አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትንግርት


#ክፍል_አርባ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ፅዮን እና ታዲዬስ እሁድ ከምሽቱ 12 ሰዓት ሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ቁጭ ብላው እሷ ለስላሳ እሱ ቢራ አዛው እየተጐነጩ ያዘዙትን መክሰስ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡የምረቃ በዓሉ ካለፈ በኃላ በሣምንታቸው ዛሬ መገናኘታቸው ነው፡፡‹‹እሺ ፅዮን ለምን ግን ወይን ነገር አትሞክሪም ነበር?››

<<አንደኛ አልኮል የሚባል ነገር ሞክሬ አላውቅም ...ሁለተኛ የማያየው ዓይኔ ሳያንስ ጠጥቼ እምሮዬንም እንዳያይ አድርጌ እንዴት ልሆን ነው?››

‹‹አይ ሳታበዢ ማለቴ እኮ ነው፡፡››

‹‹ያው መጠጣት ከጀመርኩ ቢያንስ አንድ ብርጭቆ መጨረሴ ይቀራል..ያ ማለት ደግሞ እኔን ለማስከር በቂ መጠን ነው…ግድ የለህም ለስላሳው ይብቃኝ፡፡››

‹‹ያው ብትሰክሪም እኮ እኔ አብሬሽ አለሁ ብዬ ነው፡፡››

‹‹አይ እኔ በራሴ ድክመት እራሴን ጥዬ ሰውን ደግፉኝ ማለት አይመቸኝም፡፡››

‹‹ተቀብያለሁ››አለ በጠንካራ መንፈሷ ተደስቶባት፡፡

‹‹ፂ ስለበቀደሙ ጉዳይ እንድናወራ ነው ዛሬ የቀጠርኩሽ››ወደዋናው ቁምነገር ድንገት ገባ።

‹‹ይመቸኛል..እኔም እንደዛ እንደሆነ ተስፋ በማድረግ ነው የመጣሁት..ቀጥል፡፡››

‹‹እንዴት እንደምቀጥል አላውቅም፤ብቻ…..››

‹‹ታዲ ..እኔ የ28 ዓመት ወጣት ነኝ፤በህይወቴ ብዙ ውጣ ውረድ ያየው ሰው ነኝ.. ህይወት ነጩንም ሆነ ጥቁሩን ክፍሎቿን በማፈራረቅ አሳይታኛለች፡፡አንድን ነገር ፈልጌዋለሁና የግድ አገኘዋለሁ ማለት እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡››

‹‹በህይወትማ ምንም ነገር ከልብሽ አገኘዋለሁ ብለሽ ካሰብሽ ታገኚዋለሽ፡፡››

‹‹አውቃለሁ....የሆነ ነገር አገኛለሁ ብለህ ከልብህ ከተመኘህ፤ ምኞትህንም ለማሳካት በሙሉ ጉልበትህ ከተንቀሳቀስክ የማይሳካልህ ነገር እንደሌለ እኔም አምናለሁ፤ይሄ ግን ፍቅር ላይ ሲሆን ከሚሰራበት ጊዜ ይልቅ የማይሰራበት ጊዜ ይበልጣል፡፡››

‹‹እንዴት እንዲህ ልትይ ቻልሽ…?ከፍቅር አምላክ ጋር ትንሽ የተቀያየማችሁ ይመስላል፡፡››

‹‹ትንሽ አልከው...ምን ትንሽ ብቻ ...ለአምስት አመት ተኮራርፈን በደረሰበት ላልደርስ ተማምለን… ሳይደርስብኝ ሳልደርስበት ጥሩ ጊዜ አሳልፈን ነበር ፡፡››

‹‹ታዲያ እንዴት ሆናችሁ?››

‹‹ምን እንዴት ሆናችሁ አለው... አንተን ሳገኝ መሀላዬን አፍርሼ ደጅ እየፀናሁ እያየኸኝ?››

‹‹ደጅ ጽናት አልሽው፤ለማንኛውም እስኪ በምን ተኮራርፋችሁ እንደነበረ ብትነግሪኝ ? ማለት ደስ ካለሽ…..››

ዝም አለች... ጭንቅላቷ ወደታች ተደፋ‹‹…ምን መሰለህ......››ብላ ልትቀጥል ስትል ያዘዙት መክሰስ መጣና ቀረበላቸው፡እየተጎራረሱ በሉ..ከጨረሡ በኃላ አብረው ወደ እጅ መታጠቢያው በመሄድ ታጠቡና ወደመቀመጫቸው ተመለሱ፡፡ታዲዬስ ሁለተኛ ቢራውን አዘዘ..ዛሬ ካለወትሮው ጠጣ ጠጣ አሰኝቶታል፡፡

‹‹ምነው ዝም አልከኝ ...?››አለችው ልትጀምርለት የነበረውን ታሪኳን እንድትቀጥልለት ባለመጠየቁ ቅር ብሏት...

‹‹ኧረ ዝም አላልኩሽም ….ዝም ስላልሽ እኮ ዝምታሽን ላለመረበሽ ብዬ ነው፤እኔ ዝምታዬን ከሚረቡሹኝ ንግግሬን ቢያቋርጡኝ ይሻለኛል፡፡››

‹‹እሱስ እውነትህን ነው….ግን አሁን ዝምታ ውስጥ ስላልሆንኩ አትረብሸኝም

...ይሄውልህ ታዲ እኔ የሻሸመኔ ልጅ ነኝ፡፡ ትውልዴ እስከተወሰነ ጊዜም እድገቴም እዛ ነው፡፡ አባቴን እና እናቴን አላውቃቸውም ማለቴ በአካል አላውቃቸውም...ያሳደገችኝ የአባቴ እናት አያቴ ነች ... እናቴ ገና አንድ አመት ሳይሞላኝ ነው አባቴ ክንድ ላይ ጥላኝ ሀገሩን ጥላ የጠፋችው፡፡ ከአንድ አመት በኃላ አባቴም በተራው ሁኔታዎች ስልችት ሲሉት እኔን ለእናቱ ሰጥቶኝ ውትድርና ተቀጥሮ ለጦርነት ወደ ሰሜን ይሄዳል፡፡

ከዛ በኃላ አያቴ ያለቻትን አንድ ክፍል ቤት በደባልነት አንድ ደደፎ ለሚባል ከገጠር ለትምህርት ለመጣ ልጅ አከራይታ ከእሱ ከምታገኘው ገቢ በተጨማሪም በደካማ አቅሟ ጠላ እየጠመቀች አንዳንዴም አረቄ እያወጣች በመሸጥ እኔን ማሳደግ ትጀምራለች ፡፡ስምንት ዓመት ሲሞላኝ ግን ያልታሰበ ችግር ተፈጠረ..

ዓይኖቼን ይጋርደኝ ጀመር ..በወቅቱ አያቴ እንኳን ለህክምና ለሆዴም መሙያ የሚሆን ሳንቲም ለማግኘት በመከራ ነበር ሚሳካላት…፡፡

ባቅሟ የቻለችውን ፀበሉንም የባህል መድሀኒቱንም ብትሞክርልኝም ከቀን ወደቀን እየባሰብኝ መጥቶ ከአንድ አመት በኃላ ሙሉ በሙሉ ሁለቱም አይኖቼ ታወሩ..ከዛ ትምህርቴንም ከሁለተኛ ክፍል ግማሽ ላይ አቆረጥኩ፡፡አያቴ ግራ ገባት ፡፡በሚመጣው አመት ግን ያ እቤታችን በደባልነት ይኖር የነበር ያልኩህ ተማሪው ልጅ ሚሽኖቹ ጋር ተሯሩጦ በአዳሪነት አስገባኝ፡፡ ይገርምሀል አያቴን ልክ እንደእናቱ ነበር የሚወዳት... እሷም ከእኔ ለይታ አታየውም ነበር እንዲሁ ስሙ ተከራይ ተባለ እንጂ እኛ የምንበላውን ይበላል እሱ የሚበላውን እንበላለን ስናጣ አብረን እንራባለን፡

እኔ ሚሽን በአዳሪነት ከገባሁ በኃላ አያቴ ጋር እኖር ከነበረው ኑሮ በተሻለ ሁኔታ እኖር ጀመር፤ ትምህርቴንም በጥሩ ሁኔታ መከታተል ጀመርኩ፤ድንገት ግን ምን እንደተፈጠረ ታውቃለህ? ብቸኛ ዘመዴ የሆነችው አያቴ ሞተች፡፡በወቅቱ የ5ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ… ዕድሜዬም ወደ 14 አካባቢ ተጠግቶ ነበር ..በጣም ነው የከበደኝ፡፡ ለመጽናናት በጣም አስቸግሬ ነበር፡፡ይገርምሀል እቤታችንን ተከራይቶ ነበር ያልኩህ ልጅ በወቅቱ አስረኛ ክፍል ደርሶ ነበር፡፡በአያቴን ሞት በጣም ነበር ያዘነው…፡፡

ከዛ እኔን መንከባከብ የእሱ ኃላፊነት እንደሆነ ነበር የሚያስበው፤ በሳምንት ሁለት ቀን እየመጣ ይጠይቀኝ ነበር፤ደግሞ ሲመጣ ባዶ እጁን አይመጣም..ደብተር፣እስኪሪብቶ፣የፀጉር ቅባት፣ማበጠሪያ፣ፓንት ...ብቻ የማይገዛልኝ ነገር አልነበረም፤ካጣ ካጣ የ 25 ሳንቲም ማስቲካም ቢሆን ይዞልኝ ይመጣል..ደግሞ እኮ የሚገርመው እሱም ምንም የሌለው የደሀ ገበሬ ልጅ መሆኑ ነው፡፡ ግማሽ ቀን ይማራል ኑሮውን ለመደጎም ደግሞ ግማሽ ቀን ጋራዥ ይሰራል...ከዛ በሚያገኛት ሽርፍራፊ ገንዘብ ነበር ለእኔ የሚያስፈልገኝን ነገር ይገዛልኝ የነበርው፡፡

በዛ ላይ የቤት ኪራዬን በየወሩ ቀን እንኳን ሳያስተጎጉል አምጥቶ ይሰጠኛል…ተወው ይቅር አያስፈልገኝም ብለውም አይሰማኝም...‹ነገ ብትቸገሪ ለአንድ ነገር ይሆንሻል.. አስቀምጪው >> ይለኛል...እኔ ደግሞ የተለየ ወጪ ስለሌለኝ እጄ ላይ እየተጠራቀመ ሲበዛብኝ አንድ የምወዳት አስተማሪዬ ጋር ማስቀመጥ ጀመርኩ፡፡

እንዲህ እንዲህ እያለ ቀናቶች እየነጐዱ እኔም እያደግኩ በትምህርቴም እየገፋሁ መጣሁ..በነገራችን ላይ ሙዚቃ መሳሪያ መነካካት የጀመርኩት እዛው ሻሸመኔ አይነስውራን ትምህርት ቤት እያለሁ ነበር፡፡

ስምንተኛ ክፍል ስደርስ ደደፎ 12ተኛ ክፍል ጨርሶ ነጥብ ስላልመጣለት መንጃ ፍቃድ አውጥቶ ሹፌር ሆነ፡፡በዚህን ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን መምጣቱን አቁሞ በሳምንት አንዴ
..አንዳንዴም በአስራአምስት ቀን አንዴ ይመጣ
ጀመር፡፡ሲመጣ ታዲያ ይዞልኝ የሚመጣውን
ነገር አትጠይቀኝ ... ምንም የሚቀረው ነገር
አልነበረም፤ለእኔ አይደለም ለጓደኞቼ እራሱ ይተርፍ ነበር፡፡ የጽዮን ወንድም መጣ ከተባለ ጓደኞቼ በሙሉ ጥርስ በጥርስ ነበር
👍738