አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-26
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎

ትዕግስት የአሮራ ረዳት ሆና ስራ ከጀመረች አንድ ወር አለፍት።በአንድ ወር ውስጥ ብዙ ስራለሁ፤ የመንግስቱንና የአሮራን የፍቅር ጉዳይም መስመር አስይዛለሁ ብላ እቅድ አውጥታ ነበር።እስከአሁን ግን ምንም ያገኘችው ተጨባጭ ውጤት የለም።ይሄ ነገር ግራ ሲያጋባት ከቀናት በፊት መንግስቱን ሆነ የአሮራን  አጎት እዝራን ሳታማክር አንድ ነገር ለብቸዋ ወሰነች።እነሱን ያላማከረችበት ዋና ምክንያት  በሀሳቧ ሊስማሙ   እንደማይችሉ እርግጠ ኛ ስለሆነች ነው።ነገሩን ደግሞ  የግድ  ማድረግ  እንዳለባት ተሰምቷታል።ካለዛ እረፍት አታገኝም።በውስጧ የተፈጠረውን ውዠንብር  እና  ማዕበል መሳይ ነውጥ ልታጠራ የምትችለው  በዚህ መንገድ ከሆነ ብቻ እንደሆነ እርግጠኛ ነች።።
በአንድ ወር የስራ ቆይታዋ  በአሮራ እና በአቶ ግርማ መካከል  ያለው ግንኙነት እጅግ ውስብስብና  በቀላሉ ቋጠሮ ሊፈታ የማይችል ጤናማ ያልሆነ ስውር ገመና ነው የሆነባት።እርግጥ አቶ ግርማ ወላጅ አባቷ  እንዳልሆነ ማወቅ ችላለች።ያንንም ማወቋ ነው የምታያቸውን ነገሮች እርስ በርስ በማናበብ  አንድ አይነት ትርጉምና ፍቺ ለማግኘት መባከን የጀመረችው።ያንን በንድፈ ሀሳብ ደረጃ በአእምሮዋ የደረሰችበትን መላምት በተጨባጭ ማረጋገጥ  እና በማስረጃ ማስደገፍ አለባት።ከዛ በኃላ ነው ወደ  ሌሎች ሂደቶችን መሸጋገር የምትችለው።ለሁለት ቀን የአቶ ግርማና የአሮራ መኝታ ቤት ውስጥ በድብቅ ካሜራ አስቀምጣ ነበር።አሁን በድብቅ ያስቀመጠችውን ካሜራ በድብቅ አንስታ ምን እንደተቀረፀበት ለማየት ወደክፍሎ እየገባች ነው።በራፍን ከውስጥ ቆለፈችና ላኘቶፓን ይዛ አልጋዋ ላይ ወጣች።ሜሞሪውን አወጣችና ሪደር ውስጥ ከታ ላኘቶፑ ላይ ሰካችው። እንዲጫወት ፕለይን ተጭና በጉጉት መጠበቅ ጀመረች...ረዘም ያለ ደቂቃ እንቅስቃሴ አልባ ባዶ ክፍል የተቀረፀበት ስለነበረ የምትፈልገውን ነገር ለማየት ትዕግስቷን ተፈታተናት።
ከዛ የአሮሯ ምስል ታየ...ትዕግስት  ተነቃቃች።ስልኳን በእጆ ይዛ መልዕክት ትመላለሳለች ...ከመንግስቱ ጋር እንደሆነ እርግጠኛ ነች ..መልዕክቱን ፅፋ ስትልክም ሆነ መልዕክት መጥቶላት ከፍታ ስታነብ  በፊቷ ላይ የሚረጨው ደስታና በሳቅ የታጀበ ፈገግታዋ  ልዩ ነው።"ይህቺ ልጅ ቀስ በቀስ እያፈቀረችው ነው?"ስትል አሰበች።እናም ደስ አላት።መንግስቱ በሚያፈቅራት መጠን አሮራም እሱን ካፈቀረችው የእሷ ስራ ቀላል ሆነ ማለት ነው።ቀስ በቀስ በመሀከላቸው ያለውን እንቅፋት ማስወገድ ከቻለች የተቀረውን እራሳቸው እንደሚያስተካክሉት በማመን   ፊልሙን ማየቷን ቀጠለች።
🍎ድንገት አሮሯ በርግጋ ስልኳን አጠፋፍታ ኮመዲኖ ላይ በማስቀመጥ  ለብሳ የነበረውን ልብስ ስታወላልቅ ይታያል።ከዛ ዕርቃን ገላዋን በነጭ ፒኪኒ ፓንት ብቻ ዘላ አልጋዋ ላይ  ወጥታ  ዝርግትግት ብላ ከረጅም ሰዓት በፊት 🌒እንቅልፍ እንደወሰደው ሰው ስታስመስል ይታያል።
ትእግስት ልጅቷ ምን ለመስራት እየሞከረች እንደሆነ ምንም አልገባትም።መጨረሻውን ለማወቅ በጣም ተነቃቃች።የመኝታ ቤቱ በራፍ ተከፈተ።አቶ ግርማ ወደ ውስጥ ገብቶ መኝታ
ቤቱን መልሶ ሲቆልፍ ይታያል።ከዛ በቆመበት ቁልቁል ወደአሮራ  እየተመለከተ ለሁለት ደቂቃ ያህል በመጎምዠት ከተመለከታት በኃላ ከላይ  ጀምሮ አንድ በአንድ ልብሱን እያወለቀ እዛው የወለል ምንጣፉ ላይ ሲወረውር ይታያል...እሱ እንደአሮራ እንኳን እላዩ ላይ ፓንት እንኳን አላስቀረም።መለመላውን አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ።ቀኝ እጅን አንቀሳቀሰና ቀስ ብሎ ጭኖቾ መሀከል አሳረፈ...
🍎ትዕግስት ባለችበት ሽምቅቅ አለች።
አቶ ግርማ ቀጠላ...እጆቹን  ጨኖቾ መሀከል እያርመሰመሰ ነው ።ሌላኛውን  እጅን  አነሳና ቀኝ ጡቷ ላይ ሲያሳርፍ ከእንቅልፍ እንደባነነ ሰው እንደመንጠራራት አለችና እጆቾን ዘርግታ ከተኛችበት ተነሳችና በአንገቱ ዙሪያ ጠምጥማ ከንፈሩ ላይ ተጣበቀችበት።
🍎ትዕግስት የምታየውን ነገር  ማመን ነው ያቃታት...አልጋዋን ለቃ ወረደች።ቨዲዬውን ዘጋችና ሪደሩን ነቅላ ኪሷ ውስጥ ከተተች። ክፍሏን ለቃ ወጣች ።ቀጥታ ወደአሮራ ነው የሄደችው።አሮራ እንዳየቻት የፊቷን መጨማደድና  የግንባሯን መቆጣጠር አስተውላ ደነገጠች።
"እንዴ ትጂ ምን ሆንሽ?"
"የጓደኛዬ እናት መሞታቸውን ደውለው ነግረውኝ ነው"ዋሸቻት 
"ትቀራረብ ነበር?"
"አዎ እንደእናቴ በያት..ከፈቀድሺልኝ ለቅሶ መድረስ ፈልጌ ነበር"
"ታዲያ ምን ችግር አለው ፤ሂጂአ.. ".ተንጠራርታ ከኮመዲኖ ላይ የመኪናውን ቁልፍ አነሳችና  እያቀበለቻት"እንቺ መኪናዋን ይዘሽ ሂጂ"አለቻት።
"አረ ችግር የለም ...ራይድ እጠቀማለሁ...አንቺ  ካስፈለገሽስ?"
"መውጣት ከፈለኩ መኪና የማጣ ይመስልሻል...?ለዛውም ዛሬ ከቤት የመውጣት ፕሮግራም የለኝም።እዚሁ ከታናሽ እህቴ ጋር ዘና እላለሁ።ባይሆን ሂጂ አትቁሚ"
ትዕግስት በራሷ የማስመሰል ችሎታ ተገርማ"እሺ አመሠግናለሁ"ብላ ቁልፉን ይዛ ወጣች።መኪናዋን አስነስታ ቀጥታ ወደበፊት የስራ ባታዋ ነው ያመራችው።መንግስቱን ለማግኘት።አዎ እስከአሁን ያየችውን ሆነ ገና ያላየችውን የአሮራንና የአባቷን  ድብቅ ገበና ታሳየዋለች።አርግጥ የአሮራን እና የእንጀራ አባቷን ጉድ ሲያይ በጣም እንደሚያዝን ...ለተወሰኑ ቀናት እንደሚታመም እና መኖርም እንደሚያስጠላው  እርግጠኛ ነች።ግን እድሜ ልኩን የእሷን ፍቅር እየተመኘና ተስፋ እያደረገ ለዘመናት ትንሽ ትንሽ ከሚታመም አንዴ የሚታመመውን ያህል ታሞ ቢወጣለት እንደሚሻል ወስናለች።በዛም የተነሳ መንግስቱን አግኝታ ያወቀችውን እውነት እንዲያውቅ ለማደረግ ቸኩላለች።ገስትሀውስ ደረሰችና መኪናዋን አቁማ ቀጥታ መንግስቱ ይገኝበታል ብላ ወደምታስብበት ቢሮ ሄደች።እንደምትመጣ አልደወለችለትም።ግቢ ውስጥ እንዳለ ከዘበኛው ተረድታለች።ቢሮ ደረሰች።ገፋ አደረገችና ወደውስጥ ገባች።


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍10614👏4😱3
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ምዕራፍ-27
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
////
በራፉን  ገፋ አድርጋ ገባች፡፡ባዶ ነው፡፡ቢሮው ባለ ሁለት ክፍል ስለሆነ ውስጠኛው ክፍል ይሆና ብላ አስባ ወደውስጥ ዘለቀች፡፡በራፉን ገፋ አድርጋ ስትገባ እዛም ባዶ ነው፡፡ቁጭ ብላ ለመጠበቅ አሰበችና ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡ልትደውልለት አሰበችና ስልኳን አነሳችና ቁጥሩን አውጥታ ልትደውልለት ስትል የሚተረማመስ አይነት የእግር ኮቴ እና  ድምፅ ሰማች፡፡የወንድ ድምፅ ነው፤የሴት ድምፅ ተከተለው፡፡የፊት ለፊቱ በራፍ ተከፈተና ተመልሶ ተዘጋ
‹‹ቀስ በለ ምን አጣደፈህ?››ሴቲቷ ነች ተናጋሪዋ፡፡
መለሰላት‹‹የምን ቀስ ነው… ባማረን  ጊዜ መዠረጥ አድርጎ መደብደብ ነው እንጂ ፡፡››
የሴቲቱን ማንነት መለየት አቃታት፡፡ ወንዱ እራሱ መንግስቱ ነው ፡፡ቶሎ ብላ መቀመጫዋን ለቀቀችና በሶፋ መቀመጫ እና በግድግዳው መካከል ባለ ክፍት ቦታ እራሷን ቀበረችና ሁለኔታውን ለመከታተል አራሷን አመቻቸች..ጥንዶቹ እንደተያያዙ እሷ ወዳለችበት ወደውስጠኛው ክፍል ገቡ….ሁለቱም በመስገብበገብ የለበሱት ልብስ እያወለቁ  ወዲህና ወዲያ መጣል ጀመሩ..ሴቲቱ የመጨረሻውን ፓንቷን አውልቃ በእሷ አቅጣጫ ስትወረውር የትዕግስት አፍንጫ ላይ አረፈ ..ቀስ ብላ ድምፅ ሳታሰማ አለነሳችና ከራሷ አርቃ ወረወረች፡፡ጥንዶቹ እርቃን ሰውነታቸውን መልሰው አጣበቁና ሶፋ መቀመጫው ላይ ተያይዘው ወደቁ….፡፡ሶፋውን ሲጫኑት እሷን ይበልጥ ከግድግዳ ጋር አጣበቋት….እንደምንም ትንፋሿን አምቃ ህመሟን ቻለችው፡፡
የልጅቷ ማንነት እንቆቅልሽ ሆነባት ፡፡ገስት ሀውስ ውስጥ ከሚሰሩ ጥቂት ሽቀርቅር ሴቶች  መካከል አንዷ ልትሆን እንደምትችል ገመተች፡፡ከመሀከላቸው አንዱ ሁለቱ ወደአእምሮዋ መጡባት ፡፡ በተወሸቀችበት የእነሱን በወሲብ የታሸ የደስታ ሲቃ  ማዳመጧን ቀጠለች፡፡ትዕይንቱ ከመጠናቀቁ በፊት የበራፍ መከፈትና በዘጋት ድምፅ ተሰማ…….ግራ ተጋባች፡፡ሲስገበገቡ በራፉን እንኳን እንዳልረቀሩት  ገባት፡፡፡በራፉን የከፈተው ሰው ወደ ውስጠኛው ክፍል ከመዝለቁ በፊት ሮጣ ሄዳ ‹‹አይ  ቆይ ስራ ላይ ናቸው ትንሽ ቆይታችሁ ተመለሱ››  ልትላቸው ሁሉ አማራት…አንድ  ውሳኔ ላይ ከመድረሷ በፊት የውስጠኛው ክፍልም ተበርግዶ ተከፈተ….ሌላ ሴት እንደመጣች ከስር በምታየው  በቀሚሷ ጠርዝ አወቀች፡፡
ሴትዬዋ ከመግባቷ በንዴት የጦዘ ሰይጣናዊ ተንከትካች ሳቋን ለቀቀችው፡፡ሁለቱ ጥንዶች  ከተጣበቁበት ተላቀቁና እርቃናቸውን ሴትዬዋ ፊት ለፊት ተገትረው ቆሙ…
‹‹እንዴት ሳትደውይልኝ መጣሽ?››መንግስቱ  ሴትዬዋ ላይ ጮኸባት፡፡
‹‹ጭራሽ ልትቆጣኝ ባልሆነ .. ምንቱ ሙሉ ወደቤት ያልመጣኸው ለካ እንዲህ በስራ ቢዚ ሆነህ ነው››ሴትዬዋ ልክ እንደሰማንያ ሚስቱ ተንዘረዘረችበት…. ትእግስት የሴትዬዋን ማንነት ወዲያው ድምፃን እንደሳማች  ነው የለየቻት ውቤት ነች..የመንግስቱ የአጎቱ ዋና ሚስት…ያልገባት እንዲህ ያሚያነጋራቸው ምን ምስጢር በማሀለከላቸው እንዳለ ነው
ሴትዬዋ ትንፋሽ ከወሰደች በኃላ ንግግሯን አራዘመች…‹‹ደግሞ በሌላ ሴት ምክንያት  ብትረሳኝ እኮ ችግር አልነበረውም.. ካልጠፋ ሴት በእሷ…..ግን አጎትህን ሰራህለት… በጣም ነው የምትጠላው አይደል..?
ትእግስት አሁን እንቆቅልሹ ተፈታላት፡፡በጣም ነው የደነገጠችው፡፡
መንግስቱ‹‹ ለምን እንዳዛ አልሽ?እንዴት አጎቴን እንደምጠላው አሰብሽ?›› ብሎ ጠየቃት፡፡
‹‹ከሚስቱም ከውሽማውም ጋር እንዲህ  እያቀያየርክ በገዛ ቤቱ እየተኛህ ?ባትጠላውማ እንደዛ አታደርግም….በእውነት ደህና አድርገህ እየተበቀልከው ነው..ግን ያው ተሳስተሀል ልልህ አይደለም..እንዲሁ አስገርመሀኝ እንጂ››
‹‹ታዲያ  ይገባዋል ካልሽ ምን አነጫነጨሽ..ባክሽ በራፉን ዝጊልንና የጀመርነውን እንጨርስ››አለች ትብለፅ(የመንግስቱ አጎት ሁለተኛ ሚስት)
ትእግስት በተወሸቀችበት ሆና በምትሰማውና በምታየው ነገር ጭንቅላቷ ተናወፀ..መንግስቱ እንዲህ ያደርጋል ብሎ ሌላ ሰው ቢነግራት ስም አጥፊዎች ብላ ልትደባደብ ሁሉ ትችል ነበር..አሁን ግ በገዛ አይኖቾ የሚሆነውን ሁሉ እያየች ነው፡፡
ሴትዬዋ ጩኸቷን ጨምራበት በስድብ አጥረግርጋቸው ክፍሉን ለቃለቸው ትወጣለች ብላ ስትጠብቅ ‹‹ጥሩ እንግዲያው ጨርሱ ››ብላ ወደኃላ ተመልሳ በራፉን ዘጋችና አንድ ወንበር  አንስታ ወደበሩፍ አስጠግታ በማስቀመጥ  ተቀመጠችበትና ልክ አዲስ የወጣ ሲኒማ ለማየት እንዶቋመጠ ሰው አይኖቾን አፍጥጣ ዝግጁ ሆነች፡፡
‹‹እርግጠኛ ነሽ የምናደርገውን እንደዛ ተቀምጠሸ ማየት ትፈልጊያለሽ?››መንግስቱ ግራ በመጋት ጠየቃት፡፡
‹‹ይልቅ እንትንህ እየሞሸሸ ነው…ሙሉ በሙሉ ሰውነትህ በርዶ ስሜትህ ከመጥፋቱ በፊት ቀጥል›› አለችው፡፡
ትብለጽ መንግስቱ አፈፍ አድርጋ ሶፋው ላይ ጣለችውና ከላይ ሆና እየበረደ ያለ ሰውነቱ  እንደጋና እንዲግልና እንዲወጣጠር ትረዳው ጀመር..መንግስቱ ወደሪቱሙ ለመመለስ ደቂቃዎች ቢፈጂበትም ቀስ በቀስ ግን የበላይነቱን ተረክቦ ልጅቷን  ተሸከመና ከላዩ አንስቶ ከላይ ተከመረባት..ከዛ አቋርጣ የነበረውን ጣርና ማቃሰት ደመቅ አድርጋ ቀጠለች..
ትእግስት ባለችበት ሆነ በምታየው ነገር  ሳቆ ሊያመልጣት ይተናነቃት ጀመር፡፡፡
ውቢት ቁጭ ብሎ  ትእይንን የማየት አቀም ያጣች ይመስላል… ድንገት ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቦርሳዋን አስቀምጣ የለበሰችውን ልብስ ከላይ ጀምሮ ማወላለቅ ጀመረች….ትዕግስት የምታየው ነገር ከማመን አቅሞ በላይ ስለሆነባት በድንጋጤ አይኖቾ ፈጠጡ … ውቢት እርቃኗን ከሆነች በኃላ ሄዳ በወሲብ እየቃተቱ ያሉት ጥንዶች  ተቀላቀለቻቸው…
ትእግስት መገረም ጉሮሮዋን አፈናት.ይህቺን ሴት በደንብ ታውቃታለች፡፡አሁን ካናዳ ከአባታቸው ጋር  የሄዱ ለአቅመ ሄዋን ለመድረስ እየተንደረደሩ ያሉ መንትያ ልጆች ያሏት በጣም የተረጋጋች ዘንካታ እና ደርባባ እመቤት ነበረች ፡፡በተለያየ ጊዜ ለልደትና ለባዓላት  ዝግጅት እቤት እየተጋበዘች ሄዳ ከእጇ በልታለቸ ጠጥታለች፡፡ባሏ ለእሷ ታማኝ እንዳልነበረ ብታውቅም እሷን ግን ፈፅሞ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ የምትጠረጥራ ሴት አልነበረችም፡፡ለትዳሯ ፍጸም ታማኝና ለልጆቾ ስትል መላ ነገሯን መስዋዕት አድርጋ በክብር የምትኖር ቁጥብ እመቤት አድርጋ ነበር የምታያት‹‹ ታዲያ ከመቼው እንደዚህ አበለሻሻት?›› ስትል ተገረመች፡፡
ትዕግስት አሁን እንደምታየው ማንም ከማንም አያንስም..እዚህ የመጣችበትም ጉዳይ ዋጋ የለውም..አሁን አሮራ እንዲህ ታደርጋለች ብላ ለመንግስቱ የምትነግርበት ምንም ምክንያት አይታያትም፡፡ እሱም እየሰራ ያለው ነገር ለጆሮ ሚከብድ ነውር ነው፡፡
መንግስቱና ሁለቱ ሴቶች ጣጣቸውን ጨርሰው አውልቀው በየቦታው የጣሉትን ልብስ እየለቃቀሙ ለብሰው እየተሳሳቁ  ክፍሉን ለቀው ለመውጣት ከ30 ደቂቃ በላይ ወስዶባቸዋል፡፡የእነሱን መራቅ በድምፃቸው መጥፋትና በኮቴያቸው መደብዘዝ አረጋግጣ ከተወሸቀችበት ለመውጣት ብትሞክርም ቀላል ልሆነላትም፡፡ሰውነቷ ደንዝዞ ና እግሮቾ ተሳስረው ነበር፡፡እንደምንም እራሷን ቀስ በቀስ አለማምዳና አፍታታ ከተደበቀችበት ወጣችና ሹልክ ብላ ቢሮውን ለቃ በመውጣት መኪናዋ ወደ አቆመችበት ማንም ሳያያት ሄደች….ሞተሩን አስነሳችና  በፍጥነት ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍82😱17👎85
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-28
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
ይዛ የመጣችውን ምስጢር  የማወቅ መብት እንደሌለው ወሰነች፡፡አሮራ ጋር ያለው ሀጥያት መንግስቱ ጋርም አለ፡፡አሁን አሁን ስታስብ "እነዚህ ሰዎች የእውነትም ይፋቀራሉ ?" የሚለውን  ለማመን እጅግ ነው የከበዳት፡፡ወደቤት ተመልሳ ከአሮራ ጋር መፋጠጥ አልፈለገችም፡፡የሆነ አእምሮዋን የምታሳርፍበት ቦታ መሄድ ነው የፈለገችው፡፡እና መጠጣትም አምሮታል፡፡ስትጠጣ ደግሞ ብቻዋን መሆን  አልፈገችም፡፡በብቸኝነት ውስጥ ሰምጣ ከራሷ ህሊና ጋር በጥልቀት ለመሟገት ወኔው የላትም….አንድ ሰው ትዝ አላት፡፡የአሮራ አጎት እዝራ፡፡፡እሱ በደንብ ያጣጣታል ደግሞ በይሉኝታ ባልተገራ የፍልስፍና ወሬዎቹ ከገባችበት ቁዘማና ቅብዥርዝር ያለ ስሜት መንጭቆ ያወጣታል ፡፡መኪናዋን መንዳቷን ሳታቋርጥ ስልኳን አነሳችና ልትደውልለት ቁጥሩን እየፈለገች ሳለ  ድንገት ሌላ ስልክ  ተደወለላት…አየችው፡፡ አቶ ግርማ ነው፤የአሮራ የእንጀራ አባት፡፡ትንሽ ካቅማማች በኃላ አነሳችው፡፡
‹‹ጋሽ ግርማ እንዴት ነህ?››
‹‹ትዕግስታችን አለሁልሽ…የሆነ ነገር ላስቸግርሽ ነበር››
‹‹ምን ልታዘዝ?››
‹‹በቀደም አሮራ ኪሊፕ የተቀረፀችበት  የገርጂውን ቤታችንን ታውቂዋለሽ አይደል?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ አውቀዋለው››
‹‹እባክሽ መኪና ያዢና እዛ ሄደሽ መኝታ ቤት ኮዲኖ ላይ ኤምብሎፕ አለ፡፡ እሱን ይዘሺልኝ ክለብ ትመጪያለሽ?››
‹‹እሺ ጦር ሀይሎች አካባቢ ስለሆንኩ አሁን በዚሁ ሄጄ አመጣልሀለሁ››
‹‹ምን ?አሮራ አብራሽ ነች እንዴ?››ምቾት ባልተሰማው ድምፀት ጠየቃት፡፡
‹‹አይ እሷ እቤት ነች …የግል ጉዳይ ስለነበረኝ ብቻዬን ነበር የወጣሁት፡፡ አሁን ጨርሼ ወደ ቤት በመመለስ ላይ እያለሁ ነው የደወልክልኝ፡፡››
‹‹ታዲያ በትራንስፖርት ነሽ እንዴ?››
‹‹አይ የአሮራን መኪና ይዤለሁ››
‹‹እንደዛ ከሆነ አሪፍ ነው…ሂጂና እንደነገርኩሽ አድርጊልኝ፡፡››
‹‹እሺ›› አለችና ስልኳን ዘግታ የመኪናዋን አቅጣጫ አስተካከለች፡፡
አሁን ቀጥታ ወደቤት ሄዳ አሮራን ፊት ለፊት ከመጋፈጧ በፊት ስሜቷን በደንብ አቀዝቅዛ  መረጋጋት መቻል አለበት፡፡ካለበለዚያ ያልሆነ ፊት አሳይታት ወይም የምላስ ወለምታ አጋጥሟት የሆነ ነገር ተናግራት ነገሮችን እስከወዲያኛው ታበላሽ ይሆናል፡፡እርግጥ ከአሮራ በላይ አቶ ግርማን ፊት ለፊት ማግኘት አትፈልግም፡፡‹‹ምን አይነት ሰው ነው የገዛ ልጁን በእንዲህ አይነት ሁኔታ የወሲብ ባሪያ የሚያደርገው..?››በአእምሮዋ ተደጋግሞ በመምጣት እየረበሻት ያለ ጥያቄ ነው፡፡እንደሰማችው ከሆነ ባይወልዳትም ገና አንደበቷ ተላቆ አፍ ከመፍታቷ በፊት ነው እናቷን አግብቶ አባት የሆናት፡፡ በዛ ላይ የስጋ ልጅ ታላቅ እህት ነች።በየትኛውም መመዘኛ ይህቺ ልጅ የእንጀራ ልጅ ብቻ ተብላ  የምትታለፍ አይደለችም። ዝነኛ ሰው አድርጋዋለች።በእሷ የተነሳ ናይት ክለብ በከተማዋ ቁጥር 1  ተመራጭና አንደ ጉድ ብር የሚታፍስበት ሆኗል። በአጠቃላይ ለእሱ ባንኩ ነች።ያ አልበቃ ብሎት እንዴት ህይወቷን  ያጨመላልቀዋል?ስትል ትጠይቃለች።በጣም ጠልተዋላች።ተናዳበታለችም።
ትዕግስት በዛሬው ቀን ያየችውን እና  የተረዳችው ነገር ሁሉ በአጠቃላይ  ወንዶችን  በመንገሽገሽ እንድትጠላ ነው ያደረጋት።
ለእሱ  ስትል  መስዋዕትነት ከፍላ ከፍቅሩ ልታገናኘው ስንት  ነገር ውስጥ የገባችለት መንግስትቱ እንኳን ያስቀመጠችው ቦታ  አልተገኘም። ይሄው አጀራውን በላቶ የገዛ አጎቱን ሚስቶች ያለ ልዩነት  ሲያተረማምስ በገዛ አይኗ አይታለች። እናም ለእሱ ያላት ክብርና ፍቅር ዘጭ ብሎ ወርዶባታል።
አሁን አንድነገር ወሰነች።እንደምንም ብላ የእውነትም የውሸትም ታሪክ ፈጥራ አሮራን ከሁለቱም ቀጣፊ  ወንዶች ነፃ  ልታወጣት።አዎ እዚህ ታሪክ ውስጥ ብቸኛ ሚስኪንና ሊታዘንላት የሚገባ ተጠቂ እሷ ብቻ ነች።
አዎ ከዛሬ ጀምሮ ያላት ተልዕኮ እንደዛ ነው።"እኛ ሴቶችን እስከመቼ ነው በወንዶች ስንታለል እና ስንበዘበዝ የምንኖረው?"እራሷን ጠየቀች።
" በገዛ ድክመታቸው ገብቼ ድራሻቸውን ነው የማጠፋው"ፎከረች።
የተባለችው ቤት ደረሰች።የመኪናውን ክላክስ አስጮኸችና  ተከፈተላት እና መኪናዋን ወደውስጥ አስገብታ ሞተር ሳታጠፋ ወረደች።የተባለችውን ኢንቨሎፕ ትወስድና ናይት ክለብ ስትደርስ ለአንድ ሠራተኛ ሠጥታ ለአቶ ግርማ እንዲሰጡት ትነግርና ከሰውዬው ጋር ፊት ለፊት ሳትገናኝ ከአካባቢው ትሰወራለች። ከዛ እቤት ትሄድና መኪናዋን አስቀምጣ ሹልክ ብላ ትወጣለች።
ለእዝራ ትደውልለት እና ያለበት ድረሰ ትሄዳለች።ካገኘችው በኃላ ስልኳን ታጠፋለች።ስትዝናና ስትጠጣ ታመሻለች።ከዛ እዛው ውጭ ታድርና ጥዋት እራሷን አነቃቅታ  ወደስራዋ ትመለሳለች።በአዲስ ሞራልና ኃይል ትጋፈጣቸዋለች..ምንም ቢሏት አይጨንቃትም።ዕቅዷ እንደዛ ነው።በረንዳ ላይ ደረሰች።

🍎ፊቷን ወደ ዘበኛው መልሳ"ተደውሎልሀል አይደል የመኝታ ቤቱን ቁልፍ ትሰጠኛለህ?"ስትል ጠየቀችው።
"ክፍት ነው ሂጂ ግቢ "አለና ፊቱን አዙሮ ወደ መውጫው ተጓዘ...
ትዕግስት ወደ ውስጥ ዘልቃ ገባች።ሳሎኑን አለፈችና ወደ* ውስጠኛው ክፍል ዘልቃ  ገባች።ከቀናት በፊት ለክሊፕ ቀረፃ ከአሮራ እና ከባለሞያዋች ጋር  ከአራት ቀን በላይ አሳልፋለች። እያንዳንድን ክፍል በደንብ ስለምታውቀው
አልተቸገረችም።ደረች።
🍎የመኝታ ቤቱን በራፍ ገፋ አድርጋ ከፈተች።ወደ ውስጥ ስትገባ ድንዝዝ ነው ያለችው።ወለሉ በአጠቃላይ ቀይ ፅጌረዳ አበባ ተበትኖበት ደምቋል።ጠረጴዛው  በምግብና በወይን መጠጥ ተሞልቷል።አልጋው በልዩ ዲዛይን በባለሞያ እንደተነጠፈ ያስታውቃል።እንዲሁ ሲያዩት እንቅልፍ ያመጣል።ግራ ገባት።"ማነው እንዲህ ጠብ እርግፍ ብሎ ተዘጋጅቶ ፍቅረኛውን  እየጠበቀ ያለው?"ጠየቀች።በተሣሣተ ሰዓት የተሣሣተ ቦታ እንደተገኘች እርግጠኛ ሆነች። ሰዎቹ ሳይመጡ ቶሎ የምትወስደውን ወስዳ ከአካባቢውን ለመልቀቅ  ወሰነችና ወደውስጥ ገባች። የኮመዲኖውን የላይኛውን መሳቢያ  ከፈተች.. ባዶ ነው።ቁጢጥ አለችና የስረኛውን ለመክፈት ከቁልፍ  ጋር ስትታገል ከውስጠኛው የሻወር በር የመከፈት ድምፅ ሰማች...ደነገጠችና ባለችበት አይኖቾን አቃናች።
🍎
የሰውዬውን ማነነት ተመለከተች…ሌላ መገረም‹‹እንዴ ጋሽ ግርማ…አንተ?››
‹‹አዎ እኔ ..ምነው እኔ ዘና ማለት አይገባኝም እንዴ?››
‹‹አረ እንደዛ ማለቴ አይደለም…ስለልጠበኩህ ነው…እቃውን ይዘሺልኝ ናይት ክለብ ነይ ስላልከኝ እዚህ አይሀለው ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡››
ከታች ነጭ ፎጣ አገልድሞል፤ ሌላ ነጭ ፎጣ በአንገቱ ላይ ጣል አድርጎ በውሀ የራሰ ፀጉሩን እያደራረቀ ከፊል ገላውን አራቁቶ በነፃነት ያወራል፡፡
‹‹እንግዳ አለብህ መሰለኝ?››አለችው
‹‹አረ እንግዳዬማ አንቺው ነሽ ፡፡ከኳኳታውና ትርምሱ ገለል ብዬ በፀጥታ ማሳለፍ ፈለኩና ወደእዚህ መጣሁ፡፡ ከዛ አንቺ ትዝ አልሺኝና ዘዴ ፈጥሬ ይሄንን ምርጥ ጊዜ ከምርጥ ልጅ ጋር ባሳለፍ ምን አለበት ብዬ ደወልኩልሽ…ምነው አጠፋሁ እንዴ?››
‹‹አረ አላጠፋህም…እንዲሁ የጠበቅኩት ስላልሆነ ድንገት ሆኖብኝ ነው፡፡››ከዚህ ውጭ ምትሰጠው ሌላ መልስ አልነበራትም፡፡
👍534👎1
‹‹ቁጢጥ  ባልሽበት ቀረሽ እኮ …ተነሺና ወንበር ላይ ተቀመጪ እንጂ፡››
በርግጋ ከተንበረከከችበት ከኮሚዲኖ ስር ተነሳችና ወደውጭ መራመድ  ጀመረች…አቶ ግርማ ደነገጠ‹‹ምነው ?ወዴት እየሄድሽ ነው?››
‹‹መኪናው››
‹‹መኪናው ምን ሆነ?››
‹‹ሞተር አላጠፋሁም…ሞተር አጥፍቼ መጣሁ››
‹‹እሺ ጥሩ ..ሂጂ››
ተንደርድራ እቤቱን ለቃ ወጠች፡፡

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍458🥰2
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-29
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
ትዕግስት ከመደንገጧ የተነሳ ትንፋሿ እየተቆራረጠ ነው፡፡ቤቱን ለቃ ወጣችና  መኪናዋ ውስጥ ገባች፡፤መሪዋን ተደግፋ ማሰብ ጀመረች፡፡"አሁን ምን ላድርግ? መኪናዋን አስነስቼ ግቢውን ለቅቄ ልውጣ?"እራሷን ጠየቀች።እንደዛ ብታደርግ ሰውዬው እንደንቀት ነው የሚቆጥረው፡፡ስሜን ታጠፋዋለች በሚል ስጋት ቀጥታ በዚህ ምክንያት ከስራ ሊያባርራት ድፍረት ቢያጣም ዋል አደር ብሎ በሌላ ሰበብ አንደሚያባርራት እርግጠኛ ነች…ያ ከሆነ ደግሞ አንድ ፍሬ ያለው ነገር ሳትሰራ የእስከዛሬ ልፋቷ ሆነ አዲሡ  እቅዷ  ሁሉ ገደል ገባ ማለት ነው፡፡እንደዛ እንዲሆን ደግሞ ፈፅሞ አትፈልግም።
እንደምንም ትንፋሿን  ወደውስጥ እየሳበችና ወደውጭ እየለቀቀች እራሷን አረጋጋችና ሞተሩን አጥፍታ በዝግታ እርምጃ ተመልሳ  ወደውስጥ ተራመደች፡፡መኝታ ቤት ስትገባ አቶ ግርማ ከስር ሰማያዊ ቀለም ያለው ቁምጣ .. ከላይ ነጭ ፓካውት ለብሶ በላዩ ላይ ክፍት ነጭ ሸሚዝ ጣል አድርጎበት ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ፊት ለፊቱ ያለው ብርጭቆ ላይ ወይን እየቀዳ ነበር፡፡
እንዳያት በፈገግታ ደምቆ"ግቢ ትዕግስታችን››ብሎ እየቀዳ ያለውን ጠርሙሰ ጠረጴዛው ላይ መልሶ አስቀመጠና ከመቀመጫው ተነሳና ወደበራፉ ተራመደ...ወደእሷ ሄደ ከግማሽ መንገድ ተቀበላትና የእጇን መዳፍ  ይዞ በክብር እየመራ ወንበሩን ስቦ አስቀመጣት፡፡
"እንደውም ነይ ከሆቴል የመጣ ምግብ ስለሆነ ሳይቀዘቅዝ እንብላ ...እጃችንን እንታጠብ "አለና እጇን ይዞ  ወደታጠቢያ ክፍል ይዞት ሄደ …እጃቸውን ታጥበው ተመለሱና ወንበራቸው ላይ ተመልሰው ተቀመጡ። ምግብ ቀረበ ።ተበላ። አጠናቀው እጃቸውን ተጥበው ወይናቸውን እየተጎነጩ ከአንዱ ርዕስ ወደሌላ የሚስፈነጠር ወሬያቸውን ቀጠሉ፡፡እየቆዩ ሲመጡ ትዕግስት ጨፍግጓት የነበረው ስሜት እየለቀቃት  ብስጭቷም እየተነነ ሄደና  ዘና ማለት ጀመረች፡፡
"አረ አሮር ከፈለገችኝ…ከስራዬ እንዳታባርረኝ ልሂድ"አለችው።
"እንደውም ብታባርርሽ ደስ ይለኛል››ሲል ያልጠበቀችውን መልስ ሰጣት።
"እንዴ! ለምን? ምን አጠፋው?"
"አይ ምንም አላጠፋሽም …ግን እሷ ብታባርርሽ ለእኔ ትልቅ እድል ነው፡፡እሷን በምትንከባከቢያት  ልክ እኔንም ብትንከባከቢ ገነት እንደገባሁ ነው የምቆጥረው…እና እንደዛ አይነት አገልግሎትሽ ለማግኘት የምችለው ደግሞ እሷ ስታባርርሽ ብቻ ነው"
"እና እሷ ካባረረቺኝ አንተ ትቀጥረኛለህ ማለት ነው፡?"
"ክፍያሽን ባልችልም ባንክ ሰብሬም ቢሆን እንደዛ ማድረግ ነው የምፈልገው››
ከት ብላ ሳቀች"በጣም ትወዳታለህ አይደል?"ስትል ያልጠበቀውን አደናጋሪና  ጥያቄ ጠየቀችው።
"ትወደኛለህ ነው ትወዳታለህ?"
"አረ ትወዳታለህ ወይ?"
"ማንን?"
"አሮራን ነዋ ..ልጅህን"
"በጣም... ሁለቱ ሴት ልጆቼ  ሁለት የአይን ብሌኖቼ ናቸው...በጣም ነው የምወዳቸው "ሸፋፍና እንደጠየቀችው ሸፋፍኖ መለሠላት።
‹‹አይ ጋሽ ግርማ!››
‹‹ጋሼዋን ከፌት ብትደልቺያት አሪፍ ነበር››ሲል ቅሬታውን ነገራት።
"እንዲሁ በሌጣው ግርማ ልበልህ?››
"ግርምሽም ልትይኝ ትቺያለሽ"
በሳቅ ታጅባ ፊት ለፊቷ ያለውን የወይን ብርጭቆ አነሳችና ተጎነጨችለትና መልሳ አስቀመጠች፡፡ከዛ ወደጫወታው ተመለሠች"ደፈርሺኝ ካላልከኝ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?››
"በፈለግሽው መጠንና ሁኔታ ልትደፍሪኝ  ትቺያለሽ..ማለቴ የፈለግሺውን ጥያቄ ጠይቂኝ"
ፈገግ አለችና ጥያቄዋን አስከተለች"እስከዛሬ ለምን ሳትገባ? ማለቴ የእነ አሮራ እናት ከሞተች በኃለ  ብዙ አመት ያለፈህ ይመስለኛል.. ልጆችህ አድገዋል ..ለብቻህ ይሄን ሁሉ አመት አይከብድም?›››
የሆነ ደቂቃ እንደመተከዘ አለና ‹‹እንደዛ ያደረኩት ለልጆቼ ምቾት ስል ነው።አሁን ግን እንዳልሽው ጊዜው ደረሰ ይመስለኛል።እንደመነኩሴ በተሀቅቦ ብቻዩን መኖር እየሠለቸኝ ነው።››
እንደመነኩሴ የሚለውን ቃል ስትሰማ ሳቋ ሊያመልጣት ነበረ"በጌታ ሠው እንዴት ነው የሚያስመስለው?"አለችና በውስጧ አጉረምርማ ንግግሯን ቀጠለች።"አዎ ማግባት አለብህ። ደርበብ ያለች ስንድ እመቤት የሆነች ሴት  ፈልገን ድል ባለ ሰርግ ጨፍረን እንድርሀለን››
"በቅድሚያ ግን ፍላጎትህ እንዴት አይነት ሴት ማግባት ነው ብለሽ አትጠይቂኝም….?››
"እሺ... እንደውም ያንተን ፍላጎት ጠንቅቆ ማወቁ ፍላጋውን ቀላል ያደርግልኛል››
"እግዲያው መቶ ፐርሰንት በፀባይ፣ በመልክ ፣በቁመና ፣በእድሜ ቁርጥ አንቺን የመሰለች  ብትሆንልኝ …አይኔን ሳላሽ ወዲያውኑ አገባ ነበር››
በንግግሩ ሰውነቷ ሞቀ"ምርጫህ ከባድ ነው››
"እንዴት ማለት?››
"እኔ መንታ እህት የለኝም ፣መቶ ፐርሰንት እኔን የመሰለች ሴት ማግኘት በጣም ከባድ ነው፡፡እርግጥ ማንኛውም ሰው እሱን መሰል 7 ሰው በዚህ አለም በተለያዩ ቦታ ላይ አሉ ይባላል፡፡ከነዛ በአለም ዙሪያ ከተበተኑት እኔን ከመሠሉ ሰባት ሴቶች መከካከል አንዷን ፈልጎ ማግኘት የእድሜ ልክ ልፋትን ይጠይቃል…በዛ ላይ ከሰባቱ ሶስቱ ገና ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ህፃኖች የተቀሩት ሶስት ደግሞ እድሜያቸውን የጨረሱ አሮጊቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡"አለችው።
"እኔ ግን  ስራዬ ብለሽ በቅንነት ከፈለግሽ ልጅቷን ማግኘት የሚከብድሽ አይመስለኝም››
"እንዴት አድርጌ..እስቲ ዘዴውን ንገረኝ?››
"ወንድሜ እዝራ ብዙውን ጊዜ ንግግሮቹ ፍልስፍና  ነክ ስለሆኑ ለመስማት ይከብዳል እና ምን ይላል መሰለሽ "ሰው የሚከብደው ሌላውን ፈልጎ ማግኘት አይደለም ከባዱ ነገር እራሷን ፈልጎ ማግኘት ነው "ይላል አይ የእብድ ነገር ምን ይቃዣል እል ነበር.አሁን ሳስበው ግን እውነቱን እንደሆነ ተገለፀልኝ ፡፡"
"እንዴት?"
"አታይም እንዴ ?አንቺን 100 ፐርሰንት  የምትመስል ልጅ ለማግኘት አህጉር  ከምታካልይ ለምን የእሱን አባባል አትጠቀሚበትም፡፡ከነዛ ሳበቱ አንዷ እኮ እዚሁ እቤት  ይህቺው እኔ ፊት ለፊት ተቀምጣለች፡፡ ለምን ልታያት አልፈለግሺም?"
"አረ ጫወታ" አለችና ከት ብላ ስቃ ፊቷ ያለውን ብርጭቆ በማንሳት  የቀረውን ሙሉ በሙሉ ጨልጣ ጠጣችና መልሳ አስቀመጠች ..ወንበሮን ለቃ ተነሳች፡፡
አቶ ግርማ ያላሰበው ነገር ስለሆነበት ደነገጠ ።ገና ብዙ ጫወታ፣ ገና ብዙ ተጨማሪ ክስተቶች ይኖራሉ የሚል ጉጉት ነበረው፡፡
"ምነው ያልሆነ ነገር ተናገርኩ እንዴ?"
"አረ እንደውም አስጎመዠኸኝ..እና ይህቺ ቀን እንዲሁ ጣፋጭ እንደሆነች እንድትጠናቀቅ  ፈልጋለው፡፡ሌላ ቀን በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲህ ሮማንቲክ በሆነ አቀራረብ ተዘጋጅተህ ከጋበዝከኝ ይህቺን የነገርከኝን ልጅ ካለችበት ቦታ ከአንታርቲካም ቢሆን ፈልጌ ይዤልህ ለመምጣት ሞክራለው፡፡"አለችና ጎንበስ ብላ  በስሱ ጉንጩን ሳመችው።
እሱም ከመቀመጫው ተነሳ።
ጎንበስ ብላ አልጋውን በእጇ ጣቶች በቄንጥ እየዳሰሰች"ተመልሼ እስክመጣ ግን ይሄ አልጋ እንዲህ በውበትና በጥበብ እንደተነጠፈ ይጠብቀኝ"አለችው።
"አትጠራጠሪ ...አመት ብትቆይም ይጠብቅሻል"
"አይ የዛን ያህልማ ከርፋፋ አልሆንም "
ልቡ በደስታ ደነሰች፡፡ከዛ ባላይ  ብዙ ሊጫናት እና  ነገሮችን ሊያበላሽ አልፈለገም፡፡ዛሬ መስመሩን በደንብ እንደዘረጋ እየተሰማው ነው፣ በቀጣይ ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይሉን  በመስመሩ እንዲፈስ በመልቀቅ  የፍቅር ብርሀን በመሀከላቸው እንዲረጭ  ለማድረግ ይችላል።ሳይረፍድበት የህይወት መስመሩን ማስተካከል አለበት ፡፡ይሄንን ካሰበና በውስጡ ማብሠልሰል ከጀመረ ከራረመ...ቢሆንም  መንገዱን ማግኘት አልቻለም ነበር፡፡እድሜ  ለትእግስት ልቡ የሚሰነጥቅ ውበትና ነፍስን በሚያነቃቃ ጫወታ የተነሳ የሆነ ጭላንጭል የመውጫ
👍736😁3👏1😱1
በር እየታየው ነው፡፡
መኪናዋ ደረስ ሸኛት፡፡"ጠንቀቅ  ብለሽ ንጂ››አላት
‹‹ምነው? ሰከረች ብለህ ነው?››
"አይ!  እንዲሁ አንድትጎጂብን ያለመፈለግ ስሜት በውስጤ ስለበቀለ ነው፡፡"ሲል መለሰላት።
"ስለነበረን ቆይታ ደስ ብሎኛል....ለአሮራ ግን እንዳትነግራት?"አለችው።
ይህንን አስተያየት ሆነብላ ልብን ልትነቀንቅ ነው የሠነዘረችውደ
"አረ አልነግራትም..ማለቴ ቢያንስ ጊዜው እስኪደርስ በመሀከላችን ያሚቆይ  ሚስጥር ይሁን "አላት
"አንተን የሚያስደስትህ ሀለሉ ይመቸኛል" አለችና መኪናን አስነስታ በተከፈተው በር በመውጣት አስፓልቱን ያዘችበዝግታ በጥንቃቄ መንዳት ጀመረች።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍5516😁4🔥3
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-30
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
መኝታ ቤታቸው ተያይዘው ሲገቡ ከምሽቱ 6 ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ከናይት ክለብ ነው ተያይዘው የመጡት፡፡አሮራ የአንድ ሰዓት ዝግጅት ነበራት፡፡ከአራት ሰዓት እስከአምስት ሰዓት ስድስት ዘፈኖችን ዘፍና አድናቂዎቾን አስደስታ ለሌለኛው ዘፋኝ መድረኩን ለቃ ከአባቷ ጋር ወደቤት ተመለሰች፡፡በውስጧ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ  ደስ የሚል ስሜት እየተሳማት ነው፡፡ዝግጅቷን ጀምራ እስክትጨርስ መንግስቱን ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እየተመለከታት ነበር…በሁሉም ዘፋኖቿ  መቀመጫው አካባቢ በደስታ እየዘለለ በመጨፈር እና በመደነሰ ነበር ያሳለፈው..እሷም እያንዳንዱን የፍቅር ዘፈን ስትዘፍን ወደእሱ ሰረቅ እያደርች  በማየትና  ለእሱ እየዘፈነች እንደሆነ በማሰብ ነበር ስትደሰት ያመሸችው፡፡
መኝታ ቤት ገብተው በራፍን እንደዘጉት አቶ ግርማ ጎትቶ አቀፋትና ከሰውነቱ አጣበቃት.. ከንፈሯን ጎረስውና ትንፋሽ እስኪያጥራት በረጅሙ ሳማት….
‹‹ምንድነው ይሄ ሁሉ ጉድ !ናፈቅኩህ እንዴ?››
‹‹ብታይ ዛሬ ልዩ ነበርሽ..እዛ መድረክ ላይ በልዩ ብቃት እየተ ውረገረግሽ በሚስረቀረቅ ድምፅሽ አዳራሹን ስታናጊው ምን እንደተመኘሁ ታውቂያለሽ?››
ሚለው ለመስማት በመጓጓት‹‹እንዴ ምን ተመኘህ?››አለችው ።
ወደመድረክ እሮጬ መጥቼ …ይሄንን የለበሰሽውን ልብስ ቀድጄ ከላይሽ ላይ በመጣል ያ ሁሉ ሰው እያየኝ.. ይህቺ የእኔ ፍቅር የልቤ ነግስት ነች… በማለት እዛው አሪፍ ወሲብ በማድረግ ወንዶቹ ሁሉ ምራቅ ሲውጡ መመልከት ነበር የተመኘሁት..አዎ እንደዛ ማድረግ ነበር የፈለኩት..እንደምንም በመከራ ነው እራሴን የተቆጣጠርኩት።››
‹‹ውይ ሰይጣናዊ ምኞት ነበር የተመኘኸው..ይታይህ እንደዛ አድረክ ማለት እኮ በማግስቱ  በየጋዜጣውና  በየሶሻል ሚዲያው ‹‹የክፍለ ዘመኑ ታላቁ ቅሌት… አባት ልጁን በአደባባይ ደፈራት….ታዋቂው ባለሀብት ልጁ የሆነችውን ታዋቂዋን ዘፋኝ በአደባባ ደፈራት…የርእስ አይነት ያዝጎደጉዱት ነበር››
‹‹አያደርጉትም  አይባልም..የተመኘሁትን ማድረግ ባልችልም አሁን ፈጠን በይ አናድርገው፡፡"አለና ከላይ ለብርድ ብላ የለበሰችው ጃኬት አወለቀላት…
‹‹እንዴት ነው ዝግጁ ነህ እንዴ ?››ብላ እጇን ሰዳ እንትኑን ስትጨብጠው ግትርትር ብሏል …
‹‹ኦ አባ ያስጎመዣል….ለማንኛውም እንዲሁ  እንደተገተረ ሳይላላ አቆይልኝ ..በፍጥነት ተለቃልቄ መጣሁ.. ብላ በእጇ የያዘችውን ስልኳን ኮመዲኗው ላይ ወርወር እድርጋ  ወደ ሻወር ቤት አመራች..ግርማም ልብሱን አወላለቀና እርቃን ሰውነቱን አንሶላውን ግልጦ በመግባት  መምጣቷን በናፍቆትና በመጎምዠት ይጠብቅ ጀመር፡፡
ወዲያው ግን የአሮራ ስልክ በተከታታይ ጢው… ጢው የሚል ድምጽ ማሰማት ቀጠለ..ሳያስበው ረበሸው..‹‹በዚህን ሰዓት የምን መልዕክት ነው?፡፡››እራሱን ጠየቀ…‹‹አይ እኚህ የማይሰለቻቸው ቴሌዎች ይሆናሉ›› ብሎ በማሰብ በቸልታ ሊያልፈው ሞከረ …ግን አላስቻለውም፡፡ተንጠራራና ስልኳን ከኮመዲኖዋ ላይ አነሳ ..ፓተርኑን ስለሚያውቅ በቀላሉ ከፈተው፡፡
ስድስት ሚሴጅ በተከታታይ ከአንድ ሰው ተልኮል..MG በሚል መለያ ከተመዘገበ ሰው… ‹‹MG ማን ነች?››የመጀመሪያውን ሚሴጅ ከፈተው..ከጭነቅላቱ እስከእግር ጥፍሩ የሚሰነጥቅ የድንጋጤ፤የንዴትና የቁጣ ስሜት ሰውነቱን አርገበገበው፡፡
🍎
‹የእኔ መልአክ…መድረኩ ላይ ሆነሽ እኮ 12 ክንፎችሽ እየታዩኝ ነበር….መቼስ የፍቅር ፍላፃ የመታው ሰው እንደፈለገው ቢያልም ቅዠታም ተብሎ ሊወቀስ አይገባም አይደል….?የእውነት በጣም ልዩ ነበርሽ…አንቺን በማፍቀሬ እንዴት እንድለኛ እንደሆንኩ››
🍎ሁለተኛውን ከፈተው
"አሁን ምን እየሰራሁ እንደሆነ ታውቂያለሽ? እቤቴ ገብቼ አልጋዬ ውስጥ ገብቼ ተኝቼለሁ። ከስልኬ ውስጥ በቀደም የላክሽኝ ውብ ፎቶ እየተመለከትኩ እየጎመዘው ነው፡፡ከዚህ ነጭ ቢጃማ ስር ምን አይነት ፓንት ይሆን ያደረገችው? እያልኩ አመራመራለሁ ።በሀሳቤ ጡቶችሽን አንድ ላይ አፍነው የያዙትን ጡት ማስያዛሽን እራገማለሁ….ምን አለ ነፃ ቢሆኑ እያልኩ እፈላሰፋለሁ……እና በዚህ ሁሉ ውስጥ እንዴት እንደማፈቅርሽ አስባለሁ…››ይላል
ምራቁን በሰፊው ገርገጭ አድርጎ ዋጠና ሶስተኛውን ከፈተው
🍎
‹‹አቤት ከመተኛትሽ በፊት ብትደውይልኝነና ድምፅሽን ብታሰሚኝ… ልክ ገነት ውስጥ ገፍትረሽ እንደጨመርሺኝ ነበር የምቆጥረው፡፡...አፈቅርሻለሁ እሺ

የተቀሩትን ከፍቶ ለማንበብ አቅም አላገኘም..የለበሰውን አንሶላና ብርድ ልብስ ከላዩ ላይ ገፎ አነሳ …መለመላውን አልጋውን ለቆ ወረደና ወደ ቁም ሳጥኑ ሄደ ከፈተ..ፈለግ ፈለግ አድርጎ አንድ አንሳላ አወጣ …ጠረጴዛ ላይ ያለ አንድ የበርቱካን መቁረጫ ቢላዋ አናሳና  አንሶላውን ከላይ ወደታች ብዙ ቦታ ይሸረካክተው ጀመረ….አሮራ ፎጣ አገልድማ ከሻወር ወጥታ የሚሰራውን ስታየው ግራ ተጋባች..የፊቱ መኮሳተር ሆነ ጠቅላላ ነገር ስራው ጥላው ስትገባ እንደነበረው አይደለም።
‹‹ምን እየሰራህ ነው….?››
"ምን እየሰራሁ እንደሆነ ላሳይሽ አይደል.".ብሎ ተንደርድሮ ሄደና አንገቷን አነቃት…በድንጋጤ የፎጣውን ጫፍ ስትለቀው ተንሸራቶ እግሯ ስር ወደቀ...ልክ እንደእሱ እርቃኗን ቀረች።
‹‹እንዴ አባዬ ምን እየሆንክ ነው?"
አልመለሰላትም...እየጎተተ ወሰደና ክፍል ውስጥ ያለ ግዙፍ ጠረጴዛ ላይ አስተኛት።በአንሶላው አንድ ቅዳጅ ቀኝ እጇን አሰረና ከጠረጴዛው አንድ እግር ጋር አሰረው……የሚያደርገውን ነገር ባለማመን በድንጋጤ እያየች ነው።"›ግራ እጇንም በተመሳሳይ አሰረና በተቃራኒ ባለው የጠረጴዛ እግር ጋረ አሰረው….
‹‹ደግሞ ዛሬ እንደዚህ አይነት አማረህ?››
"ዝጊ" አለና እግሮቾን ከታችኛው ጠረጴዛ እግሮች ጋር በለቀቃቅጦ አሰራት‹‹አሁን አሮራ እየሆነ ያለው ነገር የሰላም እንዳልሆነ ሙሉ በሙሉ ተረዳች፡፡ግርማ ሄደና ያወለቀውን ሱሪ አነሳ..ቀበቶውን ፈታ ...የእሷን ስልክ ከተቀመጠበት ኮመዲኖ ላይ አነሳና ወደእሷ ይዞ መጣ ፓተርኑን ሲከፍት ..ሰውነቷ ሽምቅቅ አለ፡፡
"..MG ማን ነው?"
"ጓደኛዬ ነች››በቀኝ  እጁ ይዞት የነበረውን ቀበቶ ሰነዘረ በጭኗ ላይ ሲጠመጠም ህመም ጭንቅላቷ ድረስ ተሰማት" …አረ በጌታ ምን እያደረግክነው….?"
"አትዋሺን…. ከማን ጋር ነው መሸርሞጥ የጀመርሺው..ያ መንግስቱ ቸብዬ ነው?"
በፍራቻ እየተንቀጠቀጠች ዝም አለች።
ለሁለተኛ ጊዜ ቀበቶውን ሰነዘረ ...አሁን መሀል ሰውነቷ እንብርቷ አካባቢ ነው የተጋደመው።ጣር የተቀላቀለበት ጩኸት አሰማች።

እሱ ንዴቱ ጭራሽ እየተንተከተከበት መጣ...የያዘውን ቀበቶ ወረወረና ተንደርድሮ ወደኃላው ሄደ...የኮመዲኖውን  መሳቢያ ከፈተና ሽጉጡን አወጣ... ከፈተና ጥይት ውስጡ መኖሩን አረጋግጧ አቀባበለና  ወደእሷ ቀረበ...አሮራ አይኖቾ ተስፋ በመቁረጥ ተጎለጎሉ... ፍራቻውን መቋቋም ስላልቻለች ፊኛዋ ተላቀቀና ሽንቷን አንፏለለችው..

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍9016👎7👏7🥰2
#አሮራ
ምዕራፍ-31
ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
ሽጉጡን እንደደቀነ ተጠጋት
‹‹እንዴ አባቴ !!ምን ልታደርገኝ ነው….?››እንባዋ ከአይኖቾ ረገፈ
‹‹በእኔ ላይ ማንም ሴት ልትሸረሙጥብኝ አትችልም .የእናትሽን ተግባር ነው የደገምሽው…ስለዚህ እናትሽን እንዳደረኳት ገላግልሻለሁ…››
ጭንቅላቷን የሆነ ሹል ጦር  መሳይ ነገር ጠቅ አደረጋት
‹‹ምን? እናትሽን….?ምን አድርገሀታል እናቴን?አንተነበርክ እንዴ የገደልካት?››
በጥያቄዋ እራሱ መልሶ ድንጋጤ ውስጥ ገባ….የንዴት መጥፎነቱ ይሄ ነው.. ስሜታችን ምንቆጣጠርበትን ብቃታችንን ያወርደውና ያልሆነ ነገር እንድናደርግ ወይም እንድንናገር ያደርገናል፡፡አሁን የተናገረው እውነት ለብቻው ለአመታት በልቡ ተቀምጦ የነበረ ስውር ምስጢሩ ነው፡፡ይሄ ለማንም ለሌላ ሰው ሊነገር የሚችል አልነበረም…ደግሞ ሌላ ሰው መስማት አለበት ቢባል እንኳን አሮራን በፍጽም የማያጠቃልል ምስጢር ነው፡፡ አሁን ግን አዳልጦታል፡፡
‹‹ዝም በይ ...ነገር ነገሩንማ ቀለብ ታደርጊያለሽ…››ሊሸፋፍን ሞከረ።
‹‹አንተ ቅሌታም ሽማግሌ ምን አባህ ነው ያደረከው?››
ባልጠበቀው ስድቧ ደነገጠ….እሷ አሁን ሌላ ስሜት ላይ ነች ፡፡ፍራቻው ከውስጧ  በኖ ጠፍቷል ።በምትኩ እልህ ፤ንዴትና እሳት የሚያስውጥ ቁጭት ነው ያለው….እጅ እና እግሯ መታሰሩ በጀ እንጂ በዚህን ጊዜ ወይ በጥፍሯ ትቧጭረው ነበር ካልሆነም በጥርሷ ለመዘንጠል መሞከሯ  የማይቀር ነበር፡፡
‹‹አንቺ ይሄን ያህል ተናንቀናል ..?››አለና መሬት ላይ የቀራውን የአንሶላ ቅዳጅ አነሳና አንዱን አፏ ውስጥ ጠቅጥቆ በሌላው ጆሮዋ ዙሪያ ጠምዝዞ አሰረው…..አይኖቾ በንዴት ተጎለጎሉ….
‹‹አሁን በደንብ መቀጣት አለብሽ…በዚህ ጥፋትሽ ተፀፅተሸ ፤ዳግመኛ እንደማታደርጊውም ምለሽ..ይቅርታ እስክትጠይቂ ድረስ መቀጣት አለብሽ..››አለና ሽጉጡን አስቀምጦ ወደእሷ በደንብ ተጠጋ… ጡቶቿን ጨመቃቸው..እንደበፊቱ ቢሆን በደስታ ሲቃ ታቃትት ነበር…አሁን ግን ምንም አይነት የስሜት ለውጥ እያሳየች አይደለም…እንትኑን ይዞ በስስ ፀጉር በተሸፈነ የብልቷ ስንጥቅ አካባቢ ያሸሸው ጀመር ..እንደመተኛት ብሎ የነበረው የእሱ ሲነቃቃና ሲገተር የእሷ ግን እንዳኮረፈና እንደደረቀ ነበር…ለማስገባት ሲታገል የመላጥና የመቆጥቆጥ ስሜት እስኪሰማው ድረስ አስቸግሮት ነበር…በመከራ ከውጥረቱ ለመርካት ቻለ..ሲጨርስ አስጠሊታ ስሜት ነው የተሰማው…..ግን መሸነፉን የሚያሳይ ስሜት ለእሷ ማሳየት አልፈለገም..፡፡
‹‹ስርአት የማትይዢ ከሆነ ከዚህ በላይ ቅጣት ነው የሚገጥምሽ›› ብሎ እየፎከረ  የአፏን እስር ፈታና ጨርቁንም አወጣላት፡፡
‹‹በጣም አስጠላኸኝ››አለችው….ትኩር ብሎ አያት…. ንግግሯ ለማለት ያህል ብቻ ሳይሆን የእውነትም ጥላቻ መሆኑን አይኖቾ ውስጥ የሚነደውን እሳት አይቶ ተረዳ፡፡ወደኃላተመልሷ ሊያስተካከልው ማይችለው ስህተት እንደሰራ ታወቀው፡፡
የሚያደርገው ግራ ገባው..አሁን እንደበፊቱ እየፈራችው አይደለም..ወንጀል ተጠያቂነት እሱን ሊያጠፋው የሚችል ሚስጥር ነግሯታል…ለዛውም ከገዛ ወላጅ እናቷ ጋር የተያያዘ ወንጀል…ፖሊስ ጋር ብትሄድ ያልሆነ ነገር ትቀሰቅስና ለጠላቶቹ  እሱን የሚያጠፉበት አሪፍ መጫወቻ ካርታ አሳልፋ ትሰጠዋለች፡፡ወሰነ፡፡በትክክል ተረጋጋታ ወደቀልቦ እስክትመለስ እና አሁንም ልክ እንደበፊቱ በእሱ ቁጥጥር ስር ተመልሳ ገብታ ያላትን እንዳላት ማድረግ እንደምትችል እርግጠኛ እስክትሆን ድረስ ከሰው እንድትገናኝ ማድረግ የለበትም።

እግሮቾን ቀድሞ ፈታት..እጇን ሊፈታት እየታገለ ሳለ በእርግጫ የተንጠለጠለ ቦርጩን ነረተችው….እህ ብሎ ቁጭ አለ….‹‹ገና ገድልሀለው..እናቴን ምን እንዳደረካት ትነግረኛለህ…ከዛ ለእያንዳንዱ  ለሰራሀው ስራ ትከፍላለህ..ልጅነቴን ስለተጫወትክበት ሴትነቴን ስለቆሸሽከው ስለሁሉም ትከፍላለህ፡፡››
ትንፋሹ ሲመለስ በንዴት ከተቀመጠበት ተነሳና ሽጉጡን ካስቀመጠበት አነሳ ፡፡፡በእጄታው ግንባሯን ቀወራት…እራሷን ስታ ጭንቅላቷን ወደጎን ዘንበል አደረገች….እንደብይ እብጥ አለባት..ከእዛው ቦታ ደሟ ፊን ብሎ ይወርድ ጀመረ…አሁን ደነገጠ…
‹‹ወይኔ ገደልኳት ..ወይኔ ገደልኳት..ሽጉጡን ወረወረና ቶሎ ብሎ የእጆቾን እስር ፈታ ፡፡ እየጎተተ ወሰደና አልጋ ላይ  አስተኛት፡፡አንሶላውን ጎተተና የሚፈሰው ደሞ አካባቢ በመያዝ ጆሮውን አፏ አካባቢ ደቅኖ ትንፋሿን ማዳመጥ ጀመረ፡፡ ትንሽ ትንሽ እየተቆራረጠ ትንፋሽ እንደምትተነፍስ ተሰማው ….ምን እንዲያደር ግራ ገባው፡፡ ሀኪም ቤት ሊወስዳት አይችልም…. በሰው ጥቃት መጎዳቷ ብቻ ሳይሆን ምርመራ ካደረጉ በግዳጅ እንደተደፈረችም  በቀላሉ ያውቃሉ…ከዛ ያበቃለታል..በዛ ላይ ከዳነች በኃላ እሷ ራሷ ለፖሊስ የምትሰጠው ቃል ተደራራቢ ወንጀሎቹን የሚያጋልጥ ሊሆን ይችል ይሆናል….ዝም ብሎ የምትሆነውን መጠበቅ ደግሞ አይችልም …በህይወቱ ተመሳሳይ አይነት ስህተት ለሁለተኛ ጊዜ አይሰራም…  .እናትዬውም ድንገት በጊዜያዊ ንዴት በሰነዘረባት ቦክስ ነው ከጠረጴዛ ጠርዝ ጋር ተጋጭታ እራሷን እንድትስት ያደረገው …ከዛ ከአሁን አሁን ተሸሏት ትነሳለች ብሎ ሲጠብቅ ጊዜው አለፈና ህይወቷን  አጣች….እሱም ያንን ወንጀል በቡዙ ወዳጆቹ እገዛና በከፍተኛ ብር ኃይል ነው ሊሸፋፍንና የተፈጥሮ ሞት እንደሆነ ሊያስመስል ቻለ..አሁን ግን እንደዛ አይነት እድል ላያገኝ ይችላል፡፡
ትእግስትን ሊጠራት እና  ምን ማድረግ እንዳለበት እንድታማክረው  ፈለገ ..ግን መልሶ ሀሳብን ሰረዘው...አይ እሷንም በዚህ ጉዳይ ላይ ሊተማመንባት አልቻለም……ሞባይሉን አወጣና የግል ሀኪሙ ጋር ደወለ….ብዙ ብር ይቀበለዋል እንጂ ምስጢር  ለመጠበቅ አስተማማኝ  ሰው እንደሆነ ብዙ ጊዜ ፈትኖታል…እሱ እስኪመጣ ልብሱን ለባብሶ እሷንም  ቢጃማ አልብሶ ደሙ ሊያቆም በመጣርና ትንፋሿን ሙሉ በሙሉ እንዳይቋረጥ በመፀለይ መጠበቁን ተያያዘው


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍1318🥰4😁4
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-32
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
መንግስቱ ጨንቆታል..በትክክልም ማሰብ እየቻለ አይደለም።ከትእግስት ጋር ፊት ለፊት ተቀምጠዋል። ያዘዙት  ማኪያቶ የሚጠጣው አጥቶ ቀዝቅዞል።ቸቀጣጥረው ነው የተገናኙት።
"እኔ እኮ ምንም ሊዎጥልኝ አልቻለም...እንዴት ማታ እስከስድስት ሰዓት ስራ ላይ ቆይቶ ጥዋት ለስራ ወደውጭ ሄደች ይባላል...?አኔን እሺ ተይኝ ለአንቺን  እንዴት የሆነ ፍንጭ ሳትነግር? እንዲ ሊሆንማ አይችልም....እረዳቷ አይደለሽ...?ሲሆን ሲሆን አብረሻት መሄድ የለብሽም...?እሱነ እንኳን ቢቀር የጉዞ ሰነዶን ማዘጋጀት ፣ትኬት መቁረጥ  የነበረብሽ አንቺ አልነበርሽም?"
"ነበርኩ ግን እንደዛ አልሆነም?"
"የት ነበረ ሄዳች  ያለው?.."
"ሲዊድን ...አንድ የኢትዬጰያዊ ከበርቴ የልጅ ሰርግ ላይ እንድትዘፍን ነው አለኝ"
"እሱ እኮ አይደለም የገረመኝ...ይሄ እንደሚሆን ወይ እኔ ወይ አንቺ ካልሆነም አጎቷ እዝራ እንዴት ሳያውቅ?"
"እንግዲህ አባት ተብዬው እንደነገረኝ ከሆነ ዝግጅቱ ላይ እንድትዘፍን የተመረጠችው ሌላ ዘፍኝ ነበረች...ግን ለሰርጉ አንድ ቀን ሲቀረው ድንገት እራሷን ስታ  ሆስፒታል ገባች  ... ከዛ እንድትተካት እድሉን አሮራ አገኘች ...ክፍያው ከፍተኛ ስለነበር እምቢ ማለት እንዳልቻሉና በዛ ላይ ከዚህ በፊት ሲዊድንን አይታው ሰለማታውቅ ለመሄድ እንደጓጓች ነው የነገረኝ"
"በስልክ አገናኘኝ አትይውም ነበር?"
ጥያቄው አበሳጫት"ያልጠየኩት ይመስልሀል..?.ስትረጋጋና ጊዜ ስታገኝ እራሷ ትደውልልሻለች ብሎ ፊት ነሳኝ።ምን ላድርግ ሽጉጥ ደቅኜ ከላስገድደው?"
"ቆይ ብቻዋን ነው እንዴ የሄደችው?"
"ከሁለቱ ጋርዶቾ ጋር ነው አሉ"
"ተኘሽ..ይሄ ጉዳይ ምኑም አላማረኝም።"ድፍን ሁለት መቶ ብር አወጣና ጠረጴዛ ላይ ወርውሮ  ወደ ውጭ መራመድ ጀመረ.. ተከተለችው።መኪና ውስጥ ሲገባ እሷም ገቢና ገባች።"
"እ ወዴት እንሂድ?"
"አንቺን መጀመሪያ ላድርስሽ"
"የት?"
"ወደ ቤት ነዋ!!! ተመለሺና ከእንደገና መረጃዋችን ፈትሺ...ሰውዬውንም ከእንደገና  አናግሪው...የሆነ ፍንጭ ነገር የምታገኚ ከሆነ  ክፍሏን በርብሪ...እኔ ደግሞ ወደ አየርመንገድ ሄጄ የሚረዳኝ ሰው ልፈልግ።"በዛ ተስማሙና ሰፈሯ ጥሏት ወደአየር መንገድ በረረ።
እንደገባች ቀጥታ ወደክፍሏ ነው የገባችው።ክፍሏ ውስጥ የምትሰራው ስራ ኖሯት ሳይሆን የተወሰነ ለመረጋጋትና ..ጥቂት ለማሰብ ነው።ስልኳን አወጣችና ደወለች ።
"ጋሽ ግርማ እንዴት ነህ?"
"ዛሬም ድረስ ጋሽ ግርማ ላይ ነሽ?"
""ምን ላርግ? ለምዶብኝ ነው"
"እሺ ይሁን የእኔ ቆንጆ ...ግን ምን ልታዘዝ ?"
"የት ነህ?"
"ምነው ፈለግሺኝ እንዴ?"
"አይ ብዙም አይደል። ብቻ ደባብሮኛል?"
"እንዴ ምነው ?ምን ተፈጠረ?"
"ውጭ ላለማውጣት ከሀለቃዬ ስር አስቀረኸኝ...መቼስ እኔን ጥሎ መሄድ የእሷ ሀሳብ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ?"
"አልተሳሳትሽም... የእኔ ሀሳብ ነበር...ምክንያቱ ግን አንቺ እንደምታስቢው አይደለም"
"ታዲያ እንዴት ነው?"
"በነፃነት ካንቺ ጋር ጊዜ ለማሳለፋ ስለፈለኩ ነው።  ቀስ በቀስ እያለያየዋችሁ ነው"
"እቅድህ ጥሩ ነበር። ግን አሁን እኔ በእሷ ናፍቆት እየተሰቃየሁ ነው። አንተ ደግሞ ከጎኔ ሆነህ  እንድረሳት እየረዳኸኝ አይደለህም"
"እዚህ ላይ እውነትሽን ነው..አሁን ለሆነች ስራ ራቅ ያለ ቦታ ነው ያለሁት ።ከሶስት ሰዓት በኃላ እመለሳለው።ከዛ እራት ከአዲስአበባ ውጭ አትበይኝ እንጂ የፈለግሺው ቦታ ጋብዝሻለሁ።
"ጥሩ ሶስት ሰዓት መታገስ አያቅተኝም"አለችው...ዋናው የፈለገችውን ነገር አግኝታለች።ሶስት ሰዓት አላት ማለት ነው?።በዚህ የጊዜ ክፍት  የሆነ ነገር ፈልጋ ማግኘት አለባት።
"እሺ ደህና ቆይልኝ የእኔ ቆንጆ"
"ቸው"ስልኩን ዘጋችውና ወደአሮራ መኝታ ክፍል ተንደረደረች። ደርሳ እጄታውን ስትጫን  አይከፈትም።ተቆልፏል። ቀጥታ ወደኪችን ነው የሄደችው።የቤቱን የሰራተኞች ሀላፊ ፈለገችና አገኘቻት። ለአስቸኳይ ስራ የሚፈለግ  ሰነድ ከአሮሯ ክፍል ውስጥ ማውጣት እንዳለባት  ነገረቻት።ሴትዬዋ ስራ ይዛ ስለነበር ምንም ሳትጠራጠር   ቁልፉን ከሽርጧ ኪስ ውስጥ አውጥታ ሰጠቻት ።እየተንደረደረች ሄደች ከፈተች፣ ገባች።ማንም እንዲረብሻት ስላለሰፈቸገች ከውስጥ ቆለፈችውና የክፍሉን ዙሪያ ገባ መቃኘት ጀመረች።ሁሉ ነገር ስርዓት ይዞ እንደተቀመጠ ነው።አልጋው በስርዓት ተነጥፏል።እቃዋቹ ቦታ ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል።ወደ ኮመዲኖ ተጠጋችና መሳቢያውን ሳብ አደረገችው ...ተከፈተ...የረባ ነገር የለበትም።ቁጢጥ አለችና የስረኛውን ተካፍች ልትከፍት ስትሞክር  ተቆልፏል። ተበሳጨች።ግን ወደያው የሆነ ነገር በአእምሮዋ ብልጭ አለባት... ።አንድ ቀን አሮሯ ይህን ኮመዲኖ ከፍታ ከዘጋች በኃላ ቁልፍን ከቁም ሳጥን በላይ ስታስቀምጥ አይታታለች።እሱ ነው ትዝ ይላታል።ወዲያው ተንርድራ ሄደችና ቦታውን ፈተሸች። አገኘችው።ፈጥና ሄደችና ከፈተች ።ውስጡ የተጠቀጠቀ አንሶላ አለ።"አንሷላ እዚህ ምን ይሰራል?።"በፍጥነት አወጣችው ዘረጋችው ...በደም ተጨማልቋል።ሰውነቷ ተንቀጠቀጠ... ጉሮሮዋ ደረቀ.."ወይኔ በጌታ ገደላት እንዴ?አሁን ምንድነው ማደርገው?"ሌላውን እቃ ጎልጎላ አውገጣች...ሽጉጥ እና ብዙ ወረቀቶች...እና ደግሞ ፓስፓርት እና መታወቂያ ኤቲኤም ካርድ ..በሚንቀጠቀጥ እጇ ፓስፓርቱን ከፈተችው። ውብ የሆነው የአሮሯ ፎቶ ገጭ ብሎል።እባብ እንደተጠመጠመባት አይነት ስሜት ተሰማትና ፓስፓርቱን ጣለችው።ከአካባቢው ሸሸች።
ስልኳን አወጣች...ግን ማን ጋር ልደውል እንደነበረ ጠፋት..በዚህ መሀከል ስልኳ ጠረ ።አነሳችው።
"ሄሎ..ትጂ  በዚህ ወር ውስጥ አሮሯ የምትባል ልጅ ወደሲዊዲን አልሄደችም...ሀገሩን ተሳስተሽ ይሆን እንዴ?"
"ትጂ እየሠማሺኝ ነው?"
"አዎ...ተወው ..አንድ  መረጃ አግኝቻለሁ  ...በ20 ደቂቃ ወስጥ ኤድናሞል አካባቢ እንገናኝ "
በጠቅላላ ሁኔታዋ ግራ ተጋባ"ትጂ ምን አገኘሽ ?ምንድነው የሆነው?"
"በቃ አሁን ምንም ልልህ አልችልም...ቸው "ስልኩን ዘጋችው።"እያንዳንድን ዕቃ ፣በደም የተጨማለቀውን አንሷላ፣ሽጉጡንና  ፓስፖርቷና ጭምር ከቤቱን ጠቅላላ  ቁሳቁስ ጋር የሶስት ደቂቃ ቪዲዬ ቀረፀችና ሁሉንም በባታው እንደነበረ መልሳ ክፍሉን ቆልፋ ወጣች።


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍669🔥1🥰1👏1
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ምዕራፍ-33
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
አሮራ ቢጃማ ቱታ እንደለበሰች በብርድልብስ ተጀብና አልጋ ላይ ተዘርራ ተኝታለች።በእጇ ላይ ጉልኮስ ተሰክቶል...ግንባሯ ላይ በቁስል ፕላስተር ተለጣጥፎ በፍሻ ታስሯል።
አዎ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በፀጥታ ውስጥ ከገባች ሶስት ቀን አልፏታል። ለመጀመሪያ ጊዜ አይኗን ስትገልጥ ተራራ ጭንቅላቷ ላይ ተጣጥፎ የተቀመጠ ነው የመሰላት። እራስ ምታት እየወቀራት ነው።አይኖቾን ብትገልጥም ወዲያው አካባቢዋን በጥራት አይታ ያለችበትን ቦታ መለየት አልቻለችም።ብቻ በአካባቢዋ እየተንቀሳቀሰ የሚለፈልፍ አስጠሊታ አይነት ድምፅ ይሰማታል።
"የእኔ ውድ ...እንኳንም ነቃሺልኝ...በጣም ነበር የተጨነቅኩት...በጣም አዝናለሁ...ሁለተኛ እንዲህ አይነት ነገር አይፈጠርም...."የእንጀራ አባቷ ግርማ ነው።
ድምፁ መለፍለፍን ቀጥሏል...እጆቾን አንቀሳቅሳ ጆሮዋን መድፈን ፈለገች ...ግን ለዛ የሚሆን አቅም አልነበራትም።
እንደምንም አይኖቾ ከቤቱ ብርሀን ጋር ቀስ በቀስ አለማምዳ አካቢውን ማየት ቻለች ...ያለችው የራሷ ክፍል ውስጥ አይደለም ።እርግጥ ይሄም የራሳቸው ቤት ነው። አልፎ አልፎ ከእንጀራ አባቷ ጋር በነፃነት ዘና ለማለት ሲፈልጉ ጎራ የሚሉበት ቤት ነው።ነገሮችን ለማስታወስ ሞከረች...ያ ሁሉ ትርምስ ሲፈጠር ዋናው ቤት የገዛ ክፍሏ ውስጥ ነበረች።እዛ ነው ሁሉ ነገር የሆነው ...የተሠደበችው...የተገረፈችው.... የተደበደበችው..... ሽጉጥ የተደቀነባት.... ከሁሉም በላይ ደግሞ ስለእናቷ ሞት አስደንጋጭ ዜና የሰማችው ዋናው ቤት የራሷ መኝ ታ ክፍል ሆና ነበር ።እራሷንም የሳተችው እዛ ነው።አሁን ስትነቃ ግን በብዙ ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ሌላ ቤት ውስጥ ነው እራሷን ያገኘችው።ያን ሁሉ በደል የፈፀመባት ሰው ደግሞ ከአጠገቧ ቆማ አዘቅዝቆ ወደታች እያያት ነው።ማየት ብቻም ሳይሆን እየለፈለፈባት ነው።
"ለምን እዚህ አመጣኸኝ?"ጠየቀችው።
"ግርግርና ጥያቄ እንዳይበዛብሽ ብዬ ነው የእኔ ቆንጆ?"
‹‹የኔ ቆንጆ አትበለኝ ...የአንተ ቆንጆ አይደለሁም..እኔ ያንተ ሰለባ ነኝ...ደግሞ ጥያቄ ምትፈራው አንተ ነህ እንጂ እኔ አይደለሁም።››
"አሁን ተረጋጊ..በደንብ ስትድኚ ሁሉን ነገር እንነጋገራለን።››
"ስድንማ ከእኔ ጋር አይደለም የምትነጋገረው ..ከፖሊሶች ጋር ነው የሚሆነው..የመጨረሻህ መኖሪያህ የሚሆነው ቂሊንጦ ነው››አለችው በመረረ ጥላቻ።
"እሱማ መቼም አይሆንም….››
"እናያላን …እስከዛሬ እንደእስረኛ በጠባቂ ስገባ ስወጣ ሽንት ቤት ስጋባ ሳይቀር ስታስጠብቀኝ ነበር ...ይሄን እብደት ለእኔ አስቦ ነው በማለት በየዎህነት እና በቀናነት ያለተቃውሞ ስቀበል መኖሬ በጣም ያስገርመኛል... የገዛ ወንድምህ (አጎቴ )ሳይቀር "ወደ መቃብር ሲወርድ ካልሆነ በስተቀር ድምፁ ለማይሰማ፤ እንዲሁም አንገቱ በሰይፍ እና በግንዲላ መካከል ሲጋደም ካልሆነ በስተቀር ለማያምፅ ህዝብ እዘኑለት...››እያለ ዘወትር በአሽሙር ደጋግሞ ሲነግረኝ አልነቃ ያልኩ ደደብ ሰው ነበርኩ..አሁን ግን...?
‹‹አሁን ግ ምን?ይሄ እብድ ወንድም ተብዬ ከየመፅሀፉ እየለቃቀመ የሚለፈልፈውን ከቁም ነገር ወስደሽ ካሰላሰልሽማ ያሳብድሻል››
‹‹እሱ እኮ ካንተ ጋር ሲወዳደር መለአክ ነው...በል አሁን ወደቤቴ ውሰደኝ….››
‹‹ያ የእኔ ቤት ነው።አንድ ልጅ 18 አመት ሞልቷት እራሷን ከቻለች በኃላ የወላጆቾን ቤት ትታ በመውጣት የራሷን ቤት መመስረት አለባት። ከዛሬ ጀምሮ እቤትሽ ይሄ ነው፡፡››አላት።
‹‹ምን …?ከህይወትህ በዘዴ እያስወገድከኝ ነው እንዴ?››
‹‹አይ የምትፈልጊውን ነፃነት ቀስ በቀስ እየሰጠሁሽ ነው፡፡››
‹‹አይ አይሆን ….እንዲህ ቀላል አይንልህም።››
‹‹እናያላን…ለማንኛውም አሁን ስራ ስላለብኝ ልወጣ ነው.. ከአንድ ሰዓት በኃላ ዶክተሩ መጥቶ ያይሻል ..የምትፈልጊው ነገር ካለ መጥሪያው ተጫኚ.... ጋርዶቹ በረንዳ ላይ ስላሉ የምትፈለጊውን ነገር ያቀርብልሻል››
‹‹ገደል ግባ…ስልኬን ፈልጋለሁ …..››
‹‹ስልክ አታስቢው…ቴሌቪዥን መክፈት ወይም ፊልም ማየት ከፈለግሽ ያው ሪሞቱ ..በተረፈ ስልክና ኢንተርኔት በደንብ ድነሽ እስክትነሺና ተነጋግረን ስምምነት እስክንደርስ ድረስ ከእነዚህ ነገሮች አትገናኚም..በይ ጥዋት መጥቼ አይሻለው››በማለት ከክፍሏ ለቆ ወጣ….ቀጥታ መኪናውን አስነስቶ ወደቤት ነበር የሄደው …ከትእግስት ጋር ላለው ቀጠሮ በሰዓቱ ለመድረስ ነው እቅድ።፡ይሄ ነገር መደፈራራሱ ካልቀረ ለእሱ በሚጠቅመው መንገድ መስመር ማስያዝና ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት፡፡አሁን አቅዶ እየሠራ ያለው እንደዛ ነው።
🍎🍎🍎
መንግስት እና ትዕግስት ኤድናሞን አካባቢ ያለ አንድ ካፌ ውስጥ ለብቻ ገንጠል ያለ ወንበር ይዘው ቁጭ ብለዋል፡፡
መንግስቱ የትዕግስትን ፊት መጨለም ሲያይ ሰውነቱ ራደበት… "ምን አይነት መረጃ አገኘሽ? ብሎ ሊጠይቃት እራሱ ድፍረት አላገኘም፡፡ስልኳን ከፈተችና ቪዲዬውን ከፍታ ሰጠችው...ዝም ብሎ ተቀበላትና ማየት ጀመረ….
በህይወቱ በዚህ መጠን ሰውነቱ በድንጋጤ ርዶበት አያውቅም…ስልኩ ከእጁ ተንሸራቶ እንዳይወድቅ ስለፈራ ቀስ ብሎ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው …እና አጎንብሶ ማየቱን ቀጠለ….በደም የተጨማለቀ አንሶለ…ሽጉጥና የአሮራ ፓስፖርት ...ከዛ የሆነ መኝታ ክፍል…አሁንም በደም የተነከረ አንሶላ …ከዛ ሽጉጥ ..ከዛ ደግሞ ፖስፖርት ..።ድንገት ከተቀመጠበት ተነሳ….።ተከተይኝ ብሎ ወደ መውጫው በር መራመድ ጀመረ….።ስልኳን ያዘችና ከኃላው ተከተለችው። ልትታዘዛቸው ወደእነሱ እያመራች የነበረች አስተናጋጅ ወደኃላዋ ተመለሰች፡፡
🍎ቀጥታ መኪና ውስጥ ነው የገባው …እሷም ተከትላው ገቢና ገባችና ቀበቷዋን አሰረች፡፡ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ እንደዚህ ሲያደርጋት ….አሁን እንደቅድሙ ወዴየት ልንሄድ ነው? ብላ አልጠየቀችውም። ወደፈለገው አቅጣጫ ነድቶ የፈለገው ቦታ ቢወስዳት ግድ አይሰጣትም…..ፊቷን ወደእሱ አዙራ ሁኔታው ስታየው አስፈሪ አውሬ ሆኗል….የሚያርድ ገፅታ ተላብሷል…
በቀጣይ ምን እንደሚከሰት መገመት እልቻለችም፡፡ የሆነ የተሰባበረ ልብ እየታያት ነው፡፡የአንተ ልዕለ ስብዕና የሚበቅለው በተሰበርክበት ወቅት ነው።ዘሩ የሚያጎነቁለው በስብርባሪው ቅሪት ላይ ነው።መሰበርህ ህመም ቢኖረውም ግን ደግሞ አሁን ላለህበት ማንነት ምክንያት ስለሆነ በምሬት የምታነሳው ብቻ ሳይሆን በምስጋናም የምትዘክረው ነው።ስለዚህ መሠበርህን አትጥላ ፤ሀዘንህንም አታጋኘው…..ይሄንን ዲስኩር የት እንደሰማችው አታውቅም ...ግን ትዝ አላት ..እንዴት ትዝ አላት?አታውቅም። ..ከዚህ ሀዘን በኃለ ደስታ ይመጣ ይሆን…?በደም ከጨቀየው አንሶላ ብሀላ መፅናናት ይቻል ይሆን ?ምንም መገመት አልቻለችም። ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍10119👏6🔥5🥰2
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-34
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
መንግስቱ  ትእግስትን ከጎኑ እንዳደረገ መኪናዋን በደመነፍስ እየነዳ በሰንዳፍ መስመር ከከተማ ወጣ...ትዕግስትም ስለደነዘዘች ምንም አላለችውም።ልክ ሰንዳፍ ሊደርስ አንድ ኪሎ ሜትር  ያህል  ሲቀራቸው  ወደ ግራ ታጠፈና መኪናዋን ከአስፓልት አወጣት ።ሜዳውን እየሠነጠቀ  አምስት መቶ ሜትር ያህል ከነዳ በኃላ አቆመ።ሞተሩን አጠፋና ወረደ።ትዕግስትም ተከትላው ወረደች።አረንጓዴ ሳር የለበሰው ሜዳ ላይ ቁጭ አለ።እሷም አንድ ሜትር ራቅ አለችና ከፊት ለፊቱ ቁጭ አለች።ከጃኬት ኪሱ ውስጥ ፎቶ አወጣና አትኩሮ ማየት ጀመረ...።ፎቶው የአሮሯ ነው...ይሄ የእሷ ፎቶ እስር ቤትም አብሮት የነበረ ፎቶ ነው።ይሄው ከእስር ቤት ከወጣም ከሁለት አመት በኃላም ከእሱ ጋር አለ..ፎቶውን በአዲስ እና በቅርብ በተነሳችው ዘመናይና ሽቅርቅር  ፎቶም መቀየር አልፈለገም... ስሜቱ ድፍርስርስ አለበት...ሟች ዘመዶቹ ሁሉ በምናብ ተደረደሩበት....እናትና አባቱ ናፈቁት ...እንባው ፈንቅሎት  ተዘረገፈ...ጭንቅላቱን ይዞ በመንሰቅሰቅ አለቀሰ...ትዕግስት ወደእሱ ተጠግታ አቅፋው አብራው ታለቅስ ጀመር...የተወሰነ መረጋጋት ላይ ለመድረስ ከ30 ደቂቃ በላይ ፈጀባቸው።
ድንገት"ምን ታስቢያለሽ?"ሲል ጠየቃት።
"ስለምኑ?"
"ስለአሮሯ ነዎ...የገደላት ይመስልሻል?..."
አንገቷን አቀርቅራ ዝም አለችው።በውስጧ እንደገደላት ነው እያሰበች ያለችው ...ግን እንዴት ብላ አዎ የገደላት ይመስለኛል ልትለው ትችላለ?።ከባድ ነው።
"ግን ምን  አይነት ጭካኔ ቢኖረው ነው የእሷ ገላ ላይ ጉዳት  የሚያደርሰው?ምንስ ብትበድለው እንኳን ግድያ ጥፊ ይገባታል...ሰው እንዴት የገዛ ልጅ ላይ እንዲህ ያደርጋል።"
"ልጅ ሳትሆን የእንጀራ ልጅ"
"ያው ነው..ይህቺ ልጅ እኮ ወላጅአባቷን አታውቅም ...ከህፃንነቷ ጀምሮ ያሳደጋት እሱ ነው።አባቷ ነው።"
ስለአሮራ እና ስለአባቷ ግርማ ፆታዊ ግንኙነት  የምታውቀውን ሁሉ ልትነግረው ፈለገች...ግን የሚፈጠረውን ገመተችና ዝግንን ብሏት ለጊዜውም ቢሆን መልሳ ዋጠችው...በዚህ መሠበር ላይ ሌላ መሠበር መቋቋም አይችልም ብላ አሰበች
"አሁን ምን እናድርግ...ለፓሊስ ሪፓርት እናድርግ...?"የሚል ጥያቄ አቀረበችለት።ከእሱ መልስ ስትጠብቅ ስልኳ ጮኸ...ከኪሷ አወጣችና አየችው"ወይኔ ጉዴ ...እሱ ነው...እራት ሊጋብዘኝ ቀጠሮ ነበረን"
"አንሺዋ"አላት
"አንስቼውስ?ምን እለዋለው?"
"በቃ  ታገኚዋለሻ...ቀርበን እኮ ነው የተሻለ መረጃ ማግኘት የምንችለው"
እነሱ ከመስማማታቸው በፊት ስልኩ ተቋረጠ።
"እንዴት አድርጌ ከገዳይ ጋር እራት በላለሁ..?.."ዘገነናት
"አረ በፈ ጣሪ እንደዛ አላደርግም..ይልቅ አሁን ለፓሊስ እናመልክት እና እነሱ ያደረጉትን  ያድርጉ።"
"አይሆንም ..ፓሊስ እዚህ ውስጥ አይገባም...አሁን  ከንቺ የምፈልገው በትክክል እንደገደላት የሚያረጋግጥልኝ  አንኳር መረጃ እንድታገኚልኝ ነው...ከዛ እባክህ ግደለኝ  እያለ እንስኪማፀነኝ ድረስ ቀስ በቀስ እያንዳንድን የሠውነቱን አካል በየተራ እየገነጠልኩ ለውሻ በማብላት ነው የምጨርሰው.... ደውይለት ...ደውይለትና አሁን 12፡20 ነው 1፡30 ላይ ቅጠሪው ።"
ከፍራቻዋ ሳትወጣ ደወለችቸት ...በሚንቀጠቀጥና በሚርገበገብ ድምፅ ታወራው ጀመር።
"ሄሎ አንቺ እንደዚህ ይደረጋል?"
"ምን አደረኩ?"
"እራት እንብላ ተባብለን ....ትልቅ ቀጠሮ ሰርዤ እቤት ብመጣ የለሽም..ስልክ ብደውል አታነሺም።"
"ጋሽ ግርማ በጣም ይቅርታ  ...አንድ ጓደኛዬ ታማ ሆስፒታል ገባች ብለው ሲደውሉልኝ ደንግጬ ወደ ሆስፒታል ሄድኩ..."
"ውይ የት ሆስፒታል?"
"ሚኒሊክ"
"በቃ መጣልሻለው"
ደነገጠች"አረ አትምጣ ።አሁን እኳ ወጥታ ወደ ቤት እየወሰድናት ነው...እራት የምንበላበትን ቦታ ንገረኝና እስከ 1፡30 ደርሳለው።"
"እርግጠኛ ነሽ"
"አዎ እርግጠኛ ነኝ"
"በቃ እሺ በናፍቆት እጠብቅሻለው"
"እሺ ቸው"ስልኩ ተዘጋ
"በፈጣሪ አሁን ከዚህ ከገዳይ ፊት ቁጭ ብዬ እንዴት ነው ምግብ የሚዋጥልኝ?"ተነጫነጨች።
"ለእኔም ለአሮራም ስትይ  ታደርጊዋለሽ...በይ ተነሽ እንሂድ" አለና መኪና ውስጥ ይዟት ገባ።ሞተሩን ከማስነሳቱ በፊት ከኪሱ ቼክ አዋጣና 200 ሺ ብር  የትዕግስትን ስም ፅፎበት  ፈረመና አቀበላት።
ደንግጣ"ምንድነው?ከሰውዬው ጋር እንድተኛ እየከፈልከኝ እንዳይሆን?።"
"በፍፁም ...የምታደርጊውን እያደረግሽ ያለው ለጓደኝነታችን እንደሆነ አውቃለው...ለዛም ትልቅ ክብር አለኝ ...ግን ማወቅ ያለብሽ  አሁን ከሰውዬው ጋር ጦርነት ውስጥ ልንገባ ነው...ምን እንደሚፈጠር አናውቅም...ማን ቀድሞ እንደሚወድቅም መገመት ከባድ ነው...
የመኪናውን ሞተር አስነሳና ወደአስፓልቱ አስገብቶ የመልስ ጉዞ ጀመሩ
"እና ምን እያልከኝ ነው..?ብሩ እኮ ብዙ ነው።"
"እኔ የሆነ ነገር ከሆንኩ  ሰውዬው የእጅን እንዲያገኝ ለማድረግ ትንሽም ቢሆን የምትንቀሳቀሺበት ብር ያስፈልግሻል..ለዛ ብዬ ነው"
"በፍፅም አንተ ምንም መሆን የለብህም"አለችው በመንዘርዘር
"መሆን ያለበትን ነገር እንዳይሆን ማስቀረት አንችልም... ህይወት ልክ እንደ ፊልም እስክሪፕት ነች።እዛ እስክሪኘት ላይ አፍቃሪና ተፈቃሪዋች አሉ..ገዳይና ተገዳይ ...ሀለቃና ምንዝር..ክፍና ደግ...ምጡቅና ደደብ...ሸርሙጣና  ቁጥብ በእነዚህ ሁሉ የተዋቀረ ብዙ ቅንጭብጫቢ ታሪኳች የታጨቁበት አንድ ወጥ ታሪክ  አለ...ታዲያ ይሄን እንዲያዘጋጅ የተሰጠው ዳሪክተሩ ብዙ ተዋናዬችን ይሰበስብና አንተ አፍቃሪ ሁን ...አንቺ ደግሞ ተፈቃሪ ...አንተ ትገድላለህ አንተ ደግሞ ትገደላለህ...አንተ ደደብን ትተውናለህ አንተ ደግሞ ጂንዬስ ትሆናለህ...እያለ ይደለድላል ።በዛ መሠረት ሁሉም የተሠጠውን ገፀባህሪ በብቃት ለመጫወት ጠንክሮ ይለማመዳል። ብቻውንም ሆነ ከሌላው ጋር ባለው መስተጋብር የተሠጠውን ገፀባህሪ ቦታ ለማግኘትና  ሚናውን በታማኝነት ለመወጣት  በሙሉ አቅሙ ይጥራል።ህይወትም ልክ እንደዚሁ ነው ...
ለያንዳንዳችን የምንጫወተውን የተለየ አይነት ሮል ሰጥታናለች።ልዩነቱ እስክሪኘቱ ተፅፎ አይሰጠንም በተፈጥሮ አእምሯችን ውስጥ የሚቀመጥ ነው።እና የተሠጠንን ሚና ደግሞ የእውነት  እንጫወታለን..አፍቃሪው ከልብ በነፍሱ ጭምር ያፈቅራል ..ከዳተኛውም ቀሺም ምክንያት ፈልጎ ይከዳል...የሚገድለው  ወይ በሽጉጥ ግንባር በርቅሷ ወይ ደግሞ በሳንጃ አንገት ቀንጥሷ ይገድላል።ሁላችንንም የተሠጠንን ህይወት ነው የሚኖረው "...ለተገዳይነት ተፈጥሮ ገዳይ ለመሆን መጋጋጥ  ከተፈጥሯዊ ሚና ማፈንገጥ ነው።እና   አሁን አንቺም ሚናሽን ተወጪ እኔም ሚናዬን እወጣለው። የሚሞተውም ይሞታል...ገዳዩም ይገድላል።"አላት
በዚህ ጊዜ አቶ ግርማ እንዲገናኙ የላከላት አድራሻ ጋር ደርሰው ስለነበረ መኪናዋን ቦታ አስይዞ አቆማት።
"በቃ እሺ...ስልክህን እንዳትዘጋ"አለችው።
"አልዘጋም...እና ደግሞ እዚሁ አካባቢ ነው የምጠብቅሽ..ከተቻለሽ በደንብ አስክሪውና ይዘሽው እደሪ ..አንዳንድ ሰው በስካርና በወሲብ ጡዘት ላይ እውነቱን የመለፍለፍ አመል አለው... እና ምንም ነገር ከፈለግሽ ወይ ደውይልኝ..ካልተመቸሽም ሚሴጅ ላኪልኝ"አላት።
"እውነቱ ላይ ለመድረስ የተቻለኝን አደርጋለሁ"አለችና ከመኪናው  ወረደች... እያያት አስፓልቱን ተሻጋራ አቶግርማ ወደሚጠብቃት ሆቴል ገባች።
👍668😁1
ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-34
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
መንግስቱ  ትእግስትን ከጎኑ እንዳደረገ መኪናዋን በደመነፍስ እየነዳ በሰንዳፍ መስመር ከከተማ ወጣ...ትዕግስትም ስለደነዘዘች ምንም አላለችውም።ልክ ሰንዳፍ ሊደርስ አንድ ኪሎ ሜትር  ያህል  ሲቀራቸው  ወደ ግራ ታጠፈና መኪናዋን ከአስፓልት አወጣት ።ሜዳውን እየሠነጠቀ  አምስት መቶ ሜትር ያህል ከነዳ በኃላ አቆመ።ሞተሩን አጠፋና ወረደ።ትዕግስትም ተከትላው ወረደች።አረንጓዴ ሳር የለበሰው ሜዳ ላይ ቁጭ አለ።እሷም አንድ ሜትር ራቅ አለችና ከፊት ለፊቱ ቁጭ አለች።ከጃኬት ኪሱ ውስጥ ፎቶ አወጣና አትኩሮ ማየት ጀመረ...።ፎቶው የአሮሯ ነው...ይሄ የእሷ ፎቶ እስር ቤትም አብሮት የነበረ ፎቶ ነው።ይሄው ከእስር ቤት ከወጣም ከሁለት አመት በኃላም ከእሱ ጋር አለ..ፎቶውን በአዲስ እና በቅርብ በተነሳችው ዘመናይና ሽቅርቅር  ፎቶም መቀየር አልፈለገም... ስሜቱ ድፍርስርስ አለበት...ሟች ዘመዶቹ ሁሉ በምናብ ተደረደሩበት....እናትና አባቱ ናፈቁት ...እንባው ፈንቅሎት  ተዘረገፈ...ጭንቅላቱን ይዞ በመንሰቅሰቅ አለቀሰ...ትዕግስት ወደእሱ ተጠግታ አቅፋው አብራው ታለቅስ ጀመር...የተወሰነ መረጋጋት ላይ ለመድረስ ከ30 ደቂቃ በላይ ፈጀባቸው።
ድንገት"ምን ታስቢያለሽ?"ሲል ጠየቃት።
"ስለምኑ?"
"ስለአሮሯ ነዎ...የገደላት ይመስልሻል?..."
አንገቷን አቀርቅራ ዝም አለችው።በውስጧ እንደገደላት ነው እያሰበች ያለችው ...ግን እንዴት ብላ አዎ የገደላት ይመስለኛል ልትለው ትችላለ?።ከባድ ነው።
"ግን ምን  አይነት ጭካኔ ቢኖረው ነው የእሷ ገላ ላይ ጉዳት  የሚያደርሰው?ምንስ ብትበድለው እንኳን ግድያ ጥፊ ይገባታል...ሰው እንዴት የገዛ ልጅ ላይ እንዲህ ያደርጋል።"
"ልጅ ሳትሆን የእንጀራ ልጅ"
"ያው ነው..ይህቺ ልጅ እኮ ወላጅአባቷን አታውቅም ...ከህፃንነቷ ጀምሮ ያሳደጋት እሱ ነው።አባቷ ነው።"
ስለአሮራ እና ስለአባቷ ግርማ ፆታዊ ግንኙነት  የምታውቀውን ሁሉ ልትነግረው ፈለገች...ግን የሚፈጠረውን ገመተችና ዝግንን ብሏት ለጊዜውም ቢሆን መልሳ ዋጠችው...በዚህ መሠበር ላይ ሌላ መሠበር መቋቋም አይችልም ብላ አሰበች
"አሁን ምን እናድርግ...ለፓሊስ ሪፓርት እናድርግ...?"የሚል ጥያቄ አቀረበችለት።ከእሱ መልስ ስትጠብቅ ስልኳ ጮኸ...ከኪሷ አወጣችና አየችው"ወይኔ ጉዴ ...እሱ ነው...እራት ሊጋብዘኝ ቀጠሮ ነበረን"
"አንሺዋ"አላት
"አንስቼውስ?ምን እለዋለው?"
"በቃ  ታገኚዋለሻ...ቀርበን እኮ ነው የተሻለ መረጃ ማግኘት የምንችለው"
እነሱ ከመስማማታቸው በፊት ስልኩ ተቋረጠ።
"እንዴት አድርጌ ከገዳይ ጋር እራት በላለሁ..?.."ዘገነናት
"አረ በፈ ጣሪ እንደዛ አላደርግም..ይልቅ አሁን ለፓሊስ እናመልክት እና እነሱ ያደረጉትን  ያድርጉ።"
"አይሆንም ..ፓሊስ እዚህ ውስጥ አይገባም...አሁን  ከንቺ የምፈልገው በትክክል እንደገደላት የሚያረጋግጥልኝ  አንኳር መረጃ እንድታገኚልኝ ነው...ከዛ እባክህ ግደለኝ  እያለ እንስኪማፀነኝ ድረስ ቀስ በቀስ እያንዳንድን የሠውነቱን አካል በየተራ እየገነጠልኩ ለውሻ በማብላት ነው የምጨርሰው.... ደውይለት ...ደውይለትና አሁን 12፡20 ነው 1፡30 ላይ ቅጠሪው ።"
ከፍራቻዋ ሳትወጣ ደወለችቸት ...በሚንቀጠቀጥና በሚርገበገብ ድምፅ ታወራው ጀመር።
"ሄሎ አንቺ እንደዚህ ይደረጋል?"
"ምን አደረኩ?"
"እራት እንብላ ተባብለን ....ትልቅ ቀጠሮ ሰርዤ እቤት ብመጣ የለሽም..ስልክ ብደውል አታነሺም።"
"ጋሽ ግርማ በጣም ይቅርታ  ...አንድ ጓደኛዬ ታማ ሆስፒታል ገባች ብለው ሲደውሉልኝ ደንግጬ ወደ ሆስፒታል ሄድኩ..."
"ውይ የት ሆስፒታል?"
"ሚኒሊክ"
"በቃ መጣልሻለው"
ደነገጠች"አረ አትምጣ ።አሁን እኳ ወጥታ ወደ ቤት እየወሰድናት ነው...እራት የምንበላበትን ቦታ ንገረኝና እስከ 1፡30 ደርሳለው።"
"እርግጠኛ ነሽ"
"አዎ እርግጠኛ ነኝ"
"በቃ እሺ በናፍቆት እጠብቅሻለው"
"እሺ ቸው"ስልኩ ተዘጋ
"በፈጣሪ አሁን ከዚህ ከገዳይ ፊት ቁጭ ብዬ እንዴት ነው ምግብ የሚዋጥልኝ?"ተነጫነጨች።
"ለእኔም ለአሮራም ስትይ  ታደርጊዋለሽ...በይ ተነሽ እንሂድ" አለና መኪና ውስጥ ይዟት ገባ።ሞተሩን ከማስነሳቱ በፊት ከኪሱ ቼክ አዋጣና 200 ሺ ብር  የትዕግስትን ስም ፅፎበት  ፈረመና አቀበላት።
ደንግጣ"ምንድነው?ከሰውዬው ጋር እንድተኛ እየከፈልከኝ እንዳይሆን?።"
"በፍፁም ...የምታደርጊውን እያደረግሽ ያለው ለጓደኝነታችን እንደሆነ አውቃለው...ለዛም ትልቅ ክብር አለኝ ...ግን ማወቅ ያለብሽ  አሁን ከሰውዬው ጋር ጦርነት ውስጥ ልንገባ ነው...ምን እንደሚፈጠር አናውቅም...ማን ቀድሞ እንደሚወድቅም መገመት ከባድ ነው...
የመኪናውን ሞተር አስነሳና ወደአስፓልቱ አስገብቶ የመልስ ጉዞ ጀመሩ
"እና ምን እያልከኝ ነው..?ብሩ እኮ ብዙ ነው።"
"እኔ የሆነ ነገር ከሆንኩ  ሰውዬው የእጅን እንዲያገኝ ለማድረግ ትንሽም ቢሆን የምትንቀሳቀሺበት ብር ያስፈልግሻል..ለዛ ብዬ ነው"
"በፍፅም አንተ ምንም መሆን የለብህም"አለችው በመንዘርዘር
"መሆን ያለበትን ነገር እንዳይሆን ማስቀረት አንችልም... ህይወት ልክ እንደ ፊልም እስክሪፕት ነች።እዛ እስክሪኘት ላይ አፍቃሪና ተፈቃሪዋች አሉ..ገዳይና ተገዳይ ...ሀለቃና ምንዝር..ክፍና ደግ...ምጡቅና ደደብ...ሸርሙጣና  ቁጥብ በእነዚህ ሁሉ የተዋቀረ ብዙ ቅንጭብጫቢ ታሪኳች የታጨቁበት አንድ ወጥ ታሪክ  አለ...ታዲያ ይሄን እንዲያዘጋጅ የተሰጠው ዳሪክተሩ ብዙ ተዋናዬችን ይሰበስብና አንተ አፍቃሪ ሁን ...አንቺ ደግሞ ተፈቃሪ ...አንተ ትገድላለህ አንተ ደግሞ ትገደላለህ...አንተ ደደብን ትተውናለህ አንተ ደግሞ ጂንዬስ ትሆናለህ...እያለ ይደለድላል ።በዛ መሠረት ሁሉም የተሠጠውን ገፀባህሪ በብቃት ለመጫወት ጠንክሮ ይለማመዳል። ብቻውንም ሆነ ከሌላው ጋር ባለው መስተጋብር የተሠጠውን ገፀባህሪ ቦታ ለማግኘትና  ሚናውን በታማኝነት ለመወጣት  በሙሉ አቅሙ ይጥራል።ህይወትም ልክ እንደዚሁ ነው ...
ለያንዳንዳችን የምንጫወተውን የተለየ አይነት ሮል ሰጥታናለች።ልዩነቱ እስክሪኘቱ ተፅፎ አይሰጠንም በተፈጥሮ አእምሯችን ውስጥ የሚቀመጥ ነው።እና የተሠጠንን ሚና ደግሞ የእውነት  እንጫወታለን..አፍቃሪው ከልብ በነፍሱ ጭምር ያፈቅራል ..ከዳተኛውም ቀሺም ምክንያት ፈልጎ ይከዳል...የሚገድለው  ወይ በሽጉጥ ግንባር በርቅሷ ወይ ደግሞ በሳንጃ አንገት ቀንጥሷ ይገድላል።ሁላችንንም የተሠጠንን ህይወት ነው የሚኖረው "...ለተገዳይነት ተፈጥሮ ገዳይ ለመሆን መጋጋጥ  ከተፈጥሯዊ ሚና ማፈንገጥ ነው።እና   አሁን አንቺም ሚናሽን ተወጪ እኔም ሚናዬን እወጣለው። የሚሞተውም ይሞታል...ገዳዩም ይገድላል።"አላት
በዚህ ጊዜ አቶ ግርማ እንዲገናኙ የላከላት አድራሻ ጋር ደርሰው ስለነበረ መኪናዋን ቦታ አስይዞ አቆማት።
👍325🥰2
"በቃ እሺ...ስልክህን እንዳትዘጋ"አለችው።
"አልዘጋም...እና ደግሞ እዚሁ አካባቢ ነው የምጠብቅሽ..ከተቻለሽ በደንብ አስክሪውና ይዘሽው እደሪ ..አንዳንድ ሰው በስካርና በወሲብ ጡዘት ላይ እውነቱን የመለፍለፍ አመል አለው... እና ምንም ነገር ከፈለግሽ ወይ ደውይልኝ..ካልተመቸሽም ሚሴጅ ላኪልኝ"አላት።
"እውነቱ ላይ ለመድረስ የተቻለኝን አደርጋለሁ"አለችና ከመኪናው  ወረደች... እያያት አስፓልቱን ተሻጋራ አቶግርማ ወደሚጠብቃት ሆቴል ገባች።


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍6811👎5🥰4🤔2
‹‹ባል አስይዞ ቁማር››
ምዕራፍ-35
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

በቀጠሯችን መሰረት ወደቃል ቤት እየሄደች ነው።ይህ ቀጠሮ ለእሷ ልክ እንደከዚ ቀደሞቹ ቀጠሮዎች አይነት አይደለም።ቀጠሮውን ሳታሲዘው እንኳን "ለብቻህ ለረጂም ሰዓት ነው የምፈልግህ..በምንም አይነት የማይሰረዝ የሞት ቀጠሮ ነው"ነበር ያለችው።ልክ ስድስት ሰዓት እሱ ቤት ለመገናኘት ነው የተቀጣጠሩት። ሁለት ሰዓት ከቤት ወጣች፤ የውበት ሳሎን ደንበኞቾ ጋር ሄደች ...ከጥፍሯ አንስቶ ቅንድቧን ፀጉሯን እስክታስተካክልላት አራት ተኩል ሆነ...እቤት ሄዳ በሀገሪቱ አለ በተባለች ዲዛይነር በልዩ ሁኔታ ያሰፋችውን የሀገር በሀል ቀሚስ ለብሳ እሱን ደስ ያሰኘዋል ብላ ባሰችው አለባበስ ዘንጣ መኪናዋን እሱ የሚኖርበት ግቢ አስገብታ ሳታቆም ሰዓቱ 6.03 ይል ነበር።የመኪናዋን ሞተር ከጠፋችና  ለእለቱ ልዪ ዝግጅት ማድመቂያ ይሆን ዘንድ ይዛ የመጣችውን ቶርታ ኬክ፤ውስኪ፤ሻማዎች እና ቸኮሌቶችን ከእነ ዘንቢሉ እየተንገዳገደችም ቢሆን ይዛ ወረደችና ወደ ቃል ቤት ልትታጠፍ ስትል አሮጊቷ የቤት አከራይ  ከእቤታቸው ሲወጡ ተገጣጠሙ ።
"ውይ በጌታ መጣሽ?"አሉ ከሞት የተነሳ ዘመዳቸውን ድንገት እንዳዩ አይነት ደንግጠው።አሮጌ ቷ መደንገጥ ብቻ ሳይሆን እንባቸውም እየረገፈ ነው ።
" ማዘር ምን ሆኑ?"
‹‹አረ ምንም አልሆንኩ..ምነው ጠየቅሺኝ?"
"አይ እያለቀሱ ነው ብዬ ነዋ"
"እ አይ ልጄ ጭስ ነገር ነበር ..እቤት ያው ያሮጊት ነገር ታውቂ የለ"
"በሉ እሺ"ብላ መንገዷን ስትቀጥል
"ቆይ ልጄ ቁልፍ ልስጥሸ"አሏትና አስቆሟት፡፡
ውስጧን ክፍት አለው"ምነው ቃል የለም እንዴ?››ለስለስ ባለ ድምፀት ጠየቀቻቸው ።
"ቃል ነው ያልሽው ?"አሉና ወደውስጥ መግባቱን እረስተው ፍዝዝ ብለው ቆሙ፡
"እንዴ እማማ ..ችግር አለ እንዴ?"
"አረ የለም..ማለቴ ቃል ወጣ ብሎ ነው አልቆይም ብሎል"ብለዋት ወደ ውስጥ ገብ ።
"ቃል ደግሞ በዚህ ቀን?ለዛውም እንዲህ አስጠንቅቄህ"ቃል ስሯ ሆኖ ባይሰማትም ተነጫነጨችበት ።
አሮጊቷ አምጥተው ቁልፍን ሰጧት... ነገረ ስራቸው አላማራትም‹..አይናቸውን ከዓይኔ ለምንድነው የሚያሸሹት?›ቁልፉን ተቀብላ እያልጎመጎመች ወደጓሮ ዞረችና የቃልን ቤት ከፍታ ገባች።እንደወትሮ ፅድት እንዳለ  ነው።እሷ ግን ከወትሮ የተለየ የደመቀና የፈካ እንዲሆን ነበር የፈለገችው።ለቧ ላይ እንደሚንቦገቦገው አይነት የደስታ ብርሀን እቤቱም እንደዛው ይሆናል ብላ ጠብቃ ነበር.. በሚገርም ሁኔታ ግን ምን እንኳን እቤቱ በውስጧ በፈለገችው ሆኔታ ባየሸበርቅም  ጠረጰዛው  ግን በምትወዳቸው የምግብ አይነቶች ተሞልቶል። ሞባይሏን አወጣችና ከተለያየ አቅጣጫ አንድ ሶስት ፎቶዎች አነሳችና።‹‹እንደውም ጥሩ አጋጣሚ ነው ።እስኪመለስ አንዳንድ ነገሮችን አስተካክላለሁ› ብላ አሰበችና ወደውስጥ ዘለቀች።የቤቱን መብራት አበራችው...ሌላ አነስ ያለች ጠረጰዛ የክፍሉን አንድ ግድግዳ ተጠግታ ትታያለች።የጠረጰዛውን አቅጣጫ አስተካከለችና ያመጣችውን ኬክ መሀከል ላይ አስቀመጠችው.. የውሰኪ ጠርሙሱን አወጣችና ከጎኑ  አደረገችው...ዝርግ ሰሀኖችን ፈለገችና ቸኮሌቶቾን በመዘርገፍ ቦታ ሰጠዋቸው ።
‹‹አዎ አሁን የጎደለው ሙዚቃና ቃልዬ ብቻ ነው።››አለችና ሙዚቃ ለመክፈት ወደመኝታ ቤት ገባች።ወደጂፓሱ ሄደችና ሶኬቱን ሰካችው.. እላዩ ላይ ፍላሽ ስለነበረ ከፈተችውና ድምፅን መጥና ወደሳሎን ልትመልስ ስትል አይኗ የቃልን አልጋ ላይ  አረፈ..ከተነጠፈው ሰማያዊ የአልጋ ልብስ ላይ ሁለት ነጫጭ ፓስታዎች  ተደራርበው ተቀምጠዎል።ለምን እንደሆነ ባይገባትም አልፋቸው መሄድ አልፈለገችም።ወደኃላ ተመለሰችና የአልጋው ጠርዝ ላይ በመቀመጥ አነሳቻቸው፡፡ ሁለቱንም በሁለት እጆቾ ይዛ ከላይ የተፃፈባቸውን አድራሻ አነበበች፡፡
አንደኛው‹‹ከቃል ለጊፋቲ የተፃፈ የስንብት ደብዳቤ ››ይላል።
‹‹የስንብት› ማለት ምን ማለት ነው?።አዎ ገባኝ መድህኔን ልታገባ ስለሆነ እየተሰናታት ነው…።በዚህ መጠን ተበሳጭቶብሻል ማለት ነው..ደግ አደረገ›› አለችና በውስጧ በስኬቶ በመኩራራት ፈነጠዘች፡፡
"እሱን ወደነበረበት አልጋ ላይ ወርወር በማድረግ ሁለተኛውን ገልብጣ፡፡ አድራሻውን ማየት ጀመረች፡፡ በተመሳሳይ ቀለም በአንዳ አይነት የፊደል አጣጣል የተፃፈ ነው፡፡ከቃል ለልዩ የተፃፈ የስንብት ደብዳቤ ይላል፡፡በዚህ ወቅት የቤቱ አየር ተበከለ ፤መተንፈስ ብቻ ሳይሆን አይኖቾን ከፍታ አካባቢዋን ሁሉ ማየት ነው ያቃታት.. ፖስታውን  በሚንቀጠቀጡ እጇቾ ቀዳዳ ከፈተችው፡፡
‹ልዩ እንዲህ ያደረኩት አንቺን በአካል አግኝቶ መሰናበት ቀላል ሆኖ ስላላገኘሁት ነው።አንቺና ጊፍቲ ከአባቴ ቀጥሎ በዚህች ምድር ያላችሁኝ የቅርቤም የልቤም ሰዎች ናችሁ።ልዩ እኔ ከአሁን ወዲህ የለውም...እንደምታውቂው ነፍሴ በዚህ አለም ኳኳታና ትርምስ ደስተኛ አይደለችም።ከዚህ በላይ በውስጧ መኳተን ለእኔም ሆነ በዙሪያዬ ላሉ ሰዎች መልካም መስሎ አልታየኝም።ወደእዚህች ምድር የመጣሁበትን ምክንያት ለመመርመር ፀጥታ ወደአረበበትና በፅሞና ማሰላሰል ወደምችልበት ቦታ ማለቴ ወደገዳም አምርቼያለሁ።ነግሬሽ ባላውቅም ወደእዛ መሄድ የረጅም ጊዜ ውጥኔ ነበር...ግን ያው ይህቺ አለም የራሷ የሆነ ወጥመድ አላትና እስከአሁን ሊሳካልኝ አልቻለም ነበር።
ለማንኛውም እግዚያብሄር ነገሮች እንዲከወኑ የሚፈቅድበት የራሱ የሆነ ጊዜ አለው ...እናም ዛሬ ቀኗ ሆነችና ህልሜ ተሳካ።ካዛሬ ጀምሮ እኔ የመንፈሳዊው አለም ምልምል ወታደር ሆኜ ተመርጬለሁ።ጮርቃ የሆነውን መንፈሳዊ ህይወቴንም ጥልቀት ያለው የበሰለና  ለሌላው የሚተርፍ እስኪሆን ድረስ በልምምድ ተጋለሁ ሁለት አመትም ፈጀብኝ ሀያ አመት ካልሆነም እድሜ ልክ አያስጨንቀኝም...በመንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ ወደ ሰማያዊ ንቃት ለማደግ  ምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ።እግዚያብሄርም እንደሚያግዘኝ እተማመናለሁ። አንቺም እንደምትፀልይልኝ ጥርጥር የለኝም።እንግዲህ ልዩ የህይወት አላማዬ አስገድዶኝ በመንፈሳዊ ተልዕኮ ተገድጄ ካልሆነ በስተቀር ከምሄድበት የፅሞናና የፀጥታ ቦታ ወጥቼ ወደእናንተ የምመጣ ስለማይመስለኝ ይህ  ስንብት የመጨረሻችን ነው።ግን ደግሞ በሚቀጥለው አለም በተለየ ሁኔታ እንገናኛለን የሚል የፀና እምነት አለኝ።
በስተመጨረሻ ሁለት ነገሮችን እንድታደርጊልኝ እጠይቅሻለሁ ..የመጀመሪያው ለጊፍቲ ጥሩ ጓደኛ እንድትሆኚያትና ሁለተኛው ደግሞ በተቻለሽ መጠን አባቴን እንድትጠይቂው ነው።ያው አንቺም አባት የለሽም አይደል... አባቴን ሸልሜሻለሁ።የቤቱን ዕቃ ከጊፍቲ ጋር ተማክራችሁ እንደሚሆን አድርጉት ወይ ለተቸገረ ስጡት...ብቻ እንደመሠላችሁ። በስተመጨረሻ በእጆቼ ጣቶች በጥልቅ ምስጋናና በፍፅም ፍቅር የመጨረሻ ምሳ አዘጋጅቼልሻለሁ...ጣፍጦሽ እንደምትበይው እርግጠኛ ነኝ።በይ ቸው..እስከአሁን አብረን በቆየንባቸው ጊዜያቶች ስላሳየሽኝ ደግነት፤ስለ ሰጠሸኝ ፍቅር፡ስለአጎናፀፍሽኝ ደስታ ከልቤ አመሰግናለሁ!! አመስገናለሁ!!! አመሰግናለሁ... የእግዜያብሄር መንፈስ በልብሽ ይንገስ.. .አሜን
...እራሷን ተቆጣጥራ ፌንት በልታ ወደኃላዋ ተዘርራ ሳትወድቅ  ደብዳቤውን አንብባ ጨረስችው.የዛ አይነት ፅናትና ብርታት ከየት እንዳመጣቸ ለራሷም ደነቃት...ምን እየተሠማት እንደሆነ ማወቅ አልቻለችም።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍301🥰1😢1
ልብ ወለድ በፅዮን fiction ❤️😘:
#አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-36
#ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
በየደቂቃዎ በሚሊዬን የሚሆን የሰውነታችን  ሴሎች ሞተው በሚሊዬን የሚሆኑ አዳዲስ ሴሎች ይፈጠራሉ።ያ ማለት በየቀኑ ጥቂት በጥቂት እያረጀን እንፈርሳለን...በየቀኑ ደግሞ ጥቂት በጥቂት እየታደስንና እየተወለድን እንመጣለን።አሮራ ግን አሁን እየተሰማት ያለው ፈፅሞ መታደስ አይደለም ..እንደውም ፈርሶ መበታተን የጀመረ ያለፈ ስርዓት ባረጀ ርዕዬት ሳቢያ ያስገናባው ሀልት እንደሆነች አይነት ስሜት ነው እየተሰማት ያለው…
እንዴት ግን በ22 አመቴ እንደዚህ አረጀው….?እንዴት በዚህ እድሜዬ በእንደዚህ እይነት መንገድ በሰው ተጠልፌ ለመታልና ለመክሰም ተዘጋጀው…..በብረት ፍርግርግ በተሰራ የመስታወት መስኮት አጠገብ  ባለ ወንበር ተቀምጣ አይኗን ግቢው ውስጥ ባሉ አረንጓዴ ትክሎችና አበቦች አማትራ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎችን  እራሷን በመጠየቅ እየተብሰለሰለች ነው፡፡ጋርዶቹ አሁንም በራፏ ላይ ተገትረው እየጠበቋት ነው፡፡አሮሯ ውጩ ናፍቋታል....መድረክ ላይ እየተወዛወዙ መዝፈን ናፍቋታል...የመንግስቱ ልብን የሚያቀልጡና ውስጥን የሚያሞቁ ውብ የፍቅር ሚሴጆችን ማንበብ በጣም ናፍቋታል...ከዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ እራሷን የምታወጣበትን እና ነፃ ሰው የምትሆንበትን  ቀን  ናፍቋታል።
በራፉ ተከፈተ…‹‹..ምንም አልፈልግም …ውጡልኝ››እይታውን ከመስኳቱ ወደውስጥ ሳትመልስ አምቧረቀች፡፡
ወደውስጥ ዘልቆ እየገባ‹‹እኔንም አትፈልጊኝም ማለት ነው?››አላት..አቶ ግርማ ነበረ….
ድምጹን ስትሰማ አንዘረዘራት‹‹በህይወቴ በዚህ ልክ ሰው ያስጠላኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር…››አለችው ፡፡
‹‹ጥሩ ነው….ዛሬ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ድነሽ ወደአቋምሽ ተመልሰሻል…የግንባርሽ ጠባሳም በቀላል ሰርጀሪ እንደሚስተካከል እርግጠኛ ነኝ››አላት፡፡
‹‹አዎ …ግን መገደሌ ላይቀር ወደአቋሜ መመለስ  ሆነ ጠባሳዬን በሰርጀሪ ማስወገድ ምን ይረባኛል?››
‹‹አትሳሳቺ…   ምንም ቢሆን እኮ ያስደኩሽ ልጄ እና ወለላሽን ያጠጣሺኝ  ፍቅረኛዬ ነሽ…ዝም ብዬማ አልገልሽም…ከተስማማን ለምን ገድልሻለሁ?››አለና ከፊት ለፊቷ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡
‹‹ምንድነው የምትፈልገው …?.በቃ ወደፓሊስ ጣቢያ አልሄድም….ልቀቀኝ…ማለቴ ሙሉ በሙሉ ከህይወትህ አውጣኝ…ንብረቴን አስረክበኝ ከዛ አትደረስብኝ አልደርስብህም››በማለት ለቀናት ስታብሰለስለው የከረመችውን የመደራደሪያ ሀሳብ አቀረበችለት፡፡
‹ጥሩ… ወደፖሊስ ላለመሄድ መወሰንሽ ከስሜት የፀዳ ውሳኔ እየወሰንሽ እንደሆነ የስታውቃል…..ሙሉ በሙሉ ከህይወቴ ውጣ ላልሽውም እኔም ቀድሜ አስቤ ውሳኔ ላይ የደረስኩበት ጉዳይ ስለሆነ ያስማማናል….ያልገባኝ ንብረቴ ያልሽው ነው….?የእናትሽን ውርስ እየጠየቅሽ መሆኑ ነው?››
በድንጋጤና በገረሜታ አፍጥጣ አየችው‹‹የምን ውርስ ትላለህ እንዴ…..?ከ15 አመት ጀመሬ በናይትክለብ እየዘፈንኩ ነው…በአመት ከአምስት ጉዞ በላይ ወጭ ሀገር በመሄድ እንሰራለን…አንድ አልበም አሳትሜ በዛም ብዙ ብር ተገኝቶበታል….ይሄን ቤት በእኔ ብር ነው የገዛሀው…ስሙም በእኔ ነው….አንድ ኤክስካባተር ማሽንም በስሜ እንደተገዛ ነገረኸኛል…ሌላም ብዙ ብዙ…ግን እኔ አሁን ኤክስካባተሩንና ይሄንን ቤት ብቻ ከነሰነዶቹ አስረክበኝ ነው ምልህ…..ከዛ አህቴን ስጠኝ በቃ…የራሳችን ኑሮ እንኖራለን የራስሀን ኑሮ ኑር…ልናስቸግርህ አንፈልግም፡፡››

ከትከት ብሎ ሳቀ

‹‹ምነው የሚያስቅ ነገር ተናገርኩ…?››አለችው በመፀየፍ አስተያየት፡፡
‹‹አይ ገርሞኝ ነው…. አንቺ በቃ እንደሶስት አመት  ህፃን ልጅ የተነገረሽን ሁሉ ታምኛለሽ ማለት ነው…?የምን  ኤክስካቫተር ነው በአንቺ ስም ያለው…?ማሽኑ  በእህትሽ ስም ነው ያለው….፡፡ይሄ ቤትም እንደዛው…፡፡በስምሽ ያለው አንድ ብቸኛ ነገር ቢኖር የምትነጂያት መኪና ብቻ ነው፡፡››
‹‹ምን አይነት አጋሰስ ሰው ነህ ግን..?››
‹‹አፍሽን መክፈት አቁመሽ የምልሽን ስሚኝ…አሁን ሻንጣሽን ሰብስበሽ ከዚህ ሀገር ትሄጂያለሽ…የፈለግሽን ሀገር ምረጪና ተዘጋጂ… እኔ ጉዞውን አመቻችልሻለው….በሰላምና በፀጥታ ትሄጂያለሽ…ማንንም አታገኚም ያንን ጎረምሳሽንም አታገኚም….ሄደሽም አትደውይለትም….እኔ ሳላውቅና ሳልፈቅድልሽም ወደሀገርቤት መመለስ አትችይም…እዛ አስክትለምጂና ስራ መስራት እስክትጀምሪ የምትጠቀሚበት አንድ 10ሺ ዶላር አዘጋጅልሻለው››
‹‹ቆይ ያን ያህል ጅል እመስልሀለው….?ልጅነቴን ዘርፍክ….ንብረቴን ዘርፈክህ….እናቴን ዘረፍክው…ሞራሊን ዘረፍክ …ባዶ ሙልጬን ወደውጭ ስትልከኝ አሺ ይሁን ብዬ የምሄድ ይመስልሀል…?ከዛ ይልቅ በለመደ እጅህ እንደእናቴ ብትገድለኝ እመርጣለው፡፡››
‹‹አይ እኔም አልገድልሽም..አንቺም እኔ አድርጊ እንዳልኩሽ ታደርጊያለሽ››
‹‹እንደዛ እንደማደርግ በምን እርግጠኛ ሆንክ…?አስገድደህና ጭንቅላቴ ላይ ሽጉጥ በመደቀን ኤርፖርት በራፍ ድረስ ልትወስደኝ ትችል ይሆናል…አውሮፕላን ውስጥ የምታስገባኝ ግን እንዴት አድርገህ ነው?›ስትል  ያልገባትን ጥያቄ የጠየቀችው፡፡
‹‹ለእህትሽ ስትይ የምልሽን ታደርጊያለሽ››
‹‹ማለት .?.አልገባኝም…ይእ ጉዳይ ከእህቴ ጋር ምን ያገናኘዋል?››
‹‹እህትሽ ባንቺ አለመኖር ደስተኛ የሆነች መስለኛል…መኝታ ክፍሏን ሁላ ቀይራለች…አሁን አብራኝ ነው የምትተኛው››
…አሮራ አቅለሸለሻት…ከተቀመጠችበት ወንበር ተንሸራታ ወረደችና  ወለሉ ላይ ተንበረከከች…..
‹‹አንተ..ስጋህ እኮ ነች….የአብራክህ ክፍይ…ለዛውም አንድ ፍረዬ ልጅ…››
‹‹እንግዲህ ነገርኩሸ…..እኔ አንዴ በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ስለተጨመላለቅኩ ግድ አይሰጠኝም….ይሄ ሁሉ እንዳይሆን የምትፈልጊ ከሆነ እንዳልኩሽ አድርጊ… ..አትፈታተኚኝ…በይ ቸው … ነገ ስመጣ መሄድ የምትፈልጊበትን ሀገር መርጠሸ  ጠብቂኝ ››ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳና ወጥቷ ሄደ..አሮራ እዛው በተንበረከከችበት ወለላ ላይ ዝርር ብላ ተኛች፡፡
///
ትዕግስት ከመንግስቱ ጋር ቦሌ አካባቢ የሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ቁጭ ብለው የአሮራን አጎት እዝራን እየጠበቁት ነው፡፡ስለአሮራ ጉዳይ…እስከአሁን የደረሱበትን መረጃ በመነጋር በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው በጋራ ለመወሰን ነው፡፡
‹‹ማታ እንዴት ሆንሽ››ሲል ጠየቃት መንግስቱ  ትዕግስት ማታ ከግርማ ጋርቤርጎ ውስጥ ገብታ አብራ በማደሮ ያጋጠማትን ነገር ነው የሚያወራት፡፡
‹‹ሲኦል ውስጥ ነው ያሳለፍኩት››በአጩሩ መለሰችለት፡፡
‹‹ከማትፈልጊው ሰው ጋር ለእኔ ስትይ አንድትተኚ በማድረግ በፀፀት ስቃጠል ነው ያደርኩት…..ያሰተሳሰብ ብቃቴ ደብዝዞል…..እምቢ ብትይኝ ጥሩ ነበር››አላት
‹‹አይዞህ እንደምንም አምልጬያለው››
የጨገገ ፊቱ በከፊልም ቢሆን ፈገግ አለ…‹‹አትይኝም …?እንዴት ሆኗ?››
የለበሰችውን የቀኝ እግር የጅንስ ሱሪ ወደላይ ሰበሰበችና የተጋጋጠ እግሯን አሳየችው‹‹እንዴ ምን ሆንሽ  ?አምቢ ስላልሽው ደበደበሽ እንዴ?››
‹‹አይደለም….ስናወራ አምሽተን…ለአንተ ያላኩልህን ንግግራችን ካጠናቀቅን በኃላ መተኛ ሰዓታችን ሲደርስ…ከስልኬ ሙዚቃ ከፈትኩና እንድነስ አልኩት ..እሺ ብሎኝ ስንደንስ…በመሀከል ሲያሽከርክረኝ ሆነ ብዬ ተንሸራተትኩና ወለል ላይ ተዘረርኩ… ከዛ በቃ የውሸት ስሬ ዞረ ብዬ ተዘረርኩ….እግሬን አላስነካ አልኩ…የወገቤ ስር ተበጠሰ ..እህህሀህ..ስልበት አደርኩ…በለሊት ተነስቶ የግል ሆሲፒታል ወሰደኝ..እናቴ ጋር ሄጄ ብተኛ ይሻላል አልኩት..
👍518🔥1👏1😁1
ላድርስሽ ሲለኝ…እናቴ ሀይለኛ ሴት እንደሆነችና በሰፈር መታየት እንደሌለበት ነግሬው በራይድ ሸኘኝ..ከዛ ራይዱ እዙሮ አንተ ጋር አምጥቶ ጣለኝ…››ብላ ያጋጠማትን በአጭሩ አስረዳችው፡፡
‹‹በጣም አደገኛ ሴት ነሽ ..››ሲላት አዝራ አጠገባቸው ደርሶ ሰላም ሳይላቸው ወንበር ስቦ እየተቀመጠ ነበር፡፡
ስሜታችን ከምክንያታዊነት ጋር በተቃራኒ ገፅ የሚቆም አይደለም።ግን ነገሮች በምክንያታዊ ትንተና ተደግፈው ማረጋገጫ ከማግኘታቸው በፊት ቀድመው ከፊት እራሳቸውን  ይገለፃሉ ።ቆይቶ  ግን በምክንያት እና  ሳቢያ ትንታኔ የመደገፍና የመረጋገጥ እድል ሊኖራቸው ይችላል።እና ስሜታዊ መሆን ጥሩ የሚሆኑባቸው ብዙ የህይወት አጋጣሚዋች አሉ።ትዕግስት አሁን  ያለችበት የስሜት ንረት ጥሩ ነው አይደለም አታውቅም ..ግድም አይሰጣትም….አሁን የምታውቀውን ሚስጥር  ለመናገር ወስናለች….ውሳኔዋ ምን እንደሚያስከትል መገመት አትችልም….ግን የሆነው  ይሁን ብላ ወስናለች….ሞባይሎን ከፈተችና አተ ግርማና አሮራ ንታ ቤት ቢስጥር አስቀምታ የቀረፀችው የወሲብ ግንኑነታችውን የሚያሳየውን ቪዲዬ ልታሳቸው ዝግጁ ሆነች፡፡
"ይሄንን ቨዲዬ ካየ በኃላ ለእሷ መጨነቅና መፋለሙን ይቀጥላል ወይስ ቁርጥ አርጎለት እስከጭራሹ ይጠላታል..እንደገዛ ልጁ የሚያያት አጎቷስ ምን ይሰማዋል….?"በትዕግስት አእምሮ የሚጉላሉ የስጋት ጥያቄዎች ናቸው።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍5214
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-35
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
መኪና ውስጥ ሆኖ ትዕግስትን ሲጠብቅ ሳዕታት አልፈውታል….እስከአሁን ከእሷ የተሰማ ምንም ነገር የለም….ስልኩ ደጋሞ እየተደወለት  እየበጠበጠው ነው…አነሳው
‹‹.እሺ  ምነው?››በተሰላቸ ድምጻት ጠየቃት፡፡
‹‹እንዴት ምነው …?የት ነህ ?እየጠበቅኩህ እኮ ነው.››
‹‹አልመጣም አትጠብቂኝ››ዘጋባት…የአጎቱ ሚስት ውቢት ነች
…ከደቂቃዎች በኃላ አሁንም ስልኩ ጠራ …እስከወዲያኛው ዘግቶት ቢገላገል ደስ ይለው ነበር….ግን ያንን ማድረግ አይችልም..ድንገት ትእግስት ልትፈልገው ትችላለች…ስልኩን ከዘጋው  ደግሞ አታገኘውም።
አሁን ደግሞ ትብለፅ ነች፡፡
"ሄሎ ምን ፈለግሽ?
‹‹እንዴት ምን  ፈለግሽ ?ስራ ቦታ እኮ ነኝ፡፡ እየጠበቅኩህ ነው ..ወደቤት ውሰደኝ እንጂ?
‹‹አልችልም እዛው እደሪ…››
‹‹አይ አሁኑኑ ናና እቤት ውሰደኝ….ደግሞ  ብቻዬን ማደር እፈልግም››
ደሙ ተንተከተከ‹‹.ሴትዬ እዛ ገስት ሀውስ ውስጥ ተከራይተው ብቻቸውን የተኙ ወንዶች የሉም..?››
‹‹አሉ ምነው?››
‹‹እያንኳኳሽ ከመሀከላቸው የቆመበት ወንድ  ካለ ጠይቂና  እሺ ካለሽ አብረሽው ተኚ››ጠረቀመባት፡፡
15 ደቂቃ በኃላ መልሳ ደውለች….አሁን ከቁጥጥር ውጭ እየወጣ ነወ…‹‹.አንቺ አትሰሚኝም እንዴ …አንደትደውይልኝ አልልኩሽም …››
ከቅዱሙ ቀዝቀዝና ልስልስ ብላ ‹‹..እኔ አይደለሁም ውቢት መጥታ ውለጂው እያለችኝ ነው….››
‹‹ስርሽ ነች አሁን?››
‹‹አዎ ስሬ ነች….ስልኩን ላውድ ላይ አድርጊው››
‹‹እሺ ያው እየሰማች ነው ላውድ ላይ አድርጌዋለው››
‹‹ወቢት .››.አቤት
‹‹ትብለፅ…››አቤት
‹‹ሁታችሁም እየሰመችሁኝ ነው››
‹‹አዎ መንጌ …ሁለታችንም እየሰማንህ ነው፡፡
አሁን ሁለታችሁም ተያይዛችሁ ወደትልቁ ቤት ሄዱና…ከዛ ካናዳ ላለው ባላችሁ በቪዲ ኮል ደውሉለትና አውሩት…ከዛ እርስ በርሳችሁ ተቃቅፋችሁ ተኙ…ካለበለዚያ ወንድ ገዝታችሁ ግብ…እንደፈለጋችሁ..ከሁን በኃላ ግን አንዳችሁ ብትደውሉልኝ..ያላችሁበት መጥቼ ግንባራችሁን ነው የምፈረክሰው…ጠረቀመባቸው…..ከዛ ወዲህ አልደወሉለትም…ተንፈስ አለ፡፡
ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ በስልኩ ሚሴጅ ደረሰው…፡፡
‹‹ሰውዬው አብረን ካላደርን ብሎ ሙጭች አለ….እስከአሁን ምንም የረባ ነገር አላገኘሁም….የምናድርበት ቤርጎ ቁ-202 ነው…አትጠብቀኝ ወደቤት ሄድ..ጥዋት እንገናኛለን፡፡››የሚል መልዕክት ላከችለት፡፡
በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለበት አሰበ… ስልኩን አወጣና ደወለ….
‹‹ሄሎ  የሆነ ስራ ነበረኝ››
‹‹በስልክ ማውራት አልችልም…አሁኑኑ በምልክልህ አድርሻ ና እና አግኘኝ፡፡››
አዎ ሰውዬውን ማሳፈን እንዳለበት ወስኗል…ትዕግስት .እስከ ጥዋት ድረስ ስለአሮራ ምንም ፍንጭ እና ተጨባጭ ነገር ካላመጣችለት ሰውዬውን ያሳፍነውና አንድ ስርቻ ወይም ድብቅ መጋዘን ውስጥ ወስዶ በማስገረፍ በገዛ አንደበቱ በግድ እንዲናዘዝ ያደርገዋል…ቢያንስ እሬሳዋን ያልሆነ ቦታ ጥሎት ከሆነ ያንን ሰብስቦ በክብር እንድትቀበር ያደርጋል….የሰውዬውን ቅሌትና ወንጀልም ሀገር እንዲያውቅ ያደርጋል…ግን ለመንግሰት አሳልፎ አይሰጠውም….አደባባይ ላይ ይሰቅለዋል….እና እሬሳው እንዲቃጠል ያደርጋል አዎ ውሳኔው እንደዛ ነው፡፡
ትእግስት እና አቶ ግርማ የተከራዩበት ክፍል እንደገቡ ነበር ሊከመርባት የፈለገው.."ቆይ ግረምሽዬ የት ይሄድብሀለው..ገና መጠጡን አልጠገብኩም..ትንሽ እየጠጣን እናውራ "አለችና አረጋጋችው።
"የእኔ እመቤት አንቺ ያልሽው ሁሉ ይፈጻማል" አለና ሶፋው ላይ ዘጭ ብሎ ተቀመጠ…ብርጭቆውን አነሳችን ውስኪውን ቀድታ አቀበለችው..ተጎነጨለትና አስቀመጠው..ለራሷም ቀዳችና ከጎኑ ቁጭ አለች፡፡
ከእሱ ዞር እንደማለት አለችና ስልኳን ርከርድ ላይ በማድረግ ወደእሱ ተጠግታ ተቀመጠች።
"ከአሮራ አኮ አንድ ቀን ብቻችንን ከከተማ ወጥተን ለመዝናናትና እንዲህ ዘና ለማለት ቃል ገብታልኝ ነበረ….
‹‹እርሺው….ከዛሬ በኃላ ከእሷ ጋር ለማድረግ ያሰብሽውን ከእኔ ጋር ነው ማድረግ የምትችይው››
‹‹እሱ እንኳን እውነት አይመስለኝም….ስትመጣ ቃሏን ትጠብቃለች…እንደውም ጨበራጩርጩራ ወይም ወንጪ ነው ይዛኝ የምትሄደው ››
‹‹ካልመጣችስ…?››
‹‹ካልመጣች ማለት?እንዴት ላትመጣ ትችላለች?››
‹‹እውነቱን ንገረኝ ካልሺኝ .. እዛው ሰዊድን መኖር ይሻለኛል እያለች ነው….እኔም ልፍቀድላት  ወይስ ተመለሺ ልበላት ?እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገብቼለው››
‹‹እንዴ ስራዋስ? እዚህ እኮ በጣም ታዋቂና እና ዝነኛ እየሆነች ነው…ጥሩ ኑሮ ነው የምትኖረው ...ምን አጥታ ነው ሰው ሀገር ልኑር የምትለው.?.››
‹‹እኔም እንደዛ ነበር ያልኳት ….ግን ያው እናንተ ሴትች አንዳንዴ አመላችሁ አስቸጋሪ ነው….ትምህርት እማራለሁ..ምናምን እያለች ነው››
‹‹ያንተ  የክለብ ስራ ራሱ በተወሰነ መጠን መቀዛቀዙ አይቀርም››
‹‹ለጥቂት ጊዜ አዎ…ግን መፍትሄ አላጣለትም››
‹‹እስቲ አሁን ደውልላትና አገናኘኝ…ሀሳቧን ላስቀይራት እችላለው.፡፡››
‹‹በዚህ ሰዓት…..?›
‹‹ምነው በዚህ ሰዓት እነሱ ጋር ቀን አይደለ….?›
‹‹ቢሆንም መደወል አልችለም…እኔ ስፈልግ ደውልልሀላው..እየደወልክ የምትጨቀጭቀኝ ከሆነ ስልኬን አጠፋለው ብላኛለች…..ስልኳን ካጠፋች ደግሞ ማናችንም ልናገኛት አንችልም…ተይ ባክሽ የእሷ ነገር ከባድ እየሆነብኝ ነው…ለዘላለም ላጣት ነው መሰለኝ…. ብታይ  ጭንቅ ብሎኛል..አሮራ ተመልሳ የምትመጣ አይመስለኝም››ያዘነ መስሎ አንገቱን አቀረቀረ
‹‹ቆይ ጋርዶቾ አብራዋት አይደል የሄዱት››
‹‹ወይ አነሱን እኮ አልፈልጋችሁም ብለቸው አሰናብታቸዋለች… ነገ ወይም ተነገ ወዲያ ሊመጡ እየተዘጋጁ ነው፡፡ትእግስት ተስፋ እየቆረጠች መጣች….አሮራን ገድሎ ሳይቀብራት እንዳልቀረ አሁን ወደማመኑ ላይ ነች።
"አሁን ለሊቱን ሙሉ ስለአሮራ እያወራን እና እየተከዝን እናድራልን ወይስ ስለራሳችን እናውራ…?"አላት በመሠላቸት
ወይ ያው ታውቃለህ..አይደል የእንጀራ ጉዳይ ሆኖብኝ ነው…..እሷ ከሌለች እኮ እኔም ስራ የለኝም.."
"አንቺ እኮ ከዘሬ ጀምሮ ስራ አያስፈልግሽም…"
"እና….ድንጋይ ነው የምበላው
"አይ ፍቅር ነው የምትበይው…ከዛሬ ጀምሮ የእኔ ልዬ ረዳት ሆነሽ ተቀጥረሻል…ደሞዝሽም በእጥፍ ይሆንልሻል…"አላት በኩራት ተወጣጥሮ።
"እና ልደሰት?"
"ተደሰቺ…ትንሽ ቆየት ብለን ደግሞ  እናሰድገዋለን….እንጋባ ይሆናል....ዋናው አንቺ ብቻ ጥሩ ተንከባካቢ ሁኚ፡፡"
አንጀቷ እያረረ በጥርሷ ግን እየፈገገች"በጥም ነው ምንከባከብህ እንጂ "አለችና ተንጠራርታ ጉንጩን ስማ "መጣሁ እየጠጣህ ጠብቀኝ" ብላ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባች የሻወሩን ውሀ ለቀቀችና ስልኳን ከፍታ የቀዳችውን የድምፅ ቅጂ ቀጥታ ለመንግስቱ ላከችለት፡፡
🍎🍎🍎
መንግስቱ መልዕክቱ ሲድርሰው የገዛ መኪና ውስጥ ክንዴ ከሚባል በእስር ቤት ቆይታው አብሮት ታስሮ የነበረ  አንድ  የጋንግስተር ብድን መሪ ጋር ነበር።…ገቢናውን ከፍቶ ወረደና  የተወሰነ ራቅ ብሎ ከፈተው…. አዳመጠው…. መልሶ ከፈተው አደመጠው….ወደመኪናው ተመልሶ መግባት አቃተው…መቼም ዳግመኛ አሮራን እንዳማያገኛት ገባው፣….አሁን ለእሷ ሊያደርግላት ሚችለው አንድነገር ቢኖር ሊበቀልላትና በሆነ ስርቻ በግፋ የፈሰሰ ደሞን በሌላ ደም ማጠብ ነው፡፡
👍795👎3👏2😁1
እንደምንም የመኪናውን ገቢና ከፍቶ ገባ…".ፖሊስ ሆነ ሌላ ሰው ማይደርስበት በጣም ድብቅ ቦታ እንድታዘጋጅልኝ እፈልጋለው..ያንን ማድረግ ትችላለህ?"ሲል ጠየቀው
"ቀላል ነው…"
"በጣም ታማኝና ብቃት ያላቸው ከአራት እስከ ስድስት  ሰዎች እፈልጋለው… ከዛ አንድ ሰው እንጠልፋለን፡፡"
"ይልከኸውን ማዘጋጀት ቀላልን ነው፡፡ክፍያው ነው ዋናው…"አለው።
"ክፍያው አሳሳቢ አይደለም…ዋናው በብቃት ስራውን መስራት ነው…እስከነገ አስር ሰዓት ድረስ ሁሉኑ ነገር አዘጋጅና ደውልልኝ….ከዛ ቀጣዩን እንነጋራለን….መንቀሳቀሻ ብር ጥዋት አቀብልሀለው››
"ችግር የለውም"
"አደራ"
"መንጌ ታቀኛለህ እኮ.. ያልኩትን ነገር እፈፅማለው….የማልችለውን አደርጋለው አልልም›፡፡"
"አውቃለው ለዛ ነው አንተን የመረጥኩት..በል ደህና እደር"…ክንዴ ከመኪናው ወርዶ ወደራሱ መኪና ሲሔድ እሱ የራሱን መኪና አንቀሳቀሰ…እቤቱ ሲደርስ ከሊቱ 7፡20 ሆኖ ነበር።

  ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍566👏1😁1
እኔስ ኑሬዋለሁ! ሲከፋኝ ሲደላኝ!
ከንግዲህ ተወልዶ
ሰው ለሚሆን ይብላኝ።

🔘ፀጋዬ ገብረመድህን🔘
👍70🤔9👏3
#አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-37
#ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎

ትእግስት እዝራ ዝም ብሎ ስለተቀላቀላቸው ግር ብሏት‹‹ደህና ነህ ጋሽ እዝራ?››ስትል ጠየቀችው።
‹‹እንዴት ደህና  እንደምሆን  ጠበቅሽ?….አሮራ ወደ ውጭ አልሄደችም ማለት ምን ማለት ነው..?ካልሄደች….የት ተሰወረች?››
‹‹እሱን የሚያውቀው ወንድምህ ብቻ ነው፡፡››መንግስቱ መለሰለት፡፡
‹‹ጎረምሳው ምን ለማለት ፈልገህ ነው?…አባቷ ምን ያደርጋታል ብለህ አሰብክ?››
‹‹እኔ እንጃ…አኔ ማስበው ምንም ሊያደርጋት እንደሚችል ነው ፡፡››
‹‹ተሳስተሀል…ወንድሜ አሮራን ከልጁ በላይ ነው ሚወዳት…እርግጥ አንተን ለአመታ አሳስሮሀል ..በዛም ቂም እንደያዝክበትና ሰለ እሱ ጥሩ ልታስብ እንደማትችል አውቃለው….።እረዳሀለውም…።አንተን  ብቻ ሳይሆን በእሷ ዙሪያ የሚያንዣብቡ ብዙ ጎረምሶችን አስደብድቧል ፤ጎድቷቸዋል ወይም ልክ እንደአንተ አሳስሯቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄን ሁሉ የሚያደርው ግን እሷን ከጥቃት ለመጠበቅና የማይሆን ሰው ላይ እንዳትወድቅ አብዝቶ በመጨነቅ ነው…..፡፡ እርግጥ እንደዛ አይነት አካሄዱን እኔ ፈፅሞ አልደግፈውም…ብዙ ጊዜም ተጣልተንበታል…ግን እሷን ለመጉዳት ብሎ እንደማያደርገው አውቃለው….ምን ነካህ አባቷ እኮ ነው››
ትግስት ብልጨ አለባት‹‹አይደለም...ማለቴ እሱ አባቷ ሊሆን አይችልም››
እዝራ አፍጥጦ አያት
‹‹ምን ለማለት ፈልገሽ ነው….?የስጋ አባቷ አይደለም ግን ደግሞ ከህፃንነቷ ጀምሮ ተንከባክቦ አሳድጎታል ፡፡ትምህርት ቤት እያመላለሰ አስትምሯታል….ኮትኩቶ ባለሞያ ቀጥሮ ድምፃን እንዲሞረድ በማድረግ አሁን ምታውቋትን አይነት ድምጻዊ እንድትሆን አድርጎታል ….ታዲያ ወላጅ አባቷስ ቢሆን ከእዚህ በላይ ምን  ሊያደርግላት እንዴትስ ሊያሳድጋት ይችል ነበር…?ሁለቱም ላይ ተሳስታችኋል በሚል ስሜት አፈጠጠባቸው፡፡
ትዕግስት "እንግዲህ ሁለታችሁም በተረጋጋ ስሜት የማሳያችሁን እዩ ..››አለቸና ስልኳን መሀከላቸው አድርጋ ቪዲዬውን አጫወተችው….
እርቃን የተጣጠፈ ቦርጭ ያለው የግርማ ሰውነት…ሽንቅጥቅጥ ያለ ጠይም ለጋ የአሮራ ሰውነት ሰፊ ነጭ አልጋ ልበስ የተነጠፈበት ግዙፍ አልጋ…ቪዲዬ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የሚታዩ ናቸው፡፡ግርማ እጁን ሰዶ ጡቶቾን ሲጨምቃቸው ይታያል…እጆቹን ሳያነሳ ወደ ከንፈሯ  ሄደና ጎረሳት…መንግስቱ ትንፋሽ እያጠረው ነው…..
አሮራ ግርማን  ከላዮ ላይ ገፍትራ በጥፊ ታልሰዋለች በሚል ምኞት እየተጠባበቀ ነበረ…እየተመለከተ ያለው ግን ተቃራኒውን ነው፡፡እያየ ያለው እንደዛ አይደለም…እጇቾን በአንገቱ ዙሪያ ጠመጠመችና እጇን ወደ ብልቱ  ልክ የጥዋት  ፀሀይ እየሞቀ እንዳለ አራስ ልጅ በዝግታና  በቄንጥ ታሽልት ጀመር…የእሷ እጅ ሲያርፍበት እርዝመቱም ሆነ ውፍረቱ ሲጨምር ያስታውቃል…
መንግስቱ ቪዲዬው እስኪያልቅ  ለማየት ዪያስችል አቅም አጣ….ጭንቅላቱን ያዘና መቀመጫውን ለቆ ወደሽንት ቤት ተንደረረ….. ሊያስመለልሰውም ሊያስቀምጠውም መሰለው….ጉሮሮውንም የሚቧጥጠው ነገር አለ…..ተንርድሮ ፊት ለፊት ያገኘው አንዱ መፀዳጃ ክፍል ገባና በላዩ ላይ ጠረቀመው፡
እዝራ እንደደነዘዘ ነው…ምንም አይነት የሰሜት ለውጥ እየታየበት አይደለም….ዝም ብሎ በእርጋታ የተከፈተለትን ቪዲዬ እያየ ነው..አሁን ሁለቱም እርስ በእርስ ተቆላለፈፈው እየተጮጮሁነው…..ትዕግስት የመንግስቱ  ሁኔታ ስላሳሰባት ስልኩንም ሆነ እዝራን ባሉበት ትታ ወደመንግስቱ ሄደች….
መንግስቱ እንደምንም እራሱን ለማረጋጋት ከወሰነ በኃላ ስልኩን አወጣና ደወለ…
‹‹ክንዴ…ሰውዬውን እየተከታተላችሁት ነው?…›››ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ …በቃ ይታፈን….አዎ ዛሬውኑ ከተቻለ አሁኑኑ››ትዕዛዙን አስተላለፈ…
‹‹እሺ በቃ…ወስዳችሁ ቦታው ላይ ስታደርሱት ደውሉልኝ…ወዲያው እመጣለው..››ስልኩን ዘጋው፡፡
‹‹ያለበት መፃዳጃ ቤት ተንኳኳ…ሲከፍተው ትግስት ነች…ወጣና አልፏት ሄደ …በዝምታ ከኃላው ተከተለችው፡፡ ሲደርስው እዝራ የሚያየውን ቪዲዬ  ጨርሶ ሙሉ የጅን ጠርሙስ በእጁ ይዞ ከነጠረሙሱ እያንቀደቀ እየጠጣ ነው፡፡ሁለቱም ወደየቦታቸው ተመለሱና ቁጭ አሉ፡፡
መንግስቱ በምልክት አሰታናጋጇን ጠራት…ስትመጣ….ሙሉ ብላክ ሌብል ከሁለት ብርጭቆ  ጋር አዘዛት…ትእግስት ሞባይሏን ከነበረበት ቦታ ወደራሷ አንሸራተተችና ከፍተችና ሰዓቱን አየች ..ከረፋዱ 5፡10 ይላል…ፈገግ አለች፡፡
ሰባት ሰዓት እስኪሆን ማንም ማንንም አላናገርነበር….ሁሉም መጠጣቸውን እየተጋቱ ሀሳባቸውን እያመኘዠዘጉ ነበር፡፡
የመጀመሪያውን አረፍተ ነገር የተናገረው እዝራ ነው‹‹መንግስቱ››
‹‹አቤት ጋሽ እዝራ››
‹‹ሽጉጥ አለህ…?››
‹‹አዎ››
‹‹በአንተ ስም የተመዘገበ ካልሆነ ታውሰኛለህ…ወንድሜን ከገደልኩበት በኃላ መልስልሀለው..ካልሆነም ሌላ ግዛልኝ…ብሩን እኔ ከፍላለው››

ትዕግስት አፍጥጣ አየችው..አይኑ ደም ለብሷል…የግንባሩ ስሮች ሁሉ ግትርትር ብለዋል…የተነገረው ሁሉ ከልቡ እንደሆነ እልተጠራጠችም…ፊቷን ወደ መንግስቱ አዞረች….ተመሳሳይ ፊት ገፅታ ነው የሚታያት …ሁለት በበቀልና በመጠጥ የሰከሩ ወንዶች መሀከል ቁጭ  ብላ እየተቁለጨለቀጨች መሆኗን ማመን አልቻለችም‹››
‹‹ጋሽ እዝራ አይዞህ ለእዛ አታስብ…ባይሆን እድር ምናምን ካለው እንዲዘጋጁ ንገራቸው… ሌላው ለእኔ ተውልኝ…ለአሮራ መበቀል የእኔ ሀላፊነት ነው፡፡››
‹‹እናንተ ሰዎች ምን አልባት በህይወት ኖራ የሆነ ቦታ ደብቋት ወይም ቆልፎባት ከሆነ እኮ ችግር ውስጥ እንገባለን፡፡ እናንተ  ከገደላችሁት የሚፈጠረውን አውቃችኃል…በተዘዋዋሪ እሷንም ገደላችኋት ማለት  እኮ ነው››
‹‹አይ ...ያ አይከሰትም…ከመሞቱ በፊትማ ሁሉን ነገር እንዲናዘዝ ይደረጋል…ከገደላትም የት እንደቀበራት ወስዶ ያሳየኛል…ከደበቃትም ካደበቀበት ቦታ አውጥቶ ይሰጠናል..››
‹‹ካልገደላት አትገድሉትም አይደል?›ትእግስት በማፈራረቅ ሁለቱንም በየተራ እያየች በመለማመጥ ጠየቀቻቸው።
ሁለቱ ወንዷች እርስ በርስ ተያዩ…።ለመናገር አሁንም እዝራ ቅድሚያውን ወሰደ‹‹አይ ይሄ አውሬ መሞት አለበት እኔ ምንም ሆነ ምንም እንዲሞት ነው የምፈልገው››
‹‹በቃ ይሞታል››ተስማሙና ብርጭቆቸውን አጋጩ።እና ሁሉም ወደገዛ ሀሳባቸው ተመለሱ።

የሠው ልጅ ልብ እንዲህ ቦታዋን ለቃ ብዙ ሴንቲ ሜትሮች ወደታች ዝቅ ትላለች እንዴ?እንደዛነው መንግስቱን  የተሠማው።
👍574👏3🥰2