፩ ሃይማኖት
9.01K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን

@And_Haymanot

✞ በቅዱሳን ሰማዕታት ስም ወደ ታነጸው ወደዚህ ቤተ መቅደስ እንድትመጡ ጠራኃችው። ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ክፍለ ትምህርት 18 ✞

የተሃድሶ መናፍቃን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ቤተ ክርስቲያን ብለን አንጠራም ይላሉ እነርሱ ቤተ ክርስቲያን የሚሉት ጉባኤውን ብቻ ነው እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን ቅዱሳት መጻሕፍትንና የቤተ ክርስቲያንን ቀደምት አበውን መሠረት አድርገን የተቀደሰውን ሥፍራ ቤተ ክርስቲያን እንለዋለን ነገር ግን የተሃድሶ መናፍቃኑ ምላሽ ይሆን ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት፦

✞ ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ትርጉም አለው እነርሱም፦

፩ኛ፦ የተወሰነ ቦታ (ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን)፦ ይህም በዘፀ 25፥8 ላይ "በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ" በሚለው በአምላካችን ቃል መሠረት በፈቃደ እግዚአብሔር የተገኘ በመሆኑ ነው ስለዚህ ለአምላካችን ማደሪያ የምንሰራው መቅደስ ቤተ ክርስቲያን ይባላል።

፪ኛ፦ የክርስቲያኖች ሕብረት ወይም አንድነት፦ ቅዱስ ጴጥሮስ በ1ኛ ጴጥ 5፥13 ላይ "ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል" በማለት ባስተላለፈው መልእክቱ ላይ የገለፀው በባቢሎን ያለችውን የክርስቲያኖች ማሕበር ወይም ጉባዔን የሚያመለክት ነው ስለዚህ የክርስቲያኖች ሕብረት ወይም አንድነት ቤተ ክርስቲያን ይባላል።

፫ኛ፦ እያንዳንዱ ክርስቲያን፦ ይህም ከያዕቆብ የተወለደ ሁሉ ቤተ እስራኤል እንደሚባል ሁሉ በመንፈሳዊና በምስጢራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ ምእመናን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ ቤተ ክርስቶስ እንደማለት ነው ቅዱስ ጳውሎስም በ1ኛ ቆሮ 3፥17 ላይ "ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" ብሏል ይህ ቃል እኛ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችንን ያመለክታል ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ይባላል።

☞ በእንግሊዝኛ #Church፣ በጀርመንኛ #Kirche፣ በደች #Kerke የሚሉትና ሌሎች ተመሳሳይ ስሞች ሁሉ #Kyriakon ከሚለው የግሪኩ ቃል የተገኙ ናቸው ትርጉሙም፦ "ማንኛውንም የክርስቶስ የሆነ ነገር" ማለት ነው ይህም ቃል ከመነሻው ለቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ስያሜ ይውል የነበረ ነው የላቲኑም ቃል "አቅሌስያ _ Ecclesia" እና ከእርሱ ወጥተው በልዩ ልዩ የላቲን ቤተሰብ ቋንቋዎች ጥቅም ላይ የዋሉ ተመሳሳይ ቃላት ሁሉ በመጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋሉት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ለመጥራት ነበር የላቲኑ ቃል መነሻው የግሪኩ "አቅሌሲያ" ሲሆን የቃሉ ትርጉምም "የራስ ገዝ ከተማ የዜጎች መሪ ጉባኤ" ማለት ነው።

❖ ሐዋርያት በተለያየ ቦታ በቤተ ክርስቲያን ይሰበሰቡ ነበረ ይህም፦
ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት በጽርሐ ጽዮን በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ሳሉ ነበር/የሐዋ 2፥1/
ሐዋ 11፥26 ላይም "በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ" ተብሎ ተጽፏል።

✞ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ቤተ ክርስቲያንን በቅዱሳን ስም ትሰይማለች ይህም አስቀድሞ በነብዩ ኢሳይያስ ትንቢት ተነግሮ ነበር "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ /ኢሳ 56፥4-5/ ብሎ በተናገረው መሠረት አብያተ ክርስቲያናት በቅዱሳን ስም ይጠራሉ የመጀመሪያዋም ቤተ ክርስቲያን የተሠራችው በፊልጵስዩስ ከተማ ሲሆን ይኼውም በ34 ዓ/ም ነው።

✞ ቤተ ክርስቲያን "የሰማይ ደጅ" ትባላለች አባታችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በራእይ መላእክት ሲወጡባትና ሲወርዱባት፣ እግዚአብሔርም በላይዋ ተቀምጦባት ያያትን ቦታ "ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው" አለ /ዘፍ 28፥17/ ያዕቆብ ቦታውን ያከበረበት ሥርዓት በቤተ ክርስቲያን ተጠብቆ ዛሬም አዲስ ቤተ ክርስቲያን ይከብርበታል።

የተሃድሶ መናፍቃኑ ከላይ ያየነውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታዎች ባለመረዳት ምንፍቅናቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስባል በሐዋ 17፥24 ላይ "ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም" የሚለውን ሃይለ ቃል በመጥቀስ ለማወናበድ ይጥራሉ።

☞ ለመሆኑ "ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም" ማለት ምን ማለት ነው?

✞ የእግዚአብሔርን አነዋወር በተመለከት ቅዱሳት መጻሕፍት በልዩ ልዩ መንገድ ገልጠውታል ለምሳሌ፦
በሰማይ የምትኖር /ማቴ 6፥9/፦ ይህም ክብሩን ለመናገር ነው
ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ /ዮሐ 6፥56/፦ ይህም ማለት በጸጋ አድሬበት እኖራለው ማለት ነው
ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን፤ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን /መዝ 131፥7 /፦ ይህም በአንድ በኩል እግሮቹ የቆሙበትን መስቀል በሌላ በኩልም መቅደሱን ነው

❖ በመሆኑም እግዚአብሔር ሰው በሠራው ቤት አይኖርም ማለት አይወሰንም ማለት ነው የአሕዛብ ጣዖታት በቤተ ጣዖቱ ወይም መኖርያቸው ነው በሚባለው በኦሊምፐስ ተራራ የተወሰኑ ናቸው እግዚአብሔር ግን ለመገለጫው ቦታ ይመርጣል ማለት በዚያ ቦታ ይመሰናል ማለት አይደለም ክርስቲያኖች "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?" ተብለናል /1ኛ ቆሮ 3፥16/ ያ ማለት በጸጋ አድሮባችሁ ይኖራል ማለት ነው እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእናንተ ውጭ የለም ማለት አይደለም፣ ወይም ደግሞ በእንተ ተወስኖ ይኖራል ማለት አይደለም።

ስለዚህ ተወዳጆች ይቺ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን የማትታደስ እንደመሆኗ መጠን የተሃድሶ መናፍቃን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አያስፈልግም ከሚሉት ሀሰተኛ ትምህርቶች እራሳችንን ጠብቀን በንጽህቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችን ጸንተን መኖር ነው የሚገባን የተሃድሶ መናፍቃኑም ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ተረድተው፣ ልብ ገዝተው በክርስቶስ ደም ወደ ተመሠረተችውና የገሃነም ደጆች ወደ ማይችሏት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ይመጡ ዘንድ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ምኞት ነው።

✞ አምላከ ቅዱሳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ከቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ ጠላቶች ከተሃድሶ መናፍቃን ይጠብቅልን አሜን!!!✞
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን

የተሃድሶ መናፍቃን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ቤተ ክርስቲያን ብለን አንጠራም ይላሉ እነርሱ ቤተ ክርስቲያን የሚሉት ጉባኤውን ብቻ ነው እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን ቅዱሳት መጻሕፍትንና የቤተ ክርስቲያንን ቀደምት አበውን መሠረት አድርገን የተቀደሰውን ሥፍራ ቤተ ክርስቲያን እንለዋለን ነገር ግን የተሃድሶ መናፍቃኑ ምላሽ ይሆን ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት፦
@Meserete_Yared_Asasa

✞ ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ትርጉም አለው እነርሱም፦

፩ኛ፦ የተወሰነ ቦታ (ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን)፦ ይህም በዘፀ 25፥8 ላይ "በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ" በሚለው በአምላካችን ቃል መሠረት በፈቃደ እግዚአብሔር የተገኘ በመሆኑ ነው ስለዚህ ለአምላካችን ማደሪያ የምንሰራው መቅደስ ቤተ ክርስቲያን ይባላል።

፪ኛ፦ የክርስቲያኖች ሕብረት ወይም አንድነት፦ ቅዱስ ጴጥሮስ በ1ኛ ጴጥ 5፥13 ላይ "ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል" በማለት ባስተላለፈው መልእክቱ ላይ የገለፀው በባቢሎን ያለችውን የክርስቲያኖች ማሕበር ወይም ጉባዔን የሚያመለክት ነው ስለዚህ የክርስቲያኖች ሕብረት ወይም አንድነት ቤተ ክርስቲያን ይባላል።

፫ኛ፦ እያንዳንዱ ክርስቲያን፦ ይህም ከያዕቆብ የተወለደ ሁሉ ቤተ እስራኤል እንደሚባል ሁሉ በመንፈሳዊና በምስጢራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ ምእመናን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ ቤተ ክርስቶስ እንደማለት ነው ቅዱስ ጳውሎስም በ1ኛ ቆሮ 3፥17 ላይ "ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" ብሏል ይህ ቃል እኛ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችንን ያመለክታል ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ይባላል።

☞ በእንግሊዝኛ #Church ፣ በጀርመንኛ #Kirche ፣ በደች #Kerke የሚሉትና ሌሎች ተመሳሳይ ስሞች ሁሉ #Kyriakon ከሚለው የግሪኩ ቃል የተገኙ ናቸው ትርጉሙም፦ "ማንኛውንም የክርስቶስ የሆነ ነገር" ማለት ነው ይህም ቃል ከመነሻው ለቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ስያሜ ይውል የነበረ ነው የላቲኑም ቃል "አቅሌስያ_Ecclesia" እና ከእርሱ ወጥተው በልዩ ልዩ የላቲን ቤተሰብ ቋንቋዎች ጥቅም ላይ የዋሉ ተመሳሳይ ቃላት ሁሉ በመጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋሉት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ለመጥራት ነበር የላቲኑ ቃል መነሻው የግሪኩ "አቅሌሲያ" ሲሆን የቃሉ ትርጉምም "የራስ ገዝ ከተማ የዜጎች መሪ ጉባኤ" ማለት ነው።
@Meserete_Yared_Asasa

❖ ሐዋርያት በተለያየ ቦታ በቤተ ክርስቲያን ይሰበሰቡ ነበረ ይህም፦

ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት በጽርሐ ጽዮን በኢየሩሳሌ ተሰብስበው ሳሉ ነበር/የሐዋ 2፥1/
ሐዋ 11፥26 ላይም "በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ" ተብሎ ተጽፏል።

✞ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ቤተ ክርስቲያንን በቅዱሳን ስም ትሰይማለች ይህም አስቀድሞ በነብዩ ኢሳይያስ ትንቢት ተነግሮ ነበር "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ /ኢሳ 56፥4-5/ ብሎ በተናገረው መሠረት አብያተ ክርስቲያናት በቅዱሳን ስም ይጠራሉ የመጀመሪያዋም ቤተ ክርስቲያን የተሠራችው በፊልጵስዩስ ከተማ ሲሆን ይኼውም በ34 ዓ/ም ነው።

✞ ቤተ ክርስቲያን "የሰማይ ደጅ" ትባላለች አባታችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በራእይ መላእክት ሲወጡባትና ሲወርዱባት፣ እግዚአብሔርም በላይዋ ተቀምጦባት ያያትን ቦታ "ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው" አለ /ዘፍ 28፥17/ ያዕቆብ ቦታውን ያከበረበት ሥርዓት በቤተ ክርስቲያን ተጠብቆ ዛሬም አዲስ ቤተ ክርስቲያን ይከብርበታል።

የተሃድሶ መናፍቃኑ ከላይ ያየነውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታዎች ባለመረዳት ምንፍቅናቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስባል በሐዋ 17፥24 ላይ "ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም" የሚለውን ኃይለ ቃል በመጥቀስ ለማወናበድ ይጥራሉ።

@Meserete_Yared_Asasa
☞ ለመሆኑ "ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም" ማለት ምን ማለት ነው?

✞ የእግዚአብሔርን አነዋወር በተመለከት ቅዱሳት መጻሕፍት በልዩ ልዩ መንገድ ገልጠውታል ለምሳሌ፦
በሰማይ የምትኖር /ማቴ 6፥9/፦ ይህም ክብሩን ለመናገር ነው
ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ /ዮሐ 6፥56/፦ ይህም ማለት በጸጋ አድሬበት እኖራለው ማለት ነው
ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን፤ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን /መዝ 131፥7/፦ ይህም በአንድ በኩል እግሮቹ የቆሙበትን መስቀል በሌላ በኩልም መቅደሱን ነው

❖ በመሆኑም እግዚአብሔር ሰው በሠራው ቤት አይኖርም ማለት አይወሰንም ማለት ነው የአሕዛብ ጣዖታት በቤተ ጣዖቱ ወይም መኖርያቸው ነው በሚባለው በኦሊምፐስ ተራራ የተወሰኑ ናቸው እግዚአብሔር ግን ለመገለጫው ቦታ ይመርጣል ማለት በዚያ ቦታ ይመሰናል ማለት አይደለም ክርስቲያኖች "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?" ተብለናል /1ኛ ቆሮ 3፥16/ ያ ማለት በጸጋ አድሮባችሁ ይኖራል ማለት ነው እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእናንተ ውጭ የለም ማለት አይደለም፣ ወይም ደግሞ በእንተ ተወስኖ ይኖራል ማለት አይደለም።

ስለዚህ ተወዳጆች ይቺ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን የማትታደስ እንደመሆኗ መጠን የተሃድሶ መናፍቃን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አያስፈልግም ከሚሉት ሀሰተኛ ትምህርቶች እራሳችንን ጠብቀን በንጽህቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችን ጸንተን መኖር ነው የሚገባን የተሃድሶ መናፍቃኑም ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ተረድተው፣ ልብ ገዝተው በክርስቶስ ደም ወደ ተመሠረተችውና የገሃነም ደጆች ወደ ማይችሏት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ይመጡ ዘንድ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጸሎት ነው።

❖ በዓለት ላይ ነውና ያቆማት አጽንቶ
❖ በደሙ ነውና የቀደሳት ዋጅቶ
❖ ይጠብቃልና ጠባቂዋ ተግቶ
❖ የገሀነም ደጆች አይችሏትም ከቶ

✞ አምላከ ቅዱሳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ከቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ ጠላቶች ከተሃድሶ መናፍቃን ይጠብቅልን አሜን!!!✞

✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥