በመላዋ ኢትዮጵያ ፀረ ተሃድሶ
ዘመቻው ተቀጣጥሏል
አከተመ
*★★★*
#ማስታወሻ ✔ እኔ ደግሞ ነገ ከቅዳሴ በኋላ የአጅሬ በግዋሻውን አስደማሚ የስልክ " ቀደዳ " ክፍል ሁለቱን ይፋ አወጣዋለሁ ። እናም እሰከዚያው ድረስ ይኸንን ጦማር እየኮመኮማችሁ ተረጋግታችሁ ጠብቁኝ ።
#ETHIOPIA_DUBAI_USA | የግሪሳው ሸቀጥ በሙሉ ከያለበት እየተለቀመ ወደ እሳት እየተዶለ ነው ። የስልክ ጥሪ የነበሩት የግሪሳው ቃርዳዎችም ከሚሞሪ ላይ እየተሰረዙ እየተወገዱ ነው ።
¶ ይኽ ጦማር ብዙ #Share_Share_Share ይፈልጋል ።
¶ የተዋሕዶ አናብስት የፀረ ተሃድሶው እንቅስቃሴ በመጠኑ በዚህ ጦማር ለመዳሰስ ተሞክሯል ።
መቼም ወገኖቼ እዚህ ከራየን ወንዝ ማዶ ሆኜ ያለሁበትን ደስታ አትጠይቁኝ ። እንዴት አድርጌ ልግለጸው ። ኡፍፍፍ " ያ ረቢ ገለኒ ሲሀፍገው ያ ጎፍታኮ.! እልልሃለኋ እዚህ ከወንዙ ማዶ ቁጭ ብዬ ። ሃይ ታዲያ ከዚህ በላይ ምን ልበል ።
“ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኵሉ አጽናፈ ዓለም ” ተብለው በቅዱስ ወንጌል ከጌታ በተላኩት መሰረት፤የእምዬ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ከዚህ በላይ ምን እስኪመጣ ነው የምንጠብቀው በማለት ከላይ እስከታች ድረስ በመናበብ ዓለምአቀፍ ፀረ ተሃድሶ ዘመቻ ከፍተው በሚያስደንቅ ጥበብ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ መናፍቃኑ ለመቶ ዓመታት ተዘጋጅተው በእኛ ቡድን ላይ ተወስዶ የነበረውን የጫወታ ብልጫ በሳምንታት እንቅስቃሴ በፍጥነት ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረን የጣላትን ቡድን አረፋ እንዲደፍቅ አድርገነዋል ። " ኤታባቱ " አለ ሌኒን ።
ከቤተ ጉባኤያቱ እና ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የተውጣጡ ምሩቃን መምህራንና በኹለገብ የዕቀበተ እምነት አቀራረባቸው የተመሰከረላቸው በርካታ የትሩፋት ሰባክያንና ዘማርያን በጥምረት ነው ተሰባስበው በተዋሕዶ በኩል ያለውን ክፍተት በአንድ ሳምንት ውስጥ በመድፈን የግሪሳውን ቡድን ውኃ ውኃ ያሰኙት ። " እነዚህን ጉፋያዎች ያ አማላጅ የሚሉት ፣ የሳሎኑ ጽጌሬዳ ፣ የልቤ ንጉሥ ፣ ፍሬንዴ ፣ ጓደኛዬ ፣ ወንድሜ የሚሉት ኢየሱስ እንዴት አድርጎ እንደሚያድናቸውስ አሁን ነው ማየት ።
የቡድናችንን አሰላለፍና የተሰማሩባቸውን ሥፍራዎች እንደሚከተለው ለመግለጽ እንሞክራለን ።
፩ኛ፦ ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እና መ/ር ኅሊና በለጠ እነ ግሪሳው ፓስተር አሰግድ ፣ በግዋሻው ፣ ዕጩ ፓስተር ቃለአብ ካሳዬ ፣ ምስኪኑ የበጋሻውና የአድነው ወንድሙ አሽከር የሆነው የደሴው በሪሁን ፣ እነ ዘርፌ ፣ እነምርትነሽ ፣ መርዛቸውን በተከሉባት ድሬደዋ (በድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል)፤ ነው የተሰማሩት ። በተለይ የሳቢያን ገብርኤል የእነ በጋሻው መፈንጪያም ግዛት ነበረ ። ጉባኤውን የተከታተሉና የታዘቡ የመረጃ ምንጮቼ እንደነገሩኝ ከሆነ በድሬደዋ እነ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተሃድሶን ጥርሱን አውልቀው በድዱ አስቀሩት ነው የተባለው ። ከስልክና ከቤቱ የድሬ ህዝብ የአዝማሪዎቹን ቃርዳ አስወግዶ ለእሳት ራት አድርጎታል ።
፪ኛ፦መጋቤ ሃይማኖት ተስፋዬ ሞሲሳ እና መጋቤ ሐዲስ ቀለም ወርቅ ታደሰ ደግሞ የአዝማሪት ምርትነሽ የትውልድ ሀገርና አጥቢያዋ ላይ ነው የሄዱላት ። (በይርጋለም ዐማኑኤል)፤ ወዳጄ ጨዋታው በጠላት ሜዳና ሰፈር ላይ ሆኖ አርፏል ። የተባረረ እንጂ የተጠናከረ እና አስተማማኝ የሆነ መረጃ ከይርጋለም አልደረሰኝም እንጂ የግሪሳዎቹ ሸቀጦች እንደጉድ መሰብሰባቸውን ከዚሁ ስፍራ ተነግሮኛል ።
፫ኛ፦ መ/ር ምትኩ አበራ እና ዲ/ን ታደሰ ወርቁ ደግሞ ሊቀመዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ ፣ ዘማሪት ማርታ ኃይለ ሥላሴ ፣ እና የዜማ ዕቃ ተጫወቹ የምወደውና የማከብረው ወንድሜ ኤልያስን ይዘው ወደ (በቦንጋ ኪዳነ ምሕረት)፤ነው የከተሙት ። ቦንጋ በእነ በግዋሻውና አሰግድ አማካኝነት ህዝቡን ግራ ያጋባች ከተማ ናት ። የአቶ አጥናፌ ልጆች ተአምርአየሁ አጥናፌ ፣ ደረጀ አጥናፌን የመሳሰሉ ከሃድያን የእናት ጡት ነካሾችም የፈነጩባት ከተማም ነበረች ። በሊቀጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ቸልተኝነት ተሐድሶአውያኑ ቸርች እስከመክፈት የደረሱባት የሚዛን ተፈሪ ጎረቤት ነበረች ቦንጋ ። ዛሬ በላ ወረደባታ ታዲያ ።
በቦንጋ ለጉባኤው የሚመጡ ምእመናን የከተማዋ የመኪና ባለንብረቶች መኪና በነጻ አቅርበዋል ። ዛሬ ህዝቡ በየቤቱ የተቀመጠውን የግሪሳዎቹን ቃርዳ እየለቀመ አምጥቶ በቤተክርስቲያን ሲያስረክብ ውሏል ።
፬ኛ፦ መ/ር በላይ ወርቁ እና መ/ር ተመስገን ዘገየ ደግሞ ወደ ደብረ ዘይት ቅዱስ ሚካኤል እና በአዳሚ ቱሉ ቅድስት ማርያም)፤ አቅንተው ተአምር ሲሠሩ ውለዋል ። ወንድሜ ቀሲስ አብርሃም ከደብረዘይት እንዳደረሰኝ መረጃ ከሆነ የህዝቡን ስሜት እንዲህ ነው ብሎ መግለጽ አይቻልም ነው ያለኝ ። ምድር ጠበበን ፣ ለጥምቀትና ለታላለቅ በዓላትም በዚህን ያህል መጠን የመጣ ህዝብ አላስታውስም ብሎኛል ወንድሜ ቀሲስ አብርሃም ። ወዳጄ መምህር በላይ ወርቁ ማለት ራሱን ያልገለጠና በሚፈለገው መጠን አገልግሎት አልሰጡም ብዬ ከምቆጭባቸው አገልጋዮች መካከል አንዱና ዋነኛው ወንድም ነው ። በላይ የደሴ ልጅ ነው ። ከእነ አባመፍቀሬሰብ እግር ስር ቁጭ ብሎ ያደገ ። እናም በላይ ሲያስተምር ማድመጥ የነፍስ እርካታን ይሰጣል ። በተለይ አይጀምረው እንጂ እንዲህ ተሃድሶ ላይ መዝመት ከጀመረ መመለሻም የለው ወዳጄ ። ደብረ ዘይት በበላይና በተሜ ዋይዋይ ስትል ከርማለች ። ህዝቡ በደብረ ዘይትም የግሪሳውን ቃርዳ ከቤቱ ተሸክሞ አምጥቶ ለእሳት ዳርጎታል።
፭ኛ፦ መ/ር ዐብይ መኰንን እና መ/ር ኢዮብ ይመኑ ወደ (በሻሸመኔ ቅድስት ልደታ)፤ እንደሄዱ እንጂ በዚያ የገጠማቸውን ተጠናከረ መረጃ አልደረሰኝም ። እንደደረሰኝ አቀርብላችኋለሁ
፮ኛ፦ ዶ/ር ዘሪሁን ሙላቱ እና መ/ር ዐብይ መኰንን [ በሃላባ ቅድስት ማርያም ፤ በቦዲቲ ] ቦዲቲ የተረፈ አበራ የትውልድ ሃገር ናት ፣ በካራቴ ሰንበት ተማሪዎቹን በጉባኤ መሃል አፈር ከድሜ የሚያስግጡ መነኩሴ አስተዳዳሪ የነበረባት ፣ እነበጋሻው የክህደት ቅርሻታቸውን ዘርግፈውባት የመጡባት ከተማ ናት ሃላባ ። በሃላባ እነ ዶክተር ዘሪሁን ምን እንደገጠማቸው እንዲሁ የተጠናከረ መረጃ ከስፍራው አልደረሰኝም ። ነገር ግን በእኔ በኩል ዶር ዘሪሁን የደረሰበት ከተማ በመናፍቃን ዘንድ መዓት እንደወረደባቸው ነው የምቆጥረው ። እንደው ፈረደባቸው ።
፯ኛ፦መ/ር በኃይሉ በቀለ እና መጋቤ ጥበባት ሲያምር ተክለ ማርያም (በሻኪሶ - መጋዶ)፤ ሻኪሶ የእነበጋሻው የገንዘብ ምንጭ የሆነች የወርቅ ሀገር ናት ። በዚያም ጉባኤው ምን እነደሚመስል መረጃው አልደረሰኝም ።
፰ኛ፦ መጋቤ ሐዲስ ድጋፌነህ ኃይለ ሚካኤል(በሀገረ ማርያም)፤ ሀገረ ማርያም የዘመተው ድጋፌነህ ምን እንደደረሰ ስለእሱም መረጃ አልደረሰኝም ።
፱ኛ፦መ/ር ምሕረተ አብ አሰፋ እና ዲ/ን ብሌን ጌታቸው (በዱባይ ቅዱስሚካኤልና ቅድስት አርሴማ )፤ የእነ ፓስተር አሰግድ ፣ የእነ ፓስተር ተስፉ እንዳለ ፣ የእነ ፓስተር በግዋሻው የገንዘብ ምንጭ ፣ የመዝናኛ ቦታ ፣ ለሚስትነት የሚሆኑ ቆንጆ ቆንጆ ልጃገረዶች መምረጫ ስፍራ ነበረች ። በቅዱስ ሚካኤል ስም አዳራሽ ከፍተው የፈነጩት ግሪሳዎች አሁን ቅዱስ ሚካኤልን ትተው " የዱባዩ ኢየሱስ " በለው በመክፈት ድራሻቸውን አጥፍተዋል ። ቤተክርስቲያንም በእነሱ ግዛት በነበረው ቤሪያ ላይ ታቦተ ቅዱስ ሚካኤልን እና ታቦተ ቅድስት አርሴማን ተክለው አካባቢውን ተሃድሶ ከሚባል የኢቦላ አይነት ቫይረስ አጽድተውታል ። መቼም ትናንት በ