#የዘርሲዎች_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ካርለት ድንኳናን ዘግታ ስትፅፍ የሰው ኮቴ የሰማች መሰላትና ጆሮዋን አቁማ አዳመጠች
"ካርለት?"
"የስ" ብላ ቶሎ በማስተካከል "ዬ! አለች - እንደ ሐመር ልጃገረዶችı ካርለት የጠራት ሰው ማን እንደሆነ አውቃዋለች
ደልቲ ነው ቀብራራው ጀግና የድንኳኗን ዚፕ ከፍታ ፈገግ ብላ አየችው" ሰውነቱ በአኖ (ከኦሞ ወንዝ ዳር በመጣ የተላቆጠ አፈር)
ተዥጎርጉሯል፥ ጴሮው (መሃል አናቱ ላይ ባለው ጌጥ) ላይ የተሰካው
የቀጭኔ ላባ በንፋስ ይርገበገባል ... እሱ ግን ፊቱን ዞሮ በርኮታው
ላይ ቁጭ ብሎ ጥርሱን በልምጭ ይፍቃል"
አንቺ ንብ አደለሽ
ምነው ቀፎሽን ዘጋግተሽ መቀመጥሽ
"ደልቲ ንፋሱ: ልጆችም
እንዳያስቸግሩኝ አለችው
ፈገግ ብላ እያየችው" እሱ ግን መልሷ አልተዋጠለትም ይህች ሰው! ነፋስና ልጅ የምትጠላ ምን ልትወድ ነው እህ! ብሎ ቆሽቱ
እያረረ ሃሣቡን ሳይናገር ከታጠቀው ዝናር አንድ ቀላህ አውጥቶ
ውታፏን ከፈተና በአውራ ጣቱ ጀርባ የትንባሆ ዱቄት ፈሰስ አድርጎ ጎንበስ ብሎ በአፍንጫው ቀዳዶች ሞዠቅ ሞዠቅ አድርጎ ሽቅብ ማገና በዐይኖቹ እንባ ፍጭጭ ብሎ ደጋግሞ ካስነጠሰው በኋላ
ትንባሆውን ለካርለት አቀበላት በሐመር ሴት ልጅ ትንባሆ መሳቧ ነውር የለውም! በፍቅረኞች መካከል ትንባሆ (ሱረት) መሰጣጣት ደግሞ አንዱ የመግባባታቸው ምልክት ነው።
"ሽማግሎች ለዛሬ ከብት ውጋ ብለውኝ ይኸው በሬዬን ይዠ መጣሁ" አላት ካርለት ትንባሆው ካስነጠሳት በኋላ ምክንያቱን የሰማች ቢሆንም ከእሱ አንደበት ለመስማት ብላ።
"ምነው ምናጠፋህ?" ስትለው መፋቂያውን አኘክ አኘክ አድርጎ ተፋና ረጋ ብሎ፣
"አንች ሰው ምነው ሥርዓት ቢኖርሽ ሴት በየት አገር ነው
የወንድን ጥፋት የምትጠይቀው?" አላት ደልቲ ካርለት እንዲህ
ስታጠፋ ጎንበስ ብላ እግሯን
እንድትይዝ አድርጎ ጡቷን
እንዳይመታ እየተጠነቀቀ ሁለት ሶስት ቀን በባራዛ አርጩሜ ደህና አድርጎ እየገረፈ ቢገራት ልክ እንደ ስልጡን አህያ ትሰግር እንደነበር አስታውሶ እህ! ሽማግሎች እንዳሉትስ በመታረሚያዋ ጊዜ
ስታጠፉ እኔ እንጂ ሌላ ማን ይታዘንበታል! ብሎ አዝኖ ጢቅ አድርጎ ምራቁን ተፋና ጥርሱን ይፍቅ ገባ።
"ጎይቲ ስታለቅስ ነው የምትውል አይተሃት ታውቃለህ?"አለችው ካርለት በጥያቄዋ ጎርጉራ አንድ አዲስ ነገር ባገኝ ብላ።
"ሰማሁ! እኔን እህቴን ምን የከፋ ችግር መጣባት! አዘነ
ደልቲ።
"ለዚህ ምን መፍትሔ አለው ታዲያ?" ስትል ካርለት ደልቲ
ሰረቅ አድርጎ አይቷት
"ምን መፍትሄ ይኖረዋል ሽማግሌ ያለውን መቀበል ነው እንጂ።
"ጎይቲ ከከሎ ጋር ከተጋቡ ወዲህ እኮ ሌላ ወንድ አታውቅም "እንደገና ለዓመል ያህል ሰረቅ አድርጎ እንደዘበት አያት የለበሰችው
ቆዳ የፊተኛው ክፍል ጉያዋ ውስጥ ተሸጉጦ: የቀኝ ጭኗ ውስጥ ክፍል እንደ ጥጥ ንጥት ብሎ ታየው"
"ተታናናሽ ወንድሞቹ ጋርስ አልቀበጠችም?"
"ከሎ ታናሽ ወንድም እኮ የለውም ሁሉም የእሱ ታላላቆች ናቸው"" ስትለው ታናሽ ወንድም እንደሌለው እያወቀ የረሳበት ምክንያት እየገረመው
"ተዘመዱ ወንዶችስ ጋር?" ካርለት የሰጎን ላባ የሰካበት ጴሮ የተተለተለውን ሳንቃ ደረቱን እንደ አቦ ሸማኔ ቀጠን ያለ ወገቡን አይታ ምራቋን ከምላሷ ስር መጣ ዋጠችና,
"ከማንም ጋር አልቀበጠችም ካለ ከሎ በቀር" አለችው
"እህ!" ሲል ካርለት ቀጥሎ የሚለውን ለመስማት ጆሮዋን መዘዘች እሱ ግን ጭራሽ ያልጠበቀችውን ጥያቄ
"የምጠጣው ውሃ ትሰጭኝ?" አለ ከኮዳዋ በኩባያ ቀድታ ውሃ
ስትሰጠው ቀና ብሎ አይቷት
"እሱን አንች ጠጭው፤ ለኔ በሾርቃ ስጭኝ" አላት ካርለት ውሃ ለማምጣት ሄደች ደልቲ አረማመዷን÷ ዳሌዋን ወገቧን ከኋላዋ የሚወናወነውን ቆዳዋን ጥርሱን እየፋቀ አየና ምራቁን ጢቅ አድርጎ ተፋና የበረቱ ከብቶች ቀለማቸው የተለያዬ ነው ቀይ፥
ዳልቻ: ነብርማ: ነጭ የካርለትም ቀለሟ ነጭ መሆኑ ሚስቶቹን
እንደ ከብቶቹ ቀለም ማሳመሩን ሲያስብ የደስታ ስሜት ተሰማው መልሶ ደግሞ የሐመር ልጃገረዶች እንዳለቁ ሁሉ ከዚች አግድም አደግ ጋር ቢቀርብኝስ ብሎ አሰበ አንዴ ግን አገባሻለሁ ብሏል1
ስለዚህ ቃሉን ማጠፍ አልፈለገም ግዴለም አገባታለሁ ድምጿ ግን
ምነው ተዛሬ ነገ ቃናው አይጣፍጥ? ብልግናዋና ድምጿ እንጂ ሴትነቷስ እያለ ሲያስብ ካርለት ውሃ በሾርቃ ይዛለት ብቅ አለች
ከርቀት እያያት ደሞ ደህና ገብሮ የነበረው ሰውነቷ እንደ ምስጥ ንጉስ ተመልሶ ለሰለሰ እያለ ሲያስብ ካርለት ሰው ጠርቷት
ዘወር ስትል የጀርባዋ ሰንበር ታየው ከሎ ከብት ሲዘል የተገረፈችው"
ደልቲ ትንሽ ፈርጠም ብሎ ሳቅ አለ ካርለት
አላየችውም ትዝ አለው ስትገረፍ ሰውነቷ የተንቀጠቀጠው ወድቃ
የተዘረረችው
ባለጌ! ብሎ ተቆጨና መልሶ ደግሞ አዘነላት ጀርባዋ ላይ
ያሉት የግርፊያ ሰንበሮች ጥቂት ናቸው ለሐመር ልጃገረድ ደግሞ
የግርፊያ ሰንበር ሌላው ውበቷ ሲሆን ዳንስ ቦታና ጫካ ውስጥ ወንዱ
እንደ አኮርዲዎን መጫወቻ ሰንበሮቹን በጣቱ እየነካካ የፍቅረኛውን የፍቅር ቅላፄ በማስተካከል የጋራ የፍቅር ስሜት የሚፈጥሩበት ነው
ሴቷና ወንዱ
በልጃገረድ ጀርባ ላይ ባለ የግርፊያ ሰንበር ላይ ሻካራ የእጅ ጣት ጫፎችን ማንቀሳቀስ ትናጋው በፍቅረኛው ምላስ የተነካ ያህል በስሜት ንዝረት መላ ሰውነቱ ያረግዳል ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ
የግርፊያ ሰንበሯ ጀርባዋ ላይ የበዛ ዘመደ ብዙ' ካነሰ ደግሞ ዘመደ ትንሽ ናት ይባላል ብዙ ጊዜ ልጃገረዶች እርስ በርስ
ስለዚህ ሲጨዋወቱ
ይእ! ይሄ ሁሉ ማን ሲዘል የተገረፍሽው ነው? ተብላ
የተጠየቀች እንደሆነ እጅዋን አዙራ ጀርባዋን እየዳሰሰች
ይእ! ይሄ የባልዳምቤ
ይሄ የሸረምቤ ይሄ የላሎምቤ …እያለች ትዘረዝራለች ልጃገረዷ በእነዚህ ሁሉ ዘመዶችዋ ስትፎክርና ሳትፈራ ስትገረፍ ያያት ደግሞ ስንትና ስንቱ ወንድ ተመኝቷታል ከስንቱ ጋርስ ቀብጣለች ሊያገባት የፈለገውስ እንዴት እንደሚበዛ መገመቱ አይቸግርም አንድ
የሐመር ወንድ ደግሞ ሌላው የተመኛትን ያፈቀራትን የራሱ አድርጎ ከማግባት የበለጠ ትልቅ
ክብር የለም በሐመር የጋብቻ አለም።
ካርለት ግን የተገረፈችው ለአንድ ቀን ብቻ ነው፤ የዛን ቀንም ግረፉኝ ብላ አልፎከረችም ስትገረፍም ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ
ስታለቅስ በመጨረሻም ህሊናዋን ስታ ስትወድቅ ምድረ ጎረምሳ ተሳስቆባታል እንጂ ማንም ለፍቅር አልተመኛትም ደልቲ ይህን
አስታውሶ
ወዲህ ወዲያ ስትል እንደ ፍየል ጅራት ስትወናወን እንጂ እሷስ ብትሆን ስንትና ስንት ዘመዶችዋ ከብት ሲዘሉ ብትኖር ኖሮ
የመገረፉ እድል መች ያመልጣት ነበር! እያለ ሲትከነከን ካርለት
አጠገቡ ደርሳ ውሃ የያዘ ሾርቃውን አቀበለችው
እየተጉመጠመጠ ደጋግሞ ተፋና ስምጥጥ አድርጎ ጠጥቶ ባይሮ ኢሜ ብሎ
አመሰገናት እግዜር ይስጥልኝ ለማለት
ካርለት ሾርቃውን
ሾርቃውን ልትመልስ ሄደች ያን ጊዜ ደልቲ ደሙ ፈላ ነደደው ተቀብላ ፈንጠቅ አድርጋ ደፋችውና
ይህች አሳሳች! ብሎ እራሱን ለማረጋጋት እየሞከረ ከመቀመጫው ተነሳ
"ይእ! እህ የታል አያ ደልቲ? አለ አሁን ውሃ ብሎኝ
ሰጥቸው መጣሁ አላልሽኝ?" አለች ጎይቲ ከካርለት ጋር ወደ ድንኳኗ
እየተጠጉ
"ጎይቲ አሁን እኮ እዚህ ቁጭ ብሎ ስናወራ ቆይተን ውሃ ስጭኝ ብሎኝ ሰጥቸው ሾርቃውን መልሼ: አንችን ጠርቸሽ መጣን በዚህ ቅፅበት የት ሄደ?"
"ይእ! እኔን ትጠይቂያለሽ ደሞ ይልቅ አንች ምንሽ ውስጥ ከተትሽው? አያ ደልቲ መቼም ካለ ነገር እንዲህ ሹልክ ብሎ እንደ
ሌባ አይጠፋም ተቀያየማችሁ?"
"ኧረ በጭራሽ"

👍27❤2
#ባል_አስይዞ_ቁማር
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
‹እማዬ…አንቺ እማዬ……››
እታች ምድር ቤት ሁሉም ከየክፍሉ እየወጣ እሷ ወደአለችበት የመጀመሪያ ፎቅ የሚያስወጣውን መወጣጫ ግር ብለው በመምጣት መክበብ ጀመሩ…. እናቷ ከእሷ ፊት ለፊት ካለው መኝታ ቤቷ ልብሳቸውን እንኳን በቅጡ ሳይለብስ በተለመደ ድንጋጤዋ እያለከለከች
‹‹ምን ተፈጠረ ልጄ.?ደግሞ ምን ሆነሽ ነው?››
‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ያሳደግሺኝ?››ጮህችባቸው፡፡
‹‹አረ ተረጋጊ ልጄ …እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው.?››
‹‹እኔ ለምንድነው እንደሌላው ሰው ጥሩ መሆን የማልችለው…? እኔ ለምንድነው ስርዓት የሌለኝ? አለሌ የሆንኩበት ምክንያት ምንድነው›?
እናቷ የምትለፈልፈውን ሌሎች ሰራተኞች እንዳይሰሙ በመጨናነቅ ይመስላል እቅፍ አረጓትና የሚወራጩ እጆቾን አንድ ላይ በዛ ግዙፍ ሰውነታቸው በመጭመቅ አንጠልጥለው ወደመኝታ ቤታቸው አስገቧትና አልጋዋ ላይ በማሳረፍ በራፍን ሄደው ዘጉት…እሷም ከንዴቷ እንደመብረድ ብላ ሹክክ ብላ ተነሳችና ሙሉ በሙሉ ወደ አልጋዋ ላይ ወጣች..፡፡ከውስጥ ገባችና ተኛች…፡፡በቃ ደከማት..እናቷም እንደእሷው አደረጉ፡፡ ቀስብላው ወደአልጋው ላይ ወጡና ከጎኗ በመተኛት ክንዳቸውን አንተርሰው ከራሳቸውጋር ልጥፍ አደረጓት፡፡
ሰው ሲከፋው እንዲህ እንደእሷ ሮጦ የሚወሸቅበት ጉያ ወይም ተንተርሶ የሚተኛበት ክንድ ወይም እቅፋ ውስጥ ገብቶ የውስጥ ቁጣውንና ለቅሷውን የሚያቀዘቅዘዝዝት ምሽግ ካላው እድለኛ ነው። ሲከፍ ወደ መጠጥ ቤት ሮጦ አልኮል ከመጎንጨት የሚያፈቅሩት ሰው እቅፍ ውስጥ ኩርምትምት ብሎ በማልቀስ የመረጋጋት አማራጭን መጠቀም ውጤታማና ብልሀት የታከለበት ውሳኔ ነው።በተለይ ያ ክንድ እንዲህ እንደልዩ የእናት ሲሆን የቀጥታም ሆነ የጎንዬሽ ጉዳቱ ለዜሮ የቀረበ ነው።
‹‹የእኔ እርግብ…. አንቺን የሚስተካከል ደግ የለም እኮ…ከአንቺም እኩል ለሰው አዛኝ እና ሰናይ ምግባር ያለው ልጅ ማግኘት ከባድ ነው….ይሄን እኔ ብቻ አይደለሁም ሀገር ምድሩ ነው የሚያወራው…እዚህ ቤት የሚርመሰመሱ ሰራተኞች አንቺ ሲያምሽ አብረው ሚታመሙት፤ ፈገግ ስትይ ሲገለፍጡ የሚውሉ ናቸው እኮ...የሰፈሩ አሮጌት ምረቃትን ካንቺ እኩል የተመረቀ ማን አለ..?ከአኔ ከእናትሽ ቦርሳ እየመዠረጥሽ ለሰፈር አሮጊትና ሽማጊሌ ብሬን ስታድይ፤ የተመመ ችግረኛ ስታሳክሚ ፤መማር ላቃተቻው ህፃናት ደብተርና ዩኒፎርም እየገዛሽ ስታድይ አይደል እንዴ የኖርሽው?
ልጄ እኔ እንደውም ይሄ ሁሉ ደግነትና ቸርነት ከየት አምጥታው ነው ?እያልኩ ዘወትር እንደተደምኩብሽና እንደኮራሁብሽ ነው..አንቺ ይሄ ክፍ አመል ባይጠናወትሽና ባይለክፍሽ እንከን አልባ መልአክ እኮ ነበርሽ..ልጄ ታዲያ ምን ላድርግሽ እንድትፈወሺልኝ ያልሞከርኩት ህክምና የላጠጣሁሽ ጠበል የለም..የእኔ ቆንጆ ሰው ሲቸገር ምንም ነገር ለመሞከር ይደፍራል፤አጣብቂኝ የትኛውንም የተነገረውን ነገር ያምናል፤ የትኛውንም መጥፎ የተባለ ስምምነት ይፈርማል፤የትኛውንም የሚወደውን ነገር አሳልፎ ይሰጣል።አዎ ችግር እንደዛ ያደርጋል።እኔም በዚሁ በአንቺ ችግር ምክንያት የሰራሁትን ዛሬ ልንገርሽ…ሚስጥር አድርጌ ይዤው ነበር.. እግዜር ይቅር ይበለኝና ይሄውልሽ ጠንቆይ ቤት ሁሉ እኮ መፍቴ ይሰጠኝ መስሎኝ ሄጄ ጠይቄያለሁ….ግን መፍትሄ አልተገኘም፡፡
‹‹እጄን አስቆርጪው…በእጄ አይደለ ምሰርቀው…በቃ አልፈልጋቸውም.. ሁለቱ እጆቼ ይቆረጡ፡፡››
‹‹በስመአብ በይ ልጄ ..በስመአብ…የሚነሳው በእጅ ቢሆንም ቀድሞ የሚሰርቀው እኮ እዕምሮ ነው..እምሮሽን አላስቆርጥ?››
›‹‹እማዬ ብቻ እኔ አንዲህ እየተዋረዱ መኖር ሰልችቶኛል…ትንሽ ጊዜ ነው የምሰጥሽ ….ካለበለዚያ..››
‹‹ካበለዚያ ምን?››
‹‹እራሴን አጠፋልሻለሁ..ከዛ ግልግል ነው፡፡››
‹‹አረ ተይ ልጄ…. ተይ እኔ እናትሽ እንኳን አላሳዝንሽም..?ሌላ ትርፍ ልጅ እንዳለው ሰው እንዲህ ትያለሽ..? አንቺ እኮ ከታችም ከላይም የሌለሽ ብቸኛ ልጄ የአይኔ ማረፊያ ነሽ…እኔ ባለኝ ሀብት በአለም በየትኛውም ጥግ ለዚህ ፈውስ ቢኖር የምሰስት ይመስልሻል ?ለምን ብዬ…ከሰባራ ሳንቲም አንስቶ ሙሉ ካማፓኒው ያንቺው ነው..እኔ ከአሁን ወዲህ የምኖረው እራሴን ለማስደሰት ሳይሆን አንቺ በሁሉ ነገር የተሳካልሽ ሆነሽ ስትስቂ ለማየት ነው…፡፡››
‹‹እና ታዲያ ምን አድርጊ እያልሺኝ ነው?››
‹‹ካልሆነ ለሁለተኛ ጊዜ እዛው አሜሪካ ሂጂና ትሞክሪ ይሆን ?››
‹‹እማዬ እኔ የትም ሀገር መሄድ አልፈልግም..ደግሞ የፈረንጆች የቅዠት ሀሳበ መሞከሪያ መሆን ሰልችቶኛል፡፡››
‹‹እሺ.በቃ ከመድህኔ ጋር ተማከሬ የሆነ ነገር አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ከእሱ ጋር አትማከሪ በራስሽ ከቻልሽ አድርጊ ካለበለዚያ…፡፡››
‹‹በቃ በቃ. እሱን ለእኔ ተይውና ተኚ.›
እጃቸውን ፀጉሯ ውስጥ ከተው ሲዳብሷት የሆነ ፀጥ ያለ ውቅያኖስ ውስጥ እየዋኘች ያለች መሰላት…ወዲያው እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡
✨ይቀጥላል✨

👍102❤17👏3😁3
#ህያብ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በኤርሚ
"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"
"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ
"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."
"እኔ ምንም እየገባኝ አይደለም ቢኒ ምንድነው እያወራህ ያለኸው"
"ተረጋጊ እነግርሻለሁ.... ዮናታን የያዝነው ክፍል ድረስ መጥቶ እንድናወራ ጠየቀኝ.... እሺ ብየው ተያይዘን ወደ ሆቴሉ ባር አመራን እናም ቁጭ ብለን ያልጠበኩትን ነገር ነገረኝ"
"ቀጥል ምን አለህ"
#ምሽት_8_ሰዓት_ላይ
የሆነውን ሁሉ እኔ ነኝ የምተርክላችሁ.... ቢኒያም
ከዮናታን ጋር ወደ ባሩ ከወረድን በኋላ መጠጥ አዘዘ እና
"የውልህ ቢኒያም ተረጋግተህ እንድትሰማኝና ከቻልክ እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ..."
"ለማንኛውም የምትለኝን ልስማህ" እስከዚህ ድረስ እንኳን አብሬው የመጣሁት ድጋሚ ካስተማረን F እንዳያስታቅፈኝ በሚል ፍራቻ ነው
"ሁሉም ሰው የሚያውቀው እኔ ሴት አተራማሽ እንደሆንኩ ነው። በእርግጥ እውነታም አለው ጥቂት ከማይባሉ ሴቶች ጋር ግንኙነት ነበረኝ ግን ነበር ነው ከ2 አመት በፊት በመጀመሪያ እይታ አንዲት ልጅ ልቤ ውስጥ ገባች። እናም ልክ ለሌሎቹ እንደሚሰማኝ ተራ ስሜት ነው ብዬ የነበረው ህይወቴን ለመቀጠል ሞከርኩ ግን እንደድሮው መሆን አቃተኝ። ለተወሰነ ጊዜ ስወዛገብ ከረምኩና ፍቅሬን እንዴት መግለፅ እንዳለብኝና እሷን የኔ እንዴት እንደማደርግ ማሰብ ጀመርኩ።
ልጅቷ ኮስታራ እና የማያስቀርብ ፊት ነው ያላት ያለኝ አማራጭ አብራ ከምትማራቸው ሴቶች ስለሷ ሊነግረኝ የሚችል ሰው ፈልጌ መቅረብ ነበር እናም የትናዬትን ቀረብኳት...."
"ሰውዬ ስለምን እያወራህ ነው" እዚህ ጋ መምህር መሆኑን ረሳሁ
"ቢኒያም ለኔ ሁሉም ነገር የተገለፀልኝ ዛሬ ነው.... እና ከቻልክ ተረጋግተህ ስማኝ"
"ከየትናዬት ጋር ከተቀራረብን በኋላ በተደጋጋሚ ቢሮዬ እየጠራኋት ስለ ህያብ እንድትነግረኝ አደርጋት ነበር።"
"ምን እያልክ ነው እና ህያብን አንተም ታፈቅራታለህ" ማመን ከበደኝ
"አዎ ያውም በመጀመሪያ እይታ ነው ያንበረከከችኝ ለማንም ሴት እንደዚህ ሆኜ አላውቅም። የኔ ብትሆን ብዬ በምናቤ ስስላት የነበረችን ልጅ ነው በአካል ያገኘኋት"
"እሺ ከዛስ ምን ተፈጠረ"
" የትናዬት እንኳን ጠርቻት ሳልጠራትም እየመጣች ብዙ ነገር እንዳውቅ አደረገችኝ። የምትነግረኝ ነገሮች ግን ህያብን እንድቀርብ ሳይሆን እንድፈራ እና እንድሸሽ የሚያደርግ ነበር።"
"ምን ብላህ ነው"
"በመጀመሪያ ከሷ ጋር ኢለመንተሪ ጀምሮ አብረው እንደተማሩ እና እንደምትታየው ሳይሆን ውስጥ ውስጡን ወንድ አተራማሽ እንደሆነች ነገረችኝ። አላምንም ስላት በማስረጃ አረጋገጠችልኝ።"
"መቼ ነበር ያረጋገጠችልህ ማለቴ የት"
"ከአመት በፊት ካንተ ጓደኛ ጋር ቤርጎ ሲገቡ በአይኔ በብረቱ አየሁ እናም የምትለኝ እውነት እንደሆነ አረጋገጥኩ"
"የውልህ ዮናታን ያየኸው እውነት ነው ግን እንደምታስበው አይደለም። ጓደኛችን በሀይሉን ፍቅረኛው ከድታው ሌላ ሰው ጋር ሆነች እናም እሷን ማስቀናት እንደሚፈልግ ነገረን.... እኔም ለህያብ ነገርኳትና እምቢ ብትልም በግድ አሳመንኳት ከዛ ፍቅረኛው የምታይበትን ሁኔታ አመቻችተን አብረው ወደ ክፍል ሲገቡ እንድታያቸው አደረግን። ግን አንተ እዛ እንደነበርክ ማንም አላወቀም እንዴትስ ልትገኝ ቻልክ"
"የትናዬት ናት አላምንም ስላት 'ከቢኒያም ጋር ፍቅር ፍቅር እየተጫወተች የገዛ ጓደኛው ጋር ትማግጥበታለች' አለችኝ ማረጋገጥ ከፈለክ ብላ ወደዛ ቦታ ወሰደችኝ እና በአይኔ እንዳይ አደረገችን በሰዓቱ ራሴን መቆጣተር አቅቶኝ ነበር እናም እሱን ልደበድብ እሷን ልሰድብ ስራመድ የትናዬት አስቆመችኝ.... ከዛ በኋላ የምትለኝን ሁሉ አምናት ነበር እስከ ትላንትና ድረስ..... አሁን ግን ሁሉንም ከራሷ ከህያብ ነው ማረጋገጥ የምፈልገው"
ነገሩ ካሰብኩት ውጪ ሆነብኝ የትናዬት ተንኮለኛ ብትሆንም ይህን ያክል ርቃ ትሄዳለች ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።
"እሺ ሌላስ ምን ነገረችህ"
"አንተ ፍቅረኛዋ እንደሆንክ እና አዲስ አበባ ከሌላ የወለደቻት ልጅ እንዳለቻት"
"ምንድነው የምታወራው እኔ ከህያብ ጋር አብሬ ስለምታይ ፍቅረኛዋ ነው ብትል እሺ ግን ልጅ ከየት ፈጥራ ነው የነገረችህ...." ኪሱን በርብሮ የሆነ ፎቶ አወጣና እጄ ላይ አስቀመጠልኝ። ህያብ ልጅ አቅፋ.....
"ግን እኮ እህቷም ልትሆን ትችላለች" ካልኩ በኋላ ለእናቴም ለአባቴም አንድ ነኝ ብላ የነገረችኝ ትዝ አለኝ።
"አይደለችም ልጇ ነች ይሄን አረጋግጫለሁ ግን አንተ የምታውቅ ነበር የመሰለኝ"
"ኧረ በፍፁም ግራ እያጋባህኝ ነው" ፎቶውን ተቀብሎኝ ወደ ኪሱ ከተተና
"ቢሆንም ይሄ ጉዳዬ አይደለም.... ለሷ ያለኝን ፍቅር ያለፈ ታሪኳ ሊቀይረው አይችልም የሚያሳስበኝ የአሁኑ ነው..." ግንባሩን አሸት አሸት እያደረገ ትንሽ ከቆየ በኋላ
"ቢኒያም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እናም ሳትዋሽ መልስልኝ" አለኝ
"እሺ ጠይቀኝ"
"ከህያብ ጋር ፍቅረኛሞች ናችሁ?"
"አይደለንም" ፈገግ ሲል አየሁት
"እሺ ታፈቅራታለህ" ከንግግሩ እኩል ደነገጥኩ
"አይ አላፈቅራትም" መሬት ተንበርክኮ መሳም ነው የቀረው ደግሞ ደጋግሞ ፈጣሪን አመሰገነ... ሁኔታውን ሳይ የነገረኝ ሁሉ እውነት እንደሆነ ገባኝ።
"እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ"
"ጠይቀኝ" አለኝ በፈገግታ ተሞልቶ
"የትናዬት ፍቅረኛህ ካልሆነች ወይም የሆነ ግንኙነት ከሌላችሁ እንደዛ ተጠባብቃችሁ አንገትህን ስትስምህ...." ሳያስጨርሰኝ
"እሱ ለኔም የሚገርም አጋጣሚ ነበር። ህያብ እኛ ወደተቀመጥንበት ስትመጣ እኩል አየናት እናም የትናዬት ሳላስበው ጥምጥም ብላብኝ ሳመችኝ። ደንግጬ ስለነበር ላስቆማት አልቻልኩም ምን እያረግሽ ነው ብያት ዞር ስትልልኝ ህያብ ቆማ እያየችን ነው ወዲያው አንተ መተህ ወሰድካት"
"እንጂ ምንም አይነት ግንኙነት የላችሁም"
"ቢኖረን ለምን እዋሽሀለሁ"
ወደ ያዝነው ክፍል ከተመለስኩ በኋላ ረጅም ሰዓት ወስጄ ለማሰብ ሞከርኩ ከሁሉም አንድ ነገር ደጋግሞ አቃጨለብኝ.... "ህያብን ታፈቅራታለህ"
አዎ አፈቅራታለሁ አልኩ ጮክ ብዬ ልክ እንዳንተ መጀመሪያ ያየኋት ቀን ነው ልቤን የሰረቀችው ግን ምን ያደርጋል እሷ የምታፈቅረው አንተን.... ወዲያው በንግግሬ ደንግጬ ዝምም አልኩ ደግነቱ ከራሴ ውጪ የተናገርኩትን ማንም ሊሰማ አይችልም። ፍጥጥ እንዳልኩ ነጋ ግን ከራሴ ጋር ልስማማ አልቻልኩም እውነት ህያብ የሌላ ሰው ስትሆን ማዬት እችል ይሆን???
።።።
እኔ ነኝ ህያብ!
ፍንድቅድቅ ብያለሁ ከዚህ የበለጠ ምን ሊያስደስተኝ ይችላል በማፈቅረው ሰው መፈቅርን የመሰለ ምን ነገር አለ። ከነገረኝ ነገሮች ሁሉ ዮናታን ያፈቅርሻል የሚለው ሙሉ እኔን ተቆጣጥሮኛል።
"ህያብ ደስታሽን ላበላሽ ፈልጌ ሳይሆን እባክሽ ጥያቄዬን መልሽልኝ" ጮክ ብሎ ተናገረ
"ምን አልከኝ ቢኒ" በራሴ አለም ስዋዥቅ ምን እንዳለኝም አልሰማሁትም ነበር።
"ልጅ አለሽ" ከመደንገጤ የተነሳ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ።
"ህያብ እንደጓደኛሽ የምታይኝ ከሆነ እውነቱን ንገሪኝ ልጅ አለሽ" ከተቀመጠበት ተነስቶ እጄን ያዘና አንድቀመጥ አደረገኝ ከዛ በተማፅኖ አይን አይኔን ያይ ጀመር "እባክሽ ህያብ ላስጨንቅሽ ፈልጌ አይደለም... ግን ዮናታን ፎቶ ሲያሳየኝ ተጠራጠርኩ" የባሰ ድንጋጤ
"ምን? ዮናታንም ያውቃል"
"አዎ እሱ ነው የነገረኝ ስነግርሽ እኮ አልሰማሽኝም መሰለኝ"

👍48❤8🥰2👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
‹‹ጎሽ ጥለኸኝ አልተሰወርክም…አጠገቤ አለህ ማለት ነው? ››ስትል የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈሰችና…በከፍተኛ ፍራቻ እና ጥርጣሬ ዓይኖቾን ገለጠች…..ወንዝ የሚባል ነገር ስራቸው የለም…የሲኦል ምልክትም አይታያትም…. በሳር ፤ በትናንሽ አረንጓዴ ቁጥቆጦች እና የሚያማምሩ በቀለማት በተሸቆጠቆጡ አበቦች የተሞላ ወብ ቦታ ነው…ግን ግራ አጋቢ ቦታ…፡፡
ከስር መሬት ከላይም መሬት ነው የሚታያት ..ግዙፍ ዋሻ መሰል ነው እንዳትል ምኑም ዋሻ አይመስልም…የተለመደው አይነት ምድርና ሰማይ ነው የሚታየኝ ብላም እንዳትገምት በቆመችበት መሬት እና ወደላይ አንጋጣ በምታየው መሬት(ሰማይ) መካከል ያለው ልዩነት የሚታወቀውን ሰማይ ከመሬት የሚርቀውን ያህል እርቆ አይደለም የሚገኘው…በግምት ከመቶ ሜትር አይበልጥም፣
‹‹ተገልብጠን ከምድር ስር ይሆን እንዴ ያለነው….?ማለቴ ምድርን ከታች ወደ ላይ የምናያት..ማለቴ አሁን ላለሁበት ሚስጥራዊ ቦታ ምድር ሰማይ ትሆን እንዴ…?›ስትል በውስጧ ብትጠይቅም ለመግለጽ የፈለገችውን ሀሳቡ ለእሷው ለራሷ ተምታታባት…
ትክክለኛ መልስ ለመግኘት ወደ እሱ ዞረችና ‹‹የት ነው ያለነው…..?›› ስትል ጠየቀችው
‹‹እቤቴ››አላት
አበባ.. ትንንሽ ቁጥቋጦች.. እዚህም እዛም የሚፈልቁ ምንጮች… ለጥ ያለ ማለቂያው የማይታወቅ ሜዳ ነው የሚታያት‹‹ ….ይሄ ነው ቤትህ…..?››
‹‹አይ አይደለም….››አላት ፍርጥም ብሎ
‹‹….ቆይ ቆይ…›› እሰከአሁን በሁኔታው ተመስጣ ልብ ያላለችውን ነገር አየች…., ልብስ ለብሶም ሆነ እንደዚህ ሙሉ እርቃኑን ፊት ለፊቷ ቆሞ አይታው አታውቅም ነበር….እስከዛሬ ግምሽ አካሉ በውሀ እንደተሸፈን ከእምብርቱ በላይ ነበር የምታየው….በጣም ተገረመች…የምታየው ፍጥረት ሰው አይደለም….….?ሰው ካልሆነ ታዲያ ምንድነው ከተባለ መልሱ ለመግለፅ በጣም ይከብዳል…?፡፡ ምን ተብሎ እንደምትገለጽው እሷም ምንም አልገባትም ..እንደዚህ አይነት ፍጡር እሷ አይታ አታውቅም…፡፡እግሮቹ ጣት አልባ ናቸው… ልሙጥ እና እንደሰፌድ የተዘረጉ…ወይም የዓሳ ክንፍ የመሰሉ …..ብልቱ ደግሞ ምታህለው…ያልተገረዘች የሴት ቂንጥር በሏት… ወደ ፊት እንደባቄላ ነው አጎንቁላ የምትታየው…
ወይኔ ጉዴ››አለችና ሳቋ አመለጣት…ያሳቀት …?ስንት ቀን አሁን ቢደፍረኝስ .. ?እያለች የተጨነቀችው አጉል መጨነቅ በምናቧ መጥቶባት ነው …‹‹አሁን በዚች እንኳን መድፈር ሽንቱንስ መሽናት ይችላል…?›› የሚል ሀሳብ አሰበችና ሳቋን አረዘመችው …
ሌላው በትክክል ሰው አይደለም ብላ ያሰበችው ዋናው ምክንያት ባለጭራ መሆኑ ነው..ጭራ አለው፡፡ ጭራው ደግሞ ከኃላ ከመቀመጫው የላይኛው ክፍል በቅሎ ወደታች በመሄድ በእግሮቹ መካከል አልፎ ወደፊት ተቆልምሟል.‹‹.እንደውም ከእውነተኛው ብልቱ ይልቅ ጭራውን እንደብልትነት ቢጠቀምበት ያዋጣዋል›› ስትል በውስጧ አሰበችና ድጋሚ ፈገግ አለች፡፡
‹‹ስለእኔ ተፈጥሮ አስበሽ እና ተመራምረሽ ጨረሽ?››ብሎ አስበረገጋት
‹‹አይ ምን እመራመራለሁ….?እንዲሁ አዲስ ነገር ሆኖብኝ ነው እንጂ..››በአፍረት መለሰችለት፡፡
‹‹ግን አልፈራሺኝም…››
‹ለምን እንዳልፈራውህ እኔንም ገርሞኛል…?››የእውነትም ለምን እንዳልተንቀጠቀጠች…?ለምን ፊቷን አዙራ ወደተንጣለለው ሜዳ ፈርጥጣ እንዳልሮጠች …?ለምን ያንን ጆሮ ሰንጣቂ የዘወትር ጩኸቷን እንዳላስነካችው ?ለእሷም አልገባትም…በቃ ከመደነቅና ከመገረም ውጭ በስሜቷ ላይ ያስከተለው የጥላቻውም ሆነ የፍራቻ ስሜት አልነበረም….
‹‹ስለዚህ ወደቤት መሄድ እንችላለን?›› አለና ጎንበስ ብሎ የቆመበትን አካባቢ መሬት በእጁ ሲነካ በአስገራሚ ፍጥነት አብረቅራቂ የወርቅ ሳጥን ከተሰነጠቀው መሬት ተፈልቅቆ ወጣ…..
‹‹ፓንትሽን አውልቂ››አላት
‹‹ለምን …? ምን አስበህ ነው…?››ስትል ግራ በተጋባ ስሜት ጠየቀችው፡
‹‹በዚህች ዕቃዬ ምን አስባለሁ?›› አላት እና አሳፈራት….እሷም ልትለው የፈለገችው በዚህ ዕቃህ ምን ለማድረግ አስበህ ነው…›ነበር..ያው ልቧን በትክክል ነው ያነበበው፡
‹‹እንደዚህ ሆነሽ ወደ እኔ ቤቴ መግባት አትችይም …..ጨረር ይጎዳሻል››
መከራከሯን ትታ ፓንቷን አወለቅችና እጆቾን እፍረቷ ላይ አደራርባ ቆምች….በእጁ ካንጠለጠለው ሳጥን የሆነ ሰማያዊ መልከ ያለው የጠፈርተኞችን የሚመስል ልብስ አወጣና አለበሳት….ሙሉ በሙሉ በልብሱ ተጠቀለለች …ከዛ እጁን ወደ ፊት ሲዘረጋ እስከአሁን እይታዋ ውስጥ ያልገባ ግን ከቆመችበት በአንድ ሜትር ርቀት የነበረ ወርቅማ የብረት በር ወለል ብሎ ተበረገደ……ከዛ እቤት ሳይሆን አይታ የማታውቀው በምናቧ እንኳን ገምታው የማታውቀው በተረት አለም ብቻ የሚገኝ አይነት ምትሀታዊ የዘመነ ፤ የፀዳ እና ፀጥ ረጭ ያለ ከተማ ከፊታቸው ተነጠፈ…‹‹..እርግጠኛ ነኝ ይሄ ሁሉ እስከአሁን የሆነውና ያያሁት እውነት አይደለም….ህልም ላይ ነኝ ..ገና ከእንቅልፌም አልተነሳሁም›› በማለት እራሷን ለማፅናናትም ለማረጋጋትም ሞከረች….፡፡ግን አልተሳካላትም፡፡
…ምንም አይነት እሱን መሳይም ሆነ ሌላ ፍጡር ሳታይ ነው በወርቃማ ብርሀን ያሸበረቀውን ከተማ ሰንጥቀው እሱ ቤት የደረሱት፡፡ ይዞት የገባው አንድ ከግድግዳው ሰማያዊው ብርሀን የሚተፋ ቤት ውስጥ ነው ፡፡አራት ክፍል ቢኖሩትም ሁሉም ባዶ ነበሩ..ምንም ዕቃ የላቸውም…
‹‹እንዴ…ይሄ ነው ቤትህ..?››
‹‹አዎ ምነው… ?
አልወደድሺውም…?››
‹‹አይ ቤቱማ አሪፍ ነው..ግን ባዶ እኮ ነው….ቤትን ቤት የሚያሰኘው ደግሞ ጣሪያና ግድግዳ ብቻ ሳይሆን ውስጡም የሚገኝ መጠቀሚያ ቁሳቁስ ነው….››
‹‹ባዶ…››አለና ወደውስጥ ገብቶ ግድግዳውን ተጠጋና ማብሪያ ማጥፊያ የሚመስል ነገር ተጫነ..
ተአምር ተፈጠረ…ድፍን ግድጋዳው እየተከፋፈተ ፍሪጅ …ቴሊቭዝን የመሳሰሉት ዕቃዎች… ወለሉም እየተከፈተ ጠረጵዛ ወንበር በመውጣት እቤቱን ሞሉት…. አደመቁት…..
ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉን ነገር ችላ ብሎ‹‹አረፍ በይ …››አላት
‹‹ምን ጉድ ነው….!!እስኪ መኝታ ቤትህን አሳየኝ..?››ሌላ ተአምር ለማየት ከመጓጓት የመነጨ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
መጣና እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ ይዟት ሄደ …ወደ ቀጣዩ ክፍል….በተመሳሳይ ባዶ ነበር…
-‹‹የትኛውን ልጫን …››አለችው ግድግዳ ላይ ወደተለጠፉት ማብሪያ ማጥፊያ እጇን እየሰነዘረች
‹‹አልጋ ከፈለግሽ ነጩን ተጫኚ..››
ተጫነችው፡፡
ከእምነበረድ ይሁን ከእንጨት ይሰራ ለጊዜው መለየት ያቃታትን ነጭ አንሶላ ….ነጭ አልጋልብስ የለበሰ አልጋ ከወለሉ ውስጥ ተአምራዊ በሆነ ክስተት በመውጣት ተዘረጋ…..
‹‹ወይ እዚህ ላይስ መተኛት እፈልጋለሁ..››
‹‹ታዲያ ተኚያ …ማን ከለከለሽ››
‹‹ግን ይሄንን የለበስኩትን ደባሪ ልብስ ማውለቅ እችላለሁ?››
‹‹ቆይ… ››ብሎ ወደሳሎን ሄደ…. ምን እንዳደረገ ባታውቅም ወዲያው ሰማያዊው የነበረው የቤቱ መብራት ወደ ብርማ አይነት ተለወጠ…እሱ ተመልሶ እሷ ወዳለችበት መጣ
‹‹አሁን ትችያለሽ አውልቂው››አላት፡፡
‹‹ወይ እንዴት ደባሪ መሰለህ ››አለችና ለማውለቅ ብትሞክርም የተቆላለፉትን ነገሮች እንዴት ልትፈታታቸው እንደምችል አልገባትም... ምታደርገው ግራ ገባት
‹‹አቦ ምን ቆመህ ታየኛለህ ? ናና ከእዚህ ወጥመድ ውስጥ አውጣኝ እንጂ››ቁጣ የተቀላቀለበት ልመና አሰማች፡፡

👍119❤13🤔5👎2👏2😢1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
በዓይናችን ዓይተን ከወደድነው ነገር ይልቅ በምናባችን ቀርፀን ደጋግመን የተመኘነው ነገር ወደ ጣኦትንት የመቀየር ዕድሉ ሰፊ ነው፡
የውብዳር ለብ ባለ ውሃ ሠውነቷን ተለቃልቃና ፎጣ አገልድማ ፓንቷን በእጇ ይዛ ከባኞ ቤት በመውጣት ወደ መኝታ ቤቷ ልትገባ በእርምጃ ላይ ሳለች ሁሴን የሳሎኑን በር ከፍቶ ገባ፡፡
‹‹እኔ አላምንም፡፡ ቤቱን ማን አሳየህ?›› ወደ እሱ እየተራመደች ነበር የምትናገረው፡፡
ጉንጭ ለጉንጭ ከተሳሳሙ በኋላ ግማሽ እርምጃ ራቅ በማለት አስተዋላት፡፡ ድንቡሽቡሽ ያለች የምትበላ ብስል ቀይ ወይዘሮ ነች፡፡ ያገለደመችው ሮዝ ቀለም ያለው ፎጣ ከወገቧ እስከ ጉልበቷ ሸፍኗታል፡፡ ሌላው አካሏ እንደተጋለጠ ነው፡፡ ጡቶቿ አሁንም እንደልጃገረድነቷ እንዳጎጠጎጡ ናቸው፡፡ የቆዳዋ ጥራትም አስደምሟታል፡፡
‹‹ምን ያፈዝሀል? ቁጭ በል እንጂ›› አለችው፡፡ በእሷ ውበት መደመሙን ስታስብ ውስጧን የንዝረት ስሜት ተሰማት፡፡
‹‹ለምን አልፈዝ፡፡ ጓደኛዬ ለካ ይሄንን ሠውነት እንደ አሞሌ ጨው ሲልስ እያደረ ነው እንዲህ
‹‹ኡ . ኡ . ቴ <ቅጡም የምንኩስና ነው› አለች አክስቴ.... ለማንኛውም ልብሴን ለብሼ ልምጣ.... የሚጠጣ ከፈለክ ፍሪጁን ከፈት አድርግ፡፡›› በማለት እየተውረገረገች ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡
ሁሴን ፍሪጁን ከፍቶ ቢራ አወጣና እየተጎነጨ ማሠብ ጀመረ፡፡ ስለ ሰሎሞን ነበር የሚያስበው፡፡ በመጀመሪያ የውብዳርን ያፈቀራት ጊዜ ጨርቁን መጣል ነበር የቀረው፡፡ እሷን ማግባት ካልቻለ በህይወት መኖር
እንደማይችል ደጋግሞ ሲምል ነበር፡፡ በወቅቱ ደግሞ የእሷ ቤተሠቦች ፍቃደኞች አልነበሩም፡፡ ይሁን እንጂ የእሱ ፍቅር ብርታትና መስዋዕትነት የመክፈል ፅናቱ እሷንም ሙሉ በሙሉ በፍቅሩ እንድትጠመድና ከቤተሠቦቿ ፍቃድ ውጭ አሻፈረኝ ብላ እቤቱ እንድትገባ አስገደዳት፡፡ እናም ትዳራቸው በእንደዛ አይነት ሁኔታ በጽኑ ቁርጠኝነትና በከፍተኛ ደስታ ተጀመረ፡፡ ንብረት መጣ፣ልጆች ተወለዱ፣ሁሉ ነገር የሰመረ መሰለ፡፡ዳሩ ግን ውሎ አድሮ አካል ሲቀራረብ ፍቅር ቀስ በቀስ ከመሀከል ሾልካ ተነነች፤አንዳቸው ለአንዳቸው የወዳጅ ጠላት ሆኑ፡፡
‹‹እሺ አቶ ሁሴን... ደህና ነህ?›› እስከተረከዟ የሚደርስ ረጅም አብረቅራቂ ጥቁር ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ዊግ የተቀላቀለበት ሹሩባዋ ያምራል፡፡ የሁለት ጡቶቿ አካፋይ የስምጥ ሸለቆ ስንጥቅ መስሎ በከፊል ይታያል፡፡ የተቀባችው ሽቶ የሳሎኑን አየር በሠከንድ ነበር የቀየረው፡፡
‹‹አለሁልሽ... ከውዱ ባለቤትሽ ጋር ነበር የመጣነው ግን ከበራፍ ተመለሰ፡፡››
‹‹ምነው ውሽማው ጠራችው እንዴ?›. ግዴለሽ በሆነ አሽሞጣጭ ድምፅ ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ! ውሽማው ጋር ነው የሄደው፤ወይዘሪት ገንዘብ ጋር ።
‹‹እነ ዕፀ-ህይወት ትምህርት ቤት ናቸው እንዴ? ... የጫወታውን አቅጣጫ ወደ መጣበት ጉዳይ እንዲያመራላት ነበር ጥያቄውን የሠነዘረው፡፡››
<<አዋ>>
‹‹ልደታቸው ደረሠ አሉ፡፡ ለምን ዝግጅቱ በእናንተ ወጪ እኔ ቤት አይሆንም? በዛውም እኔ አገባበታለሁ፡፡ ‹ብልጥ ዝንጀሮ በሞኝ ክምር ያገባል› አይደል የሚባለው፡፡›› ፈገግ አለች... ስለመጨቃጨቃቸው እንደሰማ እርግጠኛ ሆነች‹‹ሀሳብህ ጥሩ ነው፤ ቢያንስ ከጓደኛህ ይሻላል፡፡››
‹‹የእሱ ሀሳብ እንዴት ነው?››
‹‹እንደነገረህ ነዋ ..! ሆቴል ይዘጋጅ ነው የሚለው፡፡ አሁን አሁን ምን እያሠብኩ እንደመጣሁ ታውቃለህ፤ ለእሱ ስል ይሄንን ሳሎን ወደ ሆቴልነት በመቀየር በመጠጥ ሞልቼ ለእሱ እንዲመች ማድረግ… ፡፡››
‹‹እንግዲያው ከጓሮ ያሉትን ሰርቪስ ክፍሎችም ወደቤርጎ ቀይሪልን፤ እኔም አንዳንዴ ሴቶችን ሸጎጥ አድርጌ መጣና አረፍ እልበታለሁ።
‹‹ምን አንተስ የእሱ ጓደኛ አይደለህ፡፡››
‹‹ከእሱ በፊት እኮ የአንቺ ጓደኛ ነበርኩ…ኧረ እንደውም የዕቃ ዕቃ ባልሽ አልነበርኩ እንዴ?››
ፊቷ ቀላ፡፡ የውብዳር ሁል ጊዜ ስለ እሷ እና ስለ ሁሴን የልጅነት ታሪክ ስታስብ የሠውነቷ ሙቀት ይጨምራል፡፡ በተቀራራቢ ጊዜ አንድ ሠፈር ውስጥ ከማደጋቸው አንፃር ጣፋጭ የሆነ የልጅነት፤ ከዛም ዘሎ እስከ አሁን የዘለቀ የጓደኝነት ቁርኝት በመሀከላቸው አለ፡፡ ከሠሎሞን ጋር እንዲገናኙ መሠላል የሆናቸውም እሱ ነበር፡፡
ካለፈ ትውስታቸው እንደመባነን አለችና ‹‹አዋ እሱማ ለእኔም ጓደኛዬ ነህ፡፡ካንተ ጓደኝነት ያተረፍኳቸው ሦስት ትላልቅ ነገሮች ምን እንደሆኑ ታውቃለህ? ምርጥ ተወዳጅ ልጆች፣ብዙ ብር እና የምሁር ደደብ የሆነ ባል ናቸው፡፡ እና ላማርርህም ሆነ ላመሠግንህ ግራ ይገባኛል፡፡ ባይገርምህ ወደ ኃላ ተመልሼ ሳስብ የዛን ጊዜ ከእሱ ይልቅ አንተን ለምን እንዳልጠበስኩህ ድንቅ ይለኛል፡፡ እንደ ቤተሰብ ሆነን አብረን ማደጋችን እንደወንድምና እህት እንድንተያይ ተፅዕኖ ያሳደረብኝ ይመስለኛል፡፡ ግን እንደ አሁኑ በሳል
ሆኜ ቢሆን ኖሮ መቶ ጊዜ ደጋግሜ አንተን ነበር የምጠብሰው
‹‹ድሮም ሆነ አሁን ዱርዬ እንደሆንኩ እኮ ደጋግመሽ ነገርሽኝ ነበር››፡›› ሁሴን የድንጋጤ ንግግር ነበር የተናገረው፡፡ የውብዳር ስለ እሱ እንደዚህ አይነት ስሜት እንደሚሰማት ገምቶ አያውቅም፡፡
‹‹ዱርዬማ ዱርዬ ነህ፡፡ ግን ንፁህ ዱርዬ ነህ፡፡ አፍቃሪም ነህ፡፡ ከተረጋጋ ማህበራዊ ሕይወት ይልቅ በማዕበል የሚናወጽ ግን በደስታ የተጥለቀለቀ ሕይወት ይበልጥ ዋጋ አለው፡፡ ደስታ በሕይወት ለመኖር ምን ያህል ዋጋ እንዳለው የምትረዳው ባጣኸው ጊዜ ነው፡፡ ፍቅር አልባ ሕይወት እኮ በቃ..… ንብ አልባ ባዶ ቀፎ ማለት ነው፤ንብ የሌለበት ባዶ ቀፎ ደግሞ ማር ሊመረትበት አይችልም፡፡ ብር ምን እንደሚያደርግልህ ታውቃለህ፡፡ ቁሳዊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ያስገኝልሀል፡፡ ውጫዊ ችግሮችህን ሁሉ በቀላሉ ታስወግዳለህ፡፡ ሀብታም ሆነህ ሳለ የፍቅር ካዝናህ ባዶ ከሆነ ግን ..በቃ ቀንና ሌት ስለ እሱ ብቻ ታስባለህ፡፡ ሌሎች ፍላጎቶችህ ሁሉ ስለተሟሉ ሌላ የምትጨነቅበት ጉዳይ አይኖርማ፡፡ ስለዚህ ይበልጥ በፍቅር እጦትህ እንድትሠቃይ ትሆናለህ፡፡››
‹‹ቆይ ይሄንን ያህል እስክትማረሩ ድረስ ምን
ትሠራላችሁ፡፡ ለምን አትነጋገሩም?፡፡ የተከሰቱ
ችግሮችን በወቅቱ ለመፍታት ጥረት ለምን
አታደርጉም ? ፍቅር እኮ ዘላለማዊ ነገር አይደለም፡፡ ይወለዳል .. ያድጋል .. ይሞታል፡፡በልጅነቱ .. በወጣትነቱ አልያም አርጅቶ ሊሞት ይችላል፡፡ የዕድሜውን ርዝመት የሚወስነው ግን ሁለቱ ፍቅረኛሞች ስለፍቅር ባላቸው ግንዛቤና ለፍቅራቸው በሚያደርጉለት
እንክብካቤ መጠን ነው፡፡ እናንተም አያያዙን
ያወቃችሁበት አይመስለኝም፡፡ ሲጋቡ
አይታችሁ ተጣድፋችሁ ተጋባችሁ፤ ይሄው
ጀርባ ለመሠጣጣትም ብዙ አልዘገያችሁም፡፡ለማንኛውም በዚህ ጉዳይ ላይ ሌላ ጊዜ በእርጋታ ቁጭ ብለን በሠፊው እንነጋገርበታን፡፡
አሁን ወደ መጣሁበት ጉዳይ እንመለስ
መግባባት ስላቃታችሁ የልጆቹ የልደት ዝግጅት ጉዳይ….፡፡››
‹‹እንዳልክ እሺ፡፡መቼስ አንተ ጠይቀኸኝ ምንም ነገር እምቢ ማለት እንደማልችል ስለሚያውቅ ነው የላከህ፡፡ ከዛ በፊት ግን ስለራበኝ የሚበላ ነገር እንድታመጣ ሠራተኛዋን ልዘዛት›› በማለት ወደ ማብሠያ ክፍል አመራች፡፡
✨ይቀጥላል✨
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍131❤14👏5🔥3🎉2🤔1😢1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
..በህይወቷ እንዲህ አይነት ድንዛዜ ውስጥ ገብታ አታውቅም...የአባቷን የሙት አመት መታሰቢያ ቀን መርሳት ማለት ..በቃ እያበቃላት መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ያለፉትን ስድስት አመታት እሷ ነበረች ቀድማ ለእንጀራ እናቷ የምታስታውሳትና ለድግስ የሚያስፈልገውን ነገር ቀድማ የምታሟላው።ሳምንት ሲቀረው ጓዟን ጠቅልላ ወደአሰላ ትሄዳለች።የአባቷን ሀውልት ታሳድሳለች..አካባቢውን ታፀዳለች..በሀውልቱ ላይ ደርቀው የከሰሙ አበቦችን አስወግዳ በምትካቸው አዲስ ትተክላለች..ያሉትንም ውሀ ታጠጣለች...ቤት ውስጥ በድግሱ የእንጀራ እናቷን ትረዳለች...በዕለቱ ታዲያ አንድም ችግረኛና የኔ ቢጤ በከተማው አይቀርም፤ ቀኑን ሙሉ ወደእነሡ ቤት ሲጓዙና ከድግሱ በልተው ወደቤት ይዘው የሚሄዱትን በፌስታል ተቋጥሮላቸው የሞተውንም ነፍስ ይማር ብለው እነሱንም መርቀው ይሄዳሉ።ይሄ መታሰቢያ ባለፉት ስድስት አመታት በጠቅላላው በአሰላ ከተማ የታወቀ ነው። እሷ ግን ይሄው የዘንድሮውን ረሳችው፡፡ከአይኖቿ የሚንጠባጠበውን እንባ እያበሰች "አባዬ በጣም ይቅርታ፡፡›› አለች፡፡
በዚህ ጊዜ ቱሉ ዲምቱ የክፍያ ጣቢያ ደርሳ የክፍያ ትኬት ለመቀበል መኪናዋን አቁማ ነበር።ታናሽ ወንድሟን ካወራች በኃላ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም።ወደቤቷ ሄዳ እንኳን ቅያሪ ልብስ ለመያዝ አልሞከረችም።ጭራሽ በሀሳቧም አልመጣ፡፡ቀጥታ መኪናዋን አዙራ ወደአሰላ መሄድ ብቻ ነበር የታያት፤እያደረገች ያለውም ያንን ነው።የቤታቸው የውጭ በራፍ ጋር የመኪናዋን አፍንጫ አስጠግታ የመኪናዋን ክላክስ ስታስጓራ አስር ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር። ከሰፈሩ በግርማ ሞገሡ አንደኛ የሆነውን ፊት ለፊቷ የሚታያትን የግንብ አጥር እና ፍረንች ዶር ያሰራችው እሷ ነበረች...አጥሩን ብቻ ሳይሆን ከድሮ ቤታቸው ማለት እትብቷ ከተቀበረበት እና ካደገችበት ቤት ፊት ለፊት ያለውን ቪላ ቤት ያሰራችው እሷ ነች።ግን ይህን ሁሉ ያደረገችው ውድ አባቷ ከሞተ በኋላ ነው።በህይወት እያለ የሚወደውንና መላ ህይወቱን የለፋበትን ግቢ እንዲህ አሳምራውና ቀይራው ቢያይላት ኖሮ እንዴት ይደሰት እንደነበረ ትገምትና የብስጭት እንባዋን ትዘራለች።ሁሌ ስለእንደዚህ አይነት ጉዳይ አንስተው ከስንዱ ጋር ሲያወሩ"አሁንም እኮ መንፈሱ ያይሻል...ለእኔና ለወንድምሽ በምታረጊው ነገር ባለበት ሆኖ ይመርቅሻል..ልክ በህይወት እያለ ይኮራብሽ እንደነበረው አሁንም ይኮራብሻል..››እያለች ልታፅናናትና ከገባችበት ሀዘን መንጭቃ ልታወጣት ትሞክራለች።ግን ይህ አይነቱ የእንጀራ እናቷ የማፅናኛ ንግግር እሷን ይበልጥ ጥልቅ ወደሆነው ሀዘን ውስጥ ነው ጎትቶ የሚሸጉጣት
‹‹አባቴ ባለበት ሆኖ እኔን የሚያየኝ ከሆነማ በጣም ነው የሚያፍርብኝ...በእውነት ይህቺ ልጅ እኔ ያሳደኳት ከአብራኬ የወጣች ልጅ ነች ?››ብሎ መጠየቁ አይቀርም...ምክንያቱም በትክክልም ባለበት ሆኖ ስራዬን የሚያይ ከሆነ ቤቱን ማሳመሬን ብቻ አይደለም የሚያየው..ሚስቱን እና ልጁን መንከባከቤንና መርዳቴን ብቻ አይደለም የሚያየው አመት እየጠበቅኩ በስሙ የአሰላን ድሆች ማብላቴን ብቻ አይደለም የሚያየው...እርግጥ እነዚህን ስራዎቼን ባየ ቁጥር ፈገግ ሊል ይችል ይሆናል፡፡ግን ደግሞ በየዕለቱ በስራ ህይወቴ የማሳልፈውን ነገሮች ካየስ..?.በእየዕለት ህይወቴ የሆንኩትንና እየሆንኩ ያለሁትን የሚያይ ከሆነስ..?ልጁ አጨበርባሪ እንደሆነች ሲያይስ.?ልጁ እልል ያለች ፕሮፌሽናል ሸርሙጣ መሆኗን ሲያይስ? ከዛም አልፎ ገዳይና ቂመኛ መሆኗን ሲያይስ?››እኚህንና መሠል ነገሮችን በውስጧ እያሰበች ሽምቅቅ ትላለች።አባቷ በሄደበት በዛው እንዲመቸውና ፊቱን ወደኃላ ዞሮ እንዳያያት ዘወትር ትፀልያለች።አዎ አባቷም ሆነ ሌሎች የሚወዷት ሰዎች ከዛሬ አስር አመት በፊት የነበረችውን ሳባን ብቻ አውቀው በዛ ትዝታ እንዲኖሩ እንጂ ካዛ ወዲህ እንደ አዲስ በውስጧ በቅላ ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረቻትን አውሬዋን ሳባን እንዲያውቁ ፈፅሞ አትፈልግም...
የአሁኗን ሳባ ከእነሱ ለመደበቅ የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም።
በሀሳብ ጭልጥ ካለችበት የበራፍ መከፈት ነው ያባነናት፡፡ራጂ ነበር ..የከፈተላት።መኪናዋ አዲስ ስለሆነች አይቷት አያውቅም።ማንነቷን ስላለየ ወጣና ቀረባት፤እህቱ መሆኗን ሲያውቅ እየፈነጠዘ ሰላምም ሳይላት ወደውስጥ ሮጠ.‹‹..እናቴ ማን እንደመጣ እይ ? እናቴ አላልኩሽም እህቴ መጣች...እህቴ መጣች" ደስታውንና ፈንጠዝያውን ስታይ ውስጧ ርብሽብሽ አለባት፡፡
‹‹እንደዚህ የሚንሰፈሰፉልኝ ቤተሠቦች እያሉኝ ለምንድነው ብቸኝነት ውስጤን የሚከታትፈው? ›› ስትል እያሠበች ከገቢናው ከፍታ ወረደችና ወንድሟ ክፍት ጥሎት በሄደው ትንሹ በር ገብታ እራሷ የመኪናውን መግቢያ በራፍ ከፈተችና መኪናዋን ወደ ግቢ ውስጥ አስገብታ ገና በቅጡ ሳታቆም ስንዱ ልጇን አስከትላ እጇን እንደ ክንፍ እያርገፈገፈች ስትመጣ አየቻትና ፈጠን ብላ መኪናዋን በማቆም ወረደችና… ወደእሷ ተንደረደረች፡
አይን ለአይን ሳይተያዩ ገና ሁለት ወርም በቅጡ ያልደፈነ ቢሆንም አሁን በሰላምታ ተቃቅፈው ሲላቀሱ ላያቸው ባለፈው ሁለት አመት ጭራሽ ያልተገናኙ ነው የሚመስለው፡፡
‹‹ለመሆኑ.አለሽ…?ምነው.ከሳሽ?››ፊቷን.እየዳበሰች.በመንሰፍሰፍ.ጠየቀቻት…ስንዱ የሳባ እኩያ ብትሆንም አባቷን በማግባቷና በዛም ምክንያት እናቷ መሆን በመቻሏ ሁሌ ንግግራቸው የሀያ አመት ልዩነት በመሀከላቸው ያለ ነው የሚመስለው፡፡
ቤት እንደገባች ምግብ ተሰርቶ በልታ ቡና ተፈልቶላት ጠጥታ ለነገው ድግስ የሰፈር ሰው ሁሉ ቤታቸው ስራ ላይ ስለነበረ እነሱን ተቀላቅላ ማገዝ ብትፈልግም ራስ ምታቷ ስለተቀሰቀሰባትና ከሰው ተቀላቅላ ሆይ ሆይታ ውስጥ መሳተፉን ስላልቻለች በስንዱ ገፋፊነት እሷ መኝታ ቤት ገብታ እንድትተኛ አድርጋት ወንድሟም እየመጣ እንዳይረብሻት አስጠንቅቃው በራፉን ከውጭ ዘገታባት ወደስራዋ ሄደች፡፡
ሳባም የድሮ የአባቷ መኝታ ክፍል አባቷ ይተኛበት የነበረ አልጋ ላይ ወጥታ ኩርምት ብላ ተኛች የተወሰነ ድካም ቢኖርባትም እንቅልፍ ሊወስዳት ግን አልቻለም፡፡እስከአሁን ሁለት ጊዜ በዶክተሩ የታዘዘላትን ለሳምንት ያህል በተከታታይ ስትወሰደው የነበረውን መድሀኒት መውሰድ ነበረባት..ጥዋት ለህክምና ብላ ከቤት እንደወጣች ስላልተመለሰች አልያዘችውም ዛሬ የታዘዘላትንም ተጨማሪ መድሀኒት ወደፋርማሲ ጎራ በማለት ልትገዛ አልቻለችም..ጭራሽ ትዝም አላላት፡፡
‹‹የራሱ ጉዳይ አለችና ››ወደሀሳቧ ተመለሰች፡፡
እዚህ ቤት መምጣት .ከዛም በላይ እዚህ ክፍል መግባት… ከዛም በላይ እዚህ አልጋ ላይ ተኝቶ ስለአባቷ ማሰብ አንኳን አሁን እንደዚህ አእምሮዋ በጭንቀት እና በድባቴ ምስቅልቅል ባለበት ጊዜ ይቅርና በፊትም ራሷን መግዛትና ስሜቷን ማረቅ በምትችል ጊዜ በጣም ነበር የሚረብሻት…በጣም ነበር ሀዘን ውስጥ የሚጨምራት፡፡ይሄ ቤት የተወለደችበት ነው፡፡እናቷ የሞተችው እሷ ከተወለደች ከአንድ አመት በኃላ ነበር፡፡አዎ የአንድ አመት የልደት በዓሏ ሊከበርላት አንድ ቀን በቀረበት ጊዜ ነው፡እናትዬው ከመሞቷ በፊት ለእሷ የልደት ክብረበዓል የሚሆኑ ሁሉንም ዝግጅት አሰናድታ ጨርሳ ነበር.በድንገተኛ በሽታ ማታ ሁለት ሰዓት አመማት..ወዲያው አፋፍሰው አሰላ ሆስፒታል አስገቧት…አምስት ሰዓት ህይወቷ አለፈ፡፡ ከዛ አባትዬው ለብቻው ሆኖ ነጭ ላቡን ጠብ በማድረግ ምንም እንዳይጎልባት አድርጎ አሳደጋት፡፡ታዲያ ሁል ጊዜ የእሷ ልደት

👍79❤13👏1😁1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
ፔሩ/አማዞን ወንዝ
ዳግላስን ከኑሀሚ ነጥለው በአማዞን ወንዝ ላይ የተወሰነ ይዘውት ከተጓዙ በኋላ ሌላ እጅግ በጣም የተቀናጣ ግን ደግሞ መለስተኛ ዘመናዊ ጀልባ አጠገብ አቆሙና አሸጋገሩት፡፡ምንም እየገባው ነገር ባይኖርም ግን ደግሞ መከራከርና መጨቃጨቅ ባለመፈለጉ እንዳደረጉት እየሆነላቸው ነው፡፡ልክ ከትንሿ ጀልባ ወደቅንጡ ውሀና ዘመናዊው ጀልባ አሸጋግረውት ገና ወለሉ ላይ እንዳረፈ..አንድ ሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ፤ደማቅ ጥቁር ፀጉሯ መቀመጫዋ ላይ የደረሰ ፤መልኳ ጉርድርድ ያለ ግን ደግሞ ሳቢ የሚባል የደም ግባት ያላት ሴት ከውስጥ ወጣችና ተንደርድራ መጥታ ተጠመጠመችበት፡፡ግራ ገባው፡፡ብዥም አለበት፡፡ይህችን ሰውነቱ ላይ ተጠምጥማ በእንባ በመታጀብ እየሳመችው ያለችውን ልጅ የሆነ ቦታ የሆነ ጊዜ ያውቃታል..አዎ በአእምሮ ብልጭ ድርግም እያለችበት ነው ..ግን የት እና እንዴት እንደሚያውቃት ምንም ትዝ ያለው ነገር የለም፡፡
‹‹ቤብ..ሰላም ነህ…?ወይኔ በኢየሱስ……ምንም አልሆንክም…?›› መላ እሱነቱን እየተሸከረከረች አያች ግንባሩን ጉንጮቹን እጆቹን እያፈራረቀችና እያገለባበጠች ትሰመው ጀመር፡፡ በዙሪያቸው ያሉ ወጠምሻና አብረቅራቂ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች አንገታቸውን አቀርቅረው ዙሪያቸውን ከበው እየሆነ ያለውን በቆረጣ እየተመለከቱ ናቸው፡፡ልጅቷ እየጎተተች ወደውስጥ ይዛው ገባች ፡፡ደረጃውን እየወረዱ ወደውስጠኛው መኝታ ክፍል ይዛው ገባች፡፡ ሰፊውን ክፍል አልፋ አልጋ ወደ ተነጠፈበት መለሰተኛ ክፍል ይዛው ገባቸው፡፡ባለመሳሪያዎቹ ባሉበት በረንዳ እንደቀሩ ናቸው፡፡
ዳግላስ በገባበት የቅንጡ ጀልባዋ መኝታ ቤት ውስጥ የምታምር ድንብሽብሽ ያለች በግምት ሶስት ወይም አራት አመት የሚሆናት ጥቁር ሉጫ ፀጉሯ ግንባሯ ላይ ድፍት ብሎ ግማሽ ፊቷን የሸፈናት ልጅ ጭልጥ ያለ የሰላም እንቅልፍ ውስጥ ገብታለች፡፡ህፃኗን በትኩረት ሲያያት የሆነ ብዙ ቀለማቶች በአእምሮው ብልጭ ድርግም ብልጭ ድርግም እያሉ ይረብሹት ጀመረ፡፡በፀጥታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠና ቀኝ እጁን ወደ ልጅቷ ልኮ በቀስታ ግንባሯ ላይ የተደፋውን ፀጉሯን ከግንባሯ ላይ እያነሳ ትራሱ ላይ አስተኛው..እናትዬዋ ስሩ በፀጥታ ቆማ የሚያደርገውን እየተመለከተች ነው፡፡አሁን ሙሉ በሙሉ የልጅቷ ገፅታ ይታያል፡፡ይህቺ ልጅ ልብ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ነፍሱ ውስጥም እንዳለች እርግጠኛ ነው፡፡ይሄንን የተረዳው ደመነፍሳዊ በሆነ ስሜቱ ነው፡፡በትክክለኛው ግን ምንም ትዝ እያለው ያለ ነገር የለም፡፡
አንገቱን ቀና አደረገና ጎኑ የቆመችውን አማላይ ሴት ተመለከታት‹‹የምታግዢኝ ነገር የለም?››ሲል ጠየቃት፡፡
የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ሙሉ ፍቃደኛ እንደሆነች በሚያረጋግጥ ንግግር ‹‹ምን ላድርግልህ የእኔ ፍቅር? የፈለከውን ጠይቀኝ››አለችው፡፡
‹‹አሞኛል ..በፊት የምወስዳው መድሀኒት ወይም ኪኒን ነገር ይኖራል?፡፡››
ደነገጠች….የእሷን መደንገጥ ተከትሎ እሱም ደነገጠምም ግራ ተጋባምም‹‹ዛሬ መድሀኒትህን አልወሰድክም እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እስከማስታውሰው ድረስ ለበርካታ ቀናት ምንም አይነት መድሀኒት የወሰድኩ አይመስለኝም፡፡››
‹‹ይሄ የፓብሎ ተግባር ነበር፡፡ግን እሱ ራሱ የት እንደገባ ምንም የሚታያውቅ ነገር የለም፡፡ቆይ መጣሁ›› ብላ ሔደችና ከሁለት ደቂቃ በኃላ ሁለት ኪኒኒ ከእሽግ ውሀ ጋር ይዛ መጣች፡፡ኪኒኖቹን ከእሽጉ ፈልቅቃ አቀበለችው….‹‹ውሀውን ከፈተችና በል ዋጥና ለአንድ ሰዓት ያህል ጋደም በል… ስትነሳ ሰላም ትሆናለህ….››
‹‹አልገባሽም ..አመመኝ ስልሽ እኮ ህመም አይደለም..ምንም የማስታውሰው ነገር የለም እያልኩሽ ነው..አንቺን ጭምር ማንንም አላስታውስም››የተረዳችው ስላልመሰለው ፍርጥ አድርጎ እውነቱን ነገራት፡፡
‹‹ገባኝ የእኔ ፍቅር ..ሁሉ ነገር ይስተካከላል… ብቻ ያልኩህን አድርግ… መድሀኒቱን ዋጥና ከልጅህ ጎን ተኛ፡፡››እንዳለችው መድሀኒቱን ተቀበላትና ዋጠ፡፡ጫማውን አወለቀና ቀስ ብሎ አልጋው ላይ ወጣና ከልጁ ጎን ተኛ፡፡ፊት ለፊት ካለው የልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ አልጋ ልብስ አወጣችና አለበሰችው፡፡ ቀስ ብላ ክፍሉን ዘግታለት ወጣችና ከጠባቂዎቹ ራቅ ብላ የጀልባዋ በረንዳ ላይ ባላ ወንበር ተቀምጣ ከወንዙ ባሻገር ያለውን ጥቅጥቅ የአማዞን ደን በተመስጦ መመልከቷን ቀጠለች፡፡
ኑሀሚ ያለችበት ጎጆ የተወታተፈ በራፍ ሲከፈት ሰማችና የጨፈነ አይኗን ከፈተች፡፡ከአጋቾቾ መካከል አንዱ ነው፡፡፡አሁን እጆ ላይ ተጣብቆ ከወዲህ ወዲያ በተንቀሳቀሰች ቁጥር ቅጭልቅል እያለ የሚረብሻትን ሰንሰለት ተቆራኝቷት የነበረው ልጅ ነው፡፡በእጁ የሚበላ ነገር በሰሀን እና የሚጠጣ ውሀ በላስቲክ ኩባያ ይዞል፡፡ወደእሷ ተጠጋና በርከክ ብሎ ምግብን አስጠግቶ አስቀመጠላትና የስፓንሽ ቋንቋ ዘየ በተጫነው ግን ደግሞ ባልተደነቃቀፈ እንግሊዘኛ፡፡‹‹ተነሽ ይሄን ምግብ ብይ…ከጥቂት ጊዜ በኃላ በእግር ረጅም መንገድ መጓዛችንን ስለምንቀጥል ጥንካሬው ያስፈልግሻል፡፡››አላት፡፡
ጎኑ ላይ የያዘውን አብረቅራቂ ኮልት ሽጉጥ በጎሪጥ እየተመለከተች‹‹ወደየት ነው የምትወስዱኝ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እሱን ለአንቺ ለመናገር ፍቃዱ የለኝም፡፡››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹እባክህ…እህት የለህም..እኔ እኮ በጣም ከሩቅ አህጉር የመጣው ምስኪን ወጣት ነኝ…ምን ላደርግላችሁ ነው እንዲህ ከእኔ ጋር የምትሰቃዩት?››አሳዛኝ መስላ ለመቅረብ ሞከረች፡፡
‹‹እህት አለኝ ….ግን ላደርግልሽ የምችለው ነገር ቢኖር አንድ ምክር ላንቺ መስጠት ብቻ ነው፡፡››
‹‹ምንድነው? እባክ ንገረኝ፡፡››
‹‹ፈፅሞ የሞኝ ስራ እንዳትሰሪ…››
ያልጠበቀችው የምክር አይነት ስለነበር‹‹ምን ማለት ነው?››በማለት ጠየቀችው፡፡
‹‹ጥዋት በምንጓዝበት ጊዜ በየመሀከሉ ሁኔታሽን ስከታተለው ነበር… ለማምለጥ ወይም ለመፋለም የመፈለግ አዝማሚያ አይቼብሻለው፡፡ በእርግጠኝነት ትንሽ እንቅስቃሴ ወይም ሙከራ ካደረግሽ ከመሀከላችን አንድ ወዲያው ነው የሚደፋሽ… እመኚኝ ሌሎቹ እንደእኔ ልስልስ እና ደካማ ነገር አይደሉም፡፡ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ጭካኔም ያላቸውና ሰውን በመግደልና ድመት በመግደል መካለከል ምንም ልዩነት የማይታያቸው ገዳዬች ናቸው..እንደውም አጋነንከው ከላልሺኝ ለእነሱ ወሲብ ማድረግና ሰውን መግደል ተመሳሳይ አይነት እርካታ ነው የሚያጎናፅፋቸው፡፡››ሲል መስማት ከምትፈለገው ተቃራኒ የሆነ አስቀያሚ ዜና ነገራት፡፡
‹‹እና መጨረሻዬን ምንም ሳላውቅ ልክ እንደፋሲካ በግ ዝም ብዬ ልነዳ ?››
‹‹እኔ እንግዲህ እንደዛ የሚሻል ይመስለኛል፡፡በህይወት ነገ ተነገ ወዲያ ምን እንደሚከሰት አይታወቅም፡፡ነገ ይዛ የምትመጣውን እድል ለመጠበቅ ደግሞ ዛሬ በህይወት ቆይቶ ነገ ላይ መገኘት ያስፈልጋል፡፡በይ እንዳልኩሽ የቀረበልሽን ብይ… የእግር ኮቴ እየተሰማኝ ነው፡፡
‹‹ልሂድ››ብሎ ቁጢጥ ካለበት ምንጭቅ ብሎ ተነሳና በራፉን ከፍቶ እንደአመጣጡ ተመልሶ ሄደ፡፡

👍83❤8👎1👏1😱1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
አንድ ሰዓት የቤቱ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ጠባቧን ሳሎን ሞሏት…መጨረሻ ላይ የመጣው ፊራኦል ነበር…በእጁ አንድ ኪሎ ሙዝ ይዞ ነበር፡፡
ለሊሴ ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከእጁ መንጭቃ ተቀበለችው እና‹‹..ወንድሜ ሙዝ ገዛኸልኝ….!!! ደሞዝ ደረሰ እንዴ?››ስትል በፈገግታ ተሞልታ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ እንደምታውቂው ቀኑ ገና 18 ነው….በ18 ደግሞ ደሞዝ የለም…ስለዚህ ሙዙ ላንቺ አይደለም››ሲል መለሰላት፡፡
ለሊሴ ግራ ገብቷት‹‹ እና››ስትል አይኖቾን በማፍጠጥ ጠየቀችው፡፡
‹‹ለበሽተኛዋ ማለቴ… ለእንግዳዋ ነው››ሲል ያልጠበቀችውን መልስ ሰጣት፡፡
‹‹እ ነው…እሺ…››አለችና ፔስታሉን ወደበፀሎት ወስዳ ስሯ አስቀመጠችላት…፡፡
በሳቅና በጫወታ በደመቀ ምሽታ እራት ተበላ… ቡና ተፈልቶ ተጠጣ….ከጓዲያ የተጠቀለለ የጥጥ ፍራሽ ወጣና ወንበሮቹ ተሰብስበው ከእሷ ጎን ተነጠፈ…ለሊሴ ከጎኗ በተነጠፈው የጥጥ ፍራሽ ላይ ስትተኛ ፊራኦል ደግሞ ከእነሱ ራቅ ብሎ ግድግዳውን ተደግፎ ካለ አሮጌ ሶፋ ላይ አንድ አልጋ ልብስ ተከናንቦ ተኛ…
‹‹ለሊሴ ታዲያ ስትበራገጂ እግሯን እንድትነኪባት››
‹‹አረ አታስቢ እማዬ …እጠነቀቃለሁ፡፡››
ለሊሴ በፀሎትን ‹‹ለሊት የሆነ ነገር ከፈለግሽ ቀስቅሺኝ››አለችትና የለበሰችውን አልጋ ልብስ ተከናነበች፡፡
‹‹እሺ ቀሰቅስሻለሁ..ደህና እደሩ ››ስትል መለሰች፡፡
‹‹ደህና እደሪ….ወንድሜ ደህና እደር››
‹‹ምኑን ደህና አደርኩት ….ዛሬ ደግሞ ምን አልባት ሴኖ ትራክ ይሆናል ቤታችን ላይ የሚወጣው…. ››
‹‹ወንድሜ ደግሞ.. አሽሙራም ነገር ነህ››
‹‹እሺ መብራቱን ላጥፋው?››ፊራኦል ጠየቀ፡፡
‹‹አጥፋው››በፀሎት መለሰች፡፡
መብራቱ ጠፋ፡፡ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ሁሉም ፀጥ ያለና በእንቅልፍ የተዋጠ ይመስል ነበር..በፀሎት ግን ፈፅሞ እንቅልፍ ሊወስዳት አልቻለም...ጨለማው ውስጥ አይኗን አፍጥጣ በጭንቀት እያሰላሰለች ነበር..ይሄኔ የአባቷ ቅጥረኞች ድፍን አዲስ አበባን እየገለባበጦት እንደሚሆን እርግጠኛ ነች..
‹‹የፈለገ ቢገለባብጡ የፈለገ ያህል ቢሞክሩ አያገኙኝም….››ስትል እርግጠኛ ሆነች፡፡ስልኳን ከቤት ይዛ አለመውጣቷ አሁን ነው ያስደሰታት….እንደዛ ባታደርግ ኖሮ ያንን ተከትለው ያለችበትን ለማግኘት ይሞክሩ ነበር አሁን ግ ምንም እድል የላቸውም…አዎ አሁን ባልና ሚስቶቹ እየተናቆሩም ቢሆን እሷን በመፈለጉ አንድ ላይ ለማውራትና ለመተባበር ይገደዳሉ…ምን አልባትም ወደቀልባቸው እንዲመለሱ ምክንያት ሊሆናቸው ይችል
ይሆናል… ይሄ የእሷ ምኞት ነው፡፡ካለበለዚያም ይለይላቸውና እርስ በርስ ይገዳደሉ ይሆናል፡፡ ‹‹እንደዛ ከሆነ እስከወዲያኛው እገላገላቸዋለው››አለችና በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ እንዲሁ ስትገላበጥና ስትተክዝ እኩለ ለሊት ሆነ፡፡ በአእምሮዋ የሚጉላላው ሀሳብ ብቻ አይደለም እቅልፍ የነሳት… የእግሯም ጥዝጣዜ ጭምር ነው ፡፡በዛ ላይ ሽንቷን ወጥሯታል….‹‹እንዴት ነው የማደርገው.?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡.እንደምንም ተቆጣጥራው እስከንጊት ለማቆየት ብትጥርም አልቻለችም..አምልጧት ከመዋረዷ በፊት ከጎኗ ድብን ያለ እንቅል የተኛችውን ሊሊሴን መጣራት ጀመረች‹፡፡
‹‹ሌሊሴ….ሌሊሴ››
ያልጠበቀችው ሻካራ ድምጽ መልስ ሰጣት..‹‹አትልፊ እህቴን እንኳን በጥሪ በመድፍም ልትቀሰቅሻት አትችይም››
ግራ ተጋብታ ምን እንደምትመልስ እያሰላሰለች ሳለ መብርቱ በራ…በቁምጣና በጃፖኒ ቲሸርት ውጥርጥር ያለ ሰውነቱን በከፊል አጋልጦ ካለችበት በሶስት እርምጃ ርቀት ቆሟል…
‹‹ምን ልስጥሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ..ሽንት ቤት መሄድ ፈልጌ ነበር››ፈራ ተባ እያለች መለሰችለት፡፡
‹‹ምን ፖፖ ላምጣልሽ?››
ፖፖ ቢያመጣላት እዚህ እፍንፍን ያለ ቤት ይሄ ሁሉ ሰው ባለበት እንዴት አድርጋ እንደምትሸና አሰበችና‹‹ አይ ሽንት ቤት ነው መሄድ የፈለኩት›› በማለት መለሰችለት፡፡
‹‹እንግዲያው እሺ›› አለና ወደበራፍ በመሄድ የተቀረቀረውን በራፍ ወለል አድርጎ ከፈተና ተመልሶ ወደእሷ መጣ …ምን ሊያደርግ ነው ብላ አፍጥጣ እያየችው ሳለ በርከክ ብሎ ስሯ ተቀመጠና የለበሰችውን ብርድ ልብስ ከላዮ ላይ ገፈፈ፡፡ እጆችን በትከሻዋና በእጆቾ መካከል አሰቅስቆ አስገባ..
‹‹ምን እያደረክ ነው?››ግራ በተጋባ ድምፅ ጠየቀችው፡፡
‹‹መቼስ እንዲህ ተሰባብረሽ ልራመድ አትይም….እንደፈረደብኝ አቅፌ ሽንት ቤት እየወሰድኩሽ ነው››
‹‹አረ ተው ..እነጋሼ ብያዩን ምን ይሉናል?››
‹‹አይዞሽ እነጋሼ ልጃቸው ምን አይነት ልጅ እንደሆነና እንዴት አድርገው እንዳሳደጉት ስለሚያውቁ ምንም አይሉም…..ምን አልባት ግን ይመርቁኝ ይሆናል››አለና አንከብክቦ አቅፎ ከቤት ይዟት ወጣ፡፡የልጁ ድርጊት ፍጽም ያልጠበቀችው ስለሆን በጣም ነው የተደመመችው፡፡
እንደተሸከማት ከሰርቢስ ቤቱ ጫፍ በኩል ክፍቱን ካለ አንድ ክፍል ወስዶ ወደውስጥ ደፉን አሳለፈና ደግፎ አቆማት…ከዛ ቀኝ እጁን ዘረጋና በቀይ የኤሌክትርክ ገመድ ጫፍ ላይ የተንጠለጠለውን ማብሪያ ማጥፊያ ሲጫናው የሽንት ቤቱ መብራት ቦግ ብሎ በራና በክፍሉና በአካባቢው ያለው እይታ ወለል ብሎ አንዲታየ አደረገ …
ደረቱ ላይ ተደግፋ እንደቆመች ሽንት ቤቱን ቃኘችው..ስፋቱ ሁለት ካሬ እንኳን አይሞላም
…በዛ ላይ ከለመደችው አይነት መፀዳጃ ቤት ፍፅም የተለየና የማይነፃፀር አይነት ነው….ይህን መሰል አይነት ሽንት ቤት በምስል አንኳን አይታው የማታውቀው አይነት ነው፡፡እርግጥ ፅዳቱ የተጠበቀ በመሆን ዝግንን የሚል የመቅፈፍ አይነት ስሜት እንዲሰማት የሚያደርግ አይነት አይደለም…ቢሆንም በምቾት ዘና ብላ የምትቀመጥበት አይነት አይደለም…‹‹በቃ እንደምንም ግድግዳውን ተደግፈሽ ቁሚ..››ትዕዛዙን ስትሰማ እንደምንም የተበታተነ ሀሳቧን ሰበሰበች፡፡
እስከአሁን ደረቱን ተደግፋ መቆሟን ትዝ ሲላት እንደመደንገጥ አለችና ግራና ቀኝ እጇን የሽንት ቤቱን በራፍ ግራና ቀኝ ጉበን ይዛ ቆመች…ትቷት ወደኃላ ሸሸና መራመድ ሲጀምር
በመደንገጥና በመገረም ስሜት‹‹እንዴ? ጥለኸኝ ልትሄድ እንዳይሆን?››ስትል ጠየቀችው፡፡
እርምጃውን ሳያቋርጥ ‹‹መጣሁ..››አለና ከበራፉ አካባቢ አንድ ባዶ ሀይላንድ ላስቲክ ይዞ ወደ ቧንቧው በመሄድ ውሀ ቀድቶ ከሞላበት በኃላ ..ወደእሷ ተመለሰና እጁን አንጠራርቶ ከሽንት ቤቱ ቀዳዳ አጠገብ አስቀመጠላትና …‹‹..ግቢና እንደምንም ተቀመጪ››አላት፡፡
ወደውስጥ ዘልቃ ገባች‹‹በራፍ የለውም እንዴ?››ሌላ ያስጨነቃትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይዞሽ….ምንም አትሆኚም››አለና ወደላይ ተሰብስቦ የተጠቀለለ ጨርቅ ነገር አላቀቀና እንደመጋራጃ ወደታች ለቆ ጋረደላት…..የእግሯን ጥዝጣዞ እንደምንም ችላ በአንድ አይኗ አጨንቁራ በማየትና ነገሮችን በመቆጣጠር እደምንም ተቀምጣ ለመተንፈስ ቻለች..ጨርሳ ስትወጣ ተንደርድሮ ከበራፍ ተቀበላትን ሰቅስቆ አቀፋት፡፡
‹‹ካላስቸገርኩህ ጨረቃዋ ደስ ትላለች ..ትንሽ ውጭ መቀመጥ እንችላለን?››ስትል በልመና ቃና ጠየቀችው፡፡
‹‹እንደፈለግሽ.. ››አለና ግድግዳውን አስደግፎ አቆማትና ትቷት ወደውስጥ ሊገባ መራመድ ጀመረ…
‹‹እንዴ ብቻዬን ልቆይ እኮ አይደለም ያልኩህ ..አንተ ምትገባ ከሆነማ እኔ ብቻዬን ፈራለሁ››
‹‹በለሊት ሞተር ስትጋልቢ እንዴት ሳትፈሪ…?ለማንኛውም ወንበር ላመጣልሽ ነው››አለና ወደቤት ገባና አንድ ባለመደገፊያ ወንበር በማምጣት አደላድሎ ወስዶ አስቀመጣትና ከጎኗ ጠፍጣፋ ድንጋይ አስቀምጦ ተቀመጠ፡፡

👍55❤13
#የጣት_ቁስል
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ
ደላላው
ያዋጣኝ ይሆን ? ወይስ ያከስረኝ ? ይሆን ? ተጠራጠረ ፤ የአልባሳት ንግዱ ግን ውጤታማ አድርጎታል፡፡ እየተመላለሰ መነገዱን ቀጥሏል፡፡
የባልጪ መኪና ቶሎ ያሬድ ወደ ድሬድዋ ሊሄድ ረፍዶበት ተቻኩሏል፡፡ መኪናው ግን ሳይሞላ መውጣት አልቻም፡፡ አዳማ አርፍዶ ደረሰ፡፡ ወደ ድሬደዋ በጥዋት የሚወጣው መኪና አምልጦታል፡፡
ተናደደ ፣ ተበሳጨ፡፡ ምነው ዛሬ ባልመጣሁ ኖሯል፡፡ እንደሚረፍድብኝ እያወቅሁ፡፡ ከባልጪ መመለስ ሲኖርብኝ፡፡ ወደ አዳማ መንከርፈፍ ምን ይሉታል? ራሱን እየወቀሰ ከአሰላ መውጫ መነሃሪያ ወጥቶ በስተቀኝ በኩል ወደ ምትገኝ አንድ ሻይ ቤት አመራ፡፡
አንድን ጠቆር ያለ ወጣት ነው፡፡ ቁመተ አጭር ዳክየ፡፡ የተከረከመ ጉቶ ይመስላል፡፡ ፀጉሩ በአቧራ የተለወሰ ፣ የተንጨበረረ ፣ ቁጥርጥር ፀጉራም፡፡
ከመነሃሪያ ውጭ ቆሞ አላፊ አግዳሚውን ድሬ ፣ ድሬ አንድ ሰው የቀረው እያለ ይለፈልፋል፡፡
ቀኝ እግሩን አንስቶ ግራ እግሩን አልደገመም፡፡ ድሬ አንድ ሰው የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ ወደ ፊት መራመዱን ትቶ ወደ ኋላ ተመለሰ፡፡ ብስጭትና ንዴቱ ለቀቀው፡፡ እየተጣደፈ ድሬ ፣ ድሬ አንድ ሰው እያለ ወደ ሚለፈልፈው ደላላ ተጠጋ፡፡ እኔ አለሁ ድሬ አለ፡፡
"ኧረ! ድሬ ነህ ና ተከተለኝ፡፡ አሁን ልንወጣ ነው"፡፡ ብሎት ወደ መኪናው ወሰደው፡፡ ሂሳብ ክፈልና እዚህኛው መኪና ግባ አለው፡፡
ለመሳፈሪያ ብሎ ለይቶ ካስቀመጠው የሱሪ ኪሱ አውጥቶ ከፈለ፡፡ ደረሰኝ ግን አልተቀበለም፡፡ ደላላው ገንዘቡን ተቀብሎት ታጠፈ፡፡
ያሬድ ግባ ወደ ተባለበት አውቶቢስ ገባ፡፡ እውነትም አንድ ሰው ብቻ ነበር የቀረው፡፡ አንድ ተሳፋሪ ቀርቷት የነበረች ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡
እረዳቱ የአውቶቢሱን በር ዘጋ፡፡ ሹፌሩ መኪናውን አስነሳ፡፡ ጉዞው ከአዳማ ወደ ድሬደዋ ተጀመረ፡፡
"ምዕመናን ሂሳብ ወጣ! ወጣ! አድርጉ አለ እረዳቱ፡፡ እየተቀበለ ያሬድ ጋር ደረሰ፡፡
"ለእኔ ደረሰኝ ብቻ ስጠኝ ገንዘቡን ከፍያለሁ አለ ያሬድ፡፡
"ለማነው የከፈልከው አለ እረዳቱ?፡፡
"ሊያሳፍረኝ ይዞኝ ለመጣው ሰውየ ፡፡
"አባት የከፈሉት ሂሳብ ለእኔ አልደረሰኝም፡፡ አሁን ለእኔ ይክፈሉኝ አለ፡፡ ትህትና በተሞላበት ንግግር፡፡
"አልከፍልም" አለ ያሬድ፡፡
"እባክዎት ይክፈሉኝ" አባት ቢልም ፤ ምንም ቢል ያሬድ ሊሰማ አልቻለም፡፡ ክፈል ፣ ጭቅጭቅና ንትርኩ ተባባሰ፡፡ ሹፌር መኪናውን መንዳቱን አቆመ፡፡ በረዳቱና በያሬድ መሃል ጣልቃ ገባ
"ለምንድ ነው የማከፍለው? በነፃ ተሳፍረህ የምትሄደው የአባትህ ፈረስ አደረግከው አለ ሹፌሩ፡፡ በፊቱ ላይ የደም ስሮቹ ተወጣጠሩ፡፡
"የአባቴ ፈረስ ባይሆንም ገንዘብ ከፍየ ነው የተሳፈርኩት፡፡ ያጭበረበራችሁኝ እናንተ ናችሁ፡፡ በማስፈራራት ደግማችሁ ልታስከፍሉኝ ነው? አልከፍልም፡፡ ወደ ህግ እንሄዳለን እንጅ አለ ያሬድ፡፡
ከመኪናው ውስጥ ጎትተው አወጡት፡፡ ሊደበድቡት ተጋበዙ፡፡ ተሳፋሪዎቹ ገላገሏቸው፡፡ ክርክሩና ንትርኩ አላቋረጠም፡፡
አቶ ላንቻ ባልቻ የሚባሉ ከያሬድ ጋር አንድ ወንበር ላይ አብረው ተቀምጠዋል፡፡ ጭቅጭቁ አበሳጭቷቸዋል፡፡ ቶሎ ለመድረስ ያሰቡበት ቦታ እየረፈደባቸው ነው፡፡
"ለረዳቱ በቃ! ተወው እኔ እከፍለዋለሁ፡፡ ንትርኩን ተውና ቶሎ ቶሎ ንዳ፡፡ እውነት ይሄ ሰውዬ ሳይከፍልም የተከራከረ አይመስለኝም፡፡ የአዳማ ሞጭላፋ ጩልሌዎች ጨልፈውት ይሆናል፡፡ እንኳን የክፍለ ሃገር ሰው አግኝተው አይደለም ወፍ ከሰማይ ያወርዳሉ፡፡ ይዞት የመጣው ደላላ የሻይ ሲጠይቀው የመሳፈሪያውን ሂሳብ ተቀብሎት ላፍ ብሎ ይሆናል፡፡ ብለው የሚያጨቃጭቀውን የያሬድን ሂሳብ ከደረት ሸሚዝ ኪሳቸው አውጥተው ከፈሉለት፡፡
"አጭበርብረውኝ ነው፡፡ እንጅ እኔ እኮ ገንዘቡን ከፍያቸዋለሁ አባት አለ፡፡ እንደ መፀፀት ብሎ፡፡
"ያጭበረበሩህ ባለ መኪናዎቹ አይደሉም፡፡ ዱርዬዎች ናቸው፡፡ አንተም መኪና ውስጥ ሳትገባ መክፈል አልነበረብህም፡፡ ወይም ስትከፍል ደረሰኝ መቀበል ነበረብህ::
"እኔ መቼ አወኩ፡፡ እንደዚህ መሆኑን የት አውቄ፡፡ የእነሱ አጋዥ መስሎኝ ነው፡፡ የከፈልኩት፡፡ መቼ ሰባራ ሳንቲም አቀምሰው ነበር፡፡ ብሎ ስህተቱ የራሱ መሆኑን አውቆ የከፈሉለትን ገንዘብ ሊከፍል ከኪሱ አወጣ፡፡
አባት አመሰግናለሁ ገንዘቡን እንኩ አለ፡፡ በፊቱ ላይ የይቅርታ ምልክት እያሳየ፡፡
ገንዘቡን ለመቀበል አልፈለጉም፡፡ ተወው ችግር የለውም፡፡ አንተም ተወስዶብህ ነው፡፡ እንጅ አውቀህ አይደለም፡፡ አሁን ያወጣኸውን ገንዘብ መልሰህ ወደ ኪስህ አስገባ እኔ አልቀበልም አሉ አቶ ላንቻ፡፡
አቶ ላንቻ ከድሬደዋ አዳማ እየተመላለሱ የሚነግዱ የታወቁ ቱጃር አልባሳ ነጋዴ ናቸው፡፡ ጨዋታቸው እየሞቀ ሄደ፡፡ አቶ ላንቻ ከተደገፉበት ወንበር ቀና አሉ፡፡
"ስምህን ማን አልከኝ"? አሉት፡፡ መጀመሪያ ነግሯቸው በጭዋታ የተነሳ ዘንግተውት ይሁን ተመስሎባቸው ደግመው መጠየቃቸው፡፡
"ያሬድ እባላለሁ አለ፡፡ ፊቱን ወደ አቶ ላንቻ መለስ አድርጎ፡፡
"አሁን ወዴት ነው የምትሄደው"? ፡፡
"ወደ ድሬ የምሄደው"፡፡
"እዛው ነዋሪ ነህ ወይስ ለስራ ነው የምትሄደው?፡፡
"አይ! ለስራ ነው፡፡ ነገ እመለሳለሁ፡፡ እቤት ከመቀመጥ ብዬ ትንሽ ሳልባጅ ቢጤ ጀምሬ ነበር፡፡ ሞልቶ ለማይሞላ ነገር ስንት ገዛኸው ዘጠኝ ፤ ስንት ሸጥከው ዘጠኝ ፤ ትርፉስ ምንድነው? ዘጥ ዘጥ እንደሚባለው የበሰለውን ከማጥፋት ውጭ ድካም ነው፡፡ ውጤት የለውም አላቸው፡፡ ንግግሩ የሚያስቅ ስለነበር ፈገግ አደረጋቸው፡፡
አቶ ላንቻ አለመተዋወቅ እንጅ አልባሳት ከሆነ የምትነግደው እኔ አዳማ ድረስ አመጣልህ ነበር አሉ፡፡
"አልባሳት ይነግዳሉ እንዴ? አለ ያሬድ፡፡
"አዎ፤ ነጋዴ ነኝ፡፡ አሁንም አራግፌ እየተመለስኩ ነው፡፡
"ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ እንዴው የሰው መተዋወቂያው መንገዱ ብዙ ነው አለ ያሬድ፡፡ ያገናኛቸው አጋጣሚ እያስገረመው፡፡
"ድሬ ደንበኛ አለህ የምትረከብበት"? ፡፡
"ደንበኛ እንኳን የለኝም፡፡ የጀመርኩት ቅርብ ጊዜ ስለሆነ ደንበኛ አላበጀሁም፡፡ ከአሸዋ ሜዳ ነው የምገዛው ፡፡
የዛሬ መገናኘታችን ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ አሁን እየደረስን ስለሆነ መነሃርያ ሳንገባ ወርደን አረፍ ብለን እንነጋገራለን" አሉ ፤ አቶ ላንቻ፡፡
ከመኪና ወርደው ወደ አንድ ሪስቶራንት አመሩ፡፡ አረፍ ብለው የሚጠጣ ለስላሳ አዘዙ፡፡ በመኪና ላይ የጀመሩትን ጭውውታቸውን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
"አዳማ ውስጥ የራስዎ ቡቲክ አሎት እንዴ? አለ ያሬድ፡፡
"የራሴ እንኳን ቡቲክ የለኝም፡፡ አዳማ መነሃሪያ አካባቢ ቢያድግልኝ የሚባል የጅምላ አከፋፋይ ሱቅ አጠገብ የተከራየሁት ቡቲክ አለኝ፡፡ እዛ ነው የምሸጠው፡፡ ቦታውን ነገ አብረን ስንሄድ አሳይሃለሁ፡፡ አሁን እንሂድና እዚህ ድሬ ውስጥ ያለኝን ቡቲክ ላሳይህ፡፡ የሚያስፈልግህንም ገዝተህ እኔ በምጭንበት መኪና ጭነህ ነገ አብረን አንሄዳለን፡፡
ያሬድ ያገናኘውን አጋጣሚ እየመረቀ እንዴው ምን ዓይነት ደግ ሰው ነው፡፡ ያጋጠመኝ የእግዚአብሔር ሰው ናቸው፡፡ እያለ "አይደህና ነው፡፡ ለእኔም እዚህ ድረስ ከምለፋ ጥሩና መልካም ነው፡፡ እንዴው ውለታዎን ለመክፈል ያብቃኝ" አለ፡፡ ቀለስለስ እያለ፡፡
"አይ! ምንም ማለት አይደለም፡፡ የራሴም ስራ ነው፡፡ አሁን ከአንተ የምጠብቀው ታማኝ ሆኖ መገኘት ብቻ ነው"፡፡ ብለውት ሊያሳድሩት ወደ ቤታቸው ወሰዱት፡፡
በነጋታው በጥዋት ተነሱ፡፡ በተነጋገሩት መሰረት የሚያስፈልገውን ልብሶች ገዝቶ አብረው ወደ አዳማ ተጓዙ፡፡

👍64❤12😁1
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ዘሚካኤል ከሰዓታት በፊት የሰርጉን ስፍራ ለቆ መሄድ ነበረበት። ነገር ግን ከፀአዳ ተለይቶ መራመድ አልቻለም። ከሳምንት በፊት በእንጥልጥል የተወውን ጉዳይ መቋጫ ማበጀት አለበት፡፡በልቡ ጭራበት የሄደችው ሲኦል እሳት እየተንበለበለች መላ ሰውነቱ ትኩሳት እንደለቀቀችበት ነው…እንዴትም አድርጎ እንዴት እሱን ማስተካከል ያስፈልገዋል. ዛሬ ማታ።
ፀአዳ ለዘሚካኤል ቃል በገባችለት መሰረት ወደእሱ ለመሄድ ከውስጥ ወደአዳራሹ በተመለሰች ጊዜ በብዙ ውብና አማላይ ሴቶች ተከቦ ሲያውካካ ተመለከተችውና ከመንገዱ ለመራቅ ወሰነች - ባየችው ነገር ክፍት ነው ያላት…እንደዛ የማድረግ መብት የላትም ..ግን ከማንም ለመፎካከርና እሱን ሻሞ ለመሻማት ምንም አይነት እቅድ የላትም..እና እግሯና ወደኃላ ጎተተችና የአስተባባሪነቱን ስራዋን በትኩረት መስራቷን ጀመረች፡፡እራሷን ማሞኘት አልፈለገችም።
እሱ በእጁ ይዞ የነበረውን ባዶ ብርጭቆ በአጠገቡ በሚያልፈው አስተናጋጅ ትሪ ላይ አስቀመጠና ዓይኑን ወደ ህዝቡ መሀከል አንከራተተ። የሙሽሮቹ ዋና ተጠሪ እንደመሆኗ መጠን መጥፋት አልቻለችም። ግን እሱን ከእይታዋ ለማስወገድ እየሞከረች እንደሆነ ያስታውቅባታል፡፡‹‹እንደዛ እንድታደርጊማ አልፈቅድልሽም››ሲል ፎከረ፡፡ይሄ በእሱ ልምድ አዲስ ተሞክሮ ነበር።አንድ በሆነ አጋጣሚ ከንፈሩን የቀመሰች ሴት መልሳ ልታገኘው መከራዋን ስታይና ስትንሰፈሰፍ ነበር የሚያውቀው፣ከከበቡት ልጃገረዶች በዘዴ ተለየና እሷን ለማግኘት መጣር ጀመረ፡፡
ፀደይ ግራ በመጋባት ያለአላማ ከወዲህ ወዲያ ስትሽከረከር . ድንገት አይን አዲስ ወደእሷ ጠራቻት‹‹እ ምን ፈለግሽ?››
‹‹እኔ ምንም አልፈለኩም… ለምን ከእሱ ትደበቂያለሽ ?››
‹‹ አልተደበቅኩም›› አለች ፀአዳ፡፡
‹‹እሺ እንደዚያ ከሆነ፣ ለምንድነው ከእሱ ጎን ሆነሽ አንድ ብርጭቆ ሻምፓኝ የማትጎነጪው?ምንድነው የሚያስፈራሽ?››
‹‹እንደምታይው እሱ ብቸኛ ሰው አይደለም….ሁሉም ሰው የእሱን እዚህ ሰርግ ላይ ስለመገኘት ነው የሚያወራው -..እና ወደሰርግ አዳራሹ ከገባበት ደቂቃ አንስቶ በሰው በተለይ በሴቶች እንደተከበበ ነው››
‹‹እና ውድድሩን አላሸንፍም ብለሽ ሰጋሽ …?አዎ ከባድ ውድድር እንዳለብሽ እኔም ገምታለው።ግን እኮ ይሄንን ለመሰለ ጠንበልል አማቼ… መፋለም መቻል በራሱ እድል ነው?››
‹‹አረ በካሽ…እኔ ፀደይ ነኝ፡፡ ወንድ ለማግኘት ከሌላ ሴት ጋር የምናጠቀው። እንደው እንዳልሺው ፊልሚያ ውስጥ ልግባ ብልስ እሱ ፍላጎት ከሌለው የሚሆን ይመስልሻል…?እናስ ከእነዛ ከከተመዋ አማላይና ስብር ቅንጥስ ከሚሉ ወዳጆችሽ ጎልቼ በአይኑ የምገባ ይመስልሻል...›› በብስጭት ተንዘረዘረች፡፡
‹‹ገባሽ እኮ ..ቀድመሽ በከንፈሩ ገባሽ….ይልቅ አትንቀርፋፊ..በሰርጌ ቀን ካንቺ ጋር ከዚህ በላይ መዳረቅ አልችልም..ባሌ አየጠራኝ ነው፡፡ቻው››ብላት በቆመችበት ጥላት ሄደች፡፡
ፀደይ ለተወሰነ ደቂቃ ድንዘዝዝ አለች‹‹…ምን ላድርግ?››እራሷን ጠየቀች..፡፡ምንም ያህል ችላ ልትለውና ልትርቀው ብትሞክርም ልቧ ግን ልክ እንደማግኔት ወደእሱ እየጎተታት ነው…ወደአለበት ሄዳ ከሰውዬው ጋር ለመነጋገር ድፍረት አልነበራትም።ፊቷን አዙራም ከእሱ ርቃ ለመሰወር ብትጥርም ከዚህ የበለጠ ተጫማሪ ሳዕታትን ከእሱ ተደብቃ መቆየት እንደማትችል ልቧ ያውቃል፡፡ድንገት ስታየው ብቻውን ሆኖ ስላየችው ወደኋላ ተመለሰችና ቅዱስን ከሞግዚቷ ተቀብላ በማቀፍ እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ወደእሱ ሄደች፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…?መምጣትሽን በናፍቆት ስጠብቅ ነበር››ከአንደበቷ የሚወጡት ቃላት ልቧን በቀላሉ ማቅለጥ አቅም ነበራቸው፡፡
‹‹አልደበረህም አይደል?››
‹‹በመጠኑ…ግን በጣም የሚፈልጉትን ነገር ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥም ሆነው መጠበቅ የሆነ ደስ የሚል ስሜት አለው….እና አልከፋኝም››አላት፡፡
ዝም አለች…ምን እንደምትል ግራ ተገባች‹‹ከወንድምህ ልጅ ከቅዱስ ጋር ላስተዋውቅህ።››አለችው
ዘሚካኤል በተራው በዝምታ ተዋጠና ህፃኑን በትኩረት ማየቱን ቀጠለ። የሆነ የማያውቀው መከፋት ስሜት ውስጡን ሲያተረማምሰው ተሰማው፡፡ህፃኑን እቅፉ የተንጠለጠሉትን ውብ ጉንጮቹን እያገላበጠ ቢሰመው ደስ ይለው ነበር፤አዎ እንደዛ አይነት ፍላጎት ነበር የተሰማው፡፡ግን ከተቀመጠበት መነቃነቅ ሆነ እጆቹን ማንቀሳቀስ አልቻለም፡፡እንዲህ መሆን የለበትም ነበር፡፡እሱ በቤተሰቡ ላይ ያን አይነት መአት ከመድረሱ በፊት በጣም ሰው ወዳጅ በተለይ ዘመድ ለተባለ ሰው ልቡ ትርክክ የሚል በፍቅር የሞላ ልጅ ነበር፡፡ከክስተቱ በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ነው የሆነው፡፡ከዘመድ ጋር መነካካት መርዝ እንደመጎንጨት የሚያንገፈግፈው ነገር ሆኖል…ቢሆንም እንዲህ በጮርቃ ህፃን ላይ እንኳን የተለየ አቋም ሊኖረው አይገባም ነበር፡፡
‹‹አይዞህ አትጨናነቅ..በሂደት ጥሩ አጎቱ ትሆናለህ››አለችው፡፡
‹‹ልጁን በተመለከተ እንደጨነቀኝ እንዴት አወቀች?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡
‹‹አሁንም ብቻህን ጥዬህ ልሄድ ነው..ግን አልቆይም..ህፃኑን ለእናቱ አስረክቤ መጣሁ…››
በረጅሙ ተነፈሰ‹‹አዎ እንደዛ ይሻላል..አታስቢ ስለአንቺ እያሰብኩ ጠብቅሻለሁ፡፡››አላት፡፡
ፈገግ አለችለትና ህፃኑን ቅዱስን አቅፋ ተነስታ ሄደች፡፡ከኃላ አይኑን ተክሎ ተመለከታት..አቋሞ ልዩ ነው፡፡ተረከዘ ሎሚ የምትባል አይነት ነች..እንዲህ አይነት እግር ያላት ሴት ከድሮውም በጣም ነው የምትማርከው…ደግሞ ከሁሉም በላይ እሱ ጋር ከሚመላለሱት ሴቶች ተቃራኒ በሆነ መልኩ ምንም አይነት መዋቢያና መኳኳያ አትጠቀምም…ለምን እንደሆነ ሊገባው አልቻለም…ብትጠቀም እኮ የበለጠ ውብ ትሆን ነበር?››ሲል አሰበ፡፡‹‹ግን አንኳንም አልተጠቀመች››ሲል ደመደመ፡፡
ልጁን ለሞግዚቷ አስረክባ ብቻዋን ትመጣለች ብሎ ሲጠብቅ የወንድሙን ሚስት አስከትላ መጣች፡፡
አዲስአለም ‹‹ዘሚካኤል… በመምጣትህ በጣም ደስ ብሎናል … ዛሬ ማታ ቤታችን በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ብትገኝ እንዴት ደስ ይለናል መሰለህ …ግን ምቾት የማይሰማህ ከሆነ እንረዳሀለን….እዚህ ስለመጣህ እራሱ በእውነት በጣም ደስተኛ አድርገሀናል….ሰርጋችንም የማይረሳና የታደመው ሰው ሁሉ መቼም የሚያስታወስው እንዲሆን አድርገሀል ።››
ዘሚካኤል ደቂቃ ወስዶ እንደማሰብ ሲያደርግ ፀአዳ ጣልቃ ገብታ‹‹እባክህ እሺ ብለህ ቆይ…አይዞህ እንደአሁኑ ጣል ጣል አናደርግህም…ቃል እገባልሀለው››አለችው፡፡
ንግግሯን ስታጠናቅቅ አዲስአለምም ሆነች ዘሚካኤል አፍጥጠው እየተመለከቷት ነበር…‹‹ምንድነው የሚያስቀበጥረኝ ?››ስትል በውስጧ እራሷን ወቀሰች፡፡
ዘሚካኤል መናገር ጀመረ‹‹እሺ እቆያለው››ሲል ተናገረ፡፡
አዲስአለም ፊት በደስታ በራ‹‹አመሰግናለው..በቃ አሁን ጥያችሁ ልሂድ …አብረሽው ቆይና ይዘሽውን ነይ››አለችና ተመልሳ ሄደች፡፡
ፀአዳ ከእፍረቷ ሳትላቀቅ በዝግታ ተቀመጠችና፡፡‹‹እሺ ትላለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር››አለችው፡፡
‹‹እውነቱን ለመናገር እኔም እሺ እላለው የሚል ግምት አልነበረኝም….ቃልሽን አምኜ ነው እሺ ያልኩት››አላት፡፡
‹‹ማለት የምን ቃል?››
‹‹እንደእስካሁኑ ብቻህን በመተው እንድትደበር አላደርግህም…ከመጀመሪያው እስከፍጻሜው ከጎንህ አልለይም…›ብለሽ የገባሽልኝን ቃል ነዋ››
‹‹አንተ ይሄን ሁሉ መቼ ነው የተናገርኩት.››
‹‹.አሁን ከደቂቃዎች በፊት››
‹‹ይሁን..ለማንኛውም ማትቆጭበት ውሳኔ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው››

👍63❤13🥰2
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
///
ፀሐይ ከምዕራቡ አድማስ በላይ ልክ እንደ አንድ ግዙፍ ብርቱካንማ ዲስክ ተንጠልጥላ ነበር፣ ብሩህ ነሐስ ትመስላለች። ሰማዩ ቀዝቃዛ እና የሚረብሽ አይነት ነው፡፡ ከከተማ ወጣ ብሎ የሰሜኑ ንፋስ የጠነከረ ይመስላል። ተክለሀይማኖት ቤተክርሲቲያኑ በራፍ ጋር ስትደርስ መኪናዋን ጥግ አስይዛ አቆመችና መጀመሪያ ተሳለመች…ከዛ ቀጥታ ወደ መቃብር ስፍራዎች ነው ሄደችው። ወደ እናቷ መቃብር ሄዳ አታውቅም ስለዚህ የመቃብር ድንጋዬች ላይ የተጻፉትን ፅሁፎች እያነበበች መፈለግ ጀመረች፡፡ከአስር ደቂቃ አሰልቺ ሚመስል ፍለጋ በኋላ ተሳካላትና አገኘችው፡፡የእናቷ የመቃብር ድንጋዮች ላይ የበቀሉት ሣሮች ረዥም እና አረንጓዴ ናቸው፡፡
ወደመቃብሩ ለመጠጋት ፈራች …ከእናቷ መንፈስ ጋር ለማውራት ዝግጁ የሆነች አልመሰላትም፡፡አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው የእምነበረድ ምልክት ከመቃብሩ አናት ተተክሏል፡፡ የእናቷ ሙሉ ስም ፤ የእናቷን የትውልድ ቀን እና የሞት ቀን ተፅፎበታል፡፡እሰከዛሬ አይታ የማታውቀው ውብ የሚባል ፎቷዋ ከፅሁፎቹ በላይ አለ - ሌላ ምንም ነገር የለውም. ፡፡
‹‹ሩጫዬን ጨርሼለሁ….››የመሰለ አንድ ጥቅስ እንኳን ከስር ቢያሰፍሩበ ስትል አሰበችና ልቧ አዘነባት።መልሳ ስታስበው እርባን የሌለው ነገር እንደሆን ሲገባት ቅሬታዋን ሰረዘችው፡፡
እናቷ ሰሎሜ በጣም ወጣት እና ቆንጆ እና ሙሉ ተስፋ የነበራት ሴት ነበረች፣ነገር ግን ማንነቷ በተገቢው መንገድ እንዳይገለፅ በአጭሩ እንድትቀጭ ተደርጓል፡፡ ከመቃብር አጠገብ ተንበረከከች። በእናቷ ቀብር አጠገብ ምንም አይነት ሌላ የቅርብ ዘመድ መቃብር ባለመኖሩ ቅር አሰኛት፡፡እሷ የሚሰማትን አይነት ብቸኝነት እናቷም የሚሰማት አድርጋ ነው የወሰደችው፡፡ በውትድርና አገልግሎት ላይ እያለ የሞተ አባቷ አስከሬን እዛው በተሰዋበት ጦር ሜዳ ነው የተቀበረው፡፡ሰሎሜ ገና ልጅ እያለች የሞተው አያቷ በትውልድ ከተማው
ኮፈሌ ነው የተቀበረው።በዚህ የተነሳ የሰሎሜ መቃብር ብቸኛ ነበር። ድንጋዩን ስተነካው ከጠበቀችው በላይ ቀዝቃዛት . የእናቷን የመጀመሪያ ስም የተቀረጹትን ፊደሎች በጣቷ እየዳበሰች መረመረች፣ ከዚያም የልቧ ምት እንደሚሰማት እጇን ከፊት ለፊቱ ባለው ሳር ላይ ጫነች።ከተፈጥሮ በላይ በሆነ መንገድ ከእሷ ጋር መነጋገር እንደምትችል ማሰቧ ሞኝነት መስሎ ተሰማት ፣ ነገር ግን የደረቀ ሳር መዳፏን ሲወጋ "እናቴ" ብላ ወደቀልቧ ተመለሰች።
"ማማ. እማዬ." ስሞቹ ለምላሷ እና ለከንፈሯ እንግዳ ነገር ሆኖ ተሰሟት። ከዚህ በፊት በየትኛውም አጋጣሚ ተጠቅማበት አታውቅም።በዚህ ጊዜ ከጎን በኩል ስሟ ሲጠራ ሰማች…ግራ ገባት..የሆነ እርኩስ መንፈስ ሊተናኮላት እየሞከረ ነው የመሰላት…፡፡
"አሌክስ….›› በድንጋጤ ዙሪያውን ተመለከተች..በዚህ ስም የአዲስአበባ አብሮ አደግ ጓደኞቾ ናቸው የሚጠሯት፡፡እንዴት እዚህ ተገኙ። ሚመታው ልቧ ላይ እጇን እየጫነች፣ በፍርሃት ተንፈሰች።ዞር ስትል ያልጠበቀችውን ሰው ነው ያገኘችው፡፡
" አስደነገጥከኝ … እዚህ ምን እየሰራህ ነው?"
ጁኒየር ፍሰሀ አጠገቧ ተንበርክኮ በመቃብሩ ቆሚ ድንጋይ ላይ እቅፍ አበባ አስቀመጠ። ለአፍታ በራሱ ጥሞና አቀረቀረና ከዛ ፊቱን ወደ አለም አዙሮ ፈገግ አለላት፡፡
"በደመ ነፍስ ወደ አረፍሽበት አፓርታማ ደውዬ ነበር…ነገር ግን ስልኩ የሚያነሳ አልነበረም።"
"የነበርኩበትን ሆቴል ለቅቄያለው … የት እንደገባው እንዴት አወቅክ?"
"በዚች ከተማ ውስጥ ስለሚከወነው ሁሉም ነገር መረጃውን በቀላሉ ማግኘት እችላለው ." "ወደ መቃብር ስፍራ እንደምመጣ ግን ማንም አያውቅም።››
" በአንቺ ጫማ ውስጥ ብሆን የት እንደምሆን ለመገመት ሞከርኩኝ. በመምጣቴ እንዳላስደበርኩሽ አገምታለው."
"አይ. ምንም አይደለም…አሌክስ ስትለኝ እኮ በጣም ነው ግራ የተጋባሁት."
‹‹እንዴ ለምን?››
‹‹በዚህ ስም የተወሰኑ የቅርብ ጓደኞቼ ብቻ ናቸው የሚጠሩኝ…እዚህ እንግዳ በሆንኩበት ከተማ ይሄን ስም ተጠቅሞ የሚጠራኝ ሰው ይኖራል ብዬ እንዴት ልገምት?››
‹‹ያው እኔም ጓደኛሽ ለመሆን ካለኝ ጉጉት የተነሳ ነው ይሄን ስም የተጠቀምኩት…ባለፈው እዛ ፍርድ ቤት እራስሽን ስታስተዋውቂን ስሜ አለም ይባላል..ጓደኞቼ አሌክስ ብለው ይጠሩኛል ስትይ …እኔም አሌክስ የሚለውን ስም ስለተመቸኝ ቀለብ አድርጌ በምናቤ አስቀመጥኩት››
‹‹አይ ጥሩ ነው..ደስ ብሎኛል….ብዙ ጊዜ ወደ እናቴ መቃብር አበባ ታመጣለህ ?"ስትል ጠየቀችው፡፡
ፈጥኖ አልመለሰላትም።
" በተወለድሽበት ቀን ሆስፒታል ነበርኩ፣ ከመታጣብሽ በፊት ከነደምሽ አይቼሻለሁ።" አላት፡፡ፈገግታው ክፍት እና ሞቅ ያለ ነው፣
‹‹ጥሩ ..እሺ መጀመሪያውን ጥያቄ መልስልኝ፣ብዙ ጊዜ አበቦችን እዚህ ታመጣለህ?."
" በበዓላቶች ቀን ብቻ ነው ። እኔ ፤ አባቴ እና ኩማንደር ገመዶ በልደቷ፣ ገና፣ ፋሲካ፣ሲሆን አንድ ላይ እናመጣለን። መቃብሯን ለመንከባከብ የሚያስፈልገውን ወጪ በጋራ እንሸፍናለን።"
"ለምን ?የተለየ ምክንያት አላችሁ?"
ያልተለመደ አይነት አሰተያየት አያት….ከዛ "ሁላችንም እናትሽን እንወዳታለን…ምክንያታችን ያ ነው፡፡›› ሲል መለሰላት፡፡
ለስለስ ባለ የድምፅ ቃና "የሚገርመው ግን ከእናንተ አንደኛችሁ እንደገደላችኋት አምናለሁ" አለችው ።
" ተሳስተሻል አሌክስ ፤እኔ አልገደልኳትም።"
"አባትህስ?
እሱ ያደረገው ይመስልሃል?"
ራሱን በምሬት ነቀነቀ "አባቴ እንደ ሴት ልጅ ነበር ሚንከባከባት፡፡. እሷም እንዲሁ እንደአባቷ ነበር የምታየው."
"እና ኩማንደር ገመዶስ?"
ማብራርያ የማያስፈልግ መስሎት ትከሻውን ነቀነቀ። "ገመዶ ፈጽሞ ሊገድላት አይችልም ››
አለም በእጇ አንጠልጥላ የነበረውን ባለ ፀጉር ጃኬቷን ለበሰች ። ፀሀይዋ እየጠለቀች ነበር፣
"ዛሬ ከሰአት በኋላ በሕዝብ ቤተመጻሕፍት ውስጥ የተወሰነ ጊዜ አሳልፌ ነበር፣ የቆዩ የሀገር ውስጥ ጋዜጣ እትሞችን መለስ ብዬ ለማንበብ ሞክሬያለው።"
"ስለ እኔ የሆነ ነገር አገኘሽ?"
"ኦህ አዎ፣ ስለከነማ እግር ኳስ ቡድን ተሳትፎህ ሁሉም ነገር ተፅፏል።;;›› ተንከትክቶ ሳቀ.. ንፋሱ ቆንጆ ጸጉሩን አውለበለበለት፡
"አንተ እና ገመዶ የቡድኑ ዋና እና ምክትል አንበል ነበራችሁ።"
"በሚገርም ሁኔታ አዎ…..የማይበገሩ፣ እውነተኛ እግር ኳስ ተጫዋቾች እንደሆን ነበር የምናስበው።"
" በጊዜው ወጣት የነበረችው እናቴ ወደ ቤታችሁ የምትመጣ ንግስት ነበረች። በእረፍት ሰአት ከገመዶ ጋር ስትስማት የሚያሳይ ፎቶ አይቼያለሁ።››
ያን ፎቶግራፍ ባየች ጊዜ እንግዳ ነገር ነበር የተሰማት። በፊት አይታው አታውቅም ነበር። በሆነ ምክንያት አያቷ ከብዙዎቹ ጋር ላለማቆየት መርጣለች፣ ለብዙ ደቂቃዎች ፎቶግራፉን ካየች በኋላ እናቷ ሳትሆን እራሷ እንደሳመችው ይሰማት ጀመር። ወደ አሁኑ ጊዜ ስትመለስ፣ "እስከእዛን ጊዜ ድረስ ከእናቴ እና ከገመዶ ጋር ጓደኛ አልነበርክም አይደል?"ስትል ጠየቀችው፡፡
ጁኒየር የሳር ቅጠል አነሳና በጣቶቹ በመቆራረጥ ማውራት ጀመረ። "ዘጠነኛ ክፍል እስክደርስ ድረስ በኩየራ በሚገኝ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር የምኖረው"
"በምርጫህ?"

❤43👍6🔥1