#ስኳሬብየሽ አልነበረም
እኔ አመልክሻለሁ
እግርሽ ስር ወድቄ - እሰግድልሻለሁ?”
ስኳሬ ነሽ አንቺ - የህይወቴ ቅመም
ኑሮን ማጣፈጫ - ሳለሁ በዚህ አለም
እንዳንቺ ምወደው - ምንም ነገር የለም!!!
ብየሽ አልነበረም?
አሁን ግን አፈረስኩ፡፡
ስኳሬ ነሽ ብየ:-
አንዴ በቡናየ፣
አንዴ በሻይየ፣
አንዴ በበሶየ፣
በጥብጨ ስጠጣሽ
ሲያሻኝ በደረቁ - ስቅምሽ ስልስሽ፣
ሟሙተሽ ስታልቂብኝ
ሌላ ስኳር ገዛሁ-
ጊዜ ሳይሄድብኝ
ሱቅ ሳይዘጋብኝ፡፡