#ትወደኛለህ_ወይ?”
እኔምልሽ ውዴ፡-
ላንቺ የምሆነውን - ልብሽ እያወቀው
ስወጣ ስገባ -
“ትወደኛለህ ወይ?”- ምትይኝ ለምን ነው???
ትወደኛለህ ወይ?”
ምን ልመልስልሽ?
ምን ብየ ልንገርሽ?
“እኔ አንቺን ምወድሽ
እንደ ገነት አለም - እንደ ስውር ቦታ
ማንም አይደርስበት - የፍቅሬን ከፍታ::
እኔ አንቺን ስወድሽ:-
ልክ እንደ ልጅነት፣
እንደ እናት ጡት ወተት፤
እንደ ከረሜላ ፣
እንደ ማር ወለላ፤
ብላ ብላ ብላ
ብልሽ ታምኛለሽ?
አምነሽ ትኮሪያለሽ?
ትወደኛለህ ወይ?”
ቀላል እወድሻለሁ!
ከመውደድም አልፈሽ - ሱስ ሆነሽብኛል
ለሰከንድ ከራቅሽኝ - ፍቅርሽ ያዛጋኛል፡፡
ብቻ ምን ልበልሽ
ከምነግርሽ በላይ - በጣም እወድሻለሁ
አያድርገውና
አ.ያ.ድ.ርገውና
ድንገት አንቺን ባጣ - ራሴን አጠፋለሁ::
ብልሽ ታምኚኛለሽ?
አምነሽ ትኮሪያለሽ ???
ላንቺ የምሆነውን ልብሽ እያወቀው
ስወጣ ስገባ
“ትወደኛለህ ወይ?” ምትይኝ ለምን ነው??
“ትወደኛለህ ወይ?”
ምን ልመልስልሽ?
ምን ብየ ልንገርሽ?
እውነት ለመናገር
ተመቸሽኝ እንጂ፣ገና አልወደድኩሽም
በብዙ ነገርሽ፣ አልረካሁብሽም::
እንዲያውም
እንዲያውም
በዚህ አካሄድሽ፣ በዚህ አካሄዴ
አይቀርም አንድ ቀን፣ ሌላ ሴት መውደዴ!'
ብልሽ ታምኛለሽ?
አምነሽ ታኮርፊያለሽ?
“ትወደኛለህ ወይ?”
“በይ እውነቱን ስሚ:-
በዕርግጥ ለጋሱ አምላክ - ውበት አድሎሻል
ታዲያ ምን ዋጋ አለው
ለመወደድ ሚሆን- ፀባይ ይጎድልሻል::
ጸባይሽ ጸባየ- ካልተገጣጠሙ
ውህድ ካልፈጠሩ- በሃሳብ ካልተስማሙ
አይቼሽ
አይቼሽ
ጥርግ ነው ምለው - ባለሽበት ትቼሽ!”
ብልሽ ታምኝኛለሽ?
አምነሽ ትርቂያለሽ?
ከምታይው በላይ ጆሮሽን ታምኛለሽ ??
እ???
ምን ልልሽ መሰለሽ :-
ለኔ አይነቱ ምስኪን
ራሱን እያደማ
እንቅፋትሽን ሁሉ - ቀድሞሽ ለሚለቅም
ትወደኛለህ ወይ?”
ተብሎ አይጠየቅም።
አይጠየቅም።
🔘ሙሉቀን🔘
እኔምልሽ ውዴ፡-
ላንቺ የምሆነውን - ልብሽ እያወቀው
ስወጣ ስገባ -
“ትወደኛለህ ወይ?”- ምትይኝ ለምን ነው???
ትወደኛለህ ወይ?”
ምን ልመልስልሽ?
ምን ብየ ልንገርሽ?
“እኔ አንቺን ምወድሽ
እንደ ገነት አለም - እንደ ስውር ቦታ
ማንም አይደርስበት - የፍቅሬን ከፍታ::
እኔ አንቺን ስወድሽ:-
ልክ እንደ ልጅነት፣
እንደ እናት ጡት ወተት፤
እንደ ከረሜላ ፣
እንደ ማር ወለላ፤
ብላ ብላ ብላ
ብልሽ ታምኛለሽ?
አምነሽ ትኮሪያለሽ?
ትወደኛለህ ወይ?”
ቀላል እወድሻለሁ!
ከመውደድም አልፈሽ - ሱስ ሆነሽብኛል
ለሰከንድ ከራቅሽኝ - ፍቅርሽ ያዛጋኛል፡፡
ብቻ ምን ልበልሽ
ከምነግርሽ በላይ - በጣም እወድሻለሁ
አያድርገውና
አ.ያ.ድ.ርገውና
ድንገት አንቺን ባጣ - ራሴን አጠፋለሁ::
ብልሽ ታምኚኛለሽ?
አምነሽ ትኮሪያለሽ ???
ላንቺ የምሆነውን ልብሽ እያወቀው
ስወጣ ስገባ
“ትወደኛለህ ወይ?” ምትይኝ ለምን ነው??
“ትወደኛለህ ወይ?”
ምን ልመልስልሽ?
ምን ብየ ልንገርሽ?
እውነት ለመናገር
ተመቸሽኝ እንጂ፣ገና አልወደድኩሽም
በብዙ ነገርሽ፣ አልረካሁብሽም::
እንዲያውም
እንዲያውም
በዚህ አካሄድሽ፣ በዚህ አካሄዴ
አይቀርም አንድ ቀን፣ ሌላ ሴት መውደዴ!'
ብልሽ ታምኛለሽ?
አምነሽ ታኮርፊያለሽ?
“ትወደኛለህ ወይ?”
“በይ እውነቱን ስሚ:-
በዕርግጥ ለጋሱ አምላክ - ውበት አድሎሻል
ታዲያ ምን ዋጋ አለው
ለመወደድ ሚሆን- ፀባይ ይጎድልሻል::
ጸባይሽ ጸባየ- ካልተገጣጠሙ
ውህድ ካልፈጠሩ- በሃሳብ ካልተስማሙ
አይቼሽ
አይቼሽ
ጥርግ ነው ምለው - ባለሽበት ትቼሽ!”
ብልሽ ታምኝኛለሽ?
አምነሽ ትርቂያለሽ?
ከምታይው በላይ ጆሮሽን ታምኛለሽ ??
እ???
ምን ልልሽ መሰለሽ :-
ለኔ አይነቱ ምስኪን
ራሱን እያደማ
እንቅፋትሽን ሁሉ - ቀድሞሽ ለሚለቅም
ትወደኛለህ ወይ?”
ተብሎ አይጠየቅም።
አይጠየቅም።
🔘ሙሉቀን🔘
❤1
#ለኀጥአን_የመጣ
#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ
#ክፍል_አንድ
#በኢስማኤል_ቤህ
#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው
#መነሻ
ሴራሊዮን በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ በተፈጥሮ ሃብት ማለትም በአልማዝ፣ ወርቅ፣ ቡና፣ ብረት እና ሌሎች ማዕድናት
የታደለች ነገር ግን ድሃ ሃገር ናት።
ሴራሊዮን በ1961 ከእንግሊዝ ነጻነቷን ከተቀናጀች በኋላ ለሶስት አመታት ክቡር
ሚልተን ማርጋይ በጠቅላይ ሚኒስተርነት ስትመሯ ከቆየች በኋላ ክቡር ሚልተን ማርጋይ በ1964 አረፉ፡፡ ከክቡር ሚልተን
ህልፈት በኋላ በሀገሪቱ ሙስና ተንሰራፋ
አስተዳደራዊ ብልሹነቱ ገነነ እና የምርጫ ብጥብጦች በብዛት መታየት ጀመሩ፡፡ ይህም ሀገሪቱ እንድትዳከም እና የትምህርት ስርዓቷ እንዲወድቅ ምክንያት ሆነ። ወጣቶች ተስፋ ቆርጠው ለአማጺ ቡድኑ አማላይ መልዕክት ጆሮቸውን ሰተው ብዙዎች የአብዮት አንድነት ግንባርን ተቀላቀሉ። በእንቅርት ላይ ጆሮ
ደግፍ እንዲሉ በህገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ወደ ጠቅላይ ሚኒስተር የወጣው ሲያካ ሴቴቨንስ ሃገሪቱን ወደ አንድ ፓርቲ አገዛዝነት ለወጠ። የሲያካ አስራ ሰባት ዓመታት የፍዳ አመታት ሆኑ፦ እስራት፣ ግድያ እና ስደት: በ1985 ሲያካ ስልጣኑን ለሜጀር ጄኔራል ጆሴፍ ሞሞህ ቢያስረክብም የሃገሪቱ ችግር ከድጡ ወደ ማጡ ሆነ፡፡ በ1991 የአብዮት አንድነት ግንባር
በ ላይቤሪያው ቻርልስ ቴለር ጦር በመታገዝ የጆሴፍ ሞሞህን መንግስት ለመገርሰስ ሲንቀሳቀስ እርስ በርስ ጦርነት ተቀስቀስ።
የእርስ በርስ ጦርነቱ ለአስራ አንድ አመታት ሲቀጥል ሃገሪቱን ሙሉ ሲያካልል ከሃምሳ ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎችን ሞት ምክንያት ሆነ፡፡
=========================
ስለ ጦርነቱ ብዙ ነገር ይባላል ። አንዳንዱ ሩቅ ቦታ፣ ሌላ አገር የተከሰተ ይመስላል። ይህ ግን የቆየው ተፈናቃዩች የእኛ
ከተማ እስኪደርሱ ነው። አሁን ሁላችንም እዚህ ከኛው ሃገር እንደሆነ አውቀናል ተፈናቃዩች ቤተሰቦቻቸው እንዴት
እንደሞቱ ና የቤታቸውን መቃጠል ነገሩን።
አንዳንድ ሰዎች በጣም አዝነው ምግብ ሊሰጡዎቸው ሊያሰጠጎቸውም ወደዱ..
አብዛኞቹ ተፈናቃዩች ግን ፍቃደኛ አልሆኑም። ጦርነቱ ከዚህ ከተማ መድረሱ እንደማይቀር ያውቃሉና።
ልጆቻቸው ቀና ብለው አያዩንም። አቀርቅረው መሬት መሬት ያያሉ፥ የዛፍ መቁረጥ ድምፅ ይሁን የቤት ጣራ በሚጫወቱ ልጆች በድንጋይ ሲመታ በሚሰሙት ድምፅ ህፃናቱ በፍርሃት
ይዘላሉ፤ ይሮጣሉ። ትልልቆች ከጦርነቱ አካባቢ የመጡ ወላጆቻቸው ደግሞ ብዙ ጊዜ ከእኔ ከተማ አዋቂዎች ጋር እያወሩ
ሀሳብ ጭልጥ አድርጎ ይወስዳቸዋል። ከድካም ከመሰላቸት ና ከረሃብ በላይ አዕምሮቸውን የሚረብሽ ነገር እንዳዩ : ሁሉን ዘርግፈው ቢነግሩን ማመን የማንፈልገው አንድ ነገር እንዳዩ
ፊታቸው ላይ ይነበባል። አንዳንዴ አላፊዎቹ የሚነግሩን የተጋነነ
ፀይመስለኝ ነበር።
ስለ ጦርነት የማውቀው መፅሀፍ ላይ ካነበብኩት ወይም ፊልሞች ላይ ከተመልኩት ማለት ራንቦ ፈርስት፣ ብለድ እና የጎረቤት የላይቤሪያን በቢቢሲ ያዳመጥኩት ብቻ ነበር። በዛ
በንቦቀቅላ በአስር አመት እድሜ ስደተኞቹ ደስታቸውን ምን እንደነጠቃቸው የማወቅ የመረዳት አቅሙ አልነበረኝም::
ለመጀመሪያ ጊዜ ጦርነት የገጠመኝ በአስራ ሁለት አመቴ ነበር። ጥር ፡ 1985። ከ ጅንየር ከታላቅ ወንድሜ እና ከጓደኛየ ቶሊ ጋር ወደ ማትሩ ጆንግ የሙዚቃ ውድድር ለመሳትፍ በሄድንበት
ወቅት፡፡ሁለቱም በአንድ አመት ይበልጡ
ኛል ታላቆቼ ናቸው::የቅርብ ጓደኛዬ መሐመድ ከአባቱ ጋር የሳር ቤታቸውን እያደሱ ስለነበር መምጣት አልቻለም:: ገና በስምንት አመቴ ነው አራታችን የራፕ እና የዳንስ ቡድን የመሰረትነው፡፡
ቦምቢ ከተማ ነበር ራፕ ሙዚቃን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዳመጥኩት፡፡ አንድ አራተኛው የከተማው ነዋሪ ለ አሜሪካ
ድርጅት የሚሰሩ የውጭ ሃገር ሰዎች ነበሩ፡፡ አባቴም እዚህ ከተማ ይኖር ነበር፡፡ መዋኛ ገንዳ ላይ ለመዋኝት፧ ቴሌቭዥን
ለማየት እና በእንግዳ መቆያ የሚሰባሰቡትን ነጭ ሰዎችን
ለማየት ቦምቢ እንሄድ ነበር፡፡
አንድ ምሽት እንደ እኛ ጥቁር ወጣቶች በጣም ፍጥነት የሚያወሩበት ሙዚቃ በቴሌብዥን ተመለከትን፡፡ አራታችንም
ተመስጠን ሙዚቃውን አዳመጥን ፧ ሙዚቃዉን ለመረዳት ሞከርን፡፡ በየሳምንቱ መሰል ሙዚቃዎችን ለማጥናት ወደ ከተማ መመላለስ ጀመርን፡፡ ራፕ” እንደሚባል አናውቅም ነበር፤ ጥቁሮች እንግሊዝኛ አቀላጥፈው መናገራቸው እና የሙዚቃ ምት መጠበቃቸው ግን ገረመን፡፡
በኋላ ጅኒየር ከትምህርት ቤት ጓደኞቹ ስለ ውጭ ሃገሩ ሙዚቃ እና ዳንስ ብዙ ተማረ፡፡ ወደ ቤት ሲመጣ የሙዚቃ
ካሴቶችን ይዞ ይመጣና እኔ እና ጓደኞቼን ያለማምደናል፡፡ ሂፕሆፕ ንም አወቅን፡፡ የ ሂፕ ሆፕ ዳንስ እንቅስቃሴን፤ በዋናነት
ደግሞ ግጥሞቹን ማጥናት ያስደስተኝ ነበር፡፡ ግጥሞቹ የቃላት እውቀቴ ያሳደጉታል፡፡
አንድ ቀን እኔ እና ጓደኞቼ ሙዚቃ እያዳመጥን አባቴ መጣ i know you got a soul, ጥሩ ልብ እንዳለሽ አውቃለው የሚለውን የኤሪሪክ ቢ
እና ራኪም ሙዚቃ እያዳመጥን ነበር፡፡ አባቴ ሙዚቃዉን ሲስማ ፈገግ ብሎ ምን
እንደሚል ግን ይገባቹሃል?” ብሎ ጠየቀን፡፡ መልሳችንን ሳይሰማ
ጥሎን ሄደ እና በማንጎ ፣ ዘይቱን እና ብርቱካን ዛፍ መሃል የቅርቅሃ ወንበር ይዞ ተቀመጠ እና ቢቢሲ ራዲዮ ከፈተ፡፡ "ይሄ
ነው እንግሊዝኛ፤ ይሄን ነው ማዳመጥ ያለባችሁ አባቴ ቢቢሲ ማዳመጥ ሲቀጥል ጅኒየር ዳንሱን፤ እንዴት
ከዜማ ጋር መንቀሳቀስ እንዳለብን አሳየን፡፡ አንዳንድ ስንኞችን በቃል መያዝ ጀመርን፡፡ ስንለያይ "ሰላም ሁን ልጄ paece son" እና ሂጃለሁ ፤ወጣሁ (በቃኝ) I" ' m out የሚሉየ
ሃረጎችን ከራፕ ሙዚቃ ወሰደን መጠቀም ጀመርን፡፡ ማታ የወፎች እና የዶሮዎች ዝማሬ ይቀጥላል፡፡
ጥዋት የግጥም ደብተራችን እና ሙዚቃ ካሴቶችን በጀርባ ቦርሳችንን አንግተን ወደ ማታሩ ጆንግ ሄድን፡፡ ሰፊ ጂንስ ሱሪ በውስጥ የዳንስ ቁምጣ እና የስፖርት ቁምጣ፤ እጅጌ ሙሉ ቲ ሽርት በላይ እጅጌ ጉርድ ፤ ቲ ሸርቶች እና ማሊያዎች
እንለብስ ነበር፡፡ ሶስት ጥንድ ካልሶችን ደራርበን ቡፍ ያለ እንዲመስል እናደርግ ነበር።ሲሞቀን ልብሳችንን አውልቀን
,በትክሻ ላይ ጣል አርጎ መሄድ የጊዜው ዘናጭነት ነበር፡፡በሚቀጥለው ቀን እንመለሳለን ብለን ስላሰብን ሳንሰናበት ፤ የት እንደምንሄድ እንኳ ሳንናገር ነበር ከቤት የወጣነው፡፡ ቤታችንን
ለቀን ዳግም ላንመለስ እየሄድን እንደሆነግን አናውቅም ነበር፡፡
ገንዘብ ለመቆጠብ አስራ ስድስት ኪሎ ሜትር በእግር ለመጓዝ ወሰን፡፡ ዉብ የክረምት ወቅት ነበር፡፡ፀሃይዋም አልበረታችም፡፡እያወራን፣እየቀለድን እና እየተሯሯጥን መንገዱ ረጂም መሆኑ
ሳይስማን ተጓዝን፡፡ ወፎችን እና ዝንጀሮዎችን በአለት ደንጋይ
እየወረወርን እንበትን ነበር፡፡ ባገኘናቸው ብዙ ወንዞች ሰንዋኝ አንዱ ላይ ግን የመኪና ድምፅ ሰማን፡፡ ወንዙን በሚያቋርጠው ድልድይ ላይ መኪና ሲያልፍ ከውሃው ውጥተን በነጻ
እንዲወስደን ወደ መኪናዉ ሮጥን፡፡መድረስ ግን አልቻልነም፡፡
ስምንት ስአት አካባቢ ከአያቴ ሰፈር ካባቲ ደረስን፡፡ አያቴ ማሚ ካፓና በሚል ስም ትታወቅ ነበር፡፡ ቆንጆ ነበረች፤ ረጂም
ቁመት ሰልካካ ቆንጆ ፊት ከ ቡናማ አይን ጋር! እጇዋን ከወገቡዎ ወይም ራሷ ላይ አርጋ ትሽቀረቀራለች፡፡ እሷን ሳይ
የእናቴ ቁንጂና ከየት እንደመጣ ይገባኛል። ወንድ አያቴ ታዋቂ
አረብኛ ቋንቋ መምህር እና ባህላዊ ሐኪም ነበር። የአካባቢው ሰው
መምህር ብለው ይጠሩታል
ካባቲ ላይ ከበላን ከጠጣን በኋላ ቀጣዩን ጉዞችንን ጀመርን።አያቴ እንድናድር ፈልጋ

ነበር ነገር ግን በቀጣዩ ቀን እንደምንመለስ ነገርናት:: "ያ አባትህ እየተንከባከበህ ነው?" አለች አሳቢነትዋን በሚያሳይ ለስላሳ ድምጽ፡፡
“ለትምህርት ካልሆነ ለምንድን ነው ማታሩ ጆንግ የምትሄዱት?"
መጠየቁዋን ቀጠለች! እኛ ግን ዝም ብለን ጥያቄዋን አሳለፍን።
ከቤቷ ወጥታ ሰፈሯ መጨረሻ ድረስ ሽኘችን። በትሯን ከቀኝ ወደ ግራ እጇ አዙራ በቀኝ እጇ እያውለበለበች
ተሰናበተችን፡፡ ቀኝ እጅ የመልካም እድል ምልክት ነበር።
ከስዓታት በኋላ ማታሩ ጆንግ ደርሰን ከ ጓደኞቻችን ገብሪላ፣ ካሎኮ እና ካሊሎ ጋር ተገናኘን። ምግብ ገዝተን ከበላን
በኋላ የተሰጣኦ ውድድር መለማመጃ ቦታውን ለማየት እቅድ ያዝን።
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

#ምን_ላድርግሽ?
አንፀባራቂ አይንሽ -
እዪኝ እዪኝ ይላል ፣ እዪና ውደቁ፤
ወረርሽኙ ሳቅሽ -
ሳቁ ሳቁ ይላል ፣ በኔ ተነቃቁ::
ሸንኮራው ከንፈርሽ -
ብሉኝ ብሉኝ ይላል ፣ ግመጡኝ ግመጡኝ፤
ስም የለሽ አንገትሽ -
ሳሙኝ ሳሙኝ ይላል ፣ ምጠጡኝ ምጠጡኝ::
እንከን የለሽ ውበት - ማራኪ ስብዕና
አቅበዝባዥ ተፈጥሮ - አማላይ ቁንጂና፣
የታደልሽው የኔ
የኔ የብቻየ፧
ነይ እስኪ ልቀፍሽ
ነይ እስኪ ልሳምሽ
ልሳምሽ
ልሳምሽ
ልሳምሽ
ልሳምሽ
ብስምሽ አልጠግብሽ
ባቅፍሽም አልጠግብሽ
አትበይ ነገር - ምናባቴ ላርግሽ!??
🔘ሙሉቀን🔘
አንፀባራቂ አይንሽ -
እዪኝ እዪኝ ይላል ፣ እዪና ውደቁ፤
ወረርሽኙ ሳቅሽ -
ሳቁ ሳቁ ይላል ፣ በኔ ተነቃቁ::
ሸንኮራው ከንፈርሽ -
ብሉኝ ብሉኝ ይላል ፣ ግመጡኝ ግመጡኝ፤
ስም የለሽ አንገትሽ -
ሳሙኝ ሳሙኝ ይላል ፣ ምጠጡኝ ምጠጡኝ::
እንከን የለሽ ውበት - ማራኪ ስብዕና
አቅበዝባዥ ተፈጥሮ - አማላይ ቁንጂና፣
የታደልሽው የኔ
የኔ የብቻየ፧
ነይ እስኪ ልቀፍሽ
ነይ እስኪ ልሳምሽ
ልሳምሽ
ልሳምሽ
ልሳምሽ
ልሳምሽ
ብስምሽ አልጠግብሽ
ባቅፍሽም አልጠግብሽ
አትበይ ነገር - ምናባቴ ላርግሽ!??
🔘ሙሉቀን🔘
👍1
#ለኀጥአን_የመጣ
#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ
#ክፍል_ሁለት
#በኢስማኤል_ቤህ
#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው
ከስዓታት በኋላ ማታሩ ጆንግ ደረስን ከ ጓደኞቻችን ገብሪላ፣ ካሎኮ እና ካሊሎ ጋር ተገናኘን። ምግብ ገዝተን ከበላን
በኋላ የተሰጣኦ ውድድር መለማመጃ ቦታውን ለማየት እቅድ ያዝን። በነ ካሊድ ቤት ጠባብ ክፍል ውስጥ ትንሽየ አልጋ ላይ አራታችን በአንድ ላይ ተደራርበን አደርን፡፡ በሚቀጥለው ቀን ጅንየር፣ታሎ እና እኔ ቤት ስንቆይ ሌሎቹ ትምህርት ቤት ሄዱ። እስከ ስምንት ስዐት ይቆያሉ ሰንል ቶሎ መጡ። ቶሊ “እንዴት ቶሎ መጣቹህ ?" ብሎ ጠየቃቸው።ገብሪላ አማጺዎች ከተማችን ሞግሚሞን ላይ ጥቃት መስንዝራቸውን ከመምህራን
እንደሰማ ነገረን :: ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተዘጋ ሲነግረን ደነገጥን እየሰራን የነበረውን አቆምን።
አማጺዎቹ ከስዓት በኋላ የማዕድን ቦታዎችን እንዳጠቁ ከመምህራን ሰማን። የጥይት እሩምታ ህዝቡን ወደ ተለያዩ አቅጣጫ በተነው:: አባቶች ስራቸውን ጥለው ቤታቸውን ለመጠበቅ መጡ። ቤተሰቦቻቸው የት እንደሄዱ አያውቁም።
እናቶች ልጆቻቸውን ፍለጋ እያለቀሱ ወደ ትምህርት ቤት፣ወንዞች እና የውሃ ጉድጓዶች ሮጡ። ልጆች ደግሞ በየ መንገዱ ቤተሰቦቻቸውን ይፈልጋሉ። ተኩሱ ሲባባስ ሰዎች መፈላለጉን
ትተው እግሬ አውጭኝ ሆነ! ከተማውን ለቀው ወጡ።
"መምህራን ይሄ ከተማ ቀጣይ እንደሆነ ነግረውኛል" አለ ገብሪላ ከተቀመጠበት እየተነሳ። ጅንየር ፣ታሉ እና እኔ ቦርሳችንን ይዘን ከሌሎች ጓደኞቻችን ጋር ወደ ባህር ዳርቻ ሄድን፡፡
ብዙ ሰዎች ከማዕድን ቦታዎች ወደ ባህር ዳርቻ ይተማሉ።አንዳንዶቹ የምናውቃቸው ሰዎች ነበሩ ነገር ግን ቤተሰቦቻችን
የት እንዳሉ ሊነግሩን አልቻሉም፡፡ ተኩሱ በጣም ድንገተኛ እና አስደንጋጭ ስለነበር ሁሉም የአካባቢው ሰው በድንገት እንደሽሽ ነበር ነገሩን።
ለሶስት ስዓታት ያህል ቤተሰቦቻችን ይመጣሉ ወይም ያሉበትን የሚያውቅ ሰው ይመጣል ብለን በጭንቀት በወንዙ
ዳርቻ ላይ ቆየን። ነገር ግን ምንም ወሬ የለም፡፡ የውሃ ሽታ ሆኑብን! ቀኑ አንዳች ጉድ ያላየ የተለመደ ቀን ይመስላል።
ፀሐይዋ በነጩ ጉም ላይ ትንሳፈፋለች፣ ወፎች በዛፎች ጣሪያ ላይ ሁነው ይዘምራሉ ዛፎችም በለሆሳስ ንፋስ ይወዛወዛሉ።
ማመን አልቻልኩም! ጦርነቱ በዚህ ፍጥነት ቤታችን ይደርሳል ብየ አልገመትኩም:: በፍጽም! ትናንት ከቤት ስንወጣ አማጺዎቹ ከኛ ቅርብ መሆናቸውን የሚያሳይ አንድም ምልክት
አልነበረም::
"ምንድን ነው የምናድርገው?" ሲል ገብሪላ ጠየቀ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ሁላችንም ዝም አልን። በኋላ ቶሊ "ወደ ቤት እንሂድ፤ ሳይመሽ ቤተሰቦቻችን እንፈልጋቸው" አለ፡፡ ጅንየር እና እኔ ራሳችንን በመነቅነቅ ስምምነታችንን ገለጸን፡፡
ከሶስት ቀናት በፊት አባቴን በዝግታ እየተራመደ ከስራ ሲመለስ አይቸዋልሁ:: ባርኔጣውን በእጆቹ መሐል ይዟል ፤
ረጂም ፊቱ በጋለ ፅሐይ ተመቶ በላብ ተጠምቋል:: በቤቱ ደጃፍ ላይ ነበርኩ:: ካየሁት ቆይቻልሁ። 'ምስጋና ለእንጀራ እናቴ በእኔና በሱ መሃል የነበረውን ግንኙነት አበላሽታዋለች። ያን ቀን
ግን አባቴ ወደ ቤቱ ደረጃ ሲደርስ ፈገግ ብሎ አየኝ። ፊቴን፣ መላ ሰውነቴን አትኩሮ ተመለከተ። የእንጀራ እናቴ ስትመጣ ፊቱን
አዞረ፤ ከዛ ወደ እሷ ተመላከተ። ትንሽ ቆይቶ ወደ ውስጥ ገባ። እንባየን ቋጥሬ ወደ ጁንየር ሮጥኩ። ወደ እናታችን ቤት
ለመሄድ ዝግጅት ላይ ነበርን። በፊት አባታችን የትምህርት ክፍያ በሚከፍልን ጊዜ እናታችንን ከባዕላት በተጨማሪ በየሳምንቱ እንጠይቃት ነበር፡፡ አሁን አባታችን አልከፍልም ስላለ ትምህርት
ቤት የለም ስለዚህ በየሁለት እና ሶስት ቀናት እንጠይቃታለን::
ያን ቀን ከስዓት በኋላ እናታችንን አስቤዛ እየገዛች ገበያ ቦታ አገኘናት:: ደክሟት ፊቷ ከስሉ ዳምኖ ነበር። እኛን ስታየን
ስታቅፈን ግን በቅጸበት ፊቷ በራ። ታናሽ ወንድማችን ኢብራሂም ትምህርት ቤት እንደሆነ እና ስንመለስ እንደምናገኘው
ነገረችን። እጃችንን ይዛ ወደ
ኢብራሂም ትምህርት ቤት መራመድ ጀመርን፡፡
እናታችንን ፊትዋን ወደ እኛ አዙራ "ይቅርታ ልጆች በቂ ገንዝብ ስለሌኝ ነው እናንተን ወደ ትምህርት ቤት ያልመለስኳችሁ። እየጣርኩ ነው።” አለች፡፡ ከዛ ትንሽ ቆይታ
”አባታችሁ እንዴት ነው?” ስትል ጠየቀች::
"ደህና ይመስላል፡፡ ዛሬ አይቸው ነበር።" አልኩ
ጅንየር ምንም አልተናገረም:: ዝም አለ።
እናቴ ጅንየርን ትኩር ብላ አይን አይኑን እያየች” አባትህ ጥሩ ሰው ነው፤ በጣም ይወድሃል። መጥፎ እንጀራ እናቶች
ስለሚገጥሙት ነው” አለች::
ትምህርት ቤት ስንደርስ ትንሹ ወንድሜ ኳስ እየተጫወተ ነበር፡፡ ስምንት አመቱ ነው:: ልክ ሲያየን እየሮጠ መጥቶ ተጠመጠብን፡፡ በቁመት በልጦኝ እንደሆነ ለማወቅ ከእኔ ጋር ለማነጻጸር ሞከረ፡፡ እናቴ ሳቀች:: የትንሹ ወንድሜ ትንሽ ክብ
ፊት በራች፡፡ ሁላችንም ወደ ቤት ሄድን። ትንሹ ወንድሜ እጁን ይዥ ስራመድ ስለ ትምህርት ቤት አወራኝ፤ ማታ ደግሞ
ኳስ ተጫወትን፡፡ እናቴ ሁሉን ነገሯዋን ለኢብራሂም ሰጥታለች፣
ብቻዋን እሱን ትንከባከባለች ። ኢብራሂም አንዳንዴ ስለ አባቱ እንደሚጠይቅ ነገረችን፡፡ አባቱን እንዲያይ የተወሰኑ ቀናቶች ወስዳዋለች። ሁለቱ ሲገናኙ አባቱ ኢብራሂምን ሲያቅፈው ስታይ
ግን ታለቅሳለች። ሁለቱም በጣም ደስተኛ ይሆናሉ ትላለች፡፡በሃሳብ ትወሰዳለች::
ከዛ ጥየቃ ሁለት ቀናት በኋላ ከቤት ወጣን። አሁን ማታሩ ጆንግ ባህር ዳርቻ ላይ ቁመናል። አባቴ ባርኔጣውን በእጆቹ ይዞ ከስራ በሩጫ ሲመለስ በአይነ ሕሊናየ ይታየኛል። እናቴም ስታለቅስ ወደ ትንሽ ወንድሜ ትምህርት ቤት ስትሮጥ በአይነ ህሊናየ ተመላለስ፡ የፍርሃት ስሜት ተቆጣጠረኝ፡፡
ጅንየር፣ታሎ እና እኔ ወደ ጀልባ ዘለን ገባን ፤ በድንገት ጀልባው ሲንቀሳቀስ ለጓደኞቻችን እጆቻችንን አውለበለብን።
ጀልባዋ ከማታሩ ጆንግ ይዛን ወጣች:: በወንዙ ሌላኛው ጫፍ ደርሰን መሬት ስንረግጥ ብዙ ብዙ ሰዎች ሸሽተው እየመጡ ነበር፡፡ መጓዝ ስንጀምር ነጠላ ጫማ ራሱዋ ላይ የተሽከመች ሴትዮ እኛን ሳታየን መናገር ጀመረች" የምትሄድበት ቦታ ብዙ ደም ፈሶበታል። መልካሙ መንፈስ እንኳ ሸሺቷል ”እያለች
አልፋን ሄደች:: በወንዙ ዳር ባለው ጫካ የብዙ ሴቶች ደምጽ ይሰማል። ” ጌታ ሆይ እርዳን” የልጆቻቸውን ስሞች ይጠራሉ፡
የሱፍ፣ጃቡ፣ ፎዳይ..." ልጆች ብቻቸውን ሲጓዙ ፤ በተቀደደ ልብስ አንዳንዶቹ ያለ ውስጥ ሱሪ ”እናቴ” ፣ ”አባቴ” እያሉ
ሲጣሩ ፤ ውሾችም በህዝቡ መሃል ሲሮጡ ፤ ባለቤታቸውን ሲፈልጉ ስናይ ፈራን :: የደም ስሬ ተገታተረ፡፡
ከስድስት ኪሎ ሜትር በኋላ ከአያቴ ሰፈር ካባቲ ደረስን፡፡
ኦና ሁኗል። ከሰፈሩ እስከ ማዶ ያለው ጫካ የተዘረጋው የሰዎች ዱካ ብቻ ይታያል።
ምሽቱ ሲቃረብ ግን ብዙ ሰዎች ከማዕድን ቦታ መምጣት ጀመሩ። የጠንቋዮች ፣ በጉዞ ወላጆቻቸውን በመፈለግ የደከሙ
ና የራባቸው ልጆች ለቅሶ የምሽት ወፎች እና የዶሮዎች ዝማሬ የተካው ይመስላል። በአያቴ ቤት ደጃፍ ተቀምጠን መጠበቅ ማዳመጥ ጀመርን።
ትክክል ነን ግን፧ ወደ ማግቦ መመለስ ጥሩ ሃሳብ ነው ትላላቹህ?” ሲል ጅንየር ጠየቀን። ከመመለሳችን በፊት ግን
ቮልስዋግን ጩህት ሲሰማ ሁሉም ሰው ወደ ጫካው መሮጥ ጀመሩ። እኛም መሮጥ ጀመርን ብዙም ግን አልራቅንም። ልቤ መታ፤ ትንፋሼ ጨመረ፡፡ መኪናው አያቴ ቤት ፊት ለ ፊት ቆመ። አሽከርካሪው አልታጠቀም። ከመኪናው ወጥቶ ደም
መትፋት ጀመረ። እጁ ደም በደም ሁኗል። መትፋቱን ሲያቆም ማልቀስ ጀመረ። አዋቂ ሰው እንደ ህጻን ልጅ ሲያለቅስ
ለመጀመሪያ ጊዜ

👍2
ነው ማየው፤ ልቤ ተነካ። አንዲት ሴት እጆችዋን ትክሻው ላይ አርጋ እንዲነሳ ለመነችው:: ተነስቶ ወደ
መኪናው ሄደ። መኪናውን በሃይል ሲከፍት ሴቲቱን መቷት ወደቀች። በጆሮዋ ደም ፈሰሰ።
በመኪናው ጀርባ የሶስት ሰዎች አስክሬን ይታያል፤ የሁለት ሴቶች እና አንድ ወንድ ልጅ ደማቸው የመኪናው ወንበሮች
እና መኪናው ጣራ ላይ ይታያል። ፊቴን ለማዞር ብፈልግም አልቻልኩም፡፡ እግሬ አና መላ ሰውነቴ ደነዘዘ። በኋላ ሰውየው
ቤተሰቦቹን ይዞ ለማምለጥ ሲሞክር
እንደተተኮሰባቸው ሰማን:: ሁሉም ቤተሰቦቹ ሙተዋል። ትንሽ ያጽናናው ያቀፈችው ፣አሁን አብራው የምታለቅሰው ሴትዮዋ ቢያንስ መቅበር መቻሉም እደለኛ እንደሆነ ስትነግረው ነበር፡መቃብራቸውን ታውቃለህ አለችው:: ስለጦርነት ከእኛ የተሻለ የምታውቅ ይመስላል
ንፋሱ ረገብ ያለ ይመስላል። ቀኑ ለምሽቱ እጅ ሰጥቷል። ፅሐይ ስትጠልቅ ሰዎች ወደ ሰፈር መምጣት ጀመሩ፡፡ አንድ አባት የሞተ ልጁን ተሸክሞ መጣ፡፡ በህይወት ያለ መስሎት ነበር። አባትየው በልጁ ደም ተሸፍኗል፡፡ ደጋግሞ "ሆስፒታል አደርስሃለሁ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል” ይላል፡፡ ቀጥሎ በጥይት የተበሳሱ ወንዶች እና ሴቶች መጡ፡፡ አንዳንዶቹ ሰዎች እንደ ቆሰሉ እንኳ አያውቁም ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ራሳቸውን
ሳቱ ሌሎቹ ደግሞ አስታወኩ አቅለሸለሸኝ ራሴም ዞረብኝ፡፡መሬት ሲሽከረከር ፤ የሰዎች ድምጸ ሩቅ ሁኖ ይሰማኛል።

#ነገረ_ጦቢያ
አስራ ሶስት ወር ብርሐን - አስራ ሶስት ወር ፀሐይ
አረንጓዴ ምድር - ሰማያዊ ሰማይ፤
አዕላፍ ክዋክብት - አማላይ ጨረቃ
በተፈጥሮ ውበት - የምትታይ ደምቃ....
አገሬ ናት እሷ-
ተፈጥሮ ያሳመራት
ታሪክ ያገነናት፡፡
ከ13 ወር ፀሐይ ፣
የ13 ወር ሌሊት ገዝፎ ሚታይባት
የቀኗ ብርሐን ፣
በሌሊት ጨለማ የተሸፈነባት፣
ሰማያዊው ሰማይ ፣
በአመዳም ደመና የተጋረደባት
አረንጓዴ ምድሯ ፣
በስንፍና አረም የደራረቀባት
አገሬ ናት እሷ-
ሰዎች የበደሏት
ትውልድ ያከሰራት።
🔘በሙሉቀን🔘
አስራ ሶስት ወር ብርሐን - አስራ ሶስት ወር ፀሐይ
አረንጓዴ ምድር - ሰማያዊ ሰማይ፤
አዕላፍ ክዋክብት - አማላይ ጨረቃ
በተፈጥሮ ውበት - የምትታይ ደምቃ....
አገሬ ናት እሷ-
ተፈጥሮ ያሳመራት
ታሪክ ያገነናት፡፡
ከ13 ወር ፀሐይ ፣
የ13 ወር ሌሊት ገዝፎ ሚታይባት
የቀኗ ብርሐን ፣
በሌሊት ጨለማ የተሸፈነባት፣
ሰማያዊው ሰማይ ፣
በአመዳም ደመና የተጋረደባት
አረንጓዴ ምድሯ ፣
በስንፍና አረም የደራረቀባት
አገሬ ናት እሷ-
ሰዎች የበደሏት
ትውልድ ያከሰራት።
🔘በሙሉቀን🔘
#ሰው_እና_ዘመን
የሰው ልጅ እንደ ዘመን ነው
ዕድሜውን የሚያሳልፈው፡፡
አንዴ በጋ - አንዴ ክረምት
አንዴ ብርዳም - አንዴ ሙቀት፡፡
አንዳንዴ አይኑ ይረጥባል
አንዳንዴ- ጥርሱ ያብባል፤
አንዳንዱ- ወዙ ይረግፋል
አንዳንዴ- ፊቱ ይፈካል፡፡
የትም ይሁን
ማንም ይሁን
የሰው ልጅ እንደ ዘመን ነው - ባንድ ባህሪ የማይዘልቅ
እንባና ሳቅ የሚያጅቡት - ባህሪው የሚፈራረቅ፡፡
🔘ሙሉቀን🔘
የሰው ልጅ እንደ ዘመን ነው
ዕድሜውን የሚያሳልፈው፡፡
አንዴ በጋ - አንዴ ክረምት
አንዴ ብርዳም - አንዴ ሙቀት፡፡
አንዳንዴ አይኑ ይረጥባል
አንዳንዴ- ጥርሱ ያብባል፤
አንዳንዱ- ወዙ ይረግፋል
አንዳንዴ- ፊቱ ይፈካል፡፡
የትም ይሁን
ማንም ይሁን
የሰው ልጅ እንደ ዘመን ነው - ባንድ ባህሪ የማይዘልቅ
እንባና ሳቅ የሚያጅቡት - ባህሪው የሚፈራረቅ፡፡
🔘ሙሉቀን🔘
👍1
#ለኀጥአን_የመጣ
#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ
#ክፍል_ሶስት
#በኢስማኤል_ቤህ
#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው
የምታውቅ ይመስላል።
..ቀጥሎ በጥይት የተበሳሱ ወንዶች እና
ሴቶች መጡ፡፡ አንዳንዶቹ ሰዎች እንደ ቆሰሉ እንኳ አያውቁም ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ራሳቸውን ሳቱ ሌሎቹ ደግሞ አስታወኩ። አቅለሸለሸኝ ራሴም ዞረብኝ መሬት ሲሽከረከር ፤ የሰዎች ድምጸ ሩቅ ሁኖ ይሰማኛል።
በቀኑ መጨረሻ ያየነው ሌላው ጉዳት በጀርባዋ ህጻን ልጅ ያዘለች አንዲት ሴት ናት። ደም በልብሷ ከላይ እስከ ታች
ወርዶ በጀርባዋ መስመር ሰርቷል። ልጆዋ በጥይት ተመቶ ሙቷል። ቁማ ልጅዋን አውርዳ አስቀመጠቻት። በኋላ ወደ
ልጅዋ ቀርባ ወዘወዘቻት። በብዙ ስቃይ እና ድንጋጤ ውስጥ ስለነበረች አለቀሰች።
ጅኒየር፣ታሎ እና እኔ ተያየን ወደ ማታሩ ጆንግ መመለስ እንዳለብን ገባን። ማግቦ ከእንግዲህ ቤታችን እንደማይሆን ወላጆቻችንንም ከዛ ሊሆኑ እንደማይችሉ
ተገነዘብን፡፡ አንዳንድ የቆሰሉ ሰዎች ካባቲ ቀጣይ የአማጺዎች መዳረሻ እንደሚሆን ይናገራሉ። አማጺዎች እንዲያገኙን
አንፈልግም:: በደንብ መራመድ እንኳ ማይችሉ ሰዎች ከካባቲ ለመውጣት የቻሉትን ሁሉ እያረጉ ነው:: ወደ ማታሩ ጆንግ ስንመለስ የዛች ሴትዮዎ እና የልጅዋ ሁኔታ አእምሮየን አስጨነቅው:: ጉዞው ብዙም አልተሰማኝም። ውሃ ጠምቶኝ ጠጥቼ እንኳ ምንም ጥሩ ስሜት ሊሰማኝ አልቻለም፡፡ ያቺ ሴት
ወደመጣችበት መመለስ አልፈልግም ፤ ሁሉም ነገር እንደጠፋ የልጅዋ አይን ይናገራል።
"አንተ ነጌትቭ አስራ ዘጠኝ አመትህ ነው” ይለኝ ነበር ባባ።አባቴ ከ ነጻነት በኋላ በ1961 የሴራሊዎን ሕይወት ምን
እንደምትመስል ስጠይቀው ሁሌም መልሱ ይሄ ነበር፡፡ ምኑ ይገባሃል የሚል ምፀት ያለው መልስ! ከ1808 ዓ/ም ጀምሮ ሴራሊዮን የብሪታንያ ግዛት ነበረች::
ሚልተን ማርጋይ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር በመሆን የሴራሊዮንን ህዝብ ከዚህ አለም በሞት እስከ አረፈበት 1964 ድረስ ሃገሪቱን መርቷል::
ወንድሙ አልበርት ማርጋይ እሱን ተከትሎ እስከ 1967 ማለትም በሲያካ ስቲቨን በምርጫ እስከ ተሸነፍበት ደረስ መምራት ቻለ፡፡ ሲያካ ስቲቨን ወዲያው መፈንቅለ መንግስት ቢያጋጥመውም በ1968 እንደገና ወደ ስልጣን ተመለሰ። ከብዙ
አመታት በኋላ ሃገሪቱ የአንድ ፓርቲ ብቻ ሃገር እንደሆነች አወጀ:: የሁሉም ህዝቦች ኮንግረስም የሃገሪቱ ብቸኛው ህጋዊ
ፓርቲ ሆነ። የ”ፖለቲካው መበላሸት የሚጀመረው ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው ይል ነበር አባቴ።ስለዚህ ጦርነቱ ምን እያለ ይሆን?! አዋቂዎች አቢዮታዊ ጦርነት እንደሆነ እና ህዝቡን ከሙሰኛ
መንግስት ነጻ ለማውጣት የ ሚደረግ ጦርነት እንደሆነ ሲያወሩ ሰምቻለሁ፡፡ የትኛው የነጻነት እንቅስቃሴ ነው ንጹሃንን ህጻናትን የሚገድል? ይህንን የሚመልስ ማንም የለም::ባየሁት ነገር ልቤን ይከብድዋል ያስጨንቀኛል!
የሚታየውን ተራራ ዱሩን ሁሉ ፈራሁ።
በጣም ከመሽ ማታሩ ጆንግ ደረስኩ፡፡ ጅኒየር ና ታሎ ያየነው አስከፊና አስቃቂ ክስተት በሙሉ ለጓደኞቻችንን ነገሩዋቸው። እኔ ግን ያየሁትን ማመን ስላልቻልኩ ዝምታን መረጥኩ። ማታ ማንቀላፋት ስጀምር በህልሜ ጎኔን በጥይት ተመትቼ ቆስዬ ሰዋች ምንም ሳይረዱኝ የራሳቸውን ህይወት ለማትረፍ አልፈውኝ ሲሮጡ አየሁ።
ተንፏቅቄ ወደ ዱር ለመግባት ስሞክር ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ሰው ራሴ ላይ መሳሪያ ደቅኗል። ተኮሰ፡፡ባትቼ ከእንቅልፌ ተነሳሁ፡፡በጥርጣሬ ጎኔን ነካሁ። ፈራሁ! ህልም እና እውነታን መለየት ስላቃተኝ ፈራሁ።
ሁሌም ጥዋት ጎህ ሲቀድ ስለ ቤተሰቦቻችን ወሬ ካለ ለመስማት ወደ ማታሩ ጆንግ ባህር ዳርቻ እንወርዳለን።
ከሳምንት በኋላ ወደ ማታሩ ጆንግ የሚመጡ ስደተኞች ቁጥር ቀነሰ። ስለ ቤተሰቦቻችን ምንም ወሬ የለም። ድጋሚ የውሃ ሽታ ሆኑብን! የመንግስት ወታደሮች በማታሩ ጆንግ ተሰማርተው ኬላዎችን በባህር ዳርቻ እና በከተማው ዋና ዋና አቅጣጫዎች አቁመዋል::
ወታደሮቹ ከባድ መሳሪያዎችን አዘጋጅተው አማጺዎቹን ለመምታት ይጠባበቃሉ። አማጺዎቹ በባህር ዳርቻው በኩል እንደሚመጡ ገምተዋል። ህዝቡ በጊዜ እንዲገባ የስዓት እላፊ ከምሽቱ አንድ ስዐት በኋላ መንግስት አውጇል። ከባድ ምሽት ነበር፤ መተኛት አልቻልንም:: ሁላችንም በጊዜ ተሰባሰብን ከበን
ማውራት ጀመርን፡፡
ይሄ ነገር፦ ይሄ እብደት መቼ ይሆን የሚያበቃው? "በጥቂት ጊዜ ውስጥ የሚያበቃም አይመስለኝም፡፡" አለ ጅኒ የር ”ምን አልባት ለአንድ ና ሁለት ወር ይቆይ ይሆናል።” አለ ታሎ ጣሪያ ጣሪያ እያየ።
ገብሪላ ደግሞ ወታደሮች አመጺዎችን ከማዕድን ቦታ ለማባረር እየገሰገሱ እንደሆነ ሰምቻለሁ አለ። ጦርነቱ ወደ
የፍጻሜው ምዕራፍ ላይ እንዳለ እና ከሶስት ወር በላይ እንደማይቆይ ተማመን፡፡
ጅኒየር፣ታሎ እና እኔ ነገሮችን ለመርሳት ራፕ ሙዚቃ ማደመጥ ጀመርን፡፡ የ ሙዚቃ ካሴቶች እና ልብሶቻችንን ብቻ
ይዘን ነበር ከቤት የወጣነው:: ከቤት ደጃፍ ላይ ተቀምጨ Now That We Found Love ” ፍቅርን አሁን አገኘነው” የሚለውን የሄንሪ ዲ እና ዘ ቦይዝ ሳዳምጥ ትዝ አለኝ ። አይኔን ጨፈንኩ። ካባቲ ያየሁዋቸው አሰቃቂ ነገሮች ሁሉ
በአዕምሮዬ መጡ። ምስሎቹን ከአዕምሮዬ ለማውጣት የድሮውን
በሰላሙን ጊዜ የነበረችውን ካባቲ ማሰብ ጀመርኩ።
በአያቴ መንደር ባንድ በኩል ጥቅጥቅ ያለ ደን ሲኖር በሌላው ደግሞ የቡና እርሻ ነበር፡፡ በጫካው በኩል የሚመጣው ወንዝ ሰፈሩ ዳር፣ በወይራ ዛፎች አደርጎ ወደ ረግረጉ ይገባል። ከረግረጉ በላይ የሙዝ ማሳው እስከዛኛው አድማስ ይታያል። ብዙ ሰው ከቤቱ ጀርባ የማንጎ ዛፎች አለው።
ጥዋት ከጫካው በስተጀርባ ፅሐይ ትወጣለች። መጀመሪያ ጨረሯ በቅጠሎች መሃል ያልፋል። ከዛ አውራ ደሮ ይጮሃል፤ ድንቢጥ ወፎች በዝማሬ አዲስ ቀንን ሲያውጁ ወርቃማ ፅሐይ
ከጫካው ራስ ላይ ጉብ ብላ ትታያለች። ምሽት ላይ ዝንጀሮዎች ወደ ማደሪያቸው ለመመለስ ከዛፍ ዛፍ ሲዘሉ ይታያል። በቡናው ማሳ ደሮዎች ጫጩቶቻቸውን ከጭልፊት ይሸሽጋሉ። ከማሳው
ወዲያ ማዶ ደግሞ የወይን ዛፎች በንፋስ ሲወዛወዙ ይታያል።
አንዳንዴ የወይን ፍሬ ለቃሚ ዛፎች ላይ ወጥቶ ይታያል።
ምሽቱ በዛፎች ውዝዋዜ ድምጽ ( ቀ ቀ ቀ ቀ ) እና በሩዝ መውቀጥ ድምጽ (ድው ዱ ዱ) ታጂቦ ይገባደዳል። ድምጹ በመንደሩ ያስተጋባል። ወፎች በጥንቃቄ እንዲበሩ፣ ዶሮዎች፣እንቁራሪቶች ጉጉቶችም ወደ ማደሪያቸው እንዲመለሱ ያደርጋል። የመንደር ሰዎች ፋኖስ ወይም የተቀጣጣለ እንጨት እያበሩ ከ እርሻ ማሳቸው ይመለሳሉ፡፡
"እንደ ጨረቃ ለመሆን እንትጋ” ይላል አንድ ሽማግሌ ሰውየ ውሃ ሲቀዳ፣ ለአደን ሲሄድ ወይም የወይን ፍሬ ዛፎቹ ላይ ሲቆርጥ። አንድ ቀን አያቴን ምን ማለት እንደሆነ ጠየኳት። አባባሉ ሰዎች ሁሌም ጥሩ እንዲሆኑ እና ለሌሎች መልካም እንዲሆኑ ያስታውሳል። ስዎች የፅሐይን ግለት ፤ ከባድ ዝናብን እና ብርድን ያማርራሉ። ነገር ግን ጨረቃ ስትወጣ
ማንም አያጉረመርምም፡፡ ሁሉም ደስተኛ ነው፤ እንደየራሳቸው ሁኔታ ጨረቃን ያደንቃሉ። ህጻናት ጥላቸውን ያያሉ፤ ሰዎች ተሰባስበው ይጫወታሉ ለሊቱን በጭፈራ ያሳልፋሉ። ጨረቃዋ
ስታበራ ደስታ ይሆናል። ለዛ ነው እንደ ጨረቃ ለመሆን የምንተጋው።
።።
አየሩ ደም ደም እና የተቃጠለ ስጋ በሚሸትበት ከተማ መሐል የዛገ ካሬታ እየገፋሁ ነበር። : ንፋሱ የሲቃ ድምጾችን ያመጣል::
ተመሰቃቅለው በወደቁ ሬሳዎች መካከል ሳልፍ እጃቸውን እና እግራቸውን ያጡ ሰዎች፤ ሆዳቸው ውስጥ ቅልሃ ገብቶ
አንጀታቸው የተዘረገፈ እና በአፍንጫቸው በጆሮቻቸው ደም የፈሰሳቸውን አየሁ። በራሪዎች

👍2🥰1
በፈንጠዝያ ከደም ዥረቱ ላይ
አርፈው ደሙን ጠጥተው ይሞታሉ ::
እግሮቼን ለማየት ወደ መሬት አቀረቀርኩ። ካልሴ ከ ቁምጣ ሱሬየ በሚወርደው ደም ተጨማልቋል። ነገር ግን ምንም አይነት
ህመም አይሰማኝም፤ መቁሰሌን ማመን አልቻልኩም። የAK 47 ሙቀት ጀርባየ ላይ ይሰማኛል። መቼ እንደተኮስኩት እንኳ
አላስታውስም። መርፌ ጭንቅላቴ ላይ እንደተሰካ ይሰማኛል። የምገፋው ካሬታ በነጭ አንሶላ የተጠቀለለ ሬሳ ይዟል። ይህን ሬሳ ለምን ወደ መቃብር ቦታ እንደምወስደው አላውቅም::
መቃብር ቦታ ስደርስ ሬሳውን ከካሬተው ለማንሳት ታገልኩ።በእጆቼ ተሸክሜ የምቀብርበትን ቦታ መመልከት ጀመርኩ።
ሰውነቴ ህመም ተሰማው። በእያንዳንዱ እርምጃየ ስቃይ ከእግር ጥፍሬ እስከ ጀርባየ ይሰማኛል። ሬሳውን ወደ መሬት አውርጄ ልባሱን ማውለቅ ጀመርኩ። ከእግሩ ጀመሬ እስከ አንገቱ ፈታሁ።
ብዙ ቦታ ላይ ተመቷል፡፡ ማንቁርቱ ወደ ጉሮሮው ጀርባ ገብቷል፡፡ ፊቱ ላይ ያለውን ልብስ ስፈታ ግን የራሴን ፊት አየሁ።
ከህልሜ አለም እስክነቃ ድረስ የእንጨት ወንበር ላይ ለተወሰነ ደቂቃ ተንጋለልኩ።
ወገቤ ላይ ይወጋኛል። በኒዉ ዮርክ
ስለጀመርኩት ስለ አዲሱ ህይወቴ ለማሰብ ሞከርኩ። አዕምሮየ
አትላንቲክን አቋርጦ ወደ ሴራሊዮን ተጓዘ፡፡ AK 47 ተሽክሜ ከታዳጊ ወታደሮች እና ጥቂት አዋቂዎች ጋር በቡና እርሻ መሃል ሳልፍ ትዝ አለኝ። ምግብ እና ጥይት የሚገኝበትን ትንሽ ከተማ ለማጥቃት ዝግጅት ላይ ነበርን፡፡
የቡና እርሻውን እንዳለፍን ከሌላ የጦር ቡድን ጋር ድንገት ተገናኘን፡፡ ተኩስ ተጀመረ::
ሁሉም ሰው እስከሚወድቅ ድረስ ተኮስን፡፡ እንደ እኛ ልጆች ቢኖሩም አላዘንላቸወም፡፡ ገደልናቸው፡፡ ጥይቶቻቸውን ወሰድን፣ የያዙትንም የበሰለ ምግብ በላን።ከተቀመጥኩብት ወለል ራሴን በውሃ በተነከረ ፎጣ ጠቅልየ
ተነሳሁ። እንቅልፍ እንዳይወስደኝ ፈራሁ። ነቅቼ መቆየትም መጥፎ ትዝታ ቀሰቀሰብኝ፡፡ አንዳንዴ ይሄን ታሪኬን ሙሉ ለሙሉ መርሳት እፈልጋለሁ። ይሄ ታሪኬ፤ በጣም ወሳኝ የህይወቴ ክፍል እና
የዛሬው ማንነቴ እንደሆነ ግን አውቃለሁ። አሁን አሁን በሶስት አለም እንደምኖር ይሰማኛል። በህልሜ፣ በዛሬ አዲስ ህይወቴና በትናንትናው ትዝታ::

#የወንበር_ፍቅር
ስንት ወንበር ክፍት እያለ - ለሚያስብ ሰው የሚስማማ
ለሰውነት ማይጎረብጥ - ለህሊናም የማይገማ፤
አንድ ወንበር ላይ ሙጭጭ ብለን - ለመቀመጥ ስንጋፋ
ሰው በሰው ላይ ተመርኩዞ - ቦታ እያለ ምቾት ጠፋ።
🔘ሙሉቀን🔘
ስንት ወንበር ክፍት እያለ - ለሚያስብ ሰው የሚስማማ
ለሰውነት ማይጎረብጥ - ለህሊናም የማይገማ፤
አንድ ወንበር ላይ ሙጭጭ ብለን - ለመቀመጥ ስንጋፋ
ሰው በሰው ላይ ተመርኩዞ - ቦታ እያለ ምቾት ጠፋ።
🔘ሙሉቀን🔘
#ለኀጥአን_የመጣ
#ክፍል_አራት
#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ
#በኢስማኤል_ቤህ
#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው
እንደርስበታለን ብለን ከገመትነው ስዓት በፊት ማታሩ ጆንግ ደረሰን፡፡ ስለ ቤተሰቦቻችን ምንም ዜና የለም። በተስፋ ከመጠበቅ እና ደህንነታቸውን ከመመኘት ውጪ ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም::
አማጺዎች ከ ማታሩ ጆንግ ሃያ ኪሎ ሜትር እና ከዛ በላይ በምትርቀው ሱምብያ ከተማ መሰፈራቸውን ሰማን። ቀጥሎ አማጺዎች ደብዳቤ እንደላኩና ደብዳቤው የነሱም መምጣት፤ ስለ
እኛ እየታገሉ እንደሆነ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚፈልጉ ያትታል። መልዕክተኛው ወጣት ነው፡፡ ሰውነቱ ላይ የአማጺዎችን ስም እና አጸርሆተ ቃል ማለትም (አአግ
አብዮታዊ የአንድነት ግንባርን ተነቅሷል። ከአውራ ጣቱ ውጪ ሁሉንም ጣቶቹን ቆርጠውበታል። አውራ ጣት በብዙ ሰወች
የተለመደ የፍቅር ምልክት ነበር።
መልዕክቱ እንደደረስ ሰዎች ወደ ጫካ መሸሸግ ጀመሩ። የካሊሎ ቤተሰብ ግን እንድንቆይ እና ስንቅ ይዘን እነሱን
እንድንከተል ጠየቁን። ቆየን፡፡
ያ ምሽት በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የከተማን ህይወት የሚሰጠው የሰዎች መኖር እና መንፈሳቸው እንደሆነ ተረዳሁ። የሰዎች አለመኖር ከተማውን አስፈሪ አደረገው። ድቅድቅ ጨለማ እና ከባድ ጸጥታ! የዶሮዎች እና የወፎች ዝማሬ
እንኳ የለም። ጨለማ ፈጥኖ መጣ፤ ጨረቃም የለችም። አየሩ ከብዷል፡፡ ተፈጥሮ ራሷ የሚመጣውን የፈራች ትመስላለች።
ሰዎች ለሳምንት ያህል ተሸሸጉ። አማጺዎች ግን አልመጡም።በኋላ ሌላ መልዕክተኛ ላኩ፡፡ መልዕክተኛው ታዋቂ የካቶሊክ ካህነ ነበር፡፡ ከማስፈራራት ውጪ ካህኑን ምንም አላደረጉትም።
ቃሉን ተቀብሎ ህዝቡ ወደ ጫካ ተመልሶ ገባ። አስር ቀናት አለፉ አማጺዎች ግን አልመጡም፡፡ ነዋሪው ወደ ከተማ መመለስ ጀመረ። ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ፤ ሰዎች ወደ ዕለት ተዕለት
ኑሯቸው ተመለሱ፡፡ አምስት ቀናት በሰላም አለፉ፡፡
በመጨረሻ አማጺዎች ሲመጡ ቀላል የተኩስ ድምጽ ሰማን፡፡
ጅኒ የር፣ታሉ፣ ካሎኮ፣ ገብሬላ፣ ካሊሎ እና እኔ ቤት ውስጥ ነበረን
"ሰማቹህ?” ብለው ጠየቁ። ወታደሮች ናቸው የተኮሱት ወይስ ሌላ አካል እያልን በማሰብ ደርቀን ቆምን።
ከደቂቃዎች በኋላ ሶስት ጊዜ ተተኮሰ። አሁን ሁላችንም ፈራን።ከተማው ጸጥ ረጭ አለ። ተኩሱ ሲቀጥል። ሁሉም ተደናገጠ።በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ሰዎች መጮህ እና ወደ ተለያዩ
አቅጣጫዎች መሮጥ ጀመሩ። ሰዎች ተገፋፉ፣ አንዱ በአንዱ ላይ ወደቀ የወደቁ ሰዎችን ረግጦ ያልፋል። እናቶች ልጆቻቸውን አጡ፤ ቤተሰብ ተለያየ፤ የከተማው ነዋሪዎች ለዘመናት
የለፉበትን ጥሪት ትተው ሮጡ። ልቤ በፍጥነት ይመታል።
ወደ ማታሩ ጆንግ ለመግባት ሁለት መንገዶች አሉ።የመኪና መንገድ እና በወንዙ በማቋረጥ :: አማጺዎች ግን በየብስ በኩል እያጠቁ ሲገሰገሱ ሰዎች ወደ ወንዝ እንዲሮጡ ተገደዱ። ብዙ
ሰዎች በፍርሃት ወንዝ ውስጥ ገቡ። እስኪደክማቸው ድረስ ዋኙ:: ወታደሮቹ በቁጥር መበለጣቸውን ሲያውቁ ቀድመው ነበር ከተማውን ለቀው የወጡት :: ህዝብ ሁሉ የተመመበት
አንድ ማምለጫ መንገድ ብቻ ነበር፡፡ ተከተልናቸው። መንገዱ ጭቃ ነበር፡፡ ጭቃ የያዛቸውን አካል ጉደተኞች ማንም
አልረደቸውም፡፡ ማንም ሊረደቸው የሚፈልግ የራሱን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ አማጺዎቹ ወደ ሰው መተኮስ ጀመሩ። ሰው ከተማውን ለቆ እንዲወጣ አልፈለጉም። ነዋሪውን በተለይ
ሴቶችን እና ህጻናትን ምሽግ በማድረግ ከመከላከያ ጥቃት መዳን ይፈልጋሉ፡፡
እንደምንም ግን ወደ ማምለጫው መንገድ ስንዳረስ አማጺዎች ቀጥታ ወደ እኛ መተኮስ ጀመሩ። ሁሉንም የመሳሪያ አይነቶች ተጠቀሙ።ጥይት አዘነቡ፤ ሮኬት ና መትረየስ ተኮሱ ቦምብ ወረወሩ። እኛ ምንም አላመነታነም:: መያዝ የከፋ እንደሚሆን እናውቃለን፡፡ ከተያዝን እንመለመላለን : በጋለ ጩቤ አእግ
ብለው ደስ ያላቸው ቦታ ላይ ይጻፉብናል። ስለዚህ ማምለጥ ግድ ነው። ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ሳናርፍ በፍጥነት ሮጥን::
አማጺዎች ተስፋ ቆርጠው ወደ ማታሩ ጆንግ ተመለሱ። እኛ ግን መሮጣችንን ቀጠልን፡፡
ለብዙ ቀናት ስድስታችን ጅኒየር ታሎ ካሎኮ፣ ገብሬላ፣ ካሊ እና እኔ በቀጭን መንገድ ጥቅጥቅ ባለ ጫካ መሃል ተጓዝን፡፡ሁላችንም ሃሳብ ላይ እንመስላለን። ማውራት የለም፤ መሄድ
ብቻ:: ስለ ቤተሰቦቼ ደግሜ ላያቸው እችላለሁ ብየ አሰብኩ፡፡ማልቀስ ፈለኩ በጣም ስለ ራበኝ ግን አቅም አልነበረኝም ::
በተተወ መንደር ውስጥ ባዶ መሬት ላይ ተኛን።በሚቀጥለው ቀን ሙዝ፣ብርቱካን እና ኮኮናት ዛፍ በሚገኝበት መንደር አለፍን፡፡ ሙዙ ጥሬ ስለሆነ ቀቅለን ነበር የበላነው። ከዛ ትንሽ ብርቱካን እና ኮኮናት በላን። በቂ ምግብ ግን ማግኘት
አልቻልንም። ከቀን ቀን ረሃባችን እየተባባሰ መጣ። ስለዚህ ወደ
ማታሩጆንግ ተደብቀን በመግባት ምግብ መግዣ ገንዘብ ማግኘት አለብን፡፡ ከዚህ ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ አልነበረንም።
በመንገዳችን ጸጥ ረጭ ባለ በተከዳ ከተማ ስናልፍ አስክሬን፣የተበላሸ ምግብ ፣ የእንጨት ስራዎች፣ ልብስ እና ሌሎች
እቃዎች በየቦታው ወድቆ አየን። አስክሬን ተቆራርጦ እጅ፣ እግር እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በየቦታው ወድቋል። ይሄን ሳይ አዞረኝ፤ አቅለሸለሸኝ። የነ ካሊሎ ቤት በከተማ እንዳሉ ሌሎች
ቤቶች በሩ ተሰብሯል ተቃጥሏል። የጥይት ቀዳዳ በበሩ በኩል ሲታይ ስታር ቢራ እና ሲጋራ መጠቅለያ ደግሞ ድጃፍ ላይ ወድቋል።
ገንዘቡን ባስቀመጥኩት ቦታ ሳይነካ አገኘሁት። ገንዘቡን ካልሴ ውስጥ ከትቼ ወደ ረግረጉ ወረድን፡፡ አማጺዎች ባህር ዳርቻው አካባቢ ማማ ላይ ወጥተው ይጠብቁ ስለነበር መንፏቀቅ ነበረብን፡፡ ከመካከላችን አንድ ልጅ ትልቅ ቦርሳ አንግቶ ስለነበር ጠባቂዎች አይትውት ተኩስ ከፈቱ።ከጠባቂዎች እስክንርቅ
ድረስ በፍጥነት ሮጥን።አመሻሽ ላይ ብዙ ሰዎች ያሉበት መንደር ውስጥ ገባን፡፡
ገንዘብ ስለያዝን ምግብ ይሸጡልናል የሚል ተስፋ ነበረን።
ነገር ግን አንዳንዶቹ ለክፉ ጊዜ ምግብ መቆጠብ ስለምንፈልግ አንሸጥም ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ያለ ምንም ምክንያት አንሸጥም አሉ። ራሳችንን ወቀስን፡፡ የጦርነት ወቅት እንዲህ ተለዋዋጭ
ነው። ማንም አይቆጣጠረውም፡፡ ነገሮችን በፍጥነት መረዳትና
የመትረፌያ መንገዶችን መቀየስ ነበረብን። ያን ምሽት አማራጭ
ስላልነበረን ሰዎች ወደ መኝታ ሲሄዱ ምግብ ሰርቀን በላን::
ምግብ እና ውሃ ሳናገኝ ብዙ ስለቆየን
ጉሮራችን ተንቃቃ፣ ሆድ ቁርጠትም ተሰማን። ከንፈራችን ተጣበቀ መገጣጠሚያችንም ዝሏል። ምግብ የት እንደምናገኝ ግራ ገባን። በመጨረሻ ረሃብ ወደ ማታሩ ጆንግ እንደገና
መለሰን።
የበጋ ወቅት ስለ ነበር ሳር ቅጠሉ ቢጫ ሁኗል። በሳር መሃል እየሄድን ድንገት አማጺዎች መጡብን። ገብሬላ ላይ ሽጉጥ ደቀኑ፤ እኔ ላይ ደግሞ ጩቤ ሰነዘሩ፡ "ደንግጧል" ብሎ ከት ብሎ
ሳቀ፡፡ አልፈን ወደመጣንበት መንደር መለሱን፡፡ አማጺዎቹ እጅጌ ጉርድ ቲሽርት፣ ጂንስ ጃኬት እና ሱሪ ለብሰዋል እና አዲዳስ ጫማም ተጫምተዋል። እጃቸው ላይ ውድ ስዐቶች አስረዋል።
ሁሉም በጉልበት የተቀሙ ወይም የተዘረፍ ናቸው።
ፈራሁ! እጆቼ እና እግሬዎቼ ተንቀጠቀጡ።አማጺዎች ትንሽም እንኳ ለመንቀሳቀስ ከሞከርን እንደሚገሉን ዝተዋል።ከጓደኞቼ እንዱ ወይም ወንድሜ ቢንቀሰቀስ ለማምለጥ ቢሞክርና ቢገሉንስ ብየ ሰግቻለሁ።
በአቅራቢያው ወዳለ መንደር ስንደርስ የመንደሩን ነዎሪዎች ሴቶች ህጻናት ሳይሉ ሁሉንም አሰለፉ። መጀመሪያ ካሊሎ
ቀጥሎ እኔን እና ሌሎች ወንዶችን መረጠው ወደ ፊት እንድንመጣ አዘዙ።
"ጠንካራ ወታደሮችን እንፈልጋለን” በማለት ጅኒየር

ን ጨመሩ። እኛ እየመራን ሌሎች ሰዎች ተከትለው እንዲሄድ
ታዘዘ፡፡ ከዛ አንድ አማጺ ወደ እኛ ዙሮ " እነዚህን ሰዎች ገላችሁ ነው እኛን የምትቀላቀሉት:: ደም እንድትለምድ እና ጠንካሮች እንድትሆኑ ነው ይሄን እንድታደርጉ የምናስገድዳችሁ ።” አለ
ድንገት የተኩስ ድምጸ ተሰማ፡፡ አማጺዎቹ
በመከለል ለተኩሱ መልስ መስጠት ጀመሩ። የተሰበሰበው ህዝብ በሙሉ መሮጥ ጀመረ። ሮጥኩ : ጓደኞቼ እና ወንድሜ ተከትለውኛል። አማጺዎቹ ለቀው መሄዳቸውን ካረጋገጥን በኋላ ወደ መንደሩ ገብተን አደርን።
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
ታዘዘ፡፡ ከዛ አንድ አማጺ ወደ እኛ ዙሮ " እነዚህን ሰዎች ገላችሁ ነው እኛን የምትቀላቀሉት:: ደም እንድትለምድ እና ጠንካሮች እንድትሆኑ ነው ይሄን እንድታደርጉ የምናስገድዳችሁ ።” አለ
ድንገት የተኩስ ድምጸ ተሰማ፡፡ አማጺዎቹ
በመከለል ለተኩሱ መልስ መስጠት ጀመሩ። የተሰበሰበው ህዝብ በሙሉ መሮጥ ጀመረ። ሮጥኩ : ጓደኞቼ እና ወንድሜ ተከትለውኛል። አማጺዎቹ ለቀው መሄዳቸውን ካረጋገጥን በኋላ ወደ መንደሩ ገብተን አደርን።
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#የባንዲራ_ነገር
በኔ አይነቷ ምስኪን አገር -
የባንዲራችን ቁጥር ብዛት - ከልብሶቻችን በለጠ
የኔ አይነቱ ከንቱ ፍጡር -
ለባንዲራ ያለው ፍቅር - ወደ ሸሚዝ ተለወጠ።
ምን አይነት ነው ባንዲራችን? -
ምንድን ነው የኛ መለያ?
ምን አይነት ነው የአገሬ አርማ? -
ቀለሟ ምን ነው የኢትዮጵያ?
የልጅ ልጆቼን የሚያግባባ ፣ አያቶቼን የሚያከብር
የትላንትን የአገር ፍቅር ፣ ከነገ ጋር ሚያስተሳስር፣
ሁሉንም ኢትዮጵያውያን፣ በሙሉ ድምፅ የሚያስማማ
ምን አይነት ነው ባንዲራችን? -
ምን አይነት ነው የአገሬ አርማ???
ተረኛ ስፊዎች ሁሉ -
በፍላጎቶቻቸው ልክ ፣ቀደው ሰፍተው እየሰጡን
በቀለም ብዛት አነሁልለው ፣የባንዲራ ፍቅር አሳጡን፡፡
🔘በሙሉቀን🔘
💚 💛 ❤️
በኔ አይነቷ ምስኪን አገር -
የባንዲራችን ቁጥር ብዛት - ከልብሶቻችን በለጠ
የኔ አይነቱ ከንቱ ፍጡር -
ለባንዲራ ያለው ፍቅር - ወደ ሸሚዝ ተለወጠ።
ምን አይነት ነው ባንዲራችን? -
ምንድን ነው የኛ መለያ?
ምን አይነት ነው የአገሬ አርማ? -
ቀለሟ ምን ነው የኢትዮጵያ?
የልጅ ልጆቼን የሚያግባባ ፣ አያቶቼን የሚያከብር
የትላንትን የአገር ፍቅር ፣ ከነገ ጋር ሚያስተሳስር፣
ሁሉንም ኢትዮጵያውያን፣ በሙሉ ድምፅ የሚያስማማ
ምን አይነት ነው ባንዲራችን? -
ምን አይነት ነው የአገሬ አርማ???
ተረኛ ስፊዎች ሁሉ -
በፍላጎቶቻቸው ልክ ፣ቀደው ሰፍተው እየሰጡን
በቀለም ብዛት አነሁልለው ፣የባንዲራ ፍቅር አሳጡን፡፡
🔘በሙሉቀን🔘
💚 💛 ❤️
#ያልገባኝ
ለምድራዊ ስልጣን - ከሞት ለማያስጥል
ለማያጠግብ ንዋይ- ከምስጥ ለማይከልል፣
ውል በሌለው ምኞት - እየተደለለ
እንዴት ሰው ይኖራል - ሰው እየገደለ!!???
🔘በሙሉቀን🔘
ለምድራዊ ስልጣን - ከሞት ለማያስጥል
ለማያጠግብ ንዋይ- ከምስጥ ለማይከልል፣
ውል በሌለው ምኞት - እየተደለለ
እንዴት ሰው ይኖራል - ሰው እየገደለ!!???
🔘በሙሉቀን🔘
#ማን_ልበላት?
አያችኋት ያቺን - ከሰው ተነጥላ?
መልኬ ይኼውላችሁ - ስሜ ይቆይ ብላ፡፡
አትረዝም፣አታጥር
አትቀላ፣አትጠቁር ፤
ክሽን ያለ ቁመት ፣ ክሽን ያለ ከለር
በጣም የምትስብ ፣ በጣም የምታምር
አያችኋት ያቺን?
አትወፍር፣አትቀጥን
አትዘገይ፣አትፈጥን
የአይኖቿ ብርሐን ፣ ፅልመትን የሚያሸሽ
ለአይን የምታሳሳ ፣ ቢነኳት ምትቆሽሽ፡፡
አይችኋት ያቺን ?
ብዙም ዝም ያላለች ፣ ብዙም ማታወራ
ብዙም የማትደፍር ፣ ብዙም የማትፈራ
የማትንቅ ፣ ግን ኩሩ
የውበት ድንበሩ፡፡
ያቺን አያችኋት?
ስሟን ባላውቀውም - ስም እንዳወጣላት
ምናልባት
ምናልባት
እሷን የሚመጥን - ስም ከተገኘላት
ውቧን ማን ልበላት???
አያችኋት ያቺን - ከሰው ተነጥላ?
መልኬ ይኼውላችሁ - ስሜ ይቆይ ብላ፡፡
አትረዝም፣አታጥር
አትቀላ፣አትጠቁር ፤
ክሽን ያለ ቁመት ፣ ክሽን ያለ ከለር
በጣም የምትስብ ፣ በጣም የምታምር
አያችኋት ያቺን?
አትወፍር፣አትቀጥን
አትዘገይ፣አትፈጥን
የአይኖቿ ብርሐን ፣ ፅልመትን የሚያሸሽ
ለአይን የምታሳሳ ፣ ቢነኳት ምትቆሽሽ፡፡
አይችኋት ያቺን ?
ብዙም ዝም ያላለች ፣ ብዙም ማታወራ
ብዙም የማትደፍር ፣ ብዙም የማትፈራ
የማትንቅ ፣ ግን ኩሩ
የውበት ድንበሩ፡፡
ያቺን አያችኋት?
ስሟን ባላውቀውም - ስም እንዳወጣላት
ምናልባት
ምናልባት
እሷን የሚመጥን - ስም ከተገኘላት
ውቧን ማን ልበላት???