#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ
================
..ፎጣዋን አገልድማ ስትወጣ እሱ ደግሞ ለመግባት እርቃን ሰውነቱን በፓንት ብቻ ሆኖ ወደእሷ አቅጣጫ ሲመጣ አየችው…ዞር ብላ መንገዱን ለቀቀችለት …ቀጥታ ወደውስጥ ገባና የሻወሩን በራፍ ዘጋው…
ባለቤቷን እንዲህ እርቃኑን ስታየው ሁሌ እንደአዲስ እንደገረማት ነው፡፡ሰለብሪቲ አክተር ወይም ታዋቂ ሞዴል እኮ ነው የሚመስለው፡፡እዚህ አካባቢ እንደዚህ ቢሆን የሚባል ቅር የሚያሰኝ የአካል ክፍል የለውም‹‹ሆሆ..ለናሙና የተፈጠረ እኮ ነው የሚመስለው››አለችና ሰውነቷን አደራርቃ በምሽቱ ሶስቱን የእድሜ ልክ አድናቂዎቾና አፍቃሪዎቾ ወንዶችን ያስደምማል ያለችውን አለባበስ ለበሰች፡፡ፀጉሯን አስተካከለች፡፡የተወሰነ ሜካፕ ተጠቀመችና ሽቶ እላዮ ላይ ነስንሳ ወደሳሎን ወጣች፡፡
አለማየሁ ሰማያዊ ቀለም ያለው ሙሉ ሱፍ ለብሶ ዝንጥ ብሎ ሳሎን ቁጭ ብሎ እስኪወጡ እየጠበቃቸው ነበር፡፡
እንዳየችው ‹‹እንዴ ኩማንደር….አምባሳደር መስለሀል፡፡›› አለችው፡፡
‹‹የወደፊት እጣ ፋንታዬ ምን አልባት አምባአሳደር ሊሆን ይችላል፡፡››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ምነው አፍጥጠህ አየሀኝ…ልብሱ አልሄደብኝም እንዴ?››ሲል በጥርጣሬ ጠየቃት፡፡
‹‹አረ የሚያስደነግጥ አለባበስ ነው … እንከን አይወጣለትም ..በጣም ያምራል፡፡››
‹‹ልብሱ ብቻ ነው ሚያምረው?››ስትል ልስልስ በሆነ ቅንዝራም ድምፅ ጠየቀችው፡፡
‹‹ስለአንቺ አላዛር ሲመጣ ይነግርሻል….ያንን አስተያየት የመስጠት መብት ለጊዜው የእሱ ነው፡፡››
ግንባሯን ቋጠረች‹‹ለጊዜው ስትል…?››
‹‹ይሄ ጥያቄ ይዝለለኝ፡፡››
‹‹በጣም ተቀይረሀል ..ድሮ እንደዚህ አልነበርክም››
‹‹እንዴት ማለት?››
‹‹ከእኔ ጋር ለምትነጋገረው ነገር ስትጠነቀቅ አይቼህ አላውቅም ..እንደመጣልህ በነፃነት ነበር የምናወራው፡፡ትዝ ይልሀል ..አንተ እኮ ጓደኛዬ ብቻ አልነበርክም….አንድ ቤት ውስጥ አብረኸኝ ያደክ ወንድሜ ነህ፡፡››
‹‹አዎ..በልጆቼን በሞት ሳጣና አያቴም በቃኝ ብላ ገዳም ጥላኝ ስትገባ ..አንተም ልጄ ነህ ..ከልጄ ጋር አሳድግሀለው ብላ የወሰደችኝ እናትሽ እቴቴ ነች፡፡በእውነት ለእሷ በሚገባው መጠን አልተንከባከብኳትም…፡፡››
‹‹ተው ተው..እቴቴንማ በጣም ነው የተንከባከብካት፡፡.በየጊዜው ብር እንደምትልክላት ማላውቅ ይመስልሀል፡፡እዚህ ከተቀየርክ በኃላ እንኳን እሷን ደጋግመህ አግኝተህ እኛን ግን ለማግኘት ፍቃደኛ አልነበርክም፡፡ካንተ ደግሞ ይልቅ ደግሞ የሚገርመኝ የእሷ ያንተ ተባባሪ ሆና መደበቅ፡፡ …እንደውም አንዳንዴ ከእቴቴ ጋር ስንጣላ እኮ…‹‹ከአንቺ ይልቅ የእኔን እናትነት የተረዳው አለማየሁ ነው…››እያለች ታበሳጨኛለች፡፡እና እሷ በአንተ ደስተኛ ነች…ትንሽ ቅር ሚላት በየጊዜው በአካል ሄደህ ስለማትጠይቃት ነው፡፡በዛ ከአንተ እኔ እሻላለሁ….፡፡››
‹‹ቢሆንልኝ…ለእሷ ምንም ነገር ባደርግ ይገባታል፡፡››
‹‹ለእኔስ…ለስድስት አመት የት እንዳለህ እንኳን ደውለህ አሳውቀሐኝ አታውቅም…አለማየሁ ደወሎ እንዲህ አለ…አለማየሁ ደውሎ በባንክ ይሄንን ላከ ሲባል እንጂ አንድ ቀን ሰሎሜ ሰላም ብሎሻል…?ሰሎሜ አለማየሁ ሰለአንቺ እንዲህ ያስባል ብሎ የነገረኝ ሰው የለም..ሁል ጊዜ አእመሮዬን እንደበላኝ ነው…‹‹ምን አድርጌዋለው…?መቼ ቀን ነው ያስከፋሁት …?.የቱ ጋር ነው የተቀየመኝ? ብዬ እንደተከዝኩ ነበር..እወነቱን ለመናገር በጣም ተቀይሜህ ነበር ..ባገኝህ እንደማላናግርህ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር..ግን በእንደዛ አይነት ሁኔታ ስንገናኝ…ምንም ማድረግ አልቻልኩም...ተቀይሜህ እንደነበረ ራሱ ከእስር ተፈትቼ ቤቴ ከገባው በኃላ ነው ያስታወስኩት፡፡››
‹‹ጥሩ ነው፣ ቂመኛ አይደለሽም ማለት ነው…አንቺን ያላገኘሁሽ ግን ላላገኝሽ ስላልፈለኩ ሳይሆን ተገድጄ ነው››
‹‹ተገድጄ ስትል?››
‹‹ማለቴ….››ንግግሩን እንዳንጠለጠለ አላዛር ከእነሱ በበለጠ.. ልክ እንደእለቱ ሙሽራ ዝንጥ ብሎ ወደእነሱ ሲመጣ ስለተመለከተ ለንግግር የተከፈተ አፉን መልሶ ዘጋ፡፡
‹‹በሉ…እንሂድና …ቀደም ብለን እዛው አካባቢ ደርሰን ብንጠብቀው ይሻለል፡፡››
አለማየሁ አላዛር መጥቶ ማውራት ከማይፈልገው ነገር ስለገላገለው በመደሰት ‹‹ጥሩ …እንሂድ››አለና ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ርምጃውን ከአላዛር አስተካክሎ ወደውጭ መራመድ ጀመረ.፡፡ሰሎሜ ከኃላ ሁለቱንም በትኩረት እያየች ተከተለቻቸው፡፡ሁለቱም ፈርጣማና ወንዳወንድ የሚባሉ ናቸው፡፡ግን አላዛር ወደላይ የተሳበ መለሎ ነው፡፡
//
ከ30 ደቂቃ ጥበቃ በኋላ የተጠበቀው ሁሴን ግዙፍ ሻንጣውን በጋሪ እየገፋ ከተርሚናሉ ሲወጣ ሶስቱም በእኩል አዩት…በደስታና በጩኸት እንዲያያቸው እጃቸውን አውለበለቡለት…ሁሴን ከዛሬ ስድስት አመት በፊት እደሚያውቁት አይነት ነው፡፡ እንዳዛው ውልምጭምጭ ቀጫጫ…ባለትልቅ ጭንቅላትና ሉጫ ፀጉር…የህፃን የመሰለ ፍልቅልቅ ፊት…ነጭ ከሩቅ አይን የሚስብ በረዶ መሳይ ጥርስ ……
ሶስቱም በየተራ እየተጠመጠሙበት ሰላምታ ከሰጡትና ይዘው የመጡትን የእንኳን በሰላም መጣህ ምኞታቸውን የሚገልፅ አበባ አስታቀፉት፡፡ከዛ በኃላ አለማየሁና አላዘር ሻንጣውን ተቀብለው ወደመኪናው ወሰዱና ከኋላ ጫኑለት፡፡…በአላዛር ሹፌርነት ሰሎሜ ገቢና ከእሱ ጎን ተቀምጣ አለማየሁና ሁሴን ከኋላ ሆነው ወደቤት ጉዞ ጀመሩ፡፡
ድንገት‹‹ይገርማል…?››አለ ሁሴን፡፡
አለማየሁ‹‹ምኑ ነው የገረመህ?ከተማዋ ልደቷን የምታከብር የቢሊዬነር ብቸኛ ልጅ መሰለችህ አይደል…?››አለው፡፡
‹‹ማለት?››
‹‹አሸብርቃና ተኳኩላ …በደማቅ መብራቷች ተንቆጥቁጣ ስታያት ገርሞህ እንደሆነ ብዬ ነዋ?››
‹‹..አዎ ያልከው ነገር በጣም አስገርሞኛል..ግን እኔ ለማውራት የፈለኩት ሶስታችሁን በአንድነት መጥታችሁ ትቀበሉኛላቹሁ የሚል ምንም አይነት ግምት ስላልነበረኝ በዛ መደነቄን ነው፡፡፡፡›
ልክ እንደሁሴን እሷም ሶስቱም የልጅነት እና የአፍላ ወጣትነት ጓደኞቾ እና አፍቃሪዎቾ ከበርካታ አመታት በኋላ እንዲህ አንድ ላይ ተሰብስበው አይናቸው እሷ ላይ ሲያቁለጨለጩ በመመለከቷ እየተገረመች‹‹ምን ማለት ነው? ሶስታችንም እኩል ጓደኞችህ አይደለንም እንዴ…?ለመሆኑ መጥቶ ይቀበለኛል ብለህ የገመትከው ማንን ነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው አሌክስን ነበር፡፡እናንተን በማግስቱ ባገኛችሁ ብዬ ነበር ያሰብኩት፡፡››
‹‹አንተ …ከእኛ ይልቅ አሌክስ ቁምነገረኛ የሆነው ከመቼ ወዲህ ነው…?ነው ሰው ሀገር ከሄድክ በኃላ ፀባያችን ተምታታብህ››አለችው ሰሎሜ በመገረም፡፡
አለማየው በፈገግታ‹‹አንቺ …ሰው ሁሉ ስለእኔ ልክ እንደአንቺ የተሳሳተ ግምት ያለው ይመስልሻል እንዴ?››አላት፡፡
‹‹ተው ተው…ከመሀከላችንማ አንደኛው ቁምነገረኛና ኃላፊነትን የሚወስደው አላዛር ነው…አንተ እንደውም በዚህ ጉዳይ የመጨረሻው ሰው ነህ››አለው ሁሴን፡፡
‹‹አንተ ዲያስፖራ ለመሆኑ ዜግነትህን ቀይረሀል?››ሲል ጠየቀው፡፡
ያልጠበቀውን ጥያቄ ስለተጠየቀው ግራ ተጋባ‹‹አይ አልቀየርኩም…ግን ለምን ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ ኢትዬጵያዊ ዲያስፖራ ከሆንክ የሚጮህልህ ኤምባሲ ስለሌለ ለዚህ ንግግርህ የሆነ ሰበብ ፈልጌ ከርቸሌ ልወረውርህ ነዋ….እንደድሮ አለማየሁ ብቻ አይደለሁም..ኩማንደር አለማየሁ ነኝ፡፡››

👍63❤8👎2🔥1🥰1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
///
‹‹ልጄ አንተ እንዲሁ ሰበብ ሆናብህ እንጂ ሰሎሜን የገደልካት አንተ አይደለህም››
‹‹እማዬ አሁን በቃሽ …ባበቃለት ጉዳይ ላይ ምንም ለውጥ ላታመጪ አትድከሚ››
‹‹አይደለም..ሰሎሜን የገደልናለት እኔና ስርጉት ተባብረን ነው.››ስርጉት በተቀመጠችበት ሆና አቃሰተች….ዳኛው መተንፈስ ከበዳቸው፡፡ሳራ ግን ለማናቸውም ግድ አልነበራትም..የእሷ ዋናው ትኩረት ልጇን ከእስር ማዳን ብቻ ነው..እና ንግግሯን ቀጠለች፡፡
‹‹.የዛን ቀን አንተ እኛን ወደቤታችን ከመሸኘትህ በፊት መጠጧ ውስጥ መድሀኒት ጨምረንባት ነበር..ከ30 ደቂቃ በኃላ እንደማሳበድ አድርጓት በአንድ ሰአት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚገድላት መድሀኒት ነበር፡፡እሷ የተቀየረችብህና ከመስታወት ላይ ግንባሮሯን የከሰከሰችው በመድሀኒቱ ተጽዕኖ ነው…መስታወቱ ሆዷ ውስጥ ቢሻጥ እንኳን አልሞተችም ነበር…አባትህ መጥቶ ሀኪም ቤት ሊወስዳት መኪናው ውስጥ አስገብቶ መንገድ ከጀመረች በኃላ ነው እስትንፋሷ የተቋረጠው…ያም የሆነው በተወጋችው ውግ ወይም በፈሰሳት ደም ሳይሆን በጠጣችው መርዝ ምክንያት ነው፡፡
‹‹እማዬ ይሄን እንዴት እሰከዛሬ ሳላውቅ…?አባዬ አንተ እንዲህ መሆኑን ታውቃለህ?››ሲል አባቱ ላይ አፈጠጠበት፡፡
አቀርቅሮ የነበረው አቶ ፍሰሀ በከፊል ቀና አለና ‹‹ከአንተ እና ከአለም በስተቀር ይሄንን ጉዳይ እዚህ ቤት ያለው ሁሉም ሰው ያውቃል፡፡››ሲል እውነቱን ፍርጥም ብሎ መለሰለት፡፡
‹‹ምን አረገቻችሁ ቆይ …?ምናችሁ ላይ ደረሰች?››አለም በእንባ ታጥባ እየነፈረቀች ሳራ ላይ አፈጠጠችባት፡፡
ሳራ እሷን ችላ ብላ ወደልጇ እየተመለከተች‹‹አንተን እንዳታገባህ እና ከስርህ እንድትርቅ ለአመታት ለመናት.. አስጠነቀቅናት፤ እሷ ግን ሌላ ሰው አግብታ ወልዳ እንኳን ልትተውህ አልቻለችም…የልጄ ህይወት በእንደዛ አይነት ሁኔታ ሲበላሽ ቆሜ ማየት አልቻልኩም፡፡እኔ ስርጉትን እንድታገባ ነበር ምፈልገው፣ከልቧ በጣም የሚታፈቅርህ ሰሎሜ ሳትሆን ስርጉት እንደሆነች በደምብ አውቃለው..››
ወዲያው ሳራ ንግግሯን እንዳገባደደች ኩማንደር ተቀበላት‹‹ያው እንግዲህ መጠኑ ይለያይ እንጂ በእናትሽ ግድያ ሁላችንን የየድርሻችንን ተወጥተናል…እኔ በእለቱ እስከእራት ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር አብሬቸው የቆየሁት…ከለሊቱ ዘጠንኝ ሰዓት ጋሽ ፍሰሀ ደወለልኝ.. ስመጣ
…እናትሽ ጋሼ መኪናው ውስጥ እጥፍጥፍ ብላና በደም ተበክላ ነበር…ጋሼ የሆነውን በአጭሩ አስረዳኝና የሚሆነውን እንዳደርግ ሀላፊነቱን ለእኔ ሰጠኝ ….ነገሩ ወደህግ ከሄደ ጁኒዬር፤ሳራም ሆነች ስርጉት ዘብጥያ መውረዳቸው አይቀርም …ምን ማድረግ እንዳለብኝ ሳስብ ያ ሊቁ የተባለው እብድ በዛ ውድቅት ለሊት እየለፈለፍ በእርባታ ድርጅቱ ፊት ለፊት ባለው መንገድ ሲያልፍ አየሁት..ወዲያው ሀሳብ ብልጭ አለልኝ..ሮጥኩና ይዤው ወደውስጥ ገባው..ከማታ እራት የተረፈ ምግብና መጠጥ ስለነበረ እሱን ሰጠሁትና ስለማደርገው ነገር መዘጋጀት ጀመርኩ..የምጠቀምበት እቃ ስፈልግ የእንስሳት ዶክተሩ የህክምና ቁሳቁስ የሚይዝበትን ሳጥን በረንዳ ላይ ተቀምጦ ነበር፤አይኔ ውስጥ ገባ፣ ቶሎ አልኩና ከፈትኩት ፡፡ የቀዶ ህክምን ሚገለገሉበትን ቢላዋ አገኘሁና .. በወቅቱ በጣም ተደናግጬ ስለነበረ የማደርገውን ሁሉ የማደርገው በደመነፍስ ነበር….እና ያው ልጅ እንደገደላት እንዲመስል አደረኩና ጥዋት ለፖሊስ ተደወለ.. በኃላ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተጓዙ ሳለ አያትሽ ልጄን የገደላት እብዱ ሳይሆን እነሱ ናቸው… የሚል ወሬ መንዛት እና
አቤቱታ ማሰማት ጀመሩ…ከዛ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሰዎች ዘንድ አንዳንድ ጥርጣሬዎች ብልጭ ማለት ጀመሩ..ሬሳው በደንብ ይመርመር የሚል ግሩፕ ተነሳ…ከዛ ከጋሼ ጋር ተማከርንና የሆስፒታሉ የሬሳ ማስቀመጫ ክፍል እሳት እንዲነሳና እሬሳውም እንዲቃጠል አደረግን..በስተመጨረሻም አያትሽን ይሄንን ሀገር ለቀው ካልሄዱ አንቺን ነጥቀን እስከወዲያኛው እንዳያገኙሽ እንደምናደርግ አስፈራርተናቸው ዝም እንዲሉና ከተማውንም ለቀው እንዲሄዱ አደረግን…እናም በተጨማሪ ስለእናትሽ አሟሟት ሊነግርሽ ነበረውን ሙስጠፋንም የገደልኩት እኔ ነኝ!!የዛን ቀን እኛ ሳናየው እዛ ተደብቆ እያንዳንዱን ነገር ሲያይ ነበር….ይሄን ሁሉ ነገር ግን ፍርድ ቤት ቀርቦ ያምንልኛል ብለሽ እንዳትጠብቂ…››ሲል ንግግሩን አገባደደ፡፡
አለም ደም በለበሱ አስፈሪ አይኖቾን ኩማንደሩ ላይ አፍጥጣ‹‹ቆይ ቆይ እስኪ…ልጁ የገደላት ለማስመሰል ከሞተች በኃላ በዛ የቀዶ ጥገና ቢላዋ ደጋግመህ ወጋሀት አይደል?
…?ከዛ ደሟ ሲንፎለፎል በእጅህ እየዘቅክ እዛ ሚስኪን ልጅ ልብስ ላይ አዳረስከው …እንዳዛ አይደል ያደረከው?በቁሟ እያለች በፍቅር ልብህን ስለሰበራች ልትበቀላት ታስብ ነበር፣ግን ለማድረግ ወኔ አልነበረህም..በዛን ወቅት ግን አጋጣሚው ተመቻቸልህ..ነፍሷ ውስጧ ባይኖርም ደጋግመህ ሰጋዋን በመበሳሳት ንዴትህን ተወጣህባት….ከዛ ሬሳዋ ለምርመራ ሆስፒታል ገባ ..አንዳንድ ጥርጣሬ የሚያስነሱ ነገሮች መፈጠር ሲጀምሩ እራሳችሁን ከማንኛውም አደጋ ጥርጣሬ ለመጠበቅ አስፈላጊ ስለነበረ ጋሼ ፍሰሀ ደግሞ የሆስፒታሉ የሆነ ክፍል በእሳት እንዲያያዝ እና ሬሳዋም እንዲቃጠል እና አመድ እንዲሆነ አደረገ..ከዛ አቶ ዳኛ በዚህ ወንጀል ውስጥ ልጁ ስላለችበት ይህንን ወንጀል እንዳይጋለጥ ባለህ ስልጣን ሁሉ ተጠቅመህ ፋይሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲዘጋ አደረክ…፡፡በትክክል ተረድቼችኋለው አይደል..?እንዲህ ነው ያደረጋችሁት?
‹‹ሁሉም በመሸማቀቅ አንገታቸውን አቀርቅረው ነበር የሚሰሟት‹‹እስከአሁን እንደሰማሁት ከሆነ እኮ ጁኒዬር ብቻ አይደለም ራሱን ለህግ አሳልፎ መስጠት ያለበት …ሁላችሁም ናችሁ..እና እኔ ዳኛ ብሆን በጣም ትንሹን ፍርድ የምፈርደው በእሱ ላይ ነው….እሱ ሳያስበው…በድንገተኛ አደጋ የፈጠረው ወንጀል ነው…ሌለቻችሁ ግን አስባችሁ እና አቅድ አውጥታችሁ ደግማችሁ ደጋግማችሁ እናቴን በነፍስም በስጋም አጥፍታችኃታል….እና ነገ ወደከተማ ስንመለስ ምን እንደምታደርጉ ለማየት በጣም ጎጉቼለው….፡፡››
‹‹መቼስ ሁላችንም ሳታጠፊን እንቅልፍ አይወስድሽም አይደል…?ደስ ይበልሽ ይሄው ተሳካልሽ››አሉ ዳኛው ቅስማቸው ስብርብር ብሎ፡፡
‹‹ደስ ይበልሽ !!….ጭራሽ ደስ ይበልሽ…?.ፍርድን በአደባባይ ሲሸጦት ያዛን ጊዜ ማሰብ ነበረቦት››
‹‹አይ መሬት ያለ ሰው….በእኔ ላይ የደረሰውን ወላጅ ስትሆኚ ነው የምታውቂው….ልጄን ከእስርና ከእንግልት ለማዳን ስል ነው እዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ የገባሁት››
‹‹አይ ልጆትን ከእስር ለማትረፍ ብቻ አይደለም….ከሶሌ ኢንተርፕራይዝም የ10 ፐርሰንት የአክሲዬን ድርሻ በልጆት ስም ማግኘት ችለዋል፡፡››
‹‹ይህ ፍፁም እውነት አይደለም…ያንን አክሲዬን የገዛሁት በራሴ ብር ነው….ከወላጆቼ በውርስ ያገኘሁትን ንብረት በጠቅላላ ሸጬ ነው የገዛሁት…ያንንም ፈልጌው ሳይሆን ኩማንደሩ እና ፍሰሀ አስገድደውኝ ነው፡፡በልጄ አስፈራርተውኝ ነው››
ዳኛው የሚናገሩትን ባለማመን ቀና አለችና ኩማንደሩ ላይ አፈጠጠችበት፡፡
‹‹አዎ..እውነቱን ነው፡፡ይሄንን ወንጀል ዛላለም በመሀከላችን እንደተቀበረ እንዲቆይ እርስ በርስ የበለጠ መተሳሰር አለብን ብለን አሰብን…ከዛ ከጁኒዬር እና ከሳራ ድርሻ ላይ ተቀንሶ በስርጉት ስም አክሲዬን እንዲገዙ አደረግን….ባይሆን እኔ ቀጥታ ጠይቄ ባይሆንም ከእናትሽ ሞት በኃላ የአክሲዬን ድርሻዬ ወደ30 ፐርሰንት እንዲያድግ ሆኗል….››

❤46👍5😱2