፩ ሃይማኖት
8.99K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ድንግል ማርያምን እመቤት ማለት ይገባል? 👆👆
💗 "ቅድስት ድንግል ማርያምን መውደድ ከሚገባኝ መጠን በላይ አልፌ ወድጄያት ይሆን? ብለህ ሥጋት አይግባህ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከወደዳት በላይ ልትወዳት አትችልምና" 💗
ቅዱስ ማክሲሚሊያን ኮልብ
@And_Haymanot
🕯''የመላእክት እህት''

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለምን እህተ መላእክት ትባላለች?

እመቤታችን እህተ መላእክት ተብላ ትጠራለች፡፡ ሊቁ አባ ህርያቆስ ‹‹እህተ መላእክት፤ እመ ሰማዕታት፤ ወእግዝዕተ ፃድቃን እያለ ሲጠራት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ደግሞ ‹‹እህተ መላእክት ወእመ ኩሉ ሕዝብ … የመላእክት እህት የህዝቡ ሁሉ እናት›› ብለዋታል፡፡ አባ ህርያቆስም ሆነ አባ ጊዮርጊስ እመቤታችን የሰማዕታት፤ የፃድቃን የህዝቡ ሁሉ እናት ብለው ሲጠሯት እንዴው በራሳቸው ሳይሆን ‹‹እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ (ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል) መዝ (፹፮÷፭) የሚለውን ፍፃሜው ለድንግል ማርያም የሆነውን ቃለ ትንቢት በማስታወስና ‹‹እነኋት እናትህ›› ዮሐ (፲፱÷፪፭) በማለት ጌታችን ድንግልን በዮሐንስ ወኪልነት ከዕፀ መስቀሉ ስር ለተገኙ ክርስትያኖች በእናትነት የሰጠበትን ቃል ኪዳን በማሰብ ነው፡፡ እህተ መላዕክት ሲሏትም በምክንያት ነው፡-

🕯,ከንጽህና_አንፃር

ቅዱሳን መላእክት በባህርያቸው ንፁሐን ንኡዳን ክቡራን ናቸው፡፡ የረከሱ ፍጥረታትን በምልጃቸው ያስምራሉ እንጂ እነሱ ራሳቸው አይረክሱም፡፡ ከሃጢአት ያልተመለሱ ልበ ደንዳኖችን ሊገስጹ አሊያም እንደሰዶምና ገሞራ ሊቀጡ ይላካሉ እንጂ እነሱ ሀጥያት አይሰሩም፡፡ በአምልኮ እግዚአብሔር ፀንተው በምስጋና ተግተው በተሰጣቸው ስፍራ (በኢዮር፤ በራማ፤በኤረር፤ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት፣በመንበረ መንግስት ) በንፅህና በቅድስና ዘለአለም እስከ ዘለአለም ይኖራሉ፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ መላዕክት በንፅህና በቅድስና ኖራለች፡፡ንፅሕናዋም በሁለት መንገድ ይገለፃል፡፡ አንደኛው ‹‹ ሞት በአንድ ሰው በአዳም ምክንያት ወደ ዓለም ገባ እንዳለ ቅ/ጳውሎስ ሁሉ በአዳምና በልጆቹ ላይ በወረደ መርገመ ሃጥያት(ጥንተ አብሶ) ሲረክስ እመቤታችን ግን ይህ የቀደመ መርገም ያልነካት ንፅህት መሆኗ ነው፡፡ ኢሳ ፩÷፲፱ (የዚህን ምሳሌ በዘመነ ጌዲዮን መ/መሳ ፮÷፴፮ -፵ ይመለከቱ፡፡) 2ተኛው ከሃልዮ ከነቢብ ከገቢር ሀጥያት የነፃች በስጋም በነፍስ ሀጥያት ያላወቃት (ማርያም ድንግል ንፅህተ ስጋ ወነፍስ እንዳለ ደራሲው በመልክአ ማርያም) መሆኗ ነው ፡፡ ይህንንም ቅ/ ገብርኤል (ቡርክት አንቲ እም አንስት… ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ) በማለት መስክሮላታል፡፡ ይህ ፍፁም ንጽህናዋን አምላክ ተመለከተና በማህፀኗ አደረ በስጋም ወለደችው፡፡ እንግዲህ የድንግል ማርያም ንጽህና እንደ መላዕክቱ የባህርይና ለሁሉም ወገን በመሆኑ በንጽህና ለምትመስላቸው የመላዕክት እህት ተባለች፡፡

🕯,ከግብር_አንጻር

የእግዚአብሔርን የክብር ዙፋን የሚሸከሙ ኪሩብ (በብዙ ኪሩቤል) መላዕክት ናቸው፡፡ እነዚህ መላዕክት እግዚአብሔር ለቅዱሳን እንደታያቸው እሳታዊውን ዙፋን በደመና ይሸከማሉ፡፡ ፯ የእሳት መጋረጃዎች በዙፋኑ ዙሪያ ተከልለዋል፡፡ እመቤታችን በማኅጸኗ ዙፋንነት በሆዷ ያስቀመጠችው ያን ኪሩቤል የሚሸከሙትን እሳተ መለኮት ነው፡፡ በሰማያዊው ዙፋን ፯ የእሳት መጋረጃዎች ጌታን እንደከለሉት በድንግል ማህጸን ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ በ፯ቱ ባህርያተ ሰብእ (፫ቱ ባህርያተ ነፍስና ፬ቱ ባህርያተ ሥጋ አምላክነቱን ሰወረ፡፡ በመሆኑም በሰማይ ዙፋኑን ለሚሸከሙ መላዕክት (ኪሩብ) አምላክን ፱ወር ከ፭ቀን በማህጸኗ ዙፋንነት ያስተናገደች እመቤታችን እህታቸው ተባለች፡፡ አንድም መላእክት ዘወትር በዙፋኑ ፊት ቆመው በፍርሐትና በመንቀጥቀጥ ቅዱስ፣ ቅዱስ ፣ቅዱስ እያሉ ያመሰግኑታል፡፡ ይማጸኑታል እመቤታችንም በአማላጅነት በንጉሱ ቀኝ ትቆማለችና እህታቸው ተባለች፡፡ ‹‹ወትቀውም ንግሥት በየማንከ… ንግስቲቱ በቀኝህ ትቆማለች እንዲል›› መዝ.፵፬፡፱

🕯,ከምልጃና_ከመዳን_ሰራ_አንፃር

መዳን በእግዚአብሔር በማመን እና ህጉን ትዛዛቱን በመፈፀም ነው ፡፡ እግዚአብሔርም እንዳንጠፋ ስለሚፈልግ በእርሱ ለምናምን ለእኛ ብዙ የድህነት መንገዶችን ሰጥቶናል ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ምልጃ በዋነኝነት ሚጠቀስ ነው፡፡ ድህነት እና ንስሐን በተመለከተ መላእክትንና ድንግልን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፡፡ ሁለቱም የሰው ልጅ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ አጥብቀው ይሻሉ፡፡ ተመልሶ ወደ ህፅነ እግዚአብሔር ሲገባም ደስ ይሰኛሉ፡፡ በአንዲት ነፍስ መዳን በሰማይ መላእክት ዘንድ ታለቅ ደስታ እንደሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ድንግል ማርያምም የሰው ልጅ ብቻም ሳይሆን ፍጥረት ሁሉ ቢፅድቅላት ደስ የምትሰኝ ርህርህት እናት ናት፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያምም ሆኑ መላእክት ፍጡራን እንዲድኑ ካላቸው ጽኑዕ መሻት የተነሳ ዘወትር በጌታ ፊት ምልጃን ያቀርባሉ፡፡ ጸሎታቸውም መና የሚቀር ሳይሆን በቅድስናቸው ብዛት ካገኙት ሞገስ የተነሳ እግዚአብሔር የሚሹትን ስለሚፈፅምላቸው ሀይል ያለው ነው፡፡ ያዕ ፭፡፲፮ ስለሆነም ስለዚህ የምልጃና የድህነት ስራ ድንግል ማርያም የመላእክት እህት ተባለች ፡፡ በአጠቃላይ ድንግል ማርያም እህተ መላእክት ስትባል ከላይ ባነሳናቸው ምክንያቶች መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
​​✞ መስቀሉ አበራ ✞

እዮሐ አበባዬ መስከረም ጠባዬ(፪)
መስከረም ሲጠባ ተተክሎ ደመራ
ህዝበ ኢትዮጵያን እዩት ችቦውን ሲያበራ
በታላቁ ብርሃን በመስቀል ደመራ(፪)

በኃጢአት ጨለማ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተውጠን ሳለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የክርስቶስ መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ብርሃን ሆነልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ትምህርተ መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሆኖን ላመንነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በቃሉ ለምንድን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የእግዚአብሔር ኃይል ነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

✞ መስቀል ባንዲራችን
የነጻነት አርማችን(፪)

በኢየሩሳሌም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አይሁድ አብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ያዳናቸውን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አናውቅም ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የድሉን መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ከመሬት ቀብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስሏቸው ነበር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ውጦ የሚያስቀረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

በቀራንዮ ጎልጎታ
ጠላታችን ድል ተመታ(፪)

ንግሥቲቷ እሌኒ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በጣም የታደለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ደመራን አቁማ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ፍለጋ ጀመረች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀለ ክርስቶስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ወዴት ነው እያለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በጣን ጢስ ተመርታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀሉን አገኘች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

በመስቀል መከታ
ቆስጠንጢኖስ ድል ተመታ(፪)

ነገር ግን መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተቀብሮ አልቀረም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተራራ አፍርሶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጠላት አሳፈረ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ሲወጣ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ታላቅ ሁካታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ድውይ ሲፈወስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አንካሳው ዳነ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሙታን ተነሱ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ይመስገን ጌታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ
ክርስቲያኖች እልል በሉ (፪)

መስቀል መከታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ይሁን ጋሻችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
እንዳይደፈር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ዳር ድንበራችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኢትዮጵያ ኑሪ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በእምነት ፀንተሽ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጌታ በመስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የባረከሽ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀሉ አበራ
እንደ ፀሀይ ጮራ (፪)

መስቀሉን አምነን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተሳልመነዋል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ከክብሩ ዙፋን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በእርሱ ባርኮናል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
እንሰግድለታለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የፀጋ ስግደት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በእርሱ ላይ ስላለ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኃይለ መለኮት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀል የእኛ ጋሻ
የዲያብሎስ ድል መንሻ (፪)

የኢትዮጵያን መኩሪያ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኑ ተመልከቱልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የመስቀሉን ብርሃን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ነፀብራቁን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
እፀ መስቀሉ ነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የእኛ መከታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የተሰጠን ለእኛ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ምልክታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

በመስቀል እንመካለን
እንድንበታለን(፪)

የዳዊት ልጅ ያዕቆብ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የሀገራችን ኩራት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የኢትዮጵያ ንጉሥ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጌታን የሚፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሀገሪቱን ሲዞር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ድካሙን ሳይፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ብርሐን እያበራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

የመስቀሉ ፍቅር
በእኛ ላይ ይደር(፪)

መናገሻ እንጦጦ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የረር አምባ አመራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሲፈለግ ሰንብቶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የመስቀል ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጊሸን ላይ አገኘ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የአምባሰል ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ግማደ መስቀሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አርፏል ከዚያ ስፍራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀል መስቀላችን
የክርስቲያን ኃይላችን(፪)

የመስቀል ለታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የደመራው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኢትዮጵያውያን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተደስተው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በሀገር ልብሳቸው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አምረው ደምቀው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በአደባባዩ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተሰብስበው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ይዘምራሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

የመስቀሉ ደመራ
በኢትዮጵያ ሲያበራ(፪)

@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
"ሰይጣን የማይነካው ዕቃ "

በአንድ ሐገር ድንገት የአንድ" ጠንቋይ ዝና ከዳር ዳር ተሰማ ። ሰውዬው የማያሳየው ምትሐት የለም። አንበሳ ላለ አንበሳ፣ ነብር ላለ ነብር፣ የሞተ ዘመዴን ላለ የሞተ ዘመዱን፣ የጠፋብኝን ዕቃ
ከቤት ፈልገህ አምጣልኝ ላለ ዕቃውን ያመጣለታል። እንደሚታወቀው አጋንንት ከክብራቸው የተዋረዱ መላእክት ናቸው። መላእክት ደግሞ በፈለጉት ሁኔታ መገለጥ ይችላሉ። ይህ ጠንቋይ የሚሰጣቸውን ገጸ ባሕርይ ተቀብለው አንዴ አንበሳ፣ አንዴ ነብር፣ አንዴ ሰው እየሆኑ የሚተውኑት እንግዲህ አጋንንቱ ነበሩ። የበዚህ ጠንቋይ ዝና ወደ ንጉሱ ደረሰ። ንጉሱ ደግሞ ክርስቲያን
ቢሆንም ከመጸሐፍ ቅዱስ ይልቅ እንዲህ ያለ ተአምር እዚህ ቦታ ተፈጸመ ሲባል ለማየተት የሚሮጥ ሰው ነበር። ተአምር የሚወድ ሰው ደግሞ ክርስቲያንም ቢሆን ሰይጣን በሚሰራው ምትሐት
መታለሉ የማይቀር ነው። ስለዚህ ይህ ንጉስ የተማረውን መጽሐፍ ቅዱስ ዘንግቶ በጠንቋዩ ምትሐት አመነ።
ይህንን የሰሙ የንጉሱ ንስሐ አባት ነገሩን ሰምተው ወደ ቤተ መንግሥት ሲሮጡ ደረሱ። ሲደርሱ ንጉሡ ከቁም ነገር
አልቆጠራቸውም። እሱ የጠንቋይ ትርዒት ማየት ቀጠለ። "እስቲ አሁን ደግሞ እእእ ነጭ ፈረስ አምጣልኝ" ማለቱን ቀጠለ በነገሩ ያዘኑት "ኧረ ንጉሥ ሆይ ይተዉ፡ ይህ እኮ የሰይጣን ምትሐት ነው " ብለው ሊያስረዱት ሲሉ በቁጣ አስቆማቸው። ተአምር የሚከተል ሰው መቼስ ቢነግሩት አይሰማም። ጭራሽ
እንዲያው ለንስሐ አባቱ እንዲህ አላቸው። " የሰይጣን ስራ ነው አትበሉ፤ ቅናት ነው ይኼማ,,,, ይልቅ እርስዎም የሚፈልጉትን ነገር ይጠይቁት ያምጣልዎት!"አላቸው። ጠንቋዩ «የፈለጉትን ላምጣልውት,,,,,ምን ይፈልጋሉ,,,, " የሞተ ዘመድ አለዎት,,,,, ወይስ ከቤትዎ,,,, » አላቸው በኩራት። ካህኑ ውስጣቸው በመንፈሳዊ ቅናት ተቃጠለ። « እንግዲያውስ የፈለኩትን ማምጣት ከቻልህ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደህ ልብሰ ተክህኖዬ ውስጥ መስቀል አለ እርሱን ይዘህልኝ ና » አሉት።
ይህን ግዜ ጠንቋዩ ገና ድግምቱን ሲጀምር አጋንንቱ እላዩ ላይ ሰፍረው ጣሉት። በካህኑ ፊት ወደቀ። ሰይጣን ምንም ነገር ማምጣት ይችል ይሆናል። መስቀሉን ግን ማምጣት አይችልም።
አባቶቻችን ሰይጣን እንኳን መስቀል ቀርቶ መስቀለኛ መንገድም
አይወድም ይላሉ።
የጌታችን ቅዱስ መስቀል ሆይ ቅዱስ ዳዊት እንዳለ «ብከ ንወግዖሙ ለኩሎሙ ጸርነ»
@And_Haymanot
«በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን!»
በዲ/ን ሔኖክ ሙላት
"ከሞት ባሻገር" የተወሰደ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
"ልጇ ነው አምላኳ"
@በእንተ ዲያቆናት(ስለ ዲያቆናት)

የቅድስትና ሐዋርያዊት ኵላዊት ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ይላሉ?
፩. ዲያቆንም ኾነ ቄስ ሰሞነኛም ይኹን አይኹን፤ ለመቀደስም ኾነ ለጸሎት ቤተ መቅደስ ውስጥ መግባት ያለባቸው ሌሊት ነው። ሥርዐተ ቅዳሴ እንዲህ ይላላ፦
👌 "ሌሊት ለጸሎት ያልመጡ ቀሳውስትና ዲያቆናት ወደ ቤተ መቅደስ ይገቡ ዘንድ ያገለግሉም ዘንድ አይገባቸውም። ይኽን ትእዛዝ ቢደፋፈሩ ግን ከሕግ ትእዛዝ የወጡ ይኾናል።" [ሥርዐተ ቅዳሴ]
፪. ብዙዎቹ ዲያቆናት ልብሰ ተክህኖ ለብሶ መቀደስ፥ ሰዓታትና ማኅሌት መቆምና በንግሥ ሰዓት መስቀልና ቃጭል ይዘው ቅድመ ታቦት መኼድ እንጂ የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር መረዳት የስብከተ ወንጌል ግብር ብቻ ይመስላቸው። ፍጹም ስሕተት ነው። ከመቀደስ ባለፈ እውነተኛውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት
መማር፥ መረዳት፤ ከክህደት ትምህርት አንጥሮ መገንዘብም የመለየት ኃላፊነት አለባቸው።
➺ቅጥረኛ ስለኾንኩ እንጂ...በሚል ሳይፈልገው የሚቀድስ፦ ከታማኝ አገልጋይ ጋር ምን አንድነት አለው?
➾ቅባት ከተዋሕዶ ጋራ፥ ኑፋቄ ከአሚን(ከእምነት) ጋራ፥ ምርግትና ከጥንቆላ ጋራ፥ አውደ ነገሥት ከፍትሐ ነገሥት ጋር፥ ክህደት ከእውነተኛዋ ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ትምህርት ጋር፤ ምንም ኅብረት እንደሌላቸው አንጥሮ፥ ኵልል አድርጎ የመረዳት የማስረዳትም ግዴታ አለባቸው። ለዚኽም ነው፦
👌"የቤተ ክርስቲያን መብራት አገልጋዮቹዋም የምትኾኑ ዲያቆናት ኾይ ተኵላ ከበግ ጋራ፤ ጭላት(ጭልፊ) ከርግብ ጋራ፤ ክርዳድ ከስንዴ ጋራ እንዳይኖር ከውስጥዋ ንቀሉ፤[ቅዳሴ አትናቴዎስ] እንዲል።
፫. ደጀ ሰላም፦ የሰላም ደጅ ናት። የዲያቆናት አብነት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ መጽሐፈ ገድሉ ላይ "የቀዳሜ ሰማዕት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ አምላክ እግዚአብሔርም የዚኽን ሰው የንስሓ እንባ ተመልክቶ ይቅር አለው። ይኽ ሰውም በዚያች ቤተ ክርስቲያን ደጀ ሰላም ተቀምጦ የደረሰበትን ለሚገባውና ለሚወጣው ኹሉ መሰከረ።" [ገድለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ዘወርኃ መጋቢት]
✍️ አኹንማ የተጣሉ የሚታረቁባት፦ የሰላም ደጅ የተሰኘችው "ደጀ ሰላም" ድረስ ቢራና ዘር ማንዘሮቹ ገብተው "ምን ይኹንልህ?!" ብለን ግሮሰሪ አደረግነው። በርግጥ መጠጥ ፈጽሞ የተከለከለ ባይኾንም፤ አብዝቶ መጠጣት ግን የተገባ አለመኾኑ ለኹላችንም ግልጽ ነው። ደጀ ሰላም "የሰላም ደጅ" እንጂ 'የቢራዎች ደጅ' አይደለችምና ባይገባ ይመከራል።
✍️በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ተፈቅደው ነገር ግን ከማይበረታቱ ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው። ፈጽሞ አይጠጣም፥ ርኵስ ነው ባንልም የማይጠጣ የተሻለ አደረገ።
➣"ከስካር ተጠበቁ ሙሴ በኦሪት ዘሌዋውያን እንዳይሰክሩ አዟቸዋል። እንዲሁ እናንተ ኤጲስቆጶሳት ቀሳውስትና ዲያቆናት መጠጥን ከማብዛትና ከስካር ተጠበቁ፤ መዳራት፣ ዝሙት፣ ስግብግብነት፣ ሰውን መስደብና ማስቀየም፣ መታበይ፣ በሐሰት መማል፣ ብዙ ቁም ነገሮችን መዘንጋትና ሌሎችም ከስካር የሚመነጩ ናቸው።"[መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፲፤ ቍጥር 56]
➛"ከስካርና ወይንን ከማብዛት ተጠበቁ፤ ቃለ እግዚአብሔር የሠፈረባቸውን መጻሕፍት መጠጣትን አዘውትሩ እንጂ።" [ዝኒ ከማሁ(Ibid) ቍጥር 57]
፬. የበቁ ዲያቆናት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቅድስና ሥጋወደሙን ለመለወጥ ሲወርድ ማየት ይችላሉ።
➤"ካህን የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ ላክ ባለጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለመስዋዕትነት በቀረቡ ፅዋዕና ሕብስት ላይ መንፈስ ቅዱስ ይወርዳል፤ ዲያቆናት በቅድስና ሥጋወደሙን ለመለወጥ ሲወርድ ማየት ይችላሉ። የዲያቆናት ክብር በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ቅዱስ እስጢፋኖስ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ የክብር ቦታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሊሠጠው እንደቻለ ለነሱም ይሠጣል።"
[መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፲፩፤ ቍጥር 33]
፭. ዛሬ ላይ ዲያቆናት የት ይገኛሉ? ምን ሲያደርጉ ይገኛሉ? ክቡር ዲያቆን ሆይ! "ዙረታም" ነኝ ካልክ የት መዞር እንዳለብህ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ ይመክሩናል።
➣"ዲያቆናት የክርስቲያኖችን የመኖሪያ ቤት ወዳለበት ኹሉ እየዞሩ የተቸገሩትን ኹሉ ይጎብኙ፤ ችግራቸውንም ይመልከቱ። ጥዋትም ኾነ ማታ ምእመናኑ በስንፍና እንዳይያዙ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲተጉ ያነቃቁዋቸዋል። በሠርክ በጧትና በማታም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሁል ጊዜ እየኼዱ ያመስግኑት፤ እግዚአብሔር የዕለት ብርሃን ነው፤ ኹሉንም ይረዳል።" [መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ ፱፤ ቍጥር 66]
፮. ዲያቆናት ምንም ዓይነት ጉቦ መቀበል፥ በደም ግባት ማዳላት፤ ድሀን አይቶ ባላየ ማለፍ፤ ዝም ብሎ ስለ ሴትና ወንድ በማውራት ዋዛ ፈዛዛ በመስማት- ነገረ ዘርቅ መስማት የለባቸውም።
➤ "እናንተም የመንጋዎች ጠባቆችና ዲያቆናት ሆይ መማለጃ በመቀበልና ፊት አይቶ በማድላት ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን ታወጡት ዘንድ በደል በሌለው በንጹህ ሰው ላይ ነገር ሥራንና የሐሰት ነገርን ትሰሙ ዘንድ አይገባም። እንደዚህ ያለ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች የዲያብሎስ ወዳጆች ይኾናሉና።" [መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ምዕራፍ ፲፥ ቍጥር 55]
➣ "ዲያቆናት ድኆች ሳይለምኗቸው ፈቃዳቸውን ሊያደርጉላቸው አገባብ ነው።"[መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ምዕራፍ ፲፮፥ ቍጥር 55]
፯. ዲያቆን በድቁና የተካነ ካህን ነው። ቄስም በቅስና የተካነ ካህን ነውና በአጠቃላይ ማኅበረ ካህናት አይደለም በfb በሕዝባውያን መዋኛ ገንዳዎች እንዲዋኙና ለሕዝባውያን ገላቸውን እንዲያሳዩና ተገላልጠው እንዲታዩ፥ ቁንጣ፥ ጃፖኒ፣ ጥብቅብቅ የሚያደርጉ አልባሳት አድርጎ ውጭ መታየት ፈጽሞ አይፈቀድላቸውምና....
✍️ "አንተ ግን ትታጠብ ዘንድ በወደድህ ጊዜ የሕፃንነትህን ደም ግባትና የሰውነትህን ማማር እንዳያዩ በአንተም እንዳይሰናከሉ። አንተም እንዳትበድል፤ በእነርሱም እንዳትሰነካከል፤ ሴቶች ወደሚታጠቡበት መታጠቢያ ቤት አትግባ።"[መጽሐፈ ዲድስቅልያ፤ ምዕራፍ ፪]
👌ጸጉር አቆራረጥንም በተመለከተ ለምዕመናን ሲገልጽ የቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን የሕግና የሥርዓት መጽሐፍ የሆነው ፍትሕ መንፈሳዊ ወሥጋዊ "በተፈጠርህ ጊዜ እግዚአብሔር በሰጠህ መልክ ላይ መልክ አትጨምር። ያድግ ዘንድ ፀጉርህን አትከባከበው ተላጨው እንጂ አታሳድገው። ወጥመዳቸው ቅርብ የሆነ ሴቶችን ወደ አንተ ያመጣብህ ዘንድ አታሳምረው። ረቂቅ ልብስ አትልበስ፤ ይህች ስሕተትን ታመጣለችና፤ ቀለም የተቀባ ጫማ አትጫማ፤ በጣቶችህ የወርቅ ቀለበትን አታድርግ፤ ይህ ሁሉ የዝሙት ምልክት ነውና። ጠጉርህን ግልስልስ ብጥር አታድርገው፤ አትሠራው፤ " [ፍትሕ መንፈሳዊ፤ አንቀጽ ፲፩፤ ገጽ. 123] ካለ ለካህናቱ እንዴት ጥብቅ ይሆን???
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
@And_Haymanot
👍1
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
አስታርቂኝ


አስታርቂኝ ድንግል ማርያም /2/ 
ከልጅሽ /3/ ከመድኃኔዓለም 

አስታርቂኝ ኃጢአትን ሰርቼ 
አስታርቂኝ ጫካ ውስጥ ቆሜአለው 
አስታርቂኝ ሥራዬ አሳፍሮኝ 
አስታርቂኝ ዘወትር አነባለው 
አስታርቂኝ ልጄ አዳም ብሎ 
አስታርቂኝ አምላኬ ሲጠራ 
አስታርቂኝ እነሆኝ ለማለት 
አስታርቂኝ አንደበቴ ፈራ 
አዝ ------------ 
አስታርቂኝ ሀብትን ተካፍዬ 
አስታርቂኝ ከገዛ አባቴ 
አስታርቂኝ ከቤቴ ኮበለልኩ 
አስታርቂኝ ይሻለኛል ብዬ 
አስታርቂኝ ገፍቼ ወጥቼ 
አስታርቂኝ የቤቴን ገበታ 
አስታርቂኝ ልበላ ተመኘሁ 
አስታርቂኝ የእንስሳት ገፈራ 
አዝ--------- 
አስታርቂኝ ወደ አባቴ ልሂድ 
አስታርቂኝ አሁን ተነሥቼ 
አስታርቂኝ ይቅርታ ልጠይቅ 
አስታርቂኝ እግሩ ስር ወድቄ 
አስታርቂኝ ልጅነቴ ቀርቶ 
አስታርቂኝ አድርገኝ ባርያህ 
አስታርቂኝ ከሞያተኞችህ 
አስታርቂኝ እንደ አንዱ ቆጥረህ 
አዝ ------ 
አስታርቂኝ ገና ሩቅ ሳለው 
አስታርቂኝ አባቴ አይቶኝ 
አስታርቂኝ ወደእኔ ሮጦ 
አስታርቂኝ አቅፎ ነው የሳመኝ 
አስታርቂኝ ጠፍቶ የነበረው 
አስታርቂኝ ተገኘልኝ አለ 
አስታርቂኝ ሞቶ የነበረው 
አስታርቂኝ ደግሞ ሕያው ሆነ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot
                    
ቅዱስ ትውፊት

#ቅዱስ ትውፊት በዘመነ ሐዋርያት

✞ ቅዱስ ትውፊትን በዘመነ ሐዲስ ስንመለከትም፥ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሦስት ዓመት በላይ ሕዝቡን ደቀ መዛሙርቱን የነበረው በጹሑፍ አልነበረም ቅዱሳን ሐዋርያትም ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበሉት በወረቀት የተጻፈ ነገር አልነበረም ወንጌላውያን ከጌታ በቃል ተምረው በተግባር አይተው ኃላ የሚጽፉትን እየዞሩ አስተማሩ እንጂ አስቀድመው ጽፈው ጠቅሰው አላስተማሩም መጻሕፍት መጻፍ የጀመሩት፥ ቤተ ክርስቲያን በይፋ ከተመሰረተች ከ8 ዓመታት በኃላ ነው (ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት መጀመሪያ የተጻፈው መጽሐፍ የማቴዎስ ወንጌል ሲሆን ይኸውም በ41 ዓ/ም ላይ ነው) እስከዚህ ጊዜ ድረስ ቤተ ክርስቲያን ስትመራ የነበረው በቃልና በተግባራዊ ምልልስ ሲተላለፍ በነበረው ቅዱስ ትውፊት ነው በሌላ አገላለጽ ወንጌል ከመጻፉ በፊት፥ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን በቅዱስ ትውፊት ታውቃለች ወንጌልን ስትኖረው ነበረች

✞ ከጌታችን ጋር ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከዋለበት እየዋሉ፣ ካደረበት እያደሩ ሲየያስተምር፣ ሲጸልይ፣ ሰዎችን ሲያጽናና፣ ድውያነ ስጋን በተአምራት ድውያነ ነፍስንም በትምህርት ሲፈውስ፣ ሙታነ ሥጋንና ሙታነ ነፍስን ሕይወት ሲሰጣቸው ዐይተዋል፤ ሰምተዋል ሥርዓተ ብሉይን አሳልፎ ሥርዓተ ሐዲስን ሲሠራ ተመልክተዋል ነገር ግን ይህን ሁሉ በትውፊት ለተላውያነ ሐዋርያት (Apostolik Fathers- ተላውያነ ሐዋርያት የሚባሉት ከሐዋርያት በቀጥታ የተማሩ ክርስቲያኖች ናቸው) አስረከቡት እንጂ፥ እነርሱ ራሳቸው እንደነገሩን ሁሉንም አልጻፉልንም የጻፉልን እጅግ ጥቂቱን ብቻ ነው /ዮሐ 21፥25/ ስለዚህ ቅዱስ ትውፊት እያልነን ያለነው፥ እንዲህ አይነቱን በገቢርና በቃል ዕለት ዕለት በቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ሕይወት የሚገለጠውና አንድ ጊዜ ለቅዱሳን የተሰጠውን ሃይማኖት ነው /ይሁዳ 3/

✞ ቅዱስ ትውፊት ዋና ማዕከሉ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በሌላ አገላለጽ ቅዱስ ትውፊት ወንጌል ነው በዘመነ ብሉይ ቢነገር ይወርዳል ይወለዳል ብሎ ነው፤ በዘመነ ሐዲስ ቢነገር ደግሞ ወረደ ተወለደ ብሎ የምስራችን ለትውልድ ሁሉ በቃልም፣ በገቢርም፣ በጹሑፍም የሚያውጅ ነው፤ ቅዱስ ትውፊት "ወንድሞች ሆይ! የሰበክኁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባቹሀለው በከንቱ ካላመናችው በቀር ብታምኑስ በምን ቃል እንደ ሰበክኁላችው አሳስባችኃለው እኔ ደግሞ የተቀበልኩትን ከሁሉ በፊት ሰጠኃችው" እንዲል /1ኛ ቆሮ 15፥1/

# ትውፊትና እድገት

☞ ብዙ ሰዎች ሁልጊዜ የቀደሙትን ከተመለከትን እድገታችንና የትውልዱ የፈጠራ ችሎታ ይቋረጣል ብለው ይሰጋሉ ነገር ግን ትውፊት እድገትን አይገድብም፤ እንዲያውም እድገቱ የተስተካከለ እንዲሆን ያደርጋል

✞ ማደግ ማለት የራስን ትቶ የሌላውን ብቻ መቀበል አይደለም የራስ የሆነውን በአግባቡ መጠቀም ማለት ነው እንጂ እድገታችን እንጀራን አጥፍቶ ፓስታ ብቻ ለምን አንበላም?፣ የሐበሻ ቀሚስን አሣድደን ለምን እርቃንን የሚያጋልጠውን አንለብስም?፣ የዘመን አቆጣጠራችን ይቅርና በአውሮፓ ቀመር ይተካ፣ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ተጥሎ የነሞዛርት ቅኝት ይምጣልን አይነት ከሆነ ጉዟችን ወደ እድገት ሳይሆን አንገትን ቆርጦ ለፀጉር አበጣጠር የመጨነቅ ያህል ነው የራሳችን የሆነውን ወደን አክብረን የበለጠ የሚያድግበትን መንገድ ከሆነ ያ እድገት ተብሎ ሊጠራ ይችላል የሰጎን እንቁላል ስለጠፋ ጉልላት ይቅር አይባልም ሰጎን እናርባ ይባላል እንጂ፤ ካህን ስላጠረን ምእመኑ ይቀድስ አይባልም ልጆቻችንን እናስተምራቸውና ካህን እናድርጋቸው፣ ሹመት እናሰጣቸው ይባላል እንጂ አለም እኮ የሚጓዘው በአንድ አቅጣጫ ብቻ አይደለም በተቃራኒውም ሊያመራ ይችላል የወንጀል አሰራር፣ የውንብድና ኑሮ እየረቀቀና በቴክኖሎጂ እየተደገፈ በመጣ ቁጥር እድገት ብለን ከቆጠርን ተሳስተናል

✞ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ አበው የቀደምት አበው የቤተ ክርስቲያን አሠራር፣ የአምልኮ ስርአቱ፣ ልብሰ ተክህኖውን፣ ጽንአውን፣ ዕጣኑን፣ መንበሩን ወዘተ ከጥንቷ ቤተ መቅደስ ለቤተ ክርስቲያን እንደሚገባ አድርገው ተረከቡት እንጂ በዘመኑ ሰልጥኖ የነበረውን የግሪካዊ- ሮማ ፍልስፍና አልጨመሩበትም ይህም የሆነው ስልጣኔው፣ ፍልስፍናው፣ እውቀቱ ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን የዚህ ስጋዊ ፍልስፍና ውጤቱ እግዚአብሔርን መካድ፣ ስጋዊ ፍላጎትን ማርካት፣ ምድራዊ ድሎትን ማደላደል መሆኑን ስለተገነዘቡ ነው ለምሳሌ፦
☞ ሰዓሊያን ስዕለ ቅዱሳንን ሲስሉ ቤተ ክርስቲያን በቃልና በጹሑፍ ያቆየችውን መሠረት አድርገው ገለጡት እንጂ የራሳቸውን አመለካከትና ፍላጎት ተጠቅመው ትውፊትን በመሻር ልቦለድ ስዕል አላቀረቡም

# ቅዱስ_ትውፊት_ቅዱስ_ካልሆነው_ትውፊት_እንዴት_ይታወቃል?

✞ በቤተ ክርስቲያን ያለው ሁሉም በትውፊት የተገኘ ላይሆን ይችላል እያንዳንዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው ነገርም የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪ መንፈስ ቅዱስ የሰጣት ነው ማለት አይደለም አንዳንድ ሰዋዊ ነገሮችን ልናገኝ እንችላለን ነገር ግን እነዚህ የሰው የሆኑ ነገሮች በራሳቸው ኃጢአት ወይም ስህተት ላይሆኑ ይችላሉ ይሉቁንም ለዋናው የቤተ ክርሱቲያኒቱ ቅዱስ ትውፊት ማቀላጠፊያ ወይም ማስተላለፊያ መንገዶች ሊሆኑ ይችላሉ ለምሳሌ፦ ድምጽ ማጉያ፣ መቅረጸ ድምጽ፣ ሲዲ፣ ዲቪዲ፣ እና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል ስለዚህ ዋናውን የቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊትና ጊዜአዊው ማቀላጠፊያን ለይተን ልናውቅ ይገባናል

✞ ቤተ ክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች ጉባኤ እንደመሆኗ መጠን፥ እነዚህ ክርስቲያኖችም በተለያየ ግብረ ዓለም ሊያዙ ስለሚችሉ ይህን የዓለም ስራ ይዘው ቢመጡና ግብራቸውን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቢያሰርፁ፥ ይህ ክፉ ግብር እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሊቆጠር አይገባውም በመሆኑም ለቅዱስ ትውፊት ቀኖናዊ መመዘኛ እንዳለው ተረድተን ቅዱሱን ትውፊትና ቅዱስ ያልሆነውን ትውፊት ለይተን ልናውቅ ይገባናል /2ኛ ተሰ 2፥15/ ትውፊት ሁሉ ከሐዋርያት ተያይዞ የመጣና ሐዋርያዊ ቤተ ክርስቲያናዊ ይዘት ያለው መሆን አለበት፤ ከጥንት ጀምሮ በየትም ቦታ፥ ሁል ጊዜ በዓለም አቀፋዊት ቤተ ክርስቲያን የታመነ የተጠበቀና በተግባር ላይ የዋለ መሆን አለበት፤ በዓለም አቀፋዊት ቤተ ክርስቲያን ዘንድ መለወጥና መቋረጥ ያልተገባው መሆን አለበት

✞ እንደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምሮ ሃይማኖት የሚቀበሉት ተቀብለውም የሚኖሩት ለቀጣዩ ትውልድም ሳያፋልሱ የሚያስተላልፉት እንጂ በየጊዜው የሚጨመርበት ወይም የሚቀነስበት አይደለም በፕሮቴስታንቱ አለም ደግሞ ከካቶሊካውያኑ ፍጹም ተቃራኒ በመሆን ቅዱስ ትውፊትን አንቀበልም ይላሉ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻውን በቂ እንደሆነ ያስተምራሉ ነገር ግን ይህም ቢሆን ፍፁም የተሳሳተ ትምህርት ነው አንድ ቀላል ምሳሌ እናንሳና ትምህርታቸው ምን ያህል ስህተት እንደሆነ እናሳይ
☞ እሑድን እንደ ጌታ ቀን አድርገው ያከብራሉ በብሉይ ኪዳን እንዲከበር የታዘዘው ግን ቅዳሜ ነው /ዘፀ 20፥8/ ቅዳሜን ትተው እሑድን ማክበር ከየት አገኙት? ዳግመኛም የጌታችንን ልደት፣ ጥምቀት፣ ትንሳኤ እንዲሁም በዓለ ኃምሳ አብረውን ያከብራሉ ነገር ግን ይህን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም አይገኝም ሌላ ጥያቄም እንጨምር ወደ ዓለም ሁሉ የተሰማሩት ሐዋርያት 12 መሆናቸውን ወንጌል ይነግረናል ነገር ግን ሁሉም ጹሑፍ አልጻፉም አላስተማሩም ማለት ግን አይደለም ታዲያ ትምህርታቸው የት አለ? ትምህርታቸውን የምናገኘው
ሦስት ነገሮች ይደንቁኛል፦
፩. ከአባቱ የማያንስ ልጅ
፪. እናቱን የፈጠረ ልጅ
፫. ፈጣሪዋን የወለደች ድንግል
@And_Haymanot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
``የተፈጠረ እንጂ ያልተወለደ``
(ቢመርም ጠጣው)

ውኃ ያላረጠበው የበረሃ ተጓዥ ጥምቀት ያላራሰው; ጣዖት የለበለበው ተፈጣሪ ግን ያልተወለደ; አባት ያለው ግን ልጅ
ያልሆነ የተፈጠረ እንጂ ያልተወለደ አሕዛብ! ጸሎተ ሃይማኖታችን ላይ 318ቱ ሊቃውንት ወልድ የተወለደ እንጂ ያተፈጠረ` ብለውታል! ተወዳጆች! እኛ ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ ``የተወለድንም የተፈጠርንም እንባላለን` የተፈጠርን-
መባሉ በአርአያ ሥላሴ ስለተፈጠርን ሲሆን ፤``የተወለድንም መባሉ በጥምቀት ተወልደናልና ነው፡፡ ልዩ የሆኑት አሕዛብ መናፍቃን ግን የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ`` ናቸው፡፡
አሕዛብ/መናፍቃን ``የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ ከተባለለት አምላክ ያልተወለዱ ሆነው ቢገኙ `የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ አሰኘባቸው፡፡ መፈጠርን አግኝተዋል የነፍስ መወለድን ግን አላገኙም፤በሥጋ ተወልደዋል ከጥምቀት የሚገኝ መንፈሰ ልደት
ግን አላገኛቸውም፤በምጥ ተወልደዋል ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ በረቂቅ አልተወለዱም፤ተስዕሎተ መልክ አግኝተዋል ተሥዕሎተ ሥላሴን ግን አላገኙም ፤አካለ ሥጋን አግኝተዋል በሜሮን ግን አልከበረም፤መብለ ሥጋን ይበላሉ ቁርባኑ ግን አላሻተታቸውም፤ይጠጣሉ ጠበል ግን አልዳበሳቸውም ፤በከበረው ቤት ኖረዋል የከበረች ቤ/ክ ውስጥ ግን አልኖሩም፤ዓለምን ሁሉ ያውቃሉ ቤ/ክን ግን አያውቋትም፤ቤ/ክን ይጠሏታል እርሷ ግን ሥራቸውን እንጂ እነሱን አትጠላቸውም እነዚህም… እንደ ኦሪቱ ያልተገዘሩ ቆላፎች ሸለፈት ጌጣቸው
አንባር ዝናራቸው የሆነ በሐዲስ ኪዳኑ
የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ`` አሕዛብ ናቸው! ለማያውቁት ይሰግዳሉ የሚያውቃቸው ግን በሌላ አምላክ
ቀይረውታል እሱም ያዝንባቸዋል!
በአርአያው ፈጥሯቸው ሳለ አርአያውን ለማያውቁት ይሰግዳሉ! ከነፍስ መንጺያ ጥምቀት ይልቅ የሥጋ መንጸትን ይሻሉ!
ከክርስቶስም ሥጋና ደም ይልቅ የክርስቲያች ደም ያጸድቃቸዋል! ስለዚህ ተፈጥረዋል ግን አልተወለዱም ! ለአባትነቱ ሲል ፈጥሯቸዋል አባትነቱን ግን አላመኑለትም ምክንያቱም አልተወለዱምና! ለጌትነቱ ፈጥሯቸዋል እነሱ ግን አገልጋይነቱን አልፈለጉም! ለንጉሥነቱ ፈጥሯቸዋል ግን ስላልተወለዱ ሕዝብ መሆንን አላገኙም! በውኃ ውስጥም አልፈው ሥላሴን አላገኙም! ለፍቅሩ የሰጣቸውን ለልጅነት የሚሆን ሰውነታቸውን ለአላዊው
ዲያብሎስ ገበሩት እርሱም ለማያውቁት መስገድን ለሚያውቁት መገዳደርን አስተማራቸው! በጥምቀት መወለድን ትተው በመፈጠር ብቻ ቆሙ!
ስለዚህ ያልተወለዱት በተወለዱት ላይ አመጹ! መኖራቸው አነደዳቸው አመጹባቸውም! መኖሪያዎቻቸውን አነደዱ ስፍራዎቻቸውን ተቀራመቱ በስፍራዎቻቸውም ይጠጋሉ መሬት
ይከባሉ ጽነትን ያደርጋሉ ይቆረቁራሉ ያሰፋሉ ያስተጋባሉም የጥምቀት ውኃ ባላበረደው ሰውነት ያመኑትን ይጻረራሉ !
የተወለዱት ግን ያያሉ ይታዘቡማል ይመረምራሉ ይማጸናሉ ! አይጠሉም ይወዳሉ ሰውን ያይደለ ክፉ ግብርን ይጸየፋሉ! ስለዚህም አሕዛብ ተፈጥረው ቆሙ መወለድን ግን አልፈለጉም!
አሕዛቡ የማመናቸው መሠረት የተወለዱት ባለመኖራቸው ላይ ሆነ፤መኖራቸውን የሚያረጋግጡት የተወለዱትአለመኖራቸውን
ቅድሚያ አረጋግጠው ነው! ቢቻል ስፍራዎቻቸውን ማጥፋት ባይቻል መውረስ ባይቻል ተጠግቶ ቁር-ብትና(ብርዳም ጎረቤት፤አንድም ቁርበታም የሆነ ጎረቤት) ሆኖ መገኘት ነው! የተወለዱት ግን እንደ ልጅ ይኖራሉ - ምክንያቱም አባት አላቸውና! እንደ ባርያ ይኖራሉ -ምክንያቱም ጌታ አላቸውና !
እንደ አገልጋይም ይኖራሉ-ምክንያቱም ንጉሥ አላቸውና! በአንድነት ይኖራሉ ምክንያቱም - አንድ አምላክ አላቸውና!
ከሁሉም አስቀድሞ ደግሞ ጌታቸውን በ40/80 ቀን በውኃ ውስጥ ሦስት አካል ሆኖ አግኝተውታል! አባ አባ ማለትን አስለምዶ አንደበታቸው ሲፈታ አባታችን ሆይ ማለትን አስለምዷቸዋል! እነዚያ አሕዛብ ግን ``አባታችን ሆይ አይሉም
ምክንያቱም አባት ሳላቸው ልጅ አልሆኑለትምና! ምክንያቱም
`
የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ ናቸውና!
By:- ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሼር ዝም አንበል
@And_Haymanot
ጥምቀት ዘንድሮም ደቡብ ላይ አይከበርም ብለውናል
👉 ይግባኝ ለክርስቶስ 🙏🙏🙏
@And_Haymanot
+ መስቀል አደባባይና ቤተ ክርስቲያን +
ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
Share
ከሁለት ወራት በፊት "የጥምቀተ ባሕር ቦታዎችንና የአደባባይ በዓላትን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ልትጠቀምባቸው ትችላለች?" በሚል ርእስ የተለያዩ ባለሙያዎችን አስተያየት ያካተተ አንድ ጥናታዊ ጽሑፍ በማዘጋጀት ላይ ነበርሁ፡
ጽሑፉ እንደ ተጠናቀቀ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በዝርዝር ውይይት አደረግን፡፡ ጉዳዩን ለብፁዓን አበው ለማቅረብና ወደ ይፋ ውይይት ለመግባትም ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ ነበርን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ነገሮችን
የሚገለባብጥና ስሜት የሚነካ የሰሞኑ አሳዛኝ ክስተት ተፈጠረ::በተለይ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን በምእመናን ላይ የተደረገው አሳዛኝ ሁኔታ ፣ ከዚያ በፊትና በኋላ ሲደረጉ የነበሩት ልብ የሚያቆስሉ ስድድቦች እጅግ
የሚያሳዝኑ ነበሩ:: አሁን በዚህ ዘመን ችግር ያነሰን ይመስል ሌላ ችግር መጨመር ነበረብን? ወይ የሚያሰኝ ሆነ፡ በስሜት የምንናገራቸውና የምናደርጋቸው ነገሮች ቁጣን ከማብረድና ሥራ
የሠራን ያህል እርካታ እንዲሰማን ከማድረግ ያለፈ ውጤት እንደማያመጡ የታወቀ ነው:: በሌላው ተመልካች ዘንድም ‘ልማዳቸውን ነው ይጩኹ’ የሚል ንቀት ከማትረፍ ውጪ ምንም አያመጣም፡፡ ስለዚህ በየአቅጣጫው መፍትሔ
የምንለውን ብንጠቁምና ቤተ ክርስቲያናችንን ብናግዝ የተሻለ ስለሚሆን እኔም በምክረ ሃሳቡ ላይ የተካተቱ አንዳንድ ሃሳቦችን ጨምሬ የተሻለ ነው የምለውን መፍትሔ ለመጻፍ ግድ ሆነብኝ፡፡

1. የመስቀል አደባባይ ሕጋዊ ይዞታ ጉዳይ

ቤተ ክርስቲያን ካሏት ነገሮች በተጨማሪ ብዙ ነገሮችን ከሀገሪቱ ልትጠይቅ የሚገባት ብዙ ሚሊዮኖችን የያዘች ሕጋዊ ማንነት ያላት ተቋም ናት፡፡ በዚህ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋን በአግባቡ ከተጠቀመች አንዱን የመስቀል
አደባባይ ብቻ ሳይሆን ብዙ መስቀል አደባባዮችን ገንብታ አሁን የመወያያ ርእስ
የሆነውን የመስቀል አደባባይ የትኩረት ማእከልነቱን እስከ ማሳጣት ድረስ አቅም
ያላት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ከከተማው ስፋትና ከምእመናን ብዛት አንጻር በየክፍለ
ከተማው አንድ አንድ መስቀል አደባባዮች እንዲኖሩ ማድረግ የማትችልበትም
ምክንያት የለም፡፡ ሆኖም አሁን እንኳን ሌላ ሊጨመር ያለውም የባለቤትነት ጥያቄው አደጋ ላይ ነው፡፡ አደባባዩ የብዙኃን ዓይን ያረፈበትም በከተማው ቦታ ጠፍቶ ሳይሆን ሥፍራው በኦርቶዶክሳውያን ልብ ውስጥ ያለውን የምልክትነት ሥፍራ በመረዳት መሆኑ ግልፅ ነው:: "ሜዳው ሰፊ ነው : ፈረሶቹ ሁለት ናቸው ግን አሳልፈኝ አሳልፈኝ ይባባላሉ" እንደሚባለው ብሂል ነው:: ቤተ ክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ላይ የምታቀርበው በቂ የሰነድ ማስረጃና ታሪካዊ
እውነት እንዳላት ግልጽ ነው፡፡ ‘እውነት ነፃ ያወጣችኋል’ የሚል አምላክን እስካመነች ድረስም የተሻለውና ዋጋ ቢከፈልለትም የማያስቆጨው አካሔድ ይኼው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን መብትዋን የምታስከብረውም ታሪካዊ ሰነዶችን ፎቶ እያነሱ በማኅበራዊ ድረገጽ በመለጠፍ ወይንም ጊዜያዊ ትኩሳትን ተንፈስ በሚያደርጉ መግለጫዎች ብቻ ሳይሆን የሕግ ሰዎችን ፣ የመሬት ሰነዶች ላይ ልምድ ያላቸው
ባለሙያዎችን ፣ የዘርፉ ኤክስፐርቶች የሆኑ ልጆችዋን ያቀፈ አካልን እንዲወክላት በማድረግ ጉዳዩን በተገቢው ትኩረት እንዲፈታ በማድረግ ነው፡፡ ይህንን በማድረግ ችግሮችን ሌላ ተጨማሪ ችግር ሳይፈጥሩ መፍታት ይቻላል፡፡ ከዚያ ውጪ ግን ችግሩን ብቻ ማውሳት ምእመናን የተጠቂነት ስሜት ውስጥ እንዲገቡ
ከማድረኛ ቤተ ክርስቲያንዋንም ክብር ከማሳጣት ያለፈ ጥቅም የለውም፡፡
ይቀጥላል.....
@And_Haymanot
+ መስቀል አደባባይና ቤተ ክርስቲያን +
ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
Share
2. መስቀል አደባባይን ‘የመስቀል አደባባይ’ ማድረግ

እንደሚታወቀው መስቀል የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ በዓልዋ መሆኑ የታመነ ነው፡፡ ሆኖም የመስቀል በዓል ከመንፈሳዊ በዓልነቱ ይልቅ ፌስቲቫላዊ ቅርፁ በጣም የሚያይል አከባበር ያለው በዓል ነው፡፡ እንደሚታወቀው በበዓሉ ዕለት ቤተ ክርስቲያን ከምትጠቀምበት ሰዓት ይልቅ የተለያዩ የፖለቲካ ሰዎችና ተጋባዥ እንግዶች ርዝመቱ የማይገመት ንግግር
የሚያደርጉበት ሰዓት ይበዛል፡፡ የቤተ ክርስቲያንዋም አካላትም ከመንፈሳዊ
ስብከት ይልቅ መንግሥትንና ተጋባዥ ዲፕሎማቶችን ማእከል ያደረገ ‘የተከበሩ
አቶ እገሌ’ የሚበዛው ንግግር ሲያደርጉበት ይስተዋላል፡፡ በዓለ መስቀልም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለመዳሰስ ሰበብ ሆኖ ያገለግላል እንጂ ወደ አደባባዩ መጥቶ ስለ ጌታችን መስቀል ምንም ዓይነት ነገር ሰምቶ የሚሔድ ምዕመን የለም፡፡ በደርግ ዘመን እንኳን ከብዙ ችግር ጋር እነ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የሰበኩት ‘ዮም መስቀል ተሰብሐ’ የሚል ስብከት ተጠቃሽ ነበር፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግን መስቀል አደባባይ ላይ የሚተላለፉ መልእክቶች
እንዴት በዓሉን ከወቅታዊ ትኩሳት ጋር እናስተሳስረው በሚለው ላይ ብቻ ያተኮሩ
ናቸው፡፡ ከዚያ ውጪ መስቀል አደባባይ በአግባቡ ምሕላ እንኳን ደርሶበት አያውቅም፡፡ ሐቁን ለመናገር እንደ መስቀል በዓል አከባበርም መስቀሉን የሚቀብር ተራራ የለም፡፡
የምእመናን በዓል እንደመሆኑ ከውጪ የሚመጡ እንግዶች ሕዝቡ በዓሉን ሲያከብር መመልከት ሲገባቸው በመስቀል አደባባይ ግን ሕዝቡ የውጪ እንግዶች በዓሉን ሲያከብሩ ከሩቅ ሆኖ ይመለከታል፡፡ ነፋስ የሚያማታውን
የስፒከር ድምፅ እየተከተለ ጭብጨባ ሲሰማ ያጨበጭባል፡፡ የአደባባዩ መርሐ ግብር አስተዋዋቂ አሁን እንዲህ እየተከናወነ ነው ሲል እየሰማ ሥፍራው ላይ ያለው ሕዝብ በቤቱ በቴሌቪዥን ከሚመለከተው ሰው ያነሰ መረጃ ኖሮት ተደናብሮ ይመለሳል፡፡ አንዳንዴም ደመራው ቶሎ አልበራ ሲለው በፉጨትና
በጭብጨባ ፍጠኑ ይልና ሕዝቡ ራሱ ጧፍ በመለኮስ በዓሉን ያስጀምራል፡፡ አንድ ስብከት ሳይሰበክ ፣ አንድ መዝሙር በወጉ ሳይሰማ ሊቃውንቱ ፣ መዘምራኑ የኦሎምፒክ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት እንደሚታዩት አትሌቶች ምንም ሰዓት ሳያገኙ በጥድፊያ አልፈው እንዲያልፉ ይደረጋል፡፡ አብዛኛው የሰንበት ትምህርት ቤት
ወጣትና የማኅበራት መዘምራን መስቀል ሲመጣ እንደ ትልቅ አገልግሎት የሚያዩት ከበዓሉ ዕለት ይልቅ ለበዓሉ ሲዘጋጁ የሚያቀርቡትን ዝማሬና ወደ አደባባዩ እስከሚደርሱ ድረስ በመንገድ ላይ የሚዘምሩትን ዝማሬ ነው፡፡ የልዩ ልዩ ሚዲያ ጋዜጠኞችም መስቀሉን መቅበራቸው የተለመደ ነው፡፡ ‘የዘንድሮን የመስቀል በዓል ካለፈው ዓመት የተለየ የሚያደርገው ግድቡ በተገባደደበት ማግስት ላይ በመሆናችን ሲሆን’ የሚል ዘገባ ያቀርባሉ፡፡ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ለቃለ መጠይቅ ያቀርቡና ‘መስቀል ከሃይማኖታዊነቱ ባሻገር ለሀገር የሚያበረክታቸው እሴቶች ምን ምን ናቸው?’
‘የመስቀል በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡ ያለው ጠቀሜታ ምንድን ነው?’ የሚሉ በየዓመቱ እንደ ችቦው የማይቀሩ ችክ ምንችክ ያሉ ጥያቄዎችን ያቀርባሉ፡፡ በማግስቱም የመንግሥት ሚዲያዎች ስለ ክትፎ አሠራርና ስለ ቆጮ አዘገጃጀት ቀኑን ሙሉ ሲያብራሩና ዘፈን ሲጋብዙ ይውላሉ፡፡ ታሪኩን የማያውቅ ሰው ንግሥት እሌኒን የጉራጌ ንግሥት ፣ መስቀሉም ከክትፎ ውስጥ ተቆፍሮ የተገኘ ሊመስለው ይችላል፡፡
ብቻ በአጭሩ መስቀልን ሲያስታውስ አንድ ነገር ጨበጥሁ የሚል ሰው ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ደመራው የሚለኮስበት ውብ ሰዓት ላይ ብቻ ሕዝቡ በእልልታና በጧፍ እያጀበ ሰውነትን የሚነዝር ዝማሬ ያቀርባል፡፡ አሁን አሁን ቀረ
እንጂ ደመራው የወደቀበትን አቅጣጫ እንደ ሀገሪቱ ፖለቲካ ኮምፓስ ቆጥሮ ወዴት ወደቀ ብሎ በጭንቀት የሚጠይቅም ብዙ ሰው አለ፡፡ ከዚያ በኋላ መስቀል አደባባይ ለሰዓታት ብቻ መስቀሉን አክብሮ አገልግሎቱ ያበቃል፡፡
ይህንን በማድረግ ፈንታ ቢያንስ ከዋዜማው ጀምሮ እንኳን ቤተ ክርስቲያን አደባባዩን መጠቀም መቻል አለባት፡፡ ዓለምን ያስደመሙት የኢትዮጵያ መስቀል ዓይነቶች ለሀገር ውስጥና ለውጪ ጎብኚዎች በዐውደ ርእይ የሚታዩበትና
ለሽያጭ የሚቀርቡበት ፣ የኢትዮጵያ የመስቀል ዐውደ ጥናት የሚካሔድበትና በዘርፉ ላይ ጥናት የሠሩ ባለሙያዎች ጥናት የሚያቀርቡበት ፣ የቤተ ክርስቲያንዋ የያሬዳዊ ዜማ ሀብታት በአደባባይ የሚታዩበት ፣ በዕለቱ ተካልበው
የሚያልፉት የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በዋዜማው ምሽት አደባባዩን ሞልተው ዋዜማውን በዝማሬ የሚያሳልፉበት ፣ በዕለቱ የሚቀርበውም ትርዒት የተመጥነና ለሕዝቡ ትደራሽ እንዲሆን በባለሙያዎች የታገዘ ቢሆን ፣ ቤተ ክርስቲያንዋ በበዓሉ ላይ ለሚገኘው ሕዝብ አንዳንድ የገቢ ማሰባሰቢያ ሥራዎችን የምትሠራበት ሁኔታ ቢመቻች መስቀል አደባባይ እውነትም መስቀል አደባባይ መሆን ይችላል፡፡
@And_Haymanot
+ መስቀል አደባባይና ቤተ ክርስቲያን +
ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
Share

3. ግንቦት ልደታ


በመስቀል አደባባይ ሊከናወን የሚገባውና ከይዘቱ አንጻር ተገቢ የሆነው ሌላው የአደባባይ በዓል የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሆነው የግንቦት ልደታ በዓል ነው፡፡ ግንቦት ልደታ በቤተ ክርስቲያንዋ ከቤት ውጪ በምሽት በድምቀት
ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ነው፡፡ ይህንን በዓል በውጪ እንዲከበር ያደረገው ድንግል ማርያም የተወለደችው በቤት ውስጥ ሳይሆን በተራራ ላይ የነበረ መሆኑን ለማስታወስ ነው፡፡ ይህንን በማስመልከት ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናን
ከቤታቸው ውጪ ሆነው በዓሉን ያከብራሉ፡፡
ከዓመታት በፊት በግንቦት ልደታ በዓል ታሪክ ዙሪያ አነስተኛ ጥናታዊ ጽሑፍ በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ትእዛዝ በሠራሁና ባቀረብሁበት ወቅት ለመገንዘብ እንደቻልሁት ግንቦት ልደታ በኢትዮጵያውያን
ዘንድ እንደየ ብሔር ብሔረሰቡ የተለያየ ቅርፅ ያለው ቢሆንም ትልቅ ቦታ ሊሠጠው የሚችልና ለቱሪስት መስሕብ ለመሆን የሚችል እምቅ እሴት የያዘ ሀገራዊ ቅርስ ነው፡፡ ይህ እጅግ ድንቅ የሆነ በዓል በመስቀል አደባባይ የመከበሩን ተገቢነት ድንግል ማርያምን ከመስቀል ጋር በሚያስተሳስሩ ጸሎቶችዋና ዜማዎችዋ የምትታወቀው የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚደግፈው ነው፡፡ በብዙ ሀገራት በብሔራዊ በዓል ደረጃ የሚከበረው ይህ በዓል በቤተ ክርስቲያን ደረጃም ቢሆን በሚመጥነው ክብር ቢከበር በቤተ ክርስቲያኒቱ ተልእኮና በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚፈጥረው በጎ ተጽዕኖ ቀላል አይደለም፡፡

4. የጥምቀተ ባሕር ሜዳዎች

ቤተ ክርስቲያናችን ጥምቀተ ባሕር ላይ ሰፋፊ ሥራዎችን ለመሥራት ዕቅድ እንደያዘችና ሥራ እንደ ጀመረች ብፁዕ አቡነ ያሬድ ይፋ ያደረጉት የጃን ሜዳ ፕሮጀክትና ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በመግለጫቸው የዳሰሱአቸው ርእሰ ጉዳዮች ምስክሮች ናቸው:: ቤተ ክርስቲያናችን እነዚህን ቅዳሴ የሚደረግባቸው ክቡራት ሥፍራዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ፓርኮች ሆነው መገንባት: የሕፃናት ማጫወቻዎችና ስፖርት ማዘውተሪያዎች : ከሱስ ማገገሚያ ማእከላት ሊሆኑም ይችላሉ::
በተጨማሪም በዓላት በደረሱ ቁጥር ልዩ ልዩ ባዛሮችና መንፈሳዊ ዐውደ ርእዮች ከጉባኤያት ጋር ቢካሔዱባቸው በዓልን በስካርና ጭፈራ ከማክበር ብዙኃንን ማዳን ይቻላል:: የግንቦት ልደታ በዓልም ከመስቀል አደባባይ በተጨማሪ
በጥምቀተ ባሕር የሚካሔድ መሆን ሲችል ደብረ ታቦርና የእመቤታችን ትንሣኤ (አሸንዳም) እንዲሁ ጥምቀተ ባሕር ላይ መከበር ይችላል:: እጃችን ላይ ያሉ በጎ ዕድሎችን በአግባቡ ከተጠቀምን እጃችን ላይ የሌሉትንም እንጨምራለን:: "ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት
ትመጣለች" ዮሐ. 9:4 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 4 2014 ዓ.ም.
"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም
ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share
ያድርጉ :-
የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://tttttt.me/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/
UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
@And_Haymanot
የምስራች
🙏🙏🙏
በሆሳዕና ከተማ ጥምቀት ይከበራል🙏
እንኳን ደስ አላችሁ ተወዳጆች
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot