፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
፩ ሃይማኖት
Photo
#ጅጅጋ
* በሶማሌ ክልል በደጋህቡር ከተማ ጀረር ዞን የሚገኝ ቤተክርስቲያን ተቃጥሏል
* በጅጅጋ ከተማ የሚገኘው የምስራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያንም ቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል
* የጅጅጋ ደብረመዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ዝርፊያ ተፈፅሞበታል።
* ክርስቲያኖች እና የሱማሌ ጎሳ ያልሆነ ግድያና ማዋከብ እየደረሰበት ነው
* ሌሎች በአደጋ ላይ ያሉትን ቤተክርስቲያኖች ከአደጋ ለመታደግ የአካባቢው ማኅበረሰብ ድጋፍ ወሳኝ ነው!
" በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:28)
አምላክ ለሀገራችን ለህዝባችን እና ለቤተክርስቲያን ሰላምን ያምጣልን።🙏🙏
@And_Haymanot
ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
( ከተቃጠለው ሕዝብ ይልቅ የአቃጣዩ አያያዝ በሚያስጨንቃቸው
ሰዎች ሥር መኖር ከባድ ነው )
" ዲ/ዳንኤል ክብረት "
በሶማሌ ክልል ሰሞኑን የተሠራው ዘግናኝና አረመኔያዊ ሥራ ነው፡፡ ሰውን በቁሙ ማቃጠል፡፡ ሴቶችን መድፈር፡፡ መኪና ይዞ በየቤቱ እየዞሩ የሰው ንብረት መዝረፍ፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል፡፡ ለመሆኑ መንግሥት የለም? አንድ ክልልስ ሥልጣኑ የሰው ዘርን እስከማጥፋት ድረስ ነው? ይህን መሰሉ ግፍ ዚያድባሬ ኢትዮጵያን የወረረ ጊዜ ነበር በምሥራቁ ክፍል የተፈጸመው፡፡ ዚያድባሬ አለ ማለት ነው? የክልሉ ፕሬዚዳንት የልቡን ከሠራ በኀላ ትናንት ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መጥቶ
እንመካከር ሲል ነበር፡፡ ሰው ከተቃጠለ፡ ንብረት ከተዘረፈ፡ ቤተ ክርስቲያን ከተቃጠለ በኀላ የምን ምከከር ነው? አሁን በዚያ ክልል ስላለው ሕዝብ እንደ አዲስ ማሰብ አለብን፡፡ ሌላ መፍትሔም ማምጣት አለብን፡፡ ከተቃጠለው ሕዝብ ይልቅ የአቃጣዩ አያያዝ በሚያስጨንቃቸው ሰዎች ሥር መኖር ከባድ ነው፡፡

በሰሞኑ ግጭት የተጎዱ አብያተ ክርስቲያናትና ካህናት
1. የዋርዴር ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
ሲቃጠል ቄስ ያሬድ ኅቡዕ ተገደሉ፣
2. ቀብሪ ደኃር ደብረ መድኃኒት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
ተቃጥላለች፡፡
3. ደጋሐቡር መካነ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
ሲቃጠል ቄስ ኪዳነ ማርያም ንብረቱ ተገድለዋል፡፡
4. በጅጅጋ የምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል
እና የደብረ ሰዋስው ገዳም የተቃጠሉ ሲሆን
አባ ገብረ ማርያም አስፋው፣ መ/ር አብርሃም ጽጋቡ እና ሌላ
አንድ ካህን ተገድለው አስከሬናቸው ተቃጥሏል፡፡
5. .ጅጅጋ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል
1 ካህን ተገድሏል
6. ጅጅጋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተቃጥሏል
7. ሽላቦ ቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲን ተቃጥሏል
8. ጎዴ ቅዱስ ገብርኤል አጥሩ ተቃጥሏል @And_Haymanot
ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
Share
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
​​" አበው በተጋድሎ ያወረሱኝ ቅርሴ
የበረከቴ ምንጭ የስጋ የነፍሴ ፡
ከማንም ከምንም ሀምሳያ የሌለሽ
የዘላለም ቤቴ ጎጆዬ አንቺነሽ ፡
የማትታደሺ የምታድሽ ሁሉን
የምትታደጊው መላ አለሙን ፡
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!.............!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
@And_Haymnot
​​"ፍልሰታ መጣች"
"ሕጻኑም ወጣቱም ወንዱም ሴቱም ዕድሜው የገፋውም
ሁሉም በፍቅር የሚጾሟት፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል
ማርያም ረድዔትና በረከት የሚታፈስባት፣ ፍቅረ እግዚአብሔር
በሰው ልቡና የሚሰለጥንባት ፈሪሃ እግዚአብሔር
የሚያይልባት፣ የንሰሐና የምህረት ጾም ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡
በዓለም ያሉ ወደ ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ያሉ ወደ
ገዳማት የሚገሰግሱባት ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡"
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
@And_Haymanot
መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 ?
- - - - - - -
.....የቀጠለ።
> መናፍቃን 81 /ሰማንያ አሃዱ/ መጽሐፍ ቅዱስን የማይቀበሉባቸው ምክንያቶች እና እንዲቀበሉ የሚያስገድዳቸው ምክንያቶች እንዲሁም ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት የሉም እንዳይሉ ማስረጃዎች ፡-
-> ተቃዋሚዎች ከ66 ውጭ መጽሐፍ የለም ቢሉም ሐዋርያት ሆኑ ጌታ ከ81 መጻሐፍት እየጠቀሱ አስተምረዋል፡፡ ይህን እስቲ በማስረጃ እንመልከተው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 1. - ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር ይለናል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (ሉቃ.3፡3) - እንግዲህ ጌታችን አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ30 ዓመቱ በፊት የት ነበረ? ምን እየሰራ ነበረ? ብልን ስንጠይቅ መልሱን በ66 መጻሕፍት ውስጥ ሳይሆን
በቤተክርስቲያናችን የትውፊት መጻህፍት ውስጥ እድገቱምን እንደሚመስል በዝርዝር ተጽፎ እናገኛለን፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 2. - በማቴዎስ ወንጌል 27፡3-10 (በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥
ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን። እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ። ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ። የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው። የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ። ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት። ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ። በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው። ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ
ሠላሳ ብር ያዙ፥ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ።) በዚያን ጊዜ የነቢዩ የኤርሚያስ ቃል ተፈጸመ ይለናል ይሁዳ… እንዲህ ያለው ‹‹የእስራኤል ልጆች የተስማሙበትን የክቡርን ዋጋ ሠላሳውን ብር ወሰዱ›› ይህን ቃል የምናገኘው በስድሳ ስድስቱ ውስጥ ሳይሆን በተረፈ ኤርሚስ 7፡ 2-4 ባለው ላይ ነው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ትንቢተ ኤርሚያስን ጠቅሶ ሲጽፍልን 'በነብዩ ኤርሚያስ የተባለው ብሎን ነው፡፡' ምን
ተባለ ስንል ማቴዎስ ''የተባለውን'' እና ''ተፈጸመ'' ያለንን የምናገኘው መናፍቃኑ አንቀበለውም በሚሉት በ81 መጽሐፍት
ውስጥ ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 3. - ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፡፡ ‹‹እንፍጠር›› ሲል ከአንድ በላይ ብዛትን ሲያመለክት 2 ወይም 4 ወይም 10
ሳይሆኑ ስላሴን /ሶስትነት/ ስስት መሆናቸውን የሚነግረን በሲራክ 2፤22 ሄኖክ 5፤38 ሄኖክ 6፤24 ሄኖክ 13፤14 እዝራ ስቱኤል 4፤56 እዝራ ስቱኤል 12፤48 ሲራክ 44፤10 በግልጽ ሥላሴ እያለ በማሳየት ነው፡፡ ክብር ለቅድስት ሥላሴ ይሁን!
_ _ _ _ _ _ _
ማስረጃ 4. በሉቃስ 14:13-14 “ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ” የሚለውን ኃይለ ቃል ከጦቢት 4፡7፡10 የተገኘ ነው ‹‹ከገንዘብህም ምጽዋት ስጥ ምጽዋትም በመጸወትህ ጊዜ በገንዘብህ አትዘን፣ ከድሃም ፊትህን አትመልስ፤ እግዚአብሔርም ገጸ በረከቱን ካንተ
አይመልስም፡፡››
_ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 5. 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡2 በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። ይህ
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ የሚለውን ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ከጦቢት 4፡12 ጠቅሶ ነው ያስተማረው የተገኘ ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _ ይቀጥላል ...
መርከቧን የሚያውክ ንፋስ መቷል
አድኅነን ጌታ ሆይ ተጨንቀናል
አድኅነን ክርስቶስ ተማጽነናል

አንድ እግዚአብሔር ጥላ ተሰብስበው ሳሉ
በቀለም በጎሳ ይከፋፈላሉ
እጅግ ተናውጣለች ታንኳችን ተገፍታ
አውጅልን ደርሰህ ታላቁን ፀጥታ/2/
አዝ.....
የጥፋት እርኩሰት በመርከቧ ነግሶ
እረኛ ነኝ ይላል ተክሏው ለምድ ለብሶ
ቤተሰቤ ሁሉ ተጨንቋል በነፍሱ
ሞገዱን ገስጸው ፀጥ ይበል ንፋሱ/2/
አዝ...
እኔ በልጥ እኔ በልጥ መባባሉ በዝቷል
የትህትና መጉደል መርከቧን አውኳል
ስንጠፋ አይገድህም ብለን ስንጣራ
አንተ ግን አንተ ነህ ዛሬም ለኛ እራራ/2/
አዝ...
በቁጥር የበዙ ታንኳዎች እያሉ
አንተ ባለህበት አይሏል መዕበሉ
ዘንበል በልልን ጌታ ዝም አትበለን
በእምነት ከመዛል ከመስጠም አድህነን /2/
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
የክርስቶስ አምላካችን ሠላም ከሁላችን ጋር ይሁን ተወዳጆች በቤተክርስቲያናችን እና ሃገራችን እየደረሠ ያለውን ዘግናኝ ድርጊት እግዚአብሔር በቃ እንዲለን እና ለቤቱም እንዲነሳ በጸሎት ልንጠይቀው ይገባናል፡፡
እናት ተዋህዶ ሠውን ሠው በመሆኑ
👉 በዘር
👉 በጎሳ
👉 በቀለም
እንዲሁም ሌላውን የምትገፋ እናት አይደለችም፡፡ ለዚህም በቅርቡ በሃዋሳ ያሥጠለለቻቸው ህዝቦች ማሥረጃ ናቸው፡፡

ክርስቲያን ነህ(ሽ) ??? አዎ ከሆነ መልስህ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ልዩ ፍጥረት ነውና አክብረው መለያየት የዲያብሎስ ነውና በጭራሽ ቦታ አትስጠው፡፡

👉 ትግሬ፣ኦሮሞ፣አማራ፣ሲዳማ .... የትኛውን ነህ???? በዚህ የማንነት መሥፈርት የእግዚአብሔርን መንግስት ልትወርስ አትችልምና በዚህ አመለካከት ታጥረህ ከመንግስቱ እንዳትጎድል ፀልይ ደሞ አትርሳ ክርስቲያን ለሌላውም የሚያሥብ ነውና በጸሎትህ ለሌሎችም አንድነትን፣ፍቅርን፣ይቅርታን ለምን፡፡

🙏 አደራህን ክርስቲያን ባትሆን እንኳን ለህሊናህ ሥትል ጥሩ ሥራ፡፡

❤️ ተወዳጆች ስለ አንድነታችን እንጂ ስለ መለያየት እንድናስብ ቅድስት ርትዕት ንፅይት የሆነችው ተዋህዶ ሃይማኖታችን አታሥተምረንምና ከመለያየት እግዚአብሔር ይሰውረን
ዘረኝነት ይጥፋ ፍቅር ይንገስ
ሼር በማድረግ ዘረኝነትን አብረን እንዋጋ!
፩ ኃይማኖት
Join @And_Haymanot
@And_Haymanot
ሃሳባችሁን አድርሱን
👉 @AHati_Haymanot
Forwarded from Ethio🍀 ቢዝነስ ግሩፕ
_አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሄር!!! ቅኔ ማሕሌቱ በደም ረሰረሰ
መቅደስሕ ተቃጥሎ መሰዊያሕ ፈረሰ።
ጮሁ ምእመናን ደም እንባ አለቀሱ፤
በቅዱሱ ስፍራ ታርዷልና ቄሰ።

ሠላም መስሎን ነበር መውጣትመግባታችን፤
ለካስ በእሾሕ ታጥሯል ዙሪያው ጎዳናችን።
የጽዮን መንገዶች@haimanoteabew በእንባ ተሞልተዋል፤
የሚያምሩት ግንቦቿ በለሌት ፈርሰዋል፤

የቁጣሕን በትር ማን ይቋቋመዋል፤
የሀይልሕን ጽናት ማንስ ይችለዋል፤
የሽማግሌው ፊት አልታፈረምና፤
እንዴት ቀና እንበል እንዴት እንጽናና፤

እንደ ዘካርያስ እንደእግዚአብሄር ወዳጅ፤
ወደቁ ብዙዎች መጡና ካንተ ደጅ፤
ሕጻን አዛውንቱ ጎበዞቹ ሁሉ ተሰዉ
ለፍቅርሕ አንክድም እያሉ፤
አቤቱ የሆነብንን አስብ!!!!
@haimanoteabew
@haimanoteabew
በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም! ዮሃ 14

👉 ይህን በመያዝ ሌሎች አካላት አማላጅ ማለታቸው ትክክል ነውን?
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
ኦርቶዶክስ መልስ አላት!
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
1፤ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።

2፤ እግዚአብሔርን። አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።

3፤ እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።

4፤ በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።

5፤ ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥

6፤ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።

7፤ በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።

8፤ በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።

9፤ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።

10፤ ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።

11፤ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤

12፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።

13፤ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

14፤ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።

15፤ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።

16፤ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 91)
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጠቅላይ ቤተ ክህነት የጂጂጋ ተጎጅዎችን በዘላቂነት ለመርዳት የሚከተለውን የባንክ አካውንት ከፍቷል፡፡ የገንዘብ ርዳታ ለመስጠት ያሰባችሁ በዚህ ተጠቀሙ፡፡

1000254922898
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡፡
አራት ኪሎ ቅርንጫፍ
Share share
@And_Haymanot
መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 ?
....የቀጠለ
_ማስረጃ 6. በዮሐንስ ወንጌል 10፡22 በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤ … ‹‹የመቅደስ መታደስ በዓል›› በሌሎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አናገኘውም ግን ቅዱስ
ዮሐንስ ከመጽሐፈ መቃብያን 4 ላይ ጠቅሶ ተናገረ፡፡
_ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 7. በ ሮሜ 13፡1 ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር
ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። የሚለው ኃይለ ቃል ከሲራክ 17፡14 የተወሰደ ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 8. አዳምና ሔዋን አቤልና ቃየልን ወለዱ፡፡ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ይላል ዘፍጥረት 4፡17 በ66ቱ
መጽሐፍት ላይ ስለ አቤልና ቃየል መወለድ እንጂ ሌላ የሰው ዘር በምድር ላይ ሰለመኖራቸው ምንም አያወራም፡፡ ታድያ ይህቺ የቃየል ሚስት ከየት መጣች? ስለስዋ ምንም አይናገርም
በአለም ላይ የነበሩ ሰዎች አራት ብቻ እንደነበሩ ነበር የምናነበው፡፡ የዚህን መልስ የምናገኘው በኩፋሌ 5፡8-17 ላይ
ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 9. - ይሁዳ በመልዕክቱ ‹‹የሄኖክን ትንቢት ከመጽሐፈ ሄኖክ ጠቅሶ›› ጽፎታል (ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ
ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል (ይሁዳ 1፡ 14-15) መጽሐፈ ሄኖክ ደግሞ በስልሣ ስድስቱ መጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ የለም፡፡ ሄኖክ ትንቢት ተናገረ ብሎ ከትንቢቱ ጠቅሱ ይሁዳ በመልዕክቱ ጽፎልናል ይህም ትንቢት በሄኖክ 1፡9 ላይ በግልጹ ተቀምጦ እናገኘዋለን፡፡ እንግዲህ ይሁዳ ሄኖክ ትንቢት መናገሩን እየነገረን ተቃዋሚዎች ሄኖክ ትንቢት አልተናገረም ይሉናል፡፡ እኛስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የጻፈወን ይሁዳን እናምናለን፡፡ እሱ የተቀበለውን እንቀበላለን ጥበብ አይኮረጅም
(መጽሐፍ ቅዱስ ትውፊታዊ የአምላክ ቃል)
- - - - - - -
@And_Haymanot
-+- በመጀመሪያ እስኪ መጽሐፍ ቅዱስ ትውፊታዊ መረጃ መሆኑን እንተማመን፡፡ ትውፊት ማለት ቅብብል፣ ርክክብ ወይም
ውርስ ማለት ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ ውርስ ከቀደሙት አበው ለእኛ በርክክብ ደርሶናል፡፡ አንዱ ከሌላው የተቀበለውን ለሌላው አሳልፎ በመስጠት እስከ ዘመናችን የደረሰ እውነታ ነው፡፡
ትውፊት መጽሐፍ ቅዱስ ከመጻፉ በፊት ያለ የነበረ ነው፡፡ እንደውም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚሐብሔር ቃል መሆኑን አምነን የተቀበልነው የቀደሙት አባቶቻችን የእግዚሐብሔር ቃል መሆኑን
በትውፊት ስላስረዱን ነው፡፡
-ለምሳሌ፡-
1-ዓለም ከተፈጠረ ሺህ 486 ዘምን መጽሐፈ ሄኖክ ተጻፈ
2- እስራሄል በግብጽ ሳሉ በፈርሆን ዘመን የኢዮብ መጽሐፍ ተጻፈ
3- 3643 ዓ.ዓ. እስራሄል ከግብጽ ወጡ በዚህ ጊዜ ኦሪት ተጻፈ፣
ወዘተ. . . . . እንግዲህ ከ1486 ዘመን በፊት የተጻፈ ህግ አልነበረም፤ በዚያ ጊዜ የነበሩ አበው ይመሩ የነበሩት ሙሉ
በሙሉ በትውፊት ወይም በህገ ልቡና ነበር ማለት ነው፡፡ ከስልሳ ስድስቱ (66) መጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ሌሎች ቅዱሳት
መጻህፍትየለም የምትሉ ወይም ትውፊታዊ መረጃ አንቀበልም ለምትሉ እስኪ የሚከተለውን ጥያቄ ላቅርብ
_ _ _ _ _ _ _
1- በኦሪት ዘፍጥረት አገላለጥ ቃየንም ሆነ አቤል ሁለቱም ለእግዚሐብሔር ከስራቸው ውጤት መስዋዕት አቅርዋል፡፡ ዳሩ ግን የተቀበለው የአቤልን መስዋዕት ብቻ ነው፡፡ የቃየንን መስዋዕት ያልተቀበለው ለምንድን ነው? መቼም ለአቤል አድልቶ ነው የሚል መልስ እንደማይሰጥ እርግጣኛ ነኝ ምክንያቱም
እግዚሐብሔር ለሰው ፊት አያዳላም፡፡
2- አቤል ከበጎቹ በኩራትና ከሰቡ እግዚሐብሔር መስዋእት አቅርቧል፤ ከበጎቹ መካከል በኩራትና ስቡን ማቅረብ እንደሚገባ እንዴት አወቀ? ምክንያቱም የጽሁፍ ህግና ትዕዛዝ በዘመኑ አልነበረም
3- ‹ቃየንም ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ሄኖህንምም ወለደች› ይላል፡፡ እግዚሐብሔርወንድና ሴት አድርጎ የፈጠረው አዳምንና ሄዋንን ብቻ ነው፡፡ አዳምና ሄዋን ደግሞ የወለዱአቸው አቤልና ቃየንን እንደሆነ በምዕራፍ 4 ተገልጽዋል ፤ታዲያ የቃየን ሚስት
ማንነች? ከየትስ መጣች? ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከ66 መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑትን ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትንና ትውፍታዊ መረጃ መሰረት ማድረግ ይገባል ያለበለዚያ ጥያቄዎቹ የማይፈቱ እንቆቅልሽ ሆነው መቅረታቸው ነው?
_ _ _ _ _ _ _
- እስኪ ደግሞ ወደ ሐዲስ ኪዳን እንሂድ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ቢያንስ ቢያንስ ለ20 ዓመታት ያህል ስለ ጌታ ይማሩ የነበሩት በቃል ነበር ምክያቱም ሐዲስ ኪዳን ገና በጽሁፍ አልተቀረጸም ነበርና በቅብብል ወይም በሰሚ ያገኙትንም እነርሱ ራሳቸው ከጌታ እደተቀበሉት አድርገው ያስተምሩ ነበር ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ጳውሎስ ነው (1 ቆሮ. 11፥23-24)፡፡
ጳውሎስ ከሐዋርያት ቃል የተማረውን ለሌሎች ደግሞ አስተላለፈ፡፡ ስለዚህም ወንጌል የሚያሰኘው በጽሁፍ መስፈሩ
ብቻ ሳይሆን የሕያው የእግዚሐብሔር ቃልና የህይወት መንገድ መሆኑነው፡፡ በጌታ ጊዜ ወንጌል ገና አልተጻፈም ነበር፣
“ለሐዋርያቱም ወደ ዓለም ሒዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ”(ማር.16፥1) ይህም ሲል የሰሙት ተማሩት እንጂ በጽሁፍ ቀርጾ የሰጣቸው ወንጌል አልነበረም፡፡
_ በተጨማሪም በማርቆስ ወንጌል ም.1፥21-22 ‹ወደ ቅፍራንሆም ገቡ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማረ እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ
ጸፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ›፡፡ ይህ የክርስቶስን ተቃዋሚዎች ራሱ ያስገረማቸው ትምህርት ምን አይነት ነበር ‹ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለእርሱ በመጻህፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጎመላቸው› ሉቃ 24-27
_ ከትንሳሄው በኋላ ለሁለቱ ደቀ መዝሙር ተረጎመላቸው የመጻህፍት ትርጓሜ በየትኛው ሀዲስ ኪዳን ላይ ይገኛል? “በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ. . . ናዝሬት
ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ” ማቴ 2፥23 ይህን የተናገረው ነቢይ ማነው? በየትኛው የትንቢት መጽሐፍ ይገኛል? ማቴ 27፥9 ‹በዚያን ጊዜ በነቢዩ ኤርምያስ የተባለው ከእስራሄል ልጆችም
አንዳንዶቹ የገመቱትን የተገመተውን ዋጋ ሰላሳ ብር ያዙ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሰሪ መሬት ሰጡት የሚል ተፈጸመ› ይህስ ከየት ተገኘ? በተጨማሪም ሉቃ 2፥25-32፣ 2ኛ ጢሞ 2፥ 8፣ ዕብ 12፥ 21 ፣ ራዕይ 2 ፥14፣ ዮሐ 20፥ 30 ፣ ዮሐ 21 ፥25፣ ይሁዳ 9 እንዲሁም ዮሐ 1 ፥48 ሌሎች ማሳያዎች ናቸው፡፡

_ በአጠቃላይ እነዚህ መረጃዎች ከ66ቱ መጻህፍት የማናገኛቸውና ነገር ግን ተዋህዶ እምነት በምትጠቀምበት
ሰማንያ አህዱ ውስጥ ፍንትው ብለው የተጠቀሱ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህን የመሳሰሉ ፍሬ ሃሳቦች ስለተቀመጡበት ነው ሰማንያ አሃዱን ከሌላው ጋር ይጋጫል የሚባለው?
_ ብርሃን ዓለም ጳውሎስ ‹እንግዲያስ ወንድሞች ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን
ወግ ያዙ› ያለው (2ተኛ ተሰሎንቄ 2 15)፡፡ በቃላችንም በመልእክታችንም የተማራችሁትን ‹ወግ› ያዙ ሲል ትውፊትን ማለቱ ነው፡፡👇👇👇
መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 ?
👆👆👆...._ ፊልጵ 4፥9 ‹ከህኔ የተማራችሁትና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም እና ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ የሰላምም
አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል›፡፡ የቅዱስ ጳውሎሰ መልዕክት ግልጽ ነው፡፡ በፊልጵስዮስ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ከእርሱ ከአንደበቱ የተማሩትንና በጽሁፍ የተቀበሉትንም የሰሙትንም
ያዩትንም ሁሉ እንዲይዙ እንደያደርጉ እንጂ የተጻፈውን ብቻ እንዲይዙና እንዲጠብቅ አልነበረም፡፡ ዛሬም እኛ በትውፊት የደረሰንን ሁሉ ልንጠብቅ መንፈሳዊ ግዴታችን ነው ፡፡
_ 2ኛ ጢሞ ‹የእግዚሐብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚሐብሔር መንፈስ ያለበትን መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም
ላለው ምክር ይጠቅማል›፡፡ ምክሩም ጠቃሚና አስፈላጊ መሆኑን ተዋህዶዋውያን እናምናለን፡፡ ስለዚህም
በቤተክርስቲያናችን ያሉትን የእግዚሐብሔር መንፈስ ያለባቸውን
ቅዱሳት መጻህፍት ሁሉ ለክርስቲያናዊ ህይወታችን እንገለገልባቸዋለን፡፡

--> በመጨረሻም ኦርቶዶክሳዊያን በቤታችን ያለን መጽሐፍ ቅዱስ:-
81: የኦርቶዶክስ
73: የካቶሊክ
66: የፕሮቴስታንት
24: የአይሁድ
በሆኑንና አለመሆኑን ለይተን ተረድተን የረሳችንን የሆነውን ትክክለኛውን 81 አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስን እንጠቀም።

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን አትታደስም! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን
ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና
የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን

ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
†† † † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው
ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
†† † † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
#Zerihun_Eshetu
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጌታ ሆይ አሳ ያዝኩኝ ብዬ እባብ ጨብጫለሁ : ዳቦ አነሳሁ ብዬ ድንጋይ አንስቻለሁ። ለራሴ መምረጥ አላዉቅም። የነገሮች ዳሩ እንጂ ፍፃሜው አይታየኝም።
ድንበሩ እንጂ ግዛቱ ለኔ ስውር ነው። ሁሉን የምታይ ሁሉን
የምታውቅ አምላኬ ፍቃድህ ከሆነ ስጠኝ። ካልሆነ ከልክለኝ እንቢ ብዬ ባስቸግር እንኳ በፍቅር ቅጣኝ እንጂ ለፍቃዴ አሳልፈህ አትስጠኝ።
~~~~~~
መልካም ዕለተ ሰንበት
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ክርስቲያን ሁል ጊዜ ውጊያ አለብን ውጊያችን ከስጋና ከደም ጋር
አደለም። ወጊያችን ከመንፈስ ጋር ነው። ከማይታዩ ረቂቃን መናፍስት ጋር ከሴጣን ከዳቢሎስ ጋር ውጊያ አለብን! ማሸነፍ
የምንችለው በፃምና በፀሎት ነው!
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
"ተአምሯን የሰማ ስጋውን ደሙን እንደ ተቀበለ ይሆንለታል"።

@And_Haymanot
ለተሃድሶ መናፍቃን የተሠጠ መልሥ
(በድጋሚ የቀረበ)
ይህን ፅንሰ ሀሳብ ለመረዳት በመጀመሪያ በመቅደሙ የተፃፈውን
ቃል እንዳለ መመልከት ጠቀሜታ ይኖረዋል። አስቀድመን እንደተናገርን የታወቀ ምክንያት ኋጢአት ደዌ
ካልከለከለው በዚች ቀን ተአምሯን ሰምቶ ስጋውን ደሙን ይቀበል። ስጋውን ደሙን መቀበል ካልተቻለው ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሒድ ስጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል ይደረግልኛል
በማለት ቢሰማ ይላል የዚህን አንቀጽ መልዕክት አንድ በአንድ በመተንተን ስንመለከት የሚከተሉትን ሶስት አበይት መልዕክቶች እናገኛለን።

👉ሀ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ፦

ይህ አንቀፅ በመጀመሪያ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዋናነት የሚያስተላልፈው መልዕክት ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ የሚል ነው። ምክንያቱም በፍትሐ ነገስት ከቀዳም ሥዑር በቀር ቅዳሜ ቅዳሜ እና እሁድ እሁድ በቤተክርስቲያን ተሰብስባችሁ ስጋውን ደሙን ተቀብላችሁ ደስ ይበላችሁ ተብሎ ታዝዟል ይህም ብቻ ብቻ ሳይሆን በበረሃ ያሉ ባህታውያን ሳይቀሩ መልዐከ እግዚአብሔር ስጋወ ደሙን ሰንበት ነው። / በዓላት-ምን ?
ለምን ? እእንዴት ? ገፅ ፵፮ እና ፷፮ / ነገር ግን በስርዐተ ቤተክርስቲያን አንድ ሰው ስጋውን ደሙን እንዳይቀበል ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች ይኖራሉ።
እነዚህም በዚህ አንቀፅ የተገለፁት አንደኛ የታወቀ ምክንያት / እንደ ወሊድ ፤ ሀዘን ፤ ለቅሶ ፤ ...የመሳሰሉት ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ ኃጢዐት ነው።
ይከለክሉታል ተብለው ከተጠቁሱት በመጨረሻ የተገለፀው ደግሞ ደዌ ነው። አንድ ሰው በደዌ ምክንያት ነገር ከሰውነቱ እየወጣ፤ ደም እየፈሰሰው ይህን የመሰሉ ነገሮች እያሉበት ስጋወ ደሙን ላይቀበል ይችላል እነዚህ ሁሉ ግን ሰውየውን በቤተክርስቲያን
ቅፅር ተገኝቶ ከመፀለይ፤ ቅዱሳት መፀሀፍትን ምንባባት ከመስማት ግን ላይከለክሉት ይችላሉ። ስለዚህ አንድ ሰው እነዚህ ምክንያቶች ካልከለከሉት በቀር ስጋወን ደሙን ይቀበል በማለት ወንጌልን ይሰብካል እንጅ ከወንጌል የወጣ ቃል የለውም።

👉 ለ ቤተክርስቲያን አትቅር ፦

ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ስጋውን ደሙን መቀበል ባይቻልህ ግን ስጋውን ደሙን መቀበል አይቻለኝም ብለህ ወደ
ቤተክርስቲያን ከመሄድ አትከልከል የሚለው። ተአምረ ማርያም ከቅዳሴ በፊት ያለው የቤተክርስቲያን የፀሎት
ክፍል አንድ አካል ነው።
መቅድሙም የሚለው ፦
።።።///።።።።///።።።
#ስጋወ_ደሙን_መቀበል_ካልተቻለው_ተአምሯን_ሰምቶ_ወደ_ቤቱ_ይሂድ_ነው
።።።///።።።።///።።።
ይህም ማለት ባትቆርብም ቤተክርስቲያን አትቅር ማለት ነው።በፀሎቱ ትምህርትና በመሳሰለው መርሀግብር ሁሉ ተሳተፍ።
ዕለቱ ሰንበትና በዓላት ከሆነ አንድ ክርስቲያን ቤተክርስቲያን ካልሄደ በዚያም ተገኝቶ ካልተማረ ካላመሰገነ ክርስትናውን በምን ይገልፀዋል ?
በዚህ አገላለፅ ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሂድ የሚለውን በአስተውሎትና በቅንነት ከተመለከትነው የሚናገረው ስለተአምሯ ብቻ አይደለም። ታአምሯን አታስታጉሉ ሲል ወደ ቤተክርስቲያን ሂዳችሁ በዚያ ካለው ባለው አገልግሎት ተሳተፉ ማለት ነው። ምክንያቱም ተአምረ ማርያምን እንዴትና መቸ እንደሚነበብ
እናውቃለን። ከተአምሩም በፊት፤ ከተአምሩም በኋላ ሌሎች ፀሎቶችና
ምንባባት አሉ። ይህን አጠቃላይ አገልግሎት ለምዕመኑ በታወቀ በተረዳ ነገር በዚህ ስያሜ ማስታወቅ ክፋትም ኋጢአትም አይደለም። ሌላው አገልግሎት በዚህ አገላለፅ ለምን ጠሩት ቢባል በትርጓሜ ውዳሴ ማርያም ላይ እንደተፃፈው ሌላውን አገልግሎት በመናቅ ማቅለል ሳይሆን ለእመቤታችን ባላቸው ፍቅር ነው።

👉 ሐ አትጠራጠር፦

ሶስተኛውና የየመጨረሻው የዚህ አንቀፅ መልዕክት በታወቀ ምክንያት
+++ በዚች ዕለት +++ ስጋውን ደሙን መቀበል ባይቻልክ ለሌሎች የተደረገው አይደረግልኝም የዕለቱ በረከት አይደርሰኝም ብለህ አትጠራጠር የሚል ነው። መፀሀፉ የተአምራት መፀሀፍ እንደመሆኑ መጠን ተአምራትም
የሚደረገውና ተአምራትም የሚያሰኛቸው ከዘወትራዊ የህይወት ተግባራትና ድርጊቶች የተለየ ለሰው የማይቻል በእግዚአብሔር ብቻ የሚቻል ነገር መደረጉ በመሆኑ አንተም ይደረግልኛል
በማለት በዕምነት ከፀሎቱ ተካፍለህ ከተአምሯም ሰምተህ ብትሄድ #በዕለቱ የቆረቡትን ሰወች በረከት ታገኛለክ ማለት
ነው። ይህ ደግሞ በቅዱሳት መፀሀፍ የተፃፈ ነው። ራሱ ጌታችን በወንጌሉ የስናፍጭ ቅንጣት ታክል ዕምነት
ቢኖራችሁ ተራራ ማፍለስ፤ ባህር መክፈል..........
ሌላም ሌላም ትችላላችሁ ሲል አስተምሯል። ይህም በዕምነት ሀይል እግዚአብሔርን በረከተ እግዚአብሔርን
ታገኛላችሁ ከእግዚአብሔር ትገናኛላችሁ ማለት ነው። ስጋወ ደሙ በየሳምንቱ ወይም ከዚህ ባነሰም ይሁን በበዛም
የምንቀበለውም ለዚሁ ሀይለ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርገን ኋጢያታችን አስተስርየን በረከተ ስጋ በረከተ ነፍስ አግኝተን ለመኖር ነው። በዚያች ዕለት አልቻልክ ብሎ ባትቀበል በዕምነትም ይህን ታገኛለክና አትጠራጠር ይሉናል ሊቃውንቱ።
የየመቅደሙ መልዕክት ይኸ ሁኖ ሳለ
"አውቆ የተኛን " ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንደሚባለው ሰወችን ሆን ብሎ ለማጠራጠር ከቅዱሳን በረከት ለመለየት አጋንንት በሰወች አድረው ሊቃውንቱ ያላሉትንና ሊሉም ያላሰቡትን
ያቀርባሉ። ቤተክርስትያኒቱ " ስጋውን ደሙን አትቀበሉ " ስጋወ ደሙን መቀበልና ስጋወደሙን ሳይቀበሉ ተአምረ ማርያምን መስማት እኩል ናቸው የሚል ትምህርት አስተምራ አታውቅም እእንዲህም አታምንም።
ተአምሯን የሚሰሙትና የሚያሰሙትም ስጋውን ደሙን የተቀበሉ ወደፊትም የሚቀበሉ ናቸው እንጅ አረማውያን ወይም በስጋወ ደሙ የሚጠራጠሩ አይደሉም።
/// ይደረግልኛል በማለት ቢሰማ /// የሚለው ጊዜ የተገደበ
ነው፡፡ ታዲያ ይህ በዕውኑ ለምዕመኑ መንፈሳዊ ህይወት መጨነቅ ወይስ ለኑፋቄ ሽፋን መፈለግ ???
ምንጭ ትምህርተ ተዋህዶ አፕሊኬሽን።
ልዑል እግዚአብሔር በተዋህዶ በረት እንድንፀና ያድርገን ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ከሁላችንም ጋር
ይሁን አሜን::
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
Join @And_Haymanot
@And_Haymanot
🙏1
ትዝብት

@And_Haymanot

``አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያን ወይም በኦርቶዶክስ ለምድ ያሉ ተኩላዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ጥጎች እንዲህ ሲሉ ይሰማል፡

«ድንግል ማርያም ታማልዳለች፤እስኪ አንድ ሰው አሜን ይበል»
የዚህችን ኃይለ-ቃለ ሥርወ-ውልደት እናያለን።


አዎ ድንግል ማርያም ታማልዳለች!

ግን ይህቺን ከማን ነው ያመጣኃት?«እስኪ አንድ ሰው አሜን ይበል፥ድንግል ማርያም ታማልዳለች»
ይህ የተቃዋሚዎች ይትባሃል ነው ወዳጄ!አሜን በማያስብል ነገር ሁሉ አሜን እንድንል ማስገደድ፡እስኪ አንድ ሰውም አሜን ይበል ማለት¡
አሜን ማለት እኮ ይሁን ይደረግልን ማለት ነው!ድንግል ማርያም ታማልዳለች ማለት አሜን አያስብልም!
ይልቁንም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን ብንል፤እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ትጠብቀን ቢባል፤እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ቤተ-ዶኪማስን በበረከት እንደሞላች የእኛንም ቤት በበረከት በምህረት ትሙላልን ቢባል፤ቅድስት ድንግል ማርያም በላዔ ሰብዕን በአማላጅነቷ እንዳስማረች እኛንም እንዲሁ ታስምረን፡ታድነንም ቢባል፣ከአማላጅነቷ ፡ከዘላለማዊ ድንግልነቷ፣ወላዲተ-አምልካነቷ፣አቁራሪተ መዓትነቷ እንዲሁም ምዕራገ-ጸሎትነቷ ጋር በአጠቃላይ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሁለንተናዊ ባህርይ እና ተክለስብዕና ጋር አያይዘን ብንጸልይ አሜን እንላለን!

ከዚህ ውጪ ግን ፓስተራዊ ቃልን በኦርቶዶክሳውያን ማኅበር ላይ መናገር እጅግ ጸያፍ ነው!
እኛ ኦርቶዶክሳውያን አሜን በሉ ተብለን አይደለም አሜን ምንል፡አሜን ማለት ተዋህዶናል!አሜን ማለት ባህርያችን እንጂ በውትወታ ወይም አሜን በሉ ተብለን ምናደርገው አይደለም!
በቃላችን አሜን ስንል ከልባችን አምነን እንጂ አሜን ብለን አዳራሽ እስኪናወጥ ልንጮህ አይደለም!ኦርዶቶክሳዊ አሜን ወይም አሚን ለዛ አለው፣በምክንያት በእውነት ላይ የተመሰረተ ነው!
ኦርቶዶክሳዊው አሜን በቃል ሳይሆን በልብ ሚነገር፡ከልብም ሚመነጭ ነው!
በመጮኽ ፌሽታዊ ሆኖ ሚገለጽ ሳይሆን በአትኅቶ በተሰበረ ልብ ሚቀርብ መባዕ ነው።
እስኪ አንድ ሰው አሜን ይበል ሚል ኢ-ክርስቲያናዊ አባባልም ለእኛ ቤተክራቲያን አይመቻትም!
የእኛ እምነት በጋራ የመዳን እምንት ስለሆነ፡ማንም አሜን በሉ ሳይለን አሜን ብለን እምነታችን እንዲሁም መታመናችንን ምንገልፅበት ነው!

ለነገሩ ፕሮቴስታንታዊ ፓስተሮች እሚናገሩት ነገር አሜን ሚያስብል ስላልሆነ ሚከታተላቸውን ሕዝብ ቀድመው አሜን በል ካላሉት ስለማይል«እስኪ አንድ ሰው አሜን ይበል»ብለው ማወጃቸው አያስደንቅም!አያስደነግጥምም!
«ኢየሱስ አምላክ ነው፡ኢየሱስ ያድናል» እና ሌሎች ፓስተራዊ ሀረጋት በምን አግባብ ነው አሜን ሊያስብሉ ሚችሉት?ኢየሱስ አምላክ ነው ለሚለን አስተማሪ እኮ ሊኖረን ሚገባ አጸፋ በእውነት ኢየሱስ አምላክ ነው፡ወይም ደግሞ እንዴት አምላክ ሊሆን ይችላል ሚል አከራካሪ ጽንፍ እንጂ አሜን ማለት የአሜንን ትርጉም መሳት ነው!
«ኢየሱስ ያድናል»በዚህ ቃልስ አሜን ከማለት ይልቅ፡ኢየሱስ ማን ነው?እንዴትስ ያድናል?አዳኝነቱስ እንዴት ነው?እስከመቼስ ያድናል?ብሎ መጠየቁ የተሻለ አይመስላችሁም!
እኔ ለማለት የፈለግኩት ፕሮቴስታንታዊ አካሄድ ወደ ማኅበራችን አይግባ ነው!የመናፍቃንን ለመናፍቃን!


እኛ ግን ይሁን ይደረግልን ከማለታችን ቀድሞ በራሳችን ወይም በአባቶቻችን የተደረገ ጸሎት ስላለ ጸሎቱን ስናሳርግ የጸለይነው የሥጋም የነፍስም በረከት፡የሥጋና ነፍስን ድኅነት ያስገኝልን ስንል አሜን እንላለን!በጸሎት ውስጥ ደግሞ ምስጋና ወይም ልመና ወይም ደግሞ ምስጋናም ልመናም ይኖራሉ፡ስለሁለቱም አሜን እንላለን!

ለምሳሌ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ጸሎታችንን ስንጀምር«በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡አሜን!»እንላለን!
በዚህ ሆኅተ-ጸሎት ኃይለቃል ውስጥ ያለቸው አሜን ብዙ ትርጉም አላት!
ስናማትብ ከላይ ወደ ታች፡ከግራ ወደ ቀኝ መጨረሻ ላይም በረከት ለመቀበል የተዘጋጀ እጃችንን ወደ ሰውነታችን ማዕከላዊ ቦታ እናሳርፋለን!
ማማተብ ጸሎት ነው!ከማማተብ በኋላ አሜን ማለት ለጸለይነው ጸሎት አጸፋዊ ምላሽ ነው!
በአንድነት በሦስት ምትገለጽ እግዚአብሔር ሆይ ቅድመ ዓለም ከባህርይ አባትህ ከአብ የተወለድክ ድኅረ ዓለም ከሰማየ ሰማያት ወርደህ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልደህ ከጨለማ(ከሰዖል)ወደ ብርሃን ስለመለስኸን ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን ማለታችን ነው!
አንድም ደግሞ የቀደሙ አባቶቻችን አዳምና ወገኖቹን ከሲዖል ወደ ገነት እንደመለስ እኛንም እንዲሁ በምንጸልየው ጸሎት፡በምናቀርበው ምኅላ፡በምሰጠው መባዕ ከኃጢአት ባርነት አድነን ማለታችን ነው!
በሌላ ጊዜ ስለዚህ ኆኅተ-ጸሎት ሰፋ አድርገን ማውራት እንችላለን!



ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር!
@And_Haymanot
ተጽሀፈ በናዖድ፡
ወርኃ ነሐሴ 2010 ዓ.ም
🍋ኦሪት ምስክርነት በኹለት ወይም በሦስት እንደሚጸና ትናገራለች፡፡
በደብረ ታቦርም የወልድ የባሕርይ ልጅነት፣ የአብም የባሕርይ አባትነት በአምስት ሰማዕታት (ምስክሮች)
- በኹለት ነቢያትና በሦስት ሐዋርያት - ለሰው ኹሉ የታወቀ የተረዳ ኾነ፡፡ 🍋
በገብረ እግዚአብሔር ኪደ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
📍 መልካም በአል📍
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@And_Haymanot
@And_Haymanot
በእንተ ቅድስት ድንግል ማርያም
@And_Haymanot

ከትውልድ ሊቆጠሩ ያልተገባቸው ሐሳውያን የክፋትና የክህደትን
ቃል እንደ ጸሎት ደጋግመው ስለሚናገሩና ስለሚጽፉ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ድንግል ማርያም ያሰፈረውን ማስረጃ በአጭሩ እንዘረዝራለን ። በእምነት ያለነውን በእምነታችን ያጽናን በጥፋት መንገድ ያሉትንም ልቦናቸውን ያቅናልን ። አሜን ።

👉 1. ስለ ቅድስናዋ - የቅዱስ አምላክ እናት በመሆኗ [ኢየሱስ የጸነሰችው የወለደች ያሳደገችው የማህጸኗ ፍሬ ስለሆነ (ሉቃ 1:31:42 ፥ 2:7)] ወላዲተ አምላክ እያልን እንጠራታለን ። የቅዱስ አምላክ እናት ድንግል ማርያም ክርስቶስን ያህል መለኮታዊ አካል በማህጸኗ ስለወሰነች ቅድስት ትባላለች ። እኛ ክርስቲያኖችም ቅዱስ የተባልነው ቅዱሱ አምላክ ከርሷ ከተወለደና በቅዱስ ደሙ ከዋጀን በኋላ ነው ። ቅድስት ማርያም በነፍሷም በሥጋዋም ቅድስት ናት ። ሰው የሆነ ሁሉ ኃጢአትን ከመሥራት እንጂ ከማየት ፥ ከማሰብ ፥ ከመናገር የሚነጻ የለም። ርሷ ግን ከማየትና ከመስማት ፥ ከማሰብና
ከመናገር ሁሉ ንጽሕት ናት። ስለዚህም ድንግል በክልኤ (በሁለት ወገን ድንግል) ትባላለች። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ከእግዚአብሔር ተልኮ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ ሲላት ፥ የተለየችና የተቀደሰች መሆኗን በምስጋና
ቃል መግለጡ ነው ። ቅድስት ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተነድታ ፥ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ብላ በመጮኽ ዳግም አረጋግጣለች ። ስለዚህም የመንፈስ ቅዱስ ቃል ፥ ድንግል ማርያም ቅድስት መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን እያልን በነፍስ በሥጋ ቅድስት መሆኗን እንመሰክራለን ።

👉 2. ድንግልናዋ - ቅድስት ማርያም እመቤትነትን ከገረድነት ፥ እናትነትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የያዘች ስለሆነችም የክብር ስሟ ድንግል ወእም እም ወዓመት የሚል ነው ። ድንግልናዋም ዘለዓለማዊ ስለሆነ ድንግል ዘለዓለም እንላታለን ። በአይሁድ ዘንድ ንጽሕናና ድንግልና የተወደደ፥ የተለመደ ፥ የተቀደሰም ህግ ነበር ። ይህን ህግ አፍርሶ የሚገኝ ወደ እሳት
ይጣላል ፥ በድንጋይም ተወግሮ ይሞታል። ስለዚህም ወንድ ሚስት እስኪያገባ ፥ ሴቷም ባል እስክታገባ ድረስ በድንግልና መኖር ግዴታቸው ነው ። በመሆኑም እነዚህ ደናግሎች ከጋብቻ
በመራቅ ማለት ከሥጋዊ ሥራ ድንግል ይሁኑ እንጂ ከሐሳብ ፥ ከማየት ፥ ከመስማትና ከመናገር ድንግሎች አልነበሩም ። እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን በዘመኗ ከነበሩት ደናግል
ተለይታ ፥ ከሐሳብ ድንግል ናት ፥ ከማየትና ከመስማት ድንግል ናት ፤ ክፋት ከመሥራትም ድንግል ናት ። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያናችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ንጽሕናና ቅድስና
በመረዳት "እሞሙ ለሰማዕታት ወእኅቶሙ ለመላእክት ትምክህቶሙ ለወራዙት ወለድንግል" ማለትም "ለሰማዕታት እናታቸው ለመላእክት እህታቸው ለደናግላን ትምክህታቸው"
እያለች ታመሰግናታለች ።

👉 3. ቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና እንዲገባት ፤ እመቤታችን ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ስለሆነች ፥ ዘወትር
ምስጋና ይገባታል ። የመጽሐፍ ማስረጃዎቻችንም የሚከተሉት
ናቸው
🙏 ሀ/ የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምስጋና (ሉቃ 1:28)
🙏 ለ/ የቅድስት ኤልሳቤጥ ምስጋና (ሉቃ 1:42-43)
🙏 ሐ/ ትውልድ ሁሉ እንዲያመሰግናት የእመቤታችን የምስክርነት ቃል (ሉቃ 1:48)
🙏 መ/ አንዲት ሴት የተሸከመችህ ማኅጸን ቡርክት ናት አጥብተው ያሳደጉህ ጡቶችም ብሩካን ናቸው በማለት ያቀረበችው ምስጋና (ሉቃ 11:27)
🙏 ሠ/ ቅዱስ ጳውሎስም እግዚአብሔር ያከበረውንና የመረጣቸውን የሚከራከርና የሚወቅስ ማነው? እግዚአብሔር ያጸደቀውንስ የሚኮንን ማነው? በማለቱ (ሮሜ 8:33)
🙏 ረ/ ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ ብሎ መጽሐፍ ስለሚዘንያ (ሮሜ 13:7) እመቤታችን ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል አለች እንጅ የተወሰነ ቀንና የተለየ ህዝብ አልጠቀሰችም ፤ መልአኩም ቡርክት ነሽ አለ እንጂ ነበርሽ ብሎ ስለአለፈው ብቻ አልተናገረም ፤ ቅድስት ኤልሳቤጥም ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ አለች እንጅ ነበረሽ አላለችም ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይኸን ሁሉ አስረጅ ገንዘቧ ስላደረገች ፥ ከቀድሞ ጀምሮ ዛሬም ወደፊትም ንጹሕ
ክብርና ምስጋናን ለእመቤታችን በሰፊው ሰጥታ ስታመሰግን ትኖራለች ።

👉 4. ክብር እንደሚገባት:- ቅድስት ድንግል ማርያም ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ እርሷ በማህጸኗ ወስናለችና ፥ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነ ክብር አላት ። እንዲህም ከሆነ ከሰማይ ከምድርም እርሷ
ትበልጣለች እርስዋም ትከብራለች ማለትም በሰማይና በምድር ካሉት ከግዙፋኑና ከረቂቃኑ ፍጥረታት ሁሉ እርስዋ ትበልጣለች እርስዋም ትከብራለች ። ልዑልና ኃያል እግዚአብሔር ማህጸኗን ዙፋኑ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን አድሯልና ።
እግዚአብሔር በመንፈሱ በሰው ላይ ለማደር እንኳን ሰው አላገኘም ነበር ። ነገር ግን ቅድስት ማርያም በንጽሕና
በድንግልና ብትገኝ የልዑል እግዚአብሔር ማኅደር ለመሆን
በቃች ።
ስለዚህ ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች የሆነ ክብር ተገባት ። ጌታችን ራሱን ከዓለም ግሳንግስ አንጽቶና በድንግልና ጠብቆ ህዝብን ስለንስሐ ያስተምር የነበረውን ዮሐንስን እንኳን፥ ሴቶች ከወለዱት እንደ ዮሐንስ የለም ብሎ ሲመሰክርለት እመቤታችንንማ ከንጽሕናዋ ከድንግልናዋ ጋር የአምላክ እናት ስለሆነች ከሁሉ በላይ እንዴት በበለጠ አትከብር? አምላክ የርሷን ሥጋ ተዋሕዷል ሰውም በዚህ ሥጋና ደም
ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆ የእግዚአብሔር መንግሥትን የሚወርስ
ሆኗልና በክርስቶስ ደም ድኛለሁ የሚል የሰው ልጅ ሁሉ ሊያከብራት ይገባል ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
@And_Haymanot
@And_Haymanot