አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
578 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታሰረ_ነፃነት


#በሜሪ_ፈለቀ

የታሰርኩት አባቴን ገድዬ ነው። ፀፀት የለብኝም! 25 ዓመት ተፈርዶብኝ አጠናቀቅኩ። መውጣት ግን አልፈለግኩም።

"ከእስር ቤት መውጣት አልፈልግም!!" ቀጥተኛውና ለወህኒ ቤቱ አለቃ ሊገባው የሚችለው አገላለፅ ይሄ ስለሆነ እንጂ በእርግጥ ፍላጎቴ ከተናገርኳቸው አዘቦታዊ አራት ቃላት በላይ የተወሳሰበ ነው።

"አልገባኸኝም? እዚህ እስር ቤት መሻገት ነው የምትፈልገው?" አለኝ የዓይኑ ቋት የጠበበው ይመስል በተጎለጎለ ዓይኑ በቁመቴ ልክ እየገለበኝ።

"በቀጥታ አማርኛ አዎን እንደዛ ማለት ነው። እዚሁ መሻገት ነው የምፈልገው።"

"ሃሃሃሃሃ (ሲስቅ የዓይኑ ኳስ ብቻውን ይንቀጠቀጣል። ተሽቀንጥሮ የሚፈርጥ ስለሚመስል ውዳቂ ዓይኑ አፈር ሳይነካው እንድቀልበው መጠበቅ ያሰኘኛል።) እስረኛ ስታርበደብድ ዓለምን በእግርህ ስር ያኖርክ መሰለህኣ? ቂል ነህ አንተ ሰው? ‘አፄ’ ሲሉህ የምር የሆንክ መሰለህ? ሃሃሃሃሃ… ( ዓይኑ ቢፈናጠር ወደፊት ተለጥጦ እንደ ዝርግ ሰሃን ሰፋ ያለው የታችኛው ከንፈሩ ይቀልበው ይሆናል።)"

ዓለምን የምድር ያህል ያሰፋው ማነው? የህዋ ያህልስ? ምናልባት ያልተገኘ የህዋ አካል ተደምሮ የሚሆነውን ያህልስ ዓለምን የሚያሰፋት ማነው? ወይስ ምንድነው? ታዲያ የዓለም አድማስ ጥግ የእውቀትህ ልክ አይሆንም? የዓለም ስፋትና ጥበት ራስህ ውስጥ አይሆንም? ባወቅከው መጠን!

ሀያ አምስት ዓመታት እዚህ እስር ቤት ኖሬያለሁ። የልምዴ ጥግ ዓለሜን ጠባብ ያደርገዋል። ከዚህ ጊቢ ውጪ ያለው ዓለም ምኔም አይደለም። ምኑም አይደለሁም። የምናፍቀው የሚናፍቀኝም ሰው የለም። የታሰርኩት አባቴን ገድዬ ነው።(ዓለሜን በሰፊ ጊቢ ለማጠር እንዲመቻቸው ኢ– ሰብዓዊ የሆነ አገዳደል ይሉታል። በሱ ድብደባ  እናቴ ያለቀኗ ስትወልደኝ ሰብዓዊ ነበር። በየቀኑ እየሰከረ በአፍና በአፍንጫዋ ደም እስኪፈሳት ሲደበድባት ሰብዓዊ ነበር። እናቴ ገላዋ ላይ ካለው ቁስል ይልቅ ያን ዘግናኝ ግፍ እኔ ማየቴ ስለሚያማት በጊዜ እንድተኛላት ስትለምነኝ፣ በሰበብ ጎረቤት ስታሳድረኝ፣ ያየሁኝ ቀን ደምና እንባዋ ፊቷ ላይ ተቀላቅሎ ውስጧ ደብቃኝ ስትንሰቀሰቅ ሰብዓዊ ነበር። ልከላከለው የደረስኩ ሲመስለኝ እኔንም አብሮ ማጣጋቱም ሰብዓዊ ነበር። በጉልበት እንደተገዳደርኩት ሲገባው እኔንም እናቴንም በፀያፍ ምላሱ ሲልሰንም ሰብዓዊ ነበር። ……… ይሄ ሁሉ ነፍስ ስላልተከፈለበት ሰብዓዊ ነበር። …… በ22 ዓመቴ ጉልበቷንም ራሷንም ከፍላ እናቴ ከምታስተምረኝ የኮሌጅ ትምህርቴ ስመለስ አባቴ እየደበደባት ደርሼ ስደበድበው በእጄ ህይወቱ ማለፉ ይሄ ኢ–ሰብዓዊ ነበር።)

ሀያ አምስት ዓመታትን የተሻገረ ፀፀት የለኝም። እናቴ እዚሁ እያለሁ ታማ ሞታለች። ከዚህ ጊቢ ውጪ ያለው ዓለም ምኑ ይናፍቀኛል? እንዳለመታደል ሆኖ ከእናቴና ከአባቴ ውጪ በቅርበት የማውቀው ዘመድም ሆነ ጓደኛ አላስታውስም።

ይሄ ‘አፄ’ የሆንኩበት ዓለሜ ነው። የብረቶቹ ዝገት ዝገት የሚል ሽታ ፣ የጠባቂዎቹ ክክክክክ የሚል ሹክሹክታ ያለው ካኪ ልብስ፣ የክፍሎቹ እምክ እምክ የሚል ሽታ…… አሸርጋጅ ታሳሪ፣ በመፅሃፍ የተከበበ ፈላስፋ ወዳጅ፣ ጎማ ጎማ የሚል ደያስ(ጎማን መች ቀምሼው ነው ጣዕሙን ያወቅኩት?)፣ በልምድ የሚደላህ ድልዳል፣ …… ዓለሞቼ ናቸው።

" እንግዲህ የቅጣት ጊዜህን ጨርሰሃል። ከወንጀል ነፃ የሆነ ሰው እዚህ ልናቆይ አንችልም። ነገ ለመውጣት ተዘጋጅ!!" ጥዬው እየሄድኩ ሳቁ ይከተለኛል። አንድ ዓይኑ ተሽቀዳድማ ተስፈንጥራ ቀድማኝ እግሬ ስር የማገኛት ይመስለኛል።
                     ★    ★    ★    ★    ★

እርሱ እንዳለኝ የከበቡት ሰወች ፈርተውት እንደሚታዘዙት አልነበረም ገላዬ የታዘዘለት። በፍቅር እንጂ። ከእርሱ ውጪ ሁሉም ያውቃል። ፅዳቴን ብጨርስም ካላየሁት ቀኑን ሙሉ ተጎልቼ እንደምጠብቀው፤ ድምፁን ስሰማ በረጋ ለሊት የመብረቅ ብርቅታ እንዳስደነበረው ህፃን እንደምባትት ፤ ዓይኖቹ ከዓይኖቼ ሲጋጠሙ ላቤ በጀርባዬ ተንቆርቁሮ በቂጤ አካፋይ እንደሚያልፍ፣ በስፖርት የደነደነ ፈርጣማ ደረቱን ሲያንቀጠቅጠው ልቤ በአቃፊዋ ውስጥ እንደምትቀልጥ፣ የልጅነት ባሌ ከሞተ በኋላ ፍቅር ይሉት ነገር ቅብጠት ነው በምልበት እድሜዬ ሰማይ ላይ እንደተበታተነ ብጭቅጭቅ ደመና በፍቅሩ መበታተኔን……… ከእርሱ በቀር የሚያውቀኝ ሁሉ ያውቃል። ዛሬን እንደምጠብቅም ጭምር! እንደምወደው አውቆ ይሆን በተለየ ይቀርበኝ የነበረው? አላውቅም። ቆይ ግን ምንድነው የምለው?

‘አስር ድፍን አመታት የእስር ቤቱ ፅዳት ሆኜ ስሰራ በፍቅርህ ተንገብግቢያለሁ?’እንደዚህ ልለው አልችልም። ያን እንደበረዶ የቀዘቀዘ ፊቱን ነው የሚዘፈዝፈው።

‘የዛን እለት ታሳሪዎቹን ቋንቋ የምታስተምርበት ክፍል ጠረጴዛ ላይ ያደረግከኝን ሁሉ በቅደም ተከተል በህልሜ አየዋለሁ። ከዛን ቀን በኋላም በፊትም አይቼ የማላውቀውን ስትረካ የፈገግከውን ፈገግታህንም! ’ እንዲህ አይባልም አይደል? ‘እማ ግን ሰገጤነት አለብሽ!’ ትለኝ ነበር ልጄ ይሄን ብትሰማ! ከዛ ቀን በኋላ በጣም ተኮሳትሮ

"በሴት ላይ ግፍ መስራት አልፈልግም። አንቺ ደስ የምትዪ ሴት ነሽ የተሻለ ህይወት ይገባሻል። እየተጠቀምኩብሽ እንደሆነ ነው የተሰማኝ። ምንም እንዳላደረግን እርሺው።" ብሎኝ ነበር። ባይሆን ባይሆን……

‘ለጊዜው ስለምታርፍበት ቦታ ማሰብ የለብህም። ልጄም ዩንቨርስቲ ስለገባች ብቻዬን ነኝ። እኔጋ ታርፋለህ!’ እለዋለሁ። አዲስ አንሶላ እንደገዛሁ ይነቃብኝ ይሆን? የእግሬን ኮቴ መላልሼ ከወለሉ ላስቲክ ላይ መወልወሌንስ? ተበድሬ የሰራሁት ዶሮ ወጥ ይጣፍጠው ይሆን ብዬ መጨናነቄንስ? ይወቃ! ብቻ እኔ ቤት ይረፍ! ብቻ እኔጋ ይረፍ! ግን እንቢ ቢለኝስ?

"ሰላም ሰማሽ?" ጊቢውን ገና ስገባ ባልደረባዬ ናት የተቀበለችኝ።

"ምኑን?"

"ሰሞኑን የገባውን እስረኛ…… ህፃን ልጁን ደፍሮ የገባው እንኳን?"

"እ?"

"አፄ ገደለው።" ምንድነው ያለችው ቃላቶቹ ጭንቅላቴ ውስጥ ተዋቀጡ። ሰውየው አፄውን ገደለው ነው ያለችው? አፄው ሰውየውን ገደለው? እሷ ቀጠለች።

"ትናንትና ከእስር ቤት መውጣት አልፈልግም ብሎ ጠይቆ ነበር አሉ። እና ሰውየውን ገድሎት ድጋሚ ፍርደኛ ሆነልሽ!!"

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍3