❤ ምክረ አበው ❤️
ወዳጄ፥ ሕይወት አጭር ናት። ዛሬን እንጂ ነገን ስለመኖርህ እርግጠኛ መሆን አትችልም። ስለዚህ ዛሬን መልካም አስብ፤ ለሌሎች መልካም አድርግ። በሙሉ ልብህ እመን። ስላለህ ነገር አመስግን። ሰው አትበድል ነገር ግን ብትበድል ይቅርታን ጠይቅ፤ 🙏 ቢበድሉህም ይቅርታ እስኪጠይቁህ ሳትጠብቅ ይቅርታን አድርግ። የዋህ ሁን ነገር ግን ይቅርታ ያደረክለት ሰው ዳግም ይበድልህ ዘንድ ሞኝ አትሁን።
❖ @And_Haymanot ❖
🌸🌸 መልካም ዕለተ ሰንበት🌸🌸
🌸🌸 መልካም በአል 🌸🌸

የእመቤታችን ዕርገት´´
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን መምህር)
@And_Haymanot
በውሥጥ በጠየቃችሁን መሰረት ሥለ እመቤታችን ዕርገት ታሪክ እና ማሥረጃን በአንድ ላይ የተዘጋጀን ምላሽ ልናቀርብ ወደናል፡፡ የእናት ጡት ነካሽ ተሃድሶዎች ይህን እውነት መቀበል ቢከብዳቸው በዘርያዕቆብ ያመጣችሁት ታሪክ ነው ሢሉን ይደመጣሉ ይህ እነሱ እንደሚሉት የእመቤታችን ዕርገት ፈጠራ ሳይሆን(ላቲ ስብሃት) በአለም ላይ በተለያዩ ሃገራት የሚከበር እውነት ነው እንጂ፡፡ እነሆ ክፍል ፩
ነሐሴ 16 ቀን የእመቤታችንን ዕርገት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፤ የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር ከቆየች በኋላ፤ ዓለምን ለማዳን በዕለተ ዓርብ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜም የሚወድዳት እናቱን
ለሚወድደው ደቀ መዝሙር ለዮሐንስ “እነኋት እናትኽ” በማለት አደራ በመስጠት በዮሐንስ በኩል ለሚወድደን ለእኛ የአደራ ልጆቿ እንድንኾንና የአደራ እናታችን እንድትኾን ታላቅ ስጦታን በቀራንዮ በእግረ መስቀል ሥር ሰጠን (ዮሐ ፲፱፥፳፮‐፳፯)፡፡ በዚኽም መሠረት ሐዋርያትም ከአምላካቸው የተሰጠቻቸው የአምላካቸውን እናት ይዘው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ፸፪ት ቋንቋ ገልጾላቸው ታላቅ መንፈሳዊ ኀይልን ሰጣቸው (የሐዋ 1፥፲፬)፤ ዮሐንስም በእናትነት የተቀበላት ቅድስት ድንግል ማርያምን በቤቱ 15 ዓመት አኑሯታል፡፡ ከዚያም ልጇ ክርስቶስ
ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት፤ ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን
ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ
አለቀሱ፡፡ ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ
እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፤ ከዚያም ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች፤
ሐዋርያት በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው ለምቀኝነት አያርፉምና
ቀድሞ ልጇ ሞተ፣ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ እያስተማሩ ኖሩ ከመቃብሩም ተአምራት ይደረጋል፤ አሁን ደግሞ ርሷ ሞተች፣
ተነሣች፣ ዐረገች ብለው ሊያስተምሩ አይደል፤ “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡ ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ
የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ይቤ ዮሐንስ ወኢይገድፍ ምዕቅብናየ
ወዘንተ ብሂሎ ወድቀ በላዕሌሃ” ይላል (ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡ ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና
ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡
ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” ይላል የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ “ወዕጥን ሥጋሃ ለማርያም መዓልተ ወሌሊተ” ይላል የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን
በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ “ወፍና ሠርክ ያመጽዕ ሎቱ ራጉኤል መልአክ ኅብስተ ሰማይ” ይላል ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡ ኋላም በጌታ ፈቃድ ከተቀሩት ሐዋርያት ጋር ተገናኘ፤ ሐዋርያትም የእመቤታችንን ነገር
እንደምን እንደኾነ ሲጠይቁት ርሱም በገነት ያየውን ነገር ነገራቸው፤ እነሱም ይኽነን ታላቅ ምስጢር ዮሐንስ አይቶ እኛ
ሳናይ ብለው ሱባኤ ነሐሴ 1 ዠመሩ ነሐሴ 14 ቀን በኹለተኛው ሱባኤ ጌታ የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል፡፡
በተወደደች ዕለት ነሐሴ 16 “ወአዘዞሙ እግዚእነ ለሰብአቱ ሊቃነ መላእክት ከመ ይጸውዕዋ ለምድር” (ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ምድርን ይጠሯት ዘንድ አዘዛቸው)
እነርሱም ምድርን “ይኤዝዘኪ እግዚእነ ከመ ታውጽኢ ሥጋሃ ለእሙ ቅድስት” (ጌታችን የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ ያዝሻል) አሏት፤ ያን ጊዜ ልጇ “ንዒ ኀቤየ ወላዲትየ ከመ አዕርጊ ውስተ መንግሥተ ሰማያት” (ወደ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ እናቴ ወደኔ ነዪ) አላት፤ ያን ጊዜ በልጇ ሥልጣን የቅድስት
ድንግል ማርያም ነፍሷና ሥጋዋ ተዋሐዱ፤ ነሐሴ 16 ዕለትም ከሞት ተነሣች፡፡ ያን ጊዜ “ወረዱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት” ይላል ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ በታላቅ ግርማ ወረዱ፤ ነቢዩ ዳዊትም “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ” (ንግሥቲቱ ወርቀ ዘቦ ግምጃ ደርባ ደራርባ በቀኝኽ ትቆማለች) እያለ ይዘምርላት ነበር፤ አየሩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመላ፤ እጅግ
የሚያስደንቅ መዐዛ አካባቢን ዐወደው፡፡ ያን ጊዜ በታላቅ ክብር በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ሰማዩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመልቶ የአምላክ እናት በክብር ስታርግ ተመለከተ፤ ያን ጊዜ ነገሩ ረቆበት ምን ይኾን እያለ ሲል ቅዱሳን መላእክት
የእመቤታችን ዕርገት እንደኾነና እጅ እንዲነሣ ነገሩት፡፡ ርሱም “ከቶ ምን አርጌ ይኾን፤ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ
ቀረኊ ዛሬ ደግሞ የርሷን ትንሣኤ ሳላይ ልቅር” ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ይላል ተበጻብጾ ሊወድቅ ወደደ፤ እመቤታችንም “አይዞኽ አትዘን እነሱ ሞቴን አይተዋል እንጂ ዕርገቴን አላዩም አኹንም እመቤታችን ተነሣች ዐረገች ብለኽ ንገራቸው” ብላ ለበረከት ሰበኗን ሰጠችው፡፡ ርሱም በደስታ
ተመልቶ ሐዋርያት ያሉበት በመኼድ የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ ብሎ ጠየቃቸው፤..... ይቀጥላል
Join

የእመቤታችን ዕርገት
ክፍል ፪

ክፍል አንድን ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/795
....... እመቤታችን ሞተች ቀበርናት አሉት፤ “መቼ ሞተች?” አላቸው በጥር አሉት፤ “መቼ ቀበራችኋት?” አላቸው
በነሐሴ አሉ፤ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይኽ ነገር እንዴት ይኾናል አላቸው፤ ቅዱስ ጴጥሮስም ቶማስን ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ አላምን ብለኽ የጌታን ጐን የዳሰሰ እጅኽ ተቃጥሎ ነበር፤ አኹን ደግሞ እኛ ብንነግርኽ አላምን ትላለኽ ብሎ፤ “ወነሥአ መክርየ” ይላል መቆፈሪያ ይዞ ኼዶ ይቆፍር
ዠመር፤ ርሱም የያዘውን ይዟልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፤ ቈፍረው ሲያጧት ደነገጡ፤ ቶማስም አይዟችኊ አትደንግጡ እመቤታችን እኮ በመላእክት ምስጋና ወደ ሰማይ አረገች ብሎ
ሰበኑን አሳያቸው፤ እነርሱም ለበረከት ሰበኑን ተካፍለውታል፡፡ ዛሬም ሐዋርያዊት የኾነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያናችን ይኽነን በማሰብ በመስቀል ሥር የሰበኗ ምሳሌ
የሚኾን ሰፊ ጨርቅ ታደርጋለች፡፡
ባመቱ ቶማስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በድጋሚ ሐዋርያት ሱባኤ ሲገቡ ክብር ይግባውና ጌታችን በደመና ነጥቆ ወስዶ ሥርዓተ ቊርባንን ፈጽሞላቸው፤ ስለ እናቱ ዕርገት በዓለሙ ኹሉ ዙረው
እንዲያስተምሩ አዝዟቸዋል፡፡ እነርሱም ዓለምን ዞረው ወንጌልን ሲያስተምሩ የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገት ሰብከዋል አስተምረዋል፡፡
ጌታችን እንኳን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን በዠርባዋ ያዘለችውን በክንዶቿ የታቀፈችውን ከሥጋዋ ሥጋን
ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የኾነው ታቦቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን ትቅርና ያገለገሉት ወዳጆቹን እንኳን ሞትን ሳያዩ ወደ ሰማይ እንደወሰዳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስናነብብ፤ ለምሳሌ ሔኖክ ሞትን ሳያይ በሕይወቱ ሳለ እግዚአብሔር እንደወሰደው በዘፍ ፭፥፳፬ እና በዕብ ፲፩፥፭ ላይ ሲጠቀስ፤ ነቢዩ
ኤልያስም ሞትን ሳያይ በእሳት ሠረገላ ተነጥቆ ወደ ሰማይ እንደወጣ (፪ነገ ፪፥፲፩‐፲፪) ተጽፎልናል፡፡ በዘመነ ሐዲስም ከእግረ መስቀሉ ሥር በጌታ ሥልጣን ስለተነሡ ቅዱሳን ማቴዎስ ሲጽፍ “መቃብሮችም ተከፈቱ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ” ይለናል (ማቴ ፳፯፥፶፪-፶፫)፡፡ ሐዋርያው
ቅዱስ ጳውሎስም ወደ ሰማይ ስለመነጠቅ “ሰውን በክርስቶስ ዐውቃለኊ በሥጋ እንደ ኾነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጪ እንደ ኾነ አላውቅም እግዚአብሔር ያውቃል፤ እንዲኽ ያለው ሰው ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ
ተነጠቀ” (፪ቆሮ ፲፪፥፪) በማለት ሲናገር፤
በዕለተ ምጽአት ስለሚከናወነው ደግሞ በ፩ተሰ ፬፥፲፯ ላይ “ከዚያም በኋላ እኛ
ሕያዋን ኾነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲኹም ኹልጊዜ ከጌታ ጋር እንኾናለን” በማለት እንደገለጸው የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግልን ወደ ሰማይ ማረግ በዐይኑ የተመለከተው ዮሐንስም “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ” በማለት መስክሮላታል (ራእ ፲፩፥፲፱)፡፡....ይቆየን
፩ ኃይማኖት
ለአስተያየት 👉 @AHati_Haymanot
Join 👉 @And_Haymanot

Telegram
፩ ሃይማኖት
የእመቤታችን ዕርገት´´
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን መምህር)
@And_Haymanot
በውሥጥ በጠየቃችሁን መሰረት ሥለ እመቤታችን ዕርገት ታሪክ እና ማሥረጃን በአንድ ላይ የተዘጋጀን ምላሽ ልናቀርብ ወደናል፡፡ የእናት ጡት ነካሽ ተሃድሶዎች ይህን እውነት መቀበል ቢከብዳቸው በዘርያዕቆብ ያመጣችሁት ታሪክ ነው ሢሉን ይደመጣሉ ይህ እነሱ እንደሚሉት የእመቤታችን…

ክፍል ፫

.... ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና እንደምናገኘው በመቃብር ውስጥ
መፍረስ መበስበስ የኀጢአት ውጤት ሲኾን ትእዛዝን የጣሰውን አዳምን “ዐፈር ነኽና ወደ ዐፈርም ትመለሳለኽና” በማለት ተረግሞ ነበር (ዘፍ ፫፥፲፱)፤ በዚኽም ጌታ እስኪመጣ ድረስ
ሥጋዊ ደማዊ የኾነው ኹሉ ወደ መቃብር ሲወድቅ፤ ርሷ ግን ከእናቷ ማሕፀን ዠምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች አዳማዊ ኀጢአት ያላገኛት፣ ኀጢአት አልባ የኾነች እንዲያውም አዳምና ሔዋን ይኽነን መርገም ከመስማታቸው በፊት ከነበራቸው ንጽሕና
የበለጠ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረገች ስትኾን ክብር ይግባውና አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽነን ንጹሕ ሥጋዋንና ነፍሷን በመንሣት በተዋሐደው ሥጋ በመስቀል ተሰቅሎ ሞትንና ኀጢአትን ድል ነሥቷልና እናቱም በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ዐርጋለች፤ ርሱን በመፅነስና በመውለድ ዕድፍ ጉድፍ
ያላገኘው ያልተለወጠ ድንግልናዋ፤ የተሸከመው ማሕፀኗ፤ የታቀፉት ክንዶቿና፣ የዳሰሱት እጆቿ፤ የሳሙት ከንፈሮቿ ያሳደጉት ጡቶቿ፤ ከርሱ ጋር የተመላለሱ እግሮቿና፤ ያዘለው ዠርባዋ፤
ብሩሃት የሚኾኑ ዐይኖቿ በጎ መዐዛ ያላቸው አፍንጮቿ፤ ጸዐዶች የሚኾኑ ጥርሶቿ፤ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ብሥራትን የሰሙ ዦሮቿ ፈጽመው በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረት የለባቸውም፤ ከርሷ ሥሮችንና ጸጒርን፣ ደምንና ዐፅምን ነፍስንና ሥጋን ነሥቶ
አባቶቻችን እንደ አስተማሩን ፈጽሞ ያለመለየትና ያለመለወጥ ከመለኮቱ ጋራ አንድ ያደረገው ልጇ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትን ድል
ነሥቶ እንደተነሣ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን ርሷ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ከልጇ ከንጉሡ ቀኝ በክብር ቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የቆየ አስተምህሮ ሲኾን በነሐሴ ወር የሚውለው የፍልሰቷ ክብረ በዓል በፍልስጥኤም ውስጥ ከ፬፻ ዓመት በፊት እንዲኹም ወደ ጋውል ከ፭፻ ዓመት በፊት ደርሷል ይኽ ኹሉ ለረዥም ዘመናት የተከናወነውና የተከበረው የታሪክ
ምስክርነት የሚያስረዳን ፍጹም የኾነውን ዕርገቷን ነው፤ ስለእመቤታችን ዕርገት ያስተማሩና የጻፉ በርካቶች ጥንታውያን
የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሲኖሩ ከእነዚኽ መኻከልም በ፫፻፹ ዓ.ም በኢየሩሳሌም ጳጳስ የነበረው ጢሞቴዎስ (ድንግል
እስካኹን ድረስ ሟች ያለመኾኗ ምክንያት በርሷ ውስጥ ያደረው ጌታ ወደ ማረጊያ ክልሎች ስለወሰዳት ነው) በማለት ሞት
በሌለበት በዕረፍት ስፍራ ልጇ ያሳረጋት መኾኑን መስክሯል፡፡ በተጨማሪም ከ70 ዓ.ም ዠምሮ ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ
በነበረው ስደት በክርስቲያኖች ዘንድ ዐፅመ ቅዱሳን ከፍተኛ ስፍራ የነበረው ሲኾን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት በሙሉ እንደሚያስረዱን በዚያ የስደት ዘመን ክርስቲያኖች በድፍረትና ሐላፊነትን ተሸክመው በቈራጥነት የሰማዕታትን ሰውነት ከመግደያው ስፍራ በመውሰድ ዐፅማቸውን በክብር ይጠብቁ የነበረ ሲኾን ይኽነንም አጥብቀው በመጠበቃቸውና ለትውልድ
በማስተላለፋቸው የከበረ ዐፅማቸው ባረፈበት ቦታ ላይ ዛሬ አብያተ ክርስቲያን ታንጸውበት እጅግ በርካቶች ጐብኚዎች
እየጐበኙት ሲገኙ ለምሳሌ ያኽል የነቅዱስ ጴጥሮስ፣ የነቅዱስ ጳውሎስ፣ የነቅዱስ ቶማስ፣ የነያዕቆብ ወ.ዘ.ተ የከበረ ዐፅማቸው ስፍር ቊጥር በሌላቸው ሰዎች ከጥንት ዠምሮ እስከዛሬ ድረስ ሲጐበኝና ሲታይ የቅድስት ድንግል ማርያምን አንድ የራሷን ጠጒርና የእጇን ጥፍር አገኘኊ የምትል ምንም ሀገርና ቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ፈጽማ የለችም ምክንያቱም አምላካችን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ያደረባት የአምላክ ታቦት
ክቡር ዳዊት በመዝ ፻፴፩፥፰ ላይ “አቤቱ ወደ ዕረፍትኽ ተነሥ አንተና የመቅደስኽ ታቦት” ብሎ ትንቢት እንደተናገረላት በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ በዕረፍቱ ስፍራ አለችና ነው፡፡ ይኸውም ሊታወቅ የዓለም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን በ፬፻ ዓ.ም አካባቢ ነግሦ የነበረው ንጉሡ ማርሲያን የኢየሩሳሌሙን ፓትሪያርክ የቅድስት ድንግል ማርያም ዐፅም ካለ ወደ ቊስጥንጥንያ እንዲያመጣለት ቢጠይቀው ርሱ ግን እመቤታችን እንዳረገችና ምንም ዐይነት የርሷ ቅሪት
እንደሌለ አስረድቶ ስለ ዕርገቷ ጽፎለታል፤ የሚገርመው ቅሪቶች
ከፍተኛ ዋጋ ስላላቸው ብዙ ሰዎች ወደ ከተማቸው ጐብኚዎችን ለመሳብ ሲሉ አስመስለው ለመሥራት በመሞከራቸው ብዙዎች ተከሰው የነበረ ሲኾን ለምሳሌ አክሊለ ሦኩን መስቀሉን አስመስለው ለመሥራት ከበፊት ዠምሮ ቢሞክሩም ኾኖም ግን የቅድስት ድንግል ማርያም አካል አለን የሚልና የሚሞክር
ከጥንት ዠምሮ እስከ ዛሬ በዓለም ላይ ለምን ጠፋ? ቢባል ማንም ሰው ይኽነን ሐሰት ስለማያምንና ከሐዋርያት ጊዜ ዠምሮ እስከ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እስከ አኹንም ድረስ
የቅድስት ድንግል ማርያም አካል ፈጽሞ በምድር ላይ እንደሌለና ወደ ሰማይ በአካል እንዳረገች ስለሚታወቅ ነው፡፡
በተጨማሪም ከመዠመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን-፲፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስም የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በቤተ ክርስቲያን፣ በነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ኹሉ ሙሉ
በሙሉ የታወቀ በመኾኑ በዕርገቷ ዙሪያ ምንም ዐይነት የጥርጥር ጥያቄን ያቀረበ ማንም የለም፡፡
ዛሬ በጭፍኑ አንዳንዶች
ፕሮቴስታንቶች የካዱትን ይኽነን እውነታ የእምነቶቻቸው መሥራቾች እንኳን ደፍረው አልተናገሩትም ለምሳሌ የፕሮቴስታንት ሪፎርመር የኾነው ሄንሪች ቡሊነግር በ፲፭፻፴፱ (1539 ዓ.ም) ላይ ጣዖታትን ተቃውሞ በጻፈው መጽሐፉ ላይ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስለማረጓ ሲገልጽ (ኤልያስ በሥጋና በነፍስ ሳለ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ወጣ፤ በርሱ ስም በተሠየሙ ባንዳቸውም ቤተ ክርስቲያን
አልተቀበረም፤ ይኽም ዘላለማዊነት እግዚአብሔር ለሚያምኑበት ለነቢያቱ ድንቅና ለማይነጻጸሩ ፍጡራኑ እግዚአብሔር እንዳዘጋጀ ያሳውቀናል … በዚኽ ምክንያት የአምላክ እናት የመንፈስ ቅዱስ መቅደስ፣ አካሏ ንጹሕና ኀጢአት አልባ የኾነው የድንግል ማርያም ንጹሕ የተቀደሰ ሰውነቷ በመላእክት ታጅቦ ወደ ሰማይ እንዳረገ እናምናለን)
ዛሬ ደግሞ ጥቂቶች ይኽነን እውነት መቃወማቸው የእምነት መሪዎቻቸው እንኳን ያስተማሩትን ትምህርትና የጻፏቸውን መጻሕፍት እንዳላነበቡ ያጋልጥባቸዋል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በነሐሴ ፲፮ የቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል ብሔራዊ በዓል ተደርጎ በተለያዩ ሀገራት ይከበራል፡፡
ወስብሃት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
በተጨማሪ ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/65
Join ====>👉 @And_Haymanot

የእመቤታችን ትንሣኤ ማረጋገጫ
@And_Haymanot
✍ ተወዳጆች በቅድሚያ እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችው።
☞ የተሃድሶ መናፍቃን እኛ ኦርቶዶክሳውያን ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሞት የመነሣት ምስጢር ስንናገር እመቤታችንን አምላክ ያደረግናት ይመስላቸዋል ወይም ደግሞ እሷን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ…

የእመቤታችን ዕርገት.pdf
480.7 KB
``የእመቤታችን ዕርገት ´´
ተወዳጆች በዚህ ርዕሥ ሲቀርቡ የነበሩትን ሶስት ክፍላት በ Pdf አቅርበንላችኋል፡፡ እንድታነቡት እንጋብዛለን
ተጨማሪ ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/65
✝ @And_Haymanot✝
❤️ሞትማ በሞት ተሸንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ሃይል ያገኛል❤️

“ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ እነሆ ክረምት አለፈ ዝናቡም አልፎ ሄደ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፡፡ የዜማም ጊዜ ደረሰ የቀረ… ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፡፡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ” መኃ 2፡10-13
እልልልልልልልልልል
✞ አርጋለች ማርያም ተነስታለች ✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot
እልልልልልልልልልል
✞ አርጋለች ማርያም ተነስታለች ✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት????
❖ @And_Haymanot ❖
አንድ እህታችን በውሥጥ የላከችልን መልዕክት ነው፡፡
ስለ እመቤታችን ሲነሳ አይናቸው ደም የሚለብሰው የተሃድሶ መናፍቃን ዛሬም ከእናታችን እቅፍ ሊለዩን ተነስተዋል ከጥፋት ትምህርታቸ አንዱ
ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት። በዛ ዘመን ብንኖር ከእኛ መሃል ከአንዳችን ኢየሱስ ይወለድ ነበር ብለው ያስተምራሉ ያምናሉ።
-ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስን ከመውለድዋ በፊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠች ሴት ናት ።
እንኳን የአምላክ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም አይደለም ማንኛችንም እግዚአብሔር የፈጠረን ፍጡር ወደዚህ አለም ከመምጣታችን በፊት ለምን አላማ እንደምንወለድ
እንኳን ገና ሳንፈጠር እግዚአብሔር ያውቃል:: ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ኤርምያስ 1:5 እንዲህ ይላል ።
የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ ከማህፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ
ለአህዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።
-ቅድስት ድንግል ማርያም ለአምላክ እናት እንድትሆን ገና ሳትፈጠር እግዚአብሔር የመረጣት ሴት ናት።
ከእሷም ባይሆን ከሌላ ይወለድ ነበር ለሚሉ የጥፋት ልጆች ከእግዚአብሔር አላማና ሃሳብ ጋር የተጣሉ የእግዚአብሔርን ሃሳብ በራሳቸው አመለካከት እና ሃሳብ ለመቀየር የሚያስቡ ደፋሮች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም
እንዲወለድ ነበር የእግዚአብሔር አላማ::
ከእሷ ባይሆን ለሚሉት የእግዚአብሔር ሀሳብ ሳይሆን የቀረበት ግዜ የለምና ከእሷ ውጭ ከማንም ሊሆን አይችልም። የእግዚአብሔር ሃሳብ ከቅድስት ድንግል ማርያም እንዲወለድ እንጂ ሌሎች እንደሚፈላሰፉት ከአዳራሽ ጨፋሪዎቻቸው ሴቶች መሃከል ኢየሱስ ሊወለድ አይችልም::
ከፍጥረት ሁሉ ፣የአምላክ እናት እንድትሆን የተመረጠች ቅድስት ማርያም ብቻ ናት። ለመዳናችን ምክንያት ለሆነች ከሴቶች ሁሉ ለተለየች የአምላክ እናት ክብር ይገባታል ።
በተጨማሪም ሊታወቅ የሚገባው ማንኛውም ሠው በነብያትና በሐዋርያት መንገድ መጓዝ ከቻለ ሐዋርያት የደረሱበትን የክብር ደረጃ መድረስ ይችላል፡፡ ነገር ግን በክብር ላይ ክብር ብናገኝ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኝ ስራ ብንሠራ እንኳ ድንግል ማርያም የደረሰችበት የክብር ደረጃ ላይ መድረስ
የሚችል ሰው ማንም የለም፡፡ ወደፊትም እንደዚህ አይነት ክብር እና ጸጋ ለማንም አይሰጥም፡፡፡፡
.....ይቆየን ከሰሞኑ እመቤታችን አንዲት ድንግል እናት ሥለመሆኗ በሰፊው እንመለሳለን፡፡
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን
፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው
ለእኛም ግለጽልን።
አሜን አሜን አሜን!!!

Forwarded from ተዋህዶ ሃይማኖቴ
የድንግልን ትንሣኤ በኩረ ፕሮቴስታንት የኾነው ማርቲን ሉተርና ስዊዘርላንዳዊው ቡሊንገር እንኳ በአንክሮ ያምናሉ ቡሊንገር ትንሣኤዋን ከኤልያስ ዕርገት ጋር በማነጻጸር ሲያስተምር ሉተር ደግሞ እንዲኽ ይላል" there can be no doubt that the Virgin Mary is in heaven, how it happened we do not know ፤ ጥርጥር ሊኖር አይችልም፡ ድንግል ማርያም በሰማይ ናት፡ እንዴት ኾነ? እኛ አናውቅም" ብሏል Martin Luther's works,vol.10, pg.268
ድንግል ማርያም አልተነሣችም ለሚሉ እሆነ ብለናል፡፡
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
ድንግል ማርያም አልተነሣችም ለሚሉ እሆነ ብለናል፡፡
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
አንዲት ድንግል
@And_Haymanot
ሚያትተው፦
፩ ስለ እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና
፪ እመቤታችን አርጋ በ እግዚአብሔር ቀኝ ቆማ ስለ እኛ መማለዷ…
[[[[[[[[ተወዳጆች ነገረ ማርያምን ሥናነሳ በውሥጥ ጥያቄ የሚያነሱት በዝተዋልና የምትጠይቁ እንድትታገሱን ለማለት እንወዳለን፡፡ በተጨማሪም ሌሎች መምህራንንም ለማሳተፍ ስላሰብን Bot መሥራት የምትችሉ በውሥጥ አናግሩን
@AHati_Haymanot ]]]]]]]]]
``አንዲት ድንግል´´
✍ የተሃድሶ መናፍቃን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ከሚቃወሙበት ነገሮቹ አንዱ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልና ላይ ነው ነገር ግን መታደስ ያለበት የራሳቸው አስተምሮ እንጂ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን አይደለችም እስቲ በምድር ላይ ብቸኛ ዘላለማዊ ድንግል ስለሆነችው ስለ"አንዲቷ"ድንግል ማርያም የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ምን እንደሚል እንይ፦
✞ ቅዱስ ሉቃስ ☞ በሉቃ 1፥26 - 27 ላይ በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ በማለት አንዲት ድንግል መሆኗን ጽፎልናል።
✍ አንዲት የሚለው ቃል እንዲው ጽሁፍ ለማሳመር የገባ ቃል አይደለም መንትያ፣ አቻ፣ ወደር፣ ተወዳዳሪ... የሌለው ነገር "አንዲት" እየተባለ ይጠራል መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ "አንዲት" እያለ የገለጻቸው ነገሮች አሉ ለምሳሌ፦
☞ መዝ 26፥4 እግዚአብሔርን "አንዲት" ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ
☞ ኤፌ4፥ 5 አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት "አንዲት" ጥምቀት
☞ ሐዋ 4፥32 ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ "አንዲትም" ነፍስ ነበሩአቸው
☞ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት "በአንዲት" ክብርት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን ኃጢአት በሚሠረይባት "በአንዲት" ጥምቀትም እናምናለን ( የሃይማኖት ጸሎት)
✍ በዚህ የተነሳ ቅዱስ ሉቃስ ሲጽፍልን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ "አንዲት" ድንግል ተላከ ብሎ ጽፎልናል ነገር ግን ልናስተውል የሚገባው ነገር የአጻጻፍ ዘይቤ ቢሆን ኖሮ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ድንግል ተላከ ብሎ መጻፍ ይችል ነበር ነገር ግን የምስጢር፣ የክብር፣ የልዕልና ጉዳይ ስለሆነ ወደ "አንዲት" ድንግል ብሎ ጻፈልን ቅዱስ ሉቃስ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ሲያበስራት በቦታው አልነበረም ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ሲጽፍልን "አንዲት" ድንግል ብሎ እንዲጽፍ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶታል።
☞ ለምን ቅዱስ ሉቃስ "አንዲት" ድንግል ብሎ ጻፈልን?
1ኛ፦ የእመቤታችን ድንግልና ልዩ ስለሆነ፦ የእመቤታችን ድንግልና በዚህ ምድር ላይ ታይቶ ተሰምታ የማይታወቅ ነው ወደ ፊትም አይታወቅም ስለዚህ በተራ ቃል ሊገልጻት ስላልፈለገ "አንዲት" ድንግል ብሎ ገለጻት በምድር ላይ ብዙ ደናግላን ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን ድንግልናቸው ጊዜያው ነው የእመቤታችን ድንግልና ግን ዘላለማዊ ድንግልና ነው ብዙ ቅዱሳን ለክርስቶስ ፍቅር ሲሉ በምናኔ ጸንተው በድንግልና ኖረዋል ድንግልናቸው ግን በስጋ ነው እመቤታችን ግን በሐልዮ(በማሰብ) በነቢብ(በመናገር) በገቢር (በተግባር) ከሚሰሩ ሐጢአቶች በነፍስም በስጋም ጭምር ድንግል ናት እመቤታችን (ቅድመ ፀኒስ፣ጊዜ ፀኒስ፣ድህረ ፀኒስ፣ቅድመ ወሊድ፣ጊዜ ወሊድ፣ድህረ ወሊድ) ድንግል ነች።ስለዚህ ብቸኛ ተወዳዳሪ የሌላት ድንግል ስለሆነች ቅዱስ ሉቃስ "አንዲት" ድንግል ብሎ ገለጻት።
ልናስተውል የሚገባው ነገር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም "አንዲት" ድንግል ያስባላት ድንግልናዋ ብቻ አይደለም ነገር ግን የድንግልናዋን ቅድስና ማንሳት ስለሚገባን ነው እንጂ እኛ ኦርቶዶክሳውያን እመቤታችንን ድንግል ብለን ስንጠራት ግን እናትነትንም አስተባብራ የያዘች ናት ስለዚህ እናትነትና ድንግልናን አስተባብራ የያዘች ብቸኛ ሰው ስለሆነች "አንዲት" ድንግል ተባለች ለዛም ነው ጠቢቡ ሰሎሞን ☞ በ መኃ 4፥12 ላይ "እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት" በማለት ያወደሳት።
✍ ጠቢቡ ሰሎሞን እመቤታችንን እህቴ ያለበት ምክንያት አባቱ ዳዊት ☞ በ መዝ 44፥10 ላይ "ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ" ስላላት ነው አባት ልጄ ሲል ወንድም ደግሞ እህቴ እንደሚል ማለት ነው ነገር ግን ጠቢቡ ሰሎሞን እህቴ ብቻ ብሎ አልቀረም "ሙሽራዬ" ብሎ ቀጠለበት እንጂ እንደሚታወቀው ሙሽሪት በሰርጓ ቀን ከትኛውም ሰው በበለጠ ትልቅ ክብር ነው የሚሰጣት ስለዚህ ጠቢቡ ሰሎሞንም ሙሽራዬ በማለት ለእመቤታችን ያለውን ትልቅ ክብርና ፍቅር በመዝሙሩ ገልጿል በመቀጠልም የተቆለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ በማለት ዘላለማዊ ድንግልናዋን ነግሮናል ከተዘጋ ከታተመ ምንጭ እንዴት ፈሻሽ ይወጣል? ብለን ከጠየቅን አይወጣም ከእመቤታችን ግን በተዘጋ ድንግልና ወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ የህይወት ውኃ ምንጭ የሆነ ጌታ ተወለደ ስለዚህ የተዘጋ የውኃ ምንጭ ተባለች ለዚህም ነው ነብዩ ህዝቅኤል በትንቢቱ ☞ ሕዝ 44፥2 ላይ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል በማለት የተናገረው በር የተባለው የእመቤታችን ድንግልና ነው ይህ በር ጌታ ገብቶበታልም ወጥቶበታልም ነገር ግን በሩ አልተከፈተም ስለዚህ የምስራቅ በር የተባለችው እመቤታችን ጌታን በህቱም ድንግልና ጸንሳ በህቱም ድንግልና በመውለዷ ቅዱስ ሉቃስ "አንዲት" ድንግል ብሎ ጠርቷታል።
2ኛ፦ በእግዚአብሔር መንግስት "አንዲት" ንግስት ስለሆነች፦ ይህን ስንል ለዚህ ነው ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ☞ መዝ 44፥9 ላይ ´´ወትቀውም ንግስት በየማንከ…በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች`` ያለው ምክንያቱ ወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ በዙፋኑ ሲቀመጥ ንግስቱቲ ደሞ በቀኙ ትቆማለች ንግስቲቱ ደሞ እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት እሷም "አንዲት" ንግስት ናት ለዚህም ነው ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ በቀራንዮ ክቡር መስቀሉን ዙፋን አድርጎ አዳምን ነፃ ሲያወጣውና ዲያብሎስን ሲያስረው በቀራንዮ በመስቀሉ ስር ´ቆማ´ የነበረው:: ንግስት ከሆነች ደግሞ ስልጣን ስላላት ለአዳም መዳን ምክንያተ ድህነት የሆነች ብቸኛዋና ተነፃፃሪ የሌላት "አንዲት" ናት ስለዚህ "አንዲት" እያልን እንጠራታለን።
3ኛ፦ "አንዲት" እመ እግዚአብሔር ስለሆነች፦ ግሪኮች እመቤታችንን "ቴኦቶኮስ" ይሏታል ትርጓሜውም "የአምላክ እናት" ማለት ነው ለዛም ነው ቅድስት ኤልሳቤጥ ☞ በሉቃ 1፥43 ላይ ''የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?'' ያለችው ስለዚህ ብቸኛዋ የአምላክ እናት ስለሆነች "አንዲት" እያልን እንጠራታለን ሌሎች እናቶች ቢመሰገኑ ቅዱሳንን፣ ነገስታትን፣ ነቢያትን፣ አዋቂዎችን... ስለወለዱ ይሆናል የእኛ እመቤት ግን የዓለማት ፈጣሪን ስለወለደች ነው የምትመሰገነው ስለዚህ ቀና ስንል ወደ ሰማይ ዝቅ ስንል ወደ ቀራንዮ የማናጣት እመ አዶናይ "አንዲት" ናት።...... ቀጥሏል
👇👇👇 https://tttttt.me/And_Haymanot/817

...... የቀጠለ
4ኛ፦ በክርስቶስ የማዳን ጉዞ ውስጥ ''አንዲት'' ስለሆነች፦ ይህም
❖ ክርስቶስ በቤተልሄም ሲወለድ እናቱ እመቤታችን ነበረች
❖ ክርስቶስ ወደ ግብጽ ሲሰደድ ይዛው የተሰደደችው እመቤታችን ነበረች
❖ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም የፋሲካ በዓልን ሲከበር እመቤታችን ነበረች
❖ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ ውኃውን ወደ ወይን ሲለውጥ አማላጇ እመቤታችን ነበረች
❖ ክርስቶስ በቀራንዮ…

❖ ክርስቶስ በቀራንዮ በመስቀል ላይ እንደ ብራና ተወጥሮ ዓለምን ሲያድንና የአዳም ፍዳን ተፈጸመ ሲል ከመስቀሉ ስር እመቤታችን ነበረች
❖ በቤተ ክርስቲያን በልደት ቀን በበዓለ ሀምሳ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል በኢየሩሳሌም በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ሲወርድ እመቤታችን ነበረች... ለዛም ነው ቅዱስ ሉቃስ ☞ በሐዋ 1፥14 ላይ እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር። ያለው ስለዚህ በክርስቶስ የማዳን ጉዞ ውስጥ ከቤተልሄም እስከ ቀራንዮ ድረስ ያለች ብቸኛዋ እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ "አንዲት" ናት።
ማጠቃለያ
✍ ተወዳጆች ብዙዎች "አንዲቷን" ድንግል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ክደዋታል፣ ንቀዋታል፣ አቃለዋታል፣ ረስተዋታል፣ ሸሽተዋታል... ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ግን የመድኀናችን ምክንያት፣ የድህነታችን ተስፋ የሆነች የማትካድ፣ የማትናቅ፣ የማትቃለል፣ የማትረሳ፣ የማትሸሽ... አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደች "አንዲት" ድንግል ናት ለዛም ነው ልበ አምልክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ☞ መዝ 86፥5 ላይ እምነ ፅዮን ይብል ሰብዕ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ ያለው ጠቢቡ ሰሎሞንም በመዝሙሩ ☞ መኃ 6፥9፤ ርግቤ መደምደሚያዬም "አንዲት" ናት፤ ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት ብሎ የዘመረላት በመሆኑም ከሰው ልጆች በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደች ብቸኛዋ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ስለዚህ ከ72 አርድእት የሚመደበውና ምስለ ፍቁር ወልዳ ስዕልን የሳለው ቅዱስ ሉቃስ "አንዲት" ድንግል ብሎ ክብሯን፣ ልዕልናዋን፣ አንዲትነቷን ገልጾልናል የተሃድሶ መናፍቃኑም የራሳቸው አስተምሮ ይታደስ እንጂ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን ፈጽሞ አትታደስም።
[[[[[በቅርቡ በነገረ ማርያም ላይ የተለቀቁ ጽሑፎችን በአንድ ላይ እናቀርባለን]]]]]
✞ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልመናዋ ፍቅሯ ረድኤት በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር!!! አሜን ✞

ማንንም አባት አትበሉ´´
በምድር ላይ ማንንም አባት አትበሉ እንዲሁም ማንንም ሊቃውንት አትበሉ ብሎ ጌታ ተናግሯል ለምንድነው ኦርቶዶክሶች “አባቶች” እያላቹ የምትናገሩት ?
መልስ፡- ተቃዋሚዎች የሚያነሱት ጥቅስ በማቴዎስ 23፡9 ላይ ሲሆን
“አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ።” ይላል፡፡ ይህን ጥቅስ ከመጀመሪያው ቁጥር ጀምሮ ልብ ብለን ካነበብነው ክርስቶስ እየተናገረ ያለው
ስለ ፈሪሳውያን ነው፡፡”ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል። ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ። “ ማቴ 23፡2-3 ዋናው ጌታችን ሲያስተምር የነበረው አላማ “
እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ።” የሚለውን ነው፡፡ ምክንያቱም ፈሪሳውያን ከተግባር ይልቅ እይታን የሚወዱ እና ከፍ ብልው መታየትን የሚመርጡ አንጂ ሐይማኖትን
ከምግባር ጋር የያዙ ስላልነበሩ ነው፡፡ ክርስቶስም “አባት”.”ሊቃውንት” ብላቹ አትጠሩ ማለቱ እንደ ፈሪሳውያን ለእይታ ከሆነ እና ያለስራ ከሆነ “አባት “ ተብሎ መጠራቱ ይቅርባቹ ብሎ ሲያስተምረን ነው፡፡ ግን ቃሉን ቀጥታ ወስደን ከተረጎምነው እና በምድር ላይ ማንንም አባት ብለን መጥራት የለብንም ካልን የስጋ አባታችንንም “አባት” ብለን መጥራት ልናቆም ነው አንዲሁም ቅዱስ ጳውሎስ በተለያዩ ምዕራፎች ላይ “አባት” እያለ ቅዱሳንን መጥራቱ ስህተት ነው ወደሚል ድምዳሜ ያደርሰናል፡፡ይህ ደግሞ መንፈስ ቅዱስም በእነ ቅዱስ
ጳውሎስ ላይ አድሮ “አባት” ብለው እንዲጽፉ ማድረጉ ስህተት ነው ልንል ነው፡(ሎቱ ስብሐት) ቅዱስ ጳውሎስ ሆነ ቅዱስ ጴጥሮስ በጣም ብዙ ጊዜ አባቶች እያሉ ጠቅሰዋል።
ለምሳሌ፡- ገላ.1፡14 ''ለአባቶችም ወግ ከመጠን ይልቅ እየቀናሁ...''
ሮሜ 9፡5 ''አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥...''(እዚህ ላይ እንግዲህ አባቶች የተባሉት እነዳዊት ናቸው)፣ ሮሜ 15፡8 ''ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና
ዘንድ ደግሞም...''ዕብ 7፡4 ''የአባቶች አለቃ አብርሃም ከዘረፋው...''2ኛ ጴጥ 3፡4 ''አባቶች ከሞቱባት ጊዜ፥ ከፍጥረት
መጀመሪያ....'' ፡፡ የወንጌል ሰባኪዎች አባቶች ይባላሉ!1ኛ ቆሮንጦስ 4:15" እንደምወዳቹ 'ልጆቼ'አድርጌ ልገስፃቹ እንጂ ላሳፍራቹ ይህን አልፅፍም በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሯቹም ብዙ አባቶች የላቹም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል 'ወልጃችኃለውና..." እንግዲህ ወንድማችን, ቅዱስ ጳውሎስ
በወንጌል ወልጃችኋለው ልጆቼ ናችሁ እያለን እኛ አባታችን ነህ ብለን ብንጠራው ምንድነው ችግሩ? ምንም ችግር የለውም ምክንያቱም ቅዱስ ጳውሎስ ከሱ በፊት የነበሩትን የእምነት
ሰዎች “አባት” ብሎ እንደጠራ እኛ ደገሞ ዛሬ እሱን እና የሱን ፈለግ የተከተሉ እውነተኛ የእምነት አባቶች “አባት” ብለን
እንጠራለን! ስለዚህ የወለደ አባት ይባላል ...በወንጌል የወለደኑንም አባት ይባላሉ! አባት መባል ብቻ ያይደለ እጥፍ
ክብር ይገባቸዋል “በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥
ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።” ( 1ኛጢሞ5:17 ) ስለዚህ ሊቃውንት ብለን እንደ ክብራቸው እጥፍ ድርብ ክብር እንሰጣቸዋለን! መጽሐፍን
እንዳነበብን ቀጥታ የምንተረጉም ከሆነ እውቀታችን ከአህዘብ አይሻልም! አህዛብ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ በሉቃስ 18፡ 19 ላይ “ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር
በቀር ቸር ማንም የለም።” ብሎ ተናግሯል ብለው ጌታ ስለ ትህትና እና ስጋ ስለመልበሱ የተናገረውን ቃል ቀጥታ ወስደው ክርስቶስ ቸር አይደለም እንደሚሉ እኛም ጥቅሶችን ብቻ ይዘን
ያለ ትርጓሜ የምንጓዝ ከሆነ ክርስትናችንን ጥያቄ ውስጥ ያስገባል፡፡ መጽሀፍም “ፊደል ይገድላል “ ማለቱ ለዚህ ነው!
(source:- Matiwos amare)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል

መላእክት ተጋብተው ኖሩ....?
@And_Haymanot
እውነት መላእክት ከሠው ልጆች ጋር ተጋብተው ልጆች ወልደዋል?
መላእክት ለመሆኑ ሥጋና ደም አላቸው? መፅሐፈ ኩፋሌ 6:9 መላእክት ከሠው ጋር ተጋብተው ልጆች እንደወለዱ ይነግረናል ይህ 80 አሐዱ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለን እንመን?
በመጽሐፍ ቅዱስ አጻጻፍ በነጠላው መልአክ ወይም በብዙ መላክእት ሲባል ሦስት ዓይነት የመላእክት አተረጓጎም አለ፡-
1ኛ. “ቅዱሳን መላእክቱ” (ማቴ 28፡31) በሚልበት ጊዜ የእግዚአብሔር መልእክተኞችን በፊቱ ቆመው የሚያመሰግኑትን (ኢሳ 6፡1-3)፣ የሚጸልዩትንና የሚለምኑትን (ዘካ 1፡12-13፣ ሉቃ 13፡6-9) በፊቱ ቆመው የሚላኩትን (ሉቃ1፡27)፣ ወደ እግዚአብሔር የሰዎችን ጸሎት በእጃቸው የሚያሳርጉትን (ራእይ 8፡3-4)፣ የሚባርኩትን (ዘፍ 48፡16)፣ ሰዎችን የሚጠብቁትን (መዝ 90/91/፡11)፣ ሰዎችን ከክፉ ነገር የሚያድኑትን (መዝ
33/34/፡7)….የሚመለከት ይሆናል፡፡
እነዚህ መላእክት አይበሉም፣ አይጠጡም፣ አያገቡም፣ አይገባም፣ አይታመሙም አይሞቱም፡፡ መንፈሳዊ አካል ነው ያላቸው፡፡ “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ
የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” እንዲል (ዕብራ 1፡14)፡፡
2ኛ. ርኩሳን መላእክት አሉ፤ እነዚህ የሰዎች ጠላት ናቸው “በርኩሳን መናፍስት” (ማቴ 10፡1) እንዲል፡፡ አፈጣጠራቸውም ከቅዱሳን መላእክት ጋር አንድ ሲሆኑ በኃጢአታቸው ምክንያት ከሰማይ ወደ ምድር ተጥለዋል፤ ሐዋርያው “እግዚአብሔር
ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት” (2ኛ ጴጥ 2፡4) ያለው እነዚህን ነው፡፡ በተመሳሳይ ከቅዱሳን መላእክት ጋር በተፈጥሮ አንድ ስለሆኑ ርኩሳን መላእክትም አይበሉም፣ አይጠጡም፣ አያገቡም፣ አይገባም፣ አይታመሙም አይሞቱም፡፡ መንፈሳዊ አካልን ይዘው ሰዎችን ይዋጋሉ፡፡ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው” (ኤፌ 6፡12)፡፡ ስለእነዚህ ተዋጊዎች ዮሐንስ በራእዩ ሲጽፍ “ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር
ተጣሉ” (ራእይ 12፡3-9) ያለው ውስጥ፡- “ዲያብሎስና ሰይጣን… መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ” እያለ የሚናገረው ቅዱሳን መላእክቱን ሳይሆን ስንፍና የከሰሳቸውን መላእክት ነው “እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል” (ኢዮብ 4፡18)፡፡ እነዚህ መላእክት
በስንፍናቸው ፈጣሪ የለም ብለው መላእክትን ያስካዱ ስለሆኑ የቅጣት ጊዜ እንደ አላቸው ጌታ ሲናገር፡- “…ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” ይላል
(ማቴ 25፡41) ይህንን ጥቅስ ያየ ሰው “መላእክቱ” ስለሚል ቅዱሳን መላእክቱን ሊመስለው ይችላል፡፡ ምክንያቱም እርሱ የሚያውቀው በጠባቡ “መላእክቱ” ሲባል ቅዱሳን መላእክቱን ብቻ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰይጣን አገልጋዮችም መላእክት መባላቸውን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡
3ኛ. የተጠየቀው ጥያቄ ላይ የሚመለከት ሲሆን ሰዎች “መላእክት” ወይም “መልአክ” መባላቸውን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ አሁን መጽሐፍ ቅዱስ ሰውን መልአክ እንደሚል እንይ፡- ቅዱሳን መላእክት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ እንድንድን የሚተጉ እንጂ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለዩን አይደሉም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “… መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም
ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥… ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ” (ሮሜ 8፡38-39) ይላል፡፡
አሁን ይህንን “መላእክትም” የሚላቸው የመቅደስ አዛዦችን ነው እንጂ እነ ቅዱስ ገብርኤልን አይደለም፡፡ ሰዎች የሆኑ የመቅደስ አዛዦች አትስበኩ ክርስቶስን አምላክ ነው አትበሉ እያሉ ከአባቱ ጋር ያለውን አንድነቱን የካዱና የሚያስክዱ እንዲህ ብሎ የሚሰብክንም የሚያሳድዱ ስለሆኑ፤ አስቀድሞ ክቡር ዳዊት ይህንን የአንድነት ማሠሪያ ለመበጠስ የሚሹ ስለመሆናቸው “አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ፡፡ ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል” (መዝ 2፡2-3) ብሏል፡፡ በዚህ ቦታ “አለቆችም” የሚለው በግእዙ “መላእክቱኒ” በማለት
ጽፏል፡፡ ይህ አለቆች አዛዦችን የሚመለከት እንጂ ቅዱሳን መላእክትን የሚመለከት አይደለም፡፡ መላእክት ከእግዚአብሔር ፍቅር አይለዩምና፡፡
በተመሳሳይ ለቤተ ክርስቲያኖቻችን አለቆች የሚጠሩበት ስም እንደሆነ ዮሐንስ በተደጋጋሚ እንዲህ ብሏል፡-
“በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ…መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ” (ራእይ 2፡8-9) “በሰርዴስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። ….ሥራህን አውቃለሁ ሕያው እንደ መሆንህ ስም
አለህ ሞተህማል” (ራእይ 3፡1) “በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። …እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ
እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ” (ራእይ 3፡
14-22) በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት የቤ/ክ/ን መልአክ የሚባሉት ሰዎች
ናቸው፡፡ ምክንያቱም “መከራ” እና ማጣት በቅዱሳን መላእክት የለም፡፡ ይህ ሰው ስለሆነ “…መከራህንና ድህነትህን
አውቃለሁ” (ራእይ 2፡8-9) ይለዋል፡፡
በተመሳሳይም በቅዱሳን መላእክት መሞት የለም ነገር ግን ይህ
አለቃ ሰው ስለሆነ “ስም አለህ ሞተህማል” (ራእይ 3፡1) የሚለው ሰውን እንጂ ረቂቁን መልአክ አይደለም፡፡
በመጨረሻ የጠቀስነውም “… ንስሐም ግባ” የተባለው መልአክ (ራእይ 3፡14-22) ረቂቁን መልአክ ሳይሆን የሰው ዘር የሆነውን የቤ/ክ/ን አለቃን ነው፡፡ ባጠቃላይ “አለቆች” “መልአክ” ከተባሉ በቅዱስ ጳውሎስ ንግግርም መላእክት ተብለው ሰዎች እንደሚጠሩ ከተማርን፤
በመጽሐፈ ኩፋሌ መላእክት የሚላቸው የሰው ልጆችን እንጂ ረቂቃኑን መላእክት አይደለም፡፡ ረቂቃኑማ “መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም” (ማቴ 22፡30) መባሉ
የታወቀ ነው፡፡ መጽሐፉ ደግሞ “የአዳም ልጆች በምድር ላይ ይበዙ ዘንድ
በጀመሩ ጊዜ እንዲህ ሆነ፤ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው፡፡ የእግዚአብሔር መላእክትም …እነዚያ ላዩአቸው መልከ መልካሞች ነበሩና ከመረጡአቸው ሁሉ ሚስቶች ሊሆኑአቸው ወሰዱአቸው፤ ወንዶች ልጆችንም ወሰዱላቸው..” (ኩፋሌ 6፡9) በሚለው ውስጥ ልብ ብለን ስንመለከት “የእግዚአብሔር
መላእክትም …” የሚላቸው ሰዎችን ነው፡፡ እነዚህ በዘፍጥረት አጻጻፍ “የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን
ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ” ከሚለው ጋር አንድ ነው (ዘፍ 6፡ 2)፡፡
“የእግዚአብሔር ልጆች” የተባሉት በኩፋሌ አጻጻፍ በቅድስና በንጽሕና የኖሩት በመጠሪያ ደረጃ “የእግዚአብሔር መላእክት”
የተባሉትን ሲሆን፤ “የሰውን ሴቶች ልጆች” የተባሉት ደግሞ በኃጢአት የሚኖሩትን ነው፣ በኃጢአት ከሚኖሩት፣ ከአምልኮ እግዚአብሔር ከራቁት ጋራ
በማይመች አካሄድ መጣመድ ስለማይገባ ያ ሁሉ ጥፋት መጥቶባቸዋል፡፡ እነዚያ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ የእግዚአብሔር ልጆች፣ የእግዚአብሔር መላእክት የሚል
የማዕረግ መጠሪያ ሲሰጣቸው፡፡ በአምልኮ ባዕድና በኃጢአት የሚኖሩትን ግን የሰው ልጆች ብቻ በሚል መጠራታቸውን እናስተውል፡፡ እኛም የእግዚአብሔር ልጆች በአጋንንት ላይ አለቆች ነንና መላእክት የሚል መጠሪያ
እንዳለን ልብ ማለት ይገባል፡፡
....ቀጥሏል👇👇

....(የቀጠለ)
መጽሐፈ ኩፋሌ “መላእክት” ስላለ ብቻ ረቂቃኑን ነው ብለን የምንወድቅ ከሆነ፡-
“መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል” (ኢዮብ 4፡18)፡፡ የሚለውን ይዘን ቅዱስ ሚካኤልን ስንፍና ይከሰዋል ወደማለት
አዘቅት እንወድቃለን፡፡ “…ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” (ማቴ 25፡41) የሚለውንም አይተን ቅዱስ ገብርኤልና
ቅዱስ ሚካኤል ወደፊት በእሳት ባሕር ይጣላሉ ወደሚል ክህደት
እንወድቃለን፡፡ “… መላእክትም ቢሆኑ..ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን
እንዳይችል ተረድቼአለሁ” (ሮሜ 8፡38-39) የሚለውንም ይዘን ቅዱሳን መላእክት ከአምላክ የሚለዩ ናቸው ወደሚል የስህተት መንገድ እንጓዛለንና እንደ አገባቡ እንፍታው እንጂ፤ ባመጣለን
ተሳስተን ሰውን ወደ ስህተት ከመክተት እንቆጠብ፡፡
እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን፡፡

❖ መልካም አዲስ አመት አትበሉን!!!!!!!
@And_Haymanot
የ ፳፻፲፩ (2011) ዓ.ም የመልካም ምኞት መግለጫ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ማኅበራዊ ሚዲያዎች 'መልካም አዲስ አመት' ሲሉ "መልካም አዲስ ገረድ' ማለታቸው መሆኑን ያውቃሉ......
♦ "አመት" ተብሎ በአልፋው "አ" ሲጻፍ ሴት አገልጋይ ገረድን ይገልጻል። ለምሳሌ፦ "ተፈሥሒ ኦ አመት ወእም ድንግል ወሰማይ ሰማያዌ..." /ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ/ ሲል ገረድ(ሴት አገልጋይ) ና እናት፤ ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ ማለት ነው።
♦ "ዓመት" ሲሆን ዘመን ይሆናል። "...ርእሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ።..."/መልክአ ዮሐንስ መጥምቅ፤ ለሥእርተ ርእስከ(ለራስ ጸጉርህ)/ ሲል ደግሞ "የመጥቅዕና የአበቅቴ መጀመሪያ ርእሰ ዓመት ዮሐንስ ሆይ..." ማለት ነው።
✍ አመት የሚለው በብዙ ቁጥር አእማት ይሆናል። በዕብራይስጥ አማህ፤ በሱሪስት አምታ፤ በዐረብኛ ደግሞ አመት ይለዋል። ትርጓሜውም ሴት ባሪያ፤ ገረድ፤ ደንገጥር ማለት ነው። "...በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባሪያይቱ..." ዘፀ.11፥5 የሚለውን ግዕዙ "አመት እንተ ትነብር ዲበ ማሕረጽ።" ይለዋል። በዚህ አገባብ አማርኛው "ባሪያይቱ" የሚለውን ግዕዙ "አመት" ይላታል።
✔ ወንዶች ባሪያዎችን "አግብርት" ሲላቸው ሴቶች ባሪያዎችን ደግሞ "አእማት" ይላቸዋል። [ዘፍ.32፥5 ግዕዙን ንባብ ተመልከት]
♦ ዓመት የሚለው ደግሞ በብዙ ቁጥር "ዓመታት" ሲባል ዘመን፥ ዘመናት፥ ብዙ ቀን፥ የዕለታት ድምር ማለት ነው። "በባቢሎን ንጉሥ በብልጣሶር በመጀመሪያው ዓመት" ዳን.7፥1 የሚለውን ግዕዙ "በቀዳሚ ዓመተ መንግሥቱ።" ይለዋል። "የዕድሜህም ቁጥር ብዙ ነውና፥" ኢዮ.38፥21 የሚለውን ግዕዙ "ኊልቆ ዓመታቲከ፥" ይለዋል።
✍ ስለሆነም አንድ ሰው 'እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሰን' ሲል 'እንኳን ለአዲሷ ገረድ አደረሰን' አለ ማለት ነው። ይኼ ደሞ ጸያፍ ነው።
♦ "እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን" ሲል "እንኳን ለአዲሱ ዘመን አደረሰን ማለቱ ነው። ይኸውም የተገባ ነው።
✔ መልካም ምኞታችሁን የገለጻችሁ መስሏችሁ 'መልካም አዲስ አመት' አትበሉን!!!!!
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ

🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻
🌻🌻 አበባዩሽ 🌻🌻
🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻
እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ/2/
ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ
ደስ ደስ ይበላችሁ
ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን/2/
ጌታ አለ ብለን ደስ ብሎን
ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን/2/
ድንግል አለች ብለን ደስ ብሎን
አበባዮሽ ቅድስት/2/
ባለእንጀሮቼ ቅድስት
ቁሙ በተራ ›ቅድስት ›
በጎ ምግባርን ››ቅድስት
በእምነት እንሥራ ቅድስት ››
ዛሬ ነው ቀኑ ቅድስት ›
መመለሻችን ቅድስት ››
ይቅር እንዲለን ቅድስት ››
ቸሩ አምላካችን ቅድስት ››
አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ/2/
ድንግል ማርያምን ቅድስት
እንለምናት ቅድስት
ምሕረት የሚያሠጥ ቅድስት
ቃልኪዳን አላት ቅድስት
ጭንቀት ይርቃል ቅድስት
ይቀርባል ሰላም ቅድስት
ስሟ ሲጠራ ቅድስት
የድንግል ማርያም ቅድስት
አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ/2/
በሕገ ልቡና ጥንቱን
ፈጣሪን አውቀሸ ጥንቱን
ሕገ ነቢያት ከዓለም
ቀድመሽ ተቀበልሽ ከዓለም
በብሉይ ኪዳን ለጌታ
መሥዋእት አቀረብሽ ለጌታ
ተስፋ ካደረጉት ከአይሁድ
ከእስራኤል ቀድመሽ ከአይሁድ
ሕገ ወንጌልን በፊት
ይዘሽ ተገኘሽ በፊት
ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ጸጋ አለሽ/2/
ስለፈጸምሽ ሦስቱን ሕግጋት የፈጣሪሽን
ካለፈው ስህተት ሁላችን
እንድንመለስ ሁላችን
አዲሱ ዓመት ለሁሉ
መጣ ማቴዎስ ለሁሉ
ይህም ያልፍና በጊዜ
ይመጣል ማርቆስ በጊዜው
ሌላው ይተካል በጊዜው
ዘመነ ሉቃስ በጊዜው
ወልደ ነጎድጓድ በጊዜው
ሲደርስ ዮሐንስ በጊዜው
በየዓመቱ መጥምቁ
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁ
አደይ የብርሃን የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ አበራ2/
ኢትዮጵያ ባህል ቋንቋሽ የሚያኮራሽ/2/
ዘመኑ አልፎ ቅድስት
ሲሄድ ማቴዎስ ቅድስት
አዲሱ ዘመን ቅድስት
ሲመጣ ማርቆስ ቅድስት
እድሜን ጨምሮ ቅድስት
ለሠጠን ጤና ቅድስት
ለመድኀኔዓለም ቅድሰት
ይድረስ ምስጋና ቅድስት
አደይ የብርሃን ጮራ በማርቆስ በራ
እቴ አበባ እቴ አበባዬ አዬ ቅድስት እናቴ
እቴ አበባ ስትለኝ ከርማ አዬ ቅድስት እናቴ
መከረችኝ ደግማ ደጋግማ አዬ ቅድስት እናቴ
ቃሉን ሰማው አድምጥው ብላ እዬ ቅድስት እናቴ
አዬ ቅድስት እናቴ አዬ ቅ. እናቴ/2/
ይሸታል የእጣኑ ጢስ ሲታጠን ከመቅደሱ
በመላእክት ዜማ ካህናት ሲቀድሱ ሲታጠን ከመቅደሱ/2/
ከብረው ይቆዩን ከብርው
ከዓመት አውደ ዓመት ደርሰው
በእምነት በምግባር ጸንተው
ነጽተው ንስሓ ገብተው
ለሥጋ ወደሙ በቅተው
ከብረው ይቆዩ ከብረው
ከብረው ይቆዩ ከብረው
ከዓመት እከሰ ዓመት ደርሰው
ቅን ታዛዥ ልጅን ወልደው
ትኁት ሠው አክባሪ ሆነው
የፍቅርን ሸማ ለብሰው
ከብረው ይቆዩ ከብረው
አበባው ለምለም ቄጤማው ለምለም
ኢትዮጵያ እንዳንቺ የለም
አበባው ለምለም ቄጤማው ለምለም
ተዋሕዶ እንዳንቺ የለም
አበባው ለምለም ድንግል ማርያም
ያለአንቺ እመቤት የለም
🌻 @And_Haymanot 🌻
🌻 @And_Haymanot 🌻
🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻
🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻
፩ ኃይማኖት
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻 አበባዩሽ 🌻🌻
🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻
እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ/2/
ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ
ደስ ደስ ይበላችሁ
ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን/2/
ጌታ አለ ብለን ደስ ብሎን
ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን/2/
ድንግል አለች ብለን ደስ ብሎን
አበባዮሽ ቅድስት/2/
ባለእንጀሮቼ ቅድስት
ቁሙ በተራ ›ቅድስት ›
በጎ ምግባርን ››ቅድስት
በእምነት እንሥራ ቅድስት ››
ዛሬ ነው ቀኑ ቅድስት ›
መመለሻችን ቅድስት ››
ይቅር እንዲለን ቅድስት ››
ቸሩ አምላካችን ቅድስት ››
አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ/2/
ድንግል ማርያምን ቅድስት
እንለምናት ቅድስት
ምሕረት የሚያሠጥ ቅድስት
ቃልኪዳን አላት ቅድስት
ጭንቀት ይርቃል ቅድስት
ይቀርባል ሰላም ቅድስት
ስሟ ሲጠራ ቅድስት
የድንግል ማርያም ቅድስት
አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ/2/
በሕገ ልቡና ጥንቱን
ፈጣሪን አውቀሸ ጥንቱን
ሕገ ነቢያት ከዓለም
ቀድመሽ ተቀበልሽ ከዓለም
በብሉይ ኪዳን ለጌታ
መሥዋእት አቀረብሽ ለጌታ
ተስፋ ካደረጉት ከአይሁድ
ከእስራኤል ቀድመሽ ከአይሁድ
ሕገ ወንጌልን በፊት
ይዘሽ ተገኘሽ በፊት
ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ጸጋ አለሽ/2/
ስለፈጸምሽ ሦስቱን ሕግጋት የፈጣሪሽን
ካለፈው ስህተት ሁላችን
እንድንመለስ ሁላችን
አዲሱ ዓመት ለሁሉ
መጣ ማቴዎስ ለሁሉ
ይህም ያልፍና በጊዜ
ይመጣል ማርቆስ በጊዜው
ሌላው ይተካል በጊዜው
ዘመነ ሉቃስ በጊዜው
ወልደ ነጎድጓድ በጊዜው
ሲደርስ ዮሐንስ በጊዜው
በየዓመቱ መጥምቁ
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁ
አደይ የብርሃን የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ አበራ2/
ኢትዮጵያ ባህል ቋንቋሽ የሚያኮራሽ/2/
ዘመኑ አልፎ ቅድስት
ሲሄድ ማቴዎስ ቅድስት
አዲሱ ዘመን ቅድስት
ሲመጣ ማርቆስ ቅድስት
እድሜን ጨምሮ ቅድስት
ለሠጠን ጤና ቅድስት
ለመድኀኔዓለም ቅድሰት
ይድረስ ምስጋና ቅድስት
አደይ የብርሃን ጮራ በማርቆስ በራ
እቴ አበባ እቴ አበባዬ አዬ ቅድስት እናቴ
እቴ አበባ ስትለኝ ከርማ አዬ ቅድስት እናቴ
መከረችኝ ደግማ ደጋግማ አዬ ቅድስት እናቴ
ቃሉን ሰማው አድምጥው ብላ እዬ ቅድስት እናቴ
አዬ ቅድስት እናቴ አዬ ቅ. እናቴ/2/
ይሸታል የእጣኑ ጢስ ሲታጠን ከመቅደሱ
በመላእክት ዜማ ካህናት ሲቀድሱ ሲታጠን ከመቅደሱ/2/
ከብረው ይቆዩን ከብርው
ከዓመት አውደ ዓመት ደርሰው
በእምነት በምግባር ጸንተው
ነጽተው ንስሓ ገብተው
ለሥጋ ወደሙ በቅተው
ከብረው ይቆዩ ከብረው
ከብረው ይቆዩ ከብረው
ከዓመት እከሰ ዓመት ደርሰው
ቅን ታዛዥ ልጅን ወልደው
ትኁት ሠው አክባሪ ሆነው
የፍቅርን ሸማ ለብሰው
ከብረው ይቆዩ ከብረው
አበባው ለምለም ቄጤማው ለምለም
ኢትዮጵያ እንዳንቺ የለም
አበባው ለምለም ቄጤማው ለምለም
ተዋሕዶ እንዳንቺ የለም
አበባው ለምለም ድንግል ማርያም
ያለአንቺ እመቤት የለም
🌻 @And_Haymanot 🌻
🌻 @And_Haymanot 🌻
🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻
🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻
፩ ኃይማኖት
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
☞ መፅሀፈ ሄኖክ
@And_Haymanot
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት፣ታሪካዊትና ብሄራዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን በአለም ከምትታወቅባቸው አበይት መገለጫዎች ውስጥ በዋቢነት
የሚጠቀሱት በጥንታውያን ብሄራዊው ሊቃውንት ሲወርድ ሲዋረድ ተጠብቀው የቆዩት መፅሀፍቶቿ ዋነኛ ናቸው ከእነርሱም ውስጥ በአለም ላይ እስካሁን የሌለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ተጠብቆ የቆየው መፅሀፈ ሄኖክ አንዱ ነው ፈረንጆቹ በ18ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ቤታችን መተው እስኪዘርፉን ድረስ ስለ መፅሀፉ ሙሉ እውቀት አልነበራቸውም ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል እንዲሉ እኛ አንቀላፍተን እነርሱ ነቅተው የወሰዱትን ምስጢር እየበረበሩት ይገኛል በየአመቱ የበቁ ሊቃውንት የሚባሉ እስከ 250 የሚደርሱ በቫቲካን በመፅሀፈ ሄኖክ
ላይ ጉባኤ ይቀመጣሉ የመገኛዋ ምድር ኢትዮጵያ ያላት ተወካይ አንድ ብቻ ነው ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የመፅሀፉ ሙሉ ባለቤት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን በጉባኤው ላይ ሰው የላትም እንዲ ጉባኤ የሚሰየምለት መፅሀፈ ሄኖክ ብዙ ይባልለታል እንዲያውም የአውሮፓ ህዳሴ ስኬት የመፅሀፈ ሄኖክን ምስጢር ፈረንጆቹ መፍታታቸው ዋነኛ ምክንያት ነው የሚሉ አሉ ለዚህም በህዳሴው
ዘመን በ18ኛው መቶ ክ/ዘመን ከእኛ ከመሰረቁ ጋር ያያይዙታል ከውጪ በብዙ ብር የምንገዛቸው መድሀኒቶች እራሱ ከመፅሀፉ የተቀዱ እውቀቶች ውጤት ናቸው ይባላል በምእራቡ አለም በተለይ አሁን አሁን መፅሀፈ ሄኖክ ስሙ እጅግ ከበዙ ግኝቶችና ምርምሮች ጋር ይነሳል እንዲያውም ሳይንስ ከገደበው የምድራችን እውቀትም በላይ ይጠቀሙበታል ይባላል ይህን ሁሉ ከውጪ ብንሰማም በሀገር ቤት ግን ምንም የማይባልለት ነውና ለመሆኑ
መፅሀፈ ሄኖክ ምንድነው? ሄኖክስ ማነው? ብለን ጥያቄ እናነሳለን ሄኖክ ማለት ተሀድሶ ማለት ነው (የእናት ጡት ነካሾች የተሀድሶ መናፍቃንን ለመጥቀስ አይደለም) አዳም በምግብ ምክንያት
ብልየትን እንዳመጣ ሄኖክም ከምግብ ተከልክሎ ተሀድሶን አምጥቷልና አንድም ዛሬ በብሉይ ስጋ ገነት እንደገባ እኛም
በሁዋላ ተነስተን በሀዲስ ስጋ መንግስተ ሰማያት እንገባለንና
(ምንጭ፦ መፅሀፈ ሄኖክ አንድምታ ገፅ 1) ሄኖክ የያሬድ ልጅ ነው ልደቱን ወይም የዘር ሀረጉን ስንቆጥር አዳም ሴትን ይወልዳል ሴት ደሞ ሄኖስን ሄኖስ ቃይናንን ይወልዳል ቃይናን ደሞ መላልኤልን መላልኤል ያሬድን ይወልዳል ያሬድ ደሞ ሄኖክን ዘፍ 5:1-22 ሄኖክ የአዳም ሰባተኛ ትውልድ ነው
ስድስተኛው ትውልድ ያሬድ ሄኖክን ወልዶ ሄኖክ ደሞ ከሚስቱ ከእድኒ ማቱሳላን ይወልዳል ሄኖክ ባለ ዘመኑ ሁሉ በፍፁም እምነት እግዚአብሄርን እያገለገለ በምድር ላይ ለ 365 አመት ኖሯል ስለዚህ እንደ መፅሀፍ ቅዱስ አገላለፅ ዘፍ 5:24ላይ ሄኖክም
አካሄዱን ከእግዚአብሄር ጋር ስላደረገ አልተገኘም እግዚአብሄር ወስዶታልና ይላል ስለዚህ ሄኖክ ሞትን ሳይቀምስ ተሰውሮ ወይም ተወስዶ ሄዶዋል ማለት ነው በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ኤሊያስም
ቢያርግ የሄኖክ ግን ይለያል ምክንያቱም ሄኖክ ፓትራሪክ ነው ከጥፋት ውሀ በፊት የነበረ ሰው ነው በዛ ጊዜ የሰው ልጅ በክፋት በነበረበት ጊዜ ሄኖክ ሞትን ሳይቀምስ የጥንት በደል ወይም ምልሀተ ሀጢያት ሳይነካው ሞትን ሳያይ ሄዱዋልና። መፅሀፈ ሄኖክ አምላካዊ ከሚባሉ የመፅሀፍ ቅዱስ ቁጥሮች
በተለይም በኢ/ኦ/ተ//ቤ/ክን በ81 አሀዱ ላይ ያለ ነው አንድ መፅሀፍ አምላካዊ መፅሀፍ ለመባል በትንሹ 5ቱ አእማደ ምስጢርንና 7ቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ማካተት አለበት መፅሀፈ ሄኖክም እነዚን በሚገባ አካቶ ይዟል መፅሀፈ ሄኖክ በትንቢት፣ በታሪክም በተለያየ ገፅታው ጠቃሚ ነው ስለዚህ
አምላካዊ መፅሀፍ ነው በትንፋሰ እግዚአብሄር የተፃፈ ለራሱ ለሄኖክ የተገለፀ ነው የመጀመሪያ ፊደላት መገኘትና ሰማያዊ ምስጢር መገለፅ ጋር ተያይዞ ለሄኖክ የተገለፀለትን ነገር መፅሀፈ ሄኖክ ብለን የምንጠራው ውስጥ አካቶታል ለሄኖክ ጥበብን
በተመለከተ ስለ ፅሁፍ ጥበብ፣ ስለ ስነ-ፈለግ ጥበብ፣ ስለ ክዋክብት፣ ስለ ፀሀይ፣ ስለ ጨረቃ፣ ስለ ወር ስለ ንፋሳት... የመሳሰሉት ሀሳቦች ተገልፀውለት ለመጀመሪያ ጊዜ የጥበብ ሰው ሆኖ የተቀመጠ እንደሆነ በመፅሀፉ ሀሳብ ላይ እናገኘዋለን ከእርሱ
በፊትም ሆነ በሁዋላ እርሱ ያገኘውን ጥበብ ማንም ሰው እንዳላገኘ በራሱ ቃል ምስክርነት ሰጥቷል እንግዲህ እኔ ያየሁትን ራእይ እኔ ያየሁትን ግልፀት ከጥበብ፣ ከእውቀት ጋር በተገናኘ እኔ
እንዳየሁት ማንም አላየም ከሰውም የሚያየው የለም የሚል ሀሳብ
ተፅፎ እናገኛለን።
በመፅሀፈ ሄኖክ ላይ የበቃ እውቀት አለን የሚሉ እንኩዋን በብዙ ጉዳዮች ላይ ይከራከራሉ ከዛም በላይ ግምታዊ ትንታኔ የሚያበዙ ናቸው ከእዚህም አንዱ ሌላው ቀርቶ በፀሀፊው ማንነት ላይ
ጭምር ያለ መስማማታቸው ነው የአዳም ሰባተኛ ትውልድ ሄኖክ
በመላእክት ተመንጥቆ እንደፃፈው የሚስማሙ አሉ ሄኖክ ደሞ የማቱሳላ አባት የኖህ ደሞ ቅድመ አያት ነው እነዚህ ሄኖክ በፈጣሪ በጎ ፍቃድ በመላእክት እርዳታ የተገለፀለትን እውቀት ነው የፃፈው ሲሉ በሌላ ወገን ደግሞ መፅሀፉ በተለያየ ዘመን ተፅፏል
የሚሉም አልታጡም ለዚህም የሚያቀርቡት ምክንያት እየተጨመሩ
የመጡ ምእራፎች አሉ የሚል ነው እነዚህ ወገኖች በቀዳሚነት የሚጠቅሱት ስለመላእክት የሚናገረው ክፍል በቅ/ል/ክ 200 ተፅፏል ሲሉ ተጨመረ የሚሏቸው ደግሞ በአመተ ምህረት
የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ተፅፏል ይላሉ ከፀሀፊው ማንነት ሌላ ተፃፈ የሚሉበት ክፍለ ዘመን ጭምር አንዱ ልዩነታቸው መሆኑን ያሳያል እንዲ ሊቃውንቱ የሚነታረኩበት እስከ አሁን 3 የሚታወቁ መፅሀፈ ሄኖክ አሉ
1ኛው፦ One Henok የሚባለው አምስት ክፍል ያለው በእኛ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ሙሉ እውቅና ያለው ሄኖክ እራሱ እንደፃፈው የሚታመንለት ነው
2ኛው፦ Two Henok ና ስላቨኒክ ሄኖክ የሚባለው ነው በይዘቱ ከግእዙ ሄኖክ(One Henok) የሚለይ መፅሀፍ ነው በስላቪክ ቋንቋ ተፅፎ ተገኝቷል መፅሀፉን ያገኘው ፕ/ር ሶክሎፍ የሚባል ሰው ነው በቤልግሬድ የህዝብ ቤተ መዛግብት ውስጥ ነው ያገኘው አጥኚዎች እንደሚሉት ከግሪክ የተተረጎመ እንዳልሆነ መላምት ይሰጣሉ ይሄ መፅሀፈ ሄኖክ ጎዶሎ ነው
3ኛው፦ Three Henok ተብሎ የሚታወቀው ነው በእብራይስጥ ቋንቋ ነው ተፅፎ የተገኘው ይህ በብዙ አጥኚዎች ቀልብ ሊስብ ያልቻለ መፅሀፍ ነው ምክንያቱም አንደኛ ነገር መፅሀፉ ላይ እራቢ እሽማኤል የተባለ ሰው ከክ/ል/በሁዋላ በ164 አ/ም አካባቢ
እንደፃፈው ይናገራል ስለዚህ ሄኖክ መፅሀፈ ሄኖክን ከፃፈ በሁዋላ የተፃፈ መፅሀፍ ነው ተብሎ ስለሚታመን ትክክለኛውን ለማግኘት ይረዳል ብለው አጥኚዎች ስለማያምኑ ለጥናታቸው መሰረት ያደረጉት መፅሀፈ ሄኖክ አንድ ላይ ወይም የኢትዮጵያው ሄኖክ ላይ
ነው።
የኢትዮጵያው መፅሀፈ ሄኖክ በ5 ክፍል ይከፈላል። እርሱም፦
1ኛው ክፍል ፦ ስለ መላእክት ውድቀት የሚተርከው ክፍል ነው ይሄውም ከምእራፍ1-36 ያለው ክፍል ነው
2ኛው ክፍል፦ ስለ መፅሀፈ ምሳሌ ነው የሚናገረው ይሄውም ከምእራፍ37-71 ያለው ክፍል ነው ስለ አዳም፣ ስለ ሄዋን፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ሙክራብ ስለተለያዩ ነገሮች በምሳሌ እያደረገ
የሚናገርበት ክፍል ነው
3ኛው ክፍል፦ ስለ ቀን አቆጣጠር(Calendar) የሚተርክበት ክፍል ነው ይሄውም ከምእራፍ72-82 ያለው ሀሳብ ነው
4ኛው ክፍል፦ ራእይ ሄኖክ ይባላል ይህ ክፍል ለሄኖክ በእግዚአብሄር ገላጭነት በመላእክት እየተመራ ያየውን ራእይ
የሚናገርበት ክፍል ነው..... 👇👇👇

መፅሀፈ ሄኖክ
👆👆👆...5ኛ ክፍል፦ መልዕክተ ሄኖክ ወይም የሄኖክ መልእክት ይባላል ለልጁ ለማቱሳላ ማቱሳላ ደግሞ ከእርሱ በሁዋላ ለሚመጡት ለትውልዶቹ እንዲያስተላልፍ የፃፈለት መልእክት ነው
ስለዚህ ሙሉ የሆነውና ትክክለኛው የሄኖክ መፅሀፍን በተመለከተ
ታማኝ የሆነው የኢትዮጵያው መፅሀፈ ሄኖክ እንደሆነ ብዙ ሊቃውንት ይስማማሉ ለዚህም ነው ምስጢሩን ለመፍታት ጉባኤ እየተቀመጡ የሚመካከሩበት።
ይቀጥላል
ወስብሀት ለእግዚአብሄር