፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
መፅሀፈ ሄኖክ
ክፍል 2
ሄኖክ መፅሀፈ ሄኖክን ከፃፈ በሁዋላ መፅሀፉን ለልጁ ለማቱሳላ ይሰጠዋል ማቱሳላም ለላሜህ ላሜህም ለኖህ ኖህም ከጥፋት ውሀ በሁዋላ ለልጆቹ ይሰጣቸዋል እንዲህ እያለ እስከ ንጉስ
ሰሎሞን ዘመን ይደርሳል በንጉስ ሰሎሞን ጊዜ ኢትዮጵያዊው የንጉስ ሰሎሞን ልጅ ቀዳማዊ ምኒሊክ ታቦተ ፅዮንን ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ይዞ ሲመጣ ይዟቸው ከመጣው መፅሀፍት ውስጥ አንዱ መፅሀፈ ሄኖክ ነው ኢትዮጵያም ይሄን መፅሀፍ ጠብቃው ለብዙ ዘመናት ቆይታለች መፅሀፈ ሄኖክ ከኢትዮጵያ አጠፋፉ መፅሀፈ ሄኖክን ሰርቆ የወሰደው ጀምስ ብሩስ የተባለ ሰው ነው፡፡
@And_Haymanot
ጀምስ ብሩስ የአባይን ምንጭ ያገኘ እየተባለ ት/ቤት ሁሉ ያስተምሩናል ይህ ሰው የሰይጣን አምላኪዎች የምስጢር
ማህበራት አባል ነው በምእራቡ አለም ግን ያልተደበቀው እውነታ መፅሀፈ ሄኖክን ሰርቆ መውሰዱ ነው ፀሀፍቶች በ18ኛው መቶ ክ/ ዘመን ከኢትዮጵያ ስላመጣው መፅሀፍ አለም አወቀው እያሉ ይፅፋሉ እውነታው ግን በሀገር አሳሽነት ወደ ሀገራችን ገብቶ በጣና
ሀይቅ ከሚገኙት ገዳማትና ቤተ ክርስቲያናት ሶስት መፅሀፈ ሄኖኮችን ሰርቆ መውሰዱ ነው ከሶስቱ መፅሀፍት ውስጥ ሁለቱ በእንግሊዝና በፈረንሳይ ቤተ መፅሀፍት ሲገኙ አንዱ በጀምስ ብሩስ እጅ እንደነበረ ተፅፏል የሚገርመው ከኢትዮጵያ የተሰረቀው
መፅሀፈ ሄኖክ የተሟላ መሆኑና ትክክለኛነቱ ባይካድም የተቀዳ ነው
እያሉ ለመቀበል ሲተናነቃቸው ይስተዋላል እውነታውንም ለመሻር
የሚያቀርቡት ሀሳብ ዋነኛው መፅሀፍ ወይም የመጀመሪያው ሄኖክ የፃፈው መፅሀፍ በኢትዮጵያውያን ቋንቋ በግእዝ አይፃፍም ነው የሚሉት እናም አንድም ከግሪክ አልያም ከላቲን ተተርጉሞ
ኢትዮጵያውያን ጠብቀውት ቆይተዋል ባይ ናቸው ነገር ግን የግእዙ መፅሀፈ ሄኖክ ተተርጉሞ ቢሆን ኖሮ ልክ እንደ ኢትዮጵያው ሙሉ መፅሀፍ በሌላም ቋንቋ ተፅፎ ይገኝ ነበር ዳሩ ግን አልተገኘምና በዚህ እንኩዋን አሳማኝ እንዳልሆነ እንመለከታለን እነሱ
እንደሚሉት ከግሪክ ወይም ከላቲን አልያም ከአራማይክ ቢተረጎም
ኖሮ የኛ ሙሉ እንደሆነው እነሱም ጋር ሙሉ ይገኝ ነበርና። በእርግጥ በኢትዮጵያ የተገኙ ድንቅ ግኝቶችን ምእራባውያን ለመቀበል ሲከብዳቸው ይሄ የመጀመሪያው አይደለም የአክሱም
ሀውልት፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደር ቤተ መንግስት ህንፃዎች በኢትዮጵያውያን አልተገነቡም ሊገነቡም አይችሉም ብለው እውነታው አልዋጥ ብሏቸው ሲከራከሩ
ይደመጣሉ በዚም ተባለ በዚያ የተሟላው መፅሀፈ ሄኖክ በኢትዮጵያ ብቻ መገኘቱን ሊክዱ አይቻላቸውም ከዚህም ከመፅሀፈ ሄኖክ ጋር ኢትዮጵያን ለየት የሚያደርጋት ነገር አለ ይህም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ብቻ ናትና አምላካዊ ነው ብላ በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ያካተተችው እስከ ቅርብ አስርት አመታት የኢትዮጵያ አካል የነበረችው የኤርትራ ቤተ ክርስቲያንም ይህን ትጋራታለች።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ለምን አምላካዊ መፅሀፍ አደረገችው?

በመጀመሪያ በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የነብይነት ፀባይ ምንድነው ብለን ስንጠይቅ የሚመጣውን ማየትና ያለፈውን መናገር ነው ሄኖክም እንደ ነብይ ነው ትንቢት ይናገራል ከተናገረውም ነገር ውስጥ ለምሳሌ፦ ስለ ክርስቶስ መወለድ፣ ስለ ዳግም ምፅአትና ስለ መሳሰሉት ነገሮች ተንብዮዋል እነዚ ሁሉ ሄኖክ ከአምላኩ
የተገለፁለት ነገሮች ናቸው ይህንንም ያየው በእግዚአብሄር ገላጭነት በመልአክት መሪነት ነው ትልቁ ሊሰመርበት የሚገባው ነገር ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ኦ/ተ/ቤ/ክን ውጪ አምላካዊ ነው ብላ የተቀበለች ሀገር የለችም ይህንንም አለማድረጋቸው
የሚያስወቅሳቸው ነው። መፅሀፈ ሄኖክ ታማኝነቱን በምንመለከትበት ጊዜ ሀዋርያው ይሁዳ በምእራፍ 1:14 ላይ ሄኖክ የተናገረውን ትንቢት በራሱ መልእክት ላይ ገልፆት ይገኛል ስለዚህ ማንኛውም መፅሀፍ ደግሞ አምላካዊ
ነው ለመባል ማስረጃው በአበው መጠቀሱ ነው ከአበው ደሞ ሀዋርያ የሆነው ይሁዳ ጠቅሶት ይገኛል እንዲሁም በ2ኛ ጴጥ 2:1 ላይ ሄኖካዊ የፅሁፍ ይዘት ያለበትን ፅሁፍ እናገኛለን ይህም ስለ መላእክት መታሰርና ለፍርድ ተጠብቀው መኖራቸውን ቅዱስ
ጴጥሮስ በሚገልፅበት ጊዜ ኖህን መጥቀሱና በመፅሀፈ ሄኖክም ላይ መላእክት እነ አዛዝኤል ለፍርድ መጠበቃቸውን ሄኖክም ጴጥሮስም ገልፀውታል ይሁዳና ጴጥሮስ ከሀዋርያት ናቸው የተጠቀሱት በቀጣይ ደግሞ ስንመለከት ብዙ አበው በተለያዩ ትምህርቶቻቸውና ፁሁፎቻቸው መፅሀፈ ሄኖክን ጠቅሰውታል ከእነዚህም ውስጥ ቅዱስ አውግስጢንና ሰማእቱ ጀስቲን
ይጠቀሳሉ ስለዚህ መፅሀፉ በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በአበው መካከል ይከበራል ቤተ ክርስቲያንም ይሄን ባህልና ስርአት ተከትላ ጠብቃው ትገኛለች። ጀምስ ብሩስ የሰረቀው ሶስቱ መፅሀፍት ዛሬ ሰለጠነ የምንለው አለም አጥቶት የነበረውን መፅሀፍ በእጁ ያስገባ ዘንድ እድል ፈጥሮለታል ከግሪክ ወይም ከላቲን ተተረጎመ እያሉ የግእዙን
መሰረተ መነሻ መፅሀፍትነት ለመቀበል ቢተናነቃቸውም ግእዙን ግን ወደ ኢንግሊዘኛ፣ ጀርመንኛና ከ50 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ምስጢሩን ሊፈቱ ጉባኤ እስከ መመስረት ድረስ ይለፋሉ የመፅሀፉ መገኛ ሀገር ኢትዮጵያ በቅርብ የተገነጠለችው ኤርትራ
ስትጋራት ብቸኛ መለኮታዊ መፅሀፍ አድርጋ በመፅሀፍ ቅዱሷ ውስጥ በማካተት ትለያቸዋለች።።።።። ግን ሌሎቹ ሀገራት መፅሀፈ ሄኖክን መለኮታዊ ወይም አምላካዊ መፅሀፍ አይደለም ብለው ለምን በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ አላካተቱትም???
ይቀጥላል
ወስብሀት ለእግዚአብሄር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እውነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእውነት እናገራለሁ፣ እውነተኛ ትህትናስ ትሩፋት መስራት ነው፡፡
🍃ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ🍃
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ
መፅሀፈ ሄኖክ
ክፍል 3
ሌሎች የአለማችን ሀገራት መፅሀፈ ሄኖክን ለምን መለኮታዊ
ወይም አምላካዊ አይደለም ብለው በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ
አላካተቱትም?
ሌሎቹ ሀገራት ወይም ሀይማኖቶች ያላካተቱበት ምክንያት
የአፈንጋጮቹ መላእክት ነገረ ታሪክ ነው በመፅሀፈ ሄኖክ አዛዝኤል
በሚባል መልአክ መሪነት 200 መላእክት ከእግዚአብሄር ትእዛዝ
አፈንግጠው ወደ መሬት ወርደዋል ተብሎ ተፅፏል ወደ መሬት
የወረዱበትም ምክንያት ከሰው ልጆች ፍጥረታት በተለይም
በሴቶች ውበት ተማርከው ነው እናም በሀፀ ዝሙት ተነድፈው
ከሰው ልጆች ጋር ለመዘሞትና ልጆች ለመውለድ ወደ መሬት
ይወርዳሉ ከፈጣሪም ትእዛዝ ስለ አፈነገጡ ላለመካካድ
ተማምለው ወደ ምድር የወረዱበትንም ተራራ ኤርሞን እንዳሉት
ተፅፏል ኤርሞን ማለት አንድ ሆነን ተስማምተናል ላለመካካድ
ተማምለናል ለጥፋታችንም እርግማን ቢመጣብን በአንድነት
እንቀበለዋለን ማለት ነው።
@And_Haymanot
እነዚህ አፈንጋጭ መልአክት ለሰው ልጆች ማሳየት የሌለባቸውን
ክፉ ወይም ባእድ ነገሮችን አሳይተዋቸዋል ከአሳዩዋቸውም ነገሮች
ውስጥ ስለ ምትሀት፣ ስለ ጥንቆላ፣ ስለ ሞአርትና ስለተለያዩ
ነገሮች አስተምረዋቸዋል ከእዚህም በሁዋላ ፍዳቸው
እንደማይዘገይና ፈጥኖ እንደሚመጣ ሄኖክ ወቃሽ ሆኖ እንደቀረበ
የሚያትት ክፍል ነው እናም ይህ ደሞ መለኮታዊ አይደለም
መልአክት ፆታ የላቸውም ስለዚህ አያገቡም በማለት በመፅሀፍ
ቅዱስ ውስጥ እንዳይካተት ምክንያት ሆኗል።
ነገር ግን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለዚህ መልስ አላት እርሱም
ሁለትና ከዚያ በላይ በሚተነተንበት አንድምታ መልአክት በቀጥታ
ወረዱ ከሰው ልጆች ፍጥረታትም ጋር ዝሙት ፈፅመዋል አይደለም
ፍቺው ይህም ታሪክ ከስር መሰረቱ ሲተነተን አዳም በአቤል ፈንታ
ሴትን ይወልዳል የሴት ልጆችም ከቃዬል ልጆች በተለየ
ንፅህናቸውን ጠብቀው ደብረ ቅዱስ በሚባል ቦታ በተባህቶት
ይኖሩ ነበር የቃዬል ልጆች ደግሞ እርስ በእርሳቸው ሲንጠላጠሉ
ማለትም በፍትዎት ሲጫወቱ፣ ሲዳሩ፣ ሲዘፍኑ ይኖሩ ነበር በዚህም
ጊዜ ደቂቀ ሴት\የሴት ልጆች/ የደቂቀ ቃዬል \የቃዬል ልጆች/
በዝሙት ሲንጠላጠሉ በማየታቸው 200 ደቂቀ ሴት ከደብረ
ቅዱሳቸው ወርደው ከደቂቀ ቃዬል ጋር እርስ በእርሳቸው ተጋብተው
ግዙፉን ልጆችን ሊወልዱ ቻሉ ደቂቀ ሴትም ከደቂቀ ቃዬል
ለወለዷቸው ልጆች ለደቂቀ ቃዬል ያልተገለወውን ለምሳሌ፦ ስለ
ጦርት ስልት፣ ስለ ጦር መሳሪያዎች የመስራት ጥበብ፣ ስለ
ቅንድብ መኩዋካል፣ ስለ መአድናት፣ ስለ አለም መለወጥ፣ ስለ
መድሀኒት መቀመም፣ ስለ አፈርን ወደ ብረት መቀየር፣ ስለ ኮኮብ
ቆጠራ፣ ስለ ጊዜ ቀመርና... ስለ መሳሰሉት የበዛ ምስጢራትን
ገልፀውላቸዋል ልብ በሉ ይህ ከፈጣሪ ትእዛዝ ውጪና ለደቂቀ
ቃዬል ያልተገለጠ ነገር ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ የወለዷቸው ልጆች እጅግ በጣም ግዙፋን
መሆናቸው ነው እነዚህንም ግዙፋን ኔፊሊ እያለ ሄኖክ ይጠራቸዋል
ኔፊሊም በእውቀትና በአካል ስለገዘፉ በሰው ልጆች ላይ ገዢ ሆኑ
በምድርም ላይ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት ጨርሰው ፊታቸውን ወደ
ሰው ልጆች አዞሩ ደማቸውንም እስከ መጠጣት ደረሱ የሰው
ልጆችም እነሱን መመገብ እስኪያቅታቸው ድረስ የሰውን የላብ
ፍሬ ሁሉ ጨረሱ ከዛን ተመልሰው ሰዎችን ለመብላት ተነሱ
የመላእክቱ ወይም የደቂቀ ሴት ልጆችም በሰው ልጆች ላይ
የሚሰሩት ግፍ በረታ ይህም የሰው ልጆችን ዋይታ አበዛ ዋይታውም
እስከ ሰማየ ሰማያት ዘልቆ ለፈጣሪ ተሰማ እናም ፈጣሪ ኮብላይ
መላእክቱን \ደቂቀ ሴትን/ ይቀጡ ዘንድ እነ ቅዱስ ኡራኤልን ልኮ
በጥልቁ የምድር ጉድጉዋድ በጨለማ ይታሰሩ ዘንድ አደረገ ነገር
ግን ልጆቻቸው የሚፈፅሙት ሀጢአት አልቆመምና በዚህም የተነሳ
የምድርን ፍጥረታት ሁሉ በንፍር ውሀ ሊቀጣ እግዚአብሄር አምላክ
ወሰነ በሚል የኖህን ዘመን የጥፋት ውሀ \ማይ አይህ/ ከስር
መሰረቱ የተነተነው መፅሀፈ ሄኖክ ነው የአዳም አስረኛ ትውልድ
ኖህም ከቤተሰቡና ከተመረጡ የፍጥረታት ዘሮች ጋር እንዴት
እንደሚተርፍ ከፈጣሪ የተነገረውን በማስተላለፍ ፍጥረታት በምድር
ላይ የቀጠሉበትን ትእዛዝንም የፃፈው ሄኖክ ነው።
እናም በመፅሀፈ ሄኖክ ላይ ሄኖክ ኮብላይ መላእክት ብሎ
የጠቀሳቸው የሰማይ መልአክትን ሳይሆን በቅድስና በደብረ ቅዱስ
ይኖሩ የነበሩትን ደቂቀ ሴትን ነው እኚህ ኮብላይ መልአክት\ደቂቀ
ሴት/ ዘፍ 6:4 እንዲ ብሎ ይገልፃቸዋል
በእዚያ ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፤ ደግሞም ከዚያ በሁዋላ
የእግዚአብሄር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን
ወለዱላቸው፤ እነርሱም በድሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ሀያላን
ሆኑ። በማለት የደቂቀ ሴትን ልጆች ልክ እንደ ሄኖክ ኔፊሊ እያለ
ሲጠራቸው የደቂቀ ቃዬል ልጆችን ያገቡትን ደቂቀ ሴትን ደግሞ
የእግዚአብሄር ልጆች እያለ ይጠራቸዋል።
እነደገናም በ2ኛ ጴጥ 2:4-5 ላይ ደግሞ እግዚአብሄር ሀጢአትን
ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሀነም ጥሎ በጨለማ
ጉድጉዋድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው ለቀደመውም
አለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ፅድቅን የሚሰብከውን ኖህን
አድኖ በሀጢአተኞች አለም ላይ የጥፋት ውሀ ካገረገ...እያለ
ኮብላይ መላእክቱን\ደቂቀ ሴት/ ለፍርድ እንደሚጠበቁ የኮብላይ
መላእክቱ ልጆች ላይ ደግሞ ለቀደመው አለም ሳይራራ በኖህ
ዘመን የጥፋት ውሀን እንዳወረደ ይገልፃል።
የሚገርመው ነገር ቃል በቃል ደቂቀ ሴትን መልአክት ብለው
ሄኖክም ቅዱስ ጴጥሮስም ገልፀዋቸዋል ታዲያ ለምን የቅዱስ
ጴጥሮስን መልእክት ተቀብለው የሄኖክን መፅሀፍ አንቀበልም አሉ
ስንል ጥያቄያችን መልስ አያገኝም
ማስተዋል ያለብን ነገር በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች መልአክ
እየተባሉ ተጠርተዋል ለዚህም ምስክራችን
ራእ 3:1 በሰርዴስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ
እንዲህ ብለህ ፃፍ።
ራእ 3:7 በፊልድልፍያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ
እንዲህ ብለህ ፃፍ።
ራእ 3:14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ
እንዲህ ብለህ ፃፍ።
ተብሎ እናገኛለን መቼም የሰርዴስ፣ የፊልድልፍያና የሎዶቅያ የቤተ
ክርስቲያን መልአኮች እውነተኛዎቹ ቅዱሳን መላእክት እንዳልሆኑ
እውን ነው ስለዚህ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን መፅሀፈ ሄኖክን አምላካዊ
ቃል አድርጋ መቀበሏ ምንም ስህተት የለውም የመፅሀፈ ሄኖክ
ተቃዋሚዎች ግን መፅሀፈ ሄኖክን እያጣጣሉ ምስጢሩን ግን ሊፈቱ
ጉባኤ ይቀመጣሉ ማድረግ ያለባቸው ግን ልክ እንደ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/
ክን አምላካዊ መፅሀፍ ነው ብሎ መቀበል ነው።
ይቀጥላል
ወስብሀት ለእግዚአብሄር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ቀጣዩ ርዕሳችን

ለተሐድሶ መናፍቃን የተሠጠ ምላሽ
ዕብ 9
👉 " እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።
" (ወደ ዕብራውያን 9:28)

👉 የብሉይ ኪዳን እና የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት ልዩነት ምንድነው?
Join @And_Haymanot
@And_Haymanot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
" እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።" ዕብ 9:28
በ ዘማርያም ዘለቀ
Join @And_Haymanot
@And_Haymanot
መፅሀፈ ሄኖክ
ክፍል 4
ተወዳጆች መፅሐፈ ሄኖክ ዳሰሳችንን ቀጥለናል በዚህ ክፍልም ሳይንቲስቶች በመፅሐፈ ሄኖክ የሚያቀርቡትን ጥያቄ እንመለከታለን
@And_Haymanot
1ኛ፦ ስናየው ቃሉ ቀጥታ የአዲስ ኪዳን ነው የሚመስለው ስለዚህ የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ክርስትናቸው ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፃፉት በሁዋላ የብሉይ ኪዳን ነው አሉ እንጂ በብሉይ ኪዳን ዘመን አልተፃፈም ቃሉ እራሱ የሚናገረው ቀጥታ የአዲስ ኪዳን ቃል ነው እንዴት ይሄ የብሉይ ኪዳን መፅሀፍ ሊሆን ይችላል ብለው ጥያቄ አቅርበው ነበረ። አምላካችን ልዑለ እግዚአብሄር ግን ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን ምላሽ መስጠት ሳይጠበቅባት ምላሽ ሰቷቸዋል።
ይህም በእስራኤል ሀገር ሙት ባህር በሎጥ ዘመን ሰዶምና ገሞራ በጠፉ ጊዜ በእነሱ ላይ የወረደው እሳትና ዲን ባህር ሲሆን ሙት ባህር ተብሎ ተጠርቷል ይህ ሙት ባህር ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ በብሉይ ኪዳን ዘመን የክርስቶስን መምጣት የሚጠባበቁ ልክ እንደ ፈሪሳውያን፣ ሰዶቃውያን እንደሚባሉት ኤሴዎች የሚባሉም ነበሩ እነዚህ ኤሴዎች ተባትዮን የሚያዘወትሩ ክርስቶስን በገዳም እንጠብቀው ብለው መፅሀፍቶቻቸውን ይዘው ክርስቶስን ሲጠብቁ የኖሩ ናቸው ክርስቶስም ሲመጣ ሳያምኑት እዛው በምድረ በዳ የቀሩ ናቸው።
እናም እነዚህ ኤሴዎች ከክ/ል/በፊት 300 አመት ጀምሮ በሙት ባህር አካባቢ እንደ ገዳም በረሀ ላይ ሲኖሩ ዋሻዎች ነበሩዋቸው መፅሀፍቶቻቸውንም እዛው ቀብረው ይኖሩ ነበር ታዲያ ከዘመናት በሁዋላ በ1947 አ/ም አንድ የአረብ እረኛ ፍየሎች ወደዛ ሄደውበት ፍየሎቹን ሊመልስ ሲሄድ አንድ ፍየል የኖረ ብራና አልበላ ብሏት እያላመጠች ስትጎትት ያያታል ሲያየው መፅሀፍ ነው ለሌላ ሰው ሲያሳየው የትንቢተ ኢሳያስ ክፍል ሆኖ ተገኘ እንደዚህማ ከሆነ ብዙ መፅሀፍቶች ሳይኖረው አይቀርም ተብሎ ቦታው ሲቆፈር ከተገኙት መፅሀፍቶች ውስጥ አንዱ የመፅሀፈ ሄኖክ ክፋይ ሆኖ ተገኘ ያም የመፅሀፈ ሄኖክ ክፋይ በአለም ላይ መፅሀፈ ሄኖክ አለ ከሚሉት ጋር ሲስተያይ (ያው በክፍል 1 እንደጠቀስኩላችው ከኢትዮጵያ ውጪ ሙሉ መፅሀፈ ሄኖክ ያላት ሀገር የለችም) ኢትዮጵያ ካለው ከግእዙ መፅሀፈ ሄኖክ ጋር አንድ አይነት ሆኖ ተገኘ በዚህም መፅሀፈ ሄኖክ የብሉይ ኪዳን መፅሀፍ መሆኑን እግዚአብሄር አምላካችን መሰከረ።

2ኛ፦ ሳይንቲስቶች ከጠየቁት ጥያቄ ውስጥ ይሄ መፅሀፍ ቅዱስ የምትሉት የተፃፈው በድሮ ዘመን ነው ድሮ ደግሞ የብራና ጥቅልል ነው ያለው በእጅ ወደ ሌላ ቋንቋ ሲተረጎም፣ ሲገለበጥና ወደ አለም ሲሰራጭ ኖረ ከኦሪት ጀምሮ ለብዙ ሺ አመታት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች ሲገለበጥ የመጀመሪያው መፅሀፍ መሆናቸውን በምን እናውቃለን ተበርዘው ተጨምሮበት ወይም ተቀንሶበት ቢሆንስ ብለው ጠየቁ።
ይህም በ1947 አ/ም የተገኘው የሙት ባህር የቁምራን ዋሻ ጥቅልሎች ወጥተው አሁን ካለው መፅሀፍ ቅዱስ ጋር ሲስተያዩ አንድ አይነት ንባብ ሆኖ ተገኘ መፅሀፈ ሄኖክም ምንም ብረዛ እንዳልደረሰበት ተረጋገጠ።
ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያም መፅሀፍቶች ሳይጠፉባት ጠብቃ እንድትኖር እግዚአብሄር የመረጣት ሀገር መሆኗ ምስክር ሆነ እግዚአብሄር አዋቂ ነው የሚመጣው ትውልድ የመፅሀፍቶች በኩር የሆነውን መፅሀፈ ሄኖክን ይሄማ የብሉይ ኪዳን መፅሀፍ አይደለም ብሎ እንደሚክድ ስላወቀ በብሉይ ኪዳን ዘመን እንዲቀበር አድርጎ ከ2300 አመታት በሁዋላ በአዲስ ኪዳን ዘመን እንዲወጣ ፈቅዶ መፅሀፈ ሄኖክ በብሉይ ኪዳን ዘመን ያፃፍኩት እኔ ነኝ ብሎ መሰከረ። ይህን የመሰከረ የቅዱሳን አባቶቻችን፣ የቅዱሳን እናቶቻችን የእኛም አምላክ ልኡለ እግዚአብሄር ስሙ የተመሰገነ ይሁን። አሜን።
ይቀጥላል....
ወስብሀት ለእግዚአብሄር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
@And_Haymanot
@And_Haymanot
መፅሀፈ ሄኖክ
ክፍል 5
#የእናት_ጡት_ነካሾች_የተሀድሶ_መናፍቃን_በመፅሀፈ_ሄኖክ_ላይ_ከሚያነሱት_ጥያቄ_ውስጥ_በጥቂቱ
1፦ ሄኖክ ስለ ኖህ በተናገረው ትንቢት
ላይ
1.1፦ የመፅሀፈ ሄኖክ አዘጋጆች ለኖህ ስም የማውጣቱን ስራ ለሄኖክ አድርገውታል መፅሀፍ ቅዱስ ግን የሚለው በዘፍ 5:28 ላይ ላሜህም መቶ ሰማንያ ሁለት አመት ኖረ ልጅንም ወለደ
ስሙንም እግዚአብሄር በረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ስራችን ይህ ያሳርፈናል ሲህ ኖህ ብሎ ጠራው ነው የሚለው ብለው የማያውቁትን ይቀባጥራሉ የሚገርመው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ብትሆን ለኖህ ስም
ያወጣለት ላሜህ እንደሆነ ነው የምታስተምረው ነገርግን ሄኖክ ለልጁ ለማቱሳላ የላሜህ ልጅ ኖህ ተብሎ እንዲጠራ አስቀድሞ ነግሮታል እስኪ አንድ ጥያቄ እንጠይቃቸው እግዚአብሄር ከረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ስራችን ይህ ያሳርፈናል ሲል ኖህ
ብሎ ጠራው ተብሏል ላሜህ ይህን የተናገረው የወደፊት ጉዳይ ነው ይህ የወደፊት ጉዳይ ደግሞ ላሜህ ነብይ ካልሆነ በስተቀር እንዴት ሊተነብይ ቻለ? ላሜህ ነብይ ነው ብሎ ደግሞ መፅሀፍ
ቅዱስ አይናገርም ታዲያ እግዚአብሄር ምድሪቱን እንደሚረግማትና ኖህ ከዚህ እንደሚያሳርፋቸው ከዚህ በፊት ካልተነገረው በቀር ስለ ጉዳዩ እንዴት አወቀ? የዚህ ጥያቄ ምላሽ ሄኖክ ለልጁ ለማቱሳላ የላሜህ ልጅ ኖህ ተብሎ እንዲጠራ አስቀድሞ ነግሮታል ነው።
ስለዚህ መፅሀፈ ሄኖክ ይህን ሁሉ በማወቁ ሊመሰገንና እውነተኛ
መፅሀፍ ሊያስብለው እንጂ እንሱ እንደሚሉት የተሳሳቱ ሰዎች
የፃፉት መፅሀፍ አይደለም።

1.2 ኖህን በሄኖ 41:2 ላይ ሰውነቱም እንደ እንቁ ነጭ ሆኖ እንደ ፅጌሬዳም ቀይ ነው የራሱም ጠጉር እንደነጭ ብዝት ነው የተሸራሼ ነው አይኖቹም ያማሩ ናቸው ይላል እንደ እንቁ ነጭ እንደ ፅጌሬዳ ቀይ ካለ ከሁለቱ የትኛውን እንደሚመስል ግልፅ አይደለም ብለው
እንዲው ለመቃወም ሲሉ ብቻ መፅሀፈ ሄኖክን ይቃወማሉ፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምላሽ ግን ኖህ ምን ያህል ያማረና ልዩ እንደሆነ ለማሳየት ተፈልጎ ይህ አይነት አገላለፅ መፅሀፈ ሄኖክ
ተጠቀመ እንጂ ከሁለቱ የትኛው አይነት ነው የሚል ጥያቄ አያስነሳም ምክንያቱም እንደዚህ አይነት አገላለፅ በሌሎችም የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ተፅፎ እናገኛለንና ለምሳሌ፦ በመኋ
2:1 ላይ እኔ የሳሮን ፅጌሬዳ የቆላም አበባ ነኝ በእሾህም መካከል
እንዳለ የሱፍ አበባ እንዲሁ ወዳጄ በቆነጃጅት መካከል ናት ይላል እዚህ ላይ እኛ የትኛው አበባ የሳሮን ፅጌሬዳ፣ የቆላም አበባ ወይስ የሱፍ አበባ ብለን ብንጠይቅ መልስ አናገኝም ነገር ግን
የክርስቶስን ውበት ምን ያህል ያማረ እንደሆነ ለመግለፅ ተፈልጎ እንጂ ወይ የሳሮን ፅጌሬዳ፣ ወይ የቆላም አበባ አልያም የሱፍ አበባ ሆኖ አይደለም ስለዚህ መፅሀፈ ሄኖክን ከጠየቁ ለስም
እናምንበታለን ከሚሉት ከ66ቱ ውስጥም እነዚህን መጠየቅ አለባቸው ለተጨማሪ የእንደዚህ አይነት አገላለፅ መኋ 6:10ን
ያንብቡት።

2ኛ፦ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል
በሄኖ 6:4ላይ ዲያብሎስን የሚበቀለው አጋንንትንም የሚበቀላቸው ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ራጉኤል ነው ይላል እንደሚታወቀው ደሞ
በቀል የእግዚአብሄር ድርሻ ነው በመሆኑም ማናችንም እንዳንበቀልና በቀልን ሁሉ ለእርሱ እንድንተው ታዘናል የበቀል እርምጃ የሚወስደው ፍጡር መልአክ ወይም ራጉኤል ሳይሆን
እግዚአብሄር ነው ስለዚህ መፅሀፈ ሄኖክ የሚበቀለው ራጉኤል ማለቱ ስህተት ነው ብለው ለእግዚአብሄር የተቆረቆሩ በመምሰል ለግብር አባታቸው ለዲያብሎስ በመቆርቆር ይጠይቃሉ
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መልስ ግን ከቁጥር 1 ጀምሮ የቅዱሳን መላእክት ስማቸውና የተሰጣቸው የስራ ድርሻና ሹመትን ያሳያል ይህን ትልቅ ሹመት የሰጣቸው ደግሞ እግዚአብሄር ነው
ከተሰጣቸው ድርሻ መካከል አንዱ ዲያብሎስን መበቀል ነው ይህ
በቀል ተብሎ የተገለፀው በእግዚአብሄር ላይ ያመፁትን እግዚአብሄር ሊቀጣ ወይም ሊበቀል ሲፈልግ ቅዱሳን መላእክቱን ልኮ በእነርሱ አማካኝነት ይገስፃቸዋል ማለት ነው መረዳት ያለብን
ቅዱስ ራጉኤል ብቻ ለዚህ ተልእኮ ይላካል ማለት አይደለም ነገር ግን ይብለጥ የዚህ መልአክ መገለጫው ይህ በመሆኑ ነው ቅዱሳን መላእክት በፀሎታቸውና በምልጃቸው እኛን እንደሚራዱን ሁሉ ለመበቀልም ሊላኩ ይችላሉ።
ለምሳሌ፦ ህዝቅያስ እግዚአብሄር ከሰናክሬም እጅ እንዲያድነው ሲፀልይ "በህያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል m ስማ... እግዚአብሄር እንደሆንን ያውቁ ዘንድ
ከእጁ አድነን" በማለት ይፀልያል ኢሳ 37:17-20 ላይ በፀሎቱ የጠየቀው እግዚአብሄርን ቢሆንም ሰራዊቱን ያጠፋለት ግን የእግዚአብሄር መልአክ ነው የእግዚአብሄር መልአክ መጣ
ከአሶራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ ይላል ቁጥር 36 ላይ ስለዚህ ይህ ክፍል የሚያሳየው ሁሉን ፍርድ የሚፈርደው እግዚአብሄር ቢሆንም ፍርዱ እውን የሚሆነው ደግሞ
በተሾሙ መላእክት በኩል እንደሆነ ነው
ሌላው ደሞ ማንኛችንም እንዳንበቀል በቀልን ሁሉ ለእርሱ እንድንተው ታዘናል ብለዋል ይህን ትእዛዝ ግን እንዴት ለመላእክት ሊሰጡት እንደቻሉ ሊገባን አልቻለም ምክንያቱም ይህ ቃል
የተነገረው ለሰው ልጆች ነው የሰው ልጆች አኗኗርና የቅዱሳን መላእክት አኗኗር ደግሞ የተለያየ ነው አይ ለመላእክትም ለሰውም የተሰጠ ህግ ነው ካሉ ደግሞ እኛ በዝሙት መንፈስ ወደሴት እንዳናይ፣ ከአንድ በላይ እንዳናገባ፣እናትና አባታችንን እንድናከብር
መፆም እንደሚገባንና የመሳሰሉ ህጎችን እነሱም መፈፀም አለባቸው የሚል ሌላ የስህተት ትምህርት ውስጥ ስለሚገቡ
ስህተታቸውን እንዲያጤኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትመክራለች የማትታደስ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን በቀል የእግዚአብሄር መሆኑን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ጠንቅቃ የምታውቅ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡

ማጠቃለያ፦ የተሀድሶ መናፍቃን በ81 አሀዱና መፅሀፈ ሄኖክ ላይ ለሚያነሱት ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ በእንተ ሰማንያ አንድ አሀዱ የሚለውን መፅሀፍ እየጋበዝኩዋችው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን መፅሀፈ ሄኖክን አምላካዊ መፅሀፍ አድርጋ መቀበሏና ጠብቃ ማቆየቷ
ሊያስመሰግናት፣ ትክክለኛ ሀይማኖት መሆኗ ሊመሰከርላት ይገባል እንጂ በተቃራኒው ቤተ ክርስቲያናችንንና መፅሀፈ ሄኖክን መንቀፍ ትልቅ ስህተት ነው ስለዚህ ተጠራጣሪ ወገኖች ስለ ማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ወደ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ
ክርስቲያናችን ቀርበው ጠይቀው ማወቅና መረዳት ይኖርባቸዋል ።
የአባታችን የቅዱስ ሄኖክ ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን።
ወስብሀት ለእግዚአብሄር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot
👍1
✞መስቀል✞

@And_Haymanot

✞ ተወዳጆች በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም
አደረሰን!!! አደረሳችው ✞
የተሃድሶ መናፍቃን መስቀልን ከምልክትነት ባለፈ አያከብሩትም፣ አያማትቡም፣ አይሳለሙም፣ አይባረኩበትም እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ
በመስቀል እናማትባለን፣ በኃያልነቱ እናምናለን፣ ከጠላት እንመካበታለን፣ ዲያብሎስን እናሸንፍበታለን፣ እንሳለመዋለንም ነገር ግን ለሃራጥቃውያን ምላሽ ይሆን ዘንድ የመስቀልን ክብር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንመልከት።
✞ መስቀል በኦሪየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ
እንደ ታቦትና ስዕል ከፍተኛ ክብርና ቦታ ያለው ነው

👉✞ መስቀል የክርስቶስ ምልክት ነው፡፡ ጌታችን ስለ ዓለም መጨረሻ ሲናገር "የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል"።
ብሏል /ማቴ 24፥30/ የሰው ልጅ ምልክት የተባለ መስቀል
መሆኑን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እና ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም አስተምረዋል ጌታችን በትምህርቱ መስቀልን ከክርስቲያኖች ሕይወትና ጉዞ ጋር አያይዞም አስተምሯል፦ ☞
ማቴ 16፥24 ላይ "እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ
መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ"። ☞ ሉቃ 14፥27 ላይ ደግሞ"ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም"።
✞ ጌታችን ከሙታን በተነሣ ጊዜ በመቃብሩ አካባቢ የነበሩት
መላእክት ጌታችንን የጠሩት በመስቀሉ ነው" እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና" /ማቴ 28፥5/

👉✞ ሐዋርያትም ጌታችንን በመስቀሉ ይገልጡት ነበር "ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ" / ገላ 6፥14/
በመስቀል ስናማትብ የእግዚአብሔርን የማዳን ስራ እንመሰክራለን #በኒቅያ_ጉባኤ በ325 ዓ/ም በተወሰነው መሠረት ከግምባራችን ወደ ሆዳችን ስናማትብ የጌታችንን ከሰማየ ሰማየት ወርዶ ከድንግል ማርያም መወለዱን፣ ከግራ ወደ ቀኝ ስናማትብ ደግም ከሲዖል ወደ ገነት እኛን ማስገባቱን እንመሰክራለን "የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ
ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና" /1ኛ ቆሮ 1፥18/

❖ ቅዱስ ሄሬኔዎስ፦ "በእንጨት ምክንያት ለዕዳ ተሰጠን፤ በእንጨት ምክንያትም ከዕዳችን ነጻ ሆንን" በማለት
እንዳስተማረው መስቀል ከዕዳ ነፃ የሆንንበት ነው
✞ በብሉይ ኪዳን ሕዝበ እስራኤል ከአማሌቃውያን ጋር በተዋጉ
ጊዜ ሙሴ እጁን ዘርግቶ በመስቀል አምሳል ቆሞ ነበር "ሙሴ እጁን ባነሳ ጊዜ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር፤ እጁን ባወረደ ጊዜም አማሌቅ ድል ያደርጉ ነበር" /ዘፀ 17፥8-16/ መስቀል
በሙሴ እጅ በምሳሌው ይህን ያህል ኃይል ከነበረው በክርስቶስ ደም ከተዋጀ በኃላ አማናዊውማ እንዴት ታላቅ የሆነ ኃይል አያደርግ
✞ ያዕቆብ ኤፍሬምን እና ምናሴን ሲባርክ በመስቀል አምሳል ነው "ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ግራ፣ ምናሴንም በግራው በእስራኤል ቀኝ አደረገው፤ እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ/በግራው/ ግራ እጁንም በምናሴ ላይ አኖረ/
በቀኙ በቆመው/ እጆቹንም አስተላለፈ"። /ዘፍ 48፥13/ በብሉይ ኪዳን የነበረው ያዕቆብ በመስቀል የባረከው በረከት ለልጆቹ ደርሶላቸዋል፤ ታዲያ በሐዲስ የሚገኙ ካህናት በመስቀል
የሚባርኩት በረከትማ እንዴት አይደርስ
👉✞ ሕዝ 9፥4 ላይ "እግዚአብሔርም። በከተማይቱ በኢየሩሳሌም
መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው"። ይላል በአማርኛ "ምልክት" የተባለው በግሪኩ "tau" የተባለው ምልክት ነው ይህም በእንግሊዝኛው የ"ተ" ቅርጽ ያለው ምልክት ነው።
✞ ጣት የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው በሉቃስ ወንጌል 11፥20 ላይ ☞ "እኔ ግን በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ" ያለውን የማቴዎስ ወንጌል 12፥28 ግን ☞ "እኔ ግን
በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ" ብሎታል
እኛም በጣታችን ስናማትብ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሰይጣንን ድል ለመንሣት ማማተባችን ነው አስቀድሞም ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝ 59፥4 ላይ "ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥
ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው" ብሎ የተናገረለት ከዲያብሎስ ቀስት የምናመልጥበት ምልክት መስቀል ነው።
ስለዚህ ተወዳጆች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መስቀልን የምታከብረው፣ የምትሳለመው፣
የምታማትበው... መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርጋ እንጂ የተሃድሶ መናፍቃን እንደሚሉት በተራ የእንጨት ፍቅር አይደለም በመሆንኑ የተሃድሶ መናፍቃኑ ከስህተት ጎዳና ተመልሰው ወደ ቀጥተኛዋና ርትዒት ወደ ሆነችው ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን
ይመለሱ ዘንድ የቤተ ክርስቲያናችን ጸሎት ነው።
❖ ሞኝነት ነው ለሚጠፉት መሰናከያቸው
❖ በዓለም ጥበብ ለሚኖሩ እውነት ተስኗቸው
❖ ለጠቢብ ሰው በመንፈስ የሚኖር
❖ የመዳን ቀን እውነተኛ አርማ ነው
❖ ከገሃነም እሳት የሚያድን ነው
✞ አምላከ ቅዱሳን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ጽላት ላይ
ይጻፍልን!!! አሜን
✞✞✞
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
መስቀል በኢትዮጵያ


✞ ተወዳጆች በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን!!! አደረሳችው ✞


❖ "ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ" ገላ 6፥14 ❖

@And_Haymanot

ኢትዮጵያ ሃገራችን የክርስቲያን ደሴት ከመባሏም በላይ የእግዚአብሔር ቸርነት ያላት የበረከት የረድኤት ሀገር ናት ይኽም የጌታ ግማደ መስቀል በ14ኛው ክፍለ ዘመን በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል

☞ አመጣጡም የኢትዮጵያ ነገሥታት የግብጽ ካሊፋዎች ሀገረ ገዥዎች በኃይል ይጋፏቸው ስለነበር የግብጽ ሀገር ገዥዎች ደግሞ የግብጽን ክርስቲያኖች (ኮፕታውያን) ያሰቃዩአቸው ነበር ስለዚህ ይህ አለመግባባት እንዲወገድና የግብጽ ክርስቲያኖች ዕረፍት እንዲያገኙ በማሠብ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ ከግብጽ የአህናስ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስንና አባ ማዕምር የሚባሉ ሉዑካን ወደ ኢትዮጵያ መጡ በዚያን ጊዜ አጼ ሠይፈ አርዕደ አርፈው የልጃቸው ልጅ አጼ ዳዊት ነግሠው ነበር እነዚህ ልዑካን በኢትዮጵያውያንና በግብጻውያን ነገስታት መካከል ያለውን ቅራኔ አስወግደው ሲመለሱ አጼ ዳዊት በነበራቸው ቀና መንፈስ አቡነ ዮሐንስ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ እሌኒ ንግስት አስቆፍራ ከአስወጣችው ከጌታ ግማደ መስቀል ክፋይ ለበረከት እንዲልኩላቸው ወርቅ፣ አልማዝ፣ ገጸ በረከት አስጭነው ወደ ኢየሩሳሌም መልዕክተኞችን ላኩ መልእክተኞቹም ኢየሩሳሌም ደርሰው ገጸ በረከቱን ለፓትርያርኩ ከሰጡ በኃላ ፓትርያርኩ፦

፩፦ የጌታን ግማደ መስቀል፣ የቀኝ በኩሉን ክፋይ
፪፦ ጌታ ላይ አይሁድ የጫኑበትን (ያረጉለት) አክሊለ ሶኩን
፫፦ ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ የእመቤታችን ስዕል ላኩላቸው።

መልዕክተኞቹም ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ አጼ ዳዊት መልእክተኞቹን ለመቀበል ሲሄዱ የተቀመጡባት ባዝራ ፈረስ ጥላቸው መሞታቸውን ታሪካቸው ይናገራል መስቀሉ ወደ ሀገራችን የገባው #መስከረም 10 ቀን ነው መስቀሉ የተቀመጠው መስከረም 21 ቀን በወሎ ክፍለ ሃገር በግሸን ማርያም ነው

በዚህ ሁኔታ የገባው የጌታ መስቀል ዛሬም ድረስ ተአምራዊ ነው ይህም ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመስቀል ያላትን ታላቅ አክብሮትና ፍቅር የገለጸችበት አብይ ምስክር ነው ሕዝቡም ለመስቀል ያለውን ፍቅርና አክብሮት ለመግለጽ ይነቀሰዋል፣ በልብሱ ላይ ይጠልፈዋል ይህ ደግሞ የሚያሳየው መስቀል በኢትዮጵያውያን ዘንድ ምን ያህል ክብር እንዳለው ነው።


☞ ከተለያዩ ማዕድናት የሚሰራው መስቀል ትርጉም፦

መስቀል ከተለያዩ ማዕድናት ሊሰራ ይችላል መስቀሉ የሚሰራባቸው ማዕድናት የራሳቸው ባህርያት እንዳላቸው ሁሉ ምሳሌውን ለመግለጽ ብቁ ናቸው ብለው አባቶች ያስቀመጡትን ማየት ይገባል።

ከብረት ቢሰራ ክርስቶስ የተቸነከረበትን ችንካር ለማመልከት ነው
ከወርቅ ቢሰራ ወርቅ ንጹህ እንደሆነ ክርስቶስን ንጹሀ ባህርይ እድፈት የሌለብህ ጽኑ አንተ ነህ ብሎ ለመመስከር ነው
ከእንጨት ቢሰራ ክርስቶስ የተሰቀለው በዕጽ በእንጨት ላይ መሆኑን ለማመልከት ነው
ከብር ቢሰራ ተስፋን፣ ዕድልን ያመለክታል ይኸውም ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ ቤዛን በደሙ ከፍሏልና በእርሱ ተስፋ እንድናደርግ ያመለክተናል


መስቀል ለእኛ ክርስቲያኖች ኃይላችን፣ ጽንዐችን፣ ቤዛችን፣ መድኃኒታችን ነው "የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና" /1ኛ ቆሮ 1፥18/ ለቅዱስ መስቀል ክብርና ስግደት ይገባል ምክንያቱም በመዝ 131፥7 ላይ "እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን" ተብሎ ተጽፏልና።

❖ ሞኝነት ነው ለሚጠፉት መሰናከያቸው
❖ በዓለም ጥበብ ለሚኖሩ እውነት ተስኗቸው
❖ ለጠቢብ ሰው በመንፈስ የሚኖር
❖ የመዳን ቀን እውነተኛ አርማ ነው
❖ ከገሃነም እሳት የሚያድን ነው

ያለ መስቀል ክርስትና ያለ ተጋድሎ ቅድስና የለም!!!

✞ አምላከ ቅዱሳን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ጽላት ላይ ይጻፍልን!!! አሜን ✞✞✞
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN & Share
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
መስቀል አበባ

መስቀል አበባ ውብ አበባ 
አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ 
መስቀል አበባ ተቀብሮ ሲኖር አደይ አበባ ሥነ ስቅለቱ 
መስቀል አበባ እሌኒ አገኘች አደይ አበባ ደገኛይቱ 
መስቀል አበባ ውብ አበባ 
አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ 
መስቀል አበባ ጥራጊ ሞልተው አደይ አበባ አይሁድ በክፋት 
መስቀል አበባ ጢሱ ሰገደ አደይ አበባ መስቀሉ ካለበት 
መስቀል አበባ ውብ አበባ 
አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ 
መስቀል አበባ ወንዙ ጅረቱ አደይ አበባ ሸለቆ ዱሩ 
መስቀል አበባ አሸብርቀው ደምቀው አደይ አበባ ላንተ መሰከሩ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 ዕራየ ማርያም ላይ የተወሰኑ የብሔር ስም እየጠራ ገነት አይገቡም ይላል ለሚሉት የመናፍቅ ፓስተር መልስ

በዘማርያም ዘለቀ
👉 በግእዝ ሸ የምትባላዋ ፊደል እንደሌለች ያቃሉ?
በብሔር ሥም ለመበጥበት ለተነሡት ልብ ይሥጥልን
Share @And_Haymanot
"ውረድ ወይም ፍረድ"፣
ይሉታል እግዜርን ልባቸው ሲቆስል
ቢወርድ ፊቱ ቆመው - የሚያዩት ይመስል...
ቢፈርድ የሚተርፉ - የሚፀድቁ ይመስል
ረድኤት አሰፋ
Encoderbot file id45033 16k
👉 ዕራየ ማርያም ላይ የተወሰኑ የብሔር ስም እየጠራ ገነት አይገቡም ይላል ለሚሉት የመናፍቅ ፓስተር የተሠጠ መልስ
በዘማርያም ዘለቀ

በብሔር ሥም ለመበጥበት ለተነሡት ልብ ይሥጥልን
Size 2.2
Share @And_Haymanot
በ2011 ወደ ዩኒቨርሲቲ ለምትጓዙ ሁሉ ኑ ልጆቼ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለው ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በግቢ ጉባኤ በሚሠጡ ልዩ ልዩ ትምህርቶች ለነፍሳችሁም ስንቅ ሰንቁ... ዩኒቨርሲቲ ላወቀበት ገዳም ነውና በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ ትሆኑ ዘንድ እንመኛለን
መልካም የትምህርትና የአገልግልግሎት ዘመን ይሁንላችሁ
@And_Haymanot
በዚህ አመት ወደ ከፍተኛ ተቋም ለተሻገሩ ተማሪዎች ሼር በማድረግ ወደቤቱ እንጥራቸው
፩ ሃይማኖት
@And_Haymanot
የላሊበላ ጉዳይ
ኢትዮጵያን ስሟን ከሚያስጠሯት ታሪካዊ ቅርሶች መካከል:የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያና አንዱ ነው። በዓለማችን ቀልብን በመሳቡ በርካታ የዓለም የመረጃ
አውታራት ብዙ ዘግበውለታል ብዙም ጽፈውለታል። ይሁን እንጂ ይህ ታሪክ በዘመናችን ተጎድቶ ያለ ጠጋኝ መኖሩ እጅግ ልብ ይነካል። በተለያዩ ጊዜያት ለቅርሱ ጥበቃ ተብሎ መጠለያ ቢሰራ ችግሩን አባባሰው እንጅ አልቀረፈውም።
በቅርቡ ከአመት በፊት ጉዳዩ ተነስቶ በአዲስ አበባ ኮሚቴ
ተቋቁሞ ከኢትዮጵያ ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ወደ ሥራ ለመግባት ውይይት በመደረጉ ተስፋ ሰንቀን ነበር። ጉዳዩ ከተስፋ የዘለለ ባለመሆኑ ዛሬ የላሊበላ ህዝብ ለአቤቱታ ወጥቷል። ከዚህ በፊትም በሬዎቻችንን ሸጠን እንጠግነዋለን ብሎ ቆርጦ ቢነሳም ሰሚ አላገኘም።
ይህ ጉዳይ የማይመለከተው ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ በመሆኑም
ለጉዳዩ ቅርብ አካላት ቤተ ክህነት፣ቱሪዝም ቢሮ፣የቅርስ ጥበቃ ቢሮ፣ ዩኔስኮ ትኩረት እንዲሰጡት ማድረግ ያሻል። ይህ ካልሆነ ከሀገረ ስብከቱ ጋር በመሆን እኛ ማድረግ ያለብንን ድርሻ ተወጥተን መንከብከብ ይኖርብናል። በቅርብ ቀን የሃገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አነጋግሬ መረጃውን ለማድረስ እሞክራለሁ።
መ/ር ንዋይ ካሳሁን
@And_Haymanot
Channel photo updated
ጽኑ ሰማዕት

ጽኑ ሰማዕት የእምነት አርበኛ
አርሴማ ነይ ነይ ወደኛ
------------------------------
ነይ ነይ ቅዱስ አትናትዮስ
›› ›› በስዕለት ያገኙሽ
›› ›› ብሉይን ከሀዲስ
›› ›› ጠንቅቀሽ የተማርሽ
›› ›› በፍፁም ትህትና
›› ›› በጸሎት የተጋሽ
›› ›› አርሴማ ልዩ ነሽ
›› ›› አምላክ የመረጠሸ
-------------------------------
ነይ ነይ ውበትም ሀሰት ነው
›› ›› ደም ግባትም ከንቱ
›› ›› ንብረት ትዳር ሁሉ
›› ›› አላፊ ውዕቱ
›› ›› ንግስት መባልን
›› ›› በፍጹም ሳትሻ
›› ›› አለምን በመናቅ
›› ›› ገባች ወደዋሻ
-------------------------------------
ነይ ነይ አረመኔው ድርጣድስ
›› ›› ቢያሰቃይሽም
›› ›› ውበቴ ክርስቶስ
›› ›› ነው ብለሽ ሰበክሽ
›› ›› አንገትሽን ለሰይፍ
›› ›› አሳልፈሽ ሰጠሸ
›› ›› ክብርሽም ተገልጾ
›› ›› ለአለም አበራሽ
---------------------------------
ነይ ነይ አርአያ ልትሆኝን
›› ›› ለእኛ ለሁላችን
›› ›› ፈፅመሽ አሳየሽ
›› ›› ታላቅ ተጋድሎሽን
›› ›› ይህን አለም ድል መንሳት
›› ›› አቅቶናል እና
›› ›› አርሴማ አትለይን
›› ›› በእምነት እንድንጸና
@And_Haymanot
@And_Haymanot
በፍጥነት ሼር እናድርግ 🙏

ባህርዳር ስቴድየም የሚገባ መልዕክቱን ያድርስ

ላልይበላን መታደግ እንደሚገባን ዛሬ ኬኒያን ከኢትዮጵያ ጋር ያገናኘው ግዙፉ የባህርዳር ስታዲየም ህዝቡ ብሶቱን ሊያሰማ ይገባል! ተስፋ እናደርጋለን

ይህ ህዝብ መልዕክቱን ለዩኔስኮ ማድረሻ መንገዱ ይህ እና ይህ ብቻ ነው! እግዚአብሔር ይመስገን በእምነቱ እና በሃገሩ የማይደራደረው ጨዋ ህዝብ ይህንን ጩኸት ለማስተጋባት እንቅስቃሴዎችን እንደጀመረ በወሬ ደረጃ እየተሰማም ነው!
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ
ተጠለይ በእግዚአብሔር ታዛ


ከሚራራልን ፍቅር ከሆነው
ዘላቂ ሰላም ከእግዚአብሔር ነው
ይህን እወቂ ይህን ተረጂ
በልብሽ ጉልበት ለርሱ ስገጂ

አዝ ❖ ❖ ❖
በሠይፍ ያልቃሉ ሠይፍ የሚያነሱ
የሚራራልን ሲፈርድ ንጉሱ
በቀል የርሡ ነው አይደለም ያንቺ
በጸጋው ታጥረሽ በጸሎት በርቺ

አዝ ❖ ❖ ❖
ይህ ውጣ ውረድ ይህጉስቁልናው
በእግዚአብሔር ነው መከራ ማብቂያው
ሰላም ይሁን ሲል ይሆናል ሰላም
ያሳየሽውን ፍቅር አይረሳም

አዝ ❖ ❖ ❖
ማራት ኢትዮጵያን ማራት ሀገሬን
በየሔድኩበት መጠሪያ ስሜን
ይብቃት ሌሊቱ ይውጣላት ፀሃይ
አሁን ይዘርጋ እጅህ ከሰማይ

አዝ ❖ ❖ ❖
እንድትፈራርስ ጠላት ሸምቋል
ብርቱዉን ጉልበት ከአፈር ደባልቋል
ይህን ግፍ አስብ ዘንበል በልላት
ካንተ በስተቀር መሔጃ የላት
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
@And_Haymanot