አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
575 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ


#በክፍለማርያም

አንይኖቹ ቤዛዊት ላይ ቀሩ
እማማ ስንቅነሽ ሰፋ ያለ የአበባ ቅርፅ ያለዉ የጨርቅ ልብስ ሰጥተዋት እሱን ለብሳ ከላይ ብርድ ልብስ
ጨምረዉላት እራት ቢጤ ከቀማመሰች በኋላ መሬት ላይ ተነጥፎላት ቤዛዊት አሸልባለች።

እማማ ስንቅነሽም እንቅልፍ አልወስድ ብሏቸዉ በጥሩ ጎኑ የቤዛዊት ነገር ሲያሳስባቸዉ ምን ሊረዷት
እንደሚችሉ እየተብሰለሰሉ ሲያስቡ
በመጥፎ ጎኑ የማላዉቃትን ሴት ቤቴ አስገብቼ አንድ ነገር ብታረገኝስ እስዋስ አንድ ነገር ሆና
እዳ ዉስጥ ብትከተኝስ እያሉ ሲብሰለሰሉ
ባረጀዉ ጋቢያቸዉ አይናቸዉን ብቻ እርቃን አስቀርተዉ ቤዛዊትን እያዩ እሳቸዉንም የማይቀረዉ እንቅልፍ
በሀሳብ አስመስሎ አሸነፋቸዉ።

ቤዛዊት በጆሮዋ ሹክሹክታ መሰል ድምፅ ስትሰማ ከተኛችበት አይኗን ገለጠች
ያለችበትን ማወቅ ተስኗታል ጤንነቷ ግን የተመለሰ ይመስላል እራሷን በማወቅ ላይ ነች ወሰድ መለስ ነዉ የህመሟ ባህሪ አሁን የፍፁም
መገጨት ሁኔታዉን ሁሉ ለዋዉጦት ለዚህ አበቃት እንጂ...

"የት ነኝ?"

ፍርሀት እና ጥርጣሬ ያዘለ ቀጭን ድምጿን ለቀቀችዉ

"አንቺ ...ማን ነሽ?"

አላት የእማማ ስንቅነሽ ልጅ በሰከረ አንደበት እየተኮለታተፈ ደንገዝ ገዝ ባለዉ የቤቱ ጨለማ ዉስጥ ጃኬት ለብሶ
የቆመ የሚመስል ሰዉ ታያት ደንግጣ እጆቿን በፍጥነት
ከብርድ ልብሱ አዉጥታ ከጀርባዋ ያለዉን ግድድዳ
በእጆቿ ማሸት ጀመረች ቤቷ ይመስል ማብርያ ማጥፍያ ፍለጋ።

ሰካራሙ ልጅም ግርግዳዉን እየፎከተች መሆኑን በአትኩሮት
አይኖቹን ባለማመን አፍጥጦ ካያት በኋላ ሲያረጋግጥ
እንደመፍራት እያለ ወደ ኋላ ሲራመድ ሳያስበዉ ጥግ ይዞ የተቀመጠን ባዶ ድስት በእግሩ ስለነካዉ የድስቱ ክዳን
ድምፅ እየፈጠረ መንከባለል ጀመረ።

"ኪልልልል ኪል ኪል ኳ"

እማማ ስንቅነሽ መብራቱን ሲያበሩት ቤዛዊት እና ልጃቸዉ
ተፋጠዉ ቆመዋል

"የት ነኝ..ማን ነህ..እነ ማን ናችሁ?"

ቤዛዊት ደጋግማ ትጠይቃለች ያለችበት ግራ ገብቷት ሁለቱንም
እያፈራረቀች እያየች
"ምኗን ደሞ ይዘሽ መጣሽ"
እናቱን በአሽሙር እየተናገረ መደ መኝታ ክፍሉ እየተንገዳገደ ሄደ
"የት ነኝ ....."ቤዛዊት ያወራችዉን ደጋግሞ እያወራ እያሾፈባት
እማማ ስንቅነሽ ከአልጋቸዉ ተነስተዉ አማተቡ
ጨንቋቸዋል ምን ብለዉ ያስረዷት ነግቶ ከቤታቸዉ
በሰላም እንድትወጣ በልባቸዉ መለመን ጀመሩ።

ቤዛዊት ሁለት ክፍል ያለዉ ደሳሳ ቤት ዉስጥ እንዴት
ልትገባ እንደቻለች ስታስብ ገርሟታል ሌላ አለም ላይ ያለች
ይመስል እማማን ሌላ ፍጥረት ከሆኑ በሚል አስተያየት
እያየቻቸዉ ማሰብ ጀመረች።

ምንም የምታስታዉሰዉ ነገር የለም
አይምሮዋን አስጨነቀችዉ ማስታወስ የቻለችዉ
በመኪና ፍፁም ተገጭቶ አንፑላንስ ዉስጥ እሱ ሲገባ
ብቻ በአይምሮዋ ተቀርጿል ሌላዉን ሁሉ አታስታዉስም

"እማማ ልሂድ"

አስፈቀደቻቸዉ
"ለሊት እኮ ነዉ ልጄ ሲነጋ ትሄጃለች"
ሀዘን ባዘለ ድምፅ በጭላንጭል የሚገባዉ ብርሀን የጨረቃ
መሆኑን እየነጠሯት
እሺ ለማለት ጭንቅላትዋን ከታች ወደ ላይ ነቀነቀች
የለበሰችዉ ልብሰ የእሷ አለመሆኑን ስታስታዉስ ፊት ለፊቷ
ያሉት ሴትዮ እንዳለበሷት ገምታ እንደማፈር አለች
ቀኑን ሙሉ እርቃኗን ስትዞር መዋሏን ዘንግታዉ
እግሯ አካባቢ የድካም እና የህመም ስሜት ይሰማታል ቀኑን
ሙሉ ስትባክን የዋለችበት
ምን እንደተፈጠረ እየተሽኮረመመች እማማን ጠየቀቻቸዉ
እንደ ልጃቸዉ ቀርበዉ የሆነዉን ሁሉ እማማ ስንቅነሽ ነገሯት።

የቤዛዊት ቤተሰቦች ልጃቸዉ ከትምህርት ቤት ሳትመለስ ስታመሽ ተጨንቀዉ አባቷ ወደ ፍቃዱ ደወሉ
ፍቃዱ ትምህርት ቤት ዉስጥ ቀኑን ሙሉ እንዳላያት
ነገራቸዉ እና ስልኩ ሊዘጋ ሲል የፍፁምን በመኪና መገጨት
በማስመሰል ከንፈሩን እየመጠጠ ስለነገራቸዉ እሱ ጋር ሄዳ ይሆናል ብለዉ ተናደዉ ስልኩን ዘጉት።

ፍፁም የተኛበትን ሆስፒታል በመከራ አጊንተዉ የቤዛዊት አባት
ከብዷቸዉ ሚስታቸዉን እና ታላቅዋን ልጃቸዉን ሄደዉ
እንዲያመጧት አዘዙዋቸዉ።
የተባለዉ ሆስፒታል ደርሰዉ ወደ ዉስጥ ሲገቡ ከንፈሩ ደራርቆ
አስታዋሽ ያጣዉ ፍፁም ከህመሙ ጋር እየታገለ ነበር።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍21
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ ፡ ፡ #በክፍለማርያም አንይኖቹ ቤዛዊት ላይ ቀሩ እማማ ስንቅነሽ ሰፋ ያለ የአበባ ቅርፅ ያለዉ የጨርቅ ልብስ ሰጥተዋት እሱን ለብሳ ከላይ ብርድ ልብስ ጨምረዉላት እራት ቢጤ ከቀማመሰች በኋላ መሬት ላይ ተነጥፎላት ቤዛዊት አሸልባለች። እማማ ስንቅነሽም እንቅልፍ አልወስድ ብሏቸዉ በጥሩ ጎኑ የቤዛዊት ነገር ሲያሳስባቸዉ ምን ሊረዷት እንደሚችሉ እየተብሰለሰሉ ሲያስቡ…»
#እኛ

ሥጋና ነፍስ ያደለን
ሰምና ወርቅ ያለን
በቃል ሕብር የተፃፍን
በሆሄያት የገዘፍን
የእግዜር ቅኔዎች ነን
እኛ የተዘረፍን፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ነገረ ሕልም

በምቹ አልጋ ላይ ጐኑን አሳርፎ
በእንቅልፍ ልቡ የታየው ችግር ሁሉ አልፎ
ሲነቃ “ሕልም አለኝ አለ ያ ወገኛ፤
በደንብ ተመችቶት እንቅልፉን የተኛ፡፡
የረባ መኝታ ምቹ አልጋ ያላደለኝ
በችግሬ ብዛት እንቅልፍ እንኳ የሌለኝ
እንደምን እላለሁ?! ሳልተኛ “ሕልም አለኝ”

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#እጠብቅሻለሁ!

ከባባድ ጉዳዬን አቅልዬ ጣጥዬ
ያንቺን አስበልጬ ትመጪያለሽ ብዬ
ያንቺን አስቀድሜ
ከቀጠርሽኝ ሥፍራ
መጣሁኝ ቀድሜ
በሥፍራው የለሽም
ጭራሽ አልመጣም።
አሥሬ እያየሁኝ ሰዓት ደጋግሜ
አንቺን በመጠበቅ
በዕድሜዬ ላይ ጨመርኩ የሰዓታት እድሜ
እጠብቅሻለሁ
ካሻው ይህ ቅጽበት
የሕይውቴ ፍፃሜ
ይሁን ዘላለሜ
በአትቀሪም ተስፋ
ራሴን ስቅቅል በናፍቆት ስበስል
ትመጪያለሽ ብዬ አገኝሻለሁ ስል
ገዢ ሐሳቤ ሆነሽ አንቺን ሳብሰለስል
ጭራሽ ላትመጣ ልትቀር ነውወይ ስል
ክፉ ክፉ ሳስብ በቅናት ስከስል
መጥፎ መጥፎ ሳሳብ በአዕምሮዬ ስስል
“በሐሳብ እያነሱ
ዕድሜ ከመጨመር በጭንቅ በትካዜ
ዕድሜ መቀነሱ ይሻላል ሺ ጊዜ
በማለት ወስኜ
ደግሞም ተማምኜ
እርግጠኛ ሆኜ
ዕድሜ ይቀንሳል
አንችንም ያስረሳል
ያዋጣኛልም ስል
ሲጃራ ለኩሼ
አጭሼ አጭሼ
አንዱንም ጨርሼ
አንቺን ላለማሰብ
ዳግመኛ መልሼ
ያረሳሳኛል ስል
ደገምኩኝ ሲጃራ
አጭሼ አጭሼ
ዳግም ተመልሼ
ለኩሼ ጨርሼ
እረሳሻለሁ ስል
በሲጃራው ጭስ ውስጥ
ካንቺ ወዲያ ሃሳብ
የሌለኝ ይመስል
ጭሱ ቅርጽ ሠርቶ
ቅርጽሽን አጉልቶ
ያሳየኝ ጀመረ
ፈጥሮ ያንቺን ምስል::
የተማመንኩበት
ያረሳሳኛል ስል
መልሶ አስታወሰኝ
ወዳንቺው መለሰኝ..
ሲጃራ እያጨስኩኝ
ዕድሜ እየቀነስኩኝ
እጠብቅሻለሁ እያሰላሰልኩኝ
አንቺን እያሰብኩኝ
በጭሱ ቅርጽሽን..
አንቺን እየሳልኩኝ።

🔘ፋሲል ተካልኝ 🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በክፍለማርያም

...ከህመመ ጋር እየታገለ ነበር
የቤዛዊት እናት እና እህት ወደ ፍፁም ተጠግተዉ

"ፈጣሪ ይማርህ"

ሁለቱም በአንድነት አወሩ
ፍፁም ከአልጋዉ እንደ መነሳት እየሞከረ እና እያቃተዉ የቤዛዊት እናት እና እህት ከመምጣታቸዉ በፊት ሰዓታት ቀደም
ብላ የመጣችዉ ፍፁም ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ አስተዋጽፆ ያላት
የገጪዉ ሚስት ጠዋት ባሏን ፖሊስ ጣቢያ ጠይቃዉ ለፍፁም ለሆስፒታል የሚከፈል እና ለአንዳንድ ነገር የሚሆን
እንደ ካሳ አስባ ጠቀም ያለ ገንዘብ ይዛ ሆስፒታል ደርሳ
መክፈል የነበረበትን ክፍያ ከፋፍላ እየተመለሰች ስለነበር
ቀና እንዲል እረዳችዉ አጠገቡ ቆመች የሰማችዉ ነገር ስላለ
እያዘነች እና እንዴት መናገር እንዳለባት እየጨነቃት

"አሜን"

አለ ተደላድሎ ከተቀመጠ በኋላ
ቤዛዊት እንዴት ናት ብሎ ለመጠየቅ እና ልትጠይቀዉ ስላልመጣች የማይፀና ቅያሜ እየተሰማዉ
"ቤዛዊት እዚህ ነበረች አደል?"
እናቷ እርግጠኛ ሆነዉ ጠየቁት አዎ ነበረች የሚል መልስ እየጠበቁ
ፍፁም ምን ማለታቸዉ ነዉ ሲል አሰበ
"ከትላንት ጀምሮ ጠፍታብናለች ተስፋ ያረግነዉ አንተ ጋር ነበር
ትምህርት ቤትም አልገባችም ምን አልባት
አንተን እያስታመመችህ ከሆነ ብለን ነዉ"
የቤዛዊት እህት ቃላቶቹን ጎተት እያረገች አወራች።

ፍፁም አይኖቹን ለማሰብ አርቆ ወረወራቸዉ ልቡ የመምታት ፍጥነቱ እየጨመረ ነዉ የት ልትሄድ እንደምትችል
አሰበ ግን ቦታ አጣ የምትገኝበት ፍፁም ቤዛዊትን ከልቡ
ስለሚረዳት የእሱን መገጨት ስትሰማ ታማ ይሆን አለና ተነስቶ ለመፈለግ እግሩን ለማዉረድ ሲታገል
አጠገቡ የነበረችዉ የገጪ ሚስት
የማስመሰል ያልሆነ የእዉነትም የማይመስል ለቅሶ አለቀሰች
ታግሎ ያቃተዉ ፍፁም የሆነ ችግር እንዳለ ስለጠረጠረ
እንድትነግረዉ አንገቱን አዙሮ አፈጠጠባት

"ለጊዜዉ እግሮችህ መንቀሳቀስ አይችሉም"

የፍፁምን የታሸገ እግር እያይ ቀጠለች
"በህክምና ግን ወደፊት ይሻልሀል"
ጥርጣሬ ያለበት አወራር
ፍፁም ሳያስበዉ አይኖቹ እንባወች አቅረዉ እንዳይወርዱ
የቤዛዊት ቤተሰቦች እንዳያዩት ሲታገል ቀድመዉት ጉንጩ ላይ
የእንባ ዘለላወቹ አረፉ።

"አትዘን ደህና ትሆናለህ"

የቤዛዊት እህት በእጇ ይዛ የነበረዉን ምግብ እና ፈሳሽ ነገር
አጠገቡ ካለዉ ማስቀመጫ እያስቀመጠች እና በርታ እንዲል
የፍፁም ትከሻወች ላይ እጇቿን ጭና
"በየ ጊዜዉ እየመጣሁ እጠይቅሀለዉ
ስለ ቤዛዊትም ያለዉን ነገር አሳዉቅሀለዉ እንደሚሻልህ እርግጠኛ ነኝ"
ተስፋ ለመስጠት አስባ በእጇቿ ነካ ነካ አረገችዉ ጀርባዉን
የቤዛዊት እናትም እንዲሻለዉ እየተመኙ ነገር ግን የልጃቸዉ
መጥፋት እና እወደዋለሁ የምትለዉ ፍፁም ጋር እንኩዋን
አለመገኘትዋ እየጨነቃቸዉ ከታላቅዋ ልጃቸዉ ጋር የት መሄድ
እንዳለባቸዉ እያወሩ ፍፁምን ተሰናብተዉት ወጡ።

እማማ ስንቅነሽ ቀደም ብለዉ ተነስተዉ ትላንት እብድ ብለዉ
እየፈሩ ያስገቧት ሴት ማታ እንደጤነኛ ሰዉ ስታወራ ስለነበር
ደስ እያላቸዉ ቁርስ በልታ እንድትሄድ ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ

"ልሂድ"

ያለቻቸዉን አስታዉሰዉ ባዶ ሆዷን እንዳትሄድ ቤዛዊትን ከዚህ በፊት አያዉቋትም እስዋም አታዉቃቸዉም
ነገር ግን ከልባቸዉ እራሩላት
ነገ በኔ የሚል ሰዉ የሰዉ ህመም ይገባዋል ሰዉን ለመርዳትም
ይሞክራል እንደ እማማ ስንቅነሽ ያለ በእድሜ የበሰለ እና ፈጣሪን
የሚፈራ ደግሞ ከሚችለዉ በላይ ያረጋል።

ዉጪ እንዳለች የሚለበስ ነገር መስጠት ብቻ ሲችሉ ቤታቸዉ አሰገብተዉ አስጠለሏት ምግብም በፌስታል አርገዉ ማቀበል እየቻሉ አንድ ላይ ገበታ
አቆደሷት

"እንደምን አደሩ እማማ"

ቤዛዊት ማት በስንት ጭንቀት አስፈቅዳ የሸናችበትን ማስታጠብያ
ይዛ ሀፍረት እየያዛት ለመድፋት የተከፈተዉን በር አልፋወጣች
በትክክል ማሰብ ጀምራለች
በዛፎች የተከበበ ስፍራ አንዳንድ አነስ አነስ ያሉ የጭቃ ቤቶች
ይታያሉ እስዋ ከለመደችዉ በህንፃ ከተከበበ ሰፈር ተለየባት እንዴት እዚህ እንደመጣች ግን ማስታወስ አልቻለችም
አቅራቢያዋ ካለዉ ቦይ የያዘችዉን ደፍታ እየሮጠች ወደ እማማ
ቤት ገባች
"የት ነዉ ያለሁት ማለት የአካባቢዉ ስም"ጠየቀቻቸዉ
እማማ ስንቅነሽ የከተማ ልጅ መሆኗን በአነጋገርዋ አዉቀዋል
"የከተማ አዋሳኝ ቦታ ነዉ ያለሽዉ አሁን ቁጭ ብለሽ ቁርስ ብዪ"
አሏት እንድትታጠብ ዉሀ እያቀረቡላት በልባቸዉ የመንገዱን
እርቀት እየገመቱ መንፈስ ካላገዛት ብቻዋን በእግሯ
እዚህ ድረስ መምጣቷ እየገረማቸዉ።
እንደ ነገሩ በላ በላ ካደረገች በኋላ የፍፁምን ሁኔታ ማወቅ
ስለጓጓች ለመሄድ ተነሳች እማማ ስንቅነሽ ያለበሷትን ቀሚስ
እያየች እና ስለደግነታቸዉ እያመሰገነች ተመልሳ እንደምትመጣ
ቃል ገብታላቸዉ ስትወጣ
"አንዴ ቁሚ ልጄ"
አሉ እርጅና በተጫጫነዉ እና በደከመ ድምፅ
የሆነ የተቋጠረ ጨርቅ መፍታት ጀመሩ ዉስጡ ጥቂት ብሮች
ይታያሉ ለእራሳቸዉ ጥቂት አስቀርተዉ አብዛኛዉን የቤዛዊት እጅ
ላይ እያስቀመጡ
"በእግርሽ ይርቅሻል ባይሆን መኪና ኮረኮንቹን እደጨረሽ
ታገኚያለሽ ተሳፈሪ"
አሏት የምትሄድበትን መንገድ በእጃቸዉ እየጠቆሟት
በአይምሯቸዉ በልጅነት ወልደዋት ነገር ግን በልጅነትዋ በድንገት
የሞተችባቸዉን ሴት ልጃቸዉ ስለመጣችባቸዉ
ሀዘን መላ ሰዉነታቸዉን እየወረራቸዉ
ቤዛዊት የሰጧትን ገንዘብ ጭምድድ አድርጋ ይዛ
የእማማ ስንቅነሽ ዉለታ እና ሸክም ስለበዛባት በተለይ አሁን
ምንም ማረግ ስላልቻለች ጥምጥም ብላ አቀፈቻቸዉ።

ጥቂት አቅፋቸዉ ድጋሜ አመስግናቸዉ መራመድ ጀመረች
የፍፁም ሁኔታን ለማወቅ እየጎጎች ቀድማ የት መሄድ እንዳለባት
እያሰበች እማማ ስንቅነሽ ከአይናቸዉ እየራቀች የምትሄደዉን ልጅ እያዩ
ቅድም ያመቁትን ያጡዋትን የልጃቸዉን ሀዘን በለቅሶ ቀጠሉት
ልጃቸዉን በቤዛዊት አይን ዉስጥ ያዩ ይመስል የሆነ ነገር ሊነግሯት ያሰቡ ይመስል ሊያስቋሟት እንደመሮጥ
እየሞከሩ ወደ ፊት ለፊት ሲመለከቱ ቤዛዊት ላትታይ ጠፍታለች
በነጠላቸዉ እንባቸወን እያበሱ ሰላም እንድትሆን ለቤዛዊት
ጤናዋን እየተመኙላት ቤታቸዉ ገቡ።

ቤዛዊት ወደ ቤቷ አቅራቢያ ስትደርስ ከነ ቤዛዊት ቤት ወሬ ፈትፍቶ የሚመለሰዉ ፍቃዱ አገኛት

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1👍1
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አንድ ፡ ፡ #በክፍለማርያም ...ከህመመ ጋር እየታገለ ነበር የቤዛዊት እናት እና እህት ወደ ፍፁም ተጠግተዉ "ፈጣሪ ይማርህ" ሁለቱም በአንድነት አወሩ ፍፁም ከአልጋዉ እንደ መነሳት እየሞከረ እና እያቃተዉ የቤዛዊት እናት እና እህት ከመምጣታቸዉ በፊት ሰዓታት ቀደም ብላ የመጣችዉ ፍፁም ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ አስተዋጽፆ ያላት የገጪዉ ሚስት ጠዋት ባሏን ፖሊስ…»
#በጥሩምባ_ድምፅ

ጡ .. ጡ... ው.. ጡ!..
ውጡ... ውጡ!.ውጡ ውጡ! ..
ዝለሉ!.. ቅበጡ ተረቱን ለውጡ፡፡
አዲስ ዘመን ባተ አሮጌው ተሽኘ
ተረት ተለወጠ ዘበትም ተሰኘ
የቀበጡ ዕለትም መሞትም ተገኘ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ፍታት

እሪ በሉ አርበኞች እሪ በይ ሀገሬ
በነጭ ያልተፈታሽ ተፈታሽ በወሬ
#የአዳም_ዘሮች

አንድ ቀን፤
ጡቶቼን ብቻ ደግፎ
ከወገቤ ባሻገር ተንጠልጥሎ የሚቀር
ጥብቆ አድርጌ ብዋብ ብሽቀረቀር
ያዳም ዘር በሙሉ እምብርቴን አየብኝ
ምራቁን ዋጠብኝ ፤ ቆይ ብሎ ዛተብኝ፡፡
በሌላ ቀን ፤
አጭር ቀሚስ ባደርግ
ጭኖቼ መሐል ላይ ዓይኑን ተከለብኝ
ከአዳም ዘሮች አንዱ
ሳይጠፋው መንገዱ መንገዱን ዘጋብኝ።
የማይቀንቀሳቀስ የማይነቃነቅ እንቅፋት ሆነብኝ
ለጊዜው አማኝ ሆኜ
እንደአምላክ ለምኜ
ከንፈሬን ፈልቅቄ
ጥርሴን አሳይቼ ስቄ አሳስቄ
በአሳር በመከራ መንገድ አስለቅቄ
አልፌ ብሔድም ካንዱ አዳም እርቄ ፤
የሌላው ያዳም ዓይን ጭኖቼ ላይ አርፎ
በስሜት ተውጦ ገላዬንም ቋምጦ ሲያየኝ አሰፍስፎ
እያየሁት ከሩቅ
አገር አዳርሼ ሳልበላ በዓይን ጉዳዬን ተኩሼ
በሰላም ገባሁኝ ቤቴ ተመልሼ፡፡
ደግሞ በሌላ ቀን ፤
በእናቴ የሀገር ባሕል በቀሚስ ተውቤ
ባለዘርፍ ነጠላ ላዬ ላይ ደርቤ
“ምን ይመጣ ይሆን?” ለራሴ እያልኩኝ
ከቤቴ ወጣሁኝ መንገዴንም ያዝኩኝ
በኩራት ተጓዝኩኝ ተጓዝኩኝ ተጓዝኩኝ
አንድም ኣዳም የለም መንገድ የዘጋበኝ
ያ የሚያየኝ ሁሉ ፊቱን አዞረብኝ።
ዕድሜ ለነጠላው ዕድሜ ለቀሚሱ
ነፃነቴን ሰጠኝ የሀገር ባሕል ልበሱ።
እኒያ ሁሉ አዳም የምር የት ደረሰ??
ኧረ ወዴት አሉ??
በእጀጉ ይገርማሉ!
በዓይኔ ፈለግኳቸው ፤
ከሩቅ አየኋቸው::
በዓይኖቻቸው ሙሉ
ሌላ ጭን ሌላ እምብርት
ሌላ የሔዋን ገላ ለማየት ይሻሉ ፤
ይቅበዘበዛሉ፡፡
እንዴት ይደንቃሉ!
ከሀገር ባሕል ሸማ
ከራሱ የተስማማ
ከውብ ገላ ይልቅ የሔዋን እርቃን ነው ሥጋቸው የተጠማ፡፡
የፈረሰ-ቅኝት ጣዕም አልባ ሙዚቃ
ሁሌም በነሱ ዘንድ በፍቅር የሚስማ
እራቁት እራቁት እራቁት የሚል ነው
የአዳም ዘሮች ሁሉ የነፍሳቸው ዜማ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በክፍለማርያም

...ፍቃዱ አገኛት
እንዳያት ትወናዉን እና ማስመሰሉን ተያያዘዉ የአዞ እንባውን
ከየት እንዳመጣዉ ባይታወቅም እያነባ ተንደርድሮ ሁለቱንም
እጆቹን እንደ አሞራ ክንፍ አየር ላይ እያንሳፈፈ ሊያቅፋት ተጠጋ
"የኔ ምስኪን የት ጠፋሽብን ያልፈለኩሽ ቦታ የለም"
አደለም ሊፈልጋት ጠፍታ ብትቀር እራሱ እሷን በመፈለግ በሚል ሰበብ ከአባቷ የሚሸጎጥለት ገንዘብ በመቅረቱ በዉስጡ እየተፀፀተ

"እንዳትነካኝ"

ሊያቅፋት ያንከረፈፈዉን እጆቹን ሰበሰባቸዉ
አንዳንዶች ወዳጅ እና አሳቢ ይመስላሉ የሚገርመዉ ዉስጣቸዉ በተቃራኒዉ ጥላቻ እና መጥፎ አሳቢ ናቸዉ።

ጥላዉ ወደ ቤቷ ገባች ነገር ከጀርባዋ እየተከተላት ገብቶ

"እልልልልልልል"

ምላሱን ተጠቀመበት የልጃቸዉ መጥፋት ያስጨነቃቸዉ ቤተሰቦቿ የእልልታ ድምፅ ሲሰሙ
"ምን መጣ"
ብለዉ ግልብጥ ብለዉ ወጡ።

ፍቃዱ ቀድሟት ፊት ቆሞ እሱ ያገኛት ይመስል ቀኝ እጁን እና አይኖቹን ወደ ሰማይ ወርዉሮ ያመሰግናል
እናቷ እየሮጡ ከቤታቸዉ ደረጃ ወርደዉ አቀፏት ወድያዉ እየለቀቋት የጎደለ ሰዉነት ያላት ይመስል ዞረዉ
በአይናቸዉ መላ አካላቷን በስስት ቃኟት እንባ እንባ እያላቸዉ። እህቷም ቀጥላ አቅፋት በሀዘን እየተያዩ መላቀስ ሊጀምሩ ሲሉ አባቷ ሁሉንም እየተቆጡ
የልጃቸውን የቤዛዊትን ጭንቅላት በስስት በሁለቱም እጃቸዉ ይዘዉ ግንባሯን በፍቅር እየሳሟት እንድትገባ እጆችዋን ይዘዉ ተያይዘዉ በደስታ ወደ ቤታቸዉ ዉስጥ ዘለቁ።

ፍፁም ህመሙ እየባሰበት እየተሰቃየ ነዉ
ህመሙ ዉስጡ ድረስ ዘልቆ ይሰማዋል
የእግሮቹ ደም አዘዋዋሪ ነርቮች የሚነጥር ከበሮ ይመስል በአይምሮዉ ሲመቱ ይሰማዋል ክፍለሀገር ላሉት ዘመዶቹ እንዲያስታምሙት መደወል ቢፈልግም
ማስጨነቅ ስላልፈለገ ተወዉ ቤዛዊት መጥታ አብራዉ ብትሆን
ህመሙ የሚተወዉ እየመሰለዉ ነዉ ነገር ግን ጠፋች ብለዉ
የነገሩትን ወሬ ከሰማ ጀምሮ እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነዉ ያደረዉ።

ከንጋቱ ጋር ጠዋት የነቃዉ ፍፁም ያለ ሰዉ ድጋፍ መንቀሳቀስ
ካልቻለበት አልጋ ሆኖ በር በሩን አተኩሮ ዉጪ ዉጪዉን ያያል የቤዛዊትን መምጣት ተስፋ አርጎ እያለመነ
ብትመጣ በሚል ተስፋ እየጠበቃት ነዉ በሩቁ በበሩ መግቢያ
የምትገባ ሴት ስላየ በደስታ ተቁነጠነጠ
ቤዛዊት የመጣች ስለመሰለዉ ወደ ግንባሩ እጆቹን ሰዶ
ቆንጆ ለመመለስ አስቦ ፊቱን ጠራረገ የፊቱ ቁስል እየደረቀለት
ቢሆንም ህመሙ ግን አሁንም ድረስ ስለሚሰማዉ እጆቹን በቀስታ ነበር ፊቱ ላይ የሚያንቀሳቅሳቸዉ
አይኖቹን ድጋሜ ወደ በሩ ሰደዳቸዉ የጠባቃት ቤዛዊት አደለችም
የሆስፒታሉ ነርስ መሆንዋን ሲያረጋግጥ ተበሳጨ
ሆድ ባሰዉ ብቸኝነቱ እና ዘመድ አዝማድ ብሎ አብሮት በዚህ
በህመሙ ስዓት ከሞት አፋፍ ተመልሶ በቆየበት ጊዜ እንኳን
ከጎኑ የኔ የሚለዉ ሰዉ ስለሌለዉ
እያዘነ ማሰብ ጀመረ።

"ብሞትስ ኖሮ"
አይኖቹን ፍዝዝ አርጎ ብዙ ሰዓት ተከዘና ተመልሶ
"በመትረፌ እንደመፅናናት ሞቴን ለምን እመኛለሁ?"
ሲል እራሱን ጠይቆ ማሰቡን አቆመ።
ፍፁም የህመም ስሜቱ ሲቆይ እየባሰበት ነዉ
እራሱን ከባድ ነገር እንደተጫነበት እየተሰማዉ ነዉ ጭንቅላቱ
ማንቀሳቀስ እራሱ እየከበደዉ ከወደ ታች እግሩን መጠዝጠዝ
ሲጀምረዉ ህመሙ የተሰማዉ ቦታ ለመዳበስ በእጆቹ ለመዳበስ
በቀስታ ጎንበስ ሲል የሆነ ሰዉ የመጣ ስለመሰለዉ
"እህ እህ"
በረጅሙ እየተነፈሰ አሁንም ቤዛዊት መስላዉ ዞረ
አይኖቹ የሚያዩት ነገር ብዥ እያለበት ነዉ
ሁለት ቀጫጭን ጎማወች ያሉት የሚገፋ ወንበር የሚመስል
ነገር ታየዉ እየገፋች የምትመጣዉ ግን የገጪዉ ሚስት ነበረች

"ቤዛዊት መጣሽ መ.ጣ.ሽ..."

ፍፁም አይኖቹን መግለጥ እያቃተዉ የሚንሾካሾኩ ቃላት አዉጥቶ
ተዝፍልፎ ወደ ትራሱ ተዘረረ።

ቤዛዊት ምግብም ዉሀም አልጠጣም ፍፁም ያለበትን ንገሩኝ
ብላ ድርቅ ስላለች ነገሯት ልቧን ጭንቅ እያላት የእናቷን ነጠላ ብቻ
ከላይ ደርባ በእማማ ስንቅነሽ የቆየ ቀሚስ የፍፁምን አይኑን
አሳየኝ እያለች ወደ ሆስፒታል ገሰገሰች።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#ሸክሜ

እሳት ጐርሰሽ
እሳት ለብሰሽ
“አህያ ነህ!” አልሽኝ፤
እንደ ውሃ ሆኜ
ያልሽውን አምኜ
ትክክል ነሽ አንቺ
“አህያ ነኝ ብዬ ፣
በሰላም ሸኘሁሽ
ሰውነቴን ጥዬ፡፡
እንደአፈር ቆጠርኩት
እራሴን መልሼ፤
ከላዬ አራገፍኩሽ
በቃሌ ተንፋሼ፡፡
ሽክሜ ተቃለሽ
ነፃ ስሆን እኔ ፣
አህያም አይደለሁ
ገባኝ ሰው መሆኔ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኘ🔘
#አይነኬውን_ነክተሽ 💚 💛 ❤️

ሲኦልሽን ጫርሽው
በገሀነም ከሰል
ደሞ ያንቺም መጥፊያ
ተቃረበ መሰል።
💚 💛 ❤️
🔘ኢዛና መስፍን🔘 ለቤቲ
#የእምነት_ክህደት_ቃል

እምነት እና ክህደት ፥ እነዚህ ሁለቱ
የሚከሰቱበት ፥ አንድ ነው ቅፅበቱ፡፡

ለምሳሌ ያህል
" ታምነኛለች" ብዬ
ፍፁም አምንሽ ነበር!
እኔን በሌላ ሴት ፥ አትጠረጥሪኝም
እምነቴን ንደሽ ነው ፥ “ካድከኝ” ብትይኝም
ባላምንሽ ኖሮማ
እጠነቀቅ ነበር
ከሌላ ሴት ጋራ ፥ ተኝቼ አታዪኝም!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ድሮ_እና_ዘንድሮ

ብሉይ እንደቀላል ሚተረክ “ሚተረት በፍፁም አይደለም
መገኛ ነው ኮ ሥርወ መሠረት መነሻ የአዲስ ዓለም፡፡
በዕውቀት የላቀ በሐሳብ የመጠቀ
ሥውር ነው ምሥጢሩ ፍቺው የረቀቀ
እፁብ ድንቅ ሥራ
ታትሞ የተተወ የፍጥረታት ዱካ የፈጣሪ አሻራ፡፡
በጊዜ ታንኳ ላይ ዘመናት ተሻግሮ
“ከየት መጣን?” “ማን ነበርን?”
ይሉትን ጥያቄ መመለስ የሚችል ማሳየት ዘርዝሮ
የሩቁን ማሳያ ገፀ ትውፊታዊ ዘይቤያዊ ኑሮ
አቧራ የጋረደው ብሩህ መስታወት ነው መመልከቻ ዞሮ፡፡
“ምኑ ነው?” አንበል ድሮን ለዘንድሮ፤
ዘንድሮ “ምኑ ነው?” አንበል ለድሮ፡፡
ክበባዊ ዑደት ቁርኝት ያላቸው የርስ በርስ ተሳስሮ
ሳይነጣጠሉ
አብረው የሚኖሩ
አንድም ሁለት ናቸው ድሮ እና ዘንድሮ ፤
አንዱ አይኖርም ነበር አንዱ ባይኖር ኖሮ፡፡
👍1
#ይድረስ_ለአያ_እከሌ

እኔ'ኮ
እንዳንተ በክብር የሚጠራ የገነነ ስም የለኝም
እንኳን ሀገሬው ቀርቶ መንደሬው በቅጡ አያውቀኝም፡፡
አንተና እኔ በተፈጥሮ
በሰውነት እኩል ብንሆንም
እንደሰው እኩያመች አይደለንም እንለያያለን በዝናም ሆነ በገድል
አንተ
የታዋቂነትን አክሊል ደፍተሃል ተቀዳጅተሃል የዝነኝነትን ድል
ጊዜ ሁኔታ ፈቅዶልህ ከፍ ከፍ ብለሃል በዕድል፡፡
ታድያ
እጅ ተፍንጅ ብይዝህ የፈጠራን መንፈስ። ስትገድል
“እንዲህ አረገኝ ብል
እኔን ማንም አያምንም
የፍትሕ ሚዛኑ አዘንብሎ ወደ አንተ ነው እሚያጋድል፡፡
ስለዚህ
ልፋ እንዳለው መነኩሴ ቆብን ቀዶ እንደመስፋት
ሥራፊ.ትነት መስሎ ቢታየኝ ቢሆንብኝ ከንቱ ልፋት
ስራፈትነት መስሎ ቢታየኝ ቢሆንብኝ ከንቱ ልፋት
ክፉ ስራህን ማጋለጥ
አንተን በክፉ ማንሣት ቸግሮኛል ስምህን ማጥፋት፡፡
ፈጠራው የኔ ሳይሆን የሱ ነው" ላትል
ስምህን በክፉ ሥራህ አሥሬ ባነሳ ብጥል
“ውጉዝ ከመአርዮስ” ብል በርግማንም ባብጠለጥል
“እኔን ከምድር አያነሳኝ “አንተን" ከሰማይ አይጥል፡፡
እውነቱ እንደንጋት እያደር ቆይቶ እስከሚጠራ
እስቲ በጐ በጐውን ስለልባችን ሐቅ እናውራ፡፡
ኧረ ለመሆኑ ምን ይሰማሃል? በተራሰው ድንቅ ሥራ
ከዳር እዳር ዝናህ ሲናኝ ስምህ በአክብሮት ሲጠራ::
ለእኔ ግን ይሰማኛል ስምህ ሲገዝፍ ከተራራ
ግዘፍ ነስቶ ሕይወት ዘርቶ ነፍስ ሲዘራ።
እፁብ ድንቅ በተሰኘው የኔ ያዕምሮ ፈጠሪ-
ስትባረክ ስትመረቅ ስትደነቅ ይደንቀኛል
አንዳንዴ
የእኔን ሐሳብ እንኳን ሰረቅክ ያሰኘኛል፡፡
እናም
እየኖርኩኝ ስላኖርከኝ ከፍ ብያለሁ ዕድሜ ላንተ!
ፈጠራዬማ ነፍስ ዘርቷል ስሜ ብቻ ነው በቁሙ የሞተ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ከሞት_በኋላ

እምልልሻለሁ
ዕድሜዬን በሙሉ በሕይወት እስካለሁ
ፅኑ ቃልኪዳን ነው ፍቅሬ አፈቅርሻለሁ፡፡
ይሁንና፧
ልሆን እችል እንደሁ በሐሳቤ ምፀና
አፈር ውስጥ ስገባ
ምን እንደሚፈጠር አላውቀውምና
እራሴን አላስርም በቃለ መሐላ፡፡
እምልልሻለሁ
አንድም ሰው አላውቅም ከሞተ በኋላ
ጠልቶ ያፈቀረ አፍቅሮም የጠላ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ልትወደኝ_ነው_መሠል

“ጠላትህን ውደድ” ፥ ይላል ቅዱስ ጌታ
እያለች ስትነግረኝ ፥ ስትሰብከኝ ሰንብታ
ስብከቷን አምኜ
" 'ወድሻለሁ” ብላት ፥ በሰው ፊት አቅልላኝ
ልትወደኝ ነው መሠል ፥ ጠልታኝ ሔደች ጥላኝ ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ኀሰሳ_ሀዘን....

የሰው ልጅ ሀዘኑ
አንድም ከእርጅናው
አንድም ከሞቱ፣
ሁሉም
መች ይቀራል....
እየሰነበቱ!!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
👍1
#አምሳሉ

ስሜቴ ተናውጦ
ውስጤ ተበጥብጦ
ጓደኞቼ ይሉኛል
ለምን ይናደዳል? ስለምን ይቆጣል? "
በጭራሽ አይበሉኝ “ለምን ይለወጣል?”
እንኳን እኔ የሰው ዘር “ማሰብ እምችለው
እንዲት ትንሽ ፍጡር ደመነብስ ያደለው
ክፉ ኃይል ሲገፋው
ሲሞክር ሊያጠፋው አካሉ ይናወጣል !
ትል እንኳን ሲነኩት ይንፈረጋገጣል።
ኃይለኛ ጥቃትን መቋቋም ሲያቅተወው
መቀበል ሲያቅተው
ተንፈራግጦ እኮ ነው ትል እንኳ 'ሚሞተው፡፡
ፈጣሪ በአምሳሉ ሲፈጥረኝ ለይቶ
በፀጋ ሲያገስፈኝ ሲሰጠኝ አድልቶ
ተንፈራግጦ መሞት አልቻልኩም ተሳነኝ )
ምክንያቱም እኔ
ከትል የተለየሁ የሰው ልጅ እኮ ነኝ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘