#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....ዲላ ሆስፒታል ውስጥ አንድ አነጋጋሪ የሆነ ክስተት ተፈጠረ፡፡ ሰበቡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከየጤና ተቋማቱ ነርሶች አወዳድሮ ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ በጤና መኮንንነት ለማሰልጠን ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ዲላ
ሆስፒታል የተመረጠውን ነርስ የማውቅ ውጤት ነው፡፡ የመወዳደሪያው ዋንኛ
መስፈርት የአገልግሎት ዘመን ሲሆን በማስታወቂያው ላይ የተጠየቀው አነስተኛ
የአገልግሎት ዘመን አምስት ዓመት ሆኖ ሳለ የተመረጠው ነርስ ግን ሦስት ዓመት እኳ ያልሞላው ሆኖ ተገኘ፡፡ ይህ ሁኔታ እንኳንስ መስፈርቱን የሚያሟሉ ነርሶችን
ውድድሩ የማይመለከታቸውንም የሆስፒታሉ ሠራተኞች ሁሉ ክፉኛ አስቆጫቸው።
ተመራጩ ነርስ የውድድሩን መስፈርት ካለማሟላቱም በላይ በሆስፒታሉ ውስጥ የሙያ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቀናት እንኳ እጅግ የተወሰኑ ነበሩ።
በአውራጃው የወጣቶች ማህበር ዕህፈት ቤት ውስጥ የአንድ ዘርፍ ሃላፊ በመሆኑ በመደበኛ ስራው ላይ አዘውትሮ አይገኝም። ከጤና ባለሙያነቱ ይልቅ ፖለቲከኛነቱ
ያመዝናል። ከዚሁ ማንነቱ የተነሳ በሠራተኞቹ ዘንድ አይወደድም፡፡ ጆሮ የሚል ቅጽል ስም ወጥቶለት ሰዎች ሁሉ ይሸሹታል። እሱ ባለበት ቦታ ወሬ አይሞከርም፡፡
እንዲያውም ወደ ሆስፒታሉ ብቅ ባይል የብዙ ሠራተኞች ፍላጎት ነው፡፡ ዛሬ ለከፍተኛ የሙያ ስልጠና የተመረጠበት ሁኔታ ቢያስቆጫቸውም በዚህ ሰበብ
ከመሀላቸው በመውጣቱ የተደሰቱም አይጠፉም።
ለአስቻለው ግን ይህ አይዋጥለትም፡፡ ጆሮ ለሁለትና ለሦስት ዓመታት ከአካባቢው ገለል ቢልም ኮርሱን ሲጨርስ ይበልጥ አብጦ እና ተኮፍሶ መመለሱ እንደማይቀር ይገነዘባል። የእሱ ጭንቀት ጆሮ በማይመለከተው ውድድር ውስጥ
ገብቶ ጭራሽ አሽናፊ የሆነበት ሁኔታ ነው፡፡ ፍላጎቱም የራሱን መብትና ጥቅም ለማስከበር መንቀሳቀስ ነው:: ይህን ጥረት ለብቻው ከማድረግ ይልቅ እንደ እሱ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ለማስተባበር ምክሮ ነበር፤ ነገር ግን አልተሳካለትም፡፡ሁሉም የሰጡት ምላሽ ማን ሊሰማኝ? ምን ለውጥ ሊመጣ? ምን ህግ አለና?...ወዘተ የሚሉ ተስፋ አስቆራጭ ቃላቶችን ነበር፡፡
ይህ ዓይነቱ የሰዎች አመለካከት የአስቻለው የዘወትር ራስ ምታቱ ነው። ገዢዎች በህዝብ ላይ ከሚፈጽሙት ግፍና በደል የበለጠ የዜጎች ልበ ሙትነት ያበሳጨዋል፡፡ መብትና ጥቅምን በፈቃደኝነት አሳልፎ የመስጠት ጅልነት
ያንገበግበዋል። አሁን ሲቆሏት ኋላ እንደሚቆረጥሟት እንደማታውቅ ጥሬ መብቱ ሲረገጥ፣ ጥቅሙ ሲጨፈለቅ ዝም ብሎ የሚመለከት ሰው አንጀቱን ያቆስለዋል።ሰው እንዴት ሰሚ በሌለበት፣ ህግ በማይከበርበት፣ ግፍና በደል በተንሰራፋበት፣
አድሎና ጭቆና በነገሰበት፥ አቤት ቢባል ፍትህ በማይጎኝበት ሥርዓት ውስጥ ለመኖር ፈቃደኛ ይሆናል? በዚህ ሁኔታ ውስጥ እየኖረስ እንዴት ስው ነኝ ብሎ
ያስባል? ይላል ዘውትር። ምንም እንኳ ሰውን ሁሉ ለዚህ ዓይነቱ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ዝቅጠት ያበቃውን ታሪካዊ መነሻ የሚያውቀው ቢሆንም ግን እስከ
መቼ? ለሚል ጥያቄ መልስ እያጣ በእጅጉ ያዝናል፣ ይበሳጫል፡፡
ያም ሆኖ አስቻለው ወትሮም እንደሚያደርገው ሁሉ የበኩሉን ድርሻ ከመወጣት ወደ ኋላ አላለም። በዕለተ ሐሙስ ከጠዋቱ አንድ ሠዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ባለው ፈረቃ ስራውን ሲያከናውን ውሎ ወዲያው ወደ ቤቱ መሄድ አልፈለገም፡፡ በቀጥታ ወደ ሆስፒታሉ የአስተዳደር አገልግሉት ሃላፊ ቢሮ አመራ፥ ወደ ባርናባስ። በሩን ከፈት አድርጎ ወደ ውስጥ አየት ሲያደርግ ባርናባስ
ወየሶ በጠረጴዛው ላይ አጎንብሶ ይጽፋል፡፡ አለባበሱ ያው የተለመደው ነው፡፡ በሩ ሲከፈት ሰምቶ ዞር ሲል አስቻለው የበሩን እጀታ እንደያዘ በር ላይ ቆሞ አየው፡፡
«አቤት!» አለው ዓይኑን በአስቻለው ላይ እንደተከለ፡፡
ላነጋግርህ ፈልጌ ነበር፡፡»
ባርናባስ ፈጥኖ መልስ አልሰጠውም። ለአፍታ ያህል መልከት ካለው በኋላ እጅግ በቀዘቀዘ ስሜት ትችላለህ» አለና በእጁ ወደ እንግዳ ወንበር አመለከተው፡፡አስቻለው ገባ። ከእንግዳ ወንበሮች መካከል አንዷን ሳብ አድርጎ ቁጭ አለና
ባርናባስን በጥርጣሬ ዓይን ያየው ጀመር።
«ምን ልርዳህ?» ሲል ጠየቀው ባርናባስ መነፅሩን አውልቆ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ እያደረጉ፡፡
«ለእጩ ጤና መኮንንነት ኮርስ ውድድር ተመዝግቤ ነበር።»
«እህ!» አለው ባርናባስ በሾፍ አነጋገር።
«በውጤቱ አልተደሰትኩም!»
«ምን ጠብቀህ ነበር?»
«እመረጣለሁ ብዬ ነበራ!»
«እህ! ዝም ብሎ መመረጥ አለ እንዴ?»
«ዝም ብዬማ አይደለም፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከሆነ በአገልግሎት እኔ እበልጣለሁ፡፡ እንዲያውም ሁለት ዓመት ትርፍ አለኝ:: የተመረጠው ነርስ ግን ጭራሽ ከመስፈርቱ አነስተኛ መነሻ እንኳ ለመድረስ ሁለት ዓመት እንደሚቀረው አውቃለሁ፡፡ ታዲያ እንዴት ዝም ብለህ ትለኛለሀ?» ሲል ግንባሩን ቋጠር አድርጎ ጠየቀው::
ለመሆኑ በማስታወቂያው ላይ የተጠየቀው መስፈርት የአገልግሎት ዘመን ብቻ ነው እንዴ?
«ልጥፎችማ አሉ፤ ነገር ግን ዋናው መስፈርት የአገልግሎት ዘመን መሆኑን ማስታወቂያው በግልጽ አስቀምጧል።»
«ልጣፍ ስትል?» አለና ባርናባስ ዓይኑን ፈጠጥ አደረገ፡፡
«በቃ! ልጣፎች ማለቴ ነው፤ ለፍርደ ገምድልነት ምክንያት የሚሆኑ እንጂ ዋናውን መስፈርት የማያሽሩ!»
ቀይ ፊቱ የባሰ ደም መምሰል ጀመረ::
ባርናባስም ዓይኑ ፈጠጠ።
አፍንጫው ነፋ ሞሸሽ አለ። ወደ ጠረጴዛው መለስ ብሎ እጆቹን አቆላልፎ ተደገፈና
“ጉልህ እብዮታዊ ተሳትፎ ያደረገ የሚለውን መስፈርት ማለትህ ነው?» ሲል አስቻለውን ጠየቀው።
«ያ ይኼ አላልኩም፡፡ ግን ከሙያው ጋር የማይሄዱትን በሙሉ ማለቴ ነው::» አለው አስቻለው እሱም ጠረጴዛውን እየተደገፈ፡፡
ሁለቱም ተፋጠጡ:: ዓይን ማን ይስበር? ማን ይስበር? በሚል የሚጠባበቁ ይመስላሉ። ባርናባስ እንደገና ወደ ኋላ ወንበሩን ተደግፎ በረጅሙ ተነፈሰና
«ለማንኛውም አንተና የተመረጠው ጓድ በምንም መንገድ አንድ ልትሆነ አትችሉም።» አለው፡፡
«ምን አገናኝቶን?» አለ አስቻለው ፈርጠም ባለ አነጋገር፡፡ «የኔስ ችግር ይኸ አይደል?» አለና ባርናባስን አከታትሉ ይመለከተው ጀመር።
«ታዲያ ይኸን ካወቅህ ሌላ ምን ፈለክ?»
«እኔ እያለሁ እሱ እንዴት ተመረጠ ብዬ ነዋ!»
«ባላችሁ ልዩነት ምክንያት
ውድድሩ እኮ ለባለሙያነት እንጂ ለካድሬነት አይደለም አቶ ባርናባስ»
ባርናባስ ድንገት ቁጥት አለና «ጓድ በል! ደሞ የምን አቶ ነው?» በማለት በአስቻለው ላይ አፈጠጠ፡፡
አስቻለው ሳያስበው ፈገግ አለና ረጋ ለስለስ ባለ አነጋገርን “ ጓድ የሚለው ቃል እኮ በዓላማና
በተግባራቸው የሚመሳሰሉ
ግለሰቦች የሚጠራሩበትና
የሚሞካሹበት ቃል ነው:: ታዲያ እኔና አንተ…» ብሎ ሳይጨርስ ባርናባስ አቋረጠው፡፡
«የመጣህበትን ጨርሰሃል?»
«አልጨረስኩም!»
«ምን ቀረህ ደግሞ?»
«አመራረጡ ትክክል ስላልሆነ እንደገና ይታይ ነው የምለው! በዚህ ላይ ያለህን ኣስተያየት ስጠኝና እንጨርስ።» አላ አስቻለው ፊቱ በብስጭት ልውጥውጥ እያለ።
«በቃ! ጓዱ ባበረከተውና እያበረከተ ባለው አብዮታዊ አስተዋጽኦ ምክንያት

👍3❤1
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
...እሷም አያቷም ታጥበው እንደተመለሱ፣ ራት በልተው በየክፍላቸው ገብተው ተኙ።
ወለተጊዮርጊስ፣ ጠዋት ከእንቅልፏ ስትነቃ የት እንዳለች ግራ ገባት።ቀስ በቀስ ጐንደር ቤተመንግሥት፣ እንግዳ ማረፊያ ክፍል ውስጥ መሆኗ ተገለጠላት። በመስኮቱ ቀዳዳዎች የገባውን ብርሃን አይታ ፀሐይ መውጣቷን አወቀች። አርፍዳ እንደነቃች ገባት፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ገብቷት እዛው አረፍ ብላ ቆየች። ሲሰለቻት ተነስታ ስትወጣ፣ በር ላይ ቆመው የእሷን መውጣት የሚጠባበቁ ሁለት
ደንገጡሮች አያቷ ወዳሉበት ክፍል ወሰዷት።
አያቷ መስኮቱን ከፍተው አልጋው ላይ ጋደም ብለው የጸሎት
መጽሐፍ ያነባሉ። ስትገባ መጽሐፉን አስቀምጠው፣ “አድረሽ ነው? ሲሏት ደሕና ማደሯን ለመግለጽ እግራቸው ላይ ተጠመጠመች።በይ ተነሽ አሏት፣ ስሜታቸው ተነክቶ። ትንሽ እንደቆዩ ደንገጡሮቹ መጡላቸው። መፀዳጃ ቤት ወስደዋቸው ሲመለሱ ቁርስ አደረጉ።
ዮልያና ያረፉበት ክፍል ተመልሰው ስለ ምሳው ተወያዩ።
“ዛሬ እንግዲህ ኸጃንሆይ ጋር ማድ ምቀርቢበት ቀን ነው። እናም የነገርሁሽን ሁሉ ልብ እንድትይ። እንደገባሽ ኸደሽ በቅጡ አጎንብሰሽ እጅ ትነሽና እግር ትስሚያለሽ። ተቀመጭ እስቲለሽ ትጠብቂና ያመላከቱሽ ቦታ ኸደሽ ትቀመጫለሽ...”
የጀመሩትን ሳይጨርሱ ሁለት ደንገጡሮች በር ላይ ሆነው ለጥ ብለው እጅ ከነሱ በኋላ፣ አንደኛዋ፣ “እመቤቶቼ እንፋሎት እጥበት
እንኸዳ” አለቻቸው።
ወለተጊዮርጊስና አያቷ በደንገጡሮቹ ተከታይነት የአፄ ፋሲልንና የታላቁ ኢያሱን ቤተመንግሥታት ከኋላቸው ትተው ወደ ታች ወረዱ። የጻድቁ ዮሐንስን ቤተመዛግብት በግራ በኩል፣ ቤተመንግሥታቸውን
ወለተጊዮርጊስ በወሬ እንጂ በአካል አይታቸው የማታውቃቸውንና በስተቀኝ አልፈው፣ አንበሶቹ ቤትጋ ሲደርሱ አያቷ፣ “አንበሶች” ሲሉ ጠዋት ላይ ሲያገሱ የሰማቻቸውን አንበሶች ለማየት ቆም አለች። በአድናቆት ካስተዋለቻቸው በኋላ፣ከአንበሶቹ ቤት ጀርባ ያለውን የሣልሳዊ ዳዊትን የሙዚቃ አዳራሽ አሁንም በቀኝ በኩል ትተው ወደ ፊት አመሩ። ወለተጊዮርጊስ በየቤተመንግሥታቱ መተላለፊያ ላይ የተሰደሩት ወታደሮችና በየበሩ ላይ የቆሙት እልፍኝ አስከልካዮች
ቁጥር አስገረማት፣ ከእነሱ ጋር የመፋጠጥ ያህል ተሰማት። በመጨረሻም ቁመቱ አጠር ያለ ነገር ግን ሰፋ ያለ ግንብ ውስጥ ገቡ።
“እመቤቶቼ እኼ ንጉሦቹና እቴጌዎቹ እንፋሎት ሚገቡበት ነው” አለቻቸው፣ ከደንገጡሮቹ አንዷ ። ቀጥላም፣ “አጤ ፋሲል ናቸው ያሠሩት። እኼኛው የእቴጌዎቹ ነው። የንጉሦቹ በያኛው በኩል ነው።ልብሳችሁን ታወልቁና እነዝኸ መንጠቆዎች ላይ ትሰቅላላችሁ።ጌጦቻችሁን ደሞ እነዝኸ ውስጥ ታኖራላችሁ” አለቻቸው፣ ትንንሾቹን የድንጋይ ፉካዎች በሌባ ጣቷ እያመለከተቻቸው።
“በዝኸ በር ግቡና ኸነዛ ዳርና ዳር ያሉ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጡ። ያ ሚጨሰው አረግ እሬሳና ጦስኝ ነው። እኛ ከውጭ ሁነን እንጠብቃለን” ብላቸው ከሌላዋ ደንገጡር ጋር ተያይዘው ወጡ።
ወለተጊዮርጊስና ዮልያና ጌጦቻቸውን አስቀምጠው፣ ልብሳቸውን አውልቀው የተባለው ክፍል ውስጥ አጎንብሰው ገብተው ተቀመጡ።ክፍሉ መሃል ላይ የተደረደሩት ድንጋዮች ሲግሉ፣ “አየሽ ያነን ምታይውን ወናፍ በዚያች በምታያት ቀዳዳ አሳልፈው፣ ኸውጭ ሁነው
ደንጊያዎቹን ያግላሉ” አሏት።
ድንጋዮቹ ሲግሉ፣ ከውጭ በቀርከሀ ዋሽንት ውሃ ድንጋዮቹ ላይ ፈሰሰ። ላብ አጠመቃቸው። እንደመታፈን ሲሉ ከጣሪያው ላይ ያሉት ትንንሽ ቀዳዳዎች ከውጭ ተከፈቱላቸው።
“አየር እንዲገባ ቀዳዳዎቹን ከፈቱልን። አለያማ ታፍነን እንሞት
ነበር” አሏት።
ቀዳዳዎቹ ተመልሰው ተዘጉ።
“እንፋሎት ተመልሶ እንዲመጣልን መልሰው ዘጉት” አለች፣ ነገሩ
የገባት ወለተጊዮርጊስ።
“እንዲህ አይሁን እንጂ እኛም እኮ በእንፋሎት መታጠብ እናውቃለን
አሉ፣ ዮልያና።
እሷ ይህን ዓይነቱን ነገር ከእሳቸው ቀርቶ ከማንም ጋር አድርጋው
ባለማወቋ እፍረቱ አላስቀምጥ አላት። ሰውነቷ እየተሟሟቀ ሲመጣ ግን ዘና አለች። ከፊቷና ከራሷ ላይ የሚፈልቀውን ላብ አስር ጊዜ ስትጠራርግ አዩና፣ “አይዞሽ አሁን ያነን ሁሉ የምንገድ ድካም ድራሹን ነው ሚያጠፋልሽ” አሏት።
ሲጨርሱ ወደ ገላ መታጠቢያው ክፍል ሄደው ዙርያውን የተከበበ
ገንዳ ውስጥ መጀመሪያ እሳቸው፣ ቀጥሎ እሷ ታጥበው የክት ልብሳቸውን ለብሰው ሲወጡ፣ ወለተጊዮርጊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ አለምልማለች።
ዕረፍት እንዲያደርጉ ማረፊያ ክፍሎቻቸው ተወሰዱ።
ብዙም ሳይቆዩ ደንገጡሮቹ ለወለተጊዮርጊስ በእቅፋቸው ነጭ ረጅም የሐር ቀሚስ፣ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች ያጌጠ ጥቁር ካባ፣ የቆዳ ጫማ፣ ነጭ የሐር ሻሽና ከወርቅ የተሠሩ የአንገትና የጆሮ ጌጦች ይዘው መጡ። አንደኛዋ ታጥቦ የነበረውን ፀጉሯን ሾርባላት ሄዱ።ወለተጊዮርጊስ የመጣላትን ልብስ፣ ካባ፣ ሻሽ፣ ጫማና ጌጦች ግልጽ በሆነ አድናቆት አገላብጣ ስታይ፣ ጋደም ብለው የነበሩት አያቷ አይዋት።
በለጋ ዕድሜዋ እዚህ ደረጃ በመድረሷ ተደስተው እንባቸው ቀረር አለ። እንባቸው እንዳታይባቸው በነጠላቸው ተሸፍነው ፊታቸውን ወደ
ግድግዳው አዞሩ። ራሳቸውን አረጋግተው ነጠላቸውን ከፊታቸው ላይ ገለጥ አደረጉና ወደ እሷ ዞሩ። አሁንም የመጣላትን ዕቃ ታገላብጣለች።
“ጥሎሽ የመጣልሽም ኸዝኸ ይበልጥ እንጂ አይተናነስም። እሱን ልበሺ ስልሽ ለመንገድ አይሆንም ብለሽ የኔን ለበሽ። ለማንኛውም ጥሎሽ ይለቅ። አሁን እሱን አስቀምጭና ወደ ጃንሆይ ስትኸጂ እንዴት እንደሆነ አንዴ ተወጪልኝ” አሏት።
ልብሶቹን አልጋው ላይ በጥንቃቄ አኑራ፣ ክብ ዐይኖቿን ሰበር አድርጋ
በተመጠነ፣ ንግሥታዊ በሚመስል እርምጃ ወደ እሳቸው ስትጠጋ፣ “እኼ ነው የኔ ልዥ ። ያሳየሁሽን ሁሉ አረሳሽም። እንዲያውም አክለሽበታል” አሉና ጠጋ እንድትላቸው በእጃቸው ጠቆሟት። ተጠግታቸው
ስታጎነብስ፣ “እንዲህ ያለች ምሽት ኸየትም አያገኙ” ብለው ጉንጫን
መታ አደረጓት።
ቀና አለችና የእፍረት ሳቅ ሳቀች። “ስንት መልከ መልካም ወይዛዝርት
አለ በሚባልበት... ስንት የንጉሥ ዘር ባለበት አገር?” አለቻቸው።
በስጨት እንደማለት ብለው፣ “አንቺ ደሞ እንግዲህ ሰው ሚልሽን ስሚ አሉና ከተጋደሙበት ተነሥተው ተቀመጡ። ወገባቸውን በሁለት እጃቸው ይዘው፣ “የንጉሥ ዘር የሆነ ሁሉ መልክ አለው መሰለሽ? አንቺ ሁሉን አሟልቶ ሰቶሻል። ደሞ ጃንሆይ የንጉሥ ዘር ቢፈልጉ አጥተው? አንቺስ ብትሆኚ የንጉሥ ዘር ማዶለሽ? አንድ መኰንን አልገዛም ብሎ
ሲያውክ በጋብቻ ለማሰር፣ ጥቅም ለማስጠበቅ አሊያም ደሞ አመጥ
ለማብረድ ሲሉ መሰለሽ አንቺን ማግባት የፈለጉ? ወደውሽ ነው።
ትምርትም ቢሆን ዳዊት ደግመሻል። ጥፈትም ቢሆን ሚደርስብሽ የለ። የጐንደር ወይዛዝርት እኩሌታዎቹ ስንኳ ዳዊት አልደገሙም...
ይቅር ኻንቺ ሊተካከሉ... ኧረ እንዲያው ምንሽም አይደርሱ።”
“አየ እሚታዬ ልዥሽ ስለ ሆንኩ ነው እንደሱ ምትይው። ግና ኣንድ
ጥያቄ ልጠይቅሽ... ጃንሆይ ኸዝኸ በፊት አላገቡም ነበር እንዴ?”
“አግብተው ነበር እንጂ።”
“እህስ?”
“በእንዴት ያለ ወግ ተጋብተው እሷ የሠርጉ ምሽት እንደ ወጉ ግብር
አብልታ፣ እህል ውሃ ስንኳ ሳትቀምስ በጥኑ ታማ በበነጋው ሞተች።እደብረብርሃን ሥላሤ ነው የተቀበረች፤ ኸዛው እናታቸው ኻሉበት። መርዝ ነው ይላሉ። እንዴት ያለች አለላና ብርቱ ሴት ነበረች አሉ። ደማምና ብርቱ ይሆናቸዋል።”
“እንዴ?” አለች ወለተጊዮርጊስ፣ ሰውነቷን ያልታወቀ ነገር ወረር
አድርጓት። ተነስታ ቆመች። “እኔስ ፈራሁ። እኔንስ በመርዝ ቢገሉኝ?"

👍17❤1🔥1
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
ባህራም
ምጥ
ባህራም በሰኔ ወር የወደቀውን ፈተና እንደገና ለመፈተን
ማጥናት ጀመረ። የራሱ መኝታ ቤት ያረጀና የከረከሰ ሆኖ፣ ደምበኛ ጠረጴዛና ወምበር የለውም፡፡ እዚያ ማጥናት አልቻለም፡፡የዩኒቨርሲቲው ቤተመፃህፍት እየሄደ እንዳያጠና፣ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች ውር ውር እያሉ ሀሳቡን ይሰርቁታል። ከቀኙ፣ ከግራው፣ከፊቱ፣ ከኋላው ደሞ አስር፣ አስራ አምስት ፍራንክ ያበደሩት ሰዎች ያዩታል፣ ይከብዱታል። እነሉልሰገድ ቤት ሄዶ እንዳያጠና ወሬና
ጫጫታ ይበዛል። እኔ ቤት እየመጣ ያጠና ጀመር። ከሰአት በኋላ ሲኒማ እሄድለታለሁ፣ ሲያጠና ይውላል። ማታ እፅፋለሁ ወይም አነባለሁ፣ ሲያጠና ወይም የማኦ ትዜ ቱንግን መፃህፍት ሲያነብ ያመሻል፡፡ ጧት ግን ምንም ያህል አይሰራም፡፡ ወሬ እናበዛለን።
ጧት ገና ከእንቅልፌ ሳልነቃ መጥቶ፣ በቀስታ በሩን ከፍቶ
ገብቶ፣ ጠረጴዛው ዘንድ ተቀምጦ ሲሰራ ይቆያል። ስነቃ “Bon jour
እለዋለሁ። Bon jour ብሎኝ ቡና ይጥድና ስራውን ይቀጥላል።
አልጋዬ ውስጥ እንዳለሁ ትላንት የፃፍኩትን እመለካከታለሁ፤
አርማለሁ፣ እሰርዛለሁ፣ እቀዳለሁ። ሙሉ ሰአት ሲሆን ባህራም «አንድ ጊዜ ዜና ብንሰማ ይረብሽሀል?» ይለኛል፡፡ (የፈረንሳይ ራዲዮ በየሰአቱ አጫጭር ዜና ያሰራጫል) ራስጌዬ ያለችውን ራዲዮ እከፍታታለሁ። ባህራም ያፈላውን ቡና በዱቄት ወተት እየጠጣን ስለቪየትናም ወሬ እንሰማለን። ቪየትኮንግ የደፈጣ አሜሪካኖቹን አጥቅተዋቸው እንደሆን ባህራም ደስ ይለውና ደስታው
አላስጠና ይለዋል። መናገር ይጀምራል።ቬየትኮጎቹ ድል
ማድረጋቸው አይቀርም ይላል፡፡ ንግግሩ ቀስ ብሎ ወደ ኢራን
ይወሳስደዋል።ስለኢራን ሊነግረኝ ይጀምራል። ስለኢራን፣
ስለኮሙኒዝም፣ ስለማኦ ትዜ ቱንግ፣ ስለአሜሪካን ወራሪነትና
አጥቂነት፣ ስለካፒታሊዝም ስናወራ እንቆይና፡ ሙሉ ሰአት ሲደርስ
እንደገና ራዲዮ እንከፍታለን፡፡ ዜናው ያስደስተዋል ወይም
ያበሳጨዋል። ወሬያችንን እንቀጥላለን። የምሳ ሰአት እስኪደርስ እናወራለን፣ እናወራለን ማለት፣ በአብዛኛው እሱ ሲያወራ እኔ አዳምጠዋለሁ፤ እንዳንድ ጊዜ ጥያቄ እጠይቀዋለሁ፡፡ የነገረኝን
እያንዳንዱን ማታ ልተኛ ስል አንድ ትልቅዬ ደብተር ውስጥ አሰፍረው ነበር
አሁን ያንን ደብተር ሳነበው ባህራም ይታየኛል፡፡ እኔ አልጋ
ውስጥ ትራስ ተደግፌ ቁጭ ብዬ፡ እሱ በሽተኛ ሊጠይቅ የመጣ
ይመስል አጠገቤ ወምበር ላይ ተቀምጦ፣ በብልህ ቡናማ አይኖቹ
እያየኝ፣ ፀጉራም እጆቹን በብዙ እያንቀሳቀሰ፣ በወፍራም ልዝብ
ድምፁና በተሰባበረ ፈረንሳይኛው ሲያወራልኝ፣ ቁልጭ ብሎ
ይታየኛል
ወሬው አንድ መስመር ይዞ አይሄድም። ኢራን፣ ኒኮል፣
የባህራም ቤተሰብ፣ የባህራም ጓደኞች፣ ፈረንሳዮች፣ ጥቁሮች፣
ወጣት ኮሙኒስቶች የተባለ የኢራን አገር ማህበር፣ ትምህርት
ቤት፣ ሴቶች፣ ቡሽቲዎች፣ ጋዜጠኞች ብቻ ባህራም ያየውንና
የሰማውን ነገር፣ በህይወቱ የደረሰበትን ወይም በሌሎች ላይ
የደረሰባቸውን ነገር አሳዛኝ ነገር፣ አስደሳች ነገር፣ አስቂኝ ነገር፣
የሆነ ነገር ያወራልኝ ነበር፡፡ ስንቱን ብዬ ልናገረው እችላለሁ?
ጥቂቱን ብቻ ባጭሩ ላስፍረው፣ እንደ ባህራም ካንዱ ወደ ሌላው
እየዘለልኩ. እንደሚከተለው...
አሜሪካኖቹ ይወድቃሉ (ይላል ባህራም) ታያለህ፡፡ ስንቱን ህዝብ
ጨቁነው፣ ስንቱን አገር ፈትፍተው፣ ስንቱን መንግስት ገዝተው
ይችላሉ? አንድ ቀን ይወድቃሉ። እንኳን እንደነሱ ያለ ቂል ፈረስ
ይቅርና፣ እንደ እንግሊዝ ያለ ተንኮለኛ ቀበሮም ወድቋል። ተነስቶ ሌሎች ህዝቦችን
ጨቁኖ መውደቅ የሚቀርለት የለም፡፡ “አሜሪካኖችም ይወድቃሉ፡፡ ይወድቃሉ። ታይቶ የማይታወቅ አወዳደቅ ይወድቃሉ። ያን ጊዜ የአለም ህዝቦች እልል ይላሉ።
በአሜሪካ አግር ተረግጠው ደክመው እልል ለማለት ያህል አቅም ያነሳቸው ደሞ እፎይ ይላሉ
አሜሪካኖቹን መጀመሪያ
ሆ ቺ ሚን ከቪየትናም ያባርራቸዋል::ቀጥሎ እነ ማኦ ሴቱንግ ወይም ወራሾቹ ከሩቅ ምስራቅ ያስወጡዋቸዋል፡፡ ቀጥሎ እንግዲህ ማን ከየት እንደሚያስወጣቸው አላውቅም:: ብቻ እርግጠኛ ነኝ ያስወጡዋቸዋል። ይህን የሰው አገር ደም ጠጥቶ የወፈረ ቂጣቸውን በካልቾ እየመቱ “Yanked go home!
And stay honte!' (ያንኪ ወደ አገርህ ግባ እና እዚያው ቅር!»)
እያሉ ያስወጡዋቸዋል። ከሰው እድሜ በላይ በኖርኩ! አሜሪካ
ስትወድቅ ለማየት እንድችል ብቻ
ምን ማለትህ ነው? ለምን አልጠላቸውም? አሜሪካኖችን ያልጠላሁ ማንን ልጠላ ነው የነፃነትን ዋጋ እያወቅኩ፣ የተጨቆነ ህዝቤን እየወደድኩ፣ አሜሪካኖችን ካልጠላሁማ ሰው አይደለሁም ማለት ነው። ድንጋይ ነኝ ማለት ነው አሜሪካኖች አንድ የተቀደሰ ተግባር አላቸው:: ይኸውም፣ እባብ ያንዲትን ወፍ እንቁላል መጦ ጨርሶ ቅል ብቻ እንደሚያስቀርላት፣እነሱም ያንዲትን አገር ሀብት መጠው ጨርሰው፣ አፈርና ድንጋይ
ይተዉላታል። የኔን አገር ውሰድ። ዋና ሀብቷ ነዳጅ (ፔትሮል
ነው። ነዳጁን ከመሬት መጦ የሚወስደው አሜሪካ ነው
አንድ ቀን ሞሳዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ። ተነሳና የኢራን
ሀብት ለኢራን ህዝብ ነው አለ፡፡ አሜሪካኖቹ ተሳስተሀል አሉት፡፡
በቃል ሳይሆን በተግባር፣ የኢራን ሀብት ለአሚሪካ ነው፣ የኢራን
ሀብት ለኢራን ነው ካልክ ኮሙኒስት ነህ ማለት ነው አሉት።
ሲ.አይ.ኤ ልከው ገለበጡት። ሞሳዴግ ተይዞ ሞት ተፈረደበት። ግን ሽማግሌ በመሆኑ፣ የሞት ፍርዱ ወደ እስራት ተሻሻለለት። አሁንም ታስሯል፡፡ የኢራን ሀብት ለአሜሪካኖቹና ለሻህ ነው ያለ ሰው ግን ይሾማል ያሸለማል። ሻህ ማለት በነሲሩስ፣ በነዳርዩሽና በነኻሻር ያዥ ስመ ጥሩ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ኢራንን የሚጨቁን ጋንግስተር ማለት ነው:: አጋዦች አሉት። ህዝቡ ያረሰውን ለመንጠቅ የእርሻ ሚኒስትር ያግዘዋል። ህዝቡ ሲነግድ ከነጋዴው ለመቀማት የንግድ ሚኒስትር
ያግዘዋል። ለልዩ ልዩ አይነት ጭቆና ልዩ ልዩ ሚኒስትር አለው።
ህዝቡ በደስታ እንዲጨቆን፣ ማለትም ተጨቆንኩ ብሎ
እንዳያጉረምርም፣ ፀጥ የሚያሰኙ ያገር ግዛትና የፍርድ ሚኒስትሮች
አሉት
ያሻህን ሻህ ሚኒስትሮች፣ በተለይም የውጭ ጉዳይና ያገር ግዛት ሚኒስትሮቹ፣ ትእዛዛቸውን በቀጥታ ከዋሽንግተን ይቀበላሉ።
ምክንያቱም ኢራን የአሜሪካ የነዳጅ ማእድን ናት። ደሞ ኢራን
የሩሲያ ጎረቤት ስለሆነች፣ አሜሪካኖች በጣም ለኢራን
ይጠነቀቁላታል። አንድ ገበሬ ብዙ የምትታለብ ላም ብትኖረው
አይጠነቀቅላትም?
ሻህ ማለት ውሻ ነው፡፡ አሜሪካኖቹ ኢራንን አርደው ብልቷን ሲያወጡ እፉ ምራቅ እየሞላ በአይኑ ይከተላቸዋል፣ ሳምባ ወይም
ሌላ ቁራጭ ስጋ ጣል ያረጉለታል። እሱ ደሞ ህዝቡን ጨቁኖ
ይይዝላቸዋል። አየህ፣ ህዝቡ ተጨቁኖ ካልተያዘ፣ እንደ ሞሳዴግ
ተነስቶ የኢራን ሀብት ለኢራን ሰዎች ይላል። ስለዚህ አሜሪካኖቹ
ለህዝቡ የማይቆረቆር፣ ጥቂት ሚልዮን ብር ቢሰጡት የሚበቃው፣ ህዝቡን ጨቁኖ የሚይዝላቸው ገዥ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህ ነው ዙፋኑን
የሚጠብቁለት በሞሳዴግ ጊዜ ረብሻ ተነሳ፡፡ ሽህ ሽሽቶ ከአገር ወጣ።አሚሪካኖች መጥተወ «የኢራን ሀብት ለኢራን ሰዎች» የሚሉትን የሞሳዴግ ተከታዮች ፈጅተው፣ በዚያውም ያለ የሌለውን ኮሙኒስት አርደው ጨርሰው፣ አገሩን ጸት ካደረጉ በኋላ፣ ና ወደ ዙፋንህ
ተመለስ አሉት፡፡ ወደ ዙፋኑ ተመለሰ

👍22
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
ዉሃ ሆንሁ፣ የመጨረሻዉን ድንጋጤ ደነገጥሁ።
ከነበርሁበት የምድር በታቹ የሲራክ ፯ ማዕከል ወጥቼ በቅርበት ወደሚገኘዉ የድንግል ማርያም ገዳም ለጸሎት ገባሁ አንድ ያለኝ አቅም ጸሎት ነዉና፣ አሳፍሮኝ የማያዉቀዉን አምላክ በእናትህ እርዳኝ አልሁት ተንበርክኬ ከተንበረከክሁበት ተነስቼ በምሥራቅ በኩል ባለዉ የቅጽሩ
በር ልወጣ እየተራመድሁ ልክ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ ላይ ስደርስ፣ ደስ የሚያሰኝ የሕጻናት መዝሙር በጆሮዬ ጥልቅ አለ በክፍቱ መስኮት አስግጌ ወደ ዉስጥ ስመለከት፣ ሰልፍና ልብሳቸዉን ያሳመሩ ሕጻናት “ሀገሪትነ” የሚለዉን ነባር ዝማሬ በኅብረት ያጠናሉ። ለአጭር
አፍታ ከዝማሬያቸዉ ቀምሼ መንገዴን ልቀጥል እግሬን ሳነሳ አንድ በየት
በኩል እንደ መጣ ያላየሁት፤ 'ቤ መ' የሚል ኮድ ያለዉ ታርጋ የለጠፈ
መኪና ከሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ በር ጥሩንባዉን ነፋና ሲጢጥ ብሎ ቆመ። የታርጋዉ ኮድ ትኩረቴን ስለ ሳበዉ፣ በአዳራሹ እና በግቢዉ አጥር መካከል ወዳለዉ ሰዋራ ሥፍራ ተሰዉሬ የሚሆነዉን ሁሉ በሥርቆሽ መከታተሌን ጀመርሁ: አፍታም ሳትቆይ፣ ሕጻናቱን
እያስጠናች የነበረችዋ ወጣት ወደ በሩ ብቅ ብላ አየችዉና ልጆቹን
እንዲወጡ ጠራቻቸዉ። ሕጻናቱም በደስታ እየፈነደቁ ተሯሩጠዉ ወጥተዉ የመኪናዉ በር እስከሚከፈትላቸዉ ድረስ ተቁነጠነጡ።
“ኧረ ክፈቱልን” ይላል አንደኛዉ ሕጻን፣ አላዳርስ ብሎት በሩን ራሱ
ለመክፈት እየታገለ
“ስሚ ለማን እንደምዘምር አዉቀሻል ግን? ለመንግሥት እኮ ነዉ” ትላለች ሌላኘዋ ጓደኛዋን ለማስቀናት በሚመስል አኳኋን አንገቷን እየወዘወዘች።
“ለመግሥት? ኧረ አይባልም!” ብላ አረመቻት ያቺኛዋ፣ በሳቅ ቡፍ
እያለችባት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስም ጠርታ፣ መንግሥት ያለችዋን ልጅ አላገጠችባት።
አሁን ነዉ እንግዲህ መፍጠን አልሁት ለራሴ፡ ዕድሎች ከስንት አንድ
ከላይ ይወርዱልናል፣ አብዛኞቻችን ግን ራሳችን ነን የፈጠርናቸዉ› ሲባል
ሰምቼ ነበር በማዕከላችን በሲራክ ፯ ከስንት አንድ ከሚወርዱት ዕድሎች
አንደኛዉ ይኼዉ የዓይኔ ብረቱ ሥር ወርዶልኛል።
እንዴት ብጠቀመዉ ይሻላል?
ሁሉም ሕጻናት ከወጡ በኋላ መዝሙሩን ያስጠናችዋ ወጣት መብራቱን
አጠፋፍታ ነጠላዋንም በቅጡ እያጣፋች መጣች፡ ይኼ ሁሉ ሲሆን ሾፌሩ
አልወረደም አለመዉረዱ ሲገርመኝ፤ በሩንም ራሷ እንድትከፍትላቸዉ
ጠበቃት እሷ ደርሳ ስትከፍትላቸዉ ልጆቹ እሽቅድምድም ፈጥረዉ አይገቡ የለም እርስ በእርስ እየተጣጣሉ ገቡ፡ አሁን መኪናዉ ፊቱን አዙሮ ይሄዳል ብዬ ስጠባበቅ፣ ምን እንደ ረሳች እንጃላት፣ አስጠኛቸዉ ወረደችና ተመልሳ ወደ አዳራሹ ሮጣ ገባች። ይኸኔ ጥግ ለጥግ
ተሹለኩልኬ የአዳራሹን የኋላ በር በኃይል አንኳኳሁባት። ያለ ምንም ፋታ ደጋግሜ ሳንጓጓባት ብልጭ ብሎባት በእልህ ከፈተችልኝ።
“እ! ምንድነዉ?” አለች፣ በሩን በጥድፊያ ስትከፍተዉ እኔ በድንግዝግዙ
ዉስጥ ብቁለጨለጭባት የተመለሰችዉ ከበሮዉን ረስታዉ ኖሯል ለካ፣
በቀኝ ትከሻዋ አንግታዋለች ለኹለት ሰዓታት ሰመመን ዉስጥ የሚከተዉን ቅባት የረጨሁባቸዉ መዳፎቼን እያፋተግሁ ትንሽ የመዘናጊያ ፋታ ከሰጠኋት በኋላ ዘልዬ አፏን አፈንሁት፡ በቅጽበት መዝለፍለፍ ስትጀመርልኝ፤ ከበሮዉን በአንድ እጄ፣ እሷን ደግሞ
በሌላኛዉ እጄ ለመደገፍ ሞከርሁ፡ ሽርተት ብላ መሬት ያዘችልኝ፡ ዝቅ ብዬ እጄን በመሬቱ አሽቼ ቅባቱን ካረከስሁት በኋላ፣ ነጠላዋን ልክ እሷ ተከናንባዉ እንደነበር አድርጌ አጣፋሁትና ከበሮዉን አንስቼ አነገትሁት ክራሬንም በግራ እጄ አንጠለጠልሁትና መብራቱን አጠፋፋሁ፡፡
መኪናዉም ፊቱን አዙሮ ለመሄድ ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቀኝ፡ ከሾፌሩ ይልቅ ሕጻናቱ እንዳይለዩኝ የባሰ ስለ ሰጋሁ፣ ከበሮዉን ከኋላ ጭኜ፣ ጋቢና ገባሁ ብቻ የፈራሁትን ያህል ሳልቸገር፣ ወደ ታላቁ ቤተ መንግሥት ገባሁ የመኪና ማቆሚያዉ ላይ ስንደርስ፣ ሌላ ሰዉ ተቀብሎን ወደ
ግብዣዉ አዳራሽ ወሰደን በዚያ ስንደርስ ደግሞ አንዲት ባህላዊ ቀሚስ
የለበስች ሴት ተቀብላ ከመድረኩ ጀርባ ካሉት ክፍሎች ወደ አንደኛዉ
አስገባችን ክፍሉን ሳየዉ ጠበብ ያለ ቢመስለኝም፣ ስንገባበት ግን ጠብ
እንኳን አላልንበትም ሌላ ብዙ ሰዉ ቢጨመር ሁሉ አይጠብም፡ በዚያም
ላይ የመድረኩን ትዕይንት በቀጥታ የሚያስተላልፍልን ዘመናዊ
ቴሌቪዥን ግድግዳዉ ላይ ተሰቅሎበታል
አሁን ነዉ ጉዱ ከሕጻናቱ ጋር በደማቅ ብርሃን ልፋጠጥ ነዉ፡ መቼም ጥያቄ
መጠየቃቸዉ አይቀር፣ ወይ ደግሞ እንድናገር የሚያደርጉበት አንድ ነገር
አያጡም: ያስጠናቻቸዉ ወጣት እንዳልሆንሁ ሲያዉቁ ምን ያደርጉ
ይሆን? በተቻለኝ መጠን አንገቴን አቀርቅሬ ወዲያ ወዲህ እያልሁ ራሴን ባተሌ አደረግሁባቸዉ። ዓይናቸዉ ዉስጥ ላለመግባት ብዙ ተፍተለተልሁ መቆያ ክፍል የሰጠችን ደርባባ ሴት ተመልሳ መጣችና የመርሐ ግብሩ ቅደም ተከተል የሰፈረበት ወረቀት ሰጠችኝ፡ አስከትላም፣
የኛ ተራ እስከሚደርስ ድረስ የመጨረሻ ልምምድ ማድረግ ከፈለግን፣
ያለንበት ክፍል ድምፅ ወደ ዉጪ ስለማያስወጣ እዚሁ መለማመድ
እንደምንችል አሳወቀችኝ፡ ስለዚያ ገና ሳላመሰግናት፣ መቆያ ምግብ
እንድናዝዝ ጎንበስ ብላ ጠየቀችን፡ እንዲህ ያለችዋ ሽቁጥቁጥ ሴት ለሕጻናቱ ከተመደበች፣ ለዋናዎቹ እንግዶችማ እንዴት ያለ ሰዉ ሊመደብ እንደሚችል ገመትሁ። መቼም ትሕትናዋ ወደር አይገኝለትም: ምንም እንኳን ሕጻናቱ ምርጫቸዉን እየለዋወጡ ረዥም ሰዓት ቢወስዱባትም፣ከበሬታዋ ግን አልቀነስም፡ እኔም እንዲሁ ወዳፌ የመጣልኝን የባቄላ
ሾርባ አዘዝሁ።
የሕጻናቱን መዝሙር ተከትሎ መንዙማ የሚያቀርቡ ሙስሊም ሕጻናትም መኖራቸዉን ያወቅሁት ወረቀቱ ላይ የሰፈረዉን ዝርዝር መርሐ ግብር ከተመለከትሁ በኋላ ነበር ሰዓቴን ስመለhት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ይላል። በዕቅዱ መሠረት መዝሙር ለሚቀርብበት ተራ፣ ሃያ ደቂቃዎች ይቀራሉ ማለት ነዉ: ከፊቴ የተሰቀለዉ ቴሌቪዥን፣
የአዳራሹን ትዕይንት ቀጥታ እያመጣ ስለሚያሳየኝ፣ የተጠቀሱት መርሐ
ግብራት ያለ ምንም መጓተት በየተራቸዉ እየቀረቡ መሆኑን አዉቄያለሁ:
ሲንሾካሾኩ ሰምቼ በቀስታ ዞር ብል ሁሉም ሕጻናት አፍጥጠዉብኛል ዝምታየ ሽሽቴ፣ አድራጎቴ ሁሉ ገርሟቸዉ! ወዲያ ስልም ወዲህም ስል በዓይናቸዉ ይከታተሉኛል። የመጣዉ ይምጣ ብዬ ክንብንቤን ገለጥ
አደረግሁና፤ ማንነቴን በከፊል ነገርኋቸዉ።
“እንዴ?” ተባባሉ
“አላልኋችሁም? እግዚሐርያ አይደለችም” አለ አንደኛዉ ሕጻን፣ዉርርዱን በማሸነፍ።
“እሷስ?”
“እግዚሐርያስ?”
"በጥያቄ አካለቡኝ"
“እግዚሐርያ እኮ ድገት አሟት ተተኪልኝ ብላኝ ነዉ” አልኋቸዉ፣ መዝሙሩን ያስጠናቻቸዉ ልጅ እግዚሐርያ መባሏን ከራሳቸዉ አፍ ስላወቅሁ ስሟን መጥራቴ ለአመኔታ እንደሚያግዘኝ በማሰብ
“ኧረ ቅድም ደህና አልነበረች? ከምኔዉ አመማት?” አለ፣ ከመካከላቸዉ
ቅድም ጀምሮ ቀደም ቀደም የሚለዉ ልጅ።
“ግድየለምቆይ፤ በኋላ በስልክ አገናኛችኋለሁ: አሁን መዝሙሩን
ለመጨረሻ ጊዜ እንለማመደዉ? የማቅረቢያ ሰዓታችን እየደረሰ ነዉ። በሉ
ተነሱ። ተነሷ” አልሁ በመለማመጥም በማጣደፍም ጭምር፣ ከዚህ በላይ
እንዳይከራከሩኝ በልቤ እየጸልይሁ፡ ክራሬን እየቃኘሁ “በሉ እሺ፤
መዝሙሩን ለመዘመር፣ በአብ በወልድ በመፈስ ቅዱስ ስም…”አልኋቸዉ፣ ፋታ ላለመስጠት እዉነትም አላሳፈሩኝም፤ ብድግ ብድግ አሉልኝ፡ ከመካከላቸዉ ትንሽ ከፍ የምትለዋ ልጅ ከበሮዉን አነሳች፡ እኔም መዝሙሩን በቅጡ የምችለዉ ስለሆነ፣ እምብዛም
ሳልደነቃቀፍባቸዉ ጥሩ አድርገን አብረን ወጣነዉ

👍39
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...የሚስተር ኬን የሙዚቃ ትርዒት ሀሙስ ታይቶ ሲያበቃ ሎርድ ማውንት ስቨርን ቅዳሜውን ከኢስት ሊን ጓዙን ጠቅልሎ ለመነሳት አቀደ የጉዞው ዝግጅትም አስቀድሞ ተጀመረ ነግር ግን ቀኑ ከይረሰ በኋላ ያ ሁሉ የመነሳት ዝግጅት ለሁለተኛ ጊዜ እንዳይሰናከል አጠራጣሪ መስሎ ታየ ገና ሲነጋ ቤቱ ተሸበረ ከዌስትሊን ቀዶ ጠጋኝ ሐኪም ሚስተር ዌይን ራይት ተጠርቶሰ ከኧፕርሎ መኝታ ቤት
ገባ " ኧሮሎ አሁንም በሽታው እንደገና ክፉኛ ተቀሰቀሰበትና በጣም ተበሳጨ።
« በዚህ ዐይነት ገና ሳምንት ሁለት ሳምንት ወይም አንድ ወር እዚህ እቆይ ይሆናል » አላት ለሳቤላ ።
« በጣም አዝናለሁ... አባባ ኤስት ሊንን በጣም ስልችኸዋል " »
« መሰልቸት ይደለም ። ከኢስትሊን እንድወጣ የምፈልግበት ሌሎች ምክንያቶች አሉኝ አሁን ኮ አንቺም ወደ ሙዚቃ ትርዒት መሔድ ላትችይ ነው »
ሳቤላ ፊቷ ቀላ ። ምነው አባባ ? ላትችይ ነው አልከኝ?»
«አዎን ማን ይዞሽ ይሔዳል ? እኔ እንደ ሆንኩ ከመኝታዬ እንኳን መነሣት አልቻልኩም »
« መገኘት አለብኝ . . . አባባ " አለዚያማ እንግኛለን ብለን አስወርተን ብንቀር ዱሮውንም እንደማናደርገው አወቀን ያስወራነው ይመስልብናል " ደግሞ እንደምታውቀው ከዱሲ ቤተሰብ ጋር እዚያ ለመናኘት †ቃጥረናል " ባይሆን ሠረገላው እዚያው ያድርሰኝና እኔ ከነሱ ጋር እገባለሁ" »
« በይ እሺ ላንቺ ደስ እንዲለሽ እኔ እንኳን የምትቀሪበትን ስበብ ካገኘሽ እንዳጋጣ ቀርተሽ የምትጠቀሚበት መስሎኝ ነበር » አላት "
« በጭራሽ ! እኔ ሚስተር ኬንን ከነሙዚቃው የማልንቀው መሆኔን ዌስት ሊን እንዲያይ እፈልጋለሁ » አለች ሳቤላ እየሣቀች ።
ቀን ላይ የዊልያም ቬን በሽታ በጣም ከሚያሳስብ ደረጃ ላይ ደረሰ " ስቃዩ በጣም የሚያሰቅቅና የሚያስጨንቅ ነበር ከክፍሉ እንዳትገባ የተደረገችው ሳቤላ
ስለ በሽታው መባባስ ምንም አላወቀችም " ያን ያህል ሲያቃስት እንኳን ምንም ድምፅ ከጆሮዋ አልደረሰም » ስለዚህ ያለምንም ሐሳብና ጥርጣሬ እየሣቀችና
እየተጫወተች ደንገጡሯ ማርቨል እየረዳቻት መልበስ ጀመረች ማርቨል እመቤቷ የመረጠችውን ልብስና ጌጥ ሳትወደው እየከፋት አልብሳት አበቃች » ሳቤላ ልዩ ሁና
አጊጣና ለብሳ ወደ አባቷ ክፍል ገባች እንግዲህ ልሒድ አባባ ? » አለችው።
እሱም አዘብዝበው ያበጡትን ያይኑን ቆቦችና ደም የለበሰው ፊቱን ገለጥ አድርጎ” ሲያይ በትክክል ምን እንደምትመስል ባያረጋግጥም የምታምር ንግሥት የምታበራ መንፈስ መስላ ታየችው "ነጭ ዳንቴል ሥራ ቀሚስ ለብሳ አልማዟን በጸጉሯ ባንገቷና በክንዷ አድርጋለች " ቀሚሱ በጣም ምርጥ ከሆነ ጨርቅ የተስፋ ነበር " አልማዞቹ ከመልካሙ አንገቷና ከሚያሳሱት ክንዶቿ ላይ ሲብለጨለጩ ጫፉ
ቅልብስ ቅልብስ ብሎ የተበጠረ ከትከሻዋና ከደረቷ ወርዶ ከተኛው ጸጉሯ ጋር ልዩ ሁነው አምሮባት ነበር።
ኧርሉ ሲያያት በጣም ገረመውና ትክ ብሎ ካስተዋላት በኋላ «እንዴት ለአንድ የሙዚቃ ትርዒት እንደዚህ ሆነሽ ትለብሻለሽ ? አብደሽ ነው በጤናሽ ? » አላት
« ማርልም እንዳንተ አለችኝ » አለችው አሁንም በደስታ እየተፍነከነከች "
«እንዲያውም ልብሱንም አላቀርብም ብላኝ በግድ ነው ያስጣኋት እኔ ግን አባባ የሚስተር ኬንን ዝግጅት በደንብ ለብሰው ሊያዩት የሚገባ ትልቅ ትሮዒት
መሆኑን እነዚህ ዌስት ሊኖች እንዲያውቁት አስቤና ሆነ ብዬ ነው ያደረግሁት " »
« በአዳራሹ ያለው ሕዝብ በሙሉ እንደ ጉድ ይመለከትሻል »
« ግድ የለኝም " የፈለገ አፉን ከፍቶ ሲያየኝ ያምሽ ውጤቱን ይዠልህ እመጣለሁ " »
« ቀጣፊ በሰበቡ ለመታየት ፈልገሽ ነው እንጂ እንደዚህ የለበስሺው ግን ሳቤላ ...ኡ ኡኡ ! ኡህ ! ኡህ ! »
ሳቤላ እንደ ቆመች ድንግጥ አለች አባቷ ሲያቃስት ሰሚውን ያስጨንቅ ነበር
«ክፉ ልክፍት ! ልጄ . . . በይ ሒጂ ስናገር ይብስብኛል " »
« አባባ ልቅርና አጠገብህ ልሁንልህ ? » አለችው ኮስተር ብላ " ከማንኛውም ሐሳብና ሥራ በሽታ ይቀድማል " እንድቀር ከፈለግኸኝ ወይም የማደርግልህ ነገር
ቢኖር ልቅር " »
« እንዲያውም መሔድሺን እፈልገዋለሁ " ልታደርጊልኝ የምትችይው አንድም ምድራዊ ነገር ስለሌለ ሒጂ ይልቅስ ሚስተር ካርላይልን ያገኘሽው እንደሆነ ነገ ላነጋግረው እንደምፈልገው ንገሪው »
ማርቨል አንድ ካባ በትከሻዋ ላይ ጣል አዶረገችላትና ተዘጋጅቶ ሲጠብቅ ወደነበረው ሠረገላ ሔዳ ገባች።
የሙዚቃው ትርዒት ከገበያው ላይ ከነበረውና የከተማ አዳራሽ እየተባለ ከሚጠራው ከፍርድ ችሎት አዳራሽ ውስጥ ነበር " ድምፅ ለማስተጋባት የተመቸ
አዳራሽ ነበር ከዌስት ሊን የበለጡ በጣም የታወቁ ከተሞች እንኳን ይህን የሚያህል የሚመኩበት አዳራሽ አልነበራቸውም " ሚስተር ኬን ችሎታው በፈቀደለት መጠን ትርዒቱን ለማሳመር ሞከረ አንዲት በአራተኛ ደረጃ ልትመደብ
የምትችል ተጫወተች ከለንደን ቀጥሮ አምጥቶ ሌሎች አጃቢዎችም ከአካባቢው
አሟላ።
ባርባራ ሔርም የፈለገው ነገር ይምጣ እንጂ ትርዒቱን ሳታየው እንዶማትቀር አሳውቃ ነበር እናቷ ሚስዝ ሔር ግን ፍላጐቱም ጤንነቱም አልነበራትም" ስለዚህ
ሚስተር ሔርና ባርባራ ከሚስ እና ከሚስተር ካርላይል ጋር አብረው ለመሔድ ተነጋግረው ነበር ስለዚህ ቀደም ብለው በቡና ሰዓትላይ ለመድረስ ወደ ሚስ ካርላይል ቤት ሔዱ ከተገናኙ በኋላ በሠረገላ የመሔድ ነገር ሲነሣ ቦታው ቅርብ የምሽቱ
አየር ጥሩ ስለነበር ሚስ ካርላይል « እግሮቻችን ምን ሆኑና ነው ? » ብላ ተቃወመች " ባርባራም ከሚስተር ካርላይል ጋር እየተጫወተች በእግር መሔዱን አልጠላችውም " እነሆ ዳኛው ሔርና ሚስ ካርላይል ፊት ፊት እየተጫወቱ ሲሐዱ ባርባራና ሚስተር ካርላይል ቀረት ብለው እያወጉ ከኋላ ይከተሉ ነበር "
« እንዴት ነው አሁንስ ጠፋህሳ ? » አለችው ባርባራ "
«ሎርድ ዊልም ቬን ብቸኝነት እተሰማቸው ሲቸግሩ አየሁዋቸውና በየቀኑ ኢስት ሊን እተሻገርኩ አብሪአቸው ስለማመሽ ነው " ከእንግዲህ ግን ቅዳሜ ስለሚሔዱ በቂ ጊዜ ይኖረኛል።
« ትናንት ከደብሩ አለቃ ቤት ትመጣለህ ተብለህ ስትጠበቅ ነበር አኛም ማምሻውን ስንፈልግህ አመሸን»
« አለቃው ሚስተር ሊትልና ባለቤታቸው እንኳን የጠበቁኝ አልመሰለኝም ኢስት ሊን የራት ቀጠሮ እንደ ነበረኝ ነግሬአቸው ነበር »
« ኧረ ካልክስ አንዳንዶቹ ይህን ያህል ከዚያ ቤት የሚያመላልስህ ጉዳይ ምን እንደሆነ ይርማቸዋል " አጠቃሌለህ ኢስት ሊን ሳትግባ አትቀርም እየተባልክ ነው " እንዲያውም ሳቤላ ቬን እመቤት ሳቤላ ባትሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ምልልስ እሷን ፍለጋ ነው ተብለህ ትታማ ነበር " »
ስለኔ ይህን ያህል በማሰባቸው አመሰግናለሁ የሚሰማኝ ደስታና የምቆጥርላቸው ውለታ እመቤት ሳቤላ ቬን ከሚሰማትና ከምትቈጥርላቸው የላቀ ሊሆን ይችላል " እኔን የገረመኝ ግን ባርባራ....አንቺም ይህን የማይረባ ወሬ ከቁም ነገር ቆጥረሽ ስትደግሚው ነው " »
« ሰው እኮ ነው እንዲህ የሚለው እኔ አላልኩ » አለችውና ነገሯን በመቀጠል! «ወይዘሮ ሳቤላ ድምፀ መልካም ናት የሚሏት እውነት ነው ? መቸም ያንጐራረች እንደሆነ የድምጿ ቃና ከሰማይ የወረደ እንጂ ከሰው አንደበት የወጣ አይመስልም አሉ።
« በይ ይህን አባባልሽን እኔ እንደ ሰማሁሽ ኮርሊያ እንዳትሰማሽ " ፊቷ የመልአክ ፊት ይመስላል » ስል ስምታኝ የቁጣ መዓት እንዳወረደችብኝ እንዳታወርድብሽ» አላት እየሣቀ።

👍22❤1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
የእናታችን ታሪክ
ከአያታችን መሄድ በኋላ ከማዘንና ከመበሳጨት ውጪ ምን ማድረግ ወይም ምን ማለት ወይም ምን ሊሰማን እንደሚገባ አልገባንም እናታችን ሹራቧን መልሳ ስትለብስ ስመለከታት ልቤ በውስጤ ተርገበገበ፡ ሹራቧን ቀሚሷ
ውስጥ እየወሸቀች ወደ እኛ ዞራ ደህና እንደሚሆን ለማረጋገጫ ለሁላችንም ደስ የሚል ፈገግታ አሳየችን እንደዚያ ካለው ፈገግታ ውስጥ የሆነ ነገር መጨበጥ አለመቻሌ ያሳዝናል፡ ክሪስ አይኖቹን ወለሉ ላይ ተክሎ የተነጠፈው አሮጌ ምንጣፍ ላይ ያሉትን ዲዛይኖች በጫማው በመከተል ገና ያልተረጋጋ
ቁጣውን እየገለፀ ነው።
“አሁን ተመልከቱ አለች እናታችን በውሸት ደስታ። “ብዙምኮ አያምም። ከስጋዬ ይልቅ የተሰቃየው ክብሬ ነው እንደ ባሪያ ወይም እንደ እንስሳ መገረፍ በጣም የሚያሳፍር ነገር ነው በተለይ ደግሞ በራስህ ወላጆች።
ግን እንደዚህ አይነት ግርፊያ እንደገና ይኖራል ብላችሁ አትጨነቁ። በቃ አንድ ጊዜ ብቻ ነው: ከአባታችሁና ከእናንተ ጋር የኖርኳቸውን አይነት በደስታ የተሞሉ ተጨማሪ አስራ አምስት አመታት ለመኖር ብችል የዚህን
ግርፊያ መቶ እጥፍ እንኳን እቋቋማለሁ ነፍሴን ቢያሸማቅቃትም ያደረጉኝን
እንዳሳያችሁ አደረጉኝ...” አልጋ ላይ ተቀመጠችና ተጠግተን እንድናቅፋት እጆቿን ዘረጋችልን ሁላችንም ወደሷ ሄደን ተጠመጠምንባት እኔ ግን
ሳቅፋት እንዳላሳምማት እየተጠነቀቅኩ ነበር። መንትዮቹን ብድግ አድርጋ ጭኖቿ ላይ አስቀመጠችና ለእኛ አልጋውን መታ መታ እያደረገች አልጋው
ላይ እንድንቀመጥ ነገረችን፡ ከዚያ መናገር ጀመረች: ልትናገር የፈለገችው ነገር ለእሷ ከባድ ቢሆንም፣ እኛም ለመስማት የዚያኑ ያህል ከባድ ሆኖብን
ነበር።
“በጥንቃቄ እንድታዳምጡኝና አሁን የምነግራችሁን ነገሮች እድሜያችሁን ሙሉ እንድታስታውሷቸው እፈልጋለሁ" መናገሯን ቆም አድርጋ ግድግዳዎቹ ወደ ውጪ ያሳዩ ይመስል እና በእነሱ ውስጥ የዚህን ግዙፍ ቤት ሌሎች
ክፍሎች የምታይ ይመስል ግድግዳው ላይ አፍጥጣ ቆየችና “ይሄ እንግዳ የሆነ ቤት ነው: በውስጡ የሚኖሩት ሰዎች ግን፣ እንግዶችም ሠራተኞችም
ሳይሆኑ ወላጆቼ ናቸው- አያቶቻችሁ አክራሪ ሀይማኖተኞች ስለመሆናቸው ላስጠነቅቃችሁ ይገባ ነበር በእግዚአብሔር ማመን ጥሩና ትክክል ነገር ነው፡ ነገር ግን እምነታችሁን ከብሉይ ኪዳን ላይ የምትፈልጓቸውን ቃላት
ብቻ በመውሰድ የምታጠነክሩ ከሆነና የእናንተን ፍላጎት በሚያሟላ መንገድ የምትተረጉሙት ከሆነ፣ ያ ግብዝነት ነው፡ እና ወላጆቼም ልክ እንደዚያ ናቸው።
“አባቴ እየሞተ ነው፡ ነገር ግን ሁልጊዜ እሁድ እሁድ ተሸክመው ወደ ቤተክርስቲያን ይወስዱታል ሻል ካለው በዊልቸር ላይ፣ ከባሰበት ደግሞ ቃሬዛ ላይ አጋድመው ይወስዱትና የሚፈለግበትን አስር በመቶ አስራቱን ከአመት ገቢው ላይ ይሰጣል።
“ቤተክርስቲያኗን ለማሰራት ገንዘብ ሰጥቷል፤ መስኮቶችን ሁሉ ያስገጠመው ራሱ ነው: ቤተክርስቲያኗንና አገልግሎቱን ሁሉ ተቆጣጥሯል። በዚህም
የመንግስተ ሰማያት መንገዱ በወርቅ ላይ እንደሚሆን አረጋግጧል አባቴ በእርግጠኝነት ለቅዱስ ጴጥሮስ ጉቦ በመስጠት መንግስተ ሰማያት መግባት
እንደሚችል ያስባል። በዚያ ቤተክርስቲያን እሱ ራሱ እንደ አምላክ ወይም እንደ ቅዱስ ይታያል እናም ከቤተክርስትያን መልስ ወደ ቤቱ ሲመጣ፣
የሚፈልገውን ለማድረግ ሙሉ በሙሉ ፈቃድ እንዳለው ያስባል ምክንያቱም እዚያ የሚጠበቅበትን ሰርቶ ጨርሷል፡ በራሱ መንገድ ከፍሏል፤ ስለዚህ ከገሀነም ድኗል።
“ከሁለት ታላላቅ ወንድሞቼ ጋር ስናድግ ቤተክርስቲያን እንድንሄድ እንገደድ ነበር፡ ከአልጋ የማያስነሳ በሽታ ቢያመንም እንኳን መሄድ ነበረብን ኃይማኖት ኑሯችንን አንቆ ይዞት ነበር። መልካም ሁኑ፣ መልካም ሁኑ፣ መልካም ሁኑ፣ ሁልጊዜ የምንሰማው ይህንን ነበር ሁልጊዜም ሌሎች ሰዎች
አድርገውት የሚደሰቱበት ነገር ሁሉ እኛ ጋ ሲደርስ ኃጢአት ይሆናል። ወንድሞቼና እኔ ዋና መሄድ አይፈቀድልንም ነበር ምክንያቱ ደግሞ ዋና
መዋኘት ማለት የዋና ልብስ በመልበስ አብዛኛውን የሰውነታችንን ክፍል ለእይታ ማጋለጥ ስለሆነ ነበር። ካርታ መጫወትም ሆነ ሌሎች ቁማርን
የሚያመለክቱ ጨዋታዎችን መጫወት የተከለከለ ነበር: ወደ ዳንስ ቦታዎች መሄድ አይፈቅድልንም:: ምክንያቱ ደግሞ ምናልባት ሰውነታችን ከተቃራኒ ፆታ ሰውነት ጋር ሊነካካ ስለሚችል ሀሳቦቻችንን እንድንቆጣጠርና ስለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት እንዳናስብ መጠንቀቅ ነበረብን፡ የኃጢአት ሀሳቦች እንደ ድርጊቶቹ
ሁሉ ክፉ ናቸው እንባል ነበር እንዳናደርጋቸው ስለምንከላከላቸው ነገሮች
ብዙ መቀጠል እችላለሁ በአጠቃላይ አስደሳችና አስገራሚ የሆኑ ነገሮች ሁሉ ለእነርሱ ኃጢአት ይመስሉ ነበር ህይወት በጣም ስርዓት የበዛበት ሲሆን
ልጆች የተከለከሉትን ነገሮች ለማድረግ የበለጠ ፍላጎት እንዲያድርባቸውና እንዲያምፁ የሚያደርጋቸው የሆነ ነገር አለ ወላጆቻችን ሶስቱን ልጆቻቸውን
እንደ መልአክትና ቅዱሳን አድርገው ለማሳደግ ቢፈልጉም፣ የተሳካላቸው መጥፎ ሆነን እንድናድግ ማድረግ ብቻ ነው::"
አይኖቼ ፈጠው አፌ እንደተለጎመ ተቀመጥኩ፡ ሁላችንም እንደዚያ ሆነን ነበር መንትዮቹ ሳይቀር: “ከዚያ አንድ ቀን…” እናታችን ቀጠለች በዚህ ሁሉ መሀከል አንድ ቆንጆ ወጣት ከእኛ ጋር ሊኖር መጣ፡ አባቱ አያቴ ነበር። የሞተውም ይህ ወጣት ገና የሶስት ዓመት ልጅ ሳለ ነበር። የእናቱ ስም አሊሺያ ሲሆን፣ የአምሳ አምስት አመት ዕድሜ የነበረውን አያቴን ስታገባ ገና
አስራ ስድስት አመቷ ነበር፡ አሊሽያ በልጅነቷ ነው የሞተችው: የአያቴ ስም ጋርላንድ ክሪስቶፈር ፎክስወርዝ ነበር፡ እና እሱ ሲሞት ግማሽ ሀብቱ የሶስት አመት እድሜ ወደ ነበረው ወደ ትንሹ ልጅ ሄደ ነገር ግን አባቴ ማልኮልም ራሱን በሞግዚትነት ሰይሞ የአባትየውን ንብረት ሁሉ መቆጣጠር ቻለ።በእርግጥም የሶስት አመት ህፃን በጉዳዩ ላይ ድምፅ አልነበረውም እናቱም
እንድትደግፍ አልተደረገችም:
“አባቴ አንድ ጊዜ ሁሉንም ነገር በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋላ አሊሺያንና ትንሹን ልጅ አስወጥቶ አባረራቸው: የአሊሺያ ወላጆች ወደሚኖሩበት ሪችመንድ ሄዱና
ለሁለተኛ ጊዜ እስክታገባ ድረስ እዚያ ተቀመጡ። ከልጅነቷ ጀምሮ ትወደው ከነበረ ሰው ጋር ለተወሰነ አመት በደስታ ኖረችና እሱም ሞተ። ሁለት ጊዜ አገባች ሁለት ጊዜም ባሎቿ ሞቱባት አሁን ወላጆቿም ሞተው ስለነበር
ከትንሹ ልጇ ጋር ብቻዋን ቀረች: ከጥቂት ዓመታት በኋላ እሷም በካንሰር ሞተች፡ የዚያን ጊዜ ነው ልጇ ጋርላንድ ክሪስቶፈር ፎክስርወርዝ አራተኛ እዚህ ሊኖር የመጣው: ክሪስ ብለን ነበር የምንጠራው…” አመነታች ከዚያ
ክሪስና እኔን በክንዶቿ ጠበቅ አደረገችን፡ “…ስለማን እያወራሁ እንደሆነ አውቃችኋል? ያ ወጣት ልጅ ማን እንደሆነ ገመታችሁ?”
ተንቀጠቀጥኩ ሚስጥራዊው አጎት እና በሹክሹክታ “አባዬ የምታወሪው ስለ አባዬ ነው:” አልኩ
“አዎ” አለች። ከዚያ በከባዱ ተነፈሰች።
ትልቅ ወንድሜን ለማየት ወደፊት ሳብ አልኩ። አይኖቹ መስታወት መስለው ፊቱ ላይ መገረም እየተነበበ በፀጥታ ተቀምጧል።

👍33👏3❤1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ማርክ አልደር በመጀመሪያ ዳያና ላቭሴይንን ያያት ጊዜ ‹‹የአምላክ ያለህ! እንዳንቺ የምታምር ሴት አይቼ አላውቅም›› አላት፡፡
ያገኛት ሁሉ እንዲህ ይላታል፡፡ ዲያና ያለጥርጥር ውብ ሴት ስትሆን ጥሩ ጥሩ ልብስ መልበስም ትወዳለች፡፡ የዚያን ቀን እጀ ጉርድ ቅልጥሟ ጋ የሚደርስ ቀሚስ ለብሳ ነበር፡፡ እንዳማረባትም አውቃለች።
ማንቼስተር ከተማ ሚድላንድ ሆቴል ውስጥ ራት ግብዣ ተጠርታለች
በግብዣው ላይ ከነበሩት ከባሏ የንግድ ሸሪኮች ጋር በሙሉ ስትደንስ አመሸች ታዲያ ሁሉም አብረዋት የደነሱት ወንዶች ደረታቸው ላይ ይለጥፏታል ወይም እግሯ ላይ ይቆማሉ ሚስቶቻቸው ደግሞ በጥላቻ ዐይን አፈር ድሜ ያስግጧታል፡ ወንዶች ቆንጆ ሴት አይተው ሲቅበጠበጡ
ሚስቶች ለምን ባሎቻቸውን ትተው ሴቷ ላይ በቁጣ እንደሚያፈጡ ሁልጊዜ
ይገርማታል፡፡ እሷ እንደሆነ እነዚህን ጉረኛና በዊስኪ የደነበዙ ባሎቻቸውን
አትፈልግም፡፡
አንድ ጊዜማ የከተማውን ምክትል ከንቲባ በሰው ፊት በማዋረዷ ባሏን አሳፍራው ነበር፡ በኋላም ትንሽ እረፍት አገኝ ብላ ሲጋራ የምትገዛ መስላ ከሆቴሉ ወጥታ ሄደች፡
ኮኛኩን እየተጎነጨ ብቻውን ተቀምጧል። ልክ በክፍሉ ውስጥ የፀሃይ ብርሃን የፈነጠቀች ይመስል ስትገባ ዓይኑን ተከለባት፡ ሰውዬው አጠር ያለና እንደ ህፃን ፍልቅልቅ ያለ ፈገግታ የተላበሰ ሲሆን አሜሪካዊ መሆኑ ሁኔታው ያሳብቅበታል፡፡ ገና እንዳያት አድናቆቱን የገለፀላት ሲሆን ሰውዬው የደስ ደስ ያለው በመሆኑ ፈገግ ብትልለትም አላናገረችውም፡፡ ሲጋራዋን
ገዝታ ቀዝቃዛ ውሃ በጉሮሮዋ ለቀቀችና ወደ ዳንሱ አዳራሽ ተመለሰች፡
ሰውዬው ማን እንደሆነች ከቡና ቤቱ አስተናጋጅ ጠየቀና አድራሻዋን
እንደምንም አግኝቶ የፍቅር ግጥም ፅፎ ላከላት፡፡ ግጥሙን ስታነብ አነባች፡፡
ያስለቀሳት ብዙ ነገር ተመኝታ ሁሉንም ነገር ባለማግኘቷ ነው፡፡ ያለቀሰችው በዚች ደስታ በራቃት ከተማ የዓመት እረፍት መውጣት ከሚጠላ ባሏ ጋር ተጣብቃ በመቅረቷ ነው፡፡ ያለቀሰችው ከአምስት ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ
ጊዜ የፍቅር ግጥም በመስማቷ ነው: ያለቀሰችው ለመርቪን ያላት ፍቅር የተሟጠጠ በመሆኑ ነው፡፡
በነጋታው እሁድ ስለነበር ዳያና ቤቷ ውስጥ መሸገች፡፡ ሰኞ ዕለት ወደ
ከተማው መጽሐፍ ቤት ሄዳ ከዚህ ቀደም የተዋሰችውን መጽሐፍ መለሰችና ፊልም ቤት ገባች፡፡ ከዚያም ለእህቷ ልጆች ስጦታ ስትገዛ ዋለች፡፡ በኋላም
እራት መስሪያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ገዛችና ከከተማ ወጣ ወዳለው መኖሪያዋ
በጊዜ ለመድረስ ባቡር ላይ ተሳፈረች፡፡ ከተማ ውስጥ ስትዟዟርና ቡና ስትጠጣ የአሜሪካዊ አነጋገር ቅላፄ ያለውን ሰው ሳታገኘው በመመለሷ ተከፋች፡፡
ነገር ግን ነገሩን ስታስበው ጅልነት ሆነባት፡፡ ሰውዬውን ያየችው ለአፍታ ጊዜ ሲሆን በወቅቱም አላነጋገረችውም፡፡ ሆኖም ይህ ሰው ለዓመታት ያጣችውን ፍቅር የሚቀሰቅስባት ሆነባት፡ ታዲያ ይህ ሰውዬ ደግማ ብታገኘው ወይ ባለጌ ይሆናል፣ ወይ ወፈፌ ይሆናል፣ ወይ በሽተኛ
ይሆናል፣ ወይ ደግሞ ገላው የሚቀረና ይሆናል ብላ አሰበች
ከባቡሩ ወርዳ የቤቷን መንገድ ይዛ ስትሄድ ባልጠበቀችው ሁኔታ
ሰውዬው ወደ እሷ ሲመጣ በማየቷ ክው ከማለቷም በላይ ተርበተበተች፡፡
ፊቷ ቲማቲም መሰለ፧ልቧም መቶ ሜትር ሸመጠጠ፡፡ እሱም ሲያያት መደንገጡ ባይቀርም ሊያናግራት ቆም አለ፡፡ እሷ ግን እርምጃዋን ቀጠለች።
አልፋው ስትሄድ ‹‹ነገ ጠዋት ማዕከላዊ መጻሕፍት ቤት ጠብቀኝ›› አለችው
መልስ ይሰጠኛል ብላ ባትጠብቅም ሰውዬው ፈጣን አዕምሮ ያለው መሆኑን በኋላ ተረድታለች፡፡ ወዲያው ‹‹የትኛው ክፍል?›› አላት።
አፏ እንዳመጣላት ‹‹ባዮሎጂ ክፍል›› በማለቷ ሳቅ አለ፡፡
ቤቷ የደረሰችው በደስታ ተሞልታ ነው፡
ቤቱ ውስጥ ሰው የለም፡፡ የፅዳት ሰራተኛዋ ስራዋን ጨራርሳ የሄደች ስትሆን
መርቪን ገና አልገባም፡፡
በማግስቱ ቀጠሯቸው ቦታ መጻሕፍት ቤት ከላይ ‹‹ፀጥታ›› የሚል
ፅሁፍ የተንጠለጠለበት ቦታ ተቀምጦ አገኘችውና ‹‹ሰላም›› ስትለው ሌባ ጣቱን ከንፈሩ ላይ አድርጎ ዝም እንድትልና እንድትቀመጥ አመለከታት
ከዚያ ብጣሽ ወረቀት ላይ አንድ ነገር ፅፎ አቀበላት፡፡ ‹‹ኮፍያሽ ያምራል» የሚል ነበር፡፡ ኮፍያዋን በአንድ በኩል ገደድ አድርጋ ራሷ ላይ የደፋች በመሆኗ የግራ አይኗን ከልሎታል፡፡ ይህ ኮፍያ አደራረግ ፋሽን ሲሆን ይህን ፋሽን ለመከተል የሚደፍሩት ወኔ ያላቸው ጥቂት ሴቶች ብቻ ናቸው።
እስክርቢቶ ከቦርሳዋ አወጣችና ‹‹ኮፍያው ላንተ አይሆንም› ብላ ፅፋ
አሳየችው:፡ እሱም ‹‹የግቢዬን አበባ አስቀምጥበታለሁ›› ብሎ ሲፅፍላት በሳቅ ተንከተከተች፡፡ ‹‹ሽሽሽሽ›› አላት ዝም እንድትል፡
ዳያና ይሄ ሰውዬ ወፈፌ ነው አስቂኝ አለች በሆዷ፡፡ ከዚያ
‹‹ግጥሞችህን ወድጃቸዋለሁ›› ብላ ፃፈችለት፡፡
‹‹እኔም አንቺን ወድጄሻለሁ› ብሎ መለሰላት በፅሁፍ፡፡
‹እብድ› ስትል አሰበች፡፡ ሆኖም እምባዋ በዓይኗ ተንቆረዘዘ፡፡
‹‹ስምህን እንኳን አላውቀውም› ብላ ፃፈችለት።
ቢዝነስ ካርድ አወጣና ሰጣት፡፡ ስሙ ማርክ አልደር ሲሆን የሚኖረው ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ነው፡፡
የምሳ ሰዓት ሲደርስ ምሳ ለመብላት ወደ ምግብ ቤት ሄዱ፡ ይህን ሰዓት የመረጠችው ባሏ እንዳያገኛት ነው መቼም በዚህ ሰዓት ባሏ
አይመጣም ብላ፡፡
ከምሳ በኋላ የሙዚቃ ድግስ ለማየት ቴያትር ቤት ገቡ፡፡
ያን ቀን ማርክ የሬዲዮ ኮሜዲ ደራሲ መሆኑን፣ ለታዋቂ ኮሜዲያኖች
እንደሚደርስ፣ እንዲሁም የሬዲዮ ጣቢያ ባለቤት መሆኑን አጫወታት
እንግሊዝ አገር የመጣው ትውልዳቸው ከሊቨርፑል
ውስጥ የሚሳብ የትውልድ ዘር ሐረጎችን ለማፈላለግ መሆኑን ነገራት፡፡
ማርክ አልደር ቁመቱ አጠር ያለ ሲሆን ከዳያና አይበልጥም፧ በእሜም እኩያዋ ነው፡፡ ፊቱ ሁል ጊዜ ፈገግታ አይለየውም፡፡ በአእምሮ የበሰለ አስቂኝና ተጫዋች ሲሆን ባህሪው ልስልስ ያለ በአለባበሱ ሸጋና ፅዱ ነው የሞዛርትን ሙዚቃ የሚወድ ሲሆን ከሁሉም በላይ ግን ዳያናን ወዷታል።
እስካሁን የምታውቃቸው ወንዶች ገላዋን መተሻሸት የሚወዱ፣ ባሏ መርቪን ጀርባውን ማዞሩን አይተው እንተኛ የሚሏት፣ በመጠጥ የደነበዙና ካንቺ ፍቅር ይዞናል እያሉ የሚቀባጥሩ ዓይነት ናቸው፡:
መቼም እሷን ሳይሆን ገላዋን እንደሚፈልጉ ታውቃለች፡፡ ንግግራቸው
የማይጥም ፍሬፈርስኪ ሲሆን እሷ የምትለውን ለመስማት አይፈልጉም፡፡
ስለእሷም ማወቅ ችግራቸው አይደለም:: ማርክ ግን ከነሱ ለየት ያለ ሰው መሆኑን ከቀን ወደ ቀን ማወቅ ችላለች፡፡
መጻሕፍት ቤት በተገናኙ ማግስት መኪና ተከራየና ባህሩ ዳርቻ ወስዶ
አዝናናት፤ ሳንድዊች ጋበዛትና ከለል ያለ ቦታ ፈልገው ተሳሳሙ፡፡
ማርክ ሚድላንድ ሆቴል አልጋ የያዘ ቢሆንም ዳያና እዚያ በጣም ታዋቂ በመሆኗ ከሱ ጋር መግባት አትችልም፡፡ ከምሳ በኋላ እዚያ ከወንድ ጋር ስትገባ ብትታይ በመክሰስ ሰዓት ወሬው በከተማው በሙሉ ይዳረሳል፡በመሆኑም የማርክ ፈጣን አዕምሮ አንድ ነገር ዘየደ፡፡ ሌላ የባህር ዳርቻ ላይ የሚገኝ ከተማ በመኪና ሄደው ሻንጣ አንጠልጥለው ሆቴል ደረሱና አቶ እና ወይዘሮ አልደር ብለው ተመዝግበው አልጋ ያዙ፡፡ ከዚያም ምሳ በሉና አልጋ ላይ ወጡ፡፡
ማርክ በፀጥታ ልብሱን ማወላለቅ ጀመረ፡፡ እሷ ደግሞ እፍረት ስለያዛት
ልብሷን ያወላለቀችው በሳቅ እየተንከተከተች ነው፡፡
ይወደኝ ይሆን ብላ አልተጨነቀችም፡፡ ከመውደድም እንደሚያመልካት
አውቃለች፡፡ እሱም ጥሩ ሰው በመሆኑ አልተረበሸችም

👍16
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ከሻንቆና ከላላ የተሰባሰቡት ሽማግሎች በደልቲ ገልዲና በካርለት ጋብቻ ላይ ሸንጎ ከመቀመጣቸው በፊት በኅብረተሰቡ አጋጣሚ ላይ
ትንበያ መስጠት ይችላሉ የተባሉት፣ «ጫማ ጣዮች» ደጋግመው ጫማ በመጣል ጋብቻው ስለ መሥመሩ አስተያየታቸውን ሰጡ"
ከጫማ ጣዮቹ ቀጥሎ ደግሞ ፍየል ታርዶ «ለአንጀት አይታዎች» ቀርቦ ጋብቻውን በተመለከተ እነሱም አስተያየት እንዲሰጡ ተጠየቁ። እነሱም ተጋቢዎቹ ልጅ ስለ መውለድ አለመውለዳቸው
ሊታያቸው ባለመቻሉ ሦስት ፍየል ከታረደ በኋላ፣ «ጋብቻው ቀና ነው» በሚል ብቻ አድበስብሰው ተውት"
በእርግጥ፣ ይህ ጉዳይ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ያወያየ ሲሆን፣ በተለይም በሽማግሎቹ ዘንድ ጋብቻውን በመጠራጠር በቀጠሮ በተለያየ ጊዜያት ለመወያየት አስቻላቸው"
ካርለት አንጀት አይታዎች በሰጡት አስተያየት መደናገጧና መደነቋ አልቀረም" በሐመር ማኅበረሰብ መካን ሴት ፈላጊ እንደ ሌላት ታውቃለች" አንድ ሴት ለአባቷ ጥሎሽ ተከፍሎ ባሏ ዘንድ ከሄደች በኋላ ልጅ ሳትወልድ ብትቀር ባሏ እሷን መልሶ ታናሿን፣
ካለበለዚያም ቅርብ ዘመዷን ያገባል" ያም ሆኖ ካልተሳካለት፣ ልጅ
መውለድ ካልቻለች ላባቷ የከፈለውን ጥሎሽ ያስመልሳል ሴቷም፣
«መካን የሆነችው በውኃ ብልቷን ታጥባ ይሆናል» ተብላ ትጠረጠራለች» መካን ሴት የተገኘችበት ቤተሰብም እንደ መጥፎ
ቤተሰብ ስለሚቈጠር ጋብቻ የሚፈልገው ሁሉ ይሸሻል" ይህ ደግሞ አባት በልጆቹ ጥሎሽ ያገኘው የነበረውን ከብት፣ ፍየል፣ በግ፣ ማር
ያስቀርበታል" ከዚያም ተጨማሪ፣ ምናልባት አባትየው ሦስት ሴት
ልጆች ቢኖሩት የመጀመሪያ ልጁን ጥሎሽ ተቀብሎ ቢድርና መካን ብትሆን ሁለተኛዋን፣ ሁለተኛዋም መካን ከሆነች ሦስተኛዋን! |
ሦስተኛዋ መካን ከሆነች የዘመድ ልጅ...በመስጠት ሞክሮ ካልተቻለ ግን የተቀበለውን ጥሎሽ ይመልሳል"
«ስለዚህ አንደኛ ነገር እኔ በውኃ ስተጣጠብ ስለሚያዩ መካን ትሆናለች የሚል ግምት መጀመሪያውንም ነበራቸው" ሁለተኛ ደግሞ
አንጀት አይታዎችና ጫማ ጣይዎች ልጅ ልወልድ አለመቻሌን ለማኅበረሰቡ አስታውቀዋል። ሌላው ግን የኔው የራሴ ጉዳይ ነው
ለጥንቃቄ እንዳላረግዝ የሕክምና መከላከያ አለኝ" ስለዚህ ልወልድ
አለመቻሌን አውቀዋለሁ" እነሱም ባለመውለዴ እጅግ በጣም አምነዋል" ግንኮ እንዴት? የፍየል አንጀት ከኔ ጋር ምን አገናኘው ካርለት፣ ራሷ ለራሷ ሐሳቧን አካፍላ ራሷን ጠየቀች።
ካርለት በእውነቱ ከሆነ ጥሎሽ ከደልቲ ገልዲ ማግኘት አትሻም
ጥሎሽ አያስፈልግም ብትል ግን የሱ የግል ንብረትነቷ ማረጋገጫ አጣ ማለት ነው" ጋብቻው ከዚህ ሁሉ ቢቀርስ እንዳይባል ደግሞ እሷ ባህላዊ ግድቡን ጥሳ ጥናቷን ለማካሄድ፣ ደልቲ ደግሞ ባለጌዋን እንግዳ የራሱ አድርጎ በግርፋት ሥነ ሥርዓትንሊያስትምራት
ቈርጧል።
በግልና በተናጠል የላላና ሻንቆ ኗሪ ሲመክርና ለሽማግሎቹ
የመሰለውን አስተያየት ሲሰጥ ሰንብቶ በመጨረሻ ሽማግሎቹ በጥልቅ ከተመካከሩ በኋላ
«እንግዳዋ ምንም እንኳ በመልክና በቋንቋዋ ከእኛ ብትለይም የቦርጆ (የአምላካችን) ፍጡር ናት። እኛን ብላ፣ እኛን መርጣ መጣች እንጂ ማሌ፣ በና፣ ዳሳነች፣ ሙርሲ...ምድር ልትሄድ ይቻላት ነበር።
በእውነት ከሆነ ብልግናዋ የበዛ ነው" ይህ ደግሞ የሷ ስሕተት ሳይሆን፣ ያባቷ ስሕተት ነው» ብለው ጋብቻውን ለመቀበል ወሰኑ።
በመቀጠልም፣ «ይህች እንግዳ አባቷ በቅርብ ባለመኖሩ ደልቲ ገልዲ የሚከፍለውን ጥሎሽ የሚቀበል አባትና ጥሎሹን የሚወስን ሰው የላትም" ስለዚህ እሷ የፈለገችውን ሰው በአባትነት ትምረጥ።
ከእንግዲህ በኋሳ የምትለብሰው፣ ጠረኗ እንደ ሐመር ልጃገረዶች
እንዲሆንና እስከ አሁን የፈጸመችውን ስሕተት እሷም ራሷ ስለምታውቅ ለወደፊት የፍየል ቆዳ ለፍቶና ተሰፍቶ እንድትለብስ፣በጨሌና አንባር በማጌጥም ጸጕሯን አጠር አድርጋ አስቈርጣ ሹርባ እንድትሠራና በእግሯ እንድትሄድ» ብለው ተስማሙ"
«ባባቷ በባንኪ ሞሮ ደንብ መሠረትም ጥሩ ሴት ለመባል አባት ብላ ለምትመርጠው ወንድ ልጅ ወይም በዘመዱ ወንድ ልጅ የከብትጨዝላይ ወቅት በባራዛ አርጩሜ ዱላ ቻይ መሆኗን ለማስመስከር
ላትሸማቀቅ ፀንጋዞች (ባዕዳን) በሚባሉት ጐረምሶች እንድትገረፍና
ጀርባዋ ላይ የሚቀረው የግርፋት ምልክት ለሽማግሎችና ለአካባቢው ሰው እንዲታይ በግልጽ እንድትተወውና እንድታጌጥበት»
ተባብለው ተማመኑ።
ከሎ ሆራ የሽማግሎችን ሁኔታና አጠቃላይ ውሳኔያቸውን ለካርለት ሲነግራት ጥርሷ እስኪፋጭ ድረስ ተንቀጠቀጠች" መናገር †ሳናት" በእውነቱ ለተመለከታት የማንኛውንም ሰው አንጀት የምትበላ ሲሆን፣ በሌላ በኩልም ጋብቻ ለመፈጸም ማሰብ የግብዝነት ተግባር ነው ሊያሰኝ የሚችል ነበር።
ካርለት ከከሎ ተለይታ ሰቀላዋ ውስጥ ገብታ ምን እያደረገችና ወደፊትስ ምን ሊያጋጥማት እንደሚችል ስታስብ፣ እንባዋ
እየተንፎለፎለ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ከዚህ ቀደም የኖረችበት ዓለም
እውነት አሁን ባለችበት መሬት ላይ ሳይሆን ከሌላ ፈለክ (ፕላኔት) የመጣች እንግዳ ፍጡር የሆነች መሰላት" ሽማግሎቹ ካቀረቡላት ቅድመ ሁኔታና ባህላዊ የውጣ ውረድ ይልቅ በትንሿ የመርፌ
ቀዳዳ ሾልኮ ማለፍ እንደሚሻል ገመተች"
እሷ የምታውቀው ሕይወትና አሁን ያለችበት ዓለም የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃል ተብሎ በርቀት ልዩነት ብቻ የሚለካ
ሳይሆን፣ ፈጽሞ ሊተያይ የማይችል ሆድና ጀርባ ሆነባት"
ግርፊያ.ቆዳ መልበስ…በባዶ እግር መሄድ ...አለመታጠብ ልት
ረዳው፣ልታምነው፣
ልትሰማማው የማትፈልገው ጉዳይ ነው።ስለሆነም ይህን ፈጽሚ ማለት፣ በሷ ላይ ትልቅ ችግር መፍጠር ብቻ ሳይሆን ይቅር የማይባል ግፍ እንደ መፈጸም ያክል ነው" አባባሉን እንኳን በተግባር በቃል ልትሰማው ከበዳት።
ታላቁ የሴቶች እንቅስቃሴ ለመላው አውሮፓ ሴቶች ያጎናጸፈው መብት ብናኙ እንኳን ወደማይገኝበት መጥታ መገኘቷ፣ ከመላ ሴቶች ጎን ተነጥላ ወደ ዘንዶ አፍ የመወርወር ያህል ሆኖ ተሰማት ስለዚህ ለምን ወደዚህ ጣጣ ራሷን እንደዶለች ማሰላሰል
ጀመረች ካርለት ፍዝዝ፣ ትክዝ እያለች ቀስ በቀስ አንገቷን ወደ ሰማይ በማስገግ ወደ አውሮፓ በሐሳብ ተጓዘች።
እናቷ ሚስስ አልፈርድ፣ ታናሽ እኅቷ ሴሻ አጠገቧ ቢኖሩላት ኖሮ ጭንቀቷን ገልጻላቸው ተያይዘው ያለቅሱ ነበር። ግን ምንስ ብላ ልትገልጽላቸው ነው?
«እኔ እራሴ እንኳ ሁኔታዎች ከቍጥጥሬ ውጭ ሆነውብኝ መላ ብዬ የፈጠርኩት እንጂ እነሱማ መጀመሪያውንስ እንዴት ሊረዱኝ ይችላሉ? እናቴና እኅቴ እንዳፈቅር ገፋፍተውኛል" ለታናሽ እኅቴም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ምን ዓይነት የደስታ ስሜት እንደሚፈጥር
የነገርኳት እኔ ነኝ” ጋብቻ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ከባድ ነገር መሆኑን እንደሆነ የእንግሊዝ አገር ወጣት በየትምህርት ቤቱ፣ በቲያትርና ሲኒማው የሚያውቀው የአደባባይ ምሥጢር ነው።
«የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፍቅር ዋነኛው ቅመም ቢሆንም በራሱ ግን ፍቅር አይሆንም" ያልተፈለፈለ፣ እዶሮ እቅፍ ውስጥ ያለ እን
ቍላል እንደ ማለት ነው እንቍላሉ ነፍስ ሆኖ ከመፈጠሩ በፊት እን
ስቷ ዶሮና አውራው መገናኘት አለባቸው" የሰዎች ግንኙነት ደግሞ
ከዚህ በላይ ነው" በሐሳብ መጣጣምና መግባባት ያስፈልጋቸዋል"።

👍17
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ
ከፖርት ፕሪንስ በስተ ምስራቅ ፓርቶሪኮ ሳንጁአን ውስጥ የግል እርሻ የጀመረው አሌክስ ቀደም ሲል የስፔን ፋሽዝም
አራማጅና የጦር አባል ከነበረው ስመ ጥር አባቱ ጋር ወደ ፓርቶሪ
በተደጋጋሚ ከሄደ በኋላ ሳንጁአን ለመኖር እንዲወስን ተፈጥሮአዊ
ፍቅሩ አደፋፈረው፡
የሻምበልነት ማዕረግ የነበረው አባቱ ልጁ በእርሻ ትምህርት ሰልጥኖ ህይወቱ በእርሻ ምርት ላይ ቢመሰረት የወደፊት ዕድሉ
የተቃና ደስተኛና ሃብታም ሊሆን እንደሚችል በመከረው መሰረት
አሴክስ የአባቱን ህልም የእራሱ በማድረግ ህልሙን ለማሳካት የሚያስችለውን ጥረት ፈጽሞ በመጨረሻ ተሳካለት፡
አሌክስ ደጋግሞ ስለ እርሻ ዘመናዊ እርሻ ስለሚያስገኘው
ብልፅግና ስለ ተሻሉ የምርት ውጤቶች ማውራት እንጂ በፍቅሩ ተረትታ
እንደነፍስ ጡር ለምትብረከረከው
ፍቅረኛው ቁብ
አልነበረውም ሌላው ቀርቶ እግሩ ስር እንደምትታከከውና "ፔሙስ" ብሎ እንደሚጠራት ድመቱ ሲገናኙ እጁን ሰዶ ዳብሷት ካልያም እጆችዋን ስቦ ወደ ደረቱ አስጠግቷት አያውቅም አይብዛ እንጂ
አንድ ወቅት የፍቅር አባባሎችን ይለዋወጡ አብረውም እየተሻሹ
ጊዜያቸውን በደስታ ያሳልፉ የነበረ ቢሆንም! ያ የስሜት መመሳሰል ግን ከጠለቀ ብዙ ወራቶች ተቆጠሩ።
ይህ የቸልተኝነት ባህሪው ሸበላ ቁመናው የታከታት ደረቅ የአጨዋወት ስልቱ ሳይቀር አኜስን ለአሌክስ ያላትን ስሜት ከእለት
ወደ እለት እንዲያድግ አደረገው። አንዳንዴ እንዲያውም፡-
“አሌክስ! እባክህ ለፍቅራችን የሚሆን ጊዜ ይኑርህ? እባክህ በፍቅር
ስሜቴ አትጫወትበት!...” በማለት ምርር ብላ ስትነግረው፡-
“እባክሽ አኜስ ታገሽ!
ትዕግስት ይኑርሽ! ልትረጅኝ
ሞክሪ! በአሁኑ ሰዓት የፍቅር ስሜቴ በወደፊት ዓላማዬ እንደ ጉም ተሸፍኗል። አንድ ወቅት ግን ጉሙ ይበተናል፤ በሰማያዊው ሰማይ
ከምስራቅ ወደ ምዕራብ እንደምትጓዝ ፀሐይ የፍቅር ብርሃን ፍንትው ብሎ ይፈነጥቃል...'' ይላታል:
“አሌክስ! እኔ'ኮ ብዙ ላሳስብህ አልሻም። በሳምንት ቢያንስ
ለተወሰነ ደቂቃ እንኳ ፍቅር እንድንለዋወጥ ለማድረግ ሞክር ፧እየተጎዳሁ ነው” ስትለው፡-
“እስኪ እሞክራለሁ አንች ግን ጠንከር በይ: በህልሜ
ልትደሰች ሞክሪ በአትላንቲክ ውቅያኖስ በተከበበችው ሳን ጁን
ውስጥ የሚኖረው ቡቃያ ንፋሱ ጎንበስ ቀና ሲያደርገው ይታይሽ!
አዲዎስ ብሏት ይሄዳል።
አንድ ቀን ግን አሌክስ በጅፕ መኪናው መኖሪያዋ ድረስ መጥቶ ድንገት “ለሽርሽር እንሂድ? አላት።
“የት?” አለችው አኜስ ግራ ተጋብታ።
“ሱ..” አለ አፉን በቀኝ እጁ አመልካች ጣት እየጠበጠበ።
“አሌክስ የት እንደምንሄድ መንገሩን ባትፈልግ እንኳን ወጣ እንደምንል ቀደም ብለህ ፍንጭ መስጠት ነበረብህ: ከሰዓታት
ወይንም ከቀናት በፊት ወጣ እንደምንል ነግረኸኝ ቢሆን ኖሮ ነፍሴ በደስታ ከመዝለሏም በተጨማሪ ስሜቴ በጉጉት ተበረጋግዶ በናፍቆት ይጠብቅህ ነበር: አሁን ግን ልቤ በሐዘን ቀዝቅዛለች። ስሜቴም በድን
ነው። እኔም ስላልተዘጋጀሁ የትም መሄድ አልፈልግም” አሰችው።
ያልተለመደ ፈገግታ አሳይቶ ባልጠበቀችው መልክ የግራ እጅዋን ብድግ አድርጎ ጣቶችዋን ሳም ሳም አደረጋት፤ ጉንጯን በቀኝ
እጅ አመልካች ጣቱ ደባበሰላት: ሽቅብ አንስቶም ከንፈሯን በከንፈሩ
ደባበሰላት።
ወዲያው ልቧ ጋለች ሰውነቷ በሙቀት ተጥለቀለቀ፡
የፍቅር ሃይሏ ከየስርቻው ተሰባሰበ ስለዚህ! “ማሬ!
እንሂድ" አለችው::ሃሳቡን እንዳይለወጥ እየሰጋች: አሌክስ መኪናውን እያሽከረከረ ጭኖችዋን በቀኝ እጁ እየደባበሰ የምትሆነውን አሳጣት: ያ ጨካኙ አሌክስ ሳይሆን የፍቅር መልአክ ሆነባት…
“አሌክስ አልቻልሁም አለችው እየተስለመለመች
ጥቂት ኪሎ ሜትር እንደተጓዙ።
“ትዕግስት ጥሩ ነው..."
“ኡፍ ስብከትህን አቁም። በሰዎች ሙያ ጣልቃ አትግባ መኪናዋን ይልቁንስ አቁም አለችው በትዕዛዝ መልክ፡ መኪናዋ ወደ
ዳር ወጥታ ቆመች ሞተሯ ጠፋ።
ከተቀመጠችበት ዞር ብላ እጆችዋን ዘርግታ የአሌክስን
አንገት አቀፈችው። ተገናኙ
ረሃብተኛዋ ከንፈሩን ጎረሰቸው እፅዋት በነፋሱ ጎንበስ ቀና ይላሉ ከርቤው እየጤሰ መላዕክት
እያጀቧቸው ሽቅብ በፍቅር ስረገላ አረጉ።
“አሌክስ! እኔ አላምንም... እንዴት ደስ አለኝ ለካ እንዲህ የደስታ ምንጭ ነህ እሰይ እንኳን ታገስኩህ እንኳን ቻልኩህ እንግዲህ ዳግመኛ ከፍቅር ሠረገላችን አንወርድም አይደል! ከምድር ላይ ይልቅ እዚህ ነፍስ ነህ..." እያለች ላዩ ላይ ተንከባለለችበት
የአትላንቲክ ውቅያኖስ ማዕበል በርቀት ከቆሙት መርከቦችና አጠገባቸው ካለው የድንጋይ ግንብ ጋር እየተላተመ አረፋ ሲደፍቅ
ከኮሎምበስ መታሰቢያ ግዙፍ ሃውልት ትይዩ የሚነፍሰው ጤሮ ንፋስ በጆሮ ግንዷ እያፋጨ ሲያልፍ ግን አይኗን ገልጣ ከገነት ወደ ምድር ተመለሰች። ምድሯን ውቅያኖሱን ስታይ አስጠሏት፡ አሌክስ
አሁንም አብሯት አለ ያ ሲያደርጉ የነበረውና አሁን አጠገቧ ባለው አሌክስ መካከል ግን ልዩነት ያለ መሰላት፤ ተጠራጠረችው።
“ማሬ የት ነው ያለነው?" ከሰመመኗ እንደነቃች ጠየቀችው።
“ሁዌልቫ ነን! ለስንብት አመች በመሆኗ የምሄድበትንም ከርቀት ላሳይሽ ስለምችል ሁዌልቫን መርጨልሻለሁ" አላት ሳብ አድርጎ ወርቃማ ዞማ ፀጉሯን ስሞ፡
“ሁዌልቫ” ይህ ስም ምድር ላይ ያውም ስፔን ውስጥ
የምታውቃት ከተማ ስም ነው:
“ለምን ግን እዚህ አመጣኸኝ?” ተሸበረች:
“ለስንብት አልሁሽ እኮ! አላት ወደ እሱ ጠጋ አድርጎ
እያቀፋት ሰውነቱ ሰውነቷን ሲነካት እየዘገነናት
“የምን ስንብት?... ደግሞ እንዴት ጨካኝ ነህ?... በአንዴ ከደስታ ወደ መከራ ትመልሰኝ..." አለችና ልሳኗ ተዘጋ: አሌክስ ሲስማት ከንፈሯ እንደ በረዶ ቀዘቀዛት።
ዙሪያቸውን እንደ እንቦቀቅላ ህፃን ድክ ድክ የሚሉት
እርግቦች አንዳች ነገር እንደመጣባቸው ሁሉ ድንገት ግር ብለው ወደ
ሃይቁ አቅጣጫ በረሩ።
አኜስ የአሌክስን እጆች ወርውራ እርግቦችን
ተመለከታቸው።
እጥፍ ብለው እንደገና ሽቅብ ጎነው በረሩ: አሌክስ ፊቷን ወደ እሱ አዙሮ
“ሰርቶ መበልፀግ ስመኘው የኖርሁትን እድል በማግኘቴ
ረክቻለሁ። ፍቅራችን ከብልፅግና ማግስት.. ጆሮዋ ደነቆረ: ከዚያ በኋላ የሚለውን አልሰማችውም።
ፍቅር ከብልፅግና
ማግስት…" አባባሉ በአእምሮዋ አስተጋባ:
ዛሬን አበላሽቶ ነገን ማስዋብ ፍቅርን ገፍትሮ ጥቅምን ማቀፍ
ተምታታባት እሪ ብለሽ ጩሂ አሰኛት… መጮህ ግን ተሳናት::ለመጮሀም ኃይል ያስፈልጋል።
አሌክስን ጠላችው 1
ገፋችው... ከዚያ እርግቦቹ ወደ ሄዱበት አቅጣጫ በረረች “አዕዋፍ ለካ ወደው ከምድር ርቀው አይበሩም ብላ በአየር ላይ ለመብረር ወደ ሰማዬ ሰማያት ለመጎን ሞከረች ትናንሽ ፍጡራን የፈፀሙትን ግን መፈፀም ተሳናት።
ይህ ከሆነና ከአሌክስ በተለየች በአምስት ዓመቷ “አሽቀንጥሬ ጣልሁት ያለችው የከንፈር ወዳጅዋ አንደገና ራባት። ፍቅሩ አገርሽቶ ጤና አሳጣት ስለዚህ ፓርቶሪኮን ለመጎብኘት በሚል ሽፋን ወደ ሳንጁአን ሄደች።
ሳን ጁአን እንደደረስችም አሌክስ በሰጣት የእርሻ ጣቢያ ማዕከል አዳራሻ ሄዳ አሌክስን እንዲያገናኝዋት ጠየቀች። በእርግጥ

👍28
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
እራሴን አመም ስላደረገኝ አስፈቅጄ ወደቤት ስገባ ሶስት ሰዓትም አልሆነም።..ሹክክ ብዬ ገብቼ አልጋዬ ላይ "በመውጣት አረፍ እንዳልኩ ስልኬ ጠራ...አሁን ማንንም ቢሆን አንስቶ የማናገር ፍላጎት የለኝም የዜና ወርቅም ብትሆን እንኳን፡፡ስልኩ መጥራቱን ቀጥሏል ማንም ቢሆን ላለማንሳት ድምዳሜ ላይ ከደረስኩ ማንነቱንም ማየት አስፈላጊ አልነበረም ..እኔ ግን እጄን ሰድጄ ስልኬን አነሳሁ፡፡ እስክሪኑን ወደአይኔ አስጠጋሁ..ተፈናጥሬ ከመኝታዬ ተነሳሁና ቁጭ አልኩ..እንዳይዘጋብኝ እየተስገበገብኩ አነሳሁት..
‹‹ሄሎ የእኔ ውድ..?
"ሄሎ አባዬ እንዴት ነህ?
"አለሁልሽ ..በጣም ሰላም ነኝ..አልተኛሽም እንዴ?"
"አይ ገና ልተኛ እየተዘጋጀሁ ነው...አባዬ የእኔ ክላስ የትኛው እንደሆነ ታውቃለህ አይደል?"
በምናብ ወደ አደኩበት ቤት ፈረጠጥኩ..ሁሉንም ክፍሎች በሀሳቤ ቃኘሁ ከእነቴቴ መኝታ ቤት ቀጥሎ ያለችው ክፍል ነች አይደል?"ግምቴ መቼስ የቤቱ ትንሽዬ ህፃን ስለሆነች ለቁጥጥርም ለሊት ተነስቶ ደህንነቷን ለማየትም ቅርብ ያለው ክፍል ነው የሚመረጠው ብዬ ነው...፡፡
"አይደለም..እዛ ህፃን ሆኜ ነበር አሁን ትልቅ ስሆን የአንተና የእማዬ የነበረውን ክፍል ወሰድኩት
ደነገጥኩ"በእውነት እሱ ክፍል መኖሩ ትዝ አላለኝም ነበር፡፡ እንደዛ ያልኩት ከዛ ሁሉ ዝብርቅርቅ ክስተት በኃላ እቴቴ ክፍሉን ምንቅርቅር አድርጋ የአንድን ሳይድ ግድግዳ በመደርመስ ከሌላው ጋር በመቀላቀል ክፍሉ ለታሪክነትም እንዳይታወስ የምታደርገው ነበር የሚመስለኝ ..ለዛ ነው ያንን አይነት ጥያቄ የጠየቅኳት"
"ልጄ ሳይገኝ ያ ክፍል አይከፈትም ብላ ከእነዕቃው አሽጋበት ነበር...ከዛ እኔ አክስቴ ትልቋን ለመንኩና እሷ በሌለችበት አስከፈቼ ገባሁበት፡፡"
"ታዲያ አልተቆጣችሽም?"
"አይ ምንም አላለቺኝም ግን አለቀሰች፡፡"
እኔም አሁን አለቀስኩ የሚቆጠቁጥ እምባ በቀኝ ጉንጬ ረገፈ"የእኔ ማር እናትሽ ለእቴቴ ትደውልላታለች አይደል?"ድንገት በእምሮዬ ብልጭ ያልኝን ጥያቄ ጠየቅኳት፡፡
"ትደውልላታለች...እቴቴ ግን ትሰማታለች እንጂ አታናግራትም፡፡"
"ለምን?"
‹‹"እኔ እንጃ አባዬ...የሙት እህቴን ቃል እንድበላ አደረጋኛለች..ልጄን ወይ በህይወት አልያም ሞቶ ከሆነ ሬሳውን አግኝቼ እርሜን ሳላወጣ ከእሷ ጋር ባወራ እግዜር ይቀየመኛል ትላለች...ግን አባዬ እርም ማውጣት ማለት ምን ማለት ነው?።››
"ቁርጥ ማወቅ ማለት ነው የእኔ ልጅ"ቀላል ነው ብዬ ባልኩት ቃል ገለፅኩላት።
"አባዬ"
"ወዬ የእኔ ልጅ"
"እቃችሁን ስጎለጉል የእማዬ ማስታወሻ ደብተር አገኘሁት..ሁል ጊዜ አነበዋለሁ.. ደስ ይላል..።"
"እናትሽ ማስታወሻ ደብተር ነበራት እንዴ? እኔ አላውቅም..."
"አዎ አላት ..ትልቅ ሰማያዊ ደብተር....እና ደግሞ ስላንተ ብቻ ነው የፃፈችው...ትንሽ ትንሽ አንብቤው ስላልገባኝ ተውኩት.. ››
የእውነትም በጣም ተገርሜ "በእውነት ይገርማል .!"አልኩ ፡፡
በድንገት ማስታወሻው ላይ ያለውን ሀሳብ ለማወቅ የሚቀስፍ አይነት የጉጉት ስሜት ተሰማኝ..ልጄ የውስጤን እንዴት ማንበብ እንደቻለች አላውቅም"አባዬ ከፈለክ ትንሽ ትንሽ ፎቶ እያነሳው ልልክልህ እችላለሁ"ደ
ተነቃቃሁ"እንዴት አድርገሽ?"
"ቴሌግላም መጠቀም እኮ በጣም እችላለሁ...ለእማዬ ፎቶዬንና የፈተና ውጤቴን እያነሳሁ ሁሌ ነው የምልክላት"
"በጣም ደስ ይለኛል የእኔ ማር...በይ አሁን ተኚ"
"እሺ አባቢ ..ደህና እደር...እወድሀለሁ"
"እኔም እወድሻለሁ"
ስልኩ ተዘጋ...እራስ ምታት የሚባል ነገር ከጭንቅላቴ ተጠራርጎ ወዴት ጥርግ እንዳለ እኔ እንጃ።ልጅ መድሀኒት ነው የሚባለው ለካ ዝም ብሎ አባባል አይደለም፡፡
ስልኬ ተንጣጣ...ሚሴጅ ነው..ከልጄ ነው ከፈትኩት
‹‹ልኬያለሁ›› ይላል ወዲያው ዳታ አበራሁና ቴሌግራም ከፈትኩ .ተአምር እዬብ ሁለት ፋይል ልካልኛለች...የእኔ ቅመም ልጅ...፡፡ዳውን ሎድ አደረኩትና ከፈትኩት ፡፡ እውነትም ልምድ አላት ፡፡ፍይሉ በጥራት የሚነበብ በጥንቃቄ ተነስቶ የተላከ ነው።የእናቷን የእጅ ፅሁፍ ሳየው ሰውነቴን ነዘረኝ ፅሁፍና ምስሏ በአእምሮዬ እየተፈራረቀ ትዝታ ውስጥ ጨመረኝ...ምን አለ እህቴ ባትሆኚ።ትራሴን አስተካክዬ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩና ማንበብ ጀመርኩ።
ግንቦት 5/2008 ከምሽቱ 5 ሰዓት
እቤታችን ሲመጣ 9 አመቱ ነበር ።የመጣበትን ቀን በደንብ ነው የማስታውሰው እማዬና አባዬ ለቅሷ ብለው ወደ አዲስአባ ከሄዱ ከሳምንት በሀላ ነው ጥቁር በጥቁር ለብሰው ፊታቸው ጨልሞና ከፍቶቸው ሌላ የከፋው ፤ለንቦጩን የጣለና ግራ የገባው ልጅ ይዘው የመጡት፡፡ልጁን ቀድሞውንም አውቀዋለሁ፤ ያውቀኛል፡፡ አዲስአባ ያለችው የአክስቴ ልጅ ነው።የአሁኑ አመጣጡ ግን እንደከዚህ ቀደሙ ቦርቆና ፈንድቆ ከእኔና ከእህቶቼ ጋር ለአራት ለአምስት ቀን እቃ እቃ ተጫውቶ ለመመለስ እንዳልሆነ ገብቶኛል።
ትላልቅ ሰዎች አክስቴም ባሏም በድንገተኛ አደጋ ዘእንደሞቱ ሲያወሩ ሰምቼያለሁ ..ግን ይሄ ድንገተኛ አደጋ የተባለው ሰውን የሚገድል አውሬ ምን አይነት ነው?ስል በወቅቱ በነበረኝ የልጅነት አዕምሮዬ አሰብኩና በጣም ተበሳጨሁ። አክስቴን በተመለከተ ጣፋጭና የማይሳሳ አይነት ትዝታ ነው ያለኝ።በሶስት ወር ሆነ በስድስት ወር ልትጠይቀን ስትመጣ ..ኬክ፤ቸኮሌት፤ እና ልብስ ቀሚስ፤ ቲሸርት ጫማ ብቻ አንድ ነገር ይዛልን ትመጣ ነበር።
ትምህርት ቤት ሲዘጋ ደግሞ አዲስአባ እንሄዳለን...ያንን ቢሄድ ማለቂያ የሌለውን ከተማ በፈንጠዝያ ስንዝናናበት ቆይተን ሽክ ብለን በአዳዲስ ልብስ አሸብርቀን እንመለሳለን..አመቱን ሙሉ ከደብረብርሀን ወጥተው ለማያውቁ ጓደኞቻችን ስለአዲስአባ ተረት መሰል ታሪኮችን እየተረክን ስንጎርርባቸው እንከርማለን ለእኔ የአክስቴ ሞት ትርጉም በዛ የጨቅላነት ዕድሜዬ እንኳን በደንብ ነበር የገባኝ...ከአሁን በሀላ ከአዲስ አበባ የሚመጣልኝ ምንም ኬክ ሆነ ቸኮሌት እንደማይኖር ገባኝ..ዘናጭና ፍሽን ቀሚሶችም ከአክስቴ እንደማይበረከቱልኝ ከሁሉም በላይ ግን ክረምት መጥቶ ት/ቤት በተዘጋ ቁጥር አዲስአበባ ሄዶ መዝናናት የማይቻል መሆኑን ምን አልባትም ትልቅ ሰው እስክሆን አዲስአበባን እንደማላያት ተረዳሁ..
እና እዬቤን እማዬ ከሌሎች ሀዘንተኞች ጋር ይዛው ስትመጣ እላዩ ላይ ተጠምጥሜ አንገቱን አቅፌ አለቀስኩ..ቢያባብሉኝ እራሱ ላቆም አልቻልኩም... በወቅቱ እንደዛ ማለቀሴ አክስቴን አስታውሼ ነበር. የምታመጣልኝ ኬክና ቸኮሌትም ስላማራኝ ነበር...እናም አዲስአባም መሄድ ስለፈለኩ ግን ደግሞ እንደማልችል ስለገባኝ ነበር.፡
.ታላላቆቼ በድርጊቴ ግራ ቢጋቡም እኔ ግን በጣም አዝኜ ነበር..እና ለእዬቤ የራሱ አልጋ ከአዲስአባ እስኪመጣለት አልጋዬን አጋራሁት..እርግጥ አብዛኛውን ጊዜ እማዬ እያለ ሲቃዠና ሲንፈራገጥ እማዬ እየመጣች ወደራሷ መኝታ ቤት ትወስደውና ከማዬና አባዬ መሀል ይተኛ ነበር...እንደዛ ሲያደርግ እኔም ምን አለ አብሬው ሄጄ መሀከላቸው በተኛሁ እላለሁ፡፡እኛ ልጆቻቸው እንደው ፍርጥ እንላታለን እንጂ ከእነሱ ጋር የመተኛት እድል አናገኝም።እና በዚህ አይነት ሁኔታ እዬቤ ወንድማችን ሆነ፡፡ እቃቸው ከአዲስአባ መጣና ከእኛ ቤት እቃ ጋር ተቀላቀለ..ቤታቸውም እንደተከራየ እማዬ ስታወራ ሰምቼያለሁ። አልጋውም መጣለትና ከእኔ አልጋ ጎን ቦታ ተመቻቸለት።ግን ስንላፋና ስንጫወት ቆይተን ሳናስበው ወይ እሱ አልጋ ላይ ጥቅልል ብለን ተቃቅፈን

👍67❤3👎1🥰1