ከመንከባከብ ሲደክማቸው አይቶ አያውቅም።ልክ እንደእነሱ አማኝ ሆኖ ወደ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ አለመቻሉ እንዴት እንዳሰቃያቸው ያውቃል።ግን በተመሳሳይ ስለስጋ ወላጆቹ ያለውን ቁርጥራጭ ትውስታዎቹን ማጥፋት አልቻለም. ….አልፈለገምም ነበር።

ከረጅም ዝምታ በኋላ ቢኒያም ‹‹ኤሊያስ ልነግርህ የምችለው ነገር የበለጠ ማወቅ ከፈለግክ ከወይዘሪት ሜላት ጋር  ሄደህ ራስህ  ብትነጋገር ጥሩ ይመስለኛል››የሚል ሀሳብ አቀረበለት፡፡
ዠቨ
‹‹እንደዚያ የማደርግ ይመስለኛል›› አለ.

ዶ/ር ኤልያስ በማግስቱ አስረአንድ ሰዓት ላይ በህፃናት ማሳደጊያ በጎ አድርጎት ድርጅት ቢሮ ውስጥ ከመዘጋቱ በፊት ተገኘው። ምሳ ሰዓት ላይ ስልክ ደውሎ  ቀጠሮ ይዞ ነበር ። ወ.ሪት ሜሮን ተከትሎ ወደ ቢሮዋ ሲገባ ልቡ ከተገቢው በላይ እየመታ ነበር።

የራሄል ምስል በአእምሮው ውስጥ ድቅን አለና  ለስለስ ያለ ህመም ተሰማው። ‹‹  ዶ/ር ኤልያስ…እንኳን በሰላም መጣህ…ምን እንድረዳህ ትፈልጋለህ?›› ስትል ጠየቀችው ፡፡

‹‹ስለ ስጋ  ወላጆቼ አንዳንድ ነገሮች ሚያስረዳ ፋይል እንዳለሽ ተረድቻለሁ›› አለ ።ወ.ሪት ሜላት ጭንቅላቷን  በአውንታ ነቀነቀች። ‹‹ብዙ መረጃ አልያዘም ነገር ግን ጥቂትም ቢሆን ምን አልባት የምትፈልገውን ነገር ልታገኝበት ትችል ይሆናል::››

‹‹እና አሁን ማየት ብችል ደስ ይለኛል?››

‹‹እላይ ፎቅ ላይ በሚገኝ መዝገብ ቤት ውስጥ ነው ያለው…ትንሽ ታገሰኝ ይዤ ልምጣ  ›› ብላ እዛው የተቀመጠበት ትታው ወጥታ ሄደች፡፡
73👍7
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
አለም ወደ አፓርታማዋ  እደገባች የእጅ ቦርሳዋን እና ካፖርትዋን ወንበር ላይ አስቀመጠች
ዛሬ ከሰአት በኋላ ለዋናው አቃቢ ህጉ ደውላለት ነበር። እስካሁን እጇ ላይ ባስገባችው ግኝት ደስተኛ ሆኖ አላገኘችውም፡፡ ስራውና እርግፍ አድርጋ ወደ አዲስ አበባዋ እንድትመለስ ወይም እራሷን ካለፈው ታሪኳ ጋር እንድታስታርቅ ምርጫ አቀረበላት።እስከአሁን በሚጠበቀው ልክ ተጨባጭ ውጤት ማግኘት ያለመቻሏ የሱ ቅሬታ አንዱ ምክንያት ነበር። ዛሬ ማታ ባላት ቀጠሮ መሰረት ለዋናው አቃቢ ህግጉ የአይን እማኙን አግኝታ ያገኘችውን መረጃ ስታቀርብለት ስሜቱ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀየር እርግጠኛ ነች።
ወደ መጠጥ ቤቱ የመኪና ማቆሚያ ቦታ በገባችበትን ቅጽበት ብዙም ተስፋ እንደማይሰጥ ማወቅ ነበረባት። አምፖሎቹ ቦግ ብልጭ ድርግም ከሚለው የሸዋ በር መጠጥ ቤቶች መካከል በአንዱ ነው የቀጠራት ። ከደረሰች በላ ወደ ውስጥ አልፋ ለመግባት በጣም አመንትታ ነበር።ግን ይሄ የያዘችውን ምርመራ ከስኬት ለማድረስ መክፈል ከሚገባት መስዋዕትነት መካከል አንዱ እንደሆነ ራሷን በራሷ አሳመነችና እግሮቾን እየጎተተች ወደውስጥ ገባች፡፡በክፍሉ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው ትኩስ ስጋ እንዳየ ጥንብ አንሳ ወደ እሷ ተመለከቷት፡። የተወሰኑ ሴቶች ቢኖርም የእነሱ እይታ እንደውም ከወንዶቹ በተቃራኒ ሻካራ መስሎ ነው የተሰማት ፡፡ወደኋላ ዞራ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጋ ትታ መሮጥ ፈለገች ..ግን ያደረገችው ወደግራዋ ታጥፋ ኮርነር አካባቢ ወንበር ስባ መቀመጥ ነበር፡፡

አስተናጋጆ መጥታ

‹‹ ምን ልታዘዝ ስትላት"

‹‹እባክሽ ነጭ ወይን "ስትል አዘዘች፡፡
በስልክ ያናገራት እና ድምፁን ብቻ የሰማችው ሰው የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ዓይኗን ከአንዱ አቅጣጫ ወደሌላው በማወናጨፍ ለመገመት ሞከረች ።ግን ….አይኗ ሲንከራተት እየተካታተሉ የነበሩ አንዳንድ ወንዶች ሁኔታዋን በተለየ መንገድ ትርጉም ሰጥተውት አስፀያፊ ምልክት ሲሰጦት ነው ያወቀችው። ከዛ በኋላ አይኖቾን አደብ አስገዛችና መጠጧን እየተጎነጨች አቀርቅራ ማሰላሰሏን ቀጠለች፡፡ የምትፈልገው ሰው እዛ ሆቴል ውስጥ ካሉት ሰዎች መካከል አንዱ ከሆነ የምትወደው አይነት ሰው ሊሆን እንደማይችል አሰበችና ተረበሸች፡፡

እያጨሰች ባትሆንም በዙሪያዋ ብዙ ሰዎች የተለያየ አይነት ሲጋር እያጬሱ ስለሆነ በጭስ ደመና ታፍናለች። እና አሁንም ብቻዋን እንደተቀመጠች ነው።በመጨረሻ፣ እሷ ስትመጣ ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጦ የነበረ የተጎሳቆለ አይነት ሰው ከመቀመጫው ተነሳና ወደ እሷ አቅጣጫ መጣ። ከእሷ ጠረጴዛ ጋር ከመድረሱ በፊት ካለው ሌለኛው ጠረጴዛ ላይ ወንበር ስቦ ተቀመጠና ይዞ የመጣውን ቢራ ከፊት ለፊቱ አስቀመጠ…የሁለቱ ወንበር መደገፊያ የተደጋገፈ ስለሆነ ጅርባቸው ተጋጥሟል ማለት ይቻላል..በዛ ላይ ሰውዬው ጥቁር ኮፍያ አድርጎ ፊቱን በከፍል ስለሸፈነ ምን እንደሚመስል በትክክል ልትለየው አልቻለችም፡፡፡

አንገቱን ወደኋላ ለጥጦ"ሰው እየጠበቅሽ ነው?"ሲል ተናገረ…ድምፁ የተለየ ይመስላል፣
"እኔ መሆኔን በምን አወቅክ ?ደግሞስ ይህን ያህል ጊዜ የፈጀብህ ለምንድን ነው?"ብላ በቀዝቃዛ ድምጽ መለሰችለት።

"ድፍረቴን እያሰባሰብኩ ነበር" አለ ከቢራው እየተጎነጨለት።

‹‹ጥሩ….ከእኔ ጋር አንድ ጠረጴዛ ለመጋራት ይሄን ያህል ትፈራለህ እንዴ?››

‹‹ህይወት እኮ ነው የያዝኩት… ለምን አልፈራም?››

"ይሁን እሺ…የምትነግረኝ ነገር እንዳለህ ገምታለው…ምንድነው ?።"

"የምትፈልጊውን ሁሉ ማውራት እንችላለን " የቢራ ጠርሙስ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ ከኪሱ ብር አወጣና አስቀምጦ ‹‹..ግን መጀመሪያ ከዚህ መውጣት አለብን›› አላት፡፡

‹‹ ጥሩ የእኔ መኪና ውጭ ነው …ነጭ ቪታራ ነች"
‹‹አውቃታለው››

‹‹ሂሳብ ከፍዬ መጣሁ.. እዛ ጠብቀኝ››
ቀድሞ መራመድ ጀመረ፡፡ሹክክ ብሎ ሆቴሉን ለቆ ተሰወረ….እሷም አስተናጋጁን ጠርታ ሂሳብን ዘጋችና ግማሽ የቀረውን የወይን ጠርሙስ ባለበት ጥላ ቦርሳዋን ይዛ ወደውጭ ወጣች ..ወደ መኪናዋ ቀረበች ….ምንም ሰው በአካባቢው አይታያትም…..ወደመኪናዋ ውስጥ ገባችና ..የውስጥ መብረቱን አብርታ መጠበቅ ጀመረች…….ምንም ብቅ የሚል ሰው አልነበረም፡፡ ግራ ተጋባች…ተበሳጨች…ሰሞኑን ይደውልላት በነበረው ስልክ ደወለችለት…እንደተለመደው ይጠራል አይነሳም፡፡ማልቀስ ሁሉ አማራት..እዛው መኪናዋ ውስጥ ኩርምት እንዳለች ከአንድ ሰዓት በላይ አሳለፈች..በመጨረሻ ተስፋ ቆረጠችና አዲስ ወደ ተከራየችው አፓርታማ ነዳችው፡፡ከሀሳቧ ያባነናት የስልክ ጥሪ ድምፅ ነው… ከብስጭቷ ሳትወጣ ከአልጋዋ ተፈናጥራ ተነሳችና አነሳችው።

"ሀሎ።"

"እብድ ነው እንዴ ብለሽ አስበሻል አይደል ?"
የምታውቀውና የምትጠብቀው ድምፅ ነው።

"አንተ የት ነበርክ? ከእኔ ጋር ምን አይነት ጫወታ ነው አየተጫወትክ ያለኸው?መኪናዬ ውስጥ ተጎልቼ አንድ ሰዓት ያህል ስጠብቅህ ነበር.."

"ካንቺ ጋር ድብብቆሽ መጫወት ብፈልግ ኖሮ መልኬን እንድታይው አልፈቅድልሽም ነበር….ኩማንደሩ እዛው ነበር?"

"ምንድን ነው የምታወራው? ገማዶ እዚያ አልነበረም"

"የእኔ እመቤት ነበረ፣ በትክክል ነው ያየሁት። በቀጠሯችን መሰረት በቦታው ተገኝቻለሁ ግን ኩማንደር ገመዶ ከጀርባሽ በቅርብ ርቀት ተቀምጦ እያየሁት በአካባቢው መቆየት እና ከአንቺ ጋር ማውራቱን መቀጠል አልችልም… ፡፡››

‹‹ኩማንደሩ እየተከተለህ ነበር እንዴ?"

"እንዴት እንደዛ ያደርጋል….እኔ ምንም አይነት ህግ እልጣስኩም,…በተለይም ከፍሰሀ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች አንገቴ ስር ሲተነፍሱ. ደስ አይለኝም…ኩማንደሩ ደግሞ ከልጅነቱ ጀምሮ ከፍሰሀ ጋር ያበረ ወፍራም ሌባ ነው. የእሱ ዋነኛ ቀኝ እጁ ነው..ለማንኛውም አንቺን ተከትሎ የመጣ ይመስለኛል!!››

"ኩማንደሩ በአካባቢዬ እንዳለ አላውቅም ነበር. ሌላ ቦታ እንገናኛለን. በሚቀጥለው ጊዜ እሱ እንዳልተከተለኝ እርግጠኛ እሆናለሁ."ስትል ቃል ገባችለት፡፡

" እስቲ እናያለን።"

‹‹እናያለን ማለት ምንድነው…?ነው ወይስ የምትነግረኝ ነገር ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም፡፡.››

"ወንጀሉን ማን እንደፈፀመው አይቻለሁ እመቤት"

ተፈላጊነቱን ስታሳንስበት ተበሳጨ፡፡

"ታዲያ የት ነው የምንገናኘው?

እና መቼ?"

‹‹አሁን ህዝብ የተሰበሰበበት ቦታ አይደለም መገናኘት ያለብን ….ከቶታል ማደያ በቀኝ በኩል በምታስገባው መንገድ አንድ ሰማያዊ ቀለም የተቀባ ህንጻ አለ…. ከእሱ ፊት ለፊት
አንድ አሮጌ ሰማያዊ ባጃጅ ውስጥ ቁጭ ብዬ እጠብቅሻለው። እኔ ከኃላ ውስጥ አለሁ..ዝም ብለሽ ትገቢያለሽ።"

‹‹ባጃጁ ያንተ ነው ማለት ነው››

‹‹ከየት አባቴ አምጥቼ…የጓደኛዬ ነው..ሰሞኑን ስለታመመ እኔ ደግሞ ስራ ፈት ስለሆንኩ እየሰራሁለት ነው፡፡››

"በቃ በሰዓቱ እገኛለሁ- ግን እስከዛው ቢያንስ ስምህን ልትነግረኝ አትችልም?"

"አይ አልችልም" ስልኩን ዘጋው። አለም ተሳደበች። ከአልጋው ወርዳ ወደ መስኮቱ ሄደች ፣ መጋረጃዎችን ገለጠችና ወደውጭ ተመለከተች…የጠቆረው እና ኮከቦች የተበተሉበት ሰማይን በትኩረት አየች፡፡መጋረጃዎቹን ዘጋች፣ ወደ ስልኩ ተመለሰች፣ እና በቁጣ ውስጥ እንዳለች ሌላ ቁጥር ላይ ደወለች። የዓይን እማኝን በማስፈራራቱ በኩማንደሩ ላይ በጣም ተናደደች፣ እየተንቀጠቀጠች ነበር።ቀጥታ እሱ ላይ ነበር መደወል የፈለገችው…ግን ደግሞ ቁጥሩን አታውቅም…..የሰዓቱ መምሸት ግድ አልሰጣትም ፡፡ስልኩ ተነሳ፡፡
49👍2🥰2