#አኩራፊ_ሰው_ብዙ_ነገር_ያመልጠዋል
===
ባል እና ሚስቱ በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም በረጅም ትዝታ ተውጠዋል፡፡ መጀመሪያ ማውራት ሽንፈት መስሎ ስለታያቸው ሳይነጋገሩ መተኛ ሰዓታቸው ደረሰ፡፡
ድንገት ግን ባል የሆነ ነገር ትዝ አለው፡፡ ነገ በጠዋት የስራ ስብሰባ ለመታደም ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ በረራ አለው፡፡ ሁሌ ደሞ ወደ ስራ ሲሄድ እንቅልፋም በመሆኑ የምትቀሰቅሰው ሚስቱ ናት፡፡ እናም የነገው ስበሰባ እንዳያመልጠው ለሚስቱ "11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በአፉ መናገር ሞት መስሎ ታየው፡፡ እና ወረቀት ላይ "ነገ የስራ ስብሰባ ስላለበኝ ወደ ሌላ ሀገር እበራለው፡፡ አደራ 11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በወረቀት ፅፎ እሷ የምታየው ቦታ አስቀምጦላት ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተኛ፡፡
ጠዋት ሰውየው ከእንቅልፉ ሲነቃ ከጠዋቱ 3ሰዓት ሆኖ በረራውም ስብሰባውም አምልጦታል፡፡ "እንዴት እንደዛ አስጠንቅቄ ነግሪያት አትቀሰቅሰኝም?" ብሎ በጣም ተበሳጨ፡፡ ከአልጋው ለመነሳት ሲሞክር አንድ ወረቀት ኮመዲኖ ላይ ተቀምጦ አየ፡፡ "11 ሰዓት ሆኗል ተነስ ስብሰባ እንዳያመልጥህ" የሚል ፁፍ ተፅፎበታል፡፡
ማነው ስህተት የሰራው? ማነው ልክ?
አስተያየቶን አድርሱን @atronosebot

#ያቺን_ልጅ_ንገሯት
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት
ልከ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በሏት
አዎ እንዳገሬ ነዉ…
እንደ ምንጩ ጣእም እንደ አፈሩ ሽታ
ልጎንጭሽ የምላት…
ልዳብስሽ የምላት ጠዋትና ማታ
ለብሻት የምኖር…
እንደ ቀዩ ጃኖ እንደ ነጩ ኩታ
ጋቢዋ ነኝ እኔ…
ጠላት የተኮሰዉ ንፋስ እንዳይነካት
ሁለት ግዜ ዙሬ…
ወገቡዋ ላይ ያደርኩ የማርያም መቀነት
እንደ አገር አርጅታ…
እንደ አገር አዉግታ ደግሞ ተበሳጭታ
እድሜዉ ይሁን ንዴት ጸጉርዋን አሸብታ
አፋፉ ላይ ቁማ…ብቻዋን ቆዝማ
ድንገት ብታገኟት…
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት
ልክ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በሏት
ንገሩልኝ ዘመድ ንገሩልኝ ወገን
እኔ በሷ ፍቅር እንዴት እንደምሆን
እንደተዋለበት ጤናዉን እንዳጣ
በጠላ አስተናግር በጥብጦ እንደጠጣ
ያስለፈልፈኛል ጩህ ጩህ ያሰኘኛል
የቀኑ ሳይበቃዉ ሌሊት ያስዞረኛል
ጎርፉን እጠጣለሁ አፈር እቅማለሁ
ጎርፉን እየጠጣሁ….ሃገሬን እላለሁ
ጨለጥኳት እላለሁ
አፈሩን እየቃምኩ….ሃገሬን እላለሁ
በላሁዋት እላለሁ
ጸጉሬን እነጫለሁ ልብሴን እቀዳለሁ
እንዳይሆን እንዳይሆን እንዳይሆን ሁኛለሁ
እናም ያች የኔ…
የምጠብቃት ሴት የመጣች እንደሆን
መስከረምን አልፋ…
ጥቅምትን ተሸግራ ህዳሩ ሲታጠን
ገላየ ቆሽሾ አካላቴ ዝሎ
ገጼ ተጎሳቅሎ
ድንገት አልፋኝ ብትሄድ…
ፍቅሬ ተዘንግትዋት…
ማንነቴ ጠፍትዋት…
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት
እንዳገሩ ነበር የሚወድሽ በሏት።
🔘በሰለሞን ሳህለ🔘
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት
ልከ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በሏት
አዎ እንዳገሬ ነዉ…
እንደ ምንጩ ጣእም እንደ አፈሩ ሽታ
ልጎንጭሽ የምላት…
ልዳብስሽ የምላት ጠዋትና ማታ
ለብሻት የምኖር…
እንደ ቀዩ ጃኖ እንደ ነጩ ኩታ
ጋቢዋ ነኝ እኔ…
ጠላት የተኮሰዉ ንፋስ እንዳይነካት
ሁለት ግዜ ዙሬ…
ወገቡዋ ላይ ያደርኩ የማርያም መቀነት
እንደ አገር አርጅታ…
እንደ አገር አዉግታ ደግሞ ተበሳጭታ
እድሜዉ ይሁን ንዴት ጸጉርዋን አሸብታ
አፋፉ ላይ ቁማ…ብቻዋን ቆዝማ
ድንገት ብታገኟት…
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት
ልክ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በሏት
ንገሩልኝ ዘመድ ንገሩልኝ ወገን
እኔ በሷ ፍቅር እንዴት እንደምሆን
እንደተዋለበት ጤናዉን እንዳጣ
በጠላ አስተናግር በጥብጦ እንደጠጣ
ያስለፈልፈኛል ጩህ ጩህ ያሰኘኛል
የቀኑ ሳይበቃዉ ሌሊት ያስዞረኛል
ጎርፉን እጠጣለሁ አፈር እቅማለሁ
ጎርፉን እየጠጣሁ….ሃገሬን እላለሁ
ጨለጥኳት እላለሁ
አፈሩን እየቃምኩ….ሃገሬን እላለሁ
በላሁዋት እላለሁ
ጸጉሬን እነጫለሁ ልብሴን እቀዳለሁ
እንዳይሆን እንዳይሆን እንዳይሆን ሁኛለሁ
እናም ያች የኔ…
የምጠብቃት ሴት የመጣች እንደሆን
መስከረምን አልፋ…
ጥቅምትን ተሸግራ ህዳሩ ሲታጠን
ገላየ ቆሽሾ አካላቴ ዝሎ
ገጼ ተጎሳቅሎ
ድንገት አልፋኝ ብትሄድ…
ፍቅሬ ተዘንግትዋት…
ማንነቴ ጠፍትዋት…
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት
እንዳገሩ ነበር የሚወድሽ በሏት።
🔘በሰለሞን ሳህለ🔘
#ሂድ
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
፡
ሞከርኩ፤ እስኪታክተኝ ሞከርኩ። የገነባሁትን ላለማፍረስ፣ የለኮስኩትን ላለማዳፈን፤ ብዙ ሞከርኩ።
እሱ ግን...
በራሱ አባባል፣ "አብላጫ መቀመጫ" ሲያይ የሚንከራተት ዐይኑ አላረፍም። ከፊት ቀድመው የሚመጡ ውድር ጡቶችን ሲያይ መቅበዝበዙን አልተወም።
ሌላ ያያል።
ሌላ ይመኛል።
ሽቶ የተቀባች ባለፈች ቁጥር እንደውሻ ያለከልካል። ቅልብልብ ዐይኑ የየሴቱ ዳሌ ዳሌ ላይ ፈጥኖ ይለጠፋል።
ፍቅሬ ከእኔ ጋር እያለ፣ ገና ድሮ ጥሎኝ ሄዷል።
መቼ እለት ነው የወሰንኩት። ልክ ዓመታት እንዳልታገሰ ሰው ልክ ለዘመናት ዐይቶ ያላየ እንዳልሆነ ሰው፣ አውቆ እንደማይታረም ገባኝና የአምስት ብር ሻይ እየጠጣሁ አምስት አመታት የገነባሁትን ቤቴን ለማፍረስ ተስማማሁ።
"ሄደሀልና ሂድ" ልለው ወሰንኩ።
የተቃጠርንበት ቡና ቤት ቀድሞኝ ተቀምጦ ስፒሪሱን በአላፊ አግዳሚ ሴት ያወራርዳል። የቴኒስ ጨዋታ እንደሚመለከት ሰው ጭንቅላቱ ከቀኝ ወደ ግራ ሲወራጭ ከሩቅ ይታየኛል። ልቤ ሲረግብ ተሰማኝ። ከጀርባው ነው አመጣጤ፣ አጠገቡ ስደርስ ስልክ እንደያዘ ዐየሁ።
ቆም አልኩ።
"ተይ ባክሽ...! ምን የመሰለች ጅራታም ኮኮብ ዐየሁ መሰለሽ አሁን...ግን ካንቺ አይበልጥም....ካንቺ ቂጥ የሚበልጥ ቂጥ የለም" ሲል ሰማሁት።
ውሃ ልኬ የተዛባ መሰለኝ። አውላላ አስፋልት ላይ፣ በጠራራ ፀሐይ፣ በቂጤ ዝርፍጥ ልል ምንም አልቀረኝ። ተንገዳገድኩ። ድንጋጤ አይደለም።
ለአመታት ፍቅሩን የሚጫረቱኝ ሴቶች እንዳሉ አውቃለሁ። ሻሞ ውስጥ እንደምሳተፍ ይገባኛል።
አንዳንዴም ትራፊው እንጀሚደርሰኝ፣ እንጥፍጣፊው፣ ያለቀበቱ እንደሚመጣልኝ ዐውቃለሁ፣ ይሄኛው ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ መሰለኝ።
ላለመወሰን መፍራትን ማቆም መሰለኝ። የተደበቀው በአደባባይ ሲታይ፣ ሰው እየሰማው እንዲህ ሲል፣ ለመያዝ የፈለገ የእኔን "ሂድ በቃ" ሽኝት የጠየቀ መሰለኝ።
ላለመስማት፣ ላለመያዝ መሞከሩን ያቆመ መሰለኝ። ሰምቼ ሂድ እንድለው። ቆርጦልኝ እንዳሰናብተው። እንጥፍጣፊውንም ሊነፍገኝ፣ ያለቀበትንም ሊከለክለኝ የወሰነ መሰለኝ።
ስሜቴን በቅጡ ሳላስተናብር አጠገቡ ደርሼ ተቀመጥኩ።
"እሺ...እደውላለሁ በኋላ..." ወይም ይሄን የሚመስል ነገር ብሎ ስሉኩን ዘጋው።
ይወዳቸው በነበሩት ዐይኖቼ ዐየሁት። ሌላ በማያዩ ዐይኖቹ ዐየኝ። እንደሰማሁ አውቋል። ግን አልደነገጠም። ግምቴ ልክ ነበር።
በደም ስሬ፣ ደም ሳይሆን የበረዶ ውሃ የሚሄድ ይመስል ያንሰፈስፈኝ ጀመር። ዘፋኙ፣ "እትት በረደኝ በርሃ ላይ ቆሜ" ያለው እንዲህ ያለው ነገር ደርሶበት መሆን አለበት።
"ኤፍ..." አልኩት ያለኝን ጉልበት አስተባብሬ።
"እ...?"
ልብ አድርጉልኝ፣ "ወዬ" ዎቹ፣ "ወይ ማርዬ" ዎቹ፣ "ምን አልሽኝ" የኔ ቆንጆዎቹ፣ በ "እ..." ከተተኩ ወራት አልፈዋል።
"እ.." ይለኛል ዝም እንዳይለኝ። አለሁምም፣ የለሁምም ነገር ነው።
"እ..." "አባባሉ፣ እሰማለሁም፣ አልሰማምረ ነገር ነው።
"ከሌላ ሴት ፍቅር ይዞሃል?"
"እ?"
"ሌላ ሴት ወድሃል ወይ?"
ዝም።
መልሱን አውቀዋለሁ ።
"ታውቂያለሽ... የምታዉቂውን ባጠይቂኝ..." ዐይኖቼ ዐይኔን ሳይሸሹ፣ ያልበላውን ጸጉሩን በማፈር ሳያክ መለሰለኝ።
አላልኳችሁም?
"ህም...ነው እያልከኝ ነው ?" አልኩት ፈራ ተባ እያልኩ ።
የንፍገት ፍቅር ቢቀርብኝ እንደሚሻል ባስብም፣ የሽምያ ፍቅር ወንዝ እንደማያሻግረኝ፣ ዳገት እንደማያስወጣኝ፣ ሌቱን እንደማያነጋልኝ ባስብም፣ እውነቱን መስማት ግን ፈራሁ ግን ደገምኩት ደገምኩት።
"ነው እያልከኝ ነው ኤፊ?"
መበርታት አለብኝ። መጠንከር አለብኝ። ውራጅ ፍቅር አልፈልግም። መሄድን የሚወድ ሰው ቁጭ በል ቢሉት ትርፍ የለሽ ነው። ይሉኝታ እንጂ ፍቅር የማያቆየውን ሰው መያዝ፣ እንቅፋትነት እንጂ ሌላ ምንድን ነው?
"አዎ...ነው..." ጠንከር አድርጎ መለሰልኝ።
ውይ ሲያም። ንግግሩ እንደጥይት አቆሰለኝ። እንደ ቢላ ከተፈኝ። ከመርፌ በላይ ወጋኝ። ግን መበርታት አለብኝ።
ፍቅር ያላሰረውን እግረ ሙቅ ሆኜ ማሰር አልፈልግም። የተነሳ ልቡን፣ "በግፍ ነው" ላስቀምጠው አልሻም። የሸፈተ መንፈሱን "በትንሽ ተገስ" ልደልለው አላቅድም። ግን ሲያም።
ቃላቱ ከጥይት በላይ ያቆስላል።
ከቢላ በላይ ይከትፋል።
ከመርፌ በላይ ይዋጋል።
"እና ልተውህ...? ልትተወኝ ትፈልጋለህ ኤፍ...?
መልሱን የማውቀውን ጥያቄ ጠየኩት።
ይህችኛዋ የፍቅራችን ሬሳ ሳጥን ላይ የምትመታውን የመጨረሻውን ምስማር አቀብለኝ እንደማለት ነበረች።
"እንደሱ አደለም...ማለት...በውለታ መታሰር አልፈልግም ጥሩ ነገር አሳልፈናል ግን..." አለ አሁንም በድፍረት እያየኝ።
"ግን ምን ኤፍ..."
"የምወድሽ አይመስለኝም...ማለቴ አሁን...ዛሬ..."
ንግግሩ ስጋዬን ቦጨቀው።
.....ደም እየፈሰሰኝ ይመስለኛል።
በጆሮዬ፣ በዐይኖቼ፣....በሁለመናዬ ደም እየፈሰሰኝ ይመስለኛል። ሰውነቴ እንደጎማ ሲተነፍስ...ደግሞ ሲግል ይሰማኛል።
አመመኝ።
ፍፁም ታመምኩ።
ዐየሁት። ዐይኖቹ በፍፁም ልበ ሙሉነት ያዩኛል። የሚጠጣውን ስፒሪስ ዐየሁት። ፍቅራችን ጀምሮ እንደተወው ቀዝቃዛ ስፕሪስ ለዛ ቢስ ሆኗል። እሱ ደግሞ ሊተወው...ሊደፋው...እንጂ...ሊያሞቀው አይፈልግም
ዐየሁት።
ፍቅራችን እንደተበሳሳ ጣራ ነው።
በጠብ ጠብ ጀምሮ፣ ቀስ በቀስ እንደሚያበሰብስ...ሙሉ በሙሉ ካልተቀየረ ሁሌም እንደሚያፈስ...እንደሚያለፋ የተበሳሳ ጣራ።
እሱን በማጣቴ ሕይወቴ ውሉ የጠፋ ልቃቂት እንደሚሆን አውቃለሁ።
ፀሐዬን ሰርቆ ጭለማ ውስጥ እንደወረወረኝ እረዳለሁ። ቀስት ደመናዬን ባለ ጥቁር እና ነጭ እንዳደረገው እገነዘባለሁ።
ግን ልሂድ የሚልን ሰው አትሂድ ማለት፣ በመንገዱ ላይ እንደተቸመቸመ ጋሬጣ መሆን ነው።
እንቅፋት መሆን ነው። እንቅፋት መሆን አልፈልግም።
ሳላውቀው ተነሳሁ።
"ኤፊ..."
"ወዬ"
አያችሁልኝ! ሂድ ልለው እንደሆነ ሲያውቅ፣ "ወዬ!" አለኝ...ለደረሰብኝ ሁሉ ከዚህ በላይ ምን ምስክር ምን ያስፈልጋል?
ኤፍ...ሂድ ስለው ወዶኛል።
"ሂ....ድ...." አልኩት በ ሂ እና ድ መሃከል የኪሎ ሜትር ያህል ርቀት እያስቀመጥኩ።
ዝም አለ።
"ኤፊ.."
"ወዬ..."
"መሄድ ስለፈለግክ ሂድ...ቀድሜ ማለት ነበረብኝ...ቢሆንም ዛሬም ቢሆን ሂድ...ጊዜህን መጫረት ሰልችቶኛል...የፍቅር ትራፊ መሮኛል ስለዚህ...ሂ...ድ"
ዝም አለ።
ዝም እንጂ አልሄድም አላለም።
የመዋደዳችን ግብአተ መሬት ለመፈፀሙ ከዚህ በላይ ምን እማኝስ ያሻል?
"ኤፊ?"
"ወዬ መዐዝዬ..."
"ሂድ ግን...እግርህ ጆሮህ እስኪደርስ ብትሄድ የኔን ያህል የሚወድህ ሰው አታገኝም..." አልኩት መሄድ ጀምሬ።
ዝም አለ።
እና...
እንዲህ አድርጌ የምወደውን ሰው ሂድ አልኩት።
ለሚጎዝ እንደሚደረገው፣ ዳቦ ቆሎ ሳይሆን፣ ያልቆረጠ ልቤን ቆርጬ ሰጥቼ ላኩት።
መቀመጫዋ ያበጠ፣ ጡቷ የተወደረ፣ ሰበር ሰካ ባይ ሁላ እንዳሻት ከቀለበችው፣
መዳፍዋ የሰፋ ሁሉ፣ እንዳሻት ከዘገነችው፣ የኔ መሆኑ ካቆመ ዘመንም የለውምና ይሂድ።
....ግን እግሩ ጆሮው ላይ እስኪደርሰ ቢሄድ...እንደኔ የሚወደው ሰው ማግኘቱ ዘበት ነው።
በመንገዴ ላያ፣ ሰማዩን ቀና ብዬ ዐየሁት፣ ፀሃይቱ የት ገባች....?
ቀስተ ደመናውስ ማን በእርሳስ ሳለው..."
....መበረታታት አለብኝ
💫አለቀ💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

👍3
#ድንግልናዬስ…..?
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
ሰማዩ ጨፍግጎ በደመና ቢታጠርም ልቤ ግን በደስታ ጮቤ ረግጧል፡፡የአየሩ ቅዝቃዜ ቢያንዘፈዝፍም ውስጤ ግን በሙቀት ተጥለቅልቋል፡፡ምንያቱም ዛሬ ቀኔ ነች ፡፡የደስታ ቀኔ..፡፡ወደ አዲስ የህይወት ምዕራፍ የምሸጋገርበት፤ሙሉ ሰው ፤ሙሉ ሴት የምሆንባት የተቀደሰች የፍቅር ቀን፡፡
ይህቺን የዛሬዋን ቀን ክርስቲያኖች የክርስቶስን ዳግም መምጣት የሚናፍቁትን ያህል ናፍቄ..ጦርነት የዘመተባት ልጇ በህይወት ተርፎ መመለሱን እንደምትናፍቅ እናት ለዓመታት ናፍቄ ያገኘዋት ቀን ነች፡፡ሴት የምሆንባት ቀን ..እንቡጥነቴ ፈንድቶ ወደ አበባነት የምሸጋገርበት ልዩ ቀን ነች፡፡ከአንዱ የህይወት እርከን ወደ ሌላው የምሸጋገርባት ከወርቅ የተሰራች የህይወት ድልድይ፡፡
መኝታ ቤቱ በልዩ ሁኔታ ደምቆል፡፡፡አራቱም ኮሪደሮች ጥግ በተቀመጡ አይንን በሚማርኩ ማስቀመጫዎች ላይ የተሰኩ ነጫጭ ሻማዎች ተለኩሰው ከፍቅር ጋር የተለወሰ፤ከጉጉት ጋር የተቀየጠ…የናፍቆት ብርሀን ይረጫሉ፡፡ከቴፑ አንደበት እየተስፈነጠረ የሚወጣው የዘሪቱ ከበደ ቄንጣዊ ዜማ ውስጥን ይነዝራል፡፡መኝታ ቤቷን ወለል ያለበሰው ነጭ ምንጣፍ እላዩ ላይ ሮዝ እና ቀይ አበባ ተበትኖበት የሆነ የገነት አጸድ መስሏል፡፡
እኔና ፍቅረኛዬ በጣም ተጠጋግተን ጐን ለጐን አልጋው መሀል ቁጭ ብለናል፡፡ልቤ ደም መርጨቷን ልታቆም ትንሽ ነው የቀራት ፡፡ኸረ እንደውም አለማቆሟንም እርግጠኛ አይደለውም፡፡የምተነፍሰው አየር እያጠረኝ ነው፡፡ተስማምቼ..ፈልጌ እና ቆምጬ ነው የመጣውት፡፡ግን ደግሞ ፈርቼያለው….ደንግጬያለው…ጓጉቼያለው….ተስገብግቤያለው… ተንቀጥቅጬያለው….ተሸብሬያለው ፤እንዴት እንዴት እያደረኝ እንዳለም ለማወቅ ግራ ተጋብቼያለው፡፡
ለጊዜው እሱ ምን እየተሰማው እንዳለ መገመት አልችልም ፤ግን በመጠኑ የፈራ ይመስለኛል፡፡ቢሆንም እስከዛሬ ያካበተውን ልምድ ተጠቅሞ ሊያቀልጠኝ… ሊያሟሟኝ መወሰኑን አይን ውሀውን አይቼ ተረዳው እና በደስታ ተንቀጠቀጥኩ፡፡እጁን አንስቶ ተከሻዬ ላይ ጣል አደረገ… ቀጠለ ወደ ታች ዝቅ አደረጋቸውና ጡቶቼን ጨመቅ ጨመቅ ያደርጋቸው ጀመር…ቀጠለ ጉንጩቼን ደጋግሞ ሳማቸው…..አንገቴ ስር ሳመኝ …ደጋግሞ ሳመኝ…. እንደውም ላሰኝ ማለት ይቀላል.፡፡.እናንተዬ አንገት ስር መሳም ..ጆሮ አካባቢ መሳም እንዴ ነው እንዲህ ፍስስ የሚያደርገው..;?እኔማ ከንፈሬ ተነቅሎ አንገቴ አካባቢ እና ጆሮዬ ላይ ተለጠፈ እንዴ ?ብዬ ተጠራጥሬ ነበር፡፡ግን ከንፈሬ ቦታው ላይ መሆኑን ያረጋገጥት በመጨረሻ መነጥቶ ሲጣበቅባቸው ነው፡፡መጠጠኝ… እስክቃትት መጠጠኝ፡፡በስተመጨረሻ የኃላ እግሩ እንደተሰበረ ወንበር ወደ ኃላችን ተያይዘን ተገነደስን፡፡ሰውነቴ በእቶን እሳት የተቀጣጠለ መስሎ ተሰማኝ….ልቤም አቅም እያነሳት እና እየተልፈሰፈሰ እንደመጣ እየታወቀኝ ነው፡፡
ልብሳችንን በምን ፍጥነትና ብርታት አወላልቀን እርቃን እንደቀረን ፍፅም ትዝ አይለኝም፡፡ሰውነቴ ከሰውነቱ ሲጣበቅ…እግሮቼን ፈልቅቆ ጭኔ ውስጥ ሲመሰግ ….እንደፌዴራል ዱላ የገረረ እንትኑ ያለርህራሄ ትንሽ እንኳን ሳያባብለኝ እየሰነጣጠቀኝ እየከፋፈተኝ ወደ ውስጠቴ ሲገባ የሆነ አዲስ አይነት ጣዕም.. አዲስ አይነት ስቃይ… አዲስ አይነት ደስታ ተሰማኝ… ፡፡ሚገርም ነው ስቃይና ደስታ እንዲህ ይደባለቃል….ለቅሶና ሳቅ እነዲህ ይዋሀዳል..?ማቃተት እና ማስካካት እንዲህ ተቀይጦ ከሰው አንደበት ይሰማል….?በቃ ለዘላለም በዛው ብጠፋ ተመኘው…፡፡ወይ ጉዴ.. አዎ የእወነት ልጠፋ ነው መሰለኝ… የፍቅረኛዬ ጉልበት የዐውሬ እየሆነ ነው..የ17 ዓመት ያልፀኑ አጥንቶቼን እያደቀቃቸው ነው…ሰውነቴ እየተተረተረ…እየተበታተነ እየመሰለኝ ነው..፡፡ትንፋሼ ልትቋረጥ የሽርፍራፊ ሰከንድ ጊዜ ሲቀራት ጀግናዬ ተልዕኮውን ከፍጻሜ አድርሶ ተዝለፍልፎ ከጐኔ ተዘረረ፡፡እኔም ከደስታ እና ስቃይ ተቀይጦ የተመረተ እንባ ወደ ውጭ በዝምታ አንጠባጠብኩ………………………….
ከአምስት ደቂቃዎች የዝምታ እና የተመስጦ እረፍት ቡኃላ ፍቅሬን እተጋደመበት ትቼው እየተንሻፈፍኩ እና እየተንቀጠቀጥኩ ሻወር ልወስድ ወደ ባኞ ቤት በመጐተት ገባው፡፡
….›››››››››››››››››››››››››››››››››………..
ከአስር ደቂቃዎች ቡኃላ ስመለስ መኝታ ቤቱ ባዶ ነበር፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ድንገት አንድ የወረቀት ቁራጭ አይኔ ውስጥ ገባ አነሳውተት …የፍቅሬ የእጅ ፅሁፍ ነው፡፡ማንበብ ጀመርኩ…ይገርማል ለእኔው የተፃፈ ነው…
===
ሁለት ዓመት ሙሉ ዋሸሺኝ…በፍቅራችን ቆመርሽበት፡፡ልጃገረድ ነኝ ብለለሽ ስታጃጅይኝና ስታሾፊብኝ ከረምሽ፡፡
አሁን ማድረግ ምችለውም.. የምፈልገውም ነገር አንቺን መርሰሳት ነው..፡፡ለዛም ይረዳኝ ዘንድ ልጠጣ ሄጄያለው፡፡
በፈጠረሽ ስመለስ እቤቴ እንዳላገኝሽ…ካገኘውሽ ልገድልሽ ሁሉ እችላለው፡፡
አየሽ እኔ የቤት ሸርሙጦችን በጣም ነው የምጠየፈው፡፡
===
አንብቤ ስጨርስ አጥወለወለኝ ፡፡በደስተታ ተንተርክኮ የነበረው ልቤ ከመቅፅበት ኩምትርትር አለ፡፡እርክት ብሎ የነበረው ስሜቴ መልሶ ሙሽሽ አለ፡፡ግራ ገባኝ ፡፡ይህ ሁሉ ለዛለለም ይሚበቃ ይመስል የነበረው ደስታ በደቂቃዎች ውስጥ እንዴት እንዲህ ሊበተን ይችላል?፡፡እኔ ከእሱ ውጭ አኮ እንኳን ወሲቡ መጋራት ቀርቶ ከንፈር ተሳስሜ አላውቅም…፡፡እሱ እኮ የልቤን ድንግልና…የከንፈሬን ድንግልና ..እና አሁን ደግሞ ቀሪውንም ድንግልናዬን ነው የወሰደው…፡፡ ታዲያ የቱ ጋ ነው ችግሩ….?.እኔን እንዴት ሸርሙጣ ሊለኝ ቻለ?ቆይ ግን ክብረ -ንፅህና ማለት ምን ማለት ነው?ራሴን ጠየቅኩ…የእውነት ለእሱ ብቻ እንደተኛው… ለእሱ ብቻ እንዳስረከብኩ በምን ላረጋግጥለት እችላለው..?አዎ ትዝ አለኝ …ደም፡፡ በፍጥነት ብርድልብሱን ገለጥኩ… አንሶላዎችን አገላበጥኩ… ፍጽም ንፅህ ነው …ጠብታ ደም አይታበትም… ፡፡ወላሉ ላይ ቆምኩና የለበስኩትን ቀሚስ ወደ ላይ በመግለብ ጐንበስ ብዬ ብልቴን ፈተሸኩ፤ ዙሪያውን ፍም መስሎአል..የመቁሰል መልክቶችም ይዩበታል፡፡
ወይኔ ልጅት ምንም የዋሸውት ነገር የለም እስከዛሬ ድንግል ነበርኩ… ሴት የሆንኩት ዛሬ ነው….አዎ ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት እዚህችው አልጋ ላይ…..፡፡መጮህ አማረኝ …ማልቃስ አማረኝ ..ዕቃዎችን መሰባበር አማረኝ ..እራሴን ማጥፋት ሁሉ አማረኝ ..ግን ዝም ብይ አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብዬ አንገቴን ወደ መሬት አቀርቅሬ ከመነፍረቅ በስተቀር ለጊዜው ሌላ ምንም ነገር ማድረግ አልቻልኩም፡፡
💫ተፈፀመ💫

👍3❤1🤔1
#ሞካሪና_አስሞካሪ
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
፡
፡
"ከንፈር መሞከር እፈልጋለሁ።" አልኩት
"እስከዛሬ ተስመሽ አታውቂም።?"
"እስከዛሬ ፈልጌ አላውቅም።" ከንፈሩን አቀበለኝ።
ወራት ነጎዱ……
"ድንግል መሆን አልፈልግም" አልኩት
"ገናኮ 18 ዓመትሽ ነው ማሬ። ለምን ትንሽ አንቆይም? "
"አሁን ነው የምፈልገው።"…… አክሱሙን አቀበለኝ።
ወራት ነጎዱ………
"ጫት ለጥናት ጥሩ ነው ሲሉ ጊቢ ሰማሁ። መሞከር ፈልጋለሁ አልኩት።"
"አይ አይ አይ…… ጥሩ አይደለም ማሬ ስሞትልሽ አትሞክሪ።" አለኝ እያንገፈገፈው
"ልንገርህ ብዬ እንጂ መሞከሬ አይቀርም። እነቤቲ ዛሬ እንቅማለን ብለዋል…… " ሳልጨርስ ቀድሞ
"እሺ በቃ ፍቅሬ እሺ…… መሞከር ከፈለግሽ እኔም አብሬሽ እሞክራለሁ። ከኔጋ ቃሚ…… " ጫቱንም ፍራሹንም ሰጠኝ።…… መቃም በፈለግኩ ቁጥር ከስራ እየቀረ አብሮኝ ቃመ።
ወራት ነጎዱ………
"ልመረቅ ስለሆነ ስክር ማለት እፈልጋለሁ ክለብ ውሰደኝ" አልኩት……
"እሺ እንደፈለግሽ ሁኚ እጠብቅሻለሁ።" አለኝ…… መጠጡን ቀዳልኝ… እንደፈለግኩ ሆንኩ……
ሰዓታት ነጎዱ……
"ማጨስ እፈልጋለሁ።"
"እማ ስካሩ አይበቃም? ፕሊስ ጭሱ ይቅር? "ለአፉ አለኝ እንጂ የፈለግኩትን ሳልሞክር ማቆሚያ እንደሌለኝ ያውቃል።
"እሺ ገዝቼልሽ ልምጣ? "
"አልፈልግም የተጨሰ ግማሽ የደረሰ ሲጋራ ነው ማጨስ የምፈልገው።… እንደውም ያን ሰውዬ ስጠኝ እለዋለሁ።"
"እሺ እሺ በቃ የተጨሰ አይደል ማጨስ የምትፈልጊው? በቃ እኔ አጭሼ ሰጥሻለሁ።…… ከሌላ ሰው ከንፈር ተውሰሽ አታጨሺም! " አጭሶ ሰጠኝ። አጨስኩ።… እስክመረቅ በጨፈርኩ ቁጥር የተጨሰ ሲጋራ አቀበለኝ።
ዓመታት ነጎዱ…… ብዙ ዓመታት…… እንደተመረኩ ከሃገር ወጣሁ።…… ተራራቅን…… ከጊዜ በኋላ መገናኘት አቆምን።… አገባሁ…… ወለድኩ…… ለበዓል ወደሃገር ቤት ተመልሼ ሳለሁ መንገድ ላይ አየሁት።…… ደነዘዝኩ። ያ ሊነኩት የሚያሳሳ ቆዳው ከስሎ…… የሚያንጠራራ መለሎ ቁመናው ጎብጦ… የሚያኮራ ደልዳላ አካሉ ኮስምኖ… አይሆንም እሱ አይሆንም!
"አቁምልኝ! አቁምልኝ! "ጮህኩኝ ባሌ ላይ… ዘልዬ ወረድኩ እና እጁን ይዤ አስቆምኩት።
"እማ አንቺ ነሽ ስካሬ እያስቃዠኝ ነው? " አለኝ ከቃላቶቹ እኩል የርካሽ መጠጥ ጠረን እየተፋ
"አባ አንተ ነህ? ምን ሆነሃል? በስምአብ ምን አገኘህ? ታመህ ነበር? በስምአብ …… ደህና ነህ? ቆይ ምንድነው የተፈጠረው?"
"አንቺ እማ! አንቺ ነሽ የተከሰትሽው! ሌላ ማን አለ አንቺ "…
የሆነ የአዳም ረታ መፅሃፍ ውስጥ ያለሁ ገፀ ባህሪ የሆንኩ መሰለኝ። እንጂማ እኔ በእውነታው ይህችን ሴት ልሆን አልችልም። በሱስ ምክንያት በተደጋጋሚ አማኑኤል ሆስፒታል እንደነበረ ነገረኝ። በዛ ምክንያትም ስልክ ኖሮት ስለማያውቅ ላገኘሁ እንዳልቻልኩ አብራራልኝ……
"እማ አንቺ ማለት የምትበር ቢራቢሮ ነበርሽ…… ነፃ የሆንሽ… ነፃነትሽን የምትወጂ… ካልሞከርሽ የማታረጋግጪ…… ሁሉን ሞከርሽ እኔን ጨምሮ ሁሉን ተውሽ! ሁሉን አስሞከርኩሽ ከሁሉ ተጋባሁኝና ቀረሁ። " አለኝ።
አይ አይሆንም የአዳም አንዷ ገፀባህሪማ ሆኛለሁ።…… ነፃነት? ሌላውን የገደለ ነፃነት? በሌላው ባርነት ላይ የቆመ ነፃነት? የአባን ገፅ ያከሰለ ነፃነት?
……… አይሆንም ውሸት ነው። እኔማ እውን አይደለሁም…

👍1
#የሚነበብ_ከንፈር 💋
ያው ጀመራት እነዚህን ጉልላት የመሰሉ ዓይኖቿን ከንፈሬ ላይ ታንገዋልላቸዋለች። እንኳን ለምን ቢሮዬ እንዳስጠራኋት እኔው ራሴ አሁን እዚህ ቢሮ መሆኔን ብጠየቅ የማስታውስ አይመስለኝም።
"ዶክተር? ዶክተር? ዶክተር?” አሁን የት እንዳለሁ አወቅኩ። ግንሳ እነዚህን ዓይኖቿን ካላሳረፈቻቸው እንዴት ነው ከዚህ ሌላ ማሰብ የምችለው?
"አቤት ህሊና?” ያልኩበት ድምፀት ለምን እንደፈለገችኝ እሷ ልትነግረኝ እንጂ እኔ ያስጠራኋት አይደለም የሚመስለው።
" ለምንድነው ያስጠሩኝ ዶክተር? ችግር አለ?” ለምንድነበር ያስጠራኋት? እህህህህ ዓይኗን ከከንፈሬ ላይ ካልነቀለች ለምን እንደፈለግኳት በምን አውቃለሁ? ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እንደትያትረኛ ተንጎራደድኩ(ተንጎማለልኩ።) እኔ ያየኋቸው ጥቂት የኢትዮጵያ ትያትሮች ላይ ተዋናዩ ታሪኩ ላይ የሚጨምረው ምንም ፋይዳ የሌለውና አስፈላጊነቱ የማይገባኝ መንጎራረድ መድረኩ ላይ አንድ ሶስቴ ይንጎማለላል። እንደዛዛዛዛ አደረግኩ። እኔ ግን ዓይኗን ሽሽት ነው። ለምን እንደጠራኋት አሁን መጣልኝ።
ህሊና እኔ በማስተምርበት ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ናት። እንኳን እንደእኔ አይነቱን ዓይንአፋር እኔ ነኝ ያለ ጀግና ወንድ ብርክ የሚያሲዝ ህልም መሰል ውበት አላት። እኔ እሱ አልነበረም ችግሬ። ቆንጆ ትሁን ፉንጋ ከሴቶች ጋር ተከባብሬ የኖርኩ ሰው ነኝ። አይደርሱብኝም። አልደርስባቸውም። የህሊና ጉዳይ የተለየ ነው። በገባሁባቸው አራት ክላሶች ሁሌ ከፊት ነው የምትቀመጠው። እሱም ባልከፋ! እነኚህ አደንዛዥ ዓይኖቿን ከከንፈሬ ላይ ለደቂቃ አትነቅልም። በስህተት መስሎኝ ተከታተልኳት…… ሃሃሃሃ አቃቂያለችኝ እንጂ ሁላ…… የመጀመሪያ ቀን እቤቴ እንደገባሁ ከንፈሬን በመስታወት አየሁት። ሆ! …… ለዓመታት በልበ ሙሉነት ያስተማርኩት ሰውዬ መንተባተብ እጀምራለሁ። ላብ ያጠምቀኝ ይጀምራል።…… አንዱን ቀን ክላሱን ሳልጨርስ አቋርጬ ወጣሁ። ሆሆ!
ምንድነው የምላት? እባክሽ ዓይኖችሽን ከከንፈሬ ላይ ሰብስቢልኝ? ማስተማር ስላቃተኝ ዓይንሽን አሳርፊልኝ? ምን አስበሽ ነው እንደዚህ የምታደርጊው? ኡፍፍፍፍ……
"ዶክተር?” አለችኝ ጀርባዬን ሰጥቻት ለብዙ ደቂቃ መቆሜ ግራ ገብቷት መሰለኝ። ደሞኮ ድምፅዋ ራሱ የሆነ የፈጣሪ ምህረት የሚመስል ለዛ አለው።
"አቤት! እ…… እ…… የጠራሁሽ…” መንተባተብ ሲያስጠላ! ኸረ ዶክተር ትልቅ ሰው አይደለህ ምን ያንተባትብሃል? ራሴን ገስፃለሁ።
"ዶክተር ከንፈርዎትን ካላየሁ አልረዳዎትም።” ምን አለች? ምን አለች? ምን…… ምን?ጆሮዬ ሲሰማ ስቶት ነው።
"አቤት?” አልኳት ዓይኖቿን ሳልፈራ ተጠግቻት። ሳቅ እንደማለት አለች። መሰለኝ።
"ትንሽ የመስማት ችግር አለብኝ። ሲያወሩ ከንፈሮትን ካላነበብኩ ሁሉንም ቃላት ላልሰማ እችላለሁ። ባጋጣሚ ለሁሉም መምህሮቼ ስናገር ለርሶ ሳልነግር ቀርቼ ነው።”
የባሰው መጣ!!!

#ሁለቱ_ከንፈሮች
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
፡
፡
የሳመኝን ሰው እንኳን ስሙን መልኩ እንኳን የሚታወሰኝ ከናይት ክለቡ እልፍ የሚሽከረከር መብራት ቀለማት ጋር ተበውዞ ነው።……
የዘጠኝ ዓመት ፍቅረኛዬን ከንፈር ያስከዳኝን አሳሳሙን ግን……
ፍቅረኛዬን አልኩ እንዴ? ኸረ ከሁለት ሳምንት በኋላ የማገባው እጮኛዬ ነው። ማለቴ ነበር ማታ ያ ከይሲ እስከሳመኝ ደቂቃ ድረስ……
በቃ ተበላሁ።…… እጮኛዬን እፈልግሃለሁ ብዬ ቀጠርኩት።…… ፍትልክ ብሎ ከእጅ እንደወደቀ እቃ ያመለጠኝ
"አላገባህም! " የሚለው ቃል ነው። በቃ ዱብ ነው ነው ከአፌ የወደቀው…… ዝም አለ። አፉ ብቻ አይደለም ገፁም ዝም አለ። ተናደደ? ጠላኝ? ክፋቴ ከቃል በላይ ሆኖበት ነው? በቃ ዝም አለ…… ቀበጣጠርኩ
"ማለቴ መጋባት ያለብን አይመስለኝም።… በአንተ ምክንያትኮ አይደለም…… አንተማ ዕንቁ ነህኮ…… እኔጋ ነው ችግሩ…… "
ከኑሮ ከከበደ ዝምታ በኋላ
"ምክንያትሽን ማወቅ እፈልጋለሁ! " ብሎ የዝምታውን ጭነት ለእኔው አቀበለኝ። ጭጭ…… ፀጥ…… ልጉም…… ዲዳ
ምንድነው የምለው? አንተ ስመኸኝ እንደማታውቀው የሆነ የማላውቀው ሳስበው ሸበላ የሚሆን ሰው ሲስመኝ እኔና አንተ መጋባት እንደሌለብን እንደመገለጥ ፈነጠቀልኝ ነው የምለው?
እጮኛዬ
እጮኛዬ ከመሆኑ በፊት የረዥም ዓመት ቦይፍሬንዴ ነበረ።… ቦይፍሬንዴ ከመሆኑ በፊት የሰፈር ጓደኛዬ ነበር። ጓደኛዬ ከመሆኑ በፊት እቃእቃ በተጫወትን ቁጥር በፀብ የምንጨርስ የእቃቃ ባሌ ነበር።…… ቤተሰብ… ጓደኞቻችን… የሚያውቀን ሁሉ ፍፁም የሆንን ጥንዶች መሆናችንን ነው የሚነግረን።…… እውነት ነው። አንዲት ሴት ባል ይሁነኝ ብላ ልታልም የምትችለው መስፈርት ሁሉ አለው።…… ማታ እንደሳመኝ ልጅ የቆምኩበትን የሚያስረሳ መሳም ብቻ የለውም።
የሳመኝ ሰው
ከአሜሪካ ከመጣች ጓደኛዬጋ ክለብ ሄደን ነው። ሞቅ ባለኝ አሳቻ ሰዓት እንጨፍር አለኝ። እየጨፈርን ነበር…… የሆነ እንደመለስለስም እንደመጠንከርም…… እንደማቀፍም እንደመሳብም… እንደፍቅርም እንደጥላቻም… እንደብዙ ነገር የሆነ አያያዝ ወገቤን ይዞ ሳበኝ…… ሳመኝ ልበለው…… አይደለም…… በከንፈሩ የሆነ ዓለም ፈጠረ… ኖሬበት የማላውቅ ዓለም…… በቃ ይኸው ነው።…… ወደ ናይት ክለቡ ዓለም ስመለስ ተቆናጠርኩ። ተሳደብኩ።…… ተመነጫጭሬ ጥዬው ወደቦታዬ ተመለስኩ…… ወደ ራሴ ሳልመለስ ቀረሁ እንጂ……
"ካንቺ ስለመጣ ደስ ብሎኛል። ለሰርጉ ጓግተሽ ስለነበር ልብሽን እንዳልሰብረው ብዬ እንጂ። እኔና አንቺ ጓደኝነት እንጂ የፍቅር አይነት ቅመም በመሃከላችን እንደሌለ ካወቅኩ ቆይቻለሁ።" አላለም። አምልጦት ከአፉ ወድቆ ነው የሚሆነው ብዬ አሰብኩ። ይሄ ሁሉ ቃልማ አይወድቅበትም።
"ማለት? ማንን ስመህ ነው? " እየቀናሁ ባልሆነ……

👍2
#እኔና_አንቺ
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
፡
፡
“አንተ ሴሰኛ አይደለህም፡፡” ትዪኛለሽ። ሴሰኝነት ‘ስሜ’ መሆኑን አንቺም፣ እኔም፣ ከጎኔ የሚሻጡት ሴቶችም፣ እኔን የሚያውቁኝም ሁሉ እናውቃለን፡፡
ለራሴ ‘ያለማወቅሽን እና የዋህነትሽን’ ነገርኩት፡፡ ላንቺ ግን ዓይኖቼንም ልቤንም የጠለፈውን ህልም የመሰለ ውበት ያለው አካልሽን እያየሁ ጥርሴን ለመግለጥ ከንፈሬን አሸሸሁልሽ …….. ሚስጥር አዘል ወጋገን ያለው ፈገግታሽን መለስሽልኝ፡፡
“አንተ የእኔ በመሆንህ እድለኛ ነኝ::” አልሽኝ የሳምኩሽ እለት…….. በልቤ ሳቅኩብሽ….. በጥርሴ ሳቅኩልሽ …..
“አንተ ከንቱ ሱሰኛ አይደለህም::” አልሽኝ አስረኛ ሲጋራዬን እየተቀበልሽኝ ……. የሙሉ ጊዜ ስራዬ ሱስ መሆኑን ካንቺ በላይ የሚያውቅ አልነበረምና ግራ አጋባሽኝ፡፡
“አንተ እኮ ታታሪ ሰራተኛ ነህ፡፡ እንደማውቃቸው ሰዎች ሰነፍ አይደለህም፡፡ ለምን ስራ አትሰራም?” ያልሽኝ ቀን
‘ትፎግራለች እንዴ?’ አልኩኝ ለራሴ …… በአንድ ዓይነት የትምህርት ዘርፍ ተመርቀን አንቺ ቤተሰብሽን ስታስተዳድሪ እኔ ቤተሰቤን ሳሳርር ዓመት እንዳለፈን ካንቺ በላይ እማኝ የለኝም፡፡
ከቋመጥኩለት ገላሽ ጋር መውደቅ አጓግቶኝ እንዳንቺ የወደድኳት ሴት ያለመኖሯን ምዬ ተገዝቼ ስነግርሽ
“አምንሃለሁ፡፡ እኔን የምትዋሽበት ምክንያት አይኖርህም!!” ብለሽ ውሸታምነቴን አገዘፍሽብኝ፡፡
ማንም ወንድ ያልዘለቀው ገላሽን ስዘልቀው ………………. እድለኛነቴን ሳይሆን ‘ስላፈቀርሽኝ ራስሽን አሳልፈሽ በመስጠትሽ’ እድለኛነትሽን ነገርሽኝ እና ከደስታዬ ይልቅ ራስምታቴን አበዛሽው ………….
አብሬሽ ሆኜ ከሌሎች ብዙዎች ጋር አብሬያቸው መሆኔን ታውቂያለሻ !……….. ለቁጥር የሚታክቱ ጊዚያት ብልግናዬን ደርሰሽበታላ !……… ለተገለጠ ስድነቴ ብዙ ሰበብ ስደረድርልሽ
“ምክንያትህ አንተን ካሳመነህ ለኔ አትንገረኝ::” ብለሽ ምንም ያልበደልኩሽ ያህል ከረሳሽው ቀናቶች ብቻ ናቸዋ ያለፉት!!
አንቺ በህይወቴ እስከተከሰትሽበት ጊዜ ድረስ ሴት ልጅ …………. ልብ፣ ነፍስ፣ አዕምሮ፣ ስሜት ……..( ከሚታየው የሰውነት ክፍሏ ውጪ ያሉት የ’ሰው’ነት መለኪያ) አብሯት ስለመኖሩ አስቤ አላውቅም፡፡ የሴት ፍቺው - እኔጋ የሌለው የሴትነት አካሏ ነበር፡፡ …..
የተናገርኳቸው ቃላትም ሆነ ያደረግኩት ድርጊት ሁሉ የተለመደ ……. ቁጥራቸውን ለማላስታውሳቸው ሴቶች ሁሉ ያልኩትና ያደረግኩትን ነበር፡፡
ከመቼ ወዲህ ነው የሴት ልጅ ነፍስ ይናፍቀኝ የጀመረው? መቼ ላይ ነው የሴት ልጅ ከንፈር ከመሳም አልፎ የሚያፈልቀው ቃል ይርበኝ የጀመረው? …… ለስንተኛ ጊዜ አካልሽኝ ከተዋሃድኩት በኋላ ነበር ነፍስሽን የተዋሃድኳት?………..……… በሆነ በኔና ባንቺ ቀናት ውስጥ በአንዱ ቀን ወይም በሁሉም ቀን ነበር እንደዛ የተሰማኝ፡፡
መቼ ነው አንቺ ነህ የምትዪኝን እኔነቴን እየወደድኩት፣ የሆንኩት ራሴ እያስጠላኝ የመጣው? የትኛው ቀን ላይ ነው አንቺን ለማማለል ሳይሆን ትክክለኛ ስሜቴን ማውራት የጀመርኩት? ምን ካልሽኝ በኋላ ነው ራሴን ማረም እና ንግግሬን መቀባባት፣ ድርጊቴን መደበቅ ሳያስፈልገኝ ራሴን አሳይሽ የጀመርኩት? …….. የትኛው ቀን ላይ አንቺ ነህ ያልሽውን ሰው ለመሆን መወሰኔን አላውቅም፡፡ ከራሴ መማከሬም ትዝ አይለኝም፡፡
ብቻ…………… እግሮቼ ስራ ፍለጋ ሲኳትኑ፣ እጆቼ ሱሳቸውን ላለመከወን ሲታገሉ፣ ምላሴ ላለመዋሸት ከህሊናዬ ጋር ሲጣላ፣ ከሌላ ሴት ተኝቼ ይሰማኝ የነበረው ደስታ በበዛ ፀፀት ሲተካ………… ራሴን በቃልሽ ሳበረታ አገኘሁት፡፡
ክንዴ ሌላ ሴት አንተርሶ ሳለ ደወልሽልኝ፡፡ ‘የት መሆኔን’ ስትጠይቂኝ ለመዋሸትም ያለሁበትን ለመንገርም ቃል ከከንፈሬ አልወጣ አለኝ፡፡ ……
“ መጣሁ ህይወቴ የት ነሽ?” ነበር ያልኩሽ ……
በስምሽ የጠራሁሽ ልቤ ውስጥ መከመርሽን የሚያሳንሱብኝን ቃላት ላለመጠቀም ነበር፡፡ …….ማሬ፣ ፍቅሬ፣ እናቴ ፣ውዴ…… ሁሉንም ቁልምጫዎች ለሌላ ሴት ብያቸዋለሁ …………….
“ስትጨርሽ ደውልልኝ!!” ማለትሽ ለቸኮለች ነፍሴ አልገባትም፡፡
“ መጣሁ!!” ስልሽም በአካሌ ብቻ አልነበረም ….. በሁለንተናዬ እንጂ
“ከኔ ጋር ሆነህ ሌላ ሴት ትቀጥራለህ? ….. ስድ ነህ!!!” ብላ እንደብራቅ ጮኸችብኝ ካንቺ ጋር ሳወራ ነፍሴ መሳቋ የገባት ሴት …..
“ከዛሬ በኋላ ስድ አልሆንም!!” ብዬ የመለስኩላት እውነቴን ነበር፡፡ ……
ካንቺ ውጪ ለመጨረሻ ጊዜ የተኛኋት ሴት መሆኗን ለራሴም እያረጋገጥኩለት ነበር፡፡ ……. ልቤም እግሬም አንቺጋ ለመድረስ ተጣድፈው ሸሚዜን እየቆላለፍኩ የሆቴሉን ክፍል ለቅቄ ስወጣ ነበር ሩቅ በማይባል ቦታ ተቀምጠሸ ያየሁሽ ………… ካልሺኝ ሁሉ በጉልህ የሰማሁት ንግግርሽ
“መቼም የማትሻሻል ሴሰኛ ነህ!!” የሚለውን ነው፡፡
ላስረዳሽ አልሞክርም፡፡ አንቺ ነህ ካልሺኝ በላይ የትኛውን መሆኔን ራሴም እርግጠኛ መሆን አልቻልኩማ ………

❤1👍1
#የታሰረ_ነፃነት
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
፡
የታሰርኩት አባቴን ገድዬ ነው። ፀፀት የለብኝም! 25 ዓመት ተፈርዶብኝ አጠናቀቅኩ። መውጣት ግን አልፈለግኩም።
"ከእስር ቤት መውጣት አልፈልግም!!" ቀጥተኛውና ለወህኒ ቤቱ አለቃ ሊገባው የሚችለው አገላለፅ ይሄ ስለሆነ እንጂ በእርግጥ ፍላጎቴ ከተናገርኳቸው አዘቦታዊ አራት ቃላት በላይ የተወሳሰበ ነው።
"አልገባኸኝም? እዚህ እስር ቤት መሻገት ነው የምትፈልገው?" አለኝ የዓይኑ ቋት የጠበበው ይመስል በተጎለጎለ ዓይኑ በቁመቴ ልክ እየገለበኝ።
"በቀጥታ አማርኛ አዎን እንደዛ ማለት ነው። እዚሁ መሻገት ነው የምፈልገው።"
"ሃሃሃሃሃ (ሲስቅ የዓይኑ ኳስ ብቻውን ይንቀጠቀጣል። ተሽቀንጥሮ የሚፈርጥ ስለሚመስል ውዳቂ ዓይኑ አፈር ሳይነካው እንድቀልበው መጠበቅ ያሰኘኛል።) እስረኛ ስታርበደብድ ዓለምን በእግርህ ስር ያኖርክ መሰለህኣ? ቂል ነህ አንተ ሰው? ‘አፄ’ ሲሉህ የምር የሆንክ መሰለህ? ሃሃሃሃሃ… ( ዓይኑ ቢፈናጠር ወደፊት ተለጥጦ እንደ ዝርግ ሰሃን ሰፋ ያለው የታችኛው ከንፈሩ ይቀልበው ይሆናል።)"
ዓለምን የምድር ያህል ያሰፋው ማነው? የህዋ ያህልስ? ምናልባት ያልተገኘ የህዋ አካል ተደምሮ የሚሆነውን ያህልስ ዓለምን የሚያሰፋት ማነው? ወይስ ምንድነው? ታዲያ የዓለም አድማስ ጥግ የእውቀትህ ልክ አይሆንም? የዓለም ስፋትና ጥበት ራስህ ውስጥ አይሆንም? ባወቅከው መጠን!
ሀያ አምስት ዓመታት እዚህ እስር ቤት ኖሬያለሁ። የልምዴ ጥግ ዓለሜን ጠባብ ያደርገዋል። ከዚህ ጊቢ ውጪ ያለው ዓለም ምኔም አይደለም። ምኑም አይደለሁም። የምናፍቀው የሚናፍቀኝም ሰው የለም። የታሰርኩት አባቴን ገድዬ ነው።(ዓለሜን በሰፊ ጊቢ ለማጠር እንዲመቻቸው ኢ– ሰብዓዊ የሆነ አገዳደል ይሉታል። በሱ ድብደባ እናቴ ያለቀኗ ስትወልደኝ ሰብዓዊ ነበር። በየቀኑ እየሰከረ በአፍና በአፍንጫዋ ደም እስኪፈሳት ሲደበድባት ሰብዓዊ ነበር። እናቴ ገላዋ ላይ ካለው ቁስል ይልቅ ያን ዘግናኝ ግፍ እኔ ማየቴ ስለሚያማት በጊዜ እንድተኛላት ስትለምነኝ፣ በሰበብ ጎረቤት ስታሳድረኝ፣ ያየሁኝ ቀን ደምና እንባዋ ፊቷ ላይ ተቀላቅሎ ውስጧ ደብቃኝ ስትንሰቀሰቅ ሰብዓዊ ነበር። ልከላከለው የደረስኩ ሲመስለኝ እኔንም አብሮ ማጣጋቱም ሰብዓዊ ነበር። በጉልበት እንደተገዳደርኩት ሲገባው እኔንም እናቴንም በፀያፍ ምላሱ ሲልሰንም ሰብዓዊ ነበር። ……… ይሄ ሁሉ ነፍስ ስላልተከፈለበት ሰብዓዊ ነበር። …… በ22 ዓመቴ ጉልበቷንም ራሷንም ከፍላ እናቴ ከምታስተምረኝ የኮሌጅ ትምህርቴ ስመለስ አባቴ እየደበደባት ደርሼ ስደበድበው በእጄ ህይወቱ ማለፉ ይሄ ኢ–ሰብዓዊ ነበር።)
ሀያ አምስት ዓመታትን የተሻገረ ፀፀት የለኝም። እናቴ እዚሁ እያለሁ ታማ ሞታለች። ከዚህ ጊቢ ውጪ ያለው ዓለም ምኑ ይናፍቀኛል? እንዳለመታደል ሆኖ ከእናቴና ከአባቴ ውጪ በቅርበት የማውቀው ዘመድም ሆነ ጓደኛ አላስታውስም።
ይሄ ‘አፄ’ የሆንኩበት ዓለሜ ነው። የብረቶቹ ዝገት ዝገት የሚል ሽታ ፣ የጠባቂዎቹ ክክክክክ የሚል ሹክሹክታ ያለው ካኪ ልብስ፣ የክፍሎቹ እምክ እምክ የሚል ሽታ…… አሸርጋጅ ታሳሪ፣ በመፅሃፍ የተከበበ ፈላስፋ ወዳጅ፣ ጎማ ጎማ የሚል ደያስ(ጎማን መች ቀምሼው ነው ጣዕሙን ያወቅኩት?)፣ በልምድ የሚደላህ ድልዳል፣ …… ዓለሞቼ ናቸው።
" እንግዲህ የቅጣት ጊዜህን ጨርሰሃል። ከወንጀል ነፃ የሆነ ሰው እዚህ ልናቆይ አንችልም። ነገ ለመውጣት ተዘጋጅ!!" ጥዬው እየሄድኩ ሳቁ ይከተለኛል። አንድ ዓይኑ ተሽቀዳድማ ተስፈንጥራ ቀድማኝ እግሬ ስር የማገኛት ይመስለኛል።
★ ★ ★ ★ ★
እርሱ እንዳለኝ የከበቡት ሰወች ፈርተውት እንደሚታዘዙት አልነበረም ገላዬ የታዘዘለት። በፍቅር እንጂ። ከእርሱ ውጪ ሁሉም ያውቃል። ፅዳቴን ብጨርስም ካላየሁት ቀኑን ሙሉ ተጎልቼ እንደምጠብቀው፤ ድምፁን ስሰማ በረጋ ለሊት የመብረቅ ብርቅታ እንዳስደነበረው ህፃን እንደምባትት ፤ ዓይኖቹ ከዓይኖቼ ሲጋጠሙ ላቤ በጀርባዬ ተንቆርቁሮ በቂጤ አካፋይ እንደሚያልፍ፣ በስፖርት የደነደነ ፈርጣማ ደረቱን ሲያንቀጠቅጠው ልቤ በአቃፊዋ ውስጥ እንደምትቀልጥ፣ የልጅነት ባሌ ከሞተ በኋላ ፍቅር ይሉት ነገር ቅብጠት ነው በምልበት እድሜዬ ሰማይ ላይ እንደተበታተነ ብጭቅጭቅ ደመና በፍቅሩ መበታተኔን……… ከእርሱ በቀር የሚያውቀኝ ሁሉ ያውቃል። ዛሬን እንደምጠብቅም ጭምር! እንደምወደው አውቆ ይሆን በተለየ ይቀርበኝ የነበረው? አላውቅም። ቆይ ግን ምንድነው የምለው?
‘አስር ድፍን አመታት የእስር ቤቱ ፅዳት ሆኜ ስሰራ በፍቅርህ ተንገብግቢያለሁ?’እንደዚህ ልለው አልችልም። ያን እንደበረዶ የቀዘቀዘ ፊቱን ነው የሚዘፈዝፈው።
‘የዛን እለት ታሳሪዎቹን ቋንቋ የምታስተምርበት ክፍል ጠረጴዛ ላይ ያደረግከኝን ሁሉ በቅደም ተከተል በህልሜ አየዋለሁ። ከዛን ቀን በኋላም በፊትም አይቼ የማላውቀውን ስትረካ የፈገግከውን ፈገግታህንም! ’ እንዲህ አይባልም አይደል? ‘እማ ግን ሰገጤነት አለብሽ!’ ትለኝ ነበር ልጄ ይሄን ብትሰማ! ከዛ ቀን በኋላ በጣም ተኮሳትሮ
"በሴት ላይ ግፍ መስራት አልፈልግም። አንቺ ደስ የምትዪ ሴት ነሽ የተሻለ ህይወት ይገባሻል። እየተጠቀምኩብሽ እንደሆነ ነው የተሰማኝ። ምንም እንዳላደረግን እርሺው።" ብሎኝ ነበር። ባይሆን ባይሆን……
‘ለጊዜው ስለምታርፍበት ቦታ ማሰብ የለብህም። ልጄም ዩንቨርስቲ ስለገባች ብቻዬን ነኝ። እኔጋ ታርፋለህ!’ እለዋለሁ። አዲስ አንሶላ እንደገዛሁ ይነቃብኝ ይሆን? የእግሬን ኮቴ መላልሼ ከወለሉ ላስቲክ ላይ መወልወሌንስ? ተበድሬ የሰራሁት ዶሮ ወጥ ይጣፍጠው ይሆን ብዬ መጨናነቄንስ? ይወቃ! ብቻ እኔ ቤት ይረፍ! ብቻ እኔጋ ይረፍ! ግን እንቢ ቢለኝስ?
"ሰላም ሰማሽ?" ጊቢውን ገና ስገባ ባልደረባዬ ናት የተቀበለችኝ።
"ምኑን?"
"ሰሞኑን የገባውን እስረኛ…… ህፃን ልጁን ደፍሮ የገባው እንኳን?"
"እ?"
"አፄ ገደለው።" ምንድነው ያለችው ቃላቶቹ ጭንቅላቴ ውስጥ ተዋቀጡ። ሰውየው አፄውን ገደለው ነው ያለችው? አፄው ሰውየውን ገደለው? እሷ ቀጠለች።
"ትናንትና ከእስር ቤት መውጣት አልፈልግም ብሎ ጠይቆ ነበር አሉ። እና ሰውየውን ገድሎት ድጋሚ ፍርደኛ ሆነልሽ!!"

#መልሱልኝ_ልጄን
፡
፡
====
ይድረስ ለአባ ገዳ~ለጎሳ መሪዎች
ላገር ሽማግሌ~ለእምነት አባቶች
===
መንግስትን አምኜ~ወግ አያለሁ ብዬ
ልጄን ልኬ ነበር~ ተማሪልኝ ብዬ
ተምራ መምጫዋን~ቀኗን እያሰላሁ
ናፍቃኝ ቻል አድርጌ~ማየት እንደጓጓሁ
ልጅሽ ታግታለች~የሚል መርዶ ሰማሁ
===
ትማርልኝ ብዬ
ያይን ማረፊያዬን~ተስፋዬን ሰድጄ
ትኑር ትሙት አላውቅ~እጄን በላሁ በእጄ
እናም አሸማግሉኝ~ይቅርባት ትምህርቷ
ልጄን መልሱልኝ=ካለች በህይወቷ!!
፡
፡
====
ይድረስ ለአባ ገዳ~ለጎሳ መሪዎች
ላገር ሽማግሌ~ለእምነት አባቶች
===
መንግስትን አምኜ~ወግ አያለሁ ብዬ
ልጄን ልኬ ነበር~ ተማሪልኝ ብዬ
ተምራ መምጫዋን~ቀኗን እያሰላሁ
ናፍቃኝ ቻል አድርጌ~ማየት እንደጓጓሁ
ልጅሽ ታግታለች~የሚል መርዶ ሰማሁ
===
ትማርልኝ ብዬ
ያይን ማረፊያዬን~ተስፋዬን ሰድጄ
ትኑር ትሙት አላውቅ~እጄን በላሁ በእጄ
እናም አሸማግሉኝ~ይቅርባት ትምህርቷ
ልጄን መልሱልኝ=ካለች በህይወቷ!!