#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ባለፋ ሶስት ወር ውስጥ ተሰምቷት የማያውቅ ደስ የሚልና የሚያፅናና ስሜት ተሰማት…..እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነቷን ለመታጠብ ወደ ሻወር ቤት ገባች፡፡ግዙፉ መስታወት ፊት ቆማ የለበስችውን ቢጃማ በቁሟ አወለቀችና እዛው ከእግሯ በታች ወለሉ ላይ ረገጠችው…መላ እሷነቷን በፅሞና ተመለከተች…. ፀጉሯ በዛ ርዝመቱና ብዛቱ ጭብርር ብሎ ከመንግስት ተሰውሮ ዋሻ ውስጥ ለአመታት ተደብቆ የኖረ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ….አማላይ የነበረው የሠውነቷ ቅርፅ አሁንም እንዳለ ቢሆንም የሰውነቷ ክብደት ግን በተጋነነ ሁኔታ መቀነሱ ወደፊት ወጥተው በጉልህ የሚታዩት አጥንቶቾና ወደ ውስጥ ጎድጉደው ጭል ጭል የሚሉ አይኖቾ ምስክር ናቸው፡፡ከሁሉም በላይ ያስደነገጣት ግን የብልት ፀጉሯ ነው…ከስራዋ ባህሪ አንጻር ለአመታት በሶስት ቀን አንዴ ስትላጭ የኖረች ሴትዬ ለወራት ችላ የተባለው የብልቷ ፀጉር በአስፈሪ ሁኔታ አድጎና ተንጨፍርሮ እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ በመሀከል ስንጥቅ መኖሩን እራሱ በእጅ ዳብሰው ካልበረበሩት ማወቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ አስደነገጣት….
….የቀኝ አጇን ዘረጋችና አንገቷን ጠምዝዛ ብብቷን ተመለከተች ..ተመሳሳይ ነው፡፡ በፀጉር ከመሸፈኑም በተጨማሪ ሽታ ከሩቁ ይገፋተራል፡፡ይሄ ሁኔታ ደግሞ ይበልጥ አስገረማት፡፡
‹‹ለምንድነው ግን በቁማችንም እያለን ጭምር ለጥቂት ቀናት ትኩረታችንን ከራሳችን ላይ ስናነሳ እንዲህ በፍጥነት የምንሸተው..?››ስትል ጠየቀች፡፡መልሱን ለመመለስ ግን ብዙም አላስቸገራትም፡፡ ምክንያቱም ከማሳጅ ስራዋ ጋ ተያይዞ ከወሰደቻቸው ኮርሶች አንደኛው የሰው ልጅ አመጋገብ ስርዓት በተመለከተ ነበር ፡፡ ከሺ አመታት በፊት የሞቱ ሰዎች መቃብር ተቆፍሮ ሲገኝና የጥርሳቸው ጤንነትና ጥንካሬ ሲፈተሸ አሁን ካለው የሰው ልጅ ጋር የማይነፃጸር እጅግ ንጹህና ጠንካራ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ምክንያቱም ደግሞ አመጋገባችን ሆኖ ነው የተገኘው፡፡አሁን አብዛኛው ምግቦች ከኬሚካል ጋ ንክኪ ያላቸው… ስኳርነት የበዛባቸውንና ጤንነትን ሳይሆን ጥፍጥና መሰረት ያደረጉ ናቸው…ስለዚህ እነዚህ ገብተው ተፈጥአዊ ሰውነታችንን በክለዋል….በዛ ላይ ምንቀባቸው ቅባቶች የምንረጫቸው ሽቶዎች፤ የምንታጠብበት ሳሙና በጠቅላላ እንዲህ በቀናት ውስጥ በቁማቸንን እንድንሸት ዋና ምክንያቶች መሆናቸው ለመረዳት ብዙ ምርምርም አያስፈልግም፡፡ ወደመኝታ ቤቷ ተመለሰችና የቁም ሳጥኗን ኪስ ከፈተችና የፀጉር መላጫ ማሽኗንና መቀስ አውጥታ በመያዝ ወደ ሻወር ቤት ተመለሰች፡፡ምንም ማሰብ እና መጨነቅ አላስፈለጋትም፡፡ከፀጉሯ ጀመረች…..ከርዝመቱ ወጥራ ወደፊት እየያዘች…..ወገብ ላይ ትጎምደው ጀመር፡፡ ወለሉ በተንጨባረረ እና በተቆጣጠረ
ፀጉር ተሞላ፡፡ ባለከመከም ጎፈሬ ሆነች፡፡በመስታወቱ የተለየች አይነች እስከዛሬ እሷ ራሷ ማታውቃት አይነት ሳባን ተመለከተች፡፡መቀሷን አስቀመጠችና ማሽኗን አመቻቸችና ወደብልቶ ጎንስ ብላ እግሯን ፈርከክ በማድረግ ታጭደው ጀመረ…..ሁሉን ነገር ጨርሳ ሰውነቷን ታጥባና ፀድታ ከሻወር ለመውጣት ከ2 ሰዓት በላይ ነው የፈጀባት፡፡
ከዛ ወደመኝታዋ ተመልሳ የተወሰነ እረፍት አደረገች.. ከተኛበት ብንን አለችና ስልኳን አነሳች፡፡ እንዲህ አይነት ጥንካሬ እና ፍላጎት በደቂቃ ውስጥ ከየት እንዳመጣች አታወቅም፡፡ደወለች..ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ ዶክተር››
‹‹ሳባ ለመሆኑ በህይወት አለሽ…?ምን ነካሽ…?ሌላ ሌላው ይቅር እሺ ህክምናሽን ግን እንዴት ታቋርጪያለሽ…ያልተመቸሽ ነገር ካለም እኮ ተነጋግረን ማስተካከል እንችል ነበር..››
‹‹ምን አልተመቻትም ብለህ አሰብክ…ያደረኩት ነገር አግባብ ነበር እንዴ?›ስትል መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹እሱን ከህክምናሽ ጋር ምን አገናኘው..ምን አልባት በእኔ ህክምናውን መከታተል የሚከብድሽ ከሆነ እኮ በሀገሪቱ ያለሁት የስነ-ልቦና ሀኪም እኔ ብቻ አይደለሁም
… ተነጋግረን ሁኔታዎችን መስመር ማስያዝ እንችል ነበር››
‹‹ኖኖ ዶክተር እንደዛ አስቤ አይደለም…እኔ እንደውም አንተ ካላከምከኝ ማንም ሊያክመኝ አይችልም››አለችው፡፡
የተናገረችው ትክክል ይሁን አይን እራሷም እርግጠኛ አይደለችም…እርግጥ ከእሱ ውጭ በሌላ ሀኪም መታከም አትፈልም….ደግሞም በእሱም ቢሆን መታከሙን የምትችል መስሎ አልተሰማትም፡፡ህመሟ አካላዊ ቢሆን ችግር የለውም፡፡ ጉበቷ ወይም ኩላሊቷ ቢሆን ወይም ማህፀኗን አሟት ልብሶቾን አወላልቃ እግሮቾን አንፈርክካ መላ ሚስጥሯን ለእሱ ማሳየት ቢሆን ምንም አይመስላት ነበር፡፡…..እሱ ፊት ስትቀርብ ከኤፍሬም ጋር በገዛ ምርመራ ክፍሉ የሰራችው ነውር ነው ትዝ የሚለው የገዛ ወንድሙን ስታማግጥበት…ዝግንን አላት፡፡
‹‹እና ታዲያ ለምን እራስሽን ሰወርሽ….?እንዴት እዲህ ይጠፋል…..?ደግሞ ለህክምና ፋይል ላይ ያስመዘገብሽ መረጃ በጠቅላላ የተሳሳተ ነው….አድራሻሽን ጭምር ..አንድ ትክክል የሆነው ስልክ ቁጥርሽ ቢሆንም እሱንም ጠርቅመሽው ይሄው ስንት ወር፡፡››
ደስ አላት…ስለእሷ እንዲህ ሲጨነቅና ሲብሰለሰል መክረሙ ደብዝዞ እና ሊከስም ጫፍ ላይ ደርሶ የነበረ ተስፋዋ በጥቂቱም ቢሆን ቢል ቢል እያለ እንዲነቃቃ ተጨማሪ ነዳጅ ሆኖ ሲያነቃቃት ተሰማት፡፡
‹‹እና አሁን እንዴት ነሽ…?የት ነሽ..?ሀገር ውስጥ ነሽ?››
‹‹አዎ እዚሁ ነኝ፡፡››
‹‹እና እንዴት ነሽ?፡፡››
‹‹እኔ እንጃ ..ምን ላይ እንደሆንኩ አላውቅም…እንዴት እንደሆንኩ አላውቅም….. መኖሬን እራሱ አላውቅም….ለምን አሁን አንተ ጋ እንደደወልኩም አላውቅም….
››አለችው፡፡
ከንግግሯ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከወራት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ካገኛት እጅጉኑ የከፋ እንደሆነ ወዲያው ተረዳ….ስለእሷ ሲያስብና ሲጨነቅ የከረመው ግን ከዚህም የከፋ ነገር ላይ እራሷን ትጥላለች ብሎም ጭምር ስለሰጋ ነበር…እራሱን ያጠፋ ሰው ዜና በሶሻል ሚዲያም ሆነ በሜን እስትሪም ሚዲያ ሲሰማ ደንግጦ በንቃት ዜናውን እስከመጨረሻው ለማየት ሲጥር የነበረው እሷን አስቦ ነው፡፡አሁን ግን በከፋ ሁኔታ ላይም ሆና ቢሆን በህይወት መኖሯ ብቻ አስደሰተው፡፡
‹‹አይዞሽ ይሄ በማንኛውም ሰው ላይ በሆነ ጊዜ ላይ የሚከሰት ነው..አንቺ ደግሞ ከዕድሜሽ በላይ ብዙ ነገር ያየሽና ብዙ ነገር ምታውቂ ጠንካራ ልጅ ነሽ...እኔም ደግሞ በፈለግሽኝ ጊዜና መንገድ ከጎንሽ ነኝ፡፡››
‹‹አንተ ከጎኔ መሆንህን በመስማቴ ተደስቼያለሁ…አመሰግናለሁ፡፡››
‹‹እና መች ብቅ ትያለሽ?›
‹‹እኔ እንጃ››አለችው የምትለው ግራ ገብቷት…
‹‹እኔ እንጃ ማለት ምን ማለት ነው…ህክምናው ቢቀር አንኳን ናፍቀሺኝል… ሆስፒታል መምጣት ካስጠላሽ የፈለግሺው ቦታ መገናኘት እንችላለን፡፡››
‹‹ካልክ ነገ ስንት ሰዓት ይመችሀል?››
‹‹እንቺ የሚመችሽን ሰዓት ነገሪኝ እኔ ፕሮግራሜን አሬንጅ ማድረግ እችላለሁ›› እሷን ከማግኘት የሚቀድምበት ምንም ጉዳይ የለውም፡፡
‹‹በቃ 10 ሰዓት እንገናኝ..››
ደስ አለው….‹‹እሺ የት እንገናኝ?›› ነገረችው
‹‹ችግር የለም….እንገናኛለን…››
‹‹እሺ ዶ/ር ….አመሰግናለሁ››

👍69❤7👏4🥰2
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ሰለሞንና በፀሎት በስልክ እያወሩ ነው፡፡
‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለሽው?››ሲል ጠየቃት
‹‹ምነው ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ ..እንዲሁ ደህንነትሽ አሳስቦኝ ነው….ምን አልባት የማይመች ቦታ ካለሽ ልረዳሽ እችላለው፡፡››
‹‹ምነው ወደቤትህ ወስደህ ደብቀህ ልታኖረኝ አሰብክ››
‹‹ምነው ..ችግር አለው.?.የእውነት የማይመች ቦታ ካለሽ ንገሪኝ››
‹‹አሁን ካለሁበት ቦታ የተሻለ ሊመቸኝ የሚችለው ምን አልባት ገነት ነው….እሱንም ደግሞ ስላላየሁት እርግጠኛ አይደለሁም››
‹‹እንዴ…ከእናትና አባትሽም ቤት የተሻለ ቦታ ነኝ ነው የምትይኝ…ይሄንን ማመን አልችልም፡ ››
‹‹ነገርኩህ እኮ…››
‹‹‹እ ..ገባኝ››
‹‹ምኑ ነው የገባህ?››
‹‹ከእናትና አባት ቤት በበለጠ የሚመች ቦታ የፍቅረኛ ቤት ነው››
‹‹በጣም ተሳስተሀል..አዲስ ቤተሰብ አግኝቼለሁ…አራት ናቸው..ሽማግሌ አባትና እናት፣አንድ ዋንድ ሴትና ወንድ ልጅ አላቸው..ሁለት ክፍል ሰርቢስ ውስጥ ነው የሚኖሩት፣ኑሮቸው ከእጅ ወደአፍ ነው… ፍቅራቸው ግን ሞልቶ የፈሰሰ ነው….ለዘላለም ልጃቸው አድርገው ተቀብለውኛል…ከአሁን ወዲህ ባለው ህይወቴ ሙሉ አነሱ ወላጆቼ እና ቤተሰቦቼ እንደሆኑ እንዲቀጥሉ ምንም ነገር አደርጋለው››
‹‹የሚገርም ነው….እናትና አባትሽ ይሄንን ንግግርሽን ቢሰሙ ልባቸው የሚሰበር ይመስለኛል፡፡››
‹‹እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም…በእነሱ ስህተት ነው ከቤት የወጣሁትና እነሱን ያገኘሁት…አሁን አግኝቼ በደንብ አጣጥሜቸዋለው…እና ወደቤት ብመለስ እንኳን ወላጆቼን ከእነሱ ጋር ነው ማነፃፅራቸው…እና ለእነሱ ቀላል የሚሆንላቸው አይመስለኝም››
‹‹….ለመሆኑ ማንነትሽን ያውቃሉ?›
‹‹አይ አያውቁም.. እኔ ለእነሱ እናቷ የሞተችባት እና የእንጀራ አባቷ ሰክሮ በለሊት ሊደፍራት ሲል አምልጣ የወጣች ሚስኪን ሴት ነኝ››
‹‹ይሄንን ታሪክ አንቺ ነሽ የፈጠርሽው?››
‹‹አዎ…..››
‹‹የምትገርሚ ልጅ ነሽ ..እኔጋም መጥተሸ ተመሳሳይ ታሪክ ብትነግሪኝ አምኜ ልረዳሽ መሞከሬ አይቀርም ነበር››
‹‹የእነሱ እኮ መርዳት አይደለም….እናትና አባት መሆን ነው…..እንደልጃቸው መቀበል››
‹‹ የእውነት አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እኔ እራሱ ለመተዋወቅ ጓጓሁ› ›
‹‹መጓጓትህ ትክክል ነህ››
‹‹ነገሮች ከተስተካከሉ በኃላ ታስዋውቂኛለሽ ብዬ ገምታለው››
‹‹መጀመሪያ እስኪ እኛ ለመተዋወቅ ያብቃን››
‹‹እንዴ እኛኮ በደንብ ተዋወቅን፣ለአመታት የማውቅሽ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው..ያው አካል ለአካል አልተገናኘንም ብዬ ነው፡፡››
‹‹ባክሽ የስልኬ ጋላሪ ባንቺ ፎቶዎ ተጨናንቆል ››ብሎ ያልጠበቀችውን አስደንጋጭ ነገር ነገራት፡፡
‹‹እንዴ በምን ምክንያት?››
‹‹እንዴ ..ደንበኛዬ አይደለሽ?››
‹‹እና የሁሉንም ደንበኞችህን ፎቶ ትሰበስባለህ ማለት ነው?››
‹‹ቆንጆ እና የተለየ የሆኑትን ..አዎ››
‹‹በቻይንኛ ቆንጆ ነሽ እያልከኝ ነው፡፡››
‹‹እ..ምነው አይደለሽም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ ….ለማንኛውም ደስ የሚል ስሜት እንዲሰማኝ አድርገሀል…እና እኔስ የአንተን ፎቶ የማግኘት መብት ያለኝ አይመስልህም?››
‹‹አይ..አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እንድምታስተዋውቂኝ ቃል ካልገባሽ የምታገኚ አይመስለኝም››
‹‹አዲሶቹን ቤተሰቦቼን….እኔ እንጃ ..ስለምሰስታቸው የማደርገው አይመስለኝም››
‹‹‹ትገርሚያለሽ…፣ዋናዎቹን ቤተሰቦችሽን እኮ ተቆጣጥሬቸዋለው…..ለማንኛውም ይህን የመሰለ ቤተሰብ ስላገኘሽ ደስ ብሎኛል….ይሄውልሽ በህይወት ውስጥ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ፡፡ቅጠል የሆኑ ሰዎች… ቅርንጫፍ የሆኑ ሰዎችእና… ስር የሆኑ ሰዎች።ቅጠል የሆኑ ሰዎች ወቅትንና ሁኔታዎችን ጠብቀው ወደ ህይወትሽ የሚገብ ናቸው።ደካሞች ስለሆኑ በእነሱ ተፅዕኖ ስር ፈፅሞ እንዳትወድቂ። ከአንቺ የሚፈልጉትን የሆነ ነገር ስላለ ነው ወደህይወትሽ የሚመጡት... የመከራ ንፍስ በህይወት ዙሪያ ሲነፍስ መርገፍ ይጀምራሉ።እነዚህ ሰዎች አንቺን ማፍቀር የሚቀጥሉት በዙሪያሽ ያሉ ነገሮች ጥሩ እስከሆኑ ጊዜ ብቻ ነው።ንፋስ እንደመታው የወየበ ቅጠል ከላይሽ ላይ ተዘንጥለው ይረግፋሉ። ቅርንጫፍ ሰዎች ደግሞ በአንፃራዊነት ጠንካሮች ናቸው ግን ልትጠነቀቂያቸው ይገባል።ህይወት ጨከን ስትል መገንጠላቸው አይቀርም። ምክንያቱም ጠንከር ያለ የህይወት ጫና የመሸከም አቅም የላቸውም።ነገሮች ጨለምለም ሲሉ እና ተስፋም የሌላቸው ሲመስሉ ጥለውሽ ዞር ለማለት አያመነቱም። ሌሎቹ ልክ እንደአንቺ አዲሶቹ ቤተሰቦች ስር የሆኑ ሰዎች ናቸው። እነዚህ በህይወትሽ በጣም አስፈላጊ ሰዎች ናቸው።ለመታየት ብለው የሚሰሩት ስራ የለም።በመከራሽም በደስታሽም ጊዜ አብረውሽ ናቸው።አስከሞት የታመኑሽ ናቸው።ሲያፈቅሩሽ በነፃ ምንም መልስ ካንቺ ሳይጠብቁ ነው፣እንደዚህ አይነት አንድ ወይም ሁለት ሰው ከጎንሽ ማግኘት የህይወት ዘመን ሽልማት ነው፡፡
‹‹ጥሩ አድርገህ ገልጸኸዋል፡፡እነሱ ብቻ ሳይሆኑ፣አንተም ለእኔ ስር ነህ…በቃ ቸው…ነገ እንደዋወላለን፡፡››
‹‹ቸው …..ደህና ሆኚ››ብሎ ስልኩን ከዘጋ በኃላ …ባለበት ቆሞ ትካዜ ውስጥ ገባ..ይህቺን ልጅ በተመለከተ የተለየ አይነት ኬሚስትሪ በሰውነቱ እየተረጨ ነው….ነገሮች ወዴት እያመሩ ነው?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡
በማግስቱ……
በፀሎት ከሞላ ጎደል ጤንነቷ እየተመለሰ ነው…አረ እንደውም ድናለች ማለት ይቻላል..የእግሯ ስብራት ሙሉ በሙሉ ተጠግኖ በደንብ መራመድ ችላለች..የፊቷ ቁስለትም ሙሉ በሙሉ ጠጓል..አሁን ብቸኛ ችግሯ ፊቷ ላይ ተሸነታትሮ የሚገኘው ጠባሳ ብቻ ነው….እንግዲህ ግማሽ ፊቷን ባደረሰው በተበታተነው ጠባሳ ውስጥ ምን ያህሉ እንድሚጠፋና ከበፊት ቆዳዋ በቦታው እንደሚመለስ ምን ያህሉ ደግሞ እንዳዛው እንደሚቀር ምንም የምታውቀው ነገር የለም…ያንን ለማወቅ በርከት ያሉ ተጨማሪ የማገገሚያ ቀኖች ያስፈልጋታል…ከዛ በኃላ የቆዳ ስፔሻሊስቶች ጋር ሔዳ ሰርጀሪ መሰራትም የግድ ያስፈልጋት ይሆናል….ለጊዜው ያ እያሳሰባት አይደለም…‹‹እሱን ጊዜው ሲደርስና ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ወደቤት ከተመለስኩ በኃላ አስብበታለው››ብላ ወስናለች….አሁን ከጎኗ አቶ ለሜቻ ቁጭ ብለው እያጫወቷት ነው፡፡
‹‹ለልጆቾህ ያለህ ፍቅር ያስገርመኛል››
‹‹አይ ልጄ ሁሉም ወላጆች እኮ ልጆቻቸውን አብዝተው ይወዳሉ…››በትህትና መለሱላት፡፡
‹‹እሱን ማለቴ አይደለም..የእናንተ የተለየ ነው…አይኖችህ ከልጆቾህ ላይ አይነቀሉም….ሙሉ ትኩረትህ ልጆቾህ ላይ ነው..ስለእለት ውሏቸው ታውቃለህ….ጥዋትና ማታ አብረሀቸው ባንድ መሶብ ቀርበህ ሁለቱንም እያጎረስክ ነው የምትበላው፣ብዙ ብዙ ነገር…››
‹‹ልጄ ወድጄ አይደለም እኮ…. እንደምትይው እኔ አባትሽ በብዛት ተትረፍርፎ ያለኝ ፍቅር ነው…ገንዘብ ኖሮኝ ይሄን ስሩ ብዬ መቋቋሚያ..ወይም መነገጃ ጥሪት አልሰጣቸው….ሁል ጊዜ ታዲያ ይሄንን ነገር በምንድነው የማካክሰው ብዬ ሳስብ አንድ የማገኘው መልስ…ጊዜዬንና ፍቅሬን ሳልሰስት መስጠት ነው..አዎ ቢያንስ በዛ ነው ልክሳቸው የምችለው፡››
‹‹ግን እንሱ ምን ያህል እድለኞች መሆናቸውን ያውቃሉ?››
‹‹አይ እነሱ ሳይሆኑ እኔ ነኝ እድለኛ….ምንም ባላደርግላቸው እንኳን ማንም ፊት በኩራት አባዬ ብለው ይጠሩኛል፡፡በቀደም ለሊሴ ይሄ ፌስቡክ ነው ምን በምትሉት ነገር ላይ በተንዠረገገ ፂሜንና በጎፈረ ፀጉሬ የተነሳሁትን የተጎሳቆለ ፎቶ ለጥፋ አባዬ መልካም

👍84❤15🥰4👏4
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
:
:
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ሰሎሞን ሁለቱን ባለትዳሮች ፊት ለፊት አስቀምጦ እያወራ ነው፡፡‹‹የፈለገ ጥረት ብናደርግ ለእያንዳንዱ ብሎን የራሱን ትክክለኛ መፍቻ ካልተጠቀምን ልንፈታው አንችልም!! በህይወታችንም ውስጥ ችግሮች ሲያጋጥሙን ተረጋግተን ለችግሩ ትክክለኛ የመፍትሄ ሀሳብ ማስቀመጥና ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ካልቻልን እንዲሁ ስንባክን እና በችግሩ ውስጥ ስንዳክር ነው የምንኖረው፡፡ይሄንን በስራ አለም በትክክል እየተገበራችሁ ውጤታማ እንደሆናችሁ አውቃለው…በትዳር ህይወታችሁስ?ዋናው ጥያቄ እሱ ነው፡፡››
አቶ ኃይለልኡል ተቀበሉት‹‹ገብቶናል…እንደምንም ብለን በመሀከላችንን የተፈጠረውን ክፍተት በማስወገድ እና ፍቅራችንን መመለስ እንዳለብን በደንብ ተረድተናል…አዎ እንደምታየውም ጥሩ መሻሻል እያሳየን ይመስለኛል፡፡››
ሰለሞን ቀጠለ‹‹ጥሩ ግን ፍቅር ብቻውን በሰላም ለመኖር በቂ አይደለም፡፡በመሀከላችው ምንም አይነት ጥል የሌለ ጥንዶች በመሀከላቸው ፍቅር እንዳለ እርግጠኛ መሆን አይቻልም…እንደዛውም ዘወትር በነጋ በጣባ የሚጣሉና የሚጨቃጨቁ ጥንዶችም በመሀከላቸው ያለው ፍቅር አልቋል ወይም ቀዝቅዞል ማለት አይደለም….ከዛ ይልቅ እንዴት እርስ በርስ እንደሚግባቡ እና አንዱ የአንዱን ፍላጎት እንዴት እንደሚረዳ አልገባቸውም ማለት ነው፡፡ስለዚህ አሁን መልሳችሁ ማደስ የሚገባችሁ ፍቅራችሁን ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ የመግባባት ችሎታችሁንም ጭምር ነው፡፡አንዳችሁ ሌላችሁን በጥልቀት ለመረዳት እስከምን ድረስ ለመጓዝ ትፈቅዳላችሁ?ይሄ ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡››
ወ.ሮ ስንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገሩ‹‹ትክክል ነህ ልጄ… ለፍቀራችን መበላሸት ዋናው ምክንያት እንደውም እርስ በርስ የመግባባት ችሎታችን ስለተበላሸ ነው….እሱም እኔን እኔም እሱን ለመረዳት ምንም የምናደርገው ጥረት አልነበረም…ሁለታችንም እርስ በርስ እንከን ነበር የምፈላለገው….ያንን በደንብ ተረድቼለው፡፡››
‹‹አዎ ይሄ ችግር የእናንተ ብቻ ሳይሆን የአብዛኛው ባለትዳር ችግር ነው…አንድ ሰው በፍቅር ሲወድቅ በመጀመሪያ ስለራሱ ምቾና ደስታ እንጂ ስላፈቀረው ሰው ደህንነት አይደለም የሚጨነቀው…ሁለቱም ተጣማሪዎች በጋብቻ ጥምረት ውስጥ ለእነሱ የሚመች ሰፋ ያለ ግዛት ቶሎ ብሎ ለመያዝ ይጣጣራሉ…ሁለቱም ተመሳሳይ ፍላጎት ስላላቸው ፍትጊያ ይፈጠራል…አንዱ የሌለኛውን ድምበር ማለፍ…ይሄኛው የዛኛውን ቀይ መስመር መደፍጠጥ ይጀምራል……ከሁለት አንዱ በፍጥነት ነቅቶ ወደኃላ በመመለስ መረጋጋት ውስጥ ካልገባ ችግሩ መስመር ይስታል፡፡
እኔ 25፡50፡25 የሚል ፕሪንስፕል አለኝ፡፡በትዳር ውስጥ እሷ(ሚስትዬው) እሱ(ባልዬው) እና እነሱ (ባልና ሚስቶቹ)አሉ፡፡እና ስሜታቸው፤ፍላጎታቸው፤የህይወት አላማቸው ወ.ዘ.ተ ተጠቅልሎ መቶ ፐርሰን ቢሰጠው፡፡እሷ የግሏ ፍላጎት በግሏ የሚያስደስታት ነገር፤ መዝናኛ ቦታ፤ጓደኞች፤ 25 ፐርሰንት ትይዛለች….እሱም ለብቻው 25 ፐርሰንት ይይዛል፡፡50 ፐርሰንቱ ግን የጋራቸው ነው፡፡በጋራ የሚያቅዱበት፤በጋራ የሚሰሩበትና የሚለፉበት ቤት መስራት፤ልጆች መውለድና ማሳደግ…ወዘተ፡፡ሁል ግዜ ተሰፍሮ 25፤50፤25 ላይሆን ይችላል፡፡በተለይ ሴቶች ከእነሱ 25ፐርሰንት 10ሩን ወይም 15 ቱን ቆርሰው ለጋራቸው ያውሉታል…ወንዶች ደግሞ ከሞላ ጎደል አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከጋራቸው ላይ ቆረስ አደርገው የእነሱን 25 ፐርሰንት 30 እና 40 አንዳንዴም ከ50 በላይ ያደርሱታል..የዛን ጊዜ የጋብቻው ባላንስ ይናጋል፡፡ምሰሶው መነቃነቅ ይጀምራል..እርማት ካልተደረገለት ጋብቸውን እያከሳ ይሄድና መጨረሻ ያከትምለታል፡፡…የምናገረው ግልፅ ነው አይደል››
‹‹አዎ..በጣም ግልፅ ነው፡፡››
‹‹በምሳሌ ይበልጥ ለማስረዳት አንድ ገጠር የምትኖር አክስቴ ከአስር በላይ ባሎች አግብታለች፡፡ግማሹን እነሱ ናቸው የፈቷት ግማሾቹን እራሷ ነች ያደረገችው፡፡ከሁሉም ግን የሳበኝን አንደኛውን ልንገራችሁ፡፡አገባሁት አለች..በጣም ሰላማዊ ..ምንም አይነት ክፉ ነገር ማይናገር…የጠየቅኩትን ሁሉ የሚያሞላልኝ ሰላማዊ ሰው ነበር አለች፡፡በፊት ከለመደቻቸው ተደባባዳቢ እና ተጨቃጫቂ ባሎች ጋር የትኛውም ፀባዩ የሚገጥም
አልነበረም፡፡ግን ብዙም ሳይቆይ ሰለቻት….ሁሉ ነገር ዝም እና ጭጭ ያለ ሆነባት…በቃ ግንኙነታቸው ውስጥ ነፍስ አጣችበት ፡፡አንድ ቀን በለሊት ተነሳና በሬዎቹንና ሞፈር ቀንበሩን ይዞ ወደማሳ ወጣ …ሲሄድ ቁርስም አልሰጠችውም..ምሳም ይዛ መሄድ ቢገባትም አልወሰደችለትም..ጭራሽም አልሰራችም…በጣም የባሰው ነገር ደግሞ የቤቱን እቃ ብረትድስት ፤ሰሀን ፤ብርጭቆ አንድም ሳታስቀር ከቤት ጀምራ የቤቱን መግቢያ ደጃፍ…ወለሉን ጠቅላላ አዝረክርካ እና ሞልታ ኩርሲ ላይ ቀጭ ብላ ትጠብቀው ጀመር ፡፡.
ከዛ መጣ…ከውጭ ጀምሮ ያዝረከረከችውን እቃ አንድ በአንድ ጎንበስ ብሎ እየለቀመ…‹‹እታዋቡ …ሰላም ነሽ….?ምንም አልሆንሺብኝም አይደል….?››እያለ ሁሉንም እቃ ወደመደርደሪያ መልሶ ስሯ ቁጭ ብሎ በልምምጥ ጭንቅላቷን መዳበስ ጀመረ..
ከዛ ይህቺ አክስቴ ምን ብታደርግ ጥሩ ነው‹‹ ብድግ አለችና ሻንጣዋን ይዛ‹‹እንዴት ቁርስ አላበላሁህ ..ምሳ አለመጣሁልህ….ቤቱን እዲህ አዝረክርኬ ነው የጠበቅኩህ..ምን እስካደርግህ ነው የምትጠብቀው…?ምንም አይነት የወንድነት ወኔ የለህም እንዴ…?ሁለት ሴት አንድ ቤት አይኖርም… ነውር ነው››ብላ ጥላው ወጣች..በዛው ፈታችው ፡፡አያችሁ ትዳር በጣም ውስብስብ ግንኙነት ነው፡፡የበዛ ጭቅጭና ጥል ብቻ ሳይሆን የበዛ ሰላምና ፀጥታም ሊያፈርሰው ይችላል፡፡፡ዋናው በሁሉም ነገር ሚዛን ጠብቆ መጓዝን መልመድ ነው፡፡››
የተወሰነ ትንፋሽ ወሰደና ፊትለፊቱ ካለ የታሸገ ውሀ በማንሳት አንዴ ተጎንጭቶለት ከንፈሩን አረጣጠበና ንግግሩን ቀጠለ፣እነሱም ልክ በቅርብ ፈተና እንደደረሰበት ቸካይ ታማሪ በጥሞናና በትኩረት እየተከታተሉት ነው‹‹አሁን ልብ በሉ፣ ጥረታችን በመካለላችሁ ያላውን ግጭትና ጭቅጭቅ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይደለም..አይ እንደዛማ አይሆንም እናንተ ሰው ናቸው፣ሁለት ሰዎች ደግሞ በአንድ ጣሪያ ስር አብረው እስከኖሩ ድረስ በሆነ ነገር መነጋገራቸውና በነገሩ ላይ የተለያየ ተቃራኒ ሃሳብ ማንፀባረቃቸው አይቀርም…ስለዚህ መነጋገርና መጨቃጨቅ ኖርማል ነው…አሁን ምንድነው ምናደርገው.. በማንኛውም ጉዳይ ላይ አለመግባባት ተከስቶ ስትነጋገሩ በምን መልኩ ነው ኮምንኬት የምታደርጉት..?ነገሩን ማስረዳትና ማሳመን ላይ ነው ትኩረታችሁ ወይስ ያንን ምክንያት አድርጎ በስድብና በዘለፋ ማጥቃትና ልብ መስበር…አያችሁ ትልቁ ችግር መጋጨታችን ሳይሆን በያንዳንዱ ግጭታችን አንዳችን ለሌላቸውን የልብ ቁስለትና የነፍስ ህመም መስጠታችን ነው፡፡ማጥፋት ያለብን እርስ በርስ መወጋጋቱን ነው…አንዳችን ሌላችን ላይ በምንም አይነት ሰበብ የሚያቆስል ነገር ጦር አስበን አይደለም አምልጦን እንኳን መወርወር ለብንም፡፡እርስ በርስ ከፍ ባለ ቃላት
በተነጋገራችሁ ቁጥር ደግሞ እየተጣላችሁ መሆኑን አታስቡት..መጣላት ቃሉ እራሱ አሉታዊ ነው፡፡እየተጣላችሁ ሳይሆን በጋለ ስሜት እየተነጋገራችሁ ነው፡፡በቃ እንዲህ ነው ማሰብ ያለባችሁ፡፡እንደዛ ካሰባችሁ ቀጥታ ችግሩ በጋለ ስሜት መነጋገራችን ብቻ ስለሆነ ስሜታችሁን በማረጋጋት ነገሩን ትፈታላችሁ፡፡እየተጣላን ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ግን ጋና ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ወይም ሽማግሌ ልትፈልጉ ነው፡፡ልብ በሉ ጮክ ብሎ መናጋገር ሁል ጊዜ መጣላት አይደለም አብዛኛውን ጊዜ በጋለ ስሜት

👍79❤12
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በማግስቱ የናፈቀው ቢሮ የገባው አራት ሰዓት አካባቢ ነበር….የማታው ስካር አንጎበሩ ሙሉ በሙሉ አለቀቀውም…አሁንም ጭንቅላቱን እየወቀረው ነው፡፡ለፀሀፊው መምጣቱን
ስላልነገራት አልገባችም…ከፍቶ ገባና ቁጭ አለ ..የሚሰራው ስራ ስላልነበረ የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው..ስልክ አውጥቶ ደወለ፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…ለሊሴ?››
‹‹ደህና ነኝ ሰለሞን…እንዴት ነው ስራ?››
‹‹አሪፍ ነው..አሁን ተመልሼለሁ…ቢሮ ነው ያለሁት››
‹‹ውይ ለምን ሳትነግረኝ..ቀድሜ ገብቼ አፀዳድቼ ጠብቅህ ነበረ እኮ››
‹‹አይ ችግር የለውም..ቢሮው አሁንም ንፅና የተስተካከለ ነው››
‹‹አዎ እሱማ በሶስት ቀን አንዴ ከፍቼ አናፍሰዋለው….እና ስራህን ጨረስክ ማለት ነው?››
‹‹አይ አልጨረስኩም…በመሀል የሶስት ቀን እረፍት ስላለኝ ነው የመጣሁት…ለመሆኑ ያንቺ ነገር እንዴት ሆነ?››
‹‹የቱ?››
‹‹የሁለቱ ፍቅረኞችሽ ነገር?››
ለሊሴ ሰለሞን ባቀረበላት ሀሳብ መሰረት ከሁለት ፍቅረኞቾ መካከል አንዱን ለባልነት ለመምረጥ ምታደርገውን ጥረት ወዲያው ነበር የጀመረችው ….መጀመሪያ ነጋዴውን ለአንድ ወር ላታገኘው እንደማትችል ነግራ ከመንግስት ሰራተኛው ጋር ነበር የቀጠለችው..ሲደውልላት ትሄዳለች..ዝም ሲላት ትደውልለታልች….ከስራ መልስ ሳታገኘው ወደቤት አትገባም…እሁድ ቢያንስ ግማሹን ሰዓት ከእሱ ጋር ነች፡፡ይበልጥ ትኩረቷን ሰብስባ ከእሱ ጋር ባሳለፈች መጠን በፊት ከምታውቀው በላይ እያወቀችው …በፊት ከምታዳምጠው በላይ እያዳመጠችው መጣች፡፡አሁን ያለበትን የኑሮ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ..
የወደፊት እቅዶቹንና እነዛን እቅዶች ለማሳካት እያደረገ ያለውን ተጋድሎም እየተረዳችና እየተገነዘበች መጣች…..እሱ ላይ ያላት ቅሬታ ባገባው እኔን አኑሮ ቤተሰቦቼንም እንድረዳ የሚያበቃኝ ህይወት ሊሰጠኝ አይችልም የሚል ነበር…አሁን ስታስበው ግን ያንን ከእሱ ብቻ መጠበቅ እንደሌለባት ነው የገባት…እሱ ባለው ቁርጠኝነት ላይ እሷ ተጨምራበት ካገዘችውና ከጎኑ ሆና አብራው ከታገለች ጎዶሎው ሊሞላ የሚችል አይነት እንደሆነ ተረድታለች…ግን ውሳኔ ላይ ከመድረሷ በፊት ለእሱ የመደበችለት ወር ተገባደደ እና ለዛኛው የሰጠችውን ተመሳሳይ ምክንያት ሰጥታ ..ለአንድ ወር ያህል ልትደውልለትም ሆነ ልታገኘው እንደማትችል ነገራ ወደነጋዴው ሄደች፡፡
በእውነት ነገዴው ጋር ልክ እንደወትሮ ሁሉ ነገር ተሰርቶ ያለቀ ሆኖ ነው የጠበቃት…ቤቱ የተዘጋጀ..እቃዎቹ የተደራጁ ናቸው…አዎ እያንዳንዱን ሀብቱንና አኗኗሩን ተራ በተራ አሳያት፣ቀጥታ እንዳገባችው ሕይወቷን ወደመስራት ሳይሆን የተሰራ ህይወት ውስጥ ገብቶ ለመኖር መሞከር ብቻ እንደሚጠበቅባት ተረዳች ፣ግን ለምን ልቧ ወደኃላ እንደሚጎትታት ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም‹‹…ታግዬ ያላሸነፉኩት በሌላ እጅ የተሰራ ህይወት ምን ትርጉም ይኖረዋል?››እራሷን ጠየቀች… መልሱ ቀላል አልነበረም….፡፡
ሁሉንም ሂደት አንድ በአንድ ዘርዝራ አስረዳችው፡፡ ሰለሞንም‹‹እና ምን ተሰማሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አሁንም እንደተወዛገብኩ ነው…ግን በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱ ጥያቄዎች በፊት ከሚመላለሱት የተለዩ ናቸው…እንግዲህ እኔ በህይወቴ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ ከፍተኛ ድክመት እንደለብኝ ነው የተረዳሁት፡፡››
‹‹አይ እንደዛ አይመስለኝም …አንቺ ቀሪ ህይወትሽን አብሮሽ በደስታ የሚዘልቅና ከቤተሰቦችሽም ጋ ተሰስማምቶ የሚያኮራሽ ለፍፅምነት የተጠጋ ባል እየፈለግሽ ነው….በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ለፍጽምና የተጠጋ ነገር መምረጥ ቀላል ነገር አይደለም፡፡አንድ ታሪክ ልንገርሽ..
‹‹ደስ ይለኛል››
ደቀ መዝሙሩ መምህሩን ‹‹ፍፁምና በህይወታችን እንዴት አድርገን ነው ፍፅማዊ የሆነ ነገር መጎናፀፍ የምንችለው? ሲል ጠየቀው ፡፡ መምህሩም አሰብ አደረገና ‹‹የዚህን መልስ
እንድነግርህ ከፈለክ በፊት ለፊት በር ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ቀጥ ብለህ ግባ ።በመንገድህ ከምታገኛቸው አበቦች መካከል በጣም የሚያምረውንና ደስ ያሰኘህን ቀንጥስና በጎሮ በር ውጣ …አንዴ ያለፍከውን አበባ ከእንደገና ወደኃላ ተመልሰህ መቅጠፍ አትችልም አሉት።›› አለው ።እሱም ትዕዛዙን አክብሮ እንዳተባለው ወደ አትክልቱ ስፍራ ገባና እስከመጨረሻው ጥግ ከተጓዘ በኃላ ባዶ እጅን በጓሮ በር ወጣ።
መምህሩ ‹‹ለምንድነው አንድ ቀንበጥ አበባ እንኳን ይዘህ መውጣት ያልቻልከው?››ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ምርጥ የተባለውን አበባ ወዲያው እንደገባሁ ነበረ ያገኘሁት... ግን የተሻለ አገኛለሁ ብዬ በማሰብ ሳልቀነጥስ ወደፊት ቀጠልኩ .. መጨረሻው ላይም ደረስኩ.. ወደኃላ የመመለስ እድል ስለሌለኝ ባዶዬን ለመውጣት ተገደድኩ›› ሲል መለሰ።
መምህሩ መልሱን ሲሰሙ ፈገግ አሉና ‹‹አዎ! ትክክል ነህ ፤ህይወት እንደዛ ነው ።ፍፁምናን ለማግኘት ይበልጥ በዳከርን ቁጥር ብኩን እየሆንክ ትሄዳለህ።እውነተኛ ፍፁምናን መቼም የትም አታገኝም።››ሲሉ መለሱለት። ‹‹ገባሽ አይደል?››
‹‹አዎ ገብቶኛል››
‹‹እንግዲያው ፍፅም በምናብ አለም ካስቀመጥሽው ወንድ ጋር የሚስማማ ባል እንደማታገኚ አውቀሽ ለሚማጡት 10 ቀናት ሁለቱንም ሳታገኚ አስቢበት..ከዛ ማንኛቸው ናቸው የበለጠ የሚናፍቁሽ..የትኛው ቢያቅፍሽ ትፈልጊያለሽ ….?ማንኛቸው የልጆችሽ አባት ቢሆኑ ይሻላል..?በህልምሽ እየደጋገመ የሚመጣው የትኛው ነው?፡፡ለ10 ቀን አስቢበት፡፡››
‹‹እሺ እንደዛ አደርገላው..ግን አሁን አሁን እየገባኝ ያለው እኔ ከባሌ ምን እጠብቃለው ብቻ ሳይሆን ለባሌስ ምን ይዤለት ሄዳለው…?የሚለውን በጥልቀት ማሰብና መዘጋጀት እንዳለብኝ ነው፡፡ ››
‹‹ጎበዝ ነሽ…ይሄ ትልቅ መረዳት ነው..በይ ደህና እደሪ››
‹‹ውይ …ከመዝጋትህ በፊት…ድፍረት አይሁንብኝና ዛሬ ቤት ለምን አትመጣም››
‹‹ለምን?››
‹‹እማዬ የማሪያም ድግስ አለባት….ማህበርተኞቹ እስከ10 ሰዓት ነው የሚቆዩት 11 ሰዓት ብትመጣ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹አረ ተይ››
‹‹ምን አለበት…ቤተሰቦቼ በጣም ነው ደስ የሚላቸው››
‹‹11 ሰዓት ነው ያልሽኝ?፡፡››
‹‹አዎ 11 ሰዓት››
ብቻውን ሆኖ ስለአስቴር እያሰበ ከሚሰቃይ ከሰው ጋር ተቀላቅሎ የባጥ የቆጡን እያወራ ሊረሳት ቢሞክር እንደሚሻለው አሰበእና ‹‹በቃ እሺ መጣለሁ››አላት፡፡
‹‹በቃ አቃቂ ፖሊስ ጣቢያው ጋር ስትደርስ ደውልልኝ..ወጥቼ እቀበልሀለው››
‹‹እሺ ደውላለው››
ስልኩን ዘጋው፡፡ እሺ ማለቱን ፍጽም አላመነም….ጠበል ለመቅመስ ከሜክሲኮ
አቃቂ….ለመሆኑ በህይወቱ ጠበል የተጠራውና ጥሪውን አክብሮ የሄደው መቼ ነው..?ፍጽም አያስታውስም….
እንዳለችው …..እንደደወለላት ደቂቃ ሳታባክን ነው ወጥታ የተቀበለችው….መኪናውን
እዛው አስፓልት ዳር ፓርክ አደረገና ተከትሏት ይዛው ሄደችው.. ግን ወደሚያስደነግጥ ቦታ ነው ይዛው የሄደችው…ይሄንን ግቢ ትናንትና በዚህን ሰዓት መኪና ውስጥ ሆኖ ከአሰሪዎቹ ጋር በመሆን ሲሰልለው ነበር …‹‹ምን አይነት መገጣጠም ነው?››ለለሊሴ ምንም አይነት የመደነቅና የመገረም ስሜት ሳያሳያት ተከተላት፡፡አሁን ነገሮችን ገጣጥሞ ሲያስብ በፀሎት እሱን እንዴት እንዳገኘችውና ስልኩን ከማን እንደወሰደች ተገለፀለት፡፡

👍73❤5👎2