አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#በክፍለማርያም

በነፋሻዉ አየር በንፋሱ ዉልብታ ቅርንጫፎቹን ከወዲህ ወድያ የሚዉረገርገዉን የባህርዛፉን ግንድ ተደግፋ
ቤዛዊት የቀጠረችዉን ፍቅረኛዋን በጉጉት አይኖቿ አሻግረዉ እያዩ ትጠብቃለች።
እማማ ስንቅነሽ ትመጣለች ብለዉ ያልጠበቋትን የበፊትዋን እብድ ጤነኛ ሆና በመምጣቷ እየተደሰቱ እና አምላካቸዉን እያመሰገኑ በጠዋት መጥታ እንግዳ ስለሆነችባቸዉ ቁርስ ቢጤ ሊሰሩላት ደፋ ቀና እያሉ ነዉ።

በእርግጥ ከህልማቸዉ ጠፍታ አታዉቅም እርቃኗን ሆና በብርድ ስትንሰፈሰፍ አይናቸዉ ላይ ስለተቀረፀች
ድቅን ትልባቸዋለች በወለደ አንጀታቸዉ አፈር አልብሰዉ የቀበሯት ልጃቸዉን ያዩ ይመስል ቤዛዊትን
ሲያዩ ስፍስፍ ብለዉ ያዝኑላታል።

ፍፁም ነግቶ ልቡም በጭንቀት እንደተወጠረ ቤዛዊት ካለችዉ ቦታ ለመሄድ ለባብሶ ጨርሶ የአንድ እጁን ክራንች
ትቶ በአንዱ ብቻ እየተጠቀመ በሩን ቆልፎ ከወጣ በኋላ የፃፈችለት ወረቀትን ከኪሱ አዉጥቶ በድጋሜ ተመልክቶ
ኪሱ ዉስጥ መልሶ ሊከተዉ እየሞከረ ከጀርባዉ አከራዩ ጉሮሮአቸውን እየጠረጉ

"እህህ እንዴት አድረሀል አቶ ፍፁም?"

ፍፁም ሳያስበዉ ስለጠሩት ደንገጥ እያለ እና የቤት ኪራይ ቀን መድረሱም ትዝ እያለዉ ኪሱ ዉስጥ ከያዘዉ ዳጎስ
ያለ ገንዘብ መሀል ቆጥሮ እያወጣ ለአከራዩ እየሰጣቸዉ
"ይመስገን"
አላቸውና ስዓት እንዳያረፍድ እና ቤዛዊትን እንዳያጣት አስቦ እየተቻኮለ ወጣ።

የቤዛዊት አባት ቤዛዊት ቦርሳ አንግባ እንደወጣች ከእንቅልፋቸዉ እንደነቁ ሰራተኛቸዉ ስለነገረቻቸዉ ተናደዉ
"እዚች ልጅ ላይ ያለዉ ሴጣን መች ይሆን እረፍት የሚሰጠን"
እያሉ እያጉተመተሙ ወደ ቤዛዊት መኝታ ክፍል ደርሰዉ እንደገቡ መጀመርያ አይናቸዉ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠ
ወረቀት ላይ ስለሆነ በእጃቸዉ ሳይነኩት በእርቀት ቆመዉ ለማንበብ አንገታቸዉን ሰገግ አርገዉ አይኖቻቸውን
ሰደዱ
"አትፈልጉኝ በፈጠራችሁ አምላክ ተዉኝ"
የሚሉ ቃላቶችን ሲያነቡ ወረቀቱን አንስተዉ ጨምድደዉ እየወረወሩት
"ጥርግ በያ ለኔ ስትይ ገደል ለምን አትገቢም"
እየጮሁ ተናግረዉ በሀሳብ እና በንዴት እየተዉረገረጉ ወደ ሳሎን አምርተዉ ተለቅ ያለዉ ሶፋ ላይ
ዘፍ ብለዉ ተቀምጠዉ ቤዛዊትን ማማረር እና መራገም ጀመሩ
"የእራሷ ጉዳይ"
አሉና ስለ ቤዛዊት ላለማሰብ ፂማቸዉን በእጇቻቸዉ ሲነካኩ ቆይተዉ አይናቸዉ ከሳሎኑ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለዉ
የቤተሰብ ፎቶ ላይ ተተክሎ ቀረ
እሳቸዉ ባለቤታቸዉን አቅፈዉ ፎቶዉ ላይ ይታያሉ የቤዛዊት ታላቅ እህት እናቷን ተደግፋ ከጀርባ ቆማለች
ፊቷ ላይ ፈገግታ ይነበባል ቤዛዊት ከረሜላ አልገዛልህም እንደተባለ ህፃን አኩርፋ አባቷን ተደግፋ ትታያለች
የቤዛዊት አባት ፎቶዉን እያዩ ቆይተዉ ቤዛዊት ላይ መጨከን እና መተዉ አላስችል ስላላቸዉ
በሀዘን ተዉጠዉ ለአቶ ፍቃዱ እርዳኝ ለማለት ስልካቸዉን አዉጥተዉ መደወል ጀመሩ።

ተንኮለኛ እና ሞኝ ሰዉ አይጥመድህ ከህይወትህ ለማሶጣት በጣርክ ቁጥር የጠራከዉ ይመስለዋል
ስለዚህ ሁሌም ሲከተልህ ይኖራል
ፍቃዱ እየተጣደፈ ስራዉን ትቶ የፍፁምን እና የቤዛዊትን ህይወት ለማመሰቃቀል ወደ ፍፁም የተከራየበት ቤት
አመራ ወደ ግቢዉ ሲደርስ ቤዛዊት ኖራ እንዳትመታዉ እራሱን ለመጠበቅ እየተንሿከከ ወደ ግቢዉ ዉስጥ ዘለቀ።

የፍፁም በር ጋር ሲደርስ ከጀርባዉ ሰዉ መኖር እና አለመኖሩን ለማረጋገጥ ዙርያዉን ቃኝቶ ጆሮዉን የፍፁም በር
ላይ ለጥፎ ሲያዳምጥ ድምፅ በማጣቱ እየተገረመ በሩን ሲያንኳኳ እና ቆይቶም ለመክፈት ሲታገል ማንም አለመኖሩን ሲያዉቅ እየተበሳጨ ወደ መጣበት ሊመለስ ሲል መሬት ላይ የወደቀ ወረቀት አይቶ ጎንበስ ብሎ
ካነሳዉ በኋላ ለማንበብ ሞከረ
የቦታ አድራሻ የቀጠሮ ሰአት መልሶ መሬት ላይ ጥሎት ሹክክ ብሎ ወደ ዉጪ ወጣ
" የት ሄደዉ ይሆን "
ሲል ብዙ ካሰበ በኋላ ወረቀቱ መልስ ያለዉ ስለመሰለዉ ወረቀቱን ፍለጋ
ወደ ፍፁም ግቢ ፈገግ እያለ ተመለሰ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

.... የተከመረ የብር ብዛት በዓይነ ህሊናቸው ላይ ሄደና በደስታ ሰክረው ተቃቀፋ፡፡

አንድ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ፖስፖርት፣ ልዩ ልዩ ሰነዶች ነበሩበት፡፡ ፖስፖርቱንና ሰነዱን ቢቻል ለመመለስ ባይቻል ሊጥሉት ተስማሙ።

ቀይዋን ሲትሮይን መኪና እያከነፈ ከስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደደረሱ በንዴት ደም ስሮቹ የተገታተሩትና፤ ፀጉሩ እንደ ጃርት እሾህ የቆመው ነጭ! የበለጠ ነጭ ሆኖ፣ አስተርጓሚውን ይዞ ወደ ግቢ ዘለቁ፡፡እባክህ ወንድም ዕለታዊ የወንጀል ሪፖርት መቀበያውን ብትጠቁሙን”
ሲል ከበር ላይ የቆመውን ፖሊስ አስተርጓሚው ጠየቀው፡፡ ፖሊሱ
ሪፖርቱን የሚያስመዘግቡበትን የቢሮ ቁጥር በጣቱ አመለከታቸውና ተያይዘው ሄዱ፡፡ ከገንዘቡ የበለጠ ያበሳጨው የጠቃሚ ሰነዶቹ እና የፖስፖርቱ ጉዳይ ነበር፡፡

የዕለት ሁኔታን መዝጋቢው የተፈፀመውን ስርቆሽ በአስተርጓሚው አማካይነት ከመዘገበ በኃላ በተለይ ወንጀሉ የተፈጸመበት ሰው የውጭ ሀገር ዜጋ መሆኑና ይህ ድርጊት ከወትሮው ለየት ያለ በመሆኑ፤የጉዳዩን ክብደት ከአገር ደህንነት ጋር በማገናዘብ፤ ስለሁኔታው
ለምርመራ ሹሙ ሪፖርት ሊያደርግ ፈለገ፡፡
“አንድ ጊዜ እዚሁ ጠብቁኝ ” አለና የምርመራ ክፍል ሹም የሚል ጽሑፍ የተጻፈበትን የቢሮ በር አንኳኩቶ ወደ ውስጥ ዘለቀ፡፡

አምሽቶ በመስራት ላይ የነበረው የምርመራ ክፍል ሹም ሁኔታውን እንደሰማ አመልካቾች እንዲገቡ አደረገ፡፡ ከዚያም የተፈጠረውን ሁኔታ፤
የወንጀሉን ሂደት፤ የሌቦቹን የእንቅስቃሴ ስልት፤ አንድ በአንድ ከመዘገበ በኋላ ከበድ ያሉ ወንጀሎችን መርምሮ ተጨባጭ ውጤት በማስገኘት ረገደ ተደጋጋሚ ድል ያስመዘገበው የ፶ አለቃ ውብሸት አየለን አስበው....
“ወንጀልን ሪፖርት ማድረግ ቀላል ነው፡፡ ወንጀለኛን አድኖ በቁጥጥር፤ ስር ማዋል በተለይም በቀላሉ ዱካውን ለመያዝ አስቸጋሪ የሆነ ወንጀለኛን ፈልጎ ለማግኘት ግን ትዕግስት፤ ዘዴንና፤ጊዜን ይጠይቃል፡፡
ምናልባት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደርስበታለን ብለን በእርግጠኝነት
ባንደፍርም፤በትዕግሥት በምናካሂደው ምርመራ የሚያመልጠን ነገር ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡ ለማንኛውም ጉዳዩ ልዩ ትኩረት የምንሰጠው ይሆናል፡፡” ይህንን ከተናገረና የስልክ ቁጥሩን
ለእንግዳው ሰው ሰጥቶ ካሰናበታቸው በኋላ፣ በእልህና በቁጭት ከንፈሩን ነክሶ፣ የዚህን ወንጀል ፈጻሚዎች ጉዳይ በአስቸኳይ ከውጤት ላይ
እንደሚያደርስለት በመተማመን ፤
ጉዳዩን ለሃምሣ አለቃ ውብሸት
ለመስጠት ወሰነ....

ፈጣኑ የ፶ አለቃ ውብሸት አየለ እምነት ጥሎበትና እሱን መርጦ አለቃው ይህንን ኃላፊነት ከሰጠው ቀን ጀምሮ ሃሣቡ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ሆነ፡፡

ቁርስና ምሣውን ሳያስታውስ፤ ቀንም ሆነ ምሽት የማጣራቱን ሥራ ሲያከናውን እያንዳንዷን ጥቃቅን መረጃ ጭምር ሳይንቅ፤የወንጀሉን ሂደትና የወንጀለኞቹን ሁኔታ ሲያነፈንፍ፤ ከቆየ በኋላ ወደ አንድ ግብ የሚያመራው ፍንጭ አገኘ፡፡ በተለይ “ጋሪ” በሚል ቅጽል ስሙ
የሚታወቀው ጉጭማው ቱለማ ተደጋጋሚ የስርቆሽ ሪኮርድ ያለበት
መሆኑንና: በዚያን ዕለትም በአካባቢው ሲያንዣብብ የቆየ ጆፌ መሆኑን
ደረሰበት፡፡ አብረውት ስለነበሩትም መጠነኛ መረጃ አገኘ፡፡
ይህ ሁሉ አደን ዛሬ እንደሚያበቃና አዳኝና ታዳኝ በግልጽ ሊያፋልማቸው ወደሚያስችል አዲስ ምዕራፍ መሸጋገራቸውን አዳኝም ታዳኝም አላወቁም ነበር፡፡

መላኩ በአካባቢው ስለሚካሄደው ሁኔታ እንዲያጠናና፤ አዲስ የፖሊስ እንቅስቃሴ ካለ እንዲያስታውቃቸው ፤ ለአሰሳ ተልኳል፡፡በዛሬው ዕለት በስንዱ ቤት ልዩ ፕሮግራም ተይዟል ስንዱ ከመኖሪያ ቤቷ አንዱን ክፍል ለዛሬ የጫት ዕድምተኞቿ
አዘጋጅታላቸዋለች፡፡
ከዳር እስከ ዳር የተገጠገጠው ስጋጃ፤ በላዩ ላይ እዚህም፧ እዚያም ፈንጠር፤ ፈንጠር፤ ተደርገው በተቀመጡ አሸብራቂ ትራሶች ደምቋል።
ክፍሉ በርከት ያሉ የጫት ታዳሚዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ ሆኖ እየተጠባበቀ ነው፡፡
የሰሞኑ በሽበሽ የሰሞኑ መጠጥ የስሞኑ ደስታና ጭፈራ፣ ሲታሰብ ይህ ለእነ ጋሪ ቢያንስ እንጂ በዛ የሚባል አይደለም፡፡
ስፋ ያለው የመኝታ ክፍሏ ወለሉ ላይ ቄጠማ ተጐዝጉዞበት፤
እመሃሉ ጉብ ብሎ የሚታየው ባለሸክላው የክሰል ማንደጃ፤ በደሬ ክሰል ፍም ነዶ! እዚህም፧ እዚያም፤ ሰንደሉ ተለኩሶ ሲታይ፤ እንኳንስ የቃመውን ተመልካቹን የሚያስመረቅን ነበር፡፡

የጫቱ ፕሮግራም የሚጀመረው ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ሲሆን፤ ምርቃናው ተጋግሞ ሲያበቃ፤የጨብሲው ፕሮግራም
ይቀጥላል።
ጨብሲው ደግሞ እንደዚህ የዋዛ አይደለም፡፡ ወንድ ነኝ ያለን በእግርና በእጁ ዳዴ ብሎ እስከሚሄድ ድረስ በሚንቆረቆረው የቢራና የውስኪ ፏፏቴ መጠመቅንም የሚያጠቃልል ነበር፡፡

በዚህ የጫት ፕሮግራም ላይ የሦስቱም የሴት ጓደኞቻቸው ተጋብዘዋል፡፡ በአንድ ወቅት ከጋሪ ጋር በፍቅር አብዳ የከነፈችውና አሁን በካዛንችስ አካባቢ የመንገድ ላይ ዝሙት አዳሪ የሆነችው ሂሩት ጥሪው የተደረገላት በጓደኛዋ በሜርኩሪ አማካኝነት ነበር፡፡ሂሩት በዚህ የጫት ፕሮግራም ላይ ጋሪ የሚገኝ መሆኑን እንዳወቀች ልታስቀናው ፈለገች፡፡ አጋጣሚውን ለመጠቀም በሃሣቧ የወንድ ጓደኞቿን በሰልፍ ከደረደረች በኋላ አንደኛውን መረጠችው፡፡
ከጓደኛዬ ጋር ካልሆነ ብቻዬን አልመጣም” አለቻት ለሜርኩሪ፡፡ሂሩትዬ አንድ አይደለም ከፈለግሽ ሦስቱን መጋበዝ ትችያለሽ”አለቻት በኩራት፡፡
ሜርኩሪ ይህንን ለማለት የደፈረችው፤ የሰሞኑ ርዝቅ ፤የሰሞኑ በሽበሽ
የዋዛ እንዳልሆነ ስለምታወቅ ነበር፡፡
እንግዲያው ሦስት ሣይሆን ከቦይ ፍሬንዴ ጋር እመጣለሁ” አለቻትና በዚህ ተስማሙ፡፡
ሂሩት ለዛሬው ግብዣ የመረጠችው መልኩ እንኳንስ የሴቱን የወንድ ልጅ
ልብ የሚያስደነግጠውንና፤ የወንድነት ድንግልናውን የወሰደችለትን ሰው
ነው፡፡ይህ ሰው ለዛሬው ግብዣ በጣም ተስማሚ እንደሚሆንና ያንን እሷ በፍቅር ከንፋለት ሳለ ፍቅሯን ሳያስጨርሳት...
“ጥፊ ከዚህ ብሎ ” ያባረራት ጋሪን ሊያስቀናው ይችላል ብላ ያመነችበት
አንዱአለም ድንበሩ ነው፡፡ለአሥራ ሁለት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ሲሆን ታዳሚዎች በቀጠሮ ቦታቸው ደረሱ፡፡ዛሬ ስንዱ ለሁሉም የምትጋብዛቸው ፈገግታ እህል ትዝ አያሰኝም፡፡ ሁለመናዋ ስቆ፤ ያ ንቅሳታም ጥርሷ የበለጠ ተውቦ፤ ጥርስ
በጥርስ ሆናለች፡፡ በተለይ ጋሪን ከንፈሩን ነው የሳመችለት፡፡

በአጭር የታጠቀችው ጉርድ ቀሚስ ያንን ጠብደል ጭኗን በስፋት ያስቃኛል፡፡ በዚህ ላይ ማታ ማታ በፖርቲው ውስጥ በጨረታ የማትገኘውና፤ በበርካታ ጠጪዎች የምትታሸዋ ቆንጅዬዋ ማርታ ነች ለካዳሚነት የተመረጠችው ::ብቻ ዛሬ ምርጥ ምርጡ ሁሉ ለእነ ጋሪ ሆኗል።
ኪሣቸው ሲመነምንና፤ ዝንብ ሊወራቸው ሲጀማምር፤ ጀርባዋን እንደማትሰጣቸው ሁሉ፤ ዛሬ አፋሽ ፤አጉንባሽ ሆናላቸዋለች፡፡
በአንድ መቶ ብር የተገዛው ለምለም ጫት በእንሰት ተጠቅልሎ እዚያ እመሃላቸው ተገንድሶ፤ ሲታይ ለፋሲካ የተጣለ ሙክት ይመስላል።

ሂሩት የአንዱዓለምን ክንድ በክንዷ ቆልፋ፤ ከሜርኩሪ ጋር ከተቀጣጠሩበት ቦታ ተገናኙ፡፡ ሜርኩሪ አንዱዓለምን በእነዚያ ቀዥቃዣ ዐይኖቿ ላጠችው፡፡ በውበቱ ተደንቃ ፈዝዛ ቀረች፡፡
እንዴት ደስ የሚል ልጅ ነው በእግዚአብሔር? አደነቀችው፡፡ብዙም ሳይጓዙ ወደ ውስጥ ታጥፈው ስንዱ ቤት ደረሱ፡፡ ሦስቱ የመጨረሻ እድምተኞች ተያይዘው ሲገቡ፤ ቤቱ ተሟሙቆ ነበር፡፡ ሂሩትን እንዳየ ጋሪ ዓይኖቹ በቅናት ተበለጠጡ፡፡ በተለይ በአንዱዓለም ላይ
ፈጠው ቀሩ፡፡ ልታስቀናው እንደፈለገች ገባው፡፡
“ማን አባቷ ጠራት ይህችን ውሻ በልቡ ሰደባት፡፡

ሂሩት የጋሪ ዐይኖች በቅናት መቅላታቸውን ስትመለከት አንጀቷ
👍1
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...የሐኪሙ የስሜት ሕዋሳቶች ክፉኛ ተነቃቁ ስሟን ሳያውቁ ሳያነጋግሩ ዝም ብሎ እያዩ መውደድ ? ! እንዴት?

"ፈጽሞ አነጋግረሃት አታውቅም ? "
"እንዲያዉም ። ”
“ ስንት ጊዜ ሆናችሁ ? ”

"ስንተያይ አራት ወር ገደማ ሆኖናል"

"እሷ ከሩቅም ቢሆን ላንተ ያለት ሁኔታ እንዴት ነው?"

"እንጃላት ! መጥፎ ጓደኞች ናቸው ያሏት ።

ፊቱ ተለዋወጠ ። አርዕስተ ነገሩ ወስጥ እያሰመጠ በሄደ ቁጥር ዐይኖች እየቀሉ መጡ።

"ትወዳታለህ ? ”

“ እንዴ አዎ ! ግን ደግሞ ጠላቴም ነች እጠላታለሁ ትምህርቴን እንዳላጠና አድርጋኛለች ። ”

የቀሉት ዐይይኖቹ እንባ ሲያቀሩ ሐኪሙ ተመለከተ።

"ኳስ ጫዋታ ትወዳለህ ? ”

አቤልን ከሰመጠበት ተመስጦ ለማውጣት የቀረበ የማዘናጊያ ጥያቄ ነበር ። እውነትም አቤል ግር አለው። የማያስፈልግ ጥያቄ !

“ አ....ዎ ፥ የእጅ ኳስ ዐልፎ ዐልፎ ። ብቻ ይሄን ያህል አይደለሁም ፥ አለ ዐይኑ ላይ ያቀረረውን እንባ ወደ ውስጥ እየመለሰ።

"ሌላ ምን ጨዋታ ትወዳለህ ? በትርፍ ጊዜህ ? ”
በቃ ብዙም ጨዋታ አልወድም በትርፍ ጊዜዬም መፅሐፍ ማንበብ ነው የማዘወትረው።

ሐኪም ለጥቂት ሴኮንዶች በዝምታ የአቤልን ገጽታ ሲያጠና ከቆየ በኋላ መረጋጋቱን ሲገምት ወደ አርዕስትቱ
ነገሩ ገባ።
“ ግን አቤል ለምን ልጅቷን ቀርበህ አታነጋግራትም ? ”

“ አልችልም ! ”

ስሜቱ እንደ ገና ተለዋወጠ ቁጣ ቁጣ አለው።

ሐኪም ዘልቆ ማነጋገር እንዳማይችል ተረዳና በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄውን አበቃ ሆኖም የአቤል አመላለስ አስገርሞት ሣቁን በሆዱ አፍኖ ነበር የያዘው እወዳታለሁ ግን አላናገራትም ዝግ ፍቅር !

ሐኪሙ አቤልን የሚረዳበትን መንገድ አሰላሰለ ልጅቷን አምጥቶ የማገናኘት ሐሳበ መጣለት ፡ ሆኖም አቤል ለልጅቷ ያለው ፍቅር ሙሉ በሙሉ ጤናማ እንዳለሆነ ስለ ገመት ይህ የማያዋጣ ሃሳብ ሆነበት የባሰ ችግር ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት ያዘው ። አንዴ በተመሳሳይ ሁኔታ ያፈቀረ አንድ ወጣት ልጅቷን ፊቱ አቅርበው ሊያጨባብጡት፡ ካልገደልኩሽ ብሎ እንዳነቃት ሐኪሙ አስታወሰ። ለጊዜው መፍትሄ በማጣት በረዥሙ ተነፈሰ።

"እሺ ልጅ አቤል እንቅልፍስ አዴት ነዉ• ? ደግና ትተኛለህ፥ ?

“ አልተኛም ታግዬ ታግዬ በመከራ ነው የሚወስደኝ።

ሐኪሙ በትንሽ ፓኮ ኪኒኖች ጨምሮ ሰጠውና የሚውጥበትን ጊዜና መጠን ነግሮት ፡ “ ለእንቅልፍ ይረዳሃል ።
አለው ።

ሐኪሙ አቤልን ከማሰናበቱ በፊት የሆነ ነገር አስቦ ከመቀመጫው ተነሣና “እንድትጠብቀኝ፥ መጣሁ ” ብሎት
ወጣ ። ለአቤል ቋጠሮ ከመስጠቱ በፊት ቀደም ብሎ ተመሳሳይ ሁኔታ ያከመ አንድ ሥራ ባልደረባውን ለማማከር፤ወደ ሌላ ክፍል መሄዱ ነበር ።

በሩን ከፍቶ ሲወጣ፥ሰዎች ተኮልኩለው ተመለከተ አንድ ግዙፍ ራሰ በራ ሰውዬ ተጠግተውት “እርስዎ ጋ ነበር ዶክተር ” አሉት ።

“ ምንድነው?” እላቸው በተሰላቸ ስሜት ። በራቸውና ግዙፍ ሰውነታቸው ከብዶት ነው እንጂ ገፍቶአቸው ሊያልፍ ነበር ።

አቤል የሚባል ተማሪ ለምርመራ እርስዎጋ መግባቱን ሰምቼ ነው ። ከዩኒቨርስቲ ነው የመጣሁት ፡ እዚያው
መምህር ነኝ ” ዮናታን እንዲህ ራሳቸውን ካሰተዋወቁ በኋላ ከሐኪሙ ግጽታ ክብር ያለው ምላሽ አገኙ ።

እስክንድር አጠገባቸው ቆሞ ሁኔታውን ታዝቦአል ።ዮናታን ራሳቸውን ከማስተዋወቃቸው በፊትና በኋላ በሐኪሙ የተደረገላቸው መስተንግዶ ልዩነት እያስገረመው "የእያንዳንዱ ሰው የውስጣዊ ማንነቱ ግንባሩ ላይ መነበብ
ቢችል ምን ነበረበት ? ” ሲል አሰበ ።

“ አሁን እንዴት ነው አቤል ? አሉት ዮናታን የሐኪሙን ዐይን ዐይን እያዩ ።
ደኅና ነው ።

“ ማለቴ ፡ የሚያስተኛው ይመስልዎታል ? ምናልባት ከባሰባቸው የአዕምሮ ሕመምተኞች ጋር መቀላቀሉ መጥፎ
ይሆናል የሚል ሥጋት ይዞኝ ነው” አሉ ዮናታን ፈራ ተባ በሚል ድምፅ ።

እሱ የእኔ ሥራ ነው ” እሳቸው ሐኪሙ ቆጣ ፡ ኮራ ብሎ ፡ “ ለማንኛውም ልጁ ደኅና ነው አናስተኛውም ጠብቁትና ይዛችሁት ትሄዳላችሁ ” ብሏቸው ሔደ ።
የዮናታን ልብ ተረጋጋ ። ሥጋታቸው የለየላቸው ዕብዶች መሐል ገብቶ አቤልም እንዳይለይለት ነበር ።

የአቤል ወደዚህ ሐኪም ቤት መምጣት የነገራቸው እስክንድር ነበር ። መልእክቱን እንደ ሰው ተደናግጠው ቢሮአቸውን እንኳ ሳይቆልፉ ነበር የወጡት ከእስክንድር
ጋር ሆነው በቦልስ መኪናቸው ሲከንፉ የትራፊክ መብራቶች ሕግ መጠበቃቸውን ይጠራጠራሉ ።

እስክንድር ራሱ ከጸቡ ቦታ የደረሰው ዘግይቶ ነበር።አቤል ወደ ሐኪም ቤት ከተወሰደ በኋላ ሳምሶን ጉልቤው
ሚስተር ሆርስን ካልገደልኩ ብሎ እየተጋበዘ አስቸግሮ ነበር እስክንድር ነው አባብሎ ያስታግሠው ። ሚስተር
ሆርስ የጸቡን መነሻና ሁኔታ ረጋ ብሎ ለእስክንድር አጫወተው ያልጠበቀው ትንሽ ነግር ይህን ያህል መጉላቱን
በተመለከተ ጊዜ ፥ ሚስተር ሆርስ ራሱ ተደናግጦ ነበር ።

ዮናታን የጸቡን ሁኔታ ከእስክንድር ሲሰው ነገሩ ከትግሥት ጋር የተያያዙ መሆኑን መገመት ብዙ ጊዜ አልመወሰደባቸዉም ። “ በት ! በላት ! ” የሚለው የአቤል የተደጋገመ ጩህት የቅርብ ሚስጢሩን ለሚያውቁት ሰው በቂ ማስረጃ ነበር ።

ዮናታን አሁን አቤል ሐኪም ቤት ውስጥ እንደማይተኛ ካረጋገጥን በኋላ ሌላው ጥድፊያቸው የጸቡን መረጃ ለቢልልኝ ለመስጠት ነበር ። ሥነ ልቡናው ጥናት የሚጠቅም ነገር እንዳገኙ በመገመት ተቻኩለዋል ።

« አሁን የፈተናውን ነገር አቤል እንዴት ቢያደርግ ይሻላል ? ” አላቸው እስክንድር ዮናታንን ሐኪሙ በር ላይ እንደ ቆሙ ። አቤልን ያመጡት የዩኒቨርስቲው ባልደረቦችም አብረዋቸው የሐኪሙ በር ላይ ቆመው ነበር ።

“ ፍቃዱ ቢሆን ባይፈተን ይሻላል ግን እንጃ ” እሉ ዮናታን ፥ የአቤልን ፈቃደኝነት በተጠራጠረ ስሜት ።

አቤል ከሦስት ቀን በኋላ ለመመለስ ከሐኪም ቀጠሮ ተቀብሎ ወጣ ። በሩ ላይ ዮናታንን ሲያያቸው የቆመበት
መሬት ቁልቁል ቢውጠው በወደደ ነበር ፡ ቢሮአቸው ጠርተሎ ካነጋግሩት ወዲህ ሲገናኙ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው ። ዐይኑን ሰብሮ መሬት መሬቱን ይመልከት ጀመር ።

አሁን እንዴት ነው ? ” አሉት ዮናታንና እስክንድር በዜማና በብሩህ ድምፅ ።

“ደህና ነኝ የእንቅልፍ ኪኒንም ተሰጥቶኛል አላቸው አቤል አንገቱን እንደሰበረ ።

መደናገጡን ስለ ተመለከቱ ሁሉም ብዙ
እንዳያናግሩት ተቆጠቡ ። የማኅበራዊ ሥራ ባልደረባቸውና የዩኒቨርስቲው
ሹፌር ቀድመው እንዲሔዱ ዮናታን ነገሯቸው አቤል ከእሳቸው ገር ለመሄድ ወደ ውጪው በር አመራ።

አቤልን መሃል አድርገው ዮናታንና እስክንድር የውጭውን በር እንዳለፉ ዕርቃነ ሥጋውን የተቀመጠ አንድ ለማኝ አጋጠማቸው

አይታችሁ አትለፉኝ ፡ ዓለሞቼ ! ”

ዮናታን ዐይናቸውን ጨፍነው አስር ሳንቲም ጣሉለት። የተጎዳ ኃፍረተ ሥጋውን አጋልጦ ነበር የሚለምነው ብልቱ አብጦ ትልቅ ኳስ አክሏል።

አቤልን ለማኙን አትኩሮ ሲመለከተው አንድ ነገር ስሜቱን ጠቅ አድርጎ ወጋው መኪናው ውስጥ ገብተው ሲንቀሳቀሱም ሐሳቡ ከለማኙ ጋር ቀርቶ ነበር ።

“ ለካ አጸያፊውን የውስጥ ማንነታችንን ደብቀን የምንይዘው ገንዘብ ሲኖረን ብቻ ነው አለ በሐሳቡ የተጎዳ አፍረተስጋ እየታየው ሚስጢር የሚሸፍነው በገንዘብ ነው።ድህነት ሚስጢራችንንም ሆነ አፀያፊ ማንነታችንን አጋልጦ ያወጣዋል። ገንዘብ ባለን ጊዜ ሀፍረተ ስጋን ቀርቶ የጣት ቁስላችንን ለመደበቅ ነው የምንጥረው። ድህነት ሲመጣ ግን መደበቁ ቀርቶ በይፋ መለመኛ ይሆናል። ከሰው በኋላ ተፈጥረው የሰውን ውስጣዊ መንፈስ
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


እቅዳቸው በአሳዛኝ ሁኔታ መክሸፉን፤ መክሸፍ ብቻም ሳይሆን የሷና የሻምበል ብሩክ ፍቅር እስከ ወዲያኛው ዳግም ላይጠገን እንክትክት ብሎ መሰባበሩን ስትሰማ አዜብ ክፉኛ ደነገጠች፡፡ ምን
የማይሆን ምክር መክሬ ጉድ ያደረኳት፤ በሚል ጸጸት ተቃጠለች፡፡ ለዚህ
ችግር መንስኤው እሷ እንደሆነች
ሁሉ “እኔ ነኝ ጉድ ያደረኩሽ ትሁትዬ፡፡ እኔ ነኝ ጥፋተኛዋ፡፡ ድሮውንም ቢሆን አንቺ አይሆንም ብላሽ ነበር። አጉል የማይሆን ምክር መክሬ እዚህ ጣጣ ውስጥ የከተትኩሽ እኔ ነኝ፡፡በደሉ የኔ ነው፡፡ ወይኔ ጓደኛዬ... እዬዬ እያለች አብራት
ስታለቅስ ዋለች፡፡

እየዋለ እያደረ ግን ለትህትና ህይወት መበላሽት ዋናው ምክንያት እሷ ያለመሆንዋን፤ ትህትና ለተደጋጋሚ ፈተና የተጋለጠችው በሷ ምክንያት ሳይሆን በሌላ ሰው ጦስ መሆኑን፤እያመነች መጣች፡፡የወንጀል ድርጊቱ እንደተፈፀመባት ወዲያውኑ ህጋዊ እርምጃ ማስወሰድ ሲችሉ፤ እንደሻው የአዜብ ወላጆች የክርስትና ልጅ ነው፤ አባቱም ለትህትና ባለውለታ ናቸው፤ በሚል ሰበብ ጉዳዩን አዳፍነው፤ አለባብሰው ማለፋቸው ተገቢ ያለመሆኑ እየተገለጠላት መጣ፡፡ በዚያን ሰአት በደም ተጨማልቃ የጠበቀቻት ትህትና ታየቻት፡፡ ከዚያም ከዶክተር ባይከዳኝና
አሁን ደግሞ ከሻምበል ብሩክ ጋር ለነበራት ግንኙነት ዋናው የጸቡ
መንስኤ የእንደሻው ጦስ መሆኑ ያለጥርጥር ታወቃት፡፡ እንደሻው በሰላም
እንቅልፉን ይለጥጣል፡፡ ትህትና ግን በየቀኑ ታነባለች፡፡ በዚህ ላይ አንድም
ቀን እንኳን የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶት ይቅርታ ጠይቆ አያውቅም፡፡ስለዚህ የእጁን ማግኘት አለበት ብላ ወሰነች፡፡ በእንደሻው ምክንያት ትህትና ክብረ ንጽህናዋን፣ ሥራዋን፤ እጮኛዋን፤ አጥታለች። ግዴለም! ስትል በልቧ ዛተች፡፡

አንዱ አለም በሁኔታው ግራ ተጋብቶ.. “እታለም ሥራውን ተውሽው እንዴ?” ብሎ የጠየቃት እለት “ትንሽ ዕረፍት ወስጄ ነው
አልተውኩትም” ብላ ዋሽታው ነበር፡፡ በኋላ ግን በውሸቷ መቀጠል አልቻለችም፡፡ ሥራው ያልተስማማት በመሆኑ ያቋረጠችው መሆኑን
ገለፀችለት፡፡
“አይዞሽ ቆንጆ የቢሮ ሥራ ነው የምትይዥው፡፡ የምን ጫማ
መሸጥ ነው”? ሲል ሞራል ሰጣት፡፡
ከሥራው የበለጠ እንዱዓለምን ያሳሰበው እህቱ ይሄንን ሰሞን ሙሉ ለሙሉ መለወጧን፣ በሆነ ባልሆነ ማልቀስ ማብዛቷን፣ ሲጠሯት ቶሎ ያለመስማቷን፣ ፍዝዝ ማለቷን፣ እህል እምብዛም ያለመድፈሯን፣ እንዳትሞት ያህል ብቻ አፏ ላይ ጣል , አድርጋ በቃኝ ማለትን
ማዘውተሯን፣ ሰውነቷ እየጠወለገ መሄዱን፣ በአጠቃላይ ሻምበል ብሩክን
ካገኘች በኋላ ደስተኛ መሆን የጀመረችው ልጅ ሰሞኑን በሚገርም ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ተለውጣ በማስተዋሉ ነው፡፡

በዚህ ላይ ደግሞ እንደታላቅ ወንድሙ የሚያየው “አንዱዓለም እስቲ እንካ ይህችን ለደብተር መግዣ፣ ለፀጉርህ መስተካከያ አይዞህ በርትተህ ተማር” እያለ የሚንከባከበው የእህቱ እኛ የሻምበል ብሩክ ድምፁ እየጠፋ ነው፡፡ ነገሩ አሳሰበው፡፡ አጠራጠረው፡፡
ይሄ ሁኔታ ከሳምንት በላይ አስቆጠረ፡፡ አንዱዓለም ጥርጣሬው እየጨመረ መጣ፡፡ እህቱ ምንም ነገር ልትነግረው ፈቃደኛ አልሆነችም፡፡ መላው ቢጠፋው አዜብን ሊያማክራት ፈለገ፡፡
አዜብ አንጀቷ እየተቃጠለ፤ የዚህ ሁሉ በደል ምንጭ የሆነው እንደሻው የሚቀጣበት መንገድ ጨንቋት ውስጥ ውስጡን በንዴት ስትንጨረጨር ነው የከረመችው፡፡
አንዱዓለም ስለእህቱ ሁኔታ ሲጠይቃት፤ ተደስታ አንድም ሳታስቀር እንደሻው የፈፀመባትን ወንጀል ዘከዘከችለት፡፡ በእህቱ ላይ የተፈፀመውን ወንጀል ሲሰማ አንዱአለም በንዴት ተንዘፈዘፈ። ከዚያም
በላይ እንደ እብድ አድርጎት ነበር፡፡ ከዚያም ያንን ግፈኛ ሊበቀለው
የሚገኝበትን ቦታ ጠየቃት፡፡
አዜብ አላመነታችም፡፡ “አሳይሀለሁ” አለችው፡፡ ለዚሁ ጉዳይ ተቀጣጠሩና፤ እንደሻው የሚገኝበትን ሱቅ ልታሳየው ይዛው ሄደች፡፡
ትህትና ይህንን ሁሉ አታውቅም፡፡ ወንድሟ ከሰው ጋር ተጣልቶ አደጋ እንዳይደርስበት ስለምትሰጋ፤ በፍፁም እንዳይሰማ አዜብን አደራ ብላት ነበር፡፡ አዜብ ግን እሺ አልነግረውም ብትላትም፤ እሱ ቀድሞ ባይጠይቃት ኖሮ ቀድማ ልትነግረው ተዘጋጅታ ነበር፡፡
በሷ እምነት እንደሻው ለፈፀመው ግፍ ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡ ለወንጀሉ በቂ ቅጣቱን ማግኘት አለበት፡፡ አለበለዚያም በአፏ አላወጣችውም እንጂ ፤ በሱ ምክንያት ከባድ ችግር ላይ የወደቀች ልጅ
በመሆኗና ክብረ ንጽህናዋን የደፈረው እሱ በመሆኑ ወደደም ጠላም
ሊያገባት ይገባል ነው እምነቷ፡፡
የዚያን ዕለት አንዱዓለም እንቅልፍ በዐይኑ ሳይዞርለት ነጋ:: አንጅቱ እያረረ አደረና፤ በማግስቱ ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሲሆን ብቻውን ወደዚያ ሱቅ ሄደ፡፡
ከሱቁ ሲደርስ እንደሻው ሲጃራውን እያቦነነ አገኘው፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ሲጃራውን ምጉ ቁራጩን በእግሩ ደፈጠጠና የመጣለትን ቁርስ ሊበላ
ሻይ በመቅዳት ላይ እንዳለ፤ ዐይኖቹ እንደ በርበሬ ቀልተው፤ ፊቱ ሳምባ እንደመሰለ፤ በንዴት መላ ሰውነቱ የሚንቀጠቀጥ ወጣት በሩ ላይ ገጭ አለበት፡፡
አንዱአለም የሰራ አካላቱን እንደ ኤሌክትሪክ የሚነዝር የጥላቻ
ስሜት ወሮት ተንደርድሮ ሄደና ያንን የሻይ ማንቆርቆሪያ አንስቶ ፊቱ ላይ ቸለሰበት፡፡ እንደሻው በዚያ ትኩሳ ሻይ ተቀቀለ፡፡ በድንጋጤ ከባንኮኒው ላይ ዘሎ ወጣና ግብ ግብ ተያያዙ፡፡

አንዱዓለም በእህልና፤ በቁጭት፤ ሰይጣናዊ ጉልበት ተላብሷል፡፡
እንደሻው ግን በብርክ ስለተዋጠ ሊቋቋመው አልቻለም፡፡ እየደጋገመ ፊቱን
እንደተርብ ጠዘጠዘው፡፡ ከዚያም ትንሽ በትንሹ ከድንጋጤው ተመልሶ
አንዱዓለምን ሊያንቀው ሲዘጋጅ ጐረቤትም መንገደኛም መሀል ገባና
ገላገላቸው፡፡
አንዱዓለም እየጮኸ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ይሳደብ ጀመር፡፡
“አንተ የውሻ ልጅ!! በዚህ ብቻ የምለቅህ እንዳይመስልህ...!”
አለው፡፡ እንደሻው እየተርበተበተና በድንጋጤ ዐይኖቹ እንደተበለጠው
ይህንን ሰይጣን ማን ላከብኝ በሚል ስሜት ግራ ተጋብቶ ይመለከተዋል፡፡
አበራ በሃሣቡ ድቅን አለ፡፡ “በቃ አበራ የላከው ሰው መሆን አለበት” አለ በልቡ፡፡

መቼም አንዳንድ ግዜ ፍቅር እንደ አጀማመሩ አያልቅም፡፡
በተለይ በጥቅም ላይ የተመሰረተ ፍቅር ዕድሜው አጭር ነው፡፡ ከአበራ ጋር ንግዱን የጀመሩ ሰሞን ፍቅራቸው ሌላ ነበር። እየዋለ እያደር ሱቃቸው ሲደረጅ፣ ጠቀም ያለ ገንዘብ መምጣት ሲጀምር፣ እንደሻው ተስገበገበና፤ ሞቅ ባለው የሽርክና ፍቅራቸው ላይ ቀዝቃዛ
ውሃ ቸለሰበት፡፡
የዚያን ዕለት አበራን የተናገረው ንግግር ትዝ አለው፡፡ “አበራ እስከዛሬ ድረስ የወሰድከው ሳይታሰብ፤ ያዋጣኸውን ገንዘብ በጥሬው እመልስልሃለሁ፡፡ ግድ የለም እኔ ልጐዳ” በማለት ነበር በድንጋጤ ያስበረገገው፡፡
“እና ሱቁን የግልህ ብቻ ልታደርገው?” አበራ በንዴት እየተንቀጠቀጠ፡፡
“የንግድ ፈቃዱ የግሌ መሰለኝ፡፡እዚህ የምፍጨረጨረውም በግሌ
አንተም ከዚህ በላይ ልትጐዳኝ የምትፈልግ መሆኑን እያየኽው
አይመስለኝም” ቁርጡን ነገረው፡፡
“እሺ እንደሻው እግዚአብሔር ለሁላችንም የሥራችንን ይስጠን፡፡ አንተ ግን ሰው አይደለህም! እባብ ነህ! ያንተ ነገር በቃኝ!ሥጋዬም አይደለህ፡፡ በቃኝ! በቃኝ!” እያለ እየተማረረ እየተንቀጠቀጠ
ከሱቁ ወጥቶ የሄደው ትዝ አለው፡፡ በዚሁ ሀሳብ መሀል ግን...
የትህትና ወንድም መሆኔን እወቅ!” ለሠራኸው ሥራ በዚህ ብቻ የምንላቀቅ እንዳይመስልህ! እስከመጨረሻው እፋረድሃለሁ!!” በማለት ፎከረበት፡፡

በዚህ ጊዜ እንደሻው አመዱ ቡን አለ፡፡ እሱ እንደሆነ ትህትናን ከነመፈጠሯ ነበር የረሳት፡፡ አሁን ግን ጉድ ሊፈላ ነው፡፡ የሚበቀል ወንድም አላት ለካ !!
👍3
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


.....ናትናኤል ጊዜ ሳያጠፋ ታክሲ ተሣፍሮ ወደ ለገሃር ሄደ፡፡ ደጋግሞ ደውሎ ነበር ስልኩ የተነሳለት፡፡ቀደም ብሎ የመሥሪያ ቤቷ ጓደኛዋ ምህረትጋ ደወሎ ርብቃን አቅርቢልኝ ሲላት: እሁንም ወደ ስራ
ገበታዋ አለመመሰሏን ስትነግረው አለቅጥ ተጨነቀ፤ከራሱ ጋር ክርክር
ገጠመ፡፡ እንደታመመችና ቤቷ ደውሎ ከቻለም ሄዶ ቢያያት እንደሚሻል
ምህረት ስትነግረው መንፈሱ ሸፈተበት፡፡ ልቡ ላይ እንደጦር የተሸነቀረበት
ግን ሌላ ነበር

“በጣም አሟታል እንዴ?” አላት ምህረትን ቅንድቦቹን አጠጋግቶ፡፡ “ምንድነው በሽታዋ ማለቴ…”
“እንዴት ነው ነገሩ..ኣላወቅህም ማለት ነው? ወይስ…ናትናኤል ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች፡፡”
ድንገት እንደመሽ ሁሉ ጭልምልም አለበት ፤ ጭንቅላቱ እንደ ድንጋይ ከበደው፤ ማጅራቱን ጨምድዶ ያዘው፡፡ አንድ ቃል ብቻ ይደጋግም ጀመር “ፈጣሪዬ! . ፈጣሪዬ! ፈጣሪዬ! ስልኩን ከዘጋ በኋላ በቆመበት ተገትሮ ቀረ፡፡ እንደህፃን ልጅ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ፈለገ፡፡ “ርብቃ ... ርብቃ!” ራሱን መቆጣጠር ተሳነው “ገደል ይግባ!” ሁሉ ነገር ገደል ይግባ!” የሚንቀጠቀጥ እጁን ኪሱ ከቶ ከአንድ ቡና ቤት ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ለሰዓታት ከራሱ ጋር ተወራጨ፡፡ በመጨረሻ ከቡና ቤቱ ወጥቶ የህዝብ ስልክ ይፈልግ ጀመር፡፡

ስልኩ ቢጠራም የሚያነሳው ሰው አልነበረም፡፡ በሚንቀጠቀጥ ቀኝ
እጁ የስልኩን እጀታ ጨምድዶ ይዞ ተጠባበቀ:: ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች ስልኩ
ይጠራል፤ የማያነሳ የለም፡፡ ቀጥታ እቤቷ ድረስ ብሄድስ? አሰበ፡፡ መሄድ የለብኝም:: እሷንም ቢሆን ለባሱ አደጋ ማጋለጥ ነው የሚሆነው፡፡ ደጋግሞ ደውሎ ነበር ስልኩ የተነሳለት

“ሀሎ” አለ ስልኩ እንደተነሳ ቀድሞ፡፡ ድምፅ ተጠባበቀ፡፡ ግን ምንም
አልነበረም:: መልሶ “ሃሎ አለ የሚንቀጠቀጥ ድምፁን ማረጋጋት
እየታገለ፡፡

“ናቲ..ናናቲ” ድምጿን ከመቅጽፅት ለየው፡፡ ቢሆንም በጣም የደከመ ድምጽ ነበር፡፡
“ርብቃ! ደህና ነሽ…?”
“ናቲ...ናቲ አቃጠሉኝ..ና…” .
“ናትናኤል ነኝ ርብቃ… ጮክ በይ አይሰማኝም፡: ርብቃ መሥሪያ
ቤትሽ ደውዬ ነበር፡፡ ርብቃ… እ?… አይሰማም፡፡” ድምጿ እየደከመበት ሄደ፡፡
ሌላ ሰው ስልኩን እንደተቀበላት ተረዳ፡፡
“ሀሎ፡፡” አለ ለስለስ ያለ የወንድ ድምፅ፡፡
“ሃሎ.… እባኮት ርብቃን ነበር፡፡”
“ማን ልበል? ” .
“ሀሎ..እባኮት ርብቃን ያቅርቡልኝ::” ናትናኤል ረጋ ብሎ ጠየቀ፡፡
“ይቅርታ፡፡ትንሽ አሟታል፡፡ በስልክ መቅረብ አትችልም::
የምነግርልዎት መልዕክት ካለ.….”
"እሷኑ ለማነጋገር ስለምፈልግ ነበር፡፡” ናትናኤል ጠንከር አለ፡፡
“ይቅርታ… ስትነጋገር ስለሚደክማት ነው፡፡ መልዕክት ካሎት ልንገርሎት፡፡ ታናሽ ወንድሟ ነኝ ብስራት ነኝ፡፡”
ናትናኤል ለማስታወስ ሞከረ፡፡ ቤተሰቦቿን ብዙም አልቀረባቸውም፤ ቢሆንም ከብስራት ጋር ከአንድ ሁለት ሦስት ጊዜ ተገናኝተዋል፡፡ ብስራት ገና ሃያ ዓመት ያልሞላው ወጣት ወንድሟ ነው::

“እንደምንዋልክ ብስራት፡፡ ናትናኤል ነኝ፤
ታስታውሰኛለህ? የርብቃ..እ… ”

“እዎ እዎ አስታውስሃለሁ፡፡ እንደምንድነህ? ደህና ነህ? ምነው
ጠፋህ? ርብቃ በጣም አስባለች፡፡ ለምን ብቅ አትልም? ”

“እ..” ናትናኤል አመነታ፡፡ “ምን መሰለህ ብስራት መምጣት እንኳን አልችልም፡፡ ግን እሷ እንዴት ነች?”

“አሟታል…በጣም ነው የታመመችው ሐኪም ቤት እያመላለስናት ነው::”

“ምን አሉ ሐኪሞቹ? ማለቴ ምንድነው?” ናትናኤል በልቡ የሚንቀዋለለውን ለመጠየቅ ጭንቅ አለው::

“አላወቁላትም፡፡ ግን ምግብ አይበላላትም፤ ስትበላም አይረጋላትም፡፡
ሰውነቷ ላይ ግን ችግር የለባትም፡፡ 'ጭንቀት ነው' ነው የሚሉት ሐኪሞች፡፡
ምን እንደሚያስጨንቃት ግን ሊገባን ኣልቻለም፡፡ በጣም ደክማለች::
ናትናኤል መጥተህ ብታያት ጥሩ ነበር:: በእንቅልፍ ልቧ ሁሉ ስምህን
ትጠራላች፤ ከቀን ወደቀን እየባሰባት ነው፡፡” ናትናኤል በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ እጁን ግንባሩ ላይ ጫነ፡፡ ከራሱ ጋር ክርክር ገጠመ:: የፈለገው ይምጣ ሄዶ ያያታል፡፡ መቼም በቤቷ አካባቢ ሊያንዣብቡ ይችሉ ይሆናል፡፡ ግን ምርጫ የለውም:: ሹልክ ብሎ ገብቶ ሹልክ ብሎ ይወጣል ወሰነ::

“ብስራት መደወሌን ለማንም አትናገር ዛሬ ማታ መጥቼ አያታለሁ እሺ? ልክ ከምሽቱ አስራ ሁለት ተኩል ሲሆን ውጭ በሩጋ ጠብቀኝ” ናትናኤል ስልኩን ከዘጋ በኋላ በግራው ያንጠለጠለውን ትንሽ የሽራ
ሻንጣ ይዞ እዚያው ለገሃር ኣቅራቢያ ወዳለ አነስተኛ ቡና ቤት ተመልሶ ገባ፡፡
ጥግ ወዳለ ወንበር ሄዶ ሰውነቱን ለማርገብ፣ ለማረጋጋት በዝምታ
ተቀመጠ፡፡ በግራሶና ዘይት የተጨማለቀ ሰማያዊ ቱታ ለብሷል። ጭንቅላቱ
ላይ ያጠለቀው ዙሪያው እንደጠወለገ ቅጠል የተልፈሰፈሰው ባርኔጣ በግንባሩ
ላይ ኣዝምሞ ፊቱን ሸፍኖታል፡፡ ከደረት ኪሱ ሲጋራ አውጥቶ ከሚንቀጠቀጥ እጁ ጋር እየታገለ ከለኮሳት በኋላ ክብሪቱን እያጠፋ ሲጋራዋን ምጥጥ አደረጋት፡: “ርብቃ... ርብቃ.… ምነው አጠገብሽ መሆን ብችል!”

“ምን ልታዘዝ::” አለችው ሰማያዊ ሽርጥ ወገቧ ላይ ሸብ ያደረጎች አስተናጋጅ የለበሰውን ቆሻሻ ቱታ ስታይ ድምጿን ቆጥብን አድርጋ::

“ቡና፡፡” አላት ቀና ብሎ አያቷት የዋጠውን የሲጋራ ጭስ ቀረጁሙ እየለቀቀ፡፡

“ሂሣብ በቅድሚያ ነው የሚከፈለው፡፡” አለች ሁለት እጆቿን በጎንና ጎን የሽርጥ ክሶች ውስጥ እየወሸቀች፡፡

ከቀኝ ኪሱ ውስጥ ሣንቲሞች አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ በተን እደረገላት፡፡ ሃሳቡ ግን ሌላ ቦታ ነበር፡፡ ርብቃ ለምን ደበቀችው? «ወይስ ወሯ ገና ነው ማለት ነው ሊሆን አይችልም:: ደብቃው ነው፡፡ ግን ለምን.… ለምን?

የሚወደው ገጿ መጥቶ ፊቱ ላይ ድቅን አለበት፡፡ ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች የምህረት ድምፅ እቃጨለበት፤ አሟታል ምግብ አይበላላትም ብትበላም አይረጋላትም “ጭንቀት ነው" ነው የሚሉት ሐኪሞቹ….
የብስራት ድምፅ ደወለበት...

“አምላከኔ ምን ዓይነት ጉድ ወስጥ ነው የከተትከኝ ኣለ እምላከ ከፊት ለፊቱ ባለ ወንበር ላይ የተቀመጠ ይመስል ፊት ለፊት አፍጥጦ፡፡

ምንድነው ሊያደርግ የሚችለው? ቀጥ ብሎ ፖሊስጋ ሄዶ እጁን መስጠት፡፡ ቢገሉትስ? ይግደሉት፡፡ ከዚህ በላይ ስቃይ መሸከም አይችልም ግን ለፖሊሶችስ ምን ሆንኩ ብሎ እጁን ይሰጣል? ሁሉን ነዋ!.. የሆነውን
ሁሉ ዘርዝሮ ማውጣት ነዋ! ግን ማን ያዳምጠዋል? ማን ያምነዋል? ፍጹም!
ፖሊስ ወጥመድ ነው! እጁን መስጠት ማለት ሞቱን ማፋጠን ማለት ነው፡፡
ለማን ይበጃል መሞቱ? ለርብቃ? ስልጁ? የአብርሃም መሞት ማንን ጠቀመ?
መረጋጋት ነው ያለበት፡፡ ካሁን ወዲያ ወደኋላ ማለት አይችልም፤ መረጋጋት
ነው ያለበት፡፡

ከቁጥጥር ውጭ በሚንቀጠቀጥ ቀኝ እጁ የያዛትን ያለቀች ሲጋራ ለመጨረሻ ጊዜ መጠጣትና ከፊት ለፊቱ ጠረጴዛ ላደ በተቀመጠው የሲጋራ መተርኮሻ ውስጥ ደፈጠጣት፡፡ መረጋጋት…. መረጋጋት ነው ያለበት...

የቡና ቤቱ አስተናጋጅ ያዘዛትን ቡና አምጥታ እፊቱ ደነቀረችለት::
አንስቶ ፉት ኣላው፡፡ ስኳር አልነበረውም:: ክፉኛ መረረው፡፡ ቢሆንም ስኳር
አልጠየቃትም፡፡ ድጋሚ ፉት ኣለው፡፡ ትኩስ ቡና በጉሮሮው አልፎ በሆዱ
ሲተራመስ ስንዝር በስንዝር ተከታትለው:: ሆዱ ጩርርርር ሲል ተሰማው:: ትላንት ምሳ የበላ ነው፡፡ ቢሆንም ምግብ አላሰኘውም:: ከቡናው ድጋሚ ፉት አለለት፡፡ ሰውነቱን ማዝናናት አለበት፤ ማረጋጋት አለበት፡፡በተቀመጠበት ወንበር ላይ በደኋላ ጋለል ብሎ ዓያኖቹን ጨፈናቸው፡፡ ቀኝ እጁ ከደረት ኪሱ ገብቶ ሲጋራና ክብሪት ይዞ ተመለሰ፡፡ ርብቃ ለምን ደበቀችው? በቃ በቃ... ስለርብቃ
👍2
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


...“ሃ ሃ ሃ! ሉዊስ! አዎ! አዎ!”

ብላ በሲቃ የምታቃስተውን ሴት ሉዊስ ሮድሪጌዝ ዓይኑን ጨፍኖ የምታወጣውን የተጋነነ የሲቃ ድምፅን እየሰማ ነው፡፡ ለምንድነው ሴቶች ግን እንደዚህ የሚያደርጉት? እየሸወዱት እንደሆነ የማያውቅ ሞኝ አድርገው ይገምቱታል እንዴ? ወይስ ደግሞ ስለ እነርሱ ወሲባዊ እርካታ እሱ ደንታ ያለው ይመስላቸዋል?

ባአሁኗ ሚስቱ እና ከሌሎቹ ከፈታቸው ሚስቶቹ ጋር ሲፈጽመው ግን የተለየ እንዲሆን ያስባል፡፡ ከሚስቱ ጋር ከሆነ እውነተኛ ፍቅርን መሥራት እንደሆነ ያምናል፡፡ ሚስቱ ትታው ከሄደች በኋላ አልጋውን የወረሩት ከእነዚህ እድሜያቸው ሃያ ምናምን የሆኑ ሞዴሎችና ተዋናይ ሸርሙጦች ግን ፍቅርን ፈልገው ሳይሆን የሚወስቡት ሀብቱን ለመቀራመት እና
ዕድላቸውን ለመሞከር አይደል? እነዚህ ሴቶችን ሮድሪጌዝ የሚፈልጋቸው
ለራሱ እርካታ ብቻ ነው በቃ፡፡ እነዚህ ሴቶች ቢኖሩም፣ ቢሞቱም ደንታ
የለውም፡፡

“ግርር... አአአሀ!” እያለ ጥርሱን ገጥሞ እያቃሰተ ከስሩ የሚወስባትን አናቤላ የተባለችውን ቆንጆ እየተመለከተ በፍጥነት ይወስባት ጀመር፡፡ ወጣቷን የሚወስባት ቢሮው ውስጥ ከሚገኝ ሶፋ ላይ ነው፡፡ ወደፊትና ወደኋላ እየተንቀሳቀሰ ሲወስባትም ወጣቷ ሴት እንቅስቃሴውን እየተከተለች በዮ ጋ የሰለጠነውን ሰውነቷን አብራው ትለምጥ ጀመር፡፡

“በእግዚአብሔር! በጣም ጣፋጭ ነህ ውዴ!” አለችው እና ፓንቷን እና
ቀሚሷን ዝቅ አድርጋ በመራመድ ልታማልለው ሞከረች፡፡ እሱ ግን ወደ
ሥራው በመመለስ፣ ላፕቶፑን ከፍቶ አትኩሮቱን ወደላፕቶፑ መለሰ፡፡
ከሰዓት ላይ ከዊሊ ባደን ጋር ተደራድሮ የሚጨርሰው አንድ ጉዳይ አለው፡፡
በመቀጠልም ከሌላ አንድ ጠቃሚ ሰው ጋር በሥራ ጉዳይ ያወራና በግል አውሮፕላኑ በመሳፈር ወደ ሎስ አንጀለስ ያመራል፡፡

ከዊሊ ባደን ጋር የነበረው ድርድር እንዳሰበው በጥሩ ሁኔታ ሳይሆን
እንደተወሳሰበ ነው ያለቀው፡፡ ዊሊን ያስተዋወቀቸው ባለቤቱ ቫለንቲና ናት፡፡
ቫለንቲና ተወልዳ ያደገችው እዚሁ ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ ከመሆኑም በላይ
በተለያዩ የበጎ አድራጎት ዝግጅቶች ላይ ለብዙ ጊዚያት ተገናኝተዋል፡፡ በዚያ
ላይ ደግሞ ሁለቱም እህቶቻቸው በመጥፋታቸውና በተመሳሳይ በቫለንቲና
እህት እድሜ ላይ ትገኝ የነበረችው እህቱ ካርለትም በአደንዛዥ ዕፅ ምክንያት
ስለሞተችበት ስሜታቸውን የሚረዳዱ ይመስላሉ፡፡

ባለቤቷ ዊሊ ግን በጣም ተስገብግቦ የቢዝነስ ድርድራቸውን እያበላሸበት
ይገኛል፡፡ ዊሊ በጣም ድርቅ ብሎ የእሱን ጥቅም ብቻ በሚያስጠብቅ መልኩ
መደራደሩን ደግሞ ሉዊስ አልወደደለትም፡፡ እሱ ምንም ያህል ለጋሽ እና ቸር ከመሆኑ የተነሳ የከተማው ድሆች አለኝታ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ጎዳና ላይ
ያደገ፣ እና የጎዳና ፀበኝነቱም ከእሱ ጋር እስከ አሁን ድረስ አብሮት እንደቆየ
ሰዎች ሊያውቁ ይገባል፡፡

ያም ቢሆን ግን ወደ ሎስ አንጀለስ በሚያደርገው ጉዞ ትንሽ ጨንቆታል።
የሎስ አንጀለስ ጎዳናዎች የዊሊ ባደን ናቸው፡፡ በእነዚህ ጎዳናዎች ላይ
የሚደረጉት ጦርነቶች ደግሞ ለየት እንደሚሉ ያውቃል፡፡

በዚህ ዓይነት ውጥረት ውስጥ ስለነበረም ነበር ቀለል እንዲለው በማሰብ ከአናቤላ ጋር ወሲብ የፈፀመው፡፡

ሁሉንም ነገሮች እንደሚመረምር እንደሚተነትነው ሁሉ አሁን
እየተሰማው ያለውን ፍርሃቱንም መመርመር ጀመረ፡፡ ከባደን ጋር ያደረገው
ድርድር አንደኛው ነው፡፡ ከብዙ ጊዜ በፊት ነው የአሜሪካንን መሬት የረገጠው፡፡ እንደሁልጊዜውም ሁሉ አሁንም የአሜሪካንን መሬት መርገጥ በራሱ ጭንቀትን ይጨምርበታል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ አሁን ላይ ዋሽንግተን ውስጥ ያለው የፖለቲካ ለውጥ ለእሱ ምቾትን የሚሰጠው ነገር አይደለም፡፡
አንድ እጅግ በጣም ሀብታም የሆነ ሜክሲኳዊ፣ በኤፍቢአይ በጎ መልኩ
የሚነሳ ሀብታም፣ በጣም ጥሩ ስምና ክብር ሲኖረውም በዚህ ሰዓት ላይ ወደ
አሜሪካ መምጣቱ ጥሩ አይደለም፡፡ የፈለግከውን ያህል ሚሊዮን ዶላሮችን
ለአደንዛዥ ዕፅ ሱስ ማገገሚያ የህክምና ማዕከሎች ብትለግስ ወይንም ደግሞ
ለሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች ልገሳን በመስጠት የሰብዓዊነት ግዴታህን
ብትወጣም ይኼ ለአሜሪካ መንግሥት ምንም ማለት ላይሆን ይችላል።
ሜክሲኮ ውስጥም ችግሩን መቅረፍ የምትችል ሰው ብትሆንም እንኳን
ምንም ለውጥ አታመጣም፡፡ በቃ አንድ ጊዜ የታወቅክ (የተጠቆርክ) ሰው
እስከሆንክ ድረስ አሜሪካኖቹ ይጠሉሃል!

ዲቃሎች!' አለ በውስጡ ሉዊስ፡፡ በቃ አሜሪካኖቹ ከእነርሱ የበለጠ የሌላ
ሀገር ስኬታማ በሆኑ ሰዎችም ላይ ይቀናሉም ይመቀኛሉም፡፡ ይኼ ሰው
እንዴት ሆኖ እዚህ ስኬት ላይ እንደደረሰ የት ያውቃሉ? ሮድሪጌዝ የቢዝነስ
ሰው ነው፡፡ ይኼ ደግሞ ቀላል እና ግልብ ጉዳይ ነው፡፡ እሱ እንደሚያስበው ከሆነ ደግሞ ብቸኛው ወንጀሉ ስኬታማነቴ ነው ይላል፡፡ ግማሹ የሜክሲኮ ሲቲ የእሱ ንብረት ነው፡፡ ሌላኛው ግማሹ ደግሞ የእሱ እንደሚሆን ያምናል፡፡ ከምንም ነው የተነሳው። አብዛኞቹ አሜሪካውያን ይኖራል ብለው ከማያስቡት ቁሻሻ ድህነት ውስጥ ወጥቶ ነው ለዚህ ስኬት የበቃው፡፡

“የተጨነቅህ ይመስላል ሆዴ! እስቲ ከዚህ ድብርት ላላቅህ” ብላ አናቤላ ከኋላው ቆማ ሰፊ የኮርማ ትከሻውን በረዣዥም ጣቶቿ ታሻሸው ጀመር፡፡

የተቀባችው ሽቶ እና ብልቷ ውስጥ የረጨው የወንድ ዘሩ ተቀላቅሎ
ሲሽተው ሮድሪጌዝ ይህቺን ሴት ከቢሮው ማባረር እንዳለበት ተሰማው፡፡

“መሄድ አለብሽ፡፡ የምሠራው ሥራ አለኝ” አላት፡፡

“እውነትህን ነው?” ብላ ጠይቃ ዓይኑ ውስጥ ያለውን መልስ ስታይም
“እሺ የኔ ቆንጆ፣ ስልኬ አለህ አይደል? በቃ ደውልልኝ በቅርቡ ደግሜ ላይህ
እፈልጋለሁ” ብላው ወገቧ ላይ ያረፈውን ረዥም ፀጉሯን ከቀጭን ዳሌዋ ጋር
እያወዛወዘች እና ሂል ጫማዋን እያንቋቋች ከቢሮው ወጣች፡፡ ሉዊስ ዞር
ብሎ እንኳን አላያትም፡፡ ሚስቱን ልክ እናቱን እንደናፈቀ ልጅ ነው በጣም
የናፈቃት። ይኸው እሷ ጥላው ከሄደች በኋላ ሁሉም ነገሮች እየተበላሹበት
ነው፡፡

አናቤላ ቢሮውን ለቅቃ እንደወጣች፣ ማሪሶል የተባለችው ፀሐፊው ታማኝ እና የማያምረውን ፊቷን በቢሮው በር አሾልካ “የኮሎምቢያ ልዑካን ደርሰዋል፡፡ ሚ/ር ሮድሪጌዝ ላስገባቸው ወይስ ለትንሽ ደቂቃዎች ያህል ብቻህን መሆን ትፈልጋለህ?” ብላ በትህትና ጠየቀችው፡፡
ሉዊስም ፈገግ አለላት። ፀሐፊው ማሪሶል ነገሮችን ጥንቅቅ አድርጋ ስለምትሠራለት ይወዳታል፡፡ ብዙ ብርም ይከፍላታል፡፡ ያም ቢሆን ግን ለእሱ ያላት ታማኝነት እሱ ከሚከፍላት ደሞዝ በላይ እንደሆነም ያውቃል፡፡

“ስማያዊው ክፍል እንዲጠብቁኝ አድርጊ፡ ሻይ ቡና እያልሻቸውም ከጥቂት ጊዜ በኋላም እንደማገኛቸው ንገሪልኝ” አላት፡፡
ሉዊስ የእጅ ሰዓቱን ተመለከተና ከአራት ሰዓት በኋላ አየር ማረፊያው መገኘት እንዳለበት እና ከሰባት ሰዓት በኋላ ደግሞ የሎስ አንጀለስ ከተማ ላይ እንደሚሆን አሰበ፡፡ ምንም ያህል ባያምንም ዛሬ ግን ሲጠብቀው/ሲናፍቀው የነበረው ቀኑ ነው፡፡

ለሉዊስ ሎስ አንጀለስ ማለት በራሱ አደጋ ማለት ነው፡፡ ወይም አደጋ ውስጥ የሚከተው ቦታ ማለት ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን ሎስ አንጀለስ ማለት በራሱ ሽልማት ወይም ለሽልማት የሚያዘጋጀውን ነገሮች የሚያገኝበት ቦታ ነው፡፡ ሽልማቱ በቢዝነስም፣ በግል ሕይወቱም ነው፡፡ “አሁን መሄድ አለብኝ፡፡ ሄጄም የእኔ የሆነውን ነገር መልሼ ማግኘት አለብኝ” አለ በውስጡ፡፡

ዓይኑን ከጨፈነና ስልኩን ከዘጋ በኋላ እናቱ የሰጠችውን መቁጠሪያ ከጃኬቱ የውስጥ ኪስ አውጥቶ ያዘው የማርያምን ምስጋና ሦስት ጊዜ ለእናቱ በድጋሚ ደግሞ
👍41
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል

....ወደ ወላጆቼ ቤት በሔድኩ ቁጥር መኪናዬን የማቆማት ከአካባቢው
እርቄ ነበር። በሩን እንዳንኳኳሁ ወዲያው ተከፍቶልኝ ገባሁ። በአሁኑ ጊዜ እኔና
ያ ቤት ማንና ምን መሆናችንን ዘበኛው አሳምረው አውቀውታል። ምድረ ግቢው ውስጥ ያሉት የኮክ ዛፎች፣ ኮባዎችና ሌሉቹም አትክልቶች ሁሉ የቀድሞ
ውበታቸውን የተጎናጸፉ መስለው ታዩኝ። እንድ ጊዜ ቆም ብዩ ዙሪያውን ካየሁ
በኋላ በቀጥታ ወደ ቤት ገባሁ። መመላለሱንና ወጣ ገባ ማለቱን አዘውትሬው ስለነበር ፍርሃትም ሆነ ኃፍረት አልተጠጉኝም፡፡ እሑድ እሑድ ባለነገር እንግዳ ስለማይበዛ ከአባቴ እጅ ያንዱ መልአክ መልክአ እንቶኔ አይታጣም፡፡ ግባ ስል የአባቴ ነጭ ጋቢ ቤቱን ተጨማሪ ውበት ሰጥቶታል። እናቴ የለበሰቻት ወሃ ሰማያዊ ጥለት ያላት ቀሚስ ከሩቅ ሲመለከቷት ጭጋግ የጋረደው ሰማይ ትመስላለች።

የውብነሽ በጊዜው ስለ እኔ በምታወራው ወሬ የወላጆቼ ሸካራ ስሜት ለስልሶ ውጥረቱ በመላሳቱ መሠረታዊ አስተሳሰባቸው ሳይሆን ተራ ዕለታዊ
አስተያየታቸው በመጠኑ ተለውጧል፡፡ ሁለቱም በፈገግታ ተቀበሉኝ፡፡ በሕሊናዩ
ውስጥ የለውጥ ጮራ ጨረረ፡፡ በአቀባበላቸው የተዝናናው ሕሊናዩ እጅ አነሣሰንና ሰላምታ አሰጣጤን አሳመረው:: መምጣቴን በድምፄ ያወቀችው የውብነሽ የቤት ውስጥ ቀላል ልብስ ለብሳ ከጐኔ ተቀመጠች፡፡ በውስጤ የተጠነሰሰውን ዓላማና እምነት አባቴ ፊት በዐይነ ሐሳብ አቀረብኩት። የእኔ ለጋ እምነትና የአባቴ
ግብዝ ሐሳብ ተፋጠጡ፡፡ የእኔዋ ሐሳብ በዳመራ ነበልባል ውስጥ ዘሎ ለማለፍ
እንደሚፈልግ ሰው ስትዘጋጅና የአባቴ ግትርነት በፈሪዎች መካከል እየተጎማለለ
እንደሚያሳግድ ጀግና ተኮፍሶ ታየኝ፡፡ እናቴ ፈቷን ፈታ አድርጋ ለስስ ባለ
የእናትነት ድምዕ «አረ ዛሬስ አምሮብሃል እሰየው! አባትህ እንዳለው ልብ ልትገዛ
ነው መሰል? እየተመላለስክ መጠየቁንም ሥራዬ ብለህ ይዘኸዋል፡፡ ታዲያ እንዲህ
እንዳማረብህና ሙሽራ እንደ መሰልክ ወደ ቤትህ ናና እንደ ዱሯችን ተቻችለን
አብረን እንኑር፡፡ ዕድሜ ላባትህ እንጂ ምን ጠፍቶ! ለወግ ለማረጉ ነው እንጂ
አንተም ራስህን ችለሃል። ከእንግዲህ ልጅነት የለም። እኛም እኮ እያደር...»
አለችና ንግግሯን ሳትደመድም የተገረፈ ልጅ እንደምታባብል እናት አቆላመጠችኝ

እባቴ ወለድ ለመቀበል እንዳሰፈሰፈ አራጭ ዐይን ዐይኔን እያየ መልክአ
ጊዮርጊሱን ወደ ጋቢው ውስጥ ሸጎጠና «የውብነሽማ የእኅትነቷንም እንደሆነ
አላውቅም፡፡ ነጋ ጠባ "አገኘሁት” ነጋ ጠባ እንዴት ናችሁ ብሏል፥ እንዲህ
አድርጎ፤ እንዲህ ፈጥሮ እያለች ጥሩ ጥሩህን ታወራለች እኔስ ጉቦ ሰጥተሃታል
ልበል?» አለና ያቺን በሐሰት ተጀቡና በጉቦ የምትፌጸም ነገር ሳይታወቀው
ተናግሮ ሣቀ። በእናቴ መሪነት የሚረባ የማይረባውን ስናወራ ጥቂት ደቂቃዎች
ከቆየን በኋላ አባቴ ያቺው የወንጀለኛ መቅጫ መጽሐፉ ትዝ ስላለችው ወደ
መኝታ ቤት ገባ። ግልግል አልኩ በውስጤ። ያጠራቀምኩትን ድፍረት ቀስ በቀስ ልጠቀምበት በመፈለጌ ከናቴ ጎን ተቀመጥኩ፡፡ በእኔና በእናቴ መካከል ያለው የፍቅር ገመድ በየወዲያኒሽ የተነሣ ተገዝግዞ ላላ እንጂ ፈጽሞ ባለመበጠሱ
እንደገና ለማጥበቅ አያዳግትም፡፡ እስኪ ዛሬ እንኳ እንዲህ ጠጋ ብለህ
አጫውተኝ' የእናት ወጉ ይድረሰኝ ብላ ባሸበሸበው ፊቷ ላይ ፈገግታ
ረጨችበት። ፊቷ በመጠኑ ሽብሽብ ከማለቱ በስተቀር ወዝና ሙላቱ ባለመቀነሱ መልኳ እንደ ወጣት ሴት ባይማርክም አዲስ ርጥብ ሥጋ ትመስላለች፡፡ አንገቷን ወደ ጎን ዘንበል አድርጋ ዐይን ዐይኔን እያየች እስኪ አፈር ስበላልህ ንገረኝ፡፡ ወዲያ ወዲህ ቢሉት ምንም መላ የለው፡፡ ከእኔ ከእናትህ የምትበልጥብህና አይዞህ አይሀ የምትልህን አግኝተህ እንደሆነም አትደብቀኝ፡፡ ኧረ መቼ ነው ጓዝህን
ጠቅልለህ የምትመጣው?» አለችና ከመጀመሪያው በበለጠ ትኩር ብላ ተመለከተችኝ፡፡

ከዚያች ከምወዳትና እንደ ነፍሴ ከምሳሳላት ከየወዲያነሽ ጋር ትዳር
ይዤ ንብረት መሥርቻለሁ። ምን የመሰለ ታይቶ የማይጠገብ ወንድ ልጅ ወልደናል። እሷንም በቅርብ ጊዜ ይዣት እመጣለሁ። አስታርቃችኋለሁ” ብዬ ልንገራትና ለእኔ አንድ ግልግል፣ ለእርሷ ደግሞ ያልታሰበ መርዶ በማርዳት
'ጉዷን ልየው ይሆን?” በማለት ገና ያልበሰለና ከገለባ የቀለለ ሐሳብ አሰብኩ፡፡ ላቀረበችው ጥያቄ መልስ የምትጠባበቀዋ እናቴ በግራ እጅ ጣቶቿ አፏን እየተመተመች «በል እንጂ ንገረኝ? ምነው ሰምተህ ዝም አልክ?» ብላ ጥያቄዋን ደገመች። የጠየቀችኝን ትቼ ያሳለችኝን ጀመርኩ፡፡

«ለጠየቅሽኝ ጥያቄ መልስ ከመስጠቴ በፊት አንድ ነገር ብለምንሽ እሺ
ትይኛለሽ ወይ? አዎን ካልሽ እና ከማልሽልኝ እኔም ለጥያቄዎችሽ ሁሉ ደስ
በሚያሰኝ ሁኔታ እመልስልሻለሁ» ብዪ አዲስ ነገር ደቀንኩ፡፡
የእመ ብርሃን ያለህ! ደግሞ የምን ማይልኝ አመጣህ? እኔ እናትህ
ባልምልልህስ እንዴት ብዬ እንቢ እልሃለሁ፡፡ ካንተ ከልጂ የምሰስተው ምን ነገር አለና ነው?» ብላ የመሳቢያ ሐሳቧን አቀረበች፡፡ የአንደበቷ መላላት መንፈሴን
ሽምጥ ለማስጋለብ ረዳኝ፡፡ «ኧረ ለመሆኑ እኔ የምለምንሽንና የምጠይቅሽን ሁሉ
ዐይንሽን ሳታሺ ትፈጽሚልኛለሽ ወይ? ብዬ አዝማሚያዋን ለማወቅ በየዋህ መሰል አቀራረብ ስሜቷን ለመረዳት ጓጓሁ፡፡

«ልጄ ሙት አልልህም! የምትለኝን ሁሉ ባስፈለህ ጊዜ አደርግልሃለሁ፡፡ አንተ ልብ ግዛልኝ እንጂ፣ አንተን መንፈስ ቅዱስ ይጠጋህ እንጂ ለምን ባጉቼስ
አይሆንም» አለችና የልብ ልብ ሰጠችኝ፡፡ «ለመሆኑ» ብዬ ስጀምር ያን ምንም
ያልነበረበትን የቀሚሷን ጫፍ ልክ አቧራ እንደ ነካው እስመስዬ አራገፍኩና
ይህን አድርጌያለሁ፣ ይህን ፈጽሜያለሁ፣ ይህን አጥፍቻለሁ፣ የተጣሉ ወይም
የተኳረፉ ሰዎች አምጥቼ ታረቁልኝ እላለሁና፣ ታረቂልኝ ብዬ ብጠይቅሽ እሺ
ትይኛለሽ ወይ?» አልኩና ዙሪያ ጥምጥም ሄድኩ፡፡

እኔ ልሙትልህ! የምትጠይቀኝን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፡፡አንተ ደግሞ
በበኩልህ አባት እናቴ ቤት ብለህ ተመለስልኝ፡፡ በስተርጅና ወግ ማዕረግ አሳየኝ» ብላ ገና በመቀጠል ላይ እንዳለች ፋታ ሳልሰጥ «ምንጊዜም ብለምንሽና የፈለግሁትን ይዤ ብቀርብ ሳትቀያሚና ሳታሳፍሪ ትቀበይኛለሽ ወይ? ብዬ ውስጥ ውስጡን ለመጪው ጥቅሜ አደባሁ፡፡

የውብነሽ ጣልቃ ገብታ ወሬያችንን ባለማጨናገፏ ተደሰትኩ፡፡

«ታማኙን ወዳጄን አቡዩና!» ብላ በእምነት ፈረሷ ላይ አፈናጠጠችኝ::
«እኔ በበኩሌ ከጥቂት ቀናት በኋላ አንድ በጣም ድንቅ የሆነ ነገር ኣምጥቼ
አሳይሻለሁ» አልኩና ወደ የውብነሽ መለስ አልኩ፡፡ ልብ ለልብ በመተዋወቃችን በዐይናችን ተሣሣቅን፡፡ «እሰየው ተመስገን! አቡዩ ያውቃሉ! ምንጊዜም ረዳቴና ሰሚዩ ናቸው» ብላ እጄን ስባ ሳመችው:: ኃይለኛ ንፋስ በሌለበት ሰማይ ላይ እንደምትንሳፈፍ የማለዳ አሞራ አእምሮዬ በደስታ ተንሳፈፈች። አዝመራው ካማረልኝ የተግባር እርሻዪን ጀምሬያለሁ። የውብነሽ የወሬያችን ተካፋይ ለመሆን በመፈለጓ «አሁንስ እኔንም አስጎመዣችሁኝ የአሁኑ ፍቅራችሁስ ያጓጓል። ምነው እኔ አንድ ነገር ስለምንሽ ዓመት ሙሉ ታስደገድጊኛለሽ?» አለችና ለእኔ
የተሰጠኝን የተስፋ ቃል ሆን ብላ አጋነነችው፡፡

«አንቺ ምን ቸገረሽ ልጀ? እኔ ለስንቱ ታቦት እንደ ተሳልኩ የት አየሽና? ተማጥኜ ተማጥኜ ነው አሁንም ቢሆን ለዚህ የበቃልኝ፡፡ አንቺ ደግሞ በእኔና በልጄ መኻል ምን ጥልቅ ኣደረገሽ? የሚጠይቀኝን ሁሉ አደርግለታለሁ»
ካለች በኋላ ከደረቷ ውስጥ የምታምር አረንጓዴ መሓረብ ኣውጥታ ምንም
ጉድፍ ያልነበረባትን አፍንጫዋን ጠረገቻት፡፡

ነገር አቃኝልኝ ያልኳት ይመስል
👍3👏2
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


...የሟቹ የገበየሁ ሚስት ዓለሚቱ አደራዋን በላች፡፡ ያውም የሙት አደራ...ገበየሁ በሞተበት ዕለት “ዓለምዬ የልጆቼን ነገር አደራ!.”ብሏት ነበር እሷ ግን አደራዋን አልተወጣችም፡፡ እሱ ከሞተ ዕለት ጀምሮ የህፃናቱ
ብሩህ ተስፋ አብሮት ሞቷል። አንጀቷ ወሩ ሲሞላ የማይወለድ ጭካኔና ግዴለሽነትን አርግዞ ዘጠኝ ወር ሙሉ በማህፀኗ ተሸክማ አምጣ ወልዳ
በሽንትና በቅዘን ተጨማልቃ ባሳደገቻቸው ልጆቿ ላይ ጭምር ደንታ ቢስ አንጀተ ደንዳና ሆነች፡፡

የጎንቻ የሚጣፍጥ ጠረን፣ የጌጣጌጥ ፍቅር፣ የወሲብ ፍቅር ልቧን ስለ ሰውና፣የሰው ሀሜት አማረራትና ስለራሷ ብቻ የምታሰብ የራሷን ኑሮ ብቻ መኖር የምትፈልግ ክፉ ሰው ሆነችባቸው፡፡ ዐይኖቻቸውን ክርትት ክርትት እያደረጉ “እማምዬ አባባስ?” እያሉ የሚወተውቱ ህፃናትን ነገ ይመጣል ዛሬ ይመጣል" እያለች ስትዋሻቸው እውነት እየመሰላቸው አባታቸውን ሲጠብቁ ዛሬም ነገም አባታቸው ሲቀር፣ ተስፋቸው ተሟጠጠች።

አባታቸው የሞተ እለት የነበረው ትርምስ ሚስጥሩ ቢገባቸው ኖሮ
ሁለተኛ ላይናፍቁት ሁለተኛ አባባስ? እያሉ ላይጠይቁ ቁርጣቸውን ባወቁት ነበር፡፡ ያንን ባለማወቃቸው የድሮዋ እናታቸው ትዝታና የሟቹ አባታቸው ናፍቆት ውስጣቸውን ክፉኛ ጎዳውና ቅስማቸው ተሰበረ። አባታቸውን የማግኘት ጉጉት ከእናታቸው እንክብካቤ መጥፋት ጋር ግንባር
ፈጥሮ ተረባረበባቸውና በናፍቆት ተሰቃዩ። እየዋለ እያደር አባታቸው ከሄደበት አገር ዳግም ላይመለስ ዳግም ላያቅፋቸው ጨክኖ መሄዱን በደመነፍስ እየተረዱ ሲመጡ አንገታቸውን መድፋት ጀመሩ። በመጨረሻ ላይ
ተለቃቅመው በአቅመ ደካማዋ አያታቸው ቤት ተወረወሩ። የአያታቸው ቤት ኑሮም አልተመቻቸውም ነበር፡፡ጭራሽ የአረቄ ጠጪው፣የሰራካሙ
ማላገጫ ነው የሆኑት፡፡ዓለሚቱ ደግሞ በተቃራኒው ጉድ እስከሚባል ድረስ አማረባት። በቀድሞ ውበቷ ላይ አዲስ ውበት ፈሰሰባት... በዚያ በገበየሁ ምክንያት እንዳታጌጥ እንዳታምር የእናቷ ሙዳይ ማሟሻ ሆኖ
የከረመውን ጌጣጌጥ በአይነት በአይነቱ ታወጣው ትለዋውጠው ጀመር እድሜ ለጎንቻ! ምን ጠፍቶ? አዲስ ለብሳ አምራ ደምቃ ታየች።
ጎንቻ በወርና በአስራ አምስት ቀን ሹልክ ብሎ ጨለማ ለብሶ ይመጣና ያጠራቀመውን ፍቅሩን ስጥቶ ፍቅሯን ተቀብሎ የዘረፈውን ንብረት ዘርግፎላት በለሊቱ ይሰወራል። የጉጉት እና የድብቅ ፍቅር ስለሆነ ነው መሰል ሁለቱም እስከሚንገበገቡ ነፍሳቸው ምንጥቅ ብላ እስከምትወጣ
ድረስ ተዋደዋል፡፡ ጎንቻ የዘረፈውን ንብረት ሙሉ ለሙሉ ተረካቢዋ እሷ
ሆናለች። በፈለጋት የፈለገችውን እንድታደርግ ሙሉ የሥልጣን ውክልና ሰጥቷታል፡፡ በዚያ በወንጀል የተለወሰ፣ በንፁሀን እንባ የበሰበስ ንብረት
እየተንደላቀቀችበት ነው፡፡ እሷ በተዋበች፣ እሷ እያማረባት በሄደ መጠን ልጆቹ ደግሞ በሞራልም በአካልም እየመነመኑና እየኮሰመኑ ሄዱ።ይህ ልዩነት ደግሞ ሀሜቱን ይበልጥ አባባስው፡፡ “ልጆቿን ጣለቻቸው በገበየሁ ድካም እሷ አነጠነጠችበት” ተባለች፡፡ ውስጥ ውስጡን ሲናፈስ የቆየው ሹክሹክታም በገሀድ መስማት ጀመረ። የሽፍታው የጎንቻ ውሽማ
መሆኗና ለመገደሉ ምክንያት መሆኗ በሰፊው ተወራ። ማሽላ እያረረ ይፈካል ሆነና ይህ የሰው ሀሜት ሲለበልባት ከውጭ እየፈካች ከውስጥ ማረር ጀመረች
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ገበየሁ ከሞተ ከአንድ ዓመት ሆነው።በዚህ በአንድ ዓመት ውስጥ አእምሮዋ እረፍት አላገኘም ነበርና ኢትያን ጥላ ልጆቹን ለእናቷ ወርውራ መጥፋት ፈለገች፡፡ ጎንቻ አብራው ጫካ እንድትኖር ያቀረበላትን ጥያቄ
አልተቀበለችውም፡፡ እሷ የምትፈልገው ጫካ ለጫካ መንከራተት ሳይሆን በሞቀ በደመቅ ከተማ ውስጥ እየተምነሸነሽች ደልቷት መኖርን ነው፡፡ምናባቱ ብር እንደሆነ እድሜ ለጎንቻ!! ኢተያን ለቃ ለመሄድ ስትፈልግ የጎንቻን ነገር ለሰከንድ የማትዘነጋው ጉዳይ ነውና “
እምቢ ይሄንን አካባቢ ለቅቄ የትም አልሄድም” ይላት ይሆን? ልቧ ትንሽ ቢጠራጠርም በፍፁም
እንደዚህ እንደማይላት እርግጠኛ ሆነች።እሷን ብሎ የትም ከመሄድ ወደ ኋላ እንደማይል በፍቅሩ ፅናትና ከአንደበቱ በሚወጡ የፍቅር ቃላት ብትተማመንም እርግጠኛ መሆን አልቻለችም። ተጠራጠረች። “ፍቅርሽ ፍቅር ሆኖ የሚታየኝ ተደብቄ እየመጣሁ ሰርቄ ስቀምስሽ ነው ቢለኝስ?የለም አይለኝም፡፡ በትኩስ ፍቅራችን አምላክ ከአንደበቱ እምቢ አይወጣም"ስትል ከራሷ ጋር ተሟገተች፡፡

ቁርጡን ከጎንቻ አፍ ለመስማት ስለተጣደፈች ከወትሮው የበለጠ የቆየ መሰላት። ሀሳቧን ገልፃለት ሀሳቡን ለማወቅ ስለቸኮለች በጣም ናፈቃት።ቀኑ በእጥፍ ጨመረባት፡፡ችኮላዋ ቀኑን አራዘመባት እንጂ ከወትሮው
ቀድሞ ነበር የመጣው ጀሌው ጊርቦን አስከትሎ በተለያዩ በአስራ አምስትስተኛ ቀናቸው ደግሞ በለሊቱ ከተፍ አለላት። ከምሽቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ቤቱን ቆረቆረ፡፡ በዚያ ውድቅት ጨለማ የሚመጣ ከእርሱ ሌላ ማንም የለም። ከምንጊዜውም በበለጠ በናፍቆት ተንሰፍስፋ አንገቱ ላይ
ተጠመጠመችበት። ጎንቻ ለሷ ያለው ፍቅር እጅግ የሚያስደንቅ ነው፡፡በሌላው ላይ የሚፈፅመውን ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል ሚዛን የሚያነሳለት ደግ ስራው ቢኖር በዚያው ልክ ለዓለሚቱ ያለው ከፍተኛ ፍቅር ነው፡፡ ዓለሚቱን ማፍቀሩ፣ዓለሚቱን መውደዱ ፣በዓለሚቱ ፍቅር
መቃጠሉ ሰው የመሆን መገለጫ ብቸኛ ምልክቱ ነበር፡፡ ዓላሚቱ እሱ
ይኑርላት እንጂ ከሰው በላይ ሆናለች፡፡ አበባ መስላለች፡፡ የሁለት ልጆች እናት መሆኗ ቀርቶ እንደገና ወደ ልጃገረድነት መልኳ ተመልሳለች፡፡ጎንቻ ውሎ ይግባ እሱን ክፉ አይንካው እንጂ ምን ችግር አለ? በፍቅር እሳት ነደው የአስራ አምስት ቀን ናፍቆታቸውን ለመወጣት ግማሹን የቀራቸውን ስድስት ስዓት እየተሻሙ በስርቆሽ ፍትወት ሰከሩ፡፡ እርካታቸውም የዚያኑ ያክል ወደር የማይገኝለት ጣፋጭ ሆኖ ተሰማቸው።

“እንቺ!” አለ ጎንቻ ከባላባት ቱሬ የወሰደውን አምስት ባለ መቶ ብር
ኖቶች ወደ እጇ እየዘረጋ፡፡ ብሩን ከእጁ ሳትቀበለው ሀሳቧን ልትገልፅለት ፈለገች። የሚያስቀይማት በሃሳብሽ አልስማማም” የሚላት ከሆነ እሷ ጋ ያጠራቀመውን ጭምር ልትመልስለት፣ “ከቃልሽ አልወጣም አንቺ እንዳልሽ” የሚላት ከሆነ ደግሞ ገንዘቡን በፍቅር ልትቀበለውና ለአፀፋው ከንፈሩን በደስታ ልትስመው ዐይኖቿን ስልምልም አደረገችና ዐይን ዐይኑን ተመለከተችው፡፡

“ምነው ዓለምዬ?” አላት።
“አንድ ነገር ልጠይቅህ ነው እሺ ትለኛለህ?”
“አንቺ ጠይቀሽኝ እምቢ የምለው ነገር ይኖራል ብለሽ ታስቢያለሽ?”
“ምናልባት?"
በፍፁም አታስቢ አትጠራጠሪ!" ደስ አላት።ደረቱ ላይ ወጣችና ቁልቁል አንገቱ ስር እየሳመችው..."ጎንቻዬ አንጀቴ ጨሰ። ገላዬ ተጠበሰ፡፡ለመታገስ ሞከርኩ ግን ከአቅሜ በላይ እየሆነ መጣ፡፡ በአንድ በኩል ያንተ
ናፍቆት ሲያሰቃየኝ በሌላ በኩል ደግሞ የሰው ወሬና ሃሜት ቁም ስቅሌን እያሳየኝ ተቸገርኩ፡፡ ይቺን የበሬ ግንባር የምታክል ከተማ ለቅቄ መጥፋት እፈልጋለሁ፡፡ዕድሜ ላንተ ሁሉም ነገር የሞላ ነው፡፡ ምን ችግር አለ? ገንዘቡም ቢሆን አሁን ከያዝከው ጋር ወደ ስድስት ሺህ ብር ተጠግቷል።
እንደዚህ በናፍቆት እየተሰቃየን በወር በአስራ አምስት ቀን ሰው አየን አላየን እያልን ከምንሳቀቅና በጨለማ ውስጥ ከምንሸሸግ ነፃነታችንን አውጀን በደስታ እየተዝናናን በፍቅር ለመኖር እንድንችል ከዚህ አካባቢ ቶሎ ብለን ተያይዘን እንጥፋ! እንሂድ! እንሂድ!” አለችው።
👍1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....አንዳንዴ የጊዜ ማጠርና መርዘም በሰዎች የውስጥ ስሜት የሚለካ ይመስላል ለተጨነቀ ልብና መንፈስ አንዱ አመት በአስራ ቤት የሚቆጠር ሲመስል ለተደሰተ ደግሞ የአንድ ቀን ያህል አጭር ይሆናል እሱ ግን አሁንም ኡደቱን ሳያዛባ እየሄደ ነው። እየነጎደ ነው።የቀንና የለሊት ፍርርቅ መሰረት አድርጎ ሳምንቱን በሳምንት ወሩንም በወር እየተካ ተምዘገዘገ። ብሎ ብሎ አንድ አመት አለቀና ሌላው ተጋመሰ
እነሆ አስቻለው አስመራ ከሄደ ሁለት ዓመት ከሶስት ወሩ! ሔዋን ክበረ መንግስት ከሄደች እንኳ አንድ ዓመት ከአራት ወር ሞላት። ሔዋን በክብረ መንግስት ታፈሡ በልሁና መርዕድ ዲላ ውስጥ እየኖሩ ይህ ጊዜ ከአስቻለው ትዝታና ናፍቆት ጋር በተያያዘ በተመሳሳይ የስሜት አቆጣጠር
እያሰቡት በመከራና በስቃይ ነው ያሳለፉት። አዝግሞ፣ ተጎትቶና ተንፏቆ ነው እዚህ የደረሰው። አንድ ክፍለ ዘመን ያህል ርቆባቸዋል። ለመምህርት ሸዋዬ ደግሞ በሚያስገርም ሁኔታ አጅግ አጭር ነበር።
ሸዋዬ በአስቻለውና በሔዋን መለያየት ቀድሞ የነበረባት የመንፈስ ቁስልወደ መገረን ተቀይሮ ከቅናት ስቃይ እፎይ ብላለች፡፡ ዛሬ የሁለቱ ፍቅር የዕለት
ተዕለት ሃሳብና ጭንቋ አይደለምና ፀሎቷ በዚሁ እንዲቀጥል ብቻ ነው። በሰላም የህይወት አጋጣሚ ውስጥ ገብታለች። ኑሮዋ ሞቅ ደመቅ እያለ ነው፡፡ ማህበራዊ ግንኙነቷም እየተሻሻለ ነው፡፡ ነቃ ነቃ ብላለች። የመንፈስ መረጋጋትም ይታይባታል። የአሁኑ ይዞታዋ ዘለቄታ እንዲኖረው ደፋ ቀና ማለቷን ተያይዛዋለች።
ለዚህ ሁሉ ሰበቡ የእናቷ ከክብረ መንግስት መምጣትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሔዋንን ይዘው ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ነበር። ያ አጋጣሚ በወቅቱ የእግር እሳት ሆኖ አንገብግቧት የነበረ ቢሆንም ለዛሬው ህይወቷ መሰረት ጥሉላት
ያለፈ በመሆኑ ግን በመልካም አጋጣሚነቱ እያስታወሰችው ትኖራለች።
የሔዋን እናት በሽዋዩ ቤት አድረው በነጋታው ወደ ሔዋን ጋ ከሄዱ በኋላ ከሸዋዬ ጋር ዳግም ሳይገናኙ ነበር ወደ ክብረ መንግስት የተመለሱት። በእርግጥ
መሄዴ ነውና ደህና ሁኚ' ሊሏት ከመሄዳቸው አንድ ቀን በፊት ወደ ቤቷ ጎራ ብለው ነበር፡፡ ግን አላገኟትም፡፡ ዕለቱ ባርናባስ ወየሶ በአንድ የሶሻሊስት አገር የውጭ ትምህርት ዕድል አግኝቶ ሊሄድ ሞቅ ደመቅ ባለ ድግስ የሚሸኝበት ቀን ነበርና ሸዋዬም የድግሱ ታዳሚ በመሆን ከድግሱ ቦታ አምሽታለች። የሔዋን እናት
ቶሎ የምትመለስ መስሏቸው ከወይዘሮ ዘነቡ ጋር እያወሩና እየተጫወቱ ቢጠብቋት
ቢቆዩም እሷ ግን እስከ ምሽት ድረስ ስለቆየችባቸው መልዕክቱ በወይዘሮ ዘነቡ በኩል እንዲደርሳት አድርገው ተመልሰዋል፡፡
ሽዋዬ የእናቷን ፈጥነው ወደ ክብረ መንግስት የመመለስ ጉዳይ ፈጽሞ ያሰበችው አልነበረም፡፡ በእሷ ግምት የሚሰነሳብቱና በዚያም አጋጣሚ የእሷንና
የሑዋንን ለየብቻ የመኖር ምክንያት ዋሽታም ቢሆን ቀጥፋ እውነታውን በመሽፈን
ልታወራላቸውና ራሷን ከተጠያቂነት ለማዳን የሚያስችሉ ብዙ መንገዶችን ፈጥራ ነበር፡፡ ግን ያ ካለመሆኑም በተጨማሪ እናቷ ከታፈሠ ጋር ውለው አድረው
እንዲሁም ከወይዘሮ ዘነቡ ጋር ብዙ ተጫውተው የመመለሳቸው ነገር ክፉኛ ነበር ያስደነገጣት፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች የአስቻለውንና የሔዋንን ግንኙነት እንዲሁም እሷ በሁለቱ ፍቅረኛሞች ላይ የነበራትን አቋም እንዴት አድርገው ለእናቷ እንደሚገልጹላት ታውቃለችና በተፈጠረባት መጥፎ
አጋጣሚም እጅጉን ተበሳጭታም ተናድዳም ነበር፡፡
የእናቷን ወደ ክብረ መንግስት መመለስ ጉዳይ በስማችበት ወቅት የነበራት ምርጫ አንድ ብቻ ነበር። የጉዟውን ሁኔታ ታውቃለች፡፡ ዲላ ተነስተው በአለታ ወንዶ በኩል ነው የሚጓዙት። አለታ ወንዶ ሲደርሱ ከዲላ መኪና ላይ ወርደው ከአዲስ አበባ ወደ ክብረ መንግስት የሚሄደውን አውቶብስ መጠበቅ አለባቸው፡፡
በመሀል ቢያንስ ለሁለት ወይም ለሶስት ሰዓት ያህል አለታ ወንዶ ከተማ ይቆያሉ እናም ጠዋት ከዲላ ከተማ ተነስታ አብራቸው በመጓዝ አለታ ወንዶ
እስክሚደርሰብት ጊዜና በአለታ ወንዶ ከተማ በሚያደርጉት የቆይታ ጊዜ ውስጥ በወሬ ስትተከትካቸው ለመቆየት አስባ ይህንኑ ለመፈጸም ወስና አደረች::
በማግስቱ በጠዋት ተነሳች፡፡ እናቷን መሸንገያ የሚሆን ጥቂት ገንዘብ ቋጠረች። ወደ መናኸሪያው ገሰገሰች፡፡ ከእናቷ በፊት ቀድማ ከቦታው ደረሰች::
ሔዋን ከምትኖርበት አቅጣጫ ወደ መናኸሪያው በሚያመጣው መንገድ በርቀት ስትመለከት ስድስት ሰዎች ሲወጠ ታዩዋት። እየቀረቧት ሲሄዱ ማንነታቸውን
ለየች፡፡ እናቷ፥ ታፈሡ! በልሁ! መርዕድ፤ሔዋንና ትርፌ ናቸው፡፡ ዘንግታው እንጂ! ለካ እናቷ
መሸኘት ነበረባቸው:: ከተሸኙም በእነዚሁ ሰዎች ነው::ተበሳጨች፡፡ ከእናቷ ጋር በአንድ መኪና የመሳፈር ዕቅዷን ሰርዛ በተከታዩ ሎንችን ልትጓዝና እናቷን በአለታ ወንዶ ልትደርስባቸው፣ እዚያ በሚያደርጉት የቆይታ ጊዜ ብቻ ልታነጋግራቸውም ወሰነች፡፡ ለጊዜው በመናኻሪያው ውስጥ እንዳትታይ ወደ አንድ ሰዋራ ቦታ በመቆም የእናቷንና የሸኝዎቻቸውን እንቅስቃሴ መከታተል ጀመረች።

አሁንም የአላሰበችው ሁኔታ ተከሰተ፡፡ እሷ የምትጠብቀው የእናቷን መሄድ ብቻ ነበር፡፡ ግን ደግሞ ሔዋንም መኪና ላይ ወጥታ በመስኮት አንገትና እጇቿን
አውጥታ አፏን ቧ እድርጋ ከፍታ ምርር ብላ ስታለቅስና እጆቿን እያርገበገበች ታፈሡን ስትሰናበት አየች:: እነሱም አስከሬን ወደ ቀብር ቦታ ሸኝተው የሚመለሱ
ሀዘንተኞችን ያህል ምርር ብለው ሲያለቅሱና እጀቻቸውን እያርገበገቡ ሲሰናበቷት አየች።
«እንዴ! እሷም ልትሄድ!» አለች ሽዋዬ ለብቻዋ እየተነጋገረች። ገረማትም ደነቃትም:: ግን ለዕለቱ እቅዷ ምንም ዓይነት እንቅፋት እንደማይፈጥርባት ገመተች፣ እሷ ለእናቷ ስለሆነ ነገር ብታወራ በትዝብት ታዳምጥ እንደሆነ እንጂ
ሔዋን ደፍራ ክርክር እንደማትገጥማት ታውቃታለችና።
እነ ሔዋንና እናቷ በአለታ ወንዶ በኩል በሚሄደው አውቶብስ ተሳፍረው ከሄዱና ሽኝዎቻቸውም ከመናኸሪያው ወጥተው ወደየአቅጣጫቸው ከተበታተኑ በኋላ ሸዋዬ በቀጣይ ወደ አለታ ወንዶ የሚሄደውን መኪና ፍለጋ ጀመረች:: በእርግጥም
አንድ የመኪና ላይ ሰራተኛ የአንዲት አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በር
ከፍቶ «ወንዶ! ወንዶ! አለታ ወንዶ!» የሚል ጥሪ አሰማ። ሽዋዬ ወደ መኪናዋ ሮጣ
በመግባት የጋቢና ወንበር ይዛ ቁጭ አለች፡፡
ከአንድ ሠዓት አለፍ አለ፡፡ ያቺ መኪና ግን ቶሎ አልሞላ አለች፡፡ በዚያው ልክ ሸዋዬ ተበሳጨች ቸኩላ ጋቢና ወስጥ ቁጭ ብላ ፊትለፊት ስትመለከት በርካታ መንገደኛ ወደ መናኸሪያው ሲገባ ታያለኝ። ግን እሷ ወዴለችባት መኪና የሚገባው ሰው ከቁጥር አይገባም፡፡ ረዳቱ አሁንም "ወንዶ ወንዶ" እያለ መንገደኛ ይጠራል
ሸዋዬ ወደ ኋላ ዞር ብላ ስታይ ግን በርካታ ወንበሮች ክፍት ሆነው
ትመለከታለች: በዚያው ልክ ቀልቧ እየቆመ ትቁነጠነጥ ጀመር፡፡
ከመኪናዋ ወንበሮች ግማሽ ያህሉ በሰው ከተያዙ በኋላ ሹፌሩ ወደ መኪናዋ ገብቶ ሞተር አስነሳ፡፡ ነገር ግን ሞቅ ሞቅ ከአደረገ በኃላ ተመልሶ ሊወርድ ሲዘጋጅ ሸዋዬ አየችውና «በእናትህ ሾፌር መንገድ ላይ ትሞላለህ፥ እንሂድ» አለችው፡፡
👍6👏1
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

“ደብረ ወርቅ ማርያም የሥዕል ንጉሥ አለ።”

የአስራ ስምንት ዓመቱ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ በትምህርት የበሰለ፣
በአስተሳሰቡ የበለፀገ፣ በመልኩና በአቋሙ ያማረ ሆነላት ምንትዋብ።ፈረስ ላይ ተቀምጦ፣ ነጭ ሻሹን ሹሩባው ላይ አስሮ፣ በወርቅ ያጌጠ ካባውን ደርቦ፣ የወርቅ በትረ መንግሥቱን ጨብጦ፣ ቀይ ድባብ ተይዞለት፣ ባልደራስ አጅቦት ከግቢ ሲወጣ፣ ሕዝቡ፣ “አቤት አበቃቀሉ!
አቤት የፊቱ አወራረድ!” እያለ አደነቀው: ወደደው፤ አከበረው፤
ሰገደለት፤ “ቋረኛው ኢያሱ” የሚል ቅጽል ስምም አወጣለት።

አደን አፍቃሪው ኢያሱ እንደ በፊቱ ሰስና ድኩላን ሳይሆን፣ ዝሆን፣
አውራሪስና ጎሽ እየገደለ መምጣት ጀምረ። ምንትዋብና እናቷ ግን ለአደን በወጣ ቁጥር ወገባቸውን በገመድ እየታጠቁ፣ መሬት እየተኙ፣ እየጸሙና እንቅልፍ እያጡ ይሰነብታሉ።

ኢያሱ በድፍረቱና በጀግንነቱ ተወዳዳሪ አጣ። ስለሃገር ጉዳይም መከታተል፣ ውሳኔ መስጠትና እርምጃ መውሰድ ያዘ። ከእናቱ መዳፍ ሥር ወጥቶ የራሱ ሰው ሆነ። አክሱም ጽዮን ሄደ። የእናቱን የትውልድ
ቦታ ለማየትም ቋራ ደርሶ መጣ። አንድ ጊዜ የግዛት ማስፋፋት ፍላጎቱ አድጎ ሰቆጣ ሄዶ ተሸንፎ ቢመጣ፣ በቁጭት ወኔውን ሞልቶ ሱዳን ጠረፍ ሄደ፡፡

የገጠመውን ጦር አሸንፎ በሰላም ተመለሰ።
በሰላም ይመለስ እንጂ ከእናቱ ጋር አተካራና ቅያሜ ውስጥ ገባ።
በግራዝማች ኢያሱና በእናቱ መሃል ያለው የፍቅር ግንኙነት ይከነክነው
ገባ። ምንትዋብም ወለተእስራኤል ያለቻትን ሦስተኛ ልጇን ከወለደች
ቆይታለች።

ኢያሱ እናቱ ላይ ቅሬታና ምሬት አደረበት። ምንም እንኳ እናቱን
ቢያከብርና ቢፈራ፣ ከግራዝማች ኢያሱ ጋር ያላትን ግንኙነት ችላ
የማይለው ጉዳይ ሆነበት።

ፀሐይ መግቢያ ላይ ነው። እናትና ልጅ ቤተመንግሥት እንግዳ
መቀበያው ክፍል ተቀምጠዋል። ኢያሱ ነገር ሲገባው ታውቃለች
ምንትዋብ። ገና፣ “ኸያሱ ጋር..” ሲልና ሲጠጣበት የነበረውን የወርቅ ዋንጫ ሲያስቀምጥ፣ የንግግራቸው አቅጣጫ ወዴት እንደሆነ ገባት።

“ኸያሱ ጋር ባለሽ ግንኙነት ሰው ሁሉ ያማሻል። ቀደም ብየ ብሰማም ዕድሜየም ገና ስለነበር ፈርቸ እስተዛሬ በዝምታ ቆየሁ” አላት።

“ኢያሱ አባትህኮ ሲሞቱ ዕድሜዬ ገና ነበር። ብቸኛም ነበርሁ።
ልችም መውለድ ፈልግ ነበር። ደሞስ እንዲህ ያለው በኔ ተዠመረ?” አለችና፣ ለራሷ ዛዲያ እንዴት ልሁን ሰው መሆኔ ቀረ? እቴጌ ያሉኝ እንደሁ ሰው ማይደለሁ እንዴ? ሰው መሆን ዛዲያ ትርጉሙ ምኑ ላይ ነው? ስትል መናገር ሲጀምር ቀና አለች።

“የመዠመርና ያለመዠመር ጉዳይ ማዶል” አለ፣ እናቱ ላይ አድርጎ
በማያውቀው መንገድ ፊቱን አኮማትሮ።

ከእሷ ስሜት በላይ ክብር የሚባል ነገር አለ።

መልስ አልሰጠችውም። ስሜቱ እንደተጎዳ አውቃለች። እባክህ
አምላኬ ኸልዤ ጋር እንዳልጣላ ትግስት ስጠኝ አለች።

“ኢያሱ አንደኛ ያክስቴ ልዥ ነው” ሲል ቀጠለ። “ያባቴ እት...
የወለተስራኤል ልዥ እኮ ነው። ያባቴ ክብርስ ቢሆን፣ ስለምን ይነካል? ላንቺም ቢሆን ነውር ነው። ስለምንስ ስማችን በዝኸ ይነሳል? መልካም ስምሽንስ ስለምን ታጎድፊያለሽ? ግራማች ብትይውም ሰዉ አሁንም
ምልምል ኢያሱ ነው ሚለው። ኸዝኸ ወዲያ ውርደት ምን አለ?”

ንግግሩ ጎመዘዛት። ከንፈሯን በጥርሷ ነከስ ኣድርጋ በግራ ሌባ ጣቷ መታ መታ አደረገችው። ቁጣ ሰውነቷ ውስጥ ሲቀሰቀስ ተሰማት።

“ተው እንጂ ኢያሱ! እኔን እናትህን እንዲህ አትናገር። ምወድህ
እናትህ እንጂ ሌላ ነኝ?”

“ሰዉ ያማሻል እኮ!” ግንባሩ ኩምትር ብሏል።

“አምተው በቅቷቸዋል። ኢያሱ ... ኸግራማች ጋር ተዋልደናል እኮ!
እህቶችህ የማን ይመስሉሃል? እኔ ያባትህን ስም ለማጉደፍ ሳይሆን፣
ብቸኝነት ስላጠቃኝ ነው። ተረዳኝ እንጂ!”

“ኸዝኽ ወዲያ ውርደት ምን አለ?” የሚሉት ቃላቶቹ ረበሿት። ትክ ብላ አየችው። ፊቱ ላይ ቅያሜ አየች። ዛዲያ ዕድሜዬን እንዲሁ
ላሳልፍ ኑሯል እንዴ? አለች።

ለእሱ የክብር ጉዳይ እንደሆነ አላጣችውም። እንኳንስ የባሏን
የእህት ልጅ ባሏ የሞተባት ንግሥት ጨርሶ ሌላ ማግባት እንደሌለባት ታውቃለች።

ግን ደግሞ ውጣ ውረድ ከበዛበት የቤተመንግሥት ሕይወት ዘወር ብላ የምትዝናናበትና ሐሳቧን የምትከፍልበት ነገር ባለመኖሩ፣
አንድ ቀን ከልጇ ጋር የሚያቃቅራትና አልፎም ሊያጣላት የሚችል ነገር እንደሆነ ብታውቅም አድርጋዋለች።

ከልጇ ጋር ይህን ያህል ጠንከር ያለ ንግግር ተለዋውጠው ስለማያውቁ ቅር ብትሰኝም፣ የምትወደውንና የምትሳሳለትን ገራሙን ልጇን መቀየም
አልሆነላትም። ቅሬታና ቅይሜ በሆዷ አምቃ መሄድ አልፈለገችም።

የአባቱ ብቻ ሳይሆን የእሱ፣ ብሎም የእሷ ክብር እንደተነካበት ስላወቀች ትችቱን ተቀብላ ዋጥ ማድረግን ፈለገች።

በራሷ አምሳል ቀርጻ ያወጣችው ቢመስላትም፣ እየተመካከረች፣
ሲሻትም እየተጫነችው ያሳደገችው ልጇ ብሩህ አእምሮ ያለውና በራሱ አስተሳሰብ የሚመራ መሆኑን በመገንዘብ ልቧ ላይ ሊሰርፅ የቃጣውን
ቅሬታ ለመግታት ታገለች።

ለብቻው ለመግዛት ዕድሜው ቢፈቅድለትም፣ ለእሷ ካለው ፍቅር፣አክብሮትና ፍራቻ ጭምር የእሷን የበላይነት ተቀብሎ መኖር እንደቻለ ተገነዘበች። እሱም ቢሆን ከሥልጣኗ ለማውረድ የሚያስችለው በቂ
ምክንያት የለውም።

እንዲያውም የእሱ መንግሥት በእሷ ብርታት፣ ጥበብና ዘዴ የተሞላው አመራር መደላደሉን፣ አንዳንድ መኳንንት ቋረኞች ላይ ያላቸውን ጥላቻ አርግባ ተስማምታና አስማምታ መቆየቷን፣ ከአንዴም ሁለት
ጊዜ የተቃጣባቸውን ዓመጽ ድል መቀዳጀታቸውን፣ ሌሎችን ደግሞ
በሰላማዊ ድርድር እየፈታች ሰላም እንዲሰፍን ማድረጓን ይገነዘብ
እንደሆነ ራሷን ጠየቀች። ይህን ልታስታውሰው ግን አልፈለገችም፤
ዝም ብላ ተቀመጠች። ተነስቶ ሲወጣ በተለመደው የእናትና የልጅ ፍቅር አልተሰነባበቱም።

ከሄደ በኋላ፣ የተነጋገሩትን ሁሉ በጭንቅላቷ ከለሰችው። መቸም
እኔስ ብሆን በነገሩ ሳልጨነቅ ቀርቸ ነው? አልሆንልኝ ብሎ ነው እንጂ።ብቸኝነት አጥቅቶኝ ነው ኸኢያሱ ጋር እዚህ ሁሉ ውስጥ የገባሁት።እሱም ቢሆን እነአስቴርን የመሳሰሉ ልዦች ሰጥቶኛል። ኸንግዲህ
ምን አረጋለሁ። የአብራኬ ክፋይ እንዲህ ሲለኝ መስማት ለእኔ ደግ
ማዶል። መቸስ የክብር ጉዳይ ሆኖበት ነው። በዝኸ አልቀየመውም። እነሱ እንዳይጣሉብኝ እንጂ። ለግራማች ኢያሱ ነግረዋለሁ እያለች አሰላሰለች።

ግራዝማች ኢያሱ፡ “ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ተለውጦብኛል” ማለት
ሲያዘወትር፣ እንዳይጣሉባት ሰጋች፤ በሐሳብ ባከነች። እየቆየም በሁለቱ መሃል ነገሮች እየከረሩ፣ ግንኙነታቸው ወደ ፀብ መቀየሩ እንቅልፍ አሳጣት። አስታራቂ ሽማግሌዎች ላከች።
ይህ ሳያንሳት በመጋቤ ሥነ-ጊዮርጊስ አማካኝነት ሁለተኛው የጥላዬ ሥዕል መጣላት። የሥዕሉ ውበትና የያዘው ጥልቅ ሐሳብ
ቢያስደስታትም፣ ሁለቱም ሥዕሎች ከአንድ ሥሙር ከሚባል ሰው መምጣታቸውን በሥራው አረጋገጠች፤ ለወራት ተረበሸች።
እነዚህን ሥዕሎች የሚልከው ሰው ምን አስቦ እንደሆነ ለማወቅ
ቸገራት። እኼ ሰው ስለምን ማንነታቸው ስንኳ በማይታወቅ ሰዎች ይልካል? ይኸ ከበጎ አሳብ የመጣ ነው ወይንስ እኔን ሰላም ለመንሳት ሚደረግ እኔ ለራሴ ኸልዤ ጋር ችግር ውስጥ በገባሁበት ግዝየ ስለምን
እንደዝኸ ያለ ነገር ይገጥመኛል? አንቺ ምወድሽ ቁስቋም የዝኸን ሰው ማንነት አንቺው ግለጭልኝ እያለች ማርያምን ተለማመነች። ለሌላ ሰው የማታዋየው ምሥጢር ሆኖባት ሥዕሉን በመጣበት ጨርቅ መልሳ ጠቅልላ ከበፊተኛው ሥዕል ጋር ደብቃ አስቀመጠችው።
👍14