አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
578 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የሚነበብ_ከንፈር 💋

ያው ጀመራት እነዚህን ጉልላት የመሰሉ ዓይኖቿን ከንፈሬ ላይ ታንገዋልላቸዋለች። እንኳን ለምን ቢሮዬ እንዳስጠራኋት እኔው ራሴ አሁን እዚህ ቢሮ መሆኔን ብጠየቅ የማስታውስ አይመስለኝም።

"ዶክተር? ዶክተር? ዶክተር?” አሁን የት እንዳለሁ አወቅኩ። ግንሳ እነዚህን ዓይኖቿን ካላሳረፈቻቸው እንዴት ነው ከዚህ ሌላ ማሰብ የምችለው?

"አቤት ህሊና?” ያልኩበት ድምፀት ለምን እንደፈለገችኝ እሷ ልትነግረኝ እንጂ እኔ ያስጠራኋት አይደለም የሚመስለው።

" ለምንድነው ያስጠሩኝ ዶክተር? ችግር አለ?” ለምንድነበር ያስጠራኋት? እህህህህ ዓይኗን ከከንፈሬ ላይ ካልነቀለች ለምን እንደፈለግኳት በምን አውቃለሁ? ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እንደትያትረኛ ተንጎራደድኩ(ተንጎማለልኩ።) እኔ ያየኋቸው ጥቂት የኢትዮጵያ ትያትሮች ላይ ተዋናዩ ታሪኩ ላይ የሚጨምረው ምንም ፋይዳ የሌለውና አስፈላጊነቱ የማይገባኝ መንጎራረድ  መድረኩ ላይ አንድ ሶስቴ ይንጎማለላል። እንደዛዛዛዛ አደረግኩ። እኔ ግን ዓይኗን ሽሽት ነው። ለምን እንደጠራኋት አሁን መጣልኝ። 

ህሊና እኔ በማስተምርበት ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ናት። እንኳን እንደእኔ አይነቱን ዓይንአፋር እኔ ነኝ ያለ ጀግና ወንድ ብርክ የሚያሲዝ ህልም መሰል ውበት አላት። እኔ እሱ አልነበረም ችግሬ። ቆንጆ ትሁን ፉንጋ ከሴቶች ጋር ተከባብሬ የኖርኩ ሰው ነኝ። አይደርሱብኝም። አልደርስባቸውም። የህሊና ጉዳይ የተለየ ነው። በገባሁባቸው አራት ክላሶች ሁሌ ከፊት ነው የምትቀመጠው። እሱም ባልከፋ! እነኚህ አደንዛዥ ዓይኖቿን ከከንፈሬ ላይ ለደቂቃ አትነቅልም። በስህተት መስሎኝ ተከታተልኳት…… ሃሃሃሃ አቃቂያለችኝ እንጂ ሁላ…… የመጀመሪያ ቀን እቤቴ እንደገባሁ ከንፈሬን በመስታወት አየሁት። ሆ! …… ለዓመታት በልበ ሙሉነት ያስተማርኩት ሰውዬ መንተባተብ እጀምራለሁ። ላብ ያጠምቀኝ ይጀምራል።…… አንዱን ቀን ክላሱን ሳልጨርስ አቋርጬ ወጣሁ። ሆሆ!

ምንድነው የምላት? እባክሽ ዓይኖችሽን ከከንፈሬ ላይ ሰብስቢልኝ? ማስተማር ስላቃተኝ ዓይንሽን አሳርፊልኝ? ምን አስበሽ ነው እንደዚህ የምታደርጊው?  ኡፍፍፍፍ……

"ዶክተር?” አለችኝ ጀርባዬን ሰጥቻት ለብዙ ደቂቃ መቆሜ ግራ ገብቷት መሰለኝ። ደሞኮ ድምፅዋ ራሱ የሆነ የፈጣሪ ምህረት የሚመስል ለዛ አለው።

"አቤት! እ…… እ…… የጠራሁሽ…” መንተባተብ ሲያስጠላ! ኸረ ዶክተር ትልቅ ሰው አይደለህ ምን ያንተባትብሃል? ራሴን ገስፃለሁ።

"ዶክተር ከንፈርዎትን ካላየሁ አልረዳዎትም።” ምን አለች? ምን አለች? ምን…… ምን?ጆሮዬ ሲሰማ ስቶት ነው።

"አቤት?” አልኳት ዓይኖቿን ሳልፈራ ተጠግቻት። ሳቅ እንደማለት አለች። መሰለኝ።

"ትንሽ የመስማት ችግር አለብኝ። ሲያወሩ ከንፈሮትን ካላነበብኩ ሁሉንም ቃላት ላልሰማ እችላለሁ። ባጋጣሚ ለሁሉም መምህሮቼ ስናገር  ለርሶ ሳልነግር ቀርቼ ነው።”

የባሰው መጣ!!!

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1