፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
Channel name was changed to «፩ ኃይማኖት»
ከሞት በኋላ ያለ ህይወትና የፕሮቴስታንት አስተሳሰብ፡፡

@And_Haymanot

ከሞት በኋላ ስላለ ህይወትና በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳን ምልጃን በተመለከተ ለፕሮቴስታንት ወገኖች ማስረዳት ብንሞክር ጥቅስ የሚል ጥያቄ ይከተላል፡፡ ከዚያ ጥቅሱን ማሳየት ሲጀመር ላለመረታት ስለጥቅሶቹ የተሳሳተ ትርጉም መስጠት ወይም
አልቀበልም ወደ ማለት ይኬዳል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በሰጠን ህሊና ነገሩን ማገናዘብ ከጥቅስ ያለፈ ተጨማሪ
ማስተዋል ነውና እንካችሁ፡፡ በውኑ በአጸደ ነፍስ ሆኖ ማማለድ? አለ ወይስ የለም?
የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት ቀድሞ መጠየቅ ያለበት የሞት ትርጉምና ከሞት በኋላ ስላለው ሚና ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስለቅዱሳን ያላትን አስተምህሮና እምነት ለመቃወም ብቻ በተሳሳተ መነሻ ላይ ቆሞ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ መድረስ ራስን እንጂ ሌላ ማንንም አይጎዳም፡፡

ሞት ምንድነው? ከሞት በኋላ ያለንስ ሚና?
👉 #ፕሮቴስታንት ፡- ሞት ከምድራዊ ቤተክርስቲያንና ህብረት ፍጹም መለየት ነው፡፡ ከሞት በኋላ አንድ የፕሮቴስታንት አማኝ በምድር ስላለች ቤተክርስቲያንና አማኞች በፍጹም አይመለከተውም፡፡
ምንም ጥያቄ አያነሳም፡፡ አይጸልይምም፡፡ በሞት ምክንያት በሰማይ ያሉ የፕሮቴስታንት አማኞች ከምድራውያኑ ጋር የነበራቸው የግንኙነት ድልድይ ይቋረጣል፡፡ ሞት ፍጹም ወደ ሌላ የማይታወቅ አለም መሔድና በምድር ካለው ሕይወት መለየት
ነው፡፡ በምድር ስላለው ነገር በፍጹም ማወቅ አይችሉም፡፡ ቢችሉም ምንም ሚና የላቸውም፤ በምድር ካለች ቤተክርስቲያን ጋር በፍጹም ይቆራረጣሉ፤ በምድር ያሉትም እንዲሁ የሞቱ ፕሮቴስታንቶችን ፍጹም በሆነ መለየት ይለይዋቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ምንም ግንኙነት የለም፡፡ እንደ አለማውያን ሻማ
ከማብራት፣ ሐውልት ከመስራት ያለፈ ሌላ ነገር የለም፤ መንፈሳዊ ግንኙነቱ ፍጹም በሆነ ሁኔታ ይቋረጣል፡፡
👉 #ኦርቶዶክስ ፡- ሞት የቦታ ለውጥ እንጂ የግንኙነት መቋጫ አይደለም፡፡ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሞት ምክንያት በአጸደ ነፍስ ያሉና በምድር ያለች ቤተክርስቲያን ግንኙነት አይቋረጥም፡፡ እለት እለት ስለአብያተ ክርስቲያናት የሚያስጨንቃቸው
ክርስቲያኖች በስጋ ሲሞቱ፣ ወደ ናፍቆታቸው ወደ ክርስቶስ ሲሔዱ፤ በገነት ሲኖሩ እነርሱ ያዩትን ደስታ፣ ያገኙትን አክሊል፤ በምድር ያሉ ክርስቲያኖችም እንዲያገኙ የበለጠ ይናፍቃሉ፡፡ በምድር ሆነው የራሳቸውንም እድል ፈንታ ባላወቁበት ሁኔታ ስለሌላው ይለምኑ የነበሩ አሁን የናፈቁትን ሲያገኙ ያን ምህረትና ጽድቅ በምድር ያለነውም እንድናገኝ የበለጠ ይተጋሉ፡፡ ልዩነቱ
ቀድሞ በድካምና በትህትና ሆነው ይለምኑ ነበር፤ አሁን ግን ተሸልመዋልና በስልጣን ይለምናሉ፡፡ ቀድሞ የስጋ ድካምና ፈተና ነበረባቸው፣ አሁን ግን ከዚህ ነጻ በመሆናቸው ያለድካም ፍጹም
በሆነ ትጋት እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፤ ስለምድራዊቱም ቤተክርስቲያን ይለምናሉ፡፡
ስለሞትና ከሞት በኋላ ስላለን ሚና በምድር ያለን ኦርቶዶክሳውያንና ፕሮቱስታንቶች እንዲ ባለ ጽንፍ ተለያይተናል፡፡ ፕሮቴስታንቶች ስለሞቱ ወገኖቻቸው የሚሰጡት ትርጉምና ሚና
ኦርቶዶክሳውያን ስለሞቱና በሲኦል ካሉ ነፍሳት እንኳን ያነሰ ነው፡፡ በገነት በጽድቅ ያሉ ቅዱሳን ይቅርና በሲኦል ያሉ ነፍሳት እንኳን ቢሆኑ በዚያ ጽኑ መከራ ሆነው፣ በምድር በኃጢያት ስላለ ስለሚያውቁት ነፍስ ይገዳቸዋል፡፡ ራሳቸውን ማዳን ባይችሉ እንኳን እንደ ነዌ ያለ ልመና ማቅረብ አያቅታቸውምም፡፡ ነዌ
ስለራሱ ውኃ ለምኖ እንደማይቻል ሲረዳ ወዲያው በምድር ያሉ አምስት ወንድሞቹ ትዝ አሉት፡፡ እነርሱ ባለማወቅ ወደዚህ
መከራ እንዳይመጡ ናፈቀ፤ አብርሐምንም ለመነው፡፡ በሲኦል
ሆኖ እንዲህ ስለሌላ ሰው መጨነቅና፣ መለመን ከተቻለ በገነት ሆኖ ቢያንስ የነዌን ያህል እንኳን መጨነቅ፣ መለመን የለም ተብሎ እንዴት ይታሰባል? አንድ ፕሮቴስታንት ከሞትኩ በኋላ ገነትም ብገባ ሲኦልም ብገባ፣ በምድር ስላለችው ቤተክርስቲያን ቢያንስ እንደነዌ ወንድሞቼ ብዬ መጨነቅ፣ መለመን አልችልም ብሎ መደምደም እንዴት ያለ አስተሳሰብ ነው?
ፕሮቴስታንቶች ስለ ሞቱ ወገኖቻቸው የሚሰጡት ትርጉምና ሚና፤ በኛ በኦርቶዶክስሳውያን ዘንድ በገነት ካሉት ቅዱሳን ጋር ሳይሆን በሲኦል ካሉ ኃጥአን ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ኧረ እንዲያውም ያንሳል፡፡ እኛ በገነት ያሉ ቅዱሳን ይቅርና በሲኦል ያሉ ኃጥአን እንኳን በምድር ስላሉ ወንድሞቻቸው ሊጨነቁ፣
ሊለምኑ ይችላሉ እንላለን፡፡ ፕሮቴስታንት ግን ገነት ብንገባ እንኳን እንዲህ አናደርግም፤ በምድር ስላለች ቤተክርስቲያን አንለምንም ብለው ያምናሉ፡፡ የትኛውንም አስተሳሰብና እምነት ማራመድ ይቻላል፡፡ በአስተሳሰባችንና እምነታችን መካከል ግን የዚህን ያህል ልዩነት አለ፡፡ ከራሱ ህይወት ይልቅ ዕለት ዕለት ስለአብያተ ክርስቲያናት ሲጨነቅ የኖረው ቅዱስ ጳውሎስ አክሊል ሲሸለም፣ በገነት ሲሆን፣ ሲጸድቅ፣ ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልሆን እናፍቃለው እንዳለ፣ የሚናፍቀውን ካገኘ በኋላ በምድር ያለነውም ይህንን ክብር እንድናይ፣ የበለጠ ይተጋል፣ ይለምናል፣ እንደ ቀድሞ በትህትናና በድካም ሳይሆን በክብርና በስልጣን
ሆኖ ያለድካም ይተጋል እንጂ፣ ሁሉን እርግፍ አድርጎ ይተወዋል፤ አያገባውም ብሎ ማመን ምን ዓይነት የዋህነት ነው፡፡ ምንስ የሚሉት የመንፈሳዊ ህይወት ብስለት ማጣት ነው፡፡ የፕሮቴስታንት አገልጋይ የነበሩ ግን ከሞቱ በኋላ ፍጹም በሆነ ሁኔታ በምድር ካሉ ወንድሞቻቸው ይለያሉ፡፡ ምድራውያኑም ስለሞቱት ሻማ ከማብራትና ሐውልት ከማሰራት ያለፈ ምንም መንፈሳዊ ግንኙነት የላቸውም፡፡ ስለሆነም ኦርቶዶክሳውያን ስለዚህ ስናስብ የሞቱ ፕሮቴስታንቶች ግን ምን ነካቸው? እንዲህስ ሊሆኑ የሚችሉት የት ቢገቡ ነው? የሚል ጥያቄ ይፈጠርብናል፣ ክርስቶስ ራስ ሆኖ የመሰረታት ቤተክርስቲያንስ
በሞት ምክንያትስ እንዴት እንዲህ ትሆናለች?
በዲ/ን ሸዋፈራው አለነ
Join
👉 @And_Haymanot
👉 @And_Haymanot
እባካችሁ አድርሱልኝ:-
ትዝብት 1:- መንፈሳዊ ግሩፖች ላይ አላስፈላጊ ነገሮች ሢለጠፉ(post ሲደረጉ) እናሥተውላለን ይህ ግሩፕ የከፈቱ አድሚኖች ሀላፊነት ቢሆንም አንዳንዶቹ ብዙም የማይገቡና የማይቆጣጠሩ አሉ እናም ተጨማሪ አድሚኖችን ቢያሠሩ መልካም ይመሥለኛል፡፡
2 ሌላው ብዙዎቻችን ባለማሥተዋል ጥሩ መልዕክቶችን ወደ ግሩፖች ሼር በምናደርግበት ጊዜ ምንጫቸውን ብንለይ ... አንዳንድ የመናፍቃንን የማሥታወቅያ ሊንክ የያዙ ጥሩ የሚመሥሉ ፅሑፎችን ሼር ባናደርግ፡፡ ምክንያቱም የነሱን ቻናልና ግሩፕ በሌላ በኩል እያሥተዋወቅንም ጭምር ነውና በማሥተዋል ይሁን ለማለት እወዳለው
3 አድሚኖች የከፈቱበትን አላማ ባይዘነጉ መልካም ነው፡፡ ብዙ ግሩፖች ውይይት አይደረግባቸውም... ምንም ሥራ ሳይሠሩ አባላትን ብቻ ይዘው የተቀመጡ አሉና ይሥሩበት ለማለት እወዳለው፡፡
እግዚአብሔር ያክብርልኝ በርቱ!!
ፀዳለ ማርያም
~~~~~~~~~~~~
ጥሩ ዕይታ ሥለሆነ አቅርበነዋል በዚህ አጋጣሚ ጥሩ የሚሠሩትን ለማመሥገን እንወዳለን ሌሎቻችሁም ሐሳባችሁን አድርሱን
👉 @AHati_Haymanot
እንዲሁም ባለመመቻቸት ግሩፓችሁን መቆጣጠር ያልቻላችሁ አድሚኖችም ተጨማሪ አድሚን ማሠራት ከፈለጋችሁ አናግሩን ሌሎች አድሚኖችን እናገናኛችኋለን፡፡
ወንጌል አይከደን ለአንዲት ተዋህዶ በአንድነት እንሰራለን
@And_Haymanot
ወደ ግሩፖች ሼር በማድረግ ለውጥ እንፍጠር፡፡
@And_Haymanot
"የቅዱስ ጳውሎስ ተፈጥሮ ከእኛ ተፈጥሮ የተለየ አልነበረም፡፡
@And_Haymanot
ነፍሱ ከእኛ ነፍስ የተለየ ተፈጥሮ አልነበራትም፡፡ በዚህ እኛ በምንኖርበት ምድር እንጂ በሌላ ዓለም የሚኖር አልነበረም፡፡ ይኖር የነበረው እኛ በምንኖርበት ተመሳሳይ ዓለም፣ በተመሳሳይ አገር፣ በተመሳሳይ ሕግና ባሕል ቢኾንም ቅሉ፥ እርሱ ግን ከዚህ
በፊት ከነበሩትም፣ አሁን ካሉትም ሰዎች ኹሉ የከበረ የገነነ ነው፡፡ “ቀላሉ ክፉ ምግባርን መሥራት ነው እንጂ ምግባር
ትሩፋት መሥራትስ እጅግ ከባድ ነው” ብለው የሚቃወሙት አሁን ወዴት አሉ? ይህ ቅዱስ ሰው የእነዚህን ሰዎች ስሕተት፡- “የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የኾነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘለዓለም ብዛት ከኹሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናል” በማለት በቃሉ ያፈራርስባቸዋል (2ኛ
ቆሮ.4፡17)፡፡ ተመልከቱ! ቅዱስ ጳውሎስ የተቀበላቸው መከራዎች ቀላል ከኾኑ፥ እርሱ ከተቀበላቸው አንጻር ሲታዩ ተድላና ደስታ የኾኑት የእኛ’ማ እንዴት?
እጅግ የሚያስደንቀው ግን፥ ከመጠን በላይ ቀናኢ ከመኾኑ የተነሣ በጎ ነገርን ሲሠራ ይደርስበት የነበረውን መከራ እንደ ቀላል ማየቱ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም ቅዱስ ጳውሎስ (ለበጎ
ምግባሩ) ዋጋ የማያገኝበት ቢሆን እንኳን ምግባራትን ለመፈጸም ወደ ኋላ የማይል መሆኑ ነው፡፡ ከቅንዓቱ በስተጀርባ የሚያስበው ምንም አሳብ የለውም ነበር፡፡ እኛ “የክብር አክሊል ይሰጣችኋል” ተብለን እንኳን ቀናዕያን
ለመኾን ዳተኞች ነን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን የክብር አክሊል ባይቀበልበትም እንኳን ምግባራትን ለመፈጸም ይፋጠን ነበር፡፡ ምግባር ትሩፋት በሚሠራበት መንገድ ላይ የትኛውም ዓይነት መከራ ቢያገኘውም እንኳን በትሕትና ይቀበለው ዘንድ ይታገሥ ነበር፡፡ በሰውነቱ ድካም፣ ወይም በሌሎች ሰዎች ተጽዕኖ፣ ወይም
በልማድ ጫና፣ ወይም ይህን በመሰለ በሌላ ነገር ምንም ምን አያመካኝም ነበር፡፡ “እነዚህ ችግሮች ስላሉበኝ” ብሎ
አላመካኘም እንጂ ኃላፊነቶቹ ግን ከወታደር አለቆች ወይም ከምድራውያን ነገሥታት እጅግ የሚልቁ ነበሩ፡፡
እነዚህ ኹሉ ተደራራቢ ኃላፊነቶች፣ በእነርሱ መጠንም መከራዎች የነበሩበት ቢኾንም እንኳን ዕለት ዕለት በምግባር
ያድግ ነበር፡፡ ለቅዱስ ጳውሎስ የመከራ ብዛት ማለት የትጋት መጨመሪያ መሣሪያ ብቻ ነበሩና፡፡ እርሱ ራሱም ከዚህ በላይ የኾነውን፡- “ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ” በማለት ነግሮናል (ፊልጵ.3፡13)፡፡ እስከ ሞት በሚያደርስ መከራ ውስጥ ኾኖ
[ነገር ግን ደስተኛ ነው]፥ ሌሎች ሰዎችንም የደስታው ተሳታፊዎች ይኾኑ ዘንድ እንዲህ በማለት ይጠራቸው ነበር፡- “እናንተም ደግሞ እንዲሁ ደስ ይበላችሁ፥ ከእኔም ጋር አብራችሁ ደስ ይበላችሁ” (ፊልጵ.2፡18)፡፡ እርሱም በእያንዳንዷ በምትደርስበት መከራ፣ ጉዳትና እንግልት ሐሴት ያደርግ ነበር፡፡
ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው መልእክቱ ላይ፡- “ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም
በጭንቀትም ደስ ይለኛል” ብሏል (2ኛ ቆሮ.12፡10)፡፡ [መከራዎች] የበጎ ነገር ኹሉ ምንጭ መኾናቸውንና እርሱም
በጠላቶቹ አይበገሬ መንፈሳዊ አርበኛ እንደ ኾነ በማሳየት እነዚህ የፍትሕ መሣሪያዎች መኾናቸውን ተናግሯል፡፡
ቢደበድቡትም፣ ቢያንገላቱትም፣ እጅግም ቢሰድቡት በድል ሰልፍ ላይ እንዳለ ኾኖ፥ ገና በዚህ ምድር እያለ ብዙ የድል አክሊላትን ተቀዳጅቷል፤ ደስ ተሰኝቷል፤ “ነገር ግን በክርስቶስ ኹልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ኹሉ የዕውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይኹን” በማለትም እግዚአብሔርን አመስግኗል (2ኛ ቆሮ.2፡14)፡፡ ቃለ እግዚአብሔርን ስለማስተማር ንቀትን ውርደትንም በመቀበሉ ደስ ይሰኝ ነበር፡፡ እኛ በሕይወት ደስ እንደምንሰኝ እርሱ በሞት
(በመከራ)፣ እኛ በማግኘት ደስ እንደሚለን እርሱ በማጣት፣ እኛ
ከልክ በላይ በኾነ በዕረፍት ሐሴት እንደምናደርግ እርሱ በድካም
በጥረትም፣ እኛ በደስታ እንደምንፍነከነክ እርሱ በኀዘን፣ እኛ በጠላቶቻችን ስንነሣሣ እንደምንረካ እርሱ ግን ለጠላቶቹ በመጸለይ ተድላ ደስታ የሚያደርግ ነበር፡፡
© ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ውዳሴ ጳውሎስ፣ ድርሳን ፪
@And_Haymanot
​​ጴጥሮስ ተሰቀለ ጳውሎስ ተሰየፈ
ተዋሕዶ እያለ ኧረ ስንቱ አለፈ
ሌሎችም በእሳት በስቃይ አልፈዋል
ዘመን የማይሽረው ታሪክን ጽፈዋል
🙏እንኳን አደረሳችሁ!🙏
@And_Haymanot
Channel photo updated
​​ሥላሴን አመስግኑት

ሥላሴን አመስግኑ (2) 
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ 
ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት 
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ 
ምስጋና ይገባል ጠዋትና ማታ 

ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት 
መላእክት በሰማይ የሚዘምሩለት 
እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን 
በሰማይም በምድር እንጠራሃለን 

ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ 
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ 
ሥላሴ አምባዬ ክብሬም ናቸውና 
ሁሌ ይመሩኛል በሕይወት ጎዳና 
👉 https://tttttt.me/Konobyos/29
ወቅታዊ ትምህርት በ ቴሌግራም አጠቃቀማችን እንዲሁም የተለያዩ የእምነት አመለካከቶችን ወንድማችን ገልፆታል አድምጡት
@And_Haymanot
“ፀሎትንና ምልጃን አቀረበ” ዕብ.5:7 ሲል ምን ማለቱ ነው?

እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፡ ይህ ምን ማለት ነው?
.
ይህ ጥቅስ በማያሻማ ሁኔታ የተገለፀው ነገረ ስጋዌ(እስከ መስቀል ድረስ)ነው፡፡ ጌታችን ሊቀ ካህናት ተብሎ ነበርና በስጋው ወራት እንደ ካህናተ ኦሪት የበግና የፍየል ደም ያቀረበ አይደለም፡፡ ይልቁንም ፀሎትን እንደላም ልመናንም እንደበግ አድርጎ አቀረበ፡፡ አንድ ጊዜም ስለሆነ ያቀረበው ግዳጅ የሚፈፀም መሆኑን ሲያጠይቅ “ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ” አቀረበ አለ፡፡ “ከሞት ሊያድነው ወደሚችል” ሲልም ሰው ሁሉ በአንድ አዳም እንደሞተና በጌታም በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በኩል እንደዳነ ስለምእመናን በጌታችን መናገሩ ነው፡፡
“እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት” የሚለው “ወልድ” “በኩር” ሆኖ ሳለ አምላክነት ገንዘቡ ሆኖ ሳለ ፍፁም ሰው በመሆኑ ስለአዳም ያቀረበው ቁርጥ ልመናው ተሰማለት አምላክ ነኝ ልፅልይ አይገባኝም ሳይል ሰው በመሆኑ ታዝዟልና፡፡ ስለመታዘዙም እግዚአብሄርን ስለመፍራቱ ቢል አንድ ነው፡ በአዳም ተገብቶ ነው እንጂ ጌታችን ከመከራ መስቀል በኋላ የሚያማልድ ሆኖ አይደለም፡፡.... ይቆየን
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ከጋብቻ በኋላ ግንኙነት የሚከለከለው ለስንት ቀን ነው?

ቤተክርስቲያን አስተምሮ ተክሊል እና ሰርግ የተለያዩ ናቸው። ተክሊል ጋብቻው ሲሆን ስርጉ ደግሞ የተክሊሉ በዓል ነው። በቀደመው የቤተክርስቲያን ትውፊትም ተክሊል ሰርግ በአንድ ቀን አይፈጸሙም ነበር። ቤተክርስቲያን ተጋቢዎች ከጋብቻ /ተክሊል በኃላ ለ40 (አርባ) ቀናት በጾምና በሱባዔ ቆይተው ሰርግ ማድረግ አለባቸው የሚል ትውፊት አላቸው።

የፍትሐ ነገስት አንቀጽ 24 ትርጓሜም በጋብቻ ጊዜ የሚደረገው ሥርዓት ከዘረዘረ በኃላ እሱ ከአባቱ እሷም ከእናቷ ጋር ሲተኙ ይሰነብታሉ ፥ ቊርባኑን በሚሹበት ጊዜ እየሔዱ ይቆርባሉ አርባው ቀን ሲፈጸምም ሰርጉ ያደርጉላቸዋል ፤ ይላል ሙሹሮች ተክሊል ተፈጽሞላቸው ፤አሰቀድሞ ቆርበው ከወጡ በኋላ ወደየቤታቸው ይሔዳሉ ቢል እሱ ከአባቱ ጋር ሴቷም ከእናቷ ጋር የእየተኙ ለአርባ ቀናት ይቆያሉ።

ይህስ ከጋብቻ በኃላ ተለያይቶ መኖር አይገባም ወደ ወንዱ ቤት ይሔዳሉ ብሎ እሱ ከአባቱ ጋር ፤ ሴቷም ከእናቷ ጋር ( ከእናቷ ጋር የሚለውን የሙሸራውን እናት ለሙሽራይቱ አደርጎ መናገር ነው) እየተኙ ይሰናበታሉ ማለት ነው። በአርባ ቀን ውስጥ ሙሽራው ቤተስብ የማሰተዳደርን ሥራ ከአባቱ፣ ሙሽራይቱ ልጅ ወልዶ የማሳደግን ተግባር ከእናቷ (ከሙሽራው እናት ) እየማሩ ፣በመከከሉ እየቆረቡ ይቆያሉ።

በአርባኛው ቀን ሰርግ ይደረግላቸዋል። ይኽውም ጌታ ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት ፣ ሕሙማን ነፍስን በትምህርቱ እየፈወስ ከቦታ ፣ ቦታ እየተዘዋወረ ከማሰተማሩ በፊት በገዳመ ቆሮንቶስ 40 ቀንና ፣40 ለሊት እንደጶም፤ ሐዋርያትም ይህን ዓለም ዕጣ በዕጣ ብለው ተከፋፊለው ወንጌልን ለማሰተማር ከመውጣታቸው በፊት 40 ቀናት እንደጾሙ አብነት በማድረግ ነው።

ሙሸሮች 40 (አርባ) ቀናት የሚለያዬበት ምክኒያት ጾም ጸሎት አድርጎ፤ ሥጋ ወደሙን ደጋግሞ ተቀብሎ ትዳርንና የሚወለደውን ልጅ ለማስባረክ ነው።

እንዲሁ አድርገው ተጋብተው የተወለደው ልጅ መንፈሳዊ ቢሆን እንደ እንጦስ እንደ መቃርስ ፣ ሥጋዊ ቢሆን እንደ ቆስጠንጢኖስ እንደ አኖሬዎስ ይሆናል ፣ እንዲል ፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ (24 ገጽ 323 ) ።

ሰርጉ ከተክሊሉ የመለየቱ አሰፈላጊነቱ ደግሞ ሥጋ ወደሙ ተቀብሎ ፎቶ ለመነሣት ከመንገላታት፣ በድካም ምክኒያት ከሙወጣው ላብ ለመጠበቅና ለቅዱስ ቊርባን ሊሰጠው የሚገባው ክብር ለመስጠት ነው። መለያየቱን ምክንያት በማድረግ ሰርጉን ፊጽሞ ዓለማዊ ማደረግ ፣ ከልብስ መራቆትና ዘፈን ግን ተገቢ አይዴልም ።

በስርጉ ዕለት ለክርስቲያን በተፈቀደው መጠን ማጌጥ ፤መደሰት ፤መብላትና መጠጣት አልተከለከለም። ለሌሎች ሕይውት ሓላፊነት ለመውሰድ የሚፈጽሙ ምሥጢራት በጾም በጸሎት ፈቃደ በእግዚአብሔር ሊጠየቅባቸው ይገባል።

ጋብቻ ደግሞ እንዲ የአንዱን ሸክም ለመሽከም፥ልጅ ወልዶ ለማሳደግ የሚገጥም ምሥጢር ሰለሆነ ተጋቢዎች ለአርባ ቀናት እግዚአብሔር ደጅ እየጠኑና እየተማጸኑ መቆየት ይገባቸዋል።

40 ቀን እስኪፈጸም በጾምና በሱባኤ የሚሰነብቱትም እንደ ፍትሐ ነገሥት ከወላጆቻቸው ጋር በመተኛት ነው ። በአሁኑ ነባራዊ ሁኔታ ከእናት አባት እየተኙ ማሳለፍ የሚቻልበት ዕድል ባይመቻች እንኳን ለፈተና በማያጋልጥ ሁኔታ ማሳለፍ ይገባል።

በዚህ መሰረት በቤተክርስቲያን ትውፊት ጋብቻ ከተፈጸመበት ዕለት እስከ ስርጉ ዕለት (ለ40ቀናት) ግንኙነት ማድረግ አይቻልም። የቤተክርስቲያን ትውፊት ይህ ቢሆንም አሁን ያለው ሥርዓት ስሕተት ነው ማለትም አይደለም ።ይኽውም ተክሊልና ስርግ አንደ ቀን የሚፈጸም ቢሆንም ተዋህዶተ መርዓዊ ወመርዓት (በጥምቱ ትውፊት ጫጉላ) በዕለቱ ሰለሌለ ማለት ነው ትርጓሜ ወንጌል ስርግ ተዋህዶተ መርዓዊ ወመርዓይ የሚደረግበት ነው። ሰለሚል ስርግ ከትክሊል/ ጋብቻ ዕለት የተለየ መሆኑ ግልጽ ነው።ምክኒያቱም ሥጋ ወደሙ ተቀብሎ በዚይምኑ ዕለት ግንኙነት ሊደረግ አይቻልምና።

ጋብቻ በቅዱስ ቍርባን የሚገባው ጥንቃቄ ሊደረግለትም ይገባልና። ቅዱስ ቍርባን ከተቀበሉ በኃላ ለሁለት ቀናት ግኙነት ማድረግ የተከለከለ ነው።

ሁለት ቀን ማለት ለአርባ ስምንት ስዓት ማለት ነው። በምሳሌ ብናየው እሑድ ቅዱስ ቊርባን የተቀበሉ ባልና ሚስት መገናኘት የሚችሉት ዕለቱ ጾም ካለሆን ሐሙስ ነው ማለት ነው ።

ሦስተኛው ቀን ማክሰኞ ቢሆንም ማክስኞ ለረቡዕ አጥቢያ የሚቆጠረው ወድ ረቡዕ ሰለሆን ጾም ነው።

የሁለት ቀን ክልከላው መሠረቱ በሉቃስ ወንጌል ካህኑ ዘካርያስ ቤተ መቅደስ ሲያጥን ብሥራተ ቅዱስ ግብሬኤል ስምቶ አግልግሉቱን ጨርሶ ወደ ቤቱ ከሔደ ከሁለት ቀናት በኃላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ እንደጸነስች ሰለሚናገር በዚሁ መሠረት ነው።

አንድምታ ወንጌሉ ከሁለት ቀን ኖሮ ተገናኝቷታል። ዛሬም ሕጋውያን ሰለ ሥጋ ወደሙ ክብር ለሁለት ቀን ኑረው መገናኘት ይገባቸዋል፤በማለት በግልጽ አሰቀምጦታል።

ወስበአት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲተ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክብር ለዘለአለሙ አሜን
በ ዲ/ን ዘማርያም ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
​​ሃያል ነህ አንተ

ሃያል ነህ አንተ ሃያል
ደጉ መልአክ ገብርኤል /2/
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት
አንተ ተራዳን በእውነት /2/
በዱራ ሜዳ ላይ........ገብርኤል
ጣዎት ተዘጋጅቶ.......ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ.......ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወጥቶ.......ገብርኤል
ሲድራቅና ሚሳቅ አብናጎም ፀኑ
ጣዎቱን እረግጠው በእግዚአብሔር አመኑ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ተቆጣ ንጉሡ.......ገብርኤል
በሶስቱ ሕፃናት .......ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ.......ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት.......ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ደረሰ መልአኩ
ከሞት አዳናቸው እሳት ሳይነኩ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
እቶኑ ስር ሆነው........ገብርኤል
ዝማሬ ተሞሉ........ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው.......ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ.......ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር
አዩ መኳንንቱ የእግዚአብሔር ክብር
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ናቡከደነጾር........ገብርኤል
እጁን በአፋ ጫነ.......ገብርኤል
ሠለስቱ ደቂቅን........ገብርኤል
ከእሳት ስላዳነ.......ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከው መልአኩን
ሊያመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን.
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንኳን አደረሳችሁ
“ዝክረ ጴጥሮስ ጳጳስ ወሰማዕት ዘምስራቅ ኢትዮጵያ”
=====
(ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ከ1875-1928ዓ/ም) ሐምሌ 22 ቀን ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ በአረመኔው ፋሺስት
ኢጣሊያ ሰማዕትነትን የተቀበሉበት ዕለት
@And_Haymanot
የአባታችን በረከት ይደርብን!!!
Forwarded from አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ሽሽታችሁ በክረምት .....እንዳይሆን ፅልዩ
ማቴ [ 24÷20 ]


እንደሚታወቀው በሀገራችን ክረምት ተብሎ የሚጠራው ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ያለውን ያጠቃልላል ፡፡ በዚህ ወራት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን መግቦቱን ቸርነቱን በዝናብ አብቅሎ ማብላቱን ትሰብካለች ፡፡ በተጨማሪም የዳግም ምፅአቱን ነገር አበክራ ትናገርበታለች ፡፡ ምክንያቱም ጌታ ዳግም የሚመጣው የት ነበራችሁ ምን ሰራችሁ ብሎ መዝኖ ዋጋ ሊሰጠን ነውና ፡፡
የፅድቅ ፋሬ አፋርተን ካልጠበቅን መጠጊያ መሸሻ አጥተን የምንጨነቅበት ቀን ነውና ተዘጋጁ ትለናለች፡፡
ታዲያ ወርሃ ክረምት ከዚህ ጋር ምን አገናኝው ስንል እንደሚታወቀዉ ገበሬው በቤት ውስጥ ያለውን እኽል አውጥቶ ዘርቶ በመጀመርያው ቡቃያውን ለማየት ይጓጓል ቀጥሎም ቡቃያውንና ቅጠሉን እያየ ወደፋት ደግሞ አበባና ፍሬን ለማየት ወርኃ ጽጌን በተስፋ ይጠብቃል ፡፡ በዚህ ግዜ ሽሽት ቢመጣ ለመንገድ የሚሆን ስንቅ የለውምና ከባድ ይሆንበታል ፡፡
@pope_shenouda
ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያነም ይህን መሠረት አድርገው ቡቃያና ቅጠል እንጂ ፍሬ በማይገኝበት ክረምት ስደት አስቸጋሪ እንደሆነ ሁሉ መንፈሳዊ ፍሬ ሳናፈራ የጽድቅ ሥራ ሳንሰራ ጌታ ለፍርድ መጥቶ የት ነበራችሁ ??? ምን ሰራችሁ ??? ባለን ጊዜ ምክንያትና ምላሽ እንዳናጣ በሃይማኖት ቁመን ትሩፋት እንድንሰራና መጨረሻየን አሳምርልኝ ፍሬ ሳላፈራ ቀኑ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ እያልን በጸሎት እንድንተጋም ያስተምረናል ።።

@pope_shenouda
@pope_shenouda

ምንጭ [ስምዐ ጽድቅ ]
ፈሪሳውያን ፣ሰዱቃውያን እና ጻፎች ምንድን ናቸው?

👉 ፈሪሳውያን
👉 ሰዱቃውያን
👉 ፃፎች
ሰላም ተወዳጆች ዛሬ በጥያቄያችሁ መሠረት ለተሃድሶ መናፍቃን እና ለሌሎች ኦርቶዶክሳዊ ምላሾችን እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያገኙባቸውን ድህረ ገፆችን እነሆ ለማለት ወደናል፡፡
ኦርቶዶክስ መልስ አላት!!
ㅤዕቅበተ እምነት
👉 ✥ Youtube ✥
✥┈┈•◦◈◎❖◎◈◦•┈┈✥
ቅድስት አርሴማ ደጓ እናቴ
👉 ✥ Facebook ✥
✥┈┈•◦◈◎❖◎◈◦•┈┈✥
ሐራ ዘተዋሕዶ
👉 ✥ Blog ✥
✥┈┈•◦◈◎❖◎◈◦•┈┈✥
፩ ኃይማኖት
👉 ✥ Telegram ✥
እግዚአብሔር አብ
እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ
.
.
.
ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕት ድንግል ማርያም እመ አምላክ
.
.
.
ቅዱሳን መላእክት
ቅዱሳን ሰማዕታት
ቅዱሳን ሐዋርያት
ቅዱሳን መነኮሳት
ቅዱሳን ደናግላን
ቅዱሳን መናንያን
ፓትርያርክ
ጳጳሳት
ኤጲስ ቆጶሳት
ቆሞሳት
ቀሳውስት
ዲያቆናት
ምዕመናን
.
.
.
ቅድሳት መጽሐፍት
ንዋያተ ቅድሳት
ታቦት(መሰዊያ)
ቅድሳት ስዕላት
.
.
.
ዶግማ
ቀኖና
.
.
.
ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን
አእማደ ምሥጢራት
.
.
.
አንዲት ቤተክርስቲያን! የማትታደስ!
@And_Haymanot
እግዚአብሔር ይመስገን ይኽን ቀን ላሳየን ።
@And_Haymanot
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ አባታችን በሰላም ገብተዋል
ደስም ብሎናል
@And_Haymanot
የአባታችን በረከታቸው ይደርብን
መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 ?
- - - - - - -
መጽሐፍ ቅዱስ ባለቤቱ እግዚአብሔር ሲሆን ጸሐፊዎቹ ግን ከእርሱ የተላኩ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ ጸሐፊዎቹ ብዛታቸውም ከአርባ በላይ ሲሆን አንዳቸውም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ
አልጻፉም፡፡ “በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” 2ጴጥ 1፡20
- - - - - - -
-+- መጽሐፍ ቅዱስ አሁን በእጃችን ላይ እንዳለው በአንድ የተጠረዘ መጽሐፍ ነበር?
- መጽሀፍ ቅዱስ በአንድ ወቅት በአንድ ጊዜ ተጠርዞ የተሰጠ ወይም ከሰማይ የወረደ ሳይሆን የተለያዩ ክፍሎች በተለያዩ ጸሐፍት እና ዘመናት የተጻፉ ናቸው፡፡ በጥንት ዘመን መጸሀፍት
በጥቅል ተጠቅልልው ይቀመጡ እንደነበር ብዙ ማስረጃዎች
አሉ፡- ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ ያነበበው የነቢዩ ኢሳያስን ጥቅልል መጽሐፍ ነበረ፡- “የነቢዩን የኢሳያስን መጽሀፍ ሰጡት መጽሐፉንም
በተረተረ ጊዜ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው …….. ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ፡፡ መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ
ሰጠውና ተቀመጠ፡፡” ሉቃ 4፡17-20 ከዚህ ክፍል እንደምንረዳው ቅዱሳት መጻህፍት ለየብቻቸው በአንድነት
ሳይጠረዙ እንደነበሩ ነው፡፡
- - - - - - -
-+- ቅዱሳት መጻህፍት አሰባሰብ?
-ቅዱሳት ሐዋርያት ስለ ስርዓተ ቤተክርስትያን የተለያዩ ቀኖናትን
ደንግገዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ስለ ቅዱሳት መጻህፍት ነው፡፡ በ325 እ.ኤ.አ በኒቂያ በተካሄደው ጉባኤ ላይ እውነተኖቹን ቅዱሳት መጻህፍት ለመሰብሰብ በተወሰነው መሰረት ቅዱስ
አትናቲዎስ በ367 ዓ.ም በ39ኛው የትንሳኤ ምልዕክቱ ላይ የቅዱሳትን መጽሐፍትን እና አይነት በአብዛኛው አስታውቋል፡፡ ከዚያም በሎዶቅያ በተካሄደ ጉባኤ እና በ393፣399 እና 419
እ.ኤ.አ በሰሜን አፍሪካ ትገኝ በነበረችው ቅርጣግና /ካርቲጅ/ በተካሄዱት ጉባኤዎች ቅዱሳት መጽሐፍትን ለይቶ ለማወቅ ጥረት ተደርጓል፡፡ የካርቴጁ ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን በአንድ ላይ መጠረዝ እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት መድብል/ጥራዝ/ ተብሎ መጠራት ተጀመረ::
- - - - - - -
- - ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳት መጻሕፍት ብዛት ሰማንያ አንድ መሆኑን ትናገራለች፡፡ ዳሩ ግን በዓለም ላይ በብዛት ተሰራጭቶ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ስልሣ ስድስት ነው፡፡

- በስልሣ ስድስቱ ውስጥ የሌሉት መጻሕፍት:-
🔷 ሀ. ከ ብሉይ (2ኛ የቀኖና መጻሕፍት):-
1.መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል
2.መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ
3.መጽሐፈ ጦቢት
4.መጽሐፈ ዮዲት
5.መጽሐፈ አስቴር
6.መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ
7.መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ
8.መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ
9. መጽሐፈ ሲራክ
10.ጸሎተ ምናሴ
11. ተረፈ ኤርሚያስ
12. ሶስና.
13. መጽሐፈ ባሮክ
14. መጽሐፈ ጥበብ
15. መዝሙረ ሰልስቱ ደቂቅ
16. ተረፈ ዳንኤል
17. መጽሐፈ ኩፋሌ
18. መጽሐፈ ሄኖክ
- - - - - - -
🔷 ለ. ከሐዲስ ኪዳን:-
1. ትዕዛዘ ሲኖዶስ
2. ግስው ሲኖዶስ
3. አብጥሎ ሲኖዶስ
4. ሥርዓተ ጽዮን ሲኖዶስ
5. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ
6. መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ
7. ቀለሚንጦስ
8. ዲዲስቅሊያ (እነዚህ የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት አሁን በእጃችን በሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተካተቱም፡፡
ይህም የሆነው እያንዳንዳቸው በጣም ትልቅ መጻሕፍት በመሆናቸው ለማካተት አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ ግን ከ81
መጻሀፍት መድበን ነው የምንቆጥራቸው፡፡ ሁሉም መጻህፍት
በቤተክርስትያኖች ቤተ-መጻሀፍት ውስጥ ይገኛሉ እንዲሁም
ገዝቶ ማንበብ ይቻላል፡፡
- - - - - - -
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መጽሕፍት ሳታጓድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትቀበላለች፡፡ ዘመናዊ ነን የሚሉ እምነቶች ግን ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌላ የለም ሲሉ ይሰማሉ፣ ለዚህም የሚጠቀሱት ዩሐንስ ራዕይ መጨረሻው ላይ ያለውን ቃል ነው። ‹‹ማን በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ
መጽሐፍ የተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል››፡፡ ራእይ 22‹18
- ይህን አባባል በጥሞና ስናጤነው የዩሐንስ ራዕይን ብቻ የሚመለከት ሆኖ አናገኘዋለን፡፡ “በዚህ በትንቢት መጽሐፍ” አለ እንጂ ከዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አላለም፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “የትንቢት መጽሐፍ” ብቻ ሳይሆን የ”ወንጌል” ፣የመዝሙር፣ የመልዕክታት እና የመሳሰሉት መጽሐፍ ነው፡፡
- በተጨማሪ የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ጠፍቶ ስለነበር እንደገና ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር ገልጾለት ስለጻፈው " በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር" ብሎ የጻፈው ወጌላዊው ዮሐንስ ሳይሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው።
- ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ ከመነሻው እንደዚሁ አንድ ላይ እንደተጠረዘ ሆኖ የተገኘ አይደለም፡፡ ጻሕፍቱ በተለያየ ዘመን የነበሩ እንደሆነ ሁሉ ፣መጻሕፍቱም በተለያዩ ዘመናት የተጻፉና በአንድ ወቅት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጸሐፍ ተጽፈው አልቀው በጥራዝ መልክ እንደወጡ አድርጎ በመውሰድ የዩሐንስ
ራዕይን ማጠቃለያ ለሁሉም መጻሕፍት አድርጎ መውሰድ አለማወቅ ወይንም ተንኮል ነው፡፡
- - - - - - -
- 👉 መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ፡-
-+- የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት:-
- የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁለት አይነት የቀኖና ክፍሎችን ያካትታል እነሱም ፕሮቶካኒካል እና ዲዩትሮካኖኒካል ይባላሉ፡፡
- (የመጀመሪያ)፡- እነዚህ መጻሕፍት የተሰበሰቡት በካህኑ እዝራ ሲሆን መጀመሪያ በቀኖና መጻሕፍትነት የተመዘገቡ ናቸው፡፡ 1ኛ. መቃብያን 2፡10 “ነህምያም የነገስትን መጻሕፍት
የያዘ ቤተ መጻሕፍት አቋቁሞ ነበር“ እነዚህም መጻሕፍት በ ሶስት ይከፈላሉ እነሱም ቶራህ (አምስቱ ብሔረ ኦሪት) ፣ ነበኢም (ቀደምት ነብያት እና ደኃርት ነብያት) እና ከተቢም (ታላላቅ የታሪክ መጽሐፍትና ታናናሽ የታሪክ መጽሐፍትን ያካትታል) ተብለው ይጠራሉ፡፡ እንዲሁም
- ዲዩትሮካኖኒካል የምንላቸው አይሁድ እንደ ቀኖና መጻሕፍት የማይቀበሉዋቸው ግን እንደ አዋልድ መጻህፍት የሚቀበሉዋቸው ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ
-> አይሁዶች 24 የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን ብቻ ሲቀበሉ (የመጽሐፋቸው አቆጣጠር ከእኛ አቆጣጠር ይለያል)
-> ፕሮቴስታንቶች 39 የብሉይ ኪዳን እንዲሁም 27 የሐዲስ ኪዳን ይቀበላሉ፡፡
-> ካቶሊኮች 46 የብሉይ ኪዳን መጻህፍት እና 27 የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት ሲቀበሉ እኛ
-> ኦርቶዶክስ ተዋህዶዎች ግን 46 የብሉይ ኪዳን እና 35 የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንቀበላለን፡፡ (ከካቶሊኮች ጋር በብሉይ ኪዳን የምንቀበላቸው መጻሕፍት ላይ የአቆጣጠር እና
የመጻሕፍት ልዩነት አለ፡፡)
- እዚህ ላይ ከላይ በግልጽ እንደምንረዳው 81 የነበረው
የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ ብዛት ቀስ በቀስ በሰዎች እየተቀነሰ እንዲሁም በነበሩት ጦርነቶች መጻሐፍቱ እየጠፉ
በመምጣታቸው፣ መጀመሪያ 73 እንዲሆን በመቀጠልም ማርቲን
ሉተር ሲያምንበት ከነበረው የካቶሊክ እምነት ፣ከካቶሊክ መነኮሳት ጋር በነበረው የግል ጸብ እና የፖለቲካ ጸብ (የጀርመን ዜጋ ስለነበር የአይሁዶች ጥላቻ ስለነበረው) በነበረው ቅራኔ
ምክንያት 7 መጻህፍትን በገዛ ፈቃዱ ቀንሶ ዛሬ በምዕራብውያን ዘንድ በስፋት የተስፋፋውን እና የእኛን ሐገር ጨምሮ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ሀይል የሌላቸውን ሀገራት የተቆጣጠረውን የ66
መጻሐፍት ሊያስፋፋ ችሏል፡፡ ይቀጥላል ...