አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ትላንት ማታ ጀምሺድ ሻይ ላጠጣህ ብሎ ወሰደኝ» አለ
ሉልሰገድ። (ይህ የሚሆነው ጀምሺድ ድኖ ከተነሳ በኋላ ነው።)
ጀምሺድ በተገማመደ ፈረንሳይኛው ኮሚክ ወሬ እያወራ
ሻይውን ጨርሰው ሲያበቁ
«አንድ ነገር ሊያሳይህ?» አለው
«አሳየኝ» ሲለው፣ ከጠረጴዛው ኪስ ውስጥ ሽጉጥ አወጣ፡፡
ጥይቶችም አወጣና አጎረሰ። አንድ ቃል ሳይናገር ሽጉጡን አቀባበለ
«አሁን መተኮስ ብቻ፡፡ አንዲት ጣት። እንደዚህ» አለና ሽጉጡን
ሉልሰገድ ደረት ላይ አነጣጠረው
ሉልሰገድ ለመሳቅ እየሞከረ፣ ግን ላቡ ግምባሩ ላይ ብቅ ብቅ
እያለ ተው እንጂ። ይባርቃል» አለ፡፡ ድምፁ የሌላ ሰው ሆኖ
ተሰማው ጀምሺድ ሽጉጡን እንዳነጣጠረ
«አይባርቅ። እኔ የፈለግኩ ይባርቅ፡፡ እኔ ሳልፈለግኩ አይባርቅ» አለ። ፊቱ ላይ ዝምተኛ አይነት ቁጣ ሰፍሯል፤ አይኖቹ ውስጥ ምህረት የማያውቅ ጭካኔ አድፍጧል
ሉልሰገድ በድንጋጤና በፍርሀት ውሀ ሆኗል፡፡ ላቡ ከግምባሩ
ወደ ጐን ይወርዳል። መሀረቡን አወጣና ግምባሩን ጠረገ። እጁንም ጠረገ፡፡ አጁ ይንቀጠቀጣል። ጀምሺድ አሁን ቢተኩስስ?
ጀምሺድ ሽጉጡን ወደ ሉልሰገድ ግምባር አነጣጠረ
«አሁን እተኩስ፣ ጥይት አይኖችህ መሀል» አለ
“ምን አረግኩህ?»
«ምንም»
«እንግዲያው ሽጉጡን ወደዚያ በለዋ»
«ቆይ አንድ ነገር ሊነግርህ»
“እሱን ወደዚያ በለውና ትነግረኛለህ»
«የለም፡፡ እኔ ሲነግርህ፤ ሽጉጥ አይኖችህ መህል። ያን ጊዜ ጥሩ
ሉልሰገድ እንደገና ግምባሩን እያደረቀ እሺ ንገረኝ» አለ
“ኒኮል። ተው። በቃህ ኒኮል ቤት መሄድ የለም፡፡ ኒኮል
ስትሄድ በትልልቅ አይን ማየት የኒኮል ቂጥ በአይን መብዳት
የለም፡፡ አለዚያ ጥይት! በአይንህ መሀል! እሺ?»
«አሁን ተነሳ፡፡ ሂድ፡፡ ደህና እደር፡፡
ደህና እደር» ብሎ ሉልሰገድ ተነስቶ ወጣ። ባቡር መንገድ
ሲደርስ አስታወከው:: ብርድ ብርድ አለው
ቤቴ ሄዶ ገላውን ታጥቦ ጥርሱን ቦርሾ ወደ ከተማ ተመለሰና
አንድ ቢራ ጠጣ፡፡ ይህን ጊዜ ስድስት ሰአት ይሆናል
«አሁን የምነግርህ በሙሉ የሆነ ነገር ነው» አለኝ ሉልሰገድ ግን
እኔ ራሴ በፈቃዴ የሰራሁት አይደለም። የማደርገውን ሁሉ፥
ከማድረጌ በፊት አንድ ደቂቃ አስቀድመህ አሁን ምን ልታደርግ
ነው? ብትለኝ እንጃ ነበር የምልህ፡፡ ምክንያቱም፣ አላውቀውም
ነበር። እኔ አይደለሁማ ያደረግኩት! ውስጤ አንድ ባእድ መንፈስ ወይም አጋንንት ገብቶ ነው የሰራው፣ ሳላውቀው ይታወቀኛል የሆነ ሆኖ ምን ሰራህ?» አልኩት።

ቢራዬን ከጠጣሁ በኋላ ሰአቴን አየሁ። ስድስት ከሃያ። በቀጥታ
ኒኮል ቤት ሄድኩና አንኳኳሁ፡፡ ክፈች፣ የምነግርሽ አለኝ» አልኳት፡፡
ከፈተች። ገባሁና ወደ አንድ በኩል ገፍቻት በሩን ቆለፍኩት።
ረዥም ስስ የሌሊት ቀሚሷን ለብሳ፣ ላይዋ ላይ ከፎጣ የተሰራ የቤት ውስጥ ካፖርት ደርባለች
«ሂጂ ውሀ አምጪልኝ ጠምቶኛል» አልኳት። ስታመነታ
ገፈተርኳት። ቃል ሳትናገር ወደ ወጥ ቤቷ ሄደች፡፡ ወደ መኝታ
ገባሁና በፍጥነት ልብሴን ማውለቅ ጀመርኩ፡፡ ለምን? ብለህ ብትጠይቀኝ በጭራሽ አላውቀውም፡፡ ጋኔን ሰፍሮብኛል ብዬሀለሁ። ውሀውን ይዛ እንግዳ ቤት ስትገባ አጣችኝ፣ የት ነህ?» አለች
«ነይ ወዲህ አልኳት። ገባች፡፡ በሩ አጠገብ እንደቆመች
ቀረች። ወለሉ መሀል እጆቼን ወገቤ ላይ አድርጌ ቆሚያለሁ፣
ራቁቴን ነኝ ቁላዬ ግትር ብሎ ቆሞ፣ ትር! ትር ትር! አያለ
ዳንኪራ ይረግጣል። አስታውስ፣ ይህን የምሰራው አሁን የማወራልህ ሉልሰገድ እንዳልመስልህ። ሌላ ሰው ነኝ
«አውልቂ!» አልኳት፡፡ አቤት ድምፄ ውስጥ ያለው ትእዛዝ!
ምርጫ አልነበራትም፡፡ የውሀውን ብርጭቆ ኮሞዲኖው ላይ አስቀመጠችና፣ የፎጣ ካፖርቷንና የሌሊት ቀሚሷን አውልቃ እዚያው ወለሉ ላይ ጣለችው:: ዝም ብዬ ሳፈጥባት ጡት መያዣዋንና ሙታንቲዋን አወለቀች
«ነይ ወዲህ!» አልኳት፡፡ መጣች። ፊቴ ተምበረከከች።
አቀፈችኝ። ከዚያ በኋላ ያለውን እንዳልነግርህ : እንግዲህ መናገር የሚገባ አይመስለኝም፡፡ አየህ፣ ራቁታም ባለጌ ከመሆኗ የተነሳ ቅዱስ ምስጢር ይሆናል። እና ብናገረው ቃላቱ ያረክሱታል፡፡ ብቻ፣
ከተፈጠርኩ እንደ ትላንት ያለች ሌሊት አሳልፌ አላውቅም። እኔ
እምለው፣ እንደ ኒኮል ያለች ሴት እየበዱ ሁለት አመት ኖረው
ቢሞቱ ምን አለበት?

ጧት ወደ አምስት ሰአት ላይ ነቃሁ። ኒኮል ተኝታለች፡፡
እንዳልቀሰቅሳት ቀስ ብዬ ልብሴን ለብሼ ወጣሁ አሁንም የትላንት ሊሊቱ መንፈስ እየነዳ ጀምሺድ ቤት ወሰደኝ ገባሁና ጀምሺድን «ሻይ አፍላልኝ» አልኩት። ለምን
እንደመጣሁ ግራ ገብቶታል። ሻይውን ከጠጣን በኋላ ተነሳሁና
ቆምኩ። አይን አይኑን እያየሁ
«ትላንት ማታ የሽጉጥህን ቀዳዳ አይቼ ቆመብኝ አልኩት
እየሳቀ እና?» አለኝ
“እና እምስ አስፈለገኝ። እና ሄጀ ኒኮልን በዳኋት» ሳቁ ጠፋ፡፡ አይኖቹ ውስጥ የትላንቱ ጭካኔ ብቅ አለ። ተነሳ።
አቤት አይኖቹ ሲያስፈሩ እዚህ ጀርባዬ ውስጥ ብርድ ተሰማኝ፡፡
ተነሳና እጁን ትከሻዬ ላይ እያሳረፈ በጨካኝ አይኖቹ እያየኝ
«ጎበዝ ነህ፡፡ በጣም ጎበዝ፡፡ አንድ ቀን እገድልሀለሁ፡፡ ሂድ»
አለኝ። ትቼው ሄድኩ፡፡ አይኖቹን ሳስታውስ አሁንም ጀርባዬን
ይበርደኛል (አለኝ ሉልሰገድ ከዚህ ከሽጉጥ ፍጥጫ በኋላ ጀምሺድና ሉልሰገድ ብዙ ጊዜ፤ብዙ ቦታ አብረው ይታዩ ጀመር፡፡ ማታ ሁለቱ በጀምሺድ መኪና ይሄዱና፣ ኒስ፣ ካን ወይም ሞንቴካርሎ ቁማር ሲጫወቱ ሰንብተው ሰኞ ጧት ይመለሳሉ። ከውጭ ለሚያየው ሰው ጓደኝነታቸው እየጠበቀ ሄዴ


💫ይቀጥላል💫
👍241
#ድንቡጮ_ለምን_ለምን_ሞተ?


#አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

ሰፈራችን ውስጥ መክብብ ግሮሰሪ የምትባል አለች። ማታ ማታ ፀሐይ ሲያዘቀዝቅ ትልልቅ ሰዎች በረንዳዋ ላይ ተሰባስበው እያወሩ ጅን የሚባል መጠጥ ድርፍጭ ባሉ ብርጭቆዎች የሚጠጡባት።በግሮሰሪዋ ሁሉም ዓይነት መጠጥ ቢኖርም በረንዳ ላይ የሚቀመጡት ሽማግሌና ጎልማሶች ግን ልክ ዕድሜ ይቀጥል ይመስል ጅን ብቻ ነበር የሚጠጡት። በሯ ላይ በግራ በኩል እንደ ኤሊ ፍርግርግ
ድንጋይ የለበሰ የሚመስል ግንድ ያለው የዘንባባ ዛፍ የግሮሰሪዋ ግርማ ሞገስ ነው። ይህች የዘንባባ ዛፍ ለጥምቀት ሰፈራችንን አቋርጠዉ የሚያልፉት ሁለት ታቦታት ከመለያየታቸው በፊት የሚቆሙባት የታቦት መቆሚያ ነበረች። ባለቤቱ አባባ መክብብ ይባላሉ።አጭር፣ ሙሉ ፀጉራቸውን ነጭ ሽበት
የወረሰው፣ ከባድ ሌንስ ያለው መነፅር የሚያደርጉ ሰውዬ ናቸው።

አባባ መክብብን ባየኋቸው ቁጥር የሚገርሙኝ ሁለት ነገሮች አሉ። የመጀመሪያው ግርምቴ አፋቸው
ውስጥ ምግብ ኖረም አልኖረም በባዶው ያላምጣሉ። አፋቸው አያርፍም፤ ዝም ብሎ ያላምጣል። በፊት በፊት ማስቲካ የሚያላምጡ ይመስለኝ ነበር። ታዲያ ትልልቅ ሰዎች ማስቲካ ብዙም ስለማያላምጡ አባባ መክብብ ዘመናዊ ሽማግሌ ይመስሉኝ ነበር። በኋላ ከፍ ስል ግን እንደው ልማድ ኾኖባቸው ነው…. ሲባል ሰማሁ። ሲያወሩ ሁሉ በየመሀሉ ባዶ አፋቸውን እንደሚያላምጥ ሰው እያንቀሳቀሱ አየር ያኝካሉ። ሁልጊዜ ሙልጭ ተደርጋ የምትላጭ ትንሽ አገጫቸው ላይና ታች ከፍ ዝቅ ስትል ነው
የምትውለው። ታዲያ አንዳንዴ ሊልኩኝ ፈልገው ወይም ለሆነ ጉዳይ በባዶው በሚያኝኩት አፋቸው “አብራም” ሲሉኝ ስሜን አላምጠው የተፉት ይመስለኛል። በዛ እድሜዬ የሚመስለኝ ነገር ይበዛ ነበር።

ሁለተኛው ከአባባ መክብብ የሚገርመኝ ሱሪያቸው ነው። ሱሪያቸው ከታች እስከላይ ይገርመኛል።ከግርጌው እንደዣንጥላ ጨርቅ ወደ አንድ በኩል ተጠምዝዞ ይጠቀለልና ካልሲያቸው ውስጥ ይጠቀጠቃል። በእርግጥ የእኔም አባት እንደዛ ያደርጋል። ግን አባባ እንደዛ የሚያደርገው ዝናብ ጥሎ
መሬቱ ሲጨቀይ ብቻ ነው። አባባ መክብብ ግን ሁልጊዜም ነው የሚያጭቁት። ከላይ ደግሞ ጥቁር የቆዳ ቀበቷቸው ወገባቸው ላይ ሳይሆን ከእንብርታቸው ከፍ ብሎ ከልባቸው ሥር ... እዛ ላይ ነው ቅብትር ተደርጎ የሚታሰረው። ከነተረቱ ሰፈራችን ውስጥ የሆነ ሰው ሱሪውን ከፍ አድርጎ ከታጠቀ
“ምነው እንደአባባ መክብብ ሱሪህን ደረትህ ላይ ሰቀልከው ?” ይባላል።

ሌላም የረሳሁት ሦስተኛ አስገራሚ ነገር አለ። አባባ መክብብ ደንበኞቻቸውን እያስተናገዱ (ሁሉም ደንበኞቻቸው በርሳቸው ዕድሜ ስለሆኑ ከደንበኛ ይልቅ ጓደኞቻቸው ይመስሉኛል) ከመኪና ላይ ቢራ እያስወረዱ ወይም ግሮሰሪው በር ላይ በጉርድ የብረት በርሚል የተሞላ ፉርሽካ ተዘርግፎላቸው የሚበሉትን ሦስት ሙክት በጎቻቸውን እየተመለከቱ የሚሠሯት አንዲት ነገር አለች፤ ከእጃቸው በማትለየውና የቀንድ እጀታ ባላት የጢም መላጫቸው በደረቁ ጉንጫቸውን፣ አገጫቸውንና የአገጫቸውን ሥር ይፈገፍጋሉ ሁልጊዜ። እንደውም ሰው ሰላም ሲሉ የጢም መላጫቸውን በቀኝ እጃቸው ስለሚይዙ ለመጨበጥ አይመቻቸውም። እናም እንደጨበጧት አይበሉባቸውን
አዙረው ሰላም ወደሚሉት ሰው እጅ ይዘረጉና ነካ አድርገውት እጃቸውን ይመልሳሉ። ታዲያ የጢም መላጫቸውን የበረንዳዋ መከለያ ብረት ላይ ኳ ኳ አድርገው ያራግፏታል ! ድምፁ እስካሁን ጆሮዬ ላይ አለ።

አባባ መክብብ በመንደሩ ሰው በሙሉ “ደግ ሰው ናቸው…” ነው የሚባሉት። ግሮሰሪው በር ላይ
ለበጎቻቸው ፉርሽካ ከሚቀመጥበት ጎራዳ በርሚል ራቅ ብሎ ሰማያዊ የፕላስቲክ በርሚል በውኃ ተሞልቶ ይቀመጣል። በርሚሉ ጋር በረዶ በመሰለች የኤሌክትሪክ ገመድ ጫፏ ተበስቶ የታሰረ ቢጫ
የቲማቲም ሥዕል ያለባት የመርቲ ጣሳ አለች ... በርሚሉና ጣሳው ከድሮ ጀምሮ ስለማይነጣጠሉ
በኤሌክትሪክ ገመድ እትብት የተያያዙ እናትና ልጅ ይመስሉ ነበር። እንግዲህ አላፊ አግዳሚ የኔ ቢጤ ውኃ ከጠማው ከዛ በርሚል በጣሳዋ እየጠለቀ ይጠጣል። ትንሽ ልጆች እንደነበርን ውኃው የተለየ
ነገር ስለሚመስለን እኛም እየተደበቅን እንጠጣ ነበር። በኋላ ግን ወላጆቻችን “ማንም በሚጠጣበት እየጠጡ ኮሌራ ሊያመጡብን…” እያሉ ሲቆጡን አቆምን !

ምንጊዜም የቡሄ በዓል ሲሆን የሰፈር ልጆች ተሰባስበን አንደኛ የምንሄደው አባባ መክብብ ግሮሰሪ ነበር። ፈንታው ድንቡጮ የሚባል ጓደኛችን አውራጅ ይሆናል። አባባ መክብብ ፈንታውን በጣም ነው የሚወዱት። ጉንጩ ድንቡጭ ያለ ስለሆነ ነው መሰል 'ድንቡጮ' እያሉ ነው የሚጠሩት። በዚሁ ሰበብ ጓደኛችን ፈንታው ፈንታው ድንቡጮ ተብሎ ቀረ። ግሮሰሪዋ በር የዘንባባውን ግንድ ተገን አድርጎ
የተቀመጠ ትልቅ ድንጋይ ላይ ካርቶን ጣል አድርጎ እንደ ወንበር በመጠቀም ሊስትሮ ይሠራል።
ጫማውን የሚያስጠርገው ደንበኛ ድንጋዩ ላይ ተቀምጦ የዘንባባውን ግንድ ደገፍ ይልና ከድንጋዩ ሥር
ብሩሹን ይዞ ለሚጠብቀው ፈንታው እግሩን ያቀብለዋል። ታዲያ ያች ድንጋይ የፈንታው ድንቡጮ ድንጋይ' ነው የምትባለው። የእኛ ሰፈር አክሱም ናት. የእኛ ሰፈር ላሊበላ ናት... የእኛ ሰፈር ውቅር የሊስትሮ ወንበር ናት ... የእኛ ሰፈር አፈ ታሪክም ናት!

“በድሮ ጊዜ እግዜር ለቅዱስ ድንቡጮ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፣ 'ልጄ ድንቡጮ ሆይ፣ ምድር የእግሬ መርገጫ መሆኑን ሰምተሃል.. እንግዲህ እግሬ ምድር ላይ ሲያርፍ የወርቅ ጫማዬን ትቦርሽ ዘንድ የእግሬን ማረፊያ ድንጋይ በዚህ አስቀምጥ .. የሚል ራዕይ ተገልጦለት ከእንጦጦ ድረስ ይቺን ድንጋይ በኤኔትሬ መኪና አስጭኖ ወደዚህ ሰፈር አመጣት .…”

ታዲያ የሰፈሩ ልጆች ለቡሄ አባባ መክብብ ግሮሰሪ በር ላይ እንሄድና ጭፈራውን እናወርደዋለን።እሳቸውም በጢም መላጫቸው ግራ ቀኝ ጉንጫቸውን በደረቁ እየፈገፈጉና ብረቱ ላይ
ኳኳ አድርገው እያራገፉ ግጥማችንን በጥሞና ያዳምጣሉ፤

“እዛ ማዶ…
ሆ!
አንድ ሞተር
ሆ!
እዚህ ማዶ!
ሆ!
አንድ ሞተር!
ሆ!
የኔ አባባ መከብብ!
ሆ!
ባለ ዲሞፍተር!
"ሂዱ ወዲያ ! የምን ዲሞፍተር ነው …” ይሉና ይቆጣሉ። ረስተነው ነው እንጂ አባባ መክብብ የጦር
መሣሪያ አይወዱም። እንደውም መሣሪያ ታጥቆ ወደ ግሮሰሪያቸው የሚሄድ ደንበኛ ያስወጣሉ
እየተባለ ይወራ ነበር። ታዲያ ይችን አመላቸውን ስለምናውቅ በቁጣቸው አንደነግጥም። ፈንታው ድንቡጮ ወዲያው ግጥሙን ይቀይረዋል … እሳቸውም ወዳቋረጡት ጢም መላጨታቸው ተመልሰው
አንጋጥጠው የአገጫቸውን ሥር እየፈገፈጉ ዓይኖቻቸውን ጨረር እንዳይወጋቸው ጨፍነው
ይሰሙናል ...

“እዛ ማዶ!አንድ አፍንጮ፣
የኔ አባባ መክብብ ባለ ወፍጮ…!
እዛ ማዶ!አንድ በሬ፣
የኔ አባባ መክብብ ጀግና ገበሬ..”

ሃሃሃሃ እንደሱ ነው የሚባለው እደጉ! እደጉ! ድንቡጮ! ... ና ወዲህ …” ይሉና የጢም
መላጫቸውን ወደ ግራ እጃቸው አዘዋውረው በቀኝ እጃቸው አጭሯን የሥራ ገዋን ወደ ቀኝ ገልበው ሱሪያቸው ኪስ ውስጥ እጃቸውን ካስገቡ በኋላ በጣም ብዙ ተዘበራርቆ የተቀመጠ ብር (ድፍን የመቶና የሃምሳ ብር ኖቶች የሚበዙበት) ዘግነው ያወጣሉ። ከዝግኑ መሃል መርጠው ድፍን አምስት ብር ከለዩ
በኋላ (ይሄ ድርጊታቸው ቀልባችንን ስለሚወስደው ጭፈራችን ቀዝቀዝ ይላል…) ሌላውን ብር ወደ ኪሳቸው መልሰው ሲያበቁ ብሩ ላይ ትፍ ትፍ ብለው ድንቡጮ ግንባር ላይ ይለጥፉታል (እንደውም
ግንባሩ ለሽልማት ይመቻል) ..እኛም ሞቅ ይለናል ፤ ጭፈራውን በአዲስ ጉልበት ምርቃቱንም ለየት ባለ ፍቅር እናዥጎደጉደዋለን።
👍25🔥31
“የመክብብን ቤት!
ድገምና !!
ዓመት
ድገምነ !!
ወርቅ ይፍሰስበት!!
ድገመና !!
ዓመት .….!” አባባ መክብብ ደስ በሚል ፈገግታ በተዋበ ፊት እያዩን ይቆዩና…፣

“ወይ እነዚህ ልጆች ምርቃቱን ከየት ከየት ነው የሚያመጡት? እትየ ንግሥትን ሄዳችሁ እንኳን
አደረሰሽ' በሏት እንዳትረሱ……” ይሉናል። እትየ ንግሥትኮ ሚስታቸው ናቸው። አይገርምም?
ሲጠሯቸው እትየ ንግሥት እያሉ ነው። የእትየ ንግሥት ስም ሲነሳ ምን የመሰለ ሲነኩት ትሙክ ትሙክ የሚል ነጭ የድፎ ቁራሽ ትዝ ይለናል። የአባባ መክብብ መኖርያ ቤት ከግሮሰሪው ብዙ አይርቅም።በአስቻለው ወፍጮ ቤትጋ ወደ ግራ እጥፍ ሲባል ያለው ትልቁ ግቢ ቤት ነው።
ስንደርስ ልክ እንደራሳችን ቤት የግቢውን በር አልፈን እንገባለን። ለማዳው ውሻቸው 'አሲምባ' እንደ
እንቦሳ በዙሪያችን እየፈነጠዘ ይቀበለናል። የውሻው ስም አሲምባ ነው። ይሄ ውሻ በሁሉም የመንደሩ ነዋሪ እንደ አንድ የመንደሩ ነዋሪ ነው የሚታየው። ሥጋ ተቀቅሎ ጨው ካልተነሰነሰበት እና ሁልጊዜ
በአጃክስ ታጥቦ የሚቀመጥ ወጨት ላይ ቀርቦ ካልተሰጠው ንክች አያደርግም። እንደውም አንድ ቀን እማማ ንግሥት እኛ ቤት መጡና እናቴን እንዲህ አሏት….

“የጊወርጊስ ጠበል አለሽ እንዴ? እስቲ በእቋ ቆንጥረሽ ስጭኝ”

“ምነው ማን ታመመ እማማ ንግሥት…?” አለቻቸው ጠበሉን መቀነሻ እቃ እየፈለገች።

“ኧረ አልተሞሞም… አንድ ዉሻ ዘው ቡሎ ጎትቶ የአሲምባን ዎጩት ለከፈበት” እናቴ በሳቅ ወደቀች።እንግዲህ አንድ የመንደሩ ውሻ የእማማ ንግሥትን ውሻ እቃ “ስለለከፈው” ፀበል ረጭተው ሊቀድሱለት ነበር። እዚህ ድረስ የሚታሰብለት ውሻ ነበር።

በዛ ላይ ግዝፈቱ እና ቀይ ቆዳው ላይ አልፎ አልፎ ጣል ጣል ያደረገበት ነጭ ቡራቡሬ ቀለሙ ልዩ ውበት ያላብሰዋል።

በረንዳው ላይ የተነጠፈውን ሴራሚክ ብትራችንን እያንኳኳን እማማ ንግሥትን እናሞግሳለን…፤
የብትሩ ኳኳታ ጭፈራችንን ያደምቅልናል!

“የኔ እማማ ንግሥት የሰጠችኝ ሙክት፣

አልችለው ብየ እመንገድ ጣልኩት…”

እማማ ንግሥት በወርቅ የተሽቆጠቆጠ ተራራ የሚያህል ሹርባቸው ላይ ነጠላቸውን ጣል አድርገው
(ነጠላ የለበሰ ጉብታ) ነጭ ባለጥልፍ የሐገር ባህል ቀሚስ ደረቱ ላይ ትልቅ መስቀል የተጠለፈበት ቀሚስ ለብሰው ከቤት ብቅ ይላሉ። ባዷቸውን አይደለም፤ ጋሻ የሚያክል፣ ከስፖንጅ ፍራሽ ላይ
የተቆረጠ ትልቅ ቁራጭ ስፖንጅ የመሰለ ድፎ ከፍ አድርገው ይዘው፤ በዜማችን እየተውረገረጉ
ዳቦውን እንደዋንጫ ከፍ አድርገው እያስጨፈሩት ከሚፍለቀለቅ ፈገግታቸው ጋ ብቅ ይላሉ።አቤት ደስታችን! ምራቃችን በአፋችን ይሞላል። ዳቦውን እንደ ጎበዝ ጎል ጠባቂ የዳንቴል መረቡን በተጠንቀቅ ዘርግቶ ለቆመው አለባቸው ይሰጡታል። በዳንቴሉ ተቀብሎ ጥቅልል ያደርግና ደረቱ ላይ ለጥፎ ያቅፈዋል። ፍጥነቱን ለተመለከተው መልሰው እንዳይቀሙት የፈራ እኮ ነው የሚመስለው !

“ዓመት አውዳመት!
ድገምና!
ዓመት!
ድገምና!
የንግሥትን ቤት!
ድገመና!!
ዓመት!
ድገመና!
ወርቅ ይፍሰስበት ….”

“እደጉ ልጆቸ እድእግ በሉ !! ወርቅ ይፍሶስቦት ሟለት ትልቅ በረከት ነውኮ…፤ ከወርቅ በሏይ ሙን
አለ…? ቡዙ ተብዛዙ ቁም ነገር ያቡቋችሁ..! አቡነ አረጋዊ ጭንቅላታቹሁን ይከፋፍተውና ትሙሩቱ ይግባዓባችሁ…” ብለው ይመርቁናል። አፋቸው ይጣፍጣል። እማማ ንግሥት ኤርትራዊት ናቸው። ታዲያ በአማርኛ ሲያወሩ አንደበታቸው አይጠገብም። ጥርስ የማያስከድኑ ተጨዋች ናቸው። ሲቆጡም በዚያው ልክ ነው ይባላል ሲቆጡ አይተናቸው አናውቅም......

ይቀጥላል
👍136
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

....ከዚሀ ከሽጉጥ ፍጥጫ በኋላ ጀምሺድና ሉልሰገድ ብዙ ጊዜ፤
ብዙ ቦታ አብረው ይታዩ ጀመር፡፡ ማታ ሁለቱ በጀምሺድ መኪና
ይሄዱና፣ ኒስ፣ ካን ወይም ሞንቴካርሎ ቁማር ሲጫወቱ ሰንብተው ሰኞ ጧት ይመለሳሉ። ከውጭ ለሚያየው ሰው ጓደኝነታቸው እየጠበቀ ሄዴ..

ክረምት እየተንፏቀቀ መጣና፣ ከወርቃማው በልግ ጋር ተቃቅፋ
የነበረችውን የኤክስ ከተማ እንደ ቀናተኛ ሌላ ውሽማ በብርድ
ይገርፋት ጀመር፡፡ ሽማግሌዎቹንና አሮጊቶቹን ከየመንገዱና
ከየመናፈሻው አባረሯቸው። ልጃገረዶቹ ቆንጆ ስስ ቀሚሳቸውን
ትተው ወፍራም ሱፍ ቀሚስ፣ ሱሪና ወፍራም ሹራብ፣ ካፖርት
እየለበሱ፣ ውብ ቅርፃቸውን ከክረምቱ አይን እየሽሽጉ በበጋ ቀያይ ወይም ብር መሳይ የጥፍር ቀለም ተቀብተው ሲውለበለቡ የነበሩትን ጣቶቻቸውን በወፍራም ጓንቲ ውስጥ እየደበቁ፤ ከክፍል ወደ ምግብ ቤት፣ ከምግብ ቤት ወደ መኝታ ቤት በፍጥነት ኩስ ኩስ ይሉ ጀመር። ውብ ዳሊያቸውን እያወዛወዙ በዝግታ መራመድ፣ ፅጌረዳ ጉንጫቸውን እያሳዩ፣ በቀያይ ከንፈራቸው እየሳቁ፣ በተኳላ አይን
ጎረምሳውን መቃኘት ቀረ፡፡ (ኩሉንና የከንፈር ቀለሙን ብርድ
ስለሚሰነጣጥቀው ለአይን ደስ አይልም።) ደም የሽሽውን ነጭ
ጉንጫቸውን ግራጫ ብጤ የጎሽ ፀጉር ወረረው በየመንገዱ ዳር በተርታ የተተከሉት ዛፎች ራቁታቸውን ቆመው
የኤክስን ንፁህ ሰማይ በጭራሮዋቸው ይቧጥጡታል። ቅጠሎቹ በሙሉ ረግፈው የባቡር መንገዱን ዳርና የሰው መተላለፊያውን ሞልተውታል። ሰው በፍጥነት ሲራመድ በቡት ጫማው ይፈጫቸዋል

አንዳንድ ቀን በረዶው እንደ ጥጥ በዝግታ ይወርድና ኤክስን
በንፁህ ነጭ ሻሽ ይገንዛታል። በሱፍ የተከናነቡት ልጃገረዶችና
ጎረምሶች ሜዳ ወጥተው በረዶውን እያድቦለቦሉ ይፈነካከታሉ ይሳሳቃሉ። ትንፋሻቸው እንደ ጉም ከአፋቸው ቡልቅ ቡልቅ! ሲል ይታያል። ጥቁሮቹ በረዶው ላይ እየሆኑ ፎቶግራፍ ይነሳሉ የኤክስ ሰማይ አብዛኛውን ጊዜ ብሩህ ሰማያዊ ነው። አንዳንድ ጊዜ ውሀ አረንጓዴ ይሆናል፣ ወደ ማታ ሰአት እንደ ልጃገረዶች ጉንጭ ይቀላል። የኤክስ ሰማይ ደመና አይለብስም፡ ሁልጊዜ ራቁቱን ነው፣ ሁልጊዜ ውብ ነው፤ ሁልጊዚ ሰሳማዊ ነው። ማታ ማታ የአልማዝ ከዋክብትና የፀጥታ ሰላም ይለብሳል

ክረምት ሲሆን ሌሊቶቹ ይረዝማሉ፣ ቀኖቹ ያጥራሉ፤ ፀሀይዋ ጧት ወደ አንድ ሰአት ተኩል ላይ ትወጣና ከሰአት በኋላ ወደ አስር ተኩል ላይ መጥለቅ ትጀምራለች፤ በሽታ እንደያዘው እየማቀቀች እየደከመች ትሄዳለች። ሩቅ፣ ሩቅ ሩቅ በጣም ሩቅ ሆና ኮሳሳ ብርሀን ትልካለች። እቺ ፀሀይ በበጋው የሙቀት ምንጭ ነበረች፡ለኤክስ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች የህይወት ተስፋ ነበረች፣ አሁን ግን
ሰማዩ ተበስቶ ከውጭ የብርድ ጮራዎች የሚያስገባ ይመስላል

ብርዱ መላውን ፍጥረት ጨብጦ ያዘ፡፡ የሁላችንም ህይወት
በክረምቱ ብርድ ታሰረ፣ በቆፈን ተቋጠረ፡፡ ፀደይና ፀሀይ መጥተው
እስኪያስፈቱንና እስክንንቀሳቀስ ድረስ፣ የህይወታችን ታሪክ በያለበት ረጋ:: ተካና ጀርመኗ እኔ የማላውቀውን ግንኙነታቸውን ቀጠሉ፡፡ጀምሺድና ሉልሰገድ በኒኮል የፍትወት ገመድ ተሳስረው መለያየት አቅቷቸው፣ ጤና የለሽ ጓደኝነታቸውን ቀጠሉ፤ ለገና እረፍት ባህራም ወደ ኤክስ ሲመለስ ጊዜ፤ ኒኮልን ትተውለት ሁለቱ ተያይዘው ወደ ሞንቴ ካርሎ ሽሹ። እኔና ሲልቪ አልፎ አልፎ
እየተገናኘን፣ የቀረውን ጊዜ ስንፅፍ እንሰነብት ነበር በብርዱ ምክንያት የህይወታችን ታሪክ መፍሰሱን መለዋወጡን ትቶ፣ በያለበት ረጋ
አዳሞ የተባለው ዘፋኝ
"Tombe la neige
Tu ne viendras pas ce soir
Tombe la neige
Me crie mon desespoir..."
(በረዶው ይወርዳል
እንግዲህ ዛሬ ማታ አትመጪም
በረዶው ይወርዳል
ተስፋ መቁረጤ ይነግረኛል .. .»)
እያለ የክረምት እንጉርጉሮውን ያዜማል ..
ፀሀይዋ ቀስ በቀስ የሸሸችንን ያህል ቀስ በቀስ ትጠጋን
ጀመር። አየተቀነሰ የሚሄደው ብርድ፣ ቀጥሎም እየበረታ የሚሄደው ሙቀት፣ ረግቶ የነበረውን የፍጥረት ደም ቀስ በቀስ ያፍታታው ጀመር። መጀመሪያ አንዳንዷ ደፋር ቅጠል ብርዱን አሽንፋ አንገቷን
ብቅ ታደርጋለች፣ ራቁታቸውን የከረሙት ጭራሮ ቅርንጫፎች ላይ ስትታይ ታስደንቃለች፡ ታስደስታለች፤ የድል አድራጊው ህይወት ፊታውራሪ ነች፡ ምስጢራዊ ተአምር ነች። እንግዲህ ሌሎቹ ቅጠሎች
ይከተሉዋታል፡ የኤክስ ዛፎች በራቁት ጭራሮዋቸው ሰማዩን
መቧጨር ትተው፣ በለምለም አረንጓዴ ልብሳቸው ይወለውሉታል፣ ያፀዱታል። የኤክስ ጎረምሶችና ኮረዳዎች መጀመሪያ ካፖርትና
ጓንቲያቸውን አወለቁ፤ ቀጥሎ ሹራባቸውን አውልቀው መሳሳቅ
ጀመሩ። አንዳንድ ደፋር አሮጊት ወይም ሽማግሌ ካፖርቱን
እንደለበሰ መንገድ ላይ ይታይ ጀመር፡፡ ክረምቱ አለፈ ..

ፀደይ መጣ፡፡ የኤስ ልጃገረዶች ከባድ የክረምት ልብሳቸውን ገፈው ጥላው፣ ክረምቱ አልብሷቸው የነበረውን
አስቀያሚ ነጭ ጎሽ ፀጉር ኣራግፈው፤ የተፈጥሮ ውበታቸውን
መልበስ አመጡ፡፡ ፀጉራቸው ጭንቅላታቸው ላይ ተቆልሎ ወይም ወደ ኋላቸው እየፈሰሰ፣ ቆዳቸው ልስልስ ብሎ የፅጌረዳ ቀለም እየለበሰ፣ በቀይ ከንፈራቸው የተከበበ ጥርሳቸው በፈገግታ እያብለጨለጨ፡ ተሸሽጎ የከረመው ወጣት ቅርፃቸው እየፋፋ፣ ሹል ጡታቸው
ከፊት እየተንቀጠቀጠ፣ ያበጠ ዳሌያቸው ከኋላ እየተወዛወዘ፣ ይሄ ሁሉ ፀጋ የፀደይን መልካም ብርሀን ለብሶ በየመንገዱ እየተዘዋወረ፣ የኤክስን ጎረምሶች ምራቃቸውን ያስውጣቸው ጀመር። በብርድ ተኮራምተው የከረሙት ኮረዳዎች አሁን በሙቀት ተዝናኑ፤ እየተጯጯሁ በሳሩ ሜዳ ይፈነጩ
ይንከባለሉ ጀመር። ከጎረምሶቹ ጋር ልፊያና መተቃቀፍ ተጀመረ

ሽማግሌዎቹና አሮጊቶቹ እየወጡ የኩር ሚራሶንና የመናፈሻውን
አግዳሚ ወምበሮች ሰፈሩባቸው። እርጅና ከወጣትነት ጋር እየታከከ
የኤክስን መንገዶች በጎባጣ ጨምዳዳ እርምጃው ይንፏቀቅባቸው ጀመር የክረምቱ ብርድ ገድቦ ይዞት የነበረው ታሪካችን አሁን በፀደይ
ውቀት እንደገና መፍሰስ ጀመረ

ፀደይ ለኤክስ ብርሀንና ሙቀት ከአረንጓዴ ቀሚስ ጋር ይዞላት
ሲመጣ፤ ለተካ ችግር ይዞለት
መጣ። ባለውስታሿ ጀርመን
ታስቸግረው ጀመር። ከአንድ ያገሯ ልጅ ጋር መውጣት አመጣች፡፡
ታዛ ምን ትሽረሙ@ያለሽ? አላት። መሸርሞጥ አይደለም ማማረጥ ነው» አለችው:: እና የትኛችን ይሻላል?» አላት::በአንዳንድ ነገር እሱ ይሻላል፤ በሌላ ደሞ አንተ ትሻላለህ»አለችው። ተካን ቅናት ይሞረሙረው ጀመር

ጥፍሩን እየነከሰ «አሁን ምን ማድረግ ይሻለኛል እባክህን?»
አለኝ

«ትወዳታለህ?» አልኩት
«አዎን። ብዙ ነገር ይገባታል፡»
እሷስ ትወድሀለች?»
«አዎን»
«እንግዲያው አግባታ»
“አብደሀል? ነጭ ሚስት ይዤ ብመለስ አባቴ አይታነቅም?»
«እንግዲያው ተዋት»
እንዴት አድርጌ ልተዋት? በፊት እንኳ ቢሆን ልተዋት እችል
ነበር። አሁን ግን፣ ከዚያ ከንፍጣም ጀርመን ጋር መውጣት
ከጀመረች ወዲህ፡ ከምተዋት ብገድላት እመርጣለሁ፡፡»
«የሀበሻ ምቀኝነት ነው?» አልኩት
«አይደለም፡፡»
«ታድያስ?»
«እህ! ስለቅናት አታውቅም እንዴ? እንግዲያው ልንገርህ፡፡
አየህ፣ ስትቀና ልጅቷን በሀይል ትጠላታለህ። ብትገድላት ፈቃድህ
ነው፡፡ ግን በዚህ አለም ላይ ምን ትፈልጋለህ ቢሉህ፤ እሷን ነው
ምትፈልገው ሁሉ ነገር ይቅር ብቻ እሷ ትምጣ፡፡ ገባህ የምልህ?
ለምሳሌ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሱ ጋር የወጣች ጊዜ፣ ቤቷ ወሰድኳትና አንድ ጥፊ አላስኳት፡፡ ወዳ እስክትጠላ ልደበድባት ቆርጬ ኮቴን አወለቅኩ። ታዲያ ዳግማዊ ጥፊ ላወርድባት ስል
👍162
“Sauvage! ኣፍሪቃ ውስጥ ያለህ መሰለህ እንዴ?» አለችኝ።እንደቃጣው ቀረሁ
ዳግማዊውን ጥፊ እንደማውረድ አቅፌ ሳምኳት። ስትፍጨረጨር በጉልበት ሙታንታዋን ቀድጄ በታተንኩባት፡፡ ወደ አልጋው እንኳ እስክወስዳት አላስቻለኝም። እዚያው ምንጣፍ ላይ በዳኋት፡፡ እንደጨረስኩ ታድያ በሀይል ቀፈፈችኝ::እዚያው ወለል ላይ እንደተጋደመች ትቻት ወጥቼ ሄድኩ

«ይሄ ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ እንግዲህ የኔ
ኑሮ መቃጠል ሆኗል።»

«ሰውየውን ተይው አልካት?» አልኩት

«አዎን። 'እንዴት እተወዋለሁ? ላንተ ብዪ እንዴት እሱን
ልተወው? አንተ ልትተኛኝ ነው የምትፈልገው፡፡ እሱ ግን ሊያገባኝ
ነው ሚፈልገው:: ባይሆን ለሱ ስል አንተን እተውሀለሁ እንጂ፣
እሱንስ አልተወውም አለችኝ፡፡»
«ምን አልካት?»
«አንድ ሁለት ጥፊ አላስኳት፡፡ ስታለቅስ በግድ በዳኋት፡፡»
«እንዲህ ከቀጠልክ ትተውሀለች» አልኩት
“ተሳስተሀል፡፡ በጥፊ መትቼ በጉልበት ስደፍራት በሀይል ነው
ፍቅሬ የሚጥማት፡፡»
«እንዴት ታውቃለህ?»
«ከሁኔታዋ ያስታውቃል»
«ዋ! ጥፊው ቢቀር ይሻለሀል» አልኩት “አይገባህም። ቅናት ገና አላጋጠመህም» አለኝ
ግን አንድ ነገር ገብቶኛል፡፡ ልጅቷ ልታገባው ታጥቃ ተነስታለች

ክረምት አልፎ ፀደይ እንደገባ በፋሺስቶችና በኮሙኒስቶች
መካከል ትልቅ አምባጓሮ ተነሳ፡፡ አምስት ስድስት ፋሺስቶች ይሆኑና አንዱን ኮሙኒስት ይዘው ይደበድቡት ጀመር፡፡ ኮሙኒስቶቹ
ተማሪዎች፣ እጃቸውን ወይም ራሳቸውን በፋሻ ጠምጥመው ይታይ ጀመር። ፋሺስቶቹ ወንድ ቤት ሳይሉ ያገኙትን ኮሙኒስት
መደብደብ ሆነ። አንዷን ልጅ አራት ጎረምሶች ተጋግዘው ደበደቧትና የአፍንጫዋን አጥንት ሰበሩት። ሆስፒታል ተኛች ኮሙኒስቶቹ ከባድ የብረት መሳሪያ፣ አጭር የብረት ዱላ፣ ወይም ይህን የመሳሰለ ነገር እጅጌያቸው ውስጥ እየደበቁ ሶስት
አራት እየሆኑ መዞር ግድ ሆነባቸው። ጩቤ ወይም ሽጉጥ እየያዙ የሚዞሩም ነበሩ
ባህራምን ልጠይቀው ትምህርት ቤቱ ሄድኩና የሆነውን ሁሉ
አጫወትኩት። አብሮኝ ወደ ኤክስ መጣ፡፡ «የነገርኩህ ወሬ ደስ
ያሰኘህ ይመስላል» አልኩት

«ለኮሙኒስቶቹ እዝንላቸዋለሁ። ግን ጥሩ ነው፤ ይጠቅማቸዋል።
ለአምባጓሮ በቂ ዝግጅት የላችሁም፣ አያልኩ እጨቀጭቃቸው ነበር።
ፈረንሳይ አገር ኣምባጓሮ አይስራም፡፡ በፅሁፍና በንግግር የሰውን ሀሳብ ማናወጥ ማነቃነቅ ነው የሚያስፈልገው፤ ሲሉኝ ነበር። ብቻ የራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡ የፈረንሳይ ህዝብ ወሬ ያበዛል። ስራ፣ ጀብዱ (Action) ስትለው በቄንጠኛ ሰዋሰው ስለ አርት ሊያወራልህ ይጀምራል። ተዋቸው እነሱን። እኔን ያስደሰተኝ ሌላ ነገር ነው::»

«ምንድነው?»

ረብሻ ውስጥ ከገባሁ አመታት አለፉ። ናፍቆኛል» በተጨበጠ ቀኝ እጁ ግራ መዳፉን እየወቀጠ ረብሻ ናፍቆኛል» አለ

እንግዲህ ኤክስ ውስጥ ኮሙኒስቶቹ የሚያዘወትሩት አንድ ካፌ አላቸው። ሮያሊስቶቹ አንድ ሌላ ካፌ ያዘወትራሉ (ሮያሊስቶቹ
ፈረንሳይ ውስጥ ንጉስ ለማንገስ የሚፈልጉ ናቸው) ወንድ ለወንድ
የሚዋደዱት አንድ ካፌ አላቸው፡፡ ፋሺስቶቹም የራሳቸው ካፈ
አላቸው ኤክስ እንደገባን ባህራም ፋሺስቶቹ ካፌ ወሰደኝ። ቢራ፣ ቡና
እየጠጡ በየጠረጴዛው ያወራሉ። አብዛኛዎቹ ፂማቸውን በቄንጥ
ያስተካከሉ ወጣቶች ናቸው:: በጣም ያምራሉ

እኔና ባህራም መውጫው በር አጠገብ ያለችው ጠረጴዛ ጋ
ቁጭ ብለን ቢራ ጠጥተን ሂሳቡን ከከፈልን በኋላ፣ ባህራም
ምንም ቢመጣ ምንም፣ ከተቀመጥክበት እንዳትነሳም አለኝ
“ምን ልታረግ ነው?» ስለው

«ታያለህ» አለኝ....

💫ይቀጥላል💫
👍22👏1
#ድንቡጮ_ለምን_ለምን_ሞተ


#ሁለት(መጨረሻ)


#በአሌክስ_አብርሃም


...“እደጉ ልጆቸ እድግ በሉ !! ወርቅ ይፍሶስቦት ሟለት ትልቅ በረከት ነውኮ…፤ ከወርቅ በሏይ ሙን አለ…? ቡዙ ተብዛዙ ቁም ነገር ያቡቋችሁ..! አቡነ አረጋዊ ጭንቅላታቹሁን ይከፋፍተውና ትሙሩቱ ይግባዓባችሁ…” ብለው ይመርቁናል። አፋቸው ይጣፍጣል። እማማ ንግሥት ኤርትራዊት ናቸው። ታዲያ በአማርኛ ሲያወሩ አንደበታቸው አይጠገብም። ጥርስ የማያስከድኑ ተጨዋች ናቸው። ሲቆጡም በዚያው ልክ ነው ይባላል ሲቆጡ አይተናቸው አናውቅም እንጂ…!! አባባ መክብብ ታዲያ ሚስታቸውን ሲወዷቸው ልክ የላቸውም። አንድ ቀን እትየ ንግሥት ታመው (የደም ግፊት የሚባል ነገር ነው አሉ) አንቡላንስ ተጠርቶ ጎረቤቱ ሁሉ ሲሯሯጥ አባባ መክብብ እንደ ሕፃን ልጅ በሁለት እጆቻቸው ጭንቅላታቸውን ይዘው ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ እና ሲጮሁ አይቻቸዋለሁ ! ሰው ሁሉ እያባበላቸው!

“እትየ ንግሥት ... እናቴ፣ እህቴ፣ ጓደኛዬ ሜዳ ላይ እኔን ጥለሽ ..” እያሉ…

ባልና ሚስቱ አንዲት ልጅ አለቻቸው፤ ህደጋ የምትባል፣ ፈረንጅ አግብታ ውጭ አገር የምትኖር።በየሦስት ዓመቱ እናትና አባቷን ልትጠይቅ ስትመጣ ከታች ሰፈር ጀምሮ እስከላይ ሰፈር ድረስ
ሁሉም ቤት እየገባች ጎረቤቱን ሁሉ ትስምና ሃምሳ ሃምሳ ብር ትሰጣለች። ለትልልቅ ሰዎች ብቻ
ነው የምትሰጠው። ከእኛ መካከል የሃምሳ ብር እጣ የሚወደቅለት ፈንታው ድንቡጮ ብቻ ነበር።
የፈንታው እናት ሚስኪን ናት፤ በሽተኛ ስለሆነች ከአልጋ ላይ አትነሳም። ፈንታው አባባ መክብብ
ግሮሰሪ በረንዳ ሥር ጫማ እየጠረገ እና እየተላላከ ነው እናቱን የሚያስታምመው። አባቱ በደርግ ጊዜ ዘምቶ ይሙት ይትረፍ ሳይታወቅ በዛው ቀልጦ ቀርቷል። ያው የህደጋ ሃምሳ ብር ፈንታው ድንቡጮን የሚያካትተው ለዚህ ሳይሆን አይቀርም !

አንድ ቀን ታዲያ የስፖርት ትጥቅ ለመግዛት ከመንደርተኛው ሳንቲም እንለምናለን። በአጋጣሚ ፊት
ለፊታችን ህደጋ አሻንጉሊት የመሰለ ልጇን በደረቷ አቅፋ ስትመጣ ተገጣጠምን። ሌላውን መንደርተኛ ሳንቲም ውለድ እያልን ምናስቆም እኛ፣ ህደጋን ለምን እንደፈራናት እንጃ፤ ብቻ ገለል ብለን አሳለፍናት።
በቀጣዩ ቀን ታዲያ አስጠራችንና እንኳን በእውናችን በህልማችንም አስበነው የማናውቀውን የስፖርት
ትጥቅ ከነኳሱ ገዛችልን።

አቤ…ት! እንዴት እንደተደሰትን…! ለስንት ዓመት ታሪክ ሆኖ በመንደራችን ተወራ ! “ኳሱ የት
ይቀመጥ” በሚል በመካከላችን ከባድ ክርክር ተደርጎ እኔጋ እንዲቀመጥ ተወሰነ። የተሰማኝ ደስታ ወደር አልነበረውም። ግን ምን ያደርጋል አንድ ቀን ያ ለብዙ ሕፃናት ህልም የነበረ ኳስ ምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ጠፋ። የጠፋው ከእኛ ቤት ስለነበር በቡድኑ አባላት ዘንድ ክፉኛ አስተችቶኛል።ለረዥም ጊዜ ያኮረፉኝ የሰፈር ልጆችም ነበሩ። በእግር በፈረስ በሰፈራችን ስርቻ ሁሉ ኳሱን ፈልገን ስናጣው በቃ ወደ ጨርቅ ኳሳችን ተመለስን። አሁን ካደግን በኋላ ሳይቀር የኳሱ ነገር ሲነሳ እወቀሳለሁ።
እንደውም አሁን ካደግን በኋላ እድሜያችን ሃያዎቹ ውስጥ ገብቶ ተፈሪ የሚባለው የሰፈራችን ልጅ
(አሁን አዉስትራሊያ የሚኖር) ኢ-ሜይል ሲያደርግልኝ ስለ ኳሱ ጉዳይ አንስቶ እንዲህ ብሎኛል፣
“አቡቹ እዚህ የፈረንጅ ሕፃናት ኳሶች ይዘው ሲጫወቱ ሳይ ያች ህደጋ የገዛችልን የጣልክብን ኳስ ትዘ እያለችኝ ይቆጨኛል ሃሃሃ” አንረሳም እኮ አንዳንዴ !
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ድንገት ነበር ነገሮች የተገለባበጡት፤ ልክ እንደ መሬት መንቀጥቀጥ፣ እንደጎርፍ መጥለቅለቅ ሰፈራችን ውስጥ በአብሮ መኖር የፍቅር ቆሌ የሆኑ ነዋሪዎችን ከሥራቸው እየመነገለ ድራሻቸውን ያጠፋ ድንገቴ
ነውጥ። እንዴት ነው ሰው ድንገት ተነስቶ ትላንት አለፍኩት ወዳለው አረንቋ መልሶ የሚዘፈቀው…?
“ሲደርሱብን ምን እናድርግ” ብሎ ነገር ...

“ኤርትራ ወረረችን…” ተባለ።
“ምናባቷ ቆርጧት ይች የእናት ጡት ነካሽ!” የሚሉ ደምፍላታም ሰዎች ሰፈሩን ሞሉት። ከየት አመጡት አማርኛውን…? መቸስ ታንክ ቢሆን፣ መትረየስ፣ ቦንብ ምናምን ገዙት ይባላል፣ ወይ በእርዳታ አገኙት፤ ስድብ ከየት ተፈበረከ ... ዛቻ መቼ ተረግዞ ነው በዜማ የተወለደው…? ትላንት እንደ ቦብ ማርሌ “ፀበኞች ካልታረቁ!” እያለ ሲያቀነቅን የነበረ ድምፃዊ “ፍለጠው ቁረጠው!” ዘፈኑን ከየት መዝርጦ ቴሌቪዥኑን ሞላው፤ ወይስ ሁሉም ዘፋኝ ለክፉ ጊዜ ያስቀመጠው ዘፈን አለው? ለጦርነት ግጥምና ዜማ መፍጠር ከፍቅር ዘፈን ይቀላል? ከቀበሌ ኪነት ቡድን እስከ አገር አቀፍ ታላላቅ ዘፋኞች ዘፈናቸው አይሄድ አይመጣ አንድ - “በለው ፍለጠው ቁረጠው !!”

በዓይን ርግብግቢት ፍጥነት 'ለደኅንነታችሁ' ብለው ደህና ሰዎች ብለን ያመንናቸውን፣ ስንጣላ አስታራቂ፣ ስንቸገር ደራሽ የነበሩት ጎረቤቶቻችንን ሁሉ በአውቶብስ እየጫኑ አባረሯቸው። እማማ ንግሥትን ጨምሮ። ከመወለዳችን በፊት ኤርትራ የሄዱ የማናውቃቸው ብዙ እማማዎች ከዛም ተባርረው መጡ። ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ። ለካስ የመንግሥታት ፍርሃት እንደጅብ ያነክሳል አገርንም ያስነክሳል። አሁን እማማንግሥት ምናቸው ነው ለደህንነት የሚያሰጋው? በሹሩባቸው ውስጥ ቦምብ
እንዳይቀብሩ ነው? ወይስ በድፏቸው ውስጥ ጥይት እንዳይደብቁ ...። እማማ ንግሥት (ለደህንነት ስጋት ናቸው ተብለው የተባረሩ ቀን ማታ ህልም አለምኩ….

ቀኑ ቡሄ ይመስለኛል። የሰፈር ልጆች እንደልማዳችን ተሰባስበን እማማ ንግሥት በር ላይ ቆመን
እንጨፍራለን።

“እዛ ማዶ አንድ በረዶ!

እዚህ ማዶ አንድ በረዶ!

የኔ እማማ ንግሥት!
ፓራ ኮማንዶ ….”

የእማማ ንግሥት በር ድንገት ብርግድ ብሎ ተከፈተና፣ በወርቅና በሐገር ባህል ቀሚስ የምናውቃቸው እማማ ንግሥት፣ የወታደር ልብስና ከስክስ ጫማ ለብሰው አናታቸውም ላይ የብረት ቆብ ደፍተው ድፎ ሳይሆን ዝናሩ የተንዠረገገ መትረየስ ጠመንጃ ደግነው፣ “ አንች ዲቃላ ሁሉ … በሬ ላይ ሙናባሽ ትናጫጫለሽ አቡነ አረጋዊ ድራሽ አባትሽን ያጥፉት!” ብለው ታታታታታታታታታታታታታ
ሲያደርጉብን በተለይ እኔ ሰውነቴ ተበሳስቶ ወንፊት የሆነ ይመስለኛል…፤ እየጮህኩ ከህልሜ ባነንኩ…፤ እናቴ ከትራስጌ በኩል ቆማ “አቡቹ በስማም በል ቅዠት ነው…” ትላለች።

ያየሁትን ህልም ለማሚ ስነግራት ግን ተቆጣች…

“ምን እንደው የዛሬ ልጅ የነገሯችሁን ይዛችሁ ትጋደማላችሁ፣ ቅዠት ይተርፋችኋል ፤ በል አርፈህ
ተኛ”

አባባ መክብብ እትዬ ንግሥት ወደ ኤርትራ ከተባረሩበት ጊዜ ጀምሮ ግራ እግራቸውን ሰብስቦ
ያዛቸው፤ በከዘራ ድጋፍ ሆነ የሚራመዱት። የጢም መላጫቸውም ከእጃቸው ጠፋች። ነጭና ጥቁር ቡራቡሬ ፂም ትንሽ አገጫቸውን ሸፈነው…፤ ተዘናጉ፤ ሰፈሩ ተዘናጋ …። አንድ ቀን በግሮሰሪዋ በኩል ሳልፍ አባባ መክብብ ከዘራው እጀታ ላይ የተነባበረ እጃቸው ላይ አገጫቸውን አሳርፈው አፋቸው
ባዶ ነገር እያኘከ ትክዝ ብለው ተቀምጠዋል በቀስታ ወደ ፊትና ኋላ እየተወዛወዙ። ላልፍ ስል የውሃ ማጠራቀሚያው በርሚል ላይ ዓይኔ አረፈ፤ የሆነ ነገር ቅር አለኝ …፤ በትኩረት በርሚሉን አየሁት፤ ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ ከበርሚሉ ተነጥላ የማታውቀው የመርቲ ጣሳ በቦታዋ የለችም። ጣሳዋ ትታሰርባት የነበረችው የኤሌክትሪክ ገመድ ባዶዋን ተንጠልጥላ ነፋስ በቀስታ ያወዘውዛታል !
👍21🔥1
ከበርሚሉ ራቅ ብሎ …. የፈንታው ድንቡጭ የሊስትሮ ድንጋይ ከዘንባባዋ ሥር ባዶዋን ትታያለች።
ፈንታው ድንቡጭ“ለአገሩ ዘመተ….” መባሉን ሰምቻለሁ። ፈንታው ጋር ካደግን በኋላ ብዙም ፋታ ኖሮን አንገናኝም ነበር። ቢሆንም አንዳንዴ በዛ ሳልፍ ሰላም እንባባላለን። ጫማዬንም ይቦርሽልኛል።
እንደውም ወደ ወታደር ቤት ሊሄድ አካባቢ ጫማዬን እየቦረሸልኝ ድንገት የሐፍረት ፈገግታ ፊቱን
አጅቦት እንዲህ አለኝ (በወሬ ወሬ ተነስቶ ሳይሆን እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ..)

“አብርሽ የዛን ጊዜ ህደጋ የገዛችልን ኳስ ታስታውሳታለህ ?”

እንዴ ታዲያ ያችን ኳስ ማን ይረሳል…፣” ተሳሳቅን። ፈንታው ጫማዬን መቦረሹን ገታ አድርጎ መሬት መሬት እየተመለከተ እንዲህ አለኝ፣

“ያኔ ኳሷን ከግቢ የወሰድኳት እኔ ነበርኩ፤ እማማ ብር ፈልጋ እጄ ላይ ሳንቲም ስላልነበረኝ ለሆኑ
ልጆች ሠላሳ ብር ሸጥኩላቸው።”። ነገሩ አስደነገጠኝ። ፈንታውም ቅሬታ ባረበበት እኔም ግራ በተጋባ
ፊት ተሳሳቅን፣ እናም ሁለታችንም ወደ ጥልቅ ዝምታ ገባን። ለምን እንደነገረኝ አልገባኝም ነበር።
ፈንታው ኳሷን ወስዶ ይሸጣታል ብሎ የጠረጠረ ያኔ ማንም አልነበረም፤ ማንም !! አሁን ራሱ
ቢነገረው ማን ያምናል! ፈንታው ድንቡጮ ፊቱ ወርቅ ቢዘራ ቅንጣት የማይነካ ንፁህ ደሃ ነው።
ጫማዬን አስቦርሼ ስነሳ እንዲህ አለኝ፣ “አብርሽ ይቅርታ…”
“ኧረ አታካብድ ይሄ እኮ ተራ ነገር ነው፣” አልኩት፤ ግን ለምን እንደሆነ እንጃ ቶሎ ከአካባቢው መራቅ ፈልጌ ነበር።

ወሬው ሁሉ ጦርነት ሆነ ... ሽለላው፣ ቀረርቶው፣ መፈክሩ። እንደ ቀልድ ቃል ጥላቻ ለበሰ። ጥይትና ቦንብ ለብሶ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ላይ አደረ። ገና እሳቱ ሳይጠፋ…፣ ገና ወጣቶች እየጨፈሩ ወደ ድንበር ሊፋለሙ በጭነት መኪና ጨፈቃ መስለው ተጭነው ሲሄዱ…፣ ገና በጠዋቱ ወደፊት መንደራችን ሁነኛ ሰው መርዶ ይዞ መጣና እንደ መርፌ የሚወጋ ቀፋፊ ጤዛ መንደራችን ላይ ዘራ ...

"ፈንታው ድንቡጮ ሞተ….”

ከመጀመሪያዎቹ ዘማቾች መሐል ነበር ፈንታው ድንቡጮ..
አብሮ አደጋችን ፈንታው ሞተ።
ከአባባ መክብብ ግሮሰሪ በረንዳ ሥር ዛሬም የፈንታው ድንቡጮ ድንጋይ አለች !
ታዲያ መንደርተኛው ተሰባሰበና ለፈንታው አለቀሰ። እዛው አባባ መክብብ በረንዳ ሥር የፈንታ
ድንጋይ ላይ አለቀሰ ጎረቤቱ። አባባ መክብብ ከዘራቸውን አገጫቸው ሥር አስደግፈው ግራ ቀኝ እየተወዘወዙ እንጉርጉሮ የመሰለ ዜማ ያወጣሉ። አያለቅሱም፤ ማንንም አይመለከቱም፤ ዝም ብላ
መወዝወዝ። ሰዉ ተበታትኖ ወደየቤቱ ገብቶ እንኳን መወዛወዛቸውን አላቆሙም እስከማታ በተቀመጡበት ... እእእእእእእእእእእእእ እያሉ !

ቀበሌያችን ግቢ ውስጥ ለዘመቻ የተመለመሉ ወጣቶች የሽኝት ፕሮግራም ነበር። ሰንጋ ተጥሎ፣ ብዙ በግ ታርዶ፣ ሰዉ ቢራ እየተራጨ፣ ጀግንነታችን እየተወሳ ... አድዋ፣ ማይጨው እየተገረበ፣ አባቶች ለዘማች ወጣቶች ባንዲራ እያስረከቡ፣ ወጣቶቹ ተንበርክከው ባንዲራውን እየተረከቡ፣ እናቶች እልል
እያሉ፣ ዘፋኞች ስለአጥንት መከስከስ፣ ስለደም መፍሰስ እየዘፈኑ… “አዝማቹ ሕዝብ፣ ዘማች ልጆቹን ሂዱና ጠላቶቻችሁን አደባዩ!” ብሎ እየላካቸው ...
በቀበሌው አጥር አጠገብ እጆቼን ኪስና ኪሴ አስገብቼ ወደ ቤቴ እያዘገምኩ ነበር ወደ አስራ ሁለት
ሰዓት አካባቢ ይሆናል ማታ። ታዲያ አንድ ውሻ አጥሩ ጥግ የወደቀ የበግ አንጀት እየጎተተ በአጠገቤ አለፈ፤ ማመን አልቻልኩም፤ የእማማ ንግሥት ውሻ “አሲምባ…”

“ዘመቻ ፀሐይ ግባት በድል ተጠናቀቀ!” አለ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን። ወጣቶቹ በደስታ አገር ጠበበን። በየመንገዱ የደስታ ፌሽታና ጭፈራ ሆነ። የመኪና ጡሩምባ ጩኸት፣ የእናቶች እልልታ፣ የአባቶች ዘራፌዋ ..! የሴቶች ጉሮ ወሸባዬ ... የዘንባባ ዝንጣፊና ባንዲራ የያዙ ወጣቶች የመኪናዎች እቃ መጫኛ
ላይ እንደንብ ሰፍረው ይጨፍራሉ፣ በደስታ ይጮሃሉ። ቴሌቪዥኑ ደጋግሞ የምሥራቹን ያበስራል።

ቃለ መጠይቅ በሬዲዮ ለጀግና ወታደሮች ... ለጀግና የጦር መሪዎች፣

“እስኪ የጦር ውሎዎትን ይንገሩን…

“ሻእቢያ እንደ ፍልፈል ጉድጓድ ቆፍሮ ተደብቆ የነበረ ቢሆንም፣ ከጉድጓዱ በጀግና ልጆቻችን አውጥተን ቀብረነዋል …።” ሕዝቡ በጀግኖቹ ኮራ!! አባባ መክብብ ግሮሰሪያቸው ውስጥ በስልክ እያወሩ ነበር።ጭፈራው ያደከመን የሰፈር ልጆች ግሮሰሪዋ በረንዳ ላይ ተሰባስበን፣ የሰማነውን ጀብዱ በቴሌቪዥን ያሳዩንን የጀግኖች ውሎ ለመቶኛ ጊዜ ከአፋችን እየተነጣጠቅን እያወራን ... ያዘዝነውን ቀዝቃዛ ኮካ እንጎነጫለን።

አባባ መክብብ እያዘገሙ ወጡና አጠገባችን የበረንዳውን የብረት ደፍ ደገፍ ብለው ቆሙ። ዞር ብለው ተመለከቱንና እንደ እብድ ከት ከት ብለው ሳቁ ...ሰውነታቸው እየተርገፈገፈ ሳቁ ... ግራ ተጋብተን አየናቸው። አባባ መክብብ ሚስታቸው እትዬ ንግሥት ከሄዱ በኋላ እንኳን ሲስቁ ይቅርና የተቋጠረ ፊታቸው ሲፈታ አይተን አናውቅም ነበር።

“ሰማችሁ ልጆቼ!! ልጄ ህደጋ ከአሜሪካ ደውላ ያለችኝን ሰማችሁ...” አሉን በግርምት ተራ በተራ እየተመለከቱን…።

“ምን አለች አባባ መክብብ?” በጉጉት ጠየቅናቸው።

“አሁን እናቷ ጋር ኤርትራ ደውላ አናግራት፣ እኔንም ሰላም ልትል ነበር የደወለችው
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃም ብለው ሳቁ። አእምሯቸው የተናጋ መስሎን ፈራን። እንደ ምንም ሳቃቸውን ገቱና ፊታቸውን በምሬት ኩምትር አድርገው፣

“አስመራም ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ጉሮ ወሸባዬ እየተጨፈረ ነው እኮ ነው የምትለኝ !! ሆሆ ይች አገር እንደ ካሴት ሆነች… በዚህም ዘፈን ..፣ ስትገለበጥም ዘፈን ... ታዲያ ለድንቡጮ ማን ያልቅስ …? እኮ ድንቡጮ ለምን ሞተ …?” ብለው አንድ በአንድ ተመለከቱን። ከእኛ መልስ ሲያጡ ወደ ፈንታው ድንቡጮ ድንጋይ ዞረው በትካዜ ጭልጥ አሉ።
የፈንታው ድንቡጮ ቦታ ላይ አንድ ትንሽ ልጅ አዲስ የሊስትሮ ሳጥን ይዞ ተቀምጧል። ቀና ብዬ
ግሮሰሪው በር ላይ በግራ በኩል የቆመችውን የዘንባባ ዛፍ ተመለከትኳት፤ ለጭፈራው ቅጠሎቿን ዘንጥፈናቸው መለመላዋን ቆማለች፤ ብቻዋን የቆመች ዘንባባ ፤ ከአስመራ ዘንባባዎች መሐል አምልጣ
የመጣች መሰለችኝ፣ እዛም ጭፈራ! እዚህም ጭፈራ…” ብላ። ዘንባባዎቹ ሁሉ ወደ አስመራ ሲጫኑ በሆነ ተአምር የቀረችም መሰለኝ።

ሄደችም መጣችም ከዘንባባ ጫካዋ የተገነጠለች አብዮተኛ ዘንባባ !!

አለቀ
👍108
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

...እኔና ባህራም መውጫው በር አጠገብ ያለችው ጠረጴዛ ጋ
ቁጭ ብለን ቢራ ጠጥተን ሂሳቡን ከከፈልን በኋላ፣ ባህራም
ምንም ቢመጣ ምንም፣ ከተቀመጥክበት እንዳትነሳም አለኝ
“ምን ልታረግ ነው?» ስለው

«ታያለህ» አለኝ.

ተነሳና ወደ ሽንት ቤት በኩል መራመድ ጀመረ። አንዱ
ጎረምሳ ፋሺስት ከዚያው ሲመለስ ነበር ባህራምን የገጨው፡፡ ፋሺስቴ ሳያስብበት በልማድ “Pardon” ብሎት ሲያልፍ፣ ባህራም

«አንተ!» ብሎ ጮኸበት። ፋሺስቶቹ ወሬያቸውን አቆሙ::
ካፌው በሙሉ በፀጥታ ባህራምን ማየት ጀመረ። የገጨው ፋሺስት
ወደ ባህራም ዞሯል ባህራም

«ለምን ገጨኸኝ?» አለው

ፋሺስቱ «አንተ ነህ እንጂ የገጨኸኝ አለው

«ውሽታም ፋሺስት! ውሻ ፋሺስት! ፈሪ ፋሺስት! ወንድ ከሆንክ ተከላከል። ልገርፍህ ነው» አለና ዘሎ ትግል ያዘው። የፋሺስቱ ጀርባ ወደኔ ስለነበረ፣ ባህራም ምን እንዳደረገው ለማየት
አልቻልኩም፡፡ ብቻ ምንም ያህል ሳይታገሉ ፋሺስቱ ፍስስ ብሎ ወደ
መሬት ወደቀ፡፡ ባህራም ከበላዩ እንደቆመ ዙሪያውን ተመለከተ፡፡
ከፋሺስቶቹ ማንም አልተነሳም
ባህራም ፋሺስቶቹን እያየ «ማንም ፋሽስት እንዲገጨኝ አልፈቅድለትም፡፡ ከንግዲህ ሌላ ፋሺስት የገጨኝ እንደሆነ፣ ፂሙን
ነው ምላጭለት አለና የወደቀውን ፋሺስት ተሻግሮ ወደኔ መጣ፡፡
አብረን ወጣን
(ፋሺስቶቹ እኔን ሌላ ጊዜ ቢያገኙኝ ይደበድቡኝ ይሆን? ብዬ
ትንሽ ፈራሁ፡፡ ግን ደፍረው ጥቁር ተማሪ የሚደበድቡ አልመሰለኝም፡፡ ምክንያቱም እኛ የፈረንሳይ መንግስት እንግዶች
ማለት ነን፡፡)
ባህራም ኤክስ ውስጥ አራት ቀን ቆየ፡፡ ቀን ቀን ኮሙኒስቶቹን
ሲመካክራቸው፣ እንዴት አድርገው መከላከል ፅሁፎቻቸውን እንዴት ቢያሰራጩ እንደሚሻል፣ እና ይህን የመሳሰለ ነገር ሲነግራቸው ይውላል። ማታ ማታ ፋሺስቶቹን በየጠባቡ መንገድ ሲደበድባቸው ያመሻል፡፡ በአምስተኛው ቀን ትምህርት ቤቱ ድረስ ሸኘሁት፡፡ ስለአምቧጓሮው ሲነግረኝ፣ ስለኳስ ጨዋታ የሚያወራልኝ መስሎ ተሰማኝ፡፡ በደስታ እየገነፈለ፣ ማድፊጡን መዝለሉን፣ እጁን እንደ ሰይፍ አርጎ አንገት መምታቱን፣ እንደ ዳንስ አድርጎ ገለፀልኝ

"ማኑ ይህን ሁሉ ስስራ አይቶኝ ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር!
ያስተማረኝን ብልሀት በሙሉ ተጠቅሜበታለሁ» አለ

«ደህና ሁን» ብዬው ወደ ኤክስ ልመለስ ስል፣ ከኪሱ አንድ
እቃ አውጥቶ አሳየኝ። የፀጉር መቁረጫ መኪና «ቶንዶዝ»፡፡
ምንድነው? አልኩት፡፡ እየሳቀ «ፋሺስቶቹ ካፌ ሂድና እቺ ነገር
ኮሙኒስት መሆንዋን ትገነዘባለህ» ብሎኝ ተለያየን ኤክስ እንደደረስኩ ፋሺሰቶቹ ካፌ ገባሁ። ብዙዎቹ እጃቸውን ወይም ጭንቅላታቸውን በፋሻ ጠምጥመዋል፡፡ ግማሾቹ ፂማቸውን ላጭተዋል። ፂማቸውን ያልላጩት ደሞ ጥቁር «ቤሬ ቆብ
አርገዋል። ለካ ባህራም ኣንድ ፋሺስት በደበደበ ቁጥር ራሱን
ወይም ፂሙን ይላጭለት ኖሯል
(እኔና ባህራም ኣንድ ግሩም የሆነ ሀራኪሪ» የተባለ የጃፓን ፊልም አይተን ነበር። እዚያ ፊልም አንዱ ጎበዝ እየዞረ የጠላቶቹን
ፀጉር ይላጫል።)

ባሀራም በሄደ በአራተኛው ቀን፣ አንዲት ኮሙኒስት ልጅ ካፌ
ቁጭ ብዬ ሳለሁ መጣችና ወደ ኤክስ አንድ ነብሰ ገዳይ መጥቷል
አለችኝ። ምን አንደሆነ ማለቴ የቱ እንደሆነ አናውቅም። ግን መምጣቱን እናውቃለን፡፡ ፋሺስቶቹ ናቸው ከማርሰይ ያስመጡት። ባህራምን ሊደበድበው ወይም ሊገድለው ነው የመጣው::»
«ፋሺስት ነው?» አልኳት
«አይደለም። የተገዛ ነብሰ ገዳይ ነው» አለችኝ
ያን ጊዜውኑ ሲልቪ ቤት ሄድኩ። በአቶቡስ እንዳልሄድ
ምናልባት ፋሺስቶቹ ይከታተሉኛልና፡ ካንቺ ጋር ለሽርሽር የምንወጣ አስመስለን እንሂድ አልኳት።በመኪናዋ ሄድን። ለባህራም ነገርኩት።
ሲልቪ ቤቷ ወስዳን እራት በላን። ከዚያ ሶስታችንም ሄደን
ፋሺስቶቹ ካፌ ገብተን ሁለት ሰአት ያህል አሳለፍን። ይህን ሁሉ
ጊዜ ባህራምና ሲልቪ ያወሩ፣ ይቀልዱ፣ ይስቁ ነበር፡፡ እኔ ግን
ምንም ያህል አላወራሁም። ለባህራም ፈርቼለት ነበር፡፡ ሰውየው የቱ እንደሆነ ብናውቅ እንኳ ለመከላከል እንሞክር ነበር። አሁን ግን ከማንኛውም አቅጣጫ ጦር ሊወረወርበት በሚችልበት
ውስጥ፣ ባህራም ብቻውን የሚራመድ መስሎ ተሰማኝ
አብሬያቸው ባለማውራቴ፣ የኔ ፍርሀት ቀስ እያለ ወደ ሲልቫ
ተላለፈባት

“ፈራሁ። በጣም ፈራሁ» አለች

ባህራም «ምን ያስፈራሻል?» አላት፡፡ ግን ድምፁ እንደ ድሮ
ልዝብ መሆኑ ቀርቶ፣ ትንሽ እሾህም ሆኗል

«ማን እንደሆነ ወይም የት እንደሆነ አናውቅም፡፡ አንድ
ብቻውን መሆኑን እንኳ በእርግጥ አናውቅም፡፡»

«እና?»

አንድ ነገር ብትሆንስ? ብትሞትስ?» አለችው

እኔ? ትቀልጂያለሽ? የኛ ቤተሰብ”ኮ እስኪጃጅ ካላረጀ
አይሞትም፡፡ የኔ ወንድ አያት፣ ያባቴ አባት፣ በዘጠና ሰባት
አመታቸው ብቻቸውን ሜካ መዲና ደርሰው ተመልስዋል። ታድያ
እንደተመለሱ የቤታችን ጣራ ዝናብ ማስገባት ሲጀምር ጊዜ፣
ሊያበጁት በመስሳል ወጡ። አበጅተውት ሲወርዱ ከመሰላል ወደቁና እግራቸው ወለም ብሏቸው ሁለት ሳምንት ሙሉ እንዲተኙ ሀኪም አዘዛቸው:: ታድያ ሁለት ሳምንት እንዴት ይለፍ? ውሽማቸው ናፈቀቻቸው። እና ገና አንድ ሳምንት ሳይተኙ፣ ሌሊት ጠፍተው ውሽማቸው ቤት ሄዱ። መኝታ ቤቷ በመስኮት እገባለሁ ሲሉ ባልየው በጥይት ልባቸውን አፈረሰላቸው:: ስንቀብራቸው የኔ አባት
«አይ አባባ! አይ አባባ! እኛ ያረጀነው እያለን አንተ ወጣት
ተቀጨህ!» ብሎ አለቀሰ፡»
ስንስቅ ሲልቪ በጆሮዬ እኔ ፍርሀት አቁነጠነጠኝ፡፡ ሽንቴ መጣ» ብላኝ ወደ ሽንት ቤት ሄደች
ባህራምን «የጀምሺድን የሚመስል ታሪክ ከየት አመጣህ?» አልኩት
( ከጀምሺድ ነዋ!» አለኝ «ስማኝ፡፡ እንድ ነገር አርግልኝ።
እዚያው ትደር፡፡ እና ነገ በሌሊት ተነስቶ ማርሰይ እንዲወስዳትና
ለአንድ ሳምንት ያህል ተደብቀው እንዲቆዩ ንገረው::

ቀፈፈኝ። በባህራም ትእዛዝ ኒኮልን ጀምሺድ ቤት ወስጄ ለጀምሺድ ላስረክበው ለአንድ ሳምንት ሙሉ! በጣም ቀፈፈኝ፡፡ ግን
ምን ማድረግ እችላለሁ?
አንተም ይህን ሰሞን ተጠንቀቅ። ማታ ብቻህን አትውጣ»
አለኝ። ሲጋራ አቀጣጠለ። እጁ ትንሽ ትንሽ ይንቀጠቀጣል። ፍርሀት አሳደረብኝ
ሲልቪ ተመለሰች። ደህና እደሩ ብያቸው ሄድኩ ኒኮልን ቤቷ እገኘኋት። ጀምሺድ ቤት ስንሄድ አጣነው፡፡ ቤቱ ቁልፍ ነው። ካፌ ዶርቢቴል ሄደን ጠያየቅን፡፡ ተካ፣ ጀምሺድና ሉልሰገድ ኒስ ሄደዋል አሉን። ኒኮልና እኔ የመጨረሻውን የማታ አቶቡስ ተሳፍረን ማርሰይ ወረድን፡፡ አንድ ወሻቃ ቦታ ሆቴል
አገኘን። ባለ ሁለት አልጋ ክፍል ተከራየን። ሁለታችንም ለባህራም
ሰግተናል። አንቅልፋችን እንደማይመጣ ግልጽ ነው:: አንድ ቆሻሻ ብጤ ጭር ያለ ካፌ ገብተን ከልቫዶስ እየጠጣን፣ እያወራን፣
እየተያየን ሳቃችን እየመጣ፤ እየተሳሳቅን፣ ድንገት ሳቃችንን
አቋርጠን በፀጥታ እየተያየን፣ ስንተያይ ኒኮል በሚያስጐመጅ አኳኋን እየቀላች፣ እየቀላች፣ እየጠጣን እያወራን፤ ከአንድ ሰእት በላይ አሳለፍን፡ ሰከርን፡፡ የተረፈንን ግማሽ ጠርሙስ ካልቫዶስ ይዘነው ሞቃት ሰማይ መሀል
ሆቴላችን ስንደርስ፤ እንዳንተያይ መብራቱን አጥፍተን፣
👍20
ልብሳችንን አውልቀን፣ ወደየአልጋችን ገባን።
እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም። ሰክሬ፤ ኒኮል እዚሁ ክፍል
ውስጥ ተጋድማ እንዴት እንቅልፍ ይውሰደኝ? አስብ ጀመር፡፡
ሉልሰገድ ቡና አይነት ቢራ እየጠጣ ስለሷ የነገረኝ ሁሉ አሁን
ይታየኝ ጀመር፡፡ በሮዝ ቀለም የተከበበች ወይን ጠጅ ጨረቃ ነጭዐየኒኮል ጡት። ወተት ጭኖቿ መሀል በወርቃማ ጭራሮ የተከበበ ነበልባል የኒኮል ብልት። ይሄ ሁሉ ከኔ አራት እርምጃ ብቻ ርቆ አልጋ ውስጥ ተጠቅሉ «ቅዱስ ብልግናዋን ተከናንቦ ይጠብቀኛል። አሁን ቀስ ብዬ ሄጄ አልጋዋ ውስጥ ብገባ እንደማታባርረኝ እርግጠኛ ነበርኩ። የውሀ አረንጓዴ አይኖቿ ብዙ ነገር ነግረውኝ ነበር ግን መሄድ አልቻልኩም። በጓደኝነት
አላምንም። ግን ባሀራም እዚያ በሞትና በህይወት መካከል
እየተራመደ፣ እኔ የሱን ሴት ብነካበት፤ ከዚያ በኋላ ራሴን እንዴት ለማክበር እችላለሁ? ግን ያችን የመሰለች ሴት እንዴት ልልቀቃትን ይህን ሁሉ ጊዜ ስመኛት ቆይቼ፣ ዛሬ እድል አጋጥሞኝ ሳገኛት እንዴት ልልቀቃት? ደሞስ ባህራም ለኔ ምኔ ነው?

በጭለማው የምኞት ፍም እየጠበሰኝ ስገላበጥ
«ተኝተሀል?» አለችኝ
«የለም»
«እኔ ፈራሁ፡፡ ብቻዬን አዚህ ፈራሁ»
«ነይ ወዲህ»
በጭለማው መጥታ አልጋዬ ውስጥ ገባች። ስስ ውስጥ ልብሷን አልፎ ሙቀቷ ነካኝ፡፡ በሀይል ተጠጋችኝና፤ ሰውነቷ ከላይ እስከ ታች
እየተንቀጠቀጠ
«ፈራሁ፡፡ እኔ ፈራሁ» አለች
«አይዞሽ ማንም አይነካሽም፡፡»
«ለራሴ አልፈራሁም'ኮ። አንተ እያለህ ምን ያስፈራኛል? እኔ
የፈራሁት ለሱ ነው፡፡»
«ለሱ ከፈራሽ ሞኝ ነሽ፡፡ ፋሺስቶቹን እንዴት እንዳበሳጫቸው
አታስታውሺም?»
«ቢሆንም ፈራሁ»
«አይዞሽ! ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም።
ገላዋ ልስልስ ያለ ነው፡፡ ከሴቶች ይበልጥ ሴትነት የሰፈረበት፣
የግብረ ስጋ መቅደስ ያቀፍኩ መሰለኝ፡፡ ትንፋሿ አንገቴ ላይ የፍትወት ነበልባል ያቀጣጥላል። ሁለታችንም ወጣት ነን፣ ሁለታችንም ሰከረናል፣ ሁለታችንም ምስጢራዊ ጭለማ ውስጥ ተደብቀናል
ሁለታችንም የምኞት ማእበል የሚያናውፀው ሙቀት ውስጥ ተጠቅልለናል፣ የሁለታችንም ደም ፈልቷል። እጄን ከትከሻዋ ወረድ
ባደርግና የማባብላት አስመስዬ ወገቧን ጥብቅ አድርጌ ባቅፈው.
እንደዚህ! ደስ ማለቱ! .. ቀስ አድርጌ በቸልታ እጄን ወደታች
ሰደድ ባደርገውና ዳሌዋ ላይ ባሰርፈውስ? .. እንደዚህ!
የቡታቲዋ ጠርዝ ከእጄ ስር ታወቀኝ፤ ከገላዋ ሙቀት የባሰ የሙታንቲዋ ጠርዝ በምኞት ወጠረኝ። እኔ ሳላውቀው እጄ ሙታንቲዋ ውስጥ እየገባ አፌ አፏን ጎረሰው፡፡ የት እንደሆንኩና ማን እንደሆንኩ ረሳሁ። በመርሳቴ ደመና ላይ የባህራም ፈገግታ ብልጭ አለ እጄን ከሙታንታዋ እያወጣሁና አፌን ከአፏ እያላቀቅኩ፤ በሹክሹክታ
«ደግ አይደለም» አልኳት
«አዎን ደግ አይደለም» አለችኝ እሷም በሹክሹክታ
«ግን በጣም በጣም እፈልግሻለሁ፡፡ አንቺም ፈልገሽኛል፣ አይደለም?»
«አዎን»
«ምን ይሻላል?»
«እኔ እንጃ»
«እኔ በበኩሌ ልተውሽ አልችልም»
ዝም
«ደሞ ልተውሽ አልፈልግም። አንቺን መተው ራስን መኮነን
ነው።»
ዝም
«ምን ይሻል ይመስልሻል?»
«እኔ እንጃ»
«ባስገድድሽስ?»
«ማስገደድ አያስፈልግህም»
«እስከ ዛሬ ድረስ ያንቺን ያህል ያማረችኝ ሴት አጋጥሞኝ
አያውቅም። ደሞ እስከ ዛሬ ድረስ ሴት አግኝቼ ለሌላ ሰው ስል
ትቼያት አላውቅም፡፡ ዛሬ ግን እንዴት ልበልሽ
«ይገባኛል፡፡ ምንም ማድረግ አያስፈልግህም»
«አሁን ሁለታችንም የማናምንበት ነገር ብናደርግ በኋላ
ይቆጨናል፡፡ ግን እንድትለዪኝ አልፈልግም፡፡ ምን ይሻላል?»
«እኔ እንጃ። መብራቱን አብርተን የተረፈንን ካልቫዶስ እየጠጣን ብናወራስ?»
በመብራቱ ስንጠጣ ስናወራ ምን ያህል እንደቆየን አላስታውስም፡፡ እንዲያውም ከዚያ በኋላ ምን እንዳደረግን ወይም ምን እንደተባባልን የማስታውስ አይመስለኝም፡፡ ብቻ፣ ከአንድ አመት በፊት እንዳየሁት ህልም ሆኖ ትዝ የሚለኝ አንድ ነገር አለ።
ጠርሙሱ ውስጥ የቀረውን መጠጥ ከጨለጥነው በኋሳ፤ ራሴን ደረቷ ላይ እያንተራስኩ
«ይሄ ጡት መያዣሽ ይቆረቁረኛል» አልኳት
«ቆይ ላውልቅልህ» ብላ አውልቃው እንደገና ራሴን ደረቷ ላይ አንተራሰችልኝ፡፡ «ጡትሽ እንደ ሞቃት ሰማይ ነው፤ ሰማዩ ላይ
በፅጌረዳ ብርሀን የተከበበች ወይን ጠጅ ጨረቃ አለች» አልኳት
«ውሸታም! መቼ አየኸው?» አለችኝ
«ማየት የለብኝም»
«አሁን ዝም ብለህ ተኛ» አለችኝ
ከዚያ ወዲያ ምንም ኣላስታውስም
በነጋታው፣ ከሰአት በኋላ ወደ ስምንት ሰኣት ላይ ስነቃ፣ ኒኮል
ደረቴን ተንተርሳ ተኝታለች። አፌ ውስጥ የፋንድያ ጣእም ተሰማኝ።
ኒኮልን ቀሰቀስኳት
«ደህና ነሽ?» አልኳት
ደህና»
አፈርኩ
«ሳናውቅ የማንፈልገውን ነገር ሰራን 'ንዴ?» አልኳት
«የለም»
ኒኮልን ምሳ አብልቼ፣ ኣንድ ልብወለድ መፅሀፍ ገዛሁላትና
ሆቴል ክፍላችን ውስጥ ትቼያት ወደ ኤክስ ሄድኩ። ሲልቪ ቤት
ስገባ፣ አልጋዋ ውስጥ ተጋድማ ሲጋራ እያጨሰች ሙዚቃ ትሰማለች። የአይኖቿ ቆዳ እንደ መጥቆር ብሎ፣ የታችኛው ቆዳ አብጧል
«ምን ሆነሻል?» አልኳት ሌሊቱን አልተኛሁም
«ለምን? ባህራም የት ነው? ንገሪኝ»
ቆይ በደምብ ልንገርህ። አንተ እንደ ሄድክ፣ ትንሽ ቆይተን እኔና ባህራም ከካፌው ወጣን፡፡ እያወራን፣ ባህራም ኣንዳንድ ጊዜ
ገልመጥ እያለ ወደ ኋላ ይመለከታል፡፡ እኔን እንዳልገላመጥ ከለከለኝ። ጭለማው አስፈራኝ፡ የመንገድ መብራቶቹ በቂ ብርሀን
አልሰጡኝም፡፡ «አይዞሽ ይታየኛል። ምንም ሊያረገን አይችልም።
አለኝ። “ማን እንደሆነ አውቀሀል እንዴ?» አልኩት፡፡ «አዎን።
አይዞሽ» «አንድ ብቻውን ነው?» «አዎን አይዞሽ። በጭራሽ አትስጊ።
ብቻ እኔ የምልሽን ያለማመንታት አድርጊ።» «እሺ» «አይዞሽ።»
«እንግዲህ መንገዱ እዚያች ሶስት ትልልቅ ጥዶች ያሉባት ቦታ
ሊደርስ ይጠመዘዝና፣ አንድ ሀምሳ ሜትር ሄዶ እንደገና ይጠመዘዝ
የለ? መጀመሪያውን መጠምዘዣ እንደዞርን ሩጪ!» አለና በላይኛው
ክንዱ እንጠልጥሎ በሀይል አስሮጠኝ፡፡ ሁለተኛውን መጠምዘዣ እንዳለፍን ቆምን፡፡ ከመንገዱ ገለል አርጎ አቆመኝና፣ እሱ ከኪሱ ቆብ አውጥቶ ራሱ ሳይ ደፍቶ፣ ኮቱን አውልቆ ለኔ ሰጥቶኝ፣ መንገዱ መሀል ላይ ቆመ:: ወደ መጣንበት መንገድ ይመለከታል፡፡ እኔም
እመለከት ጀመር። ለብዙ አመታት እንደዚህ ቆመን የቆየን
መሰለኝ። ሰውየው ድንገት ከመጠምዘዣው ብቅ አለ። ባህራም ወደዚያው (ማለት ሰውየው ወዳለበት በኩል) ይራመድ ጀመር፡፡
እያፏጨ! ሰውዬው እጁን ኪሱ እንደከተተ ወደ ባሀራም ይመጣል።
አጠገብ ላጠገብ ሲደርሱ ባህራም
“Bon Seir!" አለው
"Bon soir" na narpa
«ጐን ለጐን ደረሱ። ሊተላለፉ ሆነ። ባህራም እንደሚደንስ ሰው
ወደ ሰውዬው በኩል ዘለለና በእጁ ሆዱን ነካው መሰለኝ። በቂ
መብራት ስላልነበረ በቅጡ አልታየኝም፡፡ ሆዱን ከነካው በኋላ፣
አንዲት ሰከንድ እንኳ ገና ሳታልፍ ዘሎ የሰውየውን ማጅራት
በሌላው እጁ መታው። ሰውዬው ወደፊት ታጠፈ። ወደቀ። ባህራም
እየጐተተ ከመንገዱ ወደ ዳር ወሰደው። ሁለቱንም ጨለማ ዋጣቸው እዚያው እንደቆምኩ ቀረሁ፡፡ ጭለማው ከቦኛል። አሁን
👍20👎2🤩1
ያየሁት አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሲጎዳው ነበር? በጭራሽ
አይመስልም፡፡ ሁለት ቅርፆች፣ ከልዩ ልዩ አቅጣጫ መጥተው
ተነካኩ፣ አንዱ ወደቀ፣ ያልወደቀው የወደቀውን እየጎተተ ወደ
ጭለማው አስገባው። በቃ፡፡
«አሁንም ለብዙ አመታት ብቻዬን እዚያ ጭለማ ውስጥ የቆምኩ
መሰለኝ
«አትፍሪ አይዞሽ» አለ ከአጠገቤ። ነጠርኩ። «አይዞሽ እኔ ነኝ»
አለኝ፡፡ ባሀራም ነው። ለምን እንደሆን እንጃ፣ በሄደበት መንገድ
ይመለሳል ብዬ ስጠብቅ ነበር፡፡ እሱ ግን በጭለማው በኩል
መጥቷል። ኮቱን ከኔ ወስዶ ለበሰና ቆቡን አውልቆ ኪሱ ከተተ።
በጭለማው ትንሽ ከተራመድን በኋላ ወደ ባቡር መንገድ ገባን፡፡
እግሬ ላይ ብርድ ተሰማኝ። ለካ ሳይታወቀኝ በፍርሀት ሽንቴ
አምልጦኝ ኖሯል
«እዚህ (ሲልቪ ቤት) ከደረስን በኋላ «ገደልከው?» አልኩት
የለም» አለኝ። ግን እንደገደለው እርግጠኛ ነኝ። በጩቤ ነው
የገደለው፡፡ እና ሌሊቱን ልተኛ አልቻልኩም።»
ሲልቪ ዝም አለች። እኔም ዝም አልኩ
«ፓሪስን በፀደይ አይተሀት ታውቃለህ?» አለችኝ
«የለም»
«በጣም ውብ ናት። ለአንድ ሳምንት ብንሄድ ምን
ይመስልሀል?»
«መቼ?»
«ዛሬ»
ዛሬ አልችልም፡፡ ምእራፍ ግማሽ ላይ ነኝ፡፡ ብትፈልጊ ከአንድ
ሳምንት በኋላ አንሂድ።
ባኞሽ ሙቅ ውሀ አለው?»
ገላዬን ታጥቤ ከባኞው ልወጣ ስል የወንድ ድምፅ ከሲልቪ ጋር
ሲነጋገር ሰማሁ። ልብሴን ለባብሼ ወደ መኝታዋ ስገባ፣ ባህራም
አልጋዋ ላይ ቁጭ ብሎ ሳንድዊች እየበላ ቀይ ወይን ይጠጣል። ሰው
የገደለ አይመስልም፡፡ ግን ሰው የገደለ ሰው ምን እንደሚመስል አላውቅም ኒኮል የት እንዳለች ነገርኩት ሲልቪ ተራዋን ልትጣጠብ ባኞ ቤት ገባች
ባህራም «ይቅርታ አርግልኝ፡፡ አንተ፣ ሲልቪ፣ ኒኮል ለአንድ
ሁለት ሳምንት ከኤክስ መጥፋት አለባችሁ። ኒኮልን ወደ ቤቶቿ
ወይም ወደ ሌላ ቦታ እልካታለሁ፡፡ አንተና ሲልቪ ተስማምታችሁ
ወደ አንድ ቦታ ብትጠፉ ጥሩ ነው። አየህ፣ ፋሺስቶቹ የበሰለ
አስተሳሰብ የላቸውም፡፡ ስለዚህ እኔን መጉዳት ሲያቅታቸው፣ በንዴት እናንተን ይጎዱዋችኋል። ስለዚህ ንዴታቸው ትንሽ እስኪበርድላቸው ከኤክስ ራቁ። እባካችሁን» አለኝ
በሹክሹክታ «ገደልከው?» አልኩት
ራሱን በመነቅነቅ «አዎን» አለኝ
«የመጀመሪያ ጊዜህ ነው ሰው ስትገድል?»
«ሶስተኛ ጊዜዬ ነው:: አንዱን በይሩት፣ ሌላውን ባግዳድ»
ይነግረኝ ይሆን? በማለት አየሁት። ዝም አለ፡፡ ዝም ሲል
የኢራንን ሻህ ይመስላል፡፡ እኔም ዝም አልኩት
«ፂምህን ብትላጭ ጥሩ ነው። ለመጠንቀቅ ያህል» አለኝ
«እሺ» አልኩት.....

💫ይቀጥላል💫
👍71
#አትተይኝ

እንደ ደራሽ ውሃ በፍጥነት ይሄዳል
እንዳለፈ ክረምት አይቆይም ይረሳል
ወቅት ሁሉ ይነጉዳል ሁሉም ነገር ያልፋል
በጠብ ያኳረፉን ደቂቃዎች ሁሉ
“እንዴት ለምን ?” በሚል የጥያቄ በትር
ደስተኛ ልቦች መትተው የሚገድሉ
ጊዚያቶችን እረሺ ውስጥሽ አይሣሉ
ሁሉንም ተያቸው እኛን አይወክሉ
በመጡበት መንገድ ዞረው ይሄዳሉ

እኔን ግን አትተይኝ...
ዝናብ ከሌለበት ከዛ ከሩቅ ሀገር
እኔ ላንች ፍቅር
ካለሽበት ድረስ ዝናብ እጠራለሁ
በዝናቡ ፈንታም
ስጦታ እንዲሆንሽ እንቁ አስዘንባለሁ
የእንቁው ጠብታ
ወርቃማ ብርሃን እንዲሆን አውቃለሁ
አትተይኝ አትተይኝ
እስከለተ ሞቴ
መሬቱን ቆፍሬ ጥልቁ መሃል ድረስ
አንችን ለመሸፈን ፍቅራችን ለማንገሥ
ሕጉ ንጹህ ፍቅር
ንጉሡ ውብ ፍቅር
አንቺ ደሞ ንግሥት የምትሆኝበት
አንጽልሻለሁ አዲስ ቤተ መንግሥት
ስሚኝ ብቻ ፍቅሬ
ማንም የማይገባው ልሳንን ፈጥሬ
በአዲስ መወድስ በአዲስ ዝማሬ
ሁሉን እነግራለሁ
ከሁለት ግዜ በላይ ስለተሳሳሙ
የሁለት ፍቅረኛሞች
ሁለት ንጹህ ልቦች
መሳጭ ውብ ታሪኮች
አወራልሻለሁ...
አንቺን ብሎ ወጥቶ
በዛው እንደቀረ ፍቅር ሳይሰምርለት
ነፍስ ይማር እያልኩኝ የንጉሡን ሕይወት
አወራልሻለሁ በቀን ሆነ በሌት
አትተይኝ አትተይኝ
እንዲህ ያለ ነገር መቸ ታይቶ ያውቃል ?
እሳተ ገሞራው ሲባል ጥንት አርጅቷል
ስላንቺ ከሆነ
እንደ አዲስ ተወልዶ እሳቱን ይተፋል
የመከነው መሬት የኖረው ሲቃጠል
ስላንቺ ከሆነ
ከመኸር የበዛ ውብ ስንዴ ያፈራል
ያመሻሽ ጨለማ የጀንበሯ ቅላት
የሰማይ ወጋገን የደመናው ጥለት
ስላንቺ ከሆነ
ይጋቡ የለም ወይ በመጥለቅያው ሰዓት
አትተይኝ
ተሸሽጌ ተደብቄ ከዚች ዓለም
ስትደንሺ አይሻለሁ አላለቅስም
በፈገግታሽ እስቃለሁ አላለቅስም
ስትዘፍኝም እሰማለሁ
ፈቀጅልኝ
ያንቺን ፍቃድ እሽዋለሁ
አትተይኝ አትተይኝ
እየተከተልኩሽ
ያጃቢሽን ጥላ የጥጃሽን ጥላ
የእጆችሽን ጥላ
የጥላሽን ጥላ
ያን ሁሉ ለመሆን
እየተከተልኩሽ እየተከተልኩኝ
አትተይኝ አትተይኝ

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍18😱1
#ከሰሀራ_በታች


#አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

የፍቅርተ ጂንስ ሱሪ ታጥቦ ከተሰጣበት የልብስ ማስጫ ገመድ ላይ ጠፋ፡፡ “የትኛው ሱሪ?”
የሚል ይኖራል፤ ፍቅርተ የነበራት አንድ ሱሪ ነበር፡፡ የጠፋውም ይሄው አንድ ለናቱ የሆነ ሱሪ ነው፡፡ የመንደሩ ሱሰኛ ጎረምሶች ለዕለት ሱሳቸው ማስታገሻ ወስደው ሸጠውት ይሁን አልያም ሞገደኛ ነፋስ እያግለበለበ ወስዶ አንዱ ቂርቂራ ሸጉጦት እግዜር ይወቅ፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ ከተገዛ ገና ስድስት ወር ብቻ የሆነው፣ ግርጌው ቀበኛ ከብት አኝኮ እንደተወው ጨርቅ
የተተፈተፈው የፍቅርተ ጥቁር ጅንስ ሱሪ ታጥቦ ከተሰጣበት ገመድ ላይ ጠፋ፡፡ ትልቅ የአገር
ቅርስ የጠፋ ያህል ነበር አንጀቴ ቁርጥ ያለው፡፡ ደምና አጥንት የተከፈለለት የአገር ድንበር
የተቆረሰ ያህል ነበር ውስጤ በቁጭት የተንገበገበው፡፡

በእርግጥ ይሄ ሱሪ መታጠብ ብዛት የልጅነት ጥቁር ቀለሙ ተገፍፎ ግራጫ መሆን ጀምሮ
ነበር፡፡ ኧረ እንደውም እንደ ሰው ፀጉር በስተርጅና ነጫጭ ጭረት ጣል ጣል ያደረገበት ሱሪ
ነበር፡፡ ቢሆንም እርጅናው ከሱሪው ህያው ዋጋ ላይ ሽራፊ ሳንቲም ሊቀንስ አይቻለውም፡፡
እርጅና የማያደበዝዘው እውነት፣ የዘመን ብዛት የማያጠፋው ሃቅ አለና፤ የዛ እውነት ማህደር
ነው የተወሰደው፡፡

የፍቅርተ ሱሪ ጠፋ ማለት የመንደራችን ባንዲራ ጠፋ እንደማለት ነው፡፡ ይሄ ሱሪ ተራ ሱሪ ብቻ አልነበረም፤ የማንነት መቋጠሪያ ጨርቅ፣ የተገፉ ድሆች እንባ ማበሻ መሃረም፣ የፍቅር
መክተቻ ከረጢት ነበር፡፡ ምን ያደርጋል ! ታጥቦ ከተሰጣበት ገመድ ላይ ጠፋ ፡፡

አንዳንዱ የደላው መንደርተኛ የፍቅርተ ሱሪ መጥፋቱን ሲሰማ “ይሄ ሁሉ ላይ ታች ማለት ለአንድ
አሮጌ ሱሪ ነው ?” እያለ ወደየ ጉዳዩ ይጣደፋል፡፡ “በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት” ቢባልም
ቅሉ እንዴት ሰው በራሱ ቁስል እንጨት ይሰድዳል? ስለፍቅርተ ሱሪ የማይመለከተው ማነው?

እኔ በበኩሌ የፍቅርተ ሱሪ ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ባይ ነኝ፡፡ ስንለው ስንጮኸው የኖርነው ቃል ነበር የፍቅርተ ሱሪ! አብሮን የኖረ ቃል ጨርቅ ለብሶ የተከሰተው በፍቅርተ ሱሪ ነበር፡፡ ድንገት የቀኝ እጄን ስመለከተው ሁለት ጣቶቼን ከቦታቸው ላይ ባጣቸው እንኳን የዚህን ያህል የምደነግጥ አይመስለኝም፡፡ እዚህ መዲናችን ውስጥ ያለው የአፍሪካ ህብረት ሕንፃ ድንገት ከስሩ ተነቅሎ የደረሰበት ጠፋ ሲባል የፍቅርተን ሱሪ ያህል አያስደነግጠኝም፤ ኧረ ፍቅርተ ራሷ ብትጠፋ የሱሪዋን ያህል
አታስደነግጠኝም፡፡ ስለዚህ ሱሪ የተዳፈነ ተስፋ፣ የተኮላሸ ፍቅር አለና ሱሪው ሱሪ ብቻ አልነበረም፡፡

ሱሪው የጠፋ ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ስምንት ሰዓት አካባቢ ከምማርበት ኮሌጅ ስመለስ እማማ አመለወርቅ በራቸው ስር ሁልጊዜ የሚቀመጡባት ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው አገኘኋቸው ዓይናቸው ቡዝዝ ብሎ በሀሳብ በመመሰጣቸው እስካናግራቸው ድረስ አጠገባቸው መድረሴንም
አላዩም ነበር፡፡ ለወትሮው እዚህች ድንጋይ መቀመጫ ላይ የሚቀመጡት እጃቸው አጠር ብላ
ለዕለት ቡና ብር ቢጤ ሲቸግራቸው ነበር፡፡ የድንጋይ ወንበሯ የመተከዣ መድረካቸው ናት::

“ማዘር ምነው ሰላም አይደሉም እንዴ?” አልኳቸው፤

ቀጥ ብለው እንባ ባኳተሩ ዐይኖቻቸው ተመለከቱኝና ሳግ ተናነቀው አሳዛኝ ድምፅ ፣ “የፍቅርን ሱሪ ወሰዱባት አብርሽ!” አሉኝ፤ ሊያናግሩኝ ቀና ሲሉ እያለቀሱ እንደቆዩ ፊታቸው ላይ ዳናውን የተወ እንባቸው ይናገራል፡፡

“እነማን ናቸው የወሰዱት?” አልኳቸው የሰማሁትን ባለማመን፤ ቅስም ከሚሰብር ዜና ኋላ
የተከሰተ የጅል የሚመስል ጥያቄ፡፡

“ምናውቄ ብለህ አብርሽ ! ከዚህ ከተሰጣበት ገመድ ላይ አንስተው ወሰዱት” አሉና እንባቸውን
ዘረገፉት፡፡ ድህነት እንደ ሸንኮራ መጥጦ ካደረቀው ሰውነት ይሄን ያህል እንባ ይወጣል ብዬ
አላሰብኩም ነበር፡፡ ሕይወት ምንጊዜም አዲስ እንባ አላት፡፡ከእንባቸው የበለጠ ፊታቸው ላይ
ያረበበው ሐዘንና ምሬት ያሳዝን ነበር፡፡አንጋጥጬ የልብስ ማስጫ ገመዱን ተመለከትኩት፡፡
ወዲህ የኤሌክትሪክ ምሰሶ ላይ ወዲያ ደግሞ የአንዲት ጎረቤት የቤት ጣራ ማገር ላይ የተወጠረው ገመድ የተወረረ ከተማ መስሏል፡፡ ባንዲራውን እንዳወረዱበት የሰንደቅ ምሰሶ ትከሻው ቀሏል፡፡ ባዶ !! ለፍቅርተ፣ ለእኔ፣ ለእማማ ዓመለ፣ ለመንደሩና ለአገሩ ባዶነትን ትቶልን የሄደው ማነው?

ይሄ ገመድ ባዶውን ውሎ አያውቅም ነበር፡፡ ቢጠፋ ቢጠፋ የጉግሳ አውራ ጣቱ የተሸነቆረ
ካልሲ ወይም አሁን የጠፋው የፍቅርተ ሱሪ ተሰጥቶበት ነበር የሚውለው፡፡ የፍቅርተ ሱሪና
የጉግሳ ካልሲ ሁልጊዜም ገመዱ ላይ ጎን ለጎን ተሰጥተው ስለማያቸው የልብ ወዳጆች ይመስሉኝ ነበር ፡፡የፍቅርተ ሱሪ ከፍ ያሉት ንቀውት ዝቅ ብሎ የካልሲ ጓደኛ የሆነ፡፡ ካልሲውም ቢጤዎቹ ንቀውት ቀን ከገፋው ሱሪ ጋር የዋለ ዓይነት፡፡

አንጋጥጬ ስመለከት ከገመዱ በላይ ጥርት ያለው ሰማይ ተዘርግቷል፡፡ የፍቅርተን ሱሪ የወሰዱት ሌቦች ለወትሮው ሰማዩ ላይ የማይጠፋውን ደመና የወሰዱት ይመስል ነበር፡፡ ሰማዩ ባዶ! የልብስ ማስጫው ገመድ ባዶ!! አይ አይ ሰማዩ እንኳን ባዶ አልነበረም፡፡ ነግቶ የረፈደባት የምትመስል ግማሽ ጨረቃ ትታያለች፡፡ የሱሪ ሌባው ግማሿን ጨረቃ ሸርፎ የወሰዳት ይመስል፡፡
ቆይ ግን ሱሪውን የወሰደው ሌባ ከሆነ ሌባውን ምን ነካው? እንዴት የፍቅርተን ሱሪ ይወስዳል? እሺ
ነፋስም ከሆነ ንፋሱን ምን ነካው ? አቧራ ያስነሳ፣ የቤት ጣራ ይገነጣጥል ቢፈልግ ! ያንን ከሰፈራችን ወደታች ያለውን የአድባር ዛፍ ከስሩ ገርስሶ ይጣለው ! ግን እንዴት የፍቅርተን አንድ ለእናቱ የሆነ ሱሪ ይወስዳል ? ምን ቁርጥ አድርጎት የመንደራችንን ባንዲራ ይደፍራል ? በሌባው ተቆጣሁ
በነፋሱ ተቆጣሁ ፡፡ በፈጣሪም ተቆጣሁ :: መምሬ ልሳኑ ታዲያ (የእማማ አመለ ንስሃ አባት)
የሱሪውን መጥፋት ሲሰሙ፣ እማማ አመለን ለማፅናናት ብለው ይሁን አልያም አምነውበት እንጃ
ብቻ ጥቅስ አጣቀሱ፤ “ላለው ይጨመርለታል፣ ከሌለው ግን ያለውም ይወሰድበታል ወለተ ኪዳን አይዞሽ” በዚህ ማፅናኛቸው በጣም ተበሳጨሁ፤ እንደውም በፈጣሪ ላይ የተሰማኝ ቅሬታ ተባባሰ፡፡

ፈጣሪ የሌባው እጅ ወደ ፍቅርተ ሱሪ ሲዘረጋ እንደ ደረቅ እንጨት ድርቅ አድርጎ ማስቀረት ይችል ነበር፡፡ ነፋስና ማዕበልን የሚገስጽ ፈጣሪ እንዴት ዝም አለ ? እሳት ከሰማይ የሚያወርድ አምላክ ከዚህ በላይ በደል፣ ከዚህ በላይ ግፍ ምን አለና ታገሰ ? የፍቅርተን ሱሪ የወሰደው ንፋስ ከሆነም መገሰጽ ይችል ነበር፣ ስለምን ዝም አለ ? እንኳን አጋጣሚውን አገኘሁ እንጂ ፈጣሪ ጋርማ በፍቅርተ ጉዳይ ብዙ ጥያቄ አለኝ! ብዙ ! ሲጀመር ፍቅርተን ስለምን እንዲህ አድርጎ ፈጠራት…እኮ ለምን !? ለእሱስ ለስሙ ጥሩ ነው ??

“የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው” ይሉት ብሂል ስጋ ለብሶ የተገለጠው እማማ አመለ ቤት ነበር፡፡እማማ አመለ በመልክ ይሁን በባህሪ የማይገናኙ፣ ከፆታቸው በቀር አንድ የሚያደርጋቸው አንድ
ነገር እንኳን ፈልጎ ማግኘት የሚከብድ ሁለት ሴት ልጆች ያሏቸው፣ እድሜያቸው የገፋ ደግ ሴት ነበሩ ፡፡ ከሁለት ክፍል ቤታቸው አንዷን ተከራይቼ ለአራት ዓመታት ቤታቸው ውስጥ ኖሬያለሁ፡፡
👍263🥰2🔥1
ለስሙ ሁለት ክፍል ተባለ እንጂ አብረን በደባልነት እንደኖርን ነበር የሚቆጠረው፡፡ እማማ አመለ
ከሁለቱ ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩበትን ከፍል ረግጬ የእኔ ክፍል ወደሆነችው ጓዳ አልፋለሁ፤
አንዳንዴ ታዲያ ወደ እኔ ክፍል ለማለፍ የተደረደሩትን እቃዎች መዝለል ይኖርብኛል፡፡ በተለይ
ቡና ከቀራረበ ረከቦቱን መራመድ ግድ ነበር፡፡ የእኔ ክፍል ከእነ እማማ አመለ ክፍል የሚለየው
በአንድ ስስ መጋረጃ ነበር :: እኔ ቤት ሆኖ የእነማማ አመለን ቤት አጠቃላይ እንቅስቃሴ
መመልከት ይቻላል ፤ ድንበራችን ስስ መጋረጃ ነበርና፡፡

ፍቅርተ የእማማ አመለ ሁለተኛ ልጅ ናት፡፡ ፍቅርን ጨምሮ ሁሉንም ነገር የነሳት፣ የአርባ ቀን እድሏ በየቀኑ አርባ የሰቆቃ ጅራፍ የሚያሳርፍባት መልከጥፉ ወጣት ናት፡፡ ልቅም ያለች መልከ
ጥፉ ነበረች፡፡ ቁንጅና እንደተመልካቹ ነው ቢባልም ፍቅርተን “ቆንጆ” የሚል ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም፤ ራሷን ፍቅርተን ጨምሮ፡፡

ፍቅርተን ድንገት የተመለከታት ሰው ድንገት የተከሰተ ሰይጣን ፊት የቆመ ሊመስለው ይችላል፡፡
መጀመሪያ ግማሽ ፊቷን የሞላ የሚመስለው ትልልቅ እና የተፍረከረከ ከንፈሯ ድራማ ለመስራት የተጠለቀ ጭምብል እንጂ በእርግጥም የአንዲት የአስራ ስምንት ዓመት ወጣት ከንፈር አይመስልም፣ከላይኛው ከንፈሯ የተረፈው ቦታ ላይ ለምልከት የተቀመጠው አፍንጫዋ ወደላይ ቀና ብሎ
ሰፋፊ ሸንቁሮቹ ፊት ለፊት የቆመ ተመልካች ላይ የተደገኑ መንታ የከባድ መሳሪያ አፈሙዞች .
ይመስላሉ፡፡የመርፌ ቀዳዳ የሚያካክሉ ዓይኖቿ ሁሌም ጉሽርጥ መስለው እንደቀሉ ናቸው፡፡ የፀጉሯ ነገር አይነሳ ! የፍቅርተ ፀጉር ቀለም የለውም ፤ የማለዳ ጠል የሰፈረበት የሜዳ ላይ ችፍርግ ! ስታበጥረው አሰቃቂ ፉጨት የመሰለ ድምፅ ይወጣል፡፡

ይህን ሁሉ ተፈጥሯዊ በደል የተሸከመችው ፍቅርተ በዚህ በቃሽ ቢላት ጥሩ ነበር፤ ከቁመቷም ክፉኛ በድሏታል፡፡ በእጥረቷ ላይ ሲበዛ ትልልቅ ጡቶቿና አጠቃላይ የሰውነቷ ውፍረት ተዳምሮ በሰቆቃ እንድትኖር ፈርዶባታል፡፡ በእርግጥ ሰዎች እግዜር የሰጣትን በፀጋ መቀበልና መኖር ነው ለምን ትሳቀቃለች?” የሚል ጉንጭ አልፋ ንግግር ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ግን እንደባለቤቷ ሰቆቃው ሊገባቸው አይችልም፡፡ “ምክርና ቡጢ ለሰጪው ቀላል ነው” እንዲሉ ፡፡ የልብሳቸው መዛነፍ፣ የከንፈር ቀለማቸው አለመስተካከል የሚያስጨንቃቸው ቆነጃጅት “እግዜር የሰጠውን ይሏታል፤ ይሄን ሁሉ ነገር የተሸከመችውን ፍቅርተን !

እንግዲህ የእናት ሆድ ሲዥጎረጎር ፋና ተወለደች ፤ “ያየሽ ይውደድሽ?” የሚል ምርቃት አብሯት የተወለደ፡፡ ከባህሪውም ከቁንጅናውም አትረፍርፎ የሰጣት ውብ የአስራ ዘጠኝ ዓመት ወጣት
ነበረች መልዓክ ! ፋናን ዓይኗን ትክ ብዬ ማየት አልችልም፡፡ ርዳለሁ እፈራታለሁ፡፡ቁንጅናዋ ከተለመደው የሴት ልጅ ቁንጅና ያልፋል፡፡

በዕድሜ ከእኔ ብታንስም ሁልጊዜም አጠገቧ ስቆም ትገዝፍብኛለች፡፡ ፋና ለእኔ ቆንጆ ብቻ አልነበረችም፤ የቁንጅና ማነፃፀሪያ ሚዛን የለም እንጂ፡፡ ልክ የሌለው ቁንጅና፣ ቃል የማይገልፀው መስህብ ነበራት፡፡ የፊቷ ቆዳ ነፋስ እንደቆለለው የምድረበዳ አሸዋ ለስላሳ ነበር፡፡ እንዲሁ በዓይን ሊመለከቷት በእጅ የዳሰሷት ያህል ልስላሴዋ ይሰማል፡፡ ዓይኖቿ ልብን የሚያስጨንቁ ነገሮች ናቸው፡፡ ፋና በልብ ውስጥ ለዘላለሙ የሚታተም ግን ቃል አውጥተው የማይናገሩት ቁንጅና የነበራት ልጅ ነበረች፤ ህያው ፈተና !

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንግድ ስራ ኮሌጅ (ኮሜርስ) ተማሪ ነበርኩ፡፡ ለአንድ የክፍለ ሐገር
ልጅ ይቅርና አዲስ አበባ ተወልደው ላደጉ ልጆችም ቢሆን ንግድ ስራ ኮሌጅ መማር ከባድ
ነበር፤ የመጀመሪያው ችግር ኮሌጁ ለተመደቡ ተማሪዎች የመኝታም ይሁን የምግብ አገልግሎት ስለማይሰጥ በየወሩ ለተማሪዎች እዚህ ግባ የማይባል የኪስ ገንዘብ እየከፈለ ከግቢ ውጭ እየኖሩ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ያደርጋል፡፡ ተማሪው በአካባቢው ቤት አፈላልጎ በመከራየት ትምህርቱን ይቀጥላል፡፡

ገና ከጅምሩ እዚህ ኮሌጅ መመደቤን ስሰማ አልቅስ አልቅስ እያለኝ ነበር ከክፍለ ሐገር ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት፡፡ የኮሌጁን ተማሪዎች የማሰቃየት ጀብዱ በሩቁ ሰምቻለሁ፡፡ በዛ ላይ አዲስ አበባ የመጣሁት፡፡
አዲስ ስለነበርኩና የማውቀው ሰው ስላልነበረኝ እንኳን እየዞርኩ ቤት መፈለግ ቀርቶ አምስት ርምጃ
ብራመድ ተመልሼ አልጋ የያዝኩበትን ሆቴል የማገኘው አይመስለኝም ነበር፡፡ በዚህ ግራ በተጋባሁበት ወቅት ነበር ባረፍኩበት ሆቴል አልጋ አንጣፊ በኩል የእማማ አመለን ቤት ለመከራየት የበቃሁት ::
“እንደው መንደሩም ቤቱም ይሆንህ አይመስለኝም እንጂ የሚሆንህ ከሆነ አንዲት ጎረቤታችን አንዲት ክፍል ቤት አለቻቸው” አለችኝ የሆቴሉ አልጋ አንጣፊ፡፡ ቤቱን ልናይ ጎተራ አሁን ቀለበት መንገዱ የተሰራበትን ወደቀኝ ትተን ወሎ ሰፈር የሚባለው አካባቢ ሄድን፤ በመንገዱ ግራና ቀኝ የተሰደሩት ትላልቅና ውብ ሕንፃዎች ጀርባ ውስጥ ለውስጥ ሂደን እዚህ አካባቢ ይኖራል ተብሎ የማይታሰብ ጭርንቁስ መንደር ውስጥ ገባን፡፡ እርስ በርስ ተደጋግፈው የቆሙት ቤቶች
ግድግዳ ላይ ተለጥፈው የተሰሩ የውሻ ቤቶች እንጂ የሰው ቤት አይመስሉም፡፡ “ጨረቃ ቤት”
እንደሚባሉ በኋላ ሰማሁ፡፡ አፈር አፈር የመሰሉ ሕፃናት መንደሩ ውስጥ ውር ውር ይላሉ፡፡
ትንሽ ተጉዘን ካገኘናቸው መደዳ ቤቶች ያሉበት ቦታ ስንደርስ በአንዱ በር ላይ ቆምን፡፡ ፍቅርተ
እና እናቷ እማማ አመለ ነበሩ ያናገሩኝ፡፡

እውነቱን ለመናገር ፍቅርተን ሳያት ላማትብ ቃጥቶኝ ነበር፡፡ በስመአብ በ…፡፡ ድንገት ፍቅርተን
የተመለከተ ሰው ሊሰማው የሚችለው ነገር ቢኖር ይሄው ነው፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አዲስ አበባ ውስጥ የዚህ ዓይነት ቤትም፣ የዚህች ዓይነት ልጅም ይኖራሉ ብዬ አስቤውም አልሜውም አላውቅም፡፡እንደውም ያመጣኝ አውቶብስ በትክክል አዲስ አበባ እንደጣለኝ ተጠራጠርኩ፡፡የእኔ ቤተሰቦች መካከለኛ ኑሮ የሚኖሩ የክፍለ ሐገር ሰዎች ናቸው፡፡ ያደግኩበት ቤትና ግቢ ግን በስፋትም በንፅህናም ከዚህ “ቤት” ጋር ሲወዳደር…ኧረ አይወዳደርም፡፡ ወይ አዲስ አበባ !!

“ለጊዜው እዚህ ቤት አረፍ ብዬ አገሩንና ሰዉን ስለምደው የተሻለ ቤት እፈልጋለሁ” ብዬ የአዲስ
አበባ የቤት ችግር መፈናፈኛ ያሳጣኝ እኔ ጓዳዋን በሶስት መቶ ብር ለመከራየት ተስማማሁ፡፡

ከሰዓት በኋላ አንዲት የስፖንጅ ፍራሽ ገዝቼ ካረፍኩበት ሆቴል ሻንጣዬን በመያዝ ወደተከራየሁት
“ቤት” ስመለስ ያጋጠመኝ ነገር ባንድ ራስ ሁለት አስወራኝ፡፡ “ያመጣኝ አውቶብስ አዲስ አበባ
ነው ወይስ ገነት ያወረደኝ?!”፤ ፋና በር ላይ ቆማ ነበር፡፡ ፋና የእኔ የማለዳ ጀምበር…! ፋና
የእኔ ደግ ፊት ! ሩህሩህ ፊት፣ የተከሰተች መልአክ…!
ሻንጣዬን ልትቀበለኝ እጇን ዘረጋች፡፡ ለስላሳ ጣቶቿ የእጄን መዳፍ ነኩኝ! የከተማው የኤሌክትሪክ ኃይል ሁሉ በፋና እጅ በኩል አድርጎ ልቤን ቀጥ እስኪያደርገው ነዘረኝ፡፡ አዲስ አበባ በጨለማ ተውጣ በጥቁር አዲስ አበባ ላይ ፋና የምትባል ፀሐይ ፍንትው ብላ ወጣች ! እነሆ ይህቻትና አዲስ አበባ የልዩነት አገር… ሁሉን ቻይ አዲስ አበባ! የሁሉ መኖሪያ አዲስ አበባ! ከትላልቆቹ ሕንፃዎች ኋላ ሲኦልና ገነት በፍቅር በመተሳሰብና በአንድነት ተቃቅፈው የሚኖሩባት አዲስአበባ! የአዲስ አበባ ልጅ የሆንኩ መሰለኝ፤ አዲስ አበባ ተወልጄ ያደግኩ መሰለኝ፡፡
👍20
ፋና ፋና ፋና ፋና ያለችበት ቤት ውስጥ ልኖር ነው፡፡....
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንግድ ስራ ኮሌጅ እግዜር ይስጠው፤ አካውንቲንግ ላስተምርህ ብሎ
ጠርቶ፣ ከቁጥሮች ክምር ውስጥ እውነትን ማውጣት ላስተምርህ ብሎ ጠርቶ፣ ድህነት ከቀበረው
መንደር ውስጥ የወርቅ ፍልቃቂ የመሰለች ልጅ እንዳወጣ የተላክኩ መልአክ አደረገኝ፡፡ እኔኮ ቆንጆ ሴት ሲያዩ የሚደነግጡት የፊልም አክተሮች ብቻ ይመስሉኝ ነበር፡፡ ፈዘዝኩ ! ፋናን ስመለከት ፈዘዝኩ፡፡
ከዚች ቤት እንኳን ራሴ ልወጣ ውጣም ቢሉኝ እግሬን እንደማላነሳ የገባኝ ገና ፋናን እንዳየኋት ነበር፡፡ “ለልማት መንደሩ ሊፈርስ ነው መድረሻህን ፈልግ” ቢሉኝም “አብራችሁ አፍርሱኝ ከማለት ወደኋላ እንደማልል የገባኝ የፋና ጣቶች ሲነኩኝ ነው ፡፡ማን አለ ለርስቱ የማይሞት!
ፋና እኮ ርስት ናት፤ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ የተዘረጋች
እግዚዮ ! ፋናን እዚህ መንደር ውስጥ ምን እግር ጣላት ?! መቼም ከዚህ ቤት በሆነ መንገድ
አውጥተው ቢጥሉኝ አርቀው እንደጣሉት ውሻ፣ ጫካ ወስደው እንደወረወሩት ድመት የፋናን
ኮቴ እያነፈነፍኩ ተመልሼ እዚሁ መገኘቴ አይቀርም፡፡

ማንም ችኩል ቢለኝ ግድ አይሰጠኝም፡፡ ፋናን ገና ስመለከታት ልቤ ውስጥ የማይናወጥ የፍቅር ሐውልት ቆሟል፡፡ ማንም ብትሆን ግድ አይሰጠኝም፤ ቤት ውስጥ ምንሽር የታጠቀ፣ ጓንዴ ትራሱ ስር
ያስተኛ ባሏ ቢቀመጥ፣ ሰባት ልጆቿ “እማ እማ!” እያሉ የሚንጫጩ ሴት ብትሆንም ግድ የለኝም፡፡ፋናን አየኋት፣ ወደድኳት በቃ!! ይሄ ሁሉ ነገር የሆነው አንድ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ እና ይሄን ሁሉ ሴኮንድ፣ ዘላለም የሚያህል ደቂቃ ፋናን አይቼ ባፈቅራት “ቸኮልክ” የሚለኝ ማነው?!......

ይቀጥላል
👍18
ማንኛውንም አይነት ከ 3 k (3000) ተከታይ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ድረስ ያላችሁን ቻናል ለመሸጥ ካሰባችሁ በ @buchula36 ላይ አውሩኝ አመሰግናለው።
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ጥሪ
የሳጥናኤል ኮከብ

የሴሰኝነት ጥሪ
ሲልቪ

እኔና ሲልቪ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ፓሪስ ተጓዝን። በሷ መሪነት
ከፓሪስ ጋር ይበልጥ ተዋወቅኩ። በሲልቪ አስተማሪነት ከቅናት ጋር
ይበልጥ ተዋወቅኩ፡፡ ራሴንም ይበልጥ አወቅኩ ፓሪስ በገባን በሁለት ቀናችን፣ እንደ ልማዷ አንድ ደስ የሚላት ጎረምሳ አየችና አጣድፋ ወደ ሆቴላችን ወሰደችኝ፡፡ መብራቱን አጠፋች፡፡ እንደ “ልማዷ በኔ ገላ ጎረምሳውን ተደሰተችበት፣
አቃሰተች፣ ነገሩ ሊያልቅ ሲል ጮኸች። ተኛን፡፡ ያን ጊዜ እኔም
እሷም አላወቅነውም እንጂ፣ ከኔ ጋር እንዲህ ስትሆንና ስታደርግ
የመጨረሻ ጊዜዋ ነበር ነቃሁ። ጭለማ ውስጥ ነኝ። ምን እንደቀሰቀሰኝ እንጃ:: ከጎኔ
ተንቀሳቀሰች፡፡ በእንቅልፍ ልቧ «“Non! Non! Non!" እያለች
እየተጨነቀች ተፈራገጠች። በጣም የሚያስፈራ ህልም መሆን
አለበት። እየቀሰቀስኳት
«አይዞሽ አይዞሽ፣ ከኔ ጋር ነሽ» አልኳት ራሷን እየደባበስኩ።
በሀይል እየተነፈሰች ተጠጋችኝና
«አንድ ነገር አስደነገጠኝ፡፡ መብራቱን አብራልኝ አለችኝ
አበራሁት። አይኔ ብርሀኑን ከለመደው በኋላ ታየችኝ፡፡ ጥቁር
ረዣዥም ፀጉሯ ጉንጭና አንገቷ ላይ ተጠምጥሟል፣ተለጣጥፏል። ግምባሯ ላይ ላቡ ያብለጨልጫል፡ ጠረግኩላት፣
ፀጉሯን ወደ ኋላዋ ሰበሰብኩሳት
ውሀ» አለችኝ፡፡ ራስጌ ካለው ጠርሙስ አጠጣሁዋት
«ደህና ነሽ?» ስላት፣ ሳቅ ብላ
«አጥፋው» አለችኝ። አጠፋሁት፣ አቀፍኳት
«ቅዠት ነበር፡፡ ኮሙኒስቶች የኢራንን ሻህ መንገድ ላይ
አግኝተውት በጩቤ ሲገድሉት አየሁ፡፡ በኋላ ግን ባህራም ሆነ።
«አይዞሽ ነቅተሻል፡ አይዞሽ» እያልኩ እጄን ጀርባዋ ላይ
ሳንሸራትት ትንሽ ከቆየሁ በኋላ
Tu es plutôt une mére Française qu' un sauvage Africain"
አለችኝ («ፈረንሳዊት እናት ነህ እንጂ አፍሪካዊ አረመኔ
አይደለህም ኮ») ሁለታችንም በሳቅ መንፈርፈር ጀመርን። ታድያ'ኮ ያን ያህል የሚያስቅ አልነበረም፤ ያን ጊዜ መሳቅ ስላስፈለገን ነው
እንጂ፡፡ እየተጠመጠመችብኝ፣ ደስታ ባፈነው ድምፅ
«መኖር እንዴት ጥሩ ነው!» አለችኝ
ካንቺ ጋር ሲሆኑማ!»
የኔ ካስትሮ፣ ይልቅ ካንተ ጋር ሲሆኑ ነው እንጂ፡፡»
እቅፍ አድርጌ ጉንጯን ሳምኳት። በጭለማው ላዬ ላይ ወጣች፡
እንደምትወደው ጀርባዋንና አንገቷን እያሻሸሁ
«ምን ይሰማሻል?» አልኳት
እንደምትወደኝ ይሰማኛል»
«አውቀሻል»
«የተለየ ስጦታህ ምን እንደሆነ ልንገርህ?»
«ምንድነው?»
«የሰላም
ተሰጥዎ ነው ያለህ፡፡ ካንተ ጋር ስሆን ሰላም ይሰማኛል። ካንተ ጋር ስሆን ፀፀትና ንስሀ አያስፈልገኝም፡፡»
«ፀፀትና ንስሀ?»
በተለወጠ ድምፅ
«ቅድም ስለበደልኩህ ገላህን ለጋራ ጥቅማችን ሳይሆን ለግል
ደስታዬ ስላዋልኩት»
ፀፀት ሊጀምራት እንደሆነ ገባኝ፡ አሳዘነችኝ
«የኔ ቆንጆ፡ ቂል አትሁኚ። አንቺ ገላሽን እንድደሰትበት
ትሰጪኝ የለ?» አልኳት
«አዎን»
«ታድያ እኔ ገላዬን እንድትደሰቺበት ብሰጥሽ ምናለበት?»
«ከዚያ ይለያላ»
«አስር ጊዜ ልዩ ይሁን። በናንተ አገር ፍቅር ማለት ምንድነው?
መስጠትና መቀበል አይደለም?»
«ነው»
«ታድያ ገላዬን ብሰጥሽና ተቀብለሽ ብትደሰቺበት ምን ፀፀት
ያስፈልገዋል? እኛ አገር መስጠት ማለት መስጠት ነው። ገላዬን
ከሰጠሁሽ የራስሽ ሆነ ማለት ነው፡፡ የራስሽ ከሆነ ደሞ የፈለግሽውን ልታረጊበት ትችያለሽ ማለት ነው።
«እንደሱ ሆኖ ነው እሚታይህ?»
«ነው እንጂ»
«እንዴት ጥሩ ነህ! እኔ ግን እንዴት መጥፎ ነኝ!»
እንዴት?
«ውሸታም ነኛ!»
«ውሸታም?»
«አዎን፡፡ ለምሳሌ፣ ያን ጊዜ ስትጠይቀኝ የሌላ ሰው ገላ
እያቀፍሽ በሰውየው ገላ ከኔ ጋር ተኝተሽ ታውቂያለሽ ወይ?”
አላልከኝም? እኔ ምን አልኩህ? »
«በጭራሽ አድርጌው አላውቅም አልሽኝ»
«አዎን። ግን ውሽቴን ነበር። ላንተ
መዋሸቴ በጣም ይቆጨኛል፡፡ ስለዚህ አሁን አንድ ውል እንግባ። አንተ ላለፈው ውሸቴ ይቅርታ አድርግልኝ። እኔ ደሞ ለወደፊቱ ሁልጊዜ እውነቱን እነግርሀለሁ፡፡»
«ስሚኝ የኔ ቆንጆ:: ለኔ ምንም ነገር መንገር የለብሽም፡፡»
“አውቃለሁ። ለዚህ ነው ልነግርህ የምፈልገው:: ከዚያም በላይ፣
አንተ ልትረዳኝ ትችል ይሆናል፡፡ እውነቱን ልንገርህ?»
«እሺ»
«አትጠላኝም?»
«በጭራሽ አልጠላሽም»
እሺ፡፡ ያኔ ታስታውሳለህ?»
የኔ ሻህራዝድ የኔ ቆንጆ፣ እንዴት ልረሳው እችላለሁ?»
“ተመስገንን ፍለጋ የምመጣ ይመስልህ ነበር፡፡ እኔ ግን አንተን
ለማግኘት ነበር የምመጣው፡፡ ሳይህ በጣም ደስ ትለኝ ነበር።
ካስትሮን ትመስለኝ ነበር። ስንቀልድ ስንስቅ ጥርስህን አፍህን ሳየው
አንቀህ እንድትስመኝ እመኝ ነበር፡፡ ታድያ አንተ እምቢ አልክ።
ስለዚህ ካንተ ስለይ፡ ተመስገን ጋ እሄድና አይኔን ጨፍኜ አንተን
እያሰብኩ አቅፈው ነበር፡፡»
«ያውቅ ነበር?»
«ምስኪን ተመስገን! እንዴት አርጎ ይወቅ?»
እንጃ፣ ነግረሽው ሊያውቅ ይችላል ምናልባት?»
«እንዲህ አይነት ነገር እንዴት ሊገባው ይችላል?»
»እሺ ቀጥዪ»
«ትጠላኛለህ»
«እንግዲህ ቂል አትሁኚ፡፡ በኔ የመጣ ስለምንም አለመግባባት
አትስጊ። ንገሪኝ፡፡»
«እንዴት አርጌ ልንገርህ?»
«እንደመጣልሽ»
ከነገርኩህ በኋላ ምን እንደሚመስልህ ትነግረኝ እንደሆን»
“Parole d'honneur?'' (የከበሬታ ቃልህን ሰጥተሃል?»)
“Parole d'honneur” («የከበሬታ ቃሌን ሰጥቻለሁ»)
«እሺ። እንዲህ ነው:: አየህ፣ ካንተ ጋር ግብረ ስጋ በጣም
ደስ ይለኛል። ደጋግሜ ነግሬሀለሁ፡፡ ያንተን ግማሽ እንኳ ያህል እኔን ማስደሰት የቻለበት የለም፡፡ ብቻ ምን ልበልህ፣ ታጠግበኛለህ፡፡ ግን
በሽታዬ ይመጣል። ሲመጣ ደሞ መከላከያ የለኝም። ገባህ?»
«ገና አልገባኝም
«እንዳልኩህ፤ ታጠግበኛለህ፡፡ ግን በሽታዬ ይመጣል፡፡ በጣም
ታምረኛለህ፣ በሀይል እመኝሀለሁ
«ታድያ አለሁልሽ አይደለም?»
“እንደሱ አይደለማ የምታምረኝ»
ልቤ መምታት እየጀመረ
“ታድያ እንዴት ነው?» አልኳት፣ ጐሮሮዬም መድረቅ ጀምሯል
በሀይል ታምረኛለህ፣ ምኞቱ ያንገበግበኛል። ግን ስትተኛኝ
በገዛ ገላህ እንዳይሆን ያስፈልጋል። የሌላ ወንድ ገላ ተውሰህ፣ በሱ ገላ አንተ እንድትተኛኝ ፈልጋለሁ። እንደዚህ ያማርከኝ ጊዜ፣ ካንተ
ተለይቼ መሄድ ይኖርብኛል።»
«ወዴት?» ጉሮሮዬ ጨርሶ ደርቋል
“አንተን ፍለጋ፣ ሌላ ወንድ ፍለጋ»
«ታገኚዋለሽ?»
«ምን ይመስልሀል?» ጉሮሮዋ ውስጥ ወፍራም ተንኮለኛ ሳቅ
ተሰማኝ ቅናት ማለት ይሄ ይሆን እንዴ? ታድያ ንዴቱና ብስጭቱ
የታለ? እኔን የሚሰማኝ ጥልቅ የሆነ እሳት የሆነ የሚያቃጥል
ቅንዝር! እንደ ዛሬም አንገብግቦኝ አያውቅ! ተለይታኝ ስትሄድ፣
ወፍራም ዳሌዋን እያወዛወዘች፣ ውብ ኣይኖቿን ክፍት ክድን
እያረገች፣ በፍትወተ ስጋ እስኪፈነዱ ብልታቸውን በሚያሳብጠው ፈገግታዋ የመረጠችውን እድለኛ ወንድ ስትጣራ ታየችኝ። ስጋዬ
አላስታግስ አላስችል አለኝ፣ እላዬ ላይ እንደተጋደመች በጥድፊያ
ገለበጥኳትና ጭኖቿን ፈልቅቄ ስገባ፣ በሙዚቃዊ ፈረንሳይኛዋ፣
በቅንዝር ድምፅዋ
“Ah. cheri, comme tu es sauvage! C'est delicieux"
👍20
አቀፈችኝ፡፡ (አንተዬ፣ እንዴት አውሬ ሆነሀል! ደስ ሲል!)
ዝም ጭጭ አልኩ፣ እውነትም አውሬ ሆኜ ነበር
አይ ሲልቪ! ለኔ እንዴት ደግ ነበረች! ስታባብለኝና ስታፅናናኝ
እንደ ህልም መስሎ ይታወቀኝ ነበር፡፡ ጭንቅላቴንና ትከሻዪን
እያሻሽች፣ በልዝብ ፈረንሳይኛዋ፣ በልስልስ ድምፅዋ እየደጋገመችልኝ
«አይዞህ የኔ ቆንጆ፡ ከኔ ጋር ነህ የኔ ፍቅር፤ አንተን ነው የምወደው
የኔ አበባ፣ አይዞህ ውደደኝ» ስትለኝ ይሰማኝ ነበር ..
በኋላ፣ እግሮቿ መሀል እንዳለሁ፣ ትንሽ ወደታች ገፋ አድርጋ ሆዶን አንተራሰችኝ፡፡ እጇ ጭንቅላቴን ሲያሻሽኝና የተንተራስኩት
ሆዷ ከትንፋሿ ጋር ከፍ ዝቅ ሲል፤ እሹሩሩ እንደምትለኝ የሚያጎናፅፍ፣ ሰፊ ጥልቅ የሆነ ሰላም እየተሰማኝ እንቅልፍ እያንሳፈፈ ወሰደኝ
ስነቃ ሲልቪ በውብ አይኖቿ ታየኛለች፤ አልጋው ጎን ተምበርክካ እጇን ከጉንጫ ጋር ታሻሻለች፡፡ መስኮቱ ተከፍቶ የፀደይ
ብርሀንና ነፋስ ይገባል። ውስጥ ውስጥ ውስጥ፣ ልቤ ልብ ውስጥ
ደስታው ሲመነጭ ተሰማኝ፡፡ እንደተምበረከከች እጄን ከጉንጫ ጋር እያተሻሽች
የመሄጃችን ሰአት ደርሷል ብዬ ነው የቀሰቀስኩህ፡፡ ቁርስ ይምጣልህ?» አለችኝ
«ይምጣልኝ፡፡ ለምንድነው የተምበረከክሽው?»
እኔ እንጃ። ተኝተህ ሳይህ እንዴት ታምራለህ! ፂምህን
ስትላጭ ለካ በጣም ቆንጆ ነህ!»
ተነስቼ ፊቴን ስታጠብ ፎጣውን አቀበለችኝ። ቁርስ መጥቶልን
ስንበላ ወተትና ቡናውን እሷ ቀዳችልኝ፤ ዳቦውን እሷ ቀባችልኝ።
ልብሴን ስለብስ አገዘችኝ፡፡ አይኖቿ ሲያዩኝ፣ የለመድኩት ብርሀናቸው ውስጥ አይቼው የማላውቅ ልስልስ ያለ አስተያየት ሆነብኝ
ልንወጣ ስንል፣ ጉንጯን ይዤ ወደ ታች እያየኋት
«ዛሬ ምን ሆነሻል?» አልኳት
«ምን ሆኛለሁ?»
«ለኔ ያደረብሽ ፍቅር ያደገብሽ የሰፋብሽ ይመስላል። ያለ
ልማዳችን ትንከባከቢኛለሽ።»
«ዛሬ በጭራሽ እንዳትለየኝ አደራህን። እሺ?»
«ምነው? ምን ሆነሻል?»
ቀና ብላ እያየች፣ እጆቿን ወገቤ ላይ እያሳረፈች
«ምንም አልሆንኩም፡፡ በጣም ወድጄሀለሁ። ካይኔ እንድትርቅ
አልፈልግም።»
“ምነው? ምንድነው?»
“ምንም፡፡ ወደድኩህ፡፡ ዛሬ ገና ነው ሰው መሆንህ የገባኝ»
«ከዛሬ በፊትስ?»
“እስከዛሬ ሰው ሆነህ ታይተኸኝ አታውቅም፡፡ ስለትምህርት ግድ
ያለህ፣ ስለገንዘብ ግድ የለህ፣ ጓደኛ የለህ፣ አትፈራ፣ አትበሳጭ
ብቻ ምን ልበልህ፡ ስለምንም ግድ የለህም፡፡ «La vie tu t'en fouts
perdament» («ስለ ኑሮ በጭራሽ ደንታ የለህም») ሁሉንም ሰው፣ሁሉንም ነገር፣ ከላይ ሆነህ ወደታች ነው የምታየው:: ምንም ነገር ሊያምበረከክህ አይችልም፡፡ ብቸኛ ከመሆንህ የተነሳ፣ የብረት ሰው ሊያሸንፍህ አይችልም፣ ማንም ሰው እጅ ሊያስነሳህ፣ ሊያለማምጥህ፣ሊያንበረክህ አይችልም ብቸኛ ከመሆንክ የተነሳ የብረት ሰው ነህ ማለት እስከዛሬ እንዲህ ሆነህ ነበር የምትታየኝ።
እንደምመስልሽ የብረት ሰው አይደለሁም፡ ተራ ደካማ ሰው
ነኝ፡ ፊሪ ነኝ፡ ልላት ፈለግኩ። ግን ጊዜው የመናገር ጊዜ
አልነበረም፣ የማዳመጥ ጊዜ ነበር፡፡ ንግግሯን እንድትቀጥል፣
ከሆነላትም የልቧን
እንዲወጣላት፣ ለራሴም
ምን እንደሚሰማት ለማወቅ እንድችል
«ዛሬስ እንዴት ሆኜ ታየሁሽ?» አልኳት
ትላንት ሌሊት ስታቅፈኝ ሰው ሆንክ፡ ለመጀመርያ ጊዜ ሰው
«ራስህን ረሳህ:: እኔን አምነኸኝ፣ ከኔ ጋር በመሆንህ ራስህን
መጠበቅ ስላላስፈለገህ፣ ራስህን ረሳኸው፡፡ ራስህን እጄ ውስጥ
አስገባህ፡፡ ማለቴ በላዬ መሆን ትተህ፣ ወደታች መጥተህ ከኔ እኩል ሆንክ፡ ከዚያም አልፈህ የባሰውን ወርደህ እኔ ካንተ በላይ እንድሆን ፈቀድክልኝ አመንከኝ፡፡ በናንተ አገር ቋንቋ እወድሻለሁ አልከኝ ባማርኛ አወራሁልሽ?» አልኳት፡ በጭራሽ አልታወቀኝም ነበር አዎን። ሳታውቅ ነው።
እወድሻለሁ ማለቴን እንዴት እወቅሽ?»
በድምፅህ፡፡ እንደዚያ ወደኸኝ አታውቅም፡፡ በቋንቋህ ሲሆን
ጊዜ፣ ሳታውቅ መሆኑ ሲታየኝ ጊዜ፣ በጣም ሰው ሆነህ አገኘሁህ።
ለመጀመርያ ጊዜ ፣ ፈፅመህ የኔ ሆንክ፡፡ እስካሁን የማንም ሆነህ
ስለማታውቅ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የኔ ስለሆንክ፣ ሀሴት ተሰማኝ።
በልቤ የኔ ነው! የኔ ነው! የራሴ ነው!' አልኩ፡፡ ዛሬ ጧት ደሞ
ዛሬ ጧት ደሞ?»
ተኝተህ ሳይህ እንዴት ታምራለህ! እንዴት ወጣት ነህ!
እንዴት ንፁህ ነህ! ያ ፊትህን የሚሸፍነው ፂምህ ተላጭቶ፡ እነዚያ ሁሉን ወደታች የሚያዩት አይኖችህ ተከድነው፣ ያ ሁሉን የሚንቅ አንጎልህ ተኝቶ ሳይህ፣ ጀግናው ጦረኛ አኪሌስ የጦር ትጥቁን አውልቆ ያለ አንዳች መከላከያ ተኝቶ እንደማየት ነበር፣ በፍቅር አይን ለምታይህ ሲልቪ፡፡ እና ታድያ፣ ሳይህ፣ እርጅና እያረሳሳዐእንደሚወስድህ፣ ሞት አድፍጦ አንድ ቀን ጉብ እንደሚልብህ አፈጠጠብኝ

«አንተ ይህን ሁሉ ሳትጠረጥር፣ ቆንጆ ራስህን ትራሱ ላይ
አሳርፈህ፣ ንፁህ እንቅልፍህን ትለጥጣለህ፡፡ በጭራሽ መከላከያ የሌለሀ ሆነህ ታየኸኝ። አሳዘንከኝ፡፡ አዘንኩልህና እምባዬ መጣ፡፡» ራሷን ደረቴ ላይ አንተራሰች፡፡ ጭንቅላቷን አቅፍ አደረግኩት። እንደዚህ
ቆመን ረዥም ጊዜ ቆየን፡፡ በኋላ፣ በቀስታ ቀና አድርጌ ሳያት፣
እምባዋ ይወርዳል። እየተጠጋችኝ፣
«ዛሬ እንዳትለየኝ አለችኝ
እቅፍ አደረግኳት። ብዙ ነገር ልነግራት ፈለግኩ። ግን የመናገር
ጊዜ አልነበረም፡፡ እንደተቃቀፍን እንቅልፍ አቀፈን ..

💫ይቀጥላል💫
👍26
#ከሰሀራ_በታች


#ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም


ማንም ችኩል ቢለኝ ግድ አይሰጠኝም፡፡ ፋናን ገና ስመለከታት ልቤ ውስጥ የማይናወጥ የፍቅር ሐውልት ቆሟል፡፡ ማንም ብትሆን ግድ አይሰጠኝም፤ ቤት ውስጥ ምንሽር የታጠቀ፣ ጓንዴ ትራሱ ስር
ያስተኛ ባሏ ቢቀመጥ፣ ሰባት ልጆቿ “እማ እማ!” እያሉ የሚንጫጩ ሴት ብትሆንም ግድ የለኝም፡፡ፋናን አየኋት፣ ወደድኳት በቃ!! ይሄ ሁሉ ነገር የሆነው አንድ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ እና ይሄን ሁሉ ሴኮንድ፣ ዘላለም የሚያህል ደቂቃ ፋናን አይቼ ባፈቅራት “ቸኮልክ” የሚለኝ ማነው?!.


ቤተሰቦቼ በየወሩ የሚልኩልኝ ብር ከዚህ የተሻለ ቤት እንድከራይ የሚያስችለኝ ቢሆንም ፋና
የምትባል የእግር ብረት ተጠናውታኝ በየት በኩል ! ቤቱ ለአንድ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ምኑም
የሚመች አልነበረም፡፡ ከእኔ ክፍል ኋላ የታወቀ ጠላ ቤት ነበር፤ ጫጫታው፣ ሁካታው፣ ዘፈኑ፡
ፀቡ ሁሉ ይረብሸኛል ፡፡ በሳምንት ሦስት ቀን !!

የጠላ ቤቱ ጩኸት ጋብ ሲል ኳስ የሚጫወቱ ልጆች ይተካሉ፡፡ ግድግዳየን በኳስ ሲነርቱት
የቤቴ ምርጊት አፈሩ በለጠፍኩት የግድግዳ መሸፈኛ ወረቀት ስር እየተንኮሻኮሻ ሲፈርስ
ይሰማኛል፡፡ ይህን ሁሉ ስችለው ደግሞ የጠላ ቤቱ አሻሮ ሲታመስ ፣ የጠላ ቂጣው ሲጋራ አአአሻሮ አሻሮ የሚሸትት እንኩሮ እንኩሮ የሚተነፍግ ጭስ ጠባብ ክፍሌን ይሞላታል፡፡

ይህ ሁሉ ችግር ግን ቤቱን እንድጠላው አላደረገኝም፡፡ ፋናን ስመለከት ጫጫታው የፍቅር
ሙዚቃ፣ ጭሱ ፍቅርን የሚያጥን
የገነት ከርቤ እስኪመስለኝ ይስማማኛል፡፡

እዚህ ቤት ውስጥ ለስድስት ወራት ስኖር ከፍቅርተ ጋር ተግባባን፤ እማማ አመለ ጋር የእናትና የልጅ ያህል ተቀራረብን፤ ከፋና ጋር ግን ከሰላምታ ውጭ አንዲት ቃል ተለዋውጠን አናውቅም። ፋና እዛው ተቀምጣ አንድ ቤት እየኖርን ትናፍቀኛለች ፤ አትናገር አትጋገር ! ዝም፡፡ ፋና
ቤት ውስጥ አለች ማለት ማንም ቤት ውስጥ የለም እንደማለት ነው፤ ዝምታ ይነግሳል፡፡ የፋናን
ድምፅ አንዳንዴ ለአራት ለአምስት ቀናት አልሰማውም፤ እዛው እያለች፡፡ አይገርምም ? እኔም
በቤተሰቦቼ “እሱ አይናገር አይጋገር ዝም ነው!” እየተባልኩ እሞካሽ ነበር፡፡ ጉዳቸውን ባዩ !
እዚህ ሞት የሚያስንቅ ዝምታ የሰፈረባት ጋግርታም ጋር በፍቅር ወድቄ አንድ ቃል ሲናፍቀኝ፡፡

የፋና ዝምተኝነት የጤና አልመስል ብሎኝ ነበር፡፡ እንጀራ እየበሉ ወጥ ሲያልቅባት እንኳን ወጥ
ጨምሩልኝ አትልም፡፡ ደግነቱ እናቷ እማማ አመለ ዓይናቸው ከፋና ላይ ስለማይነቀል ገና ወጡ
ሲያልቅባት በላይ በላዩ ይጨምሩላታል፡፡ ፋና በቀን ውስጥ የምትናገራቸው ቃላት ሲደመሩ
እህቷ ፍቅርተ በግማሽ ደቂቃ ከምታዘንበው ንግግር እሚበልጡ አይመስለኝም፡፡ ፍቅርተ ሙሉ
ቀን ስታወራ፣ ስትስቅ፣ ስትጫወት ነው የምትውለው፡፡ አንዳንዴ ፈገግታ የሚያጭርብኝ ነገር
ፋናና ፍቅርተ ሲያወሩ መስማት ነበር፡፡ ፍቅርተ ብቻዋን የምታወራ ነው የምትመስለው።ፋና አንድ ቃል አትመልስም፤ ፍቅርተም ብትሆን የእህቷን አመል ያወቀች ይመስል መልስ አትጠብቅም፤ ዝም ብላ ታወራለች ::

የፍቅርተን ወሬ መስማት አይሰለችም፡፡ እንደው ፍቅርተን መልኳን ሳይመለከት ድምጿን ብቻ
ያደመጠ ሰው በዓለም አንደኛዋ ቆንጆ ሴት እየተናገረች ሊመስለው ይችላል፡፡ በተለይ ሳቋ ! የፍቅርተ ውበት ግን ድምጿ ብቻ ነው:: “ስምን መልአክ ያወጣዋል” የሚባለው ብሂል እውነት
ከሆነ የፍቅርተን ስም ያወጣው መልዓክ ድምጿን ብቻ በሆነ መንገድ አድምጦ “ፍቅርተ” ብሎ
ሳይሰይማት አልቀረም፡፡

እማማ አመለወርቅ ብርቱ እናት ነበሩ፡፡ ሁለቱን ሴት ልጆቻቸውን ያሳደጉት ካለ አባት ነው፡፡
ዛፍ ቆራጭ የነበሩ ባለቤታቸው አንድ ቀን ዛፍ ሲቆርጡ የዛፉ ቅርንጫፍ የተላጠ ኤሌክትሪክ
መስመር ጋር የተነካካ ሆኖ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው አለፈ፡፡ ያኔ ፋና የሶስት፣ ፍቅርተ
የሁለት ዓመት ሕፃናት ነበሩ፡፡ እነዚህን ሁለት ልጆች ለማሳደግ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡
ያለፉበትን አሰቃቂ የድህነት መንገድ ተመልሰው ሲያስቡት ያንገሸግሻቸዋል፡፡ ታዲያ ከተቀራረብንና እኔም ከቤተሰቡ አባል እንደ አንድ ተቆጥሬ ገመናቸውን ተካፋይ ስሆን ማታ ማታ ቡና ተፈልቶ ታሪካቸውን ያወሩልኝ ነበር፡፡ እማማ አመለ ወሬ ይችላሉ፤ አሁን በሐዘን ዐይናችንን በእንባ ሞልተውት ድንገት ጣል በሚያደርጉት ቀልድ ለሐዘን የኳተረ እንባችን በሳቅ ይፈሳል፡፡

የማታ ቡና አብሬያቸው መጠጣት የጀመርኩበት ቀን ትዝ ይለኛል፡፡ በፊት ቡና ሲያፈሉ ፍቅርተ
መጋረጃዬን ገለጥ አድርጋ አንድ ስኒ ታቀብለኝና እጠጣለሁ፤ እጣኑም ቢሆን እየተጥመለመለ
መጋረጃዬን አልፎ ክፍሌ ይደርሳል ፡
“አብዬ” ይሉኛል እማማ አመለ ሲጠሩኝ እንዲህ ነው፤
“አቤት ማዘር !”
"ሁለተኛ ትጠጣለህ?”
“አይ ይበቃኛል ማዘር” እላለሁ፡፡ እየፈራሁ እንጂ ብጠጣ ደስ ይለኝ ነበር፡፡
አንድ ቀን ታዲያ ቡናው ተፈልቶ፣ እጣኑ ቤቱን ሞልቶት፣ እኔም ነቃ ብዬ ፍቅርተ መጋረጃዬን
ገለጥ አድርጋ ቡናዬን እስክታቀብለኝ ስጠብቅ እማማ አመለ ጠሩኝ፡፡
“አብዬ !”
“አቤት ማዘር”
“እንደው ከሰውም አልተፈጠርክ ? ምናለ ወዲህ ወጣ ብለህ ብትጫወት፣…ጀበናውንም እያየህ ቡና ብትጠጣ፣ እኔም እናትህ ነኝ፣ እነፍቅርዬም እህቶችህ ናቸው” አሉኝ፡፡ ይሄ የመለአክት ጥሪ ነው !
ልብሴን ቀየርኩ፤ (ምርጥ የምላትን ልብስ ነው የለበስኩት፣ ከዚህች እዚች የመጋረጃ ድንበር ለማለፍ
ሽክ!!)፡፡ እናም መጋረጃዬን ገለጥ አድርጌ ብቅ አልኩ፤ ሁሉም በአክብሮት ተቀበሉኝ፡፡ የተዘጋጀችልኝ ኩርሲ ላይ ተቀመጥኩ ፡፡ እዩት እንግዲህ እግዜር ጨዋታውን ሲያሳምረው! ፋና ፊት ለፊቴ ነው የተቀመጠችው፡፡ ከዚህ በፊት ፊት ለፊቴ ተቀምጦ የሚያውቅ ውብ ነገር ምን ነበር?…ምንም !!

በእኔና በፋና መሃል የሲኒ ረከቦት፣ ሲኒዎቹ ስድስት ጨረቃ መስለው፣ ከረከቦቱ ጎን ማጨሻው
እንደ ደመና በቀስታ ሽቅብ ወደ ጠቆረው ጣራ፣ ከሚሳብ የእጣን ጭሱ ጋር፡፡ ከስሱ የእጣን
መጋረጃ ባሻገር ፋና አንገቷን ደፍታ መሬት መሬት እየተመለከተች ተቀምጣለች፡፡ አዲስ ሰው
ስለተቀላቀልኩ ጨንቋታል፡፡ አቤት እንዲህ ፊቷ ተቀምጠው በእጣኑ ጭስ ውስጥ ሲመለከቷት
“ምነው ባልነቃሁ” በሚባልበት እንቅልፍ ውስጥ የተከሰተች ጣፋጭ ህልም ነው የምትመስለው ፋና የኔ ውብ፡፡

ድህነትን አፈር ድሜ ያስጋጠ ውበት በዚህ ጭርንቁስ ቤት ውስጥ ፊት ለፊቴ በእጣን ደመና
ተከብቦ ተቀምጧል፤ እኔም ከእግር ጥፍር እስከራስ ፀጉር በሚነዝር በሚያስረቀርቅ ደስታ
ውስጥ ህያውና ዘላለማዊ ሥዕል ላደርጋት እያጠናኋት ነው ፡፡ነፍሱ በፍቅር ፍላፃ እንደተወጋች
አይደለም የሚያሳምረው፤ የተፈቃሪውን ነፍስ ይመለከታል፤ ነገን ይመለከታል፤ በዝምታ ውስጥ ያለ ሰላምን የሚቃኙ ዐይኖች ይታደላል፡፡ ከተከዘ ፊት ፈገግታን ያወጣል፡፡ እውነትን በዓይነ ህሊናው ይቃኛል! አፍቃሪ ሠዓሊ ነው!

ከዛን ቀን ጀምሮ ፋና ጋር በእጣን ጭስ መሃል መተያየት የዘወትር ተግባራችን ነበር፡፡ የእማማ
አመለ ጣፋጭ ወግ፣ የፍቅርተ የማያባራ ሳቅና ጨዋታ፣ የፋና የማይገሰስ ዝምታና የዝምታዋ
ውበት፣ የውበቷ ግዝፈት እንደ መንፊስ በቤቱ ውስጥ ያረብብ ነበር፡፡ ያችን የድህነት ጎጆ ሙሉ
ያደረገ መልካም ቤተሰባዊ ፍቅራችን ለአራት አመታት አብሮን ኑሯል፡፡
👍274🥰4👎1
ድህነት ክፉ ነው፡፡ ድህነት ምኑም አያኮራም፤ ድህነት ያስጠላኛል፡፡ አንድ ቀን ትንሽ ራሴን
ስላመመኝ በጊዜ ወደቤት ተመለስኩ፤ ማንም አልነበረም፤ የት እንደሄዱ እኔንጃ፡፡ ወደ ክፍሌ
ገብቼ ፍራሽ ላይ በደረቴ ተደፍቼ ተኛሁ፡፡ ብዙ ሳልቆይ ፍቅርተ ከውጭ አየተጣደፈች ገባች፤
መኖሬን አላወቀችም፡፡ እኔም ካለወትሮዬ ዝም ብዬ በመጋረጃው አሻግሬ እመለከታታለሁ፡፡ አለ አይደል አንዳንዴ መናገር የሚታከትብን ጊዜ…

ፍቅርተ የሆነ ቦታ ልትሄድ በጥድፊያ ላይ እንደሆነች ታስታውቃለች፡፡ ከአሮጌው አልጋ ስር ዚፑ የተበላሸ አንድ የልብስ ማስቀመጫ ሻንጣ ጎትታ አወጣች፡፡ ይህ ሻንጣ የቤተሰቡ ብቸኛ የልብስ ማስቀመጫ ነበር፡፡ ከፈተችውና ልብስ መምረጥ ጀመረች፤ ትእይንቱ አሳዛኝ ነበር፡፡
አንዱን ታነሳና በሁለት እጆቿ ራቅ አድርጋ ይዛ እያገላበጠች ትመለከተዋለች፣ አልጋው ላይ
ትጥላለች፤ ሌላውን ታነሳለች ትጥላለች፡፡ የእማማ አመለ የክት ቀሚስና ነጠላ፣ የፋና አንድ
ሁለት ተራ ቀሚሶች እናም የፍቅርተ በርካታ ነጫጭ ቲሸርቶች…ሻንጣው ውስጥ የነበረው ልብስ በሙሉ አለቀ፡፡ ፍቅርተ ልትሄድ ላሰበችበት ቦታ የሚመጥን አንድም የረባ ልብስ
አላገኘችም፡፡ በረዥሙ ተነፈሰችና በአንድ እጁ ወገቧን ይዛ በሌላ እጁ ጠጉሯን እያከከች ግራ
ተጋብታ ለብዙ ደቂቃዎች በትካዜ ቆመች፡፡ ከዛም በቁጣ ልብሱን ከአልጋው ላይ ገፍቶ ወደ
ሻንጣው ወረወረችውና ሻንጣውን ዘግታ በእርግጫ ወደ አልጋው ስር ገፋችው፡፡ በዚህች ቅፅበት ጓደኞቿ ከውጭ ጠሯት፤

“…ፍቅር ቶሎ በይ እንጂ…ረፈደ
እኮ!”

እናንተ ሂዱ ኤልሲ ! ሌላ ቀጠሮ አለኝ ረስቼው ነበር” አለቻቸው፤ ጓደኞቿ ሄዱ፡፡ ፍቅርተ
አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች፡፡

“ኤጭ! ወይ መልክ የለኝ፣ ወይ ደህና ቤተሰብ የለኝ፣ ሰው ጋር መቀላቀያ እንኳን አንዲት ልብስ
ያጣል ሰው ?…አንዲት ልብስ..እግዚአብሄር አሁንስ ብትገለኝ ምናለበት ! በስንት ነገር ከሰው በታች ታደርገኛለህ?” አለች በምሬት፡፡ አልቅሳ ሲወጣላት እንባዋን ጠራርጋ አንዲት ትንሽ
መስተዋት ወደተሰቀለችበት ጥግ ሄደችና መስተዋቷን አውርዳ አንዴ ከንፈሯን ሰብሰብ አንዴ
ለቀቅ እያደረገች መልኳን ስትመለከት ቆየችና መስተዋቱን ወደ ቦታው እየመለሰች “አስቀያሚ”
ብላ በምሬት ተናገረች፡፡ ማታ የተለመደው ቡናችን ላይ ግን ፍቅርተ በሳቅ ስትፍለቀለቅና
ምንም ነገር ያልተሰማት ልጅ መስላ አመሸች፡፡ “ሳቅ የደስታ ምልክት ነው” የሚሉ የዋሆችን
ታዘብኳቸው፡፡

ከዛን ቀን ጀምሮ የፍቅርተን ልብሶች ማስተዋል ጀመርኩ፡፡ የፍቅርተ የሚበዙት ልብሶቿ ነጫጭ ቲሸርቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ ቲሸርቶች ከተለያዩ ድርጅቶች በነፃ የሚታደሉ የተለያዩ መፈክሮች
ደረታቸው እና ጀርባቸው ላይ በተለያዩ ቀለማት የታተሙባቸው ሲሆኑ ብዙዎቹ ለአንድ በዓል
ወይም ለሆነ ቀን መታሰቢያነት የተዘጋጁ ናቸው፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ፍቅርተ ልብስ አጥባ
ቲሸርቶቹ የተሰጡበት ቆሜ ስመለከት ገረመኝ፡፡ የፍቅርተ ቲሸርቶች ታጥበው ሲሰጡ የኢትዮጵያ ችግሮች በሙሉ ታጥበው የተሰጡ ነበር የሚመስሉት፡፡

“የእናቶች እና ህፃናት ሞት ይቁም” በቀይ ቀለም ደረቱ ላይ የተፃፈበት ቲሸርት፤

“ከ ኤች አይ ቪ ኤድስ ራሳችንን እና ቤተሰባችንን እንጠብቅ” በሰማያዊ፤

“ፖሊዮን ከኢትዮጵያ እናጠፋለን” በጥቁር፤

“መስኮት በመክፈት የቲቢ በሽታን እንከላከል” በቀይ፤

“ችግኝ በመትከል አካባቢያችንን ውብና ፅዱ እናድርግ” በአረንጓዴ፤

ከነጫጮቹ ቲሸርቶቹ ለየት ያሉት ደማቅ ቀይና ቢጫ ቲሸርቶች ደግሞ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ
አርማ የታተመባቸው ነበሩ፡፡ ፍቅርተ ብትበሳጭ እውነት አላት፡፡የዘመኗን ወጣቶች፣ የአዲስ
አበባን ቆነጃጅት በእነዚህ ቲሸርቶች መወዳደር ዘበት ነው፡፡ እያንዳንዷ ወጣት ሴት ውስጥ
እድሜ የሚያመጣው የቁንጅና ውድድር አለ፡፡ መልክ ያለው በመልኩ፣ የሌለው በዘመናዊና
ውብ ልብሶች ውድድሩ ውስጥ አለበት፡፡ በዚህ የታይታ ዘመን ግባቸው መታየት የሆነ እልፍ
አእላፍ ወጣቶች የማይታዩ መስዋዕትነቶችን የሚከፍሉት ወደው አይደለም፤ መታየት መኖርን ማረጋገጫ አንድ ምስክርነት ስለሆነባቸው እንጂ፡፡ እናም ለመታየት፣ ዕይታ ውስጥ የሚገባ አልባሳት አንዱ መስፈርት ነው፡፡ በዚህ ውድድር ላለመውደቅ የከፋ አዘቅት ውስጥ የሚወድቁትንም ቤት ይቁጠራቸው፡፡....

ይቀጥላል
👍157🥰1
አትሮኖስ pinned «#ከሰሀራ_በታች ፡ ፡ #ሁለት ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ማንም ችኩል ቢለኝ ግድ አይሰጠኝም፡፡ ፋናን ገና ስመለከታት ልቤ ውስጥ የማይናወጥ የፍቅር ሐውልት ቆሟል፡፡ ማንም ብትሆን ግድ አይሰጠኝም፤ ቤት ውስጥ ምንሽር የታጠቀ፣ ጓንዴ ትራሱ ስር ያስተኛ ባሏ ቢቀመጥ፣ ሰባት ልጆቿ “እማ እማ!” እያሉ የሚንጫጩ ሴት ብትሆንም ግድ የለኝም፡፡ፋናን አየኋት፣ ወደድኳት በቃ!! ይሄ ሁሉ ነገር የሆነው አንድ…»
#ከሰሀራ_በታች


#ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም

....ፋና ጋር መቀራረብ በጣም ከባድ ነበረ፡፡ አንዳንዴ ባህሪዋ ያበሳጨኛል፡፡ “ምናይነት የደነዘዘች ልጅ ናት” እልና ለራሴ ቁጣ ቁጣ ይለኛል፡፡ ለምን እንደ ፍቅርተ አታናግረኝም ? ሌላው ቢቀር አንድ ዓመት ሙሉ እዚህ ቤት ስኖር ቤቴን እንኳን ተሳስታ ረግጣው አታውቅም፡፡ ፍቅርተ እኮ
እናት ማለት ናት፡፡ ረፍዶብኝ ፍራሼን ሳላነጣጥፍ ከወጣሁ ፍራሼን አነጣጥፋ፣ ያዝረከረኩትን
ወረቀት አስተካክላ የሚጠጣ ውሃ ቀድታ አስቀምጣልኝ ነው የማገኘው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
ደግሞ ምግቤንም የምትሰራልኝ ፍቅርተ ናት፡፡ እች ፋና የሚሏት ዝግ ግን…ዝምታዋ ሰልችቶኝ
ነበር፡፡

የሆነ ጊዜ ታዲያ ድንገት ታመምኩ፡፡ ለሳምንት ትምህርት ቤት አልሄድኩም፤ ፍቅርተና እማማ
አመለ ተጨንቀው ሲሯሯጡ ሰነበቱ፡፡ ፋና ዝርም ብላ አታውቅም፡፡ ከዛን ጊዜ በኋላ የፉና ነገር በቃኝ፡፡ “እግዜር ይግደልህ !” ማንን ገደለ? አንድ ቀን ሳትጠይቀኝ በቃ ድኜ ተነሳሁ፡፡
ፋና የምትባል ልጅ በቃ በቃችኝ፡፡ ሳልፍ ሳገድም እወረውርላት የነበረውን ሰላምታዬን እኔም
አቆምኩ፡፡ ስገባ ብቻዋን ተቀምጣ ባገኛት እንኳን ሰላም አልላትም፡፡ እንደውም ከብስጭቴ
ብዛት ቤት ለመቀየር አሰብኩ፡፡ ግን ለእማማ አመለ ምን ሰበብ እንደማቀርብ ጨነቀኝ፡፡ ከእኔ
ከሚያገኟት የኪራይ ብር በላይ ለእኔ ያላቸው ቤተሰባዊ ፍቅር ቦታ አለው፤ ለእርሳቸው::ደግሞም ብቸኛ መተዳደሪያቸው ከእኔ የሚያገኟት የኪራይ ብር ነበረች፡፡ ምን ሆንኩ ብዬ ቤት ልውጣአ ? እች ጉልት ስወጣ ስገባ እንደ ግኡዝ ነገር ተጎልታ ማየቴ ያበሳጨኛል፡፡ ማታ ማታ ቡና ሲጠሩኝ በህመሜ አሳብቤ ልቀር ብሞክርም አልተሳካም፡፡
“ቡና ባትጠጣ እንኳን ና እና ተጫወት፤ በሽታውም ለብቻ ሲሆኑ ነው የሚጠናው” አሉኝ
እማማ አመለ፡፡ ጨዋታው እንደወትሮው አልጥምህ አለኝ፤ እጣኑ ከነከነኝ፤ ከእጣኑ ወዲያ
አቀርቅራ የምትቀመጠው ፋና ሰለቸችኝ፡፡ እወዳታለሁ፤ ግን ግኡዝ ናት በቃ ! ወይስ ከራሷ
ውበት ጋር በፍቅር ወድቃ ዓለምን ረስታለች ? ምናይነት ድንዛዜ ነው ይሄ ?
!
ፍቅርተ ጋር ቅርርባችን ተጠናክሮ ነበር፡፡ ማታ ማታ ቡናው እስከሚፈላ ደብተሯን ይዛ
ወደ ክፍሌ ትመጣለች፡፡ ግን አታጠናም፤ ቤታቸው ውስጥ ቴፕ ስለሌለ ሁልጊዜ የደብተሯ
ቦርሳ ውስጥ የምታኖረውን የአስቴርን ካሴት ይዛ ትመጣና በእኔ ቴፕ ታዳምጣለች፡፡ ግጥሙን
ሸምድዳዋለች፤ ጀምሮ እስኪጨርስ በቃሏ ትወጣዋለች፡፡ ሙዚቃውን እንደ ሙዚቃ ሳይሆን
እንደ መርዶ ነበር ፊቷን አጨፍግጋ የምታዳምጠው፡፡ አንድ ቀን ሙዚቃውን እያዳመጠች
እንባዋ በጉንጫ ላይ ኮለል ብሎ ወረደ፤

“ምን ሆንሽ ፍቅርተ” አልኳት ደንግጬ፤

“ምንም” ብላ ተነስታ ከክፍሌ ወጣች፡፡ከዛን ቀን ጀምሮ ፍቅርተ የወትሮዋ አልነበረችም፤ የሌላትን
አመል መነጫነጭ ጀመረች፡፡ ከመሬት ተነስታ ታለቅሳለች፤ በትንሽ ነገር ይከፋታል፡፡ ከወራት
ልመና በኋላ ጭንቋን ተነፈሰችው፤ ፍቅርተ ፍቅር ይዟት ነበር፡፡ ፍቅር እንደያዛት ስትነግረኝ
“እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፣ የነገስታት ንጉስ፣ የዓለም ሁሉ ፈጣሪ ኃያል! እባክህ ይህች ልጅ
ፍቅር የያዛት ከእኔ እንዳይሆን እርዳኝ” ብዬ ፀለይኩ፡፡

“ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ አብረን አንድ ክፍል ነው የተማርነው፤ ቶማስ ይባላል” ስትለኝ ሃሌሉያ!”
ብዬ ልጮኽ ቃጥቶኝ ነበር፡፡ ኡፍፍፍፍፍፍ ! አሁን እዳው ገብስ ነው ! ተረጋግቼ አዳምጣት
ጀመር፡፡ የከፍሎቿ ልጆች ተሰባስበው የተነሱትን አንድ ፎቶ እየሰጠችኝ ልጁን ጠቆመችኝ፤
ሲበዛ ቆንጆ ልጅ ነበር፡፡ ከግራና ቀኙ ሁለት ቆነጃጅት እንደ መዥገር ተጣብቀውበታል፡፡

“አንቺ የታለሽ ታዲያ!” አልኳት፤

“እኔ ፎቶ መነሳት አልወድም” አለችኝ ትክዝ ብላ፡፡ ለምን ብዬ አልጠየቅኳትም፡፡

“ከወደድሽው ስንት ጊዜ ሆነሽ?” አልኳት ፎቶውን እያየሁ፤
“እኔንጃ ግን ቆይቷል ፤ ሶስት አመት”
“እና ሦሰት ዓመት ሙሉ ስታፈቅሪው እርሱ ምን አለ ?”
“አያውቅም፡፡”
“ተነጋግራችሁ አታውቁም”
“አንድ ቀን አናግሮኛል…”
“እና ምን አለሽ?” አልኳት በጉጉት፡፡
“እርሳስ አጥቼ ስጠይቅ ሰጠኝ…ስመልስለት 'ውሰጂው! አለኝ” አለችና እዛኛው ክፍል ሄዳ አንድ
ቢጫ እርሳስ ይዛ ተመለሰች፡፡ እንደ ትልቅ ቅርስ በፍቅር እርሳሱን እየተመለከተች…፣ “አየኸው
የእሱ ነው” አለችኝ፡፡ ፊቷ ላይ የነበረው ደስታ… ናፍቆት…ፍቅር ያሳዝን ነበር፡፡ ትቀጥላለች
ብዬ ጠበቅኳት፡፡ የተነጋገሩት ግን እችኑ ነበር፡፡ አንድ ቃል “ውሰጅው” አላት፤ በቃ፡፡ ይሄ ቃል ለፍቅርተ “ንግግር” ነበር፡፡

“ለምን አታናግሪውም ታዲያ ? በቀጥታ መናገር እንኳን ባትችይ በሆነ መንገድ እንደወደድሽው
አሳውቂው፡፡ እሱም ሊወድሽ ይችላል” አልኳት እንደው ለማፅናናት እንጂ ያልኩትን ለራሴም አላመንኩበትም፡፡ ይሄ ልጅ ፍቅርተን ቢወዳት በሺ ዓመት አንድ ጊዜ የሚከሰት አጋጣሚ
አድርጌ ላየው ሁሉ እችላለሁ፡፡

በድንጋጤ አፍጥጣ እያየችኝ፣ “ትቀልዳለህ ?” አለችኝና አፏን በሁለት እጆቿ አፍና እንደዘገነነው
ሰው ሰውነቷ ተንዘረዘረ፤

“በጣም የሃብታም ልጅ ነው፤ በዛ ላይ ክላሳችን ውስጥ ካሉ ሰላሳ ሴቶች ግማሹ በሱ ፍቅር ያበዱ
ናቸው፡፡ በእረፍት ሰዓት ጎታቹ ብዙ ነው፤ በዚያ ላይ ጎበዝ ተማሪ፤ ኤጭ” ብላ በምሬት ፊቷ
አጨፈገገች፡፡ ዝም ብዬ አየኋት፤ ፍቅርተ ይበልጥ በቀረቧት ቁጥር ይበልጥ መልከጥፉ የምትሆን
ሚስኪን ነበረች፡፡ በቦዙ አይኖቿ ባዶውን እየተመለከተች ምሬቷን አምበለበለችው፡፡ የሆነ ነገር
ያስፈልግሃል፡ ለመፈቀር አንድ የሆነ ነገር ያስፈልግሃል፣ መልክ ወይም ሃብት…ብቻ የሆነ ነገር
እኔ ደግሞ ምንም የለኝም፤ መልክ የለኝ፣ ሃብት የለኝ፣ በትምህርት እንኳን እንዳላካክሰው እንደ ትምህርት የሚያስጠላኝ ነገር የለም እማማ እንዳይከፋት ነው የምማረው ቸኮኛል ከቤት
ባልወጣ ደስታዬ ነው፡ ማንንም ባላይ፡ ማንም ሳያየኝ ደስታዬ ነው አለችና እንባዋ ይፈስ ጀመር

“ፍቅርተ ለፍቅር ሃብት ፣ መልከ ምናምን ሲያስፈልግ ኖሮ እኮ አታፈቅሪም ነበር” አልኳት፡፡

ከአፌ ነጥቃ በቁጣ መናገር ጀመረች፡፡ንግግሯ በምሬት የተሞላ ነበር፡፡ “እንኳን ለፍቅር ለተራ
ሰላምታም ሀብት ያስፈልጋል ፡፡መልክ ያስፈልጋል ፡፡ አንተ አስቀያሚ ወጣት ሆነህ ታውቃለህ ? አስቀያሚ ሴት ሆነህስ ታውቃለህ ? ህመሙ አይገባህም፡፡አብርሽ መገፋቱ ስሜት አይሰጥህም….እየውልህ እንኳን አሁን ሕፃን ሆነን እኔና ፋና መንገድ ላይ ስንሄድ ያገኘን ሁሉ ፋናን አገላብጦ ጉንጯን ይስምና እኔን…” መጨረስ አልቻለችም እንባዋ ቀደማት፡፡

“አስራ ስምንት ዓመት አልፎኛል፡፡ እስካሁን አንድ ወንድ እንኳን ጠይቆኝ አያውቅም፡፡አንዳንዴ እንዴት እንደተፋቀሩ ይቅርና ያፈቀሩት ጋር እንዴት እንደተጣሉ ሴቶች ሲያወሩ እቀናለሁ..ከፍቅረኛ ጋር መጣላት በራሱ ያስቀናል፤ ይናፍቅሃል፤ ሰው ሆነህ በፍቅር መጋጨትህ ለራሱ ከሰው እኩል ያደርግሃል፡፡ የሚጣላህም የሚወድህም በሌለበት ዓለም መኖር ካለመኖር እኩል ነው” ፍቅርተ ባንዴ ተቀየረችብኝ፤ አስፈሪ ሆነችብኝ፡፡ ንፍጧ በአፍንጫዋ ተዝረከረከ፤
እንባዋ ፊቷን አጨቀየው፤ አስቀያሚነቷ ሙሉ ሆነ፡፡ ስታሳዝን!

“አስራ ስምንት ዓመት እኮ ትንሽ እድሜ ነው…ገና ነሽ ወደፊት የሚያፈቅርሽ የራስሽ ሰው
ይመጣል” አልኳት ልክ የሚያፈቅራትን ሰው የቀጠርኩት ይመስል በእርግጠኝነት፡፡ ግን ውስጤ መቼም ቢሆን ፍቅርተን የሚያፈቅር ሰው በምድር ላይ የሚፈጠር አይመስለውም፤ እናገራለሁ፤ግን የምለውን እኔም አላምንበትም፡፡
👍28