፩ ሃይማኖት
8.98K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ስራው ተሰርቷል

ተወዳጆች የመስቀል አደባባይን ጉዳይ አተራማሾቹ ባሰቡት ጉዳይ ሳይሆን በዚህ መልኩ ተጠናቋል 👏👏
=>አስተውሉ ስንተባበር ማንም አይችለንም እና ሼር በማድረግ እንዲህ ድምጻችንን እናሰማ

በቅርቡም በቻናላችን የምንተባበርባቸውን ጉዳዮች ይዘን እንገኛለን ምን ትላላችሁ?
፩ ሃይማኖት
Photo
ታፍኛለሁ!

#Ethiopia | የአረማውነት ሥራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጊዜያት
ሞክሬ አልተሳካም! በምስጢር ተቀድቶ የወጣው የቪድዮ መልእክታቸው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ታፍኛለሁ አሉ።
«ስለ ትግራይ ስናገር ድምጼ ይታፍፈናል። በትግራይ ጭካኔ
የተሞላበት የአረመናዊነት ድርጊት እንዲቆም ብዙ ጊዜ ሞክሬ አልተሳካም። ሚያዝያ 7 ያደረኩት ኢንተርቪው ታግዷል። ስቃወም ድምጼ ይታፈናል። የአለም ሚዲያ እየተናገራው እኛ
እንዳንናገር ታፍነናል።» በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ብዙ ግፍ ተሠርቷል። በትግራይ ላይ የተደረገው ግን ይበልጣል በማለት ተናግረዋል።
ለዓለም መንግሥታት፣ ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት የተለየ የድጋፍ ጥያቄ ጠይቀዋል። "የአለም ሚዲያ እየተናገረው እኛ እንዳንናገር ታፍነላል"
"ባሁን ጊዜ በሀገራችን በኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው አረመኔያዊነት፣ የአረማውነት ስራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጊዜያት ሞክሬ አልተሳካም ፤ ምክንያቱም ፍቃድ አልተሰጠም። እናገራለሁ ይመልሱታል፣ እናገራለሁ
ይመልሱታል፤ ይኸው እስካሁን ጊዜ ምንም አይነት ፍቃድ
አልተገኘም።

እናም ሁላችሁም ወገኖቻችን ማወቅ ያለባችሁ፣ እዚህ ያለውን ችግር፣ የኔን ችግር የማውቀው እኔ ነኝ።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ
ተክለሃይማኖት
@And_Haymanot
​​✞ ግንቦት ፩ እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከኢያቄምና ከሐና ስትወለድ የሆነውን ነገር ሐዋርያው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊ መጽሐፍ ሲገልጽ፡፦
@And_Haymanot
"And Joachim(ኢያቄም) said: Now I know that the Lord has been gracious unto me, and has remitted all my sins . And he went down from the temple of the Lord justified,
and departed to his own house. And her months were fulfilled, and in the ninth month Anna(ሐና) brought forth. And she said to the midwife: What have I brought forth? And she said: A girl. And said Anna: My soul has been magnified this day. And she laid her down. And the days having been fulfilled, Anna was
purified, and gave the breast to the child, and called her name Mary." The Protoevangelium of James, 5
👉 @Konobyos
👉 @And_Haymanot
አስተካክለኝና ትክክል ልኹን

@And_Haymanot

“ተወዳጅ ሆይ! እግዚአብሔር አይሰማኝም አትበል፡፡ አንተ ተናገር
እንጂ ርሱ ይሰማኻል፤ ባትናገርም ያደምጥኻል፡፡ ኾኖም ርሱ አንተን ሲሰማኅ ችግሮችኅ ይስተካከላሉ፤ ርሱን ስትሰማው ደግሞ አንተ ትስተካከላለኅ፡፡

ያልተስተካከለን ችግር የተስተካከለ
ሰው ይሻገሯል፤ ያልተስተካከለ ሰው ግን የተስተካከለን ችግርም አይሻገርም፡፡ “እንዴት?” ብለኽ ከጠየቅከኝ ግን መልሴ
“አካሔድ የማያውቀውን የተነጠፈም ጐዳና ጠልፎ ይጥለዋል” የሚል ነው፡፡ ከችግሮች ኹሉ እኛ ችግሮች ስንኾን ቀኖች ይከብዳሉ፡፡ መሣሪያው ሲበላሽ ሥራው ይበላሻል፡፡ ስለዚኽ መሣሪያው ተሠርቶ ሥራው ይሠራል፡፡ አንተ ከተበላሸኽ የሚስተካከል ነገር የለም፡፡ አንተ ከተስተካከልክ ግን ሌላው
ቢበላሽ ራስኽን ታድናለኽ፡፡ “ከምንም ነገር አንድ ነገር” ይባላልና ይሔ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ነገር ግን ወዳጄ! እውነት
እውነት እልኻለኁ እመነኝ፤ አንተ ስትስተካከል ብቻኽን አትስተካከልም፡፡ በተስተካከለ የሚስተካከሉ፣ በዳነ የሚድኑ ብዙዎች ናቸውና፡፡ የአየር ንብረቱን ዐይቶ ልብስን ማስተካከል
ካለ የዘመንን መልክ ዐይቶ ልብን ማስተካከል ተገቢ ነው እልኻለኁ፡፡ ፀጉርን ለማስተካከል ከአስተካካዩ ጋር፣ የከበረ ልብስን ለማስተካከል ከአልባሹ ጋር፣ ዕውቀትን ለማስተካከል ከመምህሩ
ጋር፣ … ትገናኛለኅ፡፡
@And_Haymanot
ሕይወትን ለማስተካከል ግን ማንን አግኝተኅ ይኾን? አንተን ለሕይወት የሠራኅ እንጂ ሌላ ማንም አያስተካክልኽም፡፡ ሰው ኹሉ ከራስኅ በላይ የሚነፍስ ነፋስ ኾኖብኅ “ለእኔ እኔ - ከእኔ ወደ እኔ” ብለኅ ከራስኅ ጋር ቃል ኪዳን ተጋብተኽ አዲስ ኑሮ ዠምረኽ ነበር፡፡ ነገር ግን ለመስተካከል ዓቅም አጥተኽ የመስተካከልን በጐ ፈቃድ ብቻ
ይዘኅ ቀረኽ፡፡ ስንት ዘመን የራስኽ ጥበብ ስንፍና፣ የራስኽ ብርታት ድካም፣ የራስኽ ሙከራ መከራ እንደኾነብኅ ዐውቂያለኹ፡፡ ስለዚኽ ለፈጠረኽ ጌታ ራስኽን አሳልፈኅ ለመስጠት ወስን፡፡ በራስኽ ላይ እንደዚኽ ዓይነቱን ውሳኔ
እንደማስተላለፍ አስቸጋሪና እጅግ ውብ የኾነ ነገር በዚኽ ዓለም ላይ አታገኝም፡፡ ወደ ፈጠረኽ መምጣትኅ ዥማሬኅ ነው፤ ከርሱ ጋር ያለው ቈይታኅ ዕድገትኅ ነው፤ ርሱን አምነኅ እንደኖርኅ አምነኅ ስትሞትም ሕይወትኅ ነው፡፡ እውነት አንተስ ዕድለኛ ነኽ!!! እናም ምክሬን ስጠቀልልኅ፡- የእውነት ልመና “ጌታ ሆይ!
አስተካክለኝና ትክክል ልኹን!” የሚል መኾኑን ደግሜ በማስታወስ ነው፡፡ “እንዳስተውል ርዳኝ፤ በሕይወትም አኑረኝ” / መዝ.118፡144/፡፡”
© ዲ/ን ቃለኣብ ካሣዬ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የእግዚአብሔርን ቅጣት ፈርቶ ንስሓ መግባትና የእግዚአብሔርን ቅድስና ፈልጎ ንስሐ መግባት ይለያያል።

☞ እውነተኛ ክርስቲያንም ንስሐ የሚገባው ገሃነመ እሳትን ፈርቶ
ሳይኾን የመንግሥተ ሰማያትን ጣዕም ስለሚናፍቅ ነው።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ክርስትና ማስቀደስ ሳይሆን መቀደስ ነው ለሚለው ኑፋቄ የተሰጠ ምላሽ

📝 @And_Haymanot

ብዙ ጊዜ ፕሮቴስታንት ወገኖቻችን ይህንን ቃል ደጋግመው ሲያነሱ እና እውነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስመስለው ፌስ ቡክ ላይ ሲለቁት ተመልክታችሁ
ይሆናል፡፡ይህንንም የሚያደርጉበት ምክንያት ቤተክርስቲያንን ለመቃወም እና ምእመኑን ከእውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን ለማውጣት እና ለዲያብሎስ ለማስረከብ በማሰብ ነው፡፡ ቤተክርስቲያናችን ዘወትር እግዚአብሔርን በልቧ በተግባርና በአምልኮ ስርአቷ ትቀድሰዋለች /
ታመሰግነዋለች/፡፡
✏️ ቅዳሴ ማለት “ቀደሰ አመሰገነ” ከሚለው የግዕዝ ቃል
የመጣ ሆኖ “ማመስገን፣ ማወደስ፣ ማገልገል” የሚል ትርጉም አለው፡፡ (ቅዳሴ ማለት ምስጋና ማለት ነው)፡፡ መናፍቃን ግን ለመተቸት ‹‹ክርስትና ማስቀደስ ሳይሆን መቀደስ ነው››እያሉ ሲፎክሩና ሲሸልሉ በሀይማኖት ያልበሰሉትንም ሲያደናግሩ እንመለከታለን መጽሐፍ ቅዱስ ስለቅዳሴ/ጌታን ስለመቀደስ ምን ይላል እስቲ እንመልከተው፡፡
@And_Haymanot
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፥15 ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። ትንቢተ ኢሳይያስ 8፥13 ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን። የማቴዎስ ወንጌል
6፥10 ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
ኦሪት ዘኍልቍ 20፥12 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና
ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም አላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 11፥2 አላቸውም። ስትጸልዩ እንዲህ በሉ። በሰማያትየምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ ታዲያ ቤተክርስቲያን ምን አጠፋች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባገኘችው ቃል ነው ቅዳሴ የምትቀድሰው/ ጌታን የምታመሰግነው።
ጌታ ለመናፍቃኑ ልቦና ይስጣቸው
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሼር ማድረግዎን አይርሱ
ከሆሳእና ክርስቲያኖች ጎን ነን በሕብረትም እንቆማለን
#Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
መልካምነት

አንድ ሰው ሶሰት ጓደኞች ነበሩት በጣም ነው የሚወዳቸው ብዙ ነገር ያደርግላቸዋል ያደርጉለታልም፡፡ አንድ ቀን አባቱ "ልጄ ጓደኞች አሉህ" አሉት "አዎ ሶስት ጓደኞች አሉኝ በጣም የሚወዱኝ የምወዳቸው" አላቸው፡፡ እርሳቸውም "ከእነዚህ ውሰጥ የልብ ጓደኛህ ማነው?" አሉት "ሁሉም" አለ "እርግጠኛ ነህ ልጄ" ሲሉት "አዎ" አለ፡፡ "እንደዚያ ከሆነ የሆነ ነገር እንፍጠርና እውነተኛ መሆናቸውን እናረጋግጥ" ይሉታና ጓደኞቹን እንዲፈትን ያደርጉታ፡፡ ልጁም አባቱ ባለው መሰረት ለአንዱ ጓደኛው ይደውልና "ያለጥፋቴ ሰው ገድለሃል ተብዪ ፍርድ ቤት ነኝ ድርሰልኝ" ይለዋል ጓደኛውም "አዝናለሁ አልችልም" ይለዋል፡፡ አሁንም ለሁለተኛው ይደውላል ሁለተኛ ጓደኛውም "ችግር የለውም እመጣለው እርዳታየም ካሰፈለገህ የምችለውን ሁሉ አደርግልሀለው ፍርድ ቤት ግን አብሬህ አልገባም አዝናለው" ይለዋል አሁንም ለሶሰተኛው ይደውላል ሶሰተኛውም "እንዴ ኧረ ችግር የለውም ደሞ ለአንተ አይደለም ፍርድ ቤት ሌላም ቦታ እመጣልሃለሁ" አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ይህ ልጅ በአባቱ ምክር እውነተኛ የህይወት ጓደኛው ማን እንደሆነ አረጋገጠ ።

ፍርድ ቤት የተባለው የሰው ልጅ ይችን ዓለም ተሰናብቶ የሚኖርባት የዘላለም ቤቱ ሲሆን

1-የመጀመሪያው አልችልም ያለው ገንዘብ ነው መቸም የሰው ልጅ በዚች ምድር ሲኖር ምን ያህል ሀብት ቢኖረው ከሞት አያሰጥለውም በሞት ጊዜ ተከትሎን አይመጣም ።

2-ሁለተኛው ፍርድ ቤቱ አመጣለው እረዳሃለሁ እንጅ አልገባም ያለው ዘመድ ወይም ጓደኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሰው ምን ያህል ቢወድህ ያለቅሳል ያዝናል ወደ ቀብር ቦታህ አብሮህ ይመጣል እንጅ መቸም አንተ ሞተሀልና ልሙት አይልም።

3- ሶሰተኛው እሰከ መጨረሻው አንተ ጋ ነኝ ያለው በዚች አለም ሰትኖር የሰራናቸው ጥሩና መልካም ሰራዎች ናቸው፡፡ በዚህ ምድር ላይ የምንሰራቸው ጥሩ ሰራወች የዘላለም ሰንቃችን ናቸው እስከ መጨረሻው ከአኛ ጋር ይከተሉናል፡፡

ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክንያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ አለውና ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና።

🍀🌸 🌸🍀
💐 @And_Haymanot 💐
🌺🍂 @And_Haymanot 🍂🌺
💐 @And_Haymanot 💐
🍂🏜💒🏜🍂
ቅዱሳን ሥዕላት


የተሃድሶ መናፍቃን ቅዱሳን ሥዕላትን አይቀበሉም፤ በሥዕል ፊትም አይጸልዩም፤ ጭራሽም ሥዕልን ማክበር ጣዖትን እንደ ማምለክ ይቆጥሩታል እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን ቅዱሳት መጽሐፍትን መሠረት አድርገን ለቅዱሳት ሥዕላት ተገቢውን ክብር እንሰጣለን።

✞ በዘፀ 20፥3 ላይ የተቀረጸውን ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸውም፣ አታምልካቸውም የሚለውን ትእዛዝ የሰጠው እግዚአብሔር አምላክ በዘፀ 25፥16 ላይ "ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ስራ" ብሎ ሙሴን አዝዟል ይህም ቅዱሳት ሥዕላት ቁጥራቸው ከጣዖት እንዳልሆነ የሚያመለክት ነው እግዚአብሔር አምላካችን የሰው ልጅን ጣዖት እንዲሰራ አያዝምና ከዚህም በተጨማሪ እስራኤል በኃጢአታቸው ምክንያት በእባብ መንጋ ሲነደፉ በዘኁ 21፥8 ላይ "እባብ ሰርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፣ የተነደፈውንም ሁሉ ሲያየው በሕይወት ይኖራል" ሲል አዝዞት ነበረ ነገር ግን ይህ እንደ ጣዖት አምልኮ አልተቆጠረም እንዲያውም በዘኁ 21፥9 ላይ "እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ" ተብሎ ተጽፏል ጌታችንም በዮሐ 3፥14 ላይ ሙሴ በምድረ በዳ የሰቀለው እባብ የእርሱ መሰቀል ምሳሌ መሆኑን አስተምሯል።

✞ ንጉሡ ሰሎሞንም የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ በሠራ ጊዜ በ1ኛ ነገ 6፥23 ላይ እንደምናነበው በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆኑ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ በዚህ የተነሳ እግዚአብሔር መምለኬ ጣዖት ነህ አላለውም እንዲያውም በሌሊት ተገለጠለት እንጂ ንጉሥ ሰሎሞንም የኪሩቤልን ሥዕል ብቻ ሳይሆን "የዘንባባ ዛፍ፣ የፈነዳም አበባ ምስል ቀርጾ" ነበር /1ኛ ነገ 6፥29-35/ ነገር ግን ይህ እንኳን የጣዖት ምስል አስቀረፀ አላስባለውም።

እኛ ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳት ሥዕላት ክብርና የአክብሮት ስግደት ይገባቸዋል እንላለን እንጂ አናመልካቸውም የአምልኮ መፈጸሚያዎች ናቸው እንላለን እንጂ የአምልኮ ስግደት አንሰግድላቸውም፤ ሥዕሎቹ በራሳቸው አንዳች ምስጢራዊ ኃይል ኖሯቸው ሳይሆን የሥዕሉ ባለቤት በሥዕሎቹ አማካኝነት ኃይሉን፣ ተአምሩን ይገልጣል ብለን ግን እናምናለን ሙሴ በበትሩ ባሕረ ኤርትራን ከፍሏል፣ ኤልሳዕ በኤልያስ ልብስ ዮርዳኖስን ከፍሎ ተሻግሯል፣ የቅዱስ ጳውሎስ ልብስ ድውያንን ፈውሷል፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ አጋንንትን አውጥቷል... እነዚህ ሁሉ ነገሮች ግን በራሳቸው አንዳች ኃይል ኖሯቸው ሳይሆን የባለቤቱን ቅድስና ያስገኘላቸው ጸጋ ነው።

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስተምረን እመቤታችን ጌታን እንደታቀፈች አድርጎ የመጀመሪያውን ሥዕል የሳለው ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው ይህም ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ሥዕላት በቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ቦታ ያመለክተናል ከዚህም በላይ በኢየሩሳሌም፣ በባዛንታይን፣ በኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በሌሎችም ሀገሮች የጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ፍርስራሾች በቁፋሮ ሲገኝ ቅዱሳን ሥዕላትም ይገኛሉ ይህም ሥዕሎችን ለመንፈሳዊ አገልግሎት መጠቀም ከጥንት ክርስቲያኖች ጀምሮ የነበረ መሆኑን ያሳያል።

❖ በ7ኛው መ/ክ/ዘ ቅዱሳት ሥዕላትን በተመለከተ አሁን የተሃድሶ መናፍቃን የያዙትን ሃሳብ ይዘው የተነሱ ሰዎች ነበሩ እነዚያኞቹ ከዚያም አልፈው ቅዱሳት መጻሕፍትን ከምድረ ገጽ ለማጥፋትም ተነስተው ነበር እነዚህ ጸላዕያነ ሥዕላት "ኢኮኖማኺያ" በመባል ይታወቁ ነበር ትርጉሙም "ሥዕላትን የሚጠሉ" ማለት ነው ይህ አስተሳሰብ በ720 ዓ/ም አካባቢ ተነስቶ እስከ 843 ዓ/ም ድረስ ለአንድ መቶ አመታት ያህል ቤተ ክርስቲያንን ሲያወዛግብ ቆየ፤ ጉዳዩ የበለጠ እንዲሰፋ ያደሰገው ደግሞ ሥዕሉን ከባለ ሥዕሉ በላይ የሚያከብሩና የሚያመልኩ ክርስቲያኖቼ/ኢኮኖላትሪያ/ መፈጠራቸው ነው።

በዘመኑ የነበሩት ነገስታት የሥዕል አጥፊዎችን ሀሳብ በመደገፋቸው ለ700 ዓመታት የተሰበሰቡ አያሌ ጥንታውያን ሥዕሎች እንዲጠፉ ተደረገ ሁኔታው ግን ሊበርድ አልቻለም ሥዕሎች አማልክት አይደሉም፣ ነገር ግን ሊከበሩ ይገባቸዋል የሚለው ሃሳብ እያየለ መጣ በዚህም ምክንያት ችግሩ በተነሳበት በባዛንታይንና ሮሜ አካባቢ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በ787 ዓ/ም ጉባዔ አድርገው "ለቅዱሳት ሥዕላት ክብር እና ሰላምታ ይገባል፤ ለእነርሱ የሚደረግ ክብር እና ሰላምታ ሁሉ ለሥዕሉ ባለቤት የሚደረግ ነው እነርሱን የሚያከብር ሁሉ በሥዕሉ ላይ የተገለጠውን ነገር ማክበሩ ነው" በሚል ወሰኑ።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህንን የአባቶቻችንን ስርአት ተከትላ ለቅዱሳት ሥዕላት ክብርና የአክብሮት ስግደት ትሰጣለች እንጂ የተሃድሶ መናፍቃኑ በሀሰት እንደሚሉት የጣዖት አምልኮ አይደለም ስለዚህ ከተሃድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርት መጠንቀቅና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለማንኛውም ጥያቄ ምላሽ ያላት መሆኑን ልናውቅ ይገባል።

አምላከ ቅዱሳን የቅዱሳን ሥዕላትን ረድኤት በረከት ያሳትፈን!!! አሜን።

@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጅማ ዩኒቨርሲቲ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ቅሬታቸውን ልከውልናል በተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ቢያቀርቡም ምላሽ ሰጪ አካል ባለመኖሩ በሶሻል ሚዲያ የሚሰማን ካለ በማለት ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል የሚመለከተው አካል ቢረዳቸው በማለት ልናቀርበው ወደናል
1ኛ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ቅዱስ የሆነው የጾም ወቅት ጾመን እንዳለፍን አይዘነጋም ሆኖም ግን ያሳለፍነውን የጾም ወቅት ተማሪዎች እንዳንጾም ተከልክለናል። በሳምንት ውስጥ ለ4 ቀን የምናቀርበውን ስጋ ብሉ አለዚያ ጦማችሁን እደሩ እየተባለ ነው ኮስትሼሪንግ በሚል የምንከፍለው እንዳለ ነው፣ እሱ አይደለም አሁን ላይ ያለው የተማሪ ጥያቄ ይሄ በሃይማኖት ጸንቶ የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ነው እስካሁን ድረስ ተማሪው ላይ እየደረሰ ያለው ጫና እጅግ ቡዙ ነው፤ ሌላው ቀርቶ ጅማ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ #ነጠላ ማድረግ የትምህርት ሂደቱን ያውካል በማለት ትከሻ ላይ ሲደረግ እንኳን "አውልቁ እና በእጅ ያዙ" ነው ምንባለው እባካችሁ የእስካሁኑ ይበቃናል ቢያንስ ይሄን እውነት ለህዝበ ክርስቲያኑ አድርሱልን፣ አሁን አንደኛ ዓመት አዳዲስ ተማሪዎች ይመጣሉ እንደሚታወቀው ከፊታችን በፍቅር የምንናፍቃት ጾመ ፍልሰታ እየተቃረበች ነው ያኔስ እንዴት ነው ሚኮነው? እኔ አላውቅም አደራ አደራ አደራ ድምጽ የለንም እና ድምጽ ሁኑን ...
--------
ተወዳጆች ባላችሁበት የሚመለከተው አካል እንዲረዳቸው እየተማጸንን ሌሎቻችሁም በጸሎት እንድታስቧቸው ለማሳሰብ እንወዳለን የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
+ ለአራት ቀናት ብቻ ለሞተው አልዓዛር ያለቀሰ ጌታ ለዘመናት በኃጢአት ለሞትን ለእኛ ምንኛ ያለቅስ ይሆን?
+ ሰውነታች በበደል ለረከሰ ፣ በምኞት መቃብር ለተቀበርን ፣ በዝሙት ለተበላሸን ፣ በጥላቻ ለሸተትን ለእኛ ክርስቶስ ምንኛ ያለቅስ ይሆን?
+ የኃጢአት ድንጋይ ተጭኖን ፣ የፍትወት መግነዝ ተጠምጥሞብን ላለን ለእኛ የጌታ ዕንባ ምን ያህል ይፈስስልን ይሆን?
+ አልዓዛርስ ውጣ ቢባል ይወጣል ፣ ካለንበት ኃጢአት መቃብር መውጣት ለማንፈልግ ለእኛ ጌታ እንደምን ያለቅስ
ይሆን?
+ የእኛ ሞት ከአልዓዛር ሞት በላይ ዘልቆ
የማይሰማው ይመስላችኋል?
+ እንዴት
አይሰማውም? ለአልዓዛር ዕንባውን ያፈሰሰው ጌታ
ለእኛ እኮ ያፈሰሰው ደሙን ነው ። ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ጅማ ዩኒቨርሲቲ

ተወዳጆች በቅርቡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚካሄደውን የእምነት ነጻነትን ማጣት እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊያኑ ላይ የሚደርሰውን በደል ማቅረባችን አይዘነጋም በውስጥ እያደረሳችሁን ያለውን ተመልክተናል
👉 መምህራኑን በእምነታቸው ከስራቸው ማፈናቀል
👉 ተማሪዎችን በጾም በነጠላ በትምህርታቸው ከሚሰሩት ፕሮጀክቶች አንስቶ ሌሎች በደሎችም እየደረሰባቸው መሆኑን በውስጥ እያደረሱን ነው
👉
👉 ስራ ላይ ላላችሁ መምህራን ክርስቲያናዊ ሃላፊነታኣችሁን እንድትወጡ ስንል በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን
👉
በተጨማሪም የሚመለከተው የቤተክርስቲያናችን አካል ይበልጥ ቢመለከተው ለማለት እንወዳለን🙏
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው።

1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ።

ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።

የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።

ሰው ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ።
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
በፈተና ጊዜ፥ ደካማው ሰው "እንደዚህ የደረሰብኝ'ኮ" እያለ የሚያመካኝበት ሌላ ሰውን ይፈልጋል፤ ብርቱው ሰው ግን በፈተናው ይጸና ዘንድ እግዚአብሔርን ይፈልጋል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት:
ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ

@And_Haymanot

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ እንመለከታለን፡፡

ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ. 6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30)
@And_Haymanot
ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡

ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)

አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ "የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ አይሹትም ፣ አይደረግምም" የሚለውን በመጥቀስ የሐዲስ ኪዳነ ታቦትን ይቃወማሉ። ቃሉ የተነገረው ለእስራኤል ቤት ሲሆን እስራኤላውያን በእርግጥም የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው አይሹትም። በኦሪት ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃልኪዳን በአዲስ ኪዳን ተተክቷል። ይህ ከሐዲስ ኪዳን መሠዊያ ጋር የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ "አዎ እስራኤል አይሹትም" ብለን እንመልሳለን።
የአሁኑ ታቦት የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት ከቀድሞው አንድ ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው::

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109)

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ.
1
2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያ

ከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡

የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡
@And_Haymanot
የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት ‹‹አንዱ ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡
ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡

ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት ደግሞ እኚሁ ጸሐፊና በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡ ‹‹In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice-Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints.

It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡
@And_Haymanot
‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) http://www.stmarkdc.org/coptic-sanctuary ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡

ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡
@And_Haymanot
አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም!
@And_Haymanot

....ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 10 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሃይማኖት አይወረስም? 🤔
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
👇👇👇👇👇👇
ሐይማኖት አይወረስም?

@And_Haymanot

ተወዳጆች የተሃድሶ መናፍቃን ሃይማኖት አያስፈልግም፤አያድንም፤አይወረስም በማለት ብዙዎችን ለማደናገር ይሞክራሉ ከዚህ በፊት በስፋት የዳሰስነው ርዕሳችን ቢሆንም በውስጥ ለጠየቀን ወንድማችን እነሆ ብለናል

ሐይማኖት አይወረስም ላልከን እንዲህ የምናምነውንም እንመሠክራለን! > እንግዲያውስ ከኃይማኖት በላይ ሊያወርሱት እና ሊወርሱት የተገባ የከበረ ነገር በዚች አለም የለም። ሰው መልካም መልካሙን ነገር ለልጆቹ ያወርሳል ከመልካም ስጦታዎች ሁሉ የሚልቀውን የዘላለም ሕይወት የሚገኝበትን ሐይማኖት ከማውረስ የበለጠ ታላቅ ውርስ እንዳውም በጭራሽ አይገኝም።

ሰው በምድር ላይ ለልጆቹ የሚሆን ታላቅ መኖሪያ ቢያወርስ ነገር ግን የዘላለም ሕይወት የሚያገኙበትን ሐይማኖቱን ግን ባያወርስ ምን ይረባቸዋል! ??
ሁለት ነገርን አደፈረስክ! መጀመሪያ ሐይማኖት ሊወረስ የተፈቀደ መሆኑን ካድክ ሲቀጥል ደግሞ በገዛ ድምዳሜክ ገባህና ሐዋርያት ከሀድያን ናቸው አልክ! እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።
አስቀድመህ በራስህ አላዋቂነት የደመደምከው ድምዳሜ ላይ የተመረጡትን ሁሉ አጋጭተሀል።
በመሰረቱ ሀይማኖት ለሰው ልጆች የተሰጠችው ልንጠብቃት እና ለትውልድም ልናወርሳት ነው።
አብርሃም አባታችን ለአይሁድም ሆነ ለሀዲስ ኪዳን ህዝቦች አባት ነው። ከህግ ለሆኑት የመገረዝ አባት ነበረ። ከእምነት ለሆንነው ደግሞ የእምነት አባት ነው። የፃድቅ አብርሃም
ሕይወት ለእኛ ምሳሌ ነው። አብርሃም እግዚአብሔር ን አመነ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረለት ነገር ግን ይህ ብቻ አልነበረም ጉዳዩ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለአብርሃም ትዛዝን ሲሰጠው ልጆችህ ቃል ኪዳኔን እንዲጠብቁ አድርግ በሚል ጠንካራ
ማሰሪያም ጭምር ነው። አብርሃምም በቤቱ ለተወለዱት ልጆች ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ገና በተወለዱ በ8 ቀናቸው ጀምሮ ይፈፅምላቸው ነበር። የእርሱን ሐይማኖት ለልጆቹ ገና በስምንት ቀን ጨቅላነታቸው እያሉ ጀምሮ እንዲቀበሉ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለሆነ ነው። ልጆችም በአባቶቻቸው
ሐይማኖት ተወስነው እንዲኖሩ ነው የጌታ ትእዛዝ። ስለዚህ ሐይማኖት ይወረሳል። ከሐይማኖት የበለጠ ለልጅ ሊያወርሱት የሚገባ መተኪያ የሌለው ውድ ነገርስ ከየት ይገኛል???
ዘፍጥረት 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን አቆማለሁ፥
#ለአንተና_ከአንተ_በኋላ_ለዘርህ_አምላክ_እሆን_ዘንድ
⁸ በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ለዘላለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ አምላክም እሆናቸዋለሁ።
⁹ እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ አንተ ደግሞ ቃል ኪዳኔን ትጠብቃለህ፥ አንተ ከአንተም በኋላ ዘርህ በትውልዳቸው።
¹⁰ በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል የምትጠብቁት ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፤ ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ።
¹¹ የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፤ በእኔና በእናንተ
መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።
¹² #የስምንት_ቀን_ልጅ_ይገረዝ ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።
¹³ በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘላለም ቃል ኪዳን ይሆናል።
¹⁴ የቍልፈቱን ሥጋ ያልተገረዘ ቈላፍ ሰው ሁሉ፥ ያች ነፍስ ከወገንዋ ተለይታ ትጥፋ፤ ቃል ኪዳኔን አፍርሳለችና።//

ሮሜ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ለተገረዙትም አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ
አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው።
¹³ የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው
የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም።
¹⁴ ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል
የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤
¹⁵ ሕጉ መቅሠፍትን ያደርጋልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም።
¹⁶-¹⁷ ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ
ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት #የሁላችን #አባት #ነው
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot