በዚያ ቀን፣ ልክ የዛሬ 82 ዓመት፣ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በተካሄደው ጭፍጨፋ አዲስ አበባና አካባቢዋ ውስጥ ብቻ ወደ 30 ሺህ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። የየካቲት 12 ሰማዕታት ቀን፣ ዘንድሮ 82ኛ ዓመቱ ላይ ነው። የካቲት 1929 ዓ.ም.የሚያክል ለኢትዮጵያ የመከራና የጽልመት ወራት ኖሮ አያውቁም። በጣም የሚገርመው፣ በዚሁ በወርኃ የካቲት 1888 ዓመተ ምህረትም ከሰባ ሺህ በላይ ወገኖቻችንን መሥዋዕት አድርገናል። ግፈኛው የንጉሥ ኡምቤርቶ ጦር፣ በጄኔራል ባራቴሪ እየተመራ ሃይማኖት ሊቀለብስ፣ መሬት ሊቆርስ፣ ነፃነታችንን ሊገስ መጥቶ ማጭድና ጎራዴ፣ ጦርና ጋሻ የያዙትን በመድፍና በዘመኑ መሳሪያዎች ፈጃቸው።
ከአርባ አንድ ዓመታት በኋላ ተመልሶ ለወረራ የመጣው በማርሻል ሩዶልፍ ግራዚያኒ የሚመራው የፋሺስትም ጦር፣ ከየካቲት 12 ቀን እስከ የካቲት 14 ድረስ ባሉት ሦስት ቀናት ከሠላሳ ሺህ በላይ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያንን ገደላቸው።
#የመታሰቢያ #ሐውልታቸው
ሀውልቱ የወራሪው የጣሊያን ወታደሮች በግፍ የጨፈጨፏቸውን 30ሺ ያህል ሰዎች ለመዘከር የቆመ ነው፡፡ ግራዚያኒ ሰራዊቱን እና መኳንንቱን ጠርቶ ፣ ህዝቡን ሰብስቦ የአሁኑ አዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ ቀደም ሲል ገነተ ልዑል በሚል ይታወቅ በነበረው በአፄ ኃይለስላሴ ቤተ መንግስት ውስጥ የተለመደ የእብሪት ንግግሩን በማሰማት ላይ ነበር፡፡ ግራዚያኒን ለመግደል አመቺ ቦታ እና ጊዜ ሲጠባበቁ የነበሩት አብርሐም ደቦጭ እና ሞገስ አሰግዶም የያዙትን ቦምብ አከታትለው ወረወሩበት፤ ግራዚያኒም ቆሰለ፡፡ ከዚያች ቅፅበት በኋላ በማንኛውም ሁኔታ የተገኘ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በግፍ ተጨፈጨፈ፡፡ አዲሰ አበባም በንፁሀን የደም ጎርፍ ተጥለቀለቀች፡፡ በህፃናት ለቅሶ በእናቶች ዋይታ ተዋጠች፡፡ በወቅቱ የተፈጠረው ሁኔታም ኢትዮጵያውያን በድፍረት እና በወኔ ጠላትን እንዲፋለሙ ብርታት ሆናቸው፡፡ እነዚህን ያለርህራሄ የተጨፈጨፉ ንፁሀን ዜጎች ለማሰታወስም ዛሬ በየካቲት 12 ሆስፒታል ፣ በአዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ እና በቀድሞዉ በአንበሳ ግቢ መካከል 6ኪሎ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የሰማዕታቱ ሃውልት ቆሟል፡፡
በዚህ ሀውልት ቀረፃ ላይ ኢትዮጳያውያን ባለሙያዎችም ተሳትፈዋል፡፡ ሀውልቱ 28 ሜትር ቁመት ያለው ሲሆን ባለ ሶስት ማዕዘንም ነው፡፡ ሀውልቱ የተሰራው በሁለት የዩጎዝላቪያ ዜግነት ያላቸው ባለሙያተኞች ሲሆን በሀውልቱ ላይ ኢትዮጵያውያን በጣሊያን ወታደሮች በግፍ ሲገደሉ የሚያሳዩ ቅርፃ ቅርፆችም ይስተዋላሉ፡፡ ሀውልቱ ከቅርፃ ቅርፆቹ ባሻገር የተለያዩ ፅሁፎችም አሉት፡፡
እባክዎን ካለዎት ጊዜ ላይ ደቂቃዎች ወስደው ይህን ፒቲሽን በመፈረም ለየካቲት 12/1929 ዓ.ም ጭፍጨፋ ሰማእታት ያሎትን አጋርነት ያሳዩ።
ቫቲካንና የጣሊያን መንግስተም ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠይቅና ተገቢውን ካሳ እንዲከፍሉ ያድርጉ።
100,000 ፊርማ ነዉ የሚያስፈልገዉ ግን እስካሁን 6558 ብቻ ነው ማግኘት የተቻለው የሁላችንም ጉዳይ ነው ትንሽ ደቂቃ ወስደን እንፈርም
https://www.gopetition.com/petitions/vatican-apology-for-ethiopian-holocaust.html
#ክብር #ለተሰውት #ሰማዕታት……..!!!

GoPetition
Ethiopian Genocide 1935-1941 and Vatican Complicities
We, the undersigned, appeal to the international community...all Governments, the United Nations, the European Union,…
👍1
#የጀርባ #ነገር
አንድ ጊዜ የመንደራችን ልጅ በምግብ ዝግጅት ተመርቃ እራት ግብዣ ጠራችን .... ሴቱ ሁሉ እራሱን እስኪስት ዘንጦ ይገባል....(ያው ሴቶች ሰንበቴም ቢጠሩ የእራት ልብስ መልበስ ይወዱ የለ) !
ያልተለበሰ አይነት ልብስ የለም የሚበዛው የተራቆተ ነው ! አጭር ቀሚስ ጫፉ መሬትን እንደመንግስተ ሰማየት የናፈቀ ........ደረቱ ተከፍቶ ከግራና ከቀኝ በጡት ማስያዣ አነሳሽነት ደረት ላይ ለአመፅ የተሰበሰበ ጡት .... ከተመልካች አይን ጋር በእትብት የተያያዘ ይመሰል መሸፈን የጠላ እንብርት ..... ብቻ እራት ተባልን እንጅ የተራቆተ ጅስም እነድናይ የተጠራን ነበር የሚመስለው (ለፍትፍት ተጠርተን ፊት ስናይ አመሸን ቢባል ....ሂሂሂ)
አጠገቤ የተቀመጡት ሰውየ ታዲያ መነፅራቸውን እያስተካከሉ አላፊ አግዳሚወቹን እንደፔንዱለም አንገታቸው እስኪቀጭ እየተወዛወዙ ሲያዮ የሜዳ ቴንስ የሚያዩ ይመስሉ ነበር ...
አንዷ በገባች ቁጥር ‹‹በስማም...እንደው እግዜርን ባትፈራ ብርድ አትፈራም ›› ይላሉ
ትንሽ ቆይተው ደግሞ ሌላኛዋን ያዩና‹‹ ትፍ አሁን ይሄ ተገቢ ነው ...እንደፈጠራት እርቃኗን .....›› ይላሉ ግን ምራቃቸውን ሲውጡ በጉሮሯቸው ላይ እንቅርታቸው ሲያወጣና ሲወርድ በግልፅ ይታይ ነበር
በመጨረሻ የሚያምር ረዥም የእራት ቀሚስ የለበሰች ልጅ ገባች.... ሰውየው ደስ አላቸው እስከአንገቷ የሚደርሰው ቀሚስ ከእጆቿ በቀር ሙሉ ነበር .....እንደውም ባለተረከዝ ጫማ ባታደርግ ቀሚሷ መሬት ይነካ ነበር
‹‹ ተባረኪ! እንዲህ ነው ባህላችን ወጋችን ጨዋ ያሳደጋት...እግዜር ለቁም ነገር ያብቃሽ ››.....እያሉ ማሞገሳቸውን ሳይጨርሱ ልጅቱ እኛ በተቀመጥንበት አለፈች .......ሰውየው ድንገት ሙገሳቸውን አቁመው ‹‹ በስመ አብ›› አሉ ከኋላዋ እያፈጠጡባት .... የልጅቱ ጀርባ ከመቀመጫዋ ከፍ ብሎ ጀምሮ ራቁት ነበር ...
‹‹ ጀርባ ሳናጠና እየሾምን . እና እየባረክን እኮ ነው ትውልድና አገር ሆድና ጀርባ እንዲሆን ምናደርገው ›› አሉና እስከመድረሻዋ በአይናቸው ሸኟት ቆንጆዋን !!
🔘አሌክስ🔘
〰አብሮነታችሁን በዚ 👍 አሳዩን〰

👍3
#ከንፈር #ግን #ሲገርም !
እኔ የምልሽ ውዴ
የጀነት በር ማለት ከንፈርሽ ነው እንዴ ?
ምናባቴ ልበል .....!
ስትስሚኝ ጊዜ
ፊቴ የነበረው ፎከታም ግድግዳ የት አባቱ ሄደ ?
ውስጤ የተገነባው የጭንቀት ባቢሎን
ከምኔው ተናደ ?
ስትስሚኝ ጊዜ
በሂሊናየ ውስጥ ያንን ሁሉ አበባ
ማን ተክሎት በቀለ ?
ይሄስ ሁሉ ደስታ
ከየት ተጠራርቶ
ውስጤ ተቆለለ ?
ተፈጥሮን ገልብጦ አናቴን በጥብጦ
ፀሃይን በምራብ አወጣት ከንፈርሽ
መገን አሳሳምሽ !!
ብትስሚኝ ጊዜ
ዝሆኖች በረሩ
እባቦች ጋለቡ
በባዶ ልቤ ውስጥ
እልፍ ሰርጎች ገቡ
አይሆንም ያልኩት ቀን
ይሄው ዛሬ ሆነ
እግርሽ እያስቃዠው ልቤ ልብ ሲያልም
ህልሜን ከሃቂቃው ያደበላለቀው
ከንፈር ግን አይገርምም ! ?
እኔ የምልሽ ውዴ
ስንት ጉድ ፀያፍ ቃል
አልፎ የሚወጣው
ይሄን ጉድ ነው እንዴ
ኧረ ጉዴ !
ማጀት ተገን አርጎ
ለፍቅር ባይሳሳም
አሁንም እላለሁ
ሳይሳም ያሳመኝ አገሬው ይሳሳም
🔘አሌክስ አብረሃም🔘
እኔ የምልሽ ውዴ
የጀነት በር ማለት ከንፈርሽ ነው እንዴ ?
ምናባቴ ልበል .....!
ስትስሚኝ ጊዜ
ፊቴ የነበረው ፎከታም ግድግዳ የት አባቱ ሄደ ?
ውስጤ የተገነባው የጭንቀት ባቢሎን
ከምኔው ተናደ ?
ስትስሚኝ ጊዜ
በሂሊናየ ውስጥ ያንን ሁሉ አበባ
ማን ተክሎት በቀለ ?
ይሄስ ሁሉ ደስታ
ከየት ተጠራርቶ
ውስጤ ተቆለለ ?
ተፈጥሮን ገልብጦ አናቴን በጥብጦ
ፀሃይን በምራብ አወጣት ከንፈርሽ
መገን አሳሳምሽ !!
ብትስሚኝ ጊዜ
ዝሆኖች በረሩ
እባቦች ጋለቡ
በባዶ ልቤ ውስጥ
እልፍ ሰርጎች ገቡ
አይሆንም ያልኩት ቀን
ይሄው ዛሬ ሆነ
እግርሽ እያስቃዠው ልቤ ልብ ሲያልም
ህልሜን ከሃቂቃው ያደበላለቀው
ከንፈር ግን አይገርምም ! ?
እኔ የምልሽ ውዴ
ስንት ጉድ ፀያፍ ቃል
አልፎ የሚወጣው
ይሄን ጉድ ነው እንዴ
ኧረ ጉዴ !
ማጀት ተገን አርጎ
ለፍቅር ባይሳሳም
አሁንም እላለሁ
ሳይሳም ያሳመኝ አገሬው ይሳሳም
🔘አሌክስ አብረሃም🔘
👍1
#አይደለም #ምኞቴ
አይደለም ምኞቴ
ለምለም አንገትሽ ላይ : ክንዶቼን መጠምጠም
ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ: ጭንሽ ማሃል መስጠም
እይደለም ምኞቴ
ከንፈርሽን ማለብ
ቀሚስሽን መግለብ
ከገላሽ ቆርሼ :ገላየን መቀለብ
ደረትሽን ማለም
ጡትሽን መሳለም
በቁንጅናሽ ጅረት : ገነቴን ማለምለም
አላማየ አይደለም::
ምኞቴን ልንገርሽ?
ካለሺበት ቦታ: ቀልቤን ማሰማራት
ወትሮ ካንቺ ጋራ: ቡና መጠራራት
ሰላም መገባበዝ: ትዝታ መጋራት
የጨለመ ፊቴን : ባይንሽ ጮራ ማድመቅ
በቃላትሽ መስከን: በሳቅሽ መጠመቅ
በጎ መንፈስሽን :ካይንሽ ላይ መሻማት
ርጋታሽን ማጥመድ : ዝምታሽን መስማት::
ከ🔘በውቄ🔘
አይደለም ምኞቴ
ለምለም አንገትሽ ላይ : ክንዶቼን መጠምጠም
ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ: ጭንሽ ማሃል መስጠም
እይደለም ምኞቴ
ከንፈርሽን ማለብ
ቀሚስሽን መግለብ
ከገላሽ ቆርሼ :ገላየን መቀለብ
ደረትሽን ማለም
ጡትሽን መሳለም
በቁንጅናሽ ጅረት : ገነቴን ማለምለም
አላማየ አይደለም::
ምኞቴን ልንገርሽ?
ካለሺበት ቦታ: ቀልቤን ማሰማራት
ወትሮ ካንቺ ጋራ: ቡና መጠራራት
ሰላም መገባበዝ: ትዝታ መጋራት
የጨለመ ፊቴን : ባይንሽ ጮራ ማድመቅ
በቃላትሽ መስከን: በሳቅሽ መጠመቅ
በጎ መንፈስሽን :ካይንሽ ላይ መሻማት
ርጋታሽን ማጥመድ : ዝምታሽን መስማት::
ከ🔘በውቄ🔘
‹‹ዓድዋ››
የሰው ልጅ ክቡር፣
ሰው መሆን ክቡር፣
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር፣
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፣ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ።
የተሰጠኝ ሕይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ።
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን፣
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
ዓድዋ ዛሬ ናት ዓድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች፣
የጥቁር ድል አምባ፣ ዓድዋ፣
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ፣
ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ።
የእጅጋየሁ ሺባባው (ጂጂ)
የሰው ልጅ ክቡር፣
ሰው መሆን ክቡር፣
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር፣
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፣ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ።
የተሰጠኝ ሕይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ።
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን፣
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
ዓድዋ ዛሬ ናት ዓድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች፣
የጥቁር ድል አምባ፣ ዓድዋ፣
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ፣
ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ።
የእጅጋየሁ ሺባባው (ጂጂ)
👍1🔥1
[ዓድዋ]
ዋ! ..... ያቺ ዓድዋ
ዋ! ...
ዓድዋ ሩቋ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋቋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋቋ።
ዓድዋ.....
ባንቺ ብቻ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና፣
አበው ታደሙ እንደገና።
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስቷ፣
የደም ትቢያ መቀነቷ።
በሞት ከባርነት ሥርየት፣
በደም በነፃነት ስለት፣
አበው የተሰውብሽ ለት።
ዓድዋ!
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ፣
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ።
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ፣
ታድማ በመዘንበልዋ።
ዐፅምሽ በትንሳኤ ንፋስ፣
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ።
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ፣
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ፣
ብር ትር ሲል ጥሪዋ፣
ድው እልም ሲል ጋሻዋ፣
ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ።
ያባ መቻል ያባ ዳኘው፣
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣
ያባ በለው በለው ሲለው፣
በለው በለው በለው በለው።
ዋ! ...... ዓድዋ .....
ያንቺን ፅዋ ያንቺን አይጣል፣
ማስቻል ያለው አባ መቻል።
በዳኘው ልብ በአባ መላው፣
በገበየሁ በአባ ጎራው፣
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው፣
በለው ብሎ በለው በለው።
ዋ! ...... ዓድዋ .....
ዓድዋ የትናንትናዋ፣
ይኸው ባንቺ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና፣
በነፃነት ቅርስሽ ዜና፣
አበው ተነሱ እንደገና።
....... ዋ! ........ ያቺ ዓድዋ፣
ዓድዋ ሩቅዋ ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ።
ዓድዋ .......
🔘ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን🔘
ዋ! ..... ያቺ ዓድዋ
ዋ! ...
ዓድዋ ሩቋ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋቋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋቋ።
ዓድዋ.....
ባንቺ ብቻ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና፣
አበው ታደሙ እንደገና።
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስቷ፣
የደም ትቢያ መቀነቷ።
በሞት ከባርነት ሥርየት፣
በደም በነፃነት ስለት፣
አበው የተሰውብሽ ለት።
ዓድዋ!
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ፣
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ።
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ፣
ታድማ በመዘንበልዋ።
ዐፅምሽ በትንሳኤ ንፋስ፣
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ።
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ፣
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ፣
ብር ትር ሲል ጥሪዋ፣
ድው እልም ሲል ጋሻዋ፣
ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ።
ያባ መቻል ያባ ዳኘው፣
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣
ያባ በለው በለው ሲለው፣
በለው በለው በለው በለው።
ዋ! ...... ዓድዋ .....
ያንቺን ፅዋ ያንቺን አይጣል፣
ማስቻል ያለው አባ መቻል።
በዳኘው ልብ በአባ መላው፣
በገበየሁ በአባ ጎራው፣
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው፣
በለው ብሎ በለው በለው።
ዋ! ...... ዓድዋ .....
ዓድዋ የትናንትናዋ፣
ይኸው ባንቺ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና፣
በነፃነት ቅርስሽ ዜና፣
አበው ተነሱ እንደገና።
....... ዋ! ........ ያቺ ዓድዋ፣
ዓድዋ ሩቅዋ ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ።
ዓድዋ .......
🔘ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን🔘
#አታውቃት #እንደሆን
ሰው እንደ ሰው ቢቆም ፥ በእናት ሐገር ምድሩ
ያለዋጋ አይደለም ፥ ወዲህ ነው ምሥጢሩ
አያት ቅድመ አያቱ ፥ ጠላትን ሲመቱ
እንደዝናብ ሲወርድ ፥ የጥይት መዓቱ
ሲንጣጣ ሲያሽካካ ፥ ጦር አውርዱ ኹላ
ያፈገፈገ የለም ፥ ከቶም ወደ ኋላ።
ከኋላ ምሽት አለች ፥ ከአንድ ወንዝ የተቀዳች
ከቀሚሷም ወርዶ ፥ የሚድኹ ልጆች
የእርሻም መሬት አለ ፥ በላብ ወዝ የራሰ
የሽምብራ ጥርጥር ፥ በወግ ያደረሰ
የቤተስኪያን ደውሉ ፥ የመስኪድ አዛኑ
ኢምንት እምነቱ ናት ፥ የሰው ማዕዘኑ።
አይሸሽም አይፈራም ፥ ያቅራራል ቀረርቶ
ሽለላ ያሰማል ፥ ዘራፍ ደረት ነፍቶ
ግዳይ እንደ ጣለ ፥ በሞት ነው የሚፈካ
ከጠላ ጠላ ነው ፥ ከማረም አይነካ
ጀግና ዕድሜ እየተጫነው ፥ ምን በመልኩ ቢጃጅ
ፈርቶ ሞት አያውቅም ፥ ጦር ቀምሶ ነው 'ሚባጅ።
ቆመህ ስትራመድ ፥ ዛሬ በነጻነት
ደፍረህ ስትናገር ፥ ቀና ብለህ ካንገት
ትርጉሙ እንዲገባህ ፥ ውሉን እንዳትስተው
ኢትዮጵያዊነትህን ፥ ሀ ብለህ መርምረው።
የማንነት ካስማዋ ፥ የአንድነት ማማዋ
አታውቃት እንደሆን ፥ ይህቺው ናት ዓድዋ።
በ 🔘እሱባለው አበራ🔘
ሰው እንደ ሰው ቢቆም ፥ በእናት ሐገር ምድሩ
ያለዋጋ አይደለም ፥ ወዲህ ነው ምሥጢሩ
አያት ቅድመ አያቱ ፥ ጠላትን ሲመቱ
እንደዝናብ ሲወርድ ፥ የጥይት መዓቱ
ሲንጣጣ ሲያሽካካ ፥ ጦር አውርዱ ኹላ
ያፈገፈገ የለም ፥ ከቶም ወደ ኋላ።
ከኋላ ምሽት አለች ፥ ከአንድ ወንዝ የተቀዳች
ከቀሚሷም ወርዶ ፥ የሚድኹ ልጆች
የእርሻም መሬት አለ ፥ በላብ ወዝ የራሰ
የሽምብራ ጥርጥር ፥ በወግ ያደረሰ
የቤተስኪያን ደውሉ ፥ የመስኪድ አዛኑ
ኢምንት እምነቱ ናት ፥ የሰው ማዕዘኑ።
አይሸሽም አይፈራም ፥ ያቅራራል ቀረርቶ
ሽለላ ያሰማል ፥ ዘራፍ ደረት ነፍቶ
ግዳይ እንደ ጣለ ፥ በሞት ነው የሚፈካ
ከጠላ ጠላ ነው ፥ ከማረም አይነካ
ጀግና ዕድሜ እየተጫነው ፥ ምን በመልኩ ቢጃጅ
ፈርቶ ሞት አያውቅም ፥ ጦር ቀምሶ ነው 'ሚባጅ።
ቆመህ ስትራመድ ፥ ዛሬ በነጻነት
ደፍረህ ስትናገር ፥ ቀና ብለህ ካንገት
ትርጉሙ እንዲገባህ ፥ ውሉን እንዳትስተው
ኢትዮጵያዊነትህን ፥ ሀ ብለህ መርምረው።
የማንነት ካስማዋ ፥ የአንድነት ማማዋ
አታውቃት እንደሆን ፥ ይህቺው ናት ዓድዋ።
በ 🔘እሱባለው አበራ🔘
አድዋ-በአፍ አይገባም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።፡።፡፡፡።።፡
አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲል
አድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደል
ላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክል
ለዛሬም ታሪክ አባት ነው፤ “ነገም ሌላ ቀን ነው” ለሚል
አድዋ ሰው-ዛብ፣ የደም-ድልድይ
አንድም ፍልሚያ፣ አንድም ራእይ
ልብ ላለው ልብ ያነዳል
ለምር ቀን ስንቅ ይሆናል!!
ነጻነት አይለመንም
ያው ጥንትም ተጽፏል በደም
አገር ድንበሯ ሲነደል፣
ያው ዛሬም ተማግሯል በፍም
የአጋም-አጥር ተደግፎ
ጎረምሳ ኮረዳም ቢስም
በወርቅ-አልጋ በእርግብ-ላባ
ተኝቶ ማደር ቢቻልም
አገር ከፍቷት ሰላም የለም
አድዋ ሞተው ሲኖሩ እንጂ ተተርኮ በአፍ አይገባም!
ዱሮም ዛሬም በአፍ አይገባም!
****
🔘በነቢይ መኮንን🔘
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።፡።፡፡፡።።፡
አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲል
አድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደል
ላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክል
ለዛሬም ታሪክ አባት ነው፤ “ነገም ሌላ ቀን ነው” ለሚል
አድዋ ሰው-ዛብ፣ የደም-ድልድይ
አንድም ፍልሚያ፣ አንድም ራእይ
ልብ ላለው ልብ ያነዳል
ለምር ቀን ስንቅ ይሆናል!!
ነጻነት አይለመንም
ያው ጥንትም ተጽፏል በደም
አገር ድንበሯ ሲነደል፣
ያው ዛሬም ተማግሯል በፍም
የአጋም-አጥር ተደግፎ
ጎረምሳ ኮረዳም ቢስም
በወርቅ-አልጋ በእርግብ-ላባ
ተኝቶ ማደር ቢቻልም
አገር ከፍቷት ሰላም የለም
አድዋ ሞተው ሲኖሩ እንጂ ተተርኮ በአፍ አይገባም!
ዱሮም ዛሬም በአፍ አይገባም!
****
🔘በነቢይ መኮንን🔘
“የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ”
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይኸን ጊዜ አበሻ፡፡
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡
መድፋን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ
እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ
የዘራውን እህል አጭዶና ወቅቶ
ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ፡፡
እንዳቀና ብሎ ለምኖ መሬት
ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አትክልት
እየመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግሥት
ለጓዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት
ተጠማኝ ሰንብቶ ሆኖ ባለርስት
ወሰን እየገፋ ጥቂት በጥቂት
እውነት እርስት ሆነው ተቀበረበት፡፡
ባሕር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደ ተልባ ስፍር ትከዳለች እንጂ
አትረጋምና ያለተወላጅ፡፡
የዳኛው አሽከሮች እየተባባሉ
ብልት መቆራረጥ አንድነት ያውቃሉ
#ዓድዋ ከከተማው ሥጋ ቆርጠው ጣሉ፡፡
የእስክንድር ፈረስ መቼ ተወለደ
የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ፡፡
ደንገላሳ ሲዘል እየተንጓደደ
የሮማውን ኩራት በእግታ አሰገደ፡፡
አገርህን ምኒልክ እንዳሁን ፈትሻት
እጁን ቀምሼ አላውቅም እያለ ሲያማህ
ቀመሰና እጅህን መጥቶ ጠላትህ
ሮም ላይ ተሰማ ለጋስ መሆንህ፡፡
አባተ በመድፋ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጐጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሃን
ዳዊቷን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል፡፡
እንደ በላዔ ሰብአ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛማ ጌታችን፡፡
(ተክለ ጻድቅ መኩሪያ)
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይኸን ጊዜ አበሻ፡፡
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡
መድፋን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ
እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ
የዘራውን እህል አጭዶና ወቅቶ
ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ፡፡
እንዳቀና ብሎ ለምኖ መሬት
ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አትክልት
እየመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግሥት
ለጓዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት
ተጠማኝ ሰንብቶ ሆኖ ባለርስት
ወሰን እየገፋ ጥቂት በጥቂት
እውነት እርስት ሆነው ተቀበረበት፡፡
ባሕር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደ ተልባ ስፍር ትከዳለች እንጂ
አትረጋምና ያለተወላጅ፡፡
የዳኛው አሽከሮች እየተባባሉ
ብልት መቆራረጥ አንድነት ያውቃሉ
#ዓድዋ ከከተማው ሥጋ ቆርጠው ጣሉ፡፡
የእስክንድር ፈረስ መቼ ተወለደ
የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ፡፡
ደንገላሳ ሲዘል እየተንጓደደ
የሮማውን ኩራት በእግታ አሰገደ፡፡
አገርህን ምኒልክ እንዳሁን ፈትሻት
እጁን ቀምሼ አላውቅም እያለ ሲያማህ
ቀመሰና እጅህን መጥቶ ጠላትህ
ሮም ላይ ተሰማ ለጋስ መሆንህ፡፡
አባተ በመድፋ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጐጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሃን
ዳዊቷን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል፡፡
እንደ በላዔ ሰብአ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛማ ጌታችን፡፡
(ተክለ ጻድቅ መኩሪያ)
👍2
#ዴዝዴሞና
ከረፋፈደ በኋላ ነበር የትያትር ቤቱ የኋላ ረድፍ ላይ ቦታ ይዞ የተቀመጠው፡፡ የያዘው ክፉ የፍቅር ልክፍት ነው በዚህ ቲያትር ቤት ውስጥ እንዲገኝ ያደረገው፡፡ ለሼክስፒር የተውኔት ድርሰቶች ፍቅርና ስሜት ኖሮት አያውቅም፡፡ እሱ ፍቅር የያዘው ከገፀባህሪዋ ስም ጋር ሞክሼ ስም ካላት የራሱ ዴዝዴሞና ጋር ነው፡፡ ክፉ የቅናት ዛር መንፈሱን ከተቆጣጠረው ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል፡፡ እርዳታ ፍለጋ ሃኪም ጋር ሄዶ “ፓራኖያ አለብህ” ተብሏል፡፡ ከወንድ ጋር ያያት ሴት ሁሉ እስዋ ትመስለዋለች፡፡ ከንግግርዋ፣ ከአዋዋልዋ፣ ከአመሻሽዋ፣ ከአለባበስዋ፣ ከጓደኞችዋ፣ ከቤተሰቦችዋ፣ከትናንት ታሪክዋ ጋር የተገናኘ የቅናት መንፈስ ተጠናውቶታል። ስልክ ስታወራ በቅናት ልቡ ይመታል፡፡ ትንሽ ካመሸች ጓደኞቿ ጋር ሁሉ እየደወለ ወይም እየሄደ ሊሰልላት ይሞክራል፡፡ ባልና ሚስት ሳይሆኑ ሌባና ፖሊስ ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ በእንቅልፍ ልብዋ የሆነ ነገር ብታልጎመጉም፣ በሱ ነገር እየተጨነቀ፣ ፍችውን ለማወቅ ሲባዝን ያድራል፡፡
ለእሷ ካለው እውር ጭፍን ፍቅር የተነሳ “ኦቴሎ”ን ሊያይ ቲያትር ቤቱ የመጨረሻ ወንበር ላይ ቢሰየምም፣ መጋረጃው ተገልጦ ቲያትሩ የጀመረው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ነበር፡፡
ቃሲዮን ሲያይ፣ እጁን ቡጢ ጨበጠ፡፡ ይሄ ነው ሚስቴን ሲዳራ የሚያድረው እያለ ጥርሱን በቁጣ ያፋጫል፡፡ ኢያጎ ለኦቴሎ በመሰሪ ቋንቋው የዴዝዴሞናን አለመታመን በጆሮው ሲያንሾካሹክ፣ እሱም ከኦቴሎ ከራሱ በላይ ቁጣው ገነፈለ፡፡
ወደዚህ ቲያትር ቤት ለመግባት ዋና ምክንያቱ፣ ፍቅረኛው ትላንት በስልክ ከወንድ ጋር ስትቀጣጠር በመስማቱ ነው፡፡ ሁሉንም ንግግር በትክክል ባይሰማም “ማዘጋጃ” እና “አስር ሰዓት” የሚሉት ቃላት ግን አላመለጡትም፡፡
ኦቴሎ በኢያጎ ስብከት በቁጣ ሲንጎራደድ፣ ድንገት አይኑ ውስጥ ገባች፡፡ ፊት ካለው ረድፍ ወንበር ላይ አንድ ጎረምሳ እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ ተቀምጧል፡፡
እሷ ለመሆንዋ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም ከአመት በፊት የገዘላትን ሻሽ አንገትዋ ላይ ጣል አድርጋዋለች፡፡ ረጅም ፀጉርዋንም ቢሆን አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ እንዴት የሚስቱ ፀጉር ይጠፋዋል፡፡ ቢሆንም የማይቀና ጥሩ ባል ለመሆን በመሞከር፣ ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ቁጥርዋን መታ፡፡ ይጠራል፡፡ ግን አይነሳም፡፡ ሻሹን በደንብ አስተዋለ፡፡ ራሱ ነው፡፡ የሚያያት ከጀርባዋ ቢሆንም፣ ከት ብላ ስትስቅ፣ ሰውየውም አብሯት ሲስቅ ተመለከተ። አሁንም ደግሞ ደወለ፡፡ ሶስቴ ከጠራ በኋላ “የደወሉላቸው ደንበኛ ስልክ ጥሪ እያስተላለፈ ነው” አለች፤ ኦፕሬተርዋ፡፡
እሱ ላይ ስልክ እየዘጋች ከማንም ውርጋጥ ጎረምሳ ጋር ስታስካካ ሊታገስ አልቻለም፡፡ ሜሴጁን ማዥጎድጎድ ጀመረ፡፡
“አንቺ ውሻ፣ ሸርሙጣ፣ ድሮስ ማን ይፈልግሻል!” አንዱ ነው፡፡
ቲያትሩ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል፡፡ ኦቴሎም የዴዝዴሞና አልፍኝ ለመግባት እርምጃውን ጀምሯል፡፡
ሁለተኛውን ሜሴጅ ጻፈ፡፡
“በረጅም እንጨት አልነካሽም፡፡ ድሮስ እኔ አላቅሽም ወዘተረፈ …”
ለሃያ ደቂቃ ያህል ስምንት ሜሴጆችን አከታትሎ ቢጽፍም፣ የፍቅረኛው ሜሴጅ የመጣው ግን ዘጠነኛውን ሊጽፍ ሲያስብ ነበር፡፡
እንዲህ ይላል፡-
“ረስተኸው ይሆናል፡፡ እኔ ግን አልረሳውም። ዛሬ የተገናኘንበት ቀን ነበር፡፡ ልክ በዛሬው ዕለት፣ ከአራት አመታት በፊት፣ ምሽቱን ወጣ ብለን እንድናሳልፍ አስቤ ነበር፡፡ ስጦታም አዘጋጅቼልሃለሁ፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ለገዛህልኝ ሻሽ እሺ ያልኩህ ጊዜ ትዝ ይልሃል፡፡ የኔ ፍቅር፤ የገዛሁልህን ሮሌከስ ሰዓት፣ ማዘጋጃ ቤት አጠገብ ካለው ስዊዝ ሰዓት ቤት ውሰድ፡፡ የኔ ፍቅር ደህና ሁን፡፡
በፍጥነት ተነስቶ እየተንደረደረ፣ ወደ ፊት ወንበሮች አመራ፡፡ ሻሹን እያየ ወደሷ ቀረበ፤ አጠገብዋ ሲደርስ ፊትዋን በእጁ አዞረው። ዴዝዴሞና አልነበረችም፡፡ ሁለቱ ፍቅረኞች በድንጋጤ ፈጠው እያዩት ነበር፡፡
ኦቴሎ ዴዝዴሞናን ያነቀው በዚያ ቅፅበት ነበር፡፡
🔘ከመሐመድ ኢድሪስ🔘

👍4
#የሴት_ክብር_በአፍሪካ
፧
ሴት ስትንኳሰስ
ሴት ስትዋረድ ~ ሴት ስትደፈር፣
በምትኖርባት
አፍሪካ በሚሏት ~ አህጉር፣
የሴቶችን ክብር
በፍትህ ዓይን ~ መዝና ስትሰፍር፣
አመት ሴትን ረስታ
አንዱን ቀን መርጣ ትኖራለች ማርች8ን ስታከብር።
፡
አይ አፍሪቃ!!!!
፧
፧
ሴት ስትንኳሰስ
ሴት ስትዋረድ ~ ሴት ስትደፈር፣
በምትኖርባት
አፍሪካ በሚሏት ~ አህጉር፣
የሴቶችን ክብር
በፍትህ ዓይን ~ መዝና ስትሰፍር፣
አመት ሴትን ረስታ
አንዱን ቀን መርጣ ትኖራለች ማርች8ን ስታከብር።
፡
አይ አፍሪቃ!!!!
፧
#እኛው #ነን...
እኛው ነን የገፋን እኛው ነን የከፋን
እኛው ነን ያጠፋን እኛው ነን የጠፋን
ከዘመን ጋር አብሮ መዘመን ተስኖን
ሰፊ ሀገር ይዘን በሀሳብ አየጠበብን
በፍቅር ተሳስቦ አብሮ መራመድ አቀበት የሆነብን
ቂም እየቆጠርን ቂም እየመነዘርን
በዛሬ መንጋጋ የትላንት ድርቆሽ የምናመነዥክ
በዛሬ ምድጃ የትላንቱን አመድ ታቅፈን የምንሞቅ
በአንድ ላይ ከመጓዝ በየፊና ሩጫ አረፋ የምንደፍቅ።
እኛው ነን እኛው ነን
ከእምነት የተፋታን ከፈጣሪ የራቅን።
እኛው ተጋፊዎች እኛው ተገፊዎች
እኛው አሳዳጆች እኛው ተሳዳጆች
ካሳለፍነው ህይወት ካሳለፍነው መከራ መማር የተሳነን
ደመና ወራሾች።
በማስመሰል ጥበብ በአድርባይ አንደበት በሸፍጥ
የሰለጠንን
ከብዞዎች ድርሻ ተሻምተን ተናጥቀን
ለአንድ ለእራሳችን በወርቅ ላይ አልማዝ በህንፃ ላይ ህንፃ ስንቆልል ስንከምር የማይሰቀጥጠን
የመንፈስ ድዊዎች የንዋይ ምርኮኞች
የወንበር ሱሰኞች የሆድ አምላኪዎች
ከሰውነት ወርደን በነፍስ የኮሰመንን የስጋ ቡኩኖች
የራሳችን ሀጢያት የራሳችንን ሲኦል እኛው ነን መርገምቶች
እኛው ነን።
🔘በጌትነት እንየው🔘

****ፍፃሜዉ****
የሚሽከረከሩ አለምን በገንዘብ
አድምቀው ያበዙ ተፈጥሮን በጥበብ ፣
-
ያገር ተወካዮች የአለማት መሪ ፣
ጎዳና የሚኖር በልቶ ፍርፋሪ ፣
-
ኑሮ ያቆሰለው ያገር ወንደላጤ፣
የተጎሳቆለ ምስኪን የኔ ቢጤ ፣
-
ጠቢብ ስአሊያን ድንቅ ሙዚቀኛ ፣
ሽጋ መልከ መልካም ታዋቂ ዝነኛ ፣
-
የኔ አይነት አመዳም ባሪያ መልከ ጥፉ ፣
እውቅ ባለሀብቶች
ሚሊዮን ተርቦ ቢሊዮን ያቀፉ ፣
አንቱ የተባሉ በስም የገዘፉ ፣
ይኖራሉ በአለም እንዲህ ተለያይተው ፣
ምድርና ሰማይ ቤታቸውን ሰርተው ።
-
ይሄ ሁሉ አዳም አንድ ሆኖ ደሙ ፣
ስጋው አፈር ሲለብስ
ሲለይ ከአለሙ ፣
መአረጉ ቀርቶ
ሁሉም በአንድ ላይ ሬሳ ነው ስሙ ።
ከቻናሉ ተከታታይ የተላከ አስተያየታችሁን አድርሱት 👉 @Sam2127
ከ🔘ሳሙኤል አዳነ🔘
11/10/08
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ