#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
“እና ደግሞ ጭራ
“የምን ጭራ? "
“ጭራ ነዋ፤ የዝንብ ማባረሪያ ጭራ፡፡”
ደግሞ ጭራ ምን ይሰራልሃል?
“ነገርኩሽኮ፡፡ ቄስ መምሰል ነው የምፈልገው::
ወር ሆነው ዘውዲቱ ቤት ዘግቶ ከተቀመጠ፡፡ ድንገት ሲሰወር
ደብዛው ሲጠፋ አውሬው እያጓራ በየስርቻው እንደሚያነፈንፍ ገምቷል፡፡
ቢሆንም አንድ ቦታ አድብቶ ጊዜ እስከወሰደ ድረስ መልሰው ጭራውን
ለመያዝ ይቸገራሉ። በዛ ጊዜ ውስጥ ራሱን ለመቀየር ጊዜ ያገኛል።
ከውዲቱ ጋር በሂሣብ ተስማምተው እዛው ሰነበተ:: . አብሯት የሚያድር ደንበኛ ያገኘች ሌሊት እፎይ ብሎ አንዴ በጀርባው አንዴ በደረቱ እየተገላበጠ ደልቶት እየተኛ ያልቀናት : ሌሊት ደግሞ የማታ ማታ እየተጎተተች መጥታ በዛችው ጠባብ ታጣፊ አልጋ ላይ እየተጋፉ ወር
አለፈ ፤ እንደምንም::
ገና ቤቷን በተከራየ በአራተኛው ቀን ነበር አላስችል ብሏት የጠየቀችው:: የጠበቀው ጥያቄ ነበር! መምጣቱ አላስደነገጠውም
አላስበረገገውም:: ተዘጋጅቷል፤ ምን እንደሚመልስላት ያውቅ ነበር፡፡
"ጺምህን ለምን አትላጨውም? ደግሞ ለምን ወጣ አትልም? ከጠዋት ጀምረህ እስከ ማታ በር ዘግተህ ምንድነው? የጤና ነው?” አለችው ጠዋት ከደንበኛ ጋር ኣድራ አረፋፍንዳ ስትመጣ ቤት ስታገኘው፡፡
“አዎ፡፡” አላት ነገሩን በአጭሩ ለመቅጨት፡፡
“ምን ማለት ነው አዎ?” አለች የምታበጥረውን ፀጉሯን ለቃ
ቁለቁል በተቀመጠበት እየተመለከታችሁ
“አዎ ነዋ፡፡” አለ ይበልጥ ገፍታ ገፍታ እስክትመጣ ወጥራ እስክትይዘው፡፡
ሁኔታው እንዳላማራት በግልጽ ታስታውቃለች። ቀሚሷን በጭንቅላቷ አውልቃ አልጋው ላይ ወርወር አደረገችውና ከፊት ለፊቷ
ያለውን ቁም ሳጠን ከፈተች፡፡
“እየው ወንድም” አለች ከቁም ሳጥኑ ውስጥ የታሰቀላ ልብስ ማውረዷን ሳታቋርጥ ፊቷን ወደሱ መልሳ፡፡ «እየው ወንድም ብሬ እስካልተቋረጠ ድረስ ዓመትም ተግተህ ብትቆይ ግድ የለኝም:: ግን ደግሞ ችግር አልፈልግም፡፡ ከፖሊስ ነው የተደበቅኽው አይደል?”
“ምን ማለትሽ ነው? እንዴት ከፖሊስ?” ደነገጠ፡፡
ተው ባክህ አለች ከቁምሳጥኗ ያወረደችውን ቀሚስ እያጠለቀች፡፡ “አሁን ማን ይሙት ዓለም በቃኝ ብለህ እኔ ጎጆ ውስጥ ሱባዔ የገባኸው ለነፍስህ ነው?”
የሚለው ጠፍቶት ዝም ብሎ ተመለከታት፡፡
“ሰርቀህ ነው! አይደል? ሰርቀህ ነው የተደሰቅኸው?“
“አይደለም… አይደለም::” አለ ፈጠን ብሎ፡፡ ለፖሊስ እንዳታሳጣው
ሰጋ፡፡
“ታዲያ ምንድነው? ወይስ ፍቅር ያዘህ ከኔ!” አለች ድንገት ስቃ፡፡
“እየው እኔ ግድ የለኝም:: ሌባ ቀርቶ የፈለከውን መሆን ትችላለህ፡፡ ግን
ልምከርህ፡፡ ከፖሊስ ከሆነ የተደበቅኸው እዚህ ተከተህ አታመልጣቸውም፡፡
አንድ ቀን ወጣ ያልክ ቀን ጋማህን ያብቱሃል፡፡ ራቅ ብለህ ሂድ፡፡ ድሬድዋ
ወይ ጅማ! እንደገንዘቡ እንደሰረቅከው ገንዘብ ብዛት፡፡”
ከተቀመጠበት ኣልጋ ላይ ተነስቶ
“ሰርቄ አይደለም ዘውዲቱ በጠባቧ ክፍል ጎርደድ ማለት ያዘ፡፡
“ታዲያ እኔ ቤት ውስጥ እናትህን ቀብረሃል? ”እይኖቿ አብረው
እየተንጎራደዱ ወገቧን ይዛ ጠየቀችው፡፡
ጊዜው እንደሚደርስ ቀድሞውኑም ገብቶታል፡፡ እንደምትጠይቀው ወጥራ እንደመትይዘው ገብቶታል፡፡የሚያሳምን ምክንያት መስጠት እንዳለበትም ተረድቷል፡፡ አለበለዚያ ለሳምንታት ቤቷ ውስጥ ተደብቆ ሊቆይ አይችልም፡፡ በአጭሩ የቤትሽን ኪራይ እስካላቋረጥኩ ድረስ አያገባሽም፡፡ ብሎ ዝም ሊያሰኛት ይችላል። ግን ደግሞ ልትፈራ ትችላለች! ወንጀል ፈጽሞ ከቤቷ የተሸሸገ ሊመስላት ይችላል:: “ውጣ!” ብትለውስ? ፖሊስ ይዛ
ከተፍ ብትልስ?ለዚህ ነው ቀደም ብሎ የሚላትን ያዘጋጀው፡፡ “ሊያስደነግጣት
አይገባም፡፡ ግን ደግሞ ልታዝንለት ይገባል። ችግሩን ተረድታ ልትረዳው
ፈቃደኛ መሆን አለባት፡፡ ቀስ ብሎ ማግባባት አለበት፡፡
“ምን መሰለሽ ዘውድዬ.…አለ ቀረብ ብሎ ግራ ክንፏን ያዝ አደረገና፡፡ “ግን አደራ…”
አይ ይሄን ያህል የሚያስጨንቅህ ከሆነ አትንገረኝ፡፡ ምን መሰለህ ከብዬ በሰላም መኖር ስለምፈልግ ብቻ ነው፡፡ ገላዬን ሽጨ የኖርኩት አንሶኝ ተባበርሽ ምንትስዬ ተብዬ ዘብጥያ መውረድ አልፈለግም፡፡ ይገባሃል አይደል?ልጅ አለኝ፡፡ የምወደው የምቀልበው ወንድ ልጅ፡፡ነገ የሚሸረሙጥ” ፈገግ አለች፡፡
ልታስከፋው እንዳልፈለገች ከሁኔታዋ ያስታውቃል፡፡ባለፉት ቀናቶች
ሳይታወቃቸው በመሃላቸው የመግባባት ስሜት ተፈጥሯል፡፡ስሙን ስትጠይቀው 'ከበደ' ብሎ እንደዋሻት ብትረዳም አላስጨነቀችውም፤ ስቃ ተወችው
ተወችው።ተከትለዋት እቤቷ ድረስ መጥተው ተጨማልቀው አጨማልቀዋት
ሳንቲም ወርውረውላት እንደሚሄዱ ደንበኛቿ እንዳልሆነ ግን ተረድታዋለች፡፡
የመጀመሪያው ማታ አብሬሽ
አልተኛም ሲላት ለይስሙላ ነበር የመሰላት፡፡ አጋጥመዎታላ! የገዛ ገንዘባቸውን ከፍለው መጥተው ተለማመጡን የሚሉ፤ ካላንቆለጳጰሳችሁን የሚሉ፤ “ያው የገዛችሁት ዕቃ” ሲባሉ የሚግደረደሩ።
ያን ቀን ማታ በል የውስጥ ልብሴን አቀብለኝ ብላው ያለችውን አቀብሏት : መብራቱን አጥፍቶ ከጎኗ አልጋው ውስጥ ሲገባ ይዘግይ እንጅ ያው እንደ አውሬ ወንድሞቹ የማታ የማታ ዘሎ እንደሚያንቃት አልተጠራጠረችም ነበር፡፡ አልጋዋ ወስጥ ገብቶ በጀርባው ተኝቶ
አንጋለወት እንደሄዱ ህፃን ጣሪያ ጣሪያውን ሲመለከት በጨለማው ውስጥ
ስታየው ደነቃት፣ቢሆንም አላመነችውም፡፡ ዘግይቶ ሊጓጉር ነው ብላ ደህና እደር አለችና በደረቷ ተገልብጣ ተኛች፡፡ እንቅልፍ ሊወስዳት ግን አልቻለም፡፡ ሰውነቷ አላርፍልሽ አላት:: . 'ከአሁን አሁን ዘሎ.. እያለች እላይ እታች የሚለውን ትንፋሹን ተከተለችው::
እንቅልፍ፡ እንዳልወሰደው እርግጠኛ ነበረች፡፡ እንዳሰበችው ሃሳቡን
ሳያቀያር ዘገየባት፡፡ ሲያነቃቃውና በጊዜ ብገላገል ብላ በእንቅልፍ ልቧ
እንዳለች ሁሉ ተወራጨችና በብርድ ልብሱ ውስጥ ክንዷን ሰድዳ አንድ
እጇን ጭኑ ላይ ጣል አደረገችው:: ተፈታተነች፡፡ ሲሸማቀቅ ተሰማት።
እጁን ሰድዶ እጇን ከላዩ ላይ አነሳና በቀስታ እራቅ አድርጎ አስቀመጠው፡፡
በእንቅልፍ ልቧ ያለች ሳይመስለው አልቀረም። ጃውሳው! በጉ! ተረጋጋች፡፡
ሳታውቀው ድብን ያለ አንቅልፍ ይዟት ጭልጥ አለ፡፡
በተከተሉት ቀናት ሳትጠይቀው ቀድሞ የተስማሙበትን የወር የቤት ኪራይ ሂሳብ ሰጣት፡፡ ከዛ በተረፈ ሆቴል እንድታመጣለት ገንዘብ እየሰጣት እራሱን ብቻ ሳይሆን እሷንም እየቀለበ ተቀመጠ፡፡ ተገኝቶ ነው?፡፡ ግን ደግሞ አቤት ብቅ አለማለቱ የተደበቀ ሰው አስመስሎታል፡፡ አንድ ክፍል ቤቷ ውስጥ ዘግቶ መቀመጥ ምን ማለት ነው? . ታዲያ ይና ዝም
ብሎ ማለፍ ይቻላል? እህእ ነገ አንዱ መርቶበት ቢያስይዘው አብራ መውረዷ እደደለም? የተካፈለች አብራ የገመጠች ይመስል ሆ!
“ልክ ነሽ! ልክ ነሽ! ይገባኛልኮ፡፡ ግን ሠርቄ አይደለም፡፡” አላት የያዛቸውን ክንዶቿን ለቆ አልጋው ላይ እየተቀመጠ፡፡
“እሺ ምንድነው ታድያ? ”
“እደው ምን መሰለሽ…” ያጠነጠነውን ይተረትር ጀመር፡፡ አራት ቀን መሉ ብቻውን በሚሆን ሰዓት እየተንጎራደደ ያጠናውን የተለማመደውን ዲስኩር ጀመረ፡፡
“በምስራበት መሥሪያ ቤት ውስጥ ረዳት የሂሣብ ክፍል ኃላፊ ሆኜ ነው የማገለግለው ዘውድዬ እኔ ትዳር ያለኝ ሰው ነኝ፤ የሁለት ልጆች አባት ነኝ:: ነገር አልሻም፤ በሠላም ሰርቼ ከቤቴ መግባት ከባለቤቱና ከልጆቼ ጋር ያገኘሁትን ተቋድሼ ማደር ነው የምሻ:: ምን መሰለሽ…” ትክ ብለው ቁልቁል የሚያዩት አይኖቿ ሰርስረውት ገቡ፡፡ ግንባሩን የምታነብ መሰሰው፡፡ሁለት እጆቹን አንስቶ ለአንድ አፍታ በመዳፎቹ ውስጥ ደበቀው ሰባራ ሳንተም አላነሳሁም ግን

👍3
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
መርማሪ ፖሊስ ሚክ ጆንሰን ካርተር በርክሌ ውድ ሽሚዙን በደንብ ማኒኩየር በተሰራው ጣቶቹ በደንብ አድርጎ አስተካከለው:: የዶክተር ሮበርትስ
ታካሚ የሆነው የኢንቨስትመንት ባንከሩ ካርተር በርክሌ ሁሉ ነገሩ ውዷ ነው፡፡ ምርጥ መኖሪያ ቤት፣ ምርጥ ምርጥ የቪንቴጅ ጃንዋር ስፖርት መኪኖች እና ሁሉም ቁጭ ያሉበት በምርጥ ሁኔታ ፈርኒሽድ የተደረገው የቤት ውስጥ ቢሮው እራሱ በጣም ውድ ነው፡፡ እንኳን እቃዎቹ ሲያወራ የሚጠቀምባቸው ቃላቶች ሁሉ በጣም የተመረጡ ናቸው፡፡
እዚህ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው እያወሩ እያሉ ካርተር ትላንትና ማታ መኝታ ቤቱ ውስጥ የሆነ ሰው ሊያስፈራራው በማሰብ የሞተ አይጥ አስቀምጦ እንደነበር እየነገረው ነበር። የሞተ አይጥን ማስቀመጣቸው የማፍያዎች ማስፈራሪያ ስልት እንደሆነ ጭምር እያስረዳው ነበር፡፡
“ይሄን ነገር ያደረጉት በእርግጥም እኔን ሊያስፈራሩ አስበው ነው፡፡ደግሞም ተሳክቶላቸዋል። ባይገርምህ መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን እናንተ ወደ እኔ ባትመጡ እንኳን እኔ እራሴ ጉዳዩን ለማመልከት ወደ እናንተ መምጣቴ አይቀርም ነበር።
ጆንሰንም ራሱን በአዎንታ በመነቅነቅ የቤቱን ዙሪያ ሲመለከት ዕቃዎቹ
በደንብ ከመወልወልም በላይ የመፅሀፍ መደርደሪያው ሼልፍም ራስን
በመገንባት ላይ እና በፋይናንስ ዙሪያ በተፃፉ መፅሀፍት በሥርዓት
ተጠቅጥቀዋል። አሁን ላይ ካርተር በርክሌይን እየተመለከተው ያለው ጆንሰን
ዶክተር ሮበርትስ ስለ ካርተር ከማስታወሻዋ ላይ ከፃፈችው ነገር ጋር
በመስማማቱ ተናደደ፡፡
ጆንሰን ካርተርን አስመልክታ ኒኪ የፃፈችውን ሲያነብ “መቀወሱ
ያልተረጋገጠ በከንቱ ስሜት ውስጥ የሚናውዝ የሜክሲኮ ወንጀለኞች
ሊገድሉት እንደሚያሳድዱት የሚናገር (ለዚህ ምንም ማረጋገጫ የሌለው)
ለረዥም ጊዜ በጭንቀት ውስጥ የኖረ። ምናልባት በልጅነቱ በደረሰበት ስቃይ
ምክንያት ሊሆን ይችላል? (ወይንም ደግሞ ሜክሲኮ ውስጥ በጉርምስናው
ዘመን ኖሯልና ምናልባት እዚያ የሆነ ነገር ተከስቶ ይሆን?) ውስጡ ያላደገ
ቋሚ የሆነ ፆታዊ ግንኙነት የሌለው እና በግንኙነት አብረውት ያሉ ሰዎችንም በጣም አድርጎ የሚቆጣጠር ነው።” ይላል ማስታወሻው፡፡
ዶክተር ሮበርትስ ካርተር በርክሌን የገለፀችበት መንገድ በሙሉ የተቀበለው ቢሆንም አንድ ነገር ረስታለች እሱም “የሰዎች አትኩሮትን (ታይታን) የሚፈልግ ባህሪ ያለው መሆኑ ነው። ይህንን ደግሞ በእሱ ላይ ያላየችው እሷም የዚህ ልክፍት ስላለባት ነው ብሎ አሰበ፡፡ ለዚህም ነው
ካርተር ከዚህ በፊት በተካሄዱት ግድያዎች ውስጥ ዋነኛ ተፈላጊ ሰው መሆኑን ለማሳየት ያጫወተውን የአይጥ ታሪክ ፈጥሮ ለጆንሰን የተናገረው።
ይሄ ቀሽም ሰው ራሱን እንደተፈላጊ ሰው ያያል ወይንም ደግሞ የሆነ እሱ ስለግድያው የሚያውቀውን ነገር እንዳላውጣጣው እያዘናጋኝ ነው
ብሎም አሰበ፡፡
“ቤትህ ውስጥ ጠባቂዎች አሉህ መሰለኝ?” ብሎ ቅድም ወደ ቤቱ ሲገባ
የተመለከታቸውን ብዙም ስልጠና እንደሌላቸው የሚያስታውቁትን የጥበቃ
ሰዎቹን አልፎ እንደገባ አስታውሶ ካርተርን ጠየቀው። ቤቱ ውስጥ ሲገባ ከጠባቂዎቹ ሌላም የሲ.ሲ.ቲቪ
ካሜራዎችንም አይቶዐካሜራዎችንም በየቦታው ገጥመሃል አይደል እንዴ?”
“አዎን ቤቱ ጥበቃ ስለሚያስፈልገው በጠባቂዎችም፣ በካሜራም ነው
የሚጠበቀው። ግን ዋናው መኝታ ቤቴ ውስጥ ካሜራ አልገጠምኩኝም” ብሎ
መለሰለት፡፡
ጆንሰንም “ለምን ዋናው መኝታ ቤትህ ውስጥ ካሜራ አላስገጠምክም?
ብሎ ጠየቀው፡፡
ባንከሩም እንዴት ይሄ አይገባህም በሚል ሀሳብ ይመስል የጎረምሳ ፈገግታ ከለገሰው በኋላ “እዚህ ጋር የተማረ ሰው ግምት ይኖርሃል ብዬ አስባለሁ። ጠባቂዎቼ ከሁሉም ካሜራዎች በቀጥታ መረጃዎች ይደርሳቸዋል።እኔ ደግሞ በግሌ የማደርጋቸውን ነገሮች ማንም እንዲያውቅብኝ አልፈልግም። ለዚያም ስል ነው በዋናው መኝታ ክፍሌ ውስጥ ካሜራ ያላስገጠምኩት፡፡ በሁሉም ወደ ቤቴ በሚያስገቡ በሮች ላይ ካሜራ
ተገጥሞባቸዋል። እሱ ላይ ብቻ ሳይሆን ፎቅ ላይም ካሜራዎችን
አስገጥሜያለሁ። ስለ እዚህ ወደ እዚህ ቤት የሚገባም ሆነ የሚወጣ ሰው
በካሜራው መታየት ይችላል” ብሎ መለሰ፡፡
“መልካም” አለና ጆንሰን በመቀጠልም “የሞተውን አይጥ መኝታ ቤትህ
ተቀምጦ ካገኘህ በኋላ መቼስ ካሜራዎቹ የቀረፁትን ቪዲዩዎች ተመልክተሀቸዋል አይደል?” ብሎ ጠየቀው፡፡
“አዎን አይቻቸዋለሁ”
“ግን ማንም ሰው አላየህም?”
ቤቴ ውስጥ ከሚሰሩ ሰዎች በስተቀር አንድም ሰውን አላየሁም። ይሄ ታዲያ አይገርምም?” ብሎ የሸሚዙን ኮሌታ በሀይል ጎተተው።
“እና እንዴት ነው ይሄ አንተ የማፍያዎች የማስፈራሪያ መንገድ ነው ብለህ ያሰብከውን የሞተውን አይጥ መኝታ ቤትህ ድረስ ሊያስቀምጡ የቻሉት?” ብሎ ጆንሰን ጠየቀ፡፡
ካርተርም ፊቱ ላይ ግራ የመጋባት ፊት እያሳየው “እኔ ይሄንን በምን አውቃለሁ? መርማሪ ፖሊሱ እንግዲህ አንተ ነህ አይደል? አንተው ንገረኝ
እንጂ” ብሎ መለስ፡፡
“እና ቪድዮው ላይ አዲስ ሰው እስካላየህ ድረስ ቤት ውስጥ የሚሰራ
ሰው ነው አይጡን መኝታ ቤትህ ያስቀመጠው ማለት ነው፡፡ አይመስልህም?”ብሎ ጠየቀው እኔ ጋር አለ ብሎ ባልጠበቀው የራሱ ትዕግስት ጭምር እየተገረመ፡፡
“ይሄማ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም እኔ እነዚህን ሰዎች ስቀጥር
የበፊት ህይወታቸውን በሚገባ አስጠንቼ እና ተጠንቅቄ ነው፡፡ ስለሆነም
አሁን አንተ የተናገርከው ነገር ሊሆን አይችልም...”
ብሎ ያሰበውን ነገር ተናግሮ ሳይጨርስ ጆንሰን አቋረጠው እና ምናልባት አይጡን ልታሳየኝ ትችላለህ? ስለዚህ አይጡን አንስቼ ምርመራ እንዲደረግበት ማድረግ እችላለሁ” አለው ከወንበሩ ላይ ተነሳ፡፡
“አይጡን ላሳይህ አልችልም” ብሎ መለሰለት፡፡ ጆንሰንም የካርተርን
መልስ ሲሰማ ዶክተር ሮበርትስ “ዝም ብሎ የቅዠት ሀሳብ የሚፈጥር ብላ
የተናገረችው ነገር ትክክል እንደሆነ አወቀ።
ለምንድነው አይጡን የማታሳየኝ?” ብሎ ኮስተር ብሎ ጠየቀው እና ለእንደዚህ አይነት ሰው ዶክተር ሮበርትስ እንዴት በየቀኑ የቴራፒስት ህክምና ልትሰጥ እንደምትችል ራሱን ጠየቀ፡፡ እንደዚህ አይነቶቹ ቴራፒስቶች አፍንጫቸው መመታት የለበትም ታዲያ?
“ትላንትና ማታ ነው አይጡን ያገኘሁት እሱን ደግሞ ነግሬሀለሁ አይደል?” ብሎ ካርተር ክርክሩን በመቀጠል “ቤቴን የምታፀዳው ሴት ደግሞ እስከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ድረስ አልመጣችም ነበር፡፡ እሷ እስክትመጣ ድረስ ደግሞ አይጡን ክፍሌ ውስጥ ልተወው አልችልም፡፡ ምክንያቱም አይጡ ምን አይነት በሽታ ይዞ እንደመጣ ማንም አያውቅም፡፡” ብሎ መለሰለት።
“እና መረጃ የሚሆነንን ነገር ነው የጣልከው?”
“መጣል ነበረብኝ”
“አይጡን ከክፍልህ ስታስወግድ ያየህ ሰው አለ?”
የለም ያው እንዳልኩህ በጣም መሽቶ ነበር” ብሎ ሲመልስለት የጆንሰን
ትዕግስት ተሟጥጦ ስላለቀ አሁንም ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ተነሳ፡፡
የታለ ቆሻሻ የምትጥልበት የቆሻሻ ማስቀመጫህ? ምናልባት አይጡ
እዚያው ቆሻሻ መጣያው ውስጥ ይኖር ይሆናል ይሄኔ” አለው ጆንሰን
ይህንን የጆንሰን ጥያቄ ሲሰማ ቢያንስ ካርተር ማፈር ነበረበት፤ ግን እሱ
ይበልጥ ድርቅ ብሎ “አሁን ላይ በእርግጠኝነት ባዶ ነው የሚሆኑት። ቆሻሻ የሚሰበስቡ ሰዎች ዛሬ በጠዋት ነው ያለወትሮ የመጡት። ያንን አስቢ
አይጡን ሌላ ቦታ ማስቀመጥ ነበረብኝ፡፡ ወይም በጣም ነው ያጠፋሁት.”ጆንሰን ወደ ዋናው የፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ ለመመለስ መኪናውን በተጨናነቀ መንገድ ላይ ሲያሽከረክር ከአንድ ሰዓት በላይ ፈጅቶበታል ጣቢያውም የደረሰው በሚያስጠላ

👍2
#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
....የውስጤን ሥቃይና የሕሊናዬን ሰፊ ጠባሳ ጠልቀው ያላዩ የቅርብ
ዘመዶቻችን «ዛሬማ ተበላሽቶ፣ የሱ ነገር እንዲህ ሆኖ ቀረ፡፡ ያየህይራድን የመሰለ
አንበሳ አባት እያለው ወግ ማዕረግ ያለማየቱ...» እያሉ ያጉመተምታሉ፡፡ ከቤት
ውጪ ማደሬ ያለ ማቋረጥ በመዘውተሩ ሁኔታውን መላው ቤተሰብ ከዳር እስከ
ዳር ዐወቀ፡፡ ደግማ ደጋግማ እናቴ እያፈረች፣ እኅቴ በተለይም የእናቴ
ምስጢረኛና የቅርብ ጓደኛ ወይዘሮ አማረች መኝታ ቤት ድረስ እየገቡ፣ ተው
ደግም አይደል የትልቅ ሰውና የጨዋ ልጅ እንዲህ አይደለም፡፡ እናትህ ብታለቅስ
ታደርስብሃለች» እያሉ ለወጉ ያህል ገሠጹኝ፡፡
እኔን የምመክራትና የምዳኛት ወደ ፊትም ሆነ ወደ ኋላ የማስኪዳት እኔው ራሴ ብቻ በመሆኔ የእነርሱን ምክር ሁሉ እንደሚያልፍ የበረዶ ውሽንፍር
ቆጠርኩት። በጠቅላላ መጻሕፍቶቼንና ልብሶቼን ውስጥ ውስጡን አንድ በአንድ
እግዥ ጨረስኩ፡፡ ከሁለትና ከሦስት ቀን አዳር በኋላ ወደ ወላጆቼ ቤት ስገባ ዘና
ብሎ የሚያናግረኝ ሰው አልነበረም፡፡
አባቴም ከቤት ውጪ በተደጋጋሚ ማደሬንና እንደ እናቴም አባባል «መዛተሌን» ቀስ በቀስ ሰማ።
«አግባ! ትዳር ንብረት ያዝ፣ እንደ ማንም የባለጌ ልጅ ሰፈር ለሰፈር
እትልከስከስ፣ ጎጆ ያስከብራል፣ ትዳር ግርማ ሞገስ ነው ያልኩህ ለዚህ ብዬ ነበር፡፡ያለበለዚያ ግን አካለ መጠን ከደረሰ ጐረምሳ ጋር ምን ያታግለኛል» ብሎ
ከነከተቴው ችላ አለኝ፡፡
ዋል አደር ብሎም «አደጋ ብቻ እንዳያገኘው እንጂ ልቡ መለስ
ሲልለትና ያበጠው ልቡ ሲሟሽሽ እንዳረጀች ውሻ ክትት ይላል» አለና ይብሱኑ ስለ እኔ የነበረውን 'አለና የለም ወይ?” እርግፍ አድርጎ ተወ፡፡
የሐሳቤ ተፃራሪ የሆነው አባቴ እንደ አህያ ሬሳ ቢጠላኝም ቅር አላለኝ፡፡ እኔ ግን «ይህ ነው ለሰው ልጅ የሚሰጠው ታላቅ የመኖር ጸጋ ብዬ ከጥላቻው ውስጥ ብርታትና እፎይታ የተሸለምኩ መሰለኝ።
ወደ ወላጆቼ ቤት ባሰኘን ጊዜ ገብቼ ባስፈለገኝ ሰዓት ውልቅ ማለት
ለመድኩ፡፡ እንደ ምኞቴ ሳልዘጋጅና ሳላስበው፣ የኑሮዬንም አዝማሚያ በሚገባ ሳላቅድ ድንገት ባለትዳር በመሆኔ ኑሮ በመጠኑ ተደናገረኝ። ሆኖም ትዳራችን የተመሠረተው በጽኑ ፍቅር ላይ በመሆኑ ፍላጎቴና ጉጉቴ ሁሉ ነጋ ጠባ
ለመሻሻልና አስደሳች ለውጥ ለማግኘት ሆነ። ወትሮ በቀላሉ ደንግጦ ይበረግግ
የነበረው አእምሮዬ የድፍረትና የወኔ ካፈያ ተርከፈከፈበት።
የየወዲያነሽን ቀኝ እጅ ያዝ አደርግና «ዛሬ ምን ያስፈልገናል?» ስላት ዐይን ዐይኔን እያየች እና የኮቴን አዝራሮች በጣቶቿ እየጠራረገች «ካለህማ....ያህል ይበቃኛል» ብላ ገንዘብ ስትጠይቀኝ የትዳርን አያያዝና አመራር ቀስ በቀስ
ለመድነው። በየወዲያነሽ በኩል የተቸገርኩበት ጉዳይ ቢኖር፡ ስትተኛም ይሁን ስትነሣ ስትበላም ይሁን ስትጠጣ አረ ተው ጌታነህ፡ ኧረ ተው! እረ ተው
ልጄን አሳየኝ? ሞቶም እንደሆነ ቁርጡን ንገረኝ ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርግ
መቼ እንዲህ ዝም ትለኝ ነበር?» እያለች ስለምትጨቀጭቀኝ ነበር፡፡ ምንም እንኳ
አንዳንድ ነገርን አገላብጠው የማያዩ ቀባጣሪዎች «ጨካኝ አረመኔ ነች» እያሉ
እንደሚያሟትና ወደ ፊትም እንደሚያባጥሏት እያሰብኩ ለጊዜው ብበሳጭም እኔ ከማንም ይበልጥ የእኔዋን እና ቅኗን የወዲያነሽን አሳምሬ ስለማውቃት አባባላቸው ሁሉ ከወሬ እንኳ የነፈሰበት ተራ ወሬ ነው ብዬ እንደ ቤት ጉድፍ ጠራርጌ ጣልኩት።
ያን በማሕፀኗ ዘጠኝ ወር ሙሉ ተሽክማ በስንት የኑሮ ሥቃይ እና ውጣ ውረድ የወለደችውን ልጅዋንና አካሏን ለማየት እያለቀሰች ብታስቸግረኝም
የእናትነት ወጓ በመሆኑ ምንም ቅር አላለኝም፡፡
አንድ ቀን እሑድ ጥዋት ለቁርስ እንደ ተቀመጥን ሳላስበውና
የሚያጋጥመኝን ሳልጠራጠር ከኪሴ እንድ ትንሽ ሰማያዊ ማኅደር አወጣሁ፡፡
በውስጡ የነበሩትን ልዩ ልዩ ሥዕሎች ተራ በተራ ስመለከት የወዲያነሽም
እጅዋን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጋ ትመለከት ነበር፡፡ የልጃችንን ሥዕል ኣየት
እንዳደረገች «ይኸውና» ብላ ባስደንጋጭ ሁኔታ ጮኸች፡፡ ከእጄ ላይ መንጭቃ
ደረቷ ላይ ለጠፈችው።
እነዚያ በእንባ ተኮትኩተው ያደጉት ዐይኖቿ የእንባ ኩልልታ እንጠፈጠፉ፡፡ ሥዕሉን ጠረጴዛው ላይ ወርውራ እግሬ ላይ ዘፍ አለች፡፡ እግሬን ባላት ጠቅላላ ኃይል ቁልቁል ጨምድዳ ስለ ያዘችው ጎትቼ ማላቀቅ አቃተኝ።
«ብዙ ሥቃይና መከራ ያየሁበት፣ ተንገላትቼ የተንከራተትኩበት የበኸር
ልጂ ነውና አለበት ድረስ ወስደሀ እሳየኝ፡፡ እናት አባትሀም ቤት ከሆነ ከሩቅ
ልየው:: ዐይኑን አይቼና ኣንድ ጊዜ ስሜው ልሙት!» ብላ ጫፈ ድልዱሙን
ጥቁር ጫማዩን ዕንባ አርከፈከፈችበት። የምይዘውና የምለቀው ጠፋኝ፡፡ ቁርጡን
ለማወቅ ቆርጣ መነሣቷን ስላወቅሁ ኣበይ ተነሽ ልብስሽን ቀያይሪና እንሂድ!
እይተሽው ለመመለስ እንጂ ይዘነው መምጣት አንችልም» አልኳት። እግሬን
ሳትለቅ አሻቅባ እያየች «እኔም ይዤው ልምጣ አልልም፣ ዐይኑን ብቻ አንድ ጊዜ
ልየው፣ በሕይወት መኖሩን ብቻ ልይ!» ብላ የልቧን አውጥታ ተናገረች።
በጉንጫ ላይ የሚንኳለለው ትኩስ እንባ የልቤን የፍቅር ወለል ቦረቦረው።ተነሥታ ወደ ጓዳ ስትገባ አረማመዷ እንኳ አሳዘነኝ። የባዕድ ሀላፊ አግዳሚ ያህል
እንኳ የማይተዋወቀችን እናትና ልጅ እንዴት አድርጌ እንደማስተዋውቅ ጭንቅ
ጥብብ አለኝ፡፡ እማምዬ እያለ በእናቱ ክንዶች ላይ ያልተዘናከተን' አልቅሶ
ያልተባበለን ሕፃን፣ ዐይኑ አይቶ ሕሊናው ያልመዘገባትን፣ አልቅሶም ይሁን በማቅ
ተንከትክቶ ዕቅፏ ላይ ያልተዘረገፈን ልጅ እንዴት አድርጌ እማማዬ እማማ
ለማሰኘት እንደምችል አጀማመሩም ሆነ አፈጻጸሙ ስማይን መቆንጠር መስሎ
በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ልብሷን ቀይራ ብቅ አለች፡፡ ኣጭር ዞማ ጸጉሯ በሚያምር ሐምራዊ ሻሽ ሽብ ተደርጓል፡፡ ኣጠገቤ መጥታ ቆም ካለች በኋላ በል አታጓጓኝ ይኸው መጣሁ! እንሂድ! » ብላ አሰፈሰፈች፡፡
የረሳችውን ሕፃን፡ ልጅሽ ይኸ ነው ብዬ ሳሳያት፣ ኣቅፋው በደስታ ስታለቅስ እና የልጁም በሁኔታው መደናገጥ ገና ከሩቁ አሽቆጠቆጠኝ፡፡
«የምንሄድበት ቦታ እኮ በጣም ሩቅ ነው» አልኳት፡፡ ግድ የለህም ስለ መንገዱ ሰማይ ጥግ ይድረስ፣ እንሂድ ብቻ' » ብላ ቆርጣ መነሳቷን ወደ በሩ በመራመድ ገለጸች፡፡ ከአስራ አምስት ደቂቃ ጉዞ በኋላ በታክሲ ዕጓለ ማውታ ግቢ ደረስን። ለሁለተኛ ጊዜ ከሴት ጋር ያዩኝ የድርጅቱ ዘበኞችና ሌሉች ሠራተኞች እርስ በርሳቸው በመተያየት ተጎሻሽሙብኝ፡፡
ሕፃናቱ ሁሉ ልዩ ልዩ ቅርዕና መልክ ያላቸው መጫወቻዎችና አሻንጉሊቶች ይዘው በምድረ ግቢው ሜዳ ላይ እንደ እውድማ ዳር ጥሬ ፈስሰዋል፡፡ ኳስ እያንከባለለ የሚጫወተውን፣ ጅዋጅዌ የሚገፈትረውን፣ ወለሉ ላይ
በተሽከርካሪዎቿ እየተገፋች የምትሽከረከር መኪና ይዞ ራን ራን ጵጵ! ቢብ! የሚለውን፣ ሜዳ መኻል እየተሯሯጡ ድብብቆሽ የሚጫወቱትን ሁሉ አየናቸው::
ለጊዜው ልጃችንን ስላጣሁት ዐመዴ ቡን አለ፡፡ እጄን ኮት ኪሴ ውስጥ
ወሽቄ ከቤት እንደ ወጣን የገዛሁለትን ከረሜላ ማሻሸት ጀመርኩ፡፡ የየወዲያነሽ
ዐይኖች በተስፋ ብርሃን ተከበቡ። የናፍቆት ጎተራቸው አፉን ከፈተ። የጉጉቷ ጥም ተንሰፈሰፈ። ዐይኖቿን ቅርብና ሩቅ ድረስ እየላከች ኣየች፡፡ ሰውነቷ የሚንቀጠቀጥ መሰለ። ውሪ ብጤ ሩጭሩጭ እያለ ባጠገቧ ባለፈ ቁጥር ዐይኖቿ እግሮቹን ተከትለው ይጓዙና በዚያው ፈዝዘው ይቀራሉ፡፡
በመኻሉ አንድ አጠር ጠበብ ያለች ነጭ ሱሪ የታጠቀና ዐመድማ ሹራብ
የደረበ ድምቡል ያለ የሚያምር ልጅ ዝንጉርጉር ቢራቢሮ በግራ እጁ ይዞ
እያንደፋደፈና እፍ እያለባት ከፊት

#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ሥራ ከጀመረ አንድ ዓመት ሞላው። ከእናትና ከእህቱ ተለይቶ በናፍቆታቸው እየተሰቃየ አንድ ድፍን ዓመት አስቆጠረ። በአማረችና በሱ መካከል የተጀመረው ጓደኝነትም ውስጥ ውስጡን የሚያብከነክን የሚያብስለስል ነገር ግን ገሀድ ያልወጣ ድብቅ ቢሆንባቸውም የሙቀት መጠኑንና የእድገት ደረጃውን ጠብቆ በመጓዝ የአንድ ዓመት ልደቱን አከበረ።
ለአዲሱ አለቃው ለልዑል ሰገድ አስጨናቂና ፈታኝ ሰው እየሆነበት
ከመጣ አንድ ዓመት ሞላው። በዩኒቨርስቲ የሚከታተለው ትምህርት አካውንቲንግ መሆኑ በፍጥነት ወደ ሂሳብ ክፍል ለመዛወር ያስቻለው ቢሆንም አዲሱ አለቃው ልኡልሰገድ በዝውውሩ ደስተኛ አልሆነም። ገናለገና በትምህርት ይበልጠኛል የወደፊት የዕድገት ተስፋዬን ያጨልምብኛል በሚል ፍርሃት ጥምድ አድርጎ ይዞታል። በአንፃሩ ደግሞ ከቀድሞው አለቃው ከሽመልስ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ተጠናክሮ ላለፈው
አንድ ሙሉ አመት የሚያስቀኑ ጓደኛሞች በመሆን ዘልቀዋል፡፡ ሁለተኛው ዓመትስ በምን ይቀጥል ይሆን? በሱ በኩል ሁለተኛው ዓመት የእናቱንና የተወለደባት ቀዬውን ናፍቆት ለመወጣት የዓመት እረፍት ፈቃዱን ወስዶ ወደ ባሌ የሚሄድበት፣ ከአማረች ጋር ያለው ግንኙነት ይበልጥ የሚጠናከርበት፡ዘይኑን አምጥቶ አዲስ አበባ ትምህርት እንድትጀምር የሚያደርግበት ዓመት እንደሚሆን ዕቅድ ይዟል::
የጌትነት እናት ኑሮዋ እያማረ ደስታዋ እየጨመረ በመሄዱ “ ተመስገን
ፈጣሪዬ ላንተ ምን ይሳንሀል?"እያለች ፈጣሪዋን ማመስገን ከጀመረች አንድ ዓመት ሞላት። ዛሬ ዕድሜ ለጌትነት ችግር ተወግዷል። በየማሳው ላይ እየዋሉ በፀሃይ መጠበስ ቀርቷል። ደብዳቤው በየጊዜው ይጎርፋል አለሁልሽ የሚላት ልጅዋ ያለማቋረጥ ተቆራጭ አድርጎላታል።"ገበያ እንዳትወጪ አቅም የለሽም እኔ አለሁ አይዞሽ!” ነው የሚላት። ወደ ዓመቱ መጨረሻ ላይ የላከው ደብዳቤ ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት ዘይኑን ወስዶ ለማስተማር ያለውን ሀሳብ የሚገልጽ ሆነ፡፡ ከእናቷ መለየቷን ባይወደውም በቅርበት አስፈላጊውን ክትትልና እገዛ እያደረገላት ጥሩ ደረጃ ላይ
እንድትደርስ ሌላ አማራጭ አልነበረውምና ይህንኑ ገልፆ ደብዳቤ ለእናቱ ጻፈላት፡፡
እናቱ አስካለ ደብዳቤው ሲደርሳት አላንገራገረችም፡፡ ሀሳቡን በደስታ ተቀበለችው። ዘይኑ ግን ሀሳብዋ ለሁለት ተከፈለ። የወንድሟን ናፍቆት ለመወጣት መሄዱን ስትፈልገው ከእናቷ መለየቱ ደግሞ ሆዷን አባባውና መንታ መንገድ ላይ ቆመች። ትንሿ ዘይኑ ለአንድና ብቸኛ ወንድሟም ሆነ ምትክ ለሌላት እናቷ ያላት ፍቅር እኩል ነው፡፡ እናት ደግሞ ዘይኑን ማጣቷ ትልቅ ጉዳት ነው። በተለይ "ማታ ማታ እቅፍ እያደረገቻት እስቲ ጀርባዬን እከኪልኝ ከፍ ዝቅ ጎሽ! አዎን እንደሱ!" የምትላት ደክሟት ስትገባ ቤቱን አሟሙቃ የምትጠብቃት ጉድ ጉድ የምትልላት
ሁሉ ሊቀር ነው። ዘይኑም ከዚያ ከምትወደው ከሚሞቃት የእናቷ ጉያ
ልትነጠል ነው፡፡ እንኮኮ እያለ ንፍጧን እየጠረገ ያሳደጋት ታላቅ ወንድሟ
ደግሞ የአባቷ ምትክ አባቷም ወንድሟም ነው። ወሬውን ከስማች በኋላ ልቧ ወደ ወንድሟ ሲጋልብ የእናቷ ፍቅር ደግሞ ሉጋም እየሆነባት በሀሳብ ስትባክን ከረመች፡ የስፈሯ ልጆች አዲስ አበባ ወንድም” አላት እያሉ ሲያደንቁላት ሲያጋንኑላት ትሰማለች፡፡ አዲስ አበባ የሚያምር የሚያጓጓ አገር መሆኑን ስለምትስማ የዘይኑ ትንሽ ልብ በመጨረሻ ላይ አዲስ አበባ በመሄድ ሃሳብ ተማረከች፡፡
"ለመሆኑ ልትልኪያት ወሰንሽ?" አሉ ወይዘሮ ዘለቃ የደብዳቤውን
መንፈስ ከተረዱ በኋላ፡፡
"ምን ይደረግ ታዲያ እትዬ ዘለቃ? ትምህርቷን መቀጠል አለባት። ያለበለዚያ ማቋረጧ ነውኮ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ብቸኝነት ነፍሱን ሊያወጣው ነው፡፡ ሄዳ ትማር ሌላ ምንም አማራጭ የለም" አለችና ዘይኑን ትኩር ብላ በጉጉትና በፍቅር አስተዋለቻት፡፡ በዘይኑ ውስጥ አልፋ ጌትነትን ቃኘች እንደ አህያ ጡት ያሏት ሁለት ልጆቿን አንዷን በእውን ሌላውን በምናቧ እያስተዋለች ሳትተነፍስ ለረጅም ጊዜ ፀጥ ብላ ቆየች። ዘይኑ ያንኑ መከረኛ ቡና እያፈላች ነበር፡፡
"አንቺ ዘይኑ አንቺስ ምን አሰብሽ?" ብለው ጠየቋት ወይዘሮ ዘለቃ።
"እኔ ምን አውቃለሁ ሂጂ ካለችኝ እሄዳለሁ ቅሪ ካለችኝ እቀራለሁ" አለች ዘይኑ።
"አየሽ ? አየሽ ?ይቺ መናጢ ልቧ ለመሄድ ከጅሏል ማለት ነው፡፡
እናትሽን ለማን ጥለሽ ነው የምትሄጂው አንቺ?! ትምህርት ቀስ ተብሎ ይደረሳል" አሏት፡፡ አሮጊቷ ልጇን መጨቅጨቃቸውን እናት አልወደደችውም፡፡ ሁለቱ ልጆቿ እርስ በርሳቸው እየተደጋገፉ "ወንድም
ጋሻዬ ዘይንዬ" እየተባባሉ እየተረዳዱ በፍቅር አብረው እንዲኖሩላት ነው
ፍላጎቷ። የራሷ ችግር ብቸኝነቷ አልታያትም፡፡ የነሱ ደስታ ነው ደስታዋ
ወንድሟ ትምጣልኝ ብሎ ከጠየቀ ምንም ማንገራገር አያስፈልግም፡፡ መነሳት ብቻ!
"ይተዋት ባክሁ አልሄድም ብትልስ መቼ እሺ እላታለሁ? ሄዳ ትማር፡፡ ዛሬ ከሁሉ የበለጠው ትምህርት ነው፡፡ ጌትዬም ሰው ሆኖ አለሁልሽ የሚለኝ ቢማር አይደል? ዋ! ልጄ በዚህ ላይ ደግሞ ማን አለው? ብቻውን በሰው ሀገር። ትሂድለትና ልቡ ትንሽ አረፍ ይበልንጂ...
የሱ ልብ ሳያርፍ እኔስ የምተኛው እንቅልፍ ምን እንቅልፍ ይሆነኛል? ትርፉ ቅዠት ነው" ዘይኑ በእናቷ አነጋገር ደስ አላት። በልቧ የአሮጊቷን ንግግር አልወደደችውም ነበር። ወደ ወንድም ጋሻዋ በሃሳቧ ተጓዘች።
አዲስ አበባ! ጓደኞቿ የሚያደንቁት ቆንጆ ከተማ! አዲስ አበባ ሄዳ ከወንድሟ ጋር የመኖሩ ነገር በጉጉት ታያት። ልቧ ወደ መሄዱ አደላ። አቤት የዘይኑ ነገር! ደስታ በደስታ ሆነች። ደግሞ ተደስታ ብዙ አልቆየችም፡፡
የእናቷ ነገር መጥቶ እንደገና ከፊቷ ድቅን አለባትና አለቀሰች። ማን እማምዬ እያለ ጀርባዋን ያሻሻታል? ማን ቡና ያፈላላታል? ማን ቤቱን ይጠራርግላታል? እናቷ በብዙ ነገር እንደምትጎዳባት ታያት። ኦና ቤት
ጣራና ግድግዳ ብቻ! አቤት ጣራና ግድግዳ ሰው ከሌለበት ሲያስጠላ?!
እንኳን ደሳሳ ጎጆ የተንጣለለ ቪላ ቤትም ቢሆን ያለሰው አያምርም። እሷ
እንደዚህ ትጨነቅ እንጂ እናቷ እንደሆነች ቆርጣለች። እህቴ ትምጣልኝ
ብሎ ከጠየቀ ጊዜ ሳታጠፋ ቶሎ ልትልክለት ወስናለች።
እናትነት ሰው በመሆን አስተዋይነት ውስጥ ብቻ ሳይሆን ሳይዘሩ ሳያርሙና ሳይኮተኩቱ በርረው በሚኖሩ አእዋፋት ላይ እንኳ ሚስጥሩ ረቂቅ ነው፡፡ ለልጇ ስትል ከድመትና ከጨለሌ ጋር ጦርነት ገጥማ በክንፏም በጥፍሯም ታግላ የምትከላከል ዶሮ፣ ግልገሏ ወደ ገደል ስትወረወር ረጅዋን ተከትላ ወደ ገደሉ የወረደችው አህያ እናት ለልጅዋ ያላትን
ልቅ ፍቅር የሚገልፅ ነው። ዘይኑም ይህንን በደንብ ታውቀዋለች። የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ሆና ባነበበችው የተረት መፅሐፍ ውስጥ በጫካ የምትኖር ዋኔ ጫጩቶችዋን በጉያዋ እንዳቀፈች ከተነሳው የሰደድ እሳት ልታስጥላቸው የከፈለችውን የህይወት ዋጋ ታውቃለች። እሳቱን ፈርታ ሳትደነብር ሳትበረግግ ጫጩቶችዋን ለማዳን እንዳቀፈቻቸው በነበልባሉ ተጠብሳና ተቃጥላ ስትሞት በስሯ የተጠለሉት ጫጩቶች በሙሉ ሳይቃጠሉ መትረፋቸውን አንብባ የእናት ፍቅር ምን ያክል ከባድ እንደሆነ አስ
ደንቋታል። የዚያን ያክል ጥሩ እናቶች እንዳሉ ሁሉ ለልጆቻቸው ደንታ ቢስ የሆኑ ምንም አይነት የልጅ ፍቅር የሌላቸው የወለዱትን እያስራቡ ሆቴል ገብተው ጮማ የሚቆርጡ ወላጆች መኖራቸው የሚካድ ኣይደለም፡፡ አንዳንዴ የእናት አንጀት ከጨከነ ከደነደነ ቦታውን የሚረከበው ክፉ መንፈስ ይሆንና የወለዱትን ልጅ ጫካ ውስጥ እንደ ውሻ ወርውሮ እስከ መጥፋትና በምናምን ጠቅልሎ ሽንት ቤት ውስጥ እስከ መጨመር ያደርሳል

👍4
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...ሳትታሰብ የተገኘቶው ትርፌ በጋሻው ለብዙዎች ያልታሰበ ደስታ
እስግኝታለች፡፡ ከሁሉም በላይ አስቻለው ተመችቶታል፡፡ ቤቱ ተዘግቶ አይውልም አይዝረከረክም፣ ኦይመሰቃቀልም፤ ትርፌ ሽክፍ አደርጋ ይዛዋለች። የሆቴል ምግብ
ትቶ ቤቱ ውስጥ መመገብ ጀምሯል። እንጻራዊ የሆነ የመንፈስ መረጋጋትም አግኝቷል፡፡ በልሁና መርዕድ እንኳ እንደ ድሮው ፍራሽ በማንጠፍ ከሰል
በማያያዝና ሻይ ወይም ቡና በማፍላት ተራ መጨቃጨቃቸውን ትተዋል።ጫታቸውን ብቻ ገዝተው በተነጠፈና በተበጃጀ ፍራሽ ላይ እግራቸውን መዘርጋት ነው፡፡ ቀሪውን ስራ ትርፌ ታቀለጣጥፈው ይዛለች፡፡
የትርፈ በአስቻለው ቤት ተመልሳ መግባት ለሔዋንም የፀጋ ያህል ሆኗል።ሔዋን የአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰደች በኋላ በወቅቱ ግዳጅ በነበረው የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ሥራ በመጀመሯ በከፊልም ቢሆን ከሸዋዬ ቁጥጥር ውጭ ሆናለች። አጋጣሚ ሆና የተመደበችው ደግሞ በዚያው በዲላ ከተማ
በዜሮ ስምንት ቀበሌ ውስጥ በመሆን ከቤት ወደ ስራ ከስራ ወደ ቤት የምትመላለሰው በአስቻለው ቤት በር ላይ ነው። እናም ስታልፍ ስታንድም ጎራ
ትልበታለች። ትርፌ ስላለች ዘወትር ክፍት ነውና አትቸገርም። ይህ ሁኔታ በእሷና በትርፌ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮት መነፋፈቅ ጀምረዋል።
አንድ ቀን ደግሞ ሁለቱን ለረጅም ሰዓት አብሮ የሚያቆይ አጋጣሚ
ተፈጠረ፡፡ የግንቦት ወር መጨረሻ አካባቢ ነው ሔዋን መሰረተ ትምህርት በምታስተምርበት ጣቢያ አካባቢ አንዲት ሴት ሞተው በለቅሶው ምክንያት በዕለቱ ማስተማር እንደማትችል ከጣቢያ ሃላፊው ይነገራታል፡፡ ከጠዋቱ ሦስት ሠዓት
አካባቢ ወደ ቤቷ ስትመለስ እግረ መንገዷን ወደ አስቻለው ቤት ጎራ ትላለች። ጊዜ ነበራትና ተረጋግታ ቁጭ በማለት ከትርፌ ጋራ ጭውውት ይጀምራሉ። ሔዋን
በአስቻለው አልጋ ላይ ትራስ ደገፍ ብላ ፣ ትርፌ ደግሞ በአልጋው ትይዩ በተነጠፈችው ፍራሽ ላይ ሆና ፊትለፊት እየተያዩ ይጫወታሉ።
«ትርፍዬ!» ስትል ጠራቻት ሔዋን፡
«ወይ እታለም፡፡»
«አገርሽ የት ነው?»
«ውይይ… እታለምዬ! በጣም ሩቅ ነው፣ ቢጠሩት እንኳ አይሰማም፡፡»
ትርፌ የገጠር ኑሮዋ ባያጎሳቁላት ኖሮ ቀይና ስልክክ ያለች፣ ዓይንና
ጥርሶቿ እዩኝ እዩኝ የሚሉ መልከ ቀና የነበረች ልጅ ትመስላለች፡፡ ያም ሆኖ አሁን ወደ አስቻለው ቤት ከተመለሰች ወዲህ ወዘናዋ እየተመለሰ መጥቷል።
«የት ቢሆን ነው ትርፍዬ?» ስትል ሔዋን ደግማ ጠየቀቻት የትርፌን
ሁለመና አየት ሰለል እያደረገች።
«ወሎዬ ነኝ፡፡»
«ውይይ... ከዚያ እዚህ ድረስ አንዴት መጣሽ?»
«ታሪኩ ብዙ ነው እታለም። ደግሞም ያሳዝናል።»
«እንዴት ትርፌ»
«በቃ ያሳዝናል፡፡»
«ከመማጣሽ ግን ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ?»
«ወደ አስር ዓመት ሊሆነኝ ነው፡፡»
«ውይይ..» አለችና ሔዋን አሁንም ግን «ግን እንዴት መጣሽ?» ስትል
ጠየቀቻት
«ተጣጥዬ»
“ማለት?»
«የወሎ ድርቅ ሲባል ሰምተሽ ታውቂያለሽ?»
«አዎ»
«በድርቁ ዘመን እኔ ህጣን ልጅ ነብርኩ። የተወለድኩት ውጫሌ እሚባል ቦታ ነው።ያኔ በድርቁ ጊዜ በአገሩ ላይ የሚበላም የሚጠጣም ጠፋ። የአገሩ ሰው ሁሉ ተነቅሎ ተሰደደ።አባቴ በድርቁ ምክንያት ቀደም ብሎ ሞቶ ስለነበር እኔና እናቴም ሕዝቡ ሲሰደድ አብረን ተሰደድን
«ወደዚህ ወደ ሲዳሞ?»
«አይደለም ወደ ደሴ ወደሚባል ከተማ ነው።»
«ታዲያ እዚያ የሚበላና የሚጠጣ አገኛችሁ?»
«እየየ እታለም! ምን ይገኛል ብለሽ? ጣጣው ብዙ ነበር፡፡» አለችና ትርፌ አሁንም በትካዜ ባህር ውስጥ ገባች፡፡ ያን በልጅነት አዕምሮዋ የተቀረፀ የርሀብ
ሁኔታ የቻለችውን ያህል ለማስታወስ ትሞክር ጀመር፡፡ ትርፌ የዚያን ጊዜ ገና
የስድስት ወይም ሰባት ዓመት ህጻን ስለነበረች ሁሉን ነገር አታውቀውም እንጂ ሁኔታው እጅጉን አሳዛኝ ነበር፡፡
«አዎ፡ እንደ ሰው ጨክኗል! የወሎ ሰማያ፡፡ ከዝናብ ሰጪ ደመናዎች ጋር ላይታረቅ የተጣላ ይመስል ቁልጭ ጥርት እንዳላ ድፍን ሶስት ዓመታት አለፉ።ፀሐይና ጨረታ ለእንዴ እንኳ በደመና ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያሉ የአየሁሽ ጨዋታ
ሳይጫወቱ በጠራው ሰማይ ላይ ተንቀለቀሉበት፡፡ በተለይ ፀሐይ በየቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት ሙሉ እየነደደች የወሎን ምድር ታነደውና ታቃጥለው ጀመር።ወንዞች ነጠፉ። ሳር ቅጠሉ ደረቀ። ዛፎች ወደ ጭራሮነት ተቀየሩ። ቢመጣ ንፋስ ቢነሳ አቧራ ብቻ ሆነ።
የወሎ ገበሬ የመጀመሪያውን የድርቅ ዓመት ቀድሞ የነበረውን ጥሪት ተጠቅሞ ሳይደናገጥ ተወጥቶት ነበር። የሁለተኛው ግን ወገቡን ሰበረው፡፡ ሶስተኛው ደግሞ ከሥሩ ነቀለው፡፡ እንኳን ለራሱ ለሰንጋ ፈረሱ የእህል ዓይነት ይመርጥ እንዳልነበረ ሁሉ እንኳን ያቀምሰው የሚቀምሰውም አጣ፡፡ በሰንጋ ፈረስ ይጋልብ የነበረ የወሎ መኳንንት፤ በሲናር በቅሎ ስትፈስ የነበረች የወሎ ወይዛዝርት ሁሉ እርካባቸው ወለቀ። ግላሳቸው ተጠቀለለ። በቅሎና ፈረሶቻቸው የአውሬና የአዕዋፍ
ሲሳይ ሆኑ። አጥንቶቻቸው ሜዳ ሙሉ ተረጩ። የረገመው ሳይታወቅ ወሎ ምዕዓት ወረደበት። የረሀብ እሳት ያቃጥለው ጀመር፡፡ በቸነፈር ተመታ።
በዚያን ጊዜ፣ በዚያን ዘመን፣ የወሎ ሕዝብ ምርጫው አንድ ብቻ ነበር፤ ስደት። አቅጣጫው ደግሞ ወደ ደሴ ከተማ፡፡ ይህም ምክንያት ነበረው፡፡ የወቅቱ
ንጉሥ ለጉብኝት ደሴ ከተማ እንደሚገቡ ተወርቶ ነበር፡፡ እሳቸው ደግሞ በሄዱበት ሁሉ ለልጆች ከረሜላ በመርጨታቸው ብቻ የቸርነት ዝናን ያተረፉ ነበሩና
የወሎ ርሃብተኛ ወደ «ቸሩ» ንጉስ በመሄድ የልመና እጁቹን ለመዘርጋት ዳር አስከዳር ተነጋግሮ ወደ ደሴ መጓዝ መትመም ጀመረ።
ከሰሜን አቅጣጫ የራያና የየጁ ሕዝብ በርሀብ የመነመነ ሰውነቱን
ብጥቅጣቂ ጨርቅ እየሸፈነ ሰንሰለት ሰርቶ ወደ ደሴ ሲግተለተል የአንባሰል ተራሮች ቁልቁል እየተመለከቱ ይታዘቡ ነበር፡፡ ከምዕራብና ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ የቦረና! የወረሂመኖ፣ የሳስታና የወገልጤና ሕዝብ ተነቅንቆ ወደ ደሴ ሲጓን በመሀል እየደከመው በገሪዶና በቦሩ ሜዳ ላይ ሲፈስ የጦሳ ተራራ መዓል ላይ ቆሞ ግራና ቀኝ እየተመለከተ ያለቅስ ነበር፡፡ ከምስራቅና ከደቡብ ምሥራቅ
ደግሞ የአውሳ የቃሎ፣ የእንቻሮና የከሚሴ ሕዝብ በበረሃ አለባበስ ዘይቤው ከወገብ በታች ሽርጥ መሳይ አገልድሞ ከወገቡ በላይ ሲያዩት ግጠው ግጠው የጣሉት
አጥንት መስሎ ወደ ደሴ ሲተምም የቦርከና ወንዝ «እናንተስ ወደ ንጉሳችሁ ሄዳችሁ፤ የእኔንስ ችግር ለአባይና ለተከዜ ማን ይንገርልኝ»
እያለ የሚያዝን ይመስል ነበር፡፡
በጋ ከክረምት የውሃ ፈረሰኛ ሲያጓራበት እንዳልነበረ ሁሉ ያኔ ግን ክው ብሎ ደርቋልና በውስጡ የነበሩ ቋጥኛች ጨው መስለው የፀሐይ ንዳድ እየፈነከታቸው ነበር፡፡
ያ ሁሉ የወሎ ርሀብተኛ በዚህ መልክ ተጉዞ ተጉዞ ደሴ ከተማ ሲደርስ ያሰበው አልሆነለትም። እንዲያውም ወደ መሀል ደሴ ከተማ መግባት እንኳ ሳይፈቀድለት ቀረ። የንጉሡ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች በየመጣበት አቅጣጫ ተሰልፈው ጠበቁት። ከስሜን በኩል የመጣውን በሮቢት ገበያ ላይ፣ ከምዕራብ በኩል የመጣውን ከሰኞ ገበያ ላይ እንዲሁም ከምስራቅና ደቡብ ምስራቅ እቅጣጫ የመጣውን
ርሀብተኛ ሀረጎ አፋፍ ላይ በተሰራ የእንጨት አጥር ውስጥ እያስገቡ አጎሩት። በቀን አንዳንድ ዳቦ ለእያንዳንዱ ርሀብተኛ እንደ ውሻ ይጥሉለት ጀመር፡፡ እንዳይነቃነቅ ይጠብቁትም ጀመር።

👍9
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
“ይደልዎ ይደልዎ”
ምንትዋብ፣ ኢያሱ በነገሠ በሁለተኛው ወር ረጅም ነጭ ሐር ቀሚስ ለብሳ፣ በወርቅና በዕንቁ የተንቆጠቆጠ ካባ በላዩ ላይ ደርባ፣ በወርቅ አጊጣ፣ ፊቷን በነጭ ዐይነ ርግብ ከልላ፣ የወርቅ በትረ መንግሥት ጨብጣና ከወርቅ የተሠራ ነጠላ ጫማ ተጫምታ ተሸልማ በወጣችው
በቅሎዋ ላይ ተሰይማ፣ የንግሥ ሥርዐት ወደሚፈጸምበት ወደ መናገሻ ግንብ አመራች።
መናገሻ ግንብ ውስጥ መሣፍንት፣ መኳንንት፣ አዛዦች፣ ካህናት፣ ሊቃውንትና ወይዛዝርት
እንደየማዕረጋቸው ቦታቸውን ይዘው የንጉሥ መሞት የሚያመጣውን ቀውስ ጠንቅቃ
የምታውቀው ምንትዋብ፣ አክሱም ጽዮን የሚደረገውን ሁለተኛውን
የኢያሱን የንግሥ ሥርዐት አስቀርታ በነገሠ በወሩ ብርሃን ሰገድ የሚል ስመ መንግሥት ከተሰጠው ከዳግማዊ ኢያሱና ከቤተሰቦቿ ጋር ስትገባ ሁሉ ተነሥቶ እጅ ነሳ።
በወርቅ ያጌጠውን የአባቱን ዘውድ የጫነውና የእሳቸውን የወርቅ
በትረ መንግሥት የጨበጠው ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ከተቀመጠበት ተነስቶ፣ “እናቴን አንግሡልኝ፣ መንግሥቴ ያለሷ አይጠናም” ሲል ተሰብሳቢዎቹ፣ “ይደልዎ ይደልዎ! ይገባታል! ይገባታል! ጎበዝ ክርስቲያን፣ አዋቂ ናት። ሽህ ዓመት ንገሥ። የቆስጦንጢኖስን ምሽት
እሌኒን ትመስላታለች” አሉ።
አንጋሹ ጽራግ ማሰሬ ማሞ ከዕንቁ፣ ከወርቅና ከብር የተሠራውንና በሻሽ ተሸፍኖ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠውን የአፄ ሚናስ የነበረውን ዘውድ አንስተው ምንትዋብ ራስ ላይ ጭነውላት ሲያበቁ ዝቅ ብለው ሰገዱላት፣ ከኢያሱ ቀኝም አስቀመጧት።
ባራኪው እልፍዮስ፣ “እዝጊሃር ክፉዎችን እንዲያሸንፉ ኃይል ይስጥዎ። ክብርዎን ያብዛልዎ። ፈሪሐ እዝጊሃርን በልብዎ ያሳድርልዎ። አቤቱ አምላካችን ሆይ! በአገልጋይህ በእቴጌ ምንትዋብ ላይ እኼን የደስታና
የክብር ዘውድ አኑር፤ እኼውም የቸርነት፣ የርህራሄ፣ የዕውቀትና የጥበብ ዘውድ ይሁንላቸው” ብሎ ሲባርካት፣ ከኋላዋ ቆመው የነበሩት ሴት የመሣፍንት ዘሮችና ወይዛዝርት ዕልልታውን አቀለጡት።
ምንትዋብ ለአምላኳ በልቧ ምስጋና አቀረበች።
ካህናት ዘመሩ፣ ወረቡ፣ ሊቃውንቱ ቅኔ አወረዱ። እንደ ንግሥተ
ሳባ፣ እቴጌ እሌኒ፣ እቴጌ ሰብለወንጌልና እቴጌ መስቀል ክብራን የመሳሰሉ የታላላቅ ሴቶች ስም እየጠቀሱ አሞካሿት። “አንቺ እሌኒ ማለት ነሽ። ልዥሸን ብርሃን ሰገድ ኢያሱን ኸጎኑ ሁነሽ እንደምትረጂው አንጠራጠርም” ሲሉ እሷ ላይ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገለፁላት።
ምንትዋብ፣ አባቷ ዕጣ ፈንታ፣ እናቷ ዕድል አያቷ ግን የተገባት ያሉትን ስትጎናፀፍ ተስተዋለ።
ሕይወት ሲሻት ለጋሥ መሆኗን አስመሰከረች።
ባለ ክራሩና ባለ መሰንቆው የውዳሴና የሙገሳ ግጥም ሲያንቆረቁር፣ፎካሪው በቀረርቶ፣ ሽላዩ በሽለላ የበኩሉን ምስጋና አበረከተ። አንዱ ሀሚና ተነሰቶ በመሰንቆ፣
በወለተጴጥሮስ ተወልዳ በንግርት፣
በእዝጊሄር ፈቃድ በነብያት ትንቢት፤
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ያገራችን ውበት፤
የምታስተባብር ጥድቅ ተሃይማኖት፣
ዳር ድንበር ጠባቂ ያባቶቿን ርስት፣
ኸዝኸ በላይ ጠጋ ኻአምላክ መሰጠት፣
ምንድን ሊሰጧት ነው ምንትዋብ ሚሏት?
እያለ ሲያሞግሳት፣ የተሰበሰበው ሰው ደግሞ እሱን አመሰገነው።
ነጋሪት እየተጎሰመ፣ መለከት እየተነፋ ከመናገሻ ግንብ በደጅ
አጋፋሪው አቀናባሪነት የፊቱን ወጀብ ሰንደቅ የያዙ፣ የእልፍኝ አሽከሮች፣ባለሟሎችና ሠይፈ ጃግሬዎች ፈንጠር ብለው እየመሩ፣ የመሃል ዐጀቡ
በእልፍኝ አስከልካዩ እየተጠበቀ፣ ኢያሱና ምንትዋብ ጎን ለጎን ሆነው
ድባብ ተይዞላቸው፣ መሣፍንት፣ መኳንንት፣ ሊቃውንት፣ ወይዛዝርት፣ግራዝማቾች፣ ቀኛዝማቾችና የጦር አበጋዞች እንደየደረጃቸው ከኋላ
እያጀቧቸው፣ ሰልፍ አስከባሪዎቹና የንጉሠ ነገሥቱ ጠባቂ የሆኑት ጋሻዐጃግሬዎቹ ተከትለው የሰልፉን ግራና ቀኝ አንጋቾች እየጠበቁ ራስ ቢትወደዱ በመጨረሻ ተሰልፈው ነገሥታቱ በዘፈንና በጭፈራ ከግቢ
ሲወጡ ካህናት፣
መንክር ግርማ መንክር ግርማ
ወልደልዑል ጸለላ መንክር ግርማ
የምትደንቅ ግርማ ሞገስን
የምትደንቅ ግርማ ሞገስ
የወልደልዑል ልጅ፣ እጅግ የላቀው አባት ልጅ፤
እያሉ፣ ምንትዋብ በወንድሟ በወልደልዑል መከታነት መንገሧን
በቅኔ ጠቅ እያደረጉ በፀናፅልና በከበሮ ዐጀቧት።
ዘውዷን እንደጫነች በቅሎዋ ላይ ተሰይማና ታጅባ፣ ወደ ሕዝቡ
አመራች። ከጐንደርና ከአካባቢዋ የመጣው ነፍጠኛ፣ ገበሬ፣ እረኛ፣
ነጋዴ፣ ወታደር፣ አንጥረኛ፣ ሸማኔ፣ ቆዳ አልፊ፣ ጥልፍ ጠላፊ፣ ሹሩባ ሠሪ መድኃኒት አዋቂ፣ ወጌሻ፣ የቤት እመቤት፣ አረቄና ጠላ ሻጭ፣ ዲያቆን ተማሪ ፣ የቁም ጸሐፊ፣ ሠዓሊ፣ ብራና ሠሪ፣ ባለክራሩና ባለመሰንቆው
ሴቱ ሹሩባውን አንዠርጎ፣ ነጠላውን አጣፍቶ፣ ወገቡን በድግ ደግፎ ማተቡ ላይ የእንጨት መስቀሉን፣ ድሪውን፣ ጨሌውን፣ ዶቃውን ቁርጭምጭሚቱ ዙርያ አልቦውን፣ የእጁ አንጓ ላይ አንባሩን ደርድሮ ገሚሱ የቀርከሀ ጃንጥላውን አጥልቶ፣ ወንዱ ፀጉሩን አጎፍሮ፣ ለምዱን ደርቦ፣ ዱላውን ትከሻው ላይ ጣል አድርጎ፣ ልጆች ጥብቋቸውን
አጥልቀው፣ ክታባቸውን አንጠልጥለው ምንትዋብ ከኢያሱ ጋር ጃን ተከል ብቅ ስትል አካባቢው ድብልቅልቁ ወጣ።
ሴቶች በዕልልታና በእስክስታ፣ ወንዶች በሆታና በጭፈራ አካባቢውን አናጉት፤ ካህናት በሽብሸባ አደመቁት። እነምንትዋብ ካለፉ በኋላ፣
ሕዝቡ መስመሩን ተከትሎ እየሮጠ ዕልል! ሆ! እያለ ዐጀባቸው።
ጐንደሬዎች እንደዛ ውበት የነገሠበት ሰው አይተው አያውቁምና በምንትዋብ ውበት ተደመሙ። “አቤት መልኳ እንደ ጠሐይ ሚያበራ አቤት ወርቅ አካል!” እያሉ ተደነቁ። በደስታ ተሳክረው ለአፄ ፋሲለደስ፣
አሁን ወጣ ጀንበር
ተደብቆ ነበር
ተብሎ እንደተዘፈነው ሁሉ ለእርሷም፣
አሁን ወጣች ጀንበር
ተሸሽጋ ነበር
እያሉ አዜሙ፤ ጨፈሩ።
አሁን ወጣች ጨረቃ፣
የምትለን ፍርድ ይብቃ።
ደስ ይበልህ ዘመድ፣
ከነገሠች በዘውድ።
ደስ ይበልሽ ወይዘሮ፣
ጭና መጣች ወገሮ።
ደስ ይበልህ ባለእጌ፤
ነገሠች እቴጌ።
ደስ ይበልህ ጐንደር፤
ቀድሞ ከፍቶህ ነበር፣
ሲሉ ጐንደሬዎች ለውዷ ከተማቸው መልካሙን ተመኙላት።
ምንትዋብ የተስፋ ጨረር ፈነጠቀችላቸው።
ዐዲስ ንጉሥ በመጣ ቁጥር የተስፋ ስንቅ ሰንቆ የሚወጣው
መልካሙን ተመኘ ለጦርነት ሳይዳረግ፣ በወታደር ሳይዘረፍ፣ ሚስቱና ልጁ ሳይደፈሩ እኖራለሁ በሚል ተስፋ፣ ከትናንቱ ዛሬ ይሻለኝ ይሆን በሚል ምኞት።
ጐንደሬዎች ምንትዋብን ወደዷት፤ ቀልቧ ገዛቸው፤ መልኳ
አባበላቸው፤ ግርማ ሞገሷ ማረካቸው፣ ኩራታቸው በእሷ ሆነ። በዓለ ንግሥናዋን አደመቁላት፤ ዐደራቸውን ሰጧት፤ ተስፋቸውን ልባቸው ጫፍ ላይ አንጠልጥለው ፎከሩላት፤ ሽለሉላት፤ ዘፈኑላት፤ ጨፈሩላት፤
ዕልል! ሆ! አሉላት።
ጥላዬ፣ ከእነአብርሃ ጋር ከካህናቱ ኋላ ሆኖ አብሮ እየዘመረ ሲሄድ
ድንገት ምንትዋብን ከኢያሱ ጋር አያት። የለበሰችው ነጭ ሐር ቀሚስ፣ፊቷን የጋረደው ነጭ ዐይነርግብ ከፀሐይዋ ብርሃን ጋር ተደምሮ ዐይኑ ላይ አንፀባረቀበት። ያየውን ሁሉ ማመን አቃተው። የባሏ ለቅሶ ላይ አዝኖላት እንባውን እንደረጨላት ሁሉ አሁን የያዘውን የደስታ ሲቃ መቆጣጠር አቃተው። እንባው ፊቱን አራሰው። እነአብርሃ እንባውን እንዳያዩበት በሰዉ መሃል ተሸለክልኮ ወጥቶ “ኸንግዲህ ደብረ ወርቅ ብመለስም አይቆጨኝ” ብሎ ወደ ቤት ሄደ።

👍16
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
በሰፊ ውብ አፏ እየሳቀችብኝ፡ እየወደደችኝ ድንገት ሳቁን እየተወች አንድ ነገር ልነግርህ እፈልግ ነበር» አለችኝ ንገሪኝ
እንዳትቆጣ፡፡ ወንድ ሆነህ አትስማኝ፡ ደራሲ ሆነህ አዳምጠኝ እንጂ
«እሺ»
"Parole d'honneur?"
"Parole d'honneur!"
«አንተን እወድሀለሁ። ከልቤ አፈቅርሀለሁ፡፡ ግን ፖልን ልረሳው
አልችልም። የመጀመሪያዬ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ ሳልጠግበው
ስለሄደብኝ ጭምር ይመስለኛል። «ይገባሀል?»
«ይገባኛል»
«እና አንድንድ ጊዜ ይናፍቀኛል፡፡ ይመስለኛል፣ በውስጤ
የልጃገረድነቴ ጊዜያት ከሱ ጋር ተዋህዷል፡፡ እና ያ ጊዜያት
ሲናፍቀኝ፣ ፖል ይናፍቀኛል። ከልቤ ላወጣው ልረሳው እሞክራለሁ።
ግን የምችል አይመስለኝም፡፡ የምልህ ይገባሀል?»
«ይመስለኛል»
«ስለዚህ ፖልን የሚመስል ሰው ሁሉ ደስ ይለኛል፤ ይስበኛል።
... እና ስለ ባህራም ልነግርህ እፈልጋለሁ፡፡»
ይናገራል ብላ ዝም አለች። መናገሩ እየከበዳት ሄዷል። ዝም
ብዬ ሳያት ቀጠለች
«አንተ ነህ ባህራምን እንድወደው ያረግከኝ፡፡ ስለሱ ብዙ ብዙ
አወራህልኝ። አራት ወር ሙሉ አወራህልኝ፡፡ ከወሬህ እንዳየሁት፣
በጣም በጣም ታከብረዋለህ። ግን እንደማውቅህ አንተ ማንንም
አታከብርም፡፡ ስለዚህ፣ ይሄ ባህራም እንዴት ያለ ሰው ቢሆን ነው? አልኩ። አንዲት ሴት እንዲህ ካለች ደሞ መመለሻ የላትም። ይህን ያባሰው ምንድነው? ከወሬህ እንደተገነዘብኩት ባህራም እንደ ፖል ያለ ሰው ነው። እንደሌላው ሰው ከተራ ጭቃ ተጠፍጥፎ አልተሰራም፡፡ ጀግናዎቹ ከሚሰሩበት ከልዩ ጭቃ ተቀርፆ፣ በልዩ ንፁህ እሳት ውስጥ ነው የተጠበሰው። ባህራምን እንደዚህ አድርገህ
ነው ያሳየኸኝ
«አንተ ያንን ያህል እያከበርከው፣ ከፖል ጋር ያንን ያህል
እየተመሳሰለ፣ እንዴት ላይለኝ ይችላል? እኔ ደሞ
እንደምታውቀኝ ነኝ:: እንዴት ላልመኘው እችላለሁ?»
«ፍቅር ይዞሻል?»
ራሷን በሀይል
እየነቀነቀች፡ ከኋላዋ ጥቁር ሀር ፀጉሯ እየተወዛወዘ፣ የደስታ ሳይሆን የመሰቃየትና የመደናገር ፈገግታ ውብ አፏን እየሸመቀቀው
እኔ እንጂ! እኔ እንጃ! እኔ እንጃ!» አለችና ራሷን ጠረጴዛው ላይ
ደፋች
ረዥም ፀጥታ
እጄን ሰድጄ ራሷ ላይ አሳረፍኩት። ቀና ብላ አየችኝ፡፡ እምባዋ
ይወርዳል
«ሶስት ፍቅር አንድ ላይ ሊይዝ ይችላል?» አለችኝ
“ሴትዮዋ ተራ ከሆነች አይችልም» አልኳት
ጠረጴዛው ላይ የነበረ እጄን ወስዳ ከጎንጯ ጋር እያተሻሸት፣
በእምባዋ እጄን እያረጠበች፡ በተጨነቀ ድምፅ
«ብዙ ጎዳሁህ፣ የኔ ቢራቢሮ?» አለችኝ
ግድ የለሽም አልኳት
«አለኝ እንጂ። ላንተ ብዙ ግድ አለኝ፡፡ ለዚህ እኮ ነው
የምነግርህ፡፡»
«አውቃለሁ»
ለኔ እንዴት ጥሩ ነህ! አሁን ምን ይሻለኛል?»
ቆንጆ ነሽ። ተወዳጅ ነሽ፡፡ ለምን አትወጂውም?»
በመሀረቤ እምባዋን እየጠረገች
«አንተስ? አትቀየምም?»
ሌሎች ጋ ትሂጂ የለ? ስለዚህ ለኔ ያው ነው»
ውይ! እንዴት ደግ ነህ!?»
«ለምን?»
ውሸትክን ነዋ» ተናፈጠች
እኔ እንድደሰት ብለህ
ትሰቃያለህ፡፡»
«የምን ስቃይ?»
መሀረቤን አጥፋ እየመለሰችልኝ
«እንግዲህ አትዋሽ። ይበቃሀል። አውቅሀለሁ'ኮ። ከምትገምተው
በላይ አውቅሀለሁ፡፡ ፊትህ ላይና አይኖችህ ውስጥ ስንትና ስንት ነገር ይታየኛል መስለህ።»
«ምን ይታይሻል?»
«ስለባህራም ስነግርህ በብዙ ነው ያዘንከው::
«ላንቺ ነዋ ያዘንኩልሽ፡፡
«እሱም ታይቶኛል። ግን ለራስህም በሀይል በመሰቃየት ላይ ነህ፡፡ እና በጣም አዝናለሁ፡፡ እንዲህ በመሆኔ በጣም አዝናለሁ፡፡»
«በማዘን የትም አይደረስም፡፡»
አውቃለሁ የኔ ቆንጆ:: ግን ማዘን አይቀርም፡፡»
ዝም ዝም ሆነ
«በኔ ብቻ ሳይሆን በባህራምም ጭምር ነው ያዘንከው። ልክ
ዝም አልኳት
«እንግዲህ ልንገርህ፡፡ እውነቱን ብታውቅ ይሻላል። ልንገርህ?»
«እሺ፡፡»
«ያን እለት ማታ ያ ሰውዬ ባህራምን ሊገድለው አልመጣም?
እና አንተ ኒኮልን ይዘህ ማርዕይ አልሄድክም? ከኒኮል ጋር
ምንም አልሰራችሁም? እውነት ተናገር፡፡»
«ምንም አልሰራንም፡፡ ይልቅ ቀጥዪ።»
«እና ሰውየውን ሲገድለው አላየሁም? እሱን ነግሬሀለሁ። እና
ከዚያ ወደ ቤት ሄድን፡፡ ባህራም ልክ ምንም እንዳልስራ በእርጋታ
ሶፋ ላይ ተቀመጠ። እኔ መጠጥ ሰጠሁትና ሶፋው ላይ አልጋ ብጤ
አነጠፍኩለት፡፡ አንጥፌ ስጨርስ 'እንግዲህ እዚህ ውስጥ ይተኛል።
ነብስ ገድሏል፤ ግን እዚህ ውስጥ ይተኛል። ከጀግና ጋር ነው'ኮ
ያለሁት። ከነብሰ ገዳይ ጋር ነው ያለሁት ብዬ አሰብኩ፡፡ ዘወር ብዬ
አየሁት። አንተ እንደ ነገርከኝ ነው። ዝም ሲል የኢራንን ሻህ
ይመስላል። ግን ማን ያውቃል? ጀግና ስለሆነ አንድ ቀን የኢራንን
ሻህ ይገድለው ይሆናል'ኮ!' ብዬ አሰብኩ
«እና በሀይል ተመኘሁት፡፡ ፍትወት ያንን ያህል አንቆ ይዞኝ
አያውቅም፡፡ ራሴን 'ተይ እንደሱ አታርጊ! - ተይ!'
እያልኩ
ከተቀመጠበት ሄድኩና እግሩ አጠገብ ተምበርክኬ ወደላይ አየሁት።
እንደ ቄስ እጁን ራሴ ላይ አሳረፈና
«ምን ሆነሻል?» አለኝ
ቀስ ብዬ ተነሳሁና አፉ ላይ ሳምኩት
አሁንም «ምን ሆነሻል?» አለኝ። ግን ገብቶታል
«ፈልጌሀለሁ» አልኩት
«እኔ አልፈልግሽም» አለ
«አውቃለሁ ትፈልገኛለህ፡፡ ትፈልገኝ የለ?»
«አዎን፡፡ ካየሁሽ ጀምሮ እንደፈለግኩሽ ነው::»
«ይኸዋ፡፡ አለሁልህ!»
«አይሆንም!»
«ለምን አይሆንም?»
«ምክንያቱን መቼ አጣሽው» አንተን ማለቱ ነው
«እሱ ንደሆነ ግድ የለውም» ኣልኩት
«እኔ ግድ አለኝ!»
«ለምን?»
«ጓደኛዬ ነው:: እፈልግሻለሁ፡፡ ግን እሺ አልልሽም። ስለዚህ
እርሺው!»
«አልረሳውም፡፡ ልረሳው አልችልም፡፡ ልረሳው አልፈልግም።
ሌሊት እመጣለሁ!» አልኩትና ሄጄ አልጋዬ ውስጥ ገባሁ፡፡ ልተወው
ቆረጥኩ። ምናልባት አንድ ሰአት ያህል ቆየሁ። ከዚያ በላይ ግን
ልቆይ አልቻልኩም፡፡ እንደዚህ አላስችል ያለኝ እሱ ስለሆነ ብቻ
ነበር፣ ወይስ ሰው ሲገድል ስላየሁት ነበር? አላውቅም፡፡ የሆነ ሆኖ፣ እሱ እዚያ ተጋድሞ እኔ እዚህ ሆኜ ልታገስ አልቻልኩም
ራቁቴን ወጣሁ፡፡ ሽቶ ተቀባሁ፡፡ ከመኝታዬ ወጣሁ፡፡ የንግዳ
ቤቱን መብራት አበራሁ። እንቅልፍ አልወሰደውም ነበር። በቀጥታ
ሄድኩና ከበላዩ ቆምኩ፡፡ ወደላይ አየኝ፡፡ ሲያየኝ ብዙ ጊዜ ቆየ፡፡
እጁን ሰደደ። ጭኔን ይዞ ወደታች ጎተተኝ
ካሸነፈኩት በኋላ ወደ አልጋዬ ሄድን፡፡»
ዝም አለች፡፡ ያችን ሌሊት እንደምታስታውስ ያስታውቃል፡፡
እንዴት ያለች ሌሊት ነበረች ይሆን? ብጠይቃት እንደማትነግረኝ
እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ስለሌሎቹ ወንዶች በሰፊው ትንገረኝ እንጂ፣
ስለነሱ ጥቃቅኑን ስጋዊ ተግባር ሳይቀር ትዘርዝርልኝ እንጂ፣
ስለፖልና ስለ ባሀራም አትነግረኝም፡፡ እኔም ስለነሱ መጠየቅ ልክ አልመሰለኝም፡፡ ዝም አልኩ። ቀጠለች
«ስለሌሊቱ ልንገርህ እንዴ?» አለችኝ
«ልትነግሪኝ ትፈልጊያለሽ?»
«አልፈልግም። ከፈለግክ ግን እነግርሀለሁ።»
ይህን ያለችኝ «ሳትፈልጊ ብትነግሪኝ ደስ አይለኝም»
እንደምላት አውቃ ነው እንጂ፡ ንገሪኝ ብላትም እንደማትነግረኝ
አውቃለሁ
«ሳትፈልጊ ብትነግሪኝ ደስ አይለኝም» አልኳት

👍16🤔3
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
አሮጌው ቤት
ከአርባ ዓመት በፊት እጅግ ጭር ያለ ሰፈር የነበረው ዛሬ ብዙ
ሕዝብ ይተራመስበታል፡፡ ገጠር መሆኑ ቀርቶ ወደ ከተማነት ተለውጧል፡፡ አካባቢው ዣን ቫልዣ ሲያውቀው ከፓሪስ ከተማ ወጣ ያለ ባላገር ነበር፡፡ዛሬ የከተማው አካል ሆኖአል፡፡ ብዙ ቤቶች ተሠርተዋል፤ መንገድም
ወጥቶለታል፡፡ ቢሆንም ግን የገጠርነት ስሜት አሁንም ይታይበታል፡፡ከመንገዱ ግራና ቀኝ ሳር በቅሎአል:: ቤቶቹም ቢሆኑ እስከዚህም የጸዱ አይደሉም፡፡ የፈረስ ገበያ ከዚያ አካባቢ ስለነበር የስፍራው ጽዳት ይህን
ያህል አያስደስትም::
ከዋናው መንገድ ትንሽ ራቅ ብሎ የሚታይ ባለአንድ ፎቅ አሮጌ ቤት
አለ፡፡ በሮቹ በምስጥ ስለተበሉ አልፎ አልፎ ቀዳዳ ይታይባቸዋል:: የቤቱ መስኮቶች በጣም ሰፋፊ ናቸው:: የመስኮቶቹ መስታወት አንዳንዶቹ ስለተሰበሩ
በካርቶን መሳይ ወረቀቶች ተሸፍነዋል :: መጋረጃዎቹም ቢሆነ
ከመበለዛቸውም በላይ ጫፍ ጫፋቸው ተቀዳደዋል:: ወደ ፎቅ በሚያስወጣው መሰላል ሲራመዱ ደረጃው እንደ መዚቃ መሣሪያ ያፍጮሃል:: በረት የመሰለ
ትልቅ ክፍል ከሩቁ ይታያል፡፡ የዚህ ክፍል ሀለቱም መስኮቶች ሰፋፊ ሲሆኑ በዚያ በኩል ወደ ውጭ በማየት በመንገድ የሚያልፈውን ማየት ይቻላል::የቤቱ ቁጥሩ 5052 ነው
ዣን ቫልዣ ከዚህ አሮጌ ቤት አጠገብ ሲደርስ ቆም ብሎ ቤቱን
አየው:: ጭልፊት የሚያሳድዳት ጫጩት የተሰወረ ከለላ እንደምትፈልግ ሁሉ እርሱም ከነዣቬር ለመሰወር ከለላ ይፈልጋል:: የዚህ ቤት አቀማመጥ
ደግሞ በጣም የተሰወረ ስለነበር የሚፈልገውን ያገኘ መሰለው፡፡ ከኪሱ ውስጥ ቁልፍ አውጥቶ በሩን ከፈተው:: ከገባ በኋላ መልሶ ዘጋው:: ኮዜትን ታቅፎ በደረጃው ወደ ፎቅ ወጣ፡፡ ደረጃውን ወጥቶ ሲጨርስ ሌላ ቁልፍ ከኪሱ አወጣ፡፡ የተቆለፈውን በር ከፍቶ ወደ አንድ ክፍል ገባ፡፡
ስፋ ካለ ክፍል ወለል ላይ ትልቅ ፍራሽ ተዘርግቷል፡፡ ጥቂት
ቦታ ወንበሮችና ጠረጴዛም አለ፡፡ የእሳት ማንደጃ ከአንድ ጥግ ይታያል:: አንድ ትንሽ የልጅ አልጋም አለ፡፡ ዣን ቫልዣ ቀስ ብሎ ኮዜት ሳትነቃ ከትንሹ አልጋ ላይ አስተኛት::
በሩን መልሶ ከዘጋ በኋላ ሻማ አበራ:: የመንገዱ መብራት ክፍሉን
ያሳይ ስለነበር ሻማ እስካበራ ድረስ በጨለማ አልተንገዳገደም:: በአለፈው ቀን እንዳደረገው ሁሉ ኮዜት ተኝታ ሳለ ዐይኑን ከዐይንዋ አላነሳም:: ለረጅም ጊዜ ኣፍጥጦ ተመለከታት:: ኮዜት ከማን ጋርና የት እንደተኛች ሳታውቅ ለብዙ ሰዓት እንቅልፍዋን ለጠጠች::
ዣን ቫልዣ ጎንበስ ብሎ እጅዋን ሳማት:: ከዘጠኝ ወር በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ እንቅልፍ ወስዶአት ሳለ የእናትዋን እጅ ስሞ ነበር፡፡
ተመሳሳይ የሆነ የሀዘኔታና የጭንቀት ስሜት ተሰማው:: ኮዜት ከተኛችበት አልጋ አጠገብ ተንበረከከ፡፡
ወገግ ብሎ ነግቷል:: ግን ልጅትዋ አሁንም እንቅልፍ እንደወሰዳት
ናት። ከባድ እቃ የጫነ ጋሪ በዚያ ሲያልፍ ያንን አሮጌ ፎቅ ቤት አነቃነቀው፡፡ ኳኳታው በኃይል ስለነበር እንኳን የትኛን የሞተን ይቀሰቅሳል ማለቱ የድምፁን ብርታት መግለጽ እንጂ ማጋነን አይሆንም::
«እመት እመቤቴ» አለች ኮዜት ፈንጠር ብላ ከአልጋው እየተነሳች::
ቀጠለችና ደግሞ መጣሁ መጣሁ» ስትል ጮኸች:: ዓይንዋን ሳትገልጥ ካልጋው ዘላ ወረደች።
እየተንጠራራች ወደ ግድግዳው ሄደች።
«ወይ ጣጣ፤ መጥረጊያው የት አለ!» አለች::
ኣሁን ዓይንዋን ገልጣለች:: በፈገግታ ያጌጠ የዣን ቫልዣን ፊት
ተመለከተች::
«እህ! ለካስ…» አለች ልጅትዋ ፧ «እንደምን አደሩ ጌታዬ::»
ቶሉ ብሎ አካባቢውን መላመድና ባለው መደሰት የልጆች ባህርይ
ነው:: ተደሳች ሁነው ሰው ያስደስታሉ፡፡
ኮዜት ካተሪንን ከአልጋዋ ስር አየቻት፡፡ ወዲያው ብድግ አድርጋ
አቀፈቻት፡፡ ከአሻንጉሊቱ ጋር እየተጫወተች ዣን ቫልዣን የመዓት ጥያቄ ጠየቀችው:: የት ነበረች? ፓሪስ ትልቅ ከተማ ነው? አሁን መዳም ቴናድዬ ከዚህ አይመጡም? ከዚህ የሚስስ ቴናድዬ ቤት ምን ያህል ይርቃል?
ሌላም፧ ሌላም፡፡ በመስኮቱ ወደ ውጭ አይታ «እንዴት ያምራል፤ እንዴት ደስ ይላል» ስትል ተናገረች::
የነበረችበት ሁኔታ በመጠኑም ቢሆን ያስፈራ ነበር፡፡ ነገር ግን
እርስዋ ነፃ የወጣች መሰላት::
«ቤቱን ልጥረግ?» ስትል ጠየቀች::
«የለም፧ ተጫወች» ሲል ዣን ቫልዣ መለሰላት::
ስትጫወት ቀኑ አለፈ:: ስላለችበት ሥፍራም ሆነ ሁኔታ ለማወቅ
ራስዋን ሳታስጨንቅ ከአሻንጉሊትዋ ጋርና ከጓደኛዋ ጋር እየተጫወተች ደስ ብሎአት ነበር የዋለችው::
በሚቀጥለው ቀን ጎሕ ሲቀድ እንዳለፈው ቀን ኮዜት ስትነቃ ለማየት ዣን ቫልዣ ከአልጋው አጠገብ ሲቀመጥ አዲስ ስሜት ተሰማው፡፡ ዣን ቫልዣ ከዚያ በፊት ምንም ነገር አፍቅሮ አያውቅም፡፡ ትዳር ሳይዝ፣ ልጅ ሳይወልድ ፤ ሴት ሳያፈቅርና የልብ ጓደኛ ሳያበጅ ለሃያ አምስት ዓመት ብቻውን ነው የኖረው:: እስር ቤት ሆኖ ኑሮው የጨለማና የስቃይ ነበር፡፡
ዣን ቫልዣ እስር ቤት ከመግባቱ አስቀድሞ ከቤቱ ሲወጣ ልቡ በተስፋ የደነደነ፤ ሐሞተ ሙሉ ሰው ነበር:: እህቱና ልጆችዋ ከሕሊናው ጨርሰው
ባይፋቱም በአሳብ የሚታዩት እጅግ ተንነው ሲሆን እነርሱን ለማግኘት ብዙ ጥረት አደረገ፡፡ ግን አላገኛቸውም:: ጊዜ እንደሚሽረው እንደማንኛውም ነገር ከጊዜ በኋላ ግን ረሳቸው:: ሌሎችም በወጣትነት ዘመኑ የሚያውቃቸው
ነገሮች ሁሉ እንደዚሁ ከሕሊናው ውስጥ መንምነው ጠፍተዋል፡፡
ኮዜትን አግኝቶ ከዚያ የስቃይና የመከራ ኑሮ ሲያወጣትና ይዞአት
ሲሄድ ስሜቱ እጅግ ይነካል፡፡ ይህም ለሰው ልጅ የነበረውን ፍቅር ቀሰቀሰበት። የፍቅሩ ጽናት ከዚህች ልጅ ዙሪያ ተሰባሰበ፡፡ ወደ ኮዜት አልጋ ጠጋ ብሎ ሲመለከታት ልቡ በደስታ ፈካ:: እናት ለልጅዋ ፍቅር እንደምትብረከረክ ሁሉ እሱም በዚህች ልጅ ፍቅር መዋጡ ገረመው፡፡
የፍቅሩ ግለትና የሀዘኔታው ብዛት ሊገባውና በቃላት ሊገልጸው ከሚችለው እርሱ ሃምሣ አምስት ዓመቱ ሲሆን እርስዋ ስምንት ዓመትዋ ነው:: ስለዚህ ፍቅሩ ግሪኮች አጋፔ ብለው የሚጠሩት እናት ለልጅዋ ያላት ፍቅር
ዓይነት እንጂ የሌላ አልነበረም፡፡
በሕይወት ዘመኑ ለሁለተኛ ጊዜ የሕይወት ተመስጦአዊና አስጨናቂ ትርኢት አየ፡፡ ከእስር ቤት ሲወጣ ያገኛቸው ጳጳስ የሕይወቱን አድማስ
ያሰፉለትና የሕይወት ጣዕም ሕያቀደዱለት የመጀመሪያው ፍጡር ናቸው፡፡
ኮዚት ደግሞ ተጨማሪ የፍቅር ጎሕ ከፈተችለት፡፡ ይህንኑ እያሰላሰለ ጥቂት ቀናት አለፉ::
አሳዛኝዋና ምስኪንዋ ኮዜትም ቢሆን ሳይታወቃት እየተለወጠች
ነበረ፡፡ እናትዋ ጥላት ስትሄድ ጨቅላ ልጅ ነበረች፡፡ በዚያን ጊዜ ምን ትመስል እንደነበር ለማስታወስ አትችልም፡፡ ልጆች እንደ ሐረግ ካገኙት ላይ እንደሚጠመጠሙ ሁሉ እርስዋም ከሰዎች ላይ ተጠምጥማ ለማፍቀር ብትሞክርም ሰዎች የማፍቀር እድል አልሰጥዋትም ነበር፡፡ እነሚስተር ቴናድዬ ፤ ልጆቻቸውና ሌሉችም ቢሆኑ ፍቅር አላሳይዋትም: ከቤታቸው
የነበረውን ውሻ ትወደው ነበር፡፡ ግን እሱም ሞተ፡፡ ውሻው ከሞተ ጀምሮ እንኳን ሰው የቤት እንሰሳም ቢሆን አላቀረባትም:: ስለዚህ ጥፋቱ የእርስዋ ባይሆንም ገና በስምንት ዓመትዋ ለሰው ፍቅር አልነበራትም:: ቢወድዋት

👍12
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...መቼም ባልቻን በግልፍተኛነት የሚያማዉ አይገኝም የጃሪምን ግልምጫ ከምንም ሳይቆጥር ፈገግ ብሎ አሳለፈዉና፣ ወደኔ መጥቶ አቀፈኝ፡ እሱን
እዚህ መሆኔን እንዴት አወቀ አይሉትም፡ እኔም በችኮላ ተንከረፈፍሁ እንጂ የትም ብሄድ ከሲራክ ፯ ማምለጥ እንደማልችል ማስተዋል ነበረብኝ፡ እንኳንስ እንደዚህ ተንዘላዝዬለት ይቅርና! የንዝህላልነቱ ንዝህላልነት ደግሞ በገዛ ስልኬ ለሸዊት ስልክ መደወሌ፡ በዚህ ስሕተቴ
እንኳንስ የሲራክ ፯ቱ ባልቻ፣ የተናቀ የመንደር ደመኛ እንኳን ሊያገኘኝ ይችላል።
ባልቻ ከመግባቱ አፍታ ሳይቆዩ እሸቴ እና ሸዊት ተከታትለዉ ገቡ።
“አንቺ?” ስል ተቀበልኋት፣ ከእሸቴ ኋላ መጥታ ለሰላምታ ስታቅፈኝ፡
“እንዲያዉ እስካሁን እያለቀሰችም ቢሆን ገና አሁን ነው የምትደርሽልኝ ማለት ነዉ?” አልኋት፣ ለቂሜ መወጫ ጠበቅ አድርጌ እያቀፍኋት።
የአሁኑ መተቃቀፋችን ትርጉሙ የትየለሌ ነዉ: አንድም በሆስፒታል
ቆይታዬ ዓይንሽን ለአፈር ብያት የነበረዉን ኩርፊያ ጨርሼ ረሳሁላት፣አንድም ለቱናት አምጭልኝ ያልኋትን ወተት ያዉም የሚሆናትን መጠጫ ጡጦ ጭምር ስላመጣችልኝ አመሰገንኋት፣ አንድም ነባሩ
ሰላምታችን እንደዚህ ነዉ፡ እንደገና እቅፍ አድርጌ ጨመቅኋት።
"እ?"
“ኧረ እኔስ ወዲያዉ ነበር የደረስሁት”
“አዎ” አለ ባልቻ፣ ክንዱን ትከሻዋ ላይ እየጫነ፡ “ወተቱን ብቻ ይዛ
ስትመጣ አግኝቻት፣ እኔ ነኝ ጡጦም ጨምራችሁ አምጡ ብዬ ከእሸቴ ጋ መልሼ የላክኋቸዉ። መቼም ምን ዶክተር ብትሆን፣ በዕድሜ ታናሼ ስለሆነች፣ በዚህ ቅር የምትሰኝብኝ አይመስለኝም”
“ኧረ በጭራሽ!” አለች፣ ወተቱን እና የጡጦ እቃዉን እያቀበለችኝ:
“ኧረ ስሚኝማ ዉቤ” አለች፣ የመደነቅ ፊቷን እየገለጠችልኝ፡፡
“ምን”
“ወንድምሽን እኮ ሊፍቱ ጋ አግኝቼዉ አሁን''
“ማንን?” አልኋት ለወጉ፣ ማንን ማለቷ እንደሆነ ባላጣዉም፡፡
“ጀሪምን ነዋ”
“እሺ”
“ምን እሺ ትይኛለሽ? ሰላምታ ከልክሎኝ ሄደ እኮ”
“ኧረ?” አልኋት፣ ከእሽጉ ዉሃ ከፍቼ ወደ ጡጦዋ እየቀነስሁ ዉሃዉ መቼ እንደ ተቀመጠልኝ ግን አላወቅሁም: ከአጠገቡ ሶፍት፣ ፎጣ እና ሌሎች አልባሌ ነገሮችም መኖራቸዉን ሳይ ማረፊያ ክፍሉን ከመያዜ
በፊትም ተቀምጠዉ እንደነበር ገባኝ፡፡
“አይገርምሽም? መቼስ ረስቶሽ ነዉ አትዪኝም ጃሪም እኔን ሊረሳ? ጉድ እኮ ነዉ! ያኔ እንዲያ …” ብላ፣ ተገርማ ቀረች፡፡ እየቆየ እንደገና በኃይል ከነከናት፡ ምክንያቷን አላጣሁትም፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሳለን ለአንድ ዕረፍት እኛ ቤት በነበርንበት ጊዜ፣ ጃሪም ዓይን አብዝቶባት ነበር
እንዲያዉም ደጋግሞ ወድጃታለሁ እንዳለኝ አስታዉሳለሁ ስሜቱን በግልጽ ለእሷ እንደ ነገራት ግን አላውቅም፡ ከአሁኑ ሁኔታዋ
እንዳስተዋልሁት ከሆነ፣ መንገር ብቻም ሳይሆን እሞትልሻለሁ› ጭምር ሳይላት እንዳልቀረ ገመትሁ ያ ሁሉ ቀርቶ አሁን ግን እንደማያዉቃት ከሆነባት፣ ባይገርማት ነበር የሚገርመኝ፡ ያዉ፣ የእኔ ጓደኛ አይደለች?
በእሱ ቤት እኮ አሁን፣ የእኔ የሆነ እና እኔ የነካሁት ሁሉ ርኩስ
ሆኖበታል።
“አጀብ ነዉ አለ ጅብ? የሆነዉስ ይሁንና በምን ዝም አሰኘሻት?” አለች፣ ቱናትን ገለጥ እያደረገቻት፡ ከጀርባዋ አጥንት ላይ ላለዉ ቁስል ጥንቃቄ አድርጋላት፣ አቀፈቻት እና ልትቀመጥ ብትፈልግ መቀመጫ አጣች: ገና
ይኸኔ ነዉ የሆቴል ማረፊያ ክፍል ዉስጥ መሆኔ ራሱ ትዝ ያላት:
የጃሪምን ፊት መንሳት ማመን አቅቷት ዋናዉን ጥያቄዋን እንደ ረሳችዉ ልብ አደረገች፡፡
“ቆይ ቆይ፣ አንቺ ግን እዚህ ምን ትሠሪያለሽ? ከእመዋ ቤት ያዉም ያን ድግስ ጥለሽ? ያዉም ይቺን ጨቅላ ይዘሽ? ምን ልትሆኚ እዚህ መጣሽ በይ?”
ይኸዋ! እንደ ፈራሁት የማርያም መንገድ እንኳን ሳታስቀርልኝ ጥያቄዋን አመጣችዉ ያልሰማሁ መስዬ ዝም ልላት ፈልጌ ነበር፡ ነገር ግን እሷን ሽሽት ዓይኔን የጣልሁበት ባልቻም ከእሷ በላይ አፈጠጠብኝ፡፡ ለራሱ ጉዳይ
ቢሆን፣ ሽንቱ እንኳን የፈለገ ወጥሮ ቢይዘዉ የሲራክ ፯ ጉዳይ ፋታ
እንደማይሰጠዉ እያወቅሁ፣ ለእኔ ሲል ነዉ አትረፍርፎ የሚሰጠኝ። እኔ ግን እንደ ደመኛ ተደብቄዉ እዚህ ሲያገኘኝ ማዘን ይበቃዉ ይሆን? እንኳን ማኩረፍ ሌላም ቢያደርግ እዉነት አለዉ፡ ግን እሱ ነዉና ሰዉዬዉ፣ መተዉ ያዉቅበታል፡ ያም ቢሆን ግን ጥያቄዋን ተጋርቷታል።
እንድመልስላት ከእሷ እኩል እየተቁለጨለጨብኝ ሳለ እሸቴ በሩን ከፍቶ ገባ፡፡ መቼ እንደ ወጣ ግን አላየሁትም ነበር፡፡ ለካንስ እመዋ ደዉላለት፣ እሷን ለማነጋገር ወጥቶ ኖሯል።
“እመዋ ናት የደወለችልኝ። (ልምጣ ወይ እያለች ነዉ፣ ትምጣ እንዴ?" አለ፣ ሳይታወቀዉ በሸዊትና
በባልቻ ከተፋጠጥሁበት ጥያቄ
ሲያስመልጠኝ፡ ባልቻ ቅር እንዳለዉም ቢሆን ቸለል አለልኝ፡ ሸዊትም እንዲሁ ቱናትን እንዳቀፈቻት ከአልጋዉ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ወተቱን ለማጥባት ሞከረች::
“እናንተ?” አለች፣ ወተቱን ልታጠጣት ሞክራ ሞክራ እንዳልሆነላት ስታዉቅ ተስፋ እየቆረጠች። “ቱናት የተለየ ልምምድ ሳያስፈልጋት
አይቀርም: ከተወለደች አንስቶ ኹለቱን ወር ሙሉ የከረመችዉ ግሉኮስ ተተክሎላት ስለነበር፣ ከጡትም ሆነ ከጡጦ ምግብ ስትሞክር ይኼ የመጀመሪያዋ ነዉ። ስለዚህ፣ እንደኔ እንደኔ አሁኑኑ ወደ ሆስፒታል ተመልሳ መግባት ያለባት ይመስለኛል” አለች፣ እኔ ደግሞ እንድሞክራት
እያቀበለችን፡ “ለጊዜዉ ጉሉኮሱም ቢሆን ማግኘት አለባት” አታዩትም
አተነፋፈሷንስ? የባሰ ሲር ሲር እያለ እኮ ነዉ። ለመሆኑ የቀጣይ
ሕክምናዋን ጉዳይ አማክራ ችሁበታል ወይ?”
“ማንን፣ ይኼዉ አንቺ አለሽል አይደል? አንቺዉ ምከሪን እጂ” አለ ባልቻ፣ እኔም እንደዚሁ ልላት ስል ቀድሞኝ፡፡
ይኼ ሙያዬ አይደለም: ስለዚህ እኔ በቅጡ ከምፈተፍት፣ ጉዳዩን ይሁነኝ ብለዉ የተማሩት
ባለሙያዎች ስላሉ ወደ እነሱ መሄድ ይኖርብናል”
«የት ናቸዉ እነሱ ታዲያ?”
“ምን እሱማ ባላውቃቸውስ በአብዛኛዉ ሆስፒታሎች አይጠፉም ነበር:: ግን የመሣሪያዎች ዉስንነት አለ: ለጊዜዉ ሕክምናዉ በኹለት
ሆስፒታሎች ብቻ እንደሚገኝ ነዉ የማዉቀዉ”
“በስመ አብ!” አለ ባልቻ፡ “ወረፋዉ አያድርስ ነዉ በይኛ''
“በጣም!”
ከመንግሥት ሆስፒታሎች መካከል ይኼን ሕመም ጉዳዬ ብሎ በብቸኝነት ሕክምና ወደሚሰጠዉ ዘዉዲቱ ሆስፒታል ሄድን፡፡ አቤት ወረፋዉ! ያሉት
አልጋዎች ዉስን ናቸዉ፤ ተመዝግቦ ተራዉን የሚጠባበቀዉ ግን የትየለሌ! እንዲያዉም የኋላ ኋላ እንደ ሰማነዉ ከሆነስ፣ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ብቻ ከሃያ ሺ የሚበልጡ ሕጻናት የቱናት ዓይነት እክል ያጋጥማቸዋል አሉ፡ ቁጥሩን አሰብሁት ስንት የሚወራላቸዉ
ወረርሽኞችም እኮ ከዚህ የከፉ አይደሉም
የቱናንት ሁኔታ አጣዳፊ መሆኑን ልናስረዳ ብንልም፣ የሚሰማን
አላገኘንም: አብዛኛዉ እዚህ የመጣዉ ሰዉ ሁሉ ቱናት ካለችበት የሚተናነስ አለመሆኑን አምነን ተቀበልን፡፡ ሆኖም ሕክምናዉን በተመለከተ እስከሚወሰንልን ድረስ፣ ባይሆን በረኀብ እንዳትሞትብን በሚል ግሉኮስ ተፈቅዶልን አንድ ጥግ ላይ ተተከለላት:: በረንዳ ላይ:
መኝታ ክፍልማ የሚታሰብም አይደለም፡
“በቃ እናንተ ሂዱ እጂ” አልኋቸዉ፣ ለግማሽ ሰዓት ያህል እንደዚሁ
እንደ ቆየን፡፡ እሳቱ የማይበርድ ችግር እየተጠባበቃቸዉ ሳለ፣ የሦስቱም እዚህ መቀመጥ ከቱናት ሕክምና ባልተናነሰ አሳስቦኛል ሸዊትም ፋታ የለሽ ሐኪም ናት፣ ባልቻም ባልቻ ነዉ፣ እሸቴም ያዉ ነዉ፡፡ “ሂዱ አረ! ሂዱ” አልሁኝ፣ እንደማግባባትም እንደማጣደፍም እያደረግሁ::
“መጨረሻዉን ሳንሰማ?” አለ ባልቻ፣ ስልክ ስልኩን ሲያይ እንዳልነበር ሁሉ፡

👍38❤1👎1🔥1
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...ሚስተር ካርላይል ወደ በሩ ሲያመራ ሮጣ ሔዳ አየችውና:
“አርኪባልድ በጣም ትቆያለህ እንዴ ? " አለችው።
“አይ ከአንድ ሰዓት የበለጠ አልቆይም ” ብሏት መልሶ በክንዶቹ እቅፍ አድርጎ ያዛት " ወዲያውም ደወለና ማርቨል መጣች።
ትጠብቀው ለነበረችው ለኮርነሊያ የማይመጣ መሆኑን እንድትነግራት ልኮ በሩን ዘጋና ሚስቱን ትክ ብሎ ሲያያት በጣም ነው የሚጨነቅልኝ ለካ ብላ አስበች " በበነጋው ጧት በቁርስ ጊዜ ኮርነሊያ አስቀድማ ቦታዋን ያዘች ቀጥለው ባልና ሚስቱ መጡ "
“ እንዴት አደርሽ...እመቤቲቱ ደኅና ተመችቶሽ አደርሽ ? ” እለቻት "
“ ደኅና ነኝ አመሰግናለሁ ” አለችና ከሚስ ካርላይል ፊት ለፊት ልትቀመጥ ስትል ያንቺ ቦታ ያ ነው...እሜቴ ” ብላ በእጅዋ ወደ ገበታው ራስጌ አመለከተቻት
ቡናውንም ፈቃድሽ ቢሆን እኔ ልቅዳልሽና ከመቅዳቱ ችግር ላድንሽ ” አለቻት።
“ ከሆነ በጣም ደስ ይለኛል ” አለች ሳቤላ።
ቁርስ ተበልቶ ሊያበቃ ሲል የሥጋ ደንበኛቸው ምን ምን ሥጋ እንደሚ
ቀርብ ለመጠየቅ መምጣቱን ፒተር ገብቶ ተናገረ መልሱ የሚጠበቀሙ ከሳቤላ ነበር።
እሷ ለራሷየዚህ ልምድ አልነበራትም " ምን እንደምትል ግራ ገብቷት ዝም አለች "
ነገረኛይቱ ኮርነሊያ ከአጠገቧ ባትኖር ኖሮ ) ከባልዋ ጋርም ቢሆን ትመካከርበት ነበር
አሁን አልቻለችም " እኅቲቱም ዝም ብላ ጠበቀቻት " ፒተርም መልስ ይዞ ለመሔድ እንደ ቆመ ቀረ
“ ጥቂት ለቅቅልና ለጥብስ የሚሆን ነገር እንዲያመጣ ብትነግረው ” አለች ሳቤላ ፈራ ተባ እያለች "
ቀስ ብላ ነበር የተናገረችው ሚስተር ካርላይልም ስለ ቤት አያያዝ ከሷ የተሻለ ስለማያውቅ የሷን ቃል ደገመው "
“ አዎን ለቅቅልና ለጥብስ የሚሆን ነገር እንዲያመጣ ለሰውየው ንግረው ፒተር አለ "
ሚስ ኮርነሊያ ብድግ አለች እንደዚህ ያለውን ትእዛዝ እየሰማች ዝም ልትል አልቻለችም " “ ለመሆኑ እንደዚህ የመሰለ ትአዛዝ ሥጋ ሻጩን ግራ እንደሚያጋባው ዐውቀሻል... እመቤት ? የሚያስፈልገውን ትእዛዝ ለዛሬ እኔ ልስጥልሽ ዓሳ ሻጩም አሁን ይመጣል ”
ከሆነስ እሺ!” ሳቤላ ከጭንቀቱ በመገላገሏ ደስ እያላት ፡ “ እኔ የዚህ ልምድ የለኝም " ወደፊት ግን የግድ መማር አለብኝ ስለ ቤት አያያዝ ምንም ነገር የማውቅ
አይመስለኝም
ሚስ ኮርኒ ምንም ሳትመልስላት ነጠቅ ነጠቅ ያለች ወታ ሔደች ሳቤላም ተይዛ እንደ ተለቀቀች ወፍ ከወንበሯ ብድግ አለችና ከባሏ ጎን ቆመቾ አበቃህ
አርኪባልድ ?
“ ማብቃቴ ነው የኔ ፍቅር ! ቡኖዬ ለካ ይኸው ይኸውና በቃ ጨረስኩ
እስኪ በግቢው ትንሽ ዘወር ዘወር እንበል ” አለችሙ እሱም ከተቀመጠበት ተነሣ ቀጭን ሽንጧን በእጁ አየዳበስ አስተውሎ አያት አሁን ሦስት ሰአት ዐልፏል እንደምታቂው ደግሞ አንድ ወር ሙሉ ቢሮ አልገባሁም"
እንባዋ ባይኗ ምላ ከኔ ጋር ብትቆይ ደስ ይለኝ ነበር " እኔስ ሁልጊዜ አብረከኝ መሆንክን እመኛለሁ » ኢስት ሊን ያላንተ ኢስት ሊን አይሆንም።
በተቻለ መጠን ካንቺ አልለይም
ፍቅሬ " አላት በጆሮዋ“ አሁን ነይና
በግቢው መኖፈሻ አብረን እንሸራሽር "
ወደ ክፍሏ ገብታ ለባበሰችና ተያይዘው ወጡ ካርላይል ስለ እህቷ ለማንሳት ምቹ አጋጣሚ ሆነለት "
እሷ ከእኛ ጋር ለመቀመጥ ትፈልጋለች ምዓ እንደምወስን አላወቅሁም በአንድ በኩል ቤቱን በማስተዳዶር ብዙ ልትጠቀምሽ ትችል ይሆናል " በሌላ በኩል
ደግሞ እኔና አንቺ ብቻችንን ብንሆን እንደ ልባችን ሆነን ደስ ብሎን የምንኖር ይመስልሻል?
ሳቤላ የተቋጠረ ፊቷ የማይፈታው ሚስ ኮርነሊያ ቋሚ ጠባቂ መሆኗን ስታስበው ልቧ ፍስስ አለ ግን ተጨናቂ ይሎኝተኛ ለሌሎች ስሜት አጥብቃ የምታስብ ረቂቅ ሰው ስለ ነበረች ምንም የቅሬታ ቃል አልተነፈሰችም “ ላንተና
ለሚስ ካርላይል ደስ የሚላችሁ ከሆነ ይሁን ” አለችው ላቤላ "
“ ሳቤላ .. ” አላት ኰስተር ብሎ።“እኔ የምፈልገው ላንቺ ደስ የሚልሽ እንዲሆን ነው " ማንኛውም ነገር እንደሚያስደስትሽ ሆኖ እንዲደራጅ እፈልጋለሁ
እኔ አሁን በሕይወቴ ዋናው ዓላማዬ ያንቺ ደስታ ነው ”
አባባሉ ከልቡ መሆኑን ሳቤላ ተረዳችው እሱን የመሰለ እውነተኛ ፍቅረኛና ጠባቂ ከጐኗ ካለ ሚስ ካርላይል የኑሮን ሰላም እንደማታበላሽባት ተሰማትና
ተዋት ትቀመጥ ፡ አርኪባልድ ... ምንም አታስቸግረንም ” አለችው "
“ እስቲ ለሁሉም ለአንድ ሁለት ወር ያህል ሁኔታውን እንየው ” አላት " እንዲህ እየተወያዩ ከመናፈሻው በር ደረሱና ሊለያት ሲል፡“ እኔስ ብቻዬን ወደ ቤት ከምመለስ አብሬህ ወደ ቢሮህ ሔጄ ጸሐፊህ በሆንኩ ደስ ይለኝ ነበር ' አለችው
እሱም በአነጋገሯ ሳቀና ተሰናብቷት ሔደ »
ሳቤላ ክፍሎቹን ሁሉ እየዞረች አየች » ሁሉም ጸጥ ብለዋል " ባባቷ ዘመን የነበራቸው ድምቀትና ሙቀት ጠፍቷል “ ከመልበሻ ክፍሏ ስትገባ ማርቨልን
ተንበርክካ የተጠፈረ ዕቃ ስትፈታ አየኘቻት " ሳቤላ ስትገባ ከእምብርክኳ ተነሣች
“ አንድ ጊዜ ላነጋግርዎ እሜቴ ? "
"ምንድነው?"
ማርቨል ከዚያ ሞቅ ሞቅ የማይል ትንሽና ቀዝቃዛ ግቢ መኖር ስለማይስማማት የእመቤቷ ፈቃድ ቢሆን ዕለቱን ለመሰናበት መፈለጓንና ይኸንኑም ተስፋ በማድረግ ዕቃዋን እንደ መጣ ያለ መፍታቷን ነገረቻት "
“ስለ አሽከሮቹ ጉዳይ አንድ የተፈጸመ ስሕተት ስለ አለ ነው " በተቻለ ፍጥነት ይታረማል " በተረፈ የሚስተር ካርላይል ቤት ምጥን ያለና ውሱን መሆኑን
ገና ከማግባቴ በፊት ነግሬሽ ነበር።
“ እመቤቴ እሱን ሁሉ እችለው ይሆናል ከሚስ ካርላይል ጋር ግን አንኳንም እንዲያውም ሁለት ግልፍተኞች ስንገናኝ አፍ እንዳንካፈትና ከዚያም አልፈን እጅ እንዳንሰናዘር እፈራለሁ እኔ በዚህ ዐይነት ሥፍር ቁጥር የሌለው ወርቅ ቢሰጡኝም አልቀመጥም " የዚህ ያሁኑ ሩብ ዓመት ደሞዜም ቢይዙብኝም ለመቅረት
አልፈልግም " ስለዚህ የተጠፈረውን ዕቃ ካደራጀሁልዎ በኋላ እንዲያሰናብቱኝ ብቻ
ነው የምለምነዎ "
ሳቤላ ፡ ማርቭል እንዳትሔድባት ለመለመን ክብሯ ባይፈቅድላትም ያለ ደንገጡር ምን እንደሚበጃት ሐሳብ ያዛት" ቢሆንም እርሳስና ወረቀት ይዛ የምትሰጣትን ዶሞዝ
አስልታ የብርና የወርቅ ገንዘቦች ከጠረጴዛው ላይ ካደረገችላት በኋላ ማርቨል . . ማግኘት ከሚገባሽ በላይ ነው " አስጠንቅቀሽና በቂ ጊዜ ሰጥተሽኝ መሔድ ነበረብሽ ” አለቻትና ትታት ወጣች " ማርቨልም እንዳለችው ትናንትናውን የገባውን ዕቃ አደራጅታ ስታበቃ ጆይስ እየሰደበቻትና እያዘነችባት ወጥታ ሔደች "
ሳቤላ ለምሣ ልብሷን ልትለብስ ወደ ክፍሏ ስትሔድ ጆይስ ተከትላት ገባች "
“ እኔ ለራሴ ስለ ወይዛዝርት ደንገጡርነት ልምድ የለኝም ነገር ግን ቢፋቅዱልኝ የምችለውን እንድረዳዎ ሚስ ካርላይል ልከውኝ ነው የመጣሁት አለቻት
ሳቤላ የሚስ ካርላይልን ደግነት በልቧ አመሰገነች "
“ የእቃዎችዎን ቁልፎች አምነው ከሰጡኝ እያሰብኩ አሰናዳልዎታልሁ ”
“እኔ ስለ ቁልፎች ምንም አላውቅም" ይዠም አላውቅ " አለቻት ሳቤላ ።ጆይስ የሚቻላትን ሁሉ ካደረገች በኋላ ' ሳቤላ ወደ ምግብ ቤት ወረዶች » ጊዜው
ወደ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ተቃርቦ ነበር ፤የራት ሰዓት ማለት ነው። ሳቤላ ሚስተር ካርላይልን ሲመጣ ለማግኘት ወደ መናፈሻው በር እያዘገመች ሔደች "
ከበሩ ዐልፋ ጥቂት ራመድ ካለች በኋላ በመንገዱ ዘቅዝቃ ብትመለከት አጣችው " ስለዚህ ተመልሳ ገብታ ከመንገዱ ትይዩ ፈንጠር ብላ ከአንድ ጥላማ ዛፍ
ሥር ተቀመጠች ወራቱ የግንቦት መገባደጃ በመሆኑ በጣም ይሞቅ ነበር ።

👍19👎1