አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...ጥላዬ፣ ከአለቃ ሔኖክ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እየመሠረተ ሲመጣ፣ብዙ ጊዜ አብሯቸው መቀመጥና መጫወት ሥዕል ከመሣል ቀጥሎ የሚያስደስተው ነገር ሆነ። ወደፊትም እንደሳቸው ጥበበኛ መሆን አበክሮ ተመኘ። ላደረጉለት ሁሉ ሲያመሰግናቸው ቢውል አላጠግበው አለ።

“አለቃ ላረጉልኝ ሁሉ እመቤቴ ምላሹን ትስጥዎ” አላቸው፣ አንድ
ቀን እንደወትሮዋቸው ግቢ ውስጥ ተቀምጠው ሲያወሩ።

“እኔኮ ማስተምረው ኸተማሪዎቸ ጥቅም አገኛለሁ ብየ ማዶል። ልክ
መምህሬ የነበሩት አለቃ ወልደሰንበት ደከመኝ ሳይሉ፣ ሚያውቁትን ሁሌ ሳይሸሽጉ እንዳሳተማሩኝ ሁሉ ተማሮቸን ማስተማር ፈልጋለሁ።ዋጋየ እናንተ ተማሮቸ ጥሩ ተምራችሁ ለጌታችን ያላችሁን እምነት፣ ክብርና ፍቅር በሥራችሁ ስታሳዩ፣ የመጻሕፍትን ምሥጢር አንብባችሁና ተረድታችሁ በሥዕል ስትገልጡ ነው። ሥዕል ዋናው ዓላማው ቤተስኪያንን ማስጌጥ ማዶል። ሥዕል እኮ ታሪክ ነው ሚነግር፤
ሥዕሉ ራሱ እኮ ወንጌል ነው። ምእመኑ የመጻሕፍቱን ምሥጢር
አውያቁም፣ አያነቡም፡ አይረዱም። ስለዝኸ የእናንተ ሥራ የመጻሕፍቱን ምሥጢር... ወንጌሉን በሥዕል እንዲረዱና መንፈሳዊነት፣ አክብሮትና
ፍራት በልባቸው እንዲያድር ማረግ ነው። ባለፈው እንደነገርኩህ ካህናቱ አምስቱን አዕማደ ምሥጢር በንባብ በሐተታ ይማራሉ።ምእመኑ ግን በሥዕል ነው ሚማር። ቀዳሚው ምሥጢረ ሥጋዌ ነው፣ኸገብርኤል ብሥራት ትጀምራለኽ። ገብርኤል ማርያምን ትፀንሲ ይላታል። ኸዚያ ልደቱን ትሥላለኸ። ልደቱን ስትሥል ሰብአ ሰገል እረኞቹም አሉ። ግዝረቱን ደሞ ቀጥለኽ መሣል ነው፤ ስምዖን አለ አሉ፣ አድግና ላሕም አሉ... ጌታን በትንፋሻቸው ያሞቁት፣ መልአኩም አብሮ ሚጠቀስ፤ ዓይኖቼ ማዳንህን ስላዩ በል ውሰደኝ ብሎ ጸልዮ
ይሞታል ። ኸዚያ ምሥጢረ ጥምቀቱ፣ ተአምራቱ፣ ቃና ዘገሊላው፣ አስተምህሮቱ አለ። ኸዚያ ምሥጢረ ቁርባንን ትሥላለህ፤ ሥቅለቱን አብረህ። ቀጥለህ ትንሣኤውንና ዕርገቱን ትሥላለህ። መጻሕፍት
በስንትና ስንት ምዕራፍ ያካተቱትን ታሪክ ሠዓሊው በጥቂት ብራናዎች አሣምሮ ቀምሮ ያስቀምጠዋል። ስለዚህ ምሥጢራቱን፣ የቱ ቀድሞ
የትኛው ሚከተል መሆኑን መመርመር ያስፈልጋል፤ የቀለም ማሳመር ብቻ ለሠዓሊነት አይበቃም።”

ጥላዬ፣ በተመስጦ አዳመጠና “እሺ የንታ፤ ንባቤንም ሥራዬንም
ተግቼ እቀጥላለሁ፤ ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ” አላቸው፣ ትምህርታቸውን ከልቡ አዳምጦ።

“ዋናው ነገር እሱ ነው... ትጋት” አሉት፣ ሌባ ጣታቸውን እያወዛወዙ። “አንተን ትጉ ሁነህ አግኝቸኻለሁ። ምን ስጦታ ያለው ቢሆን ትጋት የሌለው ተማሪ አልወድም። ሥዕል ችሎታ ቢኖርህ ትጋት ኻላሳየህ ለሥራህ ጥሩ አይሆንም። አሁን በየቦታው ያሉት የተከበሩት ሠዓሊዎች አለሱ ሌላ ንሮ የላቸውም። አንዳንድ ተማሪ ይመጣል ኸኔ ዘንድ።እንዳው ብቻ ጫር ጫር አርጎ ቤተክሲያን ውስጥ ገብቶ ሥዕል
መሣል ይፈልጋል። ይኸ እንዴት ብሎ ይሆናል? ሥዕል ቀልድ ነው
እንዴ? እኔማ እንደዚያ ያለውን ተማሪ ኸኔ ዘንድ አላቆየውም። አንተ ለሥዕልም ለቤተክሲያንም አትሆንም ብየ ነው ምሰደው። ችሎታ አለ ትጋት ምንድርነው? አይምሰልህ ጥላዬ ሥራን ትልቅ ደረጃ ሚያደርሰው ትጋት ነው። እኔስ ብሆን አንድ ተማሪ ትጋት ካላሳየ ኸሱ ጋር ስለምን
እደክማለሁ? እስቲ በል ንገረኝ?”
“ውነት ነው... ውነት ነው” አለ፣ ጥላዬ ራሱን በአዎንታ እየነቀነቀ።

ልቡ ተነካ። ሥዕል እየሣለ ቤተክርስቲያንን ማገልገል እንዳለበት ይመኝ እንጂ፣ እንደዚህ ጠለቅ ብሎ ነገሩን አስቦበት አያውቅም።በአካባቢው የሚያያቸውን ቤቶች፣ ሰዎችና እንስሳት ቤታቸው ግድግዳ
ላይ ሲሥል ቢቆይም፣ የሚሥላቸውን ምስሎች ለዘላለም ቀርጾ ማስቀመጥ ከሚመኛቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛው ምንትዋብን ነው። በተለይም
ደግሞ ነጠላ ተከናንባ ከቤተክርስቲያን ስትወጣ ያያት የነበረውን።

“ለሥዕል ያለኝ መውደድ ለብቻ ነው። ኸርሶ ዘንድ መማሬ ደሞ
ይበልጥ እንድወደው አድርጎኛል።”

“እኔም ለሥዕል ይኸ ነው ተብሎ ማይነገር ፍቅር አለኝ” አሉት።
“አለሱ ሌላ ሕይወት የለኝም። ሥዕል ሳይ እመራመራለሁ። የሠራሁትን ሥራ መልሼ ሳየው 'በውነት ይኸን የሠራኹ እኔ ነኝ ወይስ በኔ እጅ ራሱ ባለቤቱ ሣለው ብዬ እደነቃለኹ። ሥዕል የእዝጊሃር ወይም የደቂቀ
አማልክቱ ሥራ እንጂ የእኛ የደካሞቹ ፍጥረት አይመስለኝም። ጥላዬ...ሥዕል እኮ እንደ ቅኔ ከሳቴ ብርሃን ነው... የተደበቀውን ምሥጢር ሁሉ ሚገልጥ... ብርሃን ሚሰጥ። ለዝኽ ነው ቅኔን ብዙ ሊቃውንት ልሳነ መላእክት ነው ሚሉት።

ጥላዬ፣ መስማማቱን ለማሳየት ራሱን ነቀነቀ። “የንታ ሥዕል ለመማር እንደዛ ስመኝ ቆይቸ አሁን መማር በመቻሌ ዕድለኛ ሁኛለሁ።”

“ዕድል ኸሰማይ አይወድቅም” አሉት፣ ፊታቸውን ወደሱ መልሰው።
“ዕድል እንደ ሥዕል ነው። ሚገባው ዘንድ ነው ሚኸድ። ማይሆነው... ዝግጁ ሁኖ ማይጠብቀው ዘንድ አይኸድም። ወይም ማይሆነውን አይጣራም። ዕድል ልክ እንደ ሥዕል ሚፈልገውን ያውቃል፣ አውቆም
ይጣራል፣ ወይም ራሱ ወደሱ ይኸዳል። እንዳንተ ያለውን... የነፍሱን ጥሪ ሚያቀውን ኻለበት ፈልጎ ያወጣዋል። አንተም ዛዲያ ስትፈልገው፣ እሱም ሲፈልግህ... ስትፈላለጉ ቆይታችሁ ተገናኛችሁ።”

“አየ የንታ የእዝጊሃር ቸርነት ተጨምሮበት ነው።”

እዝጊሃር እኮ ማትችለውን አይሰጥህም። ጎበዝ ብትሆን ነው የሰጠህ።”

ውነት ነው አለ፣ ለራሱ።

“አሁን ይልቅ ምመክርህ” አሉት፣ ሌባ ጣታቸውን እያወዛወዙ፣ “ደብረ ወርቅ ኸደህ ሌሎች አስተማሮች ዘንድ መማርን ነው። እንደ ሌላው ትምርት ሁሉ ሥዕል እየተዘዋወርህ ስትማር ብዙ ትምርት ትቀስማለህ፣
ችሎታህንም ታዳብራለህ። ደብረ ወርቅ ታላላቅ የሥዕል መምህሮች
አሉ። እኔ እንደምታየው እያረዥሁ ነው። ኸንግዲህ እንደድሮው
ማስተማር አልችልም። አንተንም ገና ሳይህ ቀልቤ ስላረፈብህ
ተቀበልኩህ እንጂ ማስተማር እተዋለሁ እያልሁ ነበር” አሉት።

“የንታ ኸርሶ ዘንድ በቆየሁ። ኸርሶ መለየቱ ይከብደኛል።”

“ምን ይደረግ። እየደከመኝ መጣሁ።”

“ኸዝሁ ሌላ መምር ዘንድ ብቆይስ?”

“ሊቀጠበብት ኣዳሙ ዘንድ ነው እንድትማር የፈለግሁት። አዳሙ
ወደር ማይገኝለት መምህር ነው። ለኔም የረዥም ግዝየ ወዳጄ
ነው። እስታሁንም ብዙ ተማሮቸን ወደሱ ልኬያለሁ። አንተም ኸሱ
ዘንድ እንድትማር ነው ምፈልግ። ትምርትህን ስትጨርስ ተመልሰህ
ትመጣለህ።”

ጥላዬ፣ ጐንደር የዕድል በር ከፈተችልኝ፣ አለቃን መምህሬ፣ ጐንደርን ቤቴ ብሎ ተመቻችቶ ተቀምጦ፣ እንደዚህ ዓይነቱ ዱብ ዕዳ ሲመጣበት ደነገጠ፤ ሆድ ባሰው፤ መንፈሱ ተረበሸ፤ ተስፋ ሊቆርጥ ቃጣው።ከአለቃ ሔኖክ ሥር ሆኖ ታላቅ ሠዓሊ ለመሆን ያደረበትን ምኞት፣ከቤቱ ሲወጣ የሥዕል ንጉሥ ለመሆን የነበረውን ሕልም ሁሉ ጉም ሸፈነው። ደብረ ወርቅ ይሂድ ወይንም እዛው ጐንደር ሌላ አስተማሪ ዘንድ ይማር ለመወሰን አቃተው፤ ግራ ገባው። ምንትዋብን በአካል
ባያገኛትም እንኳ ከእሷ ርቆ መኖሩ ደግሞ አሳሰበው፣ አሳዘነው።....
።።።።።።።።።።፡፡።።።።።።።።።።።።

“ቁስቋም ብዙ ነገር ሰጥታኛለች፣ ወንድ ልዥ ደሞ ብትሰጠኝ።”
👍13😁1
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


...“ቁስቋም ብዙ ነገር ሰጥታኛለች፣ ወንድ ልዥ ደሞ ብትሰጠኝ።”

“ትሰጥሻለች። ምን ይሳናታል? አሁን ስለሱ አታስቢ።”

ሆዷ እየገፋ ሲመጣ፣ ጭንቀቷ በረታ። ሴት በመውለዷ ባትከፋም፣ ወንድ አለመውለዷ ቤተመንግሥት ውስጥ ሊኖረኝ ይችላል ብላ ያሰበችውን ቦታ የሚያሳጣት መሰላት።
ይበልጡንም ደግሞ ወህኒ
አምባ ያሉ የነገሥታት ዘሮች የሚወለደው ወንድ ቢሆን ሐዘናቸውን፣ ሴት ብትሆን ደግሞ ደስታቸውንና የበካፋን ተስፋ መጨናገፍ እያሰበች መንፈሷ ተበጠበጠ። የጐንደርን ታቦታት ሁሉ ተማጸነች። የእሷ
ቋረኝነት ያብከነከናቸው መሣፍንትና መኳንንት ደግሞ በካፋ ሲሄዱ ቋረኛ አልጋው ላይ የመውጣቱ ጉዳይ ሲያሳስባቸው፣ ሲያነጋግራቸውና ልባቸውን ሲሰቅለው እሷ የበለጠ ጭንቀት ውስጥ ገባች።
የቤተመንግሥት ባለሟሉ፣ የበካፋ ደጋፊ መኳንንትና ሕዝቡ ግን
በእነሱ ዘንድ ተወዳጅነትን እያተረፈች ለመጣችው፣ ለእሷ... ለምንትዋብ ወንድ ልጅ እንድትወልድ ተመኙላት።

ለወራት ቤተመንግሥት ግቢ ውስጥ፣ በየቤቱና በየመንደሩ ወሬው ተጋጋለ፤ ሞኝ መቆሚያ ላይ ተሟሟቀ፤ ጃን ተከል ላይ ተፋፋመ።የጃን ተከል ደንበኞች ወደ ሞኝ መቆሚያ ተጨማሪ ወሬ ለማሳደድ አሽቆለቆሉ። የሞኝ መቆሚያዎቹ ወደ ጃን ተከል በጥድፊያ አሻቀቡ።

መጽሐፍ ገላጩና ኮከብ ቆጣሪው ገሚሱ ወንድ፣ ሌላው ሴት ነው
ሲል ተነበየ። ገበሬው በየእርሻው፣ ነጋዴው በገበያው ላይ፣ ሴቶች ወንዝ ዳር፣ ሽማግሌና ወጣት በየጎጡ እሰጥ አገባ ያዙ፤ ተወራረዱ። የንግርት
ዓይነቶች ተወሱ። የቆራጣ ገዳም እመምኔቷ፣ የወለተጴጥሮስ ትንቢት ተወራ፣ የሰማው ላልሰማው አስተላለፈ። ወሬው ጐንደርን ተሻግሮ በየግዛቱ ተናፈሰ። ቀድሞ ስለነገሥታት የተነገሩ ሌሎች ንግርቶች
ሁሉ ለማመሳከሪያነት ቀረቡ፣ ተመረመሩ፣ ተተነተኑ።
ሃገር በወሬ ታመሰች። ወንድ ነው ሲሏት ጮቤ ስትረግጥ፣ ሴት ናት
ሲሏት ስትተክዝ ከረመች።

ምንትዋብ በበኩሏ ቀናቱ ሲያዘግሙባት፣ ወራቱ እንደ ገመድ ሲጎተቱባት ቆይታ አንድ ሌሊት ምጥ ያዛት። እናቷና አያቷ የነገሥታቱ አዋላጅ የሆኑትን ሴት በፍጥነት አስመጡ። ምንትዋብ ሌሊቱን በሙሉ ስታምጥ፣ ሴቱ “ማርያም”፣ “ማርያም” ሲል፣ በካፋ በጭንቀት ቁጭ
ብድግ ሲሉ፣ ሲጸልዩ፣ ካህናት ምህላ ሲያወርዱና የቤተመንግሥት ባለሟሎች ሲንቆራጠጡ ቆይተው ንጋት ላይ የመጀመሪያው ዕልልታ ተሰማ። በሰላም የመገላገሏ ዜና በመኾኑ ለአፄው የአፍታ እፎይታ
ቢሰጣቸውም የሕጻኑን ጸታ ለመለየት ዕልልታውን መቁጠር ጀመሩ።

ዕልልታው ተደገመ፤ የበካፋ ጭንቀትም ናረ፤ ሦስተኛውና የመጨረሻው ዕልልታ ይሰማና ወሽመጤን ይቆርጠው ይኾን ወይስ ይቀጥላል? የሚለው ጭንቀት በእያንዳንዱ ዕልልታ መሃል ያለችዋን ቅጽበት ዝንተዓለም እስክትመስል ድረስ ለጠጣት። ሦስተኛው ዕልልታ
ተሰማ። እዚኸ ላይ የበካፋ የልብ ትርታ ፀጥ አለ፤ ሌላ ዕልልታ ካልተሰማ አልቦ አልጋ ወራሽ የሚለው ሥጋት ሰቅዞ ይዟቸዋል። የጠላቶቻቸውን መደሰት፣ የወዳጆቻቸውን መሳቀቅ እየቃኙ ሳለ፣ አራተኛው የዕልልታ
ድምጽ መጣ። ወንድ ልጅ! አምስተኛውን፣ ስድስተኛውንና ሰባተኛውን ዕልልታ መስማት አላስፈለጋቸውም፤ ወንድ ልጅ ተወልዶላቸዋል! ዜናውን በመላ ቤተመንግሥቱ ግቢ ውስጥ ሲያስተጋቡት፣ ግቢው
ትርምስምሱ ወጣ።

ምንትዋብ ድካም ላይ ብትሆንም ደስታዋ ወሰን አጣ፣ በጭንቀት
የተኮማተረው ግንባሯ ተፍታታ፤ ቁስቋም ማርያምን አመሰገነች።
አፄ በካፋ በጭንቀት የሙጥኝ ይዘውት የነበረውን የጸሎት
መጽሐፋቸውን አስቀምጠው ከመኝታ ክፍላቸው ወጡ።

ምንትዋብ ወዳለችበት ገሰገሱ። ምንትዋብ እስክትጸዳዳ ጠብቀው
ሲገቡ፣ እየደጋገሙ፣ “እንኳን ማርያም ማረችሽ” አሏት። እንኰዬ
ህጻኑን ኣቅፈው ሲያሳይዋቸው የደስታ እንባ ተናነቃቸው። አልጋ ወራሽ በማግኘታቸው ሩፋኤልንና ከአንገርብ ወንዝ በስቲያ ደፈጫ የተከሏትን ኪዳነ ምሕረትን አመሰገኑ፤ ውለታቸውን በወርቅ እንደሚከፍሉ ቃል ገቡ።

ቤተመንግሥቱ ውስጥ ታላቅ ፈንጠዝያ ሆነ። ወዲያው ስፍር ቁጥር የሌለው የግባት ነፍጥ ወደላይ ተተኮሰ። የአካባቢው ሰው “ወንድ ነው!
ወንድ ነው!” እያለ ጃን ተከል ግልብጥ ብሎ ወጣ። ሴቶች ዕልልታቸውን አቀለጡት። ጐንደር የምሥራቹ ደረሳት፤ ፈነደቀች። ራቅ ካሉ ቦታዎች ሳይቀር ጐንደሬዎች እየከነፉ ጃን ተከል ደረሱ።

እቴጌ ወንድ ልዥ ተገላገሉ! ሰባት ግዝየ ሲተኮስ ቆጥሬያለሁ።
ወንድ ነው። ንጉሡ አልጋ ወራሽ አገኙ!” ይላል አንዱ።

“ሦስት ቆጥሬ ሴት ትሆን? ስል ዐራት ሲደገም እንግዲያማ ሰባት
ነው ሚሆን። ወንድ ነው ብየ ስሮጥ መጣሁ” ይላል ሌላው።
የዕጣና የውርርድ አሸናፊዎች የድል ዋጋቸውን ጠየቁ።

ንግርቶች ሁሉ እንደገና ተነገሩ። የቅድስት ወለተጴጥርስ ትንቢት
ተነሣ። “የሷ ንግርት መሬት አይወድቅም” ተባለ። በየደብሩ ካህናት ደወል አሰሙ። ዘመሩ፣ አሸበሸቡ። መነኮሳት ሕልማቸውን ተለወዋጡ: ደስታ በደስታ ሆኑ።

የበካፋ የሥልጣን ተቀናቃኞች ወሬውን ሲሰሙ ደነገጡ፤ ተስፋቸው እንደ እንፋሎት ተነነ። የማስመሰል ካባ የደረቡ አንጀታቸው ያረረ፣ወንድ ልጅ በመወለዱ ከልብ የተደሰቱ መኳንንት፣ ካህናትና ሊቃውንት
ከቅርብና ከሩቅ ደስታቸውን ለመግለፅ ወደ ቤተመንግሥት ጎረፉ።

ለሕጻኑም መልካም ምኞታቸውን አዥጎደጎዱ። ሕጻኑ በአያቱ፣ በአፄ ኣድያም ሰገድ ኢያሱ ስም ተጠራ። ግብር በየቀኑ ገባ። ኢያሱ፣ በወጉ መሠረት በአርባ ቀኑ ክርስትና ተነሣ።

ኢያሱ ከተወለደ በኋላ፣ የመጀመሪያው መስቀል ነው። ለአፄ በካፋ ዓመታዊ ሠራዊት ግባት ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው። እንደ ጎጃምና ትግራይ ካሉ ራቅ ካሉ ግዛቶች የሚመጡ አስተዳዳሪ መኳንንት
ክረምቱ ሳይገባ ግንቦት ወር ላይ እያንዳንዳቸው ሠራዊታቸውን
ይዘው ጐንደር ሲገቡ፣ እንደ ስሜንና ቤገምድር ካሉ ቅርብ ቦታዎች የሚመጡት ደግሞ ዐዲስ ዓመትን ቤታቸው ውለው ሠራዊታቸውን ይዘው ጐንደር ገብተዋል። ቤተመንግሥት ዙርያ ለየግላቸውና ይዘውት
ለመጡት ሠራዊት ድንኳን ተተክሎላቸው እዚያው አርፈዋል።

ምንትዋብና አያቷ ስለ ሠራዊት ግባቱ አስፈላጊነት ሲነጋገሩ
አያትየው፣ ነገሥታቱ እኼን በዓል ሚያደርጉት አንድም እንግዲህ
ወታደራዊ ጉልበታቸውን ለማሳየት...” ብለው ሲጀምሩ አቋረጠቻቸው።

“ለማን ነው ሚያሳዩት?”

“ለሁሉም። እሱ ብቻ ማዶል። የመኳንንቱን ታማኝነት ለማረጋገጥም ሲሉ ነው። ሌላ ደሞ... ደንብ ሲያወጡ ወይም አዋጅ ሲነግሩ መኳንንቱ
በየግዛታቸው ያነን ደንብና አዋጅ በተመሳሳይ መንገድ እንዲያስከብሩ ጭምር ነው። ሌላው ደሞ መቸም ንጉሡ መኳንንቱ እንዳያምጹባቸው...
ተቀይመዋቸው ከሆነ ደሞ ለማረጋጋትና ሰላም ለመፍጠር በጋብቻ ሚተሳሰሩበትም ግዝየ ነው። በዝኸ ግዝየ አንድ የተቀየመ መኰንን አሞኛል ብሎ ሊቀር ይችላል። እናም እኼ ግዝየ ጃንሆይ አለ ነገር ሚሉበት፣ ብዙ ነገር ሚያውቁበትና ሚስተካከል ኻለም ተሎ ብለው ሚያስተካክሉበትም ግዝየ ነው” አሏት።

የበዓሉ ዕለት፣ ምንትዋብ ከአፄ በካፋ ጎን ድባብ ተይዞላት አደባባይ ወጣች። ሥርዐቱን ለማየት እጅግ ጓግታለች። ከንጉሠ ነገሥቱ ጎን ተቀመች። ጐንደሬዎችም ይህን ታላቅ በዓል ለመታደም ሥራቸውን
ነቅለው ወጥተዋል። ፎካሪዎች በየተራ እየወጡ ወደላይ ወደታች እያሉ ፎከሩ፣ ሽለሉ። ንጉሠ ነገሥቱን አወደሱ፤ አመሰገኑ።ሽለላውና ፉከራው ሲቆም፣ በአጋፋሪ መሪነት ታላቁ ስልፍ ተጀመረ።
👍13
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ምንም እንኳን ልጇ ደሕና መሆኑንና ትምህርትና ዋናም እየተማረ እንደሆነ፣ ከፍ ሲል ደግሞ ቀስት ውርወራ፣ ጉግስና አደን እንደሚማር ብትሰማም፣ ጭንቀቷ እምብዛም ሊቀንስላት አልቻለም። ሳታስበው ግን ሁኔታዎች ተቀየሩ። ለንጉሠ ነገሥቱ ቅርብ የሆነው ዐቃቤ ሰዐቱ ዲዮስቆሮስ ንጉሠ ነገሥቱን፣ “ኢያሱ መጥቶ የቤተመንግሥት ወግ፣
አስተዳደርና ትምርት በአግባቡ ይማር፤ ባባትዎ አጥንት ይዤዎታለሁ”እያለ አላስቆም አላስቀምጥ አላቸው።

ምንትዋብ አጋዥ ያገኘች መሰላት

አንድ ቀን ያልታሰበ ነገር ተፈጠረ። የስድስት ዓመቱ ኢያሱ ሲጫወት ድንገት በቀስት የሰው ጊደር ወጋ። የጊደሩን ባለቤት ፈርቶ ከዐይን ተሰወረ። ሲፈለግ በመጥፋቱ ክርስትና አባቱ፣ የእህቱ ባል
ደጃዝማች ባስልዮስና የአካባቢው ነዋሪ በጭንቀት አካባቢውን አሰሱ::ሰፈርተኛው ሁሉ በደቦ ተከፋፍሎ ቀየውን፣ ወንዙንና ጫካውን ፈተሽ::ኢያሱ የውሃ ሽታ ሆነ። ሰዉ ተደናገጠ፣ የሚያደርገው ጠፋው። ብሎም
ኡኡታ፣ ለቅሶና ጩኸት በረከተ። ለንጉሠ ነገሥቱና ለምንትዋብ
እንዴት እንደሚነገራቸው ተመከረ።

ኢያሱ ከተደበቀበት ሲወጣ ዕልልታና ደስታ ጩኸትንና ለቅሶን
ተኩ። ማንነቱ ተደብቆ የኖረው ልጅ በዚህ አጋጣሚ ማንነቱ ታወቀ።

ደጃዝማች ባስልዮስ ግን የኢያሱ ማንነት መታወቁ አደገኛና አሳሳቢ
መሆኑን ተረድቶ በሐሳብ ማሰነ። አፄ በካፋ ጉዳዩን እንዲሰሙ አደረገ።ኢያሱም በፍጥነት ጐንደር እንዲመለስ ተደረገ። ምንትዋብ፣ እናቷና አያቷ የደስታና የእፎይታ እንባ አነቡ።

ምንትዋብ ሳትውል ሳታድር፣ ኢያሱ በተመረጡ አስተማሪዎች
ትምህርት እንዲማር አደረገች። የመንፈስ፣ የግብረገብ፣ የአካል ግንባታና የቤተመንግሥት ወግ ትምህርትም ላይ አተኮረች።
አፄ በካፋ ጠላቶቼ ይገድሉብኛል ብለው ስጋት ቢገባቸውም፣ ዝምታን ፈቀዱ። በሌላ በኩል ግን ከእሷ፣ ከእመቤት እንኰዬ፣ ከእመቤት ዮልያናና ከግራዝማች ኒቆላዎስ ጋር ብዙ ጊዜ ቆይታ መያዝ አዘወተሩ።

በተለይ ምንትዋብን፣ “አንቺ ብልህና አስተዋይ ስለ ሆንሽ እኔ ሳልኖር ኸልዤ ጋር ሁነሽ አገሬን ባግባቡ እንድትመሪ፣ እንድታስተዳድሪ።
የባሕር ማዶ አረመኔዎች አገሬ ገብተው እንዳይበጠብጡ፤ ሕዝቤንም በሃይማኖት ሆነ በሌላ እንዳይበክሉ ዐደራ” ይሏታል።

በነገሡ በዘጠነኛው ዓመት መጀመሪያ ላይ ጥቅምት ወር ውስጥ ግን፣
“ወዳጅ ዘመዴን እለያለሁ” በሚል ታመምኩ ብለው ሲደበቁ ምንትዋብ
ምሥጢር ጠበቀች። ወዲያው፣ “ንጉሡ ሊሞቱ ነው”፣ “ንጉሡ ሙተዋል” የሚል ወሬ ጐንደርን አወዛገባት። የጐንደር ከንቲባ ብላቴን ጌታ ኩቾ ከወህኒ አምባ ንጋሢ አመጣለሁ' ብሎ ሠራዊት አዘጋጀ። ወህኒ አምባዎች በበኩላቸው ወሬውን ሲሰሙ እኔ ልንገሥ፣ አንተ ንገሥ፣ የለም እሱ ይንገሥ ተባባሉ፤ ተመራረጡ፤ ተፎካከሩ።

ጐንደር እንደ ልማዷ ልትታመስ ሆነ።

በካፋ ይህን ሲሰሙ አለመታመማቸውን ለማሳየት ሐሙስ ቀን ደብረብርሃን ሥላሤ ሲሄዱ፣ መኳንንቱ በርቀት ከጋሻ ጃግሬዎች ኋላ በፈረስ ተከተሏቸው። ሕዝቡም ከየቤቱ እንደ ጎርፍ ፍንቅል ብሎ
ወጣ፡፡

በካፋ፣ ሕዝቡን፣ “ታዩኛላችሁና ወደየቤታችሁ ግቡ” ብለው አሰናበቱ።ሊቃውንት ንጉሠ ነገሥቱን በሕይወት በማየታቸው መሬት ሳሙ፤ካህናት ዘመሩ፤ ሕዝቡ ተደሰተ። ከረብሻ ዳነ። በካፋ ግን ብዙ ታዘቡ።
ወዳጅ መሳይ ሁሉ ከበስተጀርባቸው ምን እንደሚያስብ ተረዱ።

መኳንንቱን ወርቅ ሰቀላ ጠርተው፣ በአፈ ንጉሥ በኩል፣ “ምነው
ባካችሁ እንዳው ጥቂት ቀን ታምሜ ብተኛ ሽብር ማስነሳታችሁ? ስለምን ከተማዬን አስደነገጣችኋት? ሞተ ብላችሁ እንደዝኸ መሆናችሁ ተገቢ ነውን?” ሲሉ ጠየቋቸው። እንደማይተኙላቸውም ተረዱ። ሆኖም፣“እነዝኸ በልባቸው ክፋት የለም” ብለው ይቅርታ አደረጉላቸው።መሣሪያ ያነሳው ኩቾ ግን ከነተከታዮቹ ተይዞ ጊዜያዊ እስር ቤት ገብቶ ለፍርድ እንዲቀርብ ተወስኖበት ፍርድ ሸንጎ ቀረበ።

የሃገር ክህደት ወይም ሌላ ከፍተኛ ወንጀል ካልሆነ በስተቀር የዙፋን
ችሎት የማይዙት ንጉሠ ነገሥት፡ ጃን ተከል ተገኝተው ከምንትዋብ ጋር እንደወትሯቸው ቀይ ድባብ ተይዞላቸው፣ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ተቀመጡ።መሣፍንቱ፣ መኳንንቱና ሊቃውንቱ እንደየደረጃቸው ተሰየሙ። ፍትሐ ነገሥት ተርጓሚዎቹ፣ ፍርድ ሰጭዎቹና አዛዦቹ፣ ግራ ቀኝ ተችዎቹ
ሁሉ ተገኝተዋል። ዐራቱ ሊቃውንት ፍትሐ ነገሥት ይዘው ቦታቸው
ላይ ተቀመጡ። አቡኑ፣ ዐቃቤ ሰዐቱና መኳንንቱ የተለመደ ቦታቸው ላይ ሆኑ።

ኩቾና ተከታዮቹ እግራቸው በእግረ ሙቅ ታስሮ፣ ጋሻ ጃግሬዎች
ግራና ቀኝ እየጠበቋቸው በንጉሠ ነገሥቱ ትይዩ ቆሙ።ከአዛዦቹ አንደኛው፣ “ጠበቃ ኸፈለግህ ይፈቀድልኻል” አለው፣
ኩቾን።

“አያሻኝም።”

“እንግዲያማ ተጠየቅ።”

“ልጠየቅ!”

“አንድ ስጠይቅህ አንድ፣ ሁለት ስሰጥህ ሁለት መልስልኝ። ኸዝኽ
እንዳትዛነፍ በቅሎ ያግድህ። ጃንሆይ ትንሽ አሟቸው ሰንብተው
እንደነበር አልሰማህም?”

“ሰምቻለሁ።”

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ጃንሆይን አደባባይ ባታያቸው ሊሞቱ ነው ብለህ አላወራህም?”

“አላወራሁም።”

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ያለ ጃንሆይ ፈቃድ ሠራዊትህን ማንቀሳቀስ እንደማትችል
ታውቃለህ አታውቅም?”

“አውቃለሁ ።"

“ተጠየቅ!"

“ልጠየቅ!”

“ዛዲያ ስለምን ሠራዊትህን አንቀሳቅሰህ ለአመጥ ተነሳህ?”

“ለአመጥ አልተነሳሁም።”

“ምስክር ይጠራብህ?”

“ሠራዊት...”

"አንድ ስጠይቅህ አንድ፣ ሁለት ስሰጥህ ሁለት መልስልኝ ያልኩህን አጣርሰኻል። ለበቅሎ ዋስ ጥራ።”

“አላጣረስሁም።”

“አጣርሰኻል። ምስክር ይጠራብኝ ወይንም አይጠራብኝ ነበር
መልሱ።”

“ኸጥያቄህ አልወጣሁም። እማኞች ይጠሩልኝ” እያለ ወደ ሰዉ ተመለከተ ኩቾ።

“አጣርሷል! አጣርሷል! በቅሎዋን ይክፈል!” አለ፣ ሰዉ።

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ለአመጥ መሣሪያ አላነሳህም?”

“ራስ ተስፋ ኢየሱስና ቢትወደድ ስኩት ጃንሆይ ያስሩኻል ቢሉኝ
መሣሪያ አነሳሁ።”

“ተጠየቅ!”

“ልጠየቅ!”

“ምንም ሳታደርግ ጃንሆይ ስለምን ያስሩኻል? ሞተዋል ብለህ
ስላስወራህና ኸወህኒ ነጋሢ ልታመጣ ስለፈለግህ ነው እነራስ ተስፋ ኢየሱስ ያስሩኻል ያሉህ።”

ኩቾ ወደ እፄ በካፋ ተመለከተ። ሁለት እጆቹን ዘርግቶ፣ “ጃንሆይ
ይማሩኝ” ብሎ አጎነበሰ።

“ምትጠይቀው ጥያቄ አለ?” ሲል ጠየቀው አንደኛው አዛዥ ።

“የለኝም። ምሕረት ያርጉልኝ ጃንሆይ!” አለ፣ ኩቾ፣ አጎንብሶ።

ከአዛዦቹ አንደኛው ጋቢውን አስተካከለና ወደ ንጉሠ ነገሥቱ
ተመለከተ፣ “ጃንሆይ ኩቾ የቀረበበት ክስ ክህደት ነው። ክህደት ደሞ በሞት ያስቀጣል” አለ፣ ፍትሐ ነገሥቱን እያገላበጠ። “ፍታ ነገሥቱ ሚለው በንጉሥ ላይ ያመጠና ያሳመጠ በሞት ይቀጣ ነው።”

ይህን ዓይነቱ የሞት ብይን ይገባዋል አይገባውም፤ ወይንም ደግሞ ሌላ ቅጣት ይቀጣ ብለው ለመወሰን መኳንንት እንደየማዕረጋቸው እየቆሙ ከዝቅተኛው ጀምሮ እስከ ከፍተኛው ድረስ አስተያየት ሰጡ።

“ክህደት ነውና ሞት ይገባዋል!” አሉ፣ አንደኛው መኰንን።

“ግዞት ይላክ!” አሉ፣ ሌላው።

“በግርፋት ይቀየርለት!” ብለው ተቀመጡ፣ አንደኛው
“ጃንሆይ መሐሪ ናቸውና ምህረት ይደረግለትና ሹመቱን ይገፈፍ”
አሉ፣ ሌላኛው።

እንደዚህ እያለ ሁሉም ተናግረው ከጨረሱ በኋላ፣ የማሳረጊያው
ንግግር የንጉሠ ነገሥቱ በመሆኑ፣ አፈ ንጉሡ አጎንብሶ ጆሮውን
ሲሰጣቸው ሁሉም ለመስማት ጆሯቸውን ሲያቀኑ ኩቾና ተከታዮቹ
ትንፋሻቸውን ውጠው ተጠባበቁ። ይህን ሁሉ በአንክሮ የምትመለከተው ምንትዋብም ተጠባበቀች።
👍20🤩1
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

“ሺሕ ዓመት ንገሥ።"

ምንትዋብ፣ አፄ በካፋ ወደ መሠሪ እንድትመጣ ሲልኩባት፣ ሕይወቷ
ዳግም ተለወጠ። ለጥቂት ቀናት መሠሪ ሱባዔ ገብተው ስለነበር
ጨርሰው ነው ብላ አስባለች። ከእናቷና ከአያቷ ጋር መሠሪ ስትደርስ፣የበካፋ ታማኝ እልፍኝ አስከልካዮች ቴዎድሮስ፣ ገላስዮስና ድንጉዜ ዐይኖቻቸው ደም መስለዋል። እጅ ነስተዋት ስትገባ መሠሪ ከብዶታል፤
ጨላልሟል። ከወትሮው ጠባብ ሆኖባታል።

አፄ በካፋ ከተኙበት ኣልጋ ራስጌ የነፍስ አባታቸው አባ ዐደራ
መስቀላቸውን ይዘው ቆመዋል። ኒቆላዎስ ከንጉሠ ነገሥቱ ግርጌ
አቀርቅሮ ቆሟል። ምንትዋብ ርምጃዋን ገታ አድርጋ ክፍሉንም
ሰዎቹንም ቃኘች።

ነገሩ አላምር አላት። መንፈሷ ተረበሸ። ሱባዔ ላይ የነበሩት ባሏ ምን እንደደረሰባቸው መገመት አቃታት። ወደ አልጋቸው መራመድ ፈልጋ እግሮቿ አልታዘዝ አሏት፤ ትንፋሽ አጠራት። ልቧ ደረቷን ሲደልቅ እንደ ማጥወልወል አላት። ሐውልት ይመስል ደርቃ ቀረች። ዐይኗ ኒቆላዎስን ኣልፎ ንጉሠ ነገሥቱ ላይ ሲያርፍ፣ ፊታቸው ተሸፍኗል።

ዕለቱ ማክሰኞ፣ ቀኑ መስከረም አስራ ስድስት ዓመተ ምህረቱ 1723 ነው። እኒያ ቅኔ የሚቀኙት፣ መንፈሳዊ መጻሕፍትን የሚፈትሹት፣ አደን የሚወዱት፣ ለሃገራቸው ፊደላት ጥብቅና ቆመው፣ “ፊደል አሳስቶ የጻፈ
እጁ ይቆረጣል” ብለው አዋጅ የጣሉት፣ ሥነ-ጥበብ እንዲዳብር፣ ቃላት እንዲበለፅጉ የጣሩት፣ በወባ ንዳድ ርደው እንደተራ ሰው ባላባት ቤት መደብ ላይ የተኙት፣ ላይ ታች እያሉ ያመጸውን ያስገበሩት፣ ያጠፋውን አይቀጡ ቅጣት የቀጡት፣ እንደ ቀደምት ነገሥታት የሃይማኖት ክርክር
ያከራከሩትና አሻራቸውን ለመተው የራሳቸውን ግንብ የገነቡት አፄ
በካፋ በነገሠ በዘጠኝ ዓመት ከዐራት ወራቸው፣ ምንትዋብን ባገቡ በሰባት ዓመታቸውና በተወለዱ በሰላሳ ሰባት ዓመታቸው ሕይወታቸው
አልፏል።

“ምንድርነው? ጃንሆይ ምን ሁነዋል?” አለች፣ ምንትዋብ፣ ድምጾ ይርበተበታል ።
ተጠጋቻቸውና ቡሉኮውን ከፊታቸው ላይ ገለጥ አደረገችው።አፍንጫቸው ጫፍ ላይ ደም አየች፤ መላ ሰውነቷ ራደ። ኒቆላዎስ ላይ አፈጠጠች።

“ድንገት ነው የሆነው። ባፍ ባፍንጫቸው ደም ፈሰሰ... ምንም ያህል አልቆዩ ዐረፉ” አላት።

ራሷን በሁለት እጆቿ ይዛ “ኡኡኡኡ...” አለች። እናቷና አያቷ
ፈጠን ብለው ግራና ቀኝ ደገፏት።

“ምነው ሳትነግሩኝ? ስለምንስ ከፋችሁብኝ?” እያለች ጮኸች።
መሬት ላይ ተንከባለለች።

ያን ጊዜ እናቷና አያቷ አብረዋት ጮሁ። እንደ እሷ መሬት
ላይ ተንከባለሉ። መሠሪ ጩኸት በጩኸት ሆነ። ዋይታ በረከተ።
ምንትዋብ ለያዥ አስቸገረች። እነግራዝማች ኒቆላዎስ ተጨነቁ፡
ለቅሶው እንዳይሰማ። የቤተመንግሥት ባለሟሎች እንኳን እንዲሰሙ አልተፈለገም።

ምንትዋብ የምትሆነው ጠፋት። ከቶውንም የደረሰውን ማመን
አቃታት። አጎንብሳ፣ “ወዮ እኔ! ይብላኝ ለኔ” እያለች እንባዋን አዘራች።ኒቆላዎስና አባ ዐደራ ግራና ቀኝ እጆቿን ይዘው እንድትቀመጥ ግድግዳ ተጠግቶ ወደ ተቀመጠ ወንበር ሊወስዷት ሞከሩ።

“ተዉኝ... ተዉኝ! ለባሌ ላልቅስ።
ተዉኝ!” እያለች እሪ አለች።

“እቴጌ ባክዎ ለቅሶዎ እንዳይሰማ” አሏት፣ አባ ዐደራ።

“ይሰማ ይሰማ! አገር ይስማ! እኔ አለባል ልዤ አላባት መቅረታችንን...አገር ይስማ... ወዮ እኔ...ወዮ ልዢ ።”

እነኒቆላዎስ እንደ ምንም አባብለው አስቀመጧት። አንዴ ንጉሠ ነገሥቱ የተኙበትን አልጋ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጣራውን ደግሞም ወለሉን እያየች እንባዋ ረገፈ። ሐዘኗ መሪር ሆነ። የደረሰባትን ድንገተኛ ሐዘን
ጫንቃዋ መቋቋም የሚችል አልመስል አላት። ዓለም አስፈሪ ቦታ ሆነችባት። ሕይወቷ ላይ የሐዘን ጥላ አጠላችበት። የመኖር ተስፋዋን ሸረሽረችው። ትናንት ማሾ እያበራች ፈለጓን የተከተለችው መሬትም
ድንገት ጨለመችባት።

አልጋ ባልጋ የመጣው የሕይወቷ መንገድ ፍጻሜው የተቃረበ
መሰላት።

እንደገና ጩኸት ጀመረች። እነኒቆላዎስ ተደናገጡ። የእሷም
ሆነ የእናቷና የአያቷ ጩኸት እንዳይሰማ ፈሩ፤ ለማባበል ሞከሩ፤ አልሆነላቸውም። ምንትዋብን ብዙ ኃላፊነት እንደሚጠብቃት ኒቆላዎስ
ለማስረዳት ቢሞክር አልሰማ አለችው።

“ባሌ ኸሞቱ ገዳም ገብቸ መመንኮስ አለብኝ” አለችው።
እንባዋ ደረቷ ላይ ይወርዳል። ያቺ ፀዳል የመሰለች ሴት ፊቷ ድንገት
ጨለማ ለብሷል። ከመቅጽበት ዕድሜዋ ላይ ዓመታት የተጨመሩ
መስለዋል። ከዐይኗም ከአፍንጫዋም የሚወርደው ፈሳሽ አልቃሻ ሕፃን ልጅ አስመስሏታል።

ኒቆላዎስና አባ ዐደራ ተረበሹ። እናቷና አያቷ ለቅሷቸውን አቋርጠው በድንጋጤ ተመለከቷት።

“አዎ... ኸዝኸ በኋላ ምን ዓለም አለኝ? እኔም እንደ ባለቤቴ መሬት
እስትገባ ዓለሜ ምናኔ ነው። እሳቸው ሙተው እኔ እንዴት ባለም
ኖራለሁ? ልዤን ይዤ ኸዳለሁ” እያለች ጮኸች።

ኒቆላዎስ፣ “የለም የለም፤ እኼማ አይሆንም” አላት፣ ተጠግቷት።
“ደሞስ ምናኔ ማን ያደርስሻል? የጃንሆይ ጠላቶች ወይም ወህኒ
አምባ ያሉ ደጋፊዎች ምንገድ ላይ ጠብቀው አንቺንም ልዥሽንም
ይገድሏችኋል። ባይገድሏችሁ ስንኳ መውጫና መውረጃ የሌለው ወህኒ አምባ ወስደው ያስሯችኋል። ገዳም ብትገቢም ጃንሆይ ቅባት ሃይማኖት
ተከታይ ነበሩ ተብለው ስለሚጠረጠሩ እዚያ ብዙ የተዋሕዶ መነኩሴ ጠላቶች አሏቸው፤ ይጣሉሻል” አላት።

እሷ ግን፣ “በቁስቋሟ ተዉኝ! ተዉኝ” እያለች እጆቿን እያርገበገበች ተማጸነቻቸው።

ያን ጊዜ አባ ዐደራ፣ “እቴጌ መቸም መቀበል እንጂ ምን ማረግ ይቻላል? ኸሞት ሚቀር የለ። አሁን እርስዎ እንደዝኸ ሲሆኑ ሳንዘጋጅ የጃንሆይ መሞት የተሰማ እንደሁ ሁከት ይነሳል። ወህኒ ያሉትም እግረ ሙቃቸውን ፈተው ይመጣሉ። ንጉሥ ሞተ ሲባል ሚሆነውን እናውቃለን። ባክዎ ይጠንክሩልን” እያሉ ተለማመኗት።

ዮልያናም፣ “የኔ ልዥ! ባክሽ ጠንክሪ። እንደዝህ መሆን ደግ ማዶል” እያሉ እንባዋን በነጠላቸው ጠራረጉላት፣ የራሳቸውን ለመግታት
እየታገሉ።

“ልጄ በጡቴ ይዤሻለሁ! በኢያሱ ይዠሻለሁ! በምትወጃት በቁስቋም ማርያም ይዠሻለሁ! በምትወጃቸው ባባትሽ አጥንት ይሻለሁ በርቺልኝ” እያሉ እንኰዬም ሙሾ እንደሚያወርዱ ሁሉ እጃቸውን ወደ ኋላ አድርገው እንባቸውን እያዘሩ ለመኗት።

እሷ ግን እንባዋን መግታት አቃታት፤ አልጽናና አለች።

ኒቆላዎስ አንዴ እንድታዳምጠው ለምኗት የንጉሠ ነገሥቱን ኑዛዜ
ቃል በቃል ነገራት።

“ምን እንደተሰማቸው አላወቅሁም ብቻ እኔን አስጠሩኝ። ኒቆላዎስ...
ዐደራ ምልህ ልዤን... አሉኝ፣ ድምጣቸው እየተቆራረጠ። ልዤን
ኢያሱን እንድታነግሥልኝ። ለነገሥታት ሚደረገውን ሥርዐት ሁሉ... ቅባዓ ንጉሡንም ዘውዱንም... አርገህ እንዲነግሥልኝ። እናቱ ምንትዋብ
ብልህ ናት ትርዳው፤ ኸጎኑ ትሁን። እሷ አገር መምራትና... ማስተዳደር
ትችላለች። አርቆ አስተዋይና እዝጊሃር የባረካት ሰው ናት። አገሬን... አገሬን ኸልዣችን ጋር ሁና፣ ተባህር እስተ ባህር ታስተዳድር። አገሬ.. ምንም ዓይነት በደል እንዳይፈጠምባት። እኔ የዠመርሁትን ሁሉ. አጠናክረሽ ቀጥይ፤ በዐጸደ ነፍስ ኹኜም አልለይሽም በልልኝ። ሁላችሁም ቃሌን ንገሩልኝ…. ዐደራ” ብለው አንቺን እንድንጠራላቸው
ሲጠይቁ፤ ደም ባፍ ባፍንጫቸው ያለማቋረጥ ወረደ። ግዝየም አላገኙ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች።”

ምንትዋብ፣ ተናግሮ ሲጨርስ ሳግ እየተናነቃት ጣሪያውን፣
ግድግዳውን፣ ወለሉን፣ ሁሉንም በየተራ ተመለከተች። እነሱ ምን
እያሰበች እንደሆነ መገመት አቃታቸው። አንዴ እርስ በእርስ እየተያዩ ሌላ ጊዜ እሷን እያዩ ከአፉ የሚወጣውን ለመስማት ተጠባበቁ።
👍111
#ምንትዋብ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ምንትዋብ፣ ኢያሱ ራቱን እስኪበላና እስኪተኛ ጠብቃ እሷም በድንጋጤና በለቅሶ የደነዘዘ ሰውነቷን ለማሳረፍ ከጎኑ ጋደም አለች። አካሏ ዝሎ፣ መንፈሷ ረግቦ፣ እንቅልፍ በዐይኗ አልዞር አለ። አእምሮዋ በውስጡ ያለተራ ብቅ ጭልጥ የሚለውን የሐሳብ ውዥንብር መቆጣጠር ተሳነው። መላ የጠፋው አእምሮዋ ቢሰክንልኝ ብላ ከመኝታ ክፍሏ ወደ ሰገነቱ ከሚያወጡት ከሶስቱ በሮች በመካከለኛው በኩል አድርጋ ሰገነቱ ላይ ቆመች። ባሏም ብዙ ጊዜ በዛ በር እየወጡ፣ አንዳንዴም አብረው እየሆኑ ከተማውንና ግቢውን ይቃኙ ነበርና እንባ ተናነቃት።

ለሰባት ዓመታት ያህል ከእሳቸው ጋር ያሳለፈችውን ሕይወት
በሐሳቧ መለስ ብላ አየች። ንጉሠ ነገሥቱ እንደ ተራ ሰው እናት አባቷ
ቤት መደብ ላይ ተኝተው ያስታመመቻቸውን አስታወሰች። ምንትዋብ ብለው ስም ያወጡላት፣ “የኔ ዓለም” እያሉ ያቆላመጧት ሁሉ በየተራ ፊቷ ድቅን አሉባት። ምነው እንዲህ ዕድሜያቸውን አሳጠረባቸው?
አለችና ምርር ብላ አለቀሰች።

ከቤተመንግሥት ግቢ አሻግራ ጥቅጥቅ ባለው ጭለማ ውስጥ ጐንደርን ለማየት ሞከረች። ማታ ማታ ጐንደርን ያለ ከልካይ ከሚፈትሹት ጅቦች ሌላ የሚንቀሳቀስ ነገር የለም። አልፎ አልፎ ጅቦቹን ከሚያስፈራሩት
ውሾች ጩኸት በስተቀር ድምፅም አይሰማም።
ምንትዋብ ከጐንደር ወደ ራሷ ተመለሰች። ሕይወት ያልታሰበ
ፀጋ አምጥታላት መልሳ መንጠቋ ገረማት። የሕይወት መንገዶች
አለመጣጣማቸው ደነቃት። ሞት ሌላው የሕይወት ገፅታ መሆኑን
አሰበች። ሕይወት ምስጢሯን ያካፈለቻት መስሎ ተሰማት። ነገ እዛ ራሷ ረጋፊ መሆኗ በአእምሮዋ ተመላለሰና ዘገነናት። ለጊዜውም ቢሆን የመኖር ትርጉሙ ተናጋባት። የሙት ሚስት መሆኗ ወለል ብሎ
ታያት። ሞት ተስፋዋን ሁሉ ሸራረፈባት።

በዚያች ቅጽበት ሕይወቷ ዳግመኛ እንደተለወጠ ተረዳች።

መኝታ ክፍላቸው ስትገባ እንደገና እንባ አሸነፋት። ቤቱ የሚበላት፣
አልጋው ብቻዋን በመምጣቷ የሚታዘባት መሰላት። ለባሏ እንደሚገባቸው ያላዘነች፣ ያላነባች መስሎ ተሰማት። ቆም ብላ ክፍሉን ቃኘች። በርካታ
ትዝታዎች በአእምሮዋ ውስጥ ተመላለሱ። ወደ ኢያሱ ስትመለከት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ላይ ነው። ሆዷ ባባ። አባቱን ሲሰናበታቸው ምን ተሰምቶት እንደሆነ መገመት አቃታት። እመንናለሁ ብላ የእሱን ሕይወት አደጋ ልትጥል እንደነበር አስታወሰችና ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ተጠግታው ራሱን እያሻሸች፣ በዚች ምድር ላይ ካሉ ክፉ ነገሮች ሁሉ፣ከሞት ጭምር፣ ልትደብቀው እቅፏ ውስጥ ሽጉጥ አድርጋው ጋደም
አለች።

አእምሮዋ እረፍት አጥቶ እንቅልፍ በዐይኗ ሳይዞር ወፍ ተንጫጫ።
ተነስታ ወደ ሰገነቱ ወጣች። ሰማይና ምድር ገና አልተላቀቁም።
ጐንደርም ገና እንቅልፍ ላይ ናት። በቦዘዙ ዐይኖቿ ዙርያውን አየች።
የጠዋቱ ቅዝቃዜ ፊቷን ሲዳስሳት፣ ነቃ አለች።

አሻግራ ጐንደርን ወደከበቧት ተራሮች ተመለከተች። ፍም እሳት
የከበባት የምትመስለውን ፀሐይ ብቅ ስትል ስታይ የጥድፊያ ስሜት
ተሰማት። በመመርያ ኸዋና ዋናዎቹ ግቢ አዛዥና ኸሊጋባው፣
እንዲሁም ኸመሣፍንቱና ኸመኳንንቱ ጋር መክራለሁ። ጃንሆይ አገር አለ ምክር፣ ቤት አለ ማገር ይሉ ማልነበር? ኸዛ በኋላ፣ ኢያሱ በምሥጢር ይነግሣል። የልጄቼን አልጋማ ለማንም አሳልፌ አልሰጥም

ለካንስ እሷም መንገሷ ነው! ደነገጠች።

ይህ ሳይታሰብ እላይዋ ላይ የወደቀው ኃላፊነት ከየት እንደመጣ ማወቅ አቃታት። ሃገር ልታስተዳድር መሆኑ ሲገባት ታላቅ የኃላፊነት ስሜት ተጫጫናት፡፡ እሳቸው ያሰቡትን ሁሉ ሳያሳኩ አለፉ፤ እኔስ ብሆን መቸ እንደምሞት በምን አውቃለሁ? ሞት እንደሁ ለማንም አይመለስ፡ ብቻ እንዳው አንዴ የሳቸውን ቀብርና የልጄን ንግሥ
ያለምንም ሳንካ ላሳካ እያለች አእምሮዋ ውስጥ የሚወራጨውን ሐሳብ ሁሉ በየፈርጁ ማስቀመጥ ሞከረች።

ድንገት ክፉኛ የመንገሥ ፍላጎት አደረባት። ባሏ፣ “እሷ አገር
ማስተዳደር ትችላለች” ያሉት በከንቱ እንዳልሆነ፣
ስለቤተመንግሥትም ጉዳይ ቢሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት በቂ
እውቀት እንዳካበተች፣ በደጉ ጊዜ ቤተመንግሥት ውስጥ ቦታቸውን
ያመቻቸችላቸው የኒቆላዎስ፣ የወልደልዑል፣ የአርከሌድስና
የሌሎቹም መኖር ታላቅ ድጋፍ እንደሚሆናት ተረዳች። ኒቆላዎስ
እያረጀ በመምጣቱ፣ ወንድሟ ወልደልዑል ጉልህ ችሎታ በማሳየቱና ቤተመንግሥት ውስጥ የማይናቅ አስተዋጽኦም በማድረጉ ቀኝ እጇ ሊሆን እንደሚችል አመነች። ዐዲስ ማንነት ውስጧ ሲጠነሰስ ተሰማት።

ከፍተኛውን የሥልጣን ዕርከን ስትወጣ ታያት።

ልቧ መታ፤ መላ ሰውነቷ ተቅበጠበጠ። ዳግም የጥድፊያ ስሜት ተሰማት። ይህንን ዕድል ለማንም አሳልፋ ልትሰጥ እንደማትችልና የኢያሱን ሆነ የራሷን ንግሥ ለማስከበር በችሎታዋና ሥልጣንዋ ስር ያለውን ሁሉ ማድረግ እንዳለባት ለራሷ አስገነዘበች። አሁን ፊቷ ተደቅኖ
የሚታያት ምኞት ወይንም ተስፋ ሳይሆን በቅርብ ያለ፣ሊጨበጥ የሚችል በመሆኑና ከለቀቀችው፣ ካመነታች እዳው ለእሷ ብቻ ሳይሆን ለልጇ ጭምር በመሆኑ በአስቸኳይ እርምጃ መውሰድ
እንዳለባት ተረዳች።

እኔም ኢያሱም ኸነገሥን በኋላ፣ ኣመጥ እንዳይኖር ጥርጣሬ
አስወግጀ ሰዉ እኔ ላይ አመኔታ እንዲኖረው ማረግ አለብኝ። መቸም መልካም ሥራ ኸሠራሁና ጥሩ አርጌ ኻስተዳደርሁ ሰዉ ይደግፈኛል::እምነትም ይጥልብኛል አለች፣ ሞላ ባለ ልብ። ከሁን ታሪክ የምትሠራበት፣ ስሟን ካለፉት ነገሥታት ተርታ የምታሰልፍበት ወቅት
እንደተቃረበ አስተዋለች። ሃገሯ ታላቅ ጥንካሬ፣ ዘዴ፣ ቆራጥነትና
ቀናነት እንደምትጠብቅባት ተረዳች።

ከሐሳቧ ስትነቃ ምድር ለቋል፤ ጐንደር ብርሃን ለብሳለች፤ ነፍስ
ዘርታለች። ። ጐንደርን ለመጀመሪያ ጊዜ በተለየ ዐይን አየቻት። ጐንደር
ጐንደር! አለች፣ በለሆሳስ፡ ፊቷን እያዟዟረች ከተማዋን የከበቡትን
ሰንሰለታማ ተራራዎች ትክ ብላ አየቻቸው። በተፈጥሮዋ የጠላት
መከላከያ አላት አለች። እንደገና ከተማዋን ከላይ ወደታች ቃኘች።
ጐንደር... ያቺ የነገሥታቱ፣ የመሣፍንቱና የመኳንንቱ የትንቅንቅ ቦታ ሳትሆን የተለየች ጐንደር ሆና፣ እንባዋን ጠራርጋ ወጣ ገባ ስትል ታየቻት። የዕድል ማሳ ሆና እሷ ማሳው ላይ ስትዘራ ጐንደር ስታብብ፣ስታፈራ፣ ይበልጥ ገናና ስትሆን ታያት።

በራሷ አምሳል የቀረጸቻት ጐንደር ፊቷ ወለል አለች።

ጐንደርን በጃን ተከል በኩል ለማየት ወደ ላይኛው ሰገነት በደረጃ ወጣች። የሁሉ መኖሪያ፣ ሁሉን እንደ ሃይማኖቱ፣ እንደ ሙያውና እንደ ልማዱ የምታስተናግደውንና፣ መንፈሰ ለጋሷን ጐንደርን እንደ
ዐዲስ ወደደቻት፤ ከክፉ ልትታደጋት ፈቀደች። ምን ዓይነት ቦታ እንደሆነችና ሕዝቧም ምን ዓይነት እንደሆነ ይበልጥ ማወቅ ፈለገች።

ልክ በዛን ሰዐት የእሷም የጐንደርም ዕጣ የተለየ አቅጣጫ ያዘ።

እንዴ! አገሬ? አገሬስ? ጐንደር አላገር ትኖራለች እንዴ? አለች
ደረቷን እየመታች። አገሬ ውስጥ ሰላም አምጥቸ እኼ ነው ምኞቴ
አለች፣ ባሏ የነበረባቸውን ዓመጽ አስባ። ሃገሯን ልትታደጋት፣
ልታረጋጋት፣ ሰላም ልታሰፍንባት ወሰነች።

የደብረብርሃን ሥላሤ ደወል ሲደወል ከሐሳቧ ነቃች፣ ተረበሸች።

ደወሉ ለአባታቸው ለአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ ከሆላንድ ንጉሥ
የተላከ ነበርና ንጉሠ ነገሥቱ ደወሉን ሲሰሙ ከእንቅልፋቸው ብንን ብለው ሲያማትቡ፣ ተነሥተው ዳዊታቸውንና ውዳሴ ማርያማቸውን ሲደግሙ ፊቷ ላይ ድቅን አለ። አየ ያ ሁሉ ቀረ አለችና እንባዋን ጠራረገች።
👍132
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

.....ጐንደርን እንዴት አርጌ ኑሯል ጥዬ ለመኸድ፣ ጭራሹንም ልመንን አስቤ የነበረው? አገሬንስ ለማን ጥየ ነበር ገዳም ልገባ ያሰብሁት? አልኸድም፣ አገሬን እታደጋታለሁ አለች።

ምን ያህል እዚያ እንደቆመች አላወቀችም። ፀሐይዋን ስታያት ሞቅ ብላለች። እስቲ ለዝኸ ከባድ ቀን ልዘገጃጅ ብላ ወደታች ወረደች።

ተዘጋጅታ ስትጨርስ፣ ቤተሰቧን አስከትላ ወደ አሸዋ ግንብ ሄደች።
የተጠሩት መሣፍንት፣ መኳንንት፣ አቡኑ፣ ዕጨጌውና ዐቃቤ ሰዐቱ
ሲገቡ የተጠሩበትን ምክንያት መገመት አልቻሉም። እሷ ምንም
እንዳልተፈጠረ ተረጋግታ ተቀምጣለች። እነሱ ንጉሠ ነገሥቱ ከአሁን አሁን ይመጣሉ በማለት በር በሩን ይመለከታሉ። በመጨረሻም ግራዝማች ኒቆላዎስ ከተቀመጠበት ተነሥቶ በመሃከላቸው ሲቆም ፀጥታ ሰፈነ። የሁሉ ዐይን ወደ እሱ ሆነ። ቀደም ብሎ ምንትዋብ
የነገረችውን መልዕክት አስተላለፈ።

ክቡራን ሆይ! ለእናንተ ሚደርስ መልክት ኸጃንሆይ ይዠ እናንተ
ዘንድ ቀርቤአለሁ። ልዤን ኢያሱን አንግሡልኝ፤ ይቀመጥ በወንበሬ፣
ይናገር በከንፈሬ፣ ይፍረድ - ይዳኝ ላገሬ። እኔ መንኩሻለሁ፤ ገዳም
ኸጃለሁ። አልመለስም። ሁሉንም ነገር እንደሚገባ አርጉ” ብለዋል
አላቸው።

ያልታሰበ ዜና በመሆኑ ሁሉም ተደናገጡ። ንጉሠ ነገሥቱ የሞቱ
የመሰላቸውም አልጠፉ። ያንን የሚያመላክት ነገር ግን ባለማየታቸው ግራ ተጋቡ። በእውነትም መንኩሰው ይሆናል ብለው ያመኑት የንጉሠ ነገሥቱን ጥልቅ ሃይማኖተኝነት ስለሚያውቁ ለማመን ብዙም አልተቸገሩ። አባታቸው ታላቁ ኢያሱ እንደዚሁ በመጨረሻ ዘመነ ንግሥናቸው፣ “እስተ መቸ ድረስ በሥጋዊ ባሕር ጠልቄ፣ ተጨንቄ ኖራለሁ” ብለው ጣና ገዳም ገብተው ስለነበር፣ ልጅየውም የአባታቸውን
ፈለግ መከተላቸው እምብዛም የሚያጠራጥር አልሆነባቸውም።

ባንድ ቃል፣ “ይበጅ! ይበጅ! ግድ የለም፤ እኼ ፈቃደ እዝጊሃር ነው”
ብለው ተበተኑ።

ምንትዋብ ብላቴን ጌታ ዳዊትና ሻለቃ ወረኛን ከሙስሊም
ነፍጠኞችና ከፎገራ የዘዌና የቱለማ መሪዎች ጋር በመሆን በፍጥነት ሄደው ወህኒ አምባን በጥብቅ እንዲጠብቁ ትዕዛዝ ሰጠች፤ መሣሪያም
እንዲሰጣቸው አዘዘች።

ለኒቆላዎስ፣ “ከካህናቱም ኢያሱን ቀብተው እንዲያነግሡ ሊቁን
ጽራግ ማሰሬ ማሞን፣ ቄስ እልፍዮስንና ሁለቱን ጸሐፍተ ትዕዛዝ...” እያለች የንግሥ ሥርዐት የሚፈጽሙትንና ሌሎች መገኘት አለባቸው ብላ ያሰበቻቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ሰጠችው። ግራዝማች ኒቆላዎስ መልዕክቱን እጅ ነስቶ ተቀበለ።
ሐሙስ ሌሊት ግራዝማች ኒቆላዎስ፣ አፈ ንጉሥ ኢዮብና አዛዥ ባለሟሎች ዐይን ለመሸሸግ ሻሸና በተባለው የስርቆሽ መንገድ የንግሥ አርከሌድስ ምንትዋብን፣ ኢያሱን፣ ዮልያናንና እንኰዬን ከቤተመንግሥት ሥርዐት ወደሚፈፀምበት ወደ መናገሻ ግንብ ወሰዷቸው። መናገሻ ውስጥ በአፄ በካፋ ጽራግ ማሰሬነት ማዕረግ የተሾሙትንና ቤተመንግሥት ተቀማጭ የሆኑትን ንጉሥ አንጋሹ መነኩሴ ማሞ፣ ቡራኬ ሰጪው
ቄስ እልፍዮስ፣ የመናገሻ ግንብ አጋፋሪዎች አቡሊዲስ፣ ገላውዲዎስ፣ አደሩና ሌሎችም ባሉበት ምንትዋብ ዙፋን ላይ ስትቀመጥ ኢያሱ እግሯ ሥር ተቀመጠ። ኢያሱ ነገሩ እምብዛም ባይገባውም አባቱ እንደሞቱና ሊነግሥ መሆኑ ስለተነገረው የንግሥናው ደስታ ሳይሆን
የአባቱ ሞት ሐዘን ፊቱ ላይ ይታያል።

የንግሥ ሥርዐቱን ለመጀመር በጅሮንድ አብርሃም ዘውዱን ለጽራግ ማሰሬ ማሞ አቀረቡ። ጽራግ ማሰሬ ማሞም ዘውዱን አፄ በካፋ ዙፋን ላይ አስቀመጡ። ንጉሥ ሲነግሥ የሚጸለየውን ጸሎት ጸለዩ።ከመዝሙረ ዳዊት፣ ከብሉያትና ከሐዲስ ኪዳንም የተመረጡ ምንባቦችን አነበቡ። አቡነ ዘበሰማያትም ደገሙ። ኢያሱን ወደ እሳቸው አምጥተው
እጃቸውን አናቱ ላይ አስቀምጠው በአንብሮተ እድ ባረኩት፣ ጸለዩለት፡-

“አቤቱ ፍርድህን ለንጉሡ ስጠው
እውነትኸንም ለንጉሡ ልጅ
ሕዝብኸን በእውነት ይፈርድላቸው ዘንድ
ድኾችኸንም በፍትሕ ይገዛ ዘንድ
አድባር አውጋሩ የሕዝብኸን ሰላም ይቀበሉ።
ከዚያም መከሩት፣
ኰንን በጽድቅ ነዳያነ ሕዝበከ
ወአድኅኖሙ ለደቂቀ ምስኪናኒከ
ወአሕስሮ ለዕቡይ
ተስፋም ሰጡት፡-
በዘመኑ እውነት ይሠርጻል
ከባሕር እስከ ባሕርም ይገዛል
ከወንዞችም እስከ ዓለም ጥጋጥግ
ኢትዮጵያ ይገዙለታል
ጠላቶቹ ግን አፈር ይበላሉ።”

ከዚህና ከበርካታ ሌሎች ጸሎቶች በኋላ፣ በዕንቁ ያጌጠውን የአባቱን
ዘውድ ራሱ ላይ ደፉለት፣ በአባቱ ዙፋንም ላይ አስቀመጡት። ከዚያም የጫነው ዘውድ ለጌጥ የተሠራ ሳይሆን የሕዝቡን ችግርና መከራ የሚሸከምላቸው መሆኑን የሚዘክር፣ ንጉሣቸውና አገልጋያቸው መሆኑን
የሚያሳስብ እንደሆነ ተናግረው መረቁት፡ አስመረቁት፡-

“ሺሕ ዓመት ንገሥ

ወንድ ልጅ ለፈረስ፣ ሴት ልጅ ለበርኖስ አድርስ።”
አሉት፤ በዚያው የተሰበሰው ሕዝብም ይህንን ሦስት ጊዜ መላልሰው በአንድ ድምጽ አስተጋቡ።

“ዳዊት ቤት ቀርነ መድኃኒት የሆነ ንጉሥ ስላነሳልን እግዚአብሔር
ይመስገን፤” አሉ፣ ጽራግ ማሰሬ ማሞ።

ኢያሱ ዳግማዊ ኢያሱ ንጉሠ ነገሥት ተብሎ ነገሠ።

ጽራግ ማሰሬ ማሞ ዙፋኑ ስር ተንበርክከው ሰገዱለት። በዓሉ ላይ ተገኝቶ የነበረው ሁሉ ተነስቶ ለሰባት ዓመቱ ልጅ ለኢያሱ ሰገደ።

በተራው ንጉሥ ባራኪው እልፍዮስ ወደ ኢያሱ ተጠግተው የብዙ
ታላላቅ ነገሥታት ነብያትና ታላላቅ ነገስታት በረከት እንዲያድርበት መረቁት።
“የቅዱስ ዳዊት በረከት ይደርብህ። የጠቢቡ ሰለሞን ፍትሕና ጥበብ አይለይህ። የኢዮሲያስ፣ የሕዝቅያስና የቆስጠንጢኖስ በረከት ይደርብህ”እያሉ ባረኩት። በመጨረሻም ለኢያሱ ዳግመኛ ሰግደው ወደነበሩበት ተመለሱ። ዘውዱ ለትንሹ ኢያሱ ከባድ በመሆኑ ጽራግ ማሰሬ ማሞ
ከራሱ ላይ አንስተውለት በክብር ጠረጴዛው ላይ አኖሩት::

ምንትዋብ ከተቀመጠችበት ተነስታ እጆቿን ዘርግታ፣ “እኔን
ታናሺቱን ለዝኸ ክብር ላበቃኝ እዝጊሃር ምስጋና ይግባው። ፈጣሪዬ ሆይ ለኔ ለባርያህ በንጉሡ በአባቱ በአጤ በካፋ ዙፋን ላይ መቀመጥ ዘር
ስለሰጠኸኝ ክብር ምስጋና ይግባህ” ብላ ምስጋና አቀረበች። በኋላም ኢያሱን ላነገሠው ለጽራግ ማሰሬ ማሞ፣ ለአንጋሽ እንደሚደረገው አስር ሰቅለ ወርቅ እንዲሰጥ ትዕዛዝ አስተላለፈች።

ትውፊቱን ጥሳ፣ የልጇ ንግሥ ላይ ባሏን ያነገሡት አቡነ ክርስቶዶሌ
ተገኝተው ዘውድ እንዲጭኑለት እንኳን ሳታደርግ፣ መፈጸም ያለባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች ብቻ ፈጽማ የኢያሱ የንግሥ ሥርዐት በምሥጢር ያለአንዳች ኮሽታ ተጠናቀቀ።

ወዲያው ባሻ ኤልያስን አስጠርታ፣ ሲነጋ የንጉሠ ነገሥቱ ሕልፈትና
የኢያሱ መንገሥ እንዲታወጅና ለንጉሥ ቀብር የሚደረገውን ሥርዐት ሁሉ እንዲያደርግ አዘዘችው። እጅ ነስቶ ሄደ።
ጠዋት ላይ፣ በታዘዙት መሠረት እነባሻ ኤልያስ ድብ አንበሳ ይዘው
ወደ ጃን ተከል ወረዱ። ሊጋባው፣ ከአዛዡ በተቀበለው ትዕዛዝ መሠረት ነጋሪት እየጎሰመ፣ “አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ! የሞትንም እኛ፣ ያለንም እኛ ንጉሥ በካፋ ዐርፈዋል። ልጃቸው ኢያሱ ነግሠዋል፣ የሰማ ላልሰማ
ያሰማ። ጠላቶቻችን ይፈሩ፤ ወዳጆቻችን ትፍሥሕት ያድርጉ፣ ባለህበት እርጋ፤ ነጋዴም ነግድ፤ ገበሬም እረስ!” እያለ አዋጅ ነገረ።

ጐንደሬዎች ግልብጥ ብለው ወጡ። “ይበጅ! ይበጅ! ያድርግ!”
አሉ። በኢያሱ መንገሥ ተደሰቱ፤ እምብዛም ባይወዷቸውም ለበካፋም አለቀሱ።
👍131
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

... አየ ወለቴ ጠጋ ብየ ባጥናናሁሽ፡፡ እኔ አልረሳሁሽም። የሩቅ ቅርብ ሁኜ ስላንቺ አስባለሁ። ምንግዝየም ኸልቤ አትጠፊም አለ።..

ከለቅሶው በኋላ፣ ሕዝቡ ወደ መኻል ግንብ ለስንብት ሲሄድ አብሮ ሄደ። በግርግሩ መሃል ከነአብርሃ ጋር በመጠፋፋቱ፣ ከተሰናዳው የእዝን ግብር ከሕዝቡ ጋር መካፈል ሆዱ እንቢ ብሎት፣ በሰዎች ተከልሎ ምንትዋብና ኢያሱን እጅ ነስቶ አልፎ ወርቄ ቤት ሄዶ ውጭ ተቀምጦ ጠበቃቸው።

እነወርቄ እንደተመለሱ፣ አብርሃ ለብቻው ከተፍ አለ። “የት ኸዳችሁ
ነው የተጠፋፋን? ወዲህ ብል ወዲያ ብል አጣኋችሁ” አላቸው።

ሁሉም የነበሩበትን ቦታ ከተነጋገሩ በኋላ፣ ውስጥ ገብተው ወርቄ
ምሳ አቀረበች። በልተው ሲጨርሱ፣ ጠላ እየተጎነጩ ስለ ቀኑ ውሎ ማውጋት ጀመሩ።

“መቼም ሰዉ ሁሉ ሚያወራው ስለ እቴጌ ጥንካሬ ነው” አለ፣
አብርሃ። “ቀብሩን ሆነ የቅጥር ልቅሶውን እንዴት አርገው እንዳዘጋጁት ይገርማል ። ባላባቱ፣ ካህናቱና ሊቃውንቱ፣ “በርግጥም በካፋ አልሞቱም ሲሉ ነበር አሉ” አላቸው።

ጥላዬ ዝም አለ። ምንትዋብ በልጅነቷ ባሏን በማጣቷ ጉዳቷ
ተሰምቶታል። አጠገቧ ሆኖ ሊያጽናናት ባይችልም፣ ደብረ ወርቅ መመለስ ከብዶታል። በሩቅም ቢሆን ሐዘኗን መካፈል መርጧል።ምንም ቢሆን ወለቴ እኮ አብሮ አደጌ ናት። ኑሯችን እየቅል ቢሆንም በዕዘኗ ሆነ በደስታዋ የሩቅ ቅርብ ሁኜ መካፈል አለብኝ አለ፣ ለራሱ።

በሌላ በኩል አለቃ ሔኖክን ደግሞ ሳያያቸው ማረፋቸው አሳዘነው።
ደብረ ወርቅ በነበረበት ወቅት ስለእሳቸው ሲያስብ፣ የተማረውን ሁሉ ሊያወራቸው ሲመኝ ቆይቶ፣ እንደ አባት የሚያያቸውን መምህሩን ሞት ስለነጠቀው ከፋው። በሌላ በኩል ወርቄ ወላጆቿ መጥተውላት አጠገቧ
በመሆናቸው ደስ አለው። አርባቸውን ሳላወጣ አልኸድም አለ፣ ለራሱ።

ወርቄ፣ ሐሳብ ውስጥ እንደገባ አስተዋለች። ደብረ ወርቅ እስኪመለስ ድረስ የቀድሞ ቤቱ መክረም እንደሚችል ነገረችው።
አብርሃ፣ ጥላዬን ከስድስት ዓመት በኋላ፣ በማግኘቱ ደስታው መጠን
አጥቶ ነበርና፣ “ኸኔ ዘንድ ይቆያል” አላት።

እኔማ ያው ቤቱ አለ ብየ እንጂ” አለች ወርቄ፣ ጥላዬን እያየች።
“ኸብረሃም ዘንድ እየተጫወትን እንከርማለን። ኸናንተም አልለይም።አልሰማሁ ሁኘ አለቃን ሳልቀብራቸው ቀርቸ እኼው ዛሬ እንጉሥ ለቅሶ ለመድረስ በቃሁ። እንዳው አለቃን ከዛሬ ነገ አያቸዋለሁ ስል አመለጡኝ” አላት።

ወርቄ በዐይኗ ውሃ ሞላ።

“ተይ ልዤ ጠሐይ ላይ ውለሽ መጥተሽ። መቀበል ነው እንጂ ሌላ ምን ማረግ ይቻላል?” አሏት እናቷ።

አብርሃ፣ ትኩር ብሎ አያትና፣ “የአለቃ ሞት ሁላችንንም ነው የጎዳ።መጥናናት ነው እንጂ ሌላ ምን እናረጋለን። ሞት እንደሁ ያለ ነው” አላት።

“የአለቃን ነፍስ በገነት ያኑርልን። የጃንሆይንም ነፍስ እዝጊሃር
ይማር” አሉ፣ የወርቄ አባት።

“አሜን” አሉ፣ ሁለም።

“እቴጌም ቢሆኑ አሳዘኑኝ በልዥነታቸው ባላቸውን አጥተው። ዕጣ ፈንታቸው እንደኔ የሙት ሚስት መሆኑ ያሳዝናል” አለች ወርቄ ለምንትዋብም ለራሷም በማዘን።

ሁሉም አንገታቸውን ደፍተው ዝም አሉ።

አብርሃ፣ እኔማ ትምርቱስ እንዴት ሁኖለት ይሆን እያልሁ ሳስብ”
አለው ጥላዬን፣ ቤቱን የከበበውን የትካዜ ድባብ ለመቀየር።

“ትምርቱማ... ያው ኸዝኽ አንድ ዓመት አርጌ ማልነበር ወደ ደብረ
ወርቅ ማርያም የኸድሁት? ኸዛ ያገኘዃቸው መምህር... ሊቀጠበብት አዳሙ እንዴት ያሉ ሰው መሰሉህ። አለቃ ሔኖክ እሳቸው ዘንድ ስለላኩኝ እንዳመሰገንዃቸው አለሁ። ያው... ኸዝኸ እንደኸድሁ ሥጋ
ለባሾችን ሠራሁ።”

“ሰዎችን ማለቱ ነው” ሲል አብራራ አብርሃ፣ የወርቄ ወላጆች ግር
ሲላቸው አይቶ።

“ቤተስኪያን አካባቢ ያሉ ቀሳውስት፣ መነኮሳት... መምህር
የመሳሰሉትን ማለቴ ነው” አለ፣ ጥላዬ። “ታስታውሳለህ አለቃ ሔኖክ...ነፍሳቸውን ይማርና... ስዠምር ጥቁር ቀለም ብቻ ነው ምትጠቀመው ሲለኝ? ኋላ ሌሎች ዓይነት ቀለሞችም ተጠቅሜያለሁ።”

“ራስህ እያዘጋጀህ?"

ኋላ! ራስህ ነህ እንጂ ሌላ ማን ያዘጋጅልሀል? እና ... የቤተክህነት
ሰዎችን ስትሥል፣ የልብሳቸውን ሆነ የካባቸውን ቀለም አሳምረህ
ትሠራለህ። ጥምጥማቸውንም እንዲሁ ትክክል አርገህ ትሥላለህ። ንድፉ እንዳይንጋደድብህም ትጠነቃቃለህ። የልብሳቸውንና የካባቸውንም ዕጥፋት ሳይቀር ነው በጥንቃቄ ምትሠራው።”

“ስንታቸውን ሣልህ በል?”

“ምን አለፋህ ብዙዎቹን ሥያለሁ። የዠመርሁት በአንድ መነኩሴ
ነበር። መነኩሴው ሲያዩት ደስ አላቸው። ማስታወሻ ብየ ሰጠኋቸው።ሁለተኛ ሊቀጠበብት አዳሙን ነበር የሣልሁት። እሳቸውም እንደዝሁ ደስ አላቸው። እንዲህ እያልሁ ወደሚቀጥለው ተሻገርሁ።”

“ምን ሠራህ?”

“ጻድቃንን ሣልሁ። አቡነ ተክለሃይማኖትን፣ ቅዱስ ያሬድን፣ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስን፣ አቡነ ኪሮስን፣ እናታችንን ክርስቶስ ሣምራን የመሰሉትን ሣልሁ።”

“የሁሉን መልክ አውቃችሁ ነው ምትሥሉ?” ሲሉ ጣልቃ ገቡ፣
የወርቄ አባት።

“የለ... የለ... እነሱን ስንሥል መልካቸውን ስለማናውቅ... የተሰወሩ ስላለባቸውም ... ታሪካቸውን፣ ታምራቸውንና ገድላቸውን ጠንቅቀን
አውቀን ነው ምንሥል። እነሱን ለመሣል ኸመነሣታችን በፊት
ታሪካቸውንና ገድላቸውን ለማወቅ ንባብ አድርገን ነው ምንሥላቸው።
ሥጋ ወደሙን ተቀብለን ስንሠራ ደሞ ትክክለኛ መልካቸው
ይገለጥልናል” አላቸው፣ ጥላዬ።

“እህ” አሉ የወርቄ አባት፣ እንደገባቸው ለማሳወቅ ራሳቸውን
እየነቀነቁ።
“እንደ ቅኔ ነው በለኛ! እኛም እኮ ክብረ ነገሥት፣ ገድላት፣ ድርሳናት
ወንጌል... መጽሐፍ ቅዱስ... ኻላወቅን ቅኔ አንቆጥርም” አለው
አብርሃ።
“አውቀው የለ። ደሞ ሰማዕታትን ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ እንደ መርቆርዮርስና ገላውዲዮስ የመሳሰሉትን ሣልሁ። ሰማዕታት ቤተክሲያን ውስጥ ሲሣሉ በግራ በኩል ነው ሚሣሉ። ሁሉም ሚሣሉበት ቦታ ቦታ አላቸው። ሚሣሉበት ቀለምም እንደዝሁ ይለያያል። ሰማዕታት ለጌታችን ለክርስቶስ ፍቅር ሲሉ፣ ስለአዳኝነቱ ሲመሰክሩ አንገታቸው
በሠይፍ ተቀልቶ፣ ወይ ከእሳት እቶን ተጥለው ማዶል የሞቱት? እናም ያነን ያፈሰሱትን ደም ለመዘከር በቀይ ቀለም ይሣላሉ። መላዕክት የመንፈስ ቅዱስ ሕይወት በነሱ ላይ ስላደረ... ብርሃንና ተስፋ ሰጪዐስለሆኑ፣ እነሱን ለመሣል ምትጠቀመው ቀለም ደማቅ መሆን አለበት።
ደማቅ ቀለም የተስፋ ምልክት ነው። ጻድቃን.. ይኸን ዓለም ንቀው በጽድቅ ኖረው ያለፉ አባቶቻችን ደሞ ፈዘዝ ባለ ቀለም ይሣላሉ።ድንግል ማርያም ደሞ ልብሷ ከላይ በሰማያዊ፣ ከውስጥ በቀይና ምትከናነበው ደሞ በአረንጓዴ ቀለሞች ይሣላል። ምትሥለው ሥዕል
እንደ ተሣዩ ማንነትና ታሪክ ምትመርጠው ቀለም ይለያያል። ሰማያዊ መንፈሳዊ ንፅህናን ያሳያል፤ ነጭ እንደምታውቀው ብርሃን ነው፤ ብጫ
ደሞ የዠግንነት ምልክት ነው።”

“ዘይገርም!” አለ፣ አብርሃ።

“ምን አለፋህ መላዕክትን... ሰባቱን ሊቃነ መላዕክት... እነቅዱስ ገብርኤልንም ሣልሁ” ሲል ቀጠለ ጥላዬ። “መላዕክት እንደምታውቀው መከሠቻ አላቸው። ሚከሠቱበት መንገድም ይለያያል...”
“መከሠቻ?” አሉ፣ ሁሉን በጥሞና ሲያዳምጡ የቆዩት የወርቄ እናት።
“ኣዎ መገለጫ ማለቴ ነው።”
“እንዴት እንዴት ሁነው ነው ሚገለጡ?”
👍11
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

“ይደልዎ ይደልዎ”

ምንትዋብ፣ ኢያሱ በነገሠ በሁለተኛው ወር ረጅም ነጭ ሐር ቀሚስ ለብሳ፣ በወርቅና በዕንቁ የተንቆጠቆጠ ካባ በላዩ ላይ ደርባ፣ በወርቅ አጊጣ፣ ፊቷን በነጭ ዐይነ ርግብ ከልላ፣ የወርቅ በትረ መንግሥት ጨብጣና ከወርቅ የተሠራ ነጠላ ጫማ ተጫምታ ተሸልማ በወጣችው
በቅሎዋ ላይ ተሰይማ፣ የንግሥ ሥርዐት ወደሚፈጸምበት ወደ መናገሻ ግንብ አመራች።

መናገሻ ግንብ ውስጥ መሣፍንት፣ መኳንንት፣ አዛዦች፣ ካህናት፣ ሊቃውንትና ወይዛዝርት
እንደየማዕረጋቸው ቦታቸውን ይዘው የንጉሥ መሞት የሚያመጣውን ቀውስ ጠንቅቃ
የምታውቀው ምንትዋብ፣ አክሱም ጽዮን የሚደረገውን ሁለተኛውን
የኢያሱን የንግሥ ሥርዐት አስቀርታ በነገሠ በወሩ ብርሃን ሰገድ የሚል ስመ መንግሥት ከተሰጠው ከዳግማዊ ኢያሱና ከቤተሰቦቿ ጋር ስትገባ ሁሉ ተነሥቶ እጅ ነሳ።

በወርቅ ያጌጠውን የአባቱን ዘውድ የጫነውና የእሳቸውን የወርቅ
በትረ መንግሥት የጨበጠው ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ከተቀመጠበት ተነስቶ፣ “እናቴን አንግሡልኝ፣ መንግሥቴ ያለሷ አይጠናም” ሲል ተሰብሳቢዎቹ፣ “ይደልዎ ይደልዎ! ይገባታል! ይገባታል! ጎበዝ ክርስቲያን፣ አዋቂ ናት። ሽህ ዓመት ንገሥ። የቆስጦንጢኖስን ምሽት
እሌኒን ትመስላታለች” አሉ።
አንጋሹ ጽራግ ማሰሬ ማሞ ከዕንቁ፣ ከወርቅና ከብር የተሠራውንና በሻሽ ተሸፍኖ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠውን የአፄ ሚናስ የነበረውን ዘውድ አንስተው ምንትዋብ ራስ ላይ ጭነውላት ሲያበቁ ዝቅ ብለው ሰገዱላት፣ ከኢያሱ ቀኝም አስቀመጧት።

ባራኪው እልፍዮስ፣ “እዝጊሃር ክፉዎችን እንዲያሸንፉ ኃይል ይስጥዎ። ክብርዎን ያብዛልዎ። ፈሪሐ እዝጊሃርን በልብዎ ያሳድርልዎ። አቤቱ አምላካችን ሆይ! በአገልጋይህ በእቴጌ ምንትዋብ ላይ እኼን የደስታና
የክብር ዘውድ አኑር፤ እኼውም የቸርነት፣ የርህራሄ፣ የዕውቀትና የጥበብ ዘውድ ይሁንላቸው” ብሎ ሲባርካት፣ ከኋላዋ ቆመው የነበሩት ሴት የመሣፍንት ዘሮችና ወይዛዝርት ዕልልታውን አቀለጡት።

ምንትዋብ ለአምላኳ በልቧ ምስጋና አቀረበች።

ካህናት ዘመሩ፣ ወረቡ፣ ሊቃውንቱ ቅኔ አወረዱ። እንደ ንግሥተ
ሳባ፣ እቴጌ እሌኒ፣ እቴጌ ሰብለወንጌልና እቴጌ መስቀል ክብራን የመሳሰሉ የታላላቅ ሴቶች ስም እየጠቀሱ አሞካሿት። “አንቺ እሌኒ ማለት ነሽ። ልዥሸን ብርሃን ሰገድ ኢያሱን ኸጎኑ ሁነሽ እንደምትረጂው አንጠራጠርም” ሲሉ እሷ ላይ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገለፁላት።
ምንትዋብ፣ አባቷ ዕጣ ፈንታ፣ እናቷ ዕድል አያቷ ግን የተገባት ያሉትን ስትጎናፀፍ ተስተዋለ።

ሕይወት ሲሻት ለጋሥ መሆኗን አስመሰከረች።

ባለ ክራሩና ባለ መሰንቆው የውዳሴና የሙገሳ ግጥም ሲያንቆረቁር፣ፎካሪው በቀረርቶ፣ ሽላዩ በሽለላ የበኩሉን ምስጋና አበረከተ። አንዱ ሀሚና ተነሰቶ በመሰንቆ፣

በወለተጴጥሮስ ተወልዳ በንግርት፣

በእዝጊሄር ፈቃድ በነብያት ትንቢት፤

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ያገራችን ውበት፤

የምታስተባብር ጥድቅ ተሃይማኖት፣

ዳር ድንበር ጠባቂ ያባቶቿን ርስት፣

ኸዝኸ በላይ ጠጋ ኻአምላክ መሰጠት፣

ምንድን ሊሰጧት ነው ምንትዋብ ሚሏት?

እያለ ሲያሞግሳት፣ የተሰበሰበው ሰው ደግሞ እሱን አመሰገነው።
ነጋሪት እየተጎሰመ፣ መለከት እየተነፋ ከመናገሻ ግንብ በደጅ
አጋፋሪው አቀናባሪነት የፊቱን ወጀብ ሰንደቅ የያዙ፣ የእልፍኝ አሽከሮች፣ባለሟሎችና ሠይፈ ጃግሬዎች ፈንጠር ብለው እየመሩ፣ የመሃል ዐጀቡ
በእልፍኝ አስከልካዩ እየተጠበቀ፣ ኢያሱና ምንትዋብ ጎን ለጎን ሆነው
ድባብ ተይዞላቸው፣ መሣፍንት፣ መኳንንት፣ ሊቃውንት፣ ወይዛዝርት፣ግራዝማቾች፣ ቀኛዝማቾችና የጦር አበጋዞች እንደየደረጃቸው ከኋላ
እያጀቧቸው፣ ሰልፍ አስከባሪዎቹና የንጉሠ ነገሥቱ ጠባቂ የሆኑት ጋሻዐጃግሬዎቹ ተከትለው የሰልፉን ግራና ቀኝ አንጋቾች እየጠበቁ ራስ ቢትወደዱ በመጨረሻ ተሰልፈው ነገሥታቱ በዘፈንና በጭፈራ ከግቢ
ሲወጡ ካህናት፣

መንክር ግርማ መንክር ግርማ

ወልደልዑል ጸለላ መንክር ግርማ

የምትደንቅ ግርማ ሞገስን

የምትደንቅ ግርማ ሞገስ

የወልደልዑል ልጅ፣ እጅግ የላቀው አባት ልጅ፤

እያሉ፣ ምንትዋብ በወንድሟ በወልደልዑል መከታነት መንገሧን
በቅኔ ጠቅ እያደረጉ በፀናፅልና በከበሮ ዐጀቧት።
ዘውዷን እንደጫነች በቅሎዋ ላይ ተሰይማና ታጅባ፣ ወደ ሕዝቡ
አመራች። ከጐንደርና ከአካባቢዋ የመጣው ነፍጠኛ፣ ገበሬ፣ እረኛ፣
ነጋዴ፣ ወታደር፣ አንጥረኛ፣ ሸማኔ፣ ቆዳ አልፊ፣ ጥልፍ ጠላፊ፣ ሹሩባ ሠሪ መድኃኒት አዋቂ፣ ወጌሻ፣ የቤት እመቤት፣ አረቄና ጠላ ሻጭ፣ ዲያቆን ተማሪ ፣ የቁም ጸሐፊ፣ ሠዓሊ፣ ብራና ሠሪ፣ ባለክራሩና ባለመሰንቆው
ሴቱ ሹሩባውን አንዠርጎ፣ ነጠላውን አጣፍቶ፣ ወገቡን በድግ ደግፎ ማተቡ ላይ የእንጨት መስቀሉን፣ ድሪውን፣ ጨሌውን፣ ዶቃውን ቁርጭምጭሚቱ ዙርያ አልቦውን፣ የእጁ አንጓ ላይ አንባሩን ደርድሮ ገሚሱ የቀርከሀ ጃንጥላውን አጥልቶ፣ ወንዱ ፀጉሩን አጎፍሮ፣ ለምዱን ደርቦ፣ ዱላውን ትከሻው ላይ ጣል አድርጎ፣ ልጆች ጥብቋቸውን
አጥልቀው፣ ክታባቸውን አንጠልጥለው ምንትዋብ ከኢያሱ ጋር ጃን ተከል ብቅ ስትል አካባቢው ድብልቅልቁ ወጣ።

ሴቶች በዕልልታና በእስክስታ፣ ወንዶች በሆታና በጭፈራ አካባቢውን አናጉት፤ ካህናት በሽብሸባ አደመቁት። እነምንትዋብ ካለፉ በኋላ፣
ሕዝቡ መስመሩን ተከትሎ እየሮጠ ዕልል! ሆ! እያለ ዐጀባቸው።

ጐንደሬዎች እንደዛ ውበት የነገሠበት ሰው አይተው አያውቁምና በምንትዋብ ውበት ተደመሙ። “አቤት መልኳ እንደ ጠሐይ ሚያበራ አቤት ወርቅ አካል!” እያሉ ተደነቁ። በደስታ ተሳክረው ለአፄ ፋሲለደስ፣

አሁን ወጣ ጀንበር

ተደብቆ ነበር

ተብሎ እንደተዘፈነው ሁሉ ለእርሷም፣

አሁን ወጣች ጀንበር

ተሸሽጋ ነበር

እያሉ አዜሙ፤ ጨፈሩ።

አሁን ወጣች ጨረቃ፣
የምትለን ፍርድ ይብቃ።

ደስ ይበልህ ዘመድ፣
ከነገሠች በዘውድ።

ደስ ይበልሽ ወይዘሮ፣
ጭና መጣች ወገሮ።

ደስ ይበልህ ባለእጌ፤
ነገሠች እቴጌ።

ደስ ይበልህ ጐንደር፤
ቀድሞ ከፍቶህ ነበር፣

ሲሉ ጐንደሬዎች ለውዷ ከተማቸው መልካሙን ተመኙላት።

ምንትዋብ የተስፋ ጨረር ፈነጠቀችላቸው።

ዐዲስ ንጉሥ በመጣ ቁጥር የተስፋ ስንቅ ሰንቆ የሚወጣው
መልካሙን ተመኘ ለጦርነት ሳይዳረግ፣ በወታደር ሳይዘረፍ፣ ሚስቱና ልጁ ሳይደፈሩ እኖራለሁ በሚል ተስፋ፣ ከትናንቱ ዛሬ ይሻለኝ ይሆን በሚል ምኞት።

ጐንደሬዎች ምንትዋብን ወደዷት፤ ቀልቧ ገዛቸው፤ መልኳ
አባበላቸው፤ ግርማ ሞገሷ ማረካቸው፣ ኩራታቸው በእሷ ሆነ። በዓለ ንግሥናዋን አደመቁላት፤ ዐደራቸውን ሰጧት፤ ተስፋቸውን ልባቸው ጫፍ ላይ አንጠልጥለው ፎከሩላት፤ ሽለሉላት፤ ዘፈኑላት፤ ጨፈሩላት፤
ዕልል! ሆ! አሉላት።

ጥላዬ፣ ከእነአብርሃ ጋር ከካህናቱ ኋላ ሆኖ አብሮ እየዘመረ ሲሄድ
ድንገት ምንትዋብን ከኢያሱ ጋር አያት። የለበሰችው ነጭ ሐር ቀሚስ፣ፊቷን የጋረደው ነጭ ዐይነርግብ ከፀሐይዋ ብርሃን ጋር ተደምሮ ዐይኑ ላይ አንፀባረቀበት። ያየውን ሁሉ ማመን አቃተው። የባሏ ለቅሶ ላይ አዝኖላት እንባውን እንደረጨላት ሁሉ አሁን የያዘውን የደስታ ሲቃ መቆጣጠር አቃተው። እንባው ፊቱን አራሰው። እነአብርሃ እንባውን እንዳያዩበት በሰዉ መሃል ተሸለክልኮ ወጥቶ “ኸንግዲህ ደብረ ወርቅ ብመለስም አይቆጨኝ” ብሎ ወደ ቤት ሄደ።
👍16
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_ሦስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

"በእግዝሃር ፍጥረት ሴት ልሁን እንጂ ምን ይጎለኛል?”

ምንትዋብ ለራሷ፣ ለሃገሯና ለጐንደር በገባችው ቃል መሠረት
በቅድሚያ ሰላም ማስፈንንና ሃገር ማረጋጋትን መረጠች። ለዚህም
እንዲበጅና የልጇን መንግሥት ለማደላደልና ለማጠናከር ንጉሥ
ሲነግሥ እንደሚደረገው ከብርሃን ሰገድ ኢያሱ ጋር ሆና መኳንንቱን
አሸዋ ግንብ ሰብስባ ሹመት ሰጠች። ሕዝቡ የወደደውን ሹመቱ እንዲጸና አደረገች፤ የሚሻረውን ሻረች።

የልጇን መንግሥት ይበልጥ ለማጠናከር ግራዝማች ኒቆላዎስን፣ አዛዥ አርከሌድስንና ወልደልዑልን ደጃዝማች ብላ ሾመቻቸው።

በደንቡ መሠረት ግብር አገባች፣ ብላም ከመኳንንቱ ጋር ምክክር
አደረገች።በምክክሩ መሠረት ደጃዝማች ኮንቤን የጃዊና የዳሞት ገዢ ኣድርጋ በመሾሟ ቀድሞውንም አፄ በካፋ ላይ ሲያምጹ የነበሩት ጃዊዎች
ኮንቤን አንፈልግም ሲሉ እሷም ላይ አመጹባት። ለምን ሹመቱን
እንደተቃወሙ ስትጠይቅ፣ “ኸራሳችን የወጣ፣ ወግ ልማዳችንን ሚያቅ ኸራሳችን የተወለደ ይሾምልን” አሏት።

መኳንንቱን እንደገና ወርቅ ሰቀላ ውስጥ ሰብስባ መከረች።
መጽሐፉም ወኩሎ በዘትገብር ተማከር ምስለ ሰብእ፡ እስመ ዘእንበለ ምክርሰ ገቢር ዕበድ ውእቱ ማንኛውንም ስራ ስትሠራ ከሰዎች ጋር ተማከር፤ አለበለዚያ የሰነፍ ሥራ ይሆንብሀል ነው የሚለው።
መኳንንቱም፣ “እንደ ልማዳቸው እናርግላቸው” አሉ። ምንትዋብ
ተቀበለች። ሻለቃ ወረኛን ብትልክላቸው ጃዊዎች ፈነጠዙ፤ ተረጋጉ።እሷም የመጀመሪያውን የአስተዳደር ትምህርት ገበየች። እንደገናም ከኢያሱ ጋር ሆና ሃገር ላረጋጉት ሹመት ሰጠች።

ሕዝቡን አስደስታ፣ እሷም ተደሰተች፣ ሃገርም ተረጋጋች:

ደስታውና መረጋጋቱ ግን በአስተዳደር በኩል ሊገጥማት ከሚችለው ችግር ለረጅም ጊዜ ሊያድናት አለመቻሉን በመገንዘብ፣ ከመኳንንቱ ጋር ከምታደርገው ምክክር ውጭ ብዙውን ጊዜዋን ከኒቆላዎስ፣ከወልደልዑል፣ ከአርከሌድስ፣ ከአያቷ፣ ከእናቷ፣ ከአጎቷና ከአጎቷ ልጆች
ጋር እየተሰበሰበች ስለአስተዳደር መወያየትን ልማድ አደረገች።

እንደሁልጊዜያቸው አንድ ቀን እልፍኝ ውስጥ ተሰብስበው ሳለ፣
“እኔ ስንኳ” አለቻቸው። “እኔ ስንኳ ሌት ተቀን ማስበው እንዴት
ላስተዳድር እያልሁ ነው። የነገሥሁ ዕለት ድኻው ምንኛ ተስፋ
እንደጣለብኝ አይቻለሁ። ኸነሱ ተስፋ አንሼ ልገኝ አልሻም። ምኞቴ
ሁሉ ላገሬ መልካም ማረግ ነው። ሌላው ደሞ ኸመኳንንቱ መኻልም
ቋረኛ ሊገዛን?'፣ ብሎ ብሎ ቋረኛ ይንገሥ?” ሚሉ እንዳሉ አውቃለሁ።ቋረኛ ብሆን ኸነሱ እንደማላንስ ማሳየት ፈልጋለሁ። በናንተ ድጋፍ መዠመሪያ መጠናከር አለብኝ። እኔ ዋናው አገር እንዲረጋጋና የኢያሱ
አልጋ እንዲደላደል ነው ምፈልግ። የኢያሱ አልጋ እንዲደላደል ደሞ
አገር መረጋጋት አለበት።”

እንደ ባሏ የግዛት ዘመኗን አመጽ እያበረዱ ማሳለፍ አልፈቀደችም።
ይህን ስታሰላስል ወልደልዑል ሲናገር፣ ከእንቅልፏ እንደባነነች ሁሉ ራሷን ነቅነቅ ዐይኗን እርግብግብ እያደረገች አየችው።

ስሜቷን ተረድቶ ሐሳቧንም እንደሚጋራ ሊያሳያት፣ “ምታስቢው ሁሉ ይገባኛል” አላት። “ልክ ነው። ድኻው ተስፋውን ኻንቺ አኑሯልና
ቢከብድሽ አያስገርምም። ሁሉን እንደምትወጪ ግን እንተማመንብሻለን።
እንዳልሽውም ደሞ ኸቋራ ስለመጣሽ ንቀትና ጥርጣሬ አላቸው። ቋረኛ የፍየልም እረኛ ማዶል ሚሉን? ቋራን እንደዝኸ ንቀው እኼው አንቺን አፈራ። አንቺም ደሞ ማን እንደ ሆንሽ ማሳየት አለብሽ። እንዳው ነው እንጂ ኸየትም ነይ ኸየትም ሥራሽ ነው ሚያስመሰግንሽ። አሁንም
ጠንክረሽ ማስተዳደር ነው ያለብሽ። እንዳልሽው የአጤ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ አልጋ እንዲደላደል አገር መረጋጋት አለበት። አገር እንዲረጋጋ
ደሞ አንዱ ኸመኳንንቱ ጋር ስምም መሆን ነው። እነሱ ማዶሉ ለሰዉ ሚቀርቡ? ኻለነሱ የት ይሆናል ። ባለፈው የዳሞት ገዢ የነበረው ተንሴ ማሞ ብዙ ግዝየ፣ “እኒህ ቋረኞች” ሲል ተሰምቷል ። ግዝየውን ጠብቆ ማመጡ አይቀርም። ወህኒ አምባን ደሞ በሚገባ ማስጠበቅ አለብን።
እኔም ሁሉን ባይነቁራኛ እመለከታለሁ” አለና እነአርከሌድስን መልከት
አድርጎ፣ “እኛ እስታለን ድረስ ጥቃት አይደርስብሽም። አንቺም
በተፈጥሮሽ ጠንካራና አስተዋይ ነሽ” አላት።

“ላለፉት ሰባት ዓመታት ስለቤተመንግሥት ብዙ ነገር ተምሬያለሁ”አለቻቸው፣ እጆቿን ደረቷ ላይ አስቀምጣ። “እኼ ይመጣል ብየም ባይሆን ማን ምን እንደ ሆነ ሳጠና ነው የቆየሁ። ቋራ ሳለሁ እንዳው ንጉሥ አዛዥ ናዛዥ ይመስለኝ ነበር...”

ኒቆላዎስ ጣልቃ ገባ፣ “ንጉሥ በርግጥም አዛዥ ናዛዥ ነው። መኳንንቱ ብዙውን ግዝየ ኸንጉሡ በዝምድናም ይሁን በጋብቻ የተሳሰሩ ቢሆኑም ንጉሡ የፈለጉትን መኰንን በፈለጉ ግዘየ ያለ ማስጠንቀቂያ ኸማረጉ
ሊያነሱት፣ ይዞታውን ሁሉ ሊነጥቁት ይችላሉ። አይተሽ የለ እንዴ አንድ መኰንን ያለ ንጉሡ ፈቃድ መዘዋወር ስንኳ እንደማይችል? ግና ያለ መኳንንቱ መንግሥት አይጠናም። አማካሮቹ፣ የቤተመንግሥት
ምሰሶዎቹ እነሱኮ ናቸው። እነሱን በጅ ማረግና ኸነሱ መምከር ግዴታ ነው። ፍታ ነገሥቱም ያዛል። ፈላስፋውም ቢሆን 'በገዛ ራሱ ምክር ብቻ ሚኸድ ሰው ይደክመዋል፣ ኻልሆነም ነገር ወድቆ ይቀራል ይል የለ?
ደሞስ ግብር ሰብሳቢዎቹ፣ ጦርነት ሲኖር ተዋጊዎቹና አዋጊዎቹ እነሱ
ማዶሉ? ፍርድ ሸንጎ ሚቀመጡ፣ ዳኛ ሚሆኑም እነሱ ናቸው። ንጉሡ ነው ሚፈርዱ። የግዛቶቹ ሁሉ አስተዳዳሪዎችም እነሱው ናቸው። አንድ ሲፈልጉ የራሳቸውን ፍርድ ቢሰጡም፣ የነሱን ሰምተውና አመዛዝነው
መኰንን አመጸብሽ ማለት አንድ ግዛት ይዞብሽ ኸደ ማለት ነው።
ያኔ ለማስገበር ጦርነት ትገጥሚያለሽ። በመጨረሻም ኸወህኒ አንዱን አምጥተው ያነግሡብሻል።ኻንች ከሆኑ አመጥ ቢነሳ ስንኳ ሚያዳፍኑልሽ
እነሱም ናቸው። ሚያቀጣጥሉብሽም እነሱ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዝኸ አብረሽ እየመከርሽ፣ እየሾምሽና እየሸለምሽ ይዞታቸውን እየጠበቅሽና እየጨመርሽ ነው መያዝ ያለብሽ። እንካ በእንካ ነው ነገሩ። ስትሾሚ ደሞ ባለፈው እንዳረግሽው ጥሩ ሚያስተዳድረውን ትሾሚያለሽ፤
ማይጠቅመውን ታማኝ ቢሆንም ስንኳ ትሽሪያለሽ።”

“እኔ አሳቤ ያው ጃንሆይ እንደሚያረጉት ኸጥንትም ቢሆን ያለ ማዶል? የመኻሉን ጠበቅ አርጌ ይዤ የሩቁን ግዛታቸውን እንደ ልማዳቸው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ ነው.. ያው አሁን ለጃዊዎች እንዳረግነው። ዋናው ዓላማየ አገር ማረጋጋትና መንግሥት ማደላደልነው።”

“አንገብርም ብለው ኻላመጡና ድኻውን ኻልበደሉ በቀር ጣልቃ
ሳትገቢ” አላት፣ ኒቆላዎስ።

“አዎ ጣልቃ ሳልገባባቸው። መኳንንቱ ብዙ ግዝየ ኸዝኸ ይመጡ የለ? ቤታቸው ራሱ እዝሁ ቤተመንግሥት አጠገብ ነው። ምማከረውም ኸነሱ ነው። ማነንም ጦር እያነሱ ማስገበር አልፈልግም። በሰላም አንድ
ሁነን እነሱም ግብር እያገቡ፣ ድኻውን በደንቡ እያስተዳደሩ መኖርን ነው ምመርጥ። እነሱም ሆኑ ድኻው እኔ ላይ እምነት እንዲጥሉ ፈቃዴ ነው። እምነት ኻልጣሉብኝ እንዴት ማስተዳደር እችላለሁ? ጥሩ ታስተዳደርሁ ደሞ እምነት እንደሚጥሉብኝ አውቃለሁ።”

“ትክክል” አሉ፣ ዮልያና።
👍5
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...ከራስ ቢትወደድ ዘጊዮርጊስ መሸነፍ በኋላ፣ ሰላም ቀስ በቀስ በሃገሪቱ መልሶ ሰፈነ። ምንትዋብ በነገሠች በዓመቱ እንደ ቀድሞ ነገሥታት የራሷ የሆነ ቤተመንግሥት ለማሠራት ያደረባትን ጽኑ ፍቅርና ፍላጎት
ለማርካት ከባለቤቷ ከአፄ በካፋ ግንብ ጎን ቆማ ያሠራችው የተዋበውና የረቀቀው ፣ እንደ ሌሎቹ ግንቦች ሁሉ ባለ ሰቀሰቁና ባለ ሁለት ደርቡ ቤተመንግሥት የተደነቀ ሆነላት።

አፄ በካፋ በሞቱ በሁለተኛ ዓመታቸው ላይ ያሳደጓት፣ ያስተማሯት፣ በቤተመንግሥት ሥርዐት ሆነ በአስተዳደር ታንጻ እንድትወጣ የረዷት፣ አንደበተ ርቱዕዋ፣ የቤተክህነት ትምህርትና የቤተመንግሥት ወግ አዋቂዋ አያቷ ወይዘሮ ዮልያና ይህችን ምድር ጥለው ሄዱ። እሷ
ሆነች እናቷ መሪር ሐዘን ገባቸው። ዮልያና ታላቅ የቀብር ሥርዐት
ተደርጎላቸው ተቀባሩ። ምንትዋብ ተዝካራቸውንም ታላቅ ድግስ ደግሳ አወጣች።

ዮልያና በሞቱ በስድስተኛ ወራቸው ታናሽ ወንድማቸው ኒቆላዎስ ዐረፈ። ምንትዋብ ተጎዳች። ሆኖም ኒቆላዎስ በታላቅ ለቅሶና ሐዘን ተገቢው ሥርዐት ተደርጎለት ተቀበረ። ቀድሞውንም ቢሆን ለአፄ በካፋ ሁነኛ የነበረና በኋላም፣ ከእሷ ቀጥሎ ትልቁ ባለሥልጣን የነበረ፣አጋሯና በማንኛውም መንገድ ሲያግዛት፣ ሲያማክራትና ትዕዛዞቿን ሁሉ በተገቢው መንገድ ሲያስፈጽምላትና ሲፈጽምላት የቆየ ቀኝ እጇ በመሆኑ፣ የእሱ መሞት በቤተመንግሥት ውስጥ ትልቅ ክፍተት ፈጠረ።

ኒቆላዎስ ከሞተ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ምንትዋብና ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ዐዲሱ ቤተመንግሥት እልፍኝ ውስጥ እጅ የሚነሱትን መሣፍንትና መኳንንት አሰናብተው ጨርሰው፣ ኢያሱ ከአጃቢዎቹ ጋር ወጥቷል።
ምንትዋብም እልፍኟ ለመግባት ዝግጅት ላይ ነች፡፡ ደጃዝማች
ወልደልዑል ጫማውን ሳያወልቅ እልፍኝ ዘው ሲል ከአረማመዱ የሆነ ነገር እንደገጠመው አወቀች። ዛሬ ወልድየ ምንን ሁኖ ነው አለወትሮው በችኮላ ሚራመደው አለች፣ ትኩር ብላ እያየችው።

“ችግር አለ” አላት፣ የችኮላ ሰላምታ ከሰጣት በኋላ።

“የምን ችግር ወልድየ?” ከተቀመጠችበት ተነሳች።

“የጃንሆይ መኰንን የነበረው ተንሴ ማሞ ለውጊያ ታጥቋል።”

“ምን ይሁን ብሎ?” ፊቷ ጥላ ጣለበት። “ምን ይሁን ብሎ ነው አሁን ጦር ይዞ ሚነሳ?”

“ኸኢያሱ ክፍል የለኝም ብሎ። ያው ፊት እንደሰማነው፣ እኒህ
ቋረኞች እስተመቸ ነው ሚገዙን ብሎ።”

ከቋራ ስለመምጣቷ ከአያቷ ጋር ሲያወሩ፣ “ንቀታቸው... ወደ ፊት
ታቂዋለሽ” ያሉት ትዝ አላትና ራሷን በትዝብት ነቀነቀች። “እኒህ

ቋረኞች እስተመቸ ነው ሚገዙን ብሎ?” አለችና ከት ብላ የምጸት ሳቅ ሳቀች።

“አዎ እስተመቸ ነው ሚገዙን እያለ ሲቆጭ ቆይቷል” አላትና
እንድትቀመጥ በእጁ ዙፋኗን አመለከታት።

ቀጥል በሚል እጇን አወዛወዘችለት።

“አንዱም ኸተሰጠው የዳሞት ገዥነት ስለወረደ በልቡ ቂም ኣሳድሮ ነው እኼን ሊያረግ የተነሳው። ጥላቻውና እብሪቱ መጠን አጥቶ እዋጋለሁ ብሎ ነገሩን ኻዘጋጀ ሰንብቷል። “
እኼን የኩበት ካብ ሳላፈርስ
ሰው አልባልም ብሏል አሉ።”

“የኩበት ካብ?”

“የንጉሥ ኢያሱንና ያንቺን መንግሥት ማለቱ ነዋ!”

“ዛዲያማ ይጠብቀና” አለች፣ ሌባ ጣቷን እያወዛወዘች።

“ኸመጣሽ ዠምሮ ቋረኞች ላይ ያለው ግምት ምን እንደሁ
ታውቂያለሽ። አንቺም ብትሆኚ አልተሸነፍሽላቸውም፤ ወደፊትም
ታሸንፊያቸዋለሽ። ስሰማ ተንሴ ማሞ ኸዝኸ ሁሉ መጥቶ ግቢውን
አይቶ ነው አሉ የኸደው። ተመልሸ መጣለሁ ብሎ ዝቷል።”

“እንዴት ልቡ አብጧል በል? ይምጣ... ይምጣ... እስቲ እናያለን
የኩበት ካቡን ሲያፈርስ። የልዢን አልጋ ኻላስከበርሁማ እኔ ምንትዋብ ሰው ማዶለሁ” አለች።

ሰውነቷ ጋለ።

“አሳቡ አንቺንና ንጉሥ ኢያሱን መግደል ነው። መንገስ ሚፈልገውን ጠይቆ ሊመጣ ወህኒ ኸዷል። ወንድሙ ተስፋ ማሞም
ኸሱ ጋር አምጿል። ኸጎዣምም ብዙ ሠራዊት ሰብስቧል አሉ። እኛም መዘጋጀት አለብን።”
ለጥቂት ጊዜ ዝም ብላ አየችውና፣ “ሚነግሠውን ያምጣ። የትኛው
አልጋ ላይ እንደሚያስቀምጠው እናያለን። ይልቅስ አሁን ኸመሣፍንቱ፣ ኸመኳንንቱና ኸጦር አበጋዞቹ ጋር እንምከር። ለወሎና ለጎዣም ባላባትም ስለሁኔታው እናመላክታቸው። ዛሬውኑ መልክተኛ እንላክ።ጠንካራ ጦር ስላላቸው ኸነሱ ጋር ተባብረን ነው እኒህን ሰዎች መቋቋም
ምንችለው። ዛሬውኑ ሁነኛ ሰው ላክና እንዲደርሱልን አርግ::”

“በጀ፤ እንደሱ አረጋለሁ” ብሏት እጅ ነስቶ ወጣ።

የእልፍኝ አስከልካዩን ቴዎድሮስን አስጠራች።መኳንንቱና የጦር አበጋዞቹ በአስቸኳይ መሠሪ
እንዲነግራቸው ነገረችው። ኢያሱም ከግቢ እንዳይወጣ ትዕዛዝ ሰጠች።ቴዎድሮስ እጅ ነስቶ በፍጥነት ወጣ።

ዙፋኗ ላይ ተቀመጠች። “የጃንሆይ መኰንን የነበረው ተንሴ ማሞ
ለውጊያ ታጥቋል” የሚሉት የወንድሟ ቃላት ጆሮዋ ላይ አቃጨሉ::እሷንና ኢያሱን መግደል መፈለጉ አስገረማት። ኢያሱን መግደል የሚለው ቃል ዘገነናት። ልጄን በደንብ ማስጠበቅ አለብኝ አለች።

አምላኬ ልዤን ዐደራህን አለች፣ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ
መስኮቱ እየሄደች። በስተቀኝ በኩል በባሏ ግንብና በፈረስ ቤቱ መሃል ያለው ሰፊ ቦታ ላይ ኢያሱ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ባልደራሱ ያነጋግረዋል።ወደ ግቢው በር እየጠቆመ ሌባ ጣቱን ያወዛውዛል። አትውጣ ተብለሀል
ነው ሚለው አለች፣ ምንትዋብ።

በፈረሱ ዙርያ በርካታ የመሣፍንት ልጆች እየተሯሯጡ ይጫወታሉ።
አሁን እስቲ እኼ ትንሽ ልዥ ምን አረገው? ለአልጋ ብሎ ትንሽ ልዥ
ይገድላል? እሱ እንደሆን አይቀመጥበት። ደሞ ማነም ሆነ ማን ኸወህኒ አምባ ቢመጣ የኢያሱን አልጋ አይወስድም. ቁሜ ነው ሙቼ።ልዤንም አልጋውንም እከላከላለሁ አለች። ኢያሱን እያየች፣ እንደነዝኸ ልዥች በመጫወቻው ሰዐት ለሞት ሊዳርግብኝ ባሏ ያስገነቡትን
ግንብ አየችና አስታወሰቻቸው። ለካንስ እንደዝኸ እያመጡ ነው ሰላም ሲነሷቸው የከረሙት.

ኧረ ደሞ ተንሴ ማሞ ተሹሞ ኸነበረ ላይሻር ኑሯል? ስንቱ ይሻር
የለ? ሹም ሽረት ያለ ነው። ደሞ ሰነባበተ እኮ። እንዴት ያለ በቀለኛ
እያሰበችበት ስትመጣ የጋለ ስሜት በመላ አካላቷ ተሰራጨ። ጉንጫፍም መሰለ።

እኔ ምንትዋብ ምን መስየዋለሁ? ቁጭ ብየ ምጠብቀው ይመስለዋል? ይኼ ኸመጣማ አልመለስለትም፡፡ እስቲ ልዤን እንድች ብሎ ንክች ያርግ ያየኛል፣ ብላ ቀኝ እጇን ጨብጣ የመስኮቱን ደፍ መታ መታ አደረገችው። እስቲ አሁን ሰላም ሆንን ስል... ስንት ነገር ላገሬ ሳስብ እንደዝኸ ያለው ይምጣ ላገሬ ያሰብሁትን ሳላረግማ እሱ አይቀድመኝም ኸመንገዴ ላይማ አይቆምም፤ እፋለመዋለሁ። ግድ የለም መልሸ ሰላም አመጣለሁ። አንዴ የሱን ነገር ልወጣ።

ተመልሳ ሄዳ ዙፋኗ ላይ ተቀመጠች። አሁን ብናደድ ምንም ጥቅም የለው። ይልቅስ ማረግ ያለብኝን ባስብ ነው ሚሻል። በመዠመሪያ የግቢውን በሮች እንዲዘጉ ማረግ አለብኝ መጠለያ እንዳይሆናቸው ደሞ ኸግቢ ውጭ ያሉትን ዛፎች ቅርንጫፍ ሁሉ ማስቆረጥ። አሁን
ይልቅ መሣፍንቱን፣ የጦር አበጋዞቹንና መኳንንቱን ተሎ ላነጋግር።ወልድየም ተሎ ብሎ ወሎና ጎዣም መልክት ይላክ፡
👍12