፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
👉 ታቦትን ሌሎች ሃገራት እንዴት ይጠቀሙታል ?

@And_Haymanot

የተሀድሶ መናፍቃን ታቦት በሀገራችን ብቻ ያለና ሌሎች ሀገራት በተለይም አምስቱ አብያተ ቤተክርስቲያናትም ጭምር እንደሌለ አድርገው ሲቃወሙ እንመለከታለን
✞✞ በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት(oriental crurch) ታቦት የተለመደ ህግ ነው፡፡ ሥጋና ደሙንም የሚፈትቱት በታቦቱ ላይ ነው፡፡ ክርስቲያኖች አንድ ሊያውቁት የሚገባው ትልቁ ነገር በብሉይ ኪዳን የነበረው የታቦት አገልግሎት የበጎችና የጥጆች ደም በቅድስተ ቅዱሳን ፊት ለፊት የመሠዋት ስርዓት #ነበር፡፡ ይህም በእውነተኛ አምላካችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ተወግዶ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ ይለናል ዕብ 9:12 የኢየሱስ ክርስቶስ ደም እኛን ከሃጢአት ሁሉ በማጠብ የቀደመውን መስዋዕት አስወግዶ እርሱ መስዋዕት ሆኖ ከብሯል፡፡፡፡ በታቦቱም ላይ የማዳኑን ምሥጢር በመግለፅ ሰዎች ሁሉ ሥጋውን በልተው ደሙን ጠጥተው እንዲድኑ ይናገራል፡፡ ዮሐ 6:54
ይህን እውነት በመያዝ ታቦት በብሉይ ኪዳን የነበረ አገልግሎትና በአዲስ ኪዳን ያለው አገልግሎት ልዩነቱን በትክክል መረዳት ያሥፈልጋል፡፡
ለምሳሌ ግብጻውያን ታቦቱን #ሉሕ ይሉታል ፅላት ሠሌዳ ማለት ነው ያለሱ ሥጋና ደሙን አይፈትቱም፡፡ የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተብለው የሚጠሩ የግሪክ የሩሲያ፣የሮማኒያ ሌሎችም ወደ ክርስትና የተመለሱት ከአረማዊነት ስለሆነ የታቦቱን ምሥጢር አያውቁትም በታቦቱ ፈንታ ከመንበር የማይነሳ እንደ ታቦት የሚከብር የጌታ የስቅለቱ ወይም የግንዘቱ ሥዕል ያለበት የነጭ ሐር መጎናፀፊያ አላቸው፡፡ ያለሡም ሥጋና ደሙን አይፈትቱም፡፡ ይህንንም በጽርዕ "እንደምኒሲዩን" ይሉታል፡፡ "ህንየተ ታቦት" ማለት ነው፡፡ የሮማ ካቶሊኮች 'ሜንሳ' Mensa ይሉታል፡፡ ጠረጴዛ ማለት ነው፡፡ ከአምስቱ አብያተ ክርስቲያናት በቀር አዲስ ቤ/ክርስቲያን በሚሠራበት ጊዜ የአጽመ ቅዱሳን ሽራፊ እንዲቀመጥ ያዛል..... በታቦት ዙርያ ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/361

ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የማርያም ልጅ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው
@And_Haymanot
ፈራጅ ነው የኛ ጌታ

@And_Haymanot

ተወዳጆች በ social Media የእመቤታችን ተአምር ነው ሀብት እንዲኖርህ አባዛው ካልሆነ ሥራህ ኑሮህ ይዘበራረቃል የሚል የሀሠት መልእክት እንደመብዛቱ ከማባዛት እንቆጠብ መንፈስን እንመርምር እያልን ዛሬ ደሞ በውስጥ ላደረሣችሁን ተመሣሣይ የሀሠት መልእክት ጥንቃቄ እንድታደርጉ አቅርበነዋል፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት አይደለምና ከማባዛት እንቆጠብ ለማለት እንወዳለ
@And_Haymanot
የእግዚአብሔርን
መምጫ #ማንም አያውቅም ነገር ግን እግዚአብሔር መላእክቱን ትላንት ማታ መለከት ሊያስነፋ ነበር ይለናል፡፡
ይቀጥልና ጌታችን በሰማይ #ወድቆ_እያነባ_ለመነ
ዛሬም በመሥቀል እንደተሠቀለው ደሙ ይፈሳል ..... ይለናል፡፡
ተወዳጆች ይህ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ነውን? በዚህ የሀሰት ትምህርት ላይ የተጠቀሠው ሰው የጌታን መምጫ ሊጠቁምም ይቃጣዋል፡፡ ከዚህ በፊት በተደረጉ በፕሮቴስታንቱ አለም ያሉ የሐሰት ትንቢቶችን መመልከት ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይለናል
" ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።"
(የማቴዎስ ወንጌል 24:36)
" ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 24:42)
(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 3)

" #ጌታችን_በሰማይ_ወድቆ_እያነባ_ለመነ ዛሬም በመሥቀል እንደተሠቀለው ደሙ ይፈሳል ..... " ይህስ የጌታን የማዳን ስራ ከማወቅ የመጣ ነውን? ይህን የጠቀሡት ዛሬም ላይ አማላጃችን ነው ለማለት ቢሆንም ጌታችን ግን አንድ ግዜ የማስታረቅን ስራ ፈፅሞ በግርማው ተቀምጧል እንጂ እነሱ እንደሚሉት ዛሬም በእለተ አርብ እንደተሠቀለ ሆኖ ደሙ እየፈሰሰ ማራቸው አይልም
" እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤"
(ወደ ዕብራውያን 1:3)
" እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም #ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:19)
እንግዲህ ምን እንላለን የጌታን ማንነት ባለማወቅ ዛሬም እየወደቀ ይለምናል ማለት ትልቅ ክህደት ነው

(ወደ ዕብራውያን ምዕ. 9)
----------
25፤ ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን #ብዙ_ጊዜ_ሊያቀርብ_አልገባም
26፤ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።
https://tttttt.me/And_Haymanot/541
ይቆየን....
ለጠፉት ልቦናን ይስጥልን
"ማራናታ"
@And_Haymanot
@And_Haymanot

በክርስቶስ ማንነት ለሚጠይቁት ጥያቄም እነሆ ምላሽ 👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/288