#ከሞት_በኋላ_ሕይወት
ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩን ያወቀ
ፈጣሪው ብቻ ነው ከፍጡራን የላቀ፡፡
ስው የማይደርስበት መንገዱም የራቀ
ፅንፍየለሽ ነው ጉዞው ምስጢሩ የረቀቀ፡፡
“ከሞት በኋላ ሕይወት
በዕውን አለ ወይ?” ብሎ የጠየቀ
ከጥልቁ ሕዋው ሥር
ምላሹን ለመስጠት ደፍሮ የጠለቀ ፤
እስከዛሬ ድረስ
ሲገባ ነው እንጂ አይታይ ሲወጣ፣
ምስጢሩን ለመግለፅ
አንድም ፍጡር የለም ተመልሶ የመጣ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩን ያወቀ
ፈጣሪው ብቻ ነው ከፍጡራን የላቀ፡፡
ስው የማይደርስበት መንገዱም የራቀ
ፅንፍየለሽ ነው ጉዞው ምስጢሩ የረቀቀ፡፡
“ከሞት በኋላ ሕይወት
በዕውን አለ ወይ?” ብሎ የጠየቀ
ከጥልቁ ሕዋው ሥር
ምላሹን ለመስጠት ደፍሮ የጠለቀ ፤
እስከዛሬ ድረስ
ሲገባ ነው እንጂ አይታይ ሲወጣ፣
ምስጢሩን ለመግለፅ
አንድም ፍጡር የለም ተመልሶ የመጣ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘