፩ ሃይማኖት
8.98K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
#ከማኅበረ_ሥላሴ_አንድነት_ገዳም_የተላከ_መልዕክት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቢያንስ ለ 15 የተዋህዶ ልጆች Share በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ።


#በኢትዮጵያና_በመላው_ዓለም_ለምትገኙ_ኦርቶዶክስ_ክርስቲያኖች_በሙሉ_ከጥቅምት_24_እስከ_30_ከህፃናት_እስከ_ሽማግሌ_ማንም_ሳይቀር_በማህበረ_መነኮሳቱ_አማካኝነት_ፆም_ታውጇል::
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱአምላክ አሜን በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኛችሁና በደሙ የዋጃችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ በቤታችሁም ያላችሁ በህመም ምክንያት በሆስፒታል ያላችሁ በማረሚያ ቤት ያላችሁ በጦር ሜዳም ያለችሁ እንዲሁም በተለያየ ስፍራ የምትገኙ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የከበረ ሰላምታችንን በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡
እኛ ማኅበረ ስላሴ እንድነት ገዳም የምንገኝ ማኅበረ መነኩሳት በሀገራችን ሰላም መታጣት ምክንያት ከሀዘናችን ጋር አምላክ አበው ክብር ምስጋና ይግባዉ ደኅና ነን፡፡
እግዚአብሔር ገና ሃያ ሁለቱን ስነ-ፍጥረት ፈጥሮ ሳያበቃ ሳጥናኤል በዓለተ ረቡዕ በሶስተኛዉ ሰማይ በጌታ ላይ በማመጽ በጀመረዉ ጸብ ምክንያት ከመላዕክቱ ጋር ተዋግቶ ተሸንፎ ወደ
ምድር ተጥሎ እነሆ ያለ እረፍት ለሰባ ሺ አምስት መቶ አመታት በመላዉ ዓለም ደም ሲያፈስ ቆይቷል፡፡ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ፡፡ ጌታ የተሰጠዉ የቀጠሮ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ታግሶታል፡፡ አሁን ግን ከወትሮዉ ለየት ያለዉ ነገር የእግዚአብሔር ቤተ -
መቅደስ በሆነችዉና የቅዱሳን የአስራት ሀገር በተሰኘችው በኢትዮጵያ ሀገራችን የሳጥናኤል ጭፍሮች ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት ብለዉ ዘምተዉ በታሪክም ያልሰማነዉ በዘመናችንማ አይተን የማናቀዉ የአርስ በአርስ እልቂት እንኳን ከክርስቲያን ከሰብአዊ ፍጡር የማይጠበቅ ድርጊት ተፈጽሟል እየተፈጸመም ነዉ፡፡
ሰይጣን ብቻዉን ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ከሰዉ ጋር ሆኖ
በሰዉ ልብ አድሮ ግን ምንም የሚቀረዉ የሀጢያት ሥራ የለም፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፡፲፭ ላይ ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ ያለዉ የጌታ ቃል ተጥሷል፡፡
ቀድሞ አንድ ሰዉ ለሥራም ሆነ ለንግድ ወይም ለተለያየ ጉዳይ ወደ ማያዉቀዉ ወደ ሚያዉቀዉም በኢትዮጵያ ክፍላተ
ሀገር ወይም ክልል ሲዘዋወር ለሀገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ነኝ ብሎ አይጨነቅም፡፡ የእግዚአብሔር እንግዳ ተብሎ ከመሸበት ገብቶ እግሩን ታጥቦ ቤት ያፈራውን በልቶ ጠጥቶ ከመልካም
ምንጣፍ ተኝቶ አድሮ ሲነጋ ተነስቶ መርቆ ቀሪዉን ምንገድ ይጓዛል፡፡
ዛሬ ግን ያ ቀረና የእግዚአብሔር እንግዳ እራቱ ጥይትና ገጀራ መጠጡ ደም ሆኗል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ ፳፭፥፵፪ ላይ የተጠቀሰዉ እንግዳ ሆኜ ብመጣ አልተቀበላችሁኝም ብራብ አላበላችሁኝም የሚለዉ የጌታ ቃል ትዉልዱን እየተዋቀሰዉ ነዉ፡፡
በእርግጥም በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ ብሎ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንደተናገረዉ እንግዶች የሰላም ተጓዦች መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ነገር ግን የሰላም ሰዎችም አብረዉ ተጨፍልቀዉ የጥፋት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነ
እግዚአብሔር አሁንም ታግሶናል፡፡እኛ አሁን ከሞት የተረፍነዉ ከጥላ ያረፍነዉ በጽድቃችን አይደለም በቸርነቱ ለንስሐ ጊዜ ተሰጥቶን ነዉ እንጅ፡፡
ነቢያት ስለ ጥፋት ሲተነብዩ በሰዉ ልጅ ሐጥያት ከእግዚአብሔር የሚታዘዘዉን መቅሰፍት ማስገንዘባቸዉን እንጅ ጥፋት ዝም ብሎ ደርሶ የሚታዘዝ አይደለም፡፡
አሁን በኃጢያታችን ምክንያት እየተጎነጨነዉ ያለዉ መከራ ከዚህ
በፊት ብዙ የተነገረ ቢሆንም በትንቢተ ዮናስ ታሪካቸዉ እንደተጠቀሰዉ እንደ ሰብዓዊ ነነዌ ወደ እግዚአብሔር በጾም
በጸሎት ሆኖ በመለመን በማልቀስ መከራዉን ማስቀረት እንዲቻል ቅዱሳን በመጽሐፍት አስተምረዉናል፡፡
በኖህ ዘመን ምድር በዉሃ ሙላት የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት
ነዉ፡፡ በሎጥ ዘመን በሰዶም ሀገር የተቃጠለችዉና ከምድረ ገጽ
የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት ነዉ፡፡
ዛሬስ እየተሰራ ያለዉ ኃጢያት በዚያ ዘመን ከነበረዉ ያንሳልን ? ያን ጊዜስ በንስሀ ላልተመለሱ ሰዎች ፈርዶ ያጠፋቸዉ አምላክ ዛሬስ ፈርዶ ማጥፋቱ ይሳነዋል ወይ ? አይሳነዉም እንዲያዉም እንደ ዘመናችን ኃጢያት ብዛትና ክብደት
ላልፈረደብን እግዚብሔር እያመሰገንን ይህን መልዕክት በያላችሁበት ሲነበብላችሁ ከሰማችሁት በኋላ ወደ ልባችሁ ተመለሱ ከእንግዲህ ወዲህ በዘር ፣ በጎሳ ፣ በቋንቋ ፣ በሀገር ፣
በብሔር መለያየት ይብቃ ፣ መገዳደል ይብቃ ፣ መዘራረፍ ይብቃ፣መሰደድም ይብቃ አጠቃላይ የጥፋት ዘመቻ ይብቃ፡፡ ወደ ቀድሞ ኢትዮጵያዊ አንድነታቸን እንመለስ በኅብረት ተቻችለን እንኑር፡፡
የኃጢያታችንን ካባ አዉልቀን በነብስም በሥጋም የሚያድነንን የንስሐ ካባ እንልበስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፥፲፪ ላይ እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ብሎ ጌታችን ባዘዘብ መሰረት ጥላቻን አስወግደን የዘር ፣የጎሳ፣ የቋንቋ ፣ የክልል ልዩነት ሳይኖረን እርረ በእርሳችን እንዋደድ፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፬፥፳፯ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ያለዉ ጌታ ቃሉ አይለወጥም እና ይህ ከሆነ ብቻ እዉነተኛዉን ሰላም ማግኘት ይቻላል፡፡
የተከበራችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ነብዩ ኢሳያስ በትንቢቱ ምዕ ፩፥፲፱ ላይ ‹‹ እሺ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት
ትበላላችሁ እምቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኃለች የእግዚአብሔር አፍ ይህንን ተናግሯልና›› የሚለዉን የትንቢት ቃል ዛሬም በእኛ ኢትዮጵዊያን ላይ እንዳይደርስብን ለእግዚአብሔር
ቃል እንታዘዝ እና ክፋትን ሁሉ ትተን ንስሀ ገብተን የምድርና በረከት እንብላ፡፡ አለበዚያ ግን ምሕረት በእጁ የሆነ አምላክ መዓተም በእጁ ነዉና ምርጫዉ ግን የእናንተ ነዉ፡፡ በሀገራችን
ሰላም ይሰፍን ዘንድ ማንኛዉም ክርስቲያን የተጣላ ታርቆ ፣ የበደለ ክሶ ፣ ይቅር ተባብሎ ፤ ከጥቅምት ፳፬ እስከ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም ድረስ ልጅ አዋቂ ሳይለይ እስከ ዘጠኝ ሰዓት
እየጾማችሁ በሀዘን በለቅሶ ምህላ በመያዝ ከእግዚአብሔር ምህረትና ይቅርታ በጋራ እንድንለምን እኛ የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም ማኅበረ መነኮሳት ሁሉን በፈጠሩ በቅድስት ሥላሴ ስም አምላክን በወለደች በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በታላቅ አክብሮት መልዕክታችንን ለመላዉ ሕዝበ
ክርስቲያን አስተላልፈናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ሰላም ይስጥልኝ
የሞቱትን ሁሉ ነብስ ይማርልን
የጠፋዉን የተቃጠለዉን የወደመዉን ንብረት ሆሉ ይተካላችሁ አሜን ይሁን ይደረግልን
መምህር አባ ወልደ ሰንበት ነጋሽ
የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም አበመኔት
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Share share share share share share
1 ሰው ለ 15 ምዕመን
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
👍1
አንድ ለዐሥር አደረጃጀት ለኦርቶዶክሳውያን ሁሉ

@And_Haymanot

አሁን በኦሮሚያ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በደቡብ ሲዳማ እያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ጦማረ ሞቱን በእጁ ይዞ የሚንቀሳቀስ ኾኖ ተፈርዶበታል፡፡ በማንኛውም ሠዓት ምንም ዓይነት አደጋ ሊደርስ ይችላል፡፡ ምንም ዓይነት መዘናጋት አይኑር፡፡ የክርስቲያኖች በየቦታው መታረድ ላለፉት ኹለት ዓመታት እየባሰ እንጅ እየቀዘቀዘ አልመጣም፡፡
መንግሥት በተደጋጋሚ መረጃዎች ቢደርሱትም አንዲት ጠጠር እንኳ የማንሣት ያኽል ሊራዳ አልቻለም፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት መፍትሔ ያመጣሉ ሲባል እባካችሁ ዕድል ስጡን
ወደማለት ዝቅ ያለ ደረጃ ላይ መኾናቸውን ከፈረሱ አፍ በቀጥታ
ሰምተናል፡፡ ከሰማይ በታች የሚታደገን ማንም እንደሌለ ቢያንስ አሁን ሊገባን
ይገባል፡፡ የመስቀል በዓልን ለማክበር ተቸግረናል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን በእሳት መማገድ የምድጃ እሳትን የማቀጣጠል ያኽል ቀሏል፡፡ ሥጋችን ሞት አልበቃውም፡፡ እየተቆራረጠ
ለአውሬ እየተጣለ ነው፡፡ አሁንም ግን ጥቅሳቸውን ያልለወጡ ሰዎች ከመካከላችን አሉ፡፡ ራስን መከላከል ይፈቀዳል ወይ? ሲባሉ የለም ቀኝህን
ለሚመታህ ኹለተኛውን ደግሞ አዙርለት ነው የሚለው ይላሉ፡፡ እስቲ እነዚህን ሰዎች ጥቂት እንጠይቃቸው፡፡
 በጦር ሜዳ ስለ ሃይማኖታቸው ሲጋደሉ የወደቁት ግብጻዊው
አቡነ ስምዖን ይህን አያውቁም ነበርን?
 ለጣልያን ጦር አይደለም ሕዝቧ የኢትዮጵያ ምድር እንዳትገዛ
የገዘቱት ኢትዮጵያዊው ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ ተሳስተው
ነበርን? ወንድማቸው አቡነ ሚካኤልስ?
 ንጉሠ ቁዝን በኃይለ እግዚአብሔር ያስወገደው ቅዱስ
ቴዎድሮስ ሰማዕት ሕግ አፍርሶ ነበርን?
 ንጉሥ ሕርቃል ዘምቶ አጽራረ ክርስቲያንን ያስወገደው በማን
ፈቃድ ነበር?
 ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ካሌብ የመን ድረስ ተሻግረው፣ በሀገረ
ናግራን የነበሩ ክርስቲያኖችን ነጻ ያወጡት ተሳስተው ነበርን?
 ለቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ አረአያ መስቀል ሰጥቶ ሒድ
ዝመት ብሎ የላከው እግዚአብሔር የገዛ ሕጉን ሽሮ ነውን?
 በነጠላው ቃሉን እንፈጽም የሚሉት ቀኛቸውን ሲመቱ
ኹለተኛውን ሊያዞሩ ይችላሉ፡፡ ከኹለተኛው በኋላስ ምን
ያደርጋሉ?
ወዳጄ መተርጉማኑ የቃሉን ፍች አስቀምጠውልናል፡፡ በነጠላ
ትርጉም እየነጎድን ሕዝባችንን አናስበላ፡፡ ሊቃውንተ ቤተ
ክርስቲያን ቀኝህን ለሚመታህ ኹለተኛውን ደግሞ አዙርለት
ያለውን ቃል ሲተረጉሙት እንዲህ ብለውታል፡፡ ፈቃደ ሥጋህን
ተው ቢልህ ፈቃደ ነፍስህን ተውለት፡፡ ልብ በሉ ቃሉ የጉንጭ
ወይም የአካለ ሥጋ ጥቃትን ሳይኾን የሚያመለክተው ከዚያ
የላቀ ምስጢራዊ ፍች እንዳለው ነው፡፡
ለምሳሌ በመጽሐፍ “እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ
መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት” ተብሏል፡፡ በነጠላው ትርጉም
እንረዳው ከተባለ ተጠያቂው ያለውን ሁሉ ሲሰጥ ሲሰጥ ራቁቱን
እንዲቀር ነውን? ይህማ አይኾንም አባታችን አዳም ራቁቴን
ስለኾንሁ ፈራሁ ቢለው የቆዳ ልብስ አልብሶታልና፡፡ ነገር ግን
ደግ ሥራን አብዝቶ ለመሥራት አትታክት በሕገ ወንጌል ላይ ሕገ
ትሩፋትን ጨምርበት፣ በሕግ ጾም ላይ የፈቃድ ጾም አክልበት
ማለት ነው፡፡ ባልተስተካከለ ትርጉም መምታታቱን ትተን ራሳችንን ለመከላከል
ቆርጠን እና ጠንክረን እንሥራ፡፡ አሁን ክርስቲያኖች በየሚኖሩበት አካባቢ (ሩቅ ለሩቅ ካሉት ጋር አይደለም) ዐሥር ዐሥር እየኾኑ ሊሰባሰቡ ይገባል፡፡ በተለያየ ምክንያት የተኳረፈ ካለ ሽማግሌ
ሳይጠብቅ ይታረቅ፡፡ አብሮ ለመሥራት ሁሉም ልቡን ይስጥ፡፡ እየተገናኙ መምከር አለባቸው፡፡ መረጃ መለዋወጥ ይገባቸዋል፡፡ ራሳቸውን የሚያድኑበትን መንገድ ለማሰብ ከዛሬ የተሻለ ቀን
የላቸውም፡፡ አንዱ ለሌላው የሚደርስበትን መንገድ የማመቻቸት
ተግባራዊ እንቅስቃሴ ይጀምሩ፡፡ እያንዳንዳቸው በዐሥር በዐሥር
የተደራጁ ክርስቲያኖች በተወካዮቻቸው በኩል ከሌሎች በዐሥር በዐሥር ከተደራጁት ጋር የሚገናኙበት ሠንሰለት ይፈጥራሉ፡፡ የዐሥሩ መሪዎች በአምስት በአምስት ይደራጃሉ፡፡ ማለትም
ከታች ዐሥር ክርስቲያኖች ይኖራሉ፤ ከእነርሱ በላይ የዐሥሩ ተወካዮች የሚገናኙበት አንድ ዕዝ ይኖራል፤ በአጠቃላይ ከሥሩ አንድ መቶ ይኖራሉ፡፡ እነዚህ አንድ አንድ መሪዎች ይመርጣሉ፡፡ ከሌሎች አምስት ተጓዳኞች ጋር ጥምረት ይፈጥራሉ፡፡ በእነዚህ
በአምስቱ ሥር አምስት መቶ ክርስቲያኖች ይኖራሉ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ ከፍ ይላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዴት የራ መከላከሉን ስልት ምስጢር በአደባባይ ይነገራል የሚል ይኖራል፡፡ ይህ አደረጃጀት እንጅ ስልት አይደለም፡፡ ስልቱ ከአደረጃጀቱ በኋላ የሚመጣ ነው፡፡
ፀሐይ ሳይጨልምብን እንሰባሰብ!
ለማተቤ ያለ ሼር ያድርግ!
በመምህር አባይነህ ካሴ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
በጣም አስቸኳይ!!! እባካችሁ መልእክቱን አድርሱ!!!! #አሰቦት ከሴቶች ገዳም አደጋ አንዣብቧል፤
* አቤቱታቸው ለመንግሥት አካላት ይድረስ
------
ለአሰቦት ገዳም ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደገለፁልን ከሆነ በአሰቦት ገዳም በተለይም ሴት መነኮሳይያት በሚኖሩበት
ከተራራው ግርጌ አካባቢ አደጋ እንዳንዣበበ፣ ገዳማውያኑም
መኖሪያቸውን ትተው ወደ ተራራው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መሰባሰባቸው
ተነግሯል። በተለያዩ ጊዜአት የአክራሪዎች የጥቃትት ዒላማ መሆኑ
የሚታወቀም የአሰቦት አባ ሳሙኤል ገዳም ከአሰቦት ከተማ 12 ኪሜ ላይ የሚገኝ ሲሆን እናቶች መነኮሳይያት የሚኖሩበት የሴቶች ገዳም ከእግረ ደብር ይገኛል። ድንጋይ በመወርወር እና
ግቢው ውስጥ በመግባት ችግር እየተፈጠረበት ያለው ይኸው የሴቶች ገዳም መሆኑ ታውቋል። በአካባቢው ያለው መንግሥታዊ አስተዳደርም ሆነ የመከላከያ ኃይል በዚህ ታሪካዊ ገዳም ላይ ያንዣበበውን ከፍተኛ አደጋ
ተገንዝበው አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪአችንን እናስተላልፋለን። ምእመናንም ጉዳዩን ተረድተው የሚችሉትን ሁሉ ያድርጉ።
Cc. Ethiopian Federal Police Commission
ዝርዝሩን እየተከታተልን እንገልጻለን።
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሰላም ተወዳጆች እንደምን ቆያችሁልን በውስጥ በጠየቃችሁን መሠረት በቻናሉ ያለውን አገልግሎት ትምህርቶችን(ስብከቶችን) በድምፅ ልናቀርብላችሁ ወደናል በመጀመርያ እንድንዳስሰው የታሰቡት 👉 ነገረ ክርስቶስ እና 👉 ነገረ ድህነት ናቸው እንድናስቀድምላችሁ የምትፈልጉትን ምረጡ እያልን በሚለቀቁት ክፍላት ላይ ያላችሁን ጥያቄ ትምህርቱን ሥንጨርስ ጠቅለል አድርገን የምናቀርብላችሁ ይሆናል።
public poll

ነገረ ክርስቶስ – 288
👍👍👍👍👍👍👍 64%

ነገረ ድህነት – 161
👍👍👍👍 36%

👥 449 people voted so far.
👍1
ዕለቱ አርብ ነው!


ኢየሱስ ይሰቀል!
ይሰቀል ኢየሱስ!
በርባን ግን ይፈታ!
2 ሺህ ዘመን
ይኸው ትጮሃለች
ዓለም አፍ አውጥታ።
በቀያፋ ምክር
በካህናት አድማ
በጲላጦስ ስልጣን
በግፈኞች ጡጫ
ዛሬም ይወገራል
ጌታ ይሰቀላል።
እውነት ነው!
በድምጽ ብልጫና
በቲፎዞ መድረክ
ለምትመራ ዓለም
ሌባውን አንግሶ
ንፁሁን ከመሸጥ
.
.
.
ሌላ አይጠበቅም።


ምንጭ፦ ፍሬ ተዋሕዶ

@And_Haymanot
@And_Haymanot
Audio
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፩
መምህራን
መምህር ብርሃኑ አድማሥ
መምህር ገብረ መድህን እንየው
አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ኢየሱስ ክርሥቶስ ማን ነው?
ተዋህዶ ምንድነው?

አዘጋጅ ማህበረ ቅዱሳን

size 23mb
ቤተ ክርስቲያን ሆይ ÷ የክብርሽና የልዕልናሽ ፀሐይ እንደ ትላንቱ ሁሉ÷ ዛሬም አይጠልቅም!!
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
🎄 የገና ዛፍ 🎄
🎉🎊 🎁 🎁 🌲
@And_Haymanot

🎄 የገና ዛፍ የነጮች የባዕድ አምልኮ መገለጫ መሆኑን ያውቃሉ? የገና ዛፍ ታሪክና አመጣጡ የገናን ዛፍ የት መጣውን /ምንጩን/ ስናጤነው ቅዱሳት
መጻሕፍት እንዲህ ይነግሩናል። በዞራስተርን የሁለት አማልክት
ዕምነት የሚያምኑት ምዕራባውያን አዲሱን ዓመታቸውን /2017/
ተቀብለዋል። በዞራስተርን የሁለት አማልክት ዕምነት መሠረት ክፉውና ደጉ የተባሉ ሁለት አማልክቶች አሉ። እንደ ዕምነቱ አስተሳሰብ ከሆነ እዚህ ምድር ላይ የሆነው እየሆነው ያለውና
የሚሆነውም ማንኛውም ነገር በሙሉ የሚከናወነው በእነዚህ በሁለቱ አማልክቶች ፉክክር ነው። ክፉው አምላክ ከሰለጠነ /የበላይ ከሆነ/ በምድር ላይ ክፉ የሆኑ ብዙ ነገሮች ይከሰታሉ። በተቃራኒው ደግሞ ደጉ አምላክ ከሰለጠነ በጎ ነገሮች ይከሰታሉ
ማለት ነው። ምዕራባውያኑ ታዲያ ደጉን አምላካቸውን ማለትም ጣዖታቸውን ሳተርን ብለው ይጠሩታል።

በምዕራቡ ዓለም የክረምቱ ወቅት በጣም አስቸጋሪ ነው። ዛፎች ሁሉ ቅጠሎቻቸው ይረግፋሉ። ልምላሜ አይታይባቸውም። ፅድ 🎄 ግን በተፈጥሮው ይህን አስቸጋሪ ወቅት ተቋቁሞ የማለፍ ኃይል አለው። በመሆኑም ፅድ ክፉውን ዘመን /ክረምቱን/ ተቋቁሞ መልካሙ ዘመናቸው እስኪመጣላቸው ድረስ በልምላሜ ይቆይላቸዋል።
💫 ይህም ሳተርን /ደጉ አምላካቸው/ ከክፉው አምላክ ለመሸሸግ በፅድ ውስጥ ተደብቆ ይኖራል ብለው
ያመናሉ ምዕራባውያኑ። እናም ብራ ሲሆን /በእኛ መስከረም ጠባ
እንደምንለው ነው/ የደጉን አምላክ ‹‹የእንኳን ደህና መጣህ›› በዓልን በድምቀት ያከብራሉ። ምስጋና ለፅዱ ይሁንና ደጉ አምላካቸውን ደብቆ ስላቆየላቸው ባለውለታ ስለሆነ የደጉን አምላክ የእንኳን ደህና መጣህ በዓል
ሲያከብሩ ታዲያ ፅድን ለበዓላቸው ማድመቂያነት ይጠቀሙበት ነበር። ይኸው ትውፊታቸው ዛሬም ድረስ አለ። በአጭሩ ከጥንት ጀምሮ እነርሱ ይኽን በዓል የሚያከብሩት ሳተርን ለተባለው
ጣዖት /ደጉ አምላክ/ ያደርጉት የነበረው ሥርዓት ነው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን በአዋጅ
ካስፋፋበት ጊዜ ጀምሮ በውጭው ዓለም ጥንት የነበሩ ብዙ ጣዖታዊ በዓላት ክርስቲያናዊ በዓል ሆነው አሁንም ድረስ በብዙ ሀገራት እየተከበሩ ይገኛሉ። /ነገር ግን ልደትንና ትንሣኤን ጨምሮ ሌሎችም በዓላት ቢሆኑ ሥርዓታቸውን በጠበቁ መልኩ የሚከበርባቸው አንዳንድ ሀገራት እንዳሉ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ
ለማስገንዘብ ይወዳል።/

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ይኸው እስከዛሬ እኛም ይኽንኑ የባዕድና የጣኦት አምልኮ በዓላቸውን በእነሱው ልማድ መሠረት የፅድ የገና ዛፍ እየሠራን
ስናከብርላቸው ኖረናል። አባቶቻችን ሲናገሩ ‹‹እግዚአብሔር ዓለሙን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ሰው ሆኖ ዓለሙን ያዳነበት ጥበቡ እጅግ ረቂቅና ጥልቅ ነው›› ይላሉ። እንዴት ደስ የሚል
አገላለፅ ነው!!! ታዲያ ምን ዋጋ አለው? አለመታደል ሆኖ ይሁን አሊያም አለማወቃችን ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋን ይግባውና እጅግ ድንቅ የሆነውን የጌታችንን የአምላካችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ከእንደዚህ ዓይነቱ ምዕራባዊ የጣዖት በዓል ጋር ቀላቅለን እናከብራለን።
@And_Haymanot
👉 ይህ እጅግ አሳዘኝ ነገር ነው በእውነት! በአንድ ወቅት በምዕራባውያን የገና በዓል ሰሞን በ‹‹BBC channel 4›› ላይ የበዓል መርሀ ግብር /program/ ቀርቦ ነበር። በመርሀ ግብሩ ላይ የተለያዩ የዕምነት ድርጅቶች የበዓል
አከባበር፣ የጸሎትና የመዝሙር ሥርዓትና ሌሎችንም ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ከቀረቡ በኋላ የመርሀ ግብሩ መሪ
በመጨረሻ እንዲህ ነው ያለው፡- “now let us see the real Christianity” ማለትም “አሁን እውነተኛውን የክርስትና
ሃይማኖት እንመልከት” በሚል መሸጋገሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የበዓል አከባበር ስነ-ሥርዓት ማስተላለፍ ጀመረ። ካህናት አባቶች ወረብ ሲያቀርቡ፣ የቅዳሴውን ሥርዓት፣ መዝሙሩ ሲዘመር፤ ጧፉ እየበራ ወንጌሉ ሲነበብ፣ እጣኑ እየጤሰ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲቀርብ......
ሁሉንም በየተራ ማቅረብ ጀመረ። እናም እነርሱ ማለት ምዕራባውያን ስለ ዕምነት ጉዳይ እውነት የሆነውን ነገር ፍለጋ
ፊታቸውን ወደ እኛ ባዞሩበት ወቅት እኛ ደግሞ እውነተኛውን ማንነታችንን ባንጥልና የአጉል ባህል ተገዢዎች ባንሆን ብሎም በአምልኮ ጣኦታቸው ተሳታፊዎች ባንሆን መልካም ነው።
መልካም ነው ብቻም ሳይሆን መንፈሳዊና ሞራላዊ ግዴታዎችም አሉብን።
በእርግጥ እኛ የዚህ ዘመን ትውልዶች የግሎባላይዜሽን ጎርፍ ጠራርጎ የወሰደን ስለሆንንና ‹‹በጣም ስልጡኖችና ዘመናውያንም›› ስለሆንን ይህ ምን ማለት እንደሆነ ላይገባን
ይችላል፤ እንዲገባንም አንፈልግም፡፡
የሴቶቻችን እርቃን መሄድ፣ አካሎቻቸውን መነቀስና መበሳት፣ የወንዶች አለባበስና ፀጉር አቆራረጥ… እነዚህና ሌሎቹም ነገሮች በዘመናዊነት ሰበብ የመጡብን የዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውጤቶች
ናቸው፡፡ በግል አዳኝ ‹‹ኢየሱሴ›› ስም ብዙኃኑን ሕዝባችንን ፈጣሪውን አስክደው አምላክ የለሽ አደረጉትና ለግሎባላይዜሽናቸው የተመቸ ዝርው ትውልድ ፈጠሩ፡፡ አሁንማ ጭራሽ ለይቶላቸው ‹‹church of Satan›› በማለት ‹የሰይጣን ቤተክርስቲያን› ከፍተው አባሎቻቸው በሆኑ ‹‹ታዋቂ የሂፖፕ›› አቀንቃኞቻቸው አማካኝነት የአባላቶቻቸውን ቁጥር ለመጨመር
እኛም ሀገር ብቅ ብለውልናል፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት እንደግለሰብ ነፃነት አድርጋችሁ ካልተቀበላችሁ እርዳታ አንሰጣችሁምም ተባልን፡፡ እሺ እነዚህና ሌሎቹም አስከፊ ኃጢአቶቻቸውን
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እንድንቀበል ቢያስገድዱንም
ቢያንስ እኛ በራሳችን ጊዜ ለምን የራሳችንን ባሕል ድምጥማጡን
በማጥፋት የእነርሱን ባሕል እንከተላለን? የዘመናዊነት መገለጫው የራስን ባሕልና እምነት በሌሎች መተካት ሆነ
እንዴ? ድሮ ቅኝ ቅዛት ተገዝተን ቢሆን ኖሮ ምንድን ነበር የምናጣው? ቀላል ነው መልሱ፡- የራስ ማንነት፣ እምነት፣ ባሕል፣ታሪክ…አይኖረንም ነበር፡፡ አሁን ታዲያ በዘመናዊው ቅኝ አገዛዝ ሥርዓት ምክንያት እነዚህን ነገሮች አላጣናቸውም ይሆን?

🙏 እንዲያው በመድኃኔዓለም! እባካችሁ ከፊት ለፊታችን በታላቅ ጉጉትና ተስፋ የምንጠብቀውን ከድቅድቅ ጨለማ ወጥተን ብርሃን ያገኘንበትን የአማኑኤልን የልደት በዓል የገናን ዛፍ በመጠቀም ከነጮቹ ባዕድና ጣኦት አምልኮ ጋር አንቀላቅለው፡፡ ልደቱን ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደሚገባው አድርጋ ታከብረዋለችና እኛም ልጆቿ እንደሚገባው መጠን ልደቱን እናክብር፡፡ የገና ዛፍ የባዕድ አምልኮ መገለጫ ነው፡፡ ማህቶተ ቤተክርስቲያን ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ምንድን ነበር
ያለው! ‹‹ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?
የእግዚአብሔርን ታቦት በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማነው?
2ኛ ቆሮ 6፡14-16፡፡ “በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ” 2ኛ ቆሮ 13፡5፡፡ ተዘጋጀ በጀማል ሀሰን ዓሊ (ስመ ጥምቀቱ ገብረሥላሴ) የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር በሃይማኖታችንና በኦርቶዶክሳዊ ማንነታችን ያፅናን አሜን።
(የጽሑፉ ምንጮች፡- አናቆጸ ሲኦል በብርሃኑ ጐበና፤ ሐመር 5ኛ
ዓመት ቁ1፣ 1989 ዓ.ም
@And_Haymanot
@And_Haymanot
እንኳን ለ ለብርሃነ ልደቱ ፤ በሰላም አደረሳችሁ።

"በጎል ሰከበ አፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ"
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቅለለ፡
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ
🕯🕯📖📖🕯🕯
📖📖📖
" ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"
(ኢሳ 7: 14)
📖📖📖
" እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።"
(ማቴ 1: 23)
📖📖📖
" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር" ኃያል "አምላክ" የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
(ኢሳ 9: 6)
መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ:)
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
"በዓለ ጥምቀት"
@And_Haymanot
ክፍል ፩
☞1. ትርጉም

ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒ፣ በግእዝ አስተርእዮ፣ በአማርኛ
መገለጥ ፡ይባላል። ቃሉ በቀጥታ ሲተረጎም በውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጥለቅ ማለት ነው። በምሥጢረ ትርጉሙ ግን ጥምቀት ከሰባቱ ምጥጢራተ ቤተ
ክርስቲያን /ጥምቀት፣ ሜሮን፣ ቁርባን፣ ንስሐ፣ ክህነት፣ ተክሊለና ቀንዲል/ አንዱና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 3 ቁጥር 5 ላይ “… ሰው ከውኃና
ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም”ብሎ እንደተናገረው ከውኃና ከመንፈስ ተወልደን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት፣ መንግሥተ ሰማያት
የምንገባበት፣ ኃጢአታችን የሚደመሰስበትና ድኅነትን
የምናገኝበት ዐቢይ ምሥጢር ነው። ጥምቀት በምሥጢረ ሥላሴና በምሥጢረ ሥጋዌ አምኖ ለሚቀበለው ሰው ሁሉ ለኃጢአት መደምሰሻ፣ ከሥላሴ የጸጋ ልጅነት ለመቀበልና
የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የተሰጠ ልዩ የሕይወት መንገድ ነው።

☞2. አመጣጥ

የምሥጢረ ጥምቀት መሥራቹ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነገር ግን ከጌታችን ጥምቀት በፊት
አይሁድ ለመንጻትና ለኃጢአት ሥርየት /ይቅርታ/ የሚጠመቁት ጥምቀት ነበራቸው። ይኸውም እግዚአብሔር በረድኤት በሚገለጥባቸው የተቀደሱ ዕለታትና ቦታዎች ሁሉ ሰውነትንና
ልብስን ማጠብ፣ የእግዚአብሔር ቤት መገልገያ የሆኑ ዕቃዎችን ሁሉ ማጠብ ማንጻት ሥርዓትና ልምድ ነበር። የእግዚአብሔር ፈቃድ ያለበት አሠራር ነበር። ወደ ቤተ እግዚአብሔርም
ከመቅረባቸውና ለተቀደሰው አገልግሎት ከመግባታቸው አስቀድመው እግሮቻቸውንና እጆቸቸውን የመታጠብ ግዴታም ነበራቸው፡ ሰውነታቸውን የመታጠብ ግዴታም ነበራቸው።
ሰውነታቸውን ከአፍአዊ /ከውጫዊ/ እድፍ በማጠብና ንጹሕ በማድረግ በባሕርዩ ንጹሕና ቅዱስ በሆነው አምላክ ፊት ውስጣዊ ሕይወትን ንጹሕ አድርጎ የመቅረብን ሥርዓትና ምሥጢር የሚያመለክት ልማድ ነበር፦ “አሮንና ልጆቹንም ወደ መገናኛቸው ድንኳን ታቀርባቸዋለህ፤ በውኃም ታጥባቸዋለህ፣
ሙሴም አሮንና ልጆቹን አቀረበ። በውኃም አጠባቸው” /ዘዳ 29፡
4፤ ዘሌ 8፡6/። ዮሐንስ በዮርዳኖስ በኢየሩሳሌም ይሁዳ አውራጃዎች ከጌታ
ቀደም ብሎ ተልኮ “መንግሥተ ሰማያት በልጅነት፣ ልጅነት በእምትና በጥምቀት ልትሰጠ ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፣ ከኃጢአትና ከበደል ተመለሱ” እያለ ለኃጢአት ሥርየት ለንስሐ ያጠምቅ ነበር። ብዙ ሰዎችም ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ ከሱ ይጠመቁ ነበር። በብሉየ ኪዳን ዘመን በርከት ያሉ የጥምቀት
ምሳሌዎችን እናገኛለን። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑትን ለመመልከት፦

✞ 1ኛ) አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ መልከ ጼዴቅ መሄዱ የጥምቀት ምሳሌ ነው። አብርሃም የምዕመናን፣ መልከ ጼዴቅም የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌዎች ናቸው። /ዘፍ 14፡17/
✞ 2ኛ) ኢዮብ በዮርዳኖስ ተጠምቆ ከደዌው ተፈውሷል። ይህም ምእመናን ተጠምቀው ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ የመፈወሳቸው / ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ/ የመዳናቸው ምሳሌ ነው።
✞ 3ኛ) ንዕማን ሶርያዊ ተጠምቆ ከለምጹ ድኗል። /2ኛ ነገ 5፡14/። ይኸውኛውም ምእመናን ተጠምቀው ከመርገመ ሥጋ
ከመርገመ ነፍስ የመዳናቸው ምሳሌ ነው።
✞ 4ኛ) የኖኅ መርከብ የጥምቀት ምሳሌ ነው። /ዘፍ 6፡13/። ይህንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጥሮስ “ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቆየ ጊዜ ደግሞ አልታዘዙም። ይህም ውኃ
ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል። የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፣ ለእግዚአብሔር የበጎ ኅሊና ልማድ ነው
እንጂ።” ሲል ተርጉሞታል። /1ኛ ጴጥ 3፡20/
✞ 5ኛ) እሥራኤል በደመና ተጋርደው ቀይ ባሕርን መሻገራቸው የጥምቀት ምሳሌ ነው። /ዘፀ 13፡21/ ። ይኽንንም ሓዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ። ሁሉም
ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ” ሲል ተርጉሞታል። /1ቆሮ 10፡2/
✞ 6ኛ) አብርሃም ሕግ ሆኖ የተሰጠው ግዝረት የጥምቀት ምሳሌ ነው። አብርሃም ካረጀ በኋላ ቢገረዝም ልጆቹ ግን በተወለዱ በስምንተኛው ቀን እንዲገረዙ እግዚአበሔር አዝዞ ነበር። /ዘፍ 17፡9/። ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእጅ ባልተደረገ
መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ” ሲል ተርጉሞታል። /ቆላ 1፡11/። እንግዲህ ጥምቀት የግዝረት
ምሳሌ በመሆኑ በኦሪቱ ዘምን ቀን ተወስኖ ሕፃናቱ ይገረዙ እንደ ነበረ በአዲስ ኪዳንም ተወስኖ ሕፃናት ወንዶች በተወለዱ በአርባኛው ቀን፣ ሴቶቹ ደግሞ በተወለዱ በስማንያኛው ቀን
ይጠመቃሉ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም፣
በዘመነ ሉቃስ፣ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ኬሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡ /ፍት ነገ አንቀጽ 19፤ ዲድስቅ 29፤ ተረፈ ቄርሰሎስ/ በተጠመቀ ጊዜ 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር። /ሉቃ 3፡23/
ለመሆኑ ጌታችን ለምን በ30 ዓመቱ ተጠመቀ? በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር
ተልዕኮና መንፈሳዊ አገልግሎት ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር። እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ለማድ
አልነበረም። የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ፣ ተልእኮአቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ
የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው። /ዘኁ 4፡3፤ 1ኛ ዜና መዋ. 23፡24፤ ዕዝ 3፡8፤ 1ኛ ጢሞ 3፡6-10/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር። ዮሐንስ መጥምቅም
የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው።
ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40 ቀን ተሰጥቶት ያስወሰደውን ልጅነቱን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር የአዳም ልጆችን
የዕዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስሕተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው። ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ለይ በማረፉ አብ በደመና
“ይህ ልጄ ነው” ብሎ ሲመሰክርለት የምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል። /ማቴ 3፡16/
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትህትና ከገሊላ ወደ ዮረዳኖስ መጣ። ይህንንም ያደረገልን አብነት
ሊሆነን ነው። ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን “መጥተህ አጥምቀኝ” ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ተነጎዲያ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን “መጥታችሁ አጥምቁን” ባሉ ነበር። ስለዚህ እንዲህ
እንዳይሆን ነው ጌታችን “ጌታ” ሲሆን በባሪያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት
እጅ ተጠመቁ ሲል ነው። ቅደስ ዮሐንስ ጌታችን በእርሱ እጅ ለመጠመቅ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ “እኔ ባሪያህ በአንተ በጌታዬ እጅ ልጠመቅ ያስፈልገኛል እንጂ አንተ በእኔ በባሪያህ እጅ
ትጠመቅ ዘንድ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?” አለው። ጌታችንም
መልሶ “አሁንስ ፍቀድልኝ፣ እንግዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና /ትንቢተ ነቢያትን እንዲህ ልንፈጽም ያስፈልጋል/”
አለው። በዚህን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን አጠመቀው። በዚህም “መጥምቀ መለኮት” ተብሎ የቅዱስ ዮሐንስ ገናንነቱ ይነገራል፣...👇👇👇
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
👆👆👆በዓለ ጥምቀት...
ጌታችንም በባርያው እጅ በመጠመቁ ፍፁም
ትኅትናው ይነገርለታል። ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም። ምክንያቱም እርሱ እከብር አይል ክቡር፣ እጸድቅ አይል ጻድቅ
ነውና። ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን ምን እያለ እንደሚያጠምቅ አልገባውም
ነበር፡ በዚህም ምከንያት ጌታችንን “ጌታ ሆይ ሌላውን በአንተ ስም በባሕርይ አባትህ በአብ ስም፣ በባሕርይ ሕይወትህ በመንፈስ ቅዱሰ ስም አጠምቃለሁ። አንተንስ የማጠምቀው
በማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። ጌታችንም “ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሃለነ እግዚኦ፣ አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሢመቱ ለመልከጼዴቅ፣ የቡሩክ አብ ልጅ ቡሩክ ወልድ ብርሃንን የምትገልጥ ይቅር በለን። እንደ መልከጼዴቅ ክህነት አንተ
ለዘለዓለም ካህን ነህ” እያልክ አጥምቀኝ ብሎታል። ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ ምሥጢረ ሥላሴ ተገልጧል። መንፈስ
ቅዱስ በተለየ አካሉ በርግብ አምሳል ወረደ፤ አብም በተለየ አካሉ በደመና ሆኖ በማዕከለ ዮርዳኖስ የቆመውን ኢየሱስ
ክርስቶስን መለኮትን ከሥጋ ሳይለያይ አንድ አድርጎ “የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” አለ። ምክንያቱም በተለየ አካሉ ሰው ሆኖ በዮርዳኖስ የቆመው ኢየሲስ ክርስቶስ በተዋሕዶ አንድ
አካል አንድ ባሕርይ ሆኖአልና። ተገልጦ የማያውቅ ምሥጢር ተገልጧል። የመንግሥተ ሰማያት በር ይከፈትላችኋል ማለት ነው።

ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው? ይቆየን ...
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
በዓለ ጥምቀት
ክፍል ፪
ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው?
@And_Haymanot
በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች፣ ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው። ጌታ ጥምቀቱን ዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ
ነው፦ “ባሕር አይታ ሸሸች፣ ዮርዳኖስም ወደ ኋላዋ ተመለሰች፣ አንተስ ዮርዳኖእስ ወደ ኋላ የተመለስኸው ምን ሆነሃል? አቤቱ ውኈች ዐዩህ፤ ዐይተውም ፈሩህ /ጥልቆችም ተነዋወጡ፤ ውኈችም ጮሁ” /መዝ 113/114፡3-4፣ 76፡16/
ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ አንደሚገናኘ በግዝረትና በቁልፊት /በመገዘርና ባለመገዘር/ ተለያይተው የነበሩ ሕዝበና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታ
ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገለጽ ትርጉም አለው፡፤ እሥራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምድረ ርስት ገብተዋል። ያመኑ የተጠመቁ ምእመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን
ይወርሳሉ። /ዮሐ 21፡15/ ከላይ የቀረቡት ታሪኮች ለመረዳት እንደምንችለው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በዮሐንስ እጅ ነው። ለምን?
ቅዱስ ዮሐንስ በኃጢአት የተዳደፉት ሁሉ ንስሐ ገብተው የተዘጋጀላቸውን መንግሥት ወራሾች ይሆኑ ዘንድ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” እያለ ሲሰብክ ነበር። ይህ
“መንግሥተ ሰማያት በልጅነት፤ ልጅነት ደግሞ በሃይማኖት ልትሰጥ ቀርባለችና ከኃጢአት ተለይታችሁ፣ ከበደል ርቃችሁ
ቅረቡ” ማለት ነው። በነቢያት እንደተነገረውም “ የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ፣ ጥርጊያውንም አቅኑ” እያለ ድምጹን አሰምቶ ሰብኳል። ምሥጢሩንም በመጣ ጊዜ ተራራውና
ኮረበታው ተንዶ፣ ጎድጓዳው ተመልቶ፣ ሥሩ ተነቅሎ፣ ደንጊያው ተለቅሞ ለፈረስ ለሰረገላ እንዲመች ተደልድሎ እንደሚቆይ ሁሉ እናንተም የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰውነታችሁን ከኃጢአታችሁ ንጹሕ አድርጋችሁ ጠብቁ ማለት ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ ከንስሐው ስበከት በተጨማሪም ዘመን የማይቆጠርለት ሲሆን ሥጋን በመለበሱ ዘመን ተቆጥሮለት ከእርሱ በኋላ ስድስት ወር ዘግይቶ ስለሚመጣው ስለ ኢየሱስ
ክርስቶስ ማንነትም ሰብኳል፦“እኔስ ለንስሐ በውኃ አተምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል። እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤ መንሹም በእጁ ነው። አውድማውንም ስንዴውንም በጎተረው ይከታል፤ ፈጽሞ ያጠራል፤
ሰንዴወንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል። /ማቴ 3፡11፤ ዮሐ 1፡26/
“እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፤ ነገር ግን ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ። ሙሽራዪቱ ያለችው.እርሱ ሙሽራ ነው። ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው
ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል፡ እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ። እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል፡ ከላየ የሚመጣው ከሁሉ በላየ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው፣ የምድርንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው… አባት /አብ/ልጁን /ወልድን/ ይወዳል፡፤ ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል። በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን
የእግዚአብሔር ቁጣ በርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም” /ዮሐ 3፡28/።
በዚህ ስብከቱና ምስክርነቱ የተነሣ ጌታ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ። ከዚህም ጋር ጌታ ዮሐንስ ወዳለበት ኺዶ ተጠመቀ እንጂ ዮሐንስ ወደእርሱ እንዲመጣ አላደረገም። ይህም በዚህ ዓለም
ሀብት ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ሁሉ ካህናትን በየቤታችን እየመጣችሁ አጥምቁን የማለት ልምድ እንዳይኖር ሥርዓት.መወሰኑንና ጌታ መምህረ ትሕትና መሆኑን የሚያመለክት ነው።

☞ 3. የበዓሉ አከባበር

ይህ የዓለም መድኃኒት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት መታሰቢያ በዓል በመላው ዓለም በክርስቲያኖች ይከበራል። በዓሉ የሚከበርበት መሠረታዊ መልአክት ተመሳሳይ ቢሆንም የአከባበሩ ይዘት ፣ ሥርዓትና ትውፊት እንደየሀገሩ ባሕልና እንደየአብያተ ክርስቲያናቱ እምነትና
ሥረዓት የተለያየ መልክ አለው። የጥምቀት በዓል በኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በዓመታት ዑደት ከሚከበሩት ዐበይት በዓላት አንዱ ነው።
በአዳምና ሔዋን ሰብአዊ ተፈጥሮ አንድ ለሆነው ሰው ሁሉ ድኅንነተ የሰውን ሥጋ ዋሕዶ በተገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ
ደም የታነጸችው አሐቲ ቤተ ክርስቲያን በሰዎች የተለያየ አመለካከትና የእምነት ትርጉም ዛሬ በየአህጉሩና በየጎጡ
ተከፋፈላ በብዙ ስሞች ብትጠራም የጥንተ ክረስትናውን መሠረት ሳትለቅ፣ ከቀደምት አበው በተላለፈወ እምነትና ሥርዓት ጸንታ የመትጓዘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
የጥቀትን በዓል የምታስበውና የምታከብረው በሌሎቸ ዘንድ በማንኛውም ቤተ ክርስቲያን በማይታይ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትውፊትና ሥርዓት ነው፡፤ በተለይ ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ፣ ዮሐንስ ጌታን ሊያጠምቅ ወደ ዮርዳኖስ
እንደወረዱ ቤተ ክርስቲያን ታቦቷን ከመንበሯ አውጥታ ወደ ውኃ
ምንጮች /ወንዞች/ በመሄድ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓት ታከብራለች። ተከታዮቿ ምእመናንም /ሕዝበ ክርስቲያኑም/ ከታቦታቱ ጋር በየአካባቢአቸው አብረው በመውጣት ለዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን እምነት፣ ፍቅርና አክብሮት
በጋለ መንፈስ እየገለጡ በዓሉን በደማቅ ሥነ ሥርዓት ያከብራሉ፡፤ ለኢትዮጰያ ቤተ ክርስቲያን ልዩ የሆነውን ይህን ሥነ
በዓል ለመመልከት ከዓለም ዙሪያ የሚሰበሰቡ ሀገር ጎብኚዎች
ብዙዎች ናቸው።
ሐመር ፲፩ኛ ዓመት፣ ቁ. ፮፤ ጥር - የካቲት ፲፱፻፺፮ ዓ.ም.

መልካም የጥምቀት በዓል።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
​​✞ ✞ ✞ ታቦት ✞ ✞ ✞
ተወዳጆች በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ እያልን ዛሬ በታቦት ዙርያ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ይዘን ቀርበናል

☞ ታቦትን ሌሎች ሃገራት እንዴት ይጠቀሙታል?Read more


☞"ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ"

ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል?
አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ "የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ አይሹትም ፣ አይደረግምም" የሚለውን በመጥቀስ የሐዲስ ኪዳነ ታቦትን ይቃወማሉ።...
Read more


☞ ታቦት ተሽሯል? Read more
☞ ይህ ሁሉ ታቦት ከየት መጣ? Read more
☞ የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ክርስቶስ ነው ሌላውን ሽሮታል? Read more


ተጨማሪ ለማንበብ ☞ ይህን ይጫኑ
አልተሳሳትንም
###########
@And_Haymanot
ትኩረት ወደ
👉 የማንቂያ ደውል ጉባኤያት
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
የማንቂያ ደውል🔔

የማንቂያ ደወሉ ጉባኤ ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2012ዓ.ም በገርጂ ጊዮርጊስ ያመሻል። ልብ በሉ የሰማዕታቱ አጽም ያረፈበት
ቤተክርስቲያን ነዉ። እንደተለመደዉ መምህር እስቻለው በመጀመርያው ክፍል ያገለግላል ከዛም ታላቁ መምህራችን መምህር ምህረተአብ በክፍል ሁለት ትምህርት አስደማሚዉን የማንቂያ ደዉል ይደወላል ። ለሰማዕታቱ ጧፍ በህብረት እናበራለን። የማንቂያ ደወሉ ጥምረት ዘማሪያን :መሳሪያ ተጫዋችና የተዋህዶ ወጣቶች በተሰጣቸዉ ጸጋ ያገለግላሉ ። የደብሩ ስብከተ ወንገል ከሰንበት ት/ቤት ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ ዝግጅት አደርገዋል።11:00 ማንቂያዉን
ለመደወል የተቆረጠለት ሰአት ነዉ።
ታዲያ ከዚህ ጉባኤ ይቀራል? አይቀርም።

ይሄ መልእክት በተቻለ ፍጥነት #ሼር ይደረጋል፤

👉 ማክሰኞ ፡- ቀራንዮ መድኃኔዓለም
👉 ረቡዕ፡- ቦሌ መድኃኔዓለም
👉 ሐሙስ፡- ጉለሌ ሩፉኤል
👉 አርብ :- ናዝሬት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot